#Article 1: ኃይሌ ገብረ ሥላሴ (237 words)


.

ኃይሌ ፡ ገብረ ፡ ሥላሴ ፡ በሚያዝያ ፲ ፡ ቀን ፡ ፲ ፱ ፻ ፷ ፭ (1965) ዓ.ም. ፡ በአሰላ ፡ ከተማ ፣ አርሲ ፡ ክፍለ ፡ ሀገር ፡ የተወለደ ፡ አቻ ፡ ያልተገኘለት ፡ ድንቅ ፡ የረጅም ፡ ርቀት ፡ ኢትዮጵያዊ ፡ ሯጭ ፡ ነው። ኃይሌ ፡ በሩጫ ፡ ዘመኑ ፡ በ ፲ ሺህ ፣ በ ፭ ሺህ ፣ በግማሽ ፡ ማራቶን ፣ በማራቶንና ፡ እንዲሁም ፡ በሌሎቹ ፡ የሩጫ ፡ ዓይነቶች ፡ ከ ፲ ፩ ፡ በላይ ፡ የዓለም ፡ ክብረ-ወሰን ፡ ሰብሯል። ኃይሌ ፡ በሩጫ ፡ ችሎታው ፡ ጠንካራ ፡ የሆነበት ፡ ምናልባትም ፡ ከመንደሩ ፡ ከባሕር ፡ ጠለል ፡ በላይ ፡ ከፍታ ፡ ነው ፡ ተብሎ ፡ ቢታመንም ፡ የተፈጥሮ ፡ ጥንካሬው ፡ ዓለምን ፡ ያስደነቀ ፡ ብርቅዬ ፡ ኢትዮጵያዊ ፡ ነው። ኃይሌ ፡ ሦስት ፡ ጊዜ ፡ የኦሊምፒክ ፡ ወርቅ ፡ ሜዳሊያ ፡ ተሸላሚ ፡ ከመሆኑም ፡ በላይ ፡ በ፴፫ ፡ ዓመት ፡ ዕድሜው ፡ ፪ ፡ ሰዓት ፡ ከ፬ ፡ ደቂቃ ፡ በሆነ ፡ ጊዜ ፡ በመግባት ፡ የዓለምን ፡ ማራቶን ፡ ክብረ-ወሰን ፡ ሊሰብር ፡ ችሏል። ኃይሌ ፡ ገብረ ፡ ሥላሴ ፡ እስካሁን ፡ ድረስ ፡ ፳፮ ፡ የዓለም ፡ ክብረ-ወሰኖችን ፡ ሰብሯል። ሯጭ ፡ ኃይሌ ፡ ገብረ ፡ ሥላሴ ፡ በሲድኒ ፡ እና ፡ በአትላንታ ፡ ኦሊምፒኮች ፡ በ፲ ሺህ ፡ ሜትር ፡ ሩጫዎች ፡ ወርቅ ፡ አስመዝግቧል።

በ ፲፱፻፺፪ (1992) ዓ.ም. ኤንዱራንስ (Endurance) ፡ የተባለ ፡ ስለ ፡ እራሱ ፡ የእሩጫ ፡ ድል ፡ ፊልም ፡ ተሠርቷል።




#Article 2: ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ (986 words)


ቀዳማዊ ፡ ዓፄ ፡ ኃይለ ፡ ሥላሴ (ቀ.ኃ.ሥ.) ከጥቅምት ፳፫ ቀን ፲፱፻፳፫ እስከ መስከረም ፪ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓ.ም. ፡ የኢትዮጵያ ፡ ንጉሠ ፡ ነገሥት ፡ ነበሩ። ተፈሪ ፡ መኰንን ፡ ሐምሌ ፲፮ ፡ ቀን ፡ ፲፰፻፹፬ ዓ.ም. ፡ ከአባታቸው ፡ ከልዑል ፡ ራስ መኰንን ፡ እና ፡ ከእናታቸው ፡ ከወይዘሮ ፡ የሺ ፡ እመቤት ፡ ኤጀርሳ ፡ ጎሮ ፡ በተባለ ፡ የገጠር ፡ ቀበሌ ፡ ሐረርጌ ፡ ውስጥ ፡ ተወለዱ።

በ፲፰፻፺፱ ፡ የሲዳሞ ፡ አውራጃ ፡ አገረ ፡ ገዥ ፡ ሆኑ። በ፲፱፻፫ ዓ.ም. ፡ የሐረርጌ ፡ አገረ ፡ ገዥ ፡ ሆኑ። የሐረርጌ ፡ አገረ ፡ ገዥ ፡ ሲሆኑ ፣ በጣም ፡ ብዙ ፡ ሺህ ፡ ተከታዮች ፡ ነበሩዋቸውና ፡ ልጅ ፡ እያሱን ፡ ከእንደራሴነት ፡ በኅይል ፡ እንዳያስወጡ ፤ እያሱም ፡ ተፈሪን ፡ ከሐረር ፡ አገረ ፡ ገዥነት ፡ እንዳይሽሯቸው ፡ የሚል ፡ ስምምነት ፡ ተዋዋሉ። ዳሩ ፡ ግን ፡ እያሱ ፡ ሃይማኖታቸውን ፡ ከክርስትና ፡ ወደ ፡ እስልምና ፡ እንደቀየሩ ፡ የሚል ፡ ማስረጃ ፡ ቀረበና ፡ ብዙ ፡ መኳንንትና ፡ ቀሳውስት ፡ ስለዚህ ፡ ኢያሱን ፡ አልወደዱዋቸውም ፡ ነበር። ከዚህም ፡ በላይ ፡ እያሱ ፡ ተፈሪን ፡ ከሐረር ፡ ከአገረ ፡ ገዥነታቸው ፡ ለመሻር ፡ በሞከሩበት ፡ ወቅት ፡ ስምምነታቸው ፡ እንግዲህ ፡ ተሠርዞ ፡ ተፈሪ ፡ ደግሞ ፡ ለወገናቸው ፡ ከስምምነቱ ፡ ተለቅቀው ፡ በዚያን ፡ ጊዜ ፡ እሳቸው ፡ እያሱን ፡ ከእንደራሴነት ፡ አስወጡ። እንግዲህ ፡ በ፲፱፻፱ ፡ ዓ.ም. ፡ መኳንንቱ ፡ ዘውዲቱን ፡ ንግሥተ ፡ ነገሥት ፡ ሆነው ፡ አድርገዋቸው ፡ ተፈሪ ፡ ደግሞ ፡ እንደራሴ ፡ ሆኑ። ከዚህ ፡ ወቅት ፡ ጀምሮ ፡ ተፈሪ ፡ በኢትዮጵያ ፡ ውስጥ ፡ ባለሙሉ ፡ ሥልጣን ፡ ነበሩ። በመስከረም ፳፯ ፡ ቀን ፡ ፲፱፻፳፩ ፡ ዓ.ም. ፡ የንጉሥነት ፡ ማዕረግ ፡ ተጨመረላችው። በ፲፱፻፳፪ ዓ.ም ፡ ንግሥት ፡ ዘውዲቱ ፡ አርፈው ፡ ንጉሠ ፡ ነገሥት ፡ ሆኑና ፡ ጥቅምት ፳፫ ፡ ቀን ፡ ፲፱፻፳፫ ዓ.ም. ፡ ብዙ ፡ የውጭ ፡ ልዑካን ፡ በተገኙበት ፡ ታላቅ ፡ ሥነ-ሥርዓት ፡ ቅብዓ ፡ ቅዱስ ፡ ተቀብተው ፡ እሳቸውና ፡ ሚስታቸው ፡ እቴጌ ፡ መነን ፡ ዘውድ ፡ ጫኑ። 

በንግሥ ፡ በዓሉ ፡ ዋዜማ ፡ ጥቅምት ፳፪ ፡ ቀን ፡ የትልቁ ፡ ንጉሠ-ነገሥት ፡ የዳግማዊ ፡ ዓፄ ፡ ምኒልክ ፡ ሐውልት ፡ በመናገሻ ፡ ቅዱስ ፡ ጊዮርጊስ ፡ ቤተ-ክርስቲያን ፡ አጠገብ ፤ ለዘውድ ፡ በዓል ፡ የመጡት ፡ እንግዶች ፡ በተገኙበት ፡ ሥርዐት ፣ የሐውልቱን ፡ መጋረጃ ፡ የመግለጥ ፡ ክብር ለብሪታንያ ፡ ንጉሥ ፡ ወኪል ፡ ለ(ዱክ ፡ ኦፍ ፡ ግሎስተር) ፡ ተሰጥቶ ፡ ሐውልቱ ፡ ተመረቀ።

ለንግሥ ፡ ስርዐቱ ፡ ጥሪ ፡ የተደረገላቸው ፡ የውጭ ፡ አገር ፡ ልኡካን ፡ ከየአገራቸው ፡ ጋዜጠኞች ፡ ጋር ፡ ከጥቅምት ፰ ፡ ቀን ፡ ጀምሮ ፡ በየተራ ፡ ወደ ፡ አዲስ ፡ አበባ ፡ ገብተው ፡ ስለነበር ፡ ሥርዓቱ ፡ በዓለም ፡ ዜና ፡ ማሰራጫ ፡ በየአገሩ ፡ ታይቶ ፡ ነበር። በተለይም ፡ በብሪታንያ ፡ ቅኝ ፡ ግዛት ፡ በጃማይካ ፡ አንዳንድ ፡ ድሀ ፡ ጥቁር ፡ ሕዝቦች ፡ ስለ ፡ ማዕረጋቸው ፡ ተረድተው ፡ የተመለሰ ፡ መሢህ ፡ ነው ፡ ብለው ፡ ይሰብኩ ፡ ጀመር። እንደዚህ ፡ የሚሉት ፡ ሰዎች ፡ እስከ ፡ ዛሬ ፡ ድረስ ፡ ስለ ፡ ፊተኛው ፡ ስማቸው ፡ «ራስ ፡ ተፈሪ» ፡ ትዝታ ፡ ራሳቸውን ፡ «ራስታፋራይ» ፡ (ራሰተፈሪያውያን) ፡ ብለዋል። 

ዓጼ ፡ ኃይለ ፡ ሥላሴ ፡ ዘውድ ፡ እንደጫኑ ፡ የአገሪቱን ፡ የመጀመሪያ ፡ ሕገ-መንግሥት ፡ እንዲዘጋጅ ፡ አዝዘው ፡ በዘውዱ ፡ አንደኛ ፡ ዓመት ፡ በዓል ፡ ጥቅምት ፳፫ ፡ ቀን ፡ ፲፱፻፳፬ ፡ ዓ.ም. ፡ በአዲሱ ፡ ምክር ፡ ቤት ፡ (ፓርላማ) ፡ ለሕዝብ ፡ ቀረበ። ከዚህም ፡ በላይ ፡ ብዙ ፡ የቴክኖዎሎጂ ፡ ስራዎችና ፡ መሻሻያዎች ፡ ወደ ፡ ኢትዮጵያ ፡ ከውጭ ፡ አገር ፡ አስገቡ። 

በ፲፱፻፳፰ ዓ.ም. ፡ የሙሶሊኒ ፡ ፋሺስት ፡ ሠራዊት ፡ ኢትዮጵያን ፡ በወረረ ፡ ጊዜ ፡ ጃንሆይ ፡ ሕዝባቸውን ወራሪውን በሙሉ ለመቃወም እንዳስነሡና የከተት ዐዋጆቻቸው በታሪክ ገጾች ይዘገባሉ። በዐዋጅ መሠረት የዘመቻው ጊዜ እስቲያልቅ ድረስ ለሚታግሉ ነጋዶች ከቀረጥ አስተስርየት ሰጣቸው። እራሳቸው በቆራጥነት ፡ ከታገሉ ፡ በኋላ ፡ የጠላቱ ፡ ጦር ፡ ኅይል ፡ ግን ፡ በመጨረሻ ፡ ወደ ፡ እንግሊዝ ፡ አገር ፡ ለጊዜው ፡ አሰደዳቸው። ወደ ፡ ጄኔቭ ፡ ስዊስ ፡ ወደ ፡ ዓለም ፡ መንግሥታት ፡ ማኅበር ፡ ሄደው ፡ ስለ ፡ ጣልያኖች ፡ የዓለምን ፡ እርዳታ ፡ በመጠየቅ ፡ ተናገሩ። የዓለም ፡ መንግሥታት ፡ ግን ፡ ብዙ ፡ አላደረጉም። በ፲፱፻፴፪ ዓ.ም. ፡ ግን ፡ አውሮፓ ፡ ሁሉ ፡ በሁለተኛው ፡ የዓለም ፡ ጦርነት ፡ ተያዘ። የእንግሊዝ ፡ ሠራዊቶች ፡ ለኢትዮጵያ ፡ አርበኞች ፡ እርዳታ ፡ በመስጠት ፡ ጣልያኖች ፡ ተሸንፈው ፡ በ፲፱፻፴፫ ዓ.ም. ፡ ኢትዮጵያን ፡ ተዉ። ዓፄ ፡ ኃይለ ፡ ሥላሴ ፡ አዲስ ፡ አበባን ፡ እንደገና ፡ የገቡበት ፡ ቀን ፡ ከወጡበት ፡ ቀን ፡ በልኩ ፡ ዕለት ፡ አምስት ፡ ዓመት ፡ በኋላ ፡ ነበረ። 

ከዚህ ፡ በኋላ ፡ በ1948 ዓ.ም. ተሻሽሎ የወጣ የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ፡ የሕዝቦችን ፡ መብቶችና ፡ ተከፋይነት ፡ በመንግሥት ፡ አስፋፍቶ ፡ ሁለቱ ፡ ምክር ፡ ቤቶች ፡ እንደመረጡ ፡ አደረገ። በ፲፱፻፶፭ ዓ.ም. ፡ ግርማዊነታቸው ፡ የአፍሪካ ፡ አንድነት ፡ ድርጅት ፡ በአዲስ ፡ አበባ ፡ እንዲመሠረት ፡ ብዙ ፡ ድጋፍ ፡ ሰጡ። በ፲፱፻፶፰ ዓ.ም. ፡ ወደ ፡ ካሪቢያን ፡ ጉብኝት ፡ አድርገው ፡ የጃማይካ ፡ ራስታዎች ፡ ተገኛኙ። በ፲፱፻፷፯ ዓ.ም. ፡ በማርክሲስት ፡ አብዮት ፡ ደርግ ፡ ሥልጣን ፡ ያዙና ፡ እሳቸው ፡ በእሥር ፡ ቤት ፡ ታሰሩ። በሚከተለው ፡ ዓመት ፡ ከተፈጥሮ ፡ ጠንቅ ፡ እንደ ፡ አረፉ ፡ አሉ ፤ ሆኖም ፡ ለምን ፡ እንደ ፡ ሞቱ ፡ ስለሚለው ፡ ጥያቄ ፡ ትንሽ ፡ ክርክር ፡ አለ። ብዙ ፡ ራስታዎች ፡ ደግሞ ፡ አሁን ፡ እንደሚኖሩ ፡ ይላሉ።

የዓፄ ፡ ኃይለ ፡ ሥላሴ ፡ የትውልድ ፡ ስም ፡ ልጅ ፡ ተፈሪ ፡ መኮንን ፡ ነው። ስመ-መንግሥታቸው ፡ ግርማዊ ፡ ቀዳማዊ ፡ ዓፄ ፡ ኃይለ ፡ ሥላሴ ፡ ንጉሠ ፡ ነገሥት ፡ ዘኢትዮጵያ ፡ ነበር። ሞዓ ፡ አንበሣ ፡ ዘእምነገደ ፡ ይሁዳ ፡ ሥዩመ ፡ እግዚአብሔር ፡ ንጉሠ ፡ ነገሥት ፡ ዘኢትዮጵያ ፡ የሚለው ፡ የሰሎሞናዊ ፡ ሥረወ-መንግሥት ፡ ነገሥታት ፡ መጠሪያም ፡ በንጉሠ-ነገሥቱ ፡ አርማ ፡ እና ፡ ሌሎች ፡ ይፋዊ ፡ ጽሑፎች ፡ ላይ ፡ ከመደበኛው ፡ ማዕረግ ፡ ጋር ፡ ይጠቀስ ፡ ነበር። ጃንሆይ ፣ ታላቁ ፡ መሪ ፡ እና ፡ አባ ፡ ጠቅል ፡ በመባልም ፡ ይታወቁ ፡ ነበር።




#Article 3: ራስ መኮንን (296 words)


ልዑል ራስ መኮንን ወልደሚካኤል የሸዋ ንጉሥ የነበሩት የሣህለ ሥላሴ ልጅ የልዕልት ተናኘወርቅ እና የደጃዝማች ወልደሚካኤል ልጅ ናቸው። ግንቦት ፩ ቀን ፲፰፻፵፬ ዓ.ም ጎላ ወረዳ ደረፎ ማርያም በሚባል ሥፍራ ተወልደው፤ እስከ ፲፬ ዓመት ዕድሜያቸው ከአባታቸው ጋር ከኖሩ በኋላ ያጐታቸው የንጉሥ ኃይለ መለኮት ልጅ ዳግማዊ ምኒልክ ገና የሸዋ ንጉሥ እንደነበሩ፡ ወደርሳቸው ቤተ መንግሥት መጥተው፡ ባለሟል ሆኑ ።

በ፲፰፻፷፰ ዓ.ም ዕድሜያቸው ሀያ አራት ዓመት ሲሆን ከወይዘሮ የሺ እመቤት ጋር ተጋብተው ሐምሌ ፲፮ ቀን ፲፰፻፹፬ ዓ.ም የወደፊቱን ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ወለዱ።
ልዑል ራስ መኮንን የንጉሠ ነገሥቱ ዳግማዊ ምኒልክ ተወካይ ሆነው ሁለት ጊዜ የአውሮፓን አገሮች ጎብኝተዋል። በዚህ ጊዜ እሳቸው ኢጣሊያን ሲጎበኙ በነበረ ጊዜ የኢጣሊያ ጋዘጦች የውጫሌ ውልን በተመለከተ፤ «...በውጫሌ ውል ላይ ኢትዮጵያ የኢጣሊያን ጥገኝነት ተቀብላ ውል ከፈረመች በኋላ የጀርመን ንጉሠ ነገሥት ከኢትዮጵያ የሚላከውን ማንኛውንም ደብዳቤም ሆን ጉዳይ በኢጣሊያ መንግሥት በኩል መቀበል ሲገባቸው በቀጥታ ከምኒልክ የተጻፈውን ደብዳቤ ተቀብለዋል...» እያሉ የጻፉትን ራስ መኮንን ተቃውሞአቸውን ለኢጣሊያ መንግሥት ከነገሩ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ የውሉን መበላሸት ለአጤ ምኒልክ አሳወቁ። ከኢጣሊያንም ጋር በተደረገውም ጦርነት ራስ መኮንን ፲፭ ሺህ እግረኛ ወታደሮች ይዘው ከምኒልክ እና ታላላቅ ጦር አዛዦች ጋር ዘምተዋል። 

በ፲፰፻፺፰ ዓ.ም መጀመሪያ ላይ በብርቱ ስለታመሙ ለኅክምና ወደ አዲስ አበባ ለመሄድ ጥር ፬ ቀን ከከተማቸው ከሐረር ተነሱ። ጥር ፱ቀን ቡርቃ ወንዝ አድረው የጥምቀትን በዓል አክብረው ከዋሉ በኋላ ሕመሙ ስለጸናባቸው ወደ ኋላ ተመልሰው ቁልቢ ገብተው በሐኪም ይታከሙ ጀመር። እዚሁም ሲታመሙ ከቆዩ በኋላ መጋቢት ፲፫ ቀን ፲፰፻፺፰ ዓ.ም ቁልቢ ላይ አርፈው ሐረር ላይ እሳቸው በተከሉት በቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ተቀበሩ። ዐፄ ምኒልክም የአርባቸው ለቅሶ የሚለቀሰው አዲስ አበባ እንዲሆን ባዘዙት መሠረት፤ ሰኞ ሚያዝያ ፳፪ ቀን በአዲስ አበባና በዙሪያው ያሉት የየገዳማቱና የየአድባራቱ ካህናት የክርስቲያን የፍታት ጸሎት ተድርጎ በማግስቱም ማክሰኞ የጊዮርጊስ ዕለት ሚያዝያ ፳፫ቀን ፲፰፻፺፰ ዓ.ም በሰኢ ሜዳ ላይ ድንኳን ተተክሎ፤ መኳንንቱና ሠራዊቱ ተሰብስቦ የራስ መኮንን የማዕረግ ልብሳቸውና የራስ ወርቃቸው፤ ኒሻኖቻቸውና የጦር መሳሪያቸው ተይዞ ፈረስና በቅሏቸው በወርቅ እቃ ተጭነው በሠራዊቱ መካከል እየተመላለሱ ታላቅ ልቅሶ ተለቀሰላቸው። ከአልቃሾቹም አንዱ ደግነታቸውን ለማስታወስ እንዲህ ብሎ አሟሸ፤-




#Article 4: ሚስቶች በኖህ መርከብ ላይ (611 words)


ከማየ አይህ በፊት በነበሩ ዕለታት ስለ ኖሩ በኖህ መርከብ ላይ ስለ ተገኙ ስለ አራቱ ሴቶች ኦሪት ዘፍጥረት ምንም እንኳን ዝም ቢል፣ ከሌላ ምንጭ ስለነዚሁ ሴቶችና በተለይ ስለ ስሞቻቸው የተገኘው አፈ ታሪክ በርካታ ነው። 

በጥንታውያን እምነት ዘንድ፣ የሴም፣ የካምና የያፌት ሚስቶች ዕጅግ የረዘማቸው ዕድሜ ሲኖራቸው ከመጠን ይልቅ ለብዙ መቶ ዓመታት ኑረው ለያንዳንዱ ትውልድ ትንቢት እየተናገሩ ኖሩ።  እነኚህ ሲቢሎች ተብለው ለግሪኮች ለሮማውያንም እንደ ቅዱሳን መጻሕፍት የተቆጠሩት የሲቢሊን መጻሕፍት ደራሲዎች እንደ ነበሩ ታመነ። የሮማውያን ቅጂ በ397 ዓ.ም. አካባቢ በእሳት ተቃጥ ዛሬ የሚታወቁ የሲቢሊን ራዕዮች የተባሉት ሰነዶች ኦሪጂናል መሆናቸው ለምሁሮች አይመስላቸውም።  ከመጀመርያ ሲቡሎች በኋላ ሌሎች ሲቢሎች እንደ ተከተሉ ለንግሮቹም እንደ ጨመሩ ይታስባል። 

በመጽሐፈ ኩፋሌ የሴም፣ የካምና የያፌት ሚስቶች እንዲሁ ተብለው ይሰየማሉ፤

ከዚህ በላይ ሦስቱ የኖህ ልጆች ከጥቂት ዓመት በኋላ ከአራራት ሠፈር በየአቅጣጫው ሂደው ለሰው ልጆች ሁሉ እናቶቻቸው ለሆኑት ለሚስቶቻቸው ስሞች የተባሉ 3 መንደሮች እንደ መሠረቱ ይታረካል።

በኋላ ዘመን የክርስቲያን ጸሓፊ ቅዱስ አቡሊድስ (227 ዓ.ም. የሞቱ) በጽርዕ ታርጉም ዘንድ ለዚህ ተመሳሳይ የሆነ ታሪክ መዘገቡ። ነገር ግን እዚህ የሴምና የካም ሚስቶች ስሞች እንዳለዋወጡ ይመስላል። እሱ እንዲሁ፦ «የኖህ ልጆች ሚስቶች ስሞች አንዲሁ ናቸው፤ የሴም ሚስት፣ ናሐላጥ ማሕኑቅ፤ የካምም ሚስት፣ ዘድቃጥ ናቡ፣ የያፈትም ሚስት አራጥቃ ይባላሉ» ብሎ ጻፈ።

ጆን ጊል (1697-1771 እ.ኤ.አ.) በመጽሓፍ ቅዱስ ነክ አስተያይቶቹ ስለ አንድ የዓረብ አፈ ታሪክ የጻፈው እንዲሁ ነው፤ «የሴም ሚስት ስም ዛልበጥ ወይም ዛሊጥ ወይም ሳሊት ሲሆን፣ የካምም ደግሞ ናሓላጥ ተባለች፣ የያፌትም ደግሞ አረሢሢያ ተባለች።

ኪታብ አል-ማጋል የተባለው ጥንታዊ አረብኛ መጽሐፍ (ከ'ቄሌምንጦስ መጻሕፍት' መሃል)፣ በጽርዕ የተጻፈው መጽሐፍ የመዝገቦች ዋሻ (350 ዓ.ም. ገዳማ) እና የእስክንድርያ ግሪክ ኦርቶዶክስ አቡነ ዩቲኪዮስ (920 ዓ.ም. ገደማ) ሁሉ ሲስማሙ የኖህን ሚስት ሃይኬል ይሏታል፤ እርስዋም የናሙስ ልጅ፣ ናሙስም የሄኖክ ሴት ልጅ፣ ይህም ሄኖክ የማቱሳላ ወንድም እንደ ነበሩ ይላሉ። ኪታብ አል-ማጋል ደግሞ የሴም ሚስት የናሲህ ልጅ ልያ ብሎ ይሰይማታል።

የሳላሚስ አጲፋንዮስ የጻፈው ፓናሪዮን ደግሞ የኖህ ሚስት ባርጤኖስ ይላታል። በ5ኛ ክፍለ ዘመን አካባቢ በግዕዝ የተሠራው መጽሐፈ አዳምና ሕይዋን ግን የኖህ ሚስት ሃይካል ሲጠራት ይቺ የአባራዝ ልጅ፣ አባራዝም የሄኖስ ልጆች ሴት ልጅ ናት ይላል። አንዳንድ ጸሐፊ ስለዚህ የአጲፋንዮስ 'ባርጤኖስ' ማለት ከእብራይስጥ 'ባጥ-ኤኖስ' መሆኑን አጠቁሟል።.  

በ'ሲቢሊን ራዕዮች' ዘንድ፣ ከሲቢሎቹ የአንዲቱ ስም ለዛልበጥ ተመሳሳይ ነበረ፤ እሷም የ«ባቢሎን ሲቢል» ሳምበጥ ነበረች።  ከጥፋት ውሃ 900 አመት በኋላ ወደ ግሪክ አገር ሄዳ የንግሮች ጽሑፍ እንደ ጀመረች ብላ ጻፈች።  ከዚያ በላይ የጻፈችው ጽሁፍ ከማየ አይህ አስቀድሞ የነበሩ የቤተሠቧ ስሞች ይታርካል። እነሱም አባቷ ግኖስቲስ፣ እናቷ ኪርኬ፤ እህቷም ዒሲስ ናቸው። በሌሎች ጥንታዊ ምንጮች ደግሞ ሳባ የምትባል ሲቡል ኖረች።

በ15ኛ ክፍለ ዘመን አውሮፓዊ መነኩሴ አኒዮ ዳ ቪተርቦ ዘንድ፣ ከለዳዊው ቤሮሶስ (280 ዓክልበ ያህል የጻፈ) የልጆቹ ሚስቶች ፓንዶራ፣ ኖኤላ፣ ኖኤግላ የኖህም ሚስት ቲቴያ ተብለው እንደ ተሰየሙ ብለው ነበር። ነገር ግን ይህ አኒዮ ዛሬ አታላይ ጸሐፊ እንደ ነበር ይታመናል ። 

በአይርላንድ አፈ ታሪክ ስለ ሦስቱ ልጆችና ስለ ሚስቶቻቸው የሚተረተው ብዙ አለ። በዚሁ ምንጭ ሚስቶቹ ኦላ፣ ኦሊቫ፣ ኦሊቫኒ ይባላሉ። እነኚህም ስሞች የተወሰዱ ኮዴክስ ጁኒየስ ከተባለው ጥንታዊ (700 ዓ.ም.) እንግሊዝ ብራና ጥቅል ይመስላል።  ይኸው ጽሕፈት እንደ ረጅም ግጥም ሆኖ በገጣሚው በካድሞን እንደተጻፈ ይታሥባል። እዚህ ደግሞ የኖህ ሚስት ፔርኮባ ትባላለች።

የሀንጋሪ አፈ ታሪክ ደግሞ ስለ ያፌትና ኤነሕ ስለ ተባለችው ስለ ሚስቱ አንዳንድ ተረት አለበት። ይህ መረጃ የሚገኘው የአንጾኪያ ጳጳስ ሲጊልበርት ከተጻፉት ዜና መዋዕል እንደ ሆነ ይባላል።

በደቡብ ኢራቅ በሚኖሩት በጥንታዊ ማንዳያውያን ሐይማኖት ተከታዮች መጻሕፍት ዘንድ፤ የኖህ ሚስት ኑራይታ ወይም አኑራይጣ ተባለች። 

በግብጽ 1-3 ክፍለ ዘመናት ዓ.ም. የተገኘው ግኖስቲክ ሃይማኖት መጻሕፍት ዘንድ የኖህ ሚስት ኖሬያ ስትሆን መጽሐፈ ኖሬያ የሚባል ጽሕፈት ነበራቸው።

አይሁዳዊ ሚድራሽ 'ራባ' እና በ11ኛ ክፍለ-ዘመን የኖረው አይሁድ ጸሐፊ ራሺ እንዳለው የኖህ ሚስት የላሜህ ሴት ልጅና የቱባልቃይን እኅት ናዕማህ ነበረች። እንዲሁም ከ1618 ዓ.ም. ብቻ በሚታወቀው ሚድራሽ «ያሻር መጽሐፍ»፣ የኖህ ሚስት ስም የሄኖክ ልጅ ናዕማህ ተባለች።  ነገር ግን፤ ጥንታዊ መጽሀፈ ኩፋሌ ስምዋ አምዛራ ተብሎ ይሰጣል።  «ናዕማህ» የሚለው የካም ሚስት ስም ለኖህ ሚስት ስም በአይሁድ ልማድ እንደ ተሳተ ጆን ጊል ሐሳቡን አቅርቧል። 

በሮዚክሩስ («የጽጌ ረዳ መስቀል ወንድማማችነት»፤ ምስጢራዊ ማኅበር) ጽሕፈት ኮምት ደ ጋባሊስ (1672 ዓ.ም.) ዘንድ፣ የኖህ ሚስት ስም ቨስታ ትባላለች።

በመጨረሻም፣ በዩናይትድ ስቴትስ በሚገኘው በሞርሞን ሃይማኖት ('የየሱስ ክርስቶች መጨረሻ ዘመን ቅዱሳን') መጻሕፍት ዘንድ፣ የካም ሚስት ስም ኢጅፕተስ ነበረ።




#Article 5: ዋዝንቢት (217 words)


ዋዝንቢት የሦስት አጽቄ አይነት ነው። የፌንጣና የአንበጣ ዘመድ ነው። ሁለንተናው ትንሽ ለጥ ይላል፤ ረጃጅም አንቴኖችም አሉት።

ዋዝንቢት የሚታወቀው በሚያሰማው ድምጽ ነው። ድምጽ ማውጣትና ማሰማት የሚችለው  አውራው ዋዝንቢት ብቻ ነው። የተባዕቱ ዋዝንቢት ክንፍ እንደ ሚዶና ሞረድ የሚመስል ፍርግርግ ነው። ክንፎቹን በማፋተግ ድምጽ ይፈጥራል፤ የድምጹ ቅላፄ እንደየ ዋዝንቢቱ ወገን ይለያያል። ሁለት ዓይነት የዋዝንቢት ዘፈኖች አሉ፤ የጥሪ ዘፈንና የመርቢያ ዘፈን ናቸው። የጥሪ ዘፈን ዓላማ አንስት ዋዝንቢ ለመሳብ  ሲሆን ረጅምና ከፍተኛ ድምፅ ነው። ለመራባት ሲባል የሚዘፈነው ድምፅ አንስቲቱ እንስቲቱን ለማቅረብ ስለሆነ ቀስ ያለና ለስላሳ ነው። አንስት ዋዝንቢት መርፌ የሚመስል ረጅም የዕንቁላል መጣያ አላት።

በምድር ላይ 900 የሚያሕሉ የዋዝንቢት ዝርያዎች ይገኛሉ። አንዳንድ ዝርያ ሣርና ተክል ብቻ ሲበላ፣ ሌሎች ዝርዮች ደግሞ ነፍሳት ያድናሉ። ዋዝንቢት ሌሊት የሚነቃ ፍጥረት ነው። ብዙ ጊዜ ከፌንጣ ጋር ይመሳሰላል፣ በተለይ የመዝለያ እግሮቹ ከፊንጣ እግሮች አይለዩም።

በ1963 ዓ.ም. ዶ/ር ዊሊያም ከይድ ምርመራ አድርጎ አንዲት ተባይ ዝንብ ደግሞ በተባዕቱ ዘፈን እንደምትሳብ፤ ዕጯንም እንድታስቀምጥበት ቦታውን ለማወቅ እንደሚጠቅማት አገኘ። የመርባትን ድምጽ በመጠቀም የአስተናጋጇን ቦታ ለምታገኝ የተፈጥሮ ጠላት ይህች መጀመርያ ምሳሌ ሆነች። ከዚያ በኋላ ብዙ የዋዝንቢት ወገኖች ይህችን ተባይ ዝንብ ሲሸክሙ በምድር ላይ ተገኝተዋል።

በእስያ በተላይም በቻይና ዋዝንቢት ዝነኛ ለማዳ እንስሳ ሆኖ መያዙ እንደ መልካም እድል ይቈጠራል። የተያዘ ዋዝንቢት ሁሉ ማናቸውም አትክልት ወይም ሥጋ ቢሰጥ ይበላል። በአንዳንድ ባሕል ደግሞ ዋዝንቢት እንደ ምግብ ሊበላ ይችላል።

ከዕውነተኛው ዋዝንቢት አይነቶች መካከል አንዳንዶቹ እንዲህ ናቸው፦ 

ከዕውነተኛው ዋዝንቢት ጭምር፣ ከነዚሁ ውጭ አያሌ ሌላ የተዛመዱ ተሐዋስያን ወገኖች ዋዝንቢት ሊባሉ ይችላሉ፦




#Article 6: ብርቱካን (ፍሬ) (399 words)


ብርቱካን (ወይም ኦሬንጅ) ማለት የዛፍ አይነትም ሆነ በተለይ የዚሁ ዛፍ ፍሬ ማለት ነው። የሌሎች አትክልት ክልስ ሆኖ ከጥንት እንደ ለማ ይታሥባል። እርዝማኔው እስከ 10 ሜትር ድረስ ቢደርስም ዛፉ ትንሽ ይባላል፤ ቡቃያው እሾህ አለበትና ቅጠሎቹ ከ4 እስከ 10 ሳንቲሜትር ድረስ የሚዘረጉ እንደ ጥድም ወገን መቸም የማይረግፉ ናቸው። የፍሬው መጀመርያ ትውልድ በደቡብ-ምሥራቃዊ እስያ በህንደኬ፣ በቬትናም ወይም በደቡብ ቻይና ተገኘ። 

የብርቱካን እርሻ በብዙ አገሮች ምጣኔ ሀብት በጣም ታላቅ የንግድ ሥራ ነው። እዚህ ማለት በአሜሪካ፣ በሜዲቴራኔያን አገሮች፣ በሮማንያ፣ በደቡብ አፍሪካ፣ በቻይና፣ በአውስትራልያም ይከትታል። 

ብርቱካን በዓለሙ ውስጥ ሙቅ አየር በሚገኝበት በሰፊ ይበቅላል፤ የብርቱካንም ጣዕም ከጣፋጭ እስከ ኮምጣጣ ድረስ ይለያል። ፍሬው በተለመደ ይላጣል ጥሬም ሆኖ ይበላል፤ አለዚያ ለጭማቂው ይጨመቃል። ወፍራምና መራራ ልጣጩ በተለመደ ወደ ቆሻሻ ይጣላል፤ ነገር ግን በክብደትና በሙቀት አማካኝነት ውሃውን በማስወግድ፣ ለመኖ ሊጠቅም ይችላል። ባንዳንድ የምግብ አሠራር ዘዴ ደግሞ፣ እንደ ጣዕም ወይም እንደ መከሸን ይጨመራል። የልጣጩ አፍአዊው ቆዳ በልዩ መሣርያ በቀጭን ይፋቃልና ይሄ ጣዕሙ ለወጥ የሚወደድ ቅመም ያስገኛል። ከልጣጩ በታች ያለው ነጭና ሥሥ ሽፋን ስለማይረባ ይጣላል። ደግሞ የብርቱካን ዘይት አስታጋሽ መዓዛ ስላለው በሕክምና ይጠቅማል።

ከብርቱካን የተሠራ ሌላ ውጤት እንደሚከተለው ነው፦

እንዲያውም ብርቱካን፣ ሎሚ መንደሪን ወዘተ. ሁሉ የአንድ ወገን ናቸው ሁላቸው እርስ በርስ ማራባት ይችላሉ ማለት ነው። በተግባር እነኚህ አይነቶች እንጆሪ ይባላሉ ምክንያቱም ብዙ ዘር እያላቸው ሥጋቸውም ወፍራምና ለስላሳ ሆኖ ከአንድ ዕንቁላል ብቻ ያፈራሉ።

በምድር ላይ ጥቂት አይነቶች ይታረሳሉ። ለምሳሌ ጣፋጭ ብርቱካን የምትባል መጀመርያ በእስፓንያ አገር በቀለች፤ ይቺ ከሁሉ የምትወደድ አይነት ሆናለች። ጣፋጭ ብርቱካን እንደ አየሩ ሁኔታ በልዩ ልዩ መጠኖችና ቀለሞች ትገኛለች፤ አብዛኛው 12 ክፍሎች ውስጥ አሉባቸው።

የሴቪል ብርቱካን በሰፊ የምትታወቅ አሁንም በሜዲቴራኔያን አቅራቢያ በኩል የምትበቀል እጅግ ኮምጣጣ ብርቱካን ናት። ቆዳዋ ወፍራምና ስርጉዳት ያለው ነውና ማርማላታም ሆነ የብርቱካን አረቄ ለመስራት በጣም ትከብራለች። ይብራ በብርቱካን ወጥ ሲበሉ ብርቱካን የዚች አይነት ናት።

ባጋጣሚ በብራሲል አገር ውስጥ በ1812 ዓ.ም. በአንድ ገዳም በነበረ የብርቱካን እርሻ ከሆነ ድንገተኛ ለውጥ የተነሣ፤ የእምብርት ብርቱካን የሚባል አይነት መጀመርያ ተገኘ። ከዚያ በ1862 ዓ.ም. ነጠላ ቁራጭ ወደ ካሊፎርንያ ተዛዉሮ አዲስ የዓለም አቀፍ ብርቱካን ገበያ የዛኔ ተፈጠረ። ድንገተኛ ለውጡ መንታ ፍሬ ያደርጋልና ታናሹ መንታ በታላቁ ውስጥ ተሠውሮ ይገኛል። የእምብርት ብርቱካን ዘር ስለሌለው በእፃዊ ተዋልዶ ይባዛል፤ የፍሬውም መጠን ከጣፋጭ በርቱካን ይበልጣል።

ቫሌንሲያ ወይም ሙርሲያ ብርቱካን በተለይ ለጭማቂ የሚመች ጣፋጭ አይነት ነው። መንደሪን ትመስለዋለች፣ ነገር ግን ይልቁን ትንሽና ጣፋጭ ናት፤ በመጨራሻም፣ ድፍን ቀይ እምብርት የተባለው የዚህ አይነት ከነመንታው ለውጥ እንደ እምብርት በርቱካን ነው።

በድሮ ጊዜ ፖርቱጋል የምትባል አገር ለምሥራቅ አገሮች የጣፋጭ ብርቱካን ዋና አስገቢ ነበረች። ስለዚህ በብዙ ቋንቋዎች የፍሬው ስም ከዚያው መነሻ ተወስዷል። ለምሳሌ፦

ተብሎ ይሰየማል። ባብዛኛው ቋንቋዎች ግን ያለባቸው ቃል ከሳንስክሪት «ናራንጋ» የወጣ ነው፤ በሌሎችም «የቻይና ቱፋህ» (አፕል) ወይም «የወርቅ ቱፋህ» የሚተረጎሙ ቃሎች ለብርቱካን ለማለት የጠቅማቸዋል።




#Article 7: አቡጊዳ (188 words)


አቡጊዳ (Ebugida) ማለት ፊደል ነው። ከልሳነ ግዕዝ የተነሣ ነው። ቢሆንም በቅርብ ጊዜ አንዳንድ የፈረንጅ አገር ሊቅ ይህን አባባል ለቋንቋዎች ጥናት ተበድሯል። በዚሁ አነጋገር አቡጊዳ ማለት በዓለም የሚገኙ ልዩ ልዩ አይነት ጽሕፈቶች ሊያመልከት ይችላል። በየአገሮቹ ፊደላቸው አቡጊዳ የሚባለው እያንዳንዱ ፊደል ለክፍለ-ቃል ለመወከል ሲሆን ነው እንጂ እንደ እንግሊዝኛ አልፋቤት ፊደሉ ለ1 ተነባቢ ወይም ለ1 አናባቢ ብቻ ሲሆን አይደለም። ስለዚህ የግዕዙ ፊደል ይሁንና ሌሎችም ለምሳሌ ብዙ የህንድ አገር አጻጻፎች ጨምረው አቡጊዳ በሚግድጅቭጅለው ስም ይታወቃሉ። 

ብራህሚክ ወይም ደቫናጋሪ በተባሉት የህንድ አጻጻፎች በኩል እያንዳንዱ ክፍለ-ቃል በተለየ ፊደል ሲወከል የአናባቢዎች መጠን የሚታየው የፊደሉን መልክ (እንደ ግዕዝ ወይም እንደ አማርኛ) ትንሽ በመቀየሩ ነው። ስለዚህ በቋንቋ ሊቃውንት ዘንድ 'አቡጊዳዎች' ይባላሉ። በተጨማሪ፣ በካናዳ አገር ለጥንታዊ ኗሪ (ቀይ ኢንዲያን የተባሉ) ጐሣዎች ያላቸው አጻጻፍ እንደዚህ አይነት ነው፤ አናባቢው በቅርጹ የሚታየው ፊደሉን በመዞር ወይም በመገልበጥ ነውና። 

በግእዝ አቡጊዳ ለሚለው የቃሉ መነሻ ከጥንታዊ የሴም ፊደል ተራ የሚለቀመው ነበር። በግሪክም ይህ ፊደል ተራ በ A, Β, Γ, Δ ጀመረ፤ ወይም በስም አልፋ፣ ቤታ፣ ጋማ፣ ዴልታ ናቸው። ይህ ፊደል ተራ በ ሀ ሁ ሂ ሃ በሚል ቅርጽ ማለት በግእዝ፣ በካዕብ፣ በሣልስ፣ በራብእ ውስጥ ገብቶ ሲሰካ፣ አ፣ ቡ፣ ጊ፣ ዳ የሚለውን ፊደል ተራ አስገኘ። ሁሉ በሙሉ የግእዝ አቡጊዳ እንግዲህ እንደሚከተለው ሰንጠረዥ ነው።

ኣበራ ሞላ




#Article 8: ኢትዮጵያ (3389 words)


ኢትዮጵያ ወይም በይፋ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢ.ፌ.ዲ.ሪ.) በአፍሪካ ቀንድ የምትገኝ የረጅም ዘመን ታሪክ ያላት ሀገር ናት። በአፍሪካ ነፃነታቸውን ጠብቀው ለመኖር ከቻሉ ሁለት አገሮች አንዷ ነች። በህዝብ ብዛት ከአፍሪካ ኢትዮጵያ ሁለተኛ ስትሆን ፣ በቆዳ ስፋት ደግሞ አስረኛ ናት። ዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ናት።

አብዛኛዎቹ የአፍሪካ ሀገሮች ዕድሜያቸው ከአንድ ምዕተ-ዓመት የሚያንስ ሲሆን ፣ ኢትዮጵያ ግን ከጥንት ጊዜ ጀምሮ በንጉሠ-ነገሥታት እና ንግሥተ-ነግሥታት የተመራች ሀገር ናት። የሰለሞናዊው ሥርወ-መንግሥት የአመጣጡን ዘር እስከ አስረኛው ዓመተ-ዓለም ድረስ ይቆጥራል። ኢትዮጵያ የሰው ልጅ ከጥንት ጊዜ ጀምሮ የኖረባት ቦታ እንደሆነች ብዙ የሳይንሳዊ መረጃ ተግኝቷል። በበርሊን ጉባኤ በኩል የአውሮፓ ሀያላት ሀገሮች አፍሪካን ሲከፋፍሏት፣ ኢትዮጵያ ነፃነቷን ጠብቃለች። የሊግ ኦፍ ኔሽንስ (League of Nations) አባል ከነበሩት ሶስት የአፍሪካ ሀገሮች አንዷ ነበረች። ከአጭር የኢጣልያ ወረራ ጊዜ በኋላም ከየተባበሩት መንግሥታት መሥራቾች አንዷ ናት። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ብዙ የአፍሪካ ሀገራት ነፃነታቸውን ሲያገኙ፣ ሰንደቅ-አላማቸውን በኢትዮጵያ ቀለሞች ማለትም በአረንጓዴ ፣ ቢጫ እና ቀይ ላይ ነው የመሠረቱት። አዲስ አበባ ደግሞ ለየተለያዩ በአፍሪካ ላይ ላተኮሩ አለም አቀፍ ድርጅቶች መቀመጫ ሆነች።

የዛሬዋ ኢትዮጵያ የትልቅ የግዛት ለውጥ ውጤት ናት። ከሰሜን ግዛቱዋ በጣም የተቀነሰ ሲሆን በደቡብ በኩል ደግሞ ተስፋፍቷል። በ ፲፱፻፷፯ (1967) ዓ.ም.፣ ግርማዊ ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ከሥልጣን ሲወርዱ፣ የእርስ በርስ ጦርነት በሀገሩ ተባባሰ። ከዚህ ጊዜ በኋላ ኢትዮጵያ በተለያዩ የመንግሥት አይነቶች ተዳድራለች። ዛሬ አዲስ አበባ የአፍሪካ ሕብረት (African Union) እና የተባበሩት መንግሥታት የኢኮኖሚክ ኮሚሽን ለአፍሪካ መቀመጫ ናት። የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ከአፍሪካ ኃያል ሠራዊቶች አንዱ ነው። ኢትዮጵያ በአፍሪቃ የእራሷ ጥንታዊ ፊደል ያላት ሀገርም ናት።

ኢትዮጵያ ተፈጥሮ ያደላት ሀገር ናት። ከአፍሪካ ትላልቅ ተራራዎች እንዲሁም ከዓለም ከባህር ጠለል በታች በጣም ጥልቅ ከሆኑ ቦታዎች አንዳንዶቹ ይገኙባታል። ሶፍ ዑመር ከአፍሪካ ዋሻዎች ትልቁ ሲሆን ፣ ዳሎል ከዓለም በጣም ሙቅ ቦታዎች አንዱ ነው። ወደ ሰማንኒያ የሚቆጠሩ ብሔሮችና ብሔረሰቦች ዛሬ በኢትዮጵያ ይገኛሉ። ከእነዚህም ኦሮሞና አምሀራ በብዛት ትልቆቹ ናቸው። ኢትዮጵያ በኣክሱም ሓውልት፣ ከአንድ ድንጋይ ተፈልፍለው በተሰሩ ቤተ-ክርስትያኖቹዋ እና በኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊ አትሌቶቹዋ ትታወቃለች። የቡና ፍሬ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው በኢትዮጵያ ሲሆን ሀገሪቱዋ በቡናና ማር አምራችነት በአፍሪካ ቅድሚያ ይዛለች። 

ኢትዮጵያ ከዓለም ሶስቱ ትላልቅ የአብርሃም ሀይማኖቶች ጋር ታሪካዊ ግንኙነት አላት። ክርስትናን በአራተኛው ምዕተ-ዓመት ተቀብላለች። ከሕዝቡ አንድ ሁለተኛው ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስትና ነው። የመጀመሪያው የእስላም ሂጅራ ወደ ኢትዮጵያ ነው የተከናወነው። ነጋሽ በአፍሪካ የመጀመሪያው የእስላም መቀመጫ ናት። እስከ ፲፱፻፸ ዎቹ ድረስ ብዙ ቤተ-እስራኤሎች በኢትዮጵያ ይኖሩ ነበር። የራስ ተፈሪ እንቅስቃሴ ኢትዮጵያን በትልቅ ክብር ነው የሚያያት።

ግርማዊ ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ከስልጣን ከወረዱ በኋላ ድህነት በኢትዮጵያ በጣም ተስፋፍቶ ነበር። ሰማኒያ አምስት ከመቶ በላይ የሚሆነው የአባይ ወንዝ ውሀ ከሀገሩ የሚመጣ ቢሆንም በ ፲፱፻፸ ዎቹ በተከሰቱ ድርቆች በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ሞተዋል። ያንን ካሳለፈች በኋላ ሀገሪቱዋ አዲስ መንገድ በመፈለግ ላይ ትገኛለች።

አንድ-አንድ ቃላትን ስንመረምር በውስጣቸው የተደበቅ ምስጢር እናገኛለን። የተደበቀውን ምስጠር ለማግኘት ጥልቅ የታሪክና የቃላት ምርምርና ጥናት (Philology / Etimology) ማድረግ ያስፈልጋል። በብዙ ምርምርና ጥናትም ምስጢሩ የሚገለጥበት ጊዜ አለ። ለምሳሌ በግዕዝ፣ በትግርኛና፣ አማርኛ ‘አነ’፣ ‘እኔ’ የሚሉ ቃላት ስናገኝ፣ በላቲን/በእንግሊዝኛ ደግሞ ‘አይ’ (I - እንግሊዝኛ)፣ ‘ኢዮ’ (Io -ጣልያንኛ) አሏቸው። በግዕዝ፣ ትግርኛና፣ አማርኛ ‘ዓይን’ ‘ዓይኒ’ ለሚሉ ቃላት ደግሞ፣ በእንግሊዝኛ አይ (eye) እናገኛለን። በአማርኛና ትግርኛ፤ ‘ያለቀለት ጉዳይ’ ለማለት ‘ሙት፣ የሞተ ነገር’፣ ስንል በእንግሊዝኛ ‘ሙት ኢሹ’ (moot issue) ይላሉ። በግዕዝና፣ ትግርኛ፣ ‘መርዓ’ ስንል፣ በእንግሊዝኛ (marriage) ‘መረጅ’ ይላሉ። ፈርኦን (Pharaoh) ከሚባል ጥንታዊ የግብፅ ንጉሥም ወደ ግዕዝ፣ ትግርኛና አማርኛ፣ እንዲሁም ወደ እንግሊዝኛ ቃላት፤ ‘ፈሪሃ’ ‘ፍርሓት’ ‘fear’ (ፊር) ለሚሏቸው ቃላት ምንጭ የሆነ ይመስላል። ንጉሡ ታላቅና የሚፈራ የነበረ ነው የሚመስል። እነዚህን ለምሳሌ አቀረብን እንጂ እንደዚህ ብዙ የቃላት መቀራረብ እናገኛለን። “ማን ከማን ወሰደ? ታሪካዊ አመጣጡና አወራረዱስ እንዴት ነው?” የሚሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ነው የቃላት ጥናትና ምርምር የሚያስፈልግ።

አንድ-አንድ ቃላትም ከቋንቋችን ፈልቀው ይወጡና ዓለምን ዞረው ተመልሰው ሲመጡ ብርቅ አድርገን እንቀበላቸዋለን። ለምሳሌ በኃይለሥላሴ ዘመን ያኔ ልዕልት ፀሓይ ሲባል ከነበረው ሆስፒታል ጎን አዲስ የሕንፃ ኮሌጅ ተከፍቶ፣ ‘የመሃንድስ ኮሌጅ’ በመባል ይታወቅ ነበር። መሃንድስ ማለት ምን ማለት ነው? መሃንድስ ማለት መሃናስ/መሃንዳሰ ከሚል የዓረብኛ ቃል የመጣ ሲሆን፣ እርሱ ደግሞ ሃነፀ፣ ይሃንፅ፣ ማነፅ፣ ማሕፀን (ሕፃን የሚታነፅበት ቦታ) ... ወዘተ ከሚሉ የግዕዝ፣ የትግርኛና፣ የአማርኛም ቃላት ይዛመዳል። እንግዲያውስ ማነፅ ከሚለው ቃል መሃንዳስ ሆኖ ተጣመመና፣ ከዚያም መሃንድስ ተብሎ፣ ዞሮ ተመልሶ ብርቅ ቃል ሆኖብን ለሕንፃ ኮሌጀ መጠሪያ ሆነ። አሁንም ቢሆን ኢንጂኔር ለማለት መሃንድስ ሲባል እንሰማለን።

ሌላም ቃል ፋጡማ/ፋጢማ የሚል ስም ስንመለከት፣ ከነብዩ ሙሓመድ ሴት ልጆች ለአንዷ የተሰጠ መጠሪያ ነበረ። በዓረብኛ አባባል ግን ጠ/ጸ የሚለው ሳይሆን ተ የሚለው ፊዴል ድምፅ ነው። ይህም ማለት፣ ቃሉ “ፈቲማ” ብለው ሲሉ፣ ትርጉሙም፡ ፍጽምት፣ (Perfect) ማለት ነው። ስለዚህ ፈቲማ ማለት፣ ፈጺማ (ትግረኛ) ፈጸመች (አማርኛ) ማለት ነው።

ከሃያ አምስት ዓመታት በፊት ሰምና ወርቅ በተባለው የምርምር መጽሔት (1987 እ.ኤ.አ.) ያቀረብነው፣ “ኢትዮጵያ የሚለው ቃል ትርጉሙ ምን ማለት ነው? ኢትዮጲስ የሚባለው ንጉሥስ ለምን ይህ ስም ተሰጠው ... ብለን በጠየቅንበት ጊዜ አጥጋቢ መልስ ባለማግኘታችን ቋንቋ ለሚመረምሩ (liniguists) እንዲያተኩሩበት በዚሁ እንተወዋለን” በማለት ምርምሩን ደመደምነው። ይሁንና ካለፉት ሃያ አምስት ዓመታት እስከ ዛሬ የቀረበ መልስ ስላላገኘንና፣ ጥያቄውም በአዕምሮአችን ሲብላላ ስለቆየ፣ የዚህ ጥያቄ መልስ ይህ ይመስላል ብለን የደረስንበትን ጭብጥ በዚህ የምርምር ጽሑፍ ለማቅረብ ተነሳን።

፩ኛ የታሪክ ምርምር

በተክለ ጻድቅ መኩሪያ የተጻፈው “የኢትዮጵያ ታሪክ፣ ኑብያ፣ (ናፓታ-መርዌ)” በተባለው መጽሐፍ በገጽ19-22 የካም ወገን የሆኑ 22 ነገሥታትን ስምጠቅሶ፣ 55 ዓመት ከገዛው ከአክናሁስ ወይም ሳባ ፪ኛ (1985-1930 BC) ከክርስቶስ ልደት በፊት አንስቶ የ29 ነገሥታትን ስም አስቅምጦ፤ “... ራማ የተባለ የህንድ ንጉሥ ወደ ኢትዮጵያ ዘምቶ ማሸነፉንና ሕዝቡን እንደ ባርያ ...” ይገዛው እንደ ጀመረ ያትታል። ከዚያ ግን ሦስት የዮቅጣን ልጆች ተባብረው ተነስተው እሸነፉት፥ ገድለውም፣ አግዓዝያን (ነፃ አውጭዎች) ተብለው መንግሥቱን እንደ ያዙ ገልጾ፣ ከዚያ ቀጥለው የነገሡትን የ52 የኢትዮጵያ ነገሥታት ስም ይዘረዝራል። ከፊተኞቹ 29 ነገሥታትም የመጀመሪያዎቹ 10 ነገሥታት የሚከተሉት ናቸው:-

The meaning of the name Ethiopia

ከዚህም ዓምድ እንደሚታየው ኢትዮጲስ ፩ኛ ከ1856-1800 ከክርስቶስ ልደት በፊት፣ ለ56 ዓመት መንገሡ፣ ኢትዮጲስ ፪ኛው ደግሞ ከ1730-1700 ከክርስቶስ ልደት በፊት፣ ለ30 ዓመት ያህል መንገሡ በታሪክ ተጽፏል። ይህንን ያላነበቡ ምሁራኖቻችን ግን ኢትዮጵያ ማለት ከግሪክ ቋንቋ የመጣ ቃል፤ ‘ፊቱ በፀሓይ የተቃጠለ፣ የተጠበሰ፣ ያረረ ማለት ነው’ ይሉናል።

ታላቁ የግሪክ ተራኪና ባለ ቅኔ፣ ሆመር የኖረው 800 - 700 ከክርስቶስ ልደት በፊት ሲሆን፣ የግሪክ ስልጣኔ ዘመን ወይም የሄሌኒስቲክ ኤጅ (Hellenistic Age) ተብሎ የሚታወቀውም ከታላቁ እስክንድር ዘመን አንስቶ፣ ማለትም 300-30 ከክርስቶስ ልደት በፊት ድረስ ያለው ጊዜ ነው። ይህ ማለት ኢትዮጲስ ፩ኛ ከባለቅኔው ከሆመር በፊት አንድ ሺሕ ዓመት ቀድሞ የነገሠ ንጉሥ ነው።

እንግዲያውስ ምሁራኖቻችን ኢትዮጵያ ማለት ከግሪክ ቋንቋ የመጣ፤ ‘ፊቱ በፀሓይ የተቃጠለ፣ የተጠበሰ፣ ያረረ ማለት ነው’ ሲሉን፣ ሊመልሷችው የማይችሉ ሁለት ጥያቄዎች አሉን፣

ምሁራኖቻችን እነዚህን ሁለት ጥያቄዎች ሲጠየቁ፣ “አፋፍ-ላፋፍ ስትሄድ አግኝቸ ሚዳቋ፣ በጅራቷ ብይዛት ዓይኗ ፍጥጥ አለ ...” እንደሚሉት ዓይናቸውን ከማፍጠጠና ከመቅበዝበዝ በቀር ሌላ የሚያድርጉት ሆነ የሚሰጡት ምንም መልስ የላቸውም።

በግሪክ ቋንቋ Αιθιοπία (አይትዮፕያ) ማለት ፊቱ በፀሓይ የተቃጠለ፣ የተጠበሰ፣ ያረረ ማለት ለመሆኑ አያጠያይቅም። ጥያቄው፤ የትኛው ቃል ከየትኛው መጣ? ነው። ግሪኮች የአገራችን ጥቁር ሰው አይተው ነው ቃሉን ወደ ቋንቋቸው ያስገቡት፣ ወይስ የአገራችን ነገሥታት ናቸው ስማቸውን ከግሪክ ቋንቋ ወስደው ለራሳቸው መጠሪያ ያደረጉት? ጥያቄው ይህ ነው!

የዚህ ዓይነቱ የተዛባ አስተሳሰብ የተላበሰ አንድ የሃይማኖት መሪ፤ “... ድንቅና ተአምር የሆነ የእግዚአብሔር ጥበብ የሚገርም ነገር አለ፣ ዓይናችን፣ አፍንጫችንና፣ ጆሮአችን እንዴት ብሎ ለመነጽር እንደሚገጥም ሆኖ መፈጠሩ ዕጹብ አይደለም?” እያለ ሰብኳል ይባላል። ይህ ግን የትኛው ቀዳሚ፣ የትኛው ኋለኛ መሆኑን ባለማወቁ ነው። መነጽር ነው ለዓይን፣ ለአፍንጫና ለጆሮ እንዲገጥም ሆኖ የተሠራ እንጂ፣ ፊታችን ለመነጽር እንዲገጥም ሆኖ አልተፈጠረም። ጥልቀት የሌለው ዐውቃለሁ ባይነት ግን ለእንዲህ ዓይነቱ መዘላበድ ያጋልጣል።

፪ኛ የቃላትና የፊዴላት ምርምር

በመጀመሪያ (Αιθιοπία) ‘አይትዮፕያ’‘ኢትዮጵያ’ የሚሉ ቃላት ለመሆኑ የአገራችን ቃላት ናቸው ወይ ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው። ለመሆኑ ከግዕዝ፣ ከአማርኛና፣ ከትግርኛ ቋንቋዎች “ጰ” ወይም “ፐ” የሚል ፊዴል ያላቸውን ቃላት ብንፈልግ ምን እናገኛለን?

በግዕዝፅ በትግርኛና በአማርኛ ፖሊስ ከሚል ቃል ሌላ ‘ፐ’ ፊዴል ያለበት ምን ቃል አለ? ምንም ያለ አይመስለንም። የአገራችን ሰውም ፓሊስ ከማለት ‘ቦሊስ’ ማለት ነው የሚቀናው፥ ኢትዮጵያ ከማለትም ይጦብያ ማለት ይቀልለዋል። ‘ፐ’ እና ‘ጰ’ የሚባሉ ፊዴላትም ወደ አገራችን የፊዴል ሰነድ የገቡት በቅርብ ጊዜ ከመሆኑም በላይ፥ የውጭ ቃላትን ለመጻፍ እንዲያመቹ ተብሎ መሆኑ ግልጽ ነው። በፊደላት ሰንጠረጅም ከሁሉ በታች፣ ወይም ከመጨረሻ ቦታ መስፈራቸው ኋላ የመጡ ለመሆናቸው ተጨማሪ ማስረጃ ነው።

Trapezium‘ጰ’ የሚል ፊዴል ያላቸውን ቃላት የአገራችን ቋንቋዎች ብንፈልግም፤ ጴጥሮስ፣ ጳውሎስ፣ ቆጵሮስ፣ ጠረጴዛ ወዘተ... እናገኛለን። ይሁንና እነዚህ ሁሉ የውጭ ቃላት፣ ከመካከለኛው ምስራቅና ከኤውሮጳ የገቡ እንጂ የአገራችን ቃላት አይደሉም። ‘ጠረጴዛ’ የሚል ቃልም ትራፔዞይድ (trapezoid: a rectangular shaped object) ከሚለው የላቲን/የእንግሊዝኛ ቋንቋ የተገኘ እንጂ በመሰረቱ የአማርኛ ቃል አይደለም። በጥንታዊ ግዕዝ ጽሑፍም ስንመለከት፤ ‘ክሊዎፓትራ፣ የፕቶሎሚ ልጅ’ ለማለት፤ “አከልኡበጥራ፣ ወለተ በጥሊሞስ” ይላታል። ይህ የሚያሳየው “ፐ” የሚባል ፊዴል በጥንታዊ የአገራችን ቋንቋዎች ፈጽሞ እንዳልነበረ ነው። ክሊዎፓትራና አባቷ ፕቶሎሚ ግን ዘራቸው ግሪክ፣ ታላቁ እስክንድር ግብፅን አሸንፎ ከዚያው በኋላ ተክሏቸው የሄደ የግሪክ ገዢዎች ስለሆኑ፣ ስማቸው የግሪክ ስም ነው። ‘ፐ’ የሚል ፊዴልም አለበት።

ይህንን የፊዴላት ጥያቄ ያመጣነው ጥንታዊው የሁለቱ ነገሥታት ስም አጠራር ‘ኢትዮጲስ’ ወይም ‘ኢትዮፒስ’ ሊሆን እንደማይችል ለማስረዳት ነው። እንግዲያውስ ከዚህ የቃላት ምርምር የምናገኘው ነገር ካለ ይኽ ነው፤ በትክክለኛው ጥንታዊ አባባል ኢትዮጲስ፣ ኢይቶጲስ፣ ኢቶፒስ፣ አይቶፒስ... የሚሉ ስሞች ፈጽሞ የአገራችን ንገሥታት ስም ሊሆኑ እንደማይችሉ ነው።

ስለ ‘ጠ’ ፊዴል ካነሳን ደግሞ በግሪክ ቋንቋና በሌሎችም የኤውሮጳ ቋንቋዎች ‘ጠ’ የሚል ድምፅ የላቸውምና ‘ጠ’ የሚለውን በ ‘ተ’ እና ‘ፐ’ በሚሉ ፊዴላት ይተኳቸዋል። እንግዲያው ትክክለኛው አባባል ‘ይቶፒስ’ ሳይሆን “ይጦብስ” መሆን ይገባዋል እንላለን። ግሪኮች ‘ጠ’ ማለት ስላልቻሉ ነው (Αιθιοπία) ‘አይትዮፕያ’ ያሉት። እኛም ይኸው እስከ ዛሬ ኤውሮ‘ፓ’ ከማለት ኤውሮ‘ጳ’ እንደሚቀናን ማለት ነው።

የውጭ ታሪክ ጸሓፊዎች እነ ዮሴፍ ሃለቪ (Josph Halevi)፣ እኖ ሊትማን (Enno Litman)፣ ኤድዋርድ ግላሴር (Edward Glaser)፣ ኮንቲ ሮሲኒ (Conti Rossini)፣ ጂ. ሪክማንስ (G. Rickmans) የመሳሰሉትና ሌሎችም የውጭ አገር ሰዎች ያቀረቡት ጽሑፍ ይጦብያ ለማለት ስላልቻሉ ይቶፕያ፣ ኢቶፕያ፣ ሆኖ ወደ ቋንቋችን ሲተረጐም ‘ኢትዮጵያ’ ተብሎ ሊጸና ቻለ እንጂ ይህ ስም ትክክለኛ የአገራችን ይሁን የንጉሦቻችን ስም እንዳልሆነ ግልጽ ነው።

በአገራችን ታሪክ የምናገኘው ሓቅ ደግሞ፣ “ይጦብያ”፣ “ይጦብስ” የሚል ስም ለሕዝብና ለአገር ቀርቶ ለተራ ንጉሥም የማይሰጥ እንደ ነበረ ነው። ሕዝቡ ነገደ አግዓዝያን፣ አገሩ ብሔረ አግዓዚ፣ ቋንቋው ልሳነ ግዕዝ ነበር። ነገሥታቱም በየክፍለ-ሃገሩ ስም፤ የትግራይ ንጉሥ፣ የወሎ ንጉሥ፣ የጎጃም ንጉሥ፣ የሸዋ ንጉሥ... ወዘተ፣ ይባሉ ነበር። “ይጦብያ” ተብሎ የሚታወቀው ሁሉን የጠቀለለ ንጉሠ-ነገሥቱ ብቻ ነበር። ይህም የጥንቱን የይጦብስ ንጉሥን ጠቅላይ ስም ወራሽነት መያዙ ለማሳየት ሆን ብሎ የተደረገ ብልሓት ይመስላል።

ይጦብስ ማለትስ ምን ማለት ነው? በግዕዝ በትግርኛና በአማርኛም “መጥበስ” የሚል ቃል አለ። ቃሉም ሲራባ፤ ጠበሰ፣ ተጠበሰ፣ ይጠብስ፣ ትጠብስ፣ ጥቡስ፣... ወዘተ፣ እያለ ይራባል። እንግዲያውስ ይጦብስ ማለት ጥንታዊ ትርጉሙ፤ ይጠብሳል፣ ያቃጥላል፣ ኃይለኛ ንጉሥ ነው! ተብሎ ጠላቶችን ለማስፈራሪያ የወጣ ስም ይመስላል እንጂ ከግሪክ ቋንቋ ተወስዶ ለአገራችን ነገሥታት ‘ፊቱ የተጠበሰ፣ በፀሓይ የተቃጠለ’ ተብሎ የተሰጠ ስም ነው ማለት አይቻልም።

ይህንን የምንለው ኢትዮጵያ የሚለው ቃል ከግሪኮች የመጣ ነው ለሚሉት አጉል ምሁራን ስሕተታቸውን ለማሳየት ነው እንጂ፣ በየዘመናቱ ኢትዮጵያ የሚለው ቃል ልዩ-ልዩ ትርጉሞች እንደ ተሰጡት አይጠረጠርም። ለምሳሌ ኢትዮጵያ ማለት መልካም መዓዛ ያለው ዕጣን ነው የሚሉ አሉ። የለም፣ ታላቅና ጠቅላይ ማለት ነው የሚሉም አሉ። ከዘመናት ብዛትልዩ-ልዩ ትርጉሞች እንደተሰጡት አያጠራጥርም። የሚደንቀው ነገር ግን መሃነስ/መሃንደስ የሚል ቃል ዓለምን ዞሮ ወደኛ መሃንድስ ሆኖ ሲመለስ ህንፃ የሚለውን ትርጉሙን እንዳልሳተ፣ ‘ይጦብስ’ የሚለውም ቃል እንዲሁ የቃሉ አባባል ትንሽ ተወላግዶ በግሪኮች አነጋገር ‘ይቶፒስ’ ቢባልም የመቃጠልና የመጠበስ ትርጉሙን ሳይስት እንደ ተቀመጠ ለብዙ ዘመናት የቆየ ይመስላል።

እዚህ ላይ ‘ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ?’ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው። ምናልባት በይጦብስ ዘመን የአገራችን ተጓዦች ወይም ነጋዴዎች ከግሪክ ሰዎች ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ሲገናኙ፤

ከዚያ ወድያ ግሪኮችጠቆር ያለውን ሰው ባዩ ቁጥር (Αιθιοπίs) “ይጦብስ” እያሉ መጥራት ጀምረው፣ ቃሉም ወደ ቋንቋቸው ከመግባቱም በላይ፣ “ይጠብስ” የሚለውን ጥንታዊውን ትርጉም ሳይስት ለጥቁር አፍሪካዊ ሁሉ ‘ፊቱ የተጠበሰ፣ በፀሓይ የተቃጠለ’ (Αιθιοπία) ‘ኢትዮጵያ’ የሚል መጠሪያ ለመሆን የበቃ ነው የሚመስል።

ምርምራችን በዚህ ያበቃል።

ምንጭ፡ 

ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ የሰው ልጅ ከነበረባችው ቦታዎች አንዷ መሆኗ ትታወቃለች። የሰው ፍልሰት ጥናቶች ፣ የቅሪተ አካል ጥናቶችና ሌሎች የሳይንሳዊ ዘዴዎች ይህን ያረጋግጣሉ። ድንቅነሽ የምትባለው በአፋር ክልል ውስጥ የተገኘችው አጽም በአለም በዕድሜ ሁለተኛ ጥንታዊ ናት። ከ 3.2 ሚሊዮን ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ እንደኖረች ይገመታል። ሌሎችም ታዋቂ አጽሞች በኢትዮጵያ ተገኝተዋል።
ከዚህም በተጨማሪ ኢትዮጵያ የክርስትና እምነት ደሴት በመሆን የቆየች ታላቅ ሀገር ናት።

በ ፰፻ (800) ዓመተ-ዓለም አካባቢ ደአማት የሚባል መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያና ኤርትራ ተቋቋመ። በሰሜን ኢትዮጵያ የምትገኘው የሀ የደአማት ዋና ከተማ ነበረች። በየመን የሚኖሩት ሳባውያን በደአማት ላይ ተፅዕኖ እንደነበራቸው የሚታመን ሲሆን ይህ ተፅዕኖ ምን ያህል እንደሆነ ግን በእርግጥ አይታወቅም። ወደ ፬፻ (400) ዓመተ-ዓለም አካባቢ የደአማት መንግስት ከስልጣን ሲወድቅ በትናንሽ መንግስቶች ተተካ። ከነዚህ ትናንሽ መንግስቶች አንዱ አክሱም ሲሆን አካባቢውን እንደገና በአንድነት ለመግዛት ችሎ ነበር።

የአክሱማውያን ስፈን በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ጠንካራ መንግሥታዊ ማኅበረሰብ ነበር። በፋርስ ፣ ሮማ እና ቻይና ይገኙ ከነበሩ ታላላቅ መንግሥታት በወደረኛነት የሚቆጠር ትልቅ ኅይል ነበር። በ4ኛው ምእተ-ዓመት አክሱም ወደ ክርስትና ተለወጠ። በ፮ኛው ምእት ዓመት የአክሱማውያን ግዛታዊ ቁጥጥር የዛሬዋን የመን ግዛት ይጨምር ነበር። ግን በ፮ኛው እና በ ፰ኛው አምኣት የአክሱም ሥልጣኔ በእስልምና መነሣት እና መስፋፋት ተዳክሞ ለውድቀት በቃ ። ተከታዩ የዛጔ ሥርወ-መንግሥት ልክ በድንገት እንደተነሳ በድንገት ሲያበቃ ፣ ይኵኖ አምላክ ሥልጣን በ ፲፪፻፷፪ (1262) ዓ. ም. ጨበጡ ፤ እንዲያም ሲል የሰለሞናዊው ሥርወ-መንግሥትን መለሱ።
ከዚያም ለብዙ ዘመናት የሰለሞናዊው መንግስት ከጠለ።

በ ፲ ፭ኛው ምዕተ-ዓመት መጀመሪያ ኢትዮጵያ ከአክሱም ጊዜ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአውሮፓ ጋር ግንኙነት ጀመረች። ከእንግሊዝ ንጉሥ ሄነሪ አራተኛ (Henry IV) ወደ የአቢሲኒያ ንጉሠ-ነገሥት የተላከ ደብዳቤ እስከ ዛሬ ድረስ አለ። በ1428 እ.ኤ.አ. አፄ ይስሐቅ ወደ የአራጎን ንጉሥ አልፎንዞ አምስተኛ (Alfonso V) ሁለት መልክተኞች ልከው ነበር። ግን የመጀመራያው ያልተቋረጠ ግንኙነት በአፄ ልብነ ድንግል ስር ከፖርቱጋል ጋር ከ1508 እ.ኤ.አ. ጀምሮ ነው የተካሄደው።

ኢትዮጵያ በአህመድ ግራኝ ስትጠቃ ፣ ፖርቱጋል አራት መቶ ወታደሮችና የጦር መሳሪያ በመላክ ኢትዮጵያን ረድታለች። አፄ ሱስንዮስ በፖርቱጋልና እስፓንያ ተጽዕኖ እና ተጨማሪ እርዳታ ከመፈለጋቸው የተነሳ ወደ የሮማ ካቶሊክ ክርስትና ተለወጡ ፤ የኢትዮጵያ ይፋ ሀይማኖትንም አደረገቱት። ይህ ውሳኔ ወደ ግዙፍ ተቃውሞና ጦርነት አመራ። በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ከሞቱ በኋላ ፣ የአፄ ሱስንዮስ ልጅ አፄ ፋሲለደስ በ 1632 እ.ኤ.አ. ኢትዮጵያ ወደ አርቶዶክስ ክርስትና መመለሷን አወጁ። አውሮፓውያኖቹንም ከኢትዮጵያ አስወጡ።

ከ ፲፯፻፶፭ (1755) እስከ ፲፰፻፶፭ (1855) እ. ኤ. አ. ኢትዮጵያ እንደገና ከአለም ጉዳዮች ተገላ ነበር። ይህ ጊዜ «ዘመነ-መሳፍንት» ይባላል ምክኒያቱም የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥቶች በራስ ሚካኬል ስሁል ፣ ራስ ወልደ ሥላሴ ፣ ራስ ጉግሳ እና በመሳሰሉት ቁጥጥር ስር ነበሩ። ራስ ጉግሳ በ፲፯ኛው ክፍለ ዘመን ጎንደርን በመምራታቸው የቤተ-መንግሥቱን ቋንቋ ከአማርኛ ወደ ኦሮምኛ ለውጠው ነበር።

የኢትዮጵያ ግለልኘነት ያበቃው ከእንግሊዝ ጋር ግንኙነት ስትጀምር ነው። ኢትዮጵያ እንደገና የተዋሀደችው እንዲሁም የዘውዱ ስልጣን የተጠናከረው በ ፲፰፻፶፭ (1855) እ. ኤ. አ. በአፄ ቴዎድሮስ ምክኒያት ነው። የሰሜን አሮሞዎችና ትግሬዎች አመፅና የግብፆች ተደጋጋሚ ድንበር መጣስ የአፄ ቴዎድሮስ ስልጣን እንዲዳከም አደረጉት። በመጨረሻም ከእንግሊዝ ጋር በነበረው ጦርነት እስረኛ አልሆንም ብለው አፄ ቴዎድሮስ እራሳቸውን አጠፉ። በ ፲፰፻፷፰ (1868) እ. ኤ. አ. ኢትዮጵያና ግብፅ ጉራ በሚባለው ቦታ ተዋጉ። በአፄ ዮሐንስ አራተኛ የተመሩት የሰሜን ኢትዮጵያ ኃይሎች ድል ተቀናጁ።

በ ፲፰፻፹፱ (1889) እና በ ፲፰፻፺ (1890) ዎቹ እ.ኤ.አ. መጀመሪያ ፣ የሸዋ ንጉሥ ሳህለ ሥላሴ ከዚያም ዳግማዊ አፄምኒልክ በራስ ጎበና እርዳታ አማካኝነት ሀገሯን ወደ ደቡብና ምሥራቅ ማስፋፋት ጀመሩ። ከአህመድ ግራኝ ወረራ በኋላ በኢትዮጵያ ቁጥጥር ስር ያልነበሩ ፣ ሌሎች ደግሞ በማንኛው ጊዜ በኢትዮጵይ ቁጥጥር ስር ያልነበሩ ቦታዎች በዳግማዊ አፄ ምኒልክ አገዛዝ ጊዜ በኢትዮጵያ ስር ሆኑ። ከዚህ ጊዜ በኋላ የኢትዮጵያ ድንበር ብዙ አልተለወጠም። ከ ፲፰፻፹፰ (1888) እስከ ፲፰፻፺፪ (1892) እ. ኤ. አ. ድረስ የነበረው የሰፋ ድርቅ ከኢትዮጵያ ህዝብ በአንድ ሶስተኛ የሚገመተውን ቀጥፎአል።

በ ፲፰፻፹ (1880) ዎቹ እ. ኤ. አ. የአውሮፓ መንግሥቶች በበርሊን ጉባኤ ተስማምተው አፍሪካን በቅኝ ገዢነት መከፋፈል ጀመሩ። በኢትዮጵያ እና ጣልያን መካከል የነበሩ የዚያ ዘመን ውዝግቦች ወደ አድዋ ጦርነት በ ፲፰፻፹፰ (1888) ዓ. ም. አመሩ። በጦርነቱ የጣልያን ትልቅ ዘመናዊ ጦር በኢትዮጵያ ጦር ትልቅ ሽንፈት የደረሰበት መሆኑ ዓለምን አስደነቀ።

በ ፳ኛው ምእት ሁለተኛው ሩብ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ኢትዮጵያን ከልጅ ኢያሱ በኋላ መምራት ጀመሩ። ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ለአፍሪካ ሕብረት መቋቋም ትልቅ ሚና ተጫውተዋል።

የኢትዮጵያ ነጻነት በጣልያን ወረራ ከ ፲፱፻፴፮ (1936) እስከ ፲፱፻፵፩ (1941) እ. ኤ. አ. ድረስ ቢጠቃም በጀግኖችዋ መከታ ተጠብቋል። በአዚህ ጥቃት ጊዜ ዓፄ ኃይለሥላሴ በ ፲፱፻፴፭ (1935) እ. ኤ. አ. በሊግ ኦፍ ኔሽንስ (League of Nations) ፊት የሚታወስ ንግግር በአማርኛ አደረጉ። ይህ ንግግር በዓለም ታዋቂ አደረጋቸው። እንዲሁም በ ፲፱፻፴፭ (1935) እ.ኤ.አ. በ ታይም (Time) መጽሄት «የዓመቱ ሰው» አስባላቸው። ጣልያን ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ውስጥ መሳተፍ ስትጀምር ፣ እንግሊዝ ከኢትዮጵያዊ ተዋጊዎች ጋር ኢትዮጵያን ነጻ አወጣች። ግን እስከ ፲፱፻፵፫ (1943) እ. ኤ. አ. ድረስ አንዳንድ ጣልያኖች በደፈጣ ያለ ስኬት ይዋጉ ነበር። በ ፲፱፻፵፪ (1942) እ. ኤ. አ. ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ባርነት እንደ ተከለከለ አወጁ።

ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ጀግና ሆነው ቢታዩም ፣ የ ፲፱፻፸፫ (1973) እ.ኤ.አ. ዓለም አቀፍ የነዳጅ ቀውስ ፣ የምግብ ዕጥረትና የድንበር ጦርነቶች ተቃውሞ አስነሱ። ከዚያም በ ፲፱፻፸፬ (1974) እ. ኤ. አ. በሶቪየት ሕብረት የተደገፈውና በመንግስቱ ኃይለ ማርያም የተመራው ደርግ (ደርግ ማለት ኮሚቴ ማለት ነው) ዓፄ ኃይለ ሥላሴን ከስልጣን አስወረደ።

የተለያዩ መፈንቅለ መንግሥቶች ፣ የሰፋ ድርቀትና ስደተኞች የደርግ ሥርዓት ትልቅ ችግሮች ነበሩ። በ ፲፱፻፸፯ (1977) እ. ኤ. አ. ሶማሊያ ኦጋዴንን በመውረሯ የኦጋዴን ጦርነት ተነሳ። በሶቪየት ሕብረት ፣ ኩባ ፣ ደቡብ የመን ፣ ምስራቅ ጀርመንና ሰሜን ኮሪያ የመሳሪያ እርዳታ እንዲሁም ወደ ፲፭ ሺህ በሚቆጠሩ የኩባ ወታደሮች ድጋፍ አማካኝነት ደርግ ኦጋዴንን እንደገና መቆጣጠር ቻለ።

በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች በቀይ ሽብር ፣ የግዴታ ስደት ፣ ወይም ረሀብ ሞተዋል። መንግስቱ ቀይ ሽብር ያካሄደው በተቀዋሚዎች በተፈጸመው ነጭ ሽብር መልስ እንደሆነ ጠቅሷል። በ ፳፻፮ (2006) እ. ኤ. አ. መንግስቱ ኃይለ ማርያም በሌሉበት የሞት ቅጣት ተፈርዶባቸዋል።

በ ፲፱፻፹ (1980) ዎቹ መጀመሪያ የተከሰቱ ድርቀቶች ምክኒያት ስምንት ሚሊዮን የሚሆን ሕዝብ ሲራብ ፣ አንድ ሚሊዮን ደግሞ ሞተዋል። ተቃውሞ በትግራይና ኤርትራ ክልሎች ተስፋፋ። በ ፲፱፻፹፱ (1989) እ. ኤ. አ. ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ከሌሎች እንቅስቃሴዎች ጋር በመቀናጀት የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባርን መሠረተ። የሶቪየት ሕብረትም ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ድጋፍ መቀነስ ጀመረች። የኢኮኖሚ ችግሮች ተከሰቱ ፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት ተዳከመ። 

በሜይ ፲፱፻፺፩ (1991) እ. ኤ. አ. የኢ. ህ. አ. ዴ. ግ. ጦር ወደ አዲስ አበባ አመራ። የመንግስት ኃይሎች ምንም አይነት የውጭ እርዳታ ስላላገኙ ፣ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ.ን ጥቃቶች መቋቋም አልቻሉም። መንግስቱ ኃይለ ማርያም ወደ ዚምባብዌ ሄደው እስከ ዛሬ ድረስ በዛችው ሀገር ይኖራሉ። ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ. ፹ ፯ አባላት ያሉት የሽግግር መንግሥት መሠረተ። በጁን ፲፱፻፺፪ (1992) እ. ኤ. አ. የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፣ እንዲሁም በማርች ፲፱፻፺፫ (1993) እ. ኤ. አ. የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ኅብረት የሽግግር መንግሥቱን ለቀው ወጡ። በ ፲፱፻፺፬ (1994) እ. ኤ. አ. ሁለት የሕግ አውጪ ምክር ቤቶችንና የፍትሕ ስርዓትን የሚደነግግ አዲስ ሕገ መንግሥት ተፃፈ። የመጀመሪያው ምርጫ በሜይ ፲፱፻፺፭ (1995) እ.ኤ.አ. ተካሄደ። አቶ መለስ ዜናዊ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሁም ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ።

በየተባበሩት መንግሥታት ውሳኔ ኢትዮጵያና ኤርትራ በፌደሬሽን ተዋህደው ነበር። በ ፲፱፻፺፫ (1993) እ.ኤ.አ. በተካሄደውና የተባበሩት መንግሥታት በታዘበው ሕዝበ ድምፅ ፣ 

በወቅቱ ስልጣንን በጠመንጃ አፈሙዝ የያዙትና የኤርትራን መገንጠል በሚፈልጉት በህውአትና ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ አማካይነት ለኤርትራ ህዝብ ‹ባርነት› ወይንስ ‹ነፃነት› ተብሎ እንዲመርጡ ተገደው ማንም ባርነትን የሚመርጥ የለምና ነፃነትን መረጡ ተባሎ  በረሃ ገብተው ሲታገሉለት የነበረውን አላማ ስልጣናቸውን በመጠቀም አስፈፅመው ከ ፺፱ ከመቶ በላይ የሚሆነው የኤርትራ ሕዝብና በውጭ ሀገር የነበሩ ኤርትራውያን ከኢትዮጵያ መገንጠልን መርጠዋል። በሜይ ፳፬ ፣ ፲፱፻፺፫ (1993) እ. ኤ. አ. ኤርትራ ከኢትዮጵያ ነፃነቷን አወጀች።

በሜይ ፲፱፻፺፰ (1998) እ. ኤ. አ. የድንበር ውዝግብ እስከ ጁን ፳፻ (2000) እ. ኤ. አ. ወደ ቀጠለው የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት አምርቶአል። ይህ ጦርነት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚን ጎድቶአል። በሜይ ፲፭ ፣  ፳፻፭ (2005) እ.ኤ.አ. አጠቃላይ ምርጫ ቢካሄድም ተቃዋሚዎች ማጭበርበር እንደነበረ ወንጅለዋል። በአጠቃላይ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ከ ፪፻ (200) በላይ የፓርላማ መቀመጫዎችን አሸንፈዋል። ግን አንዳንድ የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ አባሎች ከምርጫው በኋላ ከነበረው ረብሻ ጋር በተያያዘ ታስረው ነበር። በአሁኑ ጊዜ ያለው የፖለቲካ ስርአት በብሄር ላይ የተመሰረተ ፌደራላዊ ስርአት ነው፡፡

ኢትዮጵያ በሰሜን ምስራቅ አፍሪካ ከ 3-14 ዲግሪ ሰሜን እና ከ 33-48 ዲግሪ ምሥራቅ የምትገኝ አገር ስትሆን የቆዳ ስፋቱዋም 1,127,127 ካሬ ኪ.ሜ. ነው። በሰሜን ከኤርትራ ፣ በምዕራብ ከሱዳንና ደቡብ ሱዳን ፣ በደቡብ ከኬኒያ ፣ እንዲሁም በምሥራቅ ከጅቡቲ እና ከሶማሊያ ጋር ትዋሰናለች። የኢትዮጵያ አብዛኛው ግዛት በተራሮች እና አንባዎች የተሞላ ሲሆን ፣ ታላቁ የምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ እነዚህኑ ከፍተኛ ቦታዎች ከሰሜን ምሥራቅ ወደ ደቡብ ምዕራብ በመጋደም ለሁለት ይከፍላቸዋል። በስምጥ ሸለቆው ዙሪያም በረሃማ የሆኑ ዝቅተኛ ቦታዎች ይገኛሉ። ይሄን መሰሉ የመልክዓ-ምድር ልዩነት አገሪቷ የተለያዩ የአየር ንብረት ፣ የአፈር ፣ የዕፅዋት እና የሕዝብ አሰፋፈር ገጽታዎች እንዲኖሯት አስችሏታል። በከፍታና በመልክዓ-ምድራዊ አቀማመጥ የተነሣ በኢትዮጵያ ውስጥ ሦስት ዓይነት የአየር-፡ ንብረት ክልሎች ይገኛሉ። እነሱም፦

ዋናው የዝናብ ወቅት ከሰኔ አጋማሽ እስከ መስከረም አጋማሽ ሲሆን ፣ ከሱ ቀደም ብሎ አልፎ አልፎ የሚጥል የበልግ ዝናብ በየካቲት እና በመጋቢት ይከሰታል። የተቀሩት ወራት በአብዛኛው ደረቅ ናቸው።

ሲዳማ ተጨማሪ ክልል ናት== አስተዳደራዊ ክልሎች ==

ከ ፲፱፻፺፮ (1996) እ.ኤ.አ. በፊት ኢትዮጵያ በ ፲፬ ክልሎች ተከፍላ ነበር። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጽያ ውስጥ ፱ አስተዳደራዊ ክልሎች ይገኛሉ። አወቃቀራቸውም በህገ-መንግስቱ በተደነገገው መሰረት «በህዝብ አሰፋፈር ፤ ቋንቋ ማንነት እና ፈቃድ ላይ» ተመስርቶ ሲሆን ክልሎቹም፦

ኢትዮጵያ ከ ፹ (80) በላይ የሚሆኑ ብሔረሰቦች የሚገኙባት «የብሄረሰቦች ሙዚየም» ልትሰኝ የቻለች ሀገር ነች። ትልልቆቹ ብሄረሰቦች ፣ የአማራ ፣ እና የኦሮሞ የትግራይ እንደሁም የሶማሌ ሲሆኑ እነዚሁ ብሄረሰቦች ከጠቅላላው የሀገሪቷ ሕዝብ ቁጥር ከ 3/4ኛ በላይ የሚሆነውን ይይዛሉ።
በሃይማኖት በኩልም ሁለቱ ትልልቅ ሃይማኖቶች ክርስትና እና እስልምና በስፋት የሚስተዋልባት አገር ናት። የክርስትና እምነት ተከታዮች ከ 55%-60 % ፣  እስልምና ከ35% እሰከ 40% እንዲሁም የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ወደ 5%-8% የሚሆነውን ይይዛሉ።

በኢትዮጵያ ውስጥ ከ ፹ በላይ ብሔር ብሔረሰቦች የሚኖሩ ሲሆን በቋንቋም በኩል ከ ፹ በላይ የሚሆኑ ቋንቋዎች የሚነገሩባት ሀገር ናት። በአሁኑ ወቅት በአብዛኛው ኢትዮጵያውያን የሚነገሩት ቋንቋዎች አማርኛ እና ኦሮምኛ ሲሆኑ ፤ አማርኛ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ያሉ ነዋሪዎች የመማሪያ ፤ የመገበያያ እንዲሁም የስራ ቋንቋ ሆኖ የቆየ በመሆኑ በአሁኑ ወቅት የስራ ቋንቋ ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ የሚነገሩት ቋንቋዎች አፍሮ-ኤስያዊ እና ናይሎ ሳህራዊ በሚባሉ ሁለት ዋና የቋንቋ ክፍሎች ሊካተቱ ይችላሉ። በአፍሮ-ኤስያዊ የቋንቋ ቤተሰብ ውስጥም ኩሻዊ፣ ኦሞአዊ እና ሴማዊ የሚባሉ ንዑስ ክፍሎች አሉ።

ኩሻዊ ከሚባሉት ቋንቋዎች ዋና ዋናዎቹ አፋን ኦሮሞ ፣ ሶማልኛ ፣ አፋርኛ ፣ ሲዳምኛ ፣ ሃዲያኛ እና ከምባትኛ ሲሆኑ ከአባይ-ሰሃራዊ የቋንቋ ምድብ የሚካተቱት በርታኛ ፣ ኩናማኛ ፣ ጉሙዝኛ ፣ ሙርሲኛ እና የመሳሰሉት ናቸው። እንደ ወላይትኛ ፣ ጋሞኛ]፣
ጎፍኛ ፣ ከፋኛ ፣ ሃመርኛ የመሳሰሉት የኦሞአዊ ቋንቋ ዘሮች ሲሆኑ አማርኛ ፣ ትግርኛ ፣ ጉራጊኛ ፣ ስልጢኛ ፣ ሀደሪኛ፣ አርጎብኛ፣
ጎፍኛ እና መሰል ቋንቋዎች ከሴማዊ ቋንቋዎች ይመደባሉ። ዘጋቢ በአወል ሙሀመድ ደራ

የሴሚቲክ ምንጭ ያላቸው እንደ ትግርኛና አማርኛ ያሉት ቋንቋዎች የራሱ የሆነ የተለየ የፊደል ስርአት ያላቸው ሲሆን ይህም ኢትዮጵያን ከአፍሪቃ ብቸኛዋ ባለ ጥንት ፊደል ሀገር ያደርጋታል። እነኚህ የሴሚቲክ ምንጭ ያላችው ቋንቋዎች ግዕዝ የተባለ በአሁኑ ወቅት ከቤተክርስትያን ውጭ ለዕለት ተዕለት ግልጋሎት ላይ የማይውል ግንድ ዘር አላቸው።

በኣሁኑ ጊዜ ግዕዝ በዩኒኮድ ዕውቅና ያገኙትን የቢለን፣ ቤንች፣ ምኢን፣ ሙርሲ፣ ሱሪ፣ ትግረ፣ ትግርኛ፣ ኣገው፣ ኣውንጂ፣ ኦሮሚፋ፣ ዓማርኛ፣ ዲዚ፣ ዳውሮ፣ ጉሙዝ፣ ጉራጌ፣ ጋሞ ጎፋ እና ግዕዝ ቋንቋዎች የሚጋሯቸውን ቀለሞችና ሌሎች ያጠቃልላል። በፊደሉ ከሚጠቀሙ ቋንቋዎች መካከል ሓረሪ ኣንዱ ነው። መጽሓፍ ቅዱስ ሙሉዉን ወይም በከፊል ከ፲፭፻፮ ዓ.ም. ጀምሮ በግዕዝ ቀለሞች በማተሚያ ቤቶች ከታተሙባቸው ቋንቋዎች መካከል ሃዲያ፣ ሲዳሞ፣ ከምባታ፣ ኦሮሞ፣ ወላይታ እና ጌዴኦ ይገኙበታል። (ደግሞ ኣበራ ሞላ ይዩ።)

በእጅ ጽሑፍና ማተሚያ ቤቶች ብቻ ይቀርብ የነበረው የግዕዝ ፊደል በ፲፱፻፹ ገደማ ኮምፕዩተራይዝድ ስለሆነ ኣጠቃቀሙ ወደ ኮምፕዩተር ዞሯል። ከእዚያም ወዲህ ፊደሉ የዩኒኮድ የዓለም ፊደላት መደብ ውስጥ ስለገባ እያንዳንዱ ቀለም የእራሱ ስፍራ ኣለው። () ይህ የኣማርኛ ውክፔድያ ድረገጽም የቀረበው በእዚሁ ፊደል ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህም ፊደሉን በእጅ ስልክ መጠቀም ተችሏል። ለፊደሉ ኣጠቃቀም ኣስፈላጊ ሆነው የተፈጠሩ ኣዳዲስ የቴክኖሎጂ ዘዴዎችም የዩናይትድ እስቴትስ የባለቤትነት መታወቂያ ወይንም ፓተንት ማግኘት ጀምረዋል።  




#Article 9: ድረ ገጽ መረብ (273 words)


የድረ ገጽ መረብ (ወይም ኢንተርኔት) በጣም ብዙ የኮምፒዩተር አውታሮችን ያያየዘ የመገናኛ መረብ ነው። በመረቡ ውስጥ ብዙ ድረ ገጽ ይገኛሉ። ከዚያ በላይ በርካታ የመነጋገርና መገናኘት መንገዶች አሉ። 

ከሁሉ አስቀድሞ የተፈጠረ ክፍለ-ኢንተርኔት «USENET» የሚባለው አገልግሎት ነው። ይህ በ1973 ዓ.ም. (1980 እ.ኤ.አ.) አካባቢ ሲጀመር በተለይ ለዩኒቨርሲቴዎችና ኮሌጆች ብቻ የታወቀ መገናኛ ሆኖ ቆየ። ይህ ጽሑፍ በተገናኙት ኮምፒውተሮች ላይ መልጠፍ የሚፈቅድ ሥርዓት ብቻ እንጂ ስዕል ወይም ሌላ ነገር አልነበረም። መጀመርያው e-mail አድራሳዎች የተሰጡት ከዚያ ዘመን ነው። ዛሬም ብዙዎች ተጠቃሚዎቹ ግን ስንኳ ስለ USENET መኖሩን አያውቁም።

መጀመርያው ድረ ገጽ የተፈጠረው በ1983 ዓ.ም. (1990 እ.ኤ.አ.) ሆነ።

ኢንተርኔት እንዴት እንደሚሰራ ለመረዳት በመጀመሪያ አገልጋይና (server) ደንበኛ (client) ምን እንደሆኑ ለይተን እንረዳ። አንድ የምግብ ቤት አስተናጋጅ ምግብ ለብዙ ተስተናጋጆች እንደሚያቀርበው፣ ሁሉ ኢንተርኔት ላይ ያለ አገልጋይ (server) የተለያዩ ነገሮችን ደንበኞቹ (clients) ይሰጣል። የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ደንበኞች ይባላሉ ማለት ነው። 

ደንበኞች የተለያየ ነገር ከአገልጋዩ ሊቀበሉ ይችላሉ። ለምሳሌ፤ እርስዎ ይህንን ድረ ገጽ ሲመለከቱ የቻሉት አገልጋዩን ድረ ገጹን እንዲልክልዎ በመጠየቅዎ ነው። በመሆኑም ይሄ አገልጋይ «ድረ ገጽ አገልጋይ» (web server) ይባላል። ሌላ አገልጋይ ደሞ መልአክት (email) ሊያቀብል ይችላል። ስለዚህም «መልአክት አገልጋይ» ይባላል።

ኢንተርኔት የአገልጋይና የደንበኞች መረብ ነው። በአብዛኛው የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ድረ ገጽ (WWW or World Wide Web) ይጠቀማሉ። ስለዚህም ደረ ገጽ የኢንተርኔት ትልቁ ጥቅም ነው። ብዙ ጊዘም ኢንተርኔትና ድረ ገጽ በስህተት አንድ መስለው ይታያሉ። ነገር ግን መረቡ፤ ማለትም ኢንተርኔት፤ ለሌላ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል። ለምሳሌ ከላይ የተጠቀሰው (USENET) የኢንተርኔት ሌላው ጥቅም ነው።

ከአንድ አገልጋይ የሚፈልጉትን ነገር ለመጠያቅ በመጀመሪያ የአገልጋዩን መጥራት ያስፈልጋል። እያንዳንዱ አገልጋይ ልዩ የሰነድ አድራሻ (URL) አለው። ይሄን የሰነድ አድራሻ በመጠቀም ከየትኛውም ቦታ አገልጋዩን መጥራት ይቻላል። ለምሳሌ www.wikipedia.org የውክፔድያ አገልጋይ የሰነድ አድራሻ ነው። አንዳንዴ አንድ ነገር ፈልገን የትኛው የሰነድ አድራሻ ላይ አንደምናገኘው ላናውቅ እንችላለን። በዚህ ጊዘ ፈላጊዎችን (search engines) እንጠቀማለን። ለምሳሌ www.google.com ጉግል ላይ የሰነድ አድራሻዎችን መፈለግ ይችላሉ።




#Article 10: አፍሪቃ (281 words)


አፍሪቃ

አፍሪቃ (አፍሪካ) ከዓለም ሁለተኛ ትልቅ አህጉር ነች። ከ869 ሚሊዮን በላይ ህዝብ በዚች አህጉር የሚኖር ሲሆን በጠቅላላ 54 ሀገሮች ይገኛሉ። ከእነዚህም ሀገሮች መሀል ናይጄሪያ በህዝብ ብዛት (127 ሚሊዮን) የመጀመሪያውን ደረጃ ስትይዝ፤ ግብፅና ኢትዮጵያ በ73 ሚሊዮን እና በ72 ሚሊዮን ህዝብ በሁለተኛና በሶስተኛ ደረጃ ይገኛሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት የህዝብ ብዛት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር ከሌሎች የፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች ጋር በመደማመር ድህነትን በማባባስ ደረጃ ትልቅ ሚና ይጫወታል፡፡

ከስድስቱ ዓለማት አንዱ አፍሪካ ነው። አፍሪካ ሰፊ ነው። የዓለምም አራተኛ ክፍል ይሆናል። ከኤውሮጳ የሚለየው በሜዴቲራኒያን ባሕር ነው። ከአሜሪካም በአትላንቲክ ውቅያኖስ ይለያል። ከኒው ዮርክም ቢሆን ወይም ከቦስቶን ከአሜሪካ የሚቀርበው ክፍል ሦስት ሺህ ማይል ይሆናል። ነገር ግን በጊብሮልታር (ጂብራልታር) 0ኩል የሆነ እንደ ሆነ ለኤውሮጳ በጣም ቅርብ ነው።

ከእስያ በኤርትራ ባሕር ይለያያል። የሆነ ሆኖ እስያ ባንድ ወገን ሱዝ ካናል በሚባለው በኩል ከአፍሪካ ጋር ተጋጥሞአል። ሙሴ ሌስፖስ መርከብ እንዲተላለፍ ብሎ አስቆፍሮ ያስከፈተው በዚህ በኩል ነው።

አፍሪካ ከሌላው ዓለም ይልቅ የታወቀው በጣም ትንሽ ነው። ኤውሮጳውያን ደኅና አድርገው አፍሪካን አልመረመሩትም። ከሕዝቡ የሚበልጡት ሻንቅሎች ናቸው። ከነዚህም ብዝዎቹ በነገድ የተለያዩ ናቸው። 

ዓየሩ ሙቀት ያለው ስለ ሆነ፣ ለመጠጊያቸው የሚፈልጉት ትንሽ ጎጆና ትንሽ ልብስ ነው። ስለዚህ ቤታቸው የተዋረደ ነው። ቅጠላቅጠሉን ጎጆ ሠርተው በትንሽ ቤት ይኖራሉ። መቸውንም ልብሳቸው አንዲት ቁራጭ ጨርቅ ናት፤ በወገባቸውም ይጠመጥሟታል።

ከሻንቅሎቹ በቀር ደግሞ ሌሎች አያሎች የአፍሪካ ዘሮች አሉ። ከግብፅ ጀምሮ እስከ ሐበሻ ድረስ ያሉት ባላገሮች የጥንት ግብፃውያንነታቸውን ሳይለቁ ከቱርኮችና ከዐረቦች ከሌሎችም የተቀላቀሉ ናቸው።

ሰሐራ የሚባለውን ልክ የሌለውን በረሃና በዙሪያው ያለውን አውራጃ ሁሉ ጨምረው ፈረሶቻቸውንና ግመሎቻቸውን ይዘው ለማሰማራት ወይም ለመዝረፍ ከአንዱ ወዳንዱ የሚዞሩ አረቦች ይዘውታል።

አፍሪካ በመላው ወደ ሥልጣኔ ያልደረሰ ነው ተብሎ ይታሰባል፤ ከሕዝቡ የሚበዙት እስላሞች ናቸው።

በመካከለኛው አፍሪካ አንበሳ፤ ዝሆን፣ አውራሪስ፣ የሜዳ አህያና ሌሎችም አራዊት ይገኙበታል። በደኑ ሁሉ ጦጣና ዝንጀሮ ይንጫጩበታል። በጫካው ውስጥ ዘንዶና ሰጎን ሞልተዋል። በሜዳው አጋዘንና ድኩላ፣ የሜዳ ፍየል ተሰማርተው ይታያሉ። በየወንዙና በየባሕሩ ጎማሬ ይታያል። አዞ በረጋ ውሃ ውስጥ ትኖራለች። አዕዋፍም በየስፍራው ሁሉ ይታያሉ።




#Article 11: ሱዳን (185 words)


ሱዳን በይፋ የሱዳን ሪፑብሊክ (አረብኛ: السودان) ከአፍሪካ በስፋት ሦስተኛ ስትሆን በአህጉሪቱ ሰሜናዊ ምስራቅ ክልል ትገኛለች። ዋና ከተማዋ ካርቱም ነው። ከግብፅ ፣ ከቀይ ባሕር ፣ ከኤርትራ ፣ ከኢትዮጵያ ፣ ከደቡብ ሱዳን፣ ከመካከለኛው የአፍሪካ ሪፑብሊክ ፣ ከቻድ ፣ እና ከሊቢያ ጋር ድንበር ትካለላለች። የአባይ ወንዝ (ናይል) ሀገሪቱዋን ወደ ምሥራቅና ምዕራብ ይከፍላል። የአረብ ባህል ደንበኛ ሲሆን አብዛኛው ሕብዝ የእስልምና ዕምነት ተከታይ ነው።

ሱዳን ከግብፅ የተጣመረ ረዥም ታሪክ አላት። የመጀመሪያው የሱዳን እርስ በርስ ጦርነት ከ1955 እስከ 1972 እ.ኤ.አ. ከዚያም ሁለተኛው የሱዳን እርስ በርስ ጦርነት ከ1983 እስከ 2005 እ.ኤ.አ. ተከስቷል። በ1989 እ.ኤ.አ. በሰላማዊ መፈንቅለ መንግሥት ኦማር ሀሳን አህመድ አል-በሽር ሥልጣን ላይ የወጡ ሲሆን እራሳቸውን የሱዳን ፕሬዝዳንት ብለው ሾመዋል። የእርስ በርስ ጦርነቱ በሰላም ውል የቆመ ሲሆን ይህ ውል ያኔ የሀገሪቱዋ ደቡባዊ ክፍል ለነበረው ቦታ ራስን የመምራት መብት ሰጥቷል። በጃኑዋሪ 2011 እ.ኤ.አ. በተካሄደው ውሳኔ ሕዝብ (referendum) መሠረት በሱዳን ፈቃድ ደቡብ ሱዳን ሐምሌ ፪ ቀን ፳፻፫ ዓ.ም. ሉዓላዊ ሀገር ሆነች።

ዋና ከተማዋ ካርቱም የሱዳን የፖለቲካ፣ ባህል እና ንግድ ማዕከል ናት። የሀገሪቱዋ መንግሥት በይፋ ፌዴራላዊ ፕሬዝዳንታዊ ሪፐብሊክ ቢሆንም ስልጣን ላይ ያለው ብሔራዊ ኮንግረስ ፓርቲ (National Congress Party) በሁሉም የመንግሥት አካላት ላይ ባለው ጥብቅ ቁጥጥር ምክንያት በብዙ የዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ ዘንድ መንግሥቱ አምባገነናዊ ተብሎ ይቆጠራል።




#Article 12: ትምህርተ፡ጤና (351 words)


የአለም ጤና ጥበቃ ድርጅት ጤንነትን እንደሚከተለው ይተነትነዋል፡፡ ጤንነት ማለት ሙሉ የሆነ የአካል፡ የስነልቦናዊ፡ እንዲሁም የማህበረሰብአዊ ደህንነት ነው፡፡ ይህም ሲባል የበሽታ አለመኖር ብቻ ጤነኝነትን አይገልፅም፡፡ 

ስለዚህም በሽታ ማለት የማንኛውንም ግለሰብ የአካል፡ የስነልቦናዊ፡ ወይም የማህበረሰብአዊ ደህንነትን የሚያቃውስ ሁኔታ ነው፡፡

በሽታ በተለያየ ጠንቅ መንገድ ሊነሳ ይችላል፡፡

በአፍሪካ እና በሌሎችም ታዳጊ ሀገሮች ውስጥ አብዛኛውን ህብረተሰብ የሚያጠቁት በሽታዎች በጥቃቅን ህዋሳት አማካኝነት የሚተላለፉ እና በምግብ እጥረት ምክንያት የሚመጡት ናቸው፡፡ የአለም ጤና ጥበቃ ድርጅት የ2004 ዓ.ም. መረጃ እንደሚያሳየው በተለይም ወባ፡ የሳምባ ነቀርሳ፡ ኤድስ እንዲሁም የህጻናት ጠቅማጥ እና የሳማባ ምች ለብዙ የምርት እና የትምህርት ሰዐታት መባከን ምክንያት ናቸው፤ እንዲሁም በየአመቱ ብዙ ህይወት ይቀጥፋሉ፡፡

በህዋሳት ምክንያት የሚመጡት በሽታዎች እንደ ህዋሳቱ እይነት የተለያየ የመተላለፊያ መንገድ ያላቸው ሲሆን ባጠቃላይ ግን እኒህ መተላለፊያ መንገዶች እንደሚከተለው ይመደባሉ፡

ከበሽተኛው አገላለፅ እና የአካል ምርመራ በተጨማሪ አንድን በሽታ በተላላፊ ህዋሳት ነው የሚመጣው ለማለት የሚያበቁ መረጃዎች ያስፈልጋሉ፤ እነዚህም መረጃዎች የተላላፊው ህዋስ ወይንም ሰውነታችን ህዋሱን በተለይ ለመከላከል የሚያመነጨው የተለየ ፀረ-ህዋስ ኬሚካል በበሽተኛው ሰውነት ውስጥ መገኘትን ያጠቃልላል፡፡ በዚህም ምክንያት በሽታውን ለመለየት የሚደረጉ ምርመራዎች ደም ወይንም ሌላ ከሰውነት የመነጨ ፈሳሽ (ሽንት፤ አክታ፤ ሰገራ፤ መግል፤ የሳምባ ልባስ ፈሳሽ፤ ወዘተ) ሊያካትቱ ይችላል፡፡

በተለያዩ በሽታዎች ምክንያት የሚመጡ የተለየ ምልክት የሚሰጡ ጉልህ የሆኑ የአካላት ላይ የቅርፅ ለውጦችን በማየትም በሽታው ምን እንደሆነ ለመለየት የሚቻል ሲሆን፤ እነኚህን ለውጦች ለማየት በመሳሪያ የታገዘ ቀጥተኛ የሆነ የውስጥ አካል እይታ (ኤንዶስኮፒ)፤ በድምፅ-መሰል ሞገዶች የታገዘ የአልትራሳውንድ ምርመራ፤ ወይንም ኤክስ ሬይ (ራጅ) እና ሌሎች ጠልቆ ለማየት የሚያስችሉ ምርመራዎች ይታዘዛሉ፡፡

በበሽታዎች የሚመጡ በአይን ለማየት የሚያዳግቱ የተለዩ የቅርፅ ለውጦችን ለማየት አንዳንድ ጊዜ የተጠቃውን አካል ክፍል በትንሹ ቆንጥሮ በመውሰድ የሚደረግ የረቂቅ ማይክሮስኮፕ ምርመራ ውጤት ፍንጭ ሊሰጥ ይችላል፡፡

ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል መሰረታዊ የሆኑ መርሆዎች አሉ። እነኚህም፡

በአሁኑ ወቅት በክትባት አማካይነት ልንከላከላቸው የምንችላቸው በሽታዎች ጥቂት ብቻ አይደሉም። ከእነዚህም መካከል፡

ከእነዚህ በተጨማሪ በለሙ ሀገሮች ሌሎች በሽታዎችን መከላከል የሚያስችሉ ክትባቶቸ አሉ። እነዚህኞቹ በተለያየ ምክንያት (ዋጋቸው ከፍተኛ መሆኑን ጨምሮ) በታዳጊ ሀገሮች በብዛት ጥቅም ላይ አልዋሉም። ከእነዚህ መሀል የመንጋጋ ቆልፍ፤ የጆሮ ደግፍ፤ የቢጫ ወባ፤ የተስቦ፤ የጉበት ልክፍት በሽታ መከላከያ ክትባቶች ይገኙበታል።

የክትባት ንጥረ ነገር የሚሰራው ከራሱ በሽታ አምጭ ከሆኑት ህዋሳት ሲሆን እነዚህን ህዋሳት በኬሚካል እና በሌላም ዘዴ በማዳከም በሽታ እንዳያሰከትሉ ግን በክትባት መልክ ቢሰጡ ሰውነታችን ለይቷቸው የበሽታ መከላከያ እንዲያዘጋጅ በማድረግ ነው። አብዛኛዎቹ ክትባቶች የሚሰጡት በመርፌ መልክ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በብዛት በስራ ላይ የዋለው የፖሊዮ ክትባት ግን በአፍ በሚሰጥ ጠብታ መልክ የተዘጋጀ ነው።




#Article 13: ኬንያ (181 words)


የኬንያ ሪፐብሊክ በምስራቅ አፍሪካ የምትገኝ ሀገር ናት። በሰሜን ከኢትዮጵያ፣ በሰሜን-ምስራቅ ከሶማሊያ፣ በደቡብ ከታንዛኒያ፣ በምስራቅ ከዩጋንዳ፣ በስሜን-ምዕራብ ከደቡብ ሱዳን፣ በደቡብ-ምስራቅ ከሕንድ ውቅያኖስ ጋር ድንበር ትጋራለች። 

አውሮፓውያን አካባቢውን ማሰስ የጀመሩት ከ፲፱ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ሲሆን የብሪታንያ መንግሥት የምሥራቅ አፍሪካ ፕሮቴክቶሬትን በ1895 እ.ኤ.አ. አቋቁሟል። ይህ ፕሮቴክቶሬት በ1920 እ.ኤ.አ. የኬንያ ግዛት ተብሎ ተሰይሟል። ነፃ የኬንያ ሪፐብሊክ በዲሴምበር 1963 እ.ኤ.አ. ታወጀ።

የኬንያ ስም የመጣው በአፍሪካ በከፍታ ሁለተኛ ከሆነው ከደብረ ኬንያ ተራራ ነው። በዚሁ ተራራ ዙሪያ የሚኖሩት ነገዶች ስሙን «ኪኛ» (በካምባኛ)፣ «ኪሪማራ» (በአመሩኛ)፣ «ኪሬኛ» (በኤምቡኛ)፣ «ኪሪኛጋ» (በኪኩዩ)፣ ወይም «ኬሪ» (በመዓሳይኛ) ይሉታል።  የነዚህ ስሞች ሁሉ ትርጉሞች «ቡራቡሬ» ሲሆኑ ይህም ደግሞ «ሰጎን» ማለት ነው፤ አመዳይ ያለበት የተራራው ጫፍ ለተመልካች ቡራቡሬ ወንድ ሰጎንን ያሳስባልና።

በኦገስት 2010 እ.ኤ.አ. በተካሄደ ውሳኔ ሕዝብ (referendum) መሠረት ከብሪታንያ የተወረሰው ሕገ መንግሥት በአዲስ ሕገ መንግሥት ተለውጧል። በአሁኑ ጊዜ ኬንያ በ፵፯ ካውንቲዎች (የአስተዳደር ክፍሎች) ተዋቅራለች። እነዚህ ካውንቲዎች በሕዝብ በተመረጡ ሰዎች የሚስተዳደሩ ሲሆን በናይሮቢ ከሚገኘው ማዕከላዊ መንግሥት በነፃነት ይንቀሳቀሳሉ።

የኬንያ ዋና ከተማ እና ትልቋ ከተማ ናይሮቢ ናት። የኬንያ ኢኮኖሚ በምሥራቅና መካከለኛው አፍሪቃ በጂ.ዲ.ፒ. (GDP) ትልቁ ነው። ግብርና በአገሪቱ ትልቅ የሥራ ዘርፍ ሲሆን ከኤክስፖርቶች መካከል ሻይ፣ ቡና እና ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ አበባዎች ይገኛሉ። እንዲሁም ቱሪስምና ፔትሮሊየም አቢይ ዘርፎች ናቸው።




#Article 14: ፀሐይ (574 words)


ፀሓይ በምድር ሥርዐተ-ፈለክ መኻል ያለች ኮከብ ናት። ምድር ሞላላ ቀለበት በሚመስል የዑደት ምሕዋር እየተጓዘች ፀሓይን ትዞራታለች። ሌሎች ሰማያዊ አካላትም፣ ፈለኮች፣ ፈለክ-አስተኔዎች፣ ጅራታም ከዋክብት እና ኅዋዊ ብናኞች በፀሓይ ዙሪያ ይዞራሉ።

ምድር በፀሓይ ዙሪያ የምታደርገውን አንድ ዙር ጉዞ ለመጨረስ አንድ ዓመት ይፈጅባታል፤ ይህን ጉዞ ስታደርግም በገዛ ራሷ ዘንጎ ወይም ምሽዋር ዙሪያ እየሾረች ነው። ምድር በፀሓይ ዙሪያ የምታደርገው ዙረት ወቅቶች በዓመታዊ ዑደት እንዲለዋወጡ ከሚያደርጉት ምክንያቶች አንዱ ሲኾን፣ በራሷ ዘንጎ ዙሪያ የምታደርገው ሹረት ደግሞ በዕለታዊ ዑደት መዓልት (ቀን) እና ሌሊት ለሚያደርጉት መፈራረቅ ምክንያት ነው።

ፀሓይ ለሥርዐተ-ፈለካችን በጣም ብሩህ የኾነ ብርሃን ትሰጣለች። ያለ ፀሓይ ብርሃን ሙቀትም ኾነ ሕይወት በምድር አይኖርም ነበር። ለምሳሌ አረንጓዴ ዕፅዋት ያለ ፀሓይ ብርሃን ሊኖሩ አይችሉም፤ ለህልውናቸው የሚያስፈልጓቸውን ካርቦን ዳይኦክሳይድ እና አልሚ ምግቦች ለማስተጻመር የሚችሉት በፀሓይ ብርሃን ብቻ ነውና።

ከምድር ይልቅ ለፀሓይ ይበልጥ ቅርብ የኾኑ ፈለኮች ለከፍተኛ ጨረር እና ግለት የተጋለጡ በመኾናቸው በምድር ላይ ላለው ዐይነት ሕይወት ተስማሚ አይደሉም። ከምድር ጋር ሲነጻጸር ከፀሓይ በጣም ርቀው ያሉ ፈለኮችም ለሕይወት መኖር ምቹ ኹኔታዎች የሏቸውም፤ በቂ ብርሃን እና ሙቀት ካለማግኘታቸው የተነሣ።

የፀሓይ አካል ለፍጹም ሉል የቀረበ ቅርጽ አለው፤ ዋልታዎቿን የሚያገናኘው ዳያሜትር ከወገቧ ዳያሜትር የሚያንሰው በ10 ኪሎ ሜትር ብቻ ነውና።

ኮከባችን ፀሓይ በሥነ ፈለክ ሊቃውንት እጅግ ብዙ ጥናት ተደርጎባታል። ኾኖም ኮከቢቱን በተመለከተ ብዙ ጥያቄዎች ገና አልተመለሱም። ለምሳሌ በገሃድ የሚታየው የፀሓይ ገጽ ስኂን 6,000 ኬ (ኬልቪን) ኾኖ ሳለ፣ የዳርቻ ከባቢ አየሯ ስኂን ከሚሊዮን ኬ በላይ እንዴት ሊኾን እንደቻለ አይታወቅም።

የፀሓይ ዕድሜ በአንዳንድ ሊቃውንት እሳቤ 4.6 ቢሊዮን ዓመት ገደማ ነውና በዕድሜ እኩሌታዋ ላይ የምትገኝ ኮከብ ተደርጋ ትታያለች። የኮከቢቱ መጠነ-ቁስ ጥንቅር 74% ሃይድሮጂን፣ 25% ሂሊየም ሲኾን፣ ቀሪው 1% ደግሞ ክብደት ያላቸው ርዝራዥ የብረቴ ንጥረ-ነገሮች ጥርቅም ነው።

ስለ ፀሓይ የሰው ልጅ ቀዳሚ መሠረታዊ ግንዛቤ ብርሃን-ሰጭ ሰማያዊ ጻሕል መኾኗን፣ ደግሞም ከአድማስ በላይ እና በታች በመኾን ለመዓልትና ሌሊት መኖር ምክንያት መኾኗን መረዳት ነበር። በብዙ የቅድመ-ታሪክ እና የጥንት ዘመን ባህሎች ፀሓይ እንደ ብርሃናዊ አምላክ ወይም እንደ ዲበ-ተፈጥሯዊ ክሥተት ትታይ ነበር። የፀሓይ አምልኮ ለምሳሌ የ-ኢንካ (ደቡብ አሜሪካ) እና አዝቴክ (የዛሬዋ ሜክሲኮ) ጥንታዊ ሥልጣኔዎች ዐይነተኛ ገጽታ ነበር። ከፀሓያዊ ክሥትቶች ጋር የተያያዙ ብዙ ጥንታዊ ሐውልቶች ተገንብተው እንደነበር ለማሰብ የሐጋይ ሶልስቲስን ለማስታወቅ የተገነቡትን የድንጋይ ሜጋሊት በምሳሌነት መጥቀስ ይቻላል። (በጣም ጐልተው ከሚታዩ ሜጋሊቶች ውስጥ ጥቂቱ በ ናባታ ፕላያ፣ ግብጽ፣ እና በ ስቶንሄንጅ፣ እንግሊዝ፣ ውስጥ ይገኛሉ።) 

ከችንክር ከዋክብት አንጻር ስትታይ ፀሓይ የግርዶሽ መስመርን ተከትላ በዞዲያክ ውስጥ በዓመት አንድ ዑደት የምታደርግ ትመስላለች። ስለዚህ በጥንት የግሪክ የሥነ-ከዋክብት ሊቃውንት ዘንድ ፀሓይ ታዋቂ ከነበሩ ሰባት ፈለኮች እንደ አንዱ ትቈጠር ነበር። በአንዳንድ ቋንቋዎች ሰባቱ የሳምንት ዕለታት በነዚህ ፈለኮች ይጠራሉ።

በምዕራቡ ዓለም ውስጥ ስለ ፀሓይ ሳይንሳዊ መግለጫ ለመስጠት ከቻሉ ቀዳሚ ሰዎች አንዱ ግሪካዊው ፈላስፋ አናክሳጎራስ ነበር። ፀሓይ በእሳታዊ ነበልባል የምትንቀለቀል እጅግ ግዙፍ የብረት ኳስ እንጂ የሄሊዮስ ሰረገላ እንዳልነበረች በምክንያት የተደገፈ ትንተና አቀረበ። ይህንን እንደ ኑፋቄ የተቈጠረ ሐተታ በማስተማሩም ታሰረ፤ በሞት እንዲቀጣም ተፈርዶበት ነበር፤ በፔሪክልስ አማላጅነት እንዲፈታ ተፈቀደለት እንጂ። 

የባለሥልጣናት መዓት የወደቀበት ሌላው የሳይንስ ሊቅ ኒቆላዎስ ቆጰርኒቆስ ነበር። በ16ኛው ምእት ውስጥ የኖረው ቆጰርኒቆስ ምድር ፀሓይን በቀለበትማ ምሕዋር ትዞራለች እንጂ፣ ፀሓይ ምድርን አትዞርም የሚል ኀልዮ አቅርቦ ነበር። በ17ኛው ምእት ጋሊሌዮ በቴሌስኮፕ ለታገዘ የፀሓይ ጥናት ፈር-ቀዳጅ ሊቅ ኾነ። አይዛክ ኒውተን ደግሞ በፕሪዝም አማካይነት የፀሓይ ብርሃን ልዩ ልዩ ቀለማት ካላቸው ብርሃናት የተጠናቀረ እንደኾነ አሳየ። 19ኛው ምእት ዊሊያም ኸርሽል የኢንፍራሬድ ጨረር ግኝት ባለቤት የኾነበት፣ በስፔክትሮስኮፕ ስለ ፀሓይ የሚደረገው ጥናትም እጅግ የመጠቀበት ምእት ኾነ።

ዛሬ በብዙ አገሮች ልማድ ፀሓይ እንደ ባህላዊ ምልክት ትታያለች። ለምሳሌ በሜክሲኮ ኪነ ጥበብ አበክራ የምትታይ ሞቲፍ በመባል ትታወቃለች።

በኛ ሥርዐተ-ፀሓይ ዋናዋ ትልቅ አካል ራሷ ፀሓይ ናት። በመላው ሥርዐተ-ፀሓይ ውስጥ ከሚገኘው ክብደት 99.86% የፀሓይ ነው። ለምሳሌ ከታላቁ ፈለክ ከጁፒተር ሲነጻጸር የፀሐይ ክብደት 1000 ዕጥፍ ይበልጣል። የፀሓይ ክብደት ከምድር 1.3 ሚሊዮን ጊዜ ይበልጣል። በጣም ግዙፍ እና ከባድ የኾነችው ኮከብ ከምድር ያለችበት ርቀት በጣም የሚያስደንቅ ነው። በምድር እና በፀሓይ መካከል ያለው ርቀት የምድርን ዳያሜትር በ12,000 ጊዜ ይበልጣል። ብርሃን ይህን ርቀት ለመጓዝ 8.5 ደቂቃ ይፈጅበታል።




#Article 15: ቢል ክሊንተን (186 words)


ዊልያም ጄፈርሰን «ቢል» ክሊንተን (እንግሊዘኛ፡ William Jefferson Bill Clinton) (የትውልድ ስም፦ ዊልያም ጄፈርስን ብላይዝ ፬ኛ፣ እንግሊዘኛ፡ William Jefferson Blythe IV) በነሐሴ 13 ቀን፣ 1938 ዓ.ም. (= 1946 እ.ኤ.አ.) በሆፕ አርካንሳው የተወለዱ ሲሆን ከ1993 እስከ 2001 እ.ኤ.ኣ. ድረስ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ነበሩ። ፕሬዝዳንት ከመሆናቸዉ በፊት አምስት ጊዜ የአርካንሳው ስቴት አስተዳዳሪ ነበሩ። 

ቢል ክሊንተን ያደጉት በሆት ስፕሪንግስ፣ አርካንሳው ነው። የቢል ክሊንተን አባት ዊሊያም ጄፈርሰን ብላይዝ ጁኚየር፣ ቢል ክሊንተን ከመወለዱ ሶስት ወር በፊት በመኪና አደጋ ሞተዋል። የቢል ክሊንተን እናት ቨርጂኒያ ክሊንተን ኬሊ፣ በ1950 እ.ኤ.ኣ. ሮጀር ክሊንተን የሚባል ሰዉ አገባች። 14 ዓመቱ ሲሆን ቢል ክሊንተን የመጨረሻ ስሙን ወደ ክሊንተን ለወጠ። ክሊንተን በጆርጅታውን ዩኒቨርሲቲ፥ ዋሽንግተን ዲ.ሲ.፣ ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ፥ ኢንግላንድ፣ እና ዬል ዩኒቨርሲቲ፥ ኮነቲኬት ተምረዋል። በ1975 እ.ኤ.ኣ. ሂለሪ ሮድሃምን አገቡና በሊትል ሮክ፥ አርካንሳው መኖር ጀመሩ። ከዚያም በዩኒቨርሲቴ ኦፍ አርካንሳው የሕግ ፐሮፌሰር ሆነው አገልግለዋል። ቢል ክሊንተን የአርካንሳው አስተዳዳሪ ሆኖ ለመጀመሪያ ጊዜ የተመረጡት በ1978 እ.ኤ.ኣ. ነው። በዛ ጊዜ ከአሜሪካ በዕድሜ ትንሹ አስተዳዳሪ ነበሩ። በ1980 እ.ኤ.ኣ. በፍራንክ ዲ ዋይት ከተሸነፉ በኋላ በ1982 እ.ኤ.ኣ. እንደገና ተመረጡ። ከዛ ጀምሮ እስከ 1992 እ.ኤ.ኣ. ድረስ ለአራት ጊዜ አስተዳዳሪ ሆነው መርተዋል። በ1984 እ.ኤ.ኣ. የአስተዳዳሪ የስልጣን ዕድሜ ከ2 ዓመት ወደ 4 ዓመት አራዝመዋል። በ1992 እ.ኤ.ኣ. ለፕሬዝዳንትነት ተወዳድርው አሸንፈዋል። በ1996 እንደገና ተወዳድረው አሸንፈዋል።




#Article 16: አዲስ አበባ (1465 words)


አዲስ ፡ አበባ (ወይም ባጭሩ «አዲስ») ፡ ተብላ ፡ የተሠየመችው ፡ እቴጌ ፡ ጣይቱ ፡ ኅዳር ፲፬ ፡ ቀን ፡ ፲፰፻፸፱ (1879) ፡ ዓ.ም. ፡ ፍልውሃ ፡ ፊን-ፊን ፡ ወደሚልበት ፡ መስክ ፡ ወርደው ፡ ሳሉ ፡ ከዚህ ፡ በፊት ፡ አይተዋት ፡ የማያውቋት ፡ አንዲት ፡ ልዩ ፡ አበባ ፡ አይተ ፡ ስለማረከቻቸው ፡ ቦታውን ፡ ‹‹አዲስ ፡ አበባ!›› ፡ አሉ ፡ ይባላል። አዲስ ፡ አበባ ፡ (ኣዲስ ኣበባ) ኢትዮጵያ ፡ ዋና ፡ ከተማ ፡ ስትሆን ፡ በተጨማሪ ፡ የአፍሪካ ፡ ሕብረት ፡ መቀመጫ ፡ እንዲሁም ፡ የብዙ ፡ የተባበሩት ፡ መንግሥታት ፡ ድርጅት ፡ ቅርንጫፎችና  ፡ ሌሎችም  ፡ የዓለም ፡ የዲፕሎማቲክ (የሰላማዊ ግንኙነት) ፡ ልዑካን ፡ መሰብሰቢያ ፡ ከተማ ፡ ናት። ራስ-ገዝ ፡ አስተዳደር  ፡ ስላላት ፡ የከተማና ፡ የክልል ፡ ማዕረግ ፡ ይዛ ፡ ትገኛለች። አብዛኞቹን ፡ የሀገሩ ፡ ቋንቋዎች ፡ የሚናገሩ ፡ ክርስቲያኖች ፡ እና ፡ ሙስሊሞች ፡ የሚኖሩባት ፡ ከተማ ፡ ናት። ከባሕር ፡ ጠለል ፡ በ2500 ፡ ሜትር ፡ ከፍታ ፡ ላይ ፡ የምትገኘው ፡ ከተማ ፡ በግምት ፡ 2,757,729 ፡ በላይ ፡ ሕዝብ ፡ የሚኖርባት ፡ በመሆኗ ፡ የሀገሪቱ ፡ አንደኛ ፡ ትልቅ ፡ ከተማ ፡ ናት።

ከተማዋ ፡ እቴጌ ፡ ጣይቱ ፡ በመረጡት ፡ ቦታ ፡ ማለትም ፡ በፍል ፡ ውሐ ፡ አካባቢ ፡ ላይ ፡ በባላቸው ፡ በዳግማዊ ፡ ምኒልክ ፡ በ፲፰፻፸፰ (1878) ዓ.ም. ፡ ተቆረቆረች። የሕዝቧ ፡ ብዛት ፡ በያመቱ ፡ 8% (ስምንት ፡ በመቶ) ፡ እየጨመረ ፡ አሁን ፡ አምስት ፡ ሚሊዮን ፡ እንደሚደርስ ፡ ይገመታል።

ከእንጦጦ ፡ ጋራ ፡ ግርጌ ፡ ያለችው ፡ መዲና ፡ የአዲስ ፡ አበባ ፡ ዩኒቨርሲቲ ፡ መገኛ ፡ ሆናለች።  ይህም ፡ በመስራቹ ፡ የቀድሞው ፡ ንጉሠ-ነገሥት ፡ ስም ቀዳማዊ ፡ ኃይለ ፡ ሥላሴ ፡ ዩኒቨርሲቲ ፡ ይባል ፡ ነበር።

አጼ ምኒልክ የሸዋ ንጉስ ሲሆኑ ደብረ እንጦጦ በደቡብ ዘመቻ ጊዜ ጠቃሚ ሆኖ ስላገኙት እዚያ ጥንታዊ የመንደር ፍርስራሽ በ1871 ዓ.ም. አይተው አንድ ያልተጨረሰ ውቅር ድንጋይ ቤተክርስቲያን ደግሞ በዚያ ጎበኙ።  ይህ ቤተክርስቲያን ከግራኝ አሕመድ በፊት እንደ ቆመ አስረዳ።
 
ሚስታቸው እቴጌ ጣይቱ ቤተክርስቲያን በእንጦጦ ላይ በጀመሩበት ወቅት፣ የምኒሊክ ዝንባሌ ወደእዚህ ስፍራ በተለይ ተሳበ፤ ሁለተኛም ቤተክርስቲያን ባቅራቢያው ሠሩ። ነገር ግን ማገዶም ሆነ ውኃ በማጣት አካባቢው መንደር ለመመሥረት አይመችም ነበር፤ ስለዚህ መስፈሪያው በውኑ የጀመረበት ከተራራው ትንሽ ወደ ደቡብ በሚገኘው ሸለቆ ውስጥ በ1878 ነበረ።  በመጀመርያ ጣይቱ ፍልወሃ ምንጭ አጠገብ ለራሳቸው ቤት ሠሩ።  ይህ ምንጭ ለቦታው ኦሮሞ ሕዝብ ፍንፍኔ ትብሎ ታወቀ፤ እዚህም እርሳቸውና የሸዋ ቤተመንግስት ወገን መታጠብ ይወዱ ነበር።  ከእዚያ በኋላ ሌሎች መኳንንቶች ከነቤተሰቦቻቸው አቅራቢያውን ሠፈሩ፤ ምኒልክም የሚስታቸውን ቤት ቤተመንግሥት እንዲሆን አስፋፉትና እስከ ዛሬ ድረስ ቤተ መንግሥት ሆኖ ቆይቷል። ምኒልክ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገሥት በሆነበት ወቅት አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ሆነች። ከእዚያ ጀምሮ ከተማዋ ዘልላ አደገች። ዛሬም በየመንገዱ ላይ ብዙ ባሕር ዛፎች የሚታዩበት ምክንያት አፄ ምኒልክ ስላስተከሏቸው ነው።

በ1928 ዓ.ም. በጦርነት ጊዜ የፋሺስቶች ሠራዊት ከተማዋን ወርረው ዋና ከተማቸውም አደረጉዋት፤ እስከ 1931 ድረስ የኢጣልያ ምስራቅ አፍሪቃ አገረ ገዥ ነበረባት። የኢጣልያ ሠራዊት በኢትዮጵያውያን አርበኞች ተደናቅፎ በእንግሊዝ ጭፍሮች ዕርዳታ በታላቅ ከተሸነፈ በኋላ፤ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ በግንቦት 1933 ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ ይህም ቀን ከወጡ ልክ ከ5 አመቶች በኋላ ነበር። ወዲያው ከተማይቱ እንደገና ዋና ከተማቸው እንድትሆን መሠረታዊ ሥራ ጀመሩ።

በ 1955 ዓ.ም. የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት (OAU) አስመሠረቱ፤ የድርጅቱም ጠቅላይ መስሪያ ቤት በአዲስ አበባ እንዲቆይ በመጋበዛቸው ሆነ።  ይህ ድርጅት በ1994 ተፈትቶ በአፍሪካ ኅብረት ተተካ፤  ጠቅላይ መሥሪያ ቤቱ ደግሞ በአዲስ አበባ አለው። የተባበሩት መንግሥታት ምጣኔ ሀብት ጉባኤ ለአፍሪቃ (United Nations Economic Commission for Africa) ደግሞ ጠቅላይ መሥሪያ ቤት ባዲስ አበባ አለው።  በ1957 ዓ.ም. አዲስ አበባ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያን ስብሰባ ሥፍራው ነበረች።

የአዲስ አበባ ከተማ ሠፈሮች ስያሜያቸውን ያገኙት በተለያዩ ምክንያቶችና አጋጣሚዎች ነው። እነዚህንም በተለያዩ ዘርፎች ከፍሎ በቅደም ተከተል ማየት ይቻላል።

በርካታዎቹ የከተማዋ ቀደምት ሠፈሮች ስያሜያቸውን ያገኙት በቤተ-መንግሥቱ ዙሪያ መሬት በጉልት መልክ በተሠጣቸው መሣፍንቶችና መኳንንቶች ስም ነው። በዚህ መልክ ስያሜያቸውን ካገኙት ሠፈሮች መካከል ራስ መኮንን ሠፈር፣ ራስ ተሰማ ሠፈር፣ ራስ ብሩ ሠፈር፣ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ሠፈር፣ ራስ ስዩም ሠፈር፣ ደጃዝማች ውቤ ሠፈር፣ ነጋድራስ ኃይለ ጊዮርጊስ ሠፈር ፣ ደጃዝማች ዘውዱ አባኮራን ሠፈር እና ሸጎሌ (የአሶሣ ገዢ በነበሩት በሼክ ሆጀሌ አል ሐሠን የተሠየመው) ሠፈር ይጠቀሳሉ።

ከእነዚህ ሠፈሮች መካከል ደጃዝማች ውቤ ሠፈር በተለይ ከጣሊያን ወረራ በፊት በሴተኛ አዳሪነት የሚተዳደሩ ነዋሪዎች በከፍተኛ ደረጃ ከሚገኙባቸው የከተማዋ ሠፈሮች አንዱ እንደነበረ ይነገራል። በዚህም ሳቢያ በስነ ቃል በርካታ ግጥሞች በዚህ ሠፈር ዙሪያ ተገጥመዋል። ከነዚህም መካከል፣

ያችም ልጅ አገባች ያችም ልጅ ታጨች።
ደጃች ውቤ ሠፈር ሲጣሉ እወዳለሁ፣
ገላጋይ መስዬ እገሊትን አያለሁ።
ደጃች ውቤ ሠፈር የሚሠራው ሥራ፣
ጠይሟን በጥፊ ቀይዋን በከዘራ»
የሚሉት ይገኙበታል።

በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ከመላው የአገሪቱ ማዕዘናት መጥተው አዲስ አበባ በሠፈሩ ብሔረሰቦች የተመሠረቱ ሠፈሮች ይጠቀሳሉ። በዚህ መልክ ከተመሠረቱት ሠፈሮች መካከል ለአብነት አደሬ ሠፈር፣ ጎፋ ሠፈር፣ ወሎ ሠፈር፣ ወርጂ ሠፈር፣ መንዜ ሠፈርና ሱማሌ ተራ ይገኙበታል። የወርጂ ሠፈርን የመሠረቱት የወርጂ ብሔረሰብ አባላት በቆዳና በበርኖስ ንግድ የተሠማሩ እንደነበሩ ይነገርላቸዋል። በተመሣሣይ መልኩ የሱማሌ ተራ ነዋሪዎች ዋነኛ መተዳደሪያ የሻይ ቤት ሥራ እንደነበር ይታመናል።

በሶስተኛ ደረጃ በተለያዩ ሙያዎች ተሠማርተው በተለይም በቤተ መንግሥቱ የተለያዩ የሥራ ድርሻዎች በነበራቸው ባለሙያዎች የተቆረቆሩ ሠፈሮችን እናገኛለን። እነዚህም ከብዙ በጥቂቱ ሠራተኛ ሠፈር፣ ዘበኛ ሠፈር፣ ሥጋ ቤት ሠፈር፣ ኩባንያ ሠፈር፣ ጠመንጃ ያዥ ሠፈር፣ ካህን ሠፈር (በኋላ ገዳም ሠፈር) ፣ ገባር ሠፈር ፣ ሠረገላ ሳቢ ሠፈርና ውሃ ስንቁ ሠፈርን ያካትታሉ። ሠራተኛ ሠፈር በአፄ ምኒልክ ቤተ-መንግሥት በዕደ ጥበባት ሙያ በተሠማሩ ነዋሪዎች የተመሠረተ ሠፈር ነው። የሠፈሩ መሥራቾች ዋነኛ ሙያ የብረታ ብረት ሥራ እንደነበረ ይነገራል። ይሄም የተለያዩ የብረታ ብረት ውጤቶችን ለምሣሌ ማረሻ፣ የፈረስ እርካብን፣ የቤት እቃዎችን፣ የጋሻና ጦር እና የጠመንጃ ዕድሳትን ይጨምራል። በቤተ መንግሥቱ በአናጢነት የተሠማሩ ባለሙያዎችም የሚኖሩት በሠራተኛ ሠፈር እንደነበር ይነገራል።

በከተማዋ ከሚኖሩት የውጭ ተወላጆችም መካከል ጥቂቶቹ የሚኖሩት በዚሁ ሠፈር ነበር። ከነዚህም የውጭ ነዋሪዎች መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱት አርመናዊው የግብረ ህንፃ ባለሙያ ሙሴ ሚናስ ሔርቤጊን ነበሩ። ዘበኛ ሠፈር የቤተ-መንግሥቱ ጠባቂዎች ወይም የዕልፍኝ ዘበኞች የሠፈሩበት ሠፈር ሲሆን፣ ገባር ሠፈር ደግሞ ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍላተ ሀገር እንደ ማር፣ እህልና ከብት በመሣሠሉት ምርቶች ዓመታዊ ግብር ለመክፈል ወደ ከተማዋ በሚመጡ ግለሰቦች የተመሠረተ ሠፈር እንደሆነ ይነገራል። የውሃ ስንቁ ሠፈር መስራቾች ደግሞ መደበኛ ክፍያ የሌላቸው እና ስንቃቸው ውሃ ብቻ የሆነ የጦሩ አባላት የሠፈሩበት ሠፈር እንደነበረ ይነገራል።

በሌላ በኩል ጥቂት የማይባሉ የአዲስ አበባ ሠፈሮች ስያሜያቸውን ያገኙት በተለያዩ አጋጣሚዎች፣ ክስተቶችና ታሪካዊ ክንዋኔዎች ነው። ሠባራ ባቡር ፣ እሪ በከንቱ ፣ ዶሮ ማነቂያ ፣ አፍንጮ በር ፣አራት ኪሎ ፣ ስድስት ኪሎ ፣ አምስት ኪሎ ፣ ጣሊያን ሠፈር፣ ሃያ ሁለት ማዞሪያ፣ ሽሮ ሜዳ እና ነፋስ ስልክ ተብለው የሚጠሩትን ሠፈሮች በዚሁ ዘርፍ መፈረጅ ይቻላል። ሰባራ ባቡር ሠፈር ስያሜውን ያገኘው ሙሴ ሰርኪስ ተርዚያን በሚባሉ አርመናዊ ነጋዴ አማካኝነት ከውጭ አገር መጥቶ አሁን ስያሜውን ባገኘበት ቦታ ተበላሽቶ በቀረው የመንገድ መሥሪያ ተሽከርካሪ (ሮለር) ምክንያት ሠፈሩ ሰባራ ባቡር እንደተባለ ይነገራል። አገሬው “የሠርኪስ ባቡር” እያለ የሚጠራው መሣሪያ አዲስ አበባ በደረሰ ጊዜ የሚከተለው ግጥም ተገጥሞለት ነበር።

ምኒልክ መልአክ ነው ልቤ ጠረጠረ።»

በሌላ በኩል ከዐድዋ ጦርነት በኋላ በድል አድራጊው የኢትዮጵያ ሠራዊት የጦር ምርኮኞች የሆኑት የጣሊያን ተወላጆች በማረፊያነት የተመረጠው ቦታ ጣሊያን ሠፈር የሚለውን ስያሜ ማግኘቱ ይታወቃል። እንደዚሁም የስድስት ኪሎ ሠፈር ፣ አራት መንገዶች መገናኛ የሆነው አካባቢ አራት ኪሎ ሠፈር በሁለቱ ሠፈሮች መካከል ያለው አካባቢ ቆይቶ አምስት ኪሎ ሠፈር የሚለውን ስያሜ ማግኘቱም የሚታወቅ ነው።

ሌላው በከተማው ከሚገኙ ዋና ዋና ሠፈሮች መካከል በከተማዋ ቀደምት ነዋሪዎች በሆኑት የኦሮሞ ተወላጆችና የቦታ ስሞች የተሰየሙ ሠፈሮችን እናገኛለን። ከነዚህም መካከል ጉለሌ ፣ ጎርዶሜ ፣ ቀበና ፣ ኮተቤ ፣የካ ፣ እንዲሁም ገርጂ እና ላፍቶ የተባሉት ሠፈሮች ለአብነት ይጠቀሳሉ። ከእነዚህም ሠፈሮች መካከል በቀበና ወንዝ ስም በተሰየመው ቀበና ሠፈር ከተገጠሙት ግጥሞች አንዱን እንመልከት።

አራዳም ለዋለ ቀበና ብርቁ ነው፣
እሱስ ላገናኘው ሴት ወይዘሮም ደግ ነው።»

በሌላ ዘርፍ ከ1928 የጣሊያን ወረራ እና የአምስት ዓመት ቆይታ ጊዜ አንዳንድ የአዲስ አበባ ቦታዎች እና ሠፈሮች የጣሊያንኛ ስያሜ አግኝተዋል። ከእነዚህም መካከል መርካቶ (የአገሬው ገበያ) ፣ ፒያሣ (የቀድሞው አራዳ) ፣ ካዛንቺስ፣ ካዛ ፖፖላሬ እና ካምቦሎጆ ዋና ዋናዎቹ ናቸው። ካዛንቺስ ስያሜውን ያገኘው አዲስ አበባ በጣሊያን ይዞታ ስር በነበረችበት ጊዜ ለከፍተኛ የጣሊያን ሹማምንት መኖሪያ ቤቶች በሠራው የጣሊያን ኩባንያ ምህፃረ ቃል ሲሆን ካዛ ፖፖላሬ ደግሞ በዝቅተኛ ደረጃ ለሚገኙ ጣሊያናዊያን ቤቶች በሠራው በካዛ ፖፖላሬ ኩባንያ ስም ነው ስያሜውን ያገኘው። በሌላ በኩል ካምቦሎጆ ሠፈር መጠሪያውን ያገኘው ካምፖ አሎጅዬ ኦፔራ (Campo Allogio Opera) ከሚለው ስም ሲሆን ይሄም ማለት የሠራተኞች ካምፕ ማለት ነው።

እንዲሁም በከተማዋ በሚገኙ አብያተ ክርስቲያን እና አጥቢያዎች የተሰየሙ ሠፈሮች ሌላው ዋነኛ ዘርፍ ነው። በዚህ ዘርፍ ከሚገኙ ሠፈሮች መካከል ተቀዳሚውን ሥፍራ የሚይዘው አራዳ ጊዮርጊስ ሠፈር ነው። አራዳ በተለይም ከጣሊያን ወረራ ቀደም ባለው ጊዜ የአዲስ አበባ የኢኮኖሚ ማዕከል ከመሆኑ አኳያና በርካታ ማሕበራዊ ክንዋኔዎችን ያስተናግድ የነበረ ሠፈር እንደመሆኑ በስነቃል ብዙ ተብሎለታል። ለአብነት

ወይ አዲስ አበባ ወይ አራዳ ጊዮርጊስ።
እስኪ አራዳ ልውጣ ብርቱካን ባገኝ፣
ትናንት ኮሶ ጠጣሁ ዛሬ መረረኝ።
ምነው በአደረገኝ ከአራዳ ልጅ መሣ፣
እንኳን ለገንዘቡ ለነፍሱ የማይሣሣ።
የአራዳ ዘበኛ ክብሬ ነው ሞገሴ፣
በቸገረኝ ጊዜ የሚደርስ ለነፍሴ» የሚሉት ይገኙባቸዋል።

በዚህ ዘርፍ የሚመደቡ ሌሎች ሠፈሮች ደግሞ አማኑኤል ፣ ዮሴፍ ፣ ኪዳነ ምሕረት ፣ ቀራኒዮ መድኃኔ ዓለም ፣ እና ቀጨኔ መድኃኔ ዓለምን ያካትታሉ። እ.ኤ.አ. ከ 1888 ዓ.ም. የዐድዋ ጦርነት ድል እና ከአዲስ አበባው ስምምነት በኋላ ጣሊያን፣ ሌሎች የአውሮፓ መንግሥታት እና አሜሪካ የአገራችንን ሉዓላዊነት በመቀበል ከኢትዮጵያ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መሥርተዋል። በዚህ ሂደት በርካታ አገሮች የነዚህን አገሮች ፈለግ በመከተል ኤምባሲዎቻቸውን በአዲስ አበባ ከፍተዋል። ከአዲስ አበባ በርካታ ሠፈሮች መካከል አንዳንዶቹ ስያሜያቸውን ያገኙት ከእነዚህ ኤምባሲዎችና ቀደም ሲል ደግሞ ከሌጋሲዮኖች ነው። ፈረንሣይ ሌጋሲዮንና ሩዋንዳ ሠፈሮች ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ናቸው። በመጨረሻም ከአዲስ አበባ ሠፈሮች መካከል አንዳንዶቹ በታዋቂ የውጭ አገር ዜጎች ስም የተሠየሙ ናቸው። ከእነዚህም መካከል ቤኒን ሠፈር እና ተረት ሠፈር ይገኙበታል። ቤኒን ሠፈር ስያሜውን ያገኘው ከጣሊያን ወረራ በፊት ተዋቂ ነጋዴ በሆኑት የአይሁድ ተወላጅ ቤኑን ሲሆን ተረት ሠፈር ደግሞ ስያሜውን ያገኘው በአዲስ አበባ ከተከፈቱት ከመጀመሪያዎቹ ሆቴሎች አንዱ በነበረው በሆቴል ዳፍራንስ ባለቤት በሆኑት ፈረንሣዊው ሙሤ ቴረስ ስም ነው።

አዲስ አበባ በዐሥር ክፍለ ከተሞች እና በዘጠና ዘጠኝ ቀበሌዎች ትከፈላለች። ዐሥሩ ክፍለ ከተሞች ከዚህ በመቀጠል የተዘረዘሩት ናቸው።




#Article 17: ናይጄሪያ (583 words)


ናይጄሪያ በይፋ የናይጄሪያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ በምዕራብ አፍሪቃ የምትገኝ አገር ናት። በሕዝብ ብዛትም ከአፍሪቃ አንደኛ ናት። ከቤኒን ፣ ቻድ ፣ ካሜሩን ፣ ኒጄር ፣ እና ከጊኒ ባሕረ ሰላጤ ጋር ድንበር ትካለላለች። በናይጄሪያ ውስጥ ትልቁ ብሔሮች ሀውዛ ፣ ኢግቦ እና ዮሩባ ናቸው። ግማሹ ሕዝብ እስላም ሲሆን ሌላው ግማሽ ደግሞ የክርስትና እምነት ይከተላል። ትንሽ የሕዝቡ ክፍልም ባህላዊ ሃይማኖቶችን ይከተላል።

የሳይንስ ጥናት እንደሚያሳየው ናይጄሪያ ከ፱ሺህ ዓመታት ከክርስቶስ ልደት በፊት ጀምሮ ነዋሪዎች እንደነበሩባት ያሳያል። በቤንዌ እና ክሮስ ወንዞች አካባቢ ያለው ሥፍራ የባንቱ ፍልሰቶች መነሻ እንደ ነበረ ይታመናል።

የናይጄሪያ ስም ከኒጄር ወንዝ ነው የተወሰደው። ናይጄሪያ በአፍሪካ በሕዝብ ቁጥር አንደኛ ስትሆን ከዓለም ደግሞ ሰባተኛ ናት። የናይጄሪያ ኢኮኖሚ በዓለም ላይ በፍጥነት በማደግ ላይ ካሉት ኢኮኖሚዎች ይመደባል። የዓለም አቀፍ ገንዘብ ፈንድ እንደሚገምተው የናይጄሪያ ኢኮኖሚ በ2011 እ.ኤ.አ. በ8% ያድጋል።

ናይጄሪያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ ሲሆን መንግሥቷ በአሜሪካ መንግሥት ላይ ነው የተመረኮዘው። የህግ አውጪው አካል አወቃቀር የዌስትሚኒስትር ሥርዓትን ይከተላል። በአሁኑ ጊዜ ጉድላክ ጆናታን ፕሬዝዳንት ናቸው። ፕሬዝዳንቱ ለሁለት የአራት ዓመት ጊዜ ሲያገለግል በሕዝቡ ነው የሚመረጠው።

የናይጄሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ሁለት አካሎች አሉት። እነዚህም ሴኔት እና የተወካዮች ምክር ቤት ናቸው። ሴኔቱ 109 መቀመጫዎች ሲኖሩት እያንዳንዱ ክልል በሶስት አባሎች ይወከላል። የአቡጃ ርዕሰ አካባቢም አንድ ተወካይ አለው። የሴኔት አባላት በሕዝብ ይመረጣሉ። የተወካዮች ምክር ቤት 360 መቀመጫዎች ሲኖሩት የእያንዳንዱ ክልል ወካዮች በሕዝብ ብዛት ነው የሚወሰነው።

ነፃነቷን በ1960 እ.ኤ.አ. ካገኘች በኋላ ናይጄሪያ ለአፍሪካ ነፃነትና ክብር መታገል ዋና የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ አድርጋለች። የደቡብ አፍሪካን አፓርታይድ ሥራዓት በመቃወም ትልቅ ሚና ተጫውታለች። በ1960ዎቹ እ.ኤ.አ. ናይጄሪያ ከእስራኤል ጋር የጠበቀ ግንኙነት የነበራት ሲሆን እስራኤል የናይጄሪያ ፓርላማ ህንጻዎችን አሰርታለች።

ናይጄሪያ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት መስራች አገር ናት። በምዕራብ አፍሪካም ሆነ በአፍሪካ በጠቅላላ ትልቅ ተጽዕኖ አላት። በተጨማሪም እንደ ኤኮዋስ ያሉ የምዕራብ አፍሪካ የትብብር ድርጅቶች መሥራች ናች።

ከ1970ዎቹ እ.ኤ.አ. ጀምሮ ናይጄሪያ ዋና የነዳች አምራች ስትሆን የኦፔክ አባል ሀገር ናት።

በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ናይጄሪያውያን በኢኮኖሚ ችግር ምክንያት ወደ አውሮፓ፣ ሰሜን አሜሪካ እና አውስትራሊያ ተሰድደዋል። ከአንድ ሚሊዮን የሚበልጡ ናይጄሪያውያን በአሜሪካን እንደ ሚኖሩ ይገመታል።

የናይጄሪያ ጦር ሠራዊት ሀገሯን የመከላከል፣ የሀገሯን ፍላጎት የማስጠበቅ እና ፀጥታ አስጠባቂ ጥረቶችን የመደገፍ ግዴታ አለበት። ሠራዊቱ የምድር፣ የባህርና የአየር ኃይል አለው። ሠራዊቱ ከነፃነት ጀምሮ በሀገሯ ታሪክ ላይ ትልቅ ሚና ተጫውቷል። በተለያዩ ጊዜያት የውትድርና ጁንታዎች ሥልጣን በመያዝ አገሯን አስተዳድረዋል።

የናይጄራያ ሠራዊት በፀጥታ ጠባቂነት ደረጃ ከ1995 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በላይቤሪያ (1997 እ.ኤ.አ.)፣ አይቮሪ ኮስት (ከ1997 እስከ 1999 እ.ኤ.አ. ) እና ሲየራ ሊዮን (ከ1997 እ.ኤ.አ. 1999 እ.ኤ.አ.) ተሰማርቷል።

በግብርና ናይጄሪያ በዋናነት ለአለም የምታቀርበው ምርቶች በተለይ ካካውና ጎማ ናቸው። እንዲሁም ፔትሮሊየም ከሚያቀርቡት አገራት 12ኛ ነች። በተጨማሪ፣ የመኪና ሥራ ድርጅት (ኢኖሶን ተሽከርካሪ መፈብረክ) ይኖራል። 

ናይጄሪያ በምዕራብ አፍሪካ በጊኒ ባሕረ ሰላጤ ላይ ትገኛለች። የቆዳ ስፋቷ 923,768 ካሬ ኪ.ሚ. ሲሆን ከዓለም ፴፪ኛዋ ትልቅ ሀገር ናት። ድንበሯ 4,047 ኪ.ሜ. ርዝመት ሲኖረው ከቤኒን 773 ኪ.ሜ.፣ ኒጄር 1,497 ኪ.ሜ.፣ ቻድ 87 ኪ.ሜ.፣ ካሜሩን 1,690 ኪ.ሜ. ትዋሰናለች። በተጨማሪም 853 ኪ.ሜ. ርዝመት ያለው ጠረፍ አላት።

በናይጄሪያ ውስጥ ከፍተኛው ቦታ ቻፓል ዋዲ ተራራ ሲሆን ከፍታው 2,419 ሜትር ከባህር ጠለል በላይ ነው። የአገሯ ዋና ወንዞች ኒጄር እና ቤንዌ ሲሆን ወደ ኒጄር ደለል ይፈሳሉ።

ናይጄሪያ በሠላሳ ስድስት ክፍላገራት እና አንድ የፌዴራል ግዛት ተከፍላለች። እነዚህ ክፍላገራት ወደ ፯፻፸፬ የአካባቢ ግዛቶች ተከፍለዋል።

ስድስት የናይጄሪያ ከተሞች ከአንድ ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች አሉባቸው። እነዚህም ሌጎስ፣ ካኖ፣ ኢባዳን፣ ካዱና፣ ፖርት ሀርኮርት እና ቤኒን ከተማ ናቸው። ሌጎስ ከ፰ ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሲኖሩባት ከሣህራ በታች በአፍሪካ ትልቁ ከተማ ናት። 

ፈዴራል ግዛት፦ አቡጃ

ተ.መ.ድ. እንደ ሚገምተው የናይጄሪያ የሕዝብ ቁጥር በ2009 እ.ኤ.አ. 154,729,000 ነበር። የ2006 እ.ኤ.አ. ብሔራዊ ቆጠራ እንደ ሚያመለክተው ከሆነ የሕዝቡ ቁጥር 140,003,542 ነበር። 

በናይጄሪያ ውስጥ ከ፪፻፶ በላይ ብሔሮች ይገኛሉ። ትልቆቹ ብሔሮች ፉላኒ ወይም ሀውዛ፣ ዮሩባ እና ኢግቦ ናቸው። ከእነሱ ቀጥሎ ደግሞ ኤዶ፣ ኢጃው፣ ካኑሪ፣ ኢቢብዮ፣ ኑፔ እና ቲቭ ይገኛሉ።

በናይጄሪያ ውስጥ የተቆጠሩት ቋንቋዎች ፭፻፳፩ ይሆናሉ። ከእነዚህም ውስጥ ፭፻፲ቹ መደበኛ ተናጋሪዎች አሏቸው። ሁለት ቋንቋዎች እንደ ሁለተኛ ቋንቋ ብቻ ነው የሚነገሩት። ዘጠኙ ደግሞ ተናጋሪ የሌላቸው የጠፉ ቋንቋዎች ናቸው።

ከእንግሊዝኛ በኋላ ዋናዎቹ ልሳናት ዮሩብኛ፣ ሐውዝኛና ኢግቦኛ ናቸው።




#Article 18: ግብፅ (1925 words)


ግብፅ ወይም ምጽር፣ ምሥር (አረብኛ مصر ) በሰሜን ምስራቅ ኣፍሪካ የምትገኝ አገር ናት። 77 ሚሊዮን ከሚሆነው ህዝቧ አብዛኛው ከናይል ወንዝ ዳርቻ በአንድ ኪሎሜትር ክልል ውስጥ ይገኛል። የግብፅ አብዛኛው መሬት በሰሃራ በረሃ ክልል ውስጥ ይገኛል። ዋና ከተማዋ ካይሮ ስትሆን ከአፍሪካም ትልቋ ከተማ ናት። ሌላ ትኩረት የሚሰጣት ከተማ አሌክሳንድሪያ (እስክንድርያ) ናት። አሌክሳንድሪያ የአገሪቱ ዋና ወደብ ስትሆን በህዝብ ብዛት ከአገሪቱ ሁለተኛ ናት።

ግብፅ በሰሜን ከሜዴቴራኒያን ባሕር በምሥራቅ ከቀይ ባሕር፤ በደቡብ ከኖብያ፤ በምዕራብ ከምድረ በዳው አገር ይዋሰናል። ነጭ አባይ በግብፅ መካከል ያደርግና ከደቡብ ወደ ምሥራቅ ይሄዳል። የአባይ ወንዝ የሚሞላው በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ነው። በግብፅ የሚዘንበው አንድ አንድ ጊዜ ብቻ ስለ ሆነ ግብፅ በአባይ ለምቶ ይኖራል።

በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ከማየ አይኅ ቀጥሎ መጀመሪያ የአፍሪካ ሕዝብ የኖኅ ልጅ የካም ዘሮች ናቸው፤ ይህ አገር ሰናዖር ለሚሉት ቅርብ ስለ ነበር የባብል ግንብ ከተሠራ በኋላ ከዚህ ተነስተው ወደ ግብፅ ወረዱ። 

የግብጽ ቀድሞ ዘመን መንግሥት ዋና ጥንታዊ ነው፤ የመሠረተውም ፈርዖን ሜኒስ የተባለው ነው። ጸሓፊው ጊዮርጊስ ስንቄሎስ (፰፻ ዓ.ም. አካባቢ የጻፈው) ይህ ፈርዖን ሜኒስ በዕውነት የካም ልጅ ምጽራይም እንደ ነበረ ገመተ።

ዳሩ ግን አባ አውሳብዮስ በጻፉት ዜና መዋዕል ዘንድ (፫፻፲፯ ዓ.ም. ተጽፎ)፣ የድሮ ግብጻዊው ባለታሪክ ማኔጦን (፫ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ.) ስለ ኋለኞቹ ግብጻውያን ሲጽፍ፣ ይኮሩበት የነበረው የታላቁ ጥንት ዘመን ከማየ አይህ አስቀድሞ እንዳለፈ፣ በኋላም በዚያው አገር ዳግመኛ ከሠፈረበት ከካም ልጅ ምጽራይም በውኑ እንደ ተወለዱ ጽፎ ነበር። ተመሳሳይ ታሪክ በእስላም ጸሐፊዎች በግብጻዊው እብን አብድ ኤል-ሀከም እና በፋርሳውያን አል-ታባሪና ሙሐመድ ቈንዳሚር መጻሕፍት ሲገኝ፣ ፒራሚዶች፣ እስፊንክስ ወዘተ. ሁሉ የተሠሩ ከጥፋት ውኃ በፊት በኖሩት ክፉ ዘሮች ሆኖ፣ ከዚያ በኋላ ግን አገሩ ለካም ተወላጅ ለምጽራይም ('ማሣር' ወይም 'መሥር') ተሠጠ ብለው ጻፉ።

በግሪኩ ጸሐፊ ሄሮዶቶስ ዘንድ፣ የግብፅ ቀድሞ ዘመን የመጀመሪያው ፈርዖን ሜኒስ ነጭ አባይን ከመነሻው ወደ ጎን መለሰና ውሃው ይፈስበት በነበረው ላይ ሜምፊስ የተባለውን ከተማ ቆረቆረ። ታላቅ ንጉሥም ስለ ነበረ ከሞተ በኋላ ሕዝቡ እንደ አምላክ አድርገው አመለኩት። በዘመናዊ አስተሳስብ፣ ይህ ላይኛ ግብጽና ታችኛ ግብጽ ያዋሐደው መጀመርያው ፈርዖን መታወቂያ ለሥነ ቅርስ ከሚታወቀው ፈርዖን «ናርመር» ከተባለው ጋር አንድ ነው። 

ናርመር (ሜኒስ) አገሩን ካዋሐደ አስቀድሞ ሌሎችም ነገሥታት (ለምሳሌ ንጉሥ ጊንጥ) በአገሩ ክፍሎች ብቻ ላይ እንደ ነገሡ ከተገኙት ቅርሶች (የመንደሮቹ መኳያ ሰሌዳ ወይም የጊንጥ ዱላ እንደሚያሳይ) ይታወቃል።

የሃይሮግሊፍ ቅርሶችና መዝገቦች ለማንበብ ችሎታው አሁን ስላለ፣ ሜኒስ ከነገሠ በኋላ የግብፅ ታሪክ በጥቂት መጠን ተገልጾአል። መጀመርያው ሥርወ መንግሥታት (፩ኛው እስከ ፮ኛው ድረስ) የቀድሞ ዘመን መንግሥት ይባላሉ። በ፩ኛው ሥርወ መንግሥት ሰባአዊ መስዋዕት በሰፊ ይደረግ ነበርና ከፈርዖኖቹ ጋራ ብዙ ሎሌዎች አብረው ይቀበሩ ነበር። የሔሩ ወገን በሴት ወገን ላይ ይበረታ ነበር። በ፪ኛው ሥርወ መንግሥት የፈርዖኖች መቃብር ከተማ ከላይኛ ግብጽ ወደ ታችኛ ግብጽ (ስሜኑ) ተዛወረ። በኋለኛ 2ኛው ሥርወ መንግሥት ዘመን የሴት ወገን ወኪል ፈርዖን ፐሪብሰን ተነሣና ያንጊዜ ትግሎች እንደ በዙ ይመስላል። በ፫ኛው ሥርወ መንግሥት መጀመርያ የሔሩ ወገን ለሥልጣን ተመልሶ፣ ነጨሪኸት የተባለው ፈርዖን የመጀመርያውን ሀረም (ፒራሚድ) አሠራ። ከርሱም በኋላ የተነሡት ታላላቅ ፈርዖኖች በጊዛ ሜዳ ላይ ፒራሚዶቻቸውን እንዲሁም የጊዛ ታላቅ እስፊንክስን ሠሩ። በ፬ኛውም ሥርወ መንግሥት የፈርዖኖች ዝሙት የገዛ እኅቶቻቸውን እስከሚያግቡ ድረስ ደረሰ። በ፭ኛው ሥርወ መንግሥት መጨረሻ ፈርዖኖች በሀረሞቻቸው ውስጥ የሀረም ጽሕፈቶች ያስቀረጹ ጀመር፤ እነኚህ ጽሕፈቶች የሔሩ ተከታዮች ወገን (ወይም «ደቂቃ ሔሩ») በሴት ተከታዮች ወገን ላይ የፈጸሙትን ጨካኝ የጭራቅነት ሥነ ስርዓት ይመሰክራሉ። ይህም አስጨናቂ ሁኔታ በ፮ኛው ሥርወ መንግሥት እየተቀጠለ ፈርዖኖቹ ዓለማቸውን ሁሉ ከነጎረቤቶቻቸውም ጋር በጽናት ይገዙ ነበር።

፮ኛው ሥርወ መንግሥት ከነገሠ በኋላ የግብፅ ታሪክ እጅግ ግልጽ ሆኖ አይታይም። በታሪክ ጸሐፍት እንደ ማኔጦን ዝርዝሮች በኩል፣ ለ፯ኛው-፰ኛው ሥርወ መንግሥታት በርካታ ስሞች ቢመዘገቡም፣ ከጥቂቶቹ ብቻ በስተቀር አንዳችም ሥነ ቅርሳዊ ማስረጃ ከቶ ስላልተገኘላቸው፣ ስሞች ብቻ ቀርተው በእውነት እንደ ኖሩ ወይም ዝም ብለው በማስመስል እንደ ተፈጠሩ አይታወቀም። ከቀድሞውም ዘመን በኋላ በእርግጥኛነት የነገሡት መጀመርያ ፈርዖኖች የግብጽ መካከለኛውን ዘመን መንግሥት የመሠረቱት በስማቸውም ውስጥ «ታ-ዊ» (ሁለቱ አገራት ወይም በዕብራይስጥ ምስራይም) የተባሉት ናቸው።

በ6ኛው ሥርወ መንግሥት መጨረሻ ኒቶክሪስ የተባለች ሴት የአገሩ ንግሥት እንደ ሆነች የሄሮዶቶስና የማኔጦን ታሪኮች ይነግራሉ። ሄሮዶቶስ እንደሚለው፣ ወንድሙዋን ግብፆች ስለ ገደሉባት እሷም ልትበቀልለት አሰበች። ለዚሁ ጉዳይ ከመሬት ውስጥ አንድ ታላቅ አዳራሽ አሠራች። ከዚያም ታላቅ ግብር አዘጋጅታ የወንድሙዋን ገዳዮች ወደዚሁ ግብር ጠራቻቸው። የተጠሩትም በግብፅ ግዛት የታወቁ ክቡራን ነበሩ። እንዲሁ ሆኖ ሳለ በድንገት ከውጪ በራሳቸው ላይ ውካታና ፍጅት ጩኸትም ተነሳ። የጥፋት ውሃ አዳራሹን ሰብሮ ገባ። ንግሥት ኒቶክሪስ አስቀድማ የወንዙን ውሃ በሚስጥር ወደ አዳራሹ እንዲገባ አድርጋ ነበርና ውሃው በዚያ ታላቅ ግብር ላይ እንዲለቀቅ አደረገች። በዚያም የገቡ ሁሉ ሰጥመው ቀሩ። ይህ የኒቶክሪስ ታሪክ በሄሮዶቶስም ሆነ በማኔጦን ቢገኝም፣ በዘመናዊ ሥነ ቅርስ አስተያየት ለዘመንዋ ምንም ማስረጃ ስላልተገኘ አሁን እንደ አፈ ታሪካዊ ንግሥት ብቻ ትቆጠራለች።

በግሪኮች የታሪክ ጸሐፍት ዘንድ ሌላ ስመ ጥሩ ፈርዖን ሲሶስትሪስ ነበር። ይህ ንጉሥ ዓለምን ለማሸነፍ አስቦ ከግብፅ ሲነሣ የሚሊዮን እኩሌታ የሚሆኑ እግረኛ ወታደሮች፣ ፳፬ ሺህ ፈረሰኞች፤ ፳፯ ሺህ የተሰናዱ ሠረገሎች እንደ ነበሩት ይተረኩ ነበር። ዝና ፈላጊነቱ በክብር ተፈጸመለትና ትልቅ ድል አገኘ። በየሄደበት ስፍራ ሁሉ ከእብነ በረድ የተሠራ ሐውልት አቆመ። የሚመጣው ትውልድ እንዳይረሳው ባቆመው ሐውልት ላይ ጽሕፈት እንዲቀረጽበት አደረገ። በብዝዎቹ ሐውልት ላይ እንዲህ የሚል ቃል ተጽፎአል።

ነገር ግን ዘመናዊ የታሪክ ጸሓፊዎች እንደዚህ አላደረገም ብለው ይጠራጠራሉ። በማኔጦን ነገሥታት ዝርዝር «ሴሶስትሪስ» የሚባል ፈርዖን በ12ኛው ሥርወ መንግሥት በፈርዖን 3 ሰኑስረት (ሰንዎስረት) ፋንታ ይታያል። ስለዚህ የሴሶስትሪስ አፈ ታሪክ ከሰንዎስረት ትዝታ እንደ ተወረደ ይታመናል።

ሺሻክ የተባለ የግብፅ ንጉሥ ኢየሩሳሌምን ስለ ያዛት የሰሎሞን ቤተ መቅደስ በዝብዞ ንዋየ ቅድሳቱን ሁሉ ጠርጉ ወሰደው።

አሚኖፌስ የተባለ ስመ ጥሩ የግብፅ ንጉሥ ነበር፤ ይህም ምናልባት ለስሙ መጥሪያ (ለመታሰቢያው) ብሎ አንድ ትልቅ መቅደስና ምስል ያቆመ ሜምኖን የተባለው ንጉሥ ሳይሆን አይቀርም። የዚህም ፍራሽ እስከ ዛሬ በቴቤስ ይታያል። ያቆመውም የድንጋይ ምስል ፀሓይ ስትወጣ ደስ የሚያሰኝ ቃል ፀሓይ ስትጠልቅ የኅዘን ቃል ያሰማል ይባላል። ዛሬም በዚያ የሚያልፉ መንገደኞች ድምፁን የሚሰሙ ይመስላቸዋል።

፭፻፳፭ ዓመት ከዘመነ ክርስትና በፊት ካምቢሲስ ንጉሠ ፋርስ ግብፅን ድል አድርጎ ነበረና ሳሜኒቱስ የተባለውን የግብፅን ንጉሥ የወይፈን ደም በግድ ስለ አስጠጣው እንደ መርዝ ሆነበትና በዚሁ ጠንቅ ሞተ።

፫፻፴፪ ዓመት ከዘመነ ክርስትና በፊት የመቄዶንያው ንጉሥ ታላቁ እስክንድር ግብፅን ድል አድርጎት ነበር። በዚህ ስፍራ እስክንድሪያ የተባለ አንድ ስመ ጥሩ ከተማ ሠራ። ይህም ከተማ በዓለም ከታወቁት ከተሞች እጅግ ጥሩ ሆኖ የተሠራና መሰል የሌለው አያል መቶ ዓመት የቆየ ቤተ መንግሥት መሆኑ ታውቆዋል። የጥንቱ ሥራው ፈራርሶ ዛሬ የሚታየው እስክንድሪያ ከጥንቱ በጣም ያነሰ ነው።

እስክንድር ሲሞት በዚሁ በእስክንድርያ ተቀበረ። ይኸው ከተማ ስመ ጥሩ በመሆኑ እስከ ዛሬ በግብፅ ዋና የንግድ ሁለተኛ ከተማ ተብሎ ይጠራል።

እስክንድር የሱ ጀኔራል የነበረውን ጵቶልሚዎስን አገሩን እንዲገዛ ሾመው። ከጵቶልሚዎስ ጀምሮ ተወላጆቹ ሁሉ የንጉሥ ዘር ተብለው ሁሉም ጵቶልሚዎስ ተብለዋል። ፪፻፺፬ ዓመት ገዝተዋል። ከነዚህም በመጨረሻ የነገሠው ጵቶልሚዎስ ዲዮናስዮስ ይባላል። በላዮ የገዛ ሚስቱ ተነሥታ ሸፈተችበትና ተዋጋችው። ጵቶልሚዎስ ዲዮናስዮስ በመጨረሻ ድል ሆነና ለማምለጥ የማይሆንበት ቢሆን በነጭ ዐባይ ወንዝ ውስጥ ገብቶ ሰጠመ። ሚስቱ ክሌዎፓትራ የተባለች የግብፅ ዋና ገዢ ሆነች። አሉ ተብለው ከሚጠሩት ቆነጃጅት አንዲቱ እርስዋ ነበረች። ስጦታዋና ተፈጥሮዋ ከውበትዋ ጋር የተካከሉ ነበሩ። ዳሩ ግን ክፉ ነበረች። ከሠራችው ሁሉ እጅግ የሚያሰቅቀው ነገር ያሥራ አንድ ዓመት ሕፃን የነበረውን የገዛ ወንድምዋን በመርዝ ማስገደልዋ ነው። ምንም ክፋትዋን ዓለም ቢያውቀው እኔ ነኝ ያለ ጀግና የውበት ማጥመጃዋን ሊቃወም የሚችል አልተገኘም። Whole paragraph is POV

ማርክ አንቶኒ የተባለ የሮማ ጀኔራል በግሪክ አገር ፊሊጵ በተባለች አውራጃ ብሩተስንና ካሲውስን ድል ባደረገ ጊዜ ከሜዴቴራኒያን ባሕር በሰሜን ምሥራቅ ወደምትሆን ወደ ሲሲሊያ እንድትመጣ ክሌዎፓትራን አስጠራት። ምክንያቱም ለብሩተስ ረድታ ነበርና ሊቀጣት አስቦ ነበር።

ክሌዎፓትራ ጥሪው እንደ ደረሳት እሺ ብላ በፍጥነት ተነሥታ በተለይ በወርቅ ባጌጠ ታንኳ ገባች። ታንኳው በሽራው ፈንታ ዋጋው የበዛ የከበረ ሐር ነበረው። ታንኳውን በብር መቅዘፊያ የሚቀዝፉት የተወደዱ ቆነጃጅት ነበሩ።

ንግሥት ክሌዎፓትራ ሐር ተጋርዶላት በመርከቡ ተደግፋ ተቀምጣ ነበረች። እንደዚህ ሁና ሲድኑስ በተባለው ወንዝ ተንሳፈፈች። ያለችበትም ታንኳ እጅግ ያማረ ነበር። እርስዋም ራስዋ የተወደደች ነበረች። የሚታየው ሁለመናዋ ሕልም ይመስል ነበር።

ከታንኳው መጋረጃ ነፋስ እየጠቀሰ የሚወስደው ሽቶ እያወደ ክሌዎፓትራ እንደ ተቃረበች ማርክ አንቶኒን አስጠነቀቀው። ከሩቅ ልብ የሚነካ የሙዚቃ ድምፅ ይሰማ ነበር። ቀጥሎ የብር መቅዘፊያው ሲብለጨለጭ ከሩቅ ይታይ ነበር።

ነገር ግን አንቶኒ የግብፆችን ንግሥት በተመለከተ ጊዜ ምንም አላሰበም። ማርክ አንቶኒ ከክሌዎፓትራ እስኪገናኝ ድረስ ክቡር ሰውና ጀግና መሆኑን አሳየ እንጂ ከዚያ በኋላ ግን ፍጹም እንደ ባሪያዋ ሆነ።

ከክሌዎፓትራና ከርሱ ክፉ አካሄድ የተነሣ ኦክታቢዎስ ከተባለ ከሌላ የሮማ ጀኔራል ጋር በግሪክ አገር አክቲውም በተባለች አውራጃ ላይ ተዋግተው አንቶኒ ድል ሆነና በገዛ ሰይፉ ወድቆ ሞተ። ክሌዎፓትራም ኦክታቢዎስ በሕይወትዋ ወደ ሮማ የወሰዳት እንደ ሆነ በሕዝብ መኻከል እንደሚያጋልጣት ተረዳችው።

ስለዚህ ለመታገሥ የማይችል ሲሆንባት ጊዜ በግብፅ አገር አንድ ዐይነት በተናከሰ ጊዜ ሕመሙ የማይሰማ መርዛም እባብ ስላለ ክሌዎፓትራ ከንደዚህ ያለ መርዛም እባብ አንዱን አሲዛ አስመጥታ ሰውነቷን አስነከሰች። ትንሽ ቆይታ ሁለመናዋ ደነዘዘ አበጠ ወዲያው ልቡዋ መምታቱን አቆመ። ውበት የነበራት ክፋዩቱ የግብፅ ንግሥት ክሌዎፓትራ እንደዚህ ሆና ፴ ዓመት ከክርስቶስ ልደት በፊት ሞተች።

ከንግሥት ክሌዎፓትራ ሞት በኋላ ግብፅ ለሮማ መንግሥት ተገዛና እስከ ዘመነ ክርስትና ፮፻፵ ዓመት ድረስ የምሥራቅ መንግሥት እየተባለ ለሮማ እንደ ተገዛ ቆየ። ከዚህ በኋላ ሳራሲኖች ድል አደረጉትና እስከ ፮፻ ዓመት ቆየ።

የሳራሲን ገዦች ያሠለጠኗቸው ማምሉኮች የተባሉት የገዛ ዘበኞቻቸው ሳራሲኖችን ከዙፋናቸው ዘርጥጠው አወረዷቸው። ቱርክ መጥቶ ድል እስኪያደርጋቸው ድረስ ማምሉኮች ግብፅን እስከ ፲፯፻፱ ገዝተዋል። ቱርኮችም ግብፅን እስከ ፲፯፻፺፰ ዓመት ገዝተዋል። ከዚህ በኋላ ናፖሊዮን ቦናፓርቲ አርባ ሺህ የሚሆን የጦር ሠራዊት ከፈረንሳይ አገር አምጥቶ፤ ግብፅን ወረረ።

ቱርኮችም ግብፅን ከያዙ ወዲህ ማምሉክ የተባለውን ጭፍራ ወደ ሥራቸው አግብተው ጠብቀውት ነበርና እነዚህ ተስፋ እስኪቆርጡ ድረስ ተከላከሉ። ጦርነቱን የሚዋጉበት ስፍራ በፒራሚዱ አጠገብ ነበር። በዚያ ሲዋጉ ሳሉ እኩሌቶቹ እዚያው ታረዱ። ሌሎቹም እየዘለሉ ወደ ነጭ ዐባይ ወንዝ ባሕር ሰጠሙ። ከዚህ ጦርነነት በኋላ ናፖሊዮን ቶሎ ብሎ ወዲያው ወደ ፈረንሳይ አገር ተመለሰ እንጂ በዚህ አልዘገየም። ሲሄድም ጀኔራል ክሌበር የተባለውን ለፈረንሳይ ጦር ጠቅላይ አድርጎት ሄደ።

ጀኔራል ክሌበር ጀግና ሰው ነበር። ዳሩ ግን ጨካኝ ነበርና ጨካኝነቱ ሕይወቱን እስከ ማጣት አደረሰው።

ይኸው ጨካኙ ጀኔራል አንድ ቀን ሼህ ሳዳ የሚባል አንድ ሽማግሌ እስላም አገኘና ውስጥ እግሩን በከዘራ አስደበደበው። ወዲያው ትንሽ እንደ ቆየ ጀኔራሉ ወደ መስጊድ ገብቶ ሳለ አንድ የተናደደ እስላም ገሠገሠና በጩቤ ቢሽጥበት ያን ጊዜውኑ ሞተ።

በ፲፰፻፩ ዓመት እንግሊዝ ፈርንሳዮችን ከግብፅ ለማስወጣት ከብዙ ጦር ጋራ ሰር ራልፍ አቤሮክሮምቢን ሰደደው። ጀኔራል መኑ የፈረንሳይ ኮማንደር ነበር። አቡኬር ላይ ተዋጉና ሰር ራልፍ አቤሮክሮምቢ ድል አደረገው። ዳሩ ግን እርሱም ራሱ ክፉኛ ቆስሎ ነበር።

በዚያው ዓመት የፈርንሳይ ጦር ተሸነፈና ከግብፅ ወጥቶ በመርከብ ተሳፍሮ ወደ ፈረንሳይ አገር ተመለሰ። ዳሩ ግን ባላገሮቹ ከፊተኞቹ ገዢዎቻቸው ከቱርኮች ይልቅ የፈረንሳይ ጀኔራል ቅን ፍርድ እየፈረደ በመልካም አገዛዝ በደንብና በሕግ ይገዛቸው ነበርና በመሄዱ እጅግ አዝነው ተላቀሱ።

የዛሬው የግብፅ ዋና ከተማ ትልቁ ካይሮ ነው። ቀድሞ ከነበረው ይልቅ የዛሬው በጣም ትንሽ ነው። ነገር ግን ፫፻ ሺህ ሰዎች ይኖሩበታል።

ከሦስትና ከአራት ሺሕ ዓመት በፊት ብዙ ሚሊዮን ሕዝብ እንደ ነበረ እጅግ ለዐይን ያማሩ ታላላቅና ሰፋፊ የነበሩ የከተሞቻቸው ፍራሽ በመገኘታቸው እንረዳለን። በጥንቱም ሆነ ወይም በዛሬው አስተያየት ስንገምተው እጅግ ደምቆ የሚታይ ከተማ እንደ ቴቤስ ያለ አይገኝም። Huge POV ባለመቶ በር ከተማ ይሉታል። በጦር ጊዜ ከዚህ ከተማ በያንዳንዱ በር የሚወጣው የጦር ሠራዊት እንደሚከተለው ነው። መሣሪያቸው የተሰናዳ ፪፻ ሠረገሎችና ፪ ሺሕ ወታደሮች ናቸው።

ከ፳፬፻ ዓመት በፊት የነበረ ካምቢሲስ የተባለ የፋርስ ንጉሥ በነበረበት ዘመን ቴቤስ ፈርሶ ነበር። የከተማው ፍራሽ ከነጭ ዐባይ ወንዝ ግራና ቀኝ ፳፯ ማይል ርቀት ተበታትኖ እስከ ዛሬ ይታያል። ከሐውልቱም ያያሎቹ ውፍረት ፲፪ ጫማ (ፊት) ይሆናል።

ከግብፆች ነገሥታት አንደኛው ዙሪያው አርባ አምስት ማይል የሚሆን ትልቅ ጉድጓድ ቆፍራችሁ ወደታች ጥልቅነት ያለው ባሕር ይሁን ብሎ ሕዝቡን አዘዛቸው። አንደኛው ንጉሥ ደግሞ ከመሬት ውስጥ አስቆፍሮ ከዕብነ በረድ የታነጸ ሦስት ሺሕ ጓዳ ያለው አዳራሽ አሠራ። ለዚህም ዘወርዋራ መንገድ ነበረው።

ከፍ ባለው ጓዳ አንዲት የተቀደሰች አዞና ግብፆችም የሚያመልኩዋቸው ሌሎች አራዊት ነበሩ። ከምድር በታች ባለው ጓዳ የግብፃውያን ነገሥታት ዐፅም ተጋድሞአል።

ደግሞ አንደ የሚያስደንቀው ሥራ መሬቱን ወደ ውስጥ ቆፍረው አለቱ ሲወጣ ያንን ወቅረው የድንጋይ ምሰሶ ያደርጉታል። ውስጥ ለውስጥ ጋሌሪ የደርብ መንገድ እያደረጉ ይሠሩታል። በዚህ ውስጥ ከሺሕ ዓመት በፊት የሞተውን ሰው ሬሳ አጋድመውት ይገኛል። ሳይለወጥ ልክ እንደ ተቀበረ ጊዜ ሆኖ ይታያል። ይህንንም ሙሚስ ይሉታል።

የግብፅ ፒራሚድ በነጭ ዐባይ ወንዝ ዳር ይገኛል። ታላቁ ፒራሚድ ከፍታው ፭፻ ጫማ (ፊት) ነው። የግብፅ ፒራሚዶች የተሠሩበትን ዘመን የሠራቸውንም ሰው ማን እንደሆነ ከቶ አይታወቅም። ለመሆኑ ግን ለመቃብራቸውና ለዘለዓለም መታሰቢያ እንዲሆኑዋቸው ጥንታውያን የግብፅ ነገሥታት አሠርተቀቸዋል ይባላል። ነገር ግን ፒራሚዱ ሳይፈርስና ሳይናድ ምንም ብዙ ዘመን ቢቆይ የሠሩት ነገሥታት እነማን እንደ ሆኑ ስማቸው ተረስቷል።

በቴቤስ አጠገብ ባንድ ሜዳ ላይ ወንድና ሴት ሆነው የሰው መልክ የሚመስሉ ሁሉ ታላላቅ ሐውልቶች አሉ፤ ቁመታቸውም ፶ ጫማ (ፊት) ይሆናል።

በግብፆች መኻከል ከሚገኘው ከቀድሞ ሥራ ሁሉ በጣም የሚያስደንቅ ሲፊክስ የሚሉት ነገር ነው። ይኸውም ከታች አካሉ የአንበሳ ሆኖ ከላይ ከራሱ ትልቅ የሴት መልክ ነው። ዛሬ እንደሚታየው ከታች ያለው አካሉ በአሸዋ ውስጥ ተቀብሯል። የላይኛው ክፍል ከምድር በላይ የሚታየው ራሱና አንገቱ ነው። ይኸውም ቁመቱ ፸ ጫማ (ፊት) ነው። የተጠረበው ከአለት ድንጋይ ነው። በሩቁ ለተመለከተው ሰው አፍንጫዋ ደፍጣጣ የሆነች ሴት ከአሸዋ ውስጥ ብቅ ያለች ይመስላል።

በጥንት ቴቤስ አጠገብ ያለው ሉክሶር የተባለው ከተማ ፍራሽ ለተመልካቹ የሚያስደንቅ ሁኖ ያለመጠን ትልቅ ነው። ከመቅደሶቹ አንዱ የጥንት ሥራ ስመ ጥሩ ይመስላል። 

ግብፃውያን ይህን የሚያስደንቅ ሥራ ሲሠሩበት በነበሩ ዘመን ከዛሬ ይልቅ የዚያን ጊዜ ብዙ ጥበብ ዐዋቂዎችና የተማሩ ሰዎች እንደነበሩ ይታያል። ጥበባቸውንና ዕውቀታቸው ከፍ ያለ እንደ ነበረ ተመልክተው የሌሎች አገር ሰዎች እንደ አስማተኞች ይገምቱዋቸው ነበር።

ግብፆች ልማደ አገር ከንቱ አምልኮት ነበራቸው። ዋናዩቱም ጣዖታቸው ኢሲስ ትባላለች፤ ባልዋም ኦሲሪስ ይባላል። ምስላቸውን ሠርተው ለነዚህ ይሰግዱላቸዋል። ኢሲስ በጣም የተከበረች ጣዖት ናት፤ ሕዝቡም አያሎች መቅደሶች ሠርተውላታል፤ በዚህም ያመልኩዋታል።




#Article 19: ታሪክ (193 words)


ታሪክ በትክክል እንደሚሰፈን ከተጻፉት መዝገቦች አንስቶ ይጀምራል።  ከዚያ አስቀድሞ ምንም የተጻፉት መዝገቦች ሳይኖሩ የነበረው ወቅት ቅድመ-ታሪክ ይባላል። 

በአለም ደረጃ መጀመርያው የታወቁት የጽሑፍ ቅርሶች ከ3125 ዓክልበ. ያሕል ሲሆኑ ከጥንታዊ ግብጽ ሥነ ቅርስ ታውቀዋል። ለምሳሌ የመንደሮቹ መኳያ ሰሌዳ እና የጊንጥ ዱላ ከዚህ ዘመን ናቸው። ስለዚህ ከ3125 ዓክልበ. በፊት ያለፈው ሁሉ የአለም «ቅድመ-ታሪክ» ነው። 

በሌላ አገር ግን የጽሑፍ መዝገቦች እንዲሁም የታሪክ መጋረጃ መከፈቱ እንደ ግብጽ ጥንታዊ አይሆንም። ለምሳሌ ከሜክሲኮ ስሜን የኖሩት ስሜን አሜሪካ ኗሪዎች እንደ ብዙ አሕጉር ሰዎች ለረጅም ዘመን የጽሑፍ አካል ባጠቃላይ ያልነበራቸው ሆነው ቀሩ። ከዚሁ የመዝገቦች ጉድለት የተነሣ ከ1500 ዓም በፊት ያለው ጊዜ ሁሉ የስሜን አሜሪካ ቅድመ-ታሪክ ሊባል ይችላል። ከ1500 ዓም በፊት የተቀረጹት አንዳንድ ጽሑፎች በተለይም የፊንቄ ቋንቋ በሰፊ በአሜሪካዎች ቢገኙም ሁላቸው በፈረንጅ ሊቃውንት  አጠያያቂ ተብለዋል።   ሆኖም ስለነዚህ የፊንቄ ቅርሶች ወዘተ. በአሜሪካ ተገኝተው የሚገልጹ መጻሕፍት ሊገኙ ይቻላል። 

ከግብጽ ጥንታዊ መንግሥት ዘመን ቀጥሎ ጥንታዊ የሆኑት የኩኔይፎርም ጽሑፍ መዝገቦች ከመስጴጦምያ ከ2500 ዓክልበ. ያህል ጀምሮ ሊታዩ ይቻላል። የአንዳንድ ሌላ አገር መዝገቦች ለምሳሌ የቻይና መዝገቦች በልማድ ተጠብቀው ደግሞ ከዚህ ዘመን ያህል ጀምሮ ይዘግባሉ፤ ነገር ግን በቻይና በሥነ ቅርስ ረገድ ከ1200 ዓክልበ. በፊት የተቀረጸው ጽሑፍ ቢኖር አልተረፈም ወይም አልተገኘም። ከ1600 ዓክልበ. በፊት የነበረውንም የሥያ ሥርወ መንግስት የምናውቀው በኋላ በተዘገቡት ጽሑፎች ብቻ ሲሆን የዚያ ዘመን ታሪክ «አፈ ታሪክ» ሊባል ይችላል። 




#Article 20: ሜሪላንድ (165 words)


ሜሪላንድ (እንግሊዝኛ፦ Maryland) በአሜሪካ የምትገኝ ስቴት ስትሆን ምዕጻረ ቃሏ MD ወይም Md. ነው። ሜሪላንድ ከአሜሪካ አስራሶስት ጥንታዊ ስቴቶች አንዷ ናት። ከሜሪላንድ ጋር የሚገናኙ ስቴቶች ፔንስልቫኚያ ፣ ቨርጂኚያ ፣ ዌስት ቨርጂኚያ ፣ እና ዴላዌር እያሉ፤ ደግሞ በኮለምቢያ ክልል (ዋሽንግተን ዲ.ሲ.)ና በአትላንቲክ ውቂያኖስ ትወሰናለች። የቼሳፒክ ወሽመጥ ስቴቱን መሃል ለመሃል ይከፍለዋል። የሜሪላንድ ከፍተኛ ቦታ የባክቦን ተራራ ጫፍ ነው። የሜሪላንድ አየር ሁኔታ ከቦታ ቦታ ይለያያል። የምስራቅ ክፍሉ ሞቃታማ በጋና መካከለኛ ክረምት የአየር ሁኔታ ሲኖረው የምዕራብ ክፍሉ ደግሞ መካከለኛ በጋ እና በጣም ቀዝቃዛ ክረምት አለው። የሜሪላንድ ጠቅላላ ምርቶች በ2003 እ.ኤ.ኣ. ወደ 212 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚገመት ነው። በዚሁ ዓመት የአንድ ሰው የዓመታዊ ገቢ በኣማካይ 37,446 የአሜሪካን ዶላር ነበር ፣ ከአገሩ 5ኛ። ከፍተኛ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ፣ ወታደራዊ ካምፖች እና የሳይንስና የሕክምና ተቋማት በዚሁ ክፍላገር ይገኛሉ። የስቴቱ ዋና ያውሮፕላን ማረፊያ ባልቲሞር-ዋሽንግተን ዓለም አቀፍ ያውሮፕላን ማረፊያ (BWI) ነው። በ1996 የሜሪላንድ ጠቅላላ የህዝብ ብዛት 5,558,058 ነው ተብሎ ይገመታል። ከዚሁ ውስጥም 583,900ቹ ወይም 10.6 በመቶ ሌላ ስቴት ወይም አገር የተወለዱ ነዋሪዎች ናቸው። አብዛኛው ህዝብ የስቴቱ መዓከላዊ ክፍል ውስጥ ይኖራል።

የህዝቡ የዘር ክፍልፋይ

የሐይማኖት ክፍልይ




#Article 21: ውክፔዲያ (2005 words)


ውክፔዲያ የ የተሟላ ትክክለኛና ነጻ መዝገበ ዕውቀት (ኢንሳይክሎፒዲያ) ነው። ማንኛውም ሰው ለውክፔዲያ  ይችላል። ውክፔዲያ፣ ውክሚዲያ የተባለ ገብረ-ሰናይ ድርጅት ከሚያካሂዳቸው ፕሮግራሞች አንዱ ነው። ወደ 272 በሚጠጉ የተለያዩ ቋንቋዎች ፅሁፎች አሉት። ውክፔዲያ በኢንተርኔት ከሚገኙ ታዋቂ መዛግብተ ዕውቀት አንዱ ነው።

ውክፔዲያ ድረ-ገፅን መሰረት ያደረገና ማንም ሰው በቀላሉ እንዲያስተካክለው ተደረጎ የተዘጋጀ፣ በብዙ ቋንቋዎች የሚቀርብ ነጻ የኢንተርኔት መዝገበ እውቀት ወይም ኢንሳይክሎፒድያ ነው። ውክፔዲያ የሚለውን ስያሜ ያገኘው “ዊኪ” (ትርጉሙ ፈጣን ማለት ነው) የሚለውን ቃል ከሀዋይኛ ቋንቋ በመወሰድና “ኢንሳይክሎፒድያ” ከሚልው የእንግሊዘኛ ቃል ጋር በማዳቀል ሲሆን እያንዳንዱ የውክፔዲያ ገጽ እራሱ ከሚይዘው መረጃ በተጨማሪ አንባቢን ይበልጥ ግነዛቤ ለማስጨበጥ ከሚረዱ ሌሎች ተዣማጅ ገፆች ጋር ያለውን የትስስር መረጃም በተጨማሪነት አካቶ የያዘ ነው።

ውክፔዲያ የተመዘገበ (የሚታወቅ) አድራሻ ሳይኖራቸው ኢንተርኔት ላይ ያለምንም ክፍያ በፈቃደኝነት የሚጽፉ የበርካታ ግለሰቦች የጋራ የትብብር ውጤት ነው። ስለሆነም ከአንዳንድ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ገደብ ከተጣለባቸው ገጾች በስተቀር ማንኛውም የኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚና ፈቃደኛ የሆነ ሰው፤ በብዕር ስም፣ ትክለኛ ስምን በመጠቀም ወይም ደግሞ ያለምንም ስምና አድራሻ፣ ዊክፔዲያ ላይ የፈለገውን ሀሳብ የማስፈርና አስተዋጾ የማድረግ አሊያም ቀድሞ በሰፈረ ጽሁፍ ላይ ተጨማሪ መረጃን የማካታት፣ ስህተትን የማረምና የማስተካከል ፈቃድ ተሰጥቶታል። 

ውክፔዲያ ከተመሰረተበት ከ2001 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በፍጥነት በማደግ ላይ ያለና በብዛት ከሚጎበኙና ኢንተርኔት ላይ ከሚገኙ በረካታ የማጣቀሻ ድረ-ገጾች መካከል አንዱ ሲሆን 2011 እ.ኤ.አ. መጋቢት ወር ብቻ ከ400 ሚሊዎን በላይ አዳዲስ ጎብኝዎች ድረገጹን እንደጎበኙት ኮም ስኮር ያካሄደው የጥናተ ዘገባ ያመለክታል። ውክፔዲያ ከ82,000 በላይ አርታኢዎች፣ ከ270 በላይ በሚሆኑ ቋንቋዎች ያጠናቀሯቸውን ከ19,000,000 በላይ የሚሆኑ መጣጥፎችን አካቶ የያዘ ድረ-ገጽ ነው። ውክፔዲያ በአሁኑ ጊዜ 3,874,529 የእንግሊዘኛ መጣጥፎችን የያዘ ሲሆን በየቀኑ ከመቶ ሺህ በላይ ጎብኝዎች እንደሚጎበኙትም ይገመታል። በተጨማሪም በተለያዬ የአለም ክፍል የሚኖሩ ግለሰቦች በሚያደርጉት የጋራ አስተዋጾ በየቀኑ ከአስር ሺህ በላይ መጣጥፎች የተለያዩ ማስተካከያዎች የሚደረግባቸው ሲሆን ሌሎች በሺዎች የሞቆጠሩ አዳዲስ መጣጥፎች ደግሞ ውክፔዲያን በየቀኑ ይቀላቀላሉ።

ምንም እንኳን መሰረታዊ የውክፔዲያ መርሆች የሚባሉት አምስት ቢሆኑም ይህንኑ መዝገበ-ዕውቀት (ኢንሳይክሎፒዲያ) ይበልጥ ለማሻሻልና ለማጎልበት የሚያግዙ ሌሎች በርካታ ፖሊሲዎችና መመሪያዎች በውክፔዲያ ማህበረሰብ ተቀርጸው ተግባር ላይ የዋሉ ሲሆን ነገር ግን እነዚህን መሰረታዊ መመሪያዎችና ደንቦች አስተዋጾ ማድረግ ካልጀመረ በስተቀር ማንኛውም ሰው የማወቅ ግደታ የለበትም። 

በሌላ በኩል፣ ውክፔዲያ አንድ ሰው ካለው የሙያ ችሎታ ይልቅ ለሚያበረክተው አስተዋፆ ትልቅ ግምት የሚሰጥ በመሆኑ፣ በተለያየ የእድሜ ክልል፣ ባህልና መነሻ (ዳራ) የሚገኝ ማንኛውም ሰው የውክፔዲያ አስገዳጅ ፖሊሲዎችን አሟልቶ እስከተገኘ ድረስ፣ ውክፔዲያ ላይ የፈለገውን መጣጥፍ እንዳንድስ የመጨመር አሊያም ማንኛውም ውክፔዲያ ላይ የሚገኝ ሌላ ጽሑፍ፣ ማጣቀሻና ምስል የማየት የማሻሻልና የማረም አንዳደም ሙሉ ለሙሉ የመለዎጥና ፈቃድ አለው። በመሆኑም ውክፔዲያ በተለያዩ አስተዋጾ አድራጎዎች በየጊዜው ማሻሻያ የሚደረግበት እንደመሆኑ መጠን፣ አድስ ከሚካተቱት መጣጥፎች ይልቅ ቀደም ሲል በድረ ገጹ የተካተቱ መጣጥፎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየታረሙና እየተሻሻሉ የሚሄዱ በመሆናቸው የተሻለ የሃሳብ ጥራት፣ የመረጃ ሚዛናዊነትና ሙሉዕነት እንደሚኖራቸው ይታመናል።

ዊክፔዲያ ነፃ ኦንላይን መዝገበ-ዕውቀትን (free encyclopedia) ለመፍጠር አላማ አድርጎ የተመሰረተና ቀደም ሲል ኑፔዲያ (Nupedia) በመባል የሚታወቅ ፕሮጀክት ውጤት ነው። ኑፔዲያ ምንም እንኳን የተሻሻለ የዕርስ-በርዕስ መገማገሚያ (peer review) መንገዶችን አካቶ የያዘና ሙያዊ ብቃት ያላቸው መጣጥፍ አቅራቢዎችን የሚጠይቅ ፕሮጀክት የነበረ ቢሆንም መጣጥፎችን አትሞ ለማውጣት ረጅም ጊዜን ይጠይቅ ነበር። በመሆኑም ይንንም ችግር ለመቅረፍ፣ በ2000 እ.ኤ.አ. የኑፔዲያ መስራቹ ጂሚ ዌልስና በዚሁ ፕሮጀክት ተቀጥሮ ይሰራ የነበረ ላሪ ሳንገር የተባለ ሌላ ግለሰብ ኑፔዲያን እንደት ማሻሻልና ሌሎች ተጨማሪ ገፅታዎችን አካቶ የሚይዝ ፕሮጀከት ማደረግ እንሚቻል የጋራ ውይይት አደረጉ። በውይይታቸውም ወቅት እንደ ግብአት የተጠቀሟቸው አብዛሐኛዎቹ ምንጮች አንድ የዊኪ ድረ-ገጽ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የየራሳቸውን አስተዋፆ ማበረከት የሚችሉበት መዳረሻ ተደርጎ ድዛይን ሊደረግ እንደሚችል አመላከቱዋቸው። በዚህም መሰረት ማንኛውም ሰው የራሱን አድስ አስተዋፆ ማበርከትና ብሎም ሌሎች የቀረቡ መረጃዎችን ማስተካክልና ማረም እንዲያስችል ተደርጎ ዲዛይን የተተደረገው የመጀመሪያው የኑፔዲያ የዊኪ ገፅ እ.ኤ.አ ጥር 10 ቀን 2001 ዓ.ም. አየር ላይ ዋለ። 

ነገር ግን ሌሎች የኑፔዲያ ፕሮጀክት አካል የነበሩ አርታኢዎችና ሀያሲዎች በኑፔዲያ ፕሮጀክት ላይ የተደረገውን የማሻሻያ ለውጥ በተለየም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የየራሳቸውን አስተዋሶ ማበርከት የሚያስችልን ድረ ገፅ(ዊኪ) ቅርፅ እዲይዝ ተደርጎ መሻሻሉን በመቃዎማቸው፣ የተሻሻለው የኑፔዲያ ፕሮጀክት አድስ የስያሜ ለውጥ በማድረግና “ዊክፔዲያ” በመባል በራሱ አድራሻ (www.wikipedia.com) አንዳንዶች ዛሬ “የዊክፔዲያ ቀን” እያሉ በሚጠሩት ጥር 15 ቀን በይፋ ስራውን ጀመረ።

ለውክፔዲያ ሳንዲዬጎ የሚገኘውንና የመጀመሪያው የድረ-ገፁ መቀመጫ በመሆን ያገለገለውን ሰርቨር ኮምፒውተርና የመረጃ ማስተላለፊያ መስመሩን (bandwidth) በርዳታ የለገሰው ጂሚ ዌልስ ነበር። በተጨማሪም በራሱ በጂሚ ዌልስ እና በሌሎች ሁለት ጓደኞቹ የተቋቋመውና በአነስተኛ የኢንተርኔት የማስታዎቂያ ስራዎች ላይ የተሰማራ ቦሚስ (bomis) የሚባል ድርጅት ሰራተኞች የነበሩና ባሁኑ ጊዜም እየሰሩ የሚገኙ ሌሎች ግለሰቦችም የራሳቸውን አስተዋፆ ለዊክፔዲያ አበርክተዋል። በዚህ ረገድ ከሚጠቀሱት፣ የቦሚስ ተባባሪ መስራችና በአሁኑ ጊዜ የድርጂቱ ዋና ስራ አስኪያጅ በመሆን እያገለገለ የሚገኘው ቲም ሸልና ፕሮገራመሩ ጃሰን ሪቺ ይጠቀሳሉ። በሌላ በኩል ዊክፔዲያ አሁን ወደ ሚታወቅበት www.wikipedia.org የአድራሻ ለውጥ ያደረገው ለትርፍ የማይንቀሳቀሰውና የራሱ የዊክፔዲያ እህት ኩባኒያ የሆነው “ዊክፔዲያ ፋውንደሽን” ከተቋቋመ በሗላ ነበር።

ውክፔዲያ ምንም እንኳ መጀመሪያ የተመሰረተው እንግሊዘኛ ቋንቋን መሰረት አድርጎ ቢሆንም እ.ኤ.አ ከግንቦት 2001 ዓ.ም. ጀምሮ ሌሎች አዳድስ ቋንቋዎችን በማካተት የበርካታ ቋንቋዎች መዳረሻ ለመሆን ችሏል። ከነዚህም መካከል ካታልኛ፣ ቻይንኛ፣ ጀርመንኛ፣ ሞስኮብኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ ዕብራይስጥ፣ ጣሊያንኛ፣ ጃፓንኛ፣ ፖርቹጋልኛና ስፓንሽኛ በግንባር ቀደምትነት ዊክፔድያን የተቀላቀሉ ቋንቋዎች ሲሆኑ፣ አረብኛ፣ ሀንጋሪኛ፣ ፖሎንኛና ሆላንድኛ ከላይ የተጠቀሱትን ቋንቋዎች በቅርብ እርቀት ተከትለው የተቀላቀሉ ሌሎች ቋንቋዎች ናቸው። በሌላ በኩል በጥር 2012 እ.ኤ.አ. በተደረገ ጥናት ዊክፔድያ ከ31 ሚሊዎን በላይ በሚሆኑ የተመዘገቡ የዊኪፒዲያ አስተዋፆ አድራጎዎችና በመላው አለም በሚገኙ ሌሎች ስፍር ቁጥር የሌላቸው ያልተመዘገቡ (የማይታወቁ) አስተዋፆ አድራጎዎች በ283 ቋንቋዎች ከ20 ሚሊዎን በላይ የሚሆኑና ማንምሰው በነፃ ሊገልባቸው የሚችሉ መጣጥፎችን አካቶ መያዙ ተረጋግጧል። በተጨማሪም ከጠቅላላው የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ውስጥ 14.5% ዊክፔዲያን እንደሚጎበኙ ተረጋግጧል።

ውክፔድያ ንብረትነቱ ዊክሜዲያ ፋውንደሽን የሚባል ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት የተመዘገበ ህጋዊ የንግድ ምልክት ነው።

ማንኛውም የኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚና ፈቃደኛ የሆነ ሰው ከአንዳንድ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ገደብ ከተጣለባቸው ገጾች በስተቀር ውክፔዲያ ላይ ስለተለያዩ ጉዳዮች (በህዎት ያሉ ሰዎችን ስም የሚያጠፉና ሌሎች የተከለከሉ ይዘት ያላቸውን ጽሁፎች ሳይጨምር) የፈለገውን ጽሁፍ የማስፈር አሊያም ስህተት የሆነን ጽሑፍ የማረምና የማስተካከል ፈቃድ ተሰጥቶታል። ይህም ያልተገደበ ፈቃድ ዊክፔዲያ በርካታ መጣጥፎችን እንዲኖሩት ያስቻለው ሲሆን፣ ከቀላል የድረ-ገጹ ተጠቃሚዎች (አንባቢዎች) ጨምሮ እስከ 91000 የሚደርሱ የተለያዩ የሙያ ባለቤት የሆኑ ግለሰቦችና በቋሚነት ዊክፔዲያን አርትኦት የሚያደርጉ ፈቃደኛ አስተዋፆ አድራጊዎችን አሉት። በመሆኑም ምንም እንኳን የድረገፁ ባለቤት ዊክፔዲያ ፋውንደሽን ቢሆንም ብዙውን ጊዜ በድረ-ገፁ ላይ በሚዎጡ የፅሁውፍ ስራዎችና የድረ-ገፁን የቀን ተቀን እንቅስቃሴዎችን በመቆጣጠሩ ረገድ የላቀ ተሳትፎ አይታይበትም።

በተጨማሪም ይህንንም የበለጠ ለማጎልበት ይረዳ ዘንድ፣ የተለያዩ የዊክፔዲያ ተጠቃሚዎችና አባሎች ግለሰባዊ ማንነታቸው/ሙያቸው/ እንደተጠበቀ ሆኖ የተሻሻለና ጥራት ያላቸው ስራ ማበርከት ይችሉ ዘንድ የተለያዩ መፍትሔዎች ተነድፈው ተግባራዊ ሆነዋል። ከነዚህም መካከል አርታኢዎች የተላያዩ ገፆችን ማስተካከልና መፍጠር የሚችሉ ሲሆን ፕሮገራመሮች ደግሞ የአርትኦት ችግር ያለባቸውን ገፆች በቀላሉ ለመከታተል የሚያስችሉ ፐፕሮገራሞችን በየጊዜው ያዘጋጃሉ። በተጨማሪም በመረጃዎች አቀራረብ ዙሪያ አንዳንድ አለመግባባቶች በአርታኢዎች መካከል ሲፈጠሩ፣ አርታኢዎች በጋራ በመሰባስብና በመወያየት ተጨባጭና የተሻለ የነገሩን/ሀሳቡን እውነታ ይወክላል የሚሉትን በመርጥ እንዲያፀድቁ የሚደረግበት አሰራርም አለ።

በተለያዩ የዊክፔዲያ ገፆች ላይ የሚገኙ ጽሑፎች የበርካታ አስተዋፆ አድራጊ ሰዎች የጋራ የትብብር ውጤቶች ናቸው። በመሆኑም ማንኛውም ለውክፔዲያ ገፅ አስተዋፆ ያደረገ ግለሰብ ፣ ገፁን በመፍጠር ሂደት ውስጥ አስተዋፆ ያበረከቱ ግለሰቦች በሚመዘገቡበት የገፁ ታሪክ መዝገብ ውስጥ የሚካተትና ያደረገው አስተዋፆም የሚመዘገብ ሲሆን ይህም ለማንኛውም ሰው በግልፅ እንዲታይ ተደርጎ ከገፁ ጋር ተያያዥ ሆኖ የሚቀርብ ነው። ምስሎችንና ሌሎች ሜዲያዎችን በተመለከተ የተመዘገበን የአስተዋፆ አድራጊነት፣ የባለቤትነት ድርሻን ወይም ደግሞ ሌሎች የመረጃ ምንጮችን በተመለከተ መረጃን ለማዎቅ ካስፈለገ፣ የተፈለገው ምስል ላይ በኮምፒውተራችን ማውስ ጠቅ በማድረግ ወይም ደግሞ በአቅራቢያው የሚገኝን የመረጃ መስጫ ምልክት (icon) በመጫን መመልከት (ማግኘት) ይቻላል።

ውክፔዲያን በቀን ከሚጎበኙ የድረ-ገጹ ተጠቃሚዎች መካከል ብዙዎቹ በድረ-ገጹ ላይ ሌሎች እንዲጎበኙ ያስቀመጡዋቸውን (ያጋሩዋቸውን) መረጃዎች ለማገኘት ሲሆን ሌሎች በርካቶች ደግሞ ያላቸውን መረጃ/እውቀት በዚሁ ድረ-ገጽ በመታገዝ ለሌሎች ተጠቃሚዎች ለማጋራት ነው። በዚሁ ተመሳሳይ ቅፅበት ደግሞ ሌሎች በርካታ መጣጥፎች ማሻሻያ ሲደረግባቸው፣ ሌሎች ስለ በርካታ ጉዳዮች የሚዳስሱ መጣጥፎች ደግሞ እንደ አድስ እየተጻፉ ውክፔዲያን ይቀላቀላሉ። በመሆኑም እስካሁን ውክፔዲያን ከተቀላለቀሉ መጣጥፎችም መካከል ከ3000 በላይ የሚሆኑ መጣጥፎች በዊክፔዲያ ማህበረሰብ “የምንጊዜም ምርጥ መጣጥፎች” በሚል የተመረጡ ሲሆን ከ13000 በላይ የሚሆኑት ደግሞ «የተሻሉ መጣጥፎች» በሚል የተመረጡ ናቸው። በተጨማሪም ውክፔዲያ ላይ የሚገኙ መረጃዎች በተለያዩ የመረጃ የደረጃ ክፍልፍሎሽ (ዝርዝሮች) ስር እየተጠናቀሩ የሚቀርቡ ሲሆን ከነዚህም መካከል የተሻለ የመረጃ የክፍፍሎሽ ይዘት ያላቸው መጣጥፎች “የምንጊዜም ምርጥ ዝርዝር” በሚል ጠመርጠዋል። በሌላ በኩል ውክፔዲያ የተለያዩ አርዕስቶች/ጉዳዮችን በተመሳሳይ ቦታ ለማጋራት የሚያስችል አስራርን የሚከተል በመሆኑ ተመሳሳይ ሃሳቦችን በተመሳሳይ አርዕስቶች ዙሪያ በማደራጀትና የተለያየ ይዘት ያላቸውን መረጃዎችን በተመሳሳይ መዳረሻ በማቅረብ ረገድ ውክፔዲያ “የምንግዜም ምርጥ መዳረሻ” በሚል የተመረጠ ድረ-ገጽ ነው።

በተለያዩ መጣጠፎች ላይ የተደረጉ የመረጃ ማሻሻያዎችን በሁለት መንገድ መከታተል ይቻላል። በተለያዩ ገፆች በቅርብ ጊዜ የተደረጉ ማሻሻያዎችን ለመመልከት በዋናው ገፅ የሚገኘውና «በቅርብ ጊዜ የተለወጡ» የሚል ርዕስ ያለውን ጽሁፍ በመጫን መመልከት ይቻላል። ማንኛውንም ለውጥ ለመመልከት ከተፈለገ ደግሞ በዋናው ገፅ የሚገኘውን “ማንኛውንም ለማየት” የሚል ርዕስ ያለውን ጽሁፍ በመመጫን መመልከት ይቻላል።

በሌላ በኩል ውክፔዲያ ከእንግሊዘኛ ቋንቋ በተጨማሪ አማርኛን ጨምሮ በሌሎች ቋንቋዎችም አገልግሎት ከመስጠቱ ባሻገር፣ የተሻሻለና ቀላል የእንግሊዝኛ ቋንቋን ጨምሮ ሌሎች ተመሳሳይ ይዘት ያላቸውን ፕሮጀክቶች ማለትም፤ መዝገበ-ቃላት፣ ጥቅሶች፣ መጸሐፍት፣ መመሪያዎች፣ ሳይንሳዊ የመረጃ ምንጮችና የዜና አገልገሎትና ሌሎች መሰል አገልገሎቶችን ከሁለት መቶ በላይ በሚሆኑ ቋንቋዎች ያቀርባል። እነዚህም የተለያዩ አግልግሎቶች፣ ከውክፔዲያ ማህበረሰብ በተጨማሪ በተናጥል በሚገኙ ሌሎች ማህበረሰቦች ክትትል፣ ቁጥጥርና ማሻሻያዎች የሚደረጉባቸው ሲሆኑ አብዛሀኛዎቹ መጣጥፎችም በሌሎች የመረጃ መጋሪያ ድረ-ገጾች በቀላሉ የማይገኙ ናቸው።

የሚከተሉት ዋና የኢትዮጵያ ቋንቋዎች  የውክፔድያ ድረ-ገጽና መርሀገብር ለተናጋሪዎቻቸው አላቸው። 

የአፋርኛ ውክፔድያ የተዘጋበት ምክንያት የአፋርኛ ዕውቀት ያላቸው ሰዎች ጉድለት በኢንተርኔት ላይ ስላለ ነው። (ደግሞ ኢንተርኔት በኢትዮጵያ ይዩ።) ዳሩ ግን ጊዜያዊ የአፋርኛ ማዘጋጀት ቦታ በ ተደርጓል። ሌሎች የዓለም ልሳናት «ጊዜያዊ» ውክፔድያዎች ወዘተ. በዚህ ይዘረዘራሉ፦ ።   መዝገበ ዕውቀት ለመጽሐፍ የሚችሉ ለቋንቋውም ቅልጥፍና ያላቸው አዛጋጆች በኖሩበት ጊዜ፣ እነዚህ «ጊዜያዊ» መርሃግብሮች ደግሞ የገዛ ድረ-ገጾቻቸውን ሊያገኙ ይችላሉ። ከዚህ በቀር በማንኛውም ሌላ ቋንቋ «ጊዜያዊ» ውክፔድያ በጥያቄ መጀምር ቀላል ነው።

ሁሉም በውኪፔዲያ የሚገኙ መጣጥፎች እርዕስ በርሳቸው እንዲገናኙ ተደርገዋል። ማንኛውም የተሰመረና ሰማያዊ ቀለም ያለው ጽሁፍ ስለተሰመረው አርዕስት የተሻለና የተብራራ መረጃ ሊሰጥ ከሚችል ሌላ ገፅ ጋር እንደተሳሰረ የሚያመለክት ሲሆን የኮምፒውተራችን ማውስ በዚህ በተሰመረና ሰማያዊ ቀለም ባለው ማንኛውም ጽሁፍ ላይ በመጠቆም የተቀመጠው ትስስር ከየትኛው ገፅ ጋር እንደሆነ መመልከት ይቻላል። 

አንባቢው እንደዚህ አይነት ትስስር ያላቸውን ሀሳቦች ለበለጠ ለመረዳት ከፈለግ በማንኛውም በተሰመረና ሰማያዊ ቀለም ባላው አርዕስት ላይ ክሊክ በማድረግ ተጨማሪ ማብራሪያ ማግኝት ይችላል። ከዚህ አይነት የገጽ-ለገጽ ትስስሮሽ በተጨማሪ አንባቢን ከሌሎች ከተለያዩ ጉዳዮች ጋር እንዲያገናኙ ሆነው የተፈጠሩ ሌሎች ትስስሮች ይኖራሉ። ለምሳሌ ያክል ከቀረበው መጣጥፍ ላይ ወደሚገኘው የመጨረሻ ገጽ የሚዎስዱ፣ ከሌሎች ውጭያዊ ጠቃሚ ድረገፆች ጋር የሚያገናኙ፣ ወደ ማጣቀሻ ምንጮች የሚወስዱና በተለያዩ ደረጃዎች/አርዕስቶች በተዋቀረ ገፅ ላይ በቀላሉ ከአንድ አርዕስት ወደ ሌላ አርዕስት ለመንቀሳቀስ የሚያገዙ ትስስሮች ይገኙበታል።ከዚህ በተጨማሪም አንዳንድ መጣጥፎች እንደ መዝገበቃላት መፍቻዎች፣ የድምፅ የመፀሐፍ ንባብ፣ ጥቅሶችን፣ የቀረበው መጣጥፍ በሌላ ቋንቋ ወደ ተጻፈ የመጣጥፉ ግልባጭ (ኮፒ) የሚወስዱና ከሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችን ከያዙ እህት ፕሮጀክቶች ጋር የሚያሰተሳስሩ ይገኙበታል።

እንደ ዊኪ (ፈጣን) የመረጃ ፍይልነታቻው በውኪፔዲያ ውስጥ የሚገኙ መጣጥፎች በሁሉም ረገድ የተሟሉ ናቸው ብሎ ለመገመት ያዳግታል። ከዚህ ይልቅ የዊኪፔዲያ የተለያዩ መጣጥፎች፣ በተከታታይ አርትኦትና ማሻሻያዎች እየተደረገባቸው ስለሚሄዱ ከቀን ወደ ቀን ይበልጥ የተሻሻለንና ትክክለኛ የሆነ መረጃን እየያዙ እንደሚመጡ ይታመናል። ስለሆነም ማንኛው የውኪፔዲያ ተጠቃሚ፤ ሁሉም መጣጥፎች ከመነሻቸው አንድ ኢንሳክሎፔዲያ ሊያሟላው የሚገባውን የጥራት ደረጃ ሊያሟሉ እንደማይችሉና ምናልባትም የተሳሳተ ይዘት ያላቸው ወይም አከራካሪ የሆኑ መረጃዎችን ሊይዙ እንደሚችሉ መገንዘብ ይኖርበታል። በርገጥም ብዙ መጣጥፎች ከመነሻቸው አጭርና የአንድዮሽ ምልከታን ብቻ በመያዝ የሚጀመሩ ሲሆን ቀስ በቀስ ግን የተለያዩ ምልከታዎችንና መረጃዎችን በማካተት ሁሉንም ሊያስማማ በሚችል ደረጃ ሙሉና ሁለገብ እየሆኑ የሚሄዱ ናቸው።  

ለዚህም እንደምከንያትነት የሚጠቀሰው፣ በርካታ የመጣጥፍ አርታኢዎችና አዘጋጆች፣ የሚያቀርቡትን መጣጥፍ ሁለገብ ይዘት እንዲኖረው ከማድረግ ይልቅ ብዙውን ጊዜ የሚያጠነጥኑት በራሳቸው የግል ፍላጎትና የአንድዮሽ ምልከታ ላይ ብቻ በመሆኑ እንደዚህ አይነት የይዘት ችግር ያለባቸውን መጣጥፎች እንደገና ላማሻሻልና ሚዛናዊ መረጃን እንዲይዙ ለማድረግ ረዘም ያለ ጊዜ የሚጠይቁ ሲሆን ምናልባትም እስከ አንድ ወር ጊዜ ድረስ የሚያስፈልጋቸው ይኖራሉ። በሌላ በኩል ደግሞ የዚህ አይነት ችግር ያላባቸውን መጣጥፎች ለማሻሻል በሚደረገው ጥረት የተለያዩ አርታኢዎች የየራሳቸውን ድርሻ ስለሚያበረክቱ መጣጥፎቹን ሁለገብ እና ሚዛናዊ ለማድረግ የሚድረገውን ጥረት በቀላሉ ለማሳካት ክፍተኛ አስተዋፆ አላቸው። በተለይም ደግሞ በተለያዩ የመጣጥፍ አርታኢዎች መካከል የሚፈጠርን አልመገባባት በቀለላሉ ለመምፈታት የሚያሰችሉ የውክፔዲያ የራሱ የሆኑ ብዛት ያላቸው ውስጣዊ የድርጅት አሰራሮች ያሉት በመሆኑ በዝህ ረገድ ያሉ አላስፈላጊ ችግሮችን በቀላሉ ማስወገድ ይቻላል። 

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ቢያንስ በመርህ ደረጃ አንድ የዊክፔዲያ መጣጥፍ ሊያሟላ ከሚገባቸው መሰረታሢ ነጥቦች መካከል፣ የሚከተሉትን መጥቀስ ይቻላል። በጥራት የተጻፈ፣ ሚዛናዊ የሆነ መረጃን የያዘ መሆን፣ ከዎገናዊነት የፀዳና መዝገባዊ ይዘት ያለው ሲሆን በተጨማሪም፣ የተሟላ፣ ሊጠቀስና ሊረጋገጥ የሚችል መረጃን የያዘ የሚሉት ይገኙበታል። በዚህም ረገድ ይህንን ስታንዳርድ ያሟሉና ከጊዜ ወደ ጊዜ በሟሟላት ላይ የሚገኙ በርካታ መጣጥፎች ያሉ ሲሆን እነዚህንም የተለያዩ የመጣጥፍ ደረጃ መለኪያ ስታንዳርዶችን አሟልተው የተገኙ በረካታ መጣጥፎች “የምንግዜም ምርጥ መጣጥፎች” በሚል ስያሜ ይታወቃሉ። ይህንንም ለማመልከት መጣጥፉ በሚገኝበት ገጽ የላይኛው የቀኝ ጥግ ላይ ትንሽ የኮኮብ ምልክት እንዲቀመጥ ይደረጋል። ነግርግን ሌሎች በረካታ መጣጥፎች፣ የተሟላ የመረጃ ማጣቀሻ ያላስቀመጡ፣ በበቂ ሁኔታ ያልተብራሩ አሊያም በፊት ከነበራቸው የተሻለ ይዘት በተጨማሪ ሌሎች ገና ያልተብራሩ አዳድስ ክፍሎችን ያካተቱ ስለሚሆኑ ይህንን “የምንግዜም ምርጥ መጣጥፎች “ የሚል ደረጃ ለማግኘት ከአንድ ወር እስከ አንድ አመት ጊዜን የሚጠይቅ የማሻሻል ስራና ያላሰለሰ ጥረትን የሚጠይቁ ናቸው።

ስለሆነም ምንም እንኳን ውክፔዲያ በብዙ ረገድ እየተሻሻለ የመጣ ቢሆንም የተለያዩ መጣጥፎች የተለያየ የሀሳብ ጥልቀትና ጥራት ሊኖራቸው ስለሚችል ዊክፔዲያን እንደ አንድ የምርምር ማጣቀሻነት ከመጠቀም ጎን ለጎን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ይመከራል። በዚህ ረገድ መረጃ በመስጠት ተጠቃሚን የሚያግዙ ገፆች የተዘጋጁ ሲሆን፣ ከነዚህም መካክል የማመላከቻና የመረጃ ገጽንና ስለ ውክፔዲያ አስተማማኝ የመረጃ ምንጭነት የተደረጉ የሶስተኛ ወገን ጥናቶችን መመልከት ይቻላል።

ውክፔዲያ ቀደም ሲል በስፋት ይውሉ ከነበሩ የህትመት ኢንሳይክሎፕዲያዎች ጋር ሲነፃጸር ከፈተኛና የራሱ የሆነ ጠቀሜታ አለው። በመጀመሪያ ደረጃም አነስተኛ የህትመትና የማስፋፋት ወጭና የሚጠይቅ መሆኑና ዝቀተኛ የሆነ የጎንዮሽ አካባቢያዊ ተፅኖች ያሉት መሀኑን ማንሳት ይቻላል። በሌላ በኩል ምንም አይነት የህትመት ስራ የማይፈለግ በመሆኑ ኮምፒውተሮች የራሳቸው የሆነ አካባቢያዊ ተጽኖ ይኖራቸዋል። 

በተጨማሪም ሁሉንም አይነት መግለጫዎችን በአንድ ገጽ አካቶ ከመያዝ ይልቅ እርስበርስ የሚዛመዱና በሌሎች የተለያዩ ገጾች የተብራሩ ጉዳዮችን ከአጫጭር ማጠቃለያዎች ጋር አጣምሮ በማቀረብ በቀላሉ መረጃን ለማግኘት ይረዳል። በመጨረሻም እንዴ ሌሎች የህትመት ኢንሳይክሎፕዲያዎች የተወሰነ የአርትኦትና የማሻሻያ ጊዜን የማይጠይቅ በመሆኑ፣ ውክፔዲያ ከሌሎች የህትመት ኢንሳይክሎፕዲያዎች ጋር ሲነጻጸር አጭር የአርትኦት ጊዜን የሚጠይቅና በማንኛውም ጊዜና ሰአት መሻሻሎችን በማደረግ መጣጠፎች ወቅታዊና ጊዜውን የተበቀ መረጃን ይዘው እንዲቀጥሉ የሚያስችል ዘመናዊ አሰራርን ይፈቅዳል።




#Article 22: የካናዳ ጥንታዊ ኗሪዎች (126 words)


የካናዳ ጥንታዊ ኗሪዎች በካናዳ አገር 1974 ዓ.ም. ሕገ መንግስት ሥር ኢንዲያን (መጀመሪያ አገሮች የተባሉ)፤ ሜቲ (ክልሶች)፤ እና እኑዊት (ወይም ኤስኪሞ) ናቸው።  እነዚህ 3 ክፍሎች አንድ ላይ ደግሞ መጀመርያ ሕዝቦች ይባላሉ። በካናዳ በተደረገው 1993 ቆጠራ ዘንድ፣ የጥንታዊ ኗሪዎች ብዛት ከ900,000 በለጠ።  በዚህ ቁጥር ውስጥ 600,000 ከመጀመርያ አገሮች ዘር፤ 290,000 ሜቲ፣ እና 45,000 እኑዊት ይከተታሉ።

የጥንታዊ ኗሪዎች ማህበራዊ ወኪሎች በካናዳ እንዲህ ናቸው፤ የመጀመርያ አገሮች ስብሰባ ለመጀመርያ አገሮች፤ እኑዊት ታፒሪት ካናታሚ ለእኑዊት፤ የሜቲ ብሔራዊ ጉባኤ ለሜቲ ናቸው።

ባለፈው ዐሥር አመት የካናዳ መንግሥት የዘውድ ጉባኤ ስለ ጥንታዊ ኗሪዎች (Royal Commission on Aboriginal Peoples) ሰበሰበ። ይህ ጉባኤ ያለፉትን መንግስት ዐቅዶች ስለ ጥንታዊ ኗሪዎች ለምሳሌ የሚሲዮን ተማሪ ቤቶች አመዛዝኖ ብዙ የአቅዋም ምክሮች ለካናዳ መንግስት አቀረበ።

ብዙ መጀመርያ አገሮች የሚኖሩት በተከለለ ቦታ ሲሆን፣ ብዙ ኗሪዎች ደግሞ ከቦታዎቹ ውጭ ይገኛሉ።  የአገሮቹ ስሞች እንደሚከተለው ናቸው፦




#Article 23: አንጎላ (624 words)


አንጎላ፣ በይፋ የአንጎላ ሪፑብሊክ (ፖርቱጊዝ: República de Angola ፣ ኪኮንጎ: Repubilika ya Ngola) በደቡብ-ምዕራብ አፍሪካ የምትገኝ ሀገር ስትሆን ከናሚቢያ ፣ ከኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ ፣ እና ከዛምቢያ ጋር ድንበር ትጋራላች። በምዕራብ ጫፍ ከአትላንቲክ ውቅያኖስ ጋር ትገናኛለች። የፖርቹጋል ቅኝ-ተገዥ ነበረች። ነዳጅ እና አልማዝ ከተፈጥሮ ሀብቶቿ የሚመደቡ ናቸው። የአንጎላ የሕግ-አስፈጻሚ ፕሬዝዳንቱን ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩን እና የሚኒስትሮች ካውንስሉን ያጠቃልላል። ሁሉም ሚኒስትሮችና ምክትል ሚኒስትሮች የሚኒስተሮች ካውንስሉን ሲሰሩ በየጊዜው እየተሰበሰቡ ስለተለያዩ የፖለቲካ ጉዳዮች ውሳኔ ይሰጣሉ። የአስራ ስምንቱ ክልሎች መሪዎች በፕሬዝዳንቱ ነው የሚመረጡት። በ1992 እ.ኤ.ኣ. የወጣ ሕገ-መንግስት የመንግስቱን አወቃቀር እና የዜጎችን መብትና ግዴታ ይዘረዝራል። ፕሬዝዳንቱ መንግሥቱ በ2006 እ.ኤ.ኣ. ምርጫ ለማድረግ ዕቅድ እነዳለው ገልጸዋል። ይህ ምርጫ ከ1992 አ.ኤ.ኣ. በኋላ የመጀመሪያው ምርጫ ነው የሚሆነው። አንጎላ ውስጥ ሶስት ዋና ብሔረሰቦች ይገኛሉ። ኦቪምቡንዱ 37% ፣ ኪምቡንዱ 25% ፣ እና ባኮንጎ 13%። ሌሎች ብሔረሰቦች ቾክዌ (ሉንዳ)፣ ጋንጉዌላ፣ ንሀኔካ-ሁምቤ፣ አምቦ፣ ሄሬሮ፣ እና ዢንዱንጋን ያጠቃልላሉ። በተጨማሪም ክልሶች (አውሮፓና አፍሪካዊ) 2% ይሆናሉ። ፖርቱጋሎች አንጎላዊ ካልሆኑ ሰዎች ብዙዎቹ ናቸው።

በአንጎላ መጀመሪያ የሠፈሩት የኮይሳን ሰዎች ነበሩ። በባንቱ ፍልሰቶች ጊዜ እነዚህ ሰዎች ወደ ደቡብ አንጎላ ሄዱ። በ1483 እ.ኤ.አ. ፖርቱጋሎች በኮንጎ ወንዝ አጠገብ ሠፈሩ። በ1575 እ.ኤ.አ. ፖርቱጋል ካቢንዳ ጋር በባሪያ ንግድ ላይ ያቶከረ ግዛት መሠረተች። በ16ኛው ክፍለ ዘመን፣ ፖርቱጋል የአንጎላ የባህር ጠረፍን ተቆጣጠረች። በተለያዩ ውሎችና ጦርነቶች የፖርቱጋል ቅኝ-ግዛት አንጎላ ተስፋፋ። የፖርቱጋል መመለሻ ጦርነትን ምክኒያት በማድረግ የደች ሪፐብሊክ ሏንዳን ከ1641 እስከ 1648 እ.ኤ.ኣ. ድረስ ተቆጣጠረች።

በ1648 እ.ኤ.ኣ. ፓርቱጋል ሏንዳን እንደገና ተቆጣጠረች። በ1650 እ.ኤ.አ. ደግሞ የተነጠቀችውን መሬት እንዳለ አስመለስች። በ1671 እ.ኤ.አ. ፑንጎ አንዶንጎ የሚባለው ቦታ ወደ ፖርቱጋል ቅኝ ግዛት ተጨመረ። ፖርቱጋል በ1670 እ.ኤ.አ. ኮንጎን እና በ1681 እ.ኤ.አ. ማታምባን ለመውረር ያደረገችው ሙከራ አልተሳካም። በ1885 እ.ኤ.አ. የበርሊን ጉባኤ የፖርቱጋል ቅኝ-ግዛት ድንበርን ከወሰነ በኋላ፣ በብሪታኒያ እና ፖርቱጋል ጥረት በኩል የባቡር-መንገድ፣ እርሻና ማዕድን ተሻሻሉ። እስከ ፳ኛው ክፍለ-ዘመን ድረስ አካባቢው ሙሉ በሙሉ በፖርቱጋል አልተመራም ነበር። በ1951 እ.ኤ.አ. ቅኝ ግዛቱ የባህር ማዶ ክፍለ-ሀገር ሆኖ ፖርቱጊዝ ምዕራብ አፍሪካ ተባለ። ፖርቱጋል አካባቢውን ወደ አምስት መቶ ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ ያህል ተቆጣጥራለች። ስለዚህም የአካባቢው ሕዝብ ነጻነት ለመውጣት ያለው ስሜት የተደበላለቀ ነበር።

አንጎላ ነጻነቷን በኅዳር ፲፱፻፷፰ ከተቀዳጀች በኋላ ግን ለብዙ አሥርተ ዓመታት የሚቀጥል የእርስ በርስ ጦርነት ገጠማት። ይህ ውጊያ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ለሞትና ስደት አብቅቷል። ከአልቮር ስምምነት በኋላ ሶስቱ ትልቅ የትግል ግንባሮች የሽግግር መንግሥትን ለማቋቋም በጃኑዋሪ 1975 እ.ኤ.አ. ተስማሙ። ነገር ግን በሁለት ወራት ውስጥ እነዚህ ግንባሮች ወደ ውጊያ ተመልሰው አገሯ ወደ ክፍፍል እያመራች ነበር። በዚህ ወቅት የቀዝቃዛው ጦርነት ኃያል አገራት የነበሩት የሶቭየት ሕብረትና አሜሪካ አንዱን ወይም ሌላውን ወገን ደግፈው ወደ ጦርነቱ ገብተዋል። ሌሎችም እንደ ፖርቱጋል፣ ብራዚል፣ ደቡብ አፍሪካና ኩባ የመሳሰሉት ሀገራትም ከማገዝ ወደ ኋላ አላሉም።

የአንጎላ የሕግ አስፈፃሚ አካል ፕሬዝዳንቱን፣ ምክትል ፕሬዝዳንቱንና የሚኒስትሮች ምክር ቤቱን ያጠቃልላል። ለብዙ ዓመታት አብዛኛው ሥልጣን በፕሬዝዳንቱ እጅ ነው ያተኮረው። የ፲፰ቱ ክልሎች አስተዳዳሪዎች በፕሬዝዳንቱ ነው የሚሾሙት።

የ1992 እ.ኤ.አ. ሕገ መንግሥት የመንግሥቱን አወቃቀርና የዜጎችን መብቶችና ግዴታዎች ይዘረዝራል። የሀገሩ ሕግ ተርጓሚ አካል የፖርቱጋል ሥርዓትን ይከተላል።

የአንጎላ ጦር ኃይሎች በመከላከያ ሚኒስቴር ስር ሲሆኑ በሦስት ይከፈላሉ። እነዚህም ምድር ኃይል፣ ባህር ኃይል እና አየር ኃይል ናቸው። የሀገሩ ጠቅላላ ሠራዊት ፻፲ ሺህ ይሆናል። የጦር ኃይሉ ንብረቶች መካከል በሩሲያ የተሰሩ ተዋጊ፣ ቦምብ ጣይና አጓጓዥ አውሮፕላኖች ይገኛሉ። አንዳንድ የጦር ኃይሉ ክፍሎች በኮንጎ ኪንሻሳና ኮንጎ ብራዛቪል ተመድበዋል።

አንጎላ፣ በ1,246,620 ካሬ ኪ.ሜ. ከኒጄር ቀጥላ ከዓለም 23ኛው ትልቅ አገር ናት። በስፋት ከማሊ ጋር ትነጻጸራለች። የአሜሪካ የቴክሳስ ክፍላገርን ሁለት ዕጥፍ ታክላለች። አንጎላ ከደቡብ በናሚቢያ፣ ከምሥራቅ በዛምቢያ፣ ከሰሜን-ምሥራቅ በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና ከምዕራብ በአትላንቲክ ውቅያኖስ ትዋሰናለች።

የአንጎላ አማካይ የባህድ ዳር የአየር ሁኔታ በክረምት 16° ሴንቲግሬድና በበጋ 21° ሴንቲግሬድ ነው። አንጎላ ሁለት ወቅቶች አሏት። እነዚህም ደረቅና ዝናባማ ናቸው።

የአንጎላ መጓጓዣዎች የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ፦

አንጎላ የሰፋ የመጓጓዛ አውታር ቢኖራትም በጊዜ ማለፍና ጦርነት ምክንያት መንገዶች አስፈላጊ ጥገኛ አልተደረገባቸውም። በአንዳንድ ቦታዎች አሽከርካሪዎች መጥፎ ቦታዎችን ለማለፍ ሲሉ ከመንገድ ውጭ ይነዳሉ። እንደዚህ ከማድረግ በፊት ግን በመንገድ ዳር ያሉ በመሬት ውስጥ ስለተቀበሩ ፈንጂዎች የሚያስጠነቅቁ ምልክቶችን ማስተዋል ያስፈልጋል።

የአንጎላ ኢኮኖሚ ትልቅ ለውጥ አሳይቷል። የሩብ ምእተ ዓመት ጦርነት ያሳደረበት ተጽእኖን አልፎ ዛሬ በዓለም ውስጥ በፍጥነት በማደግ ላይ ካሉት ኢኮኖሚዎች ይመደባል። በ2004 እ.ኤ.አ. የቻይና ኤክሲምባንክ ፪ ቢሊዮን ብር ለአንጎላ አበድሯል። ይህ ገንዘብ እንደ መንገዶች ያሉትን የአንጎላ መሠረታዊ ተቋሞች ለማሻሻል የሚውል ነው።

ዘ ኢኮኖሚስት መጽሄት በ2008 እ.ኤ.አ. እንደዘገበው ነዳጅና ዕንቁ የአንጎላ ዋና ኤክስፖርቶችና የገቢ ምንጮች ናቸው።




#Article 24: ላሊበላ (263 words)


ላሊበላ በኢትዮጵያ፣ በአማራ ክልል በቀድሞው የወሎ ክፍለ ሃገር የምትገኝ ከተማ ነች። በ ላይ የምትገኘው የላሊበላ ከተማ ከባህር ጠለል በላይ 2,500 ሜትር ከፍታ ያላት ስትሆን የህዝቡም ብዛት ወደ 11,152 ነው። 1 ላሊበላ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ቅዱሳን ከተማዎች መካከል ከአክሱም ቀጥላ በሁለተኛነት ደረጃ የምትገኝ ከተማ ስትሆን፣ ለአብዛኞቹ የክርስትና እምነት ተከታዮች እንደ ዋና የእምነት ማእከል በመሆን ታገለግላለች። የላሊበላ ነዋሪዎች በአብዛኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ናቸው።

የላሊበላን ከተማ በዋነኛነት ታዋቂ ያረጉዋት ከክ.ል. በኋላ በ13ኛው መቶ ክፍለዘመን እንደ ተሰሩ የሚነገርላቸው 11 አብያተ-ክርስቲያናት ናቸው። በኢትዮጵያ ትውፊት መሰረት እነዚህ አብያተ-ክርስቲያናት በንጉሥ ላሊበላ ዘመን በቅዱሳን መላዕክት እረዳትነት እንደተሰሩ የሚታመን ሲሆን ግርሃም ሃንኮክ የተባለው እንግሊዛዊ ፀሃፊ ግን እኤአ በ1993 ዓ.ም ባሳተመውና The Sign and the Seal በተባለው መጽሃፉ አብያተ-ክርስቲያናቱን በማነፁ ሥራ ላይ ቴምፕላርስ የሚባሉት የመስቀል ጦረኞች ተካፍለዋል ሲል አትቷል ነገር ግን ማረጋገጫ አልነበረውም።  እነዚሀ አብያተ-ክርስቲያናት ውስጥ አርባ ትንንሽ ቤተክርስቲያኖች አሉ። 

ንጉሡ ላሊበላ የሚለውን ስም ያገኘው፣ ሲወለድ በንቦች ስለተከበበ ነው ይባላል። ላል ማለት ማር ማለት ሲሆን፤ ላሊበላ ማለትም -ላል ይበላል (ማር ይበላል) ማለት አንደሆነ ይነግራል።  ውቅር ቤተክርስቲያናቱን ንጉሡ ጠርቦ የስራቸው ከመላእክት እገዛ ጋር እንደሆነ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ይነግራል። በ16ኛው ከፍለ ዘመን አውሮፓዊ ተጓዥ ላሊበላን ተመልክቶ «ያየሁትን ብናግር ማንም እንደኔ ካላየ በፍጹም አያምነኝም» ሲል ተናግሮ ነበር።

በላሊበላ 11 ውቅር ዐብያተ ክርስቲያናት ያሉ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ቤተ ጊዮርጊስ (ባለ መስቀል ቅርፁ) ሲታይ ውሃልኩን የጠበቀ ይመስላል። ቤተ መድሃኔ ዓለም የተባለው ደግሞ ከሁሉም ትልቁ ነው።
ላሊበላ (ዳግማዊ ኢየሩሳሌም) የገና በዓል ታህሳስ 29 በልዩ ሁኔታ ና ድምቀት ይከበራል፣ ቤዛ ኩሉ ተብሎ የሚጠራው በነግህ የሚደረገው ዝማሬ በዚሁ በዓል የሚታይ ልዩ ና ታላቅ ትዕይንት ነው።የሚደረገውም ከቅዳሴ በኋላ በቤተ ማርያም ሲሆን ከታች ባለ ነጭ ካባ ካህናት ከላይ ደግሞ ባለጥቁር ካብ ካህናት በቅዱስ ያሬድ ዜማ ቤዛ ኩሉ እያሉ ይዘምራሉ።




#Article 25: አክሱም (112 words)


አክሱም በሰሜን ኢትዮጵያ በትግራይ ክ/ሃገር ከአድዋ ተራራዎች አጠገብ የምትገኝ ከተማ ነች። በክርስቶስ ልደት በፊት ተመስርቶ የነበረው የአክሱም ስርወ መንግስት ማእከል ነበረች

የአክሱም ስርወ መንግስት በ12ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አካባቢ እየተዳከመ ሲመጣ የማእከላዊው መንግስት ወደ ደቡብ ተንቀሳቀሰ።
ሰባ አምስት በመቶ የሚሆነው የከተማው ነዋሪ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይ ነው። የተቀሩት ነዋሪዎች የሱኒ እስልምና ተከታዮች ናቸው። ባላቸው ታሪካዊ ተፈላጊነት ከተማ ውስጥ የሚገኙት የአክሱም ስርወ መንግስት ቅሪቶች UNESCO በ1980 የአለም ቅርስ ቦታ ተብለው ተሰይመዋል ። 

አክሱም በኢትዮጵያ የ ትግራይ ክልል ከተማ ሲሆን በማዕከላዊ ዞንና በላዕላይ ማይጨው ወረዳ ይገኛል። 
በ1998 ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን እንደተመነው የ47,320 ሰው መኖሪያ ሲሆን እነሱም 23,542 ወንዶችና 23,778 ሴቶች ይገኙበታል።

በሌላ ገለልተኛ ትምና ደግሞ የ41,197 ሰው መኖሪያ ተደርጎ ተገምቷል። የከተማው አቀማመጥ በ ላይ ነው።




#Article 26: መለስ ዜናዊ (656 words)


መለሰ ዜናዊ (የትውልድ ስማቸው ለገሠ ዜናዊ አስረስ) (ሚያዝያ ፴ ቀን ፲፱፻፵፯ ዓ/ም - ነሐሴ ፲፬ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም) የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሰው ነበሩ። በአድዋ ትግራይ የተወለዱ ሲሆን ከ፲፱፻፹፯ ዓ/ም አንስተው እስከ ዕለተ ሞታቸው ድረስ በኢትዮጵያ የጠቅላይ ሚኒስትር ሥልጣን በከፍተኛው የአመራር ቦታ ላይ ነበሩ። የኢህአዴግና የሕውሓት ሊቀመንበር በመሆን ኢህአዴግ ስልጣን ላይ ከወጣ ጀምሮ ቆይተዋል።  

አቶ መለስ ዜናዊ አባታቸው (አቶ ዜናዊ አስረስየትግራይ ተወላጅ  ሲሆኑ፣ በእናታቸው በኩል ደግሞ ኤርትራዊ  ናቸው።

መለስ በታወቀው ጀነራል ዊንጌት 2ኛ ደረጃ ተምህርት ቤት የተማሩና ከአጼ አህለስላሴ የኮከብ ተማሪዎች ሽልማት የተሸለሙ፣ ከዛም ወደ በረሃ ወርደው በታጋይነት ከመሰለፍቸው በፊት፤ የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ሜዲካል ፋክልቲ ተማሪ ነበሩ።  ትግርኛ፣አማርኛና፡ እንግሊዝኛ አቀላጥፈው መናገር ይችላሉ። 

መለስ ዜናዊ ስልጣን ላይ በነበሩባቸው ጊዜያት ለሀገራቸው ኢትዮጵያ ባደረጓቸው አስተዋፅኦዎች የኢትዮጵያ ባለውለታ ናቸው ይባላሉ፡፡ ኢትዮጵያም እንደ እርሳቸው ያለ መሪ አግኝታ እንደማታውቅ በሰፊው ይነገራል፡፡

አቶ መለስ የሚመሩት ሕውሓት የኮሎኔል መንግስቱ ኅይለ ማርያምን አምባገነናዊ መንግስት በትጥቅ ትግል ሲታገሉ ከነበሩ ድርጅቶች አንዱ ነበር። አቶ መለስ የሕወሓት አመራር ኮሚቴ መሪ ሆነው በ1971 ተመረጡ፤ ቀጥሎም በ1975 የድርጅቱ ማእከላዊ ኮሚቴ ሊቀመንበር ሆኑ። የደርግ መንግሥት ከወደቀም ጀምሮ የሕወሓትና  የኢህአዴግ ሊቀ-መንበርም ሆነው አገልግለዋል። ኢህአዴግ የአራቱ ፖለቲካ ፓርቲዎች ማለትም የኦሮሞ ህዝቦች ዲሞከራሲያዊ ድርጅት፣ የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ውህደት ነው። ወደ ስልጣን ሲመጡ በጊዜው ላቋቋሙት ጊዜያዊ መንግስት ፕረዚዳንት ሆነው ካገለገሉ በሗላ 1985 ለመጀመሪያ ጊዜ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው ተመረጡ። በጊዜው የፕረዚደንትነቱን ቦታ የተረከቡት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ናችው።

የአምባገነኑ የመንግስቱ ኃይለ ማርያም አስተዳደር እንደ ወደቀ አዲስ አበባን የተቆጣጠረው ኢአሓዴግ በሕዝብ ምርጫ ሳይሆን ብሔረሰቦችን መሰረት ባደረገ በጥቂት ግለሰቦች የሽግግር መንግሥቱ በመቋቋሙ አብዛኛውን ሕዝብና ምሁራንን በጣም አስቆጣ። 

በወቅቱ በአምባ ገነኑ ደርግ ስር ተጨቁኖ ለነበረው ድሃ ኢትዮጵያዊ የኢህአደግ ወደ ስልጣን መምጣት ሌላ አማራጭ ስላልነበር የኢሕአዴግን መንግስት ሕዝቡ ለመቀበል ስለ ተገደደ በጊዜው ኢህአዴግ ይህ ነው የተባለ ተቃውሞ አልገጠመውም። በአንጻሩ ከጅምሩ በትጥቅ ትግል ኢሕአዴግን ሲረዱ የነበሩ የአረብና የምዕራባውያን መንግስታት ከጎንህ አለን በማለት በሁለት እግሩ አንዲቆም አስችለውታል።

ይሁን እንጂ እያደር ሲመጣ የአቶ መለሰ ዚናዊ መንግስት የታገለለትን ዓላማ ስቶ ዲሞክራሲን በማፈን የነጻ ፕሬስ አፈና በማካሄድና የብአዊ መብት ረገጣ ስላበዛ ብዙ የምዕራባዊያን ድጋፍና ከማጣቱም በላይ የብዙ ሺ ኢትዮጵያዊያን ለስደት ዳርጎአል። ሆኖም ዓለም አቀፉን ሽብርተኛ ለመታገል በሚል ሽንገላ ሱማሌን በመውረሩ ምክንያት በጆርጅ ቡሽ የምትመራ አሜሪካ ቀንደኛና ዋነኛ የኢህአዴግ ደጋፊ ሆና ቀርታለች። ቀጣዩ የአሜሪካ መሪ ባራክ ኦባማም የአገራቸውን ጥቅም ለማስጠበቅ ካላቸው ፍላጎት አልቃይዳንና አልሸባብ የተባሉ የአክራሪ እስላም ቡድኖችን እየታገልኩ ነው ላለው ኢሕአዴግን ድጋፋቸውን ቀጥለዋል። 

ምንም እንኳ በደርግ የግፍ አገዛዝ የተማረረው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ኢህአዴግን ለመቀበልና አብሮ ለመስራት ወደ ኋላ ባይልም ውሎ ሲያድር ግን በኢህአዴግ የአገር ውስጥ ፖሊሲ መከፋቱ አልቀረም። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ብሎ ራሱን የስየመው ቡድን ከኢህአዴግ ጋር በመቃቃሩ ራሱን ከፓርላማውና ከካቢኔው አግልሎ ወደ ትጥቅ ትግሉ ተመለሰ።

ጠ.ሚ. መለስ የኤርትራን የመገንጠል ጥያቄ ያለምንም ማንገራገር መፍቀዳቸው ብቻ ሳይሆን ሁሉም ብሔረሰብ እንዲገነጠል የሚያስችለውን አንቀጽ በሕገ መንግስታቸው በማካተታቸው በተለይ በምሁራን ዘንድ የከረረ ተቃውሞ አስነስቶባቸዋል። ሁሉም በክልሉ በቋንቋው ይማር የተሰኘው ፖሊሲያቸውም በብዙዎች ዘንድ ጥርጣሬና መከፋፈልን በመፍጠሩ በሀገርና ከሀገር ውጭ በተደጋጋሚ የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂዶባቸዋል። 

በ1997 ዓ.ም. አጋማሽ ጠቅላላ ምርጫ ሲደረግ ከተለያዩ የፖለቲካ ህቡዕ ፓርቲዎች የተውጣጣ ቅንጅት የተሰኘ ጥምር የፖለቲካ ፓርቲ እንደ አንድ የፖለቲካ ድርጅት ተወዳደረ። በውጤቱም የዓለም ታዛቢዎች በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ ከመቶ 97 እጁ መራጭ የተቃዋሚውን ፓርቲ ቅንጅትን መረጠ። በውጤቱ የተደናገጠው የአቶ መለስ መንግስት ለመጀመሪያ ጊዜ የአዲስ አበባን ፖሊስ በፌዴራል ቁጥጥር ስር አዞረ። የአዲስ አበባ ምክር ቤትንም በኦሮሚያ መስተዳደር ስር እንዲተዳደር አዲስ ድንጋጌ አወጣ። 

ይሁን እንጂ ብዙም ገለልተኛ ታዛቢ በሌለበት ከአዲስ አበባ ውጪ ኢሕአዴግ 90 በመቶ ማሸነፉ ስለታወጀ ተቃዋሚዎች አድልዎ ተደርጎብናልና ምርጫው እንደገና ይጣራ ብለው ለከፍተኛ ፍርድ ቤት የክስ ማመልከቻ በማስገባታቸው ማጣሪያ ተካሄደ። ተቃዎሚዎች በጠቅላላው የምርጫ ውጤት ባለመስማማታቸው ያሸነፉበትን የፓርላማ ወንበር ባለመቀበል የገዢው ፓርቲ በበላይነት ከተቆጣጠረው ፓርላማ ራሳቸውን አገለሉ። 

ሚሥስ አና ጎሜዝ የተባሉ የአውሮፓ ታዛቢ ቡድን መሪ ምርጫው አድልዎና ጫና እንደነበረበት ለዓለም ሕዝብ ምስክርነታቸውን ተናገሩ። አብዛኛዎቹ ታዛቢዎች (አፍሪካ ሕብረት አና የጂሚ ካርተርማእከል) ምርጫው በኢትዮጲያ ከተካሄዱ ምርጫዎች በጣም የተሻለ መሆኑን መሰከሩ። በሺ የሚቆጠሩ የቅንጅት ደጋፊዎች በዋና ዋና ከተማዎች በመውጣት ሰላማዊ ሰልፍ በቁጣ በሚገልጹበት ጊዜ ቁጥሩ በርካታ የሆነ ሕዝብ በፖሊስ በቀጥታ በተተኮሰ ጥይት ሕይወቱን አጥቶአል። የአቶ መለስ መንግስት አብዛኛዎችን በህዝብ የተመረጡ የቅንጅት ፓርቲ አባላትንና በሺህ የሚቆጠሩ አባላትን ባገር ክህደት አና መንግስትን ለመገልበጥ በመሞከር ከሰሳቸው። ሁለት ዓመት በፈጀ የፍርድ ሂደትም ፍርድ ቤቱ የቅንጅት መሪዎችን አገርን በመክዳት ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው አገኛቸው። ይሁን እንጂ  ሁሉም የ ቅንጅት መሪዎችና አብዛኛው ደጋፊ አባላት ጥፋታቸውን አምነው ይቅርታ በመጠየቃቸው ከእስር ነጻ ወጡ።




#Article 27: ኤንመርካር (365 words)


ኤንመርካር በሱመር (ሳንጋር) ነገስታት ዝርዝር ዘንድ የኡሩክ (ኦሬክ) ከተማ መስራች ነበረ። በዚያ ዝርዝር ጽህፈት 420 (ወይም በሌላ ቅጂ 900) ዓመታት እንደ ነገሰ ይላል።  ደግሞ አባቱ የኡቱ ልጅ መስኪያጝካሸር ወደ ባሕር ገብቶ ኤንመርካር መንግስቱን ከኤአና ከተማ እንዳመጣ ይጨምራል።

የኤንመርካር ስም በሌላ የሱመር ጽሑፍ ደግሞ ተገኝቷል። «ኤንመርካርና የአራታ ንጉስ» በተባለው ተረት እሱ የኡቱ ልጅ ይባላል። (ኡቱ በሱመር እምነት የጸሓይ አምላክ ነበር።) ይህ ተረት የሰው ልጅ ልሳናት መደባለቁን ይናገራል። ኡሩክን ከመመስረቱ በላይ ታላቅ መስጊድ በኤሪዱም እንዳሰራ ይተረታል።  ለመሆኑም፣ አራታ እንዲገዛለት የሚለው መልእክት በአፍ መናገር ስለሚከብድ፣ ኤንመርካር ጽሕፈት በሸክላ ጽላት ላይ መጻፍ እንደ ፈጠረ ይላል። 

በተጨማሪ በዚሁ ጽሑፍ ኤንመርካር የዙሪያው አገሮች ልዩ ልዩ ልሳናት እንደገና አንድ እንዲሆኑ ይጸልያል። እነዚህ አገራት ሹቡር፣ ሐማዚ፣ ሱመር፣ ኡሪ-ኪ (የአካድ ዙርያ) እና የማርቱ አገር ናቸው። 

ከዚህ በላይ የኤንመርካርን መንግሥት የሚገልጹ ሦስት ተጨማሪ ጽሑፎች አሉ። «ኤንመርካርና ኤንሱሕጊርዓና» የሚባል ተረት የኤንመርካርና የአራታ መቀያየም ሲገልጽ፣ ሐማዚ ተሸንፎ እንደ ነበር ይጠቅሳል። በ«ሉጋልባንዳ በተራራ ዋሻ»፣ ኤንመርካር በአራታ ላይ ዘመቻ ሲመራ ይታያል። አራተኛውና መጨረሻውም ጽላት፣ «ሉጋልባንዳና የአንዙድ ወፍ» ኤንመርካርና ሠራዊቱ በአራታ ዙሪያ ለ1 አመት እንደ ከበቡት ይላል። ለመሆኑ ኤንመርካር 50 አመት ከነገሰ በኋላ፣ የማርቱ ሕዝብ (አሞራውያን) በሱመርና በአካድ ሁሉ ተነሥተው ኡሩክን ለመጠብቅ ግድግዳ በበረሃ መስራት እንደ ነበረበት ይጠቅሳል። 

በነዚህ መጨረሻ 2 ጽላቶች፣ ከኤንመርካር ጦር አለቆች አንድ የሚሆን ሉጋልባንዳ የሚባል ሰው ይተረታል።  በሱመር ነገሥታት ዝርዝር ዘንድ፣ ይህ ሉጋልባንዳ «እረኛው» ኤንመርካርን ወደ ኡሩክ ዙፋን ተከተለው።  ይህ ሉጋልባንዳ ደግሞ በጊልጋመሽ ትውፊት በተባለው ግጥም ዘንድ የኋለኛው ኡሩክ ንጉሥ የጊልጋመሽ አባት ነበረ። 

ዴቪድ ሮኅል የሚባል አንድ የታሪክ ሊቅ የኤንመርካርና የናምሩድ ተመሳሳይነት አመልክቷል። «-ካር» የሚለው ክፍለ-ቃል በሱመር ቋንቋ ማለት «አዳኝ» ነው። ኡሩክ ከተማ የተመሠረተ በኤንመር-ካር ነበር ሲባል፣ ደግሞ ናምሩድ፣ አዳኝ፣ በኦሪት ዘፍጥረት ምእራፍ 10 ዘንድ ኦሬክን ሰራ።  በሌላ ትውፊቶች ዘንድ ይህ ናምሩድ የባቢሎን ግንብ መሪ የሆነ ነበር።  በተጨማሪም አቶ ሮህል የኤሪዱ መጀመርያ ስም «ባቤል» እንደ ነበር ያምናል፤ እዚያም የሚገኘው የግንብ ፍረስራሽ የባቢሎን ግንብ ፍርስራሽ መሆኑን ገመተ። «ባቢሎን» ማለት የኤሪዱ መጠሪያ እንደ ነበር የሚል ማስረጃ በሌሎችም ጥናቶች አለ።
 
ሮማዊው ጸሐፊ ክላውዲዩስ አይሊያኑስ በጻፈ አንድ ትውፊት ዘንድ (200 ዓ.ም. ግድም)፣ የባቢሎን ንጉስ «ኤወኮሮስ» የተከታዩን «ጊልጋሞስ» አያት ይባላል። ይህ «ጊልጋሞስ» ማለት የኡሩክ ንጉስ ጊልጋመሽ መሆኑን የአሁኑ ሊቃውንት ስለ ገነዘቡ፣ እንዲሁም «ኤወኮሮስ» ማለት ኤንመርካር ሳይሆን አይቀርም የሚል አስተሳሰብ ያቀርባሉ። ከዚህ በላይ የከላውዴዎን ታሪክ ጸሐፊ ቤሮሶስ በጻፈው ዝርዝር መሰረት፣ ከማየ አይህ ቀጥሎ የከላውዴዎንና የአሦር መጀመርያው ንጉስ «ኤወኮዮስ» ይባላል፤ ስለዚህ የዚሁ «ኤወኮዮስ»ና የናምሩድ መታወቂያ አንድ ናቸው የሚለው አሳብ ለረጅም ዘመን የቆየ ነው።




#Article 28: አራታ (117 words)


አራታ በሱመር አፈ ታሪክ የተገኘ ጥንታዊ መንግስት ነበር።  በዚያው መሠረት አራታ ሀብታም፣ ተራራማ፣ በወንዞቹ ምንጭ ያለበት አገር ይባላል። 

በተለይ የሚታወቀው ከ4 ጥንታዊ ጽሕፈቶች ነው። እነሱም፦ 

የታሪክ ሊቃውንት ሁሉ ስለ ስፍራው በአንድነት አይስማሙም፤ ብዙዎቹ የአዘርባይጃንና የአራክስ ወንዝ አካባቢ እንደ ጠቀለለ የሚል አስተያየት አላቸው። አራታ አንዳንዴ የሚጠቀሰው በዚያች አራራት አገር በኋላ ዘመን በኖረው በኡራርቱ በሚነካ ጉዳይ ሲያውሩ ነው። ሌሎች ግን በፋርስ ወይም በዛሬው አፍጋኒስታን እንደ ነበር የሚል ግመት አላቸው። በዚህ ረገድ በሳንስክሪት ጽሕፈቶች ደግሞ «አራጣ» የሚባል አገር በአፍጋኒስታን ይገኛል። ሌሎችም አራታ  ከአፈ ታሪክ ውጭ የማይታወቅ ስለ ሆነ ሥፍራው ሊታወቅ አይችልም የሚል አስተያየት አላቸው።

በግሪኩ ሄሮዶቶስ ታሪክ፣ የፋርስ ሕዝብ «አርታዮይ» (አርታያውያን) ተባሉ (VII, 61. 150)። በሄሮዶቶስ ጊዜ የኖረ ሌላ ግሪክ ጸሐፊ ሄላኒኮስ ደግሞ እነዚህ «አርታያ» በሚባል አውራጃ እንደ ኖሩ ይመስክራል።




#Article 29: የባቢሎን ግንብ (1427 words)


በመጽሐፍ ቅዱስ ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 11 ዘንድ፣ የባቢሎን ግንብ ሰማይን እንዲደርሱ የተባበሩት ሰው ልጆች የሠሩ ግንብ ነበር። ያ ዕቅድ እንዳይከናወንላቸው ለመከልከል፣ እግዚአብሔር እያንዳንዱ በተለየ ቋንቋ እንዲናገርበት ልሳናታቸውን አደባለቀ። መግባባት አልተቻላቸውምና ስራው ቆመ። ከዚያ በኋላ፣ ሕዝቦቹ ወደ ልዩ ልዩ መሬት ክፍሎች ሄዱ። ይህ ታሪክ ብዙ የተለያዩ ዘሮችና ቋንቋዎች መኖሩን ለመግለጽ እንደሚጠቅም ይታስባል።

የሰው ልጆች ሁሉ አንድ ኅብረተሰብ ሆነው የሠፈሩባት አገር ሰናዖር ለኤፍራጥስ ወንዝ ቅርብ ነበረች። ባቢሎን በጥንታዊ አካድኛ ምንጭ በተገኘ ባቢሉ (ባብ-ኢሉ) ማለት «የአማልክት በር» ለማለት ነው። በዕብራይስጥ ትርጉም ግን የ«ባቤል» ስም «መደባለቅ» ለማለት ለሚለው ቃል ይመስላል። ከውድቀቱ በፊት የተናገረው ቋንቋ አንዳንዴ «የአዳም ቋንቋ» መሆኑ ይባላል። በታሪክ አንዳንድ ሰው በግምት ያም ሆነ ይህ ቋንቋ መጀመርያው ቋንቋ እንደ ነበር የሚለው ክርክር አቅርቧል። ለምሳሌ ቋንቋው ዕብራይስጥ፣ አራማይስጥ፣  ግዕዝ ወይም ባስክኛ ቢሆንም እንደ ነበር በልዩ ልዩ አስተያየቶች ዘንድ ተብልዋል።

በኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 10 ባቢሎን ከተማ የናምሩድ ግዛት መጀመርያ እንደ ነበር ይላል።

በሱመር (ሳንጋር) አፈ ታሪክ ተመሳሳይ ተረት አለ። በኤንመርካርና የአራታ ንጉስ የኡሩክ (ኦሬክ) ንጉስ ኤንመርካር አንድ ታላቅ መቅደስ በኤሪዱ ሲሠራ ለግንቡ የወርቅና የዕንቁ ግብር ከአራታ ያስገድዳል። አንድ ጊዜ 'ኤንኪ' የተባለውን አምላክ ኗሪ ያለባቸው አገሮች ሁሉ ወደ አንድ ቋንቋ እንዲመልሳቸው ይለምናል። (በሌላ ትርጉም ግን ኤንኪ የአገሮች ቋንቋ እንዲያደባለቅ ይላል።) እነዚህ አገሮች ስሞች ሹባር፣ ሐማዚ፣ ሱመር፣ ኡሪ-ኪ (የአካድ ዙሪያ) እና የማርቱ አገር ይባላሉ። 

በአንድ ዘመናዊ አስተሳሰብ መሠረት፣ የኤንመርካር መታወቂያ የብሉይ ኪዳን ናምሩድ አንድ ነው በመገመት የባቢሎን ግንብ ፍርስራሽ በውኑ ኤሪዱ በሚባል ከተማ ውስጥ ይገኛል ይላል። በዚህ ሀሳብ ኤሪዱ መጀመርያይቱ «ባቤል» እንደ ነበረች ማስረጃ ያቀርባል።

በኦሪተ ዘፍጥረት እግዚአብሔር ግንቡን እንዳጠፋው ወይም ሥራውን ዝም ብሎ እንዳቆመ ምንም አይለንም። መጽሐፈ ኩፋሌ ግን በታላቅ ንፋስ ግንቡን እንዳገለበጠ ይመሰክራል። የድሮ ታሪክ ጸሐፊዎች አብዴንስ፥ ቆርኔሌዎስ አሌክስንድሮስ እና ዮሴፉስ እንዲሁም የሲቢሊን ራዕዮች ሁላቸው ግንቡ በንፋሶች እንደ ተገለበጠ ጻፉ፡ 

መጽሐፈ ኩፋሌ ስለ ግንቡ ብዙ ይላል።

የአይሁድ ረቢዎች ሥነ ጽሑፍ ስለ ባቢሎን ግንብ ማገንባት ምክንያቶች የተለያዩ አስተያየቶች ያቀርባሉ። በእግዚአብሔር ላይ አመጽ እንደ ማድረግ ሚሽና ይቈጥረዋል። 

የግንቡ ሰሪዎች በአንዳንድ አይሁዳዊ ምንጭ ደግሞ «የመነጣጠል ትውልድ» ይባላሉ። እነሱ፦ «እግዚአብሔር ላየኛውን አለም ለራሱ ለመምረጥ ታቸኛውንም ለኛ ለመልቀቅ መብት የለውም፣ ስለዚህ ግንብ እንስራ፣ በጫፉም ሰይፍ የያዘ ጣኦት ይኑር፤ ከእግዚአብሔር ጋራ መዋጋት የምናስብ እንዲታይ» እንዳሉ ሚድራሽ ደግሞ ይጽፋል።

አንዳንድ ጽህፈት ደግሞ አብርሃም አስጠነቀቃቸውና ሰሪዎቹም የተቃወሙ አብሪሃም ነበር ይላል። ከዚያ በላይ በየ1656 አመታት ወሃ በምድር አፍስሶ ሰማይ ስለሚንገዳገድ እንግዲህ ማየ አይህ እንዳይዳግምብን በዓምዶች እንደግፈው ማለታቸው በአይሁዶች ታሪክ ማንበብ ይቻላል። እንኳን ተልሙድ በተባለ አይሁዳዊ መጽሐፍ ስለ ግንቡ ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር መዋጋት እንደ ፈለጉ ይመዝገባል። ፍላጻ ወደ ሰማይ ልከው በደም ተቀብቶ ሲመለስ ተበረታቱ ይላል። ጆሲፉስና አንድ ሚድራሽ ናምሩድ የስራ እቅዱ መሪ እንደ ነበር ይጽፋሉ።

ክግሪክና ከስላቮኒክ ቅጂ ብቻ የሚታወቀው 3 ባሮክ ስለ ግንብ ሲያውራ ለአይሁዳዊው ልማድ ሊስማማ ይችላል። ባሮክ በራእይ መጀመርያ የነፍሶች እረፍት ቦታ ለማየት የወሰዳል። እነዚህ በእግዚአብሔር ላይ የሁከት ግንብ የሰሩ ይባላሉ። ከዚያ በኋላ ሌላ ቦታ ያያል፣ እዚያም በውሻ መልክ፣

በስም ባይታወቅም፣ የባቢሎንን ግንብ የሚመስል ንባብ በቁርዓን ውስጥ ይገኛል። በሱራ 28፡38 እና 40፡36-37 እንደሚለው፣ ፈርዖን ወደ ሰማይ ወጥቶ የሙሴን አምላክ እንዲቃወም ሐማንን የሸክላ ግንብ እንዲሰራለት ጠየቀው።

በሱራ 2:96 ደግሞ የ'ባቢል' ስም ቢገኝም ብዙ ተጨማሪ ዝርዝር አያቀርብም ። ይሁንና በያቁጥ አል ሃርናዊ ጽሕፈት እና ልሳን ኤል አራብ በተባለ መጽሐፍ ዘንድ ስለ ግንብ ምንም ባይጻፍም የሰው ልጆች 'ባቢል' ወደሚባል ሜዳ በንፋሶች ሃይል ተወስደው እዚያ አላህ ለየወገናቸው ልዩ ልዩ ቋንቋ እንደ መደባቸውና ንፋሶች ከዚያ ሜዳ እንደ በተናቸው ይተረታል።

በ9ኛ መቶ ዘመን የነቢያትና የነገሥታት ታሪክ የጻፉት የእስላም ታሪከኛ ሙሐመድ እብን ጃሪር አል-ታባሪ ይህን የመሰለ ተረት ያቀርባል ። በዚህ መሠረት ናምሩድ ግንቡን አስገንቦ አላህ አጠፋውና የሰው ልጅ ቋንቋ ከዚያ ቀድሞ የሶርያ (አራማያ) ሲሆን የዛኔ ወደ 72 ልሣናት ይደባለቃል።

ከዚያ በላይ ደግሞ በ13ኛ መቶ ዘመን የጻፉት ሌላ የእስላም ታሪከኛ አቡ አል-ፊዳ ይህን መሰል ታሪክ ሲያወራ የአብርሃም ቅድመ-አያት ዔቦር ግንቡን ለመሥራት እምቢ ስላለ የፊተኛው ቋንቋ ዕብራይስጥ እንዲቀርለት ተፈቀደ ብሎ ይጽፋል።

የሞርሞኖች መጽሐፍ መጽሐፈ ሞርሞን ስለ ግንቡ ካለበት መረጃ አብዛኛው ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ይስማማል። በተጨማሪም በመጽሐፈ ኤጠር ዘንድ የያሮዳውያን ወገን ቋንቋቸው ሳይደባለቅ ወጥተው በስሜን አሜሪካ ሠፈሩ። ነገር ግን እነኚህ «ያሮዳውያን» የሚባል ሕዝብ እስከ ዛሬ በተገኘ ከሞርሞን በተቀር በምንም ሌላ እምነት ጽሁፍ አልታወቁም።

በሜክሲኮ እና በማዕከል አሜሪካ አፈታሪክ ውስጥ ለባቢሎን ግንብ በጣም ተመሳሳይ ተረቶች አሉ። ለምሳሌ በአንድ ተረት ዘንድ፣ ሸልኋ ከማየ አይህ ያመለጡ 7 ራጃጅሞች አንዱ ሲሆን፣ ሰማይን ለመውረር ታላቅ ፒራሚድ በቾሉላ ሠራ። አማልክት ግን በእሳት አጥፈውት የሠሪዎቹን ቋንቋ አደናገሩ። የስፓንያዊው መነኩሴ ዲየጎ ዱራን (1529-1580 የኖሩ) ሜክሲኮ ከተወረረ በኋላ ይህንን ተረት ከባለ መቶ አመት ቄስ ሰምተው ጻፉበት። 

እንዲሁም ጥንታዊ ቶልቴክ ሕዝብ ሌላ ትውፊት እንደ ነበራቸው ኗሪው የታሪክ ሊቅ ዶን ፈርዲናንድ ዳልቫ እሽትልሾችትል (1557-1640) ይጠቅሳል። በዚህ ተረት ከታላቅ ጎርፍ በኋላ የሰው ልጆች በዝተው ሌላ ጎርፍ እንዳይዳግምባቸው አንድ ረጅም ግንብ ሠሩ ይላል። ነገር ግን ልሳናታቸው ተደባልቀው ወደ ተለያዩ አገሮች ተጓዙ። 

እንደገና ሌላ ትውፊት በአሪዞና ቀይ ኢንዲያኖች ጎሣ በቶሆኖ ኦኦዳም ብሔር መካከል ይገኛል። በዚህ መሠረት ሞንተዙማ የሚባል ሃያል ከታልቅ ጎርፍ ከማምለጡ በኋላ እጅግ ክፉ ሆነና እስከ ሰማይ ድረስ የሚረዝም ቤት ለመሥራት ቢሞክር 'ታላቁ መንፈስ' በመብራቅ አጠፋው። 

ከዚያ በላይ በታዋቂው መርማሪ ዶክቶር ሊቪንግስተን ዘንድ በ1871 ዓ.ም. በንጋሚ ሀይቅ አፍሪቃ ተመሳሳይ ተረት አገኙ። በዚህ ትርጉም ግንቡ ሲወድቅ የሠሪዎቹ ራሶች ተሰባበሩ። ጸሐፊው ጄምስ ጆርጅ ፍሬዘር ደግሞ የሊቪንግስተን ወሬ በሎዚ ጎሣ አፈ ታሪክ ከሚገኝ ተረት ጋር ግንኙነቱን አጠቁሟል። በዚህ ተረት ዘንድ፣ ፈጣሪ አምላካቸው 'ኛምቤ' ወደ ሰማይ በሸረሪት ድር ሸሽቶ ክፉ ሰዎች እንዲያሳድዱት ከተራዳዎች ግንብ ቢሠሩም ተራዳዎቹ ግን ሲወድቁ ሰዎቹ ይጠፋሉ። በተጨማሪ በአሻንቲ ጎሣ እንዲህ መሰል ተረት ሲያገኝ በተራዳዎቹ ፈንታ ግን ግንቡ የተሠራ ከአጥሚት ዘነዘናዎች ክምር ነው። ፍሬዘር ደግሞ እንደነዚህ ያሉ ትውፊቶች በኮንጎ ሕዝብ እና በታንዛኒያ ጠቅሶአል፤ በነዚህ ትውፊቶች ሰዎቹ ወደ ጨረቃ ለመድረስ ሲሞክሩ ተራዳዎች ወይም ዛፎች ይከምራሉ።.

ይህን የመሠለ ታሪክ ደግሞ በጣሩ ሕዝብ እንዲሁም በካርቢና በኩኪ ብሔሮች በስሜን ሕንድ ተገኝቷል። ከዚህ በላይ በምየንማ የሚኖረው ካሬን ሕዝብ ያላቸው ልማድ ይህን አይነት ተጽእኖ ያሳያል። በዚያ ልማድ መሠረት፣ ከአዳም 30 ትውልዶች በኋላ በካሬን-ኒ አገር ታላቅ ግንብ በተተወበት ቋንቋዎችም በተደባለቀበት ጊዜ የካሬን ቅድማያቶች ከካሬን-ኒ ተለይተው ወደ አገራቸው እንደ ፈለሱ ይባላል። እንደገና በአድሚራልቲ ደሴቶች ሌላ አፈታሪክ ሰዎች እስከ ሰማይ ድረስ ታላቅ ቤቶች ለማድረስ ሞክረው ከወደቁ በኋላ ልሳናታቸው ተደባለቁ ይላል።

ኦሪት ዘፍጥረት ስለ ግንቡ ቁመት (ከፍታ) ምንም ባይነግረንም፣ በሌላ ምንጭ ግን ልዩ ልዩ መልስ ሊገኝ ይቻላል። መጽሐፈ ኩፋሌ 5,433 ክንድ እንደ ደረሰ ሲል ይህ ከዛሬ ሕንጻዎች እንኳ በእጥፍ የሚልቅ ነው። እንዲሁም በ3ኛ ባሮክ መሠረት እስከ 463 ክንድ (212 ሜትር) ድረስ መሆኑን ሲነግረን ይህ ቁመት እስከ ዘመናዊው (1881 ዓ.ም.) አይፈል ግንብ ድረስ አልተበለጠም። ናቡከደነጾር ክ.በ. 570 አካባቢ ያሠራው ግንብ 100 ሜትር ገደማ ከፍ እንዳለ ይታመናል።

በሌሎች ምንጭ ዘንድ፦

ከመካከለኛው ዘመን ጽነ ጽሁፍ መካከል በባቢሎን ግንብ የተበተኑትን ልሳናት ለመቆጠር የሚሞክሩ ታሪኮች ብዙ ናቸው። በኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 10 ውስጥ የኖህ ተወላጆች ስሞች ሁሉ ሲቆጠሩ ለያፌት ልጆች 15፣ ለካም ልጆች 30፣ ለሴም ልጆች 27 ስሞች ይሠጣል። እነዚህም ቁጥሮች ከባቤል (ባቢሎን) መደባለቅ የወጡት 72ቱ ልሣናት ሆነው ተመሠረቱ፤ ሆኖም የቋንቋዎች መታወቂያ በጊዜ ላይ ይለያይ ነበር። (የዕብራይስጥ ትርጉም ግን የይልሳና የቃይንም ስሞች ስለሌለው አይሁዳዊ ምንጮች እንደ ሚሽና ስለ '70 ልሳናት' ይናገራሉ።) 72 (ወይም 73) ልሳናት የሚሉ ጥንታዊ ምንጮች ክርስቲያናዊው ጸሐፊዎች የእስክንድርያ ቄሌምንጦስና አቡሊደስ (2ኛ ክፍለ ዘመን) እንዲሁም በ350 ዓ.ም. ገዳማ የተጻፈው በዓተ መዛግብት፤ በ365 ዓ.ም. ገደማ ፓናሪዮን የጻፉት የሳላሚስ ኤጲፋንዮስና በ404 ዓ.ም. ገደማ የግዜር ከተማ የጻፉት ቅዱስ አውግስጢኖስ ናቸው።

የሴቪሌ ኢሲዶሬ (625 አካባቢ) ስለ 72 ቋንቋዎች ቢያወራ ከኦሪት ስሞቹን ሲዘረዝር ግን የዮቅጣን ልጆች ቀርተው የአብርሃምና የሎጥ ልጆች ተተኩ፤ ስለዚህ 56 ስሞች ብቻ አሉ። ከዚያ በራሱ ዘመን ከታወቁት ወገኖች እንደ ላንጎባርዶችና ፍራንኮች ይዘረዝራል። ከዚሁ ሂሳብ ተጽእኖ የተነሣ በኋለኞቹ ታሪኮች ለምሳሌ በአይርላንድ መንኩሳዊ መጻሕፍት አውራከፕት ና ኔከሽና የ11ኛ ክፍለ ዘመን ሌቦር ጋባላ ኤረን እንዲሁም በአይሁዳዊው ሚድራሽ መጽሐፈ ያሸር፤ ሎምባርዶችና ፍራንኮች እራሳቸው የያፌት ልጅ ልጆች ስሞች ሆኑ።

ከነዚህ ሌሎች ከባቤል ስለተበተኑት ስለ 72 (ወይም 70) ልሣናት የሚናገሩት ምንጮች ብዙ ናቸው። ከነሱም፡ የነቢያትና የነገሥታት ታሪክ ከእስላማዊው መሐመድ እብን ጃሪር አል-ታባሪ (9ኛ ክፍለ ዘመን)፤ የጥንታዊ እንግሊዝኛ ግጥም ሰሎሞንና ሳቱርን፤ አይሁዳዊው ካባላ ጽሑፍ ባሒር (1166 ዓ.ም.)፤ የአይስላንዳዊው ስኖሪ ስቱርሉሶን ንዑስ ኤዳ (1190 ዓ.ም. አካባቢ)፤ በጽርዕ የተጻፈው መጽሐፈ ንቡ (1214 ዓ.ም.)፤ ጌስታ ሁኖሩም ኤት ሁንጋሮሩም (1276 ዓ.ም.)፤ የጆቫኒ ቪላኒ ታሪክ (1300 ዓ.ም.)፤ እና አይሁዳዊው ሚድራሽ ሃ-ጋዶል (14ኛ ክ.ዘ.) ናቸው። በቪላኒ ትርጉምም ግንቡ «ከማየ አይህ በኋላ 700 አመት ተጀምሮ ከአለሙ ፍጥረት እስከ ባቢሎን ግንብ መደባለቅ ድረስ 2354 አመቶች ነበሩ። በስራ ላይ ለ107 አመታት እንደ ቆዩም እናገኛለን፤ ሰዎች በዛኛ ዘመን ለረጅም ዕድሜ ይኖሩ ነበርና።» በጌስታ ሁኖሩም ኤት ሁንጋሮሩም መሠረት ግን ሥራ እቅዱን ከማየ አይህ በኋላ 200 አመት ብቻ ጀመሩ።

የ72ቱ ቋንቋዎች ልማድ እስከ ኋለኛ ዘመን ድረስ ቆየ። ስፓንያዊው ሆዜ ዴ አኮስታ በ1568 ዓ.ም. ከዚህ ቁጥር አብልጦ በፔሩ ብቻ ስንት መቶ እርስ በርስ የማይግባቡ ቋንቋዎች እንዳገኘ ተገረመ፤ ከመቶ አመት በኋላ እንደገና ፖርቱጊዙ አንቶኒዮ ቪዬራ ስለ ብራዚል ቋንቋዎች ብዛት ተመሳሳይ አስተያየት አቀረበ።

የባቢሎን ግንብ በዘመናዊ ልብ ወለድ ታሪክ፣ ፊልሞችና ጨዋታዎች ሚና ተጫውቷል። ለምሳሌ ባንድ ደራሲ ኒል ስቲቨንሶን ልብ ወልደ ታሪክ ስኖ ክራሽ፣ የግንቡ ትርጉም ሰዎች ወደ ሰማይ በመንኮራኩር የመድረስ ሙከራ ምሳሌ ነው። እንደገና በሌላ ልብ ወለድ፣ የዳግላስ አዳምስ ዘ ሂችሃይከርስ ጋይድ ቱ ዘ ጋላክሲ፣ የባቤል ዓሣ በጆሮ ውስጥ ሲገባ ማንኛውንም ቋንቋ ለማስተርጉም ችሎታ አለው። 

በ1920 ፊልሙ ሜትሮፖሊስ፣ የባቢሎን ግንብ በአለማዊ መንግሥት ሁለተኛ ይሰራል። 

ከዚሁ በላይ የባቢሎን ግንብ በበርካታ የኮምፒዩተርና የቪዴዮ ጨዋታዎች ውስጥ ይታያል። እነሱም ዚኖጊርስ፣ ፋይናል ፋንታሲ 4፣ ዱም፣ ፕሪንስ ኦፍ ፐርዝያ፡ ዘ ቱ ስሮንስ፣ ዶሺን ዘ ጃየንት፣ ሲሪየስ ሳም፡ ሰከንድ እንካውንተር፣ ፍሪስፔስ 2፣ ፔንኪለር፣ ኢሉዠን ኦቭ ጋያ፣ እና ክሩሴድር ኦቭ ሰንቲ የሚባሉ የቪዴዮ ጨዋታዎች ናቸው። እንዲሁም ሻዶው ኦቭ ዘ ኮሎሰስ፣ ሲቪላይዜሸን 3፣ ዴቪል መይ ክራይ 3፣ እና ሜጋ ማን ኤክስ፡ ኮማንድ ሚሸን በሚባሉ ጨዋታዎች የባቢሎን ግንብ ምሳሌዎች ሊታዩ ይችላሉ።




#Article 30: ፍልስፍና (454 words)


ፍልስፍና የሚለው ቃል ከግሪኩ «Philos» /ፊሎስ/ ማለትም ፍቅር እና፣ «sophos» /ሶፎስ/ (ጥበብ) የተገኘ ውሁድ ነው። በቀጥታው የጥበብ ፍቅር ወይም ፍቅረ ጥበብ ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። በመሆኑም ፍልስፍና እውቀትን፣ እውነትን፣ ጥበብን መውደድ፣ መሻት፣ መመርመር ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። ባንድ በኩል ወደ ጥበብ የተሳበ፣ ጥበብን የወደደ እንደዚሁም የጥበብ ባለሟልን የሚያመለክት ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ  ጥበብን ወዶ ሌላውም እንዲወድ ምክንያት የሚሆን ለማለት ይውላል። ይህ የጥናት ክፍል በዋናነት ነገሮችን በመላምታዊ መንገድ ለመመርመር ይሞክራል።  

የፍልስፍናን ምንነት ለማወቅ የሚጠይቃቸውን ዋነኛ ጥያቄዎች እንመልከት።

ፍልስፍና የሚመረምራችው አምስት ዋነኛ ቁምነገሮች ህላዌ፣ ግብረገብ፣ እውቀት፣ እውነት፣ እና ውበት ናቸው። ፈላስፋዎችን ለብዙ ዘመናት ሲያስጨንቁ ከቆዩ ጥያቄዎች ውስጥ 

እነዚህ ከላይ በደፈናው የተጠቀሱ ጥያቄዎች እንደ ቅደም ተከተላቸው አመክንዮአዊ፣ ሥነ-እውቀታዊ፣ ሥነ-ምግባራዊ፣ ሥነ-ኃልዮአዊ፣ እና ሥነ-ውበትአዊ በመባል ይታወቃሉ። ምንም እንኳን እነዚህ ዋነኞቹ ጥያቄዎች ይሁኑ እንጂ ብቸኞቹ አይደሉም። በተጨማሪም በመካከላቸው አንዳንድ መደራረብ ይታያል። ታዋቂው የግሪክ ፈላስፋ አሪስጣጣሊስ ሥነ-መንግሥት፣ ሥነ-ተፈጥሮ፣ ሥነ-ምድር፣ ሥነ፡ሕይወት፣ ሥነ-አየር እና ሥነ ፈለክ የፍልስፍና ክፍሎች ናቸው ብሎ ያምን ነበር። 
ሌሎች የፍልስፍና ባህሎች ከምዕራባውያን ፍልስፍና በተለየ በነዚህ ጉዳዮች ላይ በዙም አላተኮሩም። ምንም እንኳን የሂንዱ ፍልስፍና በዚህ አንፃር ከምዕራባውያኑ ቢመሳሰለም እስከ 19ኛው ምዕት-አመት ድረስ በኮሪይኛ፣ በጃፓንኛ፣ እና በቻይንኛ ውስጥ ፍልስፍና የሚል ቃል ይገኝ አልነበረም። በተለይ የቻይና ፈላስፎች ከግሪኮቹ ለየት ያለ የምደባ ስርዓት ይከተሉ ነበር።

የምዕራቡ አለም ፍልስፍና የሚጀምረው ከግሪኮች ሲሆን የመጀመሪያው ፈላስፋ ተብሎ የሚታወቀው ታሊዝ ነው። ይህ ሰው የኖረበትን ጊዜ ለማወቅ ብዙም አስቸጋሪ አይደለም። ይኸውም በ593 ዓክልበ. (ዓም) የፀሃይ ግርዶሽ እንደሚኖር በመተንበዩ ከዚህ ጊዜ የተወሰነ አመት ቀደመ ብሎ ማይሌጠስ በተባለችው የትንሹ እስያ (የአሁኑ ቱርክ) ክፍል እንደተወለደ የታወቀ ነው። ታሊዝ ዓለም እና በውስጡ ያሉ ነገሮች ሁሉ ከውሃ እንደተፈጠሩ ያምን ነበረ። ከሱ በኋላ የተነሱ የግሪክ ፈላስፎች የሱኑ መንገድ በመከተል ዓለም ከአንድ ወይም ከሌላ ነገረ እንደተፈጠረች አስተምረዋል። ለምሳሌ አናክሲሜነስ የዓለም ጥንተመሰረቷ አየር ነው ሲል፣ ሄራቅሊጠስ እሳት ነው ብሏል። አናክሲማንደር ከነዚህ ሁሉ ለየት በማለት የዓለም መሰረቷ ይህ ነው የማይባል «apeiron» ወይም የትየለሌ የሆነ ነገር ነው ይላል።

የምእራቡን ዓለም ፍልስፍና እስክ 1900 ድረስ ቅርጽ እንዳስያዙ የሚነግርላቸው ፈላስፋዎች የሚከተሉት ናቸው፡

ሶቅራጥስ፣ አሪስጣጣሪስ፣ ፕላጦ፣ አክዊናስ፣ ኤራስመስ፣ ማኪአቬሌ፣ ቶማስ ሞር፣ ሞንታጝ፣ ግሮቲየስ፣ ዴካርት፣ ሆበስ፣ ስፒኖዛ፣ ሎክ፣ ሌብኒሽት፣ በርክሌ፣ ሑሜ፣ ቮልቴይ፣ ሩሶ፣ ካንት፣ ሺለር፣ ሄግል፣ ሾፐናዎር፣ ጆን ኦስቲን፣ ጄ.ኤስ. ሚል፣ ኮምቴ፣ ዳርዊን፣ ማርክስ፣ እንግልስ፣ ፍሬደሪሕ ኚሼ፣ ዱርካሂም

የምስራቁ አለም ፍልስፍና መነሻ ኢትዮጲያ ናት፡፡እንደውም የመላው አለም፡፡
በተለይ ኮከባቸው gemini የሆኑት የሐበሻ ተወላጆች የኮከባቸውን ሀያልነት በመጠቀም ወደ አረቡ አለም በመገስገስ የምድራችንን የፍልስፍና መንገድ ቀይሠዋል፡፡

አላህ ለሚሻው ሰው ጥበብን ይሰጣል፤ ጥበብን ከአላህ የተሰጠው ሰው ብዙን መልካም ነገር በእርግጥ ተሰጦታል፦

አላህ ጥበብን ለሰው ልጆች በዐቅል እና በነቅል ይሰጣል፤ እነዚህ ሁለት የጥበብ ጭብጦችን ነጥብ በነጥብ እንይ፦

ነጥብ አንድ

የመሳሰሉት እሳቦት ይዟል። ጥበብ”craft” እራሱ፦ ሥነ-ጥበብ፣ እደ-ጥበብ፣ ኪነ-ጥበብ እና አውደ-ጥበብ ለአሉታዊ ነገር ከተጠቀሙበት ምግባረ-እኩይ”witch-craft” ሲሆን በአውንታዊ ከተጠቀምንበት ምግባረ-ስናይ”art-craft” መማሪያም ነው፤ አላህ፦ “አፈላ ተዕቂሉን” أَفَلَا تَعْقِلُون ይለናል፦

ነጥብ ሁለት

ይህም ጥበብ ክብራችን በውሥጡ ያለበትን መጽሐፍ ቁርአን ነው፤ ቁርአን ጥበብ የተሞላ መጽሐፍ ነው፦

ስለዚህ ክብራችን በውስጡ ያለበትን ይህንን ጥበብ የተሞላ መጽሐፍ መገንዘብ ግድ ይላል ማለት ነው፤ የእሳት ሰዎች “የምናገናዝብ” በነበርን ኖሮ በነዳጅ እሳት ጓዶች ውስጥ ባልሆን ነበር ብለው ይፀፀታሉ፦

(✍ከወንድም ወሒድ ዑመር)




#Article 31: የሥነ፡ልቡና ትምህርት (207 words)


ስነ ልቦና ማለት በሰው ውስጥ የሚኖር እንስሶች የሌለላቸው ነፍስ ማለት ነው። ሰው እና እንስሳት አንድ የሚያደርጋቸው ሕይወታቸው ሲሆን ህይወት ደግሞ የምትጠፋ ናት። ሰነ ልቦና ግን ከተፈጠርን ጀምሮ አብሮን የሚኖር ውስጣዊ እኛነታችን ነው።

በሙት ባሕር እስራኤል በተገኙት ብራና ጥቅሎች በአንዱ «የሥርዓት መመሪያ መጽሐፍ» በተባለ ብራና ውስጥ ለሰዎች ሁሉ ሁለት መናፍስት እንደተሾሙ ይላል፤ እነርሱም ሀሠት ወይም ትእቢት (ጥላ) እና እውነት ወይም ኅሊና (ብርሃን) ይባላሉ። ለዚህ እምነት በቤተ እስራኤል ዘንድ ተመሳሳይ ጽሁፍ አለ፤ የተሾሙ መላእክት በጐ ወይም ጥፉ አድራጎት በወርቅ ይመዝገባሉ ይላል። 

ፕላቶ በጻፈው ፋይድሮስ በተባለው ጽሑፍ፣ ሶክራቴስ እንዲህ ይላል፦ «ነፍሱን እንደ ሁለት ባለ ክንፍ ፈረሶችና የሠረገላ ነጂ እናስመስላለን። ... የሰብዓዊ ነፍስ ነጂ ሁለቱን ይነዳል፤ ከፈረሶቹ አንዱ መልካምና ከመልካም ዘር ነው፣ ሌላው ግን በባኅርይም ሆነ በዘር እጅግ ተቃራኒ ነው። ስለዚህ በኛ በኩል መንዳቱ በግድ ከባድና አስቸጋሪ ነው።» 

በዘመናዊው ሥነ ልቡና ደግሞ አእምሮ በሁለት ክፍሎች ይለያል። አንዱ ክፍል በደረታቸው የሚስቡ እንስሳት ባይኖራቸው የሚጠቡ እንስሶች ብቻ ይዘውት ነው። ሌላው ክፍል ለእንስሳት ሁሉ የጋራ ነው።

የሰው ዘር ከአብዛኛው እንስሳ ለየት የሚለው እያንዳንዱ የሚያስበው ነገር የተለያየ መሆኑ ነው። እንስሶች ያውም የአዕምሮአቸው ክብደት በጣም ዝቅተኛ የሆኑ ብቻ ናቸው አንድ ነገር ላይ አተኩረው ወይም አንዱን ተከትለው የሚሄዱት። አንዳንድ የአሳ ዘሮች፤ አንዳንድ የወፍ ዘሮች፤ በመጠኑ እንደ በግ ያሉ እንስሳዎች እንደምሳሌ ይጠቀሳሉ። ሰውን በቡድን መድቦ ይሄ እንዲህ ያስባል፤ ያ እንዲያ ያስባል ማለት የሰውን ልጅ አዕምሮ ረቂቅነት አለመገንዘብ ነው።




#Article 32: ኢትዮ ሬይን ሜከርስ (289 words)


ኢትዮ ሬይን ሜከርስ (Ethio Rain Maker) በኢትዮጵያ ውስጥ ዛፎች በመትከል ረሃብን ለመከልከል የተቋቋመ ቡድን ነው።

አሁን ወደ ምድረ በዳ መጥተው በወንድማማችነት ገነት ይሠራሉ።  በድርቅ አፈር ውስጥ የሚተክሉት ዘር ታላቅ ደን ይሆናል፤ ምድሪቱ እንደገና በሙሉ እስክትሸፈን ድረስ ረጀም ዛፎች በዝተው አረንጓዴ ክንፎቻቸውን ይዘረጋሉ።

ኢትዮ ሬይን ሜከርስ ሃገራችንን አረንጓዴ ለማልበስ የተቋቋመ ቡድን ነው።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በአለም መገናኛ ብዙሃን በረሃብ ስትጠራ፣ ህዝቦችዋ በጠኔ ሲሰቃዩ ዘመናት ተቆጥረዋል። የወገኖቻችን ስቃይ፣ የሀገራችን ኋላ ቀርነት በኢትዮጲያዊነታችን እያንዳንዳችንን ይመለከተናል። ላለፉት ሰላሳ አመታት በጎ አድራጊ ድርጅቶች በአይነትም ሆነ በጥሬ ገንዘብ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር እንደረዱን መረጃ አውጥተዋል። የኛ ስቃይ ግን አላበቃም። መከር ሲመጣ ሰብል ከማጨድና ምርት ከመሰብሰብ ይልቅ ለልመና እጁን የሚዘረጋ ኢትዮጲያዊ ቁጥር በሶስት እጥፍ ጨመረ። ይህ ሂደት መቆም አለበት። እንዴት?

አበው “ነገርን ከስሩ …” እንደሚሉት የሁሉም ችግር መፍትሔው ያለው ከመነሻው ላይ ነው። የኛ ረሐብ መንስዔው ምንድነው? በአጭሩ ለመግለጽ ያህል ለረሐባችን መንስዔ የዝናብ አለመኖር (ድርቅ) መሆኑን  ከረሐባችን ታሪክም ሆነ ጥናቱን ካካሄዱት ምሁራን መረዳት ይቻላል። ዛሬም ቢሆን ገበሬው ዝናብ በማጣቱ ሰብሉ መበላሸቱን ከአንደበቱ እየሰማን ነው።
ጦርነትን ለማቆም የጦርነት መነሻ ሃሳቦችን ማስወገድ እንጂ ጦርነትን ከጦር ሜዳ ማስቆም እንደማይቻል ሁሉ የሃገራችንንም ረሃብ ከመንስዔው እንንቀለው።

ኢትዮ ሬይን ሜከርስ፣ ኢትዮጵያ ዉስጥ ደን ማደነን (አፎረስቴሽን) ችግራችንን ከመቅረፊያ መንገዶች አንዱ እንደሆነ በማመን የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም ችግኞችን መትከል ጀምሯል። 

በ1995 ዓ.ም. ከኢትዮጵያ ቅርስ ባለ አደራ ጋር በመተባበር በእንጦጦ የተፈጥሮ መናፈሻ አስር ሺህ ችግኞችን ተክሎ ሰባ ሁለት ከመቶው (7167) ፀድቋል። በ1996 ክረምት ደግሞ ሀምሳ ሺህ ችግኞችን ለመትከል አቅዶ ሀያ ከመቶው ተጠናቋል። በአሰላ፣ በመቀሌና በባህር ዳር አንድ ሺህ ዛፎችን የሚይዙ የተፈጥሮ መናፈሻዎችንን በመስራት ላይ ነን። በ1997 ለሀገራችን የሺህ አመት ስጦታ እንስጥ በሚል መነሻ ሀሳብ እያንዳንዱ ኢትዮጲያዊ አንድ ዛፍ ተክሎ የሚንከባከብበትን እቅድ አውጥተናል። ከነዚህም አንዱ አንድ ዛፍ ለአንድ ተማሪ ነው።

የሃገራችን የዘመናት ችግር በአንድ አመትና በጥቂት ሰዎች ጥረት አይፈታም። ለዚህ አላማ መሳካት የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጥረትና እገዛ ያስፈልጋልና ሃገራችንን ከረሐብ ለመታደግ አብረን ዛፍ እንትከል። እንንከባከብም።

 (አማርኛ እና እንግሊዝኛ - Amharic  English)




#Article 33: የሕገ መንግሥት ታሪክ (811 words)


የሱመር ከተማ ላጋሽ አለቃ ኡሩካጊና በ2093 ዓክልበ. ያሕል ያዋጀ ሕገ ፍትሕ በታሪካዊ መዝገብ እስከምናውቀው ድረስ መጀመርያ የሕገ መንግሥት ሰነድ ነው። ሰነዱ እራሱ ገና አልተገኘም፤ ነገር ግን ለዜጎቹ አንዳንድ መብት እንደ ፈቀደላቸው ይታወቃል። ለምሳሌ ለመበለትና ለደሀ አደጎች ቀረጥ እንዳስቀረላቸው ድሆችንም ከሃብታሞች አራጣ እንደጠበቃቸው ይታወቃል።

ከዚህ በኋላ ብዙ መንግሥታት በተጻፈ ሕግ እንዲገዙ ልዩ ስርዓት ነበራቸው። ከተገኙት ሕግጋት ሁሉ ጥንታዊ የሆነው በ1983 ዓክልበ. የገዙ የኡር ንጉሥ የኡር-ናሙ ሕግጋት ነው። በተለይ ዕውቅ የሆኑ የጥንት መንግሥት ሕጎች የኢሲን ንጉሥ ሊፒት-እሽታር ሕግጋት (1832 ዓክልበ.) ፤ የኤሽኑና ሕግጋት (ምናልባት 1775 ዓክልበ. ግድም)፤ የባቢሎን ንጉሥ ሃሙራቢ ሕግጋት (1704 ዓክልበ.) እና፤ ሕገ ሙሴ ለእስራኤል (1661 ዓክልበ.) ናቸው። ሕገ ሙሴ በተለይ በኦሪት ዘጸአት 21 እና 22 ያህዌ አስተካክሎ ከነዚህ ሁሉ የተሻሸሉት ብያኔዎች ይጠቅልላል። በኋላ ኬጢያውያን (1488 ዓክልበ. ግድም) እና አሦር (1080 ዓክልበ. ግድም) በበኩላቸው ለራሳቸው ሕግጋት አወጡ። 

በ628 ዓክልበ.፣ ድራኮ የሚባል ጸሃፊ የአቴና ከተማ ሕግጋት ጻፈ፤ ይህም ሕግ እጅግ ጨካኝ ሆኖ ይሙት በቃ ለማንኛውም ጥፋት ወሰነ።  በ600 ዓክልበ.፣ የአቴና አለቃ ሶሎን አዲስ ሕገ መንግሥት ፈጠረ።  የሰራተኞች ሸክም አቀለለ፣ ነገር ግን ባላባትነት በልደት ሳይሆን በንብረት ብዛት እንዲቈጠር አስደረገ። ክሊስቴኔስ እንደገና በ516 ዓክልበ. በዴሞክራሲያዊ መሠረት የተሻሸለ ለአቴና  ሕገ መንግሥት አወጣ።  

የግሪክ ፈላስፋ አሪስጣጣሊስ በ350 ዓክልበ. ግድም የሕገ መንግሥት ሀሣብ ለይቶ ዐወቀ። በጽሑፎቹ የአቴና፣ የስፓርታና የካርታግና ሕገ መንግሥቶች ያነጻጽራል። በመደምደሚያው የተሻለው ሕገ መንግሥት ከንጉሣዊ፣ ከመኳንንታዊና ከሕዝባዊ ወገኖች የተደባለቀ መሆኑን ገመተ። በሀሣቡ በመንግሥት የሚከፋፈሉ ዜጎች ከማይከፋፈሉ ከባርዮችና ዜጎች ካልሆኑ ሰዎች ልዩነት አደረገ።

ሮማውያን መጀመርያ «12ቱ ሰንተረዦች» የተባለውን ሕገ መንግሥት ያወጡ በ457 ዓክልበ. ነበር። ከዚያ በኋላ አንዳንዴ የተለያዩ ሕጎችና ትእዛዛት ይጨምሩበት ነበር እንጂ እስከ መጽሐፈ ቴዎዶስዮስ ድረስ (430 ዓ.ም.) ሌላ ክምቹ ሕገ መንግሥት አልኖረም ነበር። በኋላም በምሥራቁ መንግሥት (ቢዛንታይን) በኩል መጽሐፈ ዩስጢኒያኖስ (526 ዓ.ም.) ለአውሮፓ ከፍ ያለ ተጽእኖ ነበረው። ይህም በምስራቁ ነገሥታት 3ኛ ሌዎን ኢሳውራዊ «ኤክሎጋ» (732 ዓ.ም.) እና በ1ኛ ባሲሌዎስ «ባሲሊካ» (870 ዓ.ም.) በተባሉት ሕገ ፍትሐን ተከተለ።

በሕንድ ንጉሥ አሾካ መንግሥት የአሾካ አዋጆች ሕግጋት በ264 አክልበ. መሠረቱ።

ከምዕራቡ ሮማ መንግሥት ውድቀት ደግሞ ወደ ተረፈው ሕዋእ ውስጥ ከፈለሱት ጀርመናውያን ወገኖች አብዛኛው የራሳቸውን ሕጎች ዝርዝር በጽሑፍ አወጡ። በተለይ የሚታወቁም የቪዚጎቶች አለቃ ዩሪክ ሕግ (463 ዓ.ም.)፣ የቡርጎንዳውያን ሕግጋት (እኚህ ለጀርመናውያንና ለሮማውያን የተለያየ ፍትሕ ነበራቸው)፣ የአላማናውያን ሕግጋትና፣ የፍራንኮች ሕግጋት ናቸው፤ እነዚህ ሁሉ የተጻፉት ከ492 ዓ.ም. ጀምሮ ነው። በ498 ዓ.ም. የቪዚጎቶች አለቃ 2ኛ አላሪክ መጽሐፈ ቴዎዶስዮስና አንዳንድ የተለያዩ የቀድሞ ሮማ ሐገጋት አከማችተው አዋጁአቸው። ከዚህም በኋላ የታዩ ሕጎች የሎምባርዶች ሕግጋት (635 ዓ.ም.)፣ የቪዚጎቶች አዳዲስ ሕግጋት (646 ዓ.ም.)፣ የአላማናውያን አዳዲስ ሕግጋት (722 ዓ.ም.) እና የፍሪዝያውያን ሕግጋት (777 ዓ.ም.) አሉ። በአውሮፓ አኅጉር ላይ የተጻፉት እነኚህ ፍትሖች ሁሉ በሮማይስጥ ቢጻፉም፣ በእንግሊዝ አገር ግን የተጠቀሙት ሕጎች ከኬንት ንጉሥ ኤጠልቤርት ሕጎች (594 ዓ.ም.) ጀምሮ በጥንታዊ እንግሊዝኛ የተቀነባበሩ ነበሩ። በ885 ዓ.ም. ታላቁ አልፍሬድ ይህንንና ሁለት የድሮ ፍትሖች ከሕገ ሙሴና ከሕገ ወንጌል ጋራ አጋጥመው የእንግሊዝ ሕገ መንግሥት ዶም ቦክ ሠርተዋል። 

በ596 ዓ.ም. በጃፓን 17 አንቀጽ ያለ ሕገ መንግሥት በልዑል ሾታኩ እንደተጻፈ ይታመናል። እንዲሁም በ614 ዓ.ም. ከነቢዩ መሐመድ የወጣው የመዲና ሕገ መንግሥት ዕጅግ ጥንታዊ ምሳሌ ነው።

በዌልስ በ940 ዓ.ም. አካባቢ ንጉስ ህወል ዳ ሕጎቹን ጻፉ። በዛሬው ሩሲያ ደግሞ የክዬቭ ታላቅ መስፍን ያሮስላቭ ጥበበኛው ፕራቭዳ ያሮስላቫ የተባለውን ሕገ መንግሥት በ1009 ዓ.ም. ያህል ሠሩ። ይህ ሕግ በ1046 ታድሶ በኪዬቭ ሩስ በሙሉ ህጝ ሆነ። 

በስሜን አሜሪካ የኖሩ ኗሪ ጎሣ ሆደነሾኒ 'የአፈ ቃል' ሕገ መንግሥት «ጋያነሸጎዋ» የነበራችው ከ1080-1140 ዓ.ም. አካባቢ ጀምሮ እንደሆነ ይታመናል። ይህ ሕግ በከፊል ለአሜሪካ ሕገ መንግሥት ተጽእኖ እንደነበረው ይታመናልና የአሜሪካ ምክር ቤት በ1981 ዓ.ም. ይህንን ግንዛቤ አስታወቀ። 

በእንግሊዝ አገር በ1092 ዓ.ም. ንጉስ 1 ሄንሪ የነጻነት ሥርአት የተባለውን ሰነድ አዋጀ። ይህ መጀመርያ የንጉሱን ሥልጣን ወሰኖ ንጉሡ ለቤተ ካህናትና ለቤተ መሳፍንት ወገኖች የሚገባውን እንቅብቃቤ ገለጸ። ይህም መሰረት በመኳንንቱ ሲዘረጋ በ1207 ዓ.ም. የእንግሊዝ ንጉሱን ዮሃንስ (ጆን) ማግና ካርታ («ታላቅ ሥርዓት») የሚባለውን ሰነድ እንዲፈርሙት አስገደዱዋቸው።  ከዚሁ መሃል ቁም ነገር የሆነው ንጉሡ ያለ ሕጋዊ ሂደት ማንንም ሰው እንዳይገድሉ፣ ከአገር እንዳያሳደዱ፣ ወይም እስር ቤት እንዳያስገቡ ከለከላቸው። በዚያ ወቅት ያ ሰነድ በእንግሊዝ አገር የነጻነት መሠረት ሆነ።

በ1212 እና 1222 ዓ.ም. መካከል አንድ የሳቅሰን አስተዳዳሪ አይከ ቮን ረፕጎቭ ያቀነባበረው ሕግጋት ሳቅሰንሽፒግል በአንዳንድ ጀርመን ክፍላገር እስከ 1892 ዓ.ም. ድረስ ላይኛ ሕገ መንግሥት ሆነ።  

በ1228 ዓ.ም. ሱንዲያታ ከይታ ማሊ መንግሥትን ለማወሐድ የ'አፈ ቃል' ሕገ መንግሥት አወጡ። ይህ ሕግ 'ኩሩካን ፉጋ' ተብሎ ነበር።

በ1240 አካባቢ በግብጽ አገር ቅብጡ አቡል ፋዳዒል እብን አል-አሣል ፍትሐ ነገሥት በአረብኛ ጻፉ። እብን አል-አሣል ሕጎቹን የወሰዱት በከፊል ከሃዋርያት ጽህፈቶችና ከሕገ ሙሴ፤ በከፊልም ከድሮ ቢዛንታይን ነገስታት ሕጎች ነበር። መጽሐፉ በግዕዝ ተተርጉሞ ወደ ኢትዮጵያ የገባበት ወቅት በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመን በ1450 አከባቢ እንደነበር የሚል ታሪካዊ መዝገብ አለ።  ቢሆንም መጀመርያ እንደ ሕገ ምንግሥት መጠቀሙን የተመዘገበው በዓፄ ሠርፀ ድንግል ዘመን (ከ1555 ጀምሮ) ነው። ፍትሐ ነገስት እስከ 1923 ዓ.ም. የብሄሩን ዋና ሕግ ሆኖ ቆየ።

በ1904 ዓ.ም. ዐጼ 2 ምኒልክ የዘመናዊ ሕገ መንግሥት ፅንሰ ሀሳብ ተረድተው በጸሀፊው መምሬ ብስራት አንድ ሕገ መንግሥት የሚመስል ሰነድ ታተመ፤ ይህ ግን በውነት ሕገ መንግሥት አይባልም። «በምኒሊክ ስለተቋቋሙት ሚኒስቴሮች በምሳሌ የቀረበ ጽሑፍ» በምሳሌና በትርጓሜ የእያንዳንዱን ሚኒስቴር ሥራ እንደ ሰውነት አካላት አስመሰለ። ለምሳሌ፦

የሚመስል ቋንቋ በውስጡ አለበት።

ኢትዮጵያ መጀመርያ ዘመናዊ ሕገ መንግሥት የተቀበለችው በ1923 አመተ ምኅረት በአጼ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የታወጀ ሲሆን የሕግ አማካሪ ቤቶች በሁለት ያስከፈለ ነው።  ይህ የመንግሥታቸው ዋና መሠረት ሆኖ እስከ 1948 አ.ም. አገለገለ፤ በዚያ አመት ተሻሽሎ በወጣ ሕገ መንግሥት ሕዝቦች በመንግሥት ሥራ የሚጫወቱት ሚና እንደገና ተስፋፋ።  ይህ ብቻ የአገሪቱ ሕገ መንግሥት ሆኖ እስከ 1967 አ.ም. ቆየ፤ የዛኔ በደርግ በግፍ (በሕገ መንግስት እራሱ ባልሆነ ሂደት) ተሰረዘ።




#Article 34: ኤርትራ (4516 words)


ኤርትራ በምስራቅ አፍሪካ ከሚገኙ አገሮች አንዷ ስትሆን: በስሜን-ምዕራብ ከሱዳን፣ በሰሜን-ምስራቅ ከቀይ ባህር፣ በደቡብ ከኢትዮጵያ፣ በደቡብ-ምስራቅ ጅቡቲ ጋር ድንበር ትካለላለች። ኤርትራ የሚለው ስም ከላቲኑ «Mare Eritreum» የተወሰደ እና ስረ-መሰረቱ የግሪኩ Ἐρυθρὰ θάλαττα ሐረግ ሲሆን ትርጉሙም ቀይ ማለት ነው። ይህን ስም ለአካባቢው የሰጡት ጣሊያኖች በጥር ፲፰፻፺ ቅኝ ግዛታቸውን ሲያውጁ ነበር (ተመሳሳይ ስም በጀርመኖች 1870 እና ግብጾች ፲፰፻፷ወቹ በጥቅም ላይ ውለዋል፣ ነገር ግን የትኛውን ክፍል ስሙ እንደሚመለከት ግልጽ አልነበረም)። ኤርትራ፣ እንደ ሐገር፣ በጣሊያኖች ከተመሰረተች በኋላ በ5 ልዩ ሂደቶች ውስጥ በማለፍ ነው ያሁኑን ቁመናዋን የያዘችው። ከ1890 በፊት የነበረው የአካባቢው ታሪክ በ«ኤርትራ» ስር የሚጠና ባህይሆንም ስለአዲሱ ኤርትራ ግንዛቤ ስለሚያስጨብጥ ታሪክ ተመራማሪዎች ከ፲፰፻፺ በፊት ያለውንም ታሪክ ማጥናት ተገቢ እንደሆነ ይስማማሉ።

በ1860ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ፣ የግብጹ መሪ ኢስማኤል ከዴቭ ፓሻ በናይል ተፋሰስ ላይ ሰፊ የግብጽ ቅኝ ግዛት ለማበጀት ተነሳ። ለዚህ አዲሱ ግዛቱ ካርቱምን ዋና ከተማው በማድረግ የሱዳን ግዛቱን አጸና። ቀጥሎም የቀይ ባህርን ጠረፎች በ1865 ከተቆጣጠረ በኋላ በ1870ዎቹ መጀመሪያ ሐረርንና ተሻግሮ ሕንድ ውቅያኖስ ውስጥ ግዛቶችን አበጀ። እንግዲህ በኒህ ግዛቶቹና በሱዳን መካከል የነበረው ብቸኛ መገናኛ መንገድ ካርቱም-ከሰላ- ከረን -ምፅዋ ብሎ የሚዘልቅ ነበር። ስለሆነም በ1872 ይህን ስልታዊ መንገድ የክዴቭ ፓሻ ሰራዊቶች ተቆጣጠሩ። 

መቆጣጠር ብቻ አይደለም በየመንገዱ ምሽግ እየሰሩና የአውሮጳ ምስዮናውያንን እርሻ ቦታ እየሰጡ ቅኝ ግዛት አበጁ። በዚህ ሳይቆጠቡ፣ የመንገዱን ደህንነት ዋስትና ለማስጠበቅ ሲሉ የአካባቢውን ደጋማ ክፍል መያዝ ግድ አላቸው። ደጋማው ክፍል በዚህ ወቅት በአጼ ዮሐንስ ግዛት ስር ነበር። 

ግብጾቹ አካባቢውን ለቅኝ ግዛታቸው ብለው አንድ ከማድረጋቸው በፊት በዚህ መልክዓ ምድር ሦስት እራሳቸውን የቻሉ ማዕከላት በታሪክ ይጠቀሳሉ። ታሪክ አጥኝው ካህሳይ ብርሐኔ እኒህን ሦስት ማዕከላት የጋራ ታሪክ የሌላቸው፣ ኢ-ጥገኛ ህዝቦች ይላቸዋል።

የመጀመሪያው ማዕከል በምዕራብ ቆላማ ክፍል የሚገኘው ሲሆን፣ ከመልክዓምድር አንጻር ከከሰላ እስከ ቦጎስ ያለውን ቦታ ያካልላል። በተለምዶ ባርካ የሚባለው ነው። ይህ ክፍል ትግረ ቋንቋ በሚናገሩ የቤኒ አሚር ጎሳዎች የሚመራ ቢሆንም በውስጡ ሌሎች ብሔሮችን አጠቃሎ ይዟል። አካባቢው ከደጋው የአሁኑ ኤርትራ ክፍል ይበልጥ ከሱዳኖች ጋር የበለጠ ጥብቅ ትሥሥር ነበርው። ለዚህ ምክንያቱ በ1820ዎቹ ሚርጋኒያን የእስልምና እምነትን ለቤኒ አሚሮች በመስበክ ስላስፋፉ ነበር። ሚርጋኒያ ወየም የሚርጋኒያ ቤተሰቦች ከሰላ ውስጥ ሃትሚያ በተባለ የሱፊ እስልምና ማዕከል ውስጥ ከፍተኛ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ የአንድ ቤተሰብ ሰወች ነበሩ። 

ሁለተኛው ማዕከል ከምዕራቡ ክፍል በቋንቋም ሆነ በብሔር በጣም የተለየ ነው፣ የሚገኘውም በስተምስራቅ፣ በቀይ ባሕር ጠረፍ አካባቢ ነው። መጀመሪያ ደረጃ፣ ይህ የጠረፍ አካባቢ በስመ አዱሊስ የአክሱም ዋና ግዛት ነበር። ሆኖም ከ8ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ አካባቢው በእስልምና ምህዋር ስር በመውደቁ (የዳህላክ ሡልጣኔት፣ ለምሳሌ)፣ ከመካከለኛው የኢትዮጵያ ግዛት አፈነገጠ። ምንም እንኳ የኢትዮጵያ ነገሥታት (ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ ለምሳሌ) አልፎ አልፎ አካባቢውን በማስመለስ በባሕር ምድር ስም የባሕረ ነጋሽ ግዛት አድርገው ቢያስተዳድሩትም ከ8ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የያዘውን መልክ ሊቀይር አልቻለም ። የዚህ አካባቢ ዋና ማዕከል ምፅዋ የነበረ ሲሆን በምጽዋ አረቦች ቤታቸውን ሰርተው የእስልምና ማዕከል አድርገውት ነበር። ይህን የእስልምና ማንነት በሚያፀና መልኩ ኦቶማን ቱርኮች ምጽዋን ከ1557 እስከ 1578 ባደረጉት ዘመቻ ተቆጣጥረው የቀይባሕር እስላማዊ ቅኝ ግዛታቸው አካል አደረጉት። በአካባቢው በረሃወች የሚኖሩት አፋሮች የእስልምናን ስርዓት መያዝ የጀመሩት በዚሁ ዘመን፣ በ16ኛው ክፍለ ዘመን ነበር።

ሦስተኛው ማዕከል በሁለቱ መሃል የሚገኘው ተራራማው የሐማሴን፣ ሰራየ እና አካለ ጉዛይ ግዛት ሲሆን በዚህ ቦታ ትግርኛ ተናጋሪ ክርስቲያኖች ይገኙበታል። በተለምዶ መረብ ምላሽ የሚባለው ነው። ይህ ክፍል ከጥንት ጀምሮ የኢትዮጵያ ዋና ክፍል የነበረ ነው። በአክሱም ዘመነ መንግስት የግዛቱ አይነተኛ ክፍል፣ እንዲሁም የሥርዓተ ገዳምና የክርስትና ዋና ማዕከል ነበር። ከአክሱም በኋላም ባሕር ምድር ተብሎ የሚታወቀው ግዛት ዋና እምብርት ነበር። ክፍሉ በኢትዮጵያ ከሚገኘው ሌላው የትግርኛ ተናጋሪ ጋር ካለው ቁርኝት አንጻር የሚለየው የነበር በሁለቱ ክፍሎች መካከል በሚጓዘው መረብ ወንዝ ነበር። ስለሆነም መረብ ምላሽ ተብሎ ይታወቅ ነበር። እንደማንኛው ሌላው የኢትዮጵያ ክፍል፣ የዚህ አካባቢ ታሪክ የሚያጠነጥነው ከመካከለኛው የኢትዮጵያ መንግስት ጋር በነበረው ግንኙነት ዙሪያ ነበር። የመረብ ምላሽ ዋና ክፍል ሐማሴን ሲሆን ይህ ክፍል ለዘመናት ይተዳደር የነበረው በሁለት ተፎካካሪ ቤተሰቦች ነበር፡ እነርሱም ሓዛጋ እና ሳዛጋ በመባል ይታወቃሉ። ይህ ክፍል አንድ አንድ ዘመቻወችን ወደ ቆላው ቢያደርግም፣ አልፎ አልፎም ከውጭ ሃይሎች እርዳታ ቢያገኝም፣ በአጠቃላይ ግን የአስተዳደሩ ስርዓት ሙሉ በሙሉ ኢትዮጵያዊ ባህልንና ትውፊትን የተከተለ ነበር።

ይህ በዚህ እንዳለ ነበር ግብጾች (ክዴቭ ፓሻ) እኒህን ሶስት ክፍሎች አንድ በማድረግ ከኢትዮጵያ ለይተው ለመግዛት የሞከሩት። ከላይ እንደተጠቀሰው ግብጾች ከከሰላ ምጽዋ የሚዘልቀውን መንገድ ቅኝ አድርገው ነበር ሆኖም ግን ለጸጥታ ሲሉ የደጋውን ክርስቲያን ክፍል ለመቆጣጠር ሞክሩ። በዚህ ምክንያት ከኢትዮጵያ ጋር ጦርነት ገቡ። በኖቬምበር 16፣ 1875 ላይ የአጼ ዮሐንስን ሰራዊት ጉንደት በተባለ ቦታ ገጥመው ተሸነፉ። ማርች 1-9፣ 1876 ላይ እንደገና ጉራ በተባለ ቦታ ገጥመው ከፍተኛ ሽንፈት ገጠማቸው። ይህን አይነት ክስረት ከገጠማቸው በኋላ ደጋውን ክፍል ትተው ድሮ በነበሩበት ምጽዋ-ከሰላ፣ በተለይ ቦጎስ ፣ መንገድ ላይ ተወሰነው በኢትዮጵያውያን ላይ የደፈጣ ውጊያ ማድረግ ቀጠሉ። ጠንክረው ለመከላከል ሲሉ፣ አጼ ዮሐንስ መረብ ምላሽን ለመያዝ አሰቡ፤ ስለሆነም በ1876 ዓ.ም. ራስ አሉላ እንግዳን የመረብ ምላሽ ገዥ አድርገው ሰየሟቸው። ራስ አሉላ በአገሬው ሰው እንደ ጸጉረ ልውጥ ተደርገው በመቆጠራቸው ነገሩ ቅሬታን ፈጠረ። ስለሆነም የመረብ ምላሽ የቀደመ ገዥ የነበሩት ራስ ወልደሚካኤል በግብጾች እርዳታ ሐማሴንን ለተወሰነ ጊዜ መቆጣጠር ችለው ነበር። ራስ ወልደሚካኤል በ1879 ተማርከው ለእስር ተዳረጉ። ነገሮች እንዲህ ከተደላደሉ በኋላ ራስ አሉላ በግብጾች ምሽጎች ላይ አልፎ አልፎ ዘመቻ በማድረግ ጥቃት ማድረስ ጀመሩ። በመካለሉ ማሃዲ ሱዳኖች በግብጾች ላይ በመነሳታቸው ግብጾች ከሁለት ጎን አጣብቂኝ ውስጥ ገቡ። ከአጣብቂኙ ለመገላገልና ከአካባቢው በሰላም ለመውጣት ሲሉ ግብጾቹ በ1884 ከአሉላ ጋር የሄዌት ስምምነት የተባለውን ውል ተፈራረሙ። 

ብዙም ሳይቆይ፣ ከአመት በኋላ፣ ታኅሣሥ 1885 ላይ ጣሊያኖች ምፅዋ ላይ መልህቃቸውን ጥለው ወደ መሃል መስፋፋታቸውን ጀመሩ። መስከረም 1885 ላይ አሉላና የሱዳን መሃዲስቶች ኩፊት በተባለ ቦታ ተገናኝተው ራስ አሉላ ጦርነቱን በድል ቢደመድሙም ከሰላን ለመቆጣጠር የነበራቸው እቅድ በጣሊያኖች ወደ ምጽዋ ዘልቆ መግባት ተዘናጋ። ፊታቸውን ከምዕራቡ ግንባር በመመለስ፣ ራስ አሉላ፣ ጣሊያኖችን በዶገሊ (1887) ጦርነት እንዲሁም በኮዓቲት(1888) ጦርነት ድል አደርጓቸው። ይሁንና የጣሊያኖች መስፋፋት ሊገታ አልቻለም። ለዚህ ምክንያቱ በምዕራብ የመሃዲስቶች ጦርነትና እንዲሁም የጣሊያኖች በሃይል መጠናከር ነበር። በኒህ ድርብ ጫናዎች ምክንያት 1888 ላይ የኢትዮጵያ ሠራዊት አፈግፍጎ መረብ ወንዝን ተሻገረ። 1889 ዓ.ም. ያለመንም ጦርነት የጣሊያን ሰራዊት አስመራ ገባ።

እንግዲህ በዚህ ዘመን የተፈጠረው የምዕራብ ኤርትራ(ባርካ)፣ የምጽዋዕ እስላሞች፣ የሱዳንና የግብጽ ግንኙነት ነበር በኋላ በ1950ወቹ ለተነሳው የኤርትራ ነጻነት ግንባር ጀብሃ የሚለውን አላማ መሰረት የሆነው። የኤርትራ ህዝቦች ነጻነት ግንባርም የአሉላን ጸጉረ ልውጥነትና በህዝቡ ዘንድ ያስነሳውን ማንጎራጎር እንደ-የመረብ ምላሽ ህዝብ ነጻነት ጥያቄ መነሻ አድርጎ ይወስደዋል። ይህ የታሪክ ክፍል የቱን ያክል ለ20ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያና የኤርትራ ታሪክ ሚና እንደነበረው ለመገንዘብ አዳጋች አይደለም።

የጣሊያን መንግስት በደቡብ ምዕራብ ቀይ ባህር ጠረፍ ላይ ከአንድ የመርክብ ኩባንያ ቦታዎችን በመግዛት በመሬቱ ላይ የሕጋዊ ይገባኛልን አጸና። እንዲሁም ከአካባቢው መሪዎች ጋር ውል በመፈራረም አሰብንና ቅርብ ደሴቶቿን ሐምሌ 1882 ቅኝ ግዛቶቹ እንደሆኑ አወጀ። ይህ እንግዴህ ኮሎኒያ አሰብ የሚባለው ነው። ከሶስት አመት በኋላ፣ የካቲት 1885 በእንግሊዞች መልካም ፈቃድ ምፅዋን ከግብጾች በመንጠቅ ተቆጣጠረ። ቀጥሎም ከጎጥ መሪዎች ጋር ውሎች በመፈራረም ሰምሐር እና ሳህል የሚባሉትን የሰሜን ምዕራብ ክፍሎች በሰላማዊ መንገድ ወደ ግዛታቸው ጠቀለሉ። ወደ ደቡብ ግን በጦርነትና ክፋፍሎ ማሸነፍ በሚለው የቅኝ ግዛት መንገድ መስፋፋት ጀመሩ። የመሃዲስቶችን፣ ኢትዮጵያውያንና በኢትዮጵያውን መካከል ያለውን ፉክክር በመጠቀም ሐማሴንን፣ ሰራየንና አካለ ጉዛይን ገንዘባቸው አደረጉ። ዳግማዊ አጼ ምንሊክ የአጼ ዮሐንስ ተተኪ ንጉስ እንዲሆኑ በመርዳት በቀይ ባህር ጠረፍ ላይ ያላቸውን ግዛት ህጋዊነት እንዲቀበሉ አደረጉ (የውጫሌ ውል)። የውጫሌን ውል፣ አንቀጽ 3፣ የጣሊያኖችን ግዛት በምስራቃዊው ጠለል ላይ የወሰነ ቢሆንም እነርሱ ግን ውሉን በመጣስ ግዛታቸውን እስከ መረብ ወንዝ ድረስ አስፋፉ። 1890 ላይ ይህን ግዛታቸውን ኤሪትራ ብለው ሰየሙት። 

ኤርትራን ካወጁ በኋላ ጣሊያኖች በ3ኛው አመት ህዝብ ቆጠራ አደረጉ። በዚህ ወቅት የህዝቡ ብዛት 191፣127 እንደሆነ ሊታወቅ ቻለ። በዘመኑ ከአርሶ አደሩ ክርስቲያን ደገኛ ትግርኛ ተናጋሪዎች በተጨማሪ በምዕራብ፣ ዘላን መስሊሞች ፡ ቤኒ አሚር፣ ብሌን፣ ሐባብ፣ መንሳ እና ማርያ እንዲሁም ዘላንና አርሶ አደር የሆኑት ኩናማና ናራ የተሰኙ ብሔሮች እንደሚኖሩ ታወቀ። በምስራቅና በደቡብ የባህር ጠረፎች ደግሞ አፋርና ሳሆ የተሰኙ አርብቶ አደሮች እንደሚኖሩበት ተመዘገበ።

ጣሊያኖች የግዛታቸውን ማዕከል ምፅዋ ላይ በማድርገ የቢሮክራሲ ስርዓት ዘርግተው በራሱ ላይ ወታደራዊ ገዥወች ሾሙበት። ቆይተውም ከአገሬው ወሰደው 300+ሺህ ሄክታር የሚሆነውን መሬት ለአውሮጳውያን ገበሬዎች ለመስጠት ያሰቡት እቅድ ከህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ ደርሶበት ተቋረጠ። ሚያዚያ 1894 በደጃዝማች ባህታ ሐጎስ የተነሳው አመጽ ጣሊያኖች ወደ ኢትዮጵያ፣ ትግራይ የማጥቃት ጦርነት እንዲከፍቱ አደረገ። ነገር ግን በዳግማዊ ምኒልክ የተመራው የኢትዮጵያ ሰራዊት ጣሊያኖችን በተደጋጋሚ ድል አደረጋቸው (አምባላጌ-ታህሳስ 1895፣ አድዋ - መጋቢት 1896)። በኒህ ጦርነቶች ጣሊያኖች ወደ 10፣000 ወታደሮችና 500 ሚሊዮን ሊሬ በመክሰራቸው ከዚህ በኋላ ለቅኝ ግዛታቸው የሚያወጡትን ወጭ ቀነሱ።በዚህ ጦርነት የማይረሳው ብዙ ወታደሮችም ተማርኳል የጣልያን ምርኮኛችን በካሳ እንዲለቀቁ ተስማምቷል ለኤርትራውያን የጣልያን ወታደሮች ግን ኣንድ እግራቸው እና ኣንድ እጃቸውን በመቁረጥ እንዲለቀቁ ተደርጓል የማይረሳው የኢትዮጵያ ጥቁር ታሪክ የነበረውን ጸብ ከዚህ ይጀምራል፣ከዚያ ወዲህ ጣልያኖች ከኢትዮጵያ ጋር መልካም ጉርብትና ፈለጉ እንጂ በቀደመው አጥቂነታቸው ለመቀጠል አልፈለጉም።

ከአድዋ ሽንፈት በኋላ ጣሊያኖች ከኢትዮጵያ ጋር ተፈራርመው አዲስ ገዢ፣ ፈርዲናንዶ ማርቲኒ፣ 1897 ላይ በመሾም ግዛታቸውን ማጽናት ጀመሩ። በዚህ ወቅት የቀደመው ወታደራዊ ስርዓት እንዲቋረጥ ተደርጎ አገሪቱ የብሔር ልዩነትን በሚያከበር አስተዳደር ተከፍሎ እንዲቋቋም ተደረገ። ዳህላክ፣ አፋር እና ሰምሃር አንድ ላይ ምስራቃዊ ክፍል ተብለው ከምጽዋ እንዲተዳደሩ ተደረገ። ምዕራባዊ ክፍል ከአቆርዳት እንዲተዳደር ሲደረግ ቤኒ አሚርን፣ ናራንና ኩናማ ምድርን ያጠቃልል ነበር። ከከረን ሆኖ የሚተዳደረው ደግሞ ሰሜናዊ ሐማሴን (የእስልምና ተከታይ የሆነ)፣ ቤት አሰገደና ዓድ ሼኽ ነበሩ። ቀሪው ሐማሴን ከአስመራ፣ ሰራየ ከመንደፈራ(አዲ ወግሪ) እንዲተዳደር ሲደረግ አካለ ጉዛይ ከሳሆ ጋር ተዋህዶ ከአዲ ቀይሕ ይገዛ ጀመር። ከላይ ወደታች በተዘርጋ መዋቅር የጣሊያን ባለስልጣኖች እያንዳንዱን ክፍል ያስተዳድሩ ጀመር። የአገሪቱ ዋና ከተማ ከምጽዋ ወደ አስመራ የተዛወረው በዚህ ወቅት፣ በ1898 ነበር። 

ከ1898 እስከ 1908 በተደረጉ ውሎች (ከኢትዮጵያ፣ ከአንግሎ-ግብጻዊ ሱዳንና ከጅቡቲ ጋር) መሰረት የቅኝ ግዛቱ ድንበር ታወቀ። ኢትዮጵያን ስለ ድንበሩ ለማሳመን 3 አመትና 5ሚሊዮን ሊሬ ፈጅቶባቸው ግንቦት 1900 ላይ ያሰቡት ሊሳካላቸው ቻለ። ድንበሩ ከሞላ ጎደል የመረብ፣ በለሳና ሙና ወንዞችን የታከከ ነበር። 

በ1898 ጣሊያኖች ለቅኝ ግዛታቸው አዲስ ደንብ አወጡ። ድሮ ይጠቀሙበትን የነበረውን የአገሬውን ባላባት በጭካኔ የመቅጣት መንገድ በመተው፣ ከነሱ ጋር የተሻረከውን የመሸለምና በነሱ ስር እንዲሰራ የማድረግ ዘዴን ጀመሩ። ከሕግም አንጻር የጣሊያን ሕግ ለጣሊያን ገዥወች የሚሰራ ቢሆንም የአካባቢው ሕግ ( ለምሳሌ የሙስሊሞች ሕግ) ለአካባቢው ሕዝብ እንዲሰራ አደረጉ። ከላይ ጣሊያኖች የሁሉ ገዢወች ሲሆኑ ከስር የአካባቢውን መሪወች ቀጥረው እንዲያስተዳድሩ አደረጉ። የአካባቢው ገዥወች ግብር በመሰብሰብ፣ ሕግ በማስከበርና ፍርድ በመስጠት ያገለግሉ ነበር። ይህ የአገሩን መሬት በአገሩ በሬ ዘዲያቸው የተሳካ ከመሆኑ የተነሳ በዚህ ወቅት አገሬው በአመጽ እንዳይነሳ እረድቷል፣ ቢነሳም በጣም በአናሳ ሁኔታ አልፎ አልፎ ነበር (ለምሳሌ ደጃዝማች አበራ ግዛው፣ ሙሃሙድ ኑሪና ገብረመድህን ሐጎስ ወደ ኢትዮጵያ እንዲሸሹ የተገደዱ)። ጣሊያኖቹ በዚህ ዘመን ትግርኛ ከማይናገረው ክፍል ከፍተኛ ድጋፍን አገኙ፣ ለዚህም ምክንያቱ ሕግና ሥርዓት ባሉት መመሪያቸው መሰረተ ከደጋው ወደነዚህ ክፍሎች የሚመጣውን ዘመቻ በማስቆማቸው ነበር። በወቅቱ የጣሊያኖች ዋና አላማ ፖለቲካዊ መረጋጋት ስለነበር የትግርኛ ተናጋሪውን ክፍል በአመጽ እንዳይነሳ ብዙ ስራ ሰርተዋል። ስለሆነም የትግርኛውን ክፍሎች ማህበረሰባዊ ትሥሥር ለመቆራረጥ ብዙ ሙከራወችን አድርገዋል። የካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ለተግባራቸው እንዲረዳቸው በእጅጉ ሞክረዋል። ነገር ግን ይህ ሙከራቸው ብዙ ፍሬ አላፈራም። ጣሊያኖቹ የእስላምና ተከታዩን ክፍል ድጋፍ ለማግኘት ሲሉ የእስልምና ሃይማኖትን መስፋፋት በሰፊው ይደግፉ ስለነበር። በዚህ ምክንያት የኦርቶዶክስ ተከታዩ ክፍል የካቶሊክ ቤተከርስቲያንን በመጥፎ አይን በመመልከት የትግርኛ ተናጋሪውን ህዝብ ወደ ካቶሊክ ሃይማኖት የመግባት ፍላጎት እጅግ አነስተኛ ሆነ። እንዲያውም የኦርቶዶክሱ ቤተክርስቲያን ከኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጋር በነበረው ጥብቅ ግንኙነት ምክንያት ከ1920ወቹ ጀምሮ ለቅኝ ገዥወቹ ከፍተኛ ተቃውሞ ይመጣ የነንበረው ከኒሁ አብያተ ክርስቲያናት ሆነ። 

አብላጫው የትምህርት ስራ በካቶሊክና በፕሮቴስታንት ሚስዮናውያን የሚሰራ ነበር። በመጀመሪያ፣ የአገሬው ህዝብ ዕውቀት አድማሱ እንዳይሰፋ በማሰብ እንዳይማር በህግ ተከልክሎ ነበር ። ነገር ግን ለቅኝ ግዛቱ ተላላኪዎች ለመፍጠር በማስብ አገሬው አንስተኛ የኢለመንታሪ ትምህርት እንዲማር ተፈቀደ፣ ይሄውም የሆነው በ1911 ነበር።ከ 1ኛ ክፍል እስከ 4ኛ ክፍል ነበረ፣ ጣሊያኖቹ በተጨማሪ በአስቀመጧቸው የተለያዩ መሰናክሎች ምክንያት አቅማቸው ለትምህርት ከደረሱ የአገሬው ሰዎች መካከል ከላይ የተጠቀሰውን ትምህርት ያገኙት ከ2% አይበልጡም ነበር። ቅኝ ግዛቱ፣ ኤርትራዊ ምሁር እንዳይኖር ማድረጉ የማይካድ ሃቅ ነው።

በኤርትራ ኗሪ የሆኑ ጣሊያኖች ቁጥር ቀስ በቀስ እያደገ ሄዶ 1934ዓ.ም. ላይ 4፣500 ደርሶ ነበር። በሚቀጥሉት 5 አመታት ከፍተኛ እድገትን በማሳየት፣ 1939ዓ.ም. ላይ ቁጥራቸው 75፣000 ደርሶ ነበር። ከሰፋሪ ጣሊያኖቹ ውስጥ የፋብሪካ ባለቤቶችና ገበሬዎች ቢገኙበትም አብዛኞቹ ግን መኖሪያቸውን ያደረጉት በአስመራና ምጽዋ ነበር። በ1930ወቹ መጨረሻ ላይ አንድ-አምስተኛ (20%) የሚሆኑት የአገሬው ሰዎች በከተማ ይኖሩ ነበር። በአንስተኛ ደመዎዝ እየሰሩ፣ ለአገሬው በተዘጋጁ የከተማ ክፍሎች ተወስነውና የፖለቲካ አቅም እንዳይኖራቸው የጣሊያን ዜግነት ተነፍጓቸው ይኖሩ ነበር። 

ምንም እንኳ በቅኝ ግዛት ስርዓት መሰረት አገሬውና ገዥዎቹ እኩል ባይታዩም እስከ ፋሽዝም መነሳት ድረስ የአገሬው ህዝብና ጣሊያኖቹ ከሞላ ጎደል የመደባለቅ ሁኔታ አሳይተዋል። ነገር ግን በ1930ዎቹ መጨረሻ ላይ አይን ያወጣ የአፓርታይድ ዘረኝነት ተጀመረ። በኤውሮጳውያንና በአገሬው ህዝብ መካከል ማንኛውም አይነት ጋብቻም ሆነ አብሮ መኖር በህግ ተከለከለ። 1940 ላይ የጣሊያንና አገሬው ክልሶች ሳይቀሩ የዜግነትና የትምህርት መብታቸውን በህግ አጡ።

ከ1936 ጀምሮ ኤርትራ የኢኮኖሚ እድገት ማሳየት ችሏል። በ30ዎቹ መጨረሻ 2፣198 የኢንደስትሪ ተቋሞች በአገሪቱ ተመስርተዋል። ይሁንና ጣሊያኖች አገሪቱ እራሷን እንድትችል ሳይሆን የነርሱ ጥገኛ እንድትሆን ነበር ያደረጉት፣ ለዚህ ሲሉ አብዛኛው ምርት ከውጭ ያስመጡ ነበር። ከ10-15% የሚሆነው የአገሬው ወንድ ሃይል በኢንደስትሪ፣ በእርሻና በጥቃቅን የተላላኪ ስራወች ተቀጥርው ይሰሩ ነበር። ከ1936-41 ድረስ አብዛኛውን የአግሬውን ወንድ ቀጥሮ ያሰራ የነበረው የቅኝ ገዥው ውትድርና ተቋም ነበር (40% ወይም 60፣000 ለአቅመ አዳም የደርሱ ወንዶችን)። 

እኒህ ወታደሮች ኢትዮጵያን ለመውረር ያገለገሉ ሲሆን ለዚህ ታማኝነታቸው ምክንያቱ ቅኝ ገዥወች በኤርትራ ላይ ያሰፈኑት ፖለቲካዊ መረጋጋት እንደምክንያት ይጠቀሳል። የጤና፣ የገበያ ኢኮኖሚ እንዲሁም ቁሳዊ ፍጆታ መስፋፋት በ1905ዓ.ም. 250 ሺህ ብቻ የነበረው የኤርትራ ህዝብ ወደ 614 ሺሕ በ1935 ዓ.ም. እንዲያድግ አድርጓል። ትግርኛ ተናጋሪው ክፍል በዚህ ጊዜ 54% የአገሪቱ ክፍል ነበር። እኒህ ለውጦች በአገሬው ላይ የስነ ልቦና ለውጥን አስከተሉ፣ ስለሆነም ከኢትዮጵያውያን ጐረቤቶቻቸው የተለዩ ህዝቦች የመሆን ማንነትን ፈጠረ።

ሁለተኛው የአለም ጦርነትን ተከትሎ እንግሊዞች ከአንግሎ ግብጻዊ ሱዳን በመነሳት ጥር 1941 በኤርትራ ላይ ጥቃት አደረሱ። ከሶስት ወር በኋላ የከረን ጦርነትን በማሸነፍ ሚያዝያ 1941 ሙሉ ኤርትራን ተቆጣጠሩ። የእንግሊዝ ወታደራዊ አገዛዝ(BMA) በጣሊያኖች ምትክ አገሪቱን ማስተዳደር ጀመረ። 1947 ጣሊያን በፈረመችው የሰላም ውል መሰረት ኤርትራ ለአራቱ ሃይላት ተሰጠች። ከዚህ በኋላ ኤርትራ የጣሊያን ቅኝ መሆኗ አበቃላት። 

እንግሊዞች የመጀመሪያ አላማቸው ሕግና ስርዓትን ማጽናት እንዲሁም አገሪቱን ማረጋጋት ነበር። ለዚህ ሲሉ ጣሊያኖች ሲሰሩበት የነበረውን ስርዓት ብዙ ሳይቀይሩ ነበር መግዛት የጀመሩት። በ'44 እና '47 መካከል የኤርትራን ግዛቶች በብሔር ከ5 ከፍለው እንደገና አዋቀሩት። ይህ አዲሱ አወቃቀር ከጣሊያኖቹ እምብዛም አይለም ሆኖም ግን ከረንንና አቆርዳትን አንድ በማድረግ ምዕራባዊ ግዛት ስያሜ ሰጥተው አዲስ ክፍል አድርገዋል፣ ምፅዋንና አሰብን በማዋሃድ የቀይ ባሕር ክፍል ብለው ሰይመዋል፡

እንግሊዞች ከነበረባቸው የሰው ሃይል ማነስ የተነሳ የጣሊያን ተቀጣሪወችን ሳይቀር የቀደሙትን የአገሬውን ባለስልጣኖች ሳያባርሩ ነበር ግዛታቸውን የጀመሩት። የጣሊያኖችም ህጎች በነበሩበት እንዲጸኑ ተደርገዋል። ሆኖም ግን የአፓርታይድ ስርዓቱን አስቀርተው አገሬው የጤናና የትምህርት፣ የመናገር ነጻነትና የስራ እድል ተቋዳሽ እንዲሆን አድርገዋል። የትምህርት ቤቶች ቁጥር 100 ሲደርስ በዚህ ወቅት ትምህርት በትግርኛእና አረብኛ ይሰጥ ነበር። የሁለተኛው የአለም ጦርነት ካስነሳው የኢኮኖሚ ፍላጎት አንጻር ኤርትራ የእርሻና የኢንደስትሪ ምርቷ በክፍተኛ ደረጃ አደገ። እንግሊዞቹ ወደ 256 ሺህ ሄክታር መሬት በመቆጣጠር 59ሺህ ቶን የሰብል ምርት ለመሰብሰብ ቻሉ። ኢኮኖሚው በዚህ መንገድ ከማደጉ የተነሳ ኤርትራ እርሷን የቻለች ሆነች። የተማሩ ጣሊያኖችና ወዝ አደር የአገሬው ሰወች በእንግሊዞች እየተቀጠሩ ይሰሩ ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜ የአገሬው ህዝብ የንግድ ማህበር እንዲያቋቁሙ የተፈቀደው በዚህ ጊዜ ነበር።

በጦርነቱ ወቅት ኢኮኖሚው ይደግ እንጂ፣ እንግሊዞቹ የበለጠ ትርፍ ለማግኘት ሲሉ ጣሊያኖች የዘረጉትን አብዛኛውን ኢንደስትሪና ኢንፍራስትራክቸር በመነቃቀል ሸጡ። ከአለም ጦርነት በኋላ የኢኮኖሚክ ፍላጎት ማንስ ባስነሳው ሁኔታ የኤርትራ ኢኮኖሚያዊ እድገት ተጨናገፈ። የእግንሊዙ ወታደራዊ አስተዳደር ያስቀመጠው የብድር፣ የላይሰንስ፣ የውጭ ገንዝበና የምርት ገደብ ለአገሪቱ ኢኮኖሚ መጨናገፍ ደጋፊ ነበር። የእርሻና የኢንደስትሪ ውጤቱም ከውጭ ካለው ፉክክር የማይከለከል ስለ ነበር ሌላው የኢኮኖሚው ቁስል ነበር። ይህ ሁሉ ተደማምሮ 1948ዓ.ም. ላይ የአገሪቱ ኢንደስትሪ እንዲዘጋና ወደ 10፣000 የሚጠጋ ኤርትራዊ ስራ አጥ እንዲሆን አደረገ። ኢኮኖሚያዊ ቀውሱና የዕቃወችን ውድነት ተከትሎ ብሔራዊነት ገኖ መውጣት ጀመረ። የአገሪቱ ኤኮኖሚና አስተዳደር በኤርትራውይን እንዲደረግ ጥያቄ መቅረብ ጀመረ። 

ከ1941 ጀምሮ ሁሉንም ኤርትራውያን ያሳተፈ ፀረ-ቅኝ ግዛት ማህበር -ማህበር ፍቅሪ ሐገር ተቋቁሞ ነበር። የዚህ ማህበር አላማ የህብረተሰቡን ፍላጎት ለእንግሊዞቹ ማስረዳት ነበር። ቀስ ብሎ ግን ከተማ ኗሪው ትግርኛ ተናጋሪ ክፍል ፅንፈኛ፣ ኢትዮጵያን የሚደግፍ አቋም መያዝና ማህበሩን መቆጣጠር ጀመረ። 1943 ላይ አብዛኞቹ እስልምና ተከታዮችና አንድ አንድ የደቡብና መሃከለኛ ደጋማ ክፍል ክርስቲያኖች ማህበሩን ለቀው የመለያየት እንቅስቃሴን ጀመሩ። 1946 ላይ የአንድነት ደጋፊወችና የሱዳን መከላከያ ሃይሎች (በእንግሊዞች ስር የነበሩ) አስመራ ውስጥ ደም ተፋሰሱ። ይህ ሁኔታ የፖለቲካ ውጥረትን ያስከተለና የጣሊያን ኗሪዎች በአንድነት ደጋፊዎች ከዚህ በኋላ ጥቃት እንዲደርስባቸው ያደረገ ነበር። ጥቅምት 1946 ላይ እንግሊዞች በፖለቲካ ፓርቲወች ላይ ያስቀመጡትን ዕቀባ አነሱ።

ከዚህ በተረፈ የኢትዮጵያ፣ ታላቋ ብሪታኒያና ጣሊያን የራስ-ፍላጎቶች የኤርትራን የወደፊት እድል ያወሳሰበ ጉዳይ ነበር። የታላቋ ብሪታንያ አቋም ኤርትራ እራሷን መቻል የማትችል አገር ስለሆነች ከሁለት ተከፍላ እስላሞች የሚኖሩበት ምዕራባዊው ክፍል ለሱዳን እንዲሰጥ፣ ክርስቲያን ትግርኛ ተናጋሪው ደጋ ክፍል ለኢትዮጵያ እንዲሆን ነበር። የጣሊያን ፍላጎት በተባበሩት መንግስታት ቡራኬ የኤርትራ ሞግዚት ሆና እንድታስተዳድረው፣ ያ ካልሆነ አገሪቱ ለብቻዋ እንድትሆን ነበር። የኢትዮጵያ አቋም፣ ከታሪክ፣ ከመልክዓምድር፣ ከብሔርና ከኢኮኖሚ አንጻር፣ እንዲሁም ከስትራቴጂክ ፍላጎት አንጻር፣ ማለት የባሕር በር እንዲኖራት አስፈላጊ መሆኑን በመግለጽ ኤርትራ የርሷ እንደሆነች ነበር። አጼ ሃይለ ሥላሴ በቅኝ ግዛት ወቅት የተወሰደውን መሬት ለኤርትራውያን አስመልሳለው ብለው ቃል ሲገቡ የኤርትራ ኦርቶዶክስ ቄሶች ሙሉ በሙሉ ደጋፊያቸው ሆኑ፣ በግልጽም የአንድነት ፓርቲ ደጋፊዎች ሆነው ይሰሩ ነበር።

ከ1947-48 የአራቱ ሃይሎች አጣሪ ኮሚሽን ወደ ኤርትራ ሄዶ የህዝቡን ልብ ትርታ ለማጥናት ያደረገው ሙከራ በኮሚሽነሮቹ መካከል ስምምነት ስላልፈጠረ እና የኢትዮጵያ ጣልቃ ገብነትም ለመለየቱ አስቸጋሪ ስለነበረ በ1948 ላይ ጉዳዩ ለአለም አቀፉ የተባበሩት መንግስታት መድረክ ቀረበ። እንግሊዞችና ጣሊያኖች የቤቭን ፎርዛ አቅድ የተባለውን ሰነድ ያዘጋጁት በዚህ ወቅት ነበር። በአቅዱ መሰረት ኤርትራ ከሦስት ስትከፈል ምዕራቡ እስላም ክፍል ለሱዳን፣ ደጋው ለኢትዮጵያ፣ ዓሰብና ምጽዋዕ ልዩ ግዛት እንዲሆኑ ነበር። ሆኖም ግንቦት 1949 ላይ የተካሄደው የተ.መ. ጉባኤ ሃሳቡን ውድቅ አደረገው።

ይህን ተከተሎ ኤርትራ ውስጥ ፖለቲካዊ ቀውስ ተነሳ። መስሊም ሊግ የለዘብተኛ ተራማጅ ፓርቲንና የጣሊያን ደጋፊ ፓርቲን ሃይሎች በማስተባበር ታላቅ የተገንጣይ ቡድን መሰረተ። ሆኖም ግን በአባሎቹ የሶሽዮ-ፖለቲካ መሰባጠር ምክንያት ሃይሉ የዳከመ ነበር። በዛ ላይ የጣሊያንን እንደገና መምጣት በመፍራትና የኢትዮጵያን ሙስሊሞችን ለማክበር ቃል መግባት በመከተል ብዙዎች ከኢትዮጵያ ጋር ይህ-ከሆነ ውህደት እንዲፈልጉ አደረገ። የኢኮኖሚው መንኮታኮትም በእስላሞችና ክርስቲያኖች መካካከል እንዲሁም በቋንቋ-ብሔሮች መካከል ውጥረት አስነሳ። መስሊም ሊግ ጭሰኝነትን አስወግዳለሁ በማለቱ የሙስሊም ባላባቶች ውህደትን እንዲደግፉ አደረገ።

ከብዙ ክርክርና የዲፕሎማሲ ፍትጊያ በኋላ፣ ታህሳስ 1950 ላይ የተ.መ. አጠቃላይ ጉባኤ Resolution 390 A(V) ላይ የእጅ ምርጫ በማድረግ አጸደቀ። በጸደቀው ድንጋጌ መሰረት ኤርትራ በፌዴሬሽን ከኢትዮጵያ ጋር እንድትቀጥል።ፌደረሽኑም የሁለቱም አገሮች እኩል መብት ኑሯቸው የፌደሬሽን ባንዴራ ኑሯቸው እንዲቀጥሉ ነበረ፤ the United States was instrumental in promoting Eritrea's linkage with Imperial Ethiopia, opposing the idea of an independent Eritrea, irrespective of the wishes of the Eritrean people. This was succinctly put by then US ambassador to the UN (later to become US Secretary of State) John Foster Dulles: From the point of view of justice, the opinions of the Eritrean people must receive consideration. Nevertheless the strategic interest of the United States in the Red Sea basin and the considerations of security and world peace make it necessary that the country has to be linked with our ally Ethiopia.ወደ አማርኛ ሲገለበጥ ፤የተ.መ የኤርትራን ፍላጎት ሳይሰማ ከኢትዮጵያ ጋር አቆራኛት፤የዚያን ጊዜ አምባሳደር ጆን ፎስተር ዳላስ በኋላ ዋና ጸሓፊ የሆኑት እንዳሉት «ከህግ አንጻር የኤርትራን ህዝብ ፍላጎት መሰማት ነበረበት ሆኖ ግን የኛ የተ.መ ስትራቴጂ በቀይባህር ያለንን አንጻር እና የአለም ሴኩሪቲን ለማስጠበቅ ከጓደኛችን ኢትዮጵያ እንድትቀላቀል አድርገናል» አሉ፤
When Ethiopia deposed its Emperor and became a communist state 1974–1991, the United States did not support the Eritrean rebels' struggle for independence from communist Ethiopia, but remained committed to Eritrea's linkage with Ethiopia, albeit under a different, more pro-western Ethiopian administration.ከሁለት አመት የሽግግር መንግስት በኋላ ፌዴሬሽኑ መስከረም 1952 ላይ ተግባር ላይ ዋለ።

የፌዴሬሽን አስተዳደር ለአካባቢው እንግዳ ስለነበር የተለያዩ ክፍሎች በተለያየ መልኩ እንዲተረጉሙት ሆነ። የኢትዮጵያ መንግስት ፌዴሬሽን ማለቱ ኤርትራን ወደ ኢትዮጵያ የሚያጠቃልል ነው ብሎ ተረጎመ። በኤርትራ በኩል፣ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ፌዴሬሽኑን ቢቀበሉም በአተረጓጎሙ ላይ ልዩነት አሳዩ። አንድነት አራማጆች ትርጉሙን ኢትዮጵያ በምታይበት አይን ሲመለከቱ በኢብራሂም ሱልጣን የሚመራው የኤርትራ ዲሞክራሲያዊ ግንባር የመገንጠል ደጋፊዎችን በማነሳሳት የኤርትራን ራስ ገዝነት አጉልቶ በሚያሳይ መልኩ ይተረጉሙ ነበር። 

በተ.መ. የፌዴሬሽኑ ድንጋጌ መሠረት የሁለቱን ክፍሎች ግንኙነት የሚያስተዳድሩ ልዩ ተቋማት እንዲፈጠሩ አልተደረገም። ነገር ግን በምክር ለመርዳት ያክል Imperial Federal Council የተባለ ተቋም ተበጅቶ የነበር ሲሆን በቂ ኃይል ግን አልነበረውም ። ስለዚህ እውነተኛው የፌዴራሉ መንግስት የኢትዮጵያ መንግስት ነበር። በሽግግሩ ወቅት የእንግሊዙ ወታደራዊ አስተዳደር የኤርትራን ህገ መንግስት እንዲህ ሲል ቀረጸ፣ ኤርትራ ራሱን የቻለ ግዛት ሲሆን ኤርትራዊ ዜግነትን ፣ ብሔራዊ ቋንቋን (ትግርኛና አረብኛ)፣ የተለየ ሠንደቅ አላማን፣ ማህተምንና ልዩ መንግስትን ለኤርትራ ይሰጣል። በራሱ ጉዳይ ዙሪያ ህግ ማጽደቅ ፣ ህግ ማስፈጸምና ፍርድ መፍረድ እንዲችል ለኤርትራው መንግስት ይፈቅዳል። የአካባቢውን ሥነ ንዋይ መቅረጽ፣ ግብር መሰብሰብ፣ ጤና፣ ትምህርት፣ መስተዳድር እና የፖሊስ ስራ በዚሁ በኤርትራው መንግስት ስር ይከወናሉ። የፖለቲካ ፓርቲወች፣ የንግድ ማህበራት፣ የሰው ልጅ መብቶች፣ የህትመትና የመናገር ነጻነትንም ይፈቅዳል። የፌዴራሉ መንግስት በአንጻሩ የውጭ ጉዳይን፣ መከላከያን፣ ገንዘብን፣ ፋይናንስን፣ የውጭ ንግድና የኢትዮጵያና ኤርትራን ንግድን፣ መገናኛን በተመለከተ ስልጣን ይኖረዋል። በተጨማሪ የፌዴራል መንግስቱን ስራ ለማካሄድ አንድ አይነት ግብር እንዲያወጣ ይገደድ ነበር። በዚህ ወቅት አቶ አንዳርጋቸው መሳይ (የአጼ ኃይለ ስላሴ አማች) በኤርትራ የኢትዮጵያ መንግስት ተወካይ ነበሩ። 

የኤርትራ ምክር ቤት (ባይቶ ኤርትራ) በእንግሊዞች አቀናባሪነትና አገር አቀፍ ምርጫ መጋቢት 1952ዓ.ም. ሲመሰረት በዚሁ ወቅት የኤርትራን ህገ መንግስትና የፌደሬሽኑን ደንብ አጸደቀ። እንዲሁም አቶ ተድላይ ባይሩን እንደ ዋና ስራ አስፈጻሚ ና አቶ አሊ አህመድ ሙሳ ረዳይን እንደ ፕሬዜዳንት አድርጎ መረጠ። በዚያው አመት መስከረም ላይ የኢትዮጵያም መንግስት እንዲሁ ሁለቱን አጸደቀ። መስከረም 15 ላይ የአስተዳደሩ ሃይል ወደ ፌዴራል መንግስት ተዛወረ። ከዚህ በኋላ የኢትዮጵያውም ሆነ የኤርትራው ውገኖች ለራሳቸው በሚስማማ መልኩ የፈዴሬሽኑን ደንቦች በመተርጎም ቀስ በቀስ የፖለቲካ ውጥረት ተነሳ። የአንድነት ደጋፊ የነበሩት አቶ ተድላ ባይሩ 1953 ላይ የፖለቲካ ተቃውሚዎቻቸው ወልደ አብ ወልደ ማርያምንና አብርሃ ተሰማን በመወንጀል ጥቃት ጀመሩ። የአንድነት ፓርቲ አቶ ተድላ ባይሩን በመደገፍ ኤርትራን ሙሉ በሙሉ ከኢትዮጵያ ጋር ማዋሃድ አላማው አድርጎ ተነሳ። እኒህ የአንድነት ደጋፊዎች በመንግስት ቢሮዎች ለየት ያለ ስራ የማግኘት እድል ስላገኙ የተገንጣይ ሃይሎች (የኤርትራ ዲሞክራሲያዊ ግንባር) እጅግ ተበሳጩ። በተለይ በእስላማዊው ምዕራብ ኤርትራ ግንባሩ ከፍተኛ ድጋፍን ማግኘት ጀመረ። የኢኮኖሚው እየወደቀ መሄድ፣ የግብር መጨመርና የቁሳቁሶች ዋጋ መጨመር ለውጥረቱ መባባስ አስተዋጽኦ አደረጉ። በዚህ ወቅት ኤርትራ የምታስገባውና የምታስወጣው ዕቃ ላይ 25% የግብር ጭማሪ ተደርጎ ነበር። የጣሊያን ዜጎችም በጦርነቱ ያጡትን የኢንደስትሪ፣ ማዕድን ማውጣት፣ እርሻ ወዘት መብቶች ከእንደገና በማግኘታቸው አገሬው ህዝብ እንዲበሳጭ ካደረጉት ጉዳዮች አንዱ ነበር። 

በዚያው አመት በ1953 ሙስሊም ሊግ መነሳሳትን አሳየ። እንዲያውም የእስላምናን ፍላጎትና የኤርትራን ህገ መንግስት እንደግፋለን በማለት ህዝባዊ አመጽ ማደራጀት ጀመረ። የኤርትራው ሥራ አስፈጻሚ ሊቀመንበር የህትመት ነጻነትን በመንፈግ አመጹን ለማፈን ሞከረ። 1954 ላይ ሙስሊም ሊግ በበኩሉ ለአጼ ሃይለ ስላሴ እና ለተባበሩት መንግስታት የመብቱን መታፈን በመቃወም ደብዳቤ ጻፈ። ነገር ግን ተቃውሞው አንድ ወጥ አልነበረም። በሙስሊም ሊግ ውስጥ በተነሳ ውስጣዊ ቅራኔ ኢብራሂም ሱልጣን ከሊጉ ተባረረ። የሆኖ ሆኖ ሙስሊም ሊግ በኤርትራ ምክር ቤት ባደረገው ዘመቻ አቶ ተድላ ባይሩ ምክር ቤቱ ክብር እንዲያጣና በራሱ ፓርቲ እንዲወቀስ አድርገው ነበር።

በኤርትራው ምክርቤትና በሥራ አስፈጻሚው ሊቀመንበር (ፕሬዘዳንት አሊ ረዳይ)ውጥረት የተጀመረው በዚህ ወቅት ነበር። ምክር ቤቱ ተድላ ባይሩን ከመጥላቱ የተነሳ እርሱን ከስልጣን ለማባረር አሊ ረዳን ማባረር ግድ እንዲላቸው ስለተረዱ ሴራ ማሴር ጀመሩ። ተድላ ባይሩ በበኩሉ ህገ መንግስቱ ከሚፈቅደው ጊዜ በላይ፣ ምክር ቤቱ እንዲዘጋ (ሰስፔንድ እንዲደረግ) አደረገ። የተቃዋሚው ሃይል እሮሮውን ወደቀዳማዊ አጼ ሃይለ ስላሴ በማሰማት ጣልቃ እንዲገቡ አደረገ። ንጉሱም የነገሩን ኢ-ህገ መንግስታዊነት በመመልከት አቶ ተድላ ባይሩና ፕሬዜዳንት አሊ ረዳይ ከስልጣናቸው እንዲለቁ አደረጉ። በዚህ ወቅት ቢትወደድ አስፍሐ ወልደሚካኤል ተድላ ባይሩን ተክቶ ተሾመ። አስፍሐ ወልደሚካኤል የአንድነት ፓርቲ ደጋፊ ነበሩ። ምክር ቤቱ በተራው ሼክ ሳይድ እድሪስ ሙሃመድ አዲምን (የኤርትራ ዲሞክራሲ ግንባር ተወካይ) ፕሬዚዳንት አድርጎ መረጠ። ከዚህ በኋላ በአንድነት ፓርቲና በሙስሊም ሊግ መካከል ብዙ መቆራቆስና በኋላም የሙስሊም ሊግ ከሁለት መከፍል ተፈጸመ። 

መስከረም 1956 ላይ በተደረገ የምክር ቤት ምርጫ ከ68 መቀመጫወች 32ቱን የአንድነት ፓርቲ አሸንፎ በጠንካራነት ወጣ። ከሁለተኛው የአለም ጦርነት መጨረሻ ጀመሮ በተነሳው የኢኮኖሚ ማሽቆልቆል ሽፍቶች በአገሪቱ መከሰት ጀመሩ። ህዳር 1956 ላይ አጼ ሃይለ ስላሴ ለምክር ቤቱ ባደረጉት ንግግር ኤርትራን ወደ እናት ሃገሯ ኢትዮጵያ የመመልስ ጉዳይ አንስተው ነበር። በጊዜው የአረብ አብዮት በአካባቢው እየተስፋፋ ስለነበር ለኤርትራም አስጊ ሁኔታ የፈጠረበት አጋጣሚ ነበር። ጥቅምት 1957፣ ወልደ አብ ወልደ ማርያምና ኡመር ቃዲ ለተባበሩት መንግስታት በጻፉት ደብዳቤ የኢትዮጵያና የኤርትራ መንግስታት በሚያሴሩት ሴራ የፌዴራል ደንቡ እየተሸረሸረ እንደሆነ አስገነዘቡ። የፌዴራል ባለስልጣኖች ኡመር ቃዲን በማሰር አንድ አንድ የተነሱ ሰላማዊ ሰልፎችንና አድማዎችን በማፈን ሁኔታውን አለዘቡት።

ግንቦት 1960 ላይ ምክር ቤቱ የኤርትራ አስተዳደር፣ በኢትዮጵያ ንጉስ ሃይለ ስላሴ ስር የሚለውን ስያሜ ለኤርትራ መንግስት መረጠ። ነገር ግን የኢኮኖሚው አለመረጋጋት በሰራተኛው መደብ ውስጥ አድማና ተቃውሞ አስነሳ። ይህ የኢኮኖሚ ቀውስ ኢ-ኢትዮጵያዊ ቅርጽ ነበረው። 1961 ላይ እድሪስ አዋተና ጥቂት ተከታዮቹ በስሜን ምዕራብ ኤርትራ የትጥቅ ትግል አስነሳ። ግንቦት 1962 ተማሪዎች የኤርትራ ነጻነትን በመደገፍ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ እንዲሁም በዚሁ ውቅት ኢ-ኢትዮጵያዊ ሴራ በአገሪቱ ውስጥ ተደርሶበት ከሸፈ። ሐምሌ 1962 ላይ ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ ሁኔታውን ለማረጋጋት ወደ ኤርትራ ተጉዘው ነገሮች ሊረግቡ ቻሉ። ከአምስት ወር በኋላ ህዳር15፣ 1962 የኤርትራ ምክር ቤት ባደረገው ምርጫ ፌዴሬሽኑ እንዲፈርስና ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር እንድትቀላቀል ወሰነ። ምርጫውን ተከትሎ አጼ ሃይለስላሴ የፌዴራሉን ደንብ ውድቅ በማድረግ ኤርትራ የኢትዮጵያ 14ኛ ጠቅላይ ግዛት አደረጉ።

ኤርትራ የኢትዮጵያ ክፍለ ሐገር ከሆነች በኋላ ያለው ጊዜ በሁለት ጉልህ ዘመናት ይከፈላል፣ እነርሱም የዘውዱ ጊዜና የደርግ ዘመናት ናቸው።

በዘውዱ አገዛዝ ወቅት ከኢትዮጵያ ወገን አንድ ወጥ ሳይሆን ያመነታ ሁለት አይነት አቋም ታይቷል፡ የመጀመሪያው አቋም በጠቅላይ ሚኒስትር አክሊሉ ሀብተ-ወልድ ይመራ የነበር ሲሆን አቋሙም ሙሉ በሙሉ ኤርትራን ወደ ኢትዮጵያው ስርዓት ማምጣትና ማዕከላዊነትን ማስፋፋት ነበር። ሁለተኛው አቋም ኤርትራን ከ1964-70 ያስተዳድሩ በነበሩት ራስ አስራተ ካሳ የሚመራ ሆኖ የኤርትራን ማንነት በማይነካ መልኩ፣ ግትር ያለ አቋም ሳይይዝ፣ መንግስት አስተዳደሩን እየለዋወጠ በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲተዳደር ማድረግ ነበር። ለአስራተ ካሳ አቋም መነሻ በክርስቲያን ኤርትራውያን ላይ የነበረው እምነት ነበር። ስለሆነም ኤርትራ የበለጠ ነጻነት ቢሰጣት አገሪቱ ጸንታ ትቆማለች የሚል ነበር። 

ከኤርትራኖችም አንጻር ሁለት መንታ አቋም ነበር። በተለይ ራስ አስራተ ካሳ የኤርትራ አስተዳዳሪ በነበሩበት ወቅት የተማረው ክርስቲያኑ የኤርትራ ክፍል ከሞላ ጎደል የኢትዮጵያ ደጋፊ ነበር። ብዙ የኤርትራ ክርስቲያኖች ወደ አዲስ አበባ በመሄድ በሃብት የበለጸጉ ኤርትራውያንን መቀላቀል ቀጠሉ። በቁጥር ጥቂት የማይባሉ ኤርትራውያን በዘውዱ ሥርዓት ውስጥ የመሪነት ቦታን አገኙ። በአንጻሩ ያልተማረው ወጣቱ ክፍልና፣ በእንግሊዙ ወታደራዊ አስተዳደር ስልጣን የነበረው ይህን አይነት ኢትዮጵያዊነት ሊቀበል አልቻለም። አብዛኛው የሙስሊም ክፍልም እንዲሁ አልተቀበለም። 

ብዙ የምዕራብ ኤርትራና የምጽዋ አካባቢ ሙስሊም ወጣቶች ጀብሃን (የኤርትራ ነጻነት ግንባር)ን መቀላቀል ጀመሩ። ጀብሃ በ1960ዓ.ም ካይሮ ውስጥ የተመሰረተ ግንባር ነበር። እኒህ ሙስሊሞች በጊዜው በካባቢው ተንሰራፍቶ የነበረውን መላው አረባዊነት በመዋስ የኤርትራ ህዝብ አረባዊነትን እንደ መፈክር አነገቡ። በዚያውም በአረብ አገሮች ይካሄድ የነበረውን የትጥቅ ትግል ስልት በጥቅም ላይ ማዋል ጀመሩ። የናስሪዝም እና የባቲዝም ንቅናቄዎችን ከመካከለኛው ምስራቅ በመዋስ ገንዘባቸው አደረጉ።

በ60ዎቹ መጨረሻ፣ ምንም እንኳ ጀብሃ እድገት ቢያሳይም የመላው-አረባዊነት አቋሙን በመጥላት አንጎራጓሪ ክርስቲያን ወጣት ኤርትራውያን ሊደግፉት አልቻሉም። ጠረፍ ነዋሪ ሙስሊሞች ጀብሃ በምዕራብ ሙስሊሞች የተሞላና እኛን የረሳ ነው በማለት ለመደገፍ አልፈለጉም። የመላው-አረባዊነት መፈክርም በአረብ አገሮች በተነሳ የርስ በርስ ሽኩቻ ተነኳኮተ። ከዚህ በተጨማሪ ጀብሃ ከሁለት ተከፍሎ በክርስቲያኖች አውራነት የተመሰረት -- የኤርትራ ህዝብ ነጻነት ግንባር (ሻዕቢያ) ሲቋቋም የኤርትራው ትግል ያበቃለት መሰለ ። ሆኖም ግን በጠቅላይ ግዛቱ የሚካሄደው ጦርነት የራስ አስራተ ካሳ አቋም የማይሰራ ስላስመሰለ ህዳር 1970 ላይ ራስ አስራተ ካሳ ከኤርትራ ስልጣናቸው እንዲነሱ ሆነ። ከዚህ በኋላ ወታደሮች በወታደራዊ ስልት ችግሩን እንዲፈቱ ነጻነት ተሰጣቸው።

ከኢትዮጵያ አብዮት መፈንዳት በኋላ የተነሳው ደርግም እንዲሁ ፖሊሲው ያመነታ ነበር። የደርግ የመጀመሪያው ሊቀመንበር የነበረው የኤርትራው ተወላጅ ጄኔራል አማን አንዶምአገሪቱ በኤርትራ ላይ ትከተል የነበረውን ፖሊሲ ለመገምገም ሞክሯል። በእርሱ ፖሊሲ መሰረት ኤርትራ በኢትዮጵያ ስር ሆና ነገር ግን የራሷ የፖለቲካ ማንነት እንዲኖራት የሚፈቅድ ነበር። አማን አንዶም ከተገደለ በኋላ የርሱ ፖሊሲ ተቀይሮ እስከ 1991 ድረስ የሚሰራበት ፖሊሲ በኮሌኔል መንግስቱ ሃይለማርያምአማካይነት ተፈጻሚነትን አገኘ። ይህ አዲሱ ፖሊሲ በኤርትራ እንቅስቃሴዎች ላይ ወታደራዊ ድልን በመቀዳጀት ላይ ያተኮረ ነበር። 

በዚህ ሁኔታ፣ አብቅቶለታል ተብሎ የነበረው የኤርትራ አመጽ ማንሰራራት ጀመረ። በ1970ዎቹ ሁለተኛ አጋማሽ ላይ ሻዕቢያ ሙሉ ጥቃትን ማድረስ ጀመረ። ምንም እንኳ ሁሉም ግንባሮች የኢትዮጵያን ሰራዊት የሚታገሉ የነበሩ ቢሆንም፣ ኤርትራውያን አንድ መሆን አልቻሉም ነበር። በተለይ ማርክሲስት የነበረው ሻዕቢያ ብዙ ክርስቲያን ኤርትራውያን ሲቀላቀሉት፣ ኃይሉ ከማደጉ የተነሳ፣ በመላው አረባዊነት አራማጁ ጅብሃ ላይ ጦርነት መክፈት ጀመረ። ከ1981-84 በተደረገ እርስ በርስ ጥሮነት ሻዕብያ የበላይነቱን ተጎንጻፎ ብቅ አለ። ከ80ዎቹ አጋማሽ ጀመሮ ኢትዮጵያ ውስጥ ይካሄድ የነበረው ጥርነት እየተጠናከረ ሲሄድ ሻዕቢያ ወሳኝ ድሎችን ማስመዝገብ ጀመረ። 1987 ላይ ሶቭየት ህብረት ለደርግ የሚያደርገውን እርዳታ ሲያቋርጥ ሁኔታዎች ለሻዕቢያ ተመቻቹ። መጋቢት 1988 የአፋቤት ጦርነት ተብሎ በሚታውቀው የሻዕቢያ ሰራዊት በደርግ ሰራዊት ላይ ስልታዊ የሆነ ድል ተቀዳጀ። ከዚህ በኋላ የአቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ስልጣን እየገነነ ግንባሩም ድል እየተጎናጸፈ ሄዶ ግንቦት 1991፣ በኢትዮጵያ የደርግ መውደቅን ተከትሎ ኤርትራ ኢ-ጥገኝነቷን ለማግኘት ቻለች። የኤርትራ ትግል በኢትዮጵያ ላይ ብዙ አሻራ የተወ ሲሆን በተለይ የነጻነት ግንባር ጽንሰ ሃሳብን ከአረብ አገሮች በማስመጣት በአካባቢው ማስፋፋቱ ተጠቃሽነት አለው። 

 

ኤርትራ እራሷን ከቻለች በኋላ ለተወሰነ ጊዜ የኢኮኖሚ እድገትን አሳይታለች። ሆኖም ግን ከጎረቤቶቿ ጋር የሰላም ግንኙነት አልነበራትም። ከሱዳንጋር እርስ በርስ በመወነጃጀል በ1990ወቹ የፖለቲካ ውጥረት ውስጥ ገብተው ነበር። 1995 እና 96 ደግሞ ከየመን ጋር በሐኒሽ ደሴቶች ዙሪያ ጦርነት አድርጋ 1998 ላይ በተ.መ. ውሳኔ መሰረት ደሴቶቹ ለየመን ተሰጡ። ከዚህ በኋላ ቀዝቀዝ ያለ ሰላም በሁለቱ መካከል ሰፈነ።

ከኢትዮጵያ ጋር የነበራት ግንኙነት መጀመሪያ የወዳጅነት ቢሆንም በኋላ ላይ በንግድና በባህር ወደብ አቅርቦት ዙሪያ በተነሱ ጥያቄዎች ውጥረት ገጠመ። 1998ዓ.ም. ላይ ባድሜ በተባለች የጠረፍ መንደር ዙርያ በተነሳ የድንበር ግጭት ውጥረቱ ገንፍሎ ወጥቶ ወደ ጦርነት አመራ። ከሁለት አመት ጦርነት በኋላ ታህሳስ 2000 ላይ የተ.መ. ሰላም አስከባሪ ሃይል በኢትዮጵያ-ኤርትራ ድንበር ላይ ተሰማራ። የአለም አቀፉ የድንበር ኮሚሽን ድንበሩን ለማካለል የወሰደው ውሳኔ በኤርትራ ተቀባይነት ሲያገኝ በኢትዮጵያ ዘንድ በመሪህ ደረጃ ተቀባይነትን አግኝቶ ነገር ግን በተግባር ደረጃ የቤተሰቦችንን መለያየት ይፈጥራል በሚልና ሌሎች ምክንያቶች ተቀባይነት አላገኘም። ኤርትራ በበኩሏ የተ.መ. የሰላም አስከባሪው ክፍል በስለላ ስራ የተሰማራ ነው በማለትና ጫና በመፍጠር 2008 ዓ.ም. ኤርትራን ለቆ እንዲሄድ አደረገች። በዚያው አመት ኤርትራ ወታደሮቿን በራስ ዱሜራ አካባቢ በብዛት ስታሰማራ ከጅቡቲ ጋር የድንበር ጥል ገባች። ይህን ተከትሎ በተነሳ ጦርነት ወደ 30 ሰዎች ሞቱ።

ከግንቦት 1991 በኋላ ኤርትራ ትመራ የነበረው በጊዜያዊ መንግስት ሲሆን መሪዎቹም የቀደሙት የሻዕቢያ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ነበሩ። የኤርትራምርጫ(ሚያዚያ 23-25) ከተደረገ በኋላ ግንቦት19,1993 ይሄው ጊዜያዊ አካል የኤርትራ ሽግግር መንግስት መሆኑን አወጀ። አላማውም አዲስ ህገ መንግስት እስኪጸድቅና ምርጫ እስኪካሄድ አገሪቱን ለ4 አመት ማስተዳደር ነበር። ከ5 ቀን በኋላ ኢ-ጥገኛ ኤርትራ ግንቦት 24,1993 ላይ በኦፊሴል ታወጀ። የሽግግሩ መንግስት ህግ አርቃቂ አካል (ሀገራዊ ባይቶ) 30 የሻዕቢያ ማዕከላዊ አካላትን እና 60 አዳዲስ አባላትን የያዘ ነበር። 1993 ላይ ይሄው አካል የኤርትራን የመጀመሪያ ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን መረጠ። ፕሬዜደንቱ የአገሪቱና የመንግስቱ የበላይ አካል ሲሆን በህግ አርቃቂው ኮሚቴ እና በአገሪቱ ምክር ቤት ላይ ሙሉ ስልጣን አለው። በተጨማሪ አቶ ኢሳያስ የሰራዊቱ መሪ እና የሻዕቢያ ዋና ሃላፊ በመሆን ሃይላቸው የገነነ ነው። ከ1994 ጀምሮ ሻዕቢያ ስሙን ቀይሮ ህዝባዊ ግንባር ለፍትሕና ለዲሞክራሲ PFDJ ተባለ። ግንቦት 1997 የተጠበቀው ኤርትራዊ ህገ መንግስት በጉባኤ ቢጸድቅም ተፈጻሚነት አጣ። የፓርላማ እና የፕሬዜደንት ምርጫም እንዲሁ ሳይደረግ ቀረ። 150 አባላት ያሉት የአሁኑ ሀገራዊ ባይቶ ይቀደመውን ኮሚቴ 1997 ላይ የተካ ሲሆን 75 የPFDJ ሹሞችና እና ተጨማሪ 75 የተመረጡ አባላትን አጠቃሎ ይዟል።

በአሁኑ ወቅት ኤርትራ በ6 ዞባዎች ይከፈላል። እኒህ በተራቸው በንዑስ ዞባዎች ይከፈላሉ። የዞባወቹ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ በአገሩ የውሃ አቅርቦት ጠባይ ላይ የተመሰረተ ሲሆን የኤርትራ መንግስት ይህን ያደረገበት ምክንያቱን ሲገልጽ እያንዳንዱ አስተዳደር በራሱ የእርሻ አቅም ላይ ሙሉ ቁጥጥር እንዲኖረው እና ታሪካዊ አውራጃዊ ርስበርስ ግጭቶችን በዚያው ለማስወገድ ነው። 

ዞባዎቹ እና የዞባዎቹ ክፍሎች እኒህ ናቸው:

ኣቶ ወልደአብ ወልደማሪያም፥
ዓብደል ቃድር ከቢረ
ራስ ወልደሚካኤል ፣

እድሪስ አዋተ ፣

እብራሂም ሱልጥን፣

ባሕታ ሀጎስ፣

ተድላ ባይሩ፣

አማን አንዶም

ኢሳያስ አፈወርቂ

Ibrahim Harun

Mear Mussa 

ali ibrhm 

wedi fenql 

shat efrem 

gerzgher wechu   




#Article 35: ኮምፒዩተር (323 words)


ኮምፕዩተር ማለት ማንኛውንም ኢንፎርሜሽን ፕሮሰስ የሚያደርግ ማሽን ነው። ይህንም የሚያደርገው በተርታ የተቀመጡ ትዕዛዞች በመፈጸም ነው። ለብዙ ሰዎች ኮምፒዩተር ሲባል ዐዕምሯቸው ላይ የሚመጣው የግል (ፐርሰናል) ኮምፒዩተር ነው። ነገር ግን ኮምፒዩተር ሲባል በጣም ብዙ ነገሮችን ያጠቃልላል። ላፕቶፕ ፣ ዴስክቶፕ ፣ ማይክሮ-ኮምፒዩተር ፣ ሱፐር-ኮምፒዩተር ፣ ካልኩሌተር ፣ዲጂታል ካሜራ እና ሌሎችንም ያጠቃልላል።

ቀድሞ አስሊ ማለት አንድ በሒሳባዊ ትዕዛዝ የተለያዩ የጥንት መሣሪያዎችን እየተጠቀመ ቁጥሮችን የሚያሰላ ሰው ነበር። እስከ 20ኛው ክፍለ-ዘመን ድረስ የተለያዩ ጠቃሚ መሣሪያዎች ተሰርተዋል። ከዛ በኋላ ትልልቅ ማሸኖች መሠራት ጀመሩ። እነዚህ ማሽኖች ከዛሬው ኮምፒዩተሮች(አስሊዎች) ጋር ሲወዳደሩ በጣም ትልቅና ቀርፋፋ ናቸው።

ዋና የኮምፒየተር ዐይነቶች እንደሚከተለው ነው፦

የኮምፕዩተር የውስጥ ክፍሎች የሚከተሉት ናቸው፡-

ሞኒተር 14 ኢንች፣ 15 ኢንች፣ ወዘተ. እየተባለ ይገላጻል፡፡

በፊት የነበሩት የላፕቶፕና ዴስክቶፕ ኮምፒዩተሮች ሬሾ (ርዝመት ሲካፈል ለወርድ) 4በ3(በትክክል ሲጻፍ 4:3 ይሆናል) ነበር፡፡

አሁን ደግሞ የቲያትር ሞድ የሚባለው ባለ 16፡9 ሬሾ ወይም ዋይድ ስክሪን (widescreen) በመጠቀም ላይ ናቸው፡፡

ሜሞሪ(ማስታወሻ) በባይት (Bytes) ይለካል፡፡ ከ Bytes ፊት Kilo፣ ማለትም ኪሎባይት (kilobytes)([1,024 ባይቶች ወይም Bytes ማለት ነው፡፡ ] ፣ Mega[1,048,576 ባይቶች ወይም Bytes ] ፣ Giga [1,073,741,824 ባይቶች ወይም Bytes]፣ ወዘተ የሚሉትን ቃላት በመጠቀም ኪሎባይት(kilobyte)፣ ሜጋባይት (megabyte)፣ ጊጋባይት (gigabyte)
እያልን የኮምፒዩተር ሜሞሪ መግለፅ እንገልጻለን፡፡

ለምሳሌ 10 MegaBytes ወይም ባጭሩ ሲጸፍ 10MB ይህ ማለት 10,485,760 Bytes ይሆናል ማለት ነው፡፡

ዊኪፒዲያ ላይ ያለውን ምስል ከቁጥሩ ጋር ማነጻጸር ይቻላል፡፡

ታዋቂ የኮምፕዩተር አምራቾች የሚከተሉት ናቸው፡፡ ይህ ማለት ግን እያንዳዱን የኮምፕዩተር ክፍል(ዕቃዎች)ይሠራሉ ማለት አይደለም፡፡

ድረ ገጽ---[ የአይቢኤም ድረ ገጽ ]

ድረ ገጽ---[ የዴል ድረ ገጽ]

በኢትዮጵያ የዴል ወኪል አልታ ኮምፒዩተር ነው፡ ፡አድራሻቸው ቦሌ መንገድ ሸዋ ሱፐርማርኬት ፊትለፊት ኔጃት ኮምፒዩተር ያለበት ፎቅ ላይ ነው፡፡

ድረ ገጽ---[ የኤሰር ድረ ገጽ]

በኢትዮጵያ የኤሰር ወኪል ኔጃት ኮምፒዩተር ነው፡፡ አድራሻቸው ቦሌ መንገድ ሸዋ ሱፐርማርኬት ፊትለፊት አልታ ኮምፒዩተር ያለበት ፎቅ ላይ ነው፡፡
 

ድረ ገጽ---[ የቶሺባ ድረ ገጽ]

ድረ ገጽ---[ የአፕል ድረ ገጽ] 

ድረ ገጽ---[ የኤችፒ[ድረ ገጽ]

የመጀመሪያቹ ኮምፕዩተሮች የሚሠሩት በእንግሊዝኛ ፊደል ብቻ ነበር። ቀስ በቀስ ግን የተለያዩ ኣገሮች ሊቃውንት በየራሳቸው ፊደላት እንዲሠሩ ኣደረጉ። ኮምፕዩተር በእያንዳንዱ የግዕዝ ፊደል፣ ኣኃዝና ምልክት እንዲሠራ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈጠረው ኢትዮጵያዊው ዶክተር ኣበራ ሞላ ነው። በቅርቡም አያንዳንዱ የግዕዝ ፊደል፣ ኣኃዝና ምልክት ዩኒኮድ የሚባል የዓለም ፊደላት መደብ ውስጥ መግባት ቀጥሏል።




#Article 36: ላይቤሪያ (446 words)


ላይቤሪያ (እንግሊዝኛ፦ Liberia)፣ በይፋ የላይቤሪያ ሪፐብሊክ (እንግሊዝኛ፦ Republic of Liberia)፣ በምዕራብ አፍሪካ የምትገኝ ሀገር ናት። በጊኒ፣ ኮት ዲቯር፣ ሴራሊዮን እና በአትላንቲክ ውቅያኖስ ትዋሰናለች። ላይቤሪያ የቅኝ ግዛት ሆና በ1822 እ.ኤ.አ. ከአሜሪካ በመጡ ነጻ የወጡ ባሪያዎች የተመሠረተች ሲሆን በአካባቢው ግን የተለያዩ ብሔሮች ለብዙ ምእተ አመታት ኖረዋል። መሥራቾቹ ዋና ከተማቸውን ሞንሮቪያ ብለው ለአሜሪካን ፕሬዝዳንት ጄምስ ሞንሮው ሰይመውታል። ሐምሌ ፳ ቀን ፲፰፻፴፱ ዓ/ም ነጻነት አወጁና ግዛቷ የላይቤሪያ ሪፐብሊክ ሆነች። በ1980 እ.ኤ.አ. በወታደራዊ መፈንቅለ-መንግስት የላይቤሪያ አመራር ከወረደ በኋላ ከ1989 እስከ 2005 እ.ኤ.አ. ድረስ ሀገሩዋ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችን ያፈናቀሉና የሀገሩዋን ኢኮኖሚ ያቃወሱ ሁለት የእርስ-በርስ ጦርነቶችን አይታለች።

የአንትሮፖሎጂ ምርምር እንደሚያሳየው ከሆነ፣ በላይቤሪያ ላይ ከ12ኛው ክፍለ-ዘመን ወይም ከዛ በፊት ጀምሮ ሰው ሠፍሯል። መንዴ (Mende) የሚባል ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች ወደ ምዕራብ ሲስፋፉ፣ ሌሎች ታናናሽ ብሄረሰቦችን ወደ ደቡብ ወደ አትላንቲክ ውቅያኖስ ገፍተዋቸዋል። ዴዪ፣ ባሳ፣ ክሩ፣ ጎላ እና ኪሲ የሚባሉ ጎሳዎች በአካባቢው ከመጀመሪያ ጀምሮ እንደነበሩ በማስረጃ ይታወቃል። ይህ ፍልሰት የጨመረው የማሊ ግዛት በ1375 እ.ኤ.አ. እና የሶንጋይ ግዛት በ1591 እ.ኤ.አ. ሲዳከሙ ነው። በተጨማሪም ወደ ውስጥ ያለው ሥፍራ ወደ በርሃነት እየተለወጠ ስለመጣ፣ ነዋሪዎቹ ወደ እርጥቡ ፔፐር ጠረፍ (Pepper Coast) እንዲሄዱ ተገደዱ። ከማሊና ሶንጋይ ግዛቶች የመጡ አዳዲስ ነዋሪዎች ጥጥ ማሽከርከር፣ ልብስ መስፋት፣ ብረት ማቅለጥ እና ሩዝና ማሽላ ማብቀልን የመሳሰሉ ጥበቦች ለቦታው አስተዋወቁ።

መኔ ሰዎች (ከመንዴ ወታደሮች የመጡ) አካባቢውን ከተቆጣጠሩ በኋላ ቫይ የሚባል የማሊ ግዛት ከፈረሰ በኋላ ለመሰደድ የተገደደ ብሔር ወደ ግራንድ ኬፕ ማውንት (Grand Cape Mount) የሚባለው ሥፍራ ፈለሱ። የክሩ ብሔር የቫይን ፍልሰት ተቃወሙ። ከመኔ ብሔር ጋር አንድ ላይ በመሆንም የቫይ ብሔርን ከግራንድ ኬፕ ማውንት አልፈው እንዳይስፋፉ አገዱ።

በጠረፍ ላይ የሚኖሩት ሰዎች ታንኳ ሰርተው ከካፕ-ቨርት እስከ የወርቅ ጠረፍ (Gold Coast) ድረስ ካሉት ሌሎች ምዕራብ አፍሪካውያን ጋር ይገበያዩ ነበር። የክሩ ጎሳ በመጀመሪያ ለአውሮፓውያን ሰው ያልሆኑ ነገሮችን ይሸጡ ነበር። ግን በኋላ በየአፍሪካ ባሪያ ንግድ ውስጥ መሳተፍ ጀመሩ።

የክሩ ሠራተኞች ቦታቸውን ትተው በትልቅ እርሻዎችና የግንባታ ሥራዎች ላይ ተሳትፈዋል። አንዳንዶቹም የስዊዝና ፓናማ መስኖዎች ለመገንባት ረድተዋል።

ሌላ ግሌቦ የሚባሉ ሰዎች የመኔ ጎሳ አካባቢያቸውን ሲወር፣ በኋላ የላይቤሪያ ወደ ሚሆነው ጠረፍ አመሩ።

በ1461 እ.ኤ.አ. እና 17ኛው ክፍለ-ዘመን መጨረሻ መካከል ፖርቱጋላዊ፣ ሆላንዳዊና ብራታንያዊ ነጋዴዎች በላይቤሪያ የንግድ ቦታ አቋቁመው ነበር። በተጨማሪም የአንድ የሚጥሚጣ አይነት ፍሬ በመብዛቱ ፖርቱጋላዊያን አካባቢውን Costa da Pimenta (ኮስታ ዳ ፒሜንታ) ማለትም የፍሬ ጠረፍ ብለው ሰይመውት ነበር።

በ1822 እ.ኤ.አ. የአሜሪካ የቅኝ መግዛት ማህበር ላይቤሪያን ባሪያ የነበሩ ጥቁር ሰዎች የሚላኩበት ቦታ አድርጎ አቋቋመ። ከሌሎች ባሪያ ያልነበሩ ጥቁር አሜሪካውያንም ወደ ላይቤሪያ ለመሄድ የመረጡ ነበሩ። ወደ እዛ የሄዱት አሜሪካዊ ላቤሪያዊያን በመባል ይታወቃሉ። በሐምሌ 20 ቀን 1839 ዓ.ም. እነዚህ ሰፋሪዎች የላይቤሪያ ሪፐብሊክ ነፃነትን አወጁ።

አርባ ከመቶ የሚሆነው የሀገሩ ሕዝብ ክርስቲያን ነው። ሌላ ሀያ ከመቶ የሚሆን ሕዝብ የራሱ የአገሬው ሀይማኖት አለው። የቀረው አርባ ከመቶ ሕዝብ የእስልምና እምነት ተከታይ ነው።

የላይቤሪያ ዩኒቨርሲቲ በሞንሮቪያ ይገኛል። በ1862 እ.ኤ.አ. የተከፈተ ሲሆን ከአፍሪካ ቀደምት የከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አንዱ ነው። በእርስ-በርስ ጦርነት ጊዜ በጣም የተጎዳ ሲሆን አሁን እንደገና እየተገነባ ነው። 

ከቲንግተን ዩኒቨርሲቲ በየአሜሪካ ኢጲስ ቆጶስ ቤተክርስቲያን በ1889 እ.ኤ.አ. ተመሥርቷል። ግቢው በሱዋኮኮ፣ ቦንግ የአገዛዝ ክፍል ይገኛል።




#Article 37: የናቡከደነጾር የምስል ሕልም (432 words)


የናቡከደነጾር የምስል ሕልም ከትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ 2 የተገኘ ምሳሌ ነው።

በምሳሌው ዘንድ፣ የባቢሎን ንጉስ 2 ናቡከደነጾር በሚመላለስ ቅዠት ይታወካል እሱን ግን ለማስታወስ አይችልበትም።  ሕልሙን ካልነገሩትና ካላስተረጎሙለት በቀር የሕልም አስተርጓሚዎቹን በሞት ንብረታቸውንም በማጥፋት ዛቻ ጣለባቸው።  ስላልተቻላቸው ግን የባቢሎን ጠቢባን ሁሉ እንዲሞቱ አዘዘ።

ዳንኤል ጠቢብ ስለሆነ ይህ ማለት እሱ ደግሞ እንዲጠፋ ሲሆን ወደ ንጉስ ሂዶ ሕልሙን ከነትርጉሙ እንዲናገርለት ጊዜ ይለምነዋል።  ከዚያ በኋላ የሰማይ አምላክ ሕልሙን ከነትርጉሙ ለዳንኤል ገለጸ። ወዲያው ወደ ንጉስ ተመልሶ ሕልሙ በኋለኛው ዘመን የሚሆነውን እንደሚገልጽ ይናገራል።

ዳንኤል እንደሚገልጸው በናቡከደነጾር ሕልም አንድ ታላቅ ብሩህ ምስል ወይም ጣኦት በፊቱ ሲቆም አየ።  የምስሉ ራስ ከጥሩ ወርቅ፤ ደረቱና ክንዱ ከብር፤ ሆዱ ከነሐስ፤ እግሮቹ ከብረት፤ የግር ጣቶቹም ግማሽ ከብረት ግማሽ ከሸክላ ተሠሩ።   አንድ ዓለት በድንገት ታይቶ ከብረትና ከሸክላ የተሠሩትን የእግር ጣቶች ሲመታ ምስሉ አቧራ እስከሚሆን ድረስ ንጉስ በሕልሙ አየ። የዛኔ ንፋስ አቧራውን በትኖ ድንጋዩ ምድርን ሁሉ የሚሞላ ተራራ ሆነ።

ለንጉስ ሕልሙ ምን እንደ ሆነ ከነገረው በኋላ፣ ዳንኤል አስተረጎመለት።  ናቡከደነጾር እራሱ፣ የባቢሎን ንጉስ፣ የምስሉ ወርቃማ ራስ ነው። ከባቢሎን በኋላ ሌላ የሚያንስ መንግሥት ይመጣል፣ ይህም የብረት ደረትና እጆች መሳይ ይሆናል።  ከሱ ተከትሎ ሦስተኛ የናስ መንግስት ይነሣል፤ ከዚያም አራተኛው መንግሥት እንደሚጨምቅ ብረት ሌሎቹን ሁሉ ይገዛል።  ነገር ግን ይህ አራተኛው መንግሥት ይከፋፈላል፤ በመጨረሻም ግማሽ ብረትና ግማሽ ሸክላ እንደ ነበሩት እግሮችና ጣቶች ይሆናል። 

(ይህ ማለት ከተራራው ያለ እጆች የተቀረጸው ጣኦቱንም የሚሰባብረው ድንጋይ መሆኑን ይገለጻል።)

ብዙ ጊዜ ሊቃውንትና ጻፎች ይህንን ሲአስተርጉሙ 1ኛው መንግሥት ባቢሎን፣ 2ኛው ሜዶን፣ 3ኛው ፋርስ፣ 4ኛው መቄዶን (ታላቁ እስክንድር) እንደ ሆነ የሚል እምነታቸውን ይገልጻሉ።  ጻፎቹ ይህንን የሚያስቡ ትንቢተ ዳንኤል በአንጥያኮስ አፊፋኖስ ዘመን በዳንኤል ስም በማይታወቅ ሌላ ደራሲ እንደተጻፈ ስለሚቆጥሩት ነው። ነገር ግን ወንጌልን የሚቀበሉት ክርስቲያኖች ይህንን የጻፎቹን ሀሳብ አይቀበሉም፤ ምክኒያቱም በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 24 ኢየሱስ ስለ ዳኔል ከምጻት በፊት ስለሚመጣ ኋለኛው መከራ ዘመን የነበየ ነቢይ ይለዋል።  ስለዚህ ከኢየሱስ አስቀድሞ በ200 አመት የኖረ አፊፋኖስ ሊያመልከት አይችልም። እንግዲህ የምስሉ ብረታብረቶች መታወቂያ በላይ ከተጠቀሱት ጻፎች ግምት በትንሽ ይለያያል።  በዚሁ ፈንታ ሕልሙን ከናቡከደነጾር ጀምሮ ወደፊት የእግዚአብሐር ዘላለማዊ መንግሥት እስከምትቆም ድረስ ስለ ባቢሎንና በባቢሎን መንገድ ስለሚከተሉት መንግሥታት አደረጃጀት የሚነካ ሕልም ይቆጥሩታል። 

የወርቃማ ራስ መታወቂያ በማንም አይከራክርም፤ በመጽሐፉ ናቡከደነጾርና የባቢሎን መንግሥት መሆኑ ግልጽ ነውና።  ነገር ግን በዚህ አሳብ፡ የብር ደረት የመሰለው 2ኛው መንግሥት ፋርስ ነው እንጂ ሜዶን አይሆንም።  እንዲያውም ሜዶን በታሪክ ባቢሎንን መቸም ስላልተከተለው ነው፤ ፋርስ ግን በውነት ባቢሎንን ተከተለው።  እንዲሁም ሦስተናው የነሃስ ሆድ የሆነው መንግሥት የእስክንድር ግሪክ መንግሥት እንደ ሆነ ይታስባል።  ይህ ማለት አራተኛው የብረት እግሮች መንግሥት ሮማ መሆን አለበት።  የብረትና የሸክላ ጣቶች ትርጉም  ደግሞ ምናልባት ከሮማ መንግስት አመዶች የተነሱ አገሮች እንደሚሆኑ አንዳንዴ ይባላል፤ እነዚህም መጨረሻው (ድንጋዩ ወይም የእግዚአብሐር መንግሥት) ሲደርስ የሚገዙት አገሮች ይሆናሉ። 

ጻፎቹ ትንቢተ ዳንኤል ከአንጥያኮስ ዘመን እንደ ሆነ ካላቸው ሀሳብ ውጭ፤ ምእራፉ እራሱ በናቡከደነጾር ሁለተኛው አመት እንደ ሆነ ይላል። ይህ በባቢሎን ላይ የነገሰው 2ኛው አመት 612 ዓክልበ. ሊሆን ይችላል፤ አለዚያ ጽድቅያስን ከዙፋኑ አውርዶ በይሁዳ ላይ የነገሰው 2ኛው አመት 595 ዓክልበ. ሊሆን ይችላል።




#Article 38: አልጄሪያ (128 words)


አልጄሪያ (አረብኛ፦ الجزائر‎ አል ጃዝኤር; በርበርኛ፦ ድዜየር) በይፋ የአልጄሪያ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በሰሜን አፍሪካ የምትገኝ ሀገር ናት። ከቆሳ ስፋት አኳያ በሜዲቴራንያን ባህር ዙሪያ ትልቋ ስትሆን፣ ከአፍሪካ ደግሞ ከሱዳን በኋላ ሁለተኛ ናት።

አልጄሪያ ከሰሜን ምሥራቅ በቱኒዚያ፣ ከምሥራቅ በሊቢያ፣ ከምዕራብ በሞሮኮ፣ ከደቡብ ምዕራብ በምዕራባዊ ሣህራ፣ ሞሪታኒያና ማሊ፣ ከደቡብ ምሥራቅ በኒጄር፣ ከሰሜን በሜዲቴራንያን ባህር ትዋሰናለች። ዋና ከተማዋ አልጂርዝ ሲሆን የ፳፻፫ ዓ.ም. ሕዝብ ብዛቷ ወደ 35.7 ሚሊዮን ይገመታል።

አልጄሪያ የተባበሩት መንግሥታት፣ የአፍሪካ ሕብረት፣ ኦፔክ እና ሌሎችም ዓለም አቀፍ ድርጅቶች አባል ሀገር ናት።

የሀገሯ ስም የመጣው ከአልጂርዝ ከተማ ሲሆን በድሮ ጊዜ ከዛሬዎቹ ምዕራብ ቱኒዚያና ምሥራቅ ሞርኮ አብራ ኑሚዲያ ትባል ነበር።

በጥንት ጊዜ አልጄሪያ የኑሚዲያ መንግሥት ትባል የነበረ ሲሆን ነዋሪዎቿ ደግሞ ኑሚዲያውያን ይባሉ ነበር። የኑሚዲያ መንግሥት ከካርታጎ፣ ሮማና ጥንታዊ ግሪክ ጋር ግንኙነት ነበራት። አካባቢው ለምለም እንደነበረ ሲነገር ኑሚዲያውያን ደግሞ ለኃይለኛ ፈረሰኛ ጦራቸው ይታወቁ ነበር።




#Article 39: የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር (318 words)


የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የኢትዮጵያ (እንዲሁም በኤርትራ አብያተ ክርስትያናት) ዋና ካሌንደር ነው። አዲስ ዓመት በጁሊያን ካሌንደር አቆጣጠር በኦገስት 29 ወይም 30 የሚጀምር ሲሆን በግሪጎሪያን ካሌንደር ደግሞ ከ1901 እ.ኤ.አ. እስከ 2099 እ.ኤ.አ. ድረስ በሴፕቴምበር 11 ወይም 12 ይጀምራል። በየአራት ዓመቱ አንድ ቀን ይጨመራል። በአንድ ዓመት ውስጥ አስራ-ሁለት ባለሠላሣ ቀናት እና አንድ ባለ አምስት (ስድስት በአራት ዓመት) ቀናት ያሉባቸው ወራት አሉ። 

በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ዓመታት ሁሉ በአራት መደባት ይዞራሉ፤ እነሱም ስለ ሐዋርያት ስሞች ዘመነ ማቴዎስ፣ ዘመነ ማርቆስ፣ ዘመነ ሉቃስ (ተጨማሪ የጳጉሜ ቀን የሚቀበለው) እና ዘመነ ዮሐንስ ይባላሉ።

የአመተ ምህረት ዘመናት ከጎርጎርዮስ 'አኖ ዶሚኒ' በ7 ወይም 8 አመታት የሚለይበት ምክንያት፣ ከኢየሱስ ክርስቶስ ልደት 400 አመት ያህል በኋላ አኒያኖስ እስክንድራዊ ዘመኑን ሲቆጥረው ትስብዕቱ በመጋቢት 29 1 ዓ.ም. እንደ ሆነ ስለ ገመተ ይህ በትስብዕት ዘመን 1ኛ አመት ሆኗል። ይህ አቆጣጠር በምሥራቅ ክርስቲያን አገራት ከተቀበለ በኋላም በ443 ዓ.ም. ከሮማ ፓፓና ከምሥራቅ አቡናዎች መካከል ልዩነት ደርሶባቸው፤ በ517 ሌላ መነኩሴ ዲዮኒሲዮስ ኤክሲጉዎስ ሌላ አቆጣጠር (አኖ ዶሚኒ) አቀረበ። በሱ ግምት ትስብዕቱ የተከሠተበት ቀን ከአኒያኖስ ግምት በፊት በ8 አመታት አስቀደመው። የአኖ ዶሚኒ አቆጣጠር በምዕራብ አውሮፓ ላይኛነት በማግኘቱ የትስብእት ዘመን 1 አመተ ምህረት በአኖ ዶሚኒ 9 እ.ኤ.አ. ሆነ።

የኢትዮጵያ ዘመን ኣቆጣጠር የጁልያን ዘመን ኣቆጣጠር ኣይደለም። በኣሁኑ ጊዜ በጁልያና በጎርጎርዮስ ካለንደሮች መካከል ያለው የ13 ቀናት ልዩነት ሲሆን የዓመታቱ ቍጥሮች ልዩ ኣይደሉም። 
 
በ525 ዓ.ም. ዲኖስዮስ ኤክሲጅዮስ (Dionysius Exiguus) የሚባል የሩስያ መነኩሴ የሮማው ጳጳስ መልዕክተኛም በመሆን የፋሲካን በዓል ኣወሳሰን ከግብጻውያን እንዲማር ተልኮ ነበር። እንደሚመስለኝና ኣንዳንድ ፀሓፊዎችም እንደሚሉት ኤክሲጅዮስ በ525 ዓ.ም. 532 ዓመትን ሳይጠቀም ኣልቀረም ይላሉ ዶክተር ኣበራ ሞላ።    ዲኖስየስ ኣኖ ዶሚኒ (Anno Domini ወይም ኤ.ዲ.) የሚባለውን ካለንደር በጃንዋሪ 1 ፣ 1 ኤ.ዲ. እንዲጀምር በ525 ቢወስንም በኋላም ፀሓፊዎች ጁልያን (ዩልዮስ) ካለንደር ያሉት የግብጾችንና የኢትዮጵያን ዘመን መቈጠርያዎች ስለማይመለከት እራሱን የቻለ ካለንደር ሆኖ ቆይቷል። ኤክሲጅዮስ ወደኋላ በመቍጠር ሲጀምር ይመስለኛል ኣዲሱ ካለንደር ላይ ሰባት ዓመታት ግድም የጨመረበት። የዓመታቱም ቍጥር ከግብጽ ይልቅ ወደ ኢትዮጵያ የቀረበ ነው። ጨረቃ መሬትን ስትዞርና መሬት ፀሓይን ስትዞር የሚወስዱት 532 ዓመታት (19 X 28) ተደጋጋሚ ናቸው። 

የወራት አቆጣጠር የተወረሰ ከቅብጢ ዘመን አቆጣጠር፣ ይህም የወጣ ከጥንታዊ ግብጽ ዘመን አቆጣጠር ነው። ሆኖም የወሮች ስሞች በግዕዝ ተለውጠዋል።   

 




#Article 40: ደቡብ አፍሪካ (156 words)


በደቡብ አፍሪቃ ሕገ መንግሥት መሠረት 11 ልሳናት በእኩልነት ይፋዊ ኹኔታ አላቸው። ከነዚህ መካከል ኳዙሉ ከሁሉ ብዙዎች ተናጋሪዎቹ በአገሩ ውስጥ አሉት፤ ቆሣ በቁጥር ብዛት 2ኛው ነው። ከነዚያ በኋላ በተናጋሪዎች ብዛት አፍሪካንስ 3ኛው፣ ስሜን ሶጦ 4ኛው፣ እንግሊዝኛም 5ኛው፣ ጿና 6ኛው፣ ደቡብ ሶጦ 7ኛው፣ ጾንጋ 8ኛው፣ ሷቲ 9ኛው፣ ቬንዳ 10ኛው፣ ንዴቤሌም 11ኛው ነው። ብዙ ሰዎች እስከ 6 ቋንቋዎች ድረስ የመናገር ዕውቀት አላቸው፤ ከነጭም ዜጋዎች አብዛኛው አፍሪካንስና እንግሊዝኛ ሁለቱን ይችላሉ።

ትልቁ ከተማ ጆሃንስበርግ ሲሆን ዋና ከተሞቹ ሦስት ናቸው፤ እነርሱም ኬፕ ታውን፣ ብሉምፎንቴንና ፕሪቶሪያ ናቸው። ይህ ፓርላሜንቱ በኬፕ ታውን፣ ላዕላይ ችሎቱ በብሉምፎንቴን፣ ቤተ መንግሥቱ በፕሪቶሪያ ስለ ሆነ ነው።

ስመ ጥሩ የሆኑት የደቡብ አፍሪካ ሙዚቀኞች ሂው ማሴኬላ እና ሌዲስሚስ ብላክ ማምባዞ ናቸው። የደቡብ አፍሪካ ሙዚቀኞች አሁን የራሳቸውን ዘመናዊ ሙዚቃ ዓይነት «ኳይቶ» አላቸው።

የአገሩ አበሳሰል የተለያየ ነው። ብዙ ኗሪዎች የተቀመመ በሬ ቋሊማ ጥብስ (ቡረቮርስ)፣ የበቆሎ አጥሚት (ኡምጝቁሾ)፣ የተቀመመ ዶሮ፣ እና የተቀመመ ወጥ (ካሪ) ይወድዳሉ። 

የተወደዱ እስፖርቶች እግር ኳስ፣ ክሪኬት እና ራግቢ ናቸው። 

በአገር ቤት ሜዳዎች አንበሣ፣ ቀጭኔ፣ ጉማሬ፣ ጅብና አውራሪስ ሞልተው ሊታዩ ይቻላል። 




#Article 41: ቴሌቪዥን (545 words)


 
ቴሌቪዥን የስዕል እና ድምጽ ምልክቶችን ከማሰራጫ የሚቀበል የመገናኛ ዘዴ ነው። «ቴሌ-» የሚለው ክፍል በግሪክ «ሩቅ» ማለት ቢሆን «-ቪዥን» ደግሞ ከሮማይስጥ visio /ዊዚዮ/ «ማየት» («ትርዒት») ተወስዷል። በአጠቃላይ ቴሌቪዥን ማለት ተንቀሳቃሽ ምስልን (ብዙ ጊዜ ከድምፅ ጋር) ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለማስተላለፍ የሚረዳ የመልዕክት ማስራጫ መንገድ ነው። ይህ ከሆነ ዘንዳ ቴሌቪዥን ምስል መቅጃውንም ሆነ ምስል መቀበያውን መሳሪያ ሁሉ ያጠቃልላል ግን በተለምዶ ቴሌቪዥን የምንለው ምስል መቀበያውን ብቻ ነው።

በ1873 እ.ኤ.አ. (1865 ዓም) የእንግላንድ ኤንጅኔር ውሎቢ ስሚስ ባደረገው ጥረት ጥንተ ንጥሩ ሴሌኒይም ብርሃን-አስተላልፎሽ መሆኑን ገለጸ።

በ1884 እ.ኤ.አ. ፓውል ጎትሊብ ኒፕኮው የተባለ ጀርመናዊ ክብ የሆነ ዲስክን በስፓይራል በምብሳት ይህ ዲስክ በተሽከረከረ ቁጥር ከፊትለፊቱ የሚመጣውን ብርሃን በቀዳዶቹ በማሾለክ ከሴሌኒይም በተሰራ የካሜራ ግድግዳ ላይ እንዲያርፍ አደረገ። ግድግዳው ብርሃን ሲነካው ያንን ብርሃን ወደ ኮሬንቲ ሃይል በመቀየር ምስልን በኮሬንቲ መልክ በሽቦ ለመላክ ቻለ። ነገር ግን በዚህ ጊዜ አምፕሊፋየር ስላልነበር የሚላከው ምስል እምብዛም አመርቂ አልነበረም።

ከ27 አመታት በኋላ በ1911 እ.ኤ.አ. የራሻው ቦሪስ ሮዚንግ ለመጀመሪያ ጊዜ የሲርቲን ቴክኖሎጂ በመጠቀም፣ አሁንም ለመጀመሪያ ጊዜ ተንቀሳቃሽ ምስልን ለመላክና ለመቀብል ቻለ። ነገር ግን የሚንቀሳቀሱት ምስሎች የጂዎሜትሪ ቅርጽ ነበራቸው ማለትም ሶስት ማዕዘን፣ አራት ማእዘን ወዘተ... 

ከ7 አመታት በኋላ በ1925 እ.ኤ.አ. ጆን ሎጂ ቤርድ የተሰኘው የስኮትላንድ ተመራማሪ 2ቅጥ ያላቸው ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለመላክ ቻለ ከዚያም በ1926 እ.ኤ.አ. ጥቁርና ነጭ የሆኑ ምስሎችን ለማስተላለፍ በቃ። በዚህ ጊዜ የሚላኩት ምስል ጥራት 30 መስመር በአንድ ጊዜ ነበር፣ በዚህም ምክንያት የሰውን ፊት ለመለየት አስቸጋሪ ቢሆንም ግን ይቻል ነበር። አቶ ቤርድ በ 1918 ዓ.ም. (26 January 1926 እ.ኤ.አ.) የመጀመሪያውን የቴሌቪዥን መግለጫ ሰጠ። 

በ1927 እ.ኤ.አ.  ኸርበርት አይቭስ የተሰኘው የቤል ላብራቷር ተቀጣሪ 16 የምስል ገጽታ በሰከንድ ከዋሽንግተን ዲሲ ወደ ኒውዮርክ ከተማ በሽቦ መላክ ቻለ። ቀጠል አድርጎም በራዲዮ ወደ ዊፓኒ ኒው ጀርሲ ለመላክ በቃ። በዚያው አመት ፊሎ ፍራንስዎርዝ የመጀመሪያውን የተሟላና በኤሌክትሪክ ስካኒንግ ብቻ የሚስራውን የቴሌቭዥን ስርዓት በተግባር አዋለ።.በጥር 1928 እ.ኤ.አ. (1920 ዓም) መጀመርያው የቴሌቪዥን ማሰራጫ ጣቢያ በስከነክተዲ፣ ኒው ዮርክ ተከፈተ፤ እስከ ዛሬም ድረስ ያሰራጫል።

በርግጥም የመጀመሪያው በሰፊው ተግባራዊ የሆነ የቴሌቭዥን ስርዓት ስራ ላይ የዋለው በጀርመን አገር ሲሆን ይኸውም በ1929 እ.ኤ.አ. ነው። በ1936 እ.ኤ.አ. (1928 ዓም) ጀርመን ሃገር ተደርጎ የነበረውን የኦሎምፒክ ውድድር በቴሌቭዥን ሊሰራጭ ቻለ፣ ህዝቡም ውድድሩን እቤቱ ሆኖ ቀጥታ ሲካሄድ ለማየት ቻለ።

ከዚያ መጀመርያው ጥቁርና-ነጭ ፕሮግራሚንግ በዩናይትድ ኪንግደም 1928 ዓም፤ በአሜሪካ 1933 ዓም ተደረገ። በአፍሪካ መጀመርያው ጣቢያዎች በ1952 ዓም  በናይጄሪያና ደቡብ ሮዴዝያ (አሁን ዚምባብዌ) ተሰራጩ፣ በኢትዮጵያ የቴሌቪዥን ስርጭት አገልግሎት (ኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን) የጀመረው በ1956 ዓም ሆነ።

ሁለት አገራት - እነርሱም ቱቫሉና ኪሪባስ - ምንም የራሳቸውን ቴሌቪዥን አሁን አያሰራጩም፤ ሆኖም የሌላ አገር ስርጭት እዚያ ሊታይ ይችላል።

ከዚያ ቤርድ በግንቦት 26 ቀን 1920 (ጁላይ 3, 1928 እ.ኤ.አ.) የመጀመሪያውን የከለር ቴሌቪዥን ስርጨት ሙከራ አደረገ።

ነገር ግን ከለር ቴሌቪዥን ቢፈጠረም ለሚከተሉት ብዙ ዓመታት ስርጭት ባብዛኛው ጥቁርና ነጭ ብቻ ሆኖ ቀረ። ይሄው ቴክኖዎሎጂው በጣም ውድ፣ በጣም ከባድና በትክክል ያልተስተካከለ ስለ ሆነ ነው። በየጥቂቱ ከ1946 ዓም (1954 እ.ኤ.አ.) ጀምሮ አገራት ወደ ከለር ስርጭትና ከለሩን ማሳየት የሚችል ቴሌቪዥን ወደ መሸጥ ይዛወሩ ጀመር። በጥር ወር 1946 ዓም NBC የተባለው አሜሪካዊ ስርጭት ጣቢያ በከፊሉ ወደ ከለር ተሸጋገረ፤ ብዙ ሰዎች ግን ያንጊዜ ከለር ማሳያ ቴሌቪዥን ለመግዛት ገና አልቻሉም ነበር። ከ1955 እስከ 1959 ዓም ድረስ ሌሎቹ ትልልቅ አሜሪካዊ ጣቢያዎች ABC እና CBS ደግሞ ወደ ከለር ተዛወሩ፣ የከለርም ተቀባዮች ዋጋ እየተቀነሰ የሚይዩት ሕዝብ ቁጥር ደግሞ ከዚህ በኋላ እየተጨመረ ሄደ፤ ከረጅሙ ጥቁርና-ነጭ ዘመን ቀጥሎ ከለርም በኅብረተሠብ ያመጣው ለውጥ ለግዙፍነቱ በኋላ ኢንተርኔት እንደ ሆነ ያሕል ነው። 

ጃፓን በ1952 ዓም፣ ሜክሲኮ በ1955፤ ካናዳ በ1958፣ የአውሮፓ ኅብረትና የሶቪዬት ሕብረት በ1959፣ ኮት ዲቯር በ1962፣ አውስትራሊያ በ1967 ከለር ስርጭትን ጀመሩ። በኢትዮጵያም ከለር ስርጭት ከ1976 ዓም ጀምሮ ተገኝቷል። በ1977 ዓም ሮማኒያ ከጥቁርና-ነጭ ስርጭት ወደ ከለር ማሰራጨት የለወጠ በዓለም መጨረሻው ሃገር ሆነ።




#Article 42: መንግሥት (207 words)


መንግሥት በአንድ አገር ወይም ተቋም ውስጥ ሕጎችን ለማውጣትና ለማስፈጸም ስልጣን ያለው አካል ነው። መንግሥት አንድ ሃገር ወይም ማህበረሰብ የሚስተዳደርበት ሥርዓትና ለዚህም ሲባል የተቋቋመ ኃይል ያለው አካል ነው ፡፡

ድርጅቶች ሁሉ እንደ መንግሥት ያለ አስተዳደር ሲኖራቸው ፣ መንግሥት የሚለው ቃል በተለይ በግምት 200 የሚሆኑ አገራዊ መንግስታትን በበለጠ ያመለክታል፡፡

የመንግስት አመሠራረት መቼ እንደተጀመረ በእርግጠኝነት መናገር ይቸግራል ፡፡ ሆኖም ታሪክ የጥንታዊ መንግስታትን ምስረታ ይመዘግቧል ፡፡ ከ 5,000 ዓመታት በፊት የመጀመሪያዎቹ ትናንሽ የከተማ መንግስታት ብቅ ብቅ እንዳሉ ይገመታል ፡፡  ከሶስተኛው እስከ ሁለተኛው ዓመተ ዓለም  ከእነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹ ወደ ትልልቅ አካባቢዎች በማደግ እንደ ሱመር ፣ የጥንቷ ግብፅ ፣ የኢንዲስ ሸለቆ ስልጣኔ እና ቢጫ ወንዝ ስልጣኔ የሚባሉትን ፈጥረዋል ።

ግብርና ልማት እና የውሃ ቁጥጥር ለመንግስት ማደግና መጠናከር እንደ ዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ የአንዳንድ ነገድ አለቆች የእነሱን ጎሳ ለማስተዳደር በተለያዩ የአምልኮ ሥርዓቶች ወይም ባላቸው ጥንካሬ ተመርጠው አስተዳድረዋል፣ አንዳንዴም ከጎሣው ሽማግሌዎች ጋር በመሆን መንግሥት ሆነዋአል፡፡  በግብርና የበለጠ ውጤታማ እየሆኑ መሄድ በአንድ አካባቢ የሚኖረው ህዝብ ብዛቱ እንዲጨምር አስችሏል። ይህም ​​በተለያዩ ቡድኖች መካከል የሚደረጉ ግንኙነቶች እየጨመሩ እንዲሄዱና የሚፈጠረውንም መሥተጋብር የሚቆጣጠር አካል (መንግሥት) እንዲኖር አድርጓል።

እ.ኤ.አ. ከ 17 ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ጀምሮ የሪፖብሊካዊ መንግስት ተስፋፍቷል፡፡ የእንግሊዝ፣ የአሜሪካና የፈረንሳይ አብዮቶች ለተወካይ የመንግስት ምሥረታ እድገት አስተዋጽኦ አበርክቷል ፡፡  የኮሚኒስት መንግስት የተመሠረተበት የመጀመሪያው ሠፊ ሀገር ሶቪዬት ህብረት ነው። የበርሊን ግንብ ከተደረመሰ ጊዜ ጀምሮ የሊበራል ዴሞክራሲ የተስፋፋ የመንግሥት መስተዳድር ሆኗል ።




#Article 43: ሥነ ሕይወት (144 words)


ሥነ፡ሕይወት ወይም ባዮሎጂ የሕይወት ጥናት ነው። ባዮሎጂ ሕይወት ያላቸው ነገሮች ባሕሪ፣ ጸባይ፣ አፈጣጠር እና ከአካባቢያቸው ጋር እርስ በርስም ያላቸውን ግንኙነት ያጠናል።
በባዮሎጂ ስር አጅግ በጣም ብዙ ንዑስ ጥናቶች አሉ።

ቃሉ «ባዮሎጂ» የግሪክ ቋንቋ ሲሆን፣ በግሪክኛ «ቢዮስ» (βίος) ሕይወት ማለት ሲሆን «ሎጎስ» (λόγος) ጥናት ማለት ነው።
ሥነ-ህይወት፣ የተፈጥሮ ሰገል (ጥናት) ሲሆን የሚያጠናውም ህያው ፍጥረታትን ሆኖ፣ አቋማቸውን፣ ግብረታቸውን፣ እድገታቸውን፣ አመጣጣቸውን፣ ዝግመተ-ለውጣዊ ይዘታቸውን፣ ሥርጭታቸውን እና የመሳሰሉትን ሁሉ ያካትታል። ይህ ሥነ-ጥናት እጅግ ሰፊና ጥልቅ ሲሆን ብዙ ርዕሶችንና ንዑስ ጥናቶችን ያካትታል። ዓብይ ከሆኑት ርእሶቹ መካከል አምስት የሚሆኑትን የሥነ-ህይወት ጥናት ዋልታዎች አድርጎ መጥቀስ ይቻላል። እነዚህም የሚከተሉት ናቸው፦

የሥነ ሕይወት ንዑስ-ርዕሳን የሚለዩት ፍጥረታትን በሚለኩበትና በሚያጠኑበት ዘይቤ ነው። የህያዋን ሥነ-ጥነተ-ንጥር ህይወታዊ ጥንተ-ንጥርን ያጠናል፤ የሞለኩይል ሥነ-ህይወት የተዋሰበውን ሥነህይወታዊ የሞለኩይል መዋቅር ያጠናል፤ ህዋሳዊ ሥነ-ህይወት የህይወት ገንቢ ጡብ የሆነውን የህዋሳትን ባሕርይ ያጠናል፤ ሥነ-ህይወታዊ ቅንጅታዊ ጥናት የህያዋንን የሰውነት ብልቶችና የብልቶችን መዋቅር፣ አቋማዊና ጥንተ-ንጥራዊ ግብረት ያጠናል፤ ሥነ-ህይወታዊ መዋቅር ደግሞ የሰውነት ክፍሎች ከከባቢያቸው ጋር እንዴት እንደሚሰሩና እንደሚግባቡ ያጠናል።




#Article 44: ሞሪታኒያ (109 words)


ሞሪታኒያ (አረብኛ፡ موريتانيا‎) በይፋ የሞሪታኒያ እስላማዊ ሪፐብሊክ፣ በሰሜን ምስራቅ አፍሪካ የምትገኝ ሀገር ናት። በምዕራብ ከአትላንቲክ ውቂያኖስ፣ በደቡብ-ምዕራብ ከሴኔጋል፣ በምሥራቅና ደቡብ-ምሥራቅ ከማሊ፣ በሰሜን-ምሥራቅ ከአልጄሪያ፣ እና በሰሜን-ምዕራብ ከምዕራባዊ ሣህራ ጋር ትዋሰናለች። የአገሩዋ ስም የመጣው ከጥንቱ የሞሪታኒያ መንግሥት ነው። ዋና እና ትልቁዋ ከተማዋ ኑዋክሾት ናት። 

በዛሬው ሞሪታንኒያ በመጀመሪያ የሠፈሩት የባፎር ሰዎች ነበሩ። እነዚህ ስዎች ከዘላን ሕይወት ወደ ግብርና ከተቀየሩት የመጀመሪያ የሰሃራ ሕዝቦች አንዱ ናቸው። ከ5ኛው እስከ 7ኛው ምዕተ ዓመት፣ ባፎሮች በበርበር ህዝቦች ፍልሰት ምክኒያት ተፈናቀሉ።

ብዙዎቹ የሞሪታኒያ ሕዝብ በመቆያ ግብርና ቢኖሩም ይሄ ወደ ውጭ አገር ለመላክ አይደለም። በተለይ ወደ ውጭ የሚላከው ብረት፣ ፔትሮሊየም፣ እና ዓሣ ናቸው። 

ሞሪታኒያ በ12 ዊላያ በሚባሉ ክልሎችና በአንድ የአስተዳደር አካባቢ ተከፍላልች። እነዚህም ክልሎች በ44 ሙጋታ በሚባሉ ክፍሎች ተከፍለዋል።




#Article 45: ዩጋንዳ (322 words)


ዩጋንዳ ሪፐብሊክ (ወይም ዑጋንዳ) በምስራቅ አፍሪካ የሚገኝ ሀገር ነው። በኬንያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ፣ ሩዋንዳ እና ታንዛኒያ ይዋሰናል። የዩጋንዳ ሰም የመጣው ከቡጋንዳ መንግሥት ነው። 

ከአረቦችና አውሮፓውያን በ1800ቹ ከመድረሳቸው በፊት ብዙ የሚታወቅ ነገር አልነበረም። በ15ተኛ መቶ ክፍለ-ዘመን ችዌዚ የተባለውን መንግስት በአፈ ታሪክ ይገኛል። አረቦችና አውሮፓውያን በ19ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን ሲደርሱ ብዙ መንግሥቶች በቦታው ነበሩ። እነዚህም በንዮሮ ፣ ቡሶጋ ፣ ቡጋንዳ ፣ ቶሮ እና አንኮልን ያጠቃልላሉ። ከ1894 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በታላቁ ብሪታን ስትመራ ነበር። የተለያዩ ቦታዎች ከተዋሃዱ በኋላ ዩጋንዳ በ1914 እ.ኤ.አ. ቅርጿን ያዘች። 

በ1966 እ.ኤ.አ. ጠቅላይ ሚኒስትር ሚልተን ኦቦቴ ሕገ-መንግሥቱን አፍርሰው እራሳቸውን ፕሬዝዳንት አደረጉ። በ1971 እ.ኤ.አ. ኢዲ አሚን ሀገሩን መምራት  ጀመሩ። የኢዲ አሚን አመራር 300,000 የሚገመቱ ዩጋንዳውያንን አስጨርሷል። በ1979 እ.ኤ.አ. የታንዛንያ ኃይሎች ኢዲ አሚንን ከሥልጣን ያስወግዳሉ። ሚልተን ኦቦቴ ወደ ሥልጣን ይመለሳሉ ግን በ1985 እ.ኤ.አ. እንደገና ይወርዳሉ። ያሁኑ ፕሬዝዳንት ዮወሪ ሙሴቪኒ ከ1986 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በሥልጣን ላይ ናቸው።

ፕሬዝዳነንቱ አንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ይመርጣሉ። ያሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አፖሎ ሲባምቢ ናቸው።

ዩጋንዳ በመሬት የተቆለፈች ብትሆንም ታላላቅ የውሃ አካላት አሉ። ከነዚህ ውስጥም ቪክቶሪያ ሐይቅ፣ አልበርት ሐይቅ፣ ክዮጋ ሐይቅ እና ኤድዋርድ ሐይቅ ይዘረዘራሉ። ታላላቅ ከተማዎች በቪክቶሪያ ሐይቅ አቅራቢያ ይገኛሉ። እነዚህም ካምፓላንና እንትቤን ያጠቃልላል።

ዩጋንዳ በ70 ወረዳዎች የተከፋፈለች ስትሆን እነዚህም በአራት አመራር ክልሎች ውስጥ ናቸው። አራቱ አመራር ክልሎች ሰሜናዊ ፣ ምሥራቃዊ ፣ ማዕከላዊ እና ምዕራባዊ ይባላሉ። ወረዳዎቹ በዋና ከተማዎቻቸው ነው የሚሰየሙት። 

በዩጋንዳ ውስጥ የመዳብ እና ነጭ ብረት ክምችቶት አሉ። ግብርና ዋናው የኤኮኖሚ ሴክተር ነው። ከ80 በመቶ በላዩ የስራ ኃይል በግብርና ነው የተሰማራው። ቡና  ዋናው የኤክስፖርት ትርፍ ምንጭ ነው። ከ1986 እ.ኤ.አ. ጀምሮ መንግሥቱ ከሌሎች ሀገሮችና ዓለምአቀፍ ድርጅቶች ጋር በመሆን በኢዲ አሚን ጊዜ የወደቀውን ኤኮኖሚ ለማንሳት ተጣጥሯል።

ዩጋንዳ ለብዙ ብሔረሰቦች ቤት ነው። ከነዚህ ውስጥ ግን አንድ ትልቁን ሕዝብ ብዛት የሚወክል የለም። 40 አካባቢ የሚሆኑ ቋንቋዎች ባሁኑ ጊዜ ይነገራሉ። ከነጻነት በኋላ እንግሊዝኛ ብሔራዊ ቋንቋ ተደርጓል። ብዙ ተናጋሪዎች ያሉት ቋንቋ ሉጋንዳ ሲሆን የአቴሶ ቋንቋ በሁለተኛነት ይከተላል። ኪስዋሂሊ ዋናው የንግድ ቋንቋ ነው።

ስልክ፦

ራዲዮ፦

ቴሌቪዥን፦

ኢንተርኔት፦

የዩጋንዳ የትምህርት ስርዐት የሰባት ዓመት መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት፣ ስድስት ዓመት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እና ከ3 እስከ 5 ዓመት ከሁለተኛ ደረጃ በኃላ ትምህርት ያጠቃልላል።
የትምህርት ስርዐቱ ከ1960ዎቹ እ.ኤ.አ. ጀምሮ በሥራ ላይ ውሏል።




#Article 46: አዶልፍ ሂትለር (334 words)


አዶልፍ ሂትለር (ጀርመንኛ: Adolf Hitler አዶልፍ ሂትለ) እ.አ.አ. ከ1933 ጀምሮ የጀርመን ቻንስለር እንዲሁም ከ1934 ጀምሮ ደግሞ የጀርመን መሪም (Führer) ጭምር የነበረ ሰው ነው።

ሂትለር በሚያዝያ 13 ቀን 1881 ዓ.ም. (20 አፕሪይል 1889 እ.ኤ.አ.) በዛሬይቷ ኦስትሪያ ተወለደ። በሚያዝያ 22 ቀን 1937 ዓ.ም. (30 አፕሪይል 1945 እ.ኤ.አ.) በርሊን ውስጥ ከአንድ ቀን በፊት ካገባት ሚስቱ ኤቫ ብራውን ጋር የራሱን ህይወት አጠፋ።

በ1925 ዓ.ም. መጀመርያ የሂትለር ናዚ ወገን ከጓደኞቹ ወገን ጋር በራይክስታግ ምክር ቤት ትብብር መንግሥት ለመሥራት በቂ መንበሮች አልነበራቸውም። ተቃራኒዎቻቸው የኰሙኒስት ወገን 17% መንበሮች ስለ ነበራቸው የሂትለር ወገኖች የድምጽ ብዛት ሊያገኙ አልተቻላቸውም ነበር። በዚያው ዓመት ግን ከምርጫው ትንሽ በፊት የራይክስታግ ሕንጻ በእሳት ተቃጠለ። ይህ የኰሙኒስቶች ሥራ ነው ብለው የሂትለር ወገን ኰሙኒስት ፓርቲ ቶሎ እንዲከለከል አደረጉ። ስለዚህ ከምርጫው በኋላ የኰሙኒስትን መንበሮች ስለ አጡ የሂትለርም ወገኖች አሁን ከ50% መንበሮች በላይ ስላገኙ፣ የትብብር መንግሥት ሠሩና ወዲያው በድንጋጌ አቶ ሂትለር ባለሙሉ ሥልጣን አደረጉት።

ሂትለር የጻፈው የርዮተ አለሙ ጽሑፍ «የኔ ትግል» (Mein Kampf) ሟርት ብቻ ነው። ለመጥቀስ ያህል፦ «ትኩረቴ ወደ አይሁዶች ስለ ተሳበ፣ ቪየናን ከበፊት በሌላ ብርሃን ለማየት ጀመርኩ። በሄድኩበት ሁሉ አይሁዶችን አየሁዋቸው፤ በብዛትም እያየኋቸው፣ ከሌሎች ሰዎች ፈጽሞ እንድለያቸው ጀመርኩ።»... «የግዛቱ (ኦስትሪያ-ሀንጋሪ) ዋና ከተማ የከሠተውን የዘሮች ውሑድ ጠላሁት፤ የዚህን ሁሉ የቼኮች፣ ፖሎች፣ ሀንጋርዮች፣ ሩጤኖች፣ ሰርቦች፣ ክሮዋቶች ወዘተ. የዘሮች ድብልቀት፤ በሁላቸውም መካከል፣ እንደ ሰው ልጅ መከፋፈል ሻገቶ፣ አይሁዶችና ተጨማሪ አይሁዶች።»

በነበረው ዘረኛ አስተዳደሩ 6 ሚሊዮን የአውሮፓ አይሁዶችን እና 5 ሚሊዮን ሌሎች የተለያዩ ሀገራት ህዝቦችን (በተለይም ስላቮችን) በገፍ (በሆሎኮስት) አስጨርሷል።

በሂትለር ሥር የናዚዎች ፍልስፍና በሂንዱኢዝም እንደሚገኘው በዘር የተከፋፈለ ካስት ሲስተም መመሥረት አይነተኛ ነበር። «አርያኖች» የተባሉት ዘሮች በተለይም የጀርመናውያን ብሔሮች ከሁሉ ላዕላይነት እንዲገኙ አሠቡ። ይህ ዝብረት የተነሣ በርግ ቬዳ ዘንድ በ1500 ዓክልበ. ያህል ወደ ሕንድ የወረሩት ነገዶች «አርያን» ስለ ተባሉ ነው፤ በጥንትም «አሪያና» የአፍጋኒስታን አካባቢ ስም የዘመናዊው ኢራንም ሞክሼ ነበር። በናዚዎቹ እንደ ተዛበው ግን ታሪካዊ ባይሆንም የ«አርያኖች» ትርጓሜ ጀርመናውያን ብቻ ነበሩ፤ ስላቮች (በተለይ የሩስያና የፖሎኝ ሕዝቦች) ግን አርያኖች ሳይሆኑ እንደ ዝቅተኞች ተቆጠሩ። የሂትለር እብደት እየተራመደ በ1926 ዓም የሀንጋሪ ሕዝብ ደግሞ «አርያኖች» ተደረጉ፣ በ1928 ዓም የጃፓን ሕዝብ እንኳን በይፋ «አርያኖች» ተደረጉ፤ በ1934 ዓም የፊንላንድ ሕዝብ ወደ «አርያኖች» በሂትለር ዐዋጅ ተጨመሩ። በሙሶሊኒ ሥር የፋሺስት ጣልያኖች እኛም አርያኖች ነን ቢሉም ጣልያኖች አርያን መሆናቸው በናዚዎች ዘንድ መቸም አልተቀበለም ነበር።




#Article 47: ሴኔጋል (689 words)


ሴኔጋል ወይም የሴኔጋል ሪፐብሊክ በምዕራብ አፍሪካ የሚገኝ ሀገር ነው። ሴኔጋል ከምዕራብ በሴኔጋል ወንዝ፣ ከሰሜን በሞሪታንያ፣ ክምሥራቅ በማሊ እና ክደቡብ በጊኒና ጊኒ-ቢሳው ይዋሰናል። የጋምቢያ ግዛት እንዳለ በሴኔጋል ውስጥ ነው የሚገኘው። የሴኔጋል የቆዳ ስፋት 197,000 ካሬ ኪ.ሜ. የሚጠጋ ሲሆን የሕዝብ ብዛቱ ደግሞ ወደ 14 ሚሊዮን እንደሆነ ይገመታል። የሴኔጋል የአየር ሁኔታ የየምድር ወገብ ሲሆን ደረቅና ዝናባማ ወራት ተብሎ ወደ ሁለት ይከፈላል።

የሴኔጋል ርዕሰ ከተማ ዳካር በሀገሩ የምዕራብ ጫፍ በካፕ-ቨርት ልሳነ ምድር ላይ ይገኛል። ከባህር ጠረፍ ወደ ፭፻ ኪ.ሜ. ገደማ በአትላንቲክ ውቅያኖስ ውስጥ የኬፕ ቨርድ ደሴቶች ይገኛሉ። በ፲፯ኛው ና ፲፰ኛው ክፍለ ዘመናት በቅኝ ገዢ መንግሥታት የተሠሩ የንግድ ተቋማት ከባህር ዳር ይገኛሉ።

በአካባቢው ያሉ ግኝቶች ሴኔጋል ከጥንት ጀምሮ የሚኖርበት እንደነበረ ያሳያሉ። እስልምና የአካባቢው ዋና ሀይማኖት ሲሆን ወደ ሴኔጋል የተዋወቀውም በ11ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን እንደሆነ ይታመናል። በ13ኛውና 14ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን የማንዲንጎ ግዛት በአካባቢው ላይ ተጽኖ ያደርግ ነበር። በዚሁም ጊዜ ነው የጆሎፍ ግዛት የተመሠረተው። በ15ኛው ክፍለ-ዘመን ፖርቱጋል፣ ኔዘርላንድስ እና ኢንግላንድ በአካባቢው ለመነገድ ይወዳደሩ ነበር። በ1677 እ.ኤ.አ. ፈረንሣይ ጎሪ የሚባለውን ዋና የባሪያ ንግድ ደሴት ተቆጣጠረች። ከዛም በ1850ዎቹ እ.ኤ.አ. ፈረንሣይ ቁጥጥሩዋን ወደ መላው ሴኔጋል ማስፋፋት ጀመረች።

በጃኑዋሪ 1958 እ.ኤ.አ.፣ ሴኔጋልና የፈረንሣይ ሱዳን ተቀላቅለው የማሊ ፌዴሬሽንን መሠረቱ። ይህም ፌዴሬሽን በአፕሪል 4፣ 1960 እ.ኤ.አ. ከፈረንሣይ ጋር በተፈረመው የሥልጣን ዝውውር ስምምነት አማካኝ በጁን 20፣ 1960 እ.ኤ.አ. ነጻነቱን አውጀ። በውስጣዊ የፖለቲካ ውዝግቦች ምክኒያት ፌዴሬሽኑ ክሁለት ወር በኋላ ተከፈለ። ሴኔጋልም ነጻነቱን በድጋሚ አውጀ። ሊዎፖልድ ሴንግሆርም የመጀመሪያው ፕሬዘዳንት ሆኖ በኦገስት 1961 እ.ኤ.አ. ተመረጠ። 

ፕሬዝዳንት ሊዎፖልድ ሴንግሆር ሀገሩን መምራት ከጀመረ በኋላ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ማማዱ ዲያ ጋር ባለው አለመስማማት ምክኒያት በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራ መፈንቅለ-መንግሥት በዲሴምበር 1962 እ.ኤ.አ. ተካሄደ። ይህ መፈንቅለ-መንግሥት ያለ ደም ፍስሻ የከሸፈ ሲሆን ማማዱ ዲያም ታሰረ። ከዛም ሴኔጋል የፕሬዝዳነንቱን ሥልጣን የሚያጠነክር አዲስ ሕገ-መንግሥት አሳለፈች። በ1980 እ.ኤ.አ. ፕሬዝዳንት ሴንግሆር በራሱ ፍቃድ ከሥልጣኑ የወረደ ሲሆን በ1981  እ.ኤ.ኣ. በራሱ በሊዎፖልድ ሴንግሆር የተመረጠው አብዱ ዲዮፍ ፕሬዝዳንት ሆነ።

በፌብሩዋሪ 1፣ 1982 እ.ኤ.አ.፣ ሴኔጋል ከጋምቢያ ጋር ተዋሕዳ የሴኔጋምቢያ ኮንፌዴሬሽንን መሠረተች። ከስምንት ዓመት በኋላ ግን በ1989 እ.ኤ.አ. ኮንፌዴሬሽኑ ፈረሰ። ከ1982 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በደቡባዊ ሴኔጋል በካሳማንክ አካባቢ የሚገኙ አማጺዎች ከሴኔጋል መንግሥት ጋር በየጊዜው ተጋጭተዋል። ሴኔጋል ዓለም-አቀፍ ሰላም-አስከባሪ ሃይሎችን በመላክ ትታተወቃለች። 

አብዱ ዲዮፍ ከ1981 እስከ 2000 እ.ኤ.አ. ድረስ ፕሬዝዳንት ነበረ። በሥልጣን ጊዜው አብዱ የፖለቲካ ተሳትፎን አበረታትቷል፣ መንግሥቱ በኤኮኖሚው ላይ ያለውን ቁጥጥር አሳንሷል፣ እና ሴኔጋል ክውጭ በተለይም ከታዳጊ ሀገሮች ጋር ያላትን የዲፕሎማሲ ግንኙነቶችን አጠናክሯል። አብዱ ለአራት የሥራ-ጊዜዎች ፕሬዝዳንት ሆኖ አገልግሏል። በ2000 እ.ኤ.አ. በዓለም-አቀፍ ታዛቢዎች ነጻና ዲሞክራሲያዊ በተባለ ምርጫ የአብዱ ዲዮፍ ተቀናቃኝ አብዱላይ ዋዲ አሸንፎ ፕሬዝዳንት ሆኗል።

ወደ ውጭ አገር የሚላኩ ሸቀጦች በተለይ አሣ፣ ጥጥ፣ ጨርቅ፣ ባምባራ ለውዝ (Vignea subterranea)፣ ካልሲየም ፎስፌት ናቸው።

ሴኔጋል ፕሬዝዳንታዊ ሪፐብሊክ ናት። ከ2001 እ.ኤ.አ. ጀምሮ ፕሬዝዳንቷ በየአምስት ዓመት የሚመረጥ ሲሆን ከዛ በፊት ደግሞ በየሰባት ዓመት ነበር። ያሁኑ ፕሬዝዳንት አብዱላዬ ዋዴ ሲሆኑ በማርች 2007 እ.ኤ.አ. እንደገና ተመርጠዋል።

ሴኔጋል ከ፹ በላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሏት። ፓርላማዋ ሁለት ምክር ቤቶች አሉት። አንዱ ፻፳ መቀመጫዎች ያሉት የብሔራዊ ስብሰባ (እንግሊዝኛ፦ National Assembly) ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ፻ መቀመጫዎች ያሉት ሴኔት ነው። ሴኔጋል ራሱን የቻለ ህግ ተርጓሚ አካል አላት። ዳኛዎቹ የሚሾሙት በፕሬዝዳንቱ ነው። 

በአሁኑ ጊዜ ሴኔጋል የዴሞክራሲ ሂደት ስኬታማ ነው ከሚባሉት የቀድሞ ቅኝ ተገዢ ሀገራት መካከል የምትጠቀስ ናት። የአካባቢ አስተዳዳሪዎች በፕሬዝዳንቱ ነው የሚሾሙት። ማራባውት የሚባሉ የእስልምና ሃይማኖት መሪዎችም በሴኔጋል ጠንካራ የፖለቲካ ተፅእኖ አላቸው፡

ሴኔጋል ወደ 14 ክልሎች ትከፈላለች። የክልሎችና የክልሎች ዋና ከተማዎች ስም ተመሳሳይ ነው።

ከ፪ ሚሊዮን ነዋሪዎች ያሉበት የሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር የሀገሩ ትልቁ ከተማ ነው። ሁለተኛው ፭፻ ሺህ ሰዎች የሚኖሩበት ቱባ ከተማ ነው።

ሴኔጋል ከ12.5 ሚልዮን በላይ የሚሆን ሕዝብ አላት። ከዚህ ውስጥም ወደ ፵፪ ከመቶ በገጠር ነው የሚኖረው።

የአሜሪካ የስደተኖች ኮሚቴ ባቀረበው የ2008 እ.ኤ.አ. የዓለም ስደተኞች አጠቃላይ ቅኝት መሠረት ሴኔጋል በ2007 እ.ኤ.አ. ወደ 23,800 የሚገመቱ ስደተኞች ይኖሩባታል። ከዚህ አብዛኛዎቹ የመጡት ከሞሪታኒያ ነው። ስደተኞቹ በንድዮም፣ ዶዴል እና በሴኔጋል ወንዝ አቅራቢያ በሚገኙ ሠፈሮች ይኖራሉ።

የአገር ይፋዊ ብሔራዊ ቋንቋ ፈረንሳይኛ ሲሆን ከብዙ ኗሪ ቋንቋዎች 11ዱ በተለይም ዎሎፍኛ አገራዊ ዕውቅና አላቸው። ሌሎቹ ባላንታኛ፣ ማንዲንክኛ፣ ፑላርኛ (ፉላኒኛ)፣ ሰረርኛ፣ ሶኒንክኛ፣ ኖንኛ፣ ማንካኛኛ፣ ማንጃክኛ፣ ጆላኛ እና ሀሣኒያ አረብኛ ናቸው። ፖርቱጊዝኛም በትምህርት ቤት ይማራል፣ የካቦ ቨርዴ እና የጊኔ-ቢሳው ኅብረተሠቦችም ፖርቱጊዝኛ ክሬዮል ይናገራሉ። 

ከሴኔጋል ሕዝብ 94% የእስልምና አማኞች፣ 5% ክርስትና (ባብዛኛው ካቶሊክ)፣ 1% የኗሪ አርመኔነት ተከታዮች ናቸው። የመንግሥት ሃይማኖት የለውም። 

በሴኔጋል ልማዳዊ ባሕል ግሪዮት የተባሉ ሽማግሎች ታሪኮቻቸውን በአፍ ቃል ይደግማሉ። ሴኔጋል ለሙዚቃዊ ስልቶቹ ይታወቃል፤ በተለይ የሚወድደው ዘመናዊው ስልት ምባላክስ ተብሏል። በሴኔጋል አበሳሰል በተለይ አሣ፣ ዶሮ፣ በግ፣ አተር፣ ዕንቁላል፣ በሬ ይጠቀማሉ፤ እስላም አገር እንደ ሆነው መጠን ግን አሳማ አይበላም። ኩስኩስ፣ ሩዝ፣ ስኳር ድንች፣ ምስር፣ ጥቁር-ዐይን አተር ደግሞ በሴኔጋል አበሳሰል በሰፊ ይገኛሉ።  በእስፖርት በኩል፣ ከሁሉ የሚወደደው ባህላዊው የሴኔጋል ትግል ግጥሚያ ሲሆን፣ እግር ኳስና ቅርጫት ኳስ ደግሞ እጅግ ይወደዳሉ።




#Article 48: ጋና (184 words)


ጋና በአፍሪካ አትላንቲክ ጠረፍ ላይ የተገኘ አገር ሲሆን ከ24 ሚሊዮን ኗሪዎች በላይ አሉት።

የጋና ስራ ቋንቋ እንግሊዝኛ ሲሆን፣ ሌሎች ኗሪ ቋንቋዎች በተለይም ትዊኛ (አካንኛ) በሰፊ ይነገራሉ። የ«ጋና» ስያሜ በታሪክ የድሮ «ጋና መንግሥት» ወይም «ዋጋዱጉ መንግሥት» ለማክበር በ1949 ዓም ተመረጠ። እንዲያውም ያው መንግሥት እስከ 1068 ዓም ድረስ ከጋና ወደ ስሜን-ምዕራብ በአሁኑ ማሊ ይገኝ ነበር እንጂ የዛሬውን ጋና መቸም አልገዛም። «ጋና» በትክክል  የዋጋዱጉ መንግሥት አለቆች ማዕረግ ሆኖ ነበር። ዋጋዱጉ መንግሥት በ1068 ዓም ግድም ከወደቀ ቀጥሎ፣ የአካን ብሔሮች ከዚያው ፈልሰው በዛሬው ጋና  ሠፈሩና መጀመርያ ግዛቶችን መሠረቱ። ከ1662 እስከ 1949 ዓም ድረስ የአሻንቲ መንግሥት ባካባቢው ቆየ፤ በ1894 ዓም ይህ የብሪታንያ አሻንቲ ጥብቅ ግዛት ሆነ።   

ከ1949 ዓም አስቀድሞ የዩናይትድ ኪንግደም ጥገኛ ግዛት ሲሆን በወርቅ ሀብቱ ምክንያት «የወርቅ ጠረፍ ጥገኛ ግዛት» (ጎልድ ኮስት ፕሮቴክቶሬት) በመባል ይታወቅ ነበር። ከ1984 ዓም ጀምሮ ዴሞክራሲያዊ እና ፓርላሜንታዊ መንግሥት ኖሮታል። አብዛኞቹ ኗሪዎች (70%) በተለይ በደቡቡ ክርስቲያን ሲሆኑ፣ በተለይ በስሜኑ 16% የእስልምና ተከታዮች ናቸው። የተረፉትም የኗሪ አረመኔነትን እምነቶች ይከተላሉ። 

የጋና ዋና ምርቶች ካካዎ፣ ዘይት፣ አልማዝ ናቸው። በአለሙ ከሁሉ ትልቅ የሆነው ሠው ሰራሽ ሐይቅ፣ ቮልታ ሐይቅ፣ በጋና ይገኛል። 

እግር ኳስ ከሁሉ የተወደደው እስፖርት ነው። የጋና አበሳሰል በተለይ በኮቤ፣ ጐርጠብ፣ የስኳር ድንች፣ ባቄላ፣ በቆሎ፣ ኦቾሎኒ፣ ባሚያና ሩዝ ይሠራል።




#Article 49: ዚምባብዌ (420 words)


የዚምባብዌ ሪፐብሊክ ከዚህ በፊት የሮዴዢያ ሪፐብሊክ በመባል የምትታወቅ ስትሆን፣ በደቡብ አፍሪካ የምትገኝ ወደብ-የለሽ ሀገር ናት።
ዚምባብዌ ደቡብ አፍሪካ ፣ ቦትስዋና ፣ ዛምቢያ እና ሞዛምቢክን ትዋሰናለች። የዚምባብዌ ስም የመጣው ከ«ድዚምባ ድዜማᎆ» ሲሆን በሾና ቋንቋ «የድንጋይ ቤቶች» ማለት ነው።

የድንጋይ ዘመን አዳኞች በቦታው ከአምስት ሺህ ዓመታት በፊት እንደነበሩ የሚጠቁም ብዙ መረጃ አለ። እነዚህ ሰዎች ከዛሬው ኮይሳን ብሔር ጋር የሚዛመዱ ሲሆን በባንቱ ብሔር ተተክተዋል። ህይወታቸውን የሚያሳዩ ሥዕሎች በዚምባብዌ ባሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዋሻዎች ይገኛሉ። በብረት ዘመን የነበሩ የባንቱ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች ወደ አካባቢው ከ2 ሺህ ዓመታት በፊት ፈልሰት ጀመሩ። ዛሬ የሀገሩን አራት አምስተኛ ሕዝብ ብዛት የሚሆኑት የሾና ሰዎች የዘር-ሐረጋቸው ወደ ጥንታዊው ሰዎች ያመለክታል። የታላቅ ዚምባብዌ ፍርስራሾች በመካከለኛው ዘመናት የባንቱ ስልጣኔ እንደ ነበረ ያመለክታሉ። ወደ 10ኛው ክፍለ-ዘመን አካባቢ ከሙስሊም ነጋዴዎች ጋር በኢንዲያን ባህር ላይ ንግድ ተጀመረ። ይህም ታላቅ ዚምባብዌ በ11ኛው ክፍለ-ዘመን አንድትሻሻል ረድቷል። ወርቅ ፣ የዝሆን ጥርስ እና መዳብ ይሸጡ ነበር።

በ1828 ዓ.ም.፣ በደቡባዊ ዚምባብዌ የነበሩ የሾና ህዝቦች በንዴቤሌ ብሔር ተወረው ግብር ለመክፈልና ወደ ሰሜናዊ ዚምባብዌ ለመሰደድ ተገደዱ።

በ1881 ዓ.ም. ብሪታኒያዊው ሴሲል ሮድስ ከንዴቤሌ ንጎሥ ሎቤንጉላ የማዕደን ማውጣት ፈቃድ አገኘ። ሴሲል ሮድስ በሊምፖፖ ወንዝና ታንጋኒካ ሐይቅ መካከል ያለውን ቦታ (ዛምቤዚያ ብሎ ሰይሞት) ተመሳሳይ ፈቃድ እንዲሰጡ አበረታቷል። ይህም ቦታው በብሪታኒያ ቅኝ-እንዲገዛ መንገድ ከፍቷል። በ1887 ዓ.ም.፣ የብሪታኒያ ደቡብ አፍሪካ ኮባኒያ የዛምቤዚያን ስም ወደ ሮዴዢያ (ለሴሲል ሮድስ) ለወጠ። ከዛም በ1891 ዓ.ም. ከዛምቤዚ በታች ያለው ቦታ 'ደቡባዊ ሮዴዢያ ተብሎ' በኩባኒያው ተሰየመ። ደቡባዊ ሮዴዢያ ወደፊት ዚምባብዌ ሆነ። ከዛምቤዚ በላይ ያለው ክልል ሰሜናዊው ሮዴዢያ ከተባለ በኋላ አሁን ዛምቢያ ነው።

የንዴቤሌና ሾና ሕዝቦች የሮድስ አመራር ቢቃወሙም አልተሳካም ነበር። ከዛም ነጮች በስፍራው በብዛት ሰፈሩ። ነጮችን የሚጠቅምም የቦታ ክፍፍል ተጀመረ። የዚምባብዌ የቦታ ውዝግብ እስከዛሬ ድረስ ይቀጥላል።

ደቡባዊ ሮዴዢያ እራሱን የሚያስተዳድር የብሪታኒያ ግዛት በ1916 ዓ.ም. ሆነ። በ1945 ዓ.ም. ብሪታኒያ ሁለቱን ሮዴዢያዎች ከኒያሳላንድ (አሁን ማላዊ) ጋር አገናኝታ በአንድላይ የሮዴዢና ኒያሳላንድ ፌዴሬሽን ተባሉ። ረብሻና የአፍሪካዊ ሰሜት ብሪታኒያ ፌዴሬሽኑን በ1956 ዓ.ም. እንድታፈርስ አደረጉ። በ1958 ዓ.ም. ኢያን ስሚዝ ከብሪታኒያ ነጻነት አወጀ። ከዛም በ1962 ዓ.ም. ደቡባዊ ሮዴዢያ የሮዴዢያ ሪፐብሊክ ሆነች።

በኢያን ስሚዝ የሚመራው የነጮች መንግሥት የሮዴዢያን ነጻነት በኖቬምበር 11፣ 1965 እ.ኤ.አ. አወጀ።

የብሪታኒያ መንግሥት ከስሚዝ አመራር ጋር በ1966 እና 1968 እ.ኤ.አ. ያደረገው ንግግሮች ስኬታዊ ስላልነበሩ ዩናይትድ ኔሽንስን በሮዴዢያ ላይ የኢኮኖሚ ማዕቀብ እንዲጣልባት ጠየቀች። የስሚዝ አመራር የሪፕብሊክ መንግሥት መሆኑን በ1970 እ.ኤ.አ. ቢያስታወቅም እውቅና የሰጠው ሀገር ግን የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ብቻ ነበር።

የደፈጣ ተዋጊዎች ነጮችን ማጥቃት ጀመሩ። የስሚዝ አመራር በሮበርት ሙጋቤ ከሚመራው የዚምባብዌ አፍሪካዊ ብሔራዊ ሕብረት እና በጆሱዋ ንኮሞ ከሚመራው የዚምባብዌ አፍሪካዊ ሕዝብ ሕብረት ጋር የድርድር ንግግሮችን ጀመረ። በማርች 1978 እ.ኤ.አ. የስሚዝ አመራር ሊወድቅ ሲደርስ በሊቀ ጳጳስ አቤል ሙዞርዋ በሚመሩ ሶስት ጥቁር መሪዎች ጋር የነጭ ዜጎች ደህንነት እንዲጠበቅ ስምምነት ፈረመ።

በ1979 እ.ኤ.አ. ሁሉም ፓርቲዎች በለንደን ተገናኝተው የእርስ-በርስ ጦርነቱን ለማቆም የላንካስተር ቤት ስምምነትን ፈረሙ።

ሙጋቤ በ ኅዳር 12 ቀን 2010 ዓም ማዕረጋቸውን ተዉ።




#Article 50: ማሊ (272 words)


የማሊ ሪፐብሊክ (ማሊ) በምዕራብ አፍሪካ የምትገኝ ወደብ የለሽ ሀገር ናት። ከምዕራብ አፍሪካ ሀገሮች በስፋት ሁለተኛ ናት። ከአልጄሪያ፣ ኒጄር፣ ቡርኪና ፋሶ፣ አይቮሪ ኮስት፣ ጊኔ፣ ሴኔጋል እና ሞሪታኒያ ጋር ድንበር ትዋሰናለች።

ማንዴ ሕዝቦች አውራጃውን ሠፍረው ተከታታይ መንግሥታት አጸኑ። እነዚህም የጋና መንግሥት፣ የማሊ መንግሥትና የሶንግሃይ መንግሥት ያጠቅልላሉ። በነዚህ መንግሥታት ውስጥ ቲምቡክቱ ለትምርትና ለመገበያየት ቁልፍ ከተማ ነበረች። በ1583 ዓ.ም. በሞሮኮ በተካሄደ ወረራ የሶንግሃይ መንግሥት ኃይል ለማነስ ጀመር።

ማሊ በ1880 እ.ኤ.አ. በፈረንሣይ ቅኝ ተገዝታ «ፈረንሳያዊ ሱዳን» ወይም «የሱዳን ሪፐብሊክ» ትባል ነበር። 

ፈረንሳያዊ ሱዳን በኅዳር 16 ቀን 1951 ዓ.ም. በፈረንሳያዊ ማሕበረሠብ ውስጥ 'ራስ-ገዥ ሁኔታ' አገኝታ በመጋቢት 26 1951 ዓ.ም. ከሴኔጋል ጋር አንድላይ የማሊ ፌደሬሽን ሆኑ። ይህ የማሊ ፌዴሬሽን በሰኔ 13 ቀን 1952 ነጻነት አገኘ። ነገር ግን በነሐሴ 14 ቀን ሴኔጋል ከፌዴሬሽኑ ወጣች። በመስከረም 12 ቀን 1953 ዓ.ም. ፈረንሳያዊ ሱዳን በሞዲቦ ኪየታ ስር ራሷን 'የማሊ ሬፑብሊክ' አዋጀችና ከማሕበረሰቡ ወጣች። 

ሞዲቦ ኪየታ በ1968 እ.ኤ.ኣ. በተደረገው መፈንቅለ መንግሥት ከወረደ በኋላ እስከ 1991 እ.ኤ.አ. ድረስ ማሊ በማውሳ ትራዎሬ ተመራች። በ1991 እ.ኤ.አ. የተካሄዱ ተቃውሞች ወደ መፈንቅለ-መንግሥት አመሩ። ከዚያም የተሸጋጋሪ መንግሥት ተቋቋመና አዲስ ሥነ-መንግሥት ተጻፈ። በ1992 እ.ኤ.አ. አልፋ ዑመር ኮናሬ የማሊን የመጀመሪያ ዴሞክራሲያዊ ምርጫን አሸነፉ።

ማሊ ከባሕር ጋር ግንኙነት የላትም። የሀገሩ አብዛኛው ክፍል በሰሐራ በረሃ ውስጥ ይገኛል። ከተፈጥሮ ሀብቶች ውስጥ ወርቅ፣ ዩራኒየም፣ ፎስፌት፣ ካዎሊን፣ ጨው፣ ኖራ (ላይምስቶን) ይጠቀሳሉ።

የማሊ ፓርላማ 147 ሰዎች ሲኖረው እነዚህ ተወካዮች በህዝብ ብዛት ነው የሚመረጡት።

ማሊ በስምንት ክፍለ-ሀገሮችና አንድ ከተማ ተከፋፍላለች።

ማሊ ከዓለም ደሀ ሀገሮች አንዷ ስትሆን 65 ከመቶ የሚሆነው መሬት በረሃ ነው። አብዛኛው የኤኮኖሚ እንቅስቃሴ በኒጅር ወንዝ አካባቢ ነው የሚካሄደው። 10 ከመቶ የሚሆነው ሕዝብ ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሰ የሚኖር ሲሆን 80 ከመቶ የሚሆነው የሥራ ሃይል በእርሻና ዓሣ ማጥመድ ተሰማርቷል። የኢንዱስትሪው እንቅስቃሴ በእርሻ ምርቶች ላይ ያተኩራል። የሸክላ ሥራ በሴቶች የሚከናወን ሲሆን በነጋዴዎች በገበያዎች ይሸጣል። ሸክላዎቹ የሚሰሩበት ባሕላዊ ሂደት የቱሪስት መሳቢያ ነው።




#Article 51: ሎዥባን (210 words)


ሎዥባን (lojban) በ1987 እ.ኤ.አ. የተፈጠረ አንድ ሰው ሠራሽ ቋንቋ ነው። ቋንቋው የተፈጠረ በLogical Languages Group (LLG, ትክክለኛ አሰተሳሰብ ያለው ቋንቋ ቡድን) በሚባል የዋሺንግተን ዲሲ ተቋም ነው። LLG በ1955 እ.ኤ.አ. መጀመርያ የፈጠረ ቋንቋ ሎግላን ተባለ። ሎዥባንም ከሎግላን 'ተሻሽሎ የወጣ ቋንቋ' ይባላል። የሎዥባን ስም የተወሰደ ከ'ሎግዢ' (ትክክለኛ አስተሳሰብ) እና 'ባንጉ' (ቋንቋ) ነው።

አላማቸው ስዋሰዉ በሰዎችም ሆነ በኮምፕዩተር በቀላል የሚታወቅ የትክክለኛ አስተሣሠብ ቋንቋ ለመፍጠር ነበር። ሌሎች ሰው ሰራሽ ቋንቋዎች ለምሳሌ ኤስፔራንቶ የተፈጠሩ በተለይ ከአውሮጳ ቋንቋዎች ቃላት በመልቀም ነበር። ሆኖም ሎዥባን ባሕላዊ ገለልተኝነት ለማሳየት ሙከራ እያደረገ ነው። ነገር ግን ሎዥባን ከአሥር በላይ የተማሩት ሰዎች ገና ስለሌለው እስካሁን ከድረገጽ በቀር ምንም የተደረጀ ሥነ ጽሑፍ የለውም። 

ቃላቱ በኮምፒዩተር የተፈጠሩበት መንገድ ብዙ ተናጋሪዎች ያላቸውን 6ቱ የሰው ልጅ ቋንቋዎች በማነጻጸር ነበር። እነዚህም ቋንቋዎች ቻይነኛ፣ ህንዲ/ዑርዱ፣ እንግሊዝኛ፣ እስፓንኛ፣ ዐረብኛና መስኮብኛ ናቸው። ለያንዳንዱ ቃል ስንት ድምጾች በጋራ ከነዚህ ቋንቋዎች ጋራ እንዳለው በኮምፒዩተሩ ተቆጠረ። ስለዚህ ከሁሉም ብዙ ተናጋሪዎች ለቻይነኛ በመኖራቸው ብዙዎች ድምጾች የተለቀሙ ከቻይነኛ ነበር። 

የእያንዳንዱ ቃል ሥር በ5 ፊደል ይጻፋል። ለምሳሌ፦

እነዚህ በኮምፒዩተር የተፈጠሩ ቃላት እንደ ሌላ ቋንቋ ባይመስሉም፣ ክፍሎቻቸው ግን ከትልቁ ቋንቋዎች መገኘታቸው ሊታይ ይቻላል። ለምሳሌ በፕረኑ (ሰው) የእንግሊዝኛ ፐር- (per-) ከፐርሶን (person)፣ እና የቻይንና ረን (人) ይታዩበታል። ሹክታ ደግሞ የእንግሊዝኛ -ኡክ ከቡክ (book)፣ የቻይንኛ ሹ (书)፣ እና የዐረብኛ ኪታብ ( كتاب ) ያዋሕዳል። ቫንዡ የፈረንሳይኛ ቫን (vin) እና የቻይንኛ ጅዮ (酒) ይመስላል።

የሎዥባን ስዋሰው እንደ ኮምፕዩተር ቋንቋ ይመስላል። 




#Article 52: ስዋሂሊ (134 words)


ስዋሂሊ ፡ (ወይም ፡ ኪሷሂሊ Kiswahili) ፡ በምሥራቅ ፡ አፍሪቃ ፡ የሚናገር ፡ የባንቱ ፡ ቋንቋዎች ፡ ቤተሠብ ፡ ቋንቋ ፡ ነው። የስዋሂሊ ፡ ሕዝብ (፭ ፡ ሚሊዮን ፡ ተናጋሪዎች) ፡ ልደት ፡ ቋንቋ ፡ ከመሆኑ ፡ በላይ ፡ ለ ፴ ፡ እስከ ፡ ፶ ፡ ሚሊዮን ፡ ሌሎች ፡ ሰዎች ፡ ሁለተኛ ፡ ቋንቋ ፡ ሆኗል። የስዋሂሊ ፡ ስም ፡ መነሻ ፡ ከዓረብኛ ፡ ቃል ፡ «ሰዋሂል» ፡ ነበር ፤ ይህም ፡ የ«ሳኸል» ፡ (ማለት ፡ ዳር) ፡ ብዙ ፡ ቁጥር ፡ ነው። ስለዚህ ፡ የ«ስዋሂሊ» ፡ ትርጉም ፡ የ(ባሕር) ፡ ዳረኞች ፡ ቋንቋ ፡ ሊሆን ፡ ይችላል። የቋንቋው ፡ ቤተሰብ ፡ ባንቱ ፡ ሲሆን ፡ ተናጋሪዎቹ ፡ መርከበኞችና ፡ ነጋዴዎች ፡ በመሆናቸው ፡ መጠን ፡ ከዓረብኛ ፣ ከፋርስ ፣ ከህንዲ ፣ እና ፡ ከቻይንኛ ፡ ቢሆንም ፡ ብዙ ፡ ቃሎች ፡ ተበድረዋል። 




#Article 53: የጥንተ ንጥር ጥናት (191 words)


ኬሚስትሪ ወይም የጥንተ-ንጥር ጥናት የቁሶችን አሰራር እና ጸባይ ያጠናል። 

የ«ኬሚስትሪ» ስም የሚመጣ ከእንግሊዝኛ ሲሆን እሱ የተወለደ ከ1700 ዓ.ም. አካባቢ በፊት «አልኬሚ» ከተባለ ሌላ ጥናት ነበር። ይህም አልኬሚ ዋና ዒላማ ብረት ወደ ወርቅ ለመቀየር ነበር። የማይቻል ምኞት እንደ ነበር የዛኔ ተገነዘበ። አልኬሚ የሠራ ሰው 'አልኬሚስት' ተባለ ወይም በአጭሩ 'ኬሚስት'። በኋላ ትውልድ የኬሚስት ሥራ 'ኬሚስትሪ' ተባለ። 

የ«አልኬሚ» ስም ደግሞ የወጣ ከዓረብኛ «አል-ኪሚያ» (الكيمياء ወይም الخيمياء) ማለት «የመቀየር ጥበብ» ሲሆን የዚህ ቃል መነሻ በእርግጠኝነት አይታወቅም። ወይም ከግሪክ «ቄሜያ» (χημεία, ቀላጭ ብረታብረት) ወይም ከግብጽ ዱሮ ስም «ከመት» («የከመት ጥበብ» ለማለት) ሊሆን ይችላል።

እንዲሁም በእንግሊዝኛ chemical ኬሚካል የሚለው ቃል ድምጽ ኃይል ከ«ኬሚስትሪ» ሲሆን፣ በዐማርኛ «ጥንተ ንጥር» መባሉ ከግዕዝ ነው። «ንጥር» ማለት የተነጠረ ወይም የተጠራ እንደ ንጥር ቅቤ ቢሆን ፅንሰ ሀሣቡ ከነጥሮን (ሶዲየም ከሰላ ወይም አምቦ አመድ) ጋር፣ በግሪክም /ኒትሮን/፣ ዓረብኛ /ናጥሩን/፣ ዕብራይስጥ /ኔቴር/፣ ግብጽኛ /ነቸሪት/ («የአምላክ») እንደ ተዛመደ ይታሥባል። 

ፔሪዮዳዊ ሢስተምክፍለ ጊዜአውዊ ስርአቱ ባምርኛ period የሚለውን´ ጴር ዮድ´ ተብሎ ማድመጽ ዪቻል ይሆን ? ግ እዝ የባህር ማዶን ቃል ውደራሱ ቛንቛ ማድመጽ ስፊ ልምምድ አለው፡ ሌሎች ቛንቋዎች ይህን ያደርጋሉ፡፡

                          ዚንቅ ዚንክ
                       አሞሌ
                      ሆምጣጤ
                       ኖራ
                     ዝርግፍ-ብረት
                        
   በንግሊዘኛው  ሊድ   በአማርኛው  ቴሞን  ውይም  እርሳስ
    ነሃስ
  እንቆቅ--ብረት  (ኮፐር)                   
  ኒኬል
አሴቶ አቼቶ አሴቲን
ባሩድ....ፈንጂ ማቴርያዉነት (ማቴርያል)
መርዛሜነት.... የተፍጥሮ ዘረ መሰረት (ኤሌሜንት) ባህርይ




#Article 54: መለጋሲ (123 words)


መለጋሲ (Malagasy) ከአውስትሮኔዚያን የቋንቋ ቤተሠብ ቋንቋዎች ሁሉ ምእራበኛው ሲሆን የማዳጋስካር መደበኛ ቋንቋ ነው። 1500-2000 አመታት ከዛሬ በፊት ከእንዶኔዚያ የመጡ የማዳጋስካር ኗሪዎች ቋንቋ በመሆኑ፣ ከቃላቱ መዝገብ 90% ከመቶ በቦርኔዮ እንዶኔዚያ ከተገኘው ቋንቋ ከማአንያን ጋራ ተመሳሳይ ነው። የቀሩትም 10% ቃላት በተለይ ከአፍሪቃ ቋንቋዎች (ከባንቱ) እና ከአረብኛ ተበድረዋል። 

በአረፍተ ነገር ውስጥ ግሡ ከሁሉ ይቀድማል። ይህ ተራ እንደ ዕብራይስጥ ይመስላል እንጂ ለብዙዎች ቋንቋዎች የተለመደ አይደለም። በየቃሉ ውስጥ ከመጨረሻው ክፍለ-ቃል በፊት የሆነው ክፍለ-ቃል አናባቢ ይጠበቃል፤ ሌሎቹ አናባቢዎችም ይነበነባሉ (በሙሉ አይስሙም)፤ ስለዚህ Malagasy እንደ ፈረንሳይኛ አጻጻፉ Malgache (መልጋሽ) ይመስላል። 

ነገር ግን መጨረሻው ክፍለ-ቃል -ka (-ከ), -tra (-ትረ), ወይም -na (-ነ) ሲሆን፣ የተጠበቀው ከመጨረሻው 2 በፊት የሆነው ክፍለ-ቃል ነው። በዚህ መንገድ fanorona የሚለው ቃል እንደ ፈኑርን ይመስላል። (በአጻጻፍ ረገድ፣ o የሚለው ፊደል እንደ ኡ ይመስላል፤ -i በመጨረሻ ሲሆን -y ይሆናል።)




#Article 55: ናዋትል (111 words)


ናዋትል (nāhuatl, mexìcatlàtōlli, Nawatl) በኡቶ-አዝቴካዊ የቋንቋ ቤተሠብ የሚከተት በሜክሲኮ ኗሪዎች የሚናገር ቋንቋ ነው። በተለይ እስፓንያውያን በ16ኛው መቶ ዘመን ከወረሩ አስቅደሞ በጣም ትልቅና መደበኛ ቋንቋ ሆኖ ነበር። እስከ ዛሬ ግን በ1.5 ሚሊዮን ኗሪዎች በሜክሲኮ እየተናገረ ነው። የዛሬውኑ ናዋትል ከስፓንኛ ታላቅ ተጽኖ ተቀብሏል። ኣብዛኛው ተናጋሪዎቹ ስፓንኛ ደግሞ የሚችሉ ናቸውና። 

 

ስፓንያውያን በደረሡ ጊዜ ናዋትል የራሱ ጽሕፈት ነበረው። ይህ ጽሕፈት እንደ ጥንታዊ ግብጽ ስዕል ጽሕፈት ይመስል ነበር። ነገር ግን እነዚህ ጽሑፎች በአብዛኛው በካቶሊኮች ስለ ተቃጠሉ፣ ዛሬ ቋንቋው የሚጻፈው በላቲን ፊደል (አልፋቤት) ሆኗል።

በናዋትል ሰዋስው አያሌ ባዕድ መነሻዎችና መድረሻዎች አንድላይ ሊቀጣጥሉ ይችላሉ። ስለዚህ አንድ ቃል እጅጉን እንዲረዝም ተችሏል። 

አንዳንድ ቃል በስፓንኛና በእንግሊዝኛ አማካኝነት በአለሙ ቋንቋዎች በሰፊ ይገኛሉ። ለምሳሌ የሚከተሉት የአማርኛ ቃላት መጀመርያቸው እንዲያውም ከናዋትል ቃላት ነበሩ፦




#Article 56: ብራዚል (1707 words)


ብራዚል በደቡብ አሜሪካ በመሬት ስፋትም ሆነ በሕዝብ ብዛት አንደኛዋ ትልቅ አገር ነች። በአለም አንደኛ ቡድን በእግር ኳስ አላት።

ይፋዊ ቋንቋ ፖርቱጊዝ ሲሆን መነጋገሪያው ግን በፖርቱጋል ከሚነገረው መደበኛ ፖርቱጊዝ እንደ ቀበሌኛ ትንሽ ይለያል። ከዚያ በቀር ብዙ የጥንታዊ ኗሪዎች ልሳናት የሚችሉ ጎሣዎች ይገኛሉ። አንዳንድ ማህበረሠብ ደግሞ ጀርመንኛን ወይንም ጣልኛን ይናገራል።

ሃይማኖት በብራዚል (2010)

ሃይማኖት ፣                                                                 መቶኛ

ካቶሊካዊነት                                                                 64.6%

ፕሮቴስታንት                                                                22.2%

አግኖስቲስቲዝም + ኤቲዝም + ሃይማኖት የለውም                8%

ሌሎች እምነቶች                                                            3.2%

መናፍስታዊ እምነት                                                       2%

ሕገ-መንግሥቱ የአምልኮ ነፃነትን እና የቤተክርስቲያን-መገንጠልን የመለያየት ነፃነት ያወጣል ፣ ብራዚል በይፋዊ ዓለማዊ መንግስት ያደርገዋል ፣ ምንም እንኳን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የበለጠ ልዩ መብት ብትኖራትም ማንኛውንም አይነት የሃይማኖት መቻቻል ይከለክላል.398 ከላይ የተጠቀሰው የካቶሊክ እምነት በአገሪቱ ውስጥ ትልቁ እምነት መሆኑን ነው ፣ ስለሆነም ብራዚል በዓለም ውስጥ ትልቁ የካቶሊክ ብዛት አላት ፡፡

እ.ኤ.አ. በ 2010 በተደረገው ቆጠራ መሠረት በብራዚል ውስጥ በጣም ተከታዮች ያሉባቸው ሃይማኖቶች የካቶሊክ እምነት ናቸው ፣ ይህም የህዝብ ብዛት 64.6% (123 ሚሊዮን) ይወክላል ፣ የፕሮቴስታንት እምነትም በተለያዩ ገጽታዎች (በታሪካዊ እና በ Pentecoንጠቆስጤ) በ 22.2 % (42.3 ሚሊዮን) እና መናፍስታዊነት ፣ 2% (3.8 ሚሊዮን) ተከትለዋል ፡፡ 8% (15.3 ሚሊዮን) ማንኛውንም ሃይማኖት አይከተሉም (ኤቲስት ፣ ፕሮሞሽን ፣ ፕሮቲኖች ፣ ወዘተ) ፡፡

የፌዴራል መንግሥት ፣ የክልሎች ወይም የፌዴራል አውራጃ እንዲሁም መዘጋጃ ቤቶች የየራሳቸውን የትምህርት ሥርዓቶች ማስተዳደርና ማደራጀት እንዳለባቸው የፌዴራል ሕገ መንግሥትና የመመሪያ መመሪያዎች እና ብሔራዊ ትምህርት (ኤል.ኤስ.ቢ.) ይወስናል ፡፡ እያንዳንዳቸው እነዚህ የሕዝብ ትምህርት ሥርዓቶች ገንዘብ የሚያመነጭ የራሱ የሆነ የጥገና ሥራ ኃላፊነት አለባቸው ፡፡ አዲሱ ህገ-መንግስት 25% የስቴቱን በጀት እና 18% የፌዴራል ግብር እና የማዘጋጃ ቤት ክፍያዎችን ይይዛል።

በዩኤንዲP መረጃ መሠረት እ.ኤ.አ. በ 2007 የመማሪያ ብዛቱ 90% ነበር ፣ ይህ ማለት 14.1 ሚሊዮን ብራዚላዊያን ማንበብና መጻፍ አልቻሉም ፡፡ ተግባራዊ ማንበብና መጻፍ ወደ 21.6% አድጓል ፡፡ ከ 6 እስከ 14 ዓመት ባለው ቡድን ውስጥ 97% ፣ እና ከ 15 እስከ 17 ዓመት ባለው ሰዎች ውስጥ 82.1% ነበር ፡፡ ዕድሜያቸው ከ 10 ዓመት በላይ ለሆኑት አማካይ የጥናት ጊዜ 6.9 ዓመታት ነበር ፡፡

ከፍተኛ ትምህርት የሚጀምረው ከሁለተኛ ደረጃ በሚመረቅበት ጊዜ ሲሆን ፣ በልዩ ልዩ አካዴሚያዊ ወይም ሙያዊ የሥራ መስክ ልዩ ችሎታዎችን ሊሰጡ የሚችሉ አማራጮችን ሊሰጥ ይችላል ፡፡ በትምህርት ቤቱ ላይ በመመርኮዝ ተማሪዎች በድህረ-ምረቃ ኮርሶች Stricto sensu ወይም ላato sensu ትምህርታቸውን (ዳራ) ማሻሻል ይችላሉ / ከፍተኛ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ለመከታተል በሕግ መመሪያዎች እና የትምህርት ማዕከላት ሁሉም ደረጃዎች ማጠናቀቅ ግዴታ ነው ፡፡ ተማሪው አካላዊ ፣ አእምሯዊ ፣ የእይታ ወይም የኦዲት ክፍል ቢሆን ምንም ዓይነት የአካል ጉዳት የማያደርስበት እስከሆነ ድረስ ፣ ቅድመ-ትምህርት ቤት ፣ መሠረታዊና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ያስተምራል ፡፡

የብራዚል የህዝብ ጤና ስርዓት-ሲቲማ ኒያኒ ዴ ሳኡዴ-በሁሉም የመንግስት ደረጃዎች የሚተዳደር ሲሆን የግል የጤና ሥርዓቶች ደግሞ ተጓዳኝ ሚና ይጫወታሉ የህዝብ ጤና አገልግሎቶች ለሁሉም ብራዚላዊያን እንደሚሰጡ ሁለንተናዊ ናቸው ፡፡ ነዋሪዎችን በነፃ ሆኖም የጤና ማዕከላትና ሆስፒታሎች ግንባታና ጥገና በግብር የተደገፈ በመሆኑ አገሪቱ በየዓመቱ ከ 9 በመቶው GDP ን በጤና ወጭዎች ታወጣለች ፡፡ በ 1000 ነዋሪ ሐኪሞች እና 2.4 የሆስፒታል አልጋዎች ፡፡

እ.ኤ.አ. በ 1988 ሁለንተናዊ የጤና ስርዓት ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ የተሻሻሉ መሻሻል ቢኖርም በብራዚል በሕዝባዊ ጤና ላይ አሁንም ብዙ ችግሮች አሉ ፡፡ መፍትሄ ለማግኘት ከ 2006 ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል የሕፃናቱ ከፍተኛ መጠን (2.51%) እና የእናቶች ሞት (በ 1000 የወሊድ ሞት 73,7 ሰዎች) ናቸው ፡፡ ተላላፊ ባልሆኑ ተላላፊ በሽታዎች ምክንያት እንደ የልብና የደም ቧንቧ በሽታዎች (151,00 በአንድ 100,000 ነዋሪ ሞት) እና ካንሰር (ከ 100,000 ነዋሪዎች 72.7 ሰዎች ሞት) በብራዚል ህዝብ ጤና ላይም ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራሉ ፡፡ በመጨረሻም ፣ እንደ አንዳንድ የመኪና አደጋዎች ፣ አመፅ እና ራስን ማጥፋትን ያሉ አንዳንድ ውጫዊ ግን መከላከል ምክንያቶች በአገሪቱ ውስጥ ከሞቱት የ 14.9% ሰዎች ሞት ምክንያት ሆነዋል ፡፡

የብራዚል ሥነ ጥበብ ከ 19 ኛው ክፍለዘመን መጀመሪያ በፊት በብራዚል ውስጥ ዋነኛው ዘይቤ በብራዚልነት ፣ በዘመናዊነት ፣ አገላለፅነት ፣ ኪዩቢዝም ፣ እስከ ግብረ-ሰዋዊነት ድረስ በተለያዩ ዘይቤዎች ተዳሷል ፡፡ ሆኖም የብራዚል የመጀመሪያዎቹ የጥበብ ምሳሌዎች ከ 15,000 ዓመታት ወዲህ ባለው በሴራ ዴ ካቪቫራ ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ ዋሻ ሥዕሎች ናቸው ፡፡ እንደ ቅድመ-ሀፓናዊ ጊዜዎች ካሉ ትናንሽ የሴራሚክ እና የድንጋይ ቅርፃ ቅርጾች ብቻ የተወሰዱት ፡፡ ዋና የኪነ ጥበባዊ መግለጫዎች በኋላ ፣ በዚህ ደረጃ በተደረጉት ሥዕሎች ፣ ቅርፃ ቅርጾች እና ሕንፃዎች መሠረት እንደተመለከተው በብራዚል ሥነጥበብ ውስጥ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳደረ የሥነጥበብ እንቅስቃሴ ባሮክ ነበር ፡፡

ብሄራዊ ነፃነት ከመጀመሩ ጥቂት ቀደም ብሎ ፣ የኪነ-ጥበባዊ ኢምፔሪያል አካዳሚ ተመሠረተ ፣ ከአስርተ ዓመታት በኋላ በሀገሪቱ ውስጥ የ 19 ኛው ክፍለዘመን ዋና የኪነ-ጥበብ እንቅስቃሴ ብቅ እያለ የብራዚል ሮማንቲዝም ፡፡ በዚህ ወቅት ፣ የአካዳሚክ ጥበብ ወደ “ወርቃማ ዘመን” ደርሷል ፣ እንደ ቪክቶር ሜይለሌስ እና ፔድሮ አሜሪክ ፣ ተወካዮች ከአውሮፓ አቻው የሚለዩት እንቅስቃሴዎችን በመፍጠር እንቅስቃሴን ከፈጠሩ ፡፡ እ.ኤ.አ. በ 1922 “ዘመናዊው የጥበብ ሳምንት” ተካሄደ ፡፡ ሳኦ ፓውሎ ውስጥ የብራዚላዊው ዘመናዊነት መጀመሪያ ምልክት የሆነ ክስተት ፡፡ እንደ አኒታ ማልፋቲቲ ፣ ታርላሻ አምባ አማኤል ፣ ኤሚሊኖ ዲ ካልቫካናቲ ፣ ቪሲቴ ዶ ሬጎ ሞንቴሮ ፣ ቪክቶር ብሬret ፣ ሲንዲዶ ፖርትዋንሪ እና ኦስካር ኒየሜር ያሉ አርቲስቶች ፣ በተመሳሳይ ጊዜ በብራዚል ውስጥ የኪነጥበብ ጥበባት እድገትና እድገትን እንደረዱት ፡፡ .

ብራዚል ካቴድራል ፣ በብራዚል የሥነ ሕንፃ ኦስካር ኒዬየር የተነደፈው ፣ እ.ኤ.አ. በ 1987 የዓለም ቅርስ ጣቢያ መሆኑ ተገለጸ ፡፡

በአገሪቱ ታሪክ ውስጥ ከታዩት እጅግ ግዙፍ ወንበዴዎች አንዱ የሆነው ዕረፍቱ ፡፡

የብራዚል ሲኒማ ሥነ ጥበብ በ 19 ኛው መቶ ዘመን መገባደጃ ላይ እንደ ገና የተወለደ ነው። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ለምርትዎቻቸው አዲስ ዓለም አቀፍ ዕውቅና እየሰፋ ነበር ፡፡ በርካታ የብራዚል ፊልሞች የአለምአቀፍ ሃያሲያን ዕውቅና ያገኙ እና በምድባቸው ውስጥ በጣም አስፈላጊ የሆኑ ሽልማቶችን አግኝተዋል ፡፡ ለምሳሌ ፣ ኒኒስ (በዮሴ ፓዳልታ) በሮten ቲማቲሞች መሠረት በአሜሪካ ውስጥ ምርጥ ግምገማዎች ያለው የውጭ ፊልም ነው ፣ የ ተስፋ ሰጪዎች (በ Anselmo Duarte) በካኒስ ፊልም ፌስቲቫል የፓልሜ ዲ ኦርን አሸነፈ። ኒዲድ ደ ዲዮስ (በፈርሬስ ሜየርሌል) ታይምስ መጽሔት ከተመረጡት 100 ምርጥ ፊልሞች መካከል አንዱ ሆኖ ተመረጠ።

በተቃራኒው ፣ ምንም እንኳን ቲያትር ከቅኝ ግዛት ዘመን ጀምሮ በጄይስቶቹ ወደ አገሪቱ ያስተዋወቀ ቢሆንም ፣ ይህ ጥበብ እስከ 19 ኛው ክፍለዘመን ድረስ በብራዚል ህዝብ ዘንድ ፍላጎት አልፈጠረም ፡፡ ሆኖም በ 20 ኛው ክፍለ ዘመን አምባገነናዊ አገዛዞች ውስጥ ቲያትሩ በመንግሥት ሳንሱር ቁጥጥር ስር የነበረ ሲሆን በአገሪቱ ውስጥ ሊታዩ የሚችሉትን የሥራ ዓይነቶች እና ዓይነቶች ይገድባል ፡፡ በመጨረሻው የወታደራዊ ስርዓት ውድቀት ወቅት በርካታ ብራዚላዊያን ተዋናዮች እንደ ጌራል ቶማስ ፣ ኡልሲስ ክሩዝ ወዘተ የመሳሰሉትን በሚሰማሩበት መስክ በዓለም ዙሪያ ጎልቶ ወጥተዋል ፡፡

የብራዚል ሙዚቃ በአፍሪካ ፣ በአውሮፓ እና በአሜሪኒያን ቅር influencedች ተፅእኖ ያላቸውን የተለያዩ የክልል ዘይቤዎችን ይ enል ፡፡ ከጊዜ በኋላ ሳባ ፣ ብራዚላዊ ዝነኛ ሙዚቃ ፣ ቾሮ ፣ ሴርታንጆ ፣ ቢርጋ ፣ ፎሮ ፣ ፍሮvo ፣ ማራካታ ፣ ቦሳ ኖቫ ፣ የብራዚል ዓለት እና አዜኤልን ጨምሮ በብዙ የተለያዩ ዓይነቶች ውስጥ ብሔራዊ ሙዚቃ ተፈልሷል ፡፡ አንቶኒዮ ካርሎስ ኢዮብም ፣ ሄሪ Villa-Lobos ፣ Pixinguinha እና Hermeto Pascoal በውጭ አገር በጣም የታወቁ ሙዚቀኞች በመሆናቸው የዓለም አቀፋዊ ዕውቅና አግኝተዋል ፡፡

የብራዚል ሥነ ጽሑፍ የተጀመረው በ 16 ኛው ክፍለዘመን ብራዚል ከተገኘ በኋላ በዬይቶች ከተበረታቱት የስነፅሁፍ እንቅስቃሴ የተነሱ ናቸው፡፡በመጀመሪያው ጊዜ ከፖርቹጋላዊ ሥነ ጽሑፍ ጋር የተቆራኘ ቢሆንም የነፃነት ጊዜ እና እስከ ምዕተ ዓመቱ ድረስ ነበር ፡፡ XIXX እንደ ሮማንቲሲዝም እና እውነታዊነት ባሉ እንቅስቃሴዎች ተጽዕኖ ነበር ፡፡ የብራዚል ሥነ ጽሑፍ እ.ኤ.አ. በ 1922 ከሌሎች ሀገራት ስራዎች ጋር የተጣራ ዕረፍትን ያሳለፈውን የዘመናዊ ስነ-ጥበባት ሳምንት (እ.አ.አ.) የራሱ የሆነ ትምህርት ቤቶቻቸውን ወደ ዘመናዊው እና የመጀመሪያዎቹ ትውልዶቻቸው እንዲመሰረት መጣ ፡፡ በእውነት ነፃ አውጪ ፀሐፊዎች። እንደ ማኑዌል ባንደራ ፣ ካርሎስ ዶርሞንድ ደ አንድሬስ ፣ ጆዋ ጉዋማዌስ ሮሳ ፣ ክላሲስ ሊሴሰር እና ሴሲሊያ ሜይሌስ ያሉ በርካታ ታዋቂ ብራዚላዊ ጸሐፊዎች ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የተገኙ ናቸው።

የብራዚል ሳይንሳዊ ምርት የተጀመረው በ 19 ኛው ክፍለ ዘመን የመጀመሪያዎቹ አስርት ዓመታት ውስጥ ሲሆን ፣ በፖርቱጋል ልዑል ገዥ ጁዋን ስድስተኛ የሚመራው የንጉሣዊው ቤተሰብ እና የፖርቹጋላዊው መኳንንት በሪዮ ዲ ጃኔሮ የፖርቹጋልን ናፖሊዮን ቦናpart ጦር ወረራ በመሸሽ በደረሰ ጊዜ ነበር ፡፡ እስከዚያ ጊዜ ድረስ ብራዚል ዩኒቨርሲቲዎች ወይም ሳይንሳዊ ድርጅቶች በሌሉበት የፖርቹጋላዊ ቅኝ ግዛት ነበረች ፣ ከስፔን ግዛት የአሜሪካ ቅኝ ግዛቶች በተቃራኒ ምንም እንኳን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ማንበብና መጻፍ ያልቻሉ ሰዎች ቢኖሩም ከ 16 ኛው ክፍለዘመን ጀምሮ ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ የዩኒቨርሲቲዎች ቁጥር ነበረው ፡፡ 

የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ልማት ብሔራዊ ምክር ቤት (ሲ.ሲ.ፒ.) የሳይንሳዊ እና የቴክኖሎጂ እንቅስቃሴዎችን እድገትና እድገትን የመመራት ፣ የማስተዳደር እና የማስፋፋት የመንግስት ኤጀንሲ ነው ።30 ነገር ግን በብራዚል የቴክኖሎጂ ምርምር በአብዛኛው የሚከናወነው በ የሕዝብ ዩኒቨርሲቲዎች እና የምርምር ተቋማት ፡፡ ከታወቁት የብራዚል ቴክኖሎጅያዊ ልማት ማዕከላት መካከል ኦስዋርዶ ክሩዝ ፣ Butantan ፣ የአየር ማቀፊያ ቴክኖሎጂ አጠቃላይ ትዕዛዝ ፣ እቴሬዛ ብራናርራራ ደ ፓስሲሳ አግሮፔኩሲያ እና INPE ተቋማት ናቸው ፡፡

ብራዚል በላቲን አሜሪካ ውስጥ ለማስነሻ ተሽከርካሪዎች እና ሳተላይቶች ለማምረት ትልቅ ሀብትን ስለሚመደብ በላቲን አሜሪካ ውስጥ በጣም ከተሻሻሉ የቦታ ፕሮግራሞች አንዱ ነው ፡፡ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 14 ቀን 1997 የብራዚል የጠፈር ኤጄንሲ ክፍሎቹን ለማቅረብ ከናሳ ጋር ስምምነት ተፈራረመ ፡፡ ይህ ስምምነት በሶዩዝ ተሽከርካሪ ላይ ለነበረው ማርኮ ፖንቴስ በማርች ፣ 2006 ፕላኔቷን ለመዞር የመጀመሪያዋ የብራዚል ተመራማሪ እንድትሆን የሚያስችል አጋጣሚ ፈጠረ ፡፡

ብሔራዊ ካንቺቶሮን ብርሃን ላብራቶሪ ፣ በካምፓስሳ ሳኦ ፓውሎ እስከአሁንም ድረስ በላቲን አሜሪካ ውስጥ ብቸኛው የመቧጠጫ ፍጥነት ያለው ብቸኛው ሰው ነው ፡፡

በሪዮ ዴ ጄኔሮ ግዛት ሬ Res ዴኑ የኑክሌር ነዳጅ ፋብሪካ የበለፀገው ዩራኒየም የሀገሪቱን የኃይል ፍላጎት ያሟላል ፡፡ ለአገሪቱ የመጀመሪያ የኑክሌር ባህር ሰርጓጅ ግንባታ እቅዶች አሉ፡፡ብራዚል እንዲሁ ከሦስት የላቲን አሜሪካ አገራት አን Syn ናት ፡፡ .

ብራዚል እንዲሁ እንደ አባቶች Bartolomeu Lourenço de Gusmo ፣ ሮቤርቶ ላሊ ዴ ሞራ እና ፍራንሲስ ጆአኦ ዴ አዜveዶ ፣ አልቤርቶ ሳንቶስ ዱምቦንግ ፣ ኮሎራ essሰል ፣ ማርዮ ስhenንበርግ ፣ ዮሴ ሊዬስ ሎፔስ ፣ ሊዮፖልድ Nachbin ፣ ፓውሎ ሪቢቦይም ፣ ካሳ ላቲስ ፣ አንድሪያ ፓvelል ፣ ኔሊዮ ጆሴ ኒኮላይ ፣ ኔልሰን ቤርዲን ፣ ቫል ብሬል ፣ ካርሎስ ቻግስ ፣ ኦስዋዋሮ ክሩዝ ፣ ሄሪኬክ ዴ ሮቻ ሊማ ፣ ሞሪኮዮ ሮቻ ኢ ሲልቫ እና ዩሪሲሊሌስ ዘሪቢኒ ናቸው።

የብራዚል ምግብ የአገሬው ተወላጅ እና የስደተኛ ሕዝብ ድብልቅን የሚያንፀባርቅ ከክልል ወደ ክልል በጣም ይለያያል ፡፡ ይህ የክልላዊ ልዩነቶችን ጠብቆ ለማቆየት ብሔራዊ gastronomi ን ገል definedል ፣ ከእነዚህ መካከል በጣም ጥሩ ከሆኑት መካከል Feijoada ፣ ብሄራዊ ምግብ ነው ፣ vatapá ፣ moqueca ፣ polenta እና acarajé። ብራዚል እንደ ብጊጋሬሮ እና ቤይጂንሆ ያሉ ብዙ የተለያዩ ጣፋጮች አሏት ፡፡ ብሄራዊ መጠጦች ቡናማ እና ካካዋ ናቸው ፣ በመጀመሪያ ከብራዚል የመጣ ሩቅ መጠጥ ፡፡ ይህ መጠጥ ከስኳር ዘንግ ይርቃል እናም የብሔራዊ ኮክቴል ፣ የካያፊሪንሃ ዋና ንጥረ ነገር ነው።

የተለያዩ ምግቦች ቢኖሩም አንድ የተለመደው የብራዚል ምግብ ከበቆሎ ጋር ከበሰለ ባቄላ ጋር ፣ የበሬ ወይም የአሳማ ሥጋ እንዲሁም ሰላጣ ፣ ወይንም የተቀቀለ ወይንም የተጠበሰ እንቁላል ፣ የፈረንሣይ ፍሬዎች ወይም ከፋራ የተሰራ ዱቄት ፡፡ ካሳቫ እና ጨው ያለበት ሲሆን በመሠረቱ እሱ ኦርጋንኖ ፣ የተጠበሰ ሽንኩርት እና የተጠበሰ በርሜል ሊኖረው ይችላል፡፡በአብዛኛው ክልል ውስጥ ለሚኖረው ሞቃታማ የአየር ጠባይ ምስጋና ይግባቸው እንደ ‹ማንጎ› ያሉ በርካታ ፍራፍሬዎች ይበቅላሉ ፡፡ ፣ ፓፓያ ፣ አራኪ ፣ ኩባያ ፣ ብርቱካናማ ፣ ኮኮዋ ፣ cashew ፣ ጉዋቫ ፣ የፍሬ ፍራፍሬ እና አናናስ። ከእነዚህ ፍራፍሬዎች ሁሉ ጭማቂዎች እና ቅመማ ቅመሞች ለቾኮሌት ፣ ለሻማ ፣ ለ አይስክሬም እና ለሌሎች ጣውላዎች ለማምረት አገልግሎት ላይ የሚውሉ ናቸው፡፡በኢንዱስትሪ በበለፀጉ አገራት ሁሉ ፈጣን ምግብ የሚሰጡ ብዙ ኩባንያዎች መገኘታቸው እየጨመረ ነው ፡፡ በተለይም በከተሞች ውስጥ የብራዚል ህዝብ አመጋገብ እና የአመጋገብ ስርዓት ለውጦችን ያስከትላል ፡፡

ፓውሎ ሪቢቦይም ፣ ካሳ ላቲስ ፣ አንድሪያ ፓvelል ፣ ኔሊዮ ጆሴ ኒኮላይ ፣ ኔልሰን ቤርዲን ፣ ቫል ብሬል ፣ ካርሎስ ቻግስ ፣ ኦስዋዋሮ ክሩዝ ፣ ሄሪኬክ ዴ ሮቻ ሊማ ፣ ሞሪኮዮ ሮቻ ኢ ሲልቫ እና ዩሪሲሊሌስ ዘሪቢኒ ናቸው።

ኗሪዎቹ ለእግር ኳስ ያላቸው ፍቅር አይበለጠም። ብዙ ሚሊዮን አድናቂዎች አሉት። 




#Article 57: አማራ (ክልል) (247 words)


ክልሉ የትልልቅ ወንዞች ባለቤት ሲሆን በአጠቃላይ በሦስት ዋና ዋና ተፋሰሶች ተከፋፍሎ ሊታይ የሚችል ነው። እነርሱም የዓባይ፣ የተከዜ እና የአዋሽ ተፋሰስ ናቸው። ወደነዚህ ተፋሰሶች የሚገቡና ዓመቱን በሙሉ የማይደርቁ ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ ትልልቅ ወንዞች ያሉ ሲሆን በክልሉ በጥቅም ላይ ያልዋለ ሰፊ የውሐ ሀብት መኖሩን ያመለክታሉ። ከነዚህ በተጨማሪ እንደ ጣናና አርዲቦ የመሳሰሉ ሐይቆችም በክልሉ ውስጥ ይገኛሉ። በአጠቃላይ በክልሉ ውስጥ ባሉ ትልልቅ ወንዞችና መጋቢ ወንዞች የመስኖ ልማት ለማካሄድ የሚያስችል ከፍተኛ የውሐ ሐብት ክምችት እንዳለ መገንዘብ ይቻላል። ይሁን እንጅ እስከ አሁን ጥቅም ላይ የዋለው በጣም አነስተኛ ነው።

በአመዛኙ አብዛኛው የክልሉ ምጣኔ ሀብት በግብርና እና ከብት እርባታ ላይ የተመሠረተ ነው። በአጠቃላይ ክልሉ ከፍተኛ የሆነ የሕዝብ ቁጥር፣ ለእርሻና ለእንስሳት እርባታ ተስማሚ የሆነ መሬት፣ የአየር ንብረት እና የውሐ ሀብቶች ያሉት በመሆኑ በተለይም የሰብል እና የእንስሳት ሀብት ልማት ለማካሄድ የማይናቅ አቅም አለው። በዝናብም ሆነ የመስኖ እርሻ ልማት በማስፋፋት በክልሉ በገበያ የሚውሉ የተለያዩ የአገዳ፣ የጥራጥሬ፣ የቅባት፣የአትክልትና ፍራፍሬ ሰብሎችን ማምረት ይቻላል። ጤፍ፣ ገብስ፣በቆሎ፣ ማሽላ፣ዳጉሣ፣ ስንዴ፣አተር፣ ባቄላ፣ ሽምብራ፣ ጓያ፣ምስር፣ሰሊጥ፣ ጥጥ፣ ተልባ፣ ወዘተ የመሳሰሉት በክልሉ ውስጥ ከሚመረቱ ሰብሎች መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው። በእንስሳት ሀብት ረገድም በወተት ምርታማነታቸው የታወቁ የፎገራ ዝርያዎችና በፀጉር ምርት የታወቁት የመንዝ በግ ዝርያዎች በክልሉ ይገኛሉ።

በቱሪዝም የሥራ መስክ ሊበለጽጉ ፣በሰፊው አገልግሎት ሊሰጡ የሚችሉ እና በዓለም የቅርስ መዝገብ የሰፈሩት የጐንደር ቤተ መንስግት ህንፃዎች፣ የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት፣ የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ እንዲሁም ልዩ ልዩ የቱሪዝም መስሕቦች አሉት፣ ይሁን እንጅ ክልሉ ሰፊ የሆነ የቱሪዝም እምቅ ሀብት ያለው ቢሆንም በሚፈለገው መጠን በጥቅም ላይ ውሏል ማለት አያስደፍርም። በዚህ ረገድ፤አካባቢዉ የብዙ ታሪካዊ ገዳማትና የታሪካዊ ቅርሶችም ባለሀብት ነው። ለምሳሌ ከሚጠቀሱት መኃል ፦ አደል ሚካኤል፡ ይስር ፏፏቴ፡ ባንጃ ተራራው ወዘተ...

 በ21 Dec 2012 እ.ኤ.አ. የተቃኘ

  




#Article 58: ባሕር-ዳር (280 words)


ባሕር-ዳር በድሮ ስሙ ባሕር ዳር ጊዮርጊስ  በሰሜን-ምዕራብ ኢትዮጵያ የምትገኝ ከተማ ስትሆን የአማራ ክልል ዋና ከተማ ናት። ከተማዋ በቀድሞው ጎጃም ክፍለ ሓገር ውስጥ ከጣና ሐይቅ ደቡባዊ ጫፍ ላይ ተቀምጣ ስትገኝ ባህር ዳር እንደ መቀሌና ደሴ የወረዳ ደረጃ ያላት ስፔሻል(ልዩ) ዞን ናት። በማዕከላዊ ስታትስቲክ ትመና የ167,261 ህዝብ ከነሱም መሃከል የ86,355 ወንዶችና የ80,906 ሴቶች መኖሪያ ከተማ ናት። 1700 ሜትር ከባሕር ወለል በላይ ትገኛለች። 

ባሕር-ዳር ከአዲስ አበባ 565 ኪ.ሜ ወደ ሰሜን-ሰሜን ምዕራብ ትገኛለች። ባህር ዳር ከጢስ አባይ በ30 ኪሎሜትር ስለምትርቅ ለጎብኚዎች አመቺ ቦታ ላይ ናት። ባህር ዳር የአንድ የአስፋልት ንጣፍ ያለው ኤርፖርት የሰፊ ገበያና የተለያዩ የመዝናኛ ቦታዎች እና ታሪካዊ እና ጥንታዊ ግዳማት መግኛ ቦታ ናት። 

ባሕርዳር  ከተማ  የምትገኘዉ  በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ክፍል፣ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት፣ በምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ከአዲስ አበባ በ 565 ኪሜ  ርቀት ላይ ነው፡፡ አስትሮኖሚያዊ መገኛ ቦታዋ በ 11º 38’  በሰሜን ላቲቲውድ እና በ37º15’ ምስራቅ ሎንግቲውድ  ነው፡፡

በአፈ ታሪክ እንደሚነገረው የባሕር-ዳር ስያሜን ያወጡት አፄ ሠርጸ ድንግል ሲሆኑ እሳቸውም ይሕን ታቦት የት እናስቀምጥ ተብለው በተጠየቁ ጊዜ ከባሕሩ-ዳር አድርጉ የተባሉ ሰወች ለመንደሩ ባሕር-ዳር ብለው ስያሜ አወጡለት ይባላል።

ባሕር-ዳር ከተማ የተቆረቆረችው በ1915 ዓ.ም ነው ፡፡  ባሕር-ዳር  በክልሉ ከሚገኙ የሪፎርም  ከተሞች አንድዋ ስትሆን፤  የከተማ አስተዳደር፣ 3 ሜትሮፖሊታን ክ/ከተማዎች፣  የከተማ አገልግሎት ጽ/ቤት፣ 9 የከተማ ቀበሌዎችና 4 የገጠር ቀበሌዎች  አሏት፡፡ ከተማዋ በ1998 ዓ.ም የተቀናጀ ልማት ፕላን አላት፡፡
   
የተቆረቆረችበትን ዓመት፣ የቆረቆሩትን ቀደምት ሠዎች፣ የሠፈሮችን ስሞች፣ ለባሕር-ዳር የተገጠሙትና የተዘፈኑ ታሪካዊ ግጥሞችና ስነ ቃሎች፣ ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከጎጆ ቤት ወደ አሁኑ ይዞታው አመጣጥ (ባሕር-ዳርን ስናስብ ጊዮርጊስን ሚካኤልን እና ገበያውን ከገበያው አካባቢ የነበረውን ፍርድ ቤት ነጣጥሎ ማየት አይቻልም የሚል አስተያየት ስላለ ነው)፣ ባሕር-ዳር እንደባሕር ዳርነቱ ከመቆርቆሩ በፊት በሚካኤል እና በሽመምብጥ ሠፈር አካባቢ ስለነበረው አሰፋፈር፣ ስለማዘጋጃቤቱ፣ ስለ አውቶቡስ ተራው፣ ስለ ድባነቄ ተራራ፣ እና ስለ መሳሉት፣ ስለፖሊቴክኒክ፣ ስለዓባይ ወንዝና ድልድዩ፣ ስለዓባይ ወንዝና ስለጣና ሐይቅ መገናኛ እና ስለሌሎችም ቁልፍ ነገሮችን ማቅረብ የሚችሉ አፈታሪኮች አሉ። 




#Article 59: አባይ (725 words)


HISTORY /ታሪክ
ስያሜ

 

ሀገሬው አባይ ብሎ ይጠራዋል፣ አባይ(Abay) ማለት ታላቅ ማለት ነው። ከወንዞች ሁሉ አብይ ነው። የበኩር ልጅን አባይነህ ይሉታል ታላቅ ነህ ማለታቸው ነው። አባይ ከወንዞች ሁሉ ታላቁ ነው። የቀዬው ሰው አባይ ብሎ በአክብሮት ይጥራው እንጂ፣ ስሙ ግዮን ነው። ግዮን በመፅሐፍ ቅዱስ በዘፍጥረት ምዕራፍ ሁለት ቁጥር 10 እና 13 ላይ ከኤደን ገነት ከሚወጡት አራት ወንዞች አንዱ ሆኖ ተፅፏል። ይህ ወንዝ የኢትዮጵያን ምድር ይከብባል ሲልም ይናገራል።

ghion meaning

ግዮን (Ghion)

ግዮን የሚለው ቃል የግዕዝ ሲሆን በዕብራይስጥ ጊሖን፣በፅርዕ (ግብፅ) ጌዖን  ይባላል። ትርጓሜውም “ ዘየሐውር፡ በኃይል፡ ወይርም በድምፀ ማዩ ዐቢይ ወግሩም ማለት ነው።” ወደ አማርኛ ሲገለበጥ “ የውሃውን ብዛት፣ የመልካውን(የወንዙን) ስፋት፣ያካሄዱን ኅይል፣የጩኸቱን ግርማ፣ፏፏቴውንና ተመማውን(አፈሳሰሱ)፣ድምፁ እንደ ነጎድጓድ መሆኑን ያሳያል።”

አባይ ወንዝ ኒል ይባላል(ምናልባት ናይል የሚለውን ከዚህ ወስደው ይሆናል) በግዕዝ ሰማያዊ አይነት፣ወይንም ኑግ ቀለም ኒል ይባላል።

nil meaningተሰማ ኃብተ ሚካኤል ግፀው፣ ከሣቴ ብርሀን በተባለ በ1947 ዓ.ም. በአርቲስቲክ ማተሚያ ቤት በታተመ መዝገበ ቃላታቸው በገፅ 685 ላይ “ ኒል (NIL) ሰማያዊ ቀለምን መስሎ ከጎጃም ምድር መንጭቶ፣ ጎጃምን አካቦ ወርዶ ሱዳንንም አቋርጦ አራት ሺህ ማይል ዐልፎ፣ ከሜዲትራኒያን ባሕር የሚቀላቀል ኒል፣ ዐባይ” ሲሉ ፅፈዋል። ምንም እንኳን ነጮቹ ናይል የሚለው ስም Neilos ከሚለው ከግሪክ ቃል መጣ ቢሉም፣ ኒል፣ blue ከሚለው ጋር ይስማማልና ዐባይ፣ ግዮን፣ ኒል፣ እኛ ያወጣንለት ስም መሆኑን እንመሰክራለን።

 

የዓባይ(Abay) ሸለቆ የትውልድ ሐረግ ይህ ነው።

Blue-Nile-River-Ethiopia

Eonile፣ Palenileን ወለደ፣ Palenile፣ Prinileን ወለደ፤ Prinileም የአባይን እናት፣ ታላቁን የአባይ ገደላማ ሸለቆን Neonileን ወለደ።

ባለፉት 6 ሚሊዮን ዓመታት በተለያዩ የመሬት ነውጦች ምክንያት የአባይ ሸለቆ ብዙ ጊዜ ተቀያይሯል። Eonile የተፈጠረው ከ5.4 ሚሊዮን ዓመት ገደማ የሜዲትራኒያን ባሕር ተኖ ኃይለኛ ዝናብ በመከሰቱ ምክንያት በወረደው ዝናብ ነው።

ወደ ሕንድ ውቅያኖስ ይፈስ የነበረው አባይንኳ ከ 5 ሚሊዮን ዓመታት በፊት በተከሰተ የመሬት መናድ ምክንያት አቅጣጫውን ቀይሮ ወደሰሜን መፍሰስ ጀምሯል።የጣና ሐይቅን የፈጠረው እሳተ ገሞራም የዛሬ 2.6 ሚሊዮን ዓመት የተከሰተ ነበር።

Palenile ከ1.8 ሚሊዮን ዓመት በፊት የነበረ ሲሆን ከሰሜን ተራሮች ዝቃጮችን እየጠራረገ ታላቁን ገደል ለአባይ ያሰናዳበት ወቅት ነው።

Prinile የአባይ አያት ሲሆን ከ400 000 ዓመታት በፊት ነበረ። Neonile፣ የዛሬ 12 500 ዓመት ገደማ Prinileን ተከትሎ የመጣ የአባይ እናት እንደማለት ነው።
 ከዚህም በኋላ የበረዶ ዘመን ሲጠናቀቅ ለ 6000 ዓመታት የቆየ የዝናብ ዘመን ተከስቶ ነበር።በዚህ ዘመን የነበረው ዶፍ ዝናብ፣ በኢትዮጵያ ከፍታማ ስፍራዎች ቁልቁል መሬቱን እየሸረሸረ አፈሩን እያጠበ፣ኮረቱን እየጠራረገ፣ ቋጥኞችን እየቦረቦረ፣በዘመናት ብዛት የአባይን ወንዝ ከታላቁ የአባይ ሸለቆ ጋር የሚያገናኝ ሸለቆን ፈጠረ።

 

የአባይ ውኃስ ከየት መጣ?

ከሕንድ ውቅያኖስ የሚነሳው እርጥበታማ አየር በኢትዮጵያ ተራራማ ክፍል ሲያልፍ የሙቀትgishen መጠኑ እየቀዘቀዘ ይመጣል።  ጉም ምድርን እንደሚያጠጣ፣ ያም ከሕንድ ውቅያኖስ የነፈሰው እርጥበት አዘል አየር፣ ሳይዘንብ የግሸንን ተራራን ያጠጣል።

        ከግሸን ተራራ ስር፣  ከሰቀላ ወረዳ የፈለቀው ምንጭ በግሸን ሜዳ ላይ ግልገል
 አባይን ሆኖ ይፈሳል። ግልገል አባይ,  በግሸን ሜዳ ላይ ሮጦ ከጣና ሐይቅ ሲስርግ በጣና ተውጦ አይቀርም። በጣና ላይ ተንሳፎ፣ ወደ አባይ ሸጥ ይንደረደራል።

 

 

አባይ (Abay) ከጣና ወጥቶ አርባ ኪሎ ሜትር ከተጓዘ በኋላ የአባይ ፏፏቴጋ ሲደርስ 37 ሜትር ቁልቁል  Blue-Nile-River-Ethiopiatisisatቋጥኝ ላይ ይፈጠፈጥና ሽቅብ አየሩ ላይ ተበትኖ ዳግም ቁልቁል ይወርድና ጥልቀቱ 1200 ሜትር፣ ስፋቱ 24ኪ.ሜ ወደሆነው የአባይ ሸለቆ ውስጥ ይገባና በታላቁ የአባይ ገደላማ ሸለቆ፣ በእናቱ በኢትዮጵያ ሆድ ውስጥ 800 ኪሎ ሜትር ይጓዛል። ይህ ዑደት ላለፉት 5000 ዓመታት አልተለወጠም።

የአባይ መነሾን ፍለጋ

በ460 ታሪክ ፀሐፊው ሔረዶቱስ አባይ ከሁለት ትላልቅ ተራሮች እንደሚፈልቅ ያምን ነበር። በኋላም ንጉሠ ነገሥት ኔሮ፣ አሽከሮቹ የአባይን ወንዝ እንዲከተሉ ትዕዛዝ ሰጥቷቸው መልዕክተኞቹ የሱዳን ከተማ የሆነችው ሲናር ሲቲ ከሚገኘው የሱድ ማጥ ደርሰው አባይ ከዛ ነው የሚመነጨው የሚል መልስ ይዘው ተመለሱ። ከአራተኛው እስከ አሥራ ሰባተኛው ክፍለ-ዘመን ድረስ የኢትዮጵያ ተራሮች የአባይ መፍልቂያ መሆናቸውን የገመተ የውጭ ዜጋ አልነበረም።

padez perezበ17ኛው ክፍለ ዘመን ፖርቱጋል ክርስትናን ለመታደግ ሚሲዮናውያንንና ወታደሮችን ወደ ኢትዮጵያ በላከችበት ወቅት ለመጀመሪያ ጊዜ ፓድሬ ፔሬዝ የተባለ ሚሲዮናዊ፣ ጢስ እሳትንና የላይኛውን አባይን ለማየቱ ምስክርነቱን ሰጠ።

በ18ኛው ክፍለ ዘመን ጄምስ ብሩስ የተባለ የስኮትላንድ ተወላጅ ከካይሮ እስከ ጣና ተጉዞ ለመጀመሪያ ጊዜ የአባይ መነሾ ጣና ሐይቅ ነው በማለት አወጀ።እስከዚያ ጊዜ ድረስ ማንም የውጭ ዜጋ አባይ (Abay) ከጣና እንደሚነሳ አያውቅም ነበር።

samuel bakerሳሙኤል ቤከር(1821-1893) ሪቻርድ በርተን(1821-1890)ጆን ሀኒንግ ስፔክ (1827-1864) የአባይን መነሻ ፈልገው ወደ ታንጋኒካ ሐይቅ አመሩ እንጂ አንዳቸውም ወደ ኢትዮጵያ አልመጡም።

በ1937 ቡክሀርት ባልደክኼር፣የተባለ የጀርመን ተወላጅ፣ የአባይን ምንጭ ከኢትዮጵያ ተራሮች ስር ማግኘቱን ለአለም አበሰረ።ታሪካችን በነ ባልድክኬርና በብሩስ ሲፃፍ ስታሮቹ እነሱ ናቸው።የታሪካችን ሞተር የሚንቀሳቀሰው በነሱ ነው።

ቢሆንም በ1937 ጀርመናዊው ቡርክኸርት ወደ ኢትዮጵያ ሳይመጣ ኢትዮጵያዊው አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ “መፅሐፈ ሰዋሰው ወግስ፡ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ በሚለው በ1929 ባሳተሙት መፅሐፍ በገፅ 313 

በ1995 ዓ.ም ግሼ ሜዳ ላይ ከብቶች የሚጠብቅ 11 ዓመት ያልሞላው የውልሰው የተባለ እረኛ አገኘሁና “የአባይ ምንጭ የት ነው ብዬ ስጠይቀው” መሬት ቸክሎ የተደገፈውን በትር ከመሬቱ ላይ ነቅሎ ወደ ግልገል አባይ እያሳየኝ ከዚህ ነዋ አለኝ። አባባሉ ስንት ፈረንጆች የአባይን ምንጭ አገኘን ብለው የቦረቁበት ግኝት አይመስልም።

ያ የጎጃም እረኛ “ ማስረጃህ ምንድነው?” ስለው በክረምት አባይ ሲደፈርስ ግልገል አባይ የደፈረሰ ውኃ ይዞ ጣና ይገባና ከጣና ተንሳፎ ሲወጣ ጥርት አርጎ ይታያል።” ብሎ እረኛው ጂኦሎጂስት አስገረመኝ። እዚህጋ ባለቅኔው ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን

  

(Abay)




#Article 60: ትግራይ ክልል (130 words)


ትግራይ (ክልል 1) ከኢትዮጵያ ዘጠኝ ክልሎች አንዷ ስትሆን በኢትዮጵያ ሰሜናዊ-ጫፍ ትገኛለች። ዋና ከተማዋ መቐለ ነው። ሌሎች ታዋቂ ከተሞች ውቅሮ፣ ዛላምበሳ፣ ዓብዪዓዲ ፣ዓድዋ፣ነበለት፣ ሸራሮ፣ ሰቲት ሑመራ፣ዓዲግራት፣ አኽሱም፣ ሽረ እንዳስላሰ፣ ማይጨው፣ ኾረም እና ኣላማጣ ናቸው። በኢትዮጵያ የአማራ እና አፋር ክልሎች ያዋስኑዋታል። 50,286 ካሬ ኪ.ሜ. ስትሸፍን የሕዝብ ብዛት በ1999 ህዝብ እና ቤት ቆጠራ መሰረት 4.9 ሚልዮን ነው። ትግርኛ የክልሉ ዋና ቋንቋ ነው። እምባ ኣላጀ፣ ፅበት እና ወርሐት በትግራይ ክልል ያሉ ከፍተኛ ቦታዎች ናቸው። 
ትግራይ በኢትዮጵያ ከሚገኙት ክልሎች አንዱ ሲሆን በርካታ ተፈጥሯዊ፣ ባህላዊና ታሪካዊ ሃብቶች የታደለ ክልል ነው።የሓ ጥንታዊ ቤተ መቅደስ፣ የአክሱም ጥንታዊ ሃውልቶች፣ከ4ኛው እስከ 15ኛው ክ/ዘመን እንደተሰሩ የሚታወቀው ከ120 በላይ የሚሆኑ ከኣለት ድንጋይ ተፈልፍለው የተሰሩ ውቅር ኣብያተክርስትያናትና ገዳማት እንዲሁም ሌሌች በርካታ ታሪካዊና ኣርኪኦሎጂካዊ ስፍራዎች የሚገኙበት ክልል ነው።
ትግራይን በባህልና በታሪካዊ ኣመጣጥ ከኤርትራ ነጥሎ ማየት ኣይቻለም። ሁለቱም የዳኣማትና የኣክሱም ግእዛዊ ስልጣኔ ባለቤት ናቸው። 
ዓድዋ




#Article 61: ዮሐንስ ፬ኛ (183 words)


ዓፄ ዮሐንስ ፬ኛ፣ ከአባታቸው ከተንቤን ባላባት የራስ ስኹል ሚካኤል የልጅ ልጅ ሹም ተንቤን ምርጫ እና ከናታቸው የእንደርታው ገዢ የራስ አርአያ እህት ወይዘሮ ወለተ ሥላሴ ሐምሌ ፭ ቀን ፲፰፻፳፭ ዓ.ም. ማይ በሀ በሚባል ሥፍራ ተወለዱ። 

ርዕሰ መኳንንት ደጃዝማች በዝብዝ ካሳ ሐምሌ ፮ ቀን ፲፰፻፷፫ ዓ/ም ዓፄ ተክለ ጊዮርጊስን አድዋ አካባቢ አሳም የሚባል ሥፍራ ላይ ወግተው ድል ካደረጉ በኋላ ጥር ፲፫ ቀን፲፰፻፷፬ ዓ/ም አክሱም ላይ ሥርዓተ ንግሣቸው ተፈጽሞ ዓፄ ዮሐንስ ፬ኛ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ተብለው ነገሡ።

አፄ ዮሐንስ 4ኛ ከእንግሊዝ ንግስት ጋር በመፃፃፍ ነግስናቸውን አጠናክረዋል፡፡ ይህም ተቀናቃኛቸው የነበሩት አፄ ሚኒለክን ለማስገበር ተሳክቶላቸዋል ፡፡ ከአፃ ሚኒሊክ ጋር የነበራቸውን የስልጣን ሽሚያ ለመከላከል ሲባል ደብረ ብርሃን ድረስ በመሄድ ድርድር በማድረግ የነበራቸውን ባላንጣነት አስወግደው ሚኒሊክ ንጉስ እንድባልና አፄ የሐንስ ርዕሰ ብሔር እንድሆን ተስማምተዋል ፡፡ ከዛም ደርቡሾች ጋር መተማ አካባቢ ገጥመው አፄ ዮሐንስ በጥይት   ቆስለው  በመውደቃቸው መሐድስቶች አንገታቸዉን ቆርጠው ለግብፅ ማስፈራሪያእንዳደረጉት ይነገራል፡፡ ይህ የሆነው አፄ ዮሐንስ የኦርቶዶክስ  እምነት ተከታይ በመሆናቸው  የደሴና ቦሩ ሜዳ አካባቢዎች ሙስሊሞችን በሀይል ወደ ክርስትና በማቀየራቸው ነው ፡፡ መሐድስቶችም ከዮሐንስ ጋር ጦርነት የገጠሙት ሙስሊሞችን ለመርዳት  እንደሆነ በታሪክ ይነገራል ከዚህ በፊት ግን ከግብፅፆች ጋር ጉራና ጉንዳ ጉንድ በተባሉ ቦታዎች ገጥመው ማሸነፋቸውና የሀገርን ዳር ድንበር ለማስጠበቅ  መጣጣራቸን በታሪክ  ይወሳል፡፡




#Article 62: ሊንጋላ (106 words)


ሊንጋላ (Lingala) ከባንቱ ቋንቋዎች ቤተሠብ አንድ ነው። የሚናገርበት በተለይ በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ ስሜን-ምዕራብ ክፍል፣ በኮንጎ ሪፑብሊክም፣ እንዲሁም በአንጎላና በመካከለኛው አፍሪካ ሪፑብሊክ ነው። ተናጋሪዎቹ 10 ሚልዮን ናቸው። 

የሊንጋላ መነሻ ቦባንጊ በተባለ ቋንቋ ነበር። ከኮንጎ ነጻ መንግሥት አስቀድሞ ቦባንጊ የአከባቢው መደበኛ ቋንቋ ይሆን ነበር። የቤልጅክ ንጉስ አገሩን ከያዙ በኋላ የቀኝ አገሩ መንግሥት ለማስተዳደርና ለመሰበክ ቋንቋውን ጠቃሚ ሆኖ አገኙት። ካለፈው ቦባንጊ እንዲለይ የአዲሱን ቋንቋ ስም ባንጋላ ብለው ጠሩት። ሚስዮናዊዎቹ ወዲያ (1900 አ.ም.) ባንጋላን ዳግመኛ ሲያሻሽሉ ሊንጋላ እንዲህ ተፈጠረ። 

ሊንጋላ ከፈረንሳይኛ ብዙ ቃሎች ተበድሮ ደግሞ ከፖርቱጊዝ ተጽእኖ አለ (ለምሳሌ ማንቴካ = ቅቤ፤ ሜሳ = ጠረጴዛ፤ ሳፓቱ = ጫማ) ከእንግሊዝኛም ተጽእኖ አለ (ሚሊኪ = ወተት፤ ቡኩ = መጽሐፍ)።

የጌታ ጸሎት በሊንጋላ




#Article 63: ጉጃራቲ (137 words)


ጉጃራቲ (ગુજરાતી) በህንዳዊ-አውሮፓዊ ቋንቋዎች ቤተሰብ የሚገኝ ቋንቋ ነው። በዓለሙ ውስጥ በ46 ሚልዮን ሰዎች ይናገራል፤ ከነዚህም 45.5 ሚልዮን በህንደኬ፣ 250,000 በታንዛኒያ፣ 150,000 በዩጋንዳ፣ 100,000 በፓኪስታንና 50,000 በኬንያ አሉ። በሕዝብ ብዛት የዓለሙ 23ኛ ቋንቋ ነው። በምእራብ ህንደኬ ያለው የጉጃራት ክፍላገር ይፋዊ ቋንቋ ነው። 

የጉጃር ሕዝብ ወደ ህንደኬ የደረሱ በ5ኛው መቶ ዘመን ሲሆን በ6ኛው መቶ ዘመን ዛሬ ጉጃራት በሚባለው አገር ሰፈሩ። የራሳቸውን ቋንቋ ቶሎ ትተው እንደ አገሩ ሰዎች ሳንስክሪት ለመናገር ጀመሩ። በ12ኛው ክፍለ ዘመን ግን ሳንስክሪት ተለውጦ ብዙ አዲስ ቋንቋዎች ተወለዱ። ከነዚሁም አንድ ጉጃራቲ ነበር። 

አብዛኛው ተናጋሪዎቹ የህንድ ሃይማኖት ተከታዮች ቢሆኑም ለረጅም ዘመን የእስላም ገዢዎች ስለነበሩባቸው ብዙ ቃላት የተወሰዱ ከፋርስ ሆኗል። ከዚያ በላይ በንግድ ምክንያት ብዙ ቃሎች ከፖርቱጊዝ ወይም ከእንግሊዝኛ ተበደሩ። የሚጻፍበት በራሱ ጉጃራቲ ፊደል ነው፤ ይህም ከላይኛ መስመር በማጣቱ በስተቀር የህንዲ ደቫናጋሪ ፊደል ይመስላል።

የህንዳዊ-አውሮፓዊ ቋንቋዎች ቤተሰብ በመሆኑ፣ ጉጃራቲ ለእንግሊዝኛ ሩቅ ዘመድ ይባላል። ስለዚህ ለአንዳንድ ቃል ትንሽ ተመሳሳይነት አላቸው።




#Article 64: አሪዞና (127 words)


አሪዞና (Arizona) በምዕራባዊ ዩናይትድ ስቴትስ የሚገኝ ክፍላገር ነው። ኒው ሜክሲኮ ፣ ዩታህ ፣ ኔቫዳ ፣ ካሊፎርኒያ እና ኮሎራዶ ያዋስኑታል።

የአሪዞና ሕግ-አውጪ ቅርንጫፍ የ30 ሰው ሴኔት እና የ60 ሰው ምክር-ቤት አለው። የሪፑብሊካን ፓርቲ በስቴቱ ዋነኛው ፓርቲ ነው። በ2002 እ.ኤ.አ. የአሪዞና ስቴት ሕግ-አውጪ ቅርንጫፍ በጀት 14.3 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን የሕግ-አስፈጻሚ ቅርንጫፍ በጀት ደግሞ 13.8 ቢሊዮን ዶላር ነው። የስቴቱ ሴኔተሮች እና ምክር-ቤት ተወካዮች ለሁለት-ዓመት ጊዜ ላልተወሰነ ብዛት ይመረጣሉ። ከ4 ጊዜ በላይ በተካካይ መመረጥ ግን አይችሉም። የሕግ-አስፈጻሚ ቅርንጫፍ በአስተዳዳሪ የሚመራ ሲሆን ለ4 ዓመት ሥልጣን ላይ ይቆያል። ያልተወሰነ ጊዜ መወዳደር ሲቻል ከሁለት ጊዜ በላይ ግን በተካካይ መመረጥ አይፈቀድም።

ልክ በደቡብ-ምዕራብ እንደሚገኙ ሌሎች ስቴቶች በረሃማ ነው።

ባንድ ጊዜ አሪዞና ከአሜሪካ ትልቁ የጥጥ አምራች ነበረ።

በ2004 እ.ኤ.አ. አሪዞና 5,743,834 የሚገመት የሕዝብ ብዛት አላት።

የዘር ክፍልፍል፦

ቋንቋ ክፍልፍል (እንደ 2000 እ.ኤ.አ.)፦

ጾታ፦

ሃይማኖት፦

ስቴት ዩኒቨርስቲዎች




#Article 65: ቶክ ፒሲን (111 words)


ቶክ ፒሲን (Tok Pisin) በስሜን ፓፑዋ ኒው ግኒ የሚናገር የእንግሊዝኛ ቋንቋ ዲቃላ ነው። ከእንግሊዝኛ ስዋሰው በጣም ተለውጧልና ዛሬ እንደ ራሱ ቋንቋ ይቆጠራል። የፓፑዋ ኒው ግኒ መደበኛ ቋንቋ ሆኖ በ120,000 ያሕል ተናጋሪዎችና በ4 ሚሊዮን እንደ 2ኛ ቋንቋ ይነገራል።

የቶክ ፒሲን አጀማመር በፓሲፊክ ውቅያኖስ ደሴቶች ላይ የሚኖሩ የተላያዩም ልሣናት የሚችሉ ሰራተኞች አንድላይ ለአትክልት ስፍራዎች ሲሰሩ ነበር። ብዙ ጊዜ የእነዚህ ሰራተኞች የጋራ ቋንቋ ጥቂት ቀላል እንግሊዝኛ ቃሎች ብቻ ነበር። ስለዚህ አዲስ የቋንቋ ዲቃላ ተወለደ። ከእንግሊዝኛ ብቻ ሳይሆን ብዙ ቃላት የተወሰዱ ከደሴተኞቹ ቋንቋዎች፣ ከጀርመንኛ፣ ወይም ከፖርቱጊዝ ነበር። ይህ ቋንቋ ፕጅን ተብሎ አሁን ሶስት ተወላጆች አሉት፣ እነሱም ቢስላማ (በቫኑዋቱ) ፒጂን (በሰሎሞን ደሴቶች) እና ቶክ ፒሲን ይባላሉ። ቶክ ፒሲን በአንዳንድ ትምህርት ቤት የትምህርት ቋንቋ ነው።

የአባታችን ጸሎት፦




#Article 66: ፕሬስኮት፥ አሪዞና (101 words)


ፕሬስኮት (Prescott) በያቫፓይ ካውንቲ፥ አሪዞና፥ ዩናይትድ ስቴትስ የሚገኝ ከተማ ነው። በ2000 እ.ኤ.አ. የከተማው ሕዝብ ብዛት 33,938 ነበር። ከተማው የያቫፓይ ካውንቲ መቀመጫ ነው። ከ1863 እ.ኤ.አ. እሰከ 1867 ድረስ ወደ ቱሣን ከመለወጡ በፊት የአሪዞና ዋና ከተማ ነበር። በ1877 እ.ኤ.አ. ፕሬስኮት እንደገና የአሪዞና ዋና ከተማ ሆነ። በ1889 እ.ኤ.አ. ግን ዋና ከተማው ወደ ፊኒክስ፥ አሪዞና ተለወጠ።

ፕሬስኮት በ34°34'6 ሰሜን እና 112°27'41 ምዕራብ ይገኛል። 96.6 ካሬ ኪ.ሜ. ቦታ ሲሸፍን ከዚህ ውስጥም 0.6 ካሬ ኪ.ሜ በውሃ ተሸፍኗል። 1,645.92 ሜትር ከባሕር ወለል በላይ ይገኛል።

በ2000 እ.ኤ.አ. 33,938 ሰዎች ፣ 15,098 ቤቶች እና 8,968 ቤተሰቦች በከተማው ይገኛሉ። የሕዝብ ስርጭት 353.5 በ1 ካሬ ኪ.ሜ. ነው።

እነዚህ የትምህርት ተቋሞች በፕሬስኮት ይገኛሉ፦




#Article 67: ፌኒየስ ፋርሳ (124 words)


ፌኒየስ ፋርሳ Fenius Farsa (ወይም Farsaid ፋርሳይድ) በአይርላንድ አፈ ታሪክ የእስኩቴስ ንጉስ ነበሩ። የኦጋም ጽሕፈትና የጎይደልክ ቋንቋ የፈጠሩ እንደ ነበሩ ይባላል። («ጎይደልክ» የአይርላንድና የስኮትላንድ ጥንታዊ ቋንቋ ነው።)

በ11ኛ መቶ ዘመን በወጣው መጽሐፍ ሌቦር ጋባላ ኤረን ዘንድ፣ ለናምሩድ የባቢሎን ግንብ ከሠሩት 72 አለቆች አንድ ሆነው ግንቡ ከወደቀ በኋላ ወደ እስኩቴስ ተጓዙ።

ደግሞ በአውራከፕት ና ኔከሽ በተባለው ጥንታዊ መጽሐፍ ዘንድ ፌኒየስ ከጒደል ማክ ኤሆር፣ ከያር ማክ ኔማና ከ72 ሊቅውንት ጋራ ከእስኩቴስ ተጓዙ። በናምሩድ ግንብ በኩል የተደባለቁትን ልሣናት ለማጥናት ወደ ሰናዖር ሜዳ ደረሱ። ነገር ግን ከዚያ አስቀድሞ እንደ ተበተኑ አገኝተው፣ ፌኒየስ 72ቱን ሊቃውንት ቋንቋዎቻቸውን እንዲያጥኑ ወደ ተበተኑት ሕዝቦች ልከው በግንቡ ሥፍራ ቆይተው ሥራውን አስተባበሩ። ከ10 አመታት በኋላ ትንትናው ተፈጽሞ ከተደባለቁት ልሣናት የተሻለውን መርጠው «ምርጥ ቋንቋ» ፈጥሮ በጓደኛው ጒደል ስም ቋንቋውን «ጎይደልክ» አሉት። ደግሞ ኦጋም የሚባል ጽሕፈት ፈጠሩለት።




#Article 68: ድረ ገጽ (103 words)


 
ድረ ገጽ በድረ ገጽ መረብ የሚገኝ ፋይል ነው። ይህ ድረ-ገጽ በተለያዩ የኮምፒውተር ፕሮግራም ቋንቋዎች መጻፍ ሲችል ኤች.ቲ.ኤም.ኤል. ግን ታዋቂው ነው። በድረ ገጾች ላይ ጽሁፎች እና ምስሎች ይገኛሉ። እነዚህ ጽሁፎችና ምስሎች ወደ ሌላ ድረ ገጽ ሊያገናኙ ይችላሉ። 

በድረ ገጽ ውስጥ የሚከተሉት ሊገኙ ይችላሉ፦

ድረ ገጾች ውስጥ የሚከተሉት ሊገኙ ይችላሉ ግን አይታዩም፦

በአንድ ዌብ ሰርቨር ላይ የሚገኙ የተሰባሰቡ ድረ ገጾች ዌብሳይት ይባላሉ። ዌብሳይቶች አብዛኛው ጊዜ index የሚባል የማውጫ ገጽ አላቸው። የአንድ ዌብሳይት አድራሻ ብቻ ሲጻፍ (ምሳሌ፦ www.wikipedia.org) ይህ የማውጫ ገጽ ይላካል።

ድረ ገጾችን ለማየት ብዙ መንገዶች ሲኖሩ ድረገጽ ቃኚ ግን ዋነኛው ነው።

ድረ ገጾችን ለመፍጠር አንድ ጽሁፍ መጻፊያ ሶፍትዌር ወይም ድረ ገጽ መጻፊያ ሶፍትዌር ያስፈልጋል።




#Article 69: ጉግል (683 words)


ጉግል (Google) በ1998 እ.ኤ.አ. የግለሰብ ድርጅት ሆኖ ነው የጀመረው። የጉግል ፍለጋ ዌብሳይትን የሰራው እና የሚያስተዳድረው ይሄው ድርጅት ነው።
የጉግል ዓላማ የዓለምን መረጃ ለማሰናዳት ፣ ለማቅረብና ጠቃሚ ማድረግ ነው።

ጉግል እንደ ፕሮጀክት ሆኖ በጃኑዋሪ 1996 እ.ኤ.አ. በላሪ ፔጅ እና ሰርጂ ብሪን በስታንፎርድ ዩኒቨርስቲ ነው የጀመረው።
የፕሮጀክቱ ሀሳብ የድረ ገጾችን ግንኙነት በማጥናት የተሻለ የፍለጋ አገልግሎት መሰጠት መቻል ነበር። ወደ አንድ ድረ ገጽ ብዙ መያያዣዎች ካሉ ያ ድረ ገጽ ትክክለኛ
ኢንፎርሜሽን አለው የሚለውን ሀሳብ ሞክረው ትክክለኛ መሆኑን አዩ (ይህ ዘዴ ፔጅራንክ ይባላል)፣ ለፍለጋ ድረ ገጻቸውም መሠረት ጣሉ። በእዚያ ጊዜ ፍለጋውን
የሚያስተናግደው የስታንፎርድ ዌብሳይት ነበር። አድራሻውም ነበር። ያሁኑ አድራሻቸው google.com 
በ, 1990 (Sep. 15, 1997 እ.ኤ.አ.) ነው የተመዘገበው።

በማርች 1999 እ.ኤ.አ. ድርጅቱ ወደ 165 ዩኒቨርስቲ አቬኑ, ፓሎ አልቶ መስሪያ ቤቱን አዛወረ። ከዚያ በኋላ ሌሎች ሁለት ቦታዎች ቢቀያይሩም
በ2003 እ.ኤ.አ. 1600 አምፊቲያትር ፓርክዌይ, ማውንቴን ቪው ወደ ሚገኙ ሕንጻዎች አረፉ። አብዛኛው በዚህ ጊዜ ይጠቀምበት የነበረው የኮምፒዩተር
ዕቃዎች ከኢንቴል እና አይቢኤም የተለገሡ ነበሩ።

በፍጥነት የሚያድገው የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ጉግልን ማድነቅ ጀመሩ። ተጠዋሚዎች ወደ ዌብሳይቱ ቀላል እና ዓይን የሚስብ ዲዛይን ተሳቡ። በ2000 እ.ኤ.አ.
በፍለጋ ቃላት ላይ የተመሠረቱ ማስታወቂያዎችን ማሳየት ጀመሩ። ነጻ የዌብሳይት ዲዛይን አንዲኖርና የዌብሳይቱን የመጫን ጊዜ ፈጣን እንዲሆን ማስታወቂያዎቹ የምስል ሳይሆን 
የጽሁፍ ብቻ ናቸው። ሌሎች ተወዳዳሪዎቹ እየወደቁ ሲመጡ ጉግል ግን እያደገ እና እየታወቀ መጣ።

በ, 1993 (Sep. 4, 2001 እ.ኤ.አ.) የዩናይትድ ስቴትስ ፓተንት ቢሮ የፔጅራንክ ዘዴን ፓተንት ለስታንፎርድ ዩኒቨርስቲ ሰጠ። በፌብሩዋሪ 

በ2004 እ.ኤ.አ. መጀመሪያ ጉግል በወርልድ ዋይድ ዌብ ከነበረው የፍለጋ ጥያቄዎች 84.7 በመቶውን በራሱ ዌብሳይትና በሌሎች ጓደኛ ዌብሳይቶች ያስተናግድ
ነበር። በፌብሩዋሪ 2004 እ.ኤ.አ. ያሁ! ከጉግል ጋር የነበረውን ጓደኝነት አቆመ። 

በበዓል ቀናት፣ የአንድ ነገር መታሰቢያ ቀናት እና ልዩ ቀኖች የጉግል ዌብሳይት አስቂኝ ነገሮችን ይይዛል። ከነዚህም ታዋቂው የድርጅቱን አርማ መለወጥ ነው።
ይህም 'ጉግል ዱድልስ' ይባላል። 

በየጊዜው አዲስ ነገር ከጉግል ይመነጫል። ጉግል ላብስ የሚባለው የዌብሳይቱ ክፍል አዲስ በሙከራ ያሉ ውጤቶችን ይይዛል። ይህም የተጠቃሚዎችን አስተያየት ስለሚያስገኘው 
ከተጠቃሚዎች ጋር ያለውን ግንኙነት ያዳብራል። ይህም አዲሶቹን ምርቶች አሰራር ያሻሽላል።

በዓመታት ውስጥ  ተለውጧል።

ጉግል (Google) የሚለው ቃል ጉጎል (Googol) ከሚለው የመጣ ነው። ጉጎል የሚባለው ቃል የተፈጠረው በሚልተን ሲሮታ በ1938 እ.ኤ.አ.
በዘጠኝ ዓመቱ ነው። ሚልተን ኤድዋርድ ካስነር የሚባል ማቲማቲሻን ወንድም/እሀት? ልጅ ነው። የቃሉ አጠቃቀም የጉግልን በኢንተርኔት የሚገኘውን ኢንፎርሜሽን
ለማሰናዳት ያለውን ዓላማ ያንፀባራቃል። የጉግል ጠቃላይ መምሪያ ጉግልፕሊክስ (Googleplex) ይባላል።

ዛሬ 'ጉግል' በአንዳንድ ቋንቋዎች እንደ ቃል ይወሰዳል። ትርጉሙም 'የዌብሳይት ፍለጋ ማድረግ' ነው።

የጉግል የመጀመሪያ ዕርዳታ ከአንዲ ቤክቶልሸም የተጻፈ የ$100,000 ቼክ ነው።

ጉግል እያደገ ሲመጣ ትልቅ ውድድር እየሳበ ይመጣል። አንድ ምሳሌ በጉግል እና ማይክሮሶፍት መሀል ነው። ማይክሮሶፍት ኤምኤስኤን ሰርች የሚባለውን የፍለጋ
አገልግሎት በየጊዜው እየለወጠ ከጉግል ጋር የተወዳዳሪ ቦታ እንዲይዝ ይሞክራል። ከዚህም በላይ ሁለቱ ድርጅቶች አንድአይነት አገልግሎቶችን ማቅረብ ጀምረዋል።

ጉግል 'gbrowser.com' የሚለውን የዌብ አድራሻ ስላስመዘገበ የራሱን የዌብ መቃኛ እየሰራ ነው የሚል ወሬ አለ። ለማይክሮሶፍት የሚሰሩ ብዙ ሠራተኞችም
ማይክሮሶፍትን ለቀው ለጉግል መሥራት ጀምረዋል።

ጉግል በፍለጋ አገልግሎት መሪ ስለሆነ እንደ ያሁ! ያሉትን ተወዳዳሪዎች ለማሸነፍ ይጥራል። የጉግልና ያሁ ትኩረት የተለያየ ቢሆንም ጉግል ግን አዳዲስ አገልግሎቶችን
እየከፈተ ነው። በጁን 21, 2005 እ.ኤ.አ. ጉግል እንደ ኢቤይ ያሉትን የንግድ ዌብሳይቶችን ለመወዳደር ያለውን ዕቅድ አሳውቋል።

በጉግል የመጀመሪያ ዓመታት የሠራተኞች ደሞዝ ትንሽ ነበር። በአሁኑ ጊዜ ግን ዩጉግል ሼር በከፍተኛ መጠን እያደገ ስለመጣ የሠራተኞች ደሞዝ በአንጻሩ ጨምሯል።
ከደሞዝ ሌላ ታዋቂነት እና ሌሎች ጥቅሞች ብዙ አመልካቾችን ስቧል። ከአንድ ላነሰ የሥራ ቦታ አንድ ሺህ አመልካቾች እንዳሉ ተገምቷል።

የድርጅቱ መሥራቾችና ሌሎች ዋና ሠራተኞች አንድ የአሜሪካን ዶላር እየተከፈላቸው ይሰራሉ። እነዚህ ሰዎች የድርጅቱን ብዙ ሼር ይይዛሉ። 
ማርች 31 2007 የተለቀቀው መረጃ እንደሚያመለክተው ጉግል 12238 ሰራተኞች አሉት።

የጉግል አገልግሎቶች በብዙ ሰርቨሮች ውስጥ በሚገኙ ተራ ኮምፕዩተሮች ላይ ነው ያሉት። ኮምፒዩተሮቹ የሊኑክስ ኮምፒዩተር ፕሮግራም ይጠቀማሉ።
ድርጀቱ ስለሚጠቀመው ማሽኖች ብዙ ዝርዝር ባይሰጥም በ1996 ከ60,000 በላይ ኮምፒዩተሮችን እንደሚጠቀሙ ይገመታል።

ፔጅራንክ (PageRank) ጉግል የፍለጋ ገጾቹ ላይ የዌብሳይቶችን ቅድመተከተል ለማግኘት የሚጠቀመው ዘዴ ነው። በፔጅራንክ እያንዳንዱ ዌብሳይት ቁጥር አለው።
ይህ ቁጥር ከፍ ባለ ጊዜ የዛ ዌብሳይት ደረጃ በፍለጋ ገጹ ላይ ይጨምራል። ይሄ ቁጥር የሚወሰነው ሌሎች ወደዚህ ዌብሳይት በሚያመለክቱ ዌብሳይቶች ነው። የእነዚህ 
ዌብሳይቶች ቁጥር ከፍተኛ ከሆነ የዚኛውም በአንጻሩ ይጨምራል። በኣንዳንድ ምክንያቶች የተነሳ ይህ ኣስተማማኝ ላይሆን ይችላል።

ጉግል የራሱ የተለያዩ ዕምነቶች አሉት። አንዱ 'መጥፎ ነገር ሳትሰራ ገንዘብ ማግኘት ትችላለህ' ይላል። ሊሎች ዋና ሀሳቦች
።

ሁሉም የጉግል ኢንጅነሮች 20 በመቶ የሥራ ጊዜያቸውን እነሱ በሚስባቸው ሥራ ላይ እንዲያሳልፉ ያበረታታል። ከእነዚህ ውስጥ አንዳንድ ሥራዎች የጉግል ሌላ አገልግሎት ይሆናሉ።

የጉግል መጥላይ መምሪያ ጉግልፕሌክስ (Googleplex) ይባላል። ይህ ቦታ ለሠራተኞች የተለያዩ መዝናኛዎችን ያቀፈ ነው። ከነዚህም ውስጥ የአካል ማጎልመሻ ክፍል፣ 
የተለያዩ ስፖርቶች፣ የተለያዩ ምግብና መጠጦች ይጠቀሳሉ።

የሚከተሉት የሥራ አጋሮች ናቸው፦

ጉግል ከደርዘን በላይ በሚሆኑ ሀገሮች  አሉት። የተለያዩ ሀገሮች የተለያየ ሕጎች ስላሏቸው ጉግል ሁሉንም ለማስማማት ይሞክራል።




#Article 70: ቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት (186 words)


ለአለም ጽሕፈቶች ወላጅ ሆነው የሚታስቡ 2 ተመሳሳይ ጽሕፈቶች ተገኝተዋል፣ እነሱም «ጥንታዊ የሲና ጽሕፈት»ና «የዋዲ ኤል ሖል ጽሕፈት» ይባላሉ።  «ዋዲ ኤል ሖል» በ1999 እ.ኤ.አ. በግብፅ ተገኝቶ ዕድሜው ከክ.በ. 1800 ዓመት የሚገመት ሲሆን፣ የጥንታዊ ሲና ጽሕፈት በ1904 እ.ኤ.ኣ. በደብረ ሲና በኩል ተገኝቶ ከክ.በ. 1500 ዓመት የተጻፈ ይታመናል። 

ከሲና ልሣነ ምድር በላይ አሁን ለዚህ ጽሕፈት በርካታ ምሳሌዎች በከነዓን (የዛሬው እስራኤል) ደግሞ ተገኝተዋል። በተለይ የሚታወቀው ደብረ ሲና አጠገብ ካለ አረንጓዴ ፈርጥ ማዕድን ቦታ ነው። ነገር ግን አሁን ከተገኘ ከ100 አመት በኋላ የቋንቋ ሊቃውንት ስለ ተቀረጹት ቃላት ትርጉም በሙሉ እርግጠኛ አይደሉም።

ይህ ጽሕፈት በግብጽ ውስጥ ተግኝቶ በሴማዊ ሠራተኞች እንደ ተቀረጸ ይታሰባል። የፊደሎቹ ቅርጽ ከግብጽኛ ስዕል ጽሕፈት (ሀይሮግሊፍ) ጋር ተመሳሳይ ነው። እንዲሁም ከጥንታዊ የሲና ጽሕፈት ጋርም ይመሳሰላል።  ስለዚህ ሰራተኞቹ ስእሎቹን ተበድረው ከቋንቋቸው ጋር የሚስማማ ድምጽ እንደሰጡት ይታመናል።

ለምሳሌ በጥንታዊ ግብጽኛ ቋንቋ እባብ ማለት «ጀት» ነበር። ስለዚህ በግብጽ ጽሕፈት «ጀ»ን ለማመልከት የእባብ ስዐል ጠቀመ። ነገር ግን በግብጽ ለኖሩት ሴማዊ ሰራተኞችና አገልጋዮች በቋንቋቸው የእባብ ስም በ «ነ» ስለሚጀምር የእባብ ምልክት ከ«ጀ» ወደ «ነ» ተቀየረ። 

እንዲሁም ውሃ በግብጽኛ «ነት» ስለነበር የውሃ ምልክት በድምጹ «ነ» ለመጻፍ ስራ ላይ ይውል ነበር። ደግሞ ለሴማውያን የውሀ ስም በ «መ» ስለሚጀምር (ማይ) የውሀ ምልክት በጽህፈታቸው «ነ» ሳይሆን «መ» እንዲሆን ተደረገ።




#Article 71: የዓለም ጽሕፈቶች (309 words)


ዛሬውን በሰፊ ጥቅም ላይ ያሉት የዓለም ጽሕፈቶች በ5 ዋና መደቦች ሊካፈሉ ይችላሉ። እነዚህም፦ 

በሎጎግራፊክ ጽሕፈቶች እያንዳንዱ ምልክት ወይም ሎጎግራም ለአንድ ቃል ይቆማል። የግብጽ ሃይሮግሊፎች መጀመርያ ከሎጎግራም (ስዕሎች) ብቻ ተሠራ። ዕጅግ በጥንት ቅድመ-ታሪክ ዘመን ግን የተናባቢ ምልክቶች እና የክፍለ-ቃል ምልክቶች ተጨመሩለት። 

በሌሎቹ ጥንታዊ ሎጎግራም ጽሕፈቶች ደግሞ እያንዳንዱ ምልክት ለቃል ወይም ለክፍለ-ቃል ሆኖ ይጻፍ ነበር። ከነዚህም የትንሹ እስያ ሃይሮግሊፍ፣ ኩነይፎርም ጽሕፈት፣ የማያ ሃይሮግሊፍ አሉ። 

ኣሁን የቻይና ጽሕፈት እንዲሁም ከሎጎግራም ይሠራል። የቻይና ጽሕፈት ከቻይንኛ ጭምር ለሌሎች ልሳናት እንደ ቬትናምንኛ፣ ኮሪይኛ ቀድሞ ይጠቀም ነበር። ዛሬም የቻይና ምልክቶች በጃፓንኛ ጽሕፈት ደግሞ ይገኛሉ። በቻይና ዙሪያ ሌሎች ተመሳሳይ ጽሕፈቶች ዪ ጽሕፈት፣ ታንጉት ጽሕፈት፤ የናቂ ጽሕፈት ይገኛሉ።

በሲላቢክ ጽሕፈቶች እያንዳንዱ ምልክት ለአንድ ክፍለ-ቃል ይጠቅማል። 

በ'ጥሬ ሲላቢክ' ጽሕፈቶች፣ እነኚህ ምልክቶች ለአንድ ድምጽ አይመሳሰሉም። ስለዚህ «ቴ... ታ... ቶ...» የሚሉ ፊደላት ከቶ አይመሳሰሉም፣ ለምሳሌ በጃፓንኛ በሚጠቅመው «ካታካና» በሚባል ጽሕፈት፤ እነዚህ ድምጾች テ , タ, ト ይጻፋሉ። ጃፓንኛ ደግሞ ሌላ «ሂራጋና» በተባለ ሲላቢክ ጽሕፈት ሊጻፍ ይችላል።

ሌሎች ጥሬ ሲላቢክ ጽሕፈቶች በጥንት የቆጵሮስ ጽሕፈት (Mycaenaean Greek Linear B) እና ኩነይፎርም፤ ዛሬም፦

በቋንቋ ጥናት በቅርቡ አቡጊዳ የሚለው ቃል ከኢትዮጵያ ልሳናት ተወስዶ ሌላ ትርጉም ተሰጥቶታል። በዚህ መደብ እያንዳንዱ ክፍለ-ቃል ለተመሳሳይ ድምጽ ተመሳሳይ ቅርጽ ኖሮት ይመሳሰላሉ። እያንዳንዱ ፊደል ከአንድ መሠረት ቅርጽ ጀምሮ በየአናባቢው ይለወጣል ማለት ነው። ስለዚህ ቴ... ቱ... ታ... (እንደ ግዕዝ ጽሕፈት) ሲመሳሰሉ ይታያሉ።

በዚህም መደብ ውስጥ ከኢትዮጵያ ፊደሎች ጭምር በሕንድ ዙሪያ የተገኙት ብራህሚክ ጽሕፈቶች (ዴቫናጋሪ ወዘተ.) እና የካናዳ ኗሪዎች ጽሕፈት ይከተታሉ።

በአብጃዶች እያንዳንዱ ምልክት ለአንድ ተናባቢ ይጠቅማል። አብጃዶች ከሁሉ አስቀድሞ የተለመደው የአልፋቤት አይነት ነበር። በመጀመርያ አብጃዶች አናባቢዎቹ አልተጻፉም ነበር። በዛሬው አብጃዶች ግን (የዕብራይስጥ አልፋቤት፣ የአረብኛ አልፋቤት ወዘተ...) አናባቢዎቹ በልዩ ልዩ ተጨማሪ ምልክታት ሊታዩ ይቻላል። 

አብጃዶች ለሴማዊ ቋንቋዎች የተፈጠሩ ናቸው። ከሌሎች አብጃዶች መካከል፦ 

በቀድሞውም፦

በሙሉ ፊደላት (ባለ-አናባቢ አልፋቤቶች) እያንዳንዱ ምልክት ለተናባቢ ወይም ለአናባቢ ይጠቅማል። ስሙ ከግሪክ አልፋቤት መጀመርያ 2 ፊደላት አልፋ እና ቤታ መጣ። የላቲን አልፋቤት ደግሞ ሙሉ ፊደል ነው። ከሌሎቹም ዛሬ፦

በጥንትም፦

የቦፖሞፎ አልፋቤት በታይዋን ለቻይንኛ ሲጠቀም በከፊል ሲላቢክ ነው። 
በድሮ በእስፓንያ የነበሩ ጽሕፈቶች (የተርቴሶስ አልፋቤት ወዘተ.) ሙሉ ፊደሎች ሳይሆኑ በከፊል ሲላቢክ ነበሩ። 




#Article 72: ሚስኪቶ (384 words)


ሚስኪቶ በማዕከል አሜሪካ የሚኖር ብሔር ነው። መሬታቸው ከካሜሮን ርእሰ ምድር ሆንዱራስ ጀምሮ እስከ ሪዮ ግራንዴ ወንዝ ኒካራጓ ድረስ ይዘረጋል። የራሳቸው ሚስኪቶ ቋንቋ አለ። ነገር ግን የእስፓንኛ እና የሚስኪቶ እንግሊዝኛ ፓቷ ተናጋሪዎች በትልቅ ወገን ይገኛሉ።  የሚስኪቶ እንግሊዝኛ ፓቷ የመጣ ከእንግሊዞች ጋራ ብዙ ጊዜ በማገናኘታቸው ነበር። ብዙዎቹ ክርስቲያኖች ናቸው።

በጊዜ ላይ ያመለጡ ባርዮች ከነሱ ጋር ስደት ስላገኙ ዘራቸው ተደባልቆ ክልስ ሆነ።  መሬታቸውን ለመድረስ አስቸጋሪ በመሆኑ እስፓንያውያን ሰፊ አገሩን ሲወረሩ ለሚስኪቶዎቹ ብዙ ውጤት አልነበረም።

የሚስኪቶ ባሕላዊ ኅብረተሠብ በጣም የተደራጀ ነውና የተወሰነ ፖለቲካዊ ሥራዓት አለው። ንጉስ ቢኖሯቸውም ሙሉ ሥልጣን ግን አልነበራቸውም። ከነገስታታቸው ብዙዎች የሚታወቁ ከአፈታሪክ ስለሆነ የነሱ ታሪካዊ መረጃ ሁልጊዜ ግልጽ አይደለም። መንግሥታቸው ከ1617 ዓ.ም. በፊት ጀምሮ በታሪኩ መጀመርያ የተመዘገቡት ንጉሳቸው ኦልድማን ነበሩ። በአባታቸው ዘመን ከእንግሊዞች ተገናኝተው ኦልድማን ወደ እንግሊዝ አገር ተልከው ከእንግሊዝ ንጉስ ከ1ኛ ቻርልስ ጋር ተዋወቁ። በ1732 ዓ.ም. የሚስኪቶ ንጉሥ የወዳጅነት ውል ከእንግሊዝ ጋራ ተፈራርመው በ1741 ዓ.ም. በእንግሊዝ መከታ ውስጥ ገብተው ኗሪ ተቆጣጣሪ ተሾመላቸው።

ሥልጣን በንጉሱና በአገረ ገዥ በሻለቃ ከ1740ዎቹም ጀምሮ በባሕር ኃይል አለቃ መካከል ተከፋፍሎ ነበር። በአሜሪካ ነጻነት ጦርነት ጊዜ (1767-1775) የሚስኪቶ መንግሥት በእንግሊዞች ዘንድ አገልግሎ በስፓንያ ቅኝ አገሮች ላይ አደጋ በመጣል ብዙ ድል አገኘ።

ነገር ግን በ1775 ዓ.ም. እንግሊዝ ድል ስለሆነ በፓሪስ ሰላም ቃል ኪዳን ውል የባሕር ዳር ክልል መልቀቅ ነበረበት።  በ1779 ዓ.ም. እንግሊዞች በሙሉ ወጥተው ጨርሰው ስፓንያውያን መጀመርያ በሚስኪቶ መሬት ቢደርሱም ሚስኪቶዎቹ ግን ስለ ቁጥራቸውና ስለ አርበኞቻቸው አውራጃቸውን ከማሰልጠናቸው አልተዉም።  እንግሊዞች ቢወጡም የሚስኪቶ አገር ይፋዊ ባልሆነው መከታ ወስጥ ቀረችና ብዙ ጊዜ ከእስፓንያውያን ጋር ሲከራክሩ ብሪታኒያ በጉዳዩ ውስጥ ጥልቅ ብላ ገብታለች።

እንግሊዝ አገር በማዕከል አሜሪካ በተለይም በቤሊዝ የምጣኔ ሀብት ሀሳብ ስለነበራት ሚስኪቶዎቹ ጠመንጃ እና ሌሎች አዲስ መሣሪያዎች ሊያገኙ ቻሉ። ከዚያ በኋላ ሚስኪቶዎቹ ዛምቦ ከሚባሉት ክልሶች ጋር በስፓንያውያን መስፈርያዎች በሆንዱራስ ላይ አደጋ በመጣል የተማረኩትን ኗሪዎች በባርነት ወደ አውሮፓ ሳይወሰዱ ያድኗቸው ነበር።  ደግሞ የሌሎቹን ጐሣዎች ሰዎች ሲማርኩ ወደ ጃማይካ ይሸጧቸው ወይም ሴቶቻቸውን ያግቧቸው ነበር።  ከዚህ የተነሣ በባሕላቸውም ካንድ የበለጠ ሚስት ማግባት ስለ ተፈቀደ ቁጥራቸውን ቶሎ አበዙ።

ፖለቲካዊ ሥራዓታቸው በስፓንያውያን ግዛት ዘመንና በማእከል አሜሪካ አገሮች ፌዴራሲዮን አገዛዝ ዘመን ላይ ሚስኪቶዎች ነፃነታቸውን እንዲጠብቁ አስቻላቸው። ከ1851 ጀምሮ የእንግሊዝ መንግሥት መከታ ለሆንዱራስ  በሚከተለውም አመት ለኒካራጓ ተሰጠ። የሚስኪቶ መንግሥት ራስ-ገዥ ሁኔታ ምንም ቢሰጥም ኒካራጓ ግን ወደፊት ንጉሶቻቸውን አልተቀበለችም። በ1886 ዓ.ም. ምድራቸው በኒካራጓ መንግሥት ተያዘ። በኒካራጓ መንግሥት መቸም አልተሰለጠኑምና እስከ ዛሬ ድረስ ብዙዎች የኒካራጓ ዜጎች መሆናቸውን እራሳችውን አይቆጠሩም።

በ1970ዎቹና 1980ዎቹ, የኒካራጓ ኰሙኒስት ሳንዳኒስታ መንግሥት በጦርነት 8500 ሚስኪቶዎች ከቤቶቻቸው ሲያሳድዱ እስከ መቶ መንደሮችም ድረስ ሲያጥፉ ሚስኪቶዎቹ ከጎረቤቶቻቸው ከራማና ሱሙ ጐሣዎች ጋራ ሲያባብሩ ሚሱራሳታ የሚባል ግምባር አቆሙ። ይህ ጸረ-መንግሥት ወገን የኮንትራዎች ወንበዶች ክፍል ነበረ።  




#Article 73: እንግሊዝኛ (295 words)


እንግሊዝኛ የምዕራብ-ጀርመናዊ ቋንቋዎች ቤተሠብ ቋንቋ ነው። በዓለም ላይ በብዙ አገራት ውስጥ ይነገራል። የመጀመሪያ ተናጋሪዎቹ ቁጥር 380 ሚሊዮን ያሕል ሲሆን በብዛት የምድር 3ኛው ቋንቋ ነው። ከዚህ በላይ እስከ 1 ቢሊዮን ሰዎች እንደ ሁለተኛ ቋንቋ ይችሉታል።

እንግሊዝኛ በእንግሊዝ አገር ጀመረ። አንግል እና ሴያክስ የተባሉ ጀርመናዊ ጐሣዎች መጀመርያ የተናገሩት ጥንታዊ እንግሊዝኛ ይባላል። ነገር ግን ይህ እንደ ዛሬው እንግሊዝኛ በጣም አልመሰለም። በ441 አ.ም. ጀምረው እነዚህ ጐሣዎች ከጀርመን ወጥተው በብሪታኒያ ደሴት ሰፈሩ። ቋንቋቸውም የተጻፈበት «ሩን» በተባለው ጽሕፈት ነበር። በ7ኛ መቶ ዘመን ክርስትና ከተቀበሉ በኋላ ግን ቋንቋው በላቲን ፊደል ሊጻፍ ጀመረ።

ከ9ኛ መቶ ዘመን ጀምሮ ብዙ ሠራዊት ከዴንማርክና ከኖርዌ ወደ እንግሊዝ ስለ መጡ ተመሳሳይ ቋንቋ ስለነበራቸው ያን ጊዜ እንግሊዝኛ ከጥንታዊ ኖርስ አያሌ ቃሎች ተበደረ።

በ1058 ዓ.ም. ዊሊያም 1 «አሸናፊ» ከነሠራዊቱ እንግሊዝ አገርን ወርሮ ንጉስ ከሆነ በኋላ አዲስ መንግሥት ለማቆም መኳንንቶቹን ከፈረንሳይ ከሱ ጋራ አመጣ። የእንግሊዝ መንግሥት ቋንቋ ፈረንሳይኛ ሲሆን ለረጅም ጊዜ (300 አመቶች) እንግሊዝኛ ከትምህርት ቤቶች ተከለክሎ ቋንቋው ለጽሑፍ ሳይሆን እንደ መነጋገርያ ብቻ ስለ ቀረ በዚያን ጊዜ ጠባዩ ብዙ ተለወጠ። እንግሊዝኛ በዚሁ ዘመን እጅግ ብዙ ቃላት ከፈረንሳይኛ ስለተበደረ በፍጹም ሌላ መልክ ይዞ አሁን መካከለኛ እንግሊዝኛ ይባላል። ቻውሰር የተባለው አንድ ስመ ጥሩ የመካከለኛ እንግሊዝኛ ጸሐፊ ነበር።

በ15ኛ መቶ ዘመን «ታላቅ የአናባቢ መፈራረቅ» በሚባለው ለውጥ ምክንያት፡ አናባቢዎቹ ተለውጠው የቋንቋው ድምጽ እንደገና ሌላ መልክ ያዘና ከዊሊያም ሼክስፒር ዘመን ጀምሮ «ዘመናዊ እንግሊዝኛ» ተብሏል።

እንግሊዝኛ ከሌሎቹ ልሣናት ለምሳሌ ከቻይንኛ፥ ከህንዲ፥ ከጃፓንኛ እና ከእስፓንኛ አንዳንድ አዲስ ቃላት ከመውሰድ አላቋረጠም። ከተለያዩ አገሮች የነበሩት ሊቃውንት እርስ በርስ ለመነጋገር የቻሉ የጋራ ካወቁት ልሳናት ከሮማይስጥና ከግሪክ የጥናቶቻቸውን ቃሎች በመምረጥ ነበር። እነዚያ የተክኖሎጂ ቃሎች ደግሞ ወደ እንግሊዝኛ ገቡ፤ ለምሳሌ፣ photograph (ፎቶግራፍ) ከግሪክ photo- ፎቶ (ብርሀን) እና -graph ግራፍ (ሰዕል)፤ ወይም telephone (ተለፎን) ስልክ። ስለዚህ እንግሊዝኛ ከብዙ ቋንቋዎች ይሠራል ሊባል ይችላል።

ከሷዴሽ ዝርዝር 207 ዘመናዊ እንግሊዝኛ ቃላት፣ 161 ወይም 78% በቀጥታ ከጥንታዊ እንግሊዝኛ ቃላት ተደረጁ።

ከተረፉትም 46 ቃላት መኃል፤

የተረፉት 21 ቃላት ወይም 10% የመጡ ከጥንታዊ እንግሊዝና ሲሆን፣ ከጥንታዊ እንግሊዝኛ አዲስ ትርጉም ተሰጡ።




#Article 74: ደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል (751 words)


የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች (የድሮ ክልሎች 7,8,9,10,11) በኢትዮጵያ ከሚገኙ ዘጠኝ ክልሎች አንዱ ነው። 105,887.18 ካሬ ኪ.ሜ. ቦታ 
የሚሸፍን ሲሆን በምዕራብ በጋምቤላ፣ በደቡብ ምዕራብ ከደቡብ ሱዳን፣ ሰሜን ምሥራቅና ደቡብ ምሥራቅ በኦሮሚያ፣ በደቡብ ከኬንያ ጋር ይዋሰናል። የክልሉ ዋና ከተማ ሃዋሳ ሲሆን ሌሎች ትልቅ ከተማዎች አርባ ምንጭ፣ ሆሳዕና፣ ክብረመንግሥት፣ ያቤሎ፣ አላባ፣ አገረሠላም፣ አለታዎንዶ፣ ቦዲቲ፣ ወንዶ፣ ዲላ፣ ይርጋለም፣ ጂንካ፣ ሶዶ፣ ቦንጋ፣ ሚዛን ተፈሪ ናቸው።

ክልሉ በ፲፫ ዞኖችና ፰ ልዩ ወረዳዎች በ፳፪ የከተማ አስተዳደሮች የተደራጀ ሲሆን በ፲፱፻፺፱ ዓ.ም. በተደረገው የሕዝብና ቤት ቆጠራ መሠረት 15,042,531 ሕዝብ የሚገኝበት ሲሆን ይህም ከአገሪቱ ጠቅላላ ሕዝብ 20.4% ይሸፍናል። ከዚህ በተጨማሪ በክልሉ ፶፮ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የሚኖሩ ሲሆን የእነዚህም ቋንቋዎች በአፍሮ እስያዊ (ኩሻዊ፣ ኦሞአዊ እና ሴማዊ ንዑስ ክፍሎችን ጨምሮ) እና ናይሎ ሳህራዊ የቋንቋ ቤተሰቦች ይመደባሉ።

የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በኢትዮጵያ ካርታ ውስጥ ከ34° 88′ እስከ 39°14′ ምሥራቅ ኬንትሮስና ከ4°43′ እስከ 8° 58′ ሰሜን ኬክሮስ መካከል ይገኛል። 

ክልሉ 4207 ሜትር ከፍታ ካለው የጋሞ ጐፋው ጉጌ ተራራ እስከ 376 ሜትር  ከባህር  ጠለል በላይ ከፍታ ያለው የደቡብ ኦሞው ጨልባና ቱርካና ኃይቅ አካባቢ ያለው ዝቅተኛ ቦታን ጨምሮ በርካታ የተለያየ መልክዐ ምድራዊ አቀማመጥን ይዟል። በሐሩር፣ በቆላ፣ ወይናደጋና ደጋ የአየር ንብረትን የተከፋፈለ ሲሆን ለእርሻ ከብት እርባታ ምቹ የሆነና በደንም የተሸፈነ ክልል ነው። የአዋሣ የአባያ፣ ጫሞ፣ጨው ባህርና ቱርካና የመሳሰሉ ኃይቆች ኦሞ፣ጐጀብና ብላቴ ወንዞች ባለቤትና ከገናሌ-ዳዋ ከባሮ-አኮቦ፣ ከኦሞ-ግቤ፣ በአጠቃላይ 32% የሚደርሱ ተፋሰሶችንም ይጋራል። የአጆራ፣ሎጊታና ጋቺት ፏፏቴዎች የነጭ ሣር፣ኦሞ ማዜና የማጐና የጨበራ ጩጩራ ብሔራዊ ፓርኮች የሚገኙበት ነው።

የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት የተዋቀረው በሕግ አውጭው፣ ሕግ አስፈፃሚውና የዳኝነት (ሕግ ተርጓሚ) አካላት ነው። ከሌሎች ክልሎች በተለየ መልኩ የክልሉ ፖርላማ በሁለት ምክር ቤቶች ተዋቅሯል። እነዚህም የክልሉ ምክር ቤትና የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት ናቸው። የህግ አስፈፃሚው የመስተዳድር ምክር ቤት በርዕሰ መስተዳድሩ የሚመራ ሲሆን የዳኝነት አካል በጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት ይመራል። የሁሉም አካላት አወቃቀር ከብሔረሰቦች ም/ቤት በስተቀር በተዋረድ በክልሉ ውስጥ በሚገኙ ፲፫ ዞኖች፣ ፰ ልዩ ወረዳዎች በጠቅላላ የልዩ ወረዳዎችን ጨምሮ በ፻፴፬ ወረዳዎችና ፴፱፻፲፮ ቀበሌዎች ድረስ በተመሣሣይ ሁኔታ ተዋቅሯል።

በጥናት ከተደረሰባቸው ታሪካዊ ቦታዎችና ቅርሶች ግንባር ቀደሙ በክልሉ በሁሉም ቦታ ተሠራጭቶ የሚገኝ ትክል ድንጋይ ሲሆን በአጠቃላይ ከ፲ሺህ በላይ እንደሆነ ይገመታል። ከእነዚህ ውስጥ አንድ ላይ ጥቅጥቅ ብለው በተለያዩ ሥነ ቅርጽና መልክ የተደረደሩትና የተተከሉት በጉራጌ ዞን የሚገኘው ጢያ በ1980 እ.ኤ.አ. በዩኔስኮ በዓለም ቅርስነት ተመዝግቧል። በክልሉ በርካታ ዋሻዎች ሲገኙ ከእነዚህ ውስጥ ሞቼ ቦራጐና አክርሳ ዋሻ /ወላይታ/ እና በጌዴኦ የሚገኙ የተቦረቦሩ ፭ የሥነ ድንጋይ ዋሻዎችና ቱቱ ፈላ ትክል ድንጋይ ግንባር ቀደሞቹ ናቸው።

በሌላ በኩል በክልሉ በዓለም አቀፍ ደረጃ የታወቁ የፓሊዮ አንትሮፖሎጂ አርኪዮሎዲጂ ቦታዎች ይገኛሉ። ከእነዚህ ውስጥ የታችኛው ኦሞ ሸለቆ አካባቢ /ሸንጋራ፣ ኡስኖ፣ ኪብሽና ሙርሲ አወቃቀሮ

ች (formation) የታወቀ ነው። የታችኛው ኦሞ ሸለቆ በ1980 እ.ኤ.አ. በዓለም አቀፍ ቅርስነት የዩኔስኮ መዝገብ ዝርዝር ገብቷል። ኮንሶ አካባቢ፤ ፋጀጅና ወይጦ አጭቀሬ በደቡብ ኦሞ ቡርጂ ቁሊቾ በቡርጂ ሌሎቹ የፓሊዮ አንትሮፖሎጂ ቦታዎች ይገኛሉ።

ይህ ዝርዝር የተሟላ አይደለም

ሸኮ

የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ዋነኛ የኢኮኖሚ መሠረት ግብርና ነው። ዋና ዋና ምርቶችም በቆሎ፣ ስንዴ፣ ጤፍ፣ ጥራጥሬ፣ ድንች፣ እንሰት፣ ፍራፍሬዎችና የቅባት ሰብሎች ናቸው። ዋነኛው ምርት በእህል ራስን ለመቻል የሚያስችሉ ሲሆኑ ጐን ለጐን ገበያ ተኮር የሆኑ ቡና፣ ሻይ ቅጠል፣ ጐማ ተክል ወዘተ እንዲሁም ማንጐ፣ አኘል፣ አቦካዶ፣ አናናስ፣ ፓፓያና ሙዝ በስፋት ይመረታል። የቁም ከብቶች ወተትና የወተት ተዋፅኦም ይገኛል።

ከግብርና በተጨማሪም በንግድና ኢንዱስትሪ ዘርፍ በግንባታ፣ እንጨትና ብረታ ብረት፣ ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት የተደራጁ ማኀበራት ይገኛሉ።

በ፲፱፻፺፱ ዓ.ም. የክልሉ አጠቃላይ ንፁህ የመጠጥ ውኃ ሽፋን 58% ደርሷል። ከዚህ ውስጥ የገጠሩ ሽፋን 57% ሲሆን በከተማ 66% እንዲሁም የተጠቃሚው ሕዝብ ብዛት 8.7 ሚሊዮን ድረስ እንደደረሰ መረጃዎች ያመለክታሉ።

በክልሉ ያሉ ትምህርት ተቋማት ብዛት (ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል) 3,625፣ (ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል) 144፣ የመሰናዶ (ከ9-12) 44 ነው። በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ደረጃም 64 የመንግሥትና የግል ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛዎች፣ ኮሌጆች /16ቱ አዋሣ ከተማ ውስጥ የሚገኙ/ እንዲሁም 5 ዩኒቨርሲቲዎች ይገኛሉ። አጠቃላይ የትምህርት ተሣትፎ በ፲፱፻፺፱ ዓ.ም. መረጃ መሠረት 97.9% የደረሰ ሲሆን የሴቶች ተሣትፎ ወደ 84% አድጓል። የተማሪ መምህር ጥምርታ (1-4 ክፍል) 1፡66፣(5-8) 1፡60፣ (9-10) 1፡82፣ (1-12) 1፡42  ነው።

የ፲፱፻፺፱ ዓ.ም. የጤና ቢሮ መረጃ መሠረት በክልሉ 2,287 ጤና ኬላዎች 161 ጤና ጣቢያዎችና 16 ሆስፒታሎች ይገኛሉ። በአጠቃላይ የጤና ተሣትፎ  ሽፋን 75% ደርሷል። መገናኛን በተመለከተ 2 ፖስታ ቤቶች፣ 2 ዋና ቅርንጫፍ ፖስታ ቤቶችና 44 ወኪል ፖስታ ቤቶች ሲገኙ ከ133 ከተሞች በላይ የዲጂታል አውቶማቲክና የሳተላይት ስልኮችን ይጠቀማሉ። በ፲፱፻፺፱ ዓ.ም. መረጃ መሠረት በክልሉ የሚገኙ 130 የሚደርሱ ከተሞች የኤሌክትሪክ መብራት ያገኛሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አብዛኛዎቹ የ24 ሰዓት አገልግሎት የሚሰጡ ሲሆን እጅግ በጣም ጥቂቶቹ በዲዚል ሞተር የሚንቀሣቀሱ የ12 ሰዓት አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው፡፡

ሬድዮ፣ ቴሌቭዥንና ጋዜጣን በተመለከተ ሁለት የአካባቢ ሬድዮ ጣቢያዎች /«ፉራ ትምህርት ማሠራጫ ጣቢያ» እና «ወላይታ ሶዶ»/ እና በቅርቡ የተቋቋመው የደቡብ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ (FM 100.9) አዋሣ ይገኙበታል። ጋዜጦችን በሚመለከት «የደቡብ ንጋት» የተባለው የደቡብ ክልላዊ መንግሥት ጋዜጣ፣ በአዋሣ ከተማ ሽግግር አስተዳደር በአማርኛ የሚታተም «ዜና አዋሣ»፣ «ሚረር 3» የተባለ የግል ጋዜጣና በአርባ ምንጭ ከተማ የሚታተም «ትፍላሜ» የተባለውና በክልሉ ባህልና ማስታወቂያ የሚታተም «ማህደረ ደቡብ» የተባሉ ጋዜጦችና መጽሔቶች የሚታተሙ ሲሆን በየመ/ቤቱ የሚወጡ በርካታ ዓመታዊ መጽሔቶችም ይገኙበታል። በክልሉ መንግሥት እየተዘጋጀ በየቀኑ ከሰኞ እስከ እሁድ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ የሚተላለፍ የአንድ ሰዓት የቴሌቢዥን ኘሮግራም ይገኛል።




#Article 75: የኒካራጓ ምልክት ቋንቋ (181 words)


የኒካራጓ ምልክት ቋንቋ (ISN, Idioma de Señas de Nicaragua ወይም Idioma de Signos Nicaragüense) በ1970ዎቹና በ1980ዎቹ በምዕራብ ኒካራጓ የመስማት መሳን ባለባቸው ተማሪዎች የተለማ የምልክት ቋንቋ ነው። የተለማው ከቆዩት እጅ ቋንቋዎች ሳይሆን በተማሪዎች እራሳቸው በድንገት ነበር። ስለዚህ ለቋንቋ ሊቃውንት የመነጋገር ልደት ወይም የመንስኤው ሁኔታ ለማጥናት ያስችላል።

ከ1969 ዓ.ም. በፊት በመስማት የተሳናቸው ሰዎች ኅብረተሠብ አልነበራቸውም። ከቤተሠቦቻቸው ጋራ ለመነጋገር ይቻሉ ቀላል በሆነ እጅ ንቅናቄ ብቻ ነበር።

በ1969 ዓ.ም. ግን ጆሯቸው ለማይስማ ተማሪዎች ልዩ ተምህርት ቤት በዋና ከተማ በማናጓ ስለ ተመሠረተላቸው 50 ተማሪዎች ወዲያው ትምህርታቸውን ጀመሩ። የሳንዲኒስታ አብዮት በሆነበት ወቅት (1971 ዓ.ም.) መቶ ተማሪዎች ነበሩ። በ1972 ሁለተኛ ልዩ ትምህርት ቤት ተከፍቶ በ1975 ዓ.ም. የተማሪዎች ቁጥር 400 ደረሰ። 

በመጀመርያ ትምህርት ቤቶቹ የከንፈር ማንበብና የጣት ፊደል ብቻ ለማስተማር አስበው ይህ ዘዴ ግን አልተከናወንም። ዳሩ ግን ተማሪዎቹ በትርፍ ጊዜያቸው በቤተሠቦቻቸው የተጠቀሙትን እጅ ምልክቶች እርስ በርስ ስለተማማሩ በትንሽ ጊዜ የራሳቸውን ቋንቋ ፈጠሩ።

የትምህርት ቤት አስተማሪዎች ግን ስለዚህ ልማት አላወቁም ነበር። የእጅ ምልክቶቻቸው እንደ ጨዋታ ብቻ መስሏቸው እስፓንኛ መማር ስለማይችሉ ይሆናል በማሰብ ገመቱ። እንዲግባቡ ከቶ ስላልቻሉ በመጨረሻ በ1978 ዓ.ም. ከአሜሪካ አንዲት የአሜሪካ ምልክት ቋንቋ መምህር ጁዲ ኬግል አስመጥተው እሷ ምልክቶቻቸውን በድንብ ለማጥናት ወሰነች። ያልታወቀ አዲስ ቋንቋ መሆኑን የገለጠች እርሷ ሆነች።




#Article 76: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን (2844 words)


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ኃይማኖት ተከታዮች በተለይም ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በ፴ ዓ/ም በፈለገ ዮርዳኖስ በመጥምቁ ዮሐንስ እጅ በዮርዳኖስ ባሕር የተጠመቀበትን ዕለት የሚያስታውሰው፣ ኤጲፋንያ በመባልም የሚታወቀው ደማቅ በዓል ነው። መገለጥ፣ መታየት ማለት ነው። የኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት ታሪክ የሚገኘው በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፫ ቁ ፲፫–፲፯ ውስጥ ነው።   ጌታ

በአገራችን፣ ጥር ፲ ቀን፣ በከተራ፣ በገጠር ወራጅ ውሃ የሚከተርበት፣ ታቦታት ከየአቢያተ ክርስቲያናቱ በዓሉ ወደሚከበርበት ቦታ በምዕመናን ታጅበው በዘፈንና በሆታ ይሄዳሉ። እዚያም በተዘጋጀ አቡነ ባስልዮስ ከእስክንድርያ ፓትርያርክ አቡነ ዮሳብ 2ኛ የጵጵስና ማዕረግ ተቀበሉ። ኢትዮጵያም፤ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እራሷን የቻለች ሆነች። ወደ ፶፭-፷ ሚሊዮን የሚቀርቡ ምእመናን ሲኖሩት ከምሥራቃዊ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ትልቁ ነው።

በ443 ዓ.ም. (451 እ.ኤ.አ.) በሮማው ንጉሥ መርቅያን ዘመነ መንግሥት ፮፻፶ ኤጲስ ቆጶሳት በተገኙበት የተሰበሰበው የኬልቄዶን ጉባኤ ከሮማው ሊቀ ጳጳሳት ቀዳማዊ ልዮን ክርስቶስ ሁለት የተለያዩ ባሕርያት አሉት የሚል ጽሑፍ አቅርቦላቸው ነበር። ዳሩ ግን የእስክንድርያው ፓትርያርክ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ጌታ ሁለት ባሕርያት አሉት የሚለው ትምሕርት ስሕተት ነው ብሎ ልዮንን አወገዘው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት በእምነት ተለያዩ። የቅዱስ ዲዮስቆሮስን ትምሕርት የሚከተሉ ዛሬ የአርሜኒያ፣ የሕንደኬ፣ የግብፅ፣ የሶርያ፤ የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት  ጌታችን መድኃኒታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ ከሁለት አካል አንድ አካል በመንሳት ፍፁም ሰው ፍፁም አምላክ ማለት ነው። 

የቤተ ክርስቲያን መመስረት በኢትዮጵያ የተጀመረው በወንጌል ሰባኪ ቅዱስ ፊልጶስ መሆኑ ይታወሳል (ሐዋርያት ምዕራፍ ፰)፦

በዚህ ንባብ ዘንድ ፊልጶስ ጃንደረባውን የትንቢተ ኢሳይያስ ክፍል እንዲገባው አስረድቶት በክርስትና አጠመቀው። ንግሥት ግርማዊት ህንደኬ ፯ኛ ከ፴፬ ዓ.ም. እስከ ፵፬ ዓ.ም. ገደማ በኢትዮጵያ የነገሡ ናቸው።

በ፬ኛው ምዕት ዘመን በወንድማማቾቹ በንጉሥ ኤዛና እና በንጉሥ ሳይዛና ዘመን በፍሬምናጦስ አማካይነት ክርስትና የግዛቱ ይፋዊ ሃይማኖት ሆነ። ይህ ፍሬምናጦስ በኢትዮጵያ «አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን» ተብሎ ይታወቃል። በወጣትነት ዕድሜው ከአጎቱ ከፈላስፋው ከመሮፔዎስ እና ከወንድሙ ከሲድራኮስ ጋራ መርከባቸው ስለሰመጠች ከወንድሙ ጋር ከሞት ተርፈው ምጽዋ አጠገብ ተገኙ። ወደ ነገሥታቱም ግቢ አመጧቸውና ቀስ በቀስ ከፍተኛ ተጽእኖ ያለበትን ደረጃን አገኙ። ንጉሥ ኤዛናን ደግሞ ወደ ክርስትና ለውጠው እንዲጠመቁ አደረጉ። ኤዛና ፍሬምናጦስን ለኢትዮጵያ አቡን እንዲሾም ለመጠየቅ ወደ እስክንድርያ ላኳቸውና የእስክንድርያ ጳጳስ አትናቴዎስ ፍሬምናጦስን ሾሞ ላከው። ፍሬምናጦስ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ሲሆን የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ፓትርያርክ አቡነ ባስልዮስ ደግሞ ፻፲፩ኛው መሆናቸው ነው።

እስላሞች ወደ ግብጽ ከገቡ በኋላ ከእስክንድርያ ጋር የነበረው ግንኙነት ቀጥሏል። ጸሐፊው አቡ ሳሊኅ በ፲፪ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን እንደ ገለጸው፣ ፓትርያርኩ በየዓመቱ ፪ ደብዳቤዎች ለኢትዮጵያና ለኖቢያ ነገሥታት ይጽፉ ነበር። ይህንን አደራረግ ግን አቡ ሃኪም አስቀረ። ፷፯ኛው ፓትርያርክ ቂርሎስ እንደ ኤጲስ ቆሞስ የላኩት ሰቨሩስ ሲሆኑ የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት ሁሉ እንዲያስጠበቁ ታዘዙ። በ፲፬፻፴፩ ዓ.ም. በዓጼ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመን አባ ጊዮርጊስ ከአንድ ፈረንሳዊ ጐብኚ ጋራ ስለ ሃይማኖት ስለተነጋገሩ አንድ ተልዕኮ ወደ ሮማ ተላከ። 

በ፲፭፻ ዓ.ም. ደግሞ ኢትዮጵያ ከአዳል ጋር ስትታገል ማቴዎስ የተባለ አንድ አርሜናዊ ወደ ፖርቱጋል ተልኮ የፖርቱጋል ንጉሥ እርዳታን ለመነ። ስለዚህ በ፲፭፻፲፪ ዓ.ም. የፖርቱጋል ሚሲዮን በኢትዮጵያ ደረሰ። በሚከተለው ክፍለ ዘመን ከፖርቱጋል ኢየሱሳውያን የተባሉ ሚሲዮኖች ቤተ መንግሥቱን ወደ ሮማ ካቶሊክ ሃይማኖት ለማዞር ብዙ ጣሩ። በመጨረሻ በ፲፮፻፲፯ ዓ.ም. ንጉሥ ሱስንዮስ ወደ ሮማ ካቶሊክ እምነት ተቀየሩ። ዳሩ ግን የሮማ ሃይማኖት በተዋሕዶ ፈንታ ይፋዊ መሆኑን ሕዝቡ በጣም አልወደደምና በ፲፮፻፳፭ ዓ.ም ሱስንዮስ ዘውዳቸውን ለልጃቸው ለፋሲለደስ እንዲሰጡ ተደረጉ። ፋሲለደስ ወዲያው አገሩን ወደ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መለሱ። ከዚህ በላይ በ፲፮፻፳፮ ዓ.ም ፋሲለደስ ኢየሱሳውያን አገሩን ለቅቀው እንዲሄዱ አዘዙ። በ፲፮፻፶፰ ዓ.ም. መፃሕፍታቸውም እንዲቃጠሉ አዘዙ።

ኢትዮጵያ ብሉይ ኪዳንን እና ሐዲስ ኪዳንን በሙሉ (ከነዲዩትሮካኖኒካል መፃሕፍት ጋር) በመቀበል ብቸኛ ሃገር ናት። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምትቀበላቸው ቅዱሳት መፃሕፍት ቁጥራቸው ፹፩ ሲሆን እነዚህም ፴፭ የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍትና ፵፮ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ናቸው። ይህ የቅዱሳት መጻሕፍት ቁጥር በቀኖና በ፫፻፲፰ቱ አበው ሊቃውንት የኒቂያ ገባኤ ተደንግጓል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሥነ ሕንፃ የቤተክርስቲያናት ትውፊታዊ የሥነ ሕንጻ ጥበቧ አምስት ዓይነት ነው። እነርሱም ክብ፥ መስቀል ቅርፅ፥ ዋሻ፥ ፍልፍል እና ስቀልማ ናቸው። ክብ ሕንጻ አብያተ ክርስቲያናት በብዛት በገጠሪቷ ኢትዮጵያ የሚገኙ ሲሆን፣ መስቀል ቅርጽ ያላቸው ደግሞ በከተማ አካባቢ ይገኛሉ። ዋሻ አብያተ ክርስቲያናት በብዛት በተራራማ አካባቢዎች ሲገኙ፣ ፍልፍል አብያተክርስቲያናት ደግሞ ከአንድ ቋጥኝ ተፈልፍለው የተዘጋጁ ናቸው። ሰቀልማ የሚባለው እንደ ጎንደሩ ደብረ ብርሃን ሥላሴ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው።

ትምህርት ሃይማኖት (የሃይማኖት ትምህርት) በሁለት ይከፈላል። ይኸውም፦ 1ኛ) ዶግማ፣   2ኛ) ቀኖና በሚል ነው። 'ዶግማ' ቃሉ የግሪክ ሲሆን ፍችውም እምነት ማለት ነው።

'ቀኖና' ደግሞ ቃሉ የግሪክ ሲሆን ሥርዓት ማለት ነው። ከእነዚህ ከሁለቱ ዶግማ ወይም እምነት አይጨመርበትም፤ አይቀነስበትም፤ አይሻሻልም፤ ችግርና ፈተናም ቢመጣ እስከ ሞት ድረስ አጥብቀን የምንይዘው ነው። ለምሳሌ ያህል፣ ይህን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ የፈጠረ፤ ቢመረምር እንጂ የማይመረመር ሁሉን ቻይ አምላክ፤ የሚሳነው ነገር የሌለ ፈጣሪ፤ የሰማይና የምድር ባለቤት፣ የሠራዊት ጌታ ሕያው እግዚአብሔር ነው።

እግዚአብሔር (ፈጣሪ) የአካል ሦስትነት አለው። በመለኮት፣ በመፍጠር፣ በሥልጣን፣ በአገዛዝ፣ በፈቃድ እና በመሳሰሉት ግን አንድ ነው። በሦስትነቱ አብ፥ ወልድ፥ መንፈስ ቅዱስ ሲባል፣ በአንድነቱ አንድ መለኮት፥ አንድ እግዚአብሔር ይባላል። በአዳም ምክንያት ከመጣው የዘለዓለም ሞትና ከዲያብሎስ ባርነት ነፃ የወጣነው ከሦስቱ አካላት በአንደኛው አካል ማለትም በወልድ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ይህ ዶግማ ወይም እምነት ይባላል።

ቀኖና ግን በአምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምነው ያደጉ ክርስቲያኖች የሚመሩበት ሥርዓት ስለሆነ፣ በሃይማኖት አባቶች ወይም በቅዱስ ሲኖዶስ አማካኝነት እንደጊዜው ሁኔታ የሚሻሻል በመሆኑ የሚጨመርበት፣ የሚቀነስለት ነው። ለምሳሌ ያህል እኛ ኦርቶዶክሳውያን የምንጠመቀው ሴት በተወለደች በሰማንያ ቀን፣ ወንድ በተወለደ በአርባ ቀን ነው። የተወለዱ ሕፃናት፣ ሴቷ ሰማንያ ወንዱም አርባ ቀን ሳይሞላቸው ቢታመሙና በሽታው አስጊ ቢሆን የግድ የተባለው ቀን ሳይጠበቅ በ10፣ በ20፣ በ30…ቀናቸው መጠመቅ ይችላሉ ቀኖና ነውና። በቤተ ክርስቲያናችን የቀዳስያን ብዛት መነሻው አምስት ነው። ምናልባት ከአምስቱ አንዱ፣ ሁለቱ፣ ሦስቱ ቢታጡና ሌላም ተፈልጎ እስከ መጨረሻ የማይገኝ ከሆነ፣ ከአቅም በላይም የሆነ ችግር ከገጠመ፣ ሁለቱ ወይም አንዱ ብቻ ቀድሰው ማቁረብ ይችላሉ፤ ቀኖና ነውና። በቤተ ክርስቲያናችን ታቦት ሲከብር ቤተ ክርስቲያኑን የሚዞረው ሦስት ጊዜ ነው፥ ችግር ካለ አንድ ጊዜ ብቻ ዑደት ተፈጽሞ ሊገባ ይችላል። ቀኖና ነውና፤ ስለቀኖና (ስለሥርዓት) ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ እንዲህ ሲል ጽፏል።

አሁን እንግዲህ የዶግማንና የቀኖናን ልዩነት ከተረዳን በቀጥታ ወደ ታቦቱ ጥያቄ እንሄዳለን።

ጥያቄ 1፦ ዛሬ በእኛ ቤተ ክርስቲያን ያለው ታቦት ነው? ወይስ በታቦትና በጽላት መካከል ልዩነት አለ?

መልስ፦ ታቦት የጽላት ማደሪያ ነው፤ ዘዳ 40፥20። ጽላት ደግሞ ቅዱስ ቃሉ የተጻፈበት ሰሌዳ ማለት ነው፤ ዘዳ 34፥27-28። ስለዚህ እነዚህ ሁለት ነገሮች ዛሬም በሐዲስ ኪዳን አሉ። ሆኖም ግን አሠራሩ ሙሉ በሙሉ በዘጸ 25፥10-18 ያለውን የሙሴን ሕግ የተከተለ አይደለም። ምክንያቱም፦

እንግዲህ እዚህ ላይ የሐዲስ ኪዳኑ ታቦትና ጽላት የብሉይ ኪዳኑን የታቦት አሠራርና ሥርዓት ጠንቅቆና ተከትሎ የማይሄድ ከሆነ፣ ይህ የብሉይ ኪዳኑን የታቦትና የጽላት አቀራረጽ ሥርዓት ጠንቅቆ ያልሄደ የሐዲስ ኪዳን ታቦትና ጽላት ከየት መጣ? የሚል ጥያቄም ሳያስነሳ አይቀርም።

አንባብያን ሆይ በቀጥታ ወደ ጥያቄው ከመግባታችን በፊት በዚህ ፅሑፍ ስለዶግማና ቀኖና ማብራሪያ የሰጠነው ይህን ለመሰለው ጥያቄ እንዲጠቅም ነው። አሁን ወደ ሐዲስ ኪዳን ታቦትና ጽላት ስንሄድ ቁም ነገሩ እንደሚከተለው ነው።

የሐዲስ ኪዳን የታቦትና የጽላት አቀራረጽም ሆነ አጠቃቀሙ የተወሰነውና የሚወሰነው በቀኖና ነው። ቀኖና ደግሞ እንደ ሁኔታው የሚሻሻል ነው። ሲቻል ይጨመርበታል፣ ሳይቻል ደግሞ ይቀነስለታል። እንግዲህ በቤተ ክርስቲያናችን ቀኖና ካበረከታቸው ነገሮች አንዱ የሐዲስ ኪዳን የታቦትና የጽላት አቀራረጽንና አጠቃቀምን ነው።

ስለዚህ በሐዲስ ኪዳን ታቦትን ለመቅረጽ የግራር እንጨት ባይገኝ በዘፍ 1፥31 ላይ እግዚአብሔርም የፈጠረውን (ያደረገውን) ሁሉ እጅግ መልካም እንደሆነ አየ ስለሚልና፣ እግዚአብሔር የፈጠረውን ስለማይንቅ፣ ከግራር ሌላ ከማይነቅዝ እንጨት መቅረጽ እንችላለን። ቁመቱ፣ ወርዱና ዙሪያውም እንደችሎታችን ይሆናል። በውስጥና በውጭ ስለሚሆነው የወርቅ ክብርም እንደችሎታችን ይወሰናል። ከሌለንም ወርቁ ይቀራል፣ ቀኖና ነውና።

ስለጽላቱም እንደዚሁ ነው፥ ከቻልን ከከበረ ድንጋይ፣ ከዕብነ በረድ መቅረጽ እንችላለን፤ ካልቻልን ጽላቱን ከማይነቅዝ እንጨት መቅረጽ እንችላለን። በሌላ በኩልም ከቻልን እንደ ብሉይ ኪዳኑ በአንድ ታቦት ሁለት ጽላት ማስቀመጥ እንችላለን፤ ካልቻን በአንድ ታቦት አንድ ጽላት ብቻ ይሆናል። በተጨማሪም ጽላቱን ማስቀመጫ ታቦት ባይኖረን፣ ጽላቱን ታቦት ብለን በመጥራት በጽላቱ ብቻ መጠቀም እችላለን፥ ቀኖና ነውና።

በተጨማሪም በኤር 31፥31፤ 2ኛ ቆሮ 3፥1-3፤ በዕብ 8፥8-13፣ የእኛ አካልና ልቡና የርሱ ታቦትና ጽላት ናቸውና በሐዲስ ኪዳን ለምን ታቦትና ጽላት አስፈለገ? ለምንስ ይህ ሁሉ ተፈጠረ? የሚሉ አሉ። የክርስቲያኖች  አካልና ልቡና በክርስቶስ ደም ታቦት፤ ጽላት፤ ቤተ መቅደስ መሆኑን እናምናለን። ቢሆንም፣ በሐዲስ ኪዳን ታቦትና ጽላት ያስፈለገበት ምክንያት፣ ስለአምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነትና ክብር ሲባል ነው። ምክንያቱም በብሉይ ኪዳን ክብሩን የገለጠበት፣ ቃሉን ያሰማበት፣ ሙሴን እንደባልንጀራ ያነጋገረበት የክብሩ ዙፋን ሆኖ፣ ታቦቱ በውስጡ ለሚቀመጠው ለጽላቱ ማደሪያ በመሆኑ፣ በሐዲስ ኪዳንም የሥጋውና የደሙ የክብር ዙፋን እንዲሆን ሲሆን ስለእኛ በዚህ ዓለም መከራ የተቀበለውን መድኃኔዓለም ክርስቶስን ለማክበር ሲባል ነው።

ጥያቄ 2፦ በዘዳ 31፣18፣ 32፣ 15፣ 134፥1-5፣ 2ኛ ዜና 5፥10 ያሉትን ጥቅሶች በመጥቀስ እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠው ሁለት ጽላቶችን ብቻ ነው። ነገር ግን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እነዚህን እልፍ አእላፋት ጽላት ከየት አመጣቻቸው? አራብታችሁ ቅረጹ የሚል አለ ወይ?

መልስ፦ በዘዳ 32፥19 ስንመለከት እግዚአብሔር ራሱ አዘጋጅቶ ለሙሴ የሰጠውን ሁለቱን ጽላት እሥራኤል ጣዖት ሲያመልኩ ስላገኛቸው ሙሴ ተበሳጭቶ ሰብሯቸዋል። ነገር ግን ቸርነቱ ለዘለዓለም የሆነ እግዚአብሔር አምላክ ለሙሴ የመጀመሪያዎቹን አስመስሎ እንዲሠራ ነገረው፤ ሙሴም አስመስሎ ሠራ። በዘዳ 34፥1-5 መሥራት ብቻ ሳይሆን ኣሥሩን የቃል ኪዳን ቃላትም በጽላቱ ላይ እንዲፅፍ ሙሉ ሥልጣን ከእግዚአብሔር ተሰጠው። ሙሴም ተፈቅዶለታልና አሥሩን ቃላት በጽላቱ ላይ ጻፈ። ዘዳ 34፥27-28 ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ጽላትንም ሆነ ታቦትን እያስመሰሉ ለመሥራት ሙሉ ሥልጣንን አግኝተናል። ይህን በተመለከተ አንዳንድ አባቶች፦ አዳም እንኳን በደለ አዳም ባይበድል ኖሮ አምላክ ሰው ሆኖ በቀራንዮ ስለእኛ የመሰቀሉን፣ ስለኛ የመሞቱን የፍቅር ምስጢር አናውቀውም ነበር ይላሉ። እስራኤልም በጥጃ ምስል ጣዖት አምልከው እንኳን በደሉ፣ እሥራኤል ባይበድሉ፣ ሙሴ በእግዚአብሔር የተዘጋጁት ሁለቱ ጽላት፣ የሰው ልጅም እግዚአብሔር የሠራቸውን የፊተኞቹን አስመስሎ ለመሥራት ስልጣን ባልኖረውም ነበር፥ ቢሠራም ለምን ሠራህ ለሚለው መረጃ ባላቀረበም ነበር ይላሉ። ያም ሆነ ይህ ጽላትን አስመስለን፣ አባዝተን፣ አራብተን ለመሥራት መሠረታችን፣ ሥልጣኑ ለኛ ለልጆቹ የተላለፈልን ከአባታችን ከሙሴ ነው።

በኢየሩሳሌም ይኖሩ የነበሩ አሕዛብም ሰሎሞን ያሠራው ታላቁ ቤተ መቅደስና ሁለቱ ጽላት አንሰውናል፤ በርቀት የምንገኝ እኛ የመንገድ ድካም በዝቶብናል፥ ስለዚህ በያለንበት ቤተ መቅደስ ሠርተን፣ ጽላቱን አክብረን መገልገል እንፈልጋለን እና ይፈቀድልን ብለው ጠይቀው፣ ከሁለቱ ጽላት በቀር ሌላ አልተፈቀደም ብሎ መልስ የተሰጠበት ቦታ የለም።

ያም ሆነ ይህ በሐዲስ ኪዳንም በአምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምነው በአብ፤ በወልድ፤ በመንፈስ ቅዱስ ስም ተጠምቀው፤ ሁለተኛ የድኅነት ልደት ተወልደው፣ የእግዚአብሔር ልጆች እንዲሆኑ ሥልጣን ሰጣቸው። ለክርስቲያኖችም ከፀሐይ መውጫ እስከ ፀሐይ መግቢያ ድረስ እንደሚበዙና በአዲስ ኪዳን በአምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ንጹሕ የሆነውን ቍርባን ከኢየሩሳሌም ውጭ በየቦታው ለእግዚአብሔር ማቅረብ እንደሚችሉ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል።

ይህ ትንቢት በቀጥታ ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች መሆኑ ግልጥ ነው። ምክንያቱም በብሉይ ኪዳን ቤተ መቅደስም ሆነ የዕጣን፣ የቁርባን አገልግሎት እንኳን ከፀሐይ መውጫ እስከ ፀሐይ መግቢያ ድረስ ላሉ አሕዛብ፣ በኢየሩሳሌም ከሚኖሩ የእግዚአብሔር ሕዝብ በቀር ለእስራኤል ጎረቤት አገሮች እንኳ አልተፈቀደምና። ነቢዩ ሚልክያስ ንጹሕ ዕጣን ያለው በማቴ 2፥11 ወንጌል እንደተናገረው፣ ከአሕዛብ ወገን የሆኑ ሰብአ ሰገል፣ በቤተልሔም ዋሻ ለክርስቶስ ካቀረቡት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በዓለም ያለን ክርስቲያኖች በክርስቶስ ስም ለክርስቶስ የምናቀርበው ቅዱስ ዕጣን ነው።

ንጹሕ ቍርባን የሚለውንም በማቴ 26፥26 ጌታ ኅብስቱን አንሥቶ ነገ የሚቆረሰው ሥጋዬ ይህ ነው፤ ወይኑንም አንሥቶ ነገ ስለብዙዎች ኃጢአት የሚፈስሰው ደሜ ይህ ነው ብሎ ለሐዋርያት የሰጣቸው የክርስቶስ ሥጋና ደም ነው። ንጹሕ የተባለው ርሱ በባሕርዩ ንጹሕ ሆኖ የእኛን የኃጢአት እድፍ ስለሚያነጻ ነው።

በብሉይ ኪዳን በኢየሩሳሌም ብቻ መሆን የሚገባቸው ቤተ መቅደሱ፤ ዕጣኑ፣ ቁርባኑ፣ በክርስቶስ ደም በአዲስ ሕይወት፣ በአዲስ ተፈጥሮ፤ በአዲስ ሥርዓት፣ ክርስቲያኖች ለሆንን ለዓለም ሕዝብ በየሥፍራው (በያለንበት) እንድንጠቀምባቸው ከተፈቀዱልን፣ በኢየሩሳሌም ይኖሩ የነበሩት ሁለቱ ጽላት ከፀሐይ መውጫ እስከ ፀሐይ መግቢያ ተባዝተው በዓለም ያለን ክርስቲያኖች በያለንበት በየቤተ መቅደሳችን ለሥጋውና ለደሙ የክብር ዙፋንነት ብንገለገልባቸውና የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም ብናከብርባቸው ምን የሚጎዳ ነገር ተገኘ? የሚያስደነግጠውስ ምኑ ነው? ስህተቱስ የቱ ላይ ነው?
   
እንዲሁም ኣሥርቱ ትእዛዛት የተጻፉባቸው ሁለቱ ጽላት መባዛት፣ መራባት የለባቸውም ከተባለ፣ በጽላቱ ላይ የተጻፉት ኣሥርቱ ትእዛዛት መባዛት የለባቸውም፣ ከኢየሩሳሌምም መውጣት የለባቸውም ማለት አይደለምን? ትእዛዛቱም ተከለከሉ ማለት ነውና።

በጽላቱ ላይ የተጻፉት ትእዛዛት በእግዚአብሔር ፈቃድ ከፀሐይ መውጫ እስከ ፀሐይ መግቢያ ድረስ በሚገኙ ክርስቲያኖች እጅ ገብተዋል። ይህም ያስደስታል እንጂ አያሳዝንም። ይህ ከሆነ ለሥጋውና ለደሙ (ለክርስቶስ) ክብር ሲባል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚገኙ ጽላት ምን በደል አስከተሉ? እግዚአብሔር ለቀደሙ አባቶቻችን በታቦቱ አድሮ የሠራላቸውን ድንቅ ሥራ እያስታወስን፣ እግዚአብሔርን ከማመስገን ውጭ? ደግሞም ጌታ ስለ ጸሎት ሲያስተምረን አባታችን ሆይ!... በሚለው ጸሎት ውስጥ ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች፣ እንዲሁም በምድር ትሁን... በሉ ብሏል። በዚህ መሠረት፣ በዮሐንስ ራዕይ 11፥19 ላይ ታቦቱን በሰማይ አሳይቶናል። ስለዚህ የሙሴ የቃል ኪዳኑ ታቦት በሰማይ እንዲገኝ፣ በሰማይ እንዲሆን፣ በሰማይ እንዲታይ ፈቃዱ ከሆነ፣ በምድርም እንዲሆን ፈቃድህ ይሁን ብለን ብንጠቀምበት ስህተቱ ምንድን ነው?

ጥያቄ 3፦ የሰሎሞን ቤተ መቅደስ እስኪሠራ ድረስ፣ በርግጥ ታቦቱ ከቦታ ወደ ቦታ ይዘዋወር ነበር፤ ቤተ መቅደሱ ተሠርቶ ታቦቱ ወደ ቤተ መቅደሱ ከገባ በኋላ ግን ካህናቱ ታቦቱን ተሸክመው ስለመውጣታቸው መጽሐፍ ቅዱስ አይናገርም። ታዲያ ዛሬ ክርስቶስ ደሙን ካፈሰሰ በኋላ፣ በብሉይም ሆነ በሐዲስ ኪዳን መመሪያ ሳይኖር፣ ከየት አምጥታችሁ ነው ታቦትን በየጊዜው በማውጣት የክርስቲያኖች ኅሊና ሁሉ ወደተሰቀለው ክርስቶስ መሆኑ ቀርቶ ወደ ታቦቱ የሆነው?

መልስ፦ በብሉይ ኪዳን እንኳን አይወጣም ነበር ማለት አንችልም። ምክንያቱም በችግራቸው ጊዜ ለችግራቸው መፍትሔ ያገኙ ዘንድ ከነበረበት ከድንኳኑም ቢሆን ያወጡት ነበርና ለምሳሌ፦

 

በብሉይ ኪዳን በእግዚአብሔር ቸርነት (ትእዛዝ) ካህናቱ ታቦቱን ተሸክመው እንዲወጡ ተደርጎ ካህናቱም ታቦቱን ተሸክመው በመውጣት በታቦቱ ያደረ ኃይለ እግዚአብሔር ለሕዝበ እስራኤል ያደረገውን ድንቅ ሥራ ለማሰብና እግዚአብሔርን ለማመስገን ነው። ዛሬም ለሥጋና ለደሙ የክብር ዙፋን የሆነውን፣ ቅዱስ ስሙም የተጻፈበትን ቅዱስ ታቦት በምናወጣበት ጊዜ፣ በደሙ የባረከን መድኅነ ዓለም ክርስቶስ አሁንም የሥጋውና የደሙ ዙፋን በሆነው በታቦቱ ረቂቅ ኃይሎች በማስተላለፍ በረከቱን ያበዛልናል ብለን በማመን ነው።

የተሰቀለው አምላክ መክበሩና መንገሡ ቀርቶ በየጊዜው ታቦት ወጣ እየተባለ፣ ታቦቱ ብቻ ነገሠ፣ ከበረ፣ ሕዝቡም ወደ አምልኮ ባዕድ ኮበለለ ስለሚለው ግን አንድ ሕዝብ የንጉሡን ዙፋን ሲያከብርና ሲፈራ ንጉሡን ማክበሩና መፍራቱ እንደሆነ መዘንጋት የለበትም።

እኛ የምናምነው ቅዱስ ስሙ የተጻፈበትን የክርስቶስ ሥጋና ደም፣ የክብር ዙፋን የሆነውን ታቦት ማክበራችን. በኪሩቤል ዙፋን የሚቀመጥ መድኅነ ዓለም ክርስቶስን ማክበራችን መሆኑን ነው። በታቦቱ ፊት መስገዳችንም በታቦቱ ለተጻፈው ለቅዱስ ስሙ ነው። በታቦት ፊት ለእግዚአብሔር ስም ይሰግዱ የነበሩ ኢያሱና የእስራኤል ሽማግሌዎች በረከት አገኙበት እንጂ አልተጎዱበትምና ነው፤ ኢያ 7፥6፣ ዘዳ 33፥10።

በሐዲስ ኪዳንም ድል ለነሣው ስውር መናን እሰጠዋለሁ፤ የብርሃን መጽሐፍንም እሰጠዋለሁ፤ በዚያ መጽሐፍ ውስጥ ላይ ከተቀበለው በቀር ማንም የሚያውቀው የሌለ አዲስ ስም ተጽፎበታል ራዕ 2፥17። ለዚህ ስም ደግሞ ጉልበት ሁሉ መንበርከክ እንደሚገባው መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ ይህም በሰማይና በምድር፣ በቀላያትና ከምድርም በታች ያለ ጉልበት ሁሉ ለኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይሰግድ ዘንድ ነው። አንደበትም ሁሉ ኢየሱስ ክርስቶስ በእግዚአብሔር አብ ክብር፣ ጌታ እንደሆነ ያምን ዘንድ ነው፤ ፊልጵ 2፥10-11። በዚህ መሠረት ቅዱስ ስሙ በተጻፈበት (ከነጭ ድንጋይ፣ ከእብነ በረድ፣ ከእንጨት በተሠራው) በጽላቱ ፊት ለቅዱስ ስሙ መስገድ ታላቅ የመንፈስ ጥበብ እንጂ ሞኝነት አይደለም። ምናልባት ስለታቦት፣ ስለጽላት ባለማወቅ ባጠቃቀሙ በኩል የሚሳሳቱ አባቶችን፣ እናቶችን፣ ወንድሞችንና እህቶችን በተገቢው መንገድ ማስተማር ተገቢ ነው።

ከዚህ በላይ ስለ ታቦት ከቤተ መቅደስ መውጣትና አለመውጣት መፅሐፍ ቅዱሳዊ ከመሆኑም በተጨማሪ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሆኑ መታወቅ አለበት።

ብዙዎች በሐዲስ ኪዳን ታቦትን ለመቃወም በኤር 3፥16 የተጻፈውን ጠቅሰው “በዚያ ዘመን፦ የእስራኤል ቅዱስ፣ እግዚአብሔር፣ የቃል ኪዳኑ ታቦት፣ እነኋት እያሉም በአፋቸውም አይጠሯትም፣ ከእንግዲህ ወዲህ አይሿትም” ተብሏልና ታቦት አያስፈልግም በማለት ያስተምራሉ።

እንደተባለው ታቦት ብሎ መጥራት ካላስፈለገ፣ በኤርምያስ 31፥34 ደግሞ፦ እያንዳንዱ ሰው ባልንጀራውን፣ እያንዳንዱም ወንድሙን፦ እግዚአብሔርን ዕወቅ ብሎ አያስተምርም” ተብሎ ስለተጻፈ፣ እንግዲህ ሰው ሁሉ በየዘመኑ እግዚአብሔርን እንዲያውቅ ማስተማር አያስፈልግም ማለት ነዋ! ደግሞም ጌታችን በማቴ 28፥19 “እንግዲህ ሒዱና በአብ፣ በወልድና፣ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው አሕዛብን ሁሉ አስተምሩ” ብሎ መናገሩ ስህተት መሆኑ ነዋ! በአጠቃላይ እንዲህ ነው ብሎ ከመናገር አስቀድሞ በመጽሐፍ የተጻፈው ነገር ለምንና እንዴት ባለ ሁኔታና ጊዜ መፃፉን ማጥናትና መልእክቱን (ምስጢሩን) መመርመር ይገባል እንላለን።

በመጨረሻ ግን በኢትዮጵያ ኦርቶኮክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የማርያም፣ የቅዱሳን፣ የሰማዕታት፣ የመላዕክት፣ ወዘተርፈ ታቦት እየተባለ የተሰየመበት ምክንያቱና የዚህ ስያሜ ከየት ነው የመጣው? ምንድን ነው? የሚሉ ጥያቄዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ እርግጥ ነው።

እንዲህ ተብሎ መሰየሙ በትንቢተ ኢሳይያስ 56፥46 በተገለጸው መሠረት የእግዚአብሔርን ሰንበቱን ለሚጠብቁ፣ ደስ የሚያሰኘውንም ለሚመርጡ፣ ቃል ኪዳኑንም ለሚይዙ ጃንደረቦች (ስለእግዚአብሔር መንግሥት ራሳቸውን ጃንደረባ ያደረጉ ቅዱሳን) ማቴ 19፥12 በእግዚአብሔር ቤትና በቅጥሩ የዘለዓለም መታሰቢያ እንደሚደረግላቸው የተገለጠ በመሆኑ፣ ይህን አብነት በማድረግ ጌታ ሥጋውና ደሙ የሚከብርበት ሆኖ ለቅዱሳኑም መታሰቢያ ለማድረግ ነው፤ (መዝ 111፥7)። እንዲሁም የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነውና፤ ምሳ 10፥7። በዚህ ምክንያት እንጂ በታቦቱ የሚከብረው መድኃኒተ ዓለም ክርስቶስ መሆኑ ግልጽ ሊሆን ያስፈልጋል። እግዚአብሔር አስተዋይ ልቡና ይስጠን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን።  

አለባበስ

ይኸውም ሁሉን በአግባብና በሥርዓት ስለማድረግ ነው። እህቶቻችን ላይ ማተኮር ያስፈለገው ደግሞ፦ በአብዛኛው በዚህ ረገድ ትችት የሚበዛው በእነርሱ ላይ ስለሆነ ነው። እነሆ ውድድሩ ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረና እየከፋ ነው። ለመልካም ነገር መወዳደር ባልከፋ፣ ነገር ግን በከተማችን በተለይም በዋና ዋና መንገዶች ላይ የምናየው የእህቶቻችን አለባበስ፣ አንዷ ከሌላዋ ልቃና በልጣ ለመታየት የሚደረግ ግብግብ እንደሆነ መገመት አያዳግትም።

እናቶች ይህንን ጊዜ አታሳየን ብለው ሲጸልዩ

በርግጥ እህቶቻችን በዚህ እንደማይስማሙ እናውቃለን፤ አብዛኞቹም ስለተመቸኝና የምወደው ዓይነት አለባበስ ስለሆነ ነው እንዲህ የምለብሰው ይሉናል። ይሁን እንጂ እውነቱ ሌላ ይመስላል ምክንያቱም፦

ዓላማችን ምንም ይሁን ርሱ ላይ የመከራከር ፍላጎት የለንም። ነገር ግን አለባበሳችንን እንደ ክርስቲያን እንፈትሸው ዘንድ ይገባልና መሰልጠን ይሁን ወይስ መሰይጠን? ልንለየው ይገባናል። አብዛኞቹ ሴቶች ይህን ተግባር ስልጣኔ እንጂ ስህተት ነው ብለው አያምኑም። ለእነዚህ ሴቶች ከሃይማኖት ብቻ ሳይሆን ከባሕላችን ጭምር ያፈነገጠውን የምዕራባውያንን አለባበስ መልበስ ዘመናዊነት ነው። ☛ላንቺስ?☚ መጽሐፍ ቅዱስስ ምን ይላል?

ማንኛዋም ሴት የሰውነቷን ቅርፅ የሚያሳይ ወይም ክፍትፍት ልብስ ለብሳ በመሄዷ የሁሉንም ወንዶች ስሜት መፈታተኗ ርግጥ ከመሆኑም በላይ፣ በመንፈሳዊ ሕይወት ደካማ የሆኑትን ደግሞ ለኃጢኣት አጋልጦ ይሰጣል። እዚህ ላይ የተሳሳተው በራሱ ደካማነት ነው ብሎ ምክንያት መስጠት አይቻልም። እግዚአብሔር የሚጠይቀው በማን ተሰናከለ? የሚለውን ጭምር ነውና። በክርስትና ደግሞ ሰውን ማሰናከል እጅግ የከፋ ኃጢኣት ነው። “ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን የሚያሰናክል የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ጥልቅ ባሕር መስጠም ይሻለው ነበር” ማቴ 18፥6።

አንዳንድ ሴቶች እግዚአብሔር ምን ሠራሽ? እንጂ ምን ለበስሽ? አይለኝም፣ ይላሉ። እግዚአብሔር ግን እንዲህ ይላል፦ “እንግዳ ልብስ የሚለብሱትንም ሁሉ እቀጣለው” ትን ሶፎ 1፥18። እንግዲህ የሴቶቹን እንቀበል? ወይስ የእግዚአብሔርን? ምርጫው ያንቺው ነው እህቴ። መፅሐፍ ግን እንዲህ ይላል፦ “ከስው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል” የሐዋ 5፥29። በሴቶችና በወንዶች መካከል የአለባበስ ልዩነት ሊኖር ይገባል። “ሴት የወንድን ልብስ አትልበስ፣ ወንድም የሴትን ልብስ አይልበስ፣ ይህን የሚያደርግ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነው” ዘዳ 22፥5። ታዲያ ቀሚስን የወንድ፣ ሱሪን የሴት ማን አደረገው? ይህ የሰነፍና ለስህተታቸው ምክንያትን የሚሹ ሴቶች የሚያነሱት ጥያቄ ነው። በመጀመሪያ ደረጃ እኛ ኦርቶዶክሳውያን የእግዚአብሔርን ቃል ዓውቀን ልንፈፅመው እንጂ በቃሉ ላይ የምንፍቅና ጥያቄ እናነሳ ዘንድ ተገቢ አይደለም። ግን ደግሞ ተፈጥሯችንን ብቻ በማየት ኅሊናችን ራሱ ቢናገር ሱሪ የሴት ነውን? ቀሚስስ የወንድ ነው እንዴ? “ተፈጥሮ እንኳን አያስተምራችሁምን? 1ኛ ቆሮ 11፥14። “ዳሩ ግን ማንም ሊከራከር ቢፈቅድ እኛ ወይም የእግዚአብሔር አብያተ ክርስቲያናት እንዲህ ያለ ልማድ የለንም” 1ኛ ቆሮ 11፥16። ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው ስህተት መሆኑን መናገር እንጂ መከራከር አያስፈልግም፣ ክርስትና በምርጫ ነውና። “በፊትህ እሳትና ውኃን አኑሬአለው፥ ወደ ወደድኸው እጅህን ክተት” ሲራ 15፥15። ከዚህ ላይ ግን ቀሚስ ሲባል ከውስጥ ሱሪ የማይሻለውን ብጣሽ ጨርቅ እንዲሁም ቁመቱ ረዥም ሆኖ ከሰውነት ጋር የሚጣበቀውን ዓይነት አለባበስ ማለት እንዳልሆነ ልብ እንበል።

እህቶቻችን ሆይ ማስተዋልን ትላበሱ ዘንድ እንለምናችኋለን። መሰልጠንን እና መሰይጠንንም ትለዩ ዘንድ ይሁን። ሰውነትሽ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነውና፣ ሁሉን በአግባብና በሥርዓት አድርጉለት። ደግሞም ክርስትና ራስ ወዳድነትን አብዝታ ትጠላለች፥ ምንም ነገር ስናደርግ ስለ ሌላው ሰው ልናስብ ያስፈልገናል። እኛስ ሰውን ወደ ዝሙት ሊያመራው ስለሚችል አለባበሳችን እጅግ ተጨነቅን፣ ነገር ግን ቅዱስ ጳውሎስ ወንድማችንን ስለማሰናከል ምን አለ? “መብል ወንድሜን የሚያሰናክለው ከሆነ ወንድሜን እንዳላሰናክለው ለዘለዓለም ከቶ ሥጋ አልበላም” 1ኛ ቆሮ 8፥13።

እንግዲህ ክርስትና እዚህ ድረስ ነው፥ ስለራሳችን ብቻ ሳይሆን ስለ ወንድሞችና እህቶች የምናስብባት። ለእነርሱም መሰናከያ እንዳንሆን እየተጠነቀቅን ሁሉን በአግባብና በሥርዓት የምናደርግባት፤ እምነታችንን በምግባር የምንገልጽባት ናት። “በእውኑ ኢትዮጵያዊ መልኩን፣ ነብር ዝንጉርጉርነቱን ይለውጥ ዘንድ ይችላልን? ትን ኤር 13፥27። እህቴ ሆይ አንቺም ኤርምያስ እንዳለው ኢትዮጵያዊነትሽን ጠብቂ። የምዕራባውያን በዓል ከሆነው አለባበስም ሆነ የምንዝር ጌጥ ራስሽን አርቀሽ በሚያኮራው ኢትየጵያዊ ባሕላችን ትዋቢ ዘንድ እግዚአብሔር ይርዳሽ። ስለእውነት አሁን ማን ነው ተጠያቂ፣ የጡት ካንሰር ቢይዘን? አረ እንዲያው ለመሆኑ ስንቶቻችን የጡት ካንሰር፣ የዲስክ መንሸራተት፣ የማኅፀን ካንሰር፣ እንዲሁም ሌሎች የበሽታ ጠንቆች የሚመጡብን በዚህ አለባበሳችን እንደሆነ አስበነው እናውቅ ይሆን?

ለምንድነው ኤዲት የሚደረገው

 ከሉሌ መልአኩ፤ ሦስተኛ እትም - ፲፱፻፹፮ ዓ.ም.




#Article 77: ደራስያን (106 words)


ጸጋዬ ገብረ መድህን
ሃዲስ አለማየሁ
ዳኛቸው ወርቁ
ከበደ ሚካኤል
ብርሃኑ ዘሪሁን
መንግስቱ ለማ
መስፍን ሃብተማርያም
ሙሉጌታ ጉደታ
ማሞ ውድነህ
ስብሃት ገብረ እግዚአብሄር
በዓሉ ግርማ
ሲሳይ ንጉሱ
አቤ ጉበኛ
አዳም ረታ
አረፈዓይኔ ሐጐስ
አበራ ለማ
አማረ ማሞ
አንዳርጌ መስፍን
ጃርሶ ሞትባይኖር ኪሩቤል
ሰርቅ ዳንኤል
ተስፋዬ ገብረአብ
ተስፋዬ ገሰሰ
ኢሳይያስ ልሳኑ

ወርቅ አፈራሁ ከበደ
ዓለማየሁ ማሞ
አፈንዲ ሙተቂ
ሙሉጌታ ሉሌ
ማዕረጉ በዛብህ
ጳውሎስ ኞኞ
አሰፋ ገብረ ማርያም
አጥናፍሰገድ ኪዳኔ
በእውቀቱ ስዩም
ኅሩይ ወልደሥላሴ (ብላቴን ጌታ)
ማኅተመ ሥላሴ ወልደ መስቀል (ብላቴን ጌታ)
ተክለ ሐዋርያት ተክለ ማርያም (ፊታውራሪ )
ማሞ ለማ (ሻለቃ )
አፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ
እንዳለጌታ ከበደ
ኃይሉ ገብረዮሐንስ (ገሞራው)
አለቃ ገብረሃና ገብረማሪያም
አርአያ ጌታሁን ተክለአቢብ

ማትያስ ከተማ (ወለላዬ)




#Article 78: ቤኒን (251 words)


ቤኒን ወይም በይፋ የቤኒን ሪፐብሊክ በምዕራብ አፍሪካ የምትገኝ ሀገር ናት። ከምዕራብ ቶጎን፣ ከምሥራቅ ናይጄሪያን እና ከሰሜን ቡርኪና ፋሶና ኒጄርን ትዋሰናለች። ዋና ከተማዋ ፖርቶ ኖቮ ሲሆን የመንግሥቷ መቀመጫ ግን ኮቶኑ ከተማ ናት። የቤኒን የቆዳ ስፋት ወደ 110,000 ካሬ ኪ.ሜ. ሲሆን የሕዝቧ ብዛት ደግሞ ወደ 9.05 ሚሊዮን ይገመታል።

የቤኒን ይፋ ቋንቋ ፈረንሳይኛ ሲሆን እንደ ፎንና ዮሩባ የመሳሰሉት የሀገሪቷ ባህላዊ ቋንቋዎች ሰፊ ተናጋሪ አላቸው። የሮማ ካቶሊክ ክርስትና ብዙ ተከታዮች ሲኖሩት እስላሞች፣ ፕሮቴስታኖችና የቩዱ ተከታዮችም ይገኛሉ። ቤኒን የተባበሩት መንግሥታት፣ የአፍሪካ ሕብረት እናም ሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶች አባል ናት።

ከ17ኛው እስከ 19ኛው ክፍለ ዘመን እ.ኤ.አ. የሀገሪቱ መሬት በዳሆሚ መንግሥት ነበር የሚመራው። በ17ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ የአትላንቲክ የባሪያ ንግድ በአካባቢው ሰፍቶ ስለነበር ቦታው የባሪያ ጠረፍ ይባል ነበር። በ1892 እ.ኤ.አ. ፈረንሳይ አካባቢውን በመቆጣጠር የፈረንሳይ ዳሆሚ ብላ ሰየመችው። በ1960 እ.ኤ.አ. ዳሆሚ ነፃነቷን በማግኘት ለ፲፪ ዓመታት በዴሞክራሲያዊ መንግሥት ተመርታለች።

ከ1972 እስከ 1990 እ.ኤ.አ. ሀገሪቷ በማርክሲስት ሌኒኒስት አቋም የቤኒን ሕዝባዊ ሪፐብሊክ ተብላ ተሰመች። በዚህ ጊዜ በሀገሪቷ የኢኮኖሚ ውድቀት ተከስቶ ነበር። በ1991 እ.ኤ.አ. የቤኒን ሪፐብሊክ ተመሠረተ።

ቤኒን ወደ ውጭ የሚልከው ዋንኛ ምርት ጥጥ ሲሆን ከዚህ በላይ ካሸው ለውዝ (Anacardium occidentale)፣ ኮኮነት፣ ዓሳ፣ እንጨት ወደ ውጭ ይላካሉ። ፔትሮሊየምና ወርቅም ይላካሉ። ባለፉት ዓመታት ውስጥ ቤኒን ለተግባራዊ ሳይንስ ምርመራ ጥናት አንጋፋ ማዕከል ሆናለች። 

በደቡብ ቤኒን ባሕላዊ አበሳሰል፣ በተለይ የበቆሎ ዳቦ በኦቾሎኒ ወጥ ወይም በቲማቲም ወጥ ይጠቀማል። አሳ እና ዶሮ ከሁሉ ተራ ሥጋዎች ናቸው፣ በሬ፣ ፍየልና የጫካ አይጥ ደግሞ ይበላሉ።  በስሜን ቤኒን ባሕላዊ አበሳሰል፣ በተለይ ኮቴሃሬ በበቆሎው ፈንታ ይጠቀማል።  ቤሬ ወይም አሳማ በጥብስ ወይም በወጣወጥ፣ ፎርማጆ፣ ኩስኩስ፣ ሩዝ፣ ባቄላ፣ ፍራፍሬ በሰፊው ይጠቀማሉ።  

እግር ኳስ ከሁሉ የሚወድ እስፖርት ሲሆን፣ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ቤስቦል ወደ ቤኒን ገብቷል። 




#Article 79: ፍትሐ ነገሥት (271 words)


ፍትሐ ነገሥት  በ1240 አካባቢ በግብጽ አገር ቅብጡ አቡል ፋዳዒል እብን አል-አሣል በአረብኛ የጻፉት ሕገ መንግሥት ነው። እብን አል-አሣል ሕጎቹን የወሰዱት በከፊል ከሃዋርያት ጽህፈቶችና በከፊል ደግሞ ከድሮ ቢዛንታይን ነገስታት ሕጎች ነበር። 

አንደኛው ክፍል ስለ ቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች ሲሆን የቤተክርስቲያን ስነሥርዐትና ምስጢራትን ይገልጻል። የተለቀሙት መጻሕፍት መጽሐፍ ቅዱስ የአበው ለምሳሌ የአቡሊድስና የባስሌዮስ ጽሕፈቶችና በኒቂያ ጉባኤ ወይም አንጥያኮስ ጉባኤ የተወሰኑ ሥርዓቶች ናቸው።

ሁለተኛው ክፍል ተራ ምዕመናንን (ካህን ያልሆኑ) የሚነካ ጉዳይ ያስረዳል፣ ይህም ማለት የቤተሠብ፣ የእዳና የብሔራዊ አስተዳደር የመሳሰሉትን ሕገጋት ያጠቃልላል። ይህ ክፍል ደግሞ እላይ ከተጠቀሱት ምንጮች ቢለቀምም ሌሎቹ በብዛት የተጠቀሙት መጻሕፍት «4 የነገስታት ቀኖና» የተባሉት ናቸው። አንዳንድ ሊቃውንት እነዚህን መጻሕፍት በአርእስት አሳውቀዋል:-

ከነዚህ መሃል ሦስቱ ምንጮች የባይዛንስ ንጉስ የዩስጢኒያኖስ ሕገ መንግሥት ጽኑ ተጽኖ ስላላቸው የእብን-አሣል ሥራ በተለይ እንደ ሮማ ሕጎች ይመስላል። መጀመርያ «የቀኖና ክምችት» ተባሎ ዛሬ የአረብኛ እትም «የእብን አል-አሣል ቀኖና» ይባላል። ሲጽፉት ለቅብጦች ጥቅም እንዲህን አስበው እነሱም ትልቅ ሥልጣን እንዳለው ሰነድ አከበሩት።

መጽሐፉ በግዕዝ ተተርጉሞ ወደ ኢትዮጵያ የገባበት ወቅት በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመን በ1450 ዓ.ም. አከባቢ እንደነበር የሚል ታሪካዊ መዝገብ አለ። ቢሆንም መጀመርያ እንደ ሕገ ምንግሥት መጠቀሙን የተመዘገበው በዓፄ ሠርፀ ድንግል ዘመን (ከ1555 ዓ.ም. ጀምሮ) ነው። 

የግእዝ ትርጉም በጴጥሮስ አብዳ ሳዒድ ስም ተደርጎ ለአረብኛው ሁልጊዜ ትክክለኛ አልነበረም፣ በአንዳንድም ስፍራ ቋንቋው ለአስተርጓሚው ሲያስቸግራቸው በፍጹም የተለየ ንባብ ይሰጣል። መጀመርያው ክፍል (ቤተክርስቲያን የሚነካ) ከዚህ በፊት ሲኖዶስ ተብሎ በኢትዮጵያ እንደታወቀ ሊቃውንት ገልጸዋል። ሁለተኛው ክፍል ብቻ ለኢትዮጵያ አዲስ ስለሆነ ስሙ «ፍትሐ ነገስት» የተወሰደው ከዚሁ ክፍል ነበር ይላሉ። 

ፍትሐ ነገስት እስከ 1923 ዓ.ም. የብሄሩን ዋና ሕግ ሆኖ ቆየ። ያንጊዜ ዘመናዊ ሕገ መንግሥት በአጼ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የታወጀ ቢሆንም ቀድሞ በ1922 ዓ.ም. በፍትሐ ነገሥት መሠረት አዲስ የወንጀል ሕግ ተሰጠ። ደግሞ በ1914 ዓ.ም. ንጉሥ ሳይሆኑ እንደራሴ በሆኑበት ወቅት በፍትሐ ነገስት የተገኙት ጨካኝ ቅጣቶች ሁሉ (ለምሳሌ ለስርቆት እጅ መቆረጥ) ፈጽሞ እንዲተዉ አስደርገው ነበር።




#Article 80: መንግስቱ ኃይለ ማርያም (887 words)


ይህን ታሪክ የጸፍው ግለሰብ የመንግስት ሀይለማሪያ ቀንደኛ ደጋፊ እንደሆነ ከፁሁፉ አንጸር መርዳት አያዳግትም
 ትክክለኛውን ታሪክ ከምንጭ ጋር እንደሚያስተካክልው ተስፍ አደርጋለሁ።

መንግስቱ ኃይለማሪያም በግንቦት 27 በ1941 እ.ኤ.አ. በአዲስ አበባ ተወለዱ። አባታቸው ሃምሳዓለቃ ሃይለማሪአም ወልዴ፣ እናታቸው ብዙነሽ ተሰማ ነበሩ የአሁኑ መንግስት እና ብዙ የምእራባውያን መንግስታት እሱን እንደ ኮሚኒስት ተኮር አምባገነን አድርገው የሚቆጥሩት ሲሆን የቀድሞው አምባገነን ሮበርት ሙጋቤ የጥገኝነት ጥያቄውን ከተቀበሉ ወዲህ ወደዚምባብዌ ተሰዷል ፡፡ 

ምንም እንኳን መንግስት እንደዚህ ያሉ ክሶችን በተደጋጋሚ ቢክድም በ 2006 (2008) በኢትዮጵያ አዲስ አበባ ፍ / ቤት በዘር ማጥፋት ወንጀል ተከሷል ፡፡ ሆኖም በሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል እንዲከሰስ በሄግ አልተከሰሰም ፡፡

ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለ ማርያም' ከ1966 እስከ 1983 ዓ.ም. (1974 እስከ 1991 እ.ኤ.አ.) ለ17 ዓመታት የኢትዮጵያ መሪ ነበሩ። ወደ ስልጣን የወጡት በደርግ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ንጉሠ ነገሥቱን ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን በመገልበጥ ሲሆን የአብዮቱ መሪ ሆነው ከቆዩ በኋላ በመለስ ዜናዊ በሚመራው በኢሓዴግ ሽምቅ ተዋጊ ቡድን እና በአሜሪካው የቀድሞው የሲአይኤ ዳሪክተር ሃርማንኮህ እርዳታ በ1983ዓ.ም ከስልጣን ተወገዱ። በአሁኑ የሀገሩ መንግስት እና በአብዛኞቹ የምዕራባውያን አገራት የኮሚኒስት አምባገነን ተደርጎ ፣ 
  ይህ መፈንቅለመንግስት በሲአይኤ ስውር ዘዴ የተከናወነ ሲሆን የህወሓትና የሻእብያው መሪ ከሱዳን በቦይን 777 ከቀድሞው ከሲአይኤ ዳሪክተር ከ ሃርማንኮህ ጋር ታጅበው አዲስ አበባ ገብተዋል።   ይህነው የኮሎኔል መንግሰቱ ኃይለማርያም የመንግሰቱ ግልበጣ ሳቦታጅ!! መንግስቱ ኃይለማርያም ያላሰበው ግልበጣ ተቀናብሮበት ያለአማራጭ በአየርላይ ቀረ እንጂ በራሱ ፍላጎት ሸሽቶ ዚምቡዋቤ ተሸሸገ የሚለው አባባል ከእውነት የራቀነው።   ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም በቃላቸው የሚገኙ አገር ወዳድ ጀግና ሰው እንደነበሩ እናውቃለን።
መንግሥቱ ኃይለማሪያም ወደ ርዕሰ ብሄርነት ሥልጣን ብቅ ሲሉ ገና የ፫፯ ዓመት ወጣት የነበሩ ሲሆኑ በሀረር የ3ኛ ክፍለ ጦር የመሳሪያ ግምጃ ቤት ውስጥ ይሰሩ ነበር። በወቅቱ በክፍለ ጦሩ አዛዥ የነበሩት ጀነራል ሓይሌ ባይከዳኝ የሚባሉ ኮ/ መንግስቱን በባህሪያቸው በመጠርጠራቸው ከአጠገባቸው ዞር ለማድረግ ወደ ኦጋዲን አዛውረዋቸው እንደ ነበር ይነገራል። በእዚያም ጥቂት ጊዜ በኋላ ለትምህርት ወደ አሚሪካ ሜሪላንድ ለወታደራዊ ሳይንስ ትምህርት ተላኩ። 
ከትምህርት ሲመለሱም በ3ኛ ክፍለ ጦር የመሳሪያ ግምጃ ቤት ሃላፊ ሆነው ተሾሙ። 
ከዛም በደረጃ እድገት ካገኙ በሁዋላ የአፄ ኃይለስላሴን ጨቋኝ አገዛዝ ለመገርሰስ የደርግ ኩዴታን መሰረቱ በመኮንኖች ህብረት የተመሰረተው ደርግ በአብዛኛው ተደማጭነትና የፓለቲካ ብስለት በነበራቸው በቆራጥነታቸው ታዋቂ በሆኑት በመንግስቱ ኃይለማርያም ስልታዊ አደረጃጀት ተቀናብሮ የንጉሱን ወንበር ገለበጡት ይህ በሆነ ወቅት በነበረው አለመረጋጋት በከተማው የተኩስ ልውውጥ ተደረጎነበር።
የመጀመርያውን ስልጣን በመያዝ የደርግ ሊቀመንበር ሆነው የተሾሙት ጀኔራል አማን አምዶም ነበሩ።
   በተለያየ አመታት በተለያየ ክህደትና አሻጥር የተገኙ አመራሮች ከስልጣን ሲወገዱ ቆይተው በአራ0ተኛው ዙር ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም የኢትዮጵያ የመጀመርያው ፕሬዚዳንት ለመሆን በቅተዋል። 
ወደ ስልጣን በመጡ ማግስት ሶማሊያየዚያድባሬ መንግስት በሶቭየቶች ተደግፋ ሀገራችንን ድንገት ወረረች። በወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ነበሩትን ፕሬዚዳንት ጂሚ ካርተርን ፈጣን ወታደራዊ እርዳታ ጠይቀው እሳቸውም የንጉሱ የቅርብ ወዳጅ ስለነበሩ በስዊስ ባንክ ያለውን የኢትዮጵያ ሃብት ለመንግስቱ ኃይለማርያም ከሰለመስጠት በተደረገው ውይይት የአሜሪካ እጅ ስለነበረበት መንግስቱ ነጮችን በ73 ሰአት ውስጥ ኢትዮጵያን ለቀው እንዲወጡ አድርጎ ስለነበር በዚህ ቂም ጥያቄውን ሳይቀበሉ ቀሩ። በእዚህም ምክንያት አማራጭ ያጣው ደርግና መንግሥቱ ሀገሪቱ በከፍተኛ ስጋት ላይ በመውደቋ የግድ ወደ ሞስኮ መሳሪያ ልመና ልኡካን ላኩ። በሌላ በኩል ሞስኮ ከሶማሊያ ጋር ጥቅምዋን በማወዳደር ለመንግስቱ መሳሪያ መስጠት ካስፈለገ በፊርማ ሶሻሊስት ካምፐ መግባቱን እንዲያረጋግጡ ስለ ጠየቀች ኮ/መንግሥቱ ይህን በማድረጋቸው በይፋ የሚመሩት አብዩት የሌኒኒስት ማርክሲስት መሆኑን በአዋጅ አሳወቁ። ኮ/መንግሥቱ የቼጉቬራና የሶቬቱን ማርክሲዝም አሜሪካ ለወታደራዊ ሳይንስ ትምህርት በተላኩበት ዘመን ትምህርታቸውን አጠናቀው ወደ ሃር ሳይመለሱ ወደ ሞስኮ በማምራት የራሻን ሶሻሊዝም በግላቸው ተምረው ነበር፣ወደ አገር ሲመለሱም ንጉሱ በዚህ ድርጊታቸው ለሁለት አመት በኦጋዴን በረሃ በቅጣት እንዲቆዩ ተደርጎነበር።  የመንግስቱ ስለሶቪየት ሶሸሰሊዝም ፖለቲካ እውቀት የሚያውቁት የቅርብ መኮንኖች በደርግ ኩዴታው የነቃውንና ብስለት ያለውን ደፋሩን መንግስቱ ኃይለማረወያምን ነበር በአደራጅነት የመደቡት። 
ከስምምነቱም በሁዋላ በ፪ ወር ጊዜ ውስጥ የብዙ ሚሊዮን ዶላር ታንክና የጦር መሣሪያ እርዳታ ማግኘት ብቻ ሳይሆን በሞስኮ በኩል የኩባን የጦር አማካሪዎች በማግኘታቸው የወራሪውን የሶማሊያን ኃይል መመከት ችለዋል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አሜሪካ የጭንቅ ጊዜ ጥያቄ መላሽ ሆና ባለመገኘትዋና በንጉሱ ስም በስዊስ ባንክ የተቀመጠውን በትሪሊዮን የሚቆጠር ዶላርና ወርቅ የስዊስ ባንክ ለኢትዮጵያ መንግስት እንድትመልስ መንግስቱ ኃይለማረወያም ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ በማድረጓ የአሜሪካ ትብብር በመኖሩ ምክንያት መንግስቱ ኃይለማርያም በስልጣን እስከቆዩበት ዘመን ሁሉ በዋና ጠላትነት ተፈርጀዋል። አንዳንድ ሚሲዮናዊያንንም ከአገር አባረሩ። በንጉስ ኃይለስላሴ ፊርማ በስዊስባንክ የነበረው የኢትዮጵያ ሃብት እስካሁን አልተመለሰም።  አብይ አህመድ ይህን የመጠየቅ ወኔ የለውም፣ምፅዋእት ከመለመን በቀር።
 በወቅቱ በአገር ውስጥ ግንባር ቀደም ተቃናቃኝና ተቃዋሚ ከነበረው ከኢህአፓ ጋር የከተማ ለከተማ ውጊያና መገዳደል ተጀመረ። ሁለቱም ወገኖች ቀን በቀን ግድያም ለብዙ ወጣትና አዋቂ እልቂት ምክንያት ሆኑ። 
መንግሥቱ ኃ/ማሪያም በወታደራዊ አመራር ውስጥ የተከስተው የስልጣን ዝቀጠትና ምግባረ ብልሹነት፤ የደህንነቱ ክፍል በሁለት ቢላዋ መብላት፣ ተደማምሮ ውድቀታቸውን እንዳፋጠነው የፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ።
የመንግስቱን አስተዳደር ለውድቀት ያበቃው የኮሎኔሉ አምባገነን አመራር ነው የሚሉት ተቀናቃኞቻቸውና በሁለት ቢለዋ እየበሉ አገርን ለመሸጥ ያስማሙ የነበሩ በወቅቱ  (በመኢሶን) ውስጥ ተሰግስገው የነበሩ የኦነግ ስውር ባንዳ መኮንኖችና የ(TPLF) እና የ (EPLF) ሰላዮችና አገር በሆድና በስልጣን የሸጡ የመንግስቱ ተቀናቃኞች መረጃን አሾልኮ ለተቃዋሚ ኃይሎች አሳክፎ በመስጠት እንደሆነ ይታወቃል።
በመንግስቱ ኃይለማርያምላይ የተቀነባበረ የ 16 ግዜ የመግደል ሙከራ ተደርጎባቸው አምልጠዋል።
ጠላቶቻቸው ከውስጥና ከውጭ ብዙ ስለነበሩ ለ17 አመታት ቀንና ሌሊት ሲዋጉ አገርን በልማት በምርት ዘመቻ፣በትምህርትዘመቻ፣እንዲሁም ስራአጥነትንና ሴተኛ አዳሪነትን ለማስወገድ የኢንዱስትሪ ስራዎችን በመክፈትና በማስፋፋት መሬትን ለአራሹ በመሰከፋፈል፣ ለደሃው ህዝብ ርካሽ የቤትክራይን በመደንገግ፣ለአገራቸው ከፍተኛ አገልግሎት ያበረከቱ ታላቅ መሪናቸው።   ይህን በጎ ተግባራቸውን ለመናገር የሚያንቃቸው የግል ጥቅማቸውን ከአገር ጥቅም ይልቅ አብልጠው የሚወዱ ተቀናቃኝ ሰዎች ብቻ ናቸው።
መንግሥቱ (የቀድሞው)  ርዕሰ ብሔር ማንኛውም መሪ ላይ ሊከሰት የሚችል ስህተት ነው የፈፀሙት...ስለ ሐገር ስለ ብሔራዊ ክብር እና ኩራት ግን እርሳቸው ! ከፊት ቢሠለፉ የሚገባቸውና የሚያምርባቸው ናቸው።
አብይ አህመድ አሊ 
ካልሰራ ሊተች ይገባዋል እሱ ከማ በልጦ ነው ሲቀጥል ደሞ በጥላቻ ስሜት መንግስቱን ጭራቅ አስመስሎ ማቅረብ ደስ አይልም፣ እንኩዋን መንግስቱ ሂትለርም የሰራቸው ጥሩ ስራዎች አሉት። ሲጀመር እናንተ መንግስቱን ለመተቸት ብቁ አደላችሁም ዝም ብለው ከሚፈነጩት ውስጥ ናችሁ አንብቡ በደንብ ከዛ ትፅፋላችሁ ሳያነቡና ታሪክን ሳያገላብጡ ወተት እንደጠገበች ጥጃ መፈንጨት መጨረሻው ገደል ነው!
ጠ / ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ  የተነሳውን ፎቶግራፍ ከወሰዱ በኋላ ብዙም ሳይቆይ በማኅበራዊ ሚዲያ  ላይ ፎቶግራፍ በመለጠፍ ተተቸ ፡፡
 የኮሎኔል መንግስቱን ህይወት ተቀጥፋ ለማየት የጓጉና የፎከሩ ሁሉ ቀድመዋቸው ሞተዋል!!
    የእድሜ በለፀጋው ጓድ ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም የሦስት ልጆች አባት ሲሆኑ 3ስቱም ልጆቻቸው ዶክተሮች ናቸው። ዛሬ የ 83 አመት አዛውንት ሆነው በሃራሬ በህይወት ይገኛሉ። 




#Article 81: አልፍ (219 words)


 አ ኡ ኢ ኣ ኤ እ ኦ ኧ 

አልፍ (ወይም አሌፍ) በአቡጊዳ ተራ መጀመርያው ፊደል ነው። እንዲሁም በከነዓን በአራማያ በዕብራይስጥና በሶርያ ፊደሎች መጀመርያው ፊደል አሌፍ ይባላል።  በዓረብኛ ፊደል ደግሞ መጀመርያው ፊደል አሊፍ ሲሆን በግሪክም አልፋ ይባላል።

በመጀመርያ በግዕዝ የዚህ ምልክት ምክንያት ተፈናጣሪ ተናባቢ ድምጽ ለማመልከት ነበር። ይህ ድምጽ ፍች «ነዛሪ የጉሮሮ እግድ» ይባላል። በዛሬው አማርኛ ግን ምንም ተናባቢ ሳይኖር አናባቢ ብቻ ሊያመለከት ይችላል።  (በዘመናዊ ዕብራይስጥም «አሌፍ» እንዲህ ይጠቅማል።)  በዚህ ጥቅም በአማርኛ አጻጻፍ ብዙ ጊዜ ከዐይን (ዐ) ጋራ ሊለዋውጥ ይችላል።

በአረብኛ ደግሞ «አሊፍ» ከጥንት ተፈናጣሪ ተናባቢ ድምጽ ነበር። በኋላ ግን 'አ' የሚለውን አናባቢ ብቻ ሊያመልከት መጣ። ስለዚህ ነዛሪ የጉሮሮ እግድ ለመጻፍ ሌላ አዲስ ፊደል «ኅምዛ» ተፈጠረ። 

በመጀመርያው (ግዕዝ) ቅርጽ (አ) በልሳነ ግዕዝ እንደ ሌሎቹ ፊደላት የ«ኸ» አናባቢ ድምጽ ሆነው ነበር፤ በአማርኛ ግን ድምጹ እንደ አራተኛው (ራብዕ) ቅርጽ (ኣ) አንድላይ ነው።  ቢሆንም አንዳንዴ በባዕድ ቃላት ይህ አናባቢ በቃል መጀመርያ ሲጋጠም «ኧ» የሚለው ልዩ ፊደል አለ።

የአልፍ መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት እንደ ሆነ ይታስባል።  በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ የበሬ ራስ ስዕል መስለ።  በዘመናዊ ዕብራይስጥም እስካሁን «አሉፍ» ማለት «ከብት» ማለት ነው። ለዚህም ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ «ኢሕ» ነበር።

የከነዓን «አሌፍ» እንዲሁም ከዚህ ምልክት ተወስዶ በዚያ መንገድ የዕብራይስጥና የአራማያ «አሌፍ» የአረብኛም «አሊፍ» ወለደ። ከዚህ በላይ የግሪክ አልፋቤት «አልፋ» (Α α) አባት ሆነ, እሱም የላቲን አልፋቤት (A a) ወላጅ ሆነ። ስለዚህ እነዚህ ሁሉ የአልፍ ሩቅ ዘመዶች ሊባሉ ይቻላል። በተጨማሪ የግዕዝ ቁጥር ፩ ከግሪኩ α በመወሰዱ የ«አ» ዘመድ ነው።




#Article 82: ቤት (ፊደል) (174 words)


 በ ቡ ቢ ባ ቤ ብ ቦ ቧ 

ቤት በአቡጊዳ ተራ ሁለተኛው ፊደል ነው። እንዲሁም በከነዓን በአራማያ በዕብራይስጥ በሶርያና በዓረብኛ ፊደሎች ሁለተኛው ፊደል «ቤት» ይባላል።  በግሪክም ሁለተኛው ፊደል «ቤታ» ይባላል።

በቋንቋ ጥናት የዚሁ ድምፅ ፍች «ነዛሪ የከናፍር ፈንጂ» ይባላል። በዕብራይስጥ አንድ ነጥብ በመሃል ውስጥ ሲኖር (#64305;) ድምጹ እንደ «ብ» ቢመስልም ያለዚያ ነጥብ ግን (ב) እንደ «ቭ» ይሰማል።  ለዚያም ደግሞ በአማርኛ ይህ ድምጽ «ቨ ቩ ቪ ቫ ቬ ቭ ቮ» በተለይ በባዕድ ቃላት ሲጋጠም ከ«በ...» ትንሽ ተቀይሯል።

የቤት መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት እንደ ሆነ ይታስባል።  በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ የመኖርያ ቤት ስዕል መስለ።  ለዚህም ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ ነበር፤ አጠራሩ ግን «ፐር» ነበር። (ይህም ቃል በ«ፈርዖን» ስም ይታያል።) በግብፅ የሠሩት ሴማውያን ግን በቋንቋቸው «ቤት.. ስላሉት፣ ይህ ስዕል «ብ.. ሆኖ እንዲሰማ መጣ።

የከነዓን «ቤት» እንዲሁም ከዚህ ምልክት ተወስዶ በዚያ መንገድ የዕብራይስጥና የአራማያ የአረብኛም «ቤት» ወለደ። ከዚህ በላይ የግሪክ አልፋቤት «ቤታ.. (Β β) አባት ሆነ፤ እሱም የላቲን አልፋቤት (B b) እና የቂርሎስ አልፋቤት (Б, б) እና (В, в) ወላጅ ሆነ። ስለዚህ እነዚህ ሁሉ የ«ቤት» ሩቅ ዘመዶች ሊባሉ ይቻላል። በተጨማሪ የግዕዝ ቁጥር  ፪  (ሁለት) ከግሪኩ β በመወሰዱ እሱም የ«በ» ዘመድ ነው።




#Article 83: ገምል (168 words)


 ገ ጉ ጊ ጋ ጌ ግ ጎ ጓ ጐ ጒ 

ገምል በአቡጊዳ ተራ ሦስተኛው ፊደል ነው። እንዲሁም በከነዓን በአራማያና በዕብራይስጥ ፊደሎች ሦስተኛው ፊደል «ግመል» በሶርያም ፊደል «ገመል» ይባላል። በዓረብኛ ደግሞ ተመሳሳይ ፊደል «ጂም» ተብሎ በ«አብጃድ» ተራ 3ኛ ነው። (በዘመናዊ ተራ ግን 5ኛው ነው።) በግሪክም 3ኛው ፊደል «ጋማ» ይባላል። በነዚህ ቋንቋዎች አጠራሩ «ግ» ሲሆን በዓረብኛ ግን «ጅ» ሆኗል።

የ«ግ» ድምጽ በቋንቋ ጥናት «ነዛሪ የትናጋ ፈንጂ» ይባላል።

የገምል መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት እንደ ሆነ ይታስባል።  በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ «የሚጣል ምርኩዝ» ስዕል መስለ።  ለዚህም ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ ነበር፤ አጠራሩ ግን «ቀመእ» ነበር።  በግብፅ የሠሩት ሴማውያን ግን በቋንቋቸው «ገምል» ስላሉት፣ ይህ ስዕል «ግ» ሆኖ እንዲሰማ መጣ። «ግመል»  ደግሞ የእንስሳ አይነት ሊሆን ይችላል።

የከነዓን «ግመል» እንዲሁም ከዚህ ምልክት ተወስዶ በዚያ መንገድ የዕብራይስጥና የአራማያ «ግመል» የአረብኛም «ጂም» ወለደ። ከዚህ በላይ የግሪክ አልፋቤት «ጋማ» (Γ γ) አባት ሆነ፤ እሱም የላቲን አልፋቤት (C c) , (G g) እና የቂርሎስ አልፋቤት (Г, г) እና (Ґ, ґ) ወላጅ ሆነ። ስለዚህ እነዚህ ሁሉ የ«ገምል» ሩቅ ዘመዶች ሊባሉ ይቻላል። በተጨማሪ የግዕዝ ቁጥር  ፫  (ሦስት) ከግሪኩ Γ በመወሰዱ እሱም የ«ገ» ዘመድ ነው።




#Article 84: ሆይ (135 words)


 ሀ ሁ ሂ ሃ ሄ ህ ሆ 

ሆይ (ወይም ሀውይ) በአቡጊዳ ተራ አምስተኛው ፊደል ነው። እንዲሁም በከነዓን፣  በአራማያ፣ በዕብራይስጥ እና በሶርያም ፊደሎች አምስተኛው ፊደል «ሄ» ይባላል።

በዓረብኛ ደግሞ ተመሳሳይ ፊደል «ሃእ» ተብሎ በ«አብጃድ» ተራ 5ኛ ነው።  በግሪክ አምስተኛው ፊደል «ኧፕሲሎን» ይባላል። በነዚህ ቋንቋዎች አጠራሩ «ህ» (ተናባቢ) ሲሆን በግሪክ ግን አናባቢ («ኧ») ሆኗል።

በመጀመርያው (ግዕዝ) ቅርጽ (ሀ) በልሳነ ግዕዝ እንደ ሌሎቹ ፊደላት የ«ኸ» አናባቢ ድምጽ ሆነው ነበር፤ በአማርኛ ግን ድምጹ እንደ አራተኛው (ራብዕ) ቅርጽ (ሃ) አንድላይ ነው። ይህ ስህተት እየታረመ ነው።

በአማርኛ አጻጻፍ ብዙ ጊዜ ከሐውት (ሐ) ከኀርም (ኀ) እና ከኻፍ (ኸ) ጋራ ሊለዋውጥ ይችላል። ቀድሞ ግን ድምጾቻቸው የተለያዩ ነበሩ።

የሆይ መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት እንደ ሆነ ይታስባል።  በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ የሚደሰት ሰው ስዕል መስለ።  ለዚህም ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ ነበር፤ አጠራሩ ግን «ቀእ» ነበር። በግብፅ የሠሩት ሴማውያን ግን በቋንቋቸው «ሄ» ስላሉት፣ ይህ ስዕል «ህ» ሆኖ እንዲሰማ መጣ።




#Article 85: ዋዌ (118 words)


 ወ ዉ ዊ ዋ ዌ ው ዎ 

ዋዌ (ወይም ዋው፣ ወዌ) በአቡጊዳ ተራ ስድስተኛው ፊደል ነው። እንዲሁም በከነዓን በአራማያ በዕብራይስጥና በሶርያ ፊደሎች ስድስተኛው ፊደል «ዋው» ይባላል።  በዓረብኛ ደግሞ «ዋው» በ«አብጃድ» ተራ 6ኛ ነው። (በዘመናዊ ተራ ግን 27ኛው ነው።)

በዘመናዊ ዕብራይስጥ «ዋው» (ו) ተናባቢ ሲሆን እንደ «ቭ» ይሰማል።  አናባቢ ሲሆን ግን «ኡ» ወይም «ኦ» ያመለክታል።

የዋዌ መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት እንደ ሆነ ይታስባል።  በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ የበትር ስዕል መስለ።  ለዚህም ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ «ሐጅ» ነበር። 

የከነዓን «ዋው» እንዲሁም ከዚህ ምልክት ተወስዶ በዚያ መንገድ የዕብራይስጥና የአራማያ የአረብኛም «ዋው» ወለደ። 

ከዚህ በላይ የከነዓን «ዋው» የግሪክ አልፋቤት «ዲጋማ» («ዋው») () አባት ሆነ፤ የ«ው» ድምጽ ግን ቀድሞ ከቋንቋው ጠፍቶ ዲጋማ እንደ ቁጥር ብቻ ጠቀመ። (ደግሞ ስቲግማ ይዩ።) በላቲን አልፋቤት ግን (F f) ከዲጋማ ተነሣ። 




#Article 86: ሐውት (118 words)


 ሐ ሑ ሒ ሓ ሔ ሕ ሖ ሗ

ሐውት ወይም በአነጋገር ሐመረ ሐ በአቡጊዳ ተራ ስምንተኛው ፊደል ነው። እንዲሁም በከነዓን በአራማያ በዕብራይስጥ በሶርያም ፊደሎች ስምንተኛው ፊደል ሔት ይባላል።

በዓረብኛ ደግሞ ተመሳሳይ ፊደል ሐእ (ح) ተብሎ በአብጃድ ተራ 8ኛ ነው። ኀእ የሚለው አረብኛ ፊደል (ﺥ) ደግሞ ከዚያ ወጣ።

በመጀመርያው (ግዕዝ) ቅርጽ (ሐ) በልሳነ ግዕዝ እንደ ሌሎቹ ፊደላት የኸ አናባቢ ድምጽ ሆነው ነበር፤ በአማርኛ ግን ድምጹ እንደ አራተኛው (ራብዕ) ቅርጽ (ሓ) አንድላይ ነው።

በአማርኛ አጻጻፍ ብዙ ጊዜ ከሆይ (ሀ) ከኀርም (ኀ) እና ከኻፍ (ኸ) ጋራ ሊለዋውጥ ይችላል። ቀድሞ ግን ድምጾቻቸው የተለያዩ ነበሩ።

የሐውት መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት እንደ ሆነ ይታስባል።  በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ የአጥር ስዕል መስለ።  ለዚህም ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ ሰፐአት ነበር። በሌሎች ሊቃውንት ዘንድ ግን የግቢ ወይም የገመድ ሃይሮግሊፍ ነበር




#Article 87: ዐይን (ፊደል) (107 words)


 ዐ ዑ ዒ ዓ ዔ ዕ ዖ 

ዐይን በጥንታዊ አቡጊዳ ተራ 16ኛው ፊደል ነው። እንዲሁም በከነዓን በአራማያ በዕብራይስጥ በሶርያም ፊደሎች 16ኛው ፊደል «ዐይን» ይባላል። በዓረብኛ ደግሞ ተመሳሳይ ፊደል «ዐይን» ተብሎ በ«አብጃድ» ተራ 16ኛ ነው። 

በመጀመርያው (ግዕዝ) ቅርጽ (አ) በልሳነ ግዕዝ እንደ ሌሎቹ ፊደላት የ«ኸ» አናባቢ ድምጽ ሆነው ነበር፤ በአማርኛ ግን ድምጹ እንደ አራተኛው (ራብዕ) ቅርጽ (ዓ) አንድላይ ነው። በአማርኛ አጻጻፍ ብዙ ጊዜ ከአልፍ (አ) ጋራ ሊለዋውጥ ይችላል። ቀድሞ ግን ድምጾቻቸው የተለያዩ ነበሩ።

የዐይን መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት እንደ ሆነ ይታስባል።  በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ የዐይን ስዕል መስለ።  ለዚህም ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ ነበር።  አጠራሩ ግን «ኢር» ነበር። በግብፅ የሠሩት ሴማውያን ግን በቋንቋቸው «ዐይን» ስላሉት፣ ይህ ስዕል «ዐ» ሆኖ እንዲሰማ መጣ።




#Article 88: ይሁዳዊ-ሮማንስ ቋንቋዎች (115 words)


ይህዳዊ-ሮማንስ ቋንቋዎች ከሮማንስ ቋንቋዎች የወጡት በአይሁዶችም የሚናገሩ ልሳናት ናቸው። የራሳቸው ቋንቋዎች ሆነው እስከሚቆጠሩ ድረስ ተለውጠዋል ማለት ነው።

የነኚህ ቀበሌኞች እድገት በሙሉ ግልጽ አይደለም፡፡ ወይም በቀጥታ ከይሁዳዊ-ሮማይስጥ ታደጉ ወይም ከሮማይስጥ የታደጉት ሮማንስ ቋንቋዎች ተለይተው ከያንዳንዱ ተነሡ፡፡

ይሁዳዊ-ሮማይስጥ፣ ዛርፋቲክ፣ ሿዲት፣ እና ይሁዳዊ-አራጎንኛ ሁላቸው ዛሬ አይናገሩም። መጨረሻ የሿዲት ተናጋሪ በ1969 ዓ.ም. ዐረፉ። 

ይሁዳዊ-ፖርቱጊዝ እና ካታላኒክ ቅሬታዎች ብቻ ሆነው ቆይቷል። 

'ኢታልኪያን' 2 ትውልዶች በፊት በ5000 ኢጣልያዊ-አይሁዶች ተናግሮ ዛሬ ግን በ200 mdash; በተለይ ባረጁ mdash; ሰዎች ዘንድ ብቻ ይሰማል። 

ላዲኖ በ150,000 ተናጋሪዎች መሃል እስካሁን ይሰማል። እነዚህ የሚኖሩ በተለይ በስሜን አፍሪካ እና በቱርክ ነው። አብዛኞቹ ሌላ ቋንቋ ደግሞ ይችላሉ።
 
የነዚህ ቋንቋዎች ወደፊት እርግጠኛ አይደለም። ዛሬ ዕብራይስጥ እንደገና በሰፊ ስለሚጠቅም፣ ወይም ወጣቶቹ የየአገራቸውን ቋንቋውች (እንደ ቱርክኛ) መጀመርያ ስለሚማሩ፣ ሁኔታው ብዙ ተስፋ አይሰጥም።  




#Article 89: ዕውነተኛ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን (181 words)


ዕውነተኛ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን በቤጂንግ ቻይና በ1909 ዓ.ም. የተመሠረተ ነፃ ቤተ ክርስቲያን ነው። በ6 አህጉር ላይ 1.5 ሚሊዮን የሚያሕሉ ምዕመናን አሉት። ቤተ ክርስቲያኑ በቻይና የወጣ ከጰንጤ እንቅስቃሴ የተነሣ ነው። 

ይህ ቤተ ክርስቲያን ግን የሥላሴ ጽንሰ ሐሳብ አይቀበልምና «የኢየሱስ ስም ትምሀርት» ተከታዮች ናቸው። 

የዕውነተኛ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን 5 አይነተኛ ትምሀርቶች እንደሚከተል ናቸው፦

መንግስተ ሰማያት የመውረሳችህን ዋና ነገር ገታ እየሱስ እንደግል አዳናችን በመቀበል ነው

ከዚህ ቀድሞ የውኃ ጥምቀትና መንፈስ ቅዱስ የተቀበለው መጥምቅ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ያጠምቀዋል። ተጠቃሚውም ራሱን አጎንብሶ ወደ ታች ሲመለከት በውኃ በሙሉ እንዲታጠብ ነው።»

የውኃ ጥምቀት የተቀበለ ሰው ሁሉ እግሮቹን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንዲታጠብ አለበት። በሚገባበት ጊዜ እርስ በርስ መታጣጠብ ሊሠራ ይችላል።»

ዘላለማዊ ሕይወት እናገኝ ዘንድ በመጨረሻም ቀኝ እንነሣ ዘንድ፣ ከጌታችን ሥጋ ወደም ለማሳተፍ ከሱም ጋር ለመቈረብ ያስችለናል። ይኸው ቁርባን እስከሚቻል ድረስ ብዙ ጊዜ ይደረጋል። አንድ ቂጣ እና የወይን ጭማቂ ብቻ ይጠቀማል።»

በኋላ በ1980ዎቹ የዕውነተኛ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን 10 መሠረታዊ እምነቶች ለመሆን በነዚህ 5 ዋና ትምህርቶች ላይ ሌሎች ተጨመሩ፦

ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል ሥጋ ሆኖ በመስቀል ላይ ስለ ኃጢአተኞች ቤዛነት የሞተው፣ በሦስተኛው ቀን ከሙታን የተነሣውና ወደ ሰማያት ያረገው ነው፤ እርሱ የሰው ልጆች ብቸኛ አዳኝና የሰማይና የምድር ፈጣሪ እንዲሁም እውነተኛ አምላክ ነው።




#Article 90: ሃሰኩራ ጹነናጋ (318 words)


ሃሰኩራ ሮኩኤሞን ጹነናጋ (支倉六右衛門常長, 1563–1614 ዓ.ም.) ጃፓናዊ ሳሙራይ (መኮንን) እና የሰንዳይ ዳይምዮ (ገዥ) የዳተ ማሳሙነ ሎሌ ነበሩ። ከ1605 ዓ.ም. እስከ 1612 ዓ.ም. ድረስ ወደ ሜክሲኮ፣ እስፓንያ፣ ፈረንሳይ እና ጣልያን አገሮች አምባሳደር ሆነው ይፋዊ ጉብኝት አደረጉ። ከማንም በፊት ወደ አሜሪካ አህጉር የተላኩት የጃፓን መንግሥት ልዩ ተወካይ እሳቸው ነበሩ። ከዚያ በላይ የርሳቸው ተልዕኮ በታሪክ መዝገብ የሚታወቀው መጀመርያው ጃፓናዊ-ፈረንሳያዊ ግንኙነት ሆኗል።

ስለ ልጅነታቸው ብዙ ባይታወቅም፣ በታይኮ (እንደራሴ) ሂደዮሺ በኮርያ ላይ በተደረገው ወረራ ጊዜ በ1584 እና በ1589 ዓ.ም. ዘመቻዎች ልምድ ያለው ሳሙራይ ሆነው እንደ ተሳተፉ ይታወቃል።

በ16ኛው ምዕተ ዓመት ከተካሄደው አንድሬስ ዴ ኡርዳኔታ ጉዞ ጀምረው እስፓንያውያን በፊሊፒንስ የያዙትን መሬት መሠረት አድርገው በሜክሲኮና በቻይና መካከል ፓሲፊክ ውቅያኖስን ይሻገሩ ነበር። በ1563 ዓ.ም. ማኒላ ለምሥራቅ እስያ ሁሉ መሠረታቸው ሆነላቸውና።

የስፓንያ መርከቦች አንዳንዴ በመውጅ ትይዘው በጃፓን ዳር ላይ ሲሰበሩ በዚህ አጋጣሚ ግንኙነት ከአገሩ መጣ። እስፓንያውያን የክርስትናን ሃይማኖት ወደ ጃፓን ለማስፋፋት ፈልገው ነበር። ነገር ግን ተፅእኖ ወደ ጃፓን ለመዘርጋት የተደረገው ጥረት ከኢየሱሳውያን ወገን ብርቱ ተቃውሞ አገኘ፤ እነኚህ ወንጌሉን በአገሩ ውስጥ በ1541 ዓ.ም. ስብከት ጀምረው ነበርና። ከዚያ በላይ ፖርቱጊዞችና ሆላንዶች ከጃፓን ጋር ስለነበራቸው መገበያየት ከስፓንያ ምንም ውድድር ለማየት አልወደዱም ነበር። 

በ1601 የስፓንያ ታላቅ መርከብ ሳን ፍራንሲስኮ ከማኒላ ወደ ሜክሲኮ ሲሄድ መውጅ አጋጥሞት በጃፓን ጠረፍ ላይ በቶክዮ ዙሪያ በቺቦ ሲጠፋ መርከበኞቹ በኗሪዎች አማካይነት ድነው ስላምታ ይሰጡና የመርከቡ አለቃ ሮድሪጐ ደ ቪቨሮ ከሾጉን (ደጃዝማች) ቶኩጋዋ ኢኤያሱ ጋራ ተገናኙ። 

በኅዳር 23 ቀን 1602 ዓ.ም. የስምምነት ውል ተፈራርመው፣ እስፓንያውያን በምሥራቅ ጃፓን ውስጥ አንድ ፋብሪካ ለመሥራት፣ የማዕድን ሠራተኞች ከአዲስ ስፓንያ (ሜክሲኮ) ወደ አገሩ ለማስገባት፣ የስፓንያ መርከቦች አስፈላጊነት እንደሆነባቸው ጃፓንን ለመጎብኘት ተፈቅደው፣ ደግሞ የጃፓን ተልእኮ ወደ እስፓንያ ቤተ መንግሥት እንዲጓዝ ተወሰነ።

በቶክዮ ዙሪያ ይሰብክ የነበረው መነኩሴ ሉዊስ ሶተሎ ወደ አዲስ እስፓንያ (ሜክሲኮ) አምባሳደር ሆኖ እንዲላክ ሾጉኑን አስረዳቸው። በ1602 ሶተሎ ከተረፉት እስፓንያዊ መርከበኞችና ከ22 ጃፓናውያን ጋራ ለሾጉኑ በእንግሊዛዊው ዠብደኛ በዊሊያም አዳምስ በተሠራው መርከብ በሳን ብዌና ቨንቱራ ላይ ተሣፍሮ ወደ ሜክሲኮ ተጓዘ። አዲስ እስፓንያ ደርሶ እንደራሴውን ሉዊስ ደ ቨላዝኮ አገናኘ። እሳቸው ታዋቂውን ዠብደኛ ሰባስትያን ቪዝካይኖ አምባሳደር ሆኖ ወደ ጃፓን ለመላክ ተስማሙ። በተጨማሪ ከጃፓን ወደ ምሥራቅ እንደ ሆኑ የታሰቡትን የወርቅና የብር ደሴቶች እንዲፈልግ ልዩ የሆነ ትእዛዝ መደቡት።




#Article 91: ዋና ከተማ (105 words)


ዋና ከተማ የአገር ወይም የክፍላገር መንግሥት የሚገኝበት ማዕከላዊ ከተማ ነው። ባለ ሥልጣኖች ሹሞችና መሪዎች ይሠሩበታል። 

ብዙ ጊዜ ዋና ከተማ የአገሩ ትልቁ ከተማ ይሆናል። ለምሳሌ ሞንቴቪዴዮ የኡራጓይ ታላቁ ከተማ ከመሆኑ በላይ በተጨማሪ ዋና ከተማው ነው። ቢሆንም ዋና ከተማ ሁልጊዜ ያገሩ አንደኛው ትልቅ ከተማ አይደለም። ለምሳሌ የዩናይትድ ስቴትስ ዋና ከተማ ዋሺንግተን ዲሲ ሲሆን ከአንደኛው ትልቅ ከተማው ግን ከኒው ዮርክ ከተማ ያንሳል። እንዲሁም የሕንድ ዋና ከተማ ኒው ዴሊ ከታላቁ ከተማ ከመምባይ በጣም ያንሳል።

አንዳንድ አገር ከ1 በላይ ዋና ከተማ አለው። ለምሳሌ ቦሊቪያ ሁለትና ደቡብ አፍሪካ ሦስት ዋና ከተሞች አሉት። ናውሩ ምንም ይፋዊ ዋና ከተማ የሌላት የሰላማዊ ውቅያኖስ ደሴት አገር ናት። አንዳንድ አገሮች ደግሞ የዋና ከተሞቻቸውን ሥፍራ በየጊዜው ያዛውራሉ።




#Article 92: የመርዌ ጽሕፈት (127 words)


የመርዌ ጽሕፈት ከ200 ዓክልበ. ያሕል ጀምሮ በመርዌ መንግሥት (ዛሬ ሱዳን) የመርዌ ቋንቋ የተጻፈበት ፊደል ነበር። የወጣው ከግብፃዊው ሃይሮግሊፊክና ዴሞቲክ ጽሕፈቶች ነበር። ከመርዌ መንግሥት በኋላ በተከተሉት በኖባ መንግሥታት ደግሞ ክርስትና እስከ ገባ ድረስ ምናልባት ይጠቅም ነበር፡፡ ከክርስትና በኋላ የጥንታዊ ኖባ ቋንቋ የተጻፈበት በግሪክ ፊደል ሲሆን ከዱሮ መርዌ ጽሕፈት 3 ምልክቶች ተጨምረው ነበር፡፡

በጠቅላላ 23 ምልክቶች ነበሩበት፡፡ ከነዚህ መሀል 4 አናባቢዎች፣ እነሱም /አ/, /እ/, /ኢ/, ና /ኦ/ ነበሩ፡፡  የተናባቢ ምልክቶች ለብቻ ሲታዩ የ/አ/ ድምጽ ያሰሙ ነበር፡፡ 

ለዚህ ፊደል ሁለት አይነቶች እነሱም ሃይሮግሊፊክና ዴሞቲክ ነበሩ፡፡ የሃይሮግሊፊክ ቅርጾች በተለይ የሚገኙ በሐውልቶች ነው፡፡ እሱ ከላይ እስከ ታች ይጻፍ ነበር፣ ዴሞቲክ ከቀኝ እስከ ግራ ይጻፍ ነበር፡፡ ሁለት ወይም ሦስት ነጥብ ቃላት ለመለየት ጠቀመ፡፡ 

የፊደሎቹ ፍች የገለጸው ሊቅ እንግሊዛዊው ፍራንሲስ ልወልን ግሪፊስ በ1901 ዓ.ም. ነበር፡፡ ዳሩ ግን እስከ ዛሬ ድረስ ቋንቋው እራሱ በደንብ አይታውቅም፡፡




#Article 93: ኮሪይኛ (635 words)


ኮሪይኛ (한국어 / 韓國語 / ሃን ጉክ ኧ) የኮርያ (ስሜንና ደቡብ) መደበኛ ቋንቋ ነው።

가 (ካ)
나 (ና)
다 (ታ)
라 (ራ) (ላ)
마 (ማ)
바 (ፓ)
사 (ሳ)
아 (ዓ) (ንጋ)
자 (ቻ)
차 (ጫ)
카 (ቃ)
타 (ጣ)
파 (ጳ)
하 (ሃ)

아 (አ)
야 (ያ)
어 (ኧው)
여 (የ)
오 (ኦ)
요 (ዮ)
우 (ኡ)
유 (ዩ)
으 (እ)
이 (ኢ)

안녕! (አን ንየንግ!) = ሰላምታ!
안녕하세요! (አን ንየንግ ሃ ሰይ ዮ!) = ሰላምታ!
안녕하십니까! (አን ንየንግ ሃ ሲፕ ኒ ካ?) = ሰላምታ!
감사합니다. (ካም ሳ ሃፕ ኒ ታ) = አመሰግናለሁ
고맙습니다. (ኮ ማፕ ሰፕ ኒ ታ) = አመሰግናለሁ
예. (ዬ) = አዎ
네. (ኔ) = አዎ
아니오. (አኒኦ) = አይደለም
안녕히 가세요. (አን ንየንግ ሂ ካ ሴ ዮ) = ደህና ይሁኑ!
안녕히 계세요 (አን ንየንግ ሂ ክየይ ሴ ዮ) = ደህና ይሁኑ!
미안합니다. (ሚ አን ሃፕ ኒ ታ) = ይቅርታ
미안해요. (ሚ አን ሄ ዮ) = ይቅርታ
죄송합니다. (ቾይ ሶንግ ሃፕ ኒ ታ) = ይቅርታ
천만에요. (ጨን ማን ኧይ ዮ) = ችግር የለም
축하합니다! (ጩክ ሃ ሃፕ ኒ ታ!) = ጎበዝ!
생선, 물고기 (ሴንግ ሰን፥ ሙል ኮ ኪ) = ዓሣ
나무 (ናሙ) = ዛፍ
물 (ሙል) = ውኃ
불 (ቡል) = እሳት
전기 (ቻን ኪ) = ነጎድጓድ
쌀 (ሣል) = ሩዝ
도시 (ቶሲ) = ከታማ
저녁 (ቸ ንየክ) = ማታ
사랑 (ሳ ላንግ) = ፍቅር
사랑합니다. (ሳ ላንግ ሃፕ ኒ ታ) = እወዶታለሁ
남자 (ናም ቻ) = ሰው
여자 (የ ቻ) = ሴት
월요일 (月曜日 ; Weol yo il) = ሰኞ
화요일 (火曜日 ; hwa yo il) = ማክሰኞ
수요일 (水曜日 ; su yo il) = ሮብ
목요일 (木曜日 ; mok yo il) = ሐሙስ
금요일 (金曜日 ; geum yo il) = ዓርብ
토요일 (土曜日 ; to yo il) = ቅዳሜ
일요일 (日曜日 ; il yo il) = እሑድ
하루 / 일일 / 1일 (Haru / il il) = አንድ ቀን .
일년 / 1년 (ኢል ንዮን) = አንድ አመት 
삼년 / 3년 (ሳም ንዮን) = ሶስት አመታት 
십년 / 10년 (ሲብ Nyeon) = 10 አመታት 
백년 / 100년 (በክ nyeon) = 100 አመታት  
천년 / 1000년 (ቾን Nyeon) = 1000 አመታት 

누구 (Nu gu) = ማን
사람 (Sa ram) = የሰው ልጅ
친구들 (Chin gu deul) = ጓደኛ
군대 (Gun Dae), 군사 (Gun sa) = ወታደር
독일어 (Dok il eo), 게르만 (German) = ጀርመንኛ (도이치[Do i Chi)]
프랑스어 (France eo) = ፈረንሳይኛ (프랑셰즈)
영어 (Yeong eo) = እንግሊዝኛ / 잉글리시(Ing geul Ri Si)
다리 (Da ri) = ድልድይ
기차 (Gi Cha) = ባቡር
철교 (Cheol Gyo) = የባቡር መንገድ
러시아 (Reo si a) / 노서아 (No seo a) / 아라사 (A Ra Sa) = ሩሲያ / 모스크바 (Mo s K Ba) = መስኮብ
미국 (Mi Guk) / 아메리카합중국 (America Hab jung guk) = USA / አሜሪካ
일본 (il Bon) = ጃፓን. 도쿄 / 동경[東京] (Do kyo / Dong Kyeong) = ቶክዮ
중국 (Jung kuk) = ቻይና. 베이징 / 북경[北京] (Beijing / Buk Kyeong) = በይጂንግ
모로코 (Mo ro Ko) = ሞሮኮ. 라바트 (Ra ba t) = ራባት
사우디아라비아 ሳዑዲ ዓረቢያ 리야드 (Ri ya d) = ሪያድ
대한민국 (Dae han Min guk) / 한국 (Han guk) = ደቡብ ኮርያ
서울 (Seo ul) = Seoul
독도 (Dok ko) = Dokko Island
조선민주주의인민공화국 (Jo seon Min ju ju e in min gong hwa gook) / 북한 (Buk han) = ስሜን ኮርያ
평양 (Pyeong yang) = Pyeongyang
수도 (Su do) / 특별시 (Teuk Byeol Si) = metropolitan City
(서울특별시 (Seoul Yeuk Byeol Si) = Seoul metropolitan City
고기 (Go gi) = ሥጋ
별 (Byeol) = ኮከብ
설탕 (Seol Tang) = ስኳር
민주주의 (Min ju ju e) = ዲሞክራሲ
공산주의 (Gong san ju e) / 빨갱이 (Bbal gaeng i) = ኮሙኒስት
대한민국 만세! (Dae Han Min Guk Manse!) = ኮርያ ለዘላለም!
에티오피아 만세 ! (Ethiopia Manse!) = ኢትዮጵያ ለዘላለም!
나는 평화를 사랑하죠. (Na Neun Pyeong Hwa Reul Sa rang ha Jyo) = እኔ ሰላም እወዳለሁ




#Article 94: አማርኛ (559 words)


አማርኛ ፡  የኢትዮጵያ ፡ መደበኛ ፡ ቋንቋ ፡ ነው ።      ከሴማዊ ፡ ቋንቋዎች ፡ እንደ ፡ ዕብራይስጥ ፡ ወይም ፡ ዓረብኛ ፡ አንዱ ፡ ነው። በአፍሪካ ፡ ውስጥ ፡ ደግሞ ፡ ከምዕራብ ፡ አፍሪካው ፡ ሐውሳና ፡ ከምሥራቅ ፡ አፍሪካው ፡ ስዋሂሊ ፡ ቀጥሎ ፡ 3ኛውን ፡ ቦታ ፡ የያዘ ፡ ነው። እንዲያውም ፡ 85.6 ፡ ሚሊዮን ፡ ያህል ፡ ተናጋሪዎች ፡ እያሉት ፣ አማርኛ ፡ ከአረብኛ ፡ ቀጥሎ ፡ ትልቁ ፡ ሴማዊ ፡ ቋንቋ ፡ ነው። የሚጻፈውም ፡ በአማርኛ ፡ ፊደል ፡ ነው። አማርኛ ፡ ከዓረብኛና ፡ ከዕብራይስጥ ፡ ያለው ፡ መሰረታዊ ፡ ልዩነት ፡ እንደ ፡ ላቲን ፡ ከግራ ፡ ወደ ፡ ቀኝ ፡ መጻፉ ፡ ነው።

የሐማራ * ግዛት ፡ ተብሎ ፡ የሚታወቀው ፡ ቦታ ፡ በአሁኑ ፡ መካከለኛና ፡ ደቡብ ፡ ወሎ ፡ ይገኝ ፡ እንደነበር ፡ በታሪክ ፡ ይጠቀሳል። ከክርስቶስ ፡ ልደት ፡ በፊት ፡ ከ200 - 130 ዓ.ዓ. ፡ የነበረው ፡ አጋታርከስ ፡ ስለ ፡ ቀይ ፡ ባህር ፡ እና ፡ አካባቢው ፡ ሲጽፍ ፣ ትሮጎዶላይት ፡ ያላቸው ፡ ሕዝቦች – τής Kαμάρ λέξιςα (የካማራ Camàra ቋንቋ) ወይንም ፡ Kαμάρα λέξιςα (ካማራ Camàra ቋንቋ) ይናገሩ ፡ እንደነበር ፡ ዘግቧል። ከዚህ ተነስተው ፡ የተለያዩ ፡ ታሪክ ፡ አጥኝዎች ፡ የአጋታርከስ ፡ ካማራ ፡ ቋንቋ ፡ የአሁኑ ፡ አማርኛ በወር የቋንቋ አባሪና ፡ ወላጅ ፡ እንደሆነ ፡ ያስረዳሉ።

ትክክለኛው ፡ አማርኛ ፡ አንዳንዴ ፡ «የንጉሥ ፡ ቋንቋ» ፡ ወይም ፡ ደግሞ ፡ «ልሳነ-ንጉሥ» በመሰየም ፡ ታወቋል። አማርኛ ፡ ልሳነ-ንጉሥ ፡ የሆነው ፡ በ1272 ዓ.ም. ከዛጔ ሥርወ መንግሥት ፡ በኋላ ፡ አጼ ፡ ይኩኖ ፡ አምላክ ፡ ሰሎሞናዊውን ፡ ሥርወ-መንግሥት ፡ መልሶ ፡ ሲያቋቁም ፡ ነበር። አማርኛ ፡ ልሳነ-ጽሑፍ ፡ መሆን ፡ የጀመረው ፡ በ14ኛው ፡ ክፍለ ፡ ዘመን ፡ ላይ ፡ ሲሆን ፡ ይህንንም ፡ ያደረገው ፡ ሁሉንም ፡ የግዕዝ ፡ ፈደላትን ፡ በመውሰድና ፡ 6 ፡ አዳዲስ ፡ የላንቃ ፡ ፊደላትን ፡ (ማለትም ሸ ፣ ቸ ፣ ኘ ፣ ዠ ፣ ጀ ፣ ጨ) እና ፡ ኸን ፡ በመጨመር ፡ ነበር። ነገር ፡ ግን ፡ በጽሑፍ ፡ ይበልጥ ፡ መስፋፋት ፡ የጀመረው ፡ ከአጼ ፡ ቴዎድሮስ ፡ ጀምሮ ፡ ሲሆን ፡ ለእዚህም ፡ በተለይ ፡ አስተዋጽኦ ፡ ያደረገው ፡ ጸሐፊያቸው ፡ ደብተራ ፡ ዘነብ ፡ ነበር። አማርኛ ፡ በተለይ ፡ የተስፋፋው ፡ የዳግማዊ ፡ አጼ ፡ ምኒሊክን ፡ የግዛት ፡ ማስፋፋት ፡ ዘመቻ ፡ ተከትሎና ፡ እንዲሁም ፡ ዘመናዊ ፡ ትምህርት ፡ ኢትዮጵያ ፡ ውስጥ ፡ ከተጀመረ ፡ በኋላ ፡ ነበር።

አማርኛ ለብዙ ዘመናት በእጅ ሲጻፍ ቆይቶ በ፲፱፻ ዓ.ም. ገደማ በማተሚያ መሣሪያ ሊከተብ ችሏል። የግዕዝን ፊደል በዶ/ር ኣበራ ሞላ ፈጠራ ወደ ኮምፕዩተር ገብቶ ከ፲፱፻፹ ዓ. ም. ወዲህ በኮምፕዩተር መጠቀም ከመቻሉም ሌላ በዩኒኮድ ዕውቅና ኣግኝቷል። ይህ የተስፋፋ ገጽም የቀረበው በእዚሁ ሥርዓት ሲሆን በቋንቋው የተጻፉ መረጃዎች ቊጥሮች እያደጉ ነው። የዓማርኛ ፊደልና ቋንቋም ዕውቅና እያደገ ስለመጣ በእጅ ስልኮችም በሚገባ ሥራ ላይ እየዋለ ነው። ኣፕል የቋንቋ ገበታዎቹን ሌሎችም እንዲጠቀሙበት በ፳፻፯ ዓ. ም. ስለከፈተ ዓማርኛን እንደሌሎች የዓለም ባለፊደል ቋንቋዎች መርጦ መጠቀም ተችሏል። በ፳፻፰ ዓ. ም. ግዕዝ የመጀመሪያን የኣሜሪካ የባለቤትነት መታወቂያ (ፓተንት) ኣግኝቷል። 

በየካቲት 10 ቀን 2008 ዓ.ም. አማርኛ ወደ ማናቸውም ሌላ ቋንቋ በኮምፒውተር በቀላሉ ወደሚተረጎሙት ቋንቋዎች ገብታለች። ሆኖም የትርጉሙ ጥራት ከፍ ያለ ሳይሆን ስኅተቶች የተሞላበት ሆኖ ቀርቷል።

በሷዴሽ ዝርዝር 207 ተራ ቃላት ውስጥ

በዝርዝሩ ከተረፉት ግማሽ ቃላት፣ ብዙዎች ከሌሎች የግዕዝ ሥሮች በሌላ መንገድ መጡ፣ ለምሳሌ «እርሱ» በግዕዝ «ውእቱ» ፈንታ፣ ከ«ርዕሱ» (ራሱ) ይመስላል።

ከግዕዝ ጭምር ከሰው ልጆች ልሳናት የተበደሩ ሌሎች ቃላት እንደ ዘመኑ ይለያያሉ፦ ከግሪክኛ፣ ከአረብኛ፣ ከፖርቱጊዝኛ፣ ከቱርክኛ፣ ከፈረንሳይኛ፣ ከጣልኛና ከእንግሊዝኛ ቃላት የተቀበሉባቸው ዘመኖች ኑረዋል። እንዲሁም አንዳንድ የአማርኛ ቃሎች ከግዕዝ ይልቅ እንደ ኦሮምኛ ወይም እንደ ኩሻዊ ቋንቋዎች ቃላት ይመስላሉ። 

ምሳሌዎች፦

 

 

 




#Article 95: ሞንጎልኛ (131 words)


ሞንጎልኛ (, Монгол) ከሞንጎሊክ ቋንቋ ቤተሠብ ሁሉ የታወቀውና ለአብዛኛው የሞንጎልያ ኗሪዎች ዋና ቋንቋ እንዲሁም የሞንጎልያ መደበኛ ቋንቋ ነው። ደግሞ በአካባቢው ባሉት የሩሲያና የቻይና አውራጃዎች ውስጥ ሲናገር የሩሲያ ክፍላገር ቡርያትያ እና የቻይና ክፍላገር ውስጣዊ ሞንጎልያ መደበኛ ቋንቋ እሱ ነው። በሞንጎልያ ውስጥ ካሉት ተናጋሪዎች ብዙኃን የሓልሓ ቀበሌኛ ይናገራሉ። በቻይናም ዋናው ቀበሌኛ ቻሃር ይባላል።

አንዳንድ ሊቃውንት ሞንጎልኛን ለቱርክ ምናልባትም ለጃፓንኛ ለኮሪይኛም ዝምድና እንዳለው ይቆጠሩታል። እርግጥ የተዛመደ ቋንቋ በሩሲያ የተገኘው ካልሙክኛ ነው። በሞንጎልያ ከ2 ሚሊዮን በላይ ተናጋሪዎች ሲኖሩ በአገሮቹ ሁሉ በጠቅላላ 5.7 ሚልዮን ያሕል ይችሉታል። 

ባሕላዊ የሆነው የሞንጎል ፊደል በ12ኛ ምዕተ አመት ከሶግዲያን ፊደል በኡይጉር ሕዝብ አማካይነት ወጣ። እስከ ዛሬ ድረስ በቻይና ውስጥ ሞንጎልኛ ለመጻፍ የሚጠቀመው ጽሕፈት እሱ ነው። በሞንጎልያ ግን በ1935 ዓ.ም. ይህ ባሕላዊ ጽሕፈት በቂርሎስ አልፋቤት ተተካ። ከዚህ በላይ በቻይና በኦይራት ሕዝብ ዘንድ ቶዶ ጽሕፈት በተሰየመ በሌላ አይነት ባሕላዊ ፊደል ነው ቋንቋቸው የሚጻፈው።




#Article 96: ቡሩንዲ (197 words)


የቡሪንዲ ሪፕብሊከ (ቀድሞ ኡሩንዲ (urundi) የተባለ ሲሆን) በአፍሪካ ውስጥ የምትግኝ ተንሽ አገር ናት። በሩዋንዳ፥ ታንዛኒያ፥ እና በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ ትዋሰናልች።
አገሯ ወደብ-የለሽ ብትሆንም ከታንጋንዪካ ሐይቅ ጋር ትዋሰናለች። የቡሩንዲ ዋና ከተማ እስከ ታህሳስ 2011 ዓም ድረስ ቡጁምቡራ ሲሆን ከዚያ ወደ ጊቴጋ ተዛወረ። የሀገሩ የህዝብ ብዛት ወደ 8.7 ሚሊዮን እንደሆነ ይገመታል።

የቱዋ፣ ቱትሲና ሁቱ ብሔሮች በቡሩንዲ ለአምስት ምእተ ዓመታት ያህል ኖረዋል። የቱትሲ ሕዝብ ቡሩንዲን በየንጉሥ መንግሥትነት ለሁለት መቶ ዓመታት ያህል መርቷል። ግን በ፳ኛው ክፍለ ዘመን መግቢያ ላይ፣ አካባቢው በጀርመንና ቤልጅግ ቁጥጥር ስር ላይ ኖሯል። ቡሩንዲና ሩዋንዳም አንድ ላይ ሩዋንዳ ኡሩንዲ እየተባሉ በቅኝ ግዛት ጊዜ ተጠርተዋል።

በአካባቢው የሰፈነው የፖለቲካ ቀውስ በቡሩንዲ የእርስ በርስ ጦርነት ፈጥሮአል። በአሁኑ ጊዜ ቡሩንዲ ፕሬዝዳንታዊ የተወካዮች ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሆና ትመራለች። ከሀገሩ ሕዝብ ውስጥ ፷፪ ከመቶ የሮማ ካቶሊክ እምነት ተከታይና ከ፰ እስከ ፱ ከመቶ እስላም ሲሆን የተቀረው ሌሎች የክርስትና ዕምነቶችን ወይም ባህላዊ ሃይማኖቶችን ይከተላል።

ቡሩንዲ ከዓለም አስር እጅግ ድሀ ሀገራት አንዷ ናት። የዚህ ምክንያት ከሆኑት ውስጥ ጦርነቶች፣ ሙስና፣ የትምህርት አለመስፋፋትና የኤድስ በሽታ ይጠቀሳሉ። የተፈጥሮ ሀብቶቿ መዳብና ኮባልትን ይጨምራሉ። ኤክስፖርት ከምታደርጋቸው ምርቶች መካከል ዋናዎቹ ቡናና ስኳር ናቸው።

የመጀመሪያው የቡሩንዲ ነዋሪዎች የፒግሚ ሰዎች ናቸው። ከዛም በባንቱ ሕዝቦች ባብዛኛው ተተክተዋል። በ16ኛው ክፍለ ዘመን ነጻ መንግሥት ነበረ። ከዛ በ1903 እ.ኤ.አ. የጀርመን ቅኝ ግዛት ሆነች። በአንደኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ ወደ ቤልጅግ ተላለፈች።




#Article 97: ኅዳር ፲፭ (156 words)


ኅዳር ፲፭ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፸፭ኛ ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ  ፪፻፺፩ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፺ ቀናት ይቀራሉ።
  

፲፱፻፶፮ ዓ.ም. ፕሬዚደንት ጆን ኤፍ ኬኔዲን ገድለሃል ተብሎ የተወነጀለው ሊ ሃርቪ ኦዝዋልድ ዳላስ የፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት ውስጥ ዓለም አቀፍ ጋዜጠኞችና ቴሌቪዝን ድርጊቱን ለዓለም እየሰራጩ ሳሉ፤ ጃክ ሩቢ የሚባለው ሰው ኦዝዋልድን በሽጉጥ ገደለው።

፲፱፻፶፰ ዓ.ም. አምባገነኑ ጆሴፍ ዴዚሬ ሞቡቱ በኮንጎ የመሪነትን ሥልጣን በጉልበት ጨበጠ። በ፲፱፻፷፬ ዓ.ም. የአገሪቱን ስም ቀይሮ ዛይር ተባለች። እሱም በአምባገነነንነት ሠላሣ ሁለት ዓመታት ከገዛ በኋላ በ፲፱፻፺ ዓ.ም. በኃይል ከሥልጣን ተወገደ።

፲፱፻፷፯ ዓ.ም. ዶናልድ ዮሃንሰን እና ቶም ግሬይ አፋር ክልል ውስጥ ከ ሦሥት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ዓመታት በፊት የኖረችውን የድንቅነሽን ዓጽም አገኙ።

፲፱፻፸፰ ዓ.ም. የግብጽ ወታደራዊ ፈጥኖ ደራሽ ቡድን ተጠልፎ ማልታ ደሴት ላይ ከነመንገደኞቹ በጠላፊዎቹ ቁጥጥር ስር የነበረውን የዓየር ተሽከርካሪ ሲያስለቅቁ ሃምሣ ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ። 	

፲፱፻፶፮ ዓ.ም.  – ፕሬዚደንት ጆን ኤፍ ኬኔዲን ገድለሃል ተብሎ የተወነጀለው ሊ ሃርቪ ኦዝዋልድ




#Article 98: ቴዲ አፍሮ (191 words)


ቴዲ አፍሮ (Teddy Afro) ዕውነተኛ ስሙ: ቴዎድሮስ ካሳሁን ሲሆን ከዘመናችን ወጣት ኢትዮጵያውያን ዘፋኞችና አቀንቃኞች ሁሉ እጅግ ተወዳጅ ነው። ቴዲ ለጃማይካዊው ሬጌ ኮከብ ቦብ ማርሊ የዘፈነለት የሬጌ ሙዚቃው በዓለም ዙሪያ እንዲታወቅ ያደረገው ሲሆን በተለይ ለኃይሌ ገብረ ሥላሴ ና ለሌላኛው የኦሊምፒክ ጀግና ቀነኒሳ በቀለ በኦሊምፒክስ ካሸነፉ በኋላ ያወጣቸው ወቅታዊ አልቡሞቹ ይበልጥ ታዋቂ አርገውታል። ቴዲ አፍሮን በጣም ታዋቂ ያደረግው 'ያስተሰርያል' የተባለው አልበሙ ሲሆን ስለ ፍቅር ፣ መቻቻል ፣ ህዝብ ስሜት እንዲሁም ስለመንግስታት እና ስለ ተቃዋሚዎች በ ፍቅር ለ ሃገር እድገት መስራት ዘፍኖአል። ዘፈኖቹ ብስል እና ጠንካራ ናቸው። ቴዎድሮስ ካሳሁን ሐምሌ 7 1968 በአዲስ አበባ ተወለደ።

በመኪና አደጋ ሰው ገድሎ በማምለጥ ወንጀል ተከሶ የነበረ ሲሆን፣ በፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረት 6 ዐመት አና 18000 ብር አንዲከፍል ከተወሰነበት በኋላ በእስር ቤት ውስጥ ለ 1 አመት ከ ወራት ያህል ቆይቷል። ከዚያም በተለያዩ ምክንያቶች (ይቅርታን ይጨምራል) ከ እስር እንዲፈታ ተወስኖለታል።

ፍርዱ ብዙውን ህዝብ አላሳመነም። ህዝቡ በተለያዩ አጋጣሚዎች የቴዲን መፈታት አስመልክቶ ጩሀቱን አሰምቶአል። የፍርድ ሂደቱ ግልጽ አልነበረም ከ ወንጀል ክስነት ይልቅ የፖለቲካ ትርጉም የያዘ ነበር። እና ሌሎችም ተቃውሞዎች በተለያዩ ጊዜያት ከህዝቡ ተሰምተዋል። ሲገጭ አይቻለሁ ብሎ የመሰከረበት ይርዳው ጤናው ነው። እስከማለት ነበር የህዝቡ ተቃውሞ።

ተዲ አፍሮ ከ እስር ከተፈታ በኋላ በተለያዩ ቦታዎች ትሪቶቹን አቅርቧል። በቀጣይም ሊያቀርባቸው ያሰባቸው ኮንሰርቶች እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል።




#Article 99: ሮቤል ተክለማርያም (123 words)


ሮቤል ተክለማርያም (1966 ዓ.ም. የተወለደ) በ1998 (2006) በዊንተር ኦሊምፒክስ በስካይ ኢትዮጵያን የወከለ ብቸኛና የመጀመሪያ ሰው ከመሆኑም በላይ በዊንተር ኦሊምፒክስ ጨዋታዎች አፍሪካን የወከለ መጀመርያው ስፖርተኛ ነው። 

ሮቤል በ9 አመቱ ወደ አሜሪካ ቢመጣም አገሩን በጣም ይወዳል። እስከዛሬ ድረስም አማርኛን አቀላጥፎ ይናገራል፡ 
ሮቤል በጣሊያኑ ኦሊምፒክ በውጭ አገር የሚኖሩት ኢትዮጵያውያን ባደረጉለት ከፍተኛ ማበረታት የአግሩ ባንዲራ ከሌሎች አገሮች ጎን እንዲውለበለብ እንዳስቻለው ተናግሮአል። ምንም እንክዋ ሮቤል ባደረጋቸው ውድድሮች(ተራራማና እና ሀገር አቋራጭ ስኪቲንግ) ውጤት ባያመስመዘግብም እንክዋ የኦሊምፒክ መግቢያ ሰዓት አስመዝግቦ የኢትዮጵያን ስም ማስጠራት በመቻሉ እስከ ዕድሜው መጨረሻ ኩራት እንደሚሰማው ተናግሮአል። በወቅቱ ፦ ሮቤል ለጋዜጤኞች ሲናገር «እኔ የተጨባጭ ሰው ነኝ። ዓላማዬ ይህ ኦሊምፒክ የሌሎችንም ኢትዮጵያውያን ዐይኖች እንዲከፍት ነው»  ብሎአል።   ሮቤል ተ/ማሪያም ባሁኑ ጊዜ በእሱና በታላቅ ወንድሙ በውስካንሰን የተቋቋመው ኢትዮጵያ ብሔራዊ ስካይ ፌዴሬሽንእስከ አገር ቤት ድረስ እውቅና እንዲያገኝ የበኩሉን ጥረት እያደረገ ነው። 
  




#Article 100: እሪያ (380 words)


እሪያ ወይም እፘ (ሮማይስጥ፦ Sus scrofa /ሱስ ስክሮፋ/፣ ግዕዝ፦ ሕንዚር) የዐሣማ ዓይነት የሆነ አውሬ ነው። ለማዳ ዐሣማ (S. scrofa domesticus) ከዚሁ ዝርያ መጣ።

የሚገኝባቸው አገሮች በማዕከለኛ አውሮጳ፣ በሜዲቴራኔያን አካባቢ፣ በስሜን አፍሪቃ ተራሮችም፣ በእስያ እስከ ኢንዶኔዝያ ድረስ ያጠቅልላል። ዛሬ በኢትዮጵያ ባይገኝም እሪያ በአፍሪቃ ውስጥ የሚኖር የከርከሮ (Phacochoerus africanus) ዘመድ ነው። በተጨማሪ ታላቅ የጫካ እሪያ (Hylochoerus meinertzhageni)  የሚባለው ጸጉራም የአሣማ አስተኔ አባል በጥቂት መጠን በኢትዮጵያ ውስጥ ይገኛል።  

እሪያዎች እስከ 200 ኪሎግራም ድረስ ክብደት ሊያድጉ እርዝመታቸውም እስከ 1.8 ሜትር ድረስ ሊሆኑ ይቻላል። አደጋ ቢደርስባቸው እጅግ ጥለኛዎች ሆነው በረጅም ጥርሳቸው ጉዳት ለማድረግ ችሎታ አላቸው። ነገር ግን ይህ እምባዛም ሲደረግ አብዛኛው ጊዜ እንስት እሪያ ግልገሎችዋን አስጠብቃ ለመከላከል ሲያስፈልጋት ብቻ ይሆናል። 

ከእሪያ እና ከዐሣማ መካከል ያለው ልዩነት እሪያ በጫካ ውስጥ የሚገኝ አውሬ ሲሆን ዐሣማ ግን ሰው ልጅ የለመደ ማለት ነው። ዐሳማዎችም አምልጠው ወደ ጫካ ሲመለሱ እንደገና እሪያዎች ቶሎ ይሆናሉ። የእሪያ ቆዳ ባቀመቀመ ጽጉር ይሸፈናል። አውራ እሪያ ብቻ እንደ ከርከሮ የረዠመ ጥርስ አለበት። 

የእሪያ መንጋ ቁጥር በተለመደ 20 እንስሶች ያህል ሲሆን ከ50 በላይ ያሉበት ስብሰባ ታይቶ ያውቃል። በተለመደ አንድ መንጋ 2 ወይም ሦስት እንስቶችና ግልገሎቻቸው ብቻ ናቸው። አውራዎቹ በብዛት ለብቻቸው እንጂ ከመፀው መርቢያ ወራት በስተቀር በመንጋው ውስጥ አይገኙም። የሚወልዱበት ወራት ጸደይ ሲሆን በተለመደ አምስት ግልገሎች ይወለዳሉ። እስከ 13 ድረስ ግን ሲቀፈቀፉ ታውቋል።

በብዛት እርያዎች የሌሊት እንስሶች ናቸው። ከማታ እስከ ንጋቱ ድረስ መኖ አሰብስበው በሌሊትም በመዓልትም ያርፋሉ። ምክንያቱም የሚያድኑዋቸው በተለይ በቀን የሚሄዱት ናቸው። እርያዎች ያገኙትን ማንኛውንም ነገር ያሕል ለምሳሌ ለውዝ፣ እንጆሪ፣ የበሰበሰ ሥጋ፣ ስሮች፣ ቆሻሻ፣ ነፍሳት፣ እንሽላሊት የመሰሉትን ትንንሽ ፍጡሮችና የአጋዘን ወይም የበግ ግልገሎች ሳይቀር ይበላሉ።

በአንዳንድ አገር ባሕል ስጋቸው ስለሚበላ ብቻ ሳይሆን ደግሞ በነሱ ምክንያት በሰብል ወይም በእርሻ የሚደረገውን ጉዳት ለመቀነስ ነው የሚያደኑዋቸው። 

በታሪካዊ ልማድ የእርያ ማደን በልዩ ጦር አይነት ይፈጸም ነበር። የተናደደው እሪያ የተወጋ ገላ በጦሩ በኩል በመግፋት አዳኙን እንዳያጠቃ በረጅም እጀታ ላይ ባሻገር የገጠመ አገዳ ክፍል ነበረበት። የአዳኞቹ ውሾች እንኳን የቆዳ ጥሩር ለብሰው ነበር። 

በፋርስ የእርያ አዳኝ ሌላ ዘዴ ይጠቀሙ ነበር። ከሕንድ አገር ዝሆን አምጥተው እርያዎቹን አባርረው በረግረግ ውስጥ ይከቡዋቸው ነበር። ይህን የመሰለ ትርዒት በገደል ድንጋይ ጎን ላይ በፋርስ ተቀርጾ ይገኛል።

በግሪክና በአይርላንድ አፈታሪክ ስለ እርያ ማደን ያሉ ተረቶች አሉ። በኖርስ አረመኔ እምነት አማልክታቸው ለማዳ እሪያዎች ነበሯቸው። እንዲሁም በሕንድ እምነት የቪሽኑ ሦስተኛ ትንሳኤ እሪያ ነበር። በፋርስም ስለጉብዝናው ይከበር ነበር። ደግሞ እርያ ለእንግሊዝ ንጉስ 3 ሪቻርድ ምልክት ነበር። እሪያ የእሪያም ራስ በአውሮጳ የጋሻ ስእል ስርዐት (አርማ) ብዙ ጊዜ ይታያሉ። 

ባንዳንድ አገሮች የእሪያ ጽጉር ባለፈው ዘመን ለጥርስ መፋቂያ ይጠቅም ነበር። ነገር ግን ይህ ለንጽሕና የተሻለው ነገር አልነበረም።




#Article 101: ዑዝበክኛ (230 words)


ዑዝበክኛ (O'zbek tili በላቲን ፊደል, Ўзбек тили በቂርሎስ ፊደል) በቱርክ ቋንቋዎች ቤተሠብ የሆነና የዑዝበክስታን መደበኛ ቋንቋ ነው። 18.5 ሚሊዮን ተናጋሪዎች እነርሱም የዑዝበክ ሕዝብ አሉት። በዚያ ላይ ከፋርስኛ ከዓረብኛና ከሩስኛ ከፍተኛ ተጽእኖ ተቀብሏል። 

ቢያንስ ከ600 ወይም ከ700 ዓ.ም. ጀምሮ በማእከለኛ እስያ በድሮ በተገኙ በሶግድያና ባክትርያ እና ቋራዝሚያ አገሮች የሕንዳዊ-ኢራናዊ ተናጋሪዎች በየጥቂቱ የቱርክኛ ተናጋሪዎች ተተኩ። በአካባቢው መጀመርያው የቱርክ ሥርወ መንግሥት ካራቃኒድ የተባለው ጎሣ ከ9ኛው እስከ 12ኛው ምእተ አመት ድረስ ገዝቶ ነበር። 

በ15ኛው እና 16ኛ ምእተ አመት የተስፋፋ የጫጋታይ ቋንቋ የዘመናዊ ዑዝበክ ወላጅ መሆኑ ይታመናል። ይህ ቋንቋ ከፋርስኛ እና ከዓረብኛ ብዙ ቃላት ተበድሮ ሲሆን ከ19ኛው ምዕተ አመት ጀምሮ ግን በተለይ ለመነጋገርያ እንጂ ለጽሕፈት እምባዛም አይጠቀም ነበር። 

ከ1913 ዓ.ም. አስቀድሞ ዑዝበክ እና ሣርት እንደ ተለያዩ የቱርክ ቀበሌኞች ይቆጠሩ ነበር። ከ1913 ወዲህ ግን የሶቭየት መንግሥት ሣርት የሚለው ቃል ስድብ ነውና እንግዲህ ሁለቱ ሕዝቦች ዑዝበክ ይባሉ ብሎ ዐዋጀ። ይሁንና ቀድሞ ሣርቶች ይባል የነበሩ የዑዝበክ ትውልዶች በታሪክ ዝገባ ላይ ከቶ አልነበሩም። አዲሱ የዑዝበክ ሬፑብሊክ በ1917 ዓ.ም. ሲፈጠር ደግሞ ብዙ ዑዝበኮች ምንም ደስ ባይሉም ይፋዊው ዑዝበክ የተባለው ቋንቋ የሣርቶች ቀበሌኛ ተደርጎ ነበር። ሁለቱ ቀበሌኞች እስከ ዛሬም ድረስ ጎን ለጎን በመኖር ላይ ይገኛሉ።

ከ1917 በፊት እንደ ሌሎቹ የማእከል እስያ ቋንቋዎች በአረብኛ ፊደል ይጻፍ ነበር። ከ1917 እስከ 1932 ዓ.ም. አዲሱ ይፋዊ ዑዝበክኛ ቋንቋ የተጻፈው በላቲን ፊደል ሲሆን ከዚያ በኋላ በስታሊን ዐዋጅ በቂርሎስ ፊደል ብቻ ሆኖ ነበር። ከ1984 ዓ.ም. ወዲህ እንደገና የላቲን ፊደል ቢፈቅድም ከቂርሎሱ ጋር አንድላይ በሰፊው በመጻፉ ላይ ይገኛል። በቻይና ውስጥ የኖሩት ዑዝበክ ሕዝቦች ግን የዓረብኛ ፊደል እስካሁን ይጠቅማቸዋል።




#Article 102: ቤሲክ (BASIC) (830 words)


በኮምፒውተር ፍርገማ (ፕሮግራሚንግ) ዘርፍ ቤሲክ (BASIC) የሚሰኘው የከፍተኛ ደረጃ ፍርገማ ቋንቋዎችን የሚያዝል ቤተሰብ ነው። የቃሉም ትርጉም 'መሰረታዊ' ወይም 'ቀላል' ቢሆን የተሰየመው ግን ከእንግሊዝኛው Beginner's All-purpose Symbolic Instruction Code አኅጽሮተ ቃል ነበረ። ይህም ማለት የጀማሪዎች ሙሉ-ምክንያት ምልክታዊ ትምህርታዊ ኮድ የሚያሕል ነው።

ቤሲክ መጀመሪያ በ1963 እ.ኤ.አ. ከኮምፒውተር ዘርፍ ውጭ የሚያጥኑ ተማሪዎች ኮምፒውተሮች ይጠቀሙ ዘንድ ጆን ጆርጅ ኬሜኒና ቶማስ ዩጂን ኩርትዝ አበጅተው በዳርትመስ ከሌጅ አቀረቡት። በጊዜው እያንዳንዱ ኮምፒውተር ሌሱ የሚሆን ሶፍትዌር መጻፍ ይጠይቅ በነበረበት ሁኔታ በሳይንስና በሂሳብ የተሰማሩ ሰዎች ብቻ የመስራት ዝንባሌ ነበሯቸው። ቤሲክ በሰማኒያዎቹ (እ.ኤ.አ.) በቤት ኮምፒውተሮች የተሰራጨ ሲሆን፥ ዛሬም በአንዳንድ በጣም በተለወጡ ቋንቋዎች አማካኝነት ተጠቃሚዎች አሉት።

ክ1960ዎቹ (እ.ኤ.አ.) አመታት መሃክል በፊት ኮምፒተሮች በጣም ውድና ለተወሰኑ አላማ ባላችው ስራሞች ላይ የተወሰኑ መሳሪያዎች ነበሩ። ቀላል የባች ሂደቶች (batch processing) አይነቶችን በመጥቀም በአንድ ጊዜ አንድ ስራ ብቻ ይሰሩ ነበር። በ1960ዎቹ ውስጥ የኮምፒውትር ዋጋ የትንንሽ ድርጅቶት የግዢ አቅም እስከሚፈቅደው ድረስ አሽቆለቆል። ፍትነታቸውም ክመጨመሩ የተነሳ የለስሯ የሚቀመጡበት ጊዜ ይበዛ ጀመር። የዘመኑ የፕሮግራም ቋንቋዎች አሰራር ልክ እንደ ማሽኖቹ ለተውሰኑ ሰራዎች የታለሙ (እንደ ሳይንስ ነቅ ፎርሙላዎች ወይም የጽሁፍ ሰሌዳዎች) ነበሩ። እነዚህ ባንድ ስራ የተወሰኑ ማሽኖች በመወደዳቸው፥ የቋንቋዎቹ የአሰራር ፍጥነት ከሁሉም ግጽታዎች የላቀ ወሳኝነት ነበረው። ባብዛኛው እነዚህን ቋንቋዎች መጠቀም አስቸጋሪና ሥርአት አገባችው (syntax) በጣም የተለያየ ነበር።

በዚህ ጊዜ ነው የጊዜ መጋራት (time sharing) ሃሳብ ተቀባይነት እያገኘ የመጣው። በዚህ ሲስተም ስር የዋና ማሽን የስራ አቅም ይከፋፈልና እያንዳንዱ ተጠቃሚ በየተራው አነስተኛ ጊዜ ይሰጠዋል። እነዚህ ማሽኖች በቂ ፍጥነት ስለነበራቸው አብዛኛው ተጠቃሚ ለራሱ አንድ ማሽን የተመደበለት ያስመስሉት ነበር። በቴዎሪ ደረጃ የጊዜ መጋሯት ለኮምፒውትር የሚወጣውን ወጪ በእጭጉ ቅንሰዋል:: በመቶ ለሚቆጠሩ ተጠቃሚዎች አንድ ማሺን ይበቃ ስለነበር።
 

...

...

...

የቤሲክ አረፍተ የመስመር መቀጠያ ፊደል ከሌለ መስመር መጨረሻ ላይ ያልቃሉ። በጣም አነስተኛ ቤሲክ LET, PRINT, IF and GOTO የሚሉት ትእዛዞች ይበቁታል::

የመስመር ቁጥሮች የቤት ኮምፒውተር ቤሲክን ከሚለዩ ገጽታዎች አንዱ ነው። አንዳንድ ቆይተው የመጡ የቤሲክ ተርጓሚዎች (interpreters) አምበሮ የሚመጡ RENUMBER የሚባል መስመር ቆጣሪ ትእዛዝ ነበራችው ።

አንዳንድ ዘምዝናዊ ባሲኮች የመስመር ቁጥርን ትተው አብዛኛው በሌሎች ቋንቋዎች (እንደ ሲ ና ፓስካል) የሚታወቁትን የመዝገብና (data) የመቆጣጠሪያ (control) አቀማመጥን አስገብተዋል። (አንዳንድ በመስመር ቁጥር ላይ የተመሰረቱም ቋንቋዎች እነዚህን አቀማመጦች ማስገባታችውን መመዝገብ ያሻል።)

በቅርብ የተሰሩ እንደ ቪሱአል ቤሲክ (Visual Basic) የቤሲክ ተዛማጆች እቃ አዘል ገጽታዎችን እንደ For Each...Loop ያሉ አቀማመጦችን ሰብስቦችና ተርታዎችን በጥምዝ (loop) ለመፈተሽ ቪሱአል ቤሲክ 4 አንስቶ ሲያስገቡ ብእቃ አዘለ ፍርግምና ውርስ ተብሎ የሚታወቀውን አሰራር በመቅረብ አስገብተዋል። የማህደረ እውስታ (memory) አስተዳደር ዘዴው ካብዛኛው የተደራጁ ቋንቋዎች የቀለለ ነው። ይህም ሊሆን የቻለው ቋንቋው
garbage collection ወይም የቆሻሻ ሰብሳቢ ይዞ ስለሚመጣ ነው::
 
  

ቤሲክ እንደ ሲ የውጭ ቤተ መጻህፍት (external library) የለውም። የቋንቋው ተርጓሚ (interpreter) ሰፊ ቤተ መጻህፍትና አብረውት የተገነቡ ፕሮሲጀሮች (procedures) ይይዛል: ለነዚህ ፕሮሲጀሮች አንድ ፈርጋሚ ሙያውን ለመማርም ሆነ ቀለል ያሉ ፕሮግራሞችን ለመጻፍ የሚያስፈልጉትን አብዛኞቹን መሳሪያዎች (የሂሳብ ተግባሯትን፥ የፊደል ክር-string, የማስገቢያና የማሶጪያ መስኮት፥ የስዕልና የመዘገብ መሳሪያ) ያካትታል።
አንዳንድ የቤሲክ ቤተሰብ አባል ቋንቋዎች ፈርጋሚው የራሱን ፕሮሲጀሮች እንዲጽፍ አይፈቅዱም:: ፈርጋሚው ከአንድ ቅርንጫፍ ወደሌላ ለመዘዋወር በዛት GOTOን በመጠቀም ፕሮግራሙን ይጽፋል። የዚህ ውጤት ደግሞ ለአንባቢ እጅግ አስቸጋሪ የሆነ የፕሮግራም ምንጭ (source)፥ በተለምዶ እንደ ፓስታ የተወሳሰበ ወይም spagetti code፥ አይነት ይሆናል። GOSUB የቅርንጫፍ ዝውውሩን የሚያደርገው ወደ ንዑስ ክንውኖች (አነስተኛ የፕሮግራም አካሎች) ሲሆን ባብዛኛው ያለግቤት (parameters)ና ያለሰፈር ተለዋጭ (local variable) ነው። ዘመናዊ የቤሲክ ስሪቶች እንደ ሚክሮሶፍት ኪክ ቤሲክ ሙሉ ንዑስ ክንውኖችንና (subroutines) ተግባራትን (functions) አስገብተዋል። ይህ ቤሲክ ከሌሎች ቋንቋዎች የሚለይበት አንዱ ገጽታው ነው። ቤሲክ፥ እንደ ፓስካል፥ መልስ በማይጠበቅባቸው ፕሮሴጀሮችና (ንዑስ ክንውኖች የምንላቸው) መልስ በሚሰጡት (ተግባራት) መሃከል ልዩነት ያደርጋል። ሌሎች እንደ ሁሉንም በተግባራት ስያሜ (አንዳንዶቹን ባለ ባዶ መልስ በማለት) ለዩነትን አያደርጉም።

ቤሲክ ለፊደል ክሮች (strings) ስሪ የሚያገለግሉ ጥሩ ተግባራት ያለው ቋንቋ እንደሆነ ይታወቃል። የቀድሞው የዚሁ ቤተሰብ ቋንቋዎች እንደ (LEFT$, MID$, RIGHT$) የመሳሰሉት መሰረታዊ ተግባራት በማቀፍ የፊደል ክሮችን የሚመለከቱትን ስራዎች ያቃልላሉ። የፊደል ክሮች የለት ተለት ስራዎች ላይ በተደጋጋሚ ሰላሚያጋጥሙ ከሌሎች የዘመኑ ቋንቋዎች በዚህ ረገድ ብልጫ አሳይቷል።

የቀድሞው የዳርትሙንት ቤሲክ ለቁጥርና ለፊደል ክር አይነቶችን ብቻ ድጋፍ ይሰጥ ነበር። የሙሉ ቁጥሮች (integers) አይነቶች አልነበሩም። ቁጥሮች በሙሉ ባለነጥብ (floating points) ነበሩ። የፊደል ክሮች አለ ተለዋዋጭ ርዝመት ነበሩ። ቤሲክ የፊደል ክርም ሆነ የቁጥር ተርታዎችን (arrays) እንዲሁ ባለሁለት ማአዘን ተርታዎችን የሚደግፍ ወይም የሚይዝ ቋንቋ ነበር።

ማንኛው ዘምዝናዊ የቤሲክ ቤተሰብ ቋንቋ ቢያንስ ቁጥሮችንና የፊደል ክሮችን ይይዛል። 
...

ጀማሪ የቤሲክ ፈርጋሚዎች የቤት ኮምፒውትሯቸው ላይ የሚጀምሩት በ ከርኒጋንና ሪቺ አማካኝነት እውቅና ያገኘውን ሰላም አለም ፍርግም አይደለም። ይልቁኑ የሚቀጥለውን የማያባራ ጥምዝ የሚመስል ነው።

 10 PRINT BOB IS AWESOME!
 20 GOTO 10

ክላሲክ ወይም የቀድሞው ቤሲክ፤ ይህ ምሳሌ በስራአት የተደራጀ መሆኑን GOTO ን መጠቀም የግድ ወደተመሰቃቀለ የፍርግም እንደማያመሯ ያሳያል።

 10 INPUT What is your name: ; U$
  20 PRINT Hello ; U$
  30 REM
  40 INPUT How many stars do you want: ; N
  50 S$ = 
  60 FOR I = 1 TO N
  70 S$ = S$ + *
  80 NEXT I
  90 PRINT S$
  100 REM
  110 INPUT Do you want more stars? ; A$
  120 IF LEN(A$) = 0 THEN GOTO 110
  130 A$ = LEFT$(A$, 1)
  140 IF (A$ = Y) OR (A$ = y) THEN GOTO 40
  150 PRINT Goodbye ;
  160 FOR I = 1 TO 200
  170 PRINT U$;  ;
  180 NEXT I
  190 PRINT

 INPUT What is your name; UserName$
 PRINT Hello ; UserName$
 DO
    INPUT How many stars do you want; NumStars
    Stars$ = 
    Stars$ = REPEAT$(*, NumStars)   '  
    Answer$ = LEFT$(Answer$, 1)
 LOOP WHILE  UCASE$(Answer$) = Y
 PRINT Goodbye ;
 FOR I = 1 TO 200
    PRINT UserName$;  ;
 NEXT I
 PRINT




#Article 103: የኮርያ ጦርነት (2322 words)


የኮርያ ጦርነት በኮርያ ከሰኔ 18 1942 እስከ ኃምሌ 20 1945 የተዋገ ጦርነት ነበር።

የኮሪያ ዘማቾች ትውስታ

ሬሳ እንኳ አልተማረከብንም”   “አለመማረክ የጀግንነት ጉዳይ አይደለም”

በአምስት ዙር ኮርያ ከዘመቱት 6037 ኢትዮጵያውያን መካከል 122ቱ በጦርነቱ ሞተዋል፡፡ አንዳቸውም አልተማረኩም ሳይማረኩ ግዳጃቸውን ፈጽመው ከተመለሱት  350ው የዛሬ 20 ዓመት የኢትዮጵያ ኮርያ ዘማቾች ማህበርን መስርተው ሰሞኑን የዘመቻውን 61ኛ ዓመት አክብረዋል፡፡ የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ መልካሙ ተክሌ ከአስር አለቃ ዘነበወርቅ በላይነህ እና ከየኢትዮጵያ ኮሪያ ዘማቾች ማህበር ፕሬዝደንት ኮሎኔል መለሰ ተሰማ ጋር አጭር ቃለምልልስ አድርጓል፡፡

ለኮሪያ ዘመቻ እንዴት ነው የተመረጡት?

በመሠረቱ የገበሬ ልጅ ነኝ፡፡ ለኮሪያ ዘመቻ ተብዬ አይደለም ወደ ወታደራዊ ዘመቻ የገባሁት፡፡ በጣልያን ወረራ ወቅት በሕፃንነቴ ከአባቴ ጋር ጫካ ለጫካ ተንከራትቻለሁ፡፡ በ1939 ዓ.ም ወታደርነት ተቀጠርኩ፡፡ የተወለድኩት በ1922 ዓ.ም ነው፡፡ ወታደር በሆንኩ በአምስት ወይ በስድስት ዓመት ኮርያ ዘመትኩ፡፡ እውነቱን ለመናገር ስዘምት ማንበብና መፃፍ አልችልም ነበር፡፡

አሁንም ድረስ?

አይደለም፡፡ እዚያው ኮርያ እያለሁ ዘመድ ደብዳቤ ፃፈልኝ፡፡ ሃምሳ አለቃ ንጉሤ ወልደሚካኤል የሚባል ጓደኛዬን ፃፍልኝ ስለው ሂድ አልጽፍም አለኝ፡፡ ንዴት ያዘኝና ወንጌሌ ቆስጣ ለሚባሉ አለቃዬ ጋዜጣ ስጡኝና ፊደል ልማርበት አልኳቸው፡፡ ፊደል ጭምር ሰጡኝ፡፡ በዚያው በጓደኞቼ አጋዥነት ተለማምጄ ስሜን መፃፍ ቻልኩ፡፡ በሦስት ወር ደብዳቤ ለቤተሰብ ጽፌ ደብዳቤዬ እንደደረሳቸው ቤተሰቦቼ ሌላ ደብዳቤ ላኩልኝ፡፡ ጥሩ አለቆች ስለነበሩኝም እዚህ ስመለስ ጫካ ወስደው ጥቁር ሰሌዳ በማሸከም ያስተምሩን ነበር፡፡ የማታ ትምህርትም ገብቼ ነበር፡፡ ዘመቻውን ከሦስተኛው ቃኘው ጋር በኮሎኔል ወልደዮሐንስ ሽታ አዝማችነት ነበር የዘመትኩት፡፡

እዚያ ሲደርሱ ከነበረው ምን ያስታውሳሉ?

የመጀመሪያውን ቅኝት ስንወጣ በእኔ መቶ አዛዥነት ነበር፡፡ የመጀመርያው ተኩስ ሞትና መቁሰልም የደረሰው በእኛ ላይ ነው፡፡ የዘመትነው በግንቦት ወር 1945 ዓ.ም ነበር፡፡ የመጀመሪያው ቃኘው የዘመተው በ1943 ዓ.ም ነበር፡፡ አንድ ሞቶብን ሁለት ቆሰሉ፡፡ አንደኛው ቁስለኛ እጁ ተቆረጠ፡፡ የሞተውንና ቁስለኞቹን ይዘን ወደ ወገን ጦር ተቀላቀልን፡፡

ሁለተኛው የጦር ግንባር ከፍተኛው የቲቮ ተራራ ነው፡፡ እዚያ ላይ በመከላከል ላይ ነበርን፡፡ ጓደኛዬ እዚህ ውስጥ አለ (በጦርነቱ የተሰውትን ሃውልት እያሳዩ) በዳኔ ነገዎ ይባላል፡፡ መከላከያ ውስጥ አንድ ላይ ነበርን፡፡ ባንከር አለ፡፡ ድንገት ቢተኮስ እዚያ እንግባ ስለው እምቢ አለ፡፡ እየጐተትኩት እያለሁ ጥይት ተተኮሰ፡፡ እሱን በጣጥሶ ሲጥል እኔን አፈር ከአንገት በታች ቀበረኝ፡፡ ጥይቱ እያበራ ሲመጣ እኔ ዘልዬ ስወድቅ እሱን በጣጠሰው፡፡ ከ45 ደቂቃ ቁፋሮ በኋላ ነው ያወጡኝ፡፡ ከዚያ የጓደኛዬን ሰውነት በዳበሳ ፈልገን በራሱ ሸራ አድርገን ለመቃብር አበቃነው፡፡ ጦርነቱ ባይቆም ያ ሁሉ ሠራዊት ያልቅ ነበር፡፡

ግን አንድም አልተማረከም?

አንድም አልተማረከም፡፡ ዘማቹ ይፋቀራል፡፡ ይከባበራል፡፡ ጓደኛህ ቢሞት እንኳ ሬሳውን ጥለህ አትሄድም፡፡ ሬሳ እንኳ አልተማረከብንም፡፡ አመት ከሰባት ወር እዚያ ቆይቻለሁ፡፡ ጦርነቱም የቆመው እዚያ እያለን ነው፡፡ ከዚያም በኋላ በየቀጠናው ጥበቃ እናደርግ ነበር፡፡

አሁን በእርቁ ለሰሜን ኮርያ ተሰጠ እንጂ ከ300 ኪሎ ሜትር በላይ ወደ ሰሜን ዘልቀናል፡፡ ብዙ ምሽግ መቆፈራችን ነው አንድም እዚያ ብዙ ያቆየን፡፡ ሀገሩም የራሱን ጦር እስኪያደራጅ መቆየቱ የግድ ነበር፡፡ ነሐሴ 29/1946 ዓ.ም ተመልሰን አዲስ አበባ ገባን፡፡ ሌሎቹ የተማረኩት ምን አልባት በምቾት ብቻ መኖር ስለለመዱ ይመስለኛል፡፡ እኔ ከወገኔ ተለይቼ እጄን የምሰጥበት ምክንያት የለም፡፡ ሄጄ ማን እጅ ነው የምገባው? ጠላት እጅ፡፡ ስም ያለው ሞት መሞት እንጂ ሁለት ሞት አልሞትም፡፡

የመጀመሪያው ቃኘው ሻለቃ ሲሄድ እርስዎ የት ነበሩ?

ሠራዊት ውስጥ ነበርኩ፤ ሐረር የልዑል መኮንን ቤተመንግስት ጥበቃ ላይ ነበርን፡፡ በ1944 ወደ አዲስ አበባ ተዛውረን መጣን፡፡ ከዚያ ተመልምዬ ነው ወደ ኮርያ ለመሄድ የበቃሁት፡፡ እንዴት እንደተመለመልን አላውቅም፡፡ ይኼን የሚያውቁት መልማዮቹ ናቸው፡፡ የታዘዘውን ፈፃሚ ጠንካራ ሞራል ያለው ሠራዊት ተመርጧል፡፡

ከማን ጋር የምትዋጉት? የውጊያ ብቃታቸውስ ምን ይመስላል?

እነዚያ ሰሜን ኮርያ፣ ሶቭየት ሕብረት፣ ቻይናና ተባባሪዎቻቸው ናቸው፡፡ ብርቱ ስልት አላቸው፡፡ በጨበጣ ውጊያ የወደቀልህ መስሎ መትቶ ይጥልሃል፡፡ የእኛዎቹ በተለይ አሜሪካኖች እጅግ ዘመናዊ የጦር መሣሪያ ታንክ፣ መድፍ… ታንክ ላይ የሚጠመደው ጀነራል መድፋቸውማ የተለየ ነው፡፡ ይኼ መድፍ በጣም በርቀት መምታት የሚችል ነው፡፡ እዚህ ሲተኮስ እዚያ ፈንድቶ ርቀቱን ይጨምራል፡፡ አውሮፕላኖችም አሉት - የኛ ወገን፡፡ አንድ ጦር ከተከበበ በአየር ይመታል አካባቢው፡፡ በዚህ መልኩ 70ሺህ ያህል የተቀናቃኝ ጦር ተደምስሷል፡፡ ከእኛ ግን 18 ብቻ ነው የሞተው፤ ተከቦ ከነበረው፡፡

የቋንቋና የባህል ችግር አልገጠማችሁም?

እኛ ከማንም ጋር ግንኙነት የለንም፡፡ ግንኙነት ያለው ከዋናው መምሪያ ነው፡፡ አገናኝ መኮንኖች እዚያ የተባለውን ይነግሩናል እንጂ ከሕዝብ ጋር በፍፁም አንገናኝም፡፡ ስንገናኝም በጥቅሻ ነው፡፡ ያለነው እልም ያለ ገጠር ውስጥ በመሆኑ ከተማ ወጥቶ በእረፍት ጊዜ መዝናናት የሚባል ነገር የለም፡፡ ብንታመም ሻምበላችን ውስጥ ሕክምና አለ፡፡ አንድ ጊዜ ታምሜ ነበር፡፡ እዚያ ታክሜ ከአቅም በላይ ስለሆነባቸው ሌላ ሀኪም ቤት ተላኩ፤ ወዲያውኑ በሄሊኮፕተር ፑዛን ከተማ ሄድኩ፡፡ ለ20 ቀን ያህል ታክሜ ተመልሻለሁ፡፡ ሕክምናቸው በጣም ጥሩ ነው፡፡

በዚህ አጋጣሚ ከዚያ ሀገር ሴት ጋር በፍቅር መውደቅ ጋብቻ እና የመሳሰሉት አይኖሩም?

ጋብቻ ሳይሆን ከጋብቻ ውጪ ከዚያ ሀገር ሴቶች ልጅ የወለዱ ወታደሮቻችን አሉ፤ ከኮሪያ ሳይሆን ከጃፓን ፍቃድ ስንወጣ ጃፓን ነበር የምንሄደው፡፡ ፍቅር ይዟቸው ሲለያዩ የተላቀሱም አሉ፡፡

እርስዎስ?

እንዲህ አይነት ጣጣ ውስጥ አልገባሁም፡፡ ጃፓን ፍቃድ ሄጃለሁ፡፡ ግን ልጅነትም አለ፡፡ ሀኪም ቤት ውስጥ በተኛሁ ጊዜ ግን አንድ ችግር ገጥሞኛል፡፡

ምን አይነት ችግር?

አንዲት ነጭ አሜከካዊት ሻምበል የሕክምና ባለሙያ ነበረች፡፡ ፑዛን ጋውን ለብሳ መጣች፡፡ አልኮል የፈሰሰበት ሙቅ ውሃ እና ፎጣ ይዛ ገላህን ልጠበው ልሸው አለችኝ፡፡ በፍፁም እንዴት ተደርጐ አልኳት፡፡ በኋላ አሁን ስሙን የረሳሁት አስተርጓሚ ጠራች፡፡ ለምን እምቢ ትላለህ ገላህን ልጠብህ እኮ ነው ያለችህ አለኝ፡፡

ከዚህ ስሄድ እንኳን ላገባ ሴት አላውቅም፡፡ ራሴ መታጠብ ስችል ሴት እንዴት ያጥበኛል አልኩ፡፡ ሳቀብኝና ነግሯት ለኔ ችግር የለውም አለኝ፡፡ በኋላ ስታጥበኝ የሷንም ፍላጐት በማየቴ ሰውነቴ ጋለ፤ ፍላጐቴ ተነሳሳ፡፡ ይኼኔ “ኧረ ባክህ” ብዬ ስነግረው ሳቀና ነገራት፡፡ ችግር የለውም ብላ አንድም የሰውነቴ ክፍል ሳይቀር አገላብጣ አጠበችኝ፡፡ ትንሽ ቆይታ ልብሷን ለውጣ ለእኔም ልብስ ይዛ መጣች፡፡ ይዛኝ ሄደች፡፡ የዚያኑ እለት ግንኙነት አደረግን፡፡

የመጀመሪያዬ እሱ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ግን ለምን እንደሆነ ጠላኋት፡፡ ተመልሼ ሀኪም ቤት ተኛሁ፡፡ ሳያት ሁሉ እሸፋፈን ነበር፤ ከጥላቻዬ የተነሳ፡፡ ሳልቆይ ለአለቃዬ ለአስተርጓሚው ነገርኩት፡፡ ድኛለሁ ይላል ይውጣ ተባለ፡፡ እሷ አይወጣም ብላ እንደገና ስምንት ቀን አቆየችኝ፡፡ ከአንዴ በላይ አብረን አልወጣንም፤ እምቢ አልኩ፡፡ በዚሁ መንስኤ ለ15 ቀን ታምሜአለሁ፡፡

ሕክምና ሳይጨርሱ ነው ከሻምበሏ ጋር የወጣችሁት?

ሕክምናማ ጨርሼ እኮ ነው መታጠቡ የመጣው፡፡

ጥሬ ስጋ ስትበሉ የውጭ ዜጐች አይተው ይሸሹዋችሁ ነበር የሚባለው እውነት ነው?

ይኼንን እኔም እንዳንተው ነው የሰማሁት፡፡ ይህንን አደረገ የተባለው ሻለቃ ተፈራ ወልደትንሣኤ ነው ይባላል፡፡ ከመጀመሪያ ዙር ዘማቾች፡፡ እንደዘመተ መንጉሱ በማቀዝቀዣ ታሽጐ ቁርጥ ሥጋ ይላካል - ለጦሩ ንጉሱ የላኩላችሁን ተመገቡ ተብሎ ምግብ ቤት (ሚንስ ቤት) ይመገባሉ፡፡ የጦሩ አባላት ተመግበው የተረፈውን የመጀመሪያ ሕክምና እርዳታ የምንሰጥበት እቃ አለ፡፡ ያን ሥጋ በላስቲክ ጠቅልሎ ይዟል መሠለኝ፡፡ በልቶ ሲጠግብ ጦርነት ይታዘዛል፡፡

ከውጊያ በኋላ ድል አድርገው ሲጨረሱ በድካምና በረሃብ ቁጭ ይላሉ፡፡ በያዘው ሴንጢ እየቆረጠ ያንን ሥጋ ይበላል፡፡ ይህንን አንዲት ቻይናዊት ፈርታ ተደብቃ አይታዋለች፡፡ ደንግጣ ሰው የሚበሉ እንግዳ ሰዎች መጡ ብላ አስወራች፡፡ ከዚያን ወዲህ ነው እንዲህ መወራት የጀመረው፡፡ ሰው በላ መጣ አሉን፡፡

እርስዎ በስንት የጦር ግንባሮት ተሳትፈዋል?

ሁለት ናቸው፡፡ አንደኛው ዮክ ተራራ የጦር ግንባር ነው፡፡ ሁለተኛው ችቦ ነው፡፡ ከነዚህ ውጪ የለም፡፡

በጣም የሚያስታውሱት የኢትዮጵያም ሆነ የሌላ ሀገር ወታደር?

አንድ ግዳጅ ላይ አንድ የመቶ አዛዥ ማንደፍሮ የማነህ ይባላሉ፡፡ ቅኝት ይወጣሉ፡፡ የኛ ሰራዊት ቅኝት ከመውጣቱ በፊት አሜሪካ የማረከቻቸውን የቻይና ወታደሮች አሰልጥና በስለላ ታሰማራ ነበር፡፡ ለእነሱና ለእኛ የተሰጠው ቦታ የተለያየ ነው፡፡ ለመቶ አለቃው ተነግሯል፡፡ ቻይናዎቹ የኛን ይዞታ ይዘው ይጠብቋቸዋል፡፡

የኛዎቹ ሊይዙ ሲሉ ተኩስ ከፈቱባቸው፡፡ የሞቱት ሞቱ፡፡ ቁስለኞችን ውሰዱ ተባልን፡፡ በዚያን ጊዜ እኔ ተመለመልኩና ሂድ ቁስለኛ አምጣ ተብዬ ተላኩኝ፡፡ በሸክም ነው የምናመጣው፤ ያውም ተራራ እና ጨለማ ነው፡፡ ተሸክሜ ሳንጃ ሰክቻለሁ፣ ጠመንጃዬ እንደጎረሰ ነው፡፡ ተሸክሜ ዳገት እየወጣሁ ትንሽ ሲቀረን አንሸራቶኝ ስወድቅ ሰውየውም ወደቀ፡፡ እኔን አጥፍቶ ሊያመልጥ ሲያስብ ቻይናዊው ቀና ብሎ ይቃኛል፣ ቶሎ ብዬ ርምጃ ወሰድኩ፡፡

አሁን ኑሮ እንዴት ነዉ?

የቀበሌ ቤት ተከራይቼ ነው የምኖረው፡፡ እዚህ የኢትዮጵያ ኮርያ ዘማቾች ማህበር በጥበቃ ሰራተኝነት አገለግላለሁ፡፡ ፍላጎት ያለው ያገልግል ሲባል ተቀጠርኩ፡፡ ከምኖርባት ሽሮሜዳ አፍንጮ በር በእግር መንቀሳቀሱን ወድጄዋለሁ፡፡ ደመወዙ ግን  አይወራም አይጠቅምም፡፡

ዘጠኝ ልጆች አሉኝ፡፡ ሦስቱ አግብተዋል፡፡ ሌሎቹ ገና ናቸው፡፡ አንደኛው ልዴ መለሰ ዘነበወርቅ ይባላል ደቡብ ኮርያ ለትምህርት ቢሄድም ከእኔ ጋር እንዳለ ነው የሚቆጠረው፡፡ 249 ብር ነበር የሚከፈለኝ በብዙ ጭቅጭቅ ለቀን እንሄዳለን ስንል ነው መሠለኝ 294 ብር ሆኗል፡፡ የጡረታ አበሉ 310 ብር ነው፡፡ በፊት ደመወዛችን 15 ብር ነበር፡፡ ያውም አምስቱ ብር ተያዥ ነው፡፡ 10 ብር እንቀበላለን፡፡ ሦስት ኪሎ ስንዴም ይሰፈርልናል፡፡ ቤተሰብና ትዳር ስለሌለን ብር ከሃምሳ ሸጠናት ከሰልና ሳሙና እንገዛበት ነበር፡፡

ትዳርስ እንዴት መሠረቱ?

በ1957 ዓ.ም በ32 ዓመቴ ነው ያገባሁት፡፡ እናት አባቴ ናቸው የዳሩኝ፡፡ ከሰራዊቱ ወጥቼ በሲቪል ስራ ላይ ነበርኩ - አየር መንገድ ውስጥ፡፡ አባቴን ከሀገር መውጣቴ ካልቀረ አልመለሥም ዳረኝ ስለው እሺ አለ፡፡ አግኝቼልሃለሁና ናና እያት አለኝ፤ ሰሜን ሸዋ ደብረሊባኖስ አካባቢ ነው የቤተሰቦቼ ቤት፤ ሄድኩ፡፡

አይንህ አይኔ፣ አንደበትህ አንደበቴ ነው፤ ማየቴ ምን ጥቅምና ትርፍ አለው፤ አንተ ባየኻት እስማማለሁ አልኩት፡፡ ያየሁአት የሰርጉ እለት ነው፡፡ የሰርጉ እለት ስገባ ሴቶቹ በሀገራችን ባህል መሠረት ተሸፋፍነዋል፡፡ እናት አባቷንም አላውቅም፡፡ ወላጅ አባቷ ማነው አልኩ? እኔ ነኝ አሉ፡፡

እርስዎ ነዎት?  ስል አዎ አሉ፡፡ ያውቁኛል ስል ኧረ ልጄ አላውቅህም አሉኝ፡፡ ዘነበወርቅ በላይነህ እባላለሁ አልኳቸው፡፡ አንተ ነህ ሲሉኝ አዎ … ልጅም ፈቅደውልኛል ሲላቸው አዎ አሉኝ፡፡ በሉ ስለማላውቃት ይስጡኝ አልኳቸው፡፡

ገልጠው ይቺ ነች ልጄ አሉ፡፡ ተሞሽራ ከተቀመጠችበት፡፡ ወ/ሮ አሥራት አለሙ፣ የልጆቼን እናት፣ ባለቤቴን እንደዚህ ነው ያገባኋት፡፡ አገር ቤት ተጋባንና አዲስ አበባ ሽሮሜዳ መኖር ጀመርን፡፡

ማህበራችሁ እንዴት ተመሠረተ?

ማህበሩ የተመሠረተው በ1994 ዓ.ም ነው፡፡ ከዚያ በፊት በነበሩት መንግስታት ድጋፍ ማጣት ማህበሩ አልተቋቋመም ነበር፡፡ በሁለት ትልልቅ ምክንያቶች ነው የተቋቋመው፡፡ አንደኛው:- ሀገራችን ኢትዮጵያ በዘመኑ ከሰለጠኑት መንግስታት አንፃር ምን ቦታ እንደነበራት ለማሳየት ነው፡፡

ሌላው ሀገራችን የሰጠችንን መወጣታችንንና ታሪክ መስራታችንን ለትውልድ ለማስተላለፍ ነው፡፡

ኮርያ ለመዝመት እንዴት ተመረጡ፣ እድሜዎ ስንት ነው?

እንዴት እንደተመረጥን አናውቀውም፡፡ መኮንኖች ስለሆንን ማን ይሂድ ማን ይቅር የሚለውን የሚያውቁት አለቆቻችን ናቸው፡፡ ሚሊተሪ አካዳሚ ስንገባ ወታደር እንደምንሆን እናውቃለን፡፡ አካዳሚው የንጉሠ ነገሥቱ የክብር ዘበኛ ጦር አካዳሚ ነው፡፡ ቪላ ሳህለሥላሴ ይባላል የሠለጠንበት ቦታ፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ ነው፡፡ ሦስተኛ ኮርሰኞች ነን፡፡ ትምህርታችንን ከሌሎቹ በሰባት ወር ቀድመን ነው የፈፀምነው፡፡ በዚያን ጊዜ የነበረው ከፍተኛ ክፍል ስምንተኛ ስለነበር ከስምንተኛ ክፍል ነው የገባሁት፡፡ የጦር አካዳሚውን ትምህርት እንደጨረስን የኮርያ ዘመቻ ወሬ ተሰማ፡፡ እኛ ሚያዝያ 3 ተመርቀን በማግስቱ ሚያዝያ 4 ጓደኞቻችን ዘመቱ፤ በመጀመሪያ ቃኘው፡፡ እኔ በሁለተኛው ቃኘው የሄድኩት በ1944 ዓ.ም ነው፡፡

ስትሄዱ እንዴት ነበረ ጉዞው?

ወደ ለገሃር ማክ በሚባል ወታደራዊ መኪና ሄድን - ከጃንሜዳ፡፡ ከዚያ በባቡር ወደ ጅቡቲ፤ ከዚያም በመርከብ ደቡብ ኮርያ፡፡  ደቡባዊ የወደብ ከተማ የሆነችው ፑዛን ከሃያ ሁለት ቀን የባህር ላይ ጉዞ በኋላ ገባን፡፡ ከዚያም እንደገና በመኪና ተሳፍረን እዚያው አካባቢ ከአየር ፀባዩ እና ከጦር መሣሪያው ጋር ተለማመድን፡፡ በሌላ ባቡር ሁለት ቀን ተጉዘን ገባን፡፡ እንደገና በአሜሪካ መኪና ተጭነን ግንባር ደረስን፡፡ ያኔ ኮርያ ስደርስ የ21 ዓመት ከሰባት ወር ልጅ ነበርኩ፡፡

ሚስት ሳያገቡ ነበር የሄዱት?

ኡ…እንኳን ላገባ የሴት ጓደኛ አልነበረኝም፡፡ እንደዛሬው ልጆች አልነበርንም፡፡

እዚያስ አንዷን ደቡብ ኮርያዊት የመተዋወቅ ነገር?

የሄድነው ለጦርነት ነው እንጂ ለሽርሽር አይደለም፡፡ ከነሱ ጋር የምንገናኘው በሦስት ወር አንድ ጊዜ ከጦር ግንባር እረፍት ለማድረግ ስንመለስ ነው፡፡ በዚያን ጊዜ አቅራቢያችን ወዳሉ ከተሞች እንሄዳለን፤ ጃፓንም ድረስ፡፡ በእንደዚህ አይነት አጋጣሚ ተጠቃቅሶ መግባባትና መጫወት አይቀርም፡፡ ጦርነት ውስጥ ሆነህ እጮኛ ለመያዝ ሚስት ለማግባት መመኘቱ ጥሩ ነው፡፡ እድሉ ግን ይገኛል ወይ ነው ጥያቄው፡፡ መቀባበጡ ግን እድሜአችን ስለነበር አልቀረም፡፡

እንዴት ትግባቡ ነበር?

በጫወታ ለመግባባት እኮ ምልክት ይበቃል፡፡ ለእረፍት ስንመለስ ጦር ሜዳ መኖራችንንም እንረሳዋለን፡፡ ምክንያቱም ዘመናዊ አቅርቦት ነበር፡፡ ከመከላከያ መስመር እንኳ ከቻልክ በየአምስቱ ቀን ሻወር አለ፡፡ እዚያ እየታጠብክ የለበስከውን ጥለህ አዲስ ልብስ ትለብሳለህ፡፡

ተግባብቶ ትዳር የያዘ ወይ ፍቅረኛ የነበረውና የወለደ አልነበረም?

ይኖራል፡፡ ከኛ በላይ ያሉት ይኖራሉ፡፡ እኛ የመቶ አዛዦች ነን፡፡ ከፍተኛ መኮንኖችና አዛዦቻችን ማለት ነው፡፡ ጠና ያሉ ናቸው፡፡ አራት አምስት ልጅ ከወለዱ በኋላ የዘመቱ ይገኙባቸዋል፡፡ ያላየሁትን አልመሠክርም ሲያደርጉ አላየሁም፡፡ እኛ ብንቀብጥ ብንቀብጥ ከጓደኞቼ ጋር ነው፡፡ ከአዛዦቼ ጋር ሆኜ ደግሞ መቅበጥም አልችልም፡፡

የባህልና የቋንቋ ግጭትስ?

ትክክለኛውን ለመናገር ከነሱ ጋር የባህል ልውውጥ የለንም፡፡ ምክንያቱም በሄድንበት ቦታ ሁሉ የሚቀርብልን ምግብ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አንድ አይነት ምግብ ነው፤ የጦር ግንባር መዘርዘረ ምግብ፡፡ ወደ ሕዝብ የሚያቀርብ የለንም፡፡ በጦሩ ወረዳም ሕዝቡ የለም፡፡

ጥሬ ሥጋ በመብላታችሁ “ሰው በሎች” ብለው ሲሸሿችሁ ነበር የሚባለውስ?

ሊሆን ይችላል፡፡ እኔ በነበርኩበት ጊዜ ይኼ አልተፈፀመም፡፡ ወሬውን ሰምቼዋለሁ፡፡ በዐይኔ ያየሁት ነገር የለም፡፡ በዘመትኩበት ጊዜ እንዲህ አልተደረገም፡፡ ኮርያዎች ከዚያ በፊት ጥሬ ሥጋ አልበሉ ይሆናል፡፡ ተቀቅሎ የሚበላ ጥሬ ሥጋ ግን ይቀርብልሃል፡፡ ሃበሾች ያ ደስ ብሏቸው በልተው ሊሆን ይችላል፡፡

ለምንድነው አንድም ሰው ያልተማረከው?

አለመማረክ የጀግንነትና የጉብዝና ጉዳይ አይደለም፡፡ አለመማረክ የአመራር ውጤት ነው፡፡ እያንዳንዱ ሰው የት እንዳለ የት እንደወደቀ ዝርዝር ቁጥጥር በምታደርግበት ጊዜ የቆሰለውን፣ የወደቀውን ሰው ታውቃለህ፡፡

አንድ ሰው ከጓደኞቹ መሃል ሲጠፋ የት እንደወደቀ ትፈልጋለህ፡፡ ይኼ ለእኛ መሠረታዊ ትምህርታችን ነው፡፡ አጥቅተህም ቦታ ከያዝክ በኋላ ሰዎችህን ትቆጣጠራለህ፡፡ እዚያ ስታጣው የት እንደደረሰ ትፈልገዋለህ፡፡ አንድም ቀን አልሸሸንም፡፡ ምናልባት ሽሽት ላይ ሊሆን ይችላል፡፡ ሰዎችን ለመቆጣጠር ሲያቅትህ ነፍስህን ብቻ ለማውጣት ስትሸሽ ያን ጊዜ ሰዎችህ ሊማረኩ ይችላሉ፡፡

በስንት ውጊያዎች ተሳትፈዋል?

ሻለቃው በተዋጋባቸው ውጊያዎች ሁሉ ተሳትፌአለሁ፡፡ አምስት ዋና ዋና ውጊያዎች ነበሩ፡፡ ከዚያ በተረፈ የሽምቅ፣ የደፈጣ ውጊያዎች አሉ፡፡ በነዚህ ሁሉ ተካፍያለሁ፡፡ ስለዚህ መቁጠር ያስቸግራል፡፡

ውጊያ ላይም ሆነ በሌላ አጋጣሚ ትዝ የሚልዎት ሰው ካለ?

የሰማሁትን ሳይሆን ያየሁትን ልንገርህ፡፡ በነበርኩበት ግንባር እንደ ጥላዬ ወንድም አገኘሁ ያሉትን አስታውሳለሁ፡፡ እንደ ሞገሥ አልዩ ያሉትንም አስታውሳለሁ፡፡ በጦር ሜዳ ውስጥ ገብተው ሙያ እየሰሩ ሕይወታቸው አልፏል፡፡ ጓደኛዬ በቀለ ገብረ ኪዳን ደግሞ አብረን ቅኝት ወጣን፡፡ ሁላችም በያለንበት ተከበብን፡፡ በኋላ እንደምንም አድርገን ከዚያ ሰብረን ወጣን፡፡ ጠላት በሚሸሽበት ጊዜ እሱ ከጎኔ ወድቋል፡፡ እሱን አንስቼ አንድ ቦታ ላይ አስቀምጬ ረርዳታ ጠየኩ፡፡ ክፉኛ ቆስሎ ነበር፡፡ መማረክ የሚመጣው እንዲህ አይነቱ ቦታ ላይ ነበር፡፡ ያን ጊዜ እንኳን አልተማረክንም፤ ሦስት አራት ቦታ ላይ ተከበን በነበርንበት ጊዜ፡፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ አንድ ጓደኛዬ ከፊቴ ቀድሞ ይኼዳል፡፡ ቁርስ ሰዓት ላይ ነው እኔ ከኋላ ነኝ፡፡ ቁርሳችንን በልተን ስንመጣ ከኋላ ተተኮሰብን፡፡ ጥይቱ ልክ እሱ ላይ ያርፋል፡፡ ሲፈነዳ በጭሱ ተሸፈነ፡፡ ሞተ ብዬ ሳስብ ጭሱ ፈገግ ሲል ቆሞ አየሁት፡፡ ሮጬ ስሄድ ሰውነቱ በሙሉ ደም ነው፡፡ “ሞገሴ” ስለው “እ…” አለኝ፡፡ “ደህና ነህ?” ስለው “ደህና ነኝ አንተስ?” አለኝ፡፡ “ደህና ነኝ ይኸ የምን ደም ነው?” ስለው ደሙን አይቶ ወደቀ፡፡ ያ ትንሽ አስደነገጠኝ፡፡ ሳልነግረው ብደግፈው ሮኖ ምናልባት አይወድቅም ነበር፡፡ ወዲያው አምቡላንስ ጠየቅን፡፡ ታክሞ ዳነ፡፡ መለሰ ዘርይሁን ደግሞ ነበር፡፡ ኮርያኖች መከላከያ መሥመራችንን በሽቦ ያጥራሉ፡፡ በጠላት መድፍ ተደብድቦ የሳሳ አለ፡፡

ያ ጠላት እንዲያጠቃ መከላከያ ነው ቀድሞውኑ፡፡ ያንን ለማሳጠር ጠይቀን የኮርያ ሰርቪስ ቡድን የሚባል አለ፡፡ እሾሃም ሽቦውን ያጥራሉ፡፡ ብረቱን ለመትከል ድምፅ ሲያሰሙ ያንን የሰማ ጠላት ከባድ መሣርያ ይተኩሳል፡፡ ሲመጣ መሃከላቸው ያርፋል፡፡ ብዙዎቹ ቆሰሉ፡፡ አንዳንዶቹ ሞቱ፡፡ አንድ ወታደር እርዱኝ ብሎ ጮኸ፤ ቆስሎ፡፡ በኃይል ጮኸ፡፡ ወታደሮቻችን ያለ ትዕዛዝ ከዚያ መንቀሳቀስ አይችሉም፡፡ መለሰ ዘርይሁን ግን አላስችል ብሎት ከሁለት ሦስት ወታደሮች ጋር ዘሎ ይወጣና ሁሉም ቁስለኞች ተሸክመው የቆሰሉትን ወደ መስመር ሲመልሱ፣ ሁለተኛውን ሰው ሲታደግ ሌላ ፈንጂ መጣና ሁለቱንም አብሮ ገደላቸው፡፡ በደም የተሳሰረ ወዳጅነት የምንለው አሁን ያ ነው፡፡ አንድ ሰውም ቢሆን ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ አንድ ሰውም ቢሆን ኮርያዊ ነው፡፡ የሁለቱ ደም ተቀላሏልና በደም የተሳሰረ ወዳጅነት እንላለን፡፡

የአሁን ኑሮዎ እንዴት ነው?

ጃንሆይ የሰጡን አንድ ነገር ነው፡፡ ወደ ኮርያ ስንሄድ አንድ ሰንደቅ ዓላማ ሰጥተውናል፡፡ ይኼን ሰንደቅ ዓላማ መመርያ አድርጋችሁ እንድትዘምቱ፣ በተሰማራችሁበት ቦታ ጀግንነት ሠርታችሁ በደረታችሁ ላይ ልዩ ምልክት አድርጋችሁ በኩራት ስትመለሱ በአደራ የሰጠናችሁን አርማ መልሳችሁ እንድታስረክቡን ነው ያሉት፡፡ ያንን መልሰን አስረክበናቸዋል፡፡ ጃንሆይ ስለወታደርነት የተናገሩት አንደ ነገር አለ፡፡ “ወታደርና ጊዜው” የሚለው የክብር ዘበኛ የመጀመርያው የወታደር ጋዜጣ አለ፡፡ እዚያ ላይ ያሰፈሩት ምንድነው.. “የጦር ሰው ፖለቲካን መልመድ ወላዋይነትን ያስከትላል፡፡ ሲታዘዝም ለምን ማለት ሃፍረት ነው” ብለዋል፡፡ የሄድነው ታዘን ነው፡፡ ስንመለስ ይህን አድርጉልን አላለንም፤ እሳቸውም አላደረጉልንም፡፡ ኮንጎም ዘምቻለሁ፡፡ ከዚያ ስመለስ ትንሽ ፍራንክ ተጠራቅማ ጠብቃኝ ነበር፡፡ በዚያች ፍራንክ ቦታ ገዛሁኝ፡፡ በቦታዋ በደርግ ጊዜ ቤት ሰራሁባት፤ ሳትወረስ ጠብቃኝ ነበር፡፡ ከሰራሁም በኋላ አልተወረሰችም፡፡ ትንንሽ ትንንሽ ቤቶች ሠርቻለሁ፡፡ ያንን እያከራየሁ ስለምኖር በጣም ጥሩ ኑሮ ነው የምኖረው፤ ከጓደኞቼ አንፃር ስመለከተው፡፡

እንዴት ገዙ?

ልጆቼ ይረዱኛል፡፡ የመኪና ዋጋም የዋጋ ግሽበቱም እንዲህ አልነበረም፤ እኔ መኪና ስገዛ፡፡ ሦስት ወንድ ሦስት ሴት ልጆች አሉኝ፡፡ ኢንጂነሮች፣ የሕግ ባለሙያዎች ወዘተ ናቸው፡፡ በባህላችን ልጅ አይቆጠርም፡፡

የደቡብ ኮርያ መንግስት ለማህበራችሁ ስላደረገው ድጋፍ ቢያብራሩልኝ?

የተለየ ነገር አላደረገም፡፡ ነገር ግን ለኮርያ ዘማች ልጆች የነፃ ትምህርት እድል ሰጥቷል፡፡ ለዘማቹ ያደረገው የጎላ ነገር የለም፡፡ ነገር ግን ኮርያኖች መጀመርያ በተሰለፍንበት የጦር ግንባር አካባቢ ለምቶ ከተማ ካደረጉ በኋላ፣ በተለይ ቹንቾን በተባለ አካባቢ የማህበራችንን ሕንፃና ሐውልት በከንቲባ አርከበ እቁባይ ጊዜ ሠርቶልናል፡፡

ሌላው የኮርያ ወርልድ ቪዥን፤  በሰባት ሚሊዮን ብር መዝናኛ ማዕከል ለመሥራት ቃል ገብተዋል፡፡ ምስጋናውን ከቻልክ በኮርያንኛ አስተላልፍልን፡፡ ሕንፃውን ቶሎ እንዲጀምሩ አስታውስልን፡፡




#Article 104: ሩሲያ (179 words)


ሩሲያ (መስኮብኛ፦ Россия /ሮሲያ/) ወይም የሩሲያ ፌዴሬሽን (መስኮብኛ፦ Российская Федерация /ሮሲስካያ ፍየድየራትሲያ/) በአውሮፓ እና እስያ አህጉሮች ውስጥ የምትገኝ አገር ናት። በ17,075,200 ካሬ ኪ.ሜ. ከዓለም በመሬት ስፋት አንደኛ ስትሆን በሕዝብ ብዛትም ከዓለም ስምንተኛ ናት። ሩስያ ከኖርዌ፣ ፊንላንድ፣ ኤስቶኒያ፣ ሌትላንድ (ላቲቪያ)፣ ሊትዌኒያ፣ ፖላንድ፣ ቤላሩስ፣ ዩክሬን፣ ጆርጂያ፣ አዘርባይጃን፣ ካዛኪስታን፣ የቻይና ሕዝባዊ ሬፑብሊክ፣ ሞንጎሊያ እና ሰሜን ኮሪያ ጋር ድንበር አላት።

ሩሲያ በጠፈር እና በጦር መሳሪያ ቴክኖሎጂ በጣም የተራቀቀች ናት፡፡ 

ዳሩ ግን ሌሎች ራሻዊ ሊቃውንት የ«ሩስ» ስም ከስዊድን እንደ መጣ አይቀበሉም። በተለይ አንድ የሳርማትያ ወይም እስኩቴስ ወገን ሮክሶላኒ ተብሎ ከ100 ዓክልበ. እስከ 350 ዓም ግድም በአካባቢው ይገኝ ነበር።  በአንድ አስተሳሰብ የሮክሶላኒ ስም ከ«ሮስ» እና ከ«አላኒ» (አላኖች) ውሑድ ይሆናል። እንዲሁም ከ90 እና 550 ዓም መካከል «ሩጊ» (ሩጋውያን) የተባለ ምሥራቅ ጀርመናዊ ወገን ይጠቀስ ነበር፤ በኋላ በኪዬቫን ሩስ ዘመን የሮማይስጥ ሰነዶች ብዙ ጊዜ ለሩስ «ሩጊ» ይሉዋቸው ነበር። 

በ1275 ዓም የሞስኮ ግዛት ተመሠረተ፤ በኋላም የሞስኮ ታላቅ መስፍን በሌሎቹ ሩስያ ግዛቶች ላዕላይነት አገኘ።  እስከ 1714 ዓም ድረስ ታላቁ ፕዮትር  የሩስያ ግዛት (1714-1909 ዓ.ም.) እስካዋጀ ድረስ፣ መንግሥቱ በሮማይስጥ «ሞስኮቪያ»፣ በእንግሊዝኛም Muscovy /መስኮቪ/ ይባል ነበር። በአማርኛ ይህ ስም «መስኮብ» ተጽፎ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ሲቆይ ቋንቋውም ሩስኛ ደግሞ «መስኮብኛ» በመባል  ይታወቃል። 




#Article 105: የቶሪኖ ከፈን (147 words)


የቶሪኖ ከፈን ወይም መከፈኛ ጨርቅ የተሰቀለ ሰው ምስል የሚታይበት ጥንታዊ በፍታ ነው። ዛሬ የሚገኘው በቶሪኖ ጣልያ ባለበት ቤተ ክርስትያን በመሆኑ «የቶሪኖ ከፈን» ይባላል። ይሄው በፍታ በመቃብር ውስጥ ሲቆይ ኢየሱስ ክርስቶስን የከፈነው እንደሆነ በሱም ላይ ምስሉ በተአምር እንደተቀረጸ የሚያምኑ ጥቂቶች አይደሉም። ሌሎች ግን የጥርጣሬ ባሕርይ ይዘው ይህን ሳይቀበሉ በሰው ልጅ ሰዓሊነት እንደ ተፈጠረ ባዮች ናቸው። ስለዚህ ከበፍታው የተነሣ ብዙ ክርክሮች ሲደረጉበት ውለዋል። 

ከሁሉ የሚያስገርመው ዕድሜው ካሜራ ወይም ፎቶ የማንሣት ዕውቀት መቸም ከኖረ ምናልባት ወደ 1800 ዓመታት በፊት የሚጠጋው ምስል እራሱ የፎቶ ኔጋቲቭ በመሆኑ ሲሆን፡ ምስሉ መጀመርያ በግልጽ የታየበት ወቅት በግንቦት 21 ቀን 1890 ዓ.ም. ሴኮንዶ ፒያ የተባለ አንድ የፎቶ አንሺ ፎቶውን ካነሣ በኋላ ያነሣው ፎቶ በታጠበ ጊዜ ኔጋቲቩን አይቶ በዚያን ጊዜ ምስሉ እራሱ የፎቶ ኔጋቲቭ እንደሆነ ተረዳ። ከ1818 ዓ/ም አስቀድሞ ስለ ፎቶ ኔጋቲቭ ምንም ዕውቀት አለመኖሩ እርግጠኛ ነው። ሆኖም ይህ በፍታ በታሪክ መዝገብ ቢያንስ ከ1349 ዓ.ም. መገኘቱ ደግሞ እርግጠኛ ነው። ስለዚህ ምስሉን በተመለከተ በቀላል የማይመለሱ ብዙ ጥያቄዎች ቀርተዋል።




#Article 106: ሀዲስ ዓለማየሁ (246 words)


ደራሲ ዶ/ር ሀዲስ ዓለማየሁ (ሃዲስ ኣለማየሁ) ከአባታቸው ከቄስ ዓለማየሁ ሰለሞን እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ደስታ ዓለሙ በደብረ ማርቆስ አውራጃ በጎዛመን ወረዳ በእንጾር ኪዳነ ምኅረት ቀበሌ በጥቅምት ፯ ቀን 1902 ዓ.ም. ተወለዱ። ገና በጨቅላ እድሜያቸው በቤተ ክርስቲያን የሚሰጠውን ትምህርት በቤተሰባቸው አጠገብና ባባታቸው አገር ደብረኤልያስ ሄደው የግእዝ ትምሕርት ቤት ቅኔ ተቀኝተዋል።  የቤተክርስቲያን ስርዐታትንና መንፈሳዊ ትምህርትን በጎጃም ገዳማት በደብረ ኤልያስ፣ በደብረ ወርቅና በዲማ ከቀሰሙ በኋላ ወደ በ፲፱፻፲፰ ዓ.ም. አዲስ አበባ በመሄድ በስዊድን ሚሽነሪ ትምህርት ቤት በኋላም በራስ ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን ተከታተሉ። ለትንሽ ጊዜ በአስተማሪነት ሥራ ተሰማርተው እንዳገለገሉ የፋሽስት ጣሊያን ወረራ ተከሰተ። 

የኢጣልያ ወረራ ሲከሰት ከልዑል ራስ ዕምሩ ኃይለ ሥላሴ ጦር ጋር በምዕራብ ኢትዮጵያ በአርበኝነት ሲዋጉ ቆይተው በመያዛቸው ጣሊያን ከልዑል ራስ ዕምሩ ጋር በግዞት ለሰባት ዓመታት በፖንዞ ደሴትና በሊፓሪ ደሴት ታስረው ቆይተዋል።
 
ከዚያም የተባባሪ ኃያላት ወታደሮች በ1935 ዓ.ም. ሲያስመልጧቸው በተመለሱበት ጊዜ በትምህርታቸው እንደገና በኦክስፎርድ ከገፉ በኋላ በተለያዩ የመንግስት ተቋማት በተለይም በትምህርት ሚኒስቴር ለረጅም ጊዜ አገልግለዋል።

ሀዲስ ዓለማየሁ በርካታ የስነጽሑፍ ሥራዋችን አበርክተዋል። ከነዚህም ውስጥ ታላቅ አድናቆትንና እውቅናን ያተረፈው ሥራቸው ፍቅር እስከ መቃብር (1958) በሁለት የተለያዩ መደቦች ውስጥ የሚገኙ የሁለት ሰዎች የፍቅር ታሪክ ላይ ሲያተኩር፤ በጊዜው የነበረውን ወግና ልማድ ይገልጻል። እንዲሁም በ1970 ወንጀለኛው ዳኛ በ 1980 ደግሞ ስለ ማህበራዊ ጉዳዮችና ስለ ጣሊያን ውርስ የሚዳስሰውን የልም እዣት የተሰኙትን ልብ ወለድ ታሪኮች ለንባብ አቅርባዋል። 

ከዚህ ባሻገር:

የተሰኙት ጽሁፎችና የሌሎች በርካታ ሥራዎች ባለቤት ናቸው።

ሀዲስ ዓለማየሁ በኢትዮጵያ የስነ ጽሑፍ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽዖ በማበርከታቸው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዶክቶርነት ማዕረግ ተሰጥቷቸዋል።  ደራሲው በኅዳር 26 ቀን 1996 ዓ.ም. በ94 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። 

ሃዲስ በዝነኛው መጽሓፋቸው ያስተዋወቁትን የሞክሼ ፊደላት ቅነሳ ከተቃወሙት ኣንዱ ዶ/ር ኣበራ ሞላ ናቸው።




#Article 107: ነሐሴ ፳፭ (142 words)


ነሐሴ ፳፭ 
 
በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፶፭ ኛው ዕለት  ነው።  ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነሉቃስ  ፲፩ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ማቴዎስ፤ ማርቆስ እና ዮሐንስ  ደግሞ ፲ ዕለታት ይቀራሉ።

፲፱፻፵፱ ዓ/ም የቀድሞዋ ማላያ (የአሁኗ ማሌዢያ) ነጻነቷን ከብሪታንያ ተቀዳጀች።

፲፱፻፶፬ ዓ/ም ትሪንዳድ እና ቶባጎ የሚባሉት የካሪቢያ ባሕር ደሴቶች ነጻነታቸውን ከብሪታንያ ተቀዳጁ።

፲፱፻፹፫ ዓ/ም የኪርጊዝስታን ሪፑብሊክ ከሶቪዬት ሕብረት ሥር ነጻ ወጣች።

፲፱፻፹፬ ዓ/ም በኮንጎ ሪፑብሊክ በተካሄደው ዴሞክራሲያዊ ምርጫ  ፓስካል ሊሱባ በፕሬዚዳንትነት ተመረጡ።

፲፱፻፹፱ ዓ/ም የብሪታንያ አልጋ ወራሽ የልዑል ቻርልስ ባለቤት ዲያና የዌልስ ልዕልት በመኪና አደጋ ፓሪስ ከተማ አረፉ።

፳፻ ዓ/ም በመሐንዲስ ኃይሉ ሻውል የሚመራው መስከረም ፲፬ ቀን ፲፱፻፺፰ ዓ/ም የተዋሐደው ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ስሙን በመለወጥ የመላው ኢትዮጵያ  አንድነት ድርጅት ተብሎ ተሰየመ፡፡

 

 
፲፱፻፷፩ ዓ/ም የዓለም የከባድ ሚዛን የቡጢ ውድድር መደብ ቻምፒዮና የነበረው ኢጣልያ አሜሪካዊው ሮኪ ማርሲያኖ አረፈ።

፲፱፻፹፱ ዓ/ም የብሪታንያ አልጋ ወራሽ የልዑል ቻርልስ ባለቤት ዲያና የዌልስ ልዕልት በመኪና አደጋ ፓሪስ ከተማ አረፉ። 




#Article 108: ነሐሴ ፳፮ (154 words)


ነሐሴ ፳፮ 
 
በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፶፮ ኛው ዕለት  ነው።  ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነሉቃስ  ፲ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ማቴዎስ፤ ማርቆስ እና ዮሐንስ  ደግሞ ፱ ዕለታት ይቀራሉ።

፲፯፻፯ ዓ/ም በአውሮፓ ንጉዛት በረዥምነት አንደኛው ንጉሥ ሉዊ ፲፬ኛ ለ፸፪ ዓመታት በፈረንሳይ ዙፋን ላይ ከተቀመጡ በኋላ በዛሬው ዕለት አረፉ። 

፲፱፻፲፭ ዓ/ም በጃፓን ውስጥ በተነሳ የመሬት እንቅጥቅጥ አደጋ በቶክዮ እና ዮኮሃማ ከተሞች እስከ መቶ ሃምሳ ሺህ ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ።

፲፱፻፴፩ ዓ/ም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የአዶልፍ ሂትለር ናዚ ጀርመን ሠራዊቶች ፖላንድን ሲወሩ ብሪታንያ እና ፈረንሳይ በአጋርነት ጀርመን ላይ ጦርነት አወጁ።

፲፱፻፶፫ ዓ/ም ራስ አዳል (አዳል ተራራ) በተባለ ቦታ በሀሚድ ኢድሪስ አዋቴ እጅ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የፖሊስ አባል ሲገደል የኤርትራ ነጻነት ትግል በይፋ ተጀመረ።

፲፱፻፷፩ ዓ/ም በሊቢያ ንጉዛት ውስጥ የተነሳው አብዮት ንጉሥ ኢድሪስን ከሥልጣን አስወርዶ ያሁኑን መሪዋን ሙአማር ጋዳፊን ሥልጣን አስጨበጠ።

፲፱፻፸፫ ዓ/ም በመካከለኛው የአፍሪቃ ሪፑብሊክ የተካሄደው ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት አገሪቱን ከነጻነት ጀምሮ የመሩትን ፕሬዚደንቱን ዴቪድ ዳኮን ከሥልጣን አወረደ።

 

 
፲፯፻፯ ዓ/ም የፈረንሳይ ንጉሥ ሉዊ ፲፬ኛ አረፉ። 




#Article 109: ካሽሚርኛ (129 words)


ካሽሚርኛ (ካሽሚሪ) የህንዳዊ-አውሮፓዊ ቋንቋዎች ቤተሰብ ቋንቋ ሲሆን በተለይ የሚናገርበት በካሽሚር አካባቢ በ 7.1 ሚልዮን ሰዎች ነው። ካሽሚርም ዛሬ በሕንድ በፓኪስታንና በቻይና የተከፋፈለ አውራጃ ነው። 

ይህ ቋንቋ ዛሬ በአብዛኛው የተጻፈ ቋንቋ ሳይሆን የሕዝብ መነጋገርያ ብቻ ነው። ሆኖም ድሮ ከ9ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በሻራዳ ጽሕፈት፣ አሁንም በአረብ አልፋቤት ወይም በዴቫናጋሪ ጽሕፈት የተጻፈ አንዳንድ ሥነ ጽሑፍ ይኖራል። በታሪክ ከሁሉ አስቀድሞ የተገኘው የካሽሚርኛ ሰነድ የላለሽቫሪ (እሷም ሴት ገጣሚ የሆነች) ግጥሞች ከ14ኛው ምዕተ ዓመት ናቸው። 

በቅርብ ጊዜ በፖለቲካ ሳቢያ የማይምነት ጉዳይ በብዛት ቸል ይባል ነበር። መደበኛ ወይም ይፋዊ ቋንቋ የትም ቦታ እንኳን አልነበረም። ባለፉት አስርተ ዓመታቶች በአንዳንድ ከፍተኛ መካነ ጥናት ቋንቋው ቢማርም፣ በልጆች ትምህርት ቤት አይሰማም ነበር። ይህ ሁኔታ ግን በ2001 ዓ.ም. ተሻሸለ፤ አሁን በሕንድ ጃሙና ካሽሚር ግዛት አንደኛ ደረጃ ታማሪ በሙሉ ካሽሚርኛን መማር ያስፈልጋል። 

በኢንተርኔት ላይ  አለ። ጥቂት የካሽሚርኛ መጽሔቶች በመታተም ላይ ይገኛሉ።




#Article 110: ማይጨው (185 words)


ማይጨው (ትግርኛ ) በስሜን ኢትዮጵያ ያለች ታሪካዊ ከተማ ናት። ከአዲስ አበባ 665 ኪሎ ሜትር ወደ ስሜን በአዲስ አበባ-መቐለ መንገድ በትግራይ ክልል ደቡባዊ ክፍል ስትገኝ ኬክሮሷና ኬንትሮሷ   ከፍታዋም 2,479 ሜትር ነው። 

በ1997 ዓ.ም. ከማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ በቀረበው ቁጥር መሠረት የማይጨው ጠቅላላ ሕዝብ ቁጥር 34,379 ሰዎች እንደ ነበር ይገመታል። ከነዚህም 16,702 ወንዶችና 17,222 ሴቶች ነበሩ። በ1984 ብሄራዊ ቆጠራ ግን 19,757 ኗሪዎች ነበሩ። 

በማይጨው አካባቢ ግጥሚያ በ 1928 ዓ.ም. በጣልያን ጦርነት ጊዜ የፋሺስት ሃያላት በመሳርያዎች ምክንያት ድል አድርገው ወደ አዲስ አበባ ቀረቡ። በጦርነቱም የተሰውት አርበኞች አባቶች አፅም በከተማዋ ደቡባዊ ክፍል በሚገኘው 
ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስትያን በተዘጋጀላቸው ቦታ በክብር አርፎ ይገኛል፡፡

በተጨማሪም መሬት ለኣራሹ (የኢትየጵያ ተማሪዎች አመፅ) መሪ እና የወቅቱ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሰቲ የተማሪዎች ፕሬዚደንት የነበረው በዘውዳዊ ስርዓት ታጣቂዎች የተገደለው ጥላሁን ይግዛው መቃብር በከተማዋ በሚገኘው ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስትያን (ማርያም ሕዝባ) ላይ ይገኛል፡፡

በከተማዋ  ካሉት የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መካከል ራያ ዩኒቨርሲቲ፣ አንጋፋው ማይጨው ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ፣ ጥላሁን ግዛው ቴክኒክ ኮሌጅ እና ማይጨው እርሻ ኮሌጅ ይጠቀሳሉ፡፡ ራያ ቢራ ፋብሪካ እና ማይጨው ፓርቲክል ቦርድ (ችፑድ ፋብሪካ) በከተማዋ ይገኛሉ፡፡

በአጠቃላይ ከተማዋ በኢትዮጵያ ካሉ ለኑሮ አመቺ ከሆኑሞ ም ር ጥ  አካባቢዎች መካከል ትጠቀሳለች፡፡ 

የሃይለ ሓጎስ እና የሓማሴን ሓድገምበስ የትውልድ አገር ነች




#Article 111: ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ (106 words)


ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ወገን ነው። በኢንጂ. ሃይሉ ሻውል የሚመራ የኢትዮጵያ ህዝብ ፓርቲ ነው።
ይህ ፓርቲ በግንቦት 7 ቀን 1997 ለሚካሄደው ምርጫ ተመሳሳይ አቋም ያላቸውን መኢአድን ኢዴአፓ-ማድህንን ኤዴሊንና ለዚሁ አላማ የተመሰረተውን ቀስተ ደመናን የሚያካትት ስብስብ ሆኖ የተመሰረተ ነው። በ1997 ኣ.ም በተደረገው አገር አቀፍ ምርጫ ቅንጅት ከፍተኛ ውጤት በማምጣት (በአንዳንድ ውገኖችም አሸንፏል በመባል) ይታወቃል። የአዲስ አበባን አስተዳደር ማሸነፉም በተቀናቃኙ ፓርቲ በኢህአዴግ የታመነ ነው።

ይሁን እንጂ በስልጣን ላይ ያለው መንግስትባልተረጋገጠ ሁኔታ በምርጫ በማሰነፉና ከምርጫ በኋላ የተደረጉት ድርድሮች ዘልቀው ባለመሄዳችው ከፍተኛ አለመረጋጋት ተፈጥሮ ቆይቶ መንግስት የቅንጅት መሪዎችን እንዲሁም ተቃውሞ ያስሙትን ብዙ ወገኖችን በተለያዩ ክሶች ወንጅሎ በእስራት ይዞዋቸው ይገኛል። ሆኖም ጥቂት የቅንጅት አባሎች የፓርላማ ወንበራችውንም ተረክበው በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው።




#Article 112: ጸጋዬ ገብረ መድህን (567 words)


ፀጋዬ ገብረመድኅን (1928-1998) ቦዳ ተብላ በምትታውቅ አምቦ ካተማ አካባቢ በምትገኝ ተራራማ ቦታ ተወለዱ። በአምቦ ማአረገ ሕይወት  ቀ.ኃ.ሥ. ትምህርት ቤት ከዚያም ጀነራል ዊንጌትና በአዲስ አበባ የንግድ ትምህርት ቤት በአገር ውስጥ ትምህርታችውን ከገፉ በኋላ በቺካጎ ብላክስቶን በህግ ትምህርት ተመርቀው በ1952 እንደ ወጡ በለንደን ከተማ የቴአትር ትምህርት በሮያል ኮርት ቴአትርና በፓሪስ ኮሜዲ ፍራንሴዝ ተከታትለዋል። ከ1954 እስከ 1964 የብሔራዊ ቴአትር በአርቲስቲክ ዳይሬክተርነት አገለግለዋል። ከዚያም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴአትር ዲፓርትመንትን አቋቁመዋል።
ሆኖም በ1960ዎቹ ደርግ አብዛኛውን የቴአትር ሥራዎቻቸውን ሲያግድ እሳቸውንም ለማሰር በቅቷል።

ብላቴን ሎሬት ጸጋዬ በርካታ ግጥሞችን፥ የቴአትር ሥራዎችን የተለያዩ መጣጥፎችንና ዘፈኖችን አበርክታዋል።
ጸጋዬ በ1990 ለጉበት በሽታ ሕክምና በመሻት ወደ ማንሃታን በሄዱበት አርፈዋል። በአዲስ አበባ በቅድስት ሥላሴ ቤተክርቲያን ተቀብረዋል። 
ነፍሳቸውን በአብርሃም እቅፍ ያኑርልን::

እንደ፡ አዉሮፓ፡ አቈጣጠር፡ በ 2002 ዓ.ም. የብላቴን ሎሬት ጸጋዬ፡ ገብረ መድህን፡ ግጥም፡ (Proud to be African) አዲስ፡ በተመሰረተው፡ የአፍሪካ፡ ኣንድነት፡ ማሕበር፡ በሕዝብ፥
መዝሙርነት፡ ተመርጧል።

ከሳቸዉ፡ ጽሁፎች፡ መካከል፡ የሚከተሉት፡ ዪገኛሉ ።
...
.....

ዝክረ ፀጋዬlt;br

ብላቴን ጌታ ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድሕን እነሆ በሞት ከተለየን ድፍን አራት አመታት ተቆጠሩ። ትዝታም አራተኛ ሙት አመቱን (February 25, 2006) በማሰብ ስራዎቹን በግርድፉም ቢሆን በማውሳት እነሆ የፀጋዬ ዝክር ትላለች።lt;br

የእረፍት ዋዜማ፦lt;br
ፀጋዬ ከማረፉ አራት አመታት ቀደም ብሎም በዶ/ር ኄራን ሠረቀብርሃን አማካይነት በዋሽንግተን ዲሲ የፀጋዬ ግጥሞች በሲዲ ተቀርፀው ተመርቀዋል። 1 የስንብት ዝግጅት ይሆን። ትንቢት አስቀድሞ ለነገር እንዲሉ።lt;br

ፀጋዬ ከማረፉ አስራ አምስት ቀን አስቀድሞ የ«አንድምታ» ባልደረባ አናግሮት ነበር። እስኪ ሁለቱን የሎሬት ፀጋዬን ጥኡም ወጎች ላስቀድም።lt;

በአፄ ምኒልክ ዘመን እንግሊዞች ቱርካና ሃይቅ አካባቢ ዝሆን ያድኑ ነበርና አንዴ አደናቸውን ተከትለው ሲገስግሱ ከኢትዮጵያ ኬላ ደርሰው ኖሮ ድንበር አላሳልፍ ካሉ የኬላ ጠባቂዎች ጋር የተኩስ ልውውጥ ይደረግና ከአዳኞቹ አንዱ በዚሁ ምክንያት ይሞታል። እንግሊዞችም አቤቱታ ያሰሙና ነገሩ አባ መላ (ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ) ዘንድ ይደርሳል። እንግሊዞቹ ያለአግባብ ሰው እንደተገደለባቸው አመልክተው የደም ካሳ እንዲሆናቸው ከኢትዮጵያ ድንበር ውስጥ መሬት እንዲሰጣቸው ነበር የጠየቁት። አባመላ ነገሩን ያጠኑና ችግር እንደሌለው ለእንግሊዞቹ ይገልጻሉ። ነገሩ ከመፈጸሙ በፊት ግን “ይኸ ህግ እናንተ ሃገርም እንደሚሰራበት ማየት ስለምንሻ በሰነድ መልክ ረቂቁ ካለ እስቲ እንየው። እውነት የእንግሊዝ ሰው የዌልስን ሰው ቢገድል እንግሊዝ ከመሬቷ ለዌልስ የምትሰጥ ከሆነ እኛም እንሰጣለን። እሱም የሚሆነው ለተገደለብን የኬላ ጠባቂ ካሳ የሚሆን ከቱርካና ሃይቅ አካባቢ መሬት ከተረከብን ይሆናል ብለው መለሷቸው።lt;

ሌላው ደግሞ የሎሬት ፀጋዬ ከ«ሕይወት ቢራቢሮ»  መታተም ጋራ ተያይዞ ለአንድምታ ባልደረባ ያወጋው ነው። መጀመሪያ የግጥሟን ቅንጫቢ ነቢይ መኮንን ከተረካው እነሆ!lt;br 

ቀን አብረሽ አብበሽ ውለሽ፣ ሲመሽ አብረሽ መስለምለሙ?...lt;
አስተምሪኝ ቢራ ቢሮ፣ ሰው ለመባል አለኝታዬlt;
ቀድሞ የት ነው መነሻዬlt
ሲመሽ የት ነው መድረሻዬ...lt;
ሲተረትማ ሲወጋ፣ ከየብልጭታው ውጋጋንlt;
የሰው አራዊት የአእዋፍ፣ ውስብስብ ነገደ-ጉንዳንlt;
ሲነሳ ሲሮጥ ሲደፋ፣ ሲያጋድል ሲያዛባ ሚዛንlt;
በማይመጠን ታላቅ ኃይል፣ በተፈጥሮ ግዙፍ ሥልጣንlt;
ሊፍተለተል ይወለዳል፣ ሳይነቃ ይወድማል ይባላልlt;br
ልደቱ ዕድሜና ሞቱ፣ አለማቋረጥ ይጓዛል፤lt;br
ይኸ ይሆን አልፋ - ኦሜጋ? ይኸ ይሆን አስቀድሞ ቃል?»  lt;
ፀጋዬ እንዲህ አለ። «እሷ ግጥም በጋዜጣ ታትማ በወጣች ማግስት መንግስቱ ለማ ከቢሮዬ መጥቶ ቢራውን እስቲ አምጣው ወይስ ዝም ብለህ ነው ቢራ ቢሮ ያልከው» ብሎ እንደቀለደብኝ ትዝ ይለኛል።ትንሽ ትከዝ ብሎም «መንግስቱ ምን የመሰለ ደማም ቋንቋ የነበረው ሰው ነበር።አሁን እኮ ደማም ቋንቋ የሚናገር ሰው ሁሉ ጠፋ»።አፈሩ ይቅለለውና ሎሬት ፀጋዬ የኛን ትውልድ lt;lt;ጫት አመንዣኪ ትውልድ ነበር የሚለው።እንዲህ እንደነሱ ዘመን ባይጎሉም ውድድሩም ቢጠናባቸውም አሁንም እኮ አንቱ የተባሉ ወጣት ደራሲያን ገጣሚያን አሉን። ጊዜው ሲደርስ እንዘክራቸዋለን።lt;br

አምቦ አካባቢ ልዩ ስሟ ቦዳ ከኦሮሞና ከአማራ ወገኖቹ የተወለደው ፀጋዬ ገና በልጅነቱ ነበር ሶስቱ ቋንቋዎች አማርኛ፡ እንግሊዘኛና ኦሮሞኛ የተገሩለት። በትምሕርት እየጎለመሰ ሲሄድም ደራሲነቱን ገጣሚነቱን እንዲያ ሲልም ፀሃፊ-ተውኔትነቱን በዋነኛነት በጎልማሳነት ዘመኑ ደግሞ ማህበረሰባዊ ሃያሲነት እና የአፍሪካ የሰው ዘር እና የቅብጥ ቋንቋ እና ባህል ጠቢብነትን አክሎበት እስከ እለተ ህልፈቱ ዘልቋል። በኩላሊት በሽታ መለከፉ እና አለመዳኑን እንዲያም ሲል በጉብዝናው ወራት ያላሰበውን ስደት በሕክምና ሳቢያ የአብራኩ ክፋይ ልጆቹ ወዳሉበት አሜሪካ አቅንቶ በዚያው አሸልቧል። የማሳረጊያ ግጥሙም ይህንን ተስፋ ቢስነትን አመላካች ይሆን።lt;br
የማይነጋ ሕልም ሳልምlt;br
                የማይድን በሽታ ሳክምlt;
                የማያድግ ችግኝ ሳርምlt;
                የሰው ሕይወት ስከረክምlt;
                እኔ ለኔ ኖሬ አላውቅምlt;




#Article 113: ሰኞ (132 words)


ሰኞ በእሑድ እና በማክሰኞ መሀከል የሚገኝ በብዙ አገሮች የሳምንቱ ሁለተኛ ቀን፣ በሌሎች ብዙዎች ዘንድ (ለምሣሌ፦ የአውሮፓ አገሮች) ደግሞ የመጀመሪያ ቀን ነው።

የሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን እሑድ በሆነባቸው አገሮችም ጭምር ብዙዎች ሰኞን የመጀመሪያ አድርገው ይወስዱታል። ይህም በአብዛኛው ለብዙ ሰራተኞችና ተማሪዎች ከቅዳሜ እና እሑድ እረፍት በኋላ የመጀመሪያው የሥራ ወይም የትምህርት ቀን በመሆኑ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ይህ እውነታ ሰኞን በአንዳንዶች ዘንድ እንደ መጥፎ ቀን እንዲቆጠር አድርጎታል።

በኢትዮጵያ ውስጥ በአንዳንዶች ዘንድ ሰኔ አንድ ሰኞ ቀን ከዋለ መጥፎ ነው የሚል ምንም ሳይንሳዊም ሆነ ኃይማኖታዊ መሠረት የሌለው አጉል እምነት አለ። ሰኔና ሰኞ መነሻው አንድ ሰኞ ቀን በዋለ ሰኔ አንድ ተግባር ላይ በዋለ አዋጅ ሳይሆን እንደማይቀር ይገመታል። አዋጁ በኢትዮጵያ ውስጥ መኪና የሚነዳበትን የመንገዱን ክፍል የቀየረ ነበር፤ በመንገዱ በግራ ክፍል መነዳቱ ቀርቶ በቀኝ ክፍል እንዲነዳ የሚያዝ አዋጅ ነበረ። በተፈጠረው ለውጥ ብዙ አደጋ በመድረሱ፡ ከዚያ ጀምሮ ሰኔና ሰኞ ሲገጣጠሙ እንደመጥፎ እድል ይታያል። 




#Article 114: ጎንደር ከተማ (142 words)


ጎንደር ቀደም ሲል የጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዛሬ የጎንደር ክፍለ ሐገር እና የጥንትዋ ኢትዮጵያ ዋና ከተማ ነበር። ጎንደር ክፍለህገር በሰባት አውራጅዎች ይከፈላል። እነዚህም አውራጃዎች ከነዋና ከተማቸው የሚከተሉት ናቸው፤ ወገራ አውራጃ ዋና ከተማው ዳባት፣ ሰሜን አውራጃ ዋና ከተማው ደባርቅ፣ ደብረታቦር አውራጃ ዋና ከተማው ደብረታቦር፣ ሊቦ አውራጃ ዋና ከተማው አዲስ ዘመን፣ ጋይት አውራጃ ዋና ከተማው ንፋስ መውጫ፣ ጭልጋ አውራጃ ዋና ከተማው አይክል፣ ጎንደር ዙሪያ አውራጅ ዋና ከተማው ጎንደር ናቸው።ዛሬ በስሜን ጎንደር ዞን በአማራ ክልል ሲገኝ ከጣና ሃይቅ ሰሜን አንገረብ ወንዝ ላይ ከሰሜን ተራራ ወደ ደቡብ ምእራብ ሰፍሮ ይገኛል። በ  ላይ ነው። አጼ ፋሲለደስ ጎንደርን እንደ ዋና ከተማነት ለመጀመሪያ ጊዜ ይጠቀሙ  እንጂ ከዚያ በፊት በአካባቢው ሰወች ይኖሩበት እንደነበር ታሪክ አለ። ሆኖም ግን ከተማው በታሪክ የገነነው አጼ ፋሲለደስ በአሁኑ ፋሲል ግቢ ወይም የነገሥታት ግቢ ውስጥ የፋሲል ግንብን በ1636 ሲያንጽ ነበር። 

የማእከላዊ እስታቲስቲክ ባለስልጣን በ1998 ቁጥሩ ጎንደር 194,773 የህዝብ ብዛት ስትይዝ ከነሱም 97,625 ወንዶች ሲሆኑ 97,148 ሴቶች ናችው።




#Article 115: ሐረር (764 words)


ሐረር ከአዲስ አበባ ደቡብ ምስራቅ በአምስት መቶ ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ የምስራቅ ኢትዮጵያ ከተማ ናት። በዘመኑ የአስተዳደር መዋቅር የሃረሪ ክልል ዋና ከተማ ናት። በ1,885 ሜትር ከፍታ ላይ፣ የወይና ደጋ የአይር ጠባይ በተላበሰ ቦታ ላይ አርፋለች። በምድር መጋጠሚያ ውቅር  ላይ ናት። በ1987 ዓመተ ምህረቱ የህዝብ ቆጠራ መሰረት ሐረር 76,378 ሕዝብ ይኖርባታል።

ሐረር ለዘመናት ከፍተኛ የንግድ ማዕከል ሆና ስትኖር ከመሃል አገር፣ ከአፍሪካ ቀንድ እና ከአረብ አገራት ጋር በንግድ መንገዶች ስትገናኝ ከቀሪው አለም ጋር ደግሞ በቀይ ባህር ወደቦች አማካኝነት ትገናኝ ነበር።

የሐረር ጀጎል ግንብ ከ1998 ጀምሮ በዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ዝርዝር ውስጥ ይገኛል። በእስልምና ሃይማኖት 4ኛዋ የተቀደሰች ቦታ ተብላም ስትታወቅ  82 መስጊዶች፤ አንዳንዶቹ ከ10ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የነበሩ፤ እንዲሁም 102 የቀብር ቦታዎች አሉዋት።

. ዋግነር፣ ዘ ዲክሽነሪ ኦፍ ኢትዮጵያን ባዮግራፊ፣ ገጽ 1፣ ቮልዩም 1፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የኢትዮጵያ ጥናት ኢንስቲትዩት፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ።

እኛ እርስበእርስ ስንናከስ ወይናደጋማዋ ሐረር እርስ በእርሱ ከሚበላላው ጅብ ጋር ሳይቀር ተግባብቶ የሚኖርባት ከተማ ናት፡፡
   ሐረር ከአዲስ አበባ ደቡብ ምስራቅ በአምስት መቶ ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ የምስራቅ ኢትዮጵያ ከተማ ናት። በዘመኑ የአስተዳደር መዋቅር የሃረሪ ክልል ዋና ከተማ ናት። በ1,885 ሜትር ከፍታ ላይ፣ የወይና ደጋ የአይር ጠባይ በተላበሰ ቦታ ላይ አርፋለች።  በ1987 ዓመተ ምህረቱ የህዝብ ቆጠራ መሰረት ሐረር 76,378 ሕዝብ ይኖርባታል።
ሐረር ለዘመናት ከፍተኛ የንግድ ማዕከል ሆና ስትኖር ከመሃል አገር፣ ከአፍሪካ ቀንድ እና ከአረብ አገራት ጋር በንግድ መንገዶች ስትገናኝ ከቀሪው አለም ጋር ደግሞ በቀይ ባህር ወደቦች አማካኝነት ትገናኝ ነበር።
የሐረር ጀጎል ግንብ ከ1998 ጀምሮ በዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ዝርዝር ውስጥ ይገኛል። በእስልምና ሃይማኖት 4ኛዋ የተቀደሰች ቦታ ተብላም ስትታወቅ 82 መስጊዶች፤ አንዳንዶቹ ከ10ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የነበሩ፤ እንዲሁም 102 የቀብር ቦታዎች አሉዋት
  ኣው-ባዲር፣ አው-ባድር፣ አባዲር፦ (ዑመር አርሪዳ) (በግምት ወደ ፲፫ ኛው ክ/ዘ)፦ በ ፲፫ ኛው ክ/ዘመን ውስጥ የተፃፈውና ስለ ሐረር ጥንታዊ አፈታሪካዊ ታሪክ የሚዘክረው 'ፋዝ መዲናት ሐረር' የተባለው ያልታተመ መጽሐፍ እንደሚገልጸው አባድር (ዑመር አርሪዳ) እጅግ ከተከበሩት የሐረር ሼኽዎች ውስጥ አንዱና ዋንኛው ናቸው። በዚሁ መጽሓፍ አገላለጽ መሠረት፡ አባድር ከሌሎች በርካታ ሼኾች ጋር በመሆን ከሂጃዝ በ፮፻፩፪ ሂጅሪያ (1216 እ.ኤ.አ) ተነስተው ሐረር ከገቡ በኋላ በአካባቢው የጎሣ እና ኃይማኖት መሪዎች ተመርጠው ዒማም ሆኑ። 
 የሀረር ህዝብ ታሪክ ፣ ባህል እና ማንነት ከሀረር ከተማ ጋር በእጅጉ የተቆራኘ ነው፡፡ ሀረሪዎች በረዥም ዘመን የስልጣኔ ታሪካቸው ያፈሯቸው ተንቀሳቃሽ እና የማይንቀሳቀሱ እንዲሁም የሚዳሰሱ እና የማይዳሰሱ በርካታ ቁሳዊ እና መንፈሳዊ ቅርሶች ባለቤት ናቸው፡፡ ከእነዚህ ቅርሶች መካከልም የከተማዋ ልዩ መለያ ምልክት ከመሆንም አልፎ እ.ኤ.አ በ2006 በአለም ቅርስነት የተመዘገበው የጀጎል ግንብ በቀዳሚነት ይጠቀሳል፡፡በግንቡ ውስጥም ከ82 በላይ መስኪዶች እና በርከት ያሉ የሀረሪ ባህላዊ ቤቶች ይገኛሉ፡፡
ሀረር ከፍተኛ የስልጣኔ እድገት ደረጃ ላይ በደረሰችበት በ16ኛው ክፍለ ዘመንም በምስራቅ አፍሪካ የእስልምና ሀይማኖት ትምህርት እና የንግድ ማዕከል ሆናም አገልግላለች፡፡ ይህም የበርካታ ታሪካዊ እና ባህላዊ ቅርሶች ባለቤት እንድትሆን አድርጓታል፡፡ የጀጎል ግንብ የሀረሪ ህዝብ የኪነ ህንፃ ችሎታውን የሚያስመሰክር የታሪክ እና የጥበብ መዘክር ነው፡፡ ይህ ግንብ በ16ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ በአሚር ኑርአማካኝነት እንደተገነባም ይነገራል፡፡ሐረር እንኳን ዛሬ ቀን ዘምኖ ትናንትናም ቢሆን ስንቱ ባህር አቋርጦ የከተመባት፤ ስንቱ ቅጥሯ ገብቶ ለትውልድ የተረፈ ትዝታ ያስቀመጠባት የውበትና የጥበብ መዲና ናት፡፡ የኢትዮጵያ ኢስላማዊ ኪነ ህንጻና ባህል ማንምም ሳይመስል፤ ሃይማኖታዊ መሰረቱን ሳይጥል የነገሰባት መዲና፤ ያው ጀጉልን መዞር ነው፡፡ 
በየቦታው መቆም፡፡ በየቦታው ማየት….በየቦታው መደምም…ጀጉልን ገብተው ይኖሯታል እንጂ አይጽፏትም፡፡  
 ጀጉልን ውስጥ ለውስጥ ከጀመርናት መቆሚያ የለውምና ከጊዜ እየተሻማን በበራፍ በበራፍ እንለፍ
ሀረር ከቅርስነት ባሻገር እ.ኤ.አ በ2003/4 በሰላም ፣ በመቻቻል ፣ በመፈቃቀር እና በልማት ከተማነት አለም አቀፍ ሽልማት እና እውቅናን አግኝታለች፡፡ ይህም የተለያየ እምነት ፣ ባህል እና ቋንቋ ያላቸው ህዝቦች ለዘመናት በሰላም እና በፍቅር የኖሩባት እና ዛሬም የሚኖሩባት ከተማ በመሆኗ የተቀዳጀችው ክብር እና እውቅና ነው፡፡
ሀረር ዩኔስኮ ዕውቅናን የቸራት በዓለም ቅርስ ብቻ አይደለም፡፡ ከኪነ ህንጻዎቿ ልቀት ባለፈ ህያው ሆኖ ዛሬም እየኖረ ባለው ሰዋዊ እሴት ምርጥ ነሽ ብሏታል፡፡ ፈረስ መጋላ ይሉታል ሀረሮች  ከፊት ለፊቱ የአሚር አብዱላሂ አደራሽ አለ፡፡ ሀረር መድኃኒዓለም በር ላይ፡፡ ጀጉል በሀገራችን በርካታ መስጂዶች የሚገኙባት ከተማ ናት፡፡ 
በግንብ የተከበበው ቅጥሯ ውስጥ የሚገኘው የመድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን ከተማዋ ዩኔስኮ የተባለውን ዓለም አቀፋዊ ትኩረት ስባ የመቻቻልና የሰላም ተምሳሌት የተባለ እውቅና እንድትቀበል አድርጓታል፡፡ በረዣዥም የመስጂድ ሚናራዎች የታጀበው የሀረር መድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን በ27 በድምቀት ይነግሳል፡፡ የጀጉል መንገዶች ከጁምአ ዕለት ድምቀት በተጨማሪ በተለየ 27 ነጠላ ለባሾች ከየአሉበት ወደ ቅጥሯ የሚገቡበት ሌላ ትዕይንት ያስተናግዳሉ፡፡ 
ምዕተ ዓመት የተሻገረው ይህ ቤተ ክርስቲያን ንጉሰ ነገስቱ አጼ ምኒሊክ ኢትዮጵያን በሚመሩበት ራስ መኮንን የሀረርጌ ገዢ በነበሩበት ዘመን የታነጸ ነው፡፡ ያሰሩት ራስ መኮንን ናቸው፡፡ ክቧ ቤተክርስቲያን ውብ ናት፡፡ ዛፎቿ ጥቂት ናቸው ነገር ግን ከግቢዋ ስፋት አኳያ ጥሩ አድርገው አጅበዋታል፡፡ 
ዛሬ ከሁሉም አቅጣጫ ሰው ወደ ጀጉል እያመራ ነው፡፡ ሐረር ወይም ዱክ በር ከሚባለው በሗላ በተሽከርካሪ ማለፍ አይቻልም፡፡ ይሄ አጋጣሚ ሌላ ትዕይንት ፈጥሯል፡፡ ነጠላ ያጣፉ ጧፍ የያዙናና ሂጃብ የለበሱ መንገደኞች በጋራ እየተሳሳቁ መንገዱን ሞልተውታል፡፡ እጣንና ጧፍ የዘረጉ ነዋየ ቅድሳት የሚሸጡ መንገዱን ዳርና ዳር ይዘውታል፡፡ የኔ ቢጤዎች ስለ መድሐኒያለም እያሉ ይለምናሉ፡፡ 
መላው የሐረር ህዝብ አቦ እንወድሃለን! ሀገርን ለማጥፋት ለመበታተን ቀን ከሌት የሚተጋ መንግስት መሳይ ጊዜ አንግሶት እየገዛን ቢሆንም አንተም እንደኛው በቁምም በስጋም እየሞትክ ቢሆንም አብሽሩ እኛ አንድ ሆነን ሽ የሆንን ኢትዮጵያውያንነን! 
የመጣብንን ሰይጣናዊ የጥፋት ውሃ ከአምላክ ጋር አንድ ከሆን እናከሽፈዋለን!!!  ኢትዮጵያ ማለት መንፈስ ነው፣ እሱም አንድነት ማለት ነው፡፡ ኢትዮጵያ የፍቅር ሀገር የመቻቻል ምድር ለዘላለም ትንሩልን!!!!




#Article 116: ጀርመን (255 words)


ጀርመን ወይንም በይፋ ስሙ የጀርመን ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ በመካከለኛ አውሮፓ የሚገኝ ታሪካዊ አገር ነው። አገሩ 16 ክልሎች ሲኖሩት ዋናና ትልቁ ከተማውም በርሊን ነው።

ጀርመን አንድ ይፋዊ ቋንቋ ብቻ አለው እርሱም ጀርመንኛ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ብዙ ልዩ ልዩ የጀርመንኛ ቀበሌኞች በአገሩ ይገኛሉ። ለአንዳንድ ሰዎች ጀርመን «የገጣሚዎችና የአሳቢዎች አገር» በመባል ታውቋል። በዓመታት ላይ በሥነ ጽሑፍ፣ በሥነ ጥበብ፣ በፍልስፍና፣ በሙዚቃ፣ በሲኒማ፣ እና በሳይንስ ዘርፎች በርካታ አስተዋጽኦች በማቅረባቸው ጀርመናውያን በዓለም ዝነኛነት አገኝተዋል፤ እንዲሁም መኪና የሚባለውን ፈጠራ በማስለማት ፈር ቀዳጅ ሆኑ። ጀርመን ደግም ስለ ቋሊማና ቢራዎች ልዩነት ብዛት የገነነ ሆኗል።  እግር ኳስ በጀርመን ከሁሉ የተወደደው እስፖርት ነው። 

የራይን ወንዝ አቅራቢያ በጥንት ከሁሉ በፊት የተሰፈረው ሲሆን እዚያ አንዳንድ ጥንታዊ የሮሜ መንግሥት ድልድይ፣ አምባ፣ ወይም ፍርስራሽ ሊታይ ይችላል። የጀርመን ሕዝብ በብዛት ክርስቲያኖች ናቸው፤ በስደትም ወደ አገራቸው ለደረሱት ሰዎች በጠቅላላው ሰላምታ ሰጪዎች ናቸው።  የበርሊን ግድግዳ በፈረሰበትና «የቅዝቃዛ ጦርነት» በጨረሰበት ወቅት የጀርመን ዳግመኛ መወሐድ ተከሠተ። በዚያ ሰዓት የቀድሞ አገራት ምሥራቅ ጀርመንና ምዕራብ ጀርመን አብረው የአሁኑን ጀርመን መንግሥት ፈጠሩ። 

ብዙ የጀርመን ሰዎች በዓለም ዙሪያ ስመ ጥሩ ናቸው። ይህም ደራሲዎች ያኮብ ግሪምና ወንድሙ ቭልሄልም ግሪም፣ ባለቅኔው ዮሐን ቩልፍጋንግ ቮን ጌጠ፣ የፕሮቴስታንት ንቅናቄ መሪ ማርቲን ሉጠር፣ ፈላስፋዎች ካንት፣ ኒሺና ሄገል፣ ሳይንቲስቱ አልቤርት አይንስታይን፣ ፈጠራ አፍላቂዎች ዳይምለር፣ ዲዝልና ካርል ቤንዝ፣ የሙዚቃ ቃኚዎች ዮሐን ሴባስትያን ባክ፣ ሉድቪግ ቫን ቤትሆቨን፣ ብራምዝ፣ ስትራውስ፣ ቫግነርና ብዙ ሌሎች ይከትታል። 

እጅግ ቁም ነገር የሆነ ጠቃሚ ፈጠራ ማሳተሚያ፤ ዮሐንስ ጉተንቤርግ በሚባል ሰው በ1431 ዓ.ም. ተጀመረ። ስለዚህ ተጓዦች ከውጭ አገር ሲመልሱ በአውሮፓ ያለው ሰው ሁሉ እርግጡን በቶሎ ያውቀው ነበር።   አሁን ጀርመን «ዶይቸ ቨለ» በሚባል ራዲዮን ጣቢያ ላይ ዜና በእንግሊዝኛ ያሠራጫል።  የጀርመን ሕዝብ ባማካኝ ከአውሮፓ ሁሉ ቴሌቪዥንን የሚወድዱ ሲሆኑ ፺ ከመቶ ሰዎች ወይም ሳተላይት ወይም ገመድ ቴሌቪዥን አላቸው። 




#Article 117: ደሴ (127 words)


ደሴ ወይም ላኮመልዛ በወሎ ክፍለ ሃገር የሚገኝ ከተማ ሲሆን በድሮ አጠራሩ ወይራ አምባ ይሰኝ ነበር። የወይና ደጋ አየር ጸባይ ያለው ይህ ከተማ፣ በከተማነት ታዋቂ እየሆነ የመጣው በዓፄ ዮሐንስ ፬ኛ ዘመን እንደሆነ ይጠቀሳል።  የአካባቢው መሬት ከእሳተ ጎሞራ ቅሪት የሚመነጭ ስለሆነ፣ በንጥረ ነገር የዳበርና ለምነት ስለሚያሳይ፣ ከተማው በ20ኛው ክፍለዘመን በፍጠነት እንዲያድግና በኋላም በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ እና ደርግ ዘመን ወሎ ተብሎ ለተሰየመው ክፍለ ሃገር ዋና ከተማ እንዲሆን ዋና አስተዋጽዖ አድርጓል።

እንደ አርመን ኢምባሲ ታሪካዊ ሰነድ፣ የአርመን ክርስቲያኖች በ7ኛው ክፍለ ዘመን በአረቦች በተነሳባቸው ወከባ ምክንያት ብዙዎች ተሰደው በአሁኑ ደሴ ከተማ አካባቢ እንደሰፈሩና በኋላ ቅዱስ እስጢፋኖስ የተሰኘውን ገዳም በሐይቅ እንደመሰረቱ ያትታል። በዚህ አካባቢ አርመኖች የመስፋፋትና የመጎልበት ሁኔታ እያሳዩ ስለመጡ አካባቢው የአርመን ደሴት  እስከመባል እንደደረሰና በኋላ  በ16ኛው ክፍለ ዘመን በግራኝ አህመድ ወረራ ምክንያት ካሉበት ተነቅለው በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች እንደተበተኑ ይሄው የኢምባሲ ሰነድ ያትታል




#Article 118: አዋሳ (111 words)


አዋሳ ከአዋሳ ሃይቅ በታላቁ ሪፍት ቫሌ/ስምጥ ሸለቆ  ላይ የሚገኝ ከተማ ነው። የደቡብ ሕዝቦች ክልል ዋና ከተማ ስትሆን በሲዳማ ዞን ተገኛለች። የአዲስ አበባ-ናይሮቢ መንገድ ላይ በላቲቱደና ሎንጁቱድ  ላይ ናት። አዋሳ በውበትዋና በትልቅነትዋ ባሁኑ ጊዜ ታላቅ የቱሪስት መስህብ ያላት ነች። 

በማዕከአዊ ስታቲስቲክ ባለስልጣን ትመና የ119,623 ሰው መኖሪያ ስትሆን ከነሱም 60,378  ወንዶች 59,245 ሴቶች ሆነው ተተምነዋል። አዋሳ የቀድሞ ሲዳሞ ክፍለ ሓገር ዋና ከተማ የነበረች የደቡብ ዩኒቨርሲቲ፥ የአንድ ኤርፖርትና የሰፊ ገበያ ማዕከል ናት። አዋሳ ከ1998 ዓ.ም. ጀምሮ ሃዋሳ በመባል የታወቃል። ይህን ተመርክዞ የደቡብ ዩኒቨርሲቲ ሃዋሳ በመባል ስሙ ተቀይሮአል።

የሃዋሳ ከተማ በአሁን ሰዓት በከፍተኛ ደረጃ እያደገች ያለች ከተማ ሰትሆን ወደ 600,000 ነዋሪ እንደሚገኝባት ይገመታል። ከተማዋን በሰሜን ኦሮምያ በደቡብ ዲላ በምዕራብ ከምባታ በ ምስራቅ አለታ ወንዶ ያዋስኑዋታል።




#Article 119: ጋምቤላ (ከተማ) (781 words)


ጋምቤላ በምዕራብ ኢትዮጵያ የምትገኝ ከተማ ስተሆን ጋምቤላ ሕዝቦች ክልል ዋና ከተማ ናት። በላቲቱድና በሎንጂቱድ     ላይ ትገኛለች።

በ1998 የማዕከላዊ የስታትስቲክ ትመና መሰረት የ31,282 ሰዎች መኖሪያ ስትሆን ከነሱም መሃከል 16,163 ወንዶችና 15,119 ሴቶች ይገኙባታል። ጋምቤላ የአኑአክና የኑር ጎሳዎች መኖሪያ ስትሆን የየራሰችው ገበያ በጋምቤላ አላችው። ከተማዋ የአንድ ኤርፖርት ባለቤትና የጋምበላ ብሄራዊ ፓርክ ተጓዳኝ ናት።

ጋምቤላ የተመሰረተችብት ምክኒያት በባሮ ወንዝ ላይ ባላት አቀማመጥ ነው። ይህ ወንዝ በጊዜ ኢትዮጵያና እንግሊዝ ቡና ወዘተ. ወደ ሱዳንና ወደ ግብጽ ለመላክ ምቹ መንገድ መሆኑን ሁለቱም በማመናችው ነው። በ1902 እ.ኤ.አ. አጼ ምኒልክ ለእንግሊዝ ባሮ ወንዝ ላው አንድ ወደብ እንዲጠቀም ይፈቅዱና በ1907 እ.ኤ.አ. በስራ ላይ ከቀረጥ ቢሮ ጭምር ይውላል። በሱዳን የምድር ባቡር ኩባንያ የሚተዳደር የመርክብ አገልግሎት 1,366 ኪሎ ሜትር በመጓዝ ጋምቤላን ከካርቱም ጋር ያገናኛታል።

በሪቻርድ ፓንክርስት ዝገባ መሰረት በክረምት በወር ሁለት ጊዜ መርከቦች ሲመላለሱ ወንዙን ሲወርዱ 7 ቀናት፣ ሲወጡ ደግሞ 11 ቀናት ይፈጅባቸው ነበር።

ጋምቤላ በጣሊያን የምሰራቅ አፍሪካ ግዛት በ1936 እ.ኤ.አ. ተጠቃላ፥ በ1941 እ.ኤ.አ. በአንድ ከባድ ውጊያ በኋላ ወደ እንግሊዝ አስተዳደርነት ትዘዋውራ ነበር። ሱዳን ነጻ በወጣችበት በ1948 ዓ.ም. ለኢትዮጵያ ተመለሰች። በባሮ ላይ ያለው ወደብ በደርግ ጊዜ እንደተዘጋ ሆኖ፥ ይከፈት ይሆናል የሚል ተስፋ አለ።

በሦስት ዞኖችና በአንድ ልዩ ወረዳ ሥር በሚገኙ 13 ወረዳዎች፣ በ241 ቀበሌዎችና በአንድ የከተማ አስተዳደር የተዋቀረችው ጋምቤላ ጠቅላላ የቆዳ ስፋቷ 30,065 ካሬ ኪሎ ሜትር ነው፡፡ ሃያ በመቶው የክልሉ መሬት በደን የተሸፈነ ነው፡፡ ጋምቤላ በሰሜንና በምሥራቅ ከኦሮሚያ ክልል ጋር ስትዋሰን፣ በደቡብ ምዕራብ ከአዲሲቱ ደቡብ ሱዳን ጋር በሰፊው ትዋሰናለች፡፡ ከአዲስ አበባ በ776 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው የጋምቤላ ከተማ በቅርቡ 100ኛ ዓመት የልደት በዓሏን ያከበረች ሲሆን፣ እንደ ብዙዎቹ የአገሪቱ ዕድሜ ጠገብ ከተሞች ዘርፈ ብዙ ችግሮችን የምትጋፈጥ የበረሃ ገነት ነች፡፡ ከ60 ሺሕ በላይ ነዋሪዎች ያላት ጋምቤላ በአብዛኛው የሚኖሩባት

እንግሊዞች በቅኝ ግዛት ዘመን ሱዳንን በሚያስተዳድሩበት ወቅት ለወታደራዊም ሆነ ለንግድ እንቅስቃሴው መናኸሪያ በማድረግ ሲጠቀሙባት እንደነበር በታሪክ የሚነገርላት ጋምቤላ፣ ከ19ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ጀምሮ የኢትዮጵያ አካል እንደነበረችና በኋላም ሱዳን እ.ኤ.አ በ1956 ነፃነቷን ስትቀዳጅ በኢትዮጵያ የአስተዳደር ክልል ሙሉ ለሙሉ መካተቷም በታሪክ ድርሳናት ተወስቷል፡፡ በክልሉ አምስት ብሔረሰቦች ይኖራሉ፡፡ ጋምቤላ በእነዚህ ብሔረሰቦች የእርስ በርስ ግጭትና በአካባቢው ድንበርተኛ በሆነችው ሱዳን ለረዥም ዓመታት በቆየው የእርስ በርስ ጦርነት ስትታመስ መኖሯም ይታወቃል፡፡

ዚህም ከአገሪቱ ታላላቅ ተፋሰሶች አንዱ በሆነው የባሮ ወንዝ ላይ ረዥም የተባለውን ድልድይ በመገንባት የአካባቢውን ሁኔታ ሲያረጋጋ፣ ለፕሬዚዳንት መንግሥቱ ኃይለ ማርያምም ለየት ያለ አድናቆትንና ፍቅርን ያስገኘላቸው አጋጣሚ እንደነበርም በአካባቢው ነዋሪዎች በስፋት ይወሳል፡፡ አሁንም ድረስ በከተማዋ ጋምቤላ አቋርጦ የሚያልፈው ባሮ ወንዝ ላይ በተገነባው ድልድይ በአንድ በኩል ብቻ በርከት ያለ ሕዝብ ሲጓጓዝ የተመለከተ ጎብኚ ምክንያቱ ምን እንደሆነ ሲጠይቅ፣ ከነዋሪዎች ‹‹ኮሎኔሌ መንግሥቱ የተራመዱበት ጥግ ስለሆነ ነው›› የሚል ምላሽ ሊያገኝ ይችላል፡፡

በእርግጥ በተደጋጋሚ ጊዜ እንደሚደመጠው የቀድሞው መሪ በባሮ ወንዝ ላይ ባስገነቡት ድልድይ የአካባቢው ነዋሪዎች የእርስ በርስ ግንኙነታቸውን ከማጠናከር ባለፈ፣ በኢኮኖሚያዊ ፋይዳው ተጠቃሚ በመሆናቸው እሳቸው ጥለው ያለፉት ከፍተኛ ቅርስ መሆኑን ይመሰክራሉ፡፡ በአንፃሩ የከተማው የትራፊክ አስተናባሪዎች እግረኞች ብቻ ሳይሆኑ ተሽከርካሪዎችም ጭምር በተራ የሚተላለፉት የድልድዩን ደኅንነት ለመጠበቅ ታስቦ እንደሆነ በመግለጽ የመጀመሪያውን አስተያየት ያጣጥሉታል፡፡ ‹‹መንግሥቱ የባሮን ድልድይ በማሠራቱ ዘለዓለማዊ ፍቅርን በእኛ ዘንድ አኑሯል፤›› ያሉት የዕድሜ ባለፀጋው አኩሉ ኦጆን፣ ምናልባትም ፕሬዚዳንቱ በቆዳ ቀለማቸው ለጋምቤላ ሕዝቦች ቅርብ ከመሆናቸው ጋር በተያያዘ ትክክለኛ የአገር መሪ እንደነበሩም በማወደስ ጭምር ፈገግታ የተሞላበት አስተያየታቸውን ይሰጣሉ፡፡

የቀድሞው መሪ በጋምቤላ የባሮ ወንዝ ድልድይን ብቻ ሳይሆን የጋምቤላ አውሮፕላን ማረፊያን ያስገነቡ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ በአካባቢው ሕዝብ የተለየ ቦታ እንዳላቸው ቢነገርም፣

ጋምቤላ ከመጀመሪያው ጀምሮ በሕወሃት አስተዳደር ክፉኛ ተጎድታለች፤ በመሬቷ ልማትና በከርሰ ምድር ሃብቷ ምክንያት በዐባይ ጸሐዬና በዶ/ር ገብረአብ ባርናባስ የተመራ በ1994 የተጀመረው የዘር ማጥፋት አሁንም ሙሉ ለሙሉ ቆሟል ለማለት ያስቸግራል፣ በቅርቡ በመዥነገሮች ላይ የሕወሃት ወታደሮች የፈጸሙትን ጭፈጨፋ ስናስብ!

በክልሏ የተፈጥሮ ሃብት ላይም የተካሄደውና የሚካሄደው ጭፍጨፋ በሃገራችን በሁሉም መልኩ በሲቪል ማኅበረስብና የመንግሥቱን መዋቅር በሚቆጣጠረው የንዑስ ብሄረሰብ ወኪል የሆነው በጦር ኃይል የሚደገፈው ሕወሃት የሚፈጽመው የጥፋትና የጠላትነንት ሥራ ብዙ ማስረጃዎች እየቀረቡበት ነው። 

የኢትዮጵያን ተተኪ የሌለው የተፈጥሮ ሃብት በብር 16.7 ሚሊዮን ክፍያ በባዕዳን በማስጨፍጨፍ፡ ሕወሃትና ጭፍሮቹን በሃገሪቱ ላይ ያላቸውን የጠላትነት ጥላቻ አረጋግጠዋል። ይህ ድርጊትም ባዕድ ቅኝ ገዥ ከሚያደርገው ተለይቶ የሚታይ አይደለም – 

በጋምቤላ ክልል ማጃንግ ዞን ጎደሬ ወረዳ ጉማሬ ቀበሌ ውስጥ ይገኛል፡፡ የጉማሬ ደን ከ1,800 እስከ 2,200 ሜትር ከፍታ ላይ ደልዳላ ቦታ ይዞ ከተራራው ወደታች ሲወርድ ቁልቁለታማ ሸለቆዎች በብዛት ያሉበት ነው፡፡ ከዚህ ተራራማና በጥቅጥቅ ተፈጥሯዊ ደን የተሸፈነ ምድር በርካታ ወንዞችና ወንዞችን የሚፈጥሩ ምንጮች ይነሳሉ፡፡ በአጠቃላይ 40 የሚደርሱ ምንጮችና ወንዞች ከአባቢው የሚነሱ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ሻይ፣ ጋጃ፣ ካጃዲ፣ ፋኒና ቢታሽ ተጠቃሾች ናቸው፡፡

ከአካባቢው የሚነሱ የውኃ ምንጮች በኢትዮጵያ ከሚገኙ 12 ተፋሰሶች አንዱ የሆነው የባሮ አኮቦ ተፋሰስ አካል ናቸው፡፡ የጋምቤላ ክልል እስትንፋስ የሆነው ባሮ አኮቦ ወንዝ የነጭ ዓባይ ትልቅ ገባር እንደሆነ ይታወቃል፡፡

በሌላ በኩል ለውኃ አካላቱ መሠረት የሆነው የአካባቢ ተፈጥሯዊ ደን በርካታ አገር በቀል ዛፎችን ያካተተ ነው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ቀረሮና ገተማ ዛፎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡

የገተማ ዛፍ አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴን ጨምሮ በርካታ ኢንቨስተሮችና የአካባቢው ንብ አናቢዎች ማር እንዲያመርቱ ምክንያት የሆነ ነው፡፡ የገተማ ዛፍ የተለየ ጥራት ያለው የማር ምርት ማስገኘት የሚችል መሆኑን የአካባቢው ማኅበረሰብ ይተርክለታል፡፡

ከማር ምርት በተጨማሪ ተፈጥሯዊው የጉማሬ ደን በርካታ ቅመማ ቅመሞች የሚገኝበት መሆኑም ይነገርለታል፡፡ ነገር ግን የህንዱ ኩባንያ ቬርዳንታ ሐርቨስትስ ያለ በቂ ጥናት ቦታውን መረከቡ የአካባቢውን ብዝኃ ሕይወት እየጎዳ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡

የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በ1997 ዓ.ም. ተመሥርቶ በ1999 ዓ.ም. ነው ሥራ የጀመረው፡፡ ዩኒቨርሲቲው በቤንች ማጂ ዞን በ52 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ቴፒ ከተማ ውስጥ ይገኛል፡፡




#Article 120: ሞልዶቭኛ (160 words)


ሞልዶቭኛ (молдовеняскэ / moldovenească ሞልዶቨኛስክዕ) በሞልዶቫ ሬፑብሊክና በትራንስኒስትሪያ የሚናገር የሮማንኛ አይነት ነው። በሞልዶቫ ሕገ መንግሥት መሰረት ሞልዶቭኛ የአገሪቱ መደበኛ ቋንቋ ሲሆን አብዛኞቹ የቋንቋ ምሁሮች ግን ከይፋዊ ሮማንኛና ከይፋዊ ሞልዶቭኛ መካከል ምንም ልዩነት የለም ባዮች ናቸው።

ሞልዶቭኛ ማለት ደግሞ የሞልዶቫና የስሜን ሮማንያ ቀበሌኛ ሊሆን ይችላል። 

ሞልዶቭኛ የሚጻፍበት ፊደል ወይም በላቲን አልፋቤት ወይም በቂርሎስ አልፋቤት ሊሆን ይችላል። አሁኑኑ የላቲን አልፋቤት በሞልዶቫ ሬፑብሊክ ይፋዊ ሲሆን በትራንስኒስትሪያ ግን የቂርሎስ አልፋቤት ይፋዊ ነው። ቅድም ሲል የሶቭየት ኅብረት ክፍላገር ስትሆን እስከ 1989 እ.ኤ.አ. ድረስ የቂርሎስ አልፋቤት በሞልዳቪያን ሶቭየት ሶሻሊስት ሪፑብሊክ ውስጥ የቂርሎስ ጽሕፈት ይፋዊ ነበር።

ሞልዶቭኛ ከሮማንኛ የተለየ ቋንቋ መሆኑ በጣም የሚያከራከር ጉዳይ ነው። ሆኖም የሞልዶቫ ሕገ መንግሥት ይፋዊ ከማድረጉ በላይ በትራንስኒስትሪያ ከሩስኛና ዩክሬንኛ ጋራ መደበኛነት አለው። የትራንስኒስትሪያ ነጻነት ግን ከሌሎች አገራት ገና አልተቀበለም።

የሞልዶቫ ሳይንስ ተቋም ቋንቋውን ቢያስተዳድርም 'ሮማንኛ' ይለዋል። የሮማኒያ መካነ ጥናት ደግሞ ለሮማንያ ቋንቋ ሲያስተዳድር አንዳንድ ከ1989 በኋላ ያደረገው የአጻጻፍ ለውጥ በሞልዶቫ ውስጥ አልተቀበለም። ስለዚህ ከሁለቱ ይፋዊ ቋንቋዎች መካከል ጥቃቅን የአጻጻፍ ለውጥ ይኖራል። ከዚህ አጠገብ ከሁለቱ አገሮች መነጋገርያዎች መካከል ሌሎች ትንንሽ ለውጦች አሉ።




#Article 121: የሲቢሊን መጻሕፍት (373 words)


የሲቢሊን መጻሕፍት በግሪክ የተጻፉ የትንቢት ግጥሞች ክምችት ነበሩ። በአፈ ታሪክ የጥንታዊ ሮማ ንጉሥ ታርኲኒዩስ ሱፐርቡስ ከአንዲት ሲቢል (ሴት ነቢይ) ገዝተዋቸው በሮማ መንግሥት ታሪክ ታላቅ አደጋ በተከሠተበት ወቅት እኚህ ትንቢቶች ይማከሩ ነበር።

የዛሬው ምሁሮች እኚህ መጻሕፍትና ዛሬ የታወቁት በክርስትና አባቶችም ከ2ኛ ክፍለዘመን እስከ 5ኛ ክፍለዘመን ድረስ በሰፊ የተጠቀሱት የሲቢሊን ራዕዮች አንድ አይደሉም ባዮች ናቸው። 

መጻሕፍቱ ደግሞ ለግሪኮች ታወቁ። መጀመርያ የታዩ በገርጊስ በደብረ ኢዳ (ለጥሮአስ ትንሹ እስያ ቅርብ የሆነ) በአፖሎ ቤተ መቅደስ በ7ኛው ክፍለዘመን ዓክልበ እንደ ነበር ይታመናል። ደራሲይቱ የሄሌስፖንት ሲቢል ተባለች። ከዚያ ክምችቱ ከገርጊስ ወደ ኤሩትራይ (በምሥራቅ ትንሹ እስያ) እንዳለፈ የኤሩትራይ ሲቢልም ሥራ እንደ ተባለ ይታመናል። ይኸውም ክምችት ከዚያ እስከ ኩማይ ጣልያ ከዚያም እስከ ሮማ ከተማ እንደ ተጓዘ ይመስላል።

በአይኔይድ ደራሲ ቪርጂል ዘንድ አይኔያስ ወደ ሢኦል ሳይጓዝ የኩማይ ሲቢልን አማከሮ ነበር። ንጉሥ ታርኲንዮስ ከኩማይ ሲቡል እንዴት እንደ ገዟቸው ዝነኛም አፈ ታሪክ ነበር። እርሷ ዘጠኝ የትንቢት መጻሕፍት ክምችት ለታርኲን ለመሸጥ ብታስብ እሳቸው ውድ በመሆኑ እምቢ ብለው ሦስቱን እንዳቃጠለች ይተረታል። ከዚያ በኋላ ስድስቱን ቀሪዎች መጻሕፍት ለፊተኛው ዋጋ ለመሸጥ አሰበች። ሁለተኛ እምቢ ብለው ሌላ ሶስት አቃጠለች። በመጨረሻ ሶስቱን የተረፉ መጻሕፍት እንዳይጠፉ ለዚህ ዋጋ ገዙና በሮማ በዩፒተር ቤተ መቅደስ አኖሯቸው።

መጻሕፍቱም ለ2 የሮማ ባለሥልጣናት አደራ ተሰጡ። ከ375 ዓክልበ. ጀምሮ አሥር ጠባቂዎች -- አምሥት ከባለሥልጣናት ወገንና አምሥት ከተራ ዜጎች ወገን -- ተሾሙላቸው። ከዚህ በኋላ (ምናልባት በሱላ ጊዜ 96-86 ዓክልበ.) ቁጥራቸው እስከ 15 ተጨመረ። የኚህ ጠባቂዎች ተግባር ከአስጊ ሁኔታዎች ለማለፍ ተገቢ ስርዓት ምን እንደ ሆነ ማማከር ነበር። ሆኖም ስርአቱን ብቻ እንጂ ምስጢራዊ ትንቢቱን እራሱን አልገለጹም ነበር።

የመጻሕፍቱ ተጽእኖ የምሥራቅ አማልክትን ለምሳሌ አፖሎ፣ «ታላቂቱ እናት» ኩቤሌ እና ኬሬስ፣ እንዲሁም የግሪኮች አረመኔ እምነት ወደ ሮማ አረመኔ ሃይማኖት አስገባ። 

ግጥሞቹ በግሪክ ስለተጻፉ ጠባቂዎቹ ሁልጊዜ በሁለት የግሪክ አስተርጓሚዎች ይረዱ ነበር። የዩፒተር መቅደስ በ91 ዓክልበ. በተቃጠለበት ወቅት ግን ጠፉ። ስለዚህ የሮማ ላይኛ ምክር ቤት (ሴናት) በ84 ዓክልበ. ተልእኮዎች ተመሳሳይ ትንቢቶች አገኝተው እንዲተኩ ላኩዋቸው። በተለይም ትንቢቶች የተለቀሙ ከትሮይ ከኤሩትራይ ከሳሞስ ደሴት ከአፍሪካ (ማለት የዛሬ ቱኒዚያ) በጣልያም ከሲሲልያ ደሴትና ከቲቡር ነበር። አዲሱን ክምችት ወደ ሮማ ካመጡ በኋላ የሮማ ቄሶች እውነት የመሠላቸውን ለይተው ሌሎቹን ግን ከክምችቱ ጣሉ። 

የሮማ ንጉሠ ነገሥት አውግስጦስ በ20 ዓክልበ. ወደ አፖሎ መቅደስ አዛውሮአቸው ተመርምረው አዲስ ቅጂ ተደረገ። እዚያ እስከ 397 ዓ.ም. ቆዩ። በዚያን ጊዜ የአሪዮስ ክርስትና ትምህርት አራማጅ የሆነ ስቲሊኮ እንዳቃጠላቸው ይባላል።

በ2ኛው ክፍለዘመን ደራሲ የትራሌስ ፍሌጎን መጽሐፍ የጉዶች መጽሐፍ ወይም መታሠቢያ ውስጥ ከሲቡላውያን መጻሕፍት 70 መስመሮች ተጠቀሱ። ይህ ጥቅስ ስለ አንድ ፍናፍንት ልደትና ስለ ጣኦቶች መሥዋዕት ሥርአት ይናገራል። 

በታሪክ ከተመዘገቡት ምክሮች መኻል ፦




#Article 122: የሲቢሊን ራዕዮች (317 words)


የሲቢሊን ራዕዮች በግሪክ የተጻፉ በ12 መጻሕፍት ተከፋፍለው የትንቢት ግጥሞች ክምችት ናቸው። እነሱ የሲቢል (ሴት ነቢይ) ሥራ ናቸው ይላሉ። ይሁንና የዛሬ ሊቃውንት እኚህ ትንቢቶች በአይሁዶች ወይም በክርስቲያኖች ተጽፈው ዕውነተኛ የሲቢሊን መጻሕፍት ሊሆኑ አይችሉም ባዮች ናቸው። ትንቢቶቹ የተባሉ ከድርጊቶቹ በኋላ ተነበዩና ከ2ኛው መቶ ዘመን ዓክልበ እስከ 6ኛ መቶ ዘመን ከክርስቶስ በኋላ መጻፍ ነበረባቸው ሲሉ ይክራክራሉ። ምክንያቱም ከትንቢቶቹ መኃል ብዙዎች ስለ መሢህ ወይም ስለ ሌላ መጽሐፍ ቅዱስ ነክ ጉዳይ የሚነበዩ ናቸው። ለሎችም ደግሞ ስለ ሮማ መንግሥት ዕድልና ታሪክ ስለሚነበዩ ስለዚህ ከድርጊቶቹ በኋላ መነበይ ነበረባቸው ይላሉ የዛሬው ምሁራን።

ቢሆንም እነዚህ መጻሕፍት የአይሁድና የክርስትና ሃይማኖት ነክ ጉዳዮች ብቻ ሳይሆን ከግሪክና ከሮማ አረመኔ ሃይማኖት የተለቀሙ ብዙ ስሞች ወይም ሃሳቦች ይገኙባቸዋል። ለምሳሌ ከግሪክ ጸሐፊዎች ሆሜርና ሄሲዮድ፣ እንዲሁም ከብሉይ ኪዳን ስለ ኤደን ገነት ስለ ኖህና ስለ ባቢሎን ግንብ የሚል ወሬ አለባቸው።

በጥንት የታወቁት 'ሲቢሊን መጻሕፍት' በሮማ ከተማ በቤተ መቅደስ ይጠበቁ ሲሆን በ90 አመት ዓክልበ በእሳት ተቃጠሉ። ስለዚህ የሮማ ላይኛ ምክር ቤት (ሴናት) በ84 ዓክልበ ተልእኮዎች ተመሳሳይ ትንቢቶች አገኝተው እንዲተኩ ላኩዋቸው። ከዚያ እስከ 397 ዓ.ም. ቆዩ። በዚያን ጊዜ የአሪዮስ ክርስትና ትምህርት አራማጅ የሆነ ስቲሊኮ እንዳቃጠላቸው ይባላል። ነገር ግን ስለ ይዞታቸው ብዙ አይታወቅምና ከሚታወቁት 'ሲቢሊን ራዕዮች' ጋር አንድላይ አይሆኑም ብለው ምሁራን ይገመታሉ። 

አንድ ክርስቲያን ፈላስፋ አቲናጎራስ አቴናዊው ክርስቲያኖች በአረመኔ ሮማ መንግሥት በተሠቃዩበት ወቅት በ168 ዓ.ም. ወደ ቄሣር ማርቆስ አውሬሊዮስ 'አቤቱታ ለክርስቲያኖቹ' ሲጽፍ ከነዚህ ዛሬም እውቅ ከሆኑት ንግሮች ቃል ለቃል በሰፊ መጥቀሱ እርግጠኛ ነው። የጠቀሳቸው ከነሆሜርና ሄሲዮድ ጋር ሲሆን ብዙ ጊዜ 'እነዚህ መጻሕፍት ሁሉ ለቄሣር ታዋቂ ናቸው' ብሎ ጻፈ። በዚህ ጊዜ መጻሕፍቱ በሮማ ገና ይገኙ ነበርና ስለዚህ ምናልባት ከሲቢሊን ራዕዮች አንዳንድ ትክክለኛ እንደ ሆነ ይቻላል።

ሌሎች የክርስትና አባቶችና ሃዋርያት ደግሞ የሲቢሊን ራዕዮችን ጠቀሱ። ቴዎፊሎስ ዘአንጾኪያ የአንጾኪያ ጳጳስ (170 ዓ.ም. አካባቢ) ቀለምንጦስ ዘእስክንድርያ (190 ዓ.ም. አካባቢ) ላክታንትዮስ (295 ዓ.ም. አካባቢ) እና ቅዱስ አውግስጢኖስ (390 ዓ.ም. አካባቢ) ሁላቸው ጠቅሰዋቸዋል ። ዩስቲኑስ ሰማዕት (140 ዓ.ም. አካባቢ) ደግሞ አንዳንድ የሱማይ ሲቢል ትንቢቶች ጠቅሰዋል። ይህ ጥቅስ ግን ዛሬ በሚታወቁት ንግሮች መሓል አይገኝም። 

የሚከተለው ታዋቂ ጥቅስ የባቢሎን ግንብን ታሪክ ይመስላል።

ከሶስተኛው መጽሐፍ መስመሮች 119-147፦

(III: 119-147)

(III: 1004-1031) - ሲቢሊቱ ስለ ራሷ ታሪክ የምትለው:-




#Article 123: ማሞ ውድነህ (277 words)


ማሞ ውድነሀህሀህሀህሀህህ የቴአትር ደራሲ፥ ጋዜጠኛና ለ12 አመት የቀድሞው የኢትዮጵያ ደራሲዎች ማኅበር ሊቀ መንበር ነበሩ ። በአቡነ ጳውሎስ በሚመራው የሃይማኖት ኮሚቴ ውስጥ በኤርትራና በኢትዮጵያ መካከል ሰላምን ለማምጣት ጥረት ካደረጉ ሰዎችም አንዱ ነበሩ። የ54 መጻህፍት ደራሲና ተርጓሚ የነበሩት አቶ ማሞ በማስታወቂያ ሚኒሰቴር ስር በሚታተሙ ጋዜጦችና መጽሔቶች  በጋዜጠኝነት የሰሩ ሲሆን  የፖሊስና እርምጃው  ጋዜጣ መስራችና ተባባሪ ዋና አዘጋጅ ነበሩ፡፡ በኤርትራ ጠቅላይ ግዛት የማስታወቂያ ሚኒስቴር ተጠሪ ሆነዉ በተመደቡበት የጋዜጠኝነትና  የፖለቲካ ስራ በተጨማሪ ህብረት በተሰኘዉ ሳምንታዊ የአማርኛ ጋዜጣ ዘገባዎችና ትንታኔዎች ያቀርቡ ነበር።

ባደረባቸዉ ሕመም ምክንያት በተለያዩ ሆስፒታሎች ህክምናቸዉን ሲከታተሉ የነበሩት አቶ ማሞ ዓርብ የካቲት ፳፫ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል፡፡ፀሎተ ፍትሐቱ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳዉሎስ ፓትሪያሪክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ መሪነት ተፈፅሟል፡፡ አስክሬናቸውም በደራሲ ሐዲስ ዓለማየውና ሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድኅን መካነ መቃብር አጠገብ አርፏል፡፡ በቀብራቸዉ ላይ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶ/ር  ቴዎድሮስ አድሃኖም ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ወርቅነህ ገበየሁ የቀድሞዉ የአዲስ አበባ ከንቲባዎች  ከንቲባ ዘውዴ ተክሉና ከንቲባ ብርሃነ ደሬሳ ተገኝተዋል፡፡ 

ጥቅምት ፲፪ ቀን ፲፱፻፳፫ ዓ.ም. በቀድሞው የወሎ ክፍለ ሃገር በዋግ አውራጃ ዐምደ ወርቅ ከተማ ከአባታቸው አቶ ውድነህ ተፈሪና ከእናታቸው ወይዘሮ አበበች ወልደየስ የተወለዱት ማሞ ውድነህ በፋሺስት ኢጣልያ ወረራ ጊዜ ወላጆቻቸውን አጥተዋል። የሕይወት አጋጣሚ በሻጊያን በቦምብ ከደደቡት ፓይለቶች አንዱን እንዲያገኙ አብቅቶያችው ይቅር እንዳሉት በአንድ ጽሁፋቸው ዘግበዋል ። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በ 15 አመታቸው የጀመሩት አቶ ማሞ በተለያዩ ችግሮች ምክኒያት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን መጨረስ ባይችሉም በአዲስ አበባ እና አስመራ ውስጥ የሚታተሙ ፖሊስ እና እርምጃው፣ህብረት እና የዛሬይቱ ኢትዮጲያ የተሰኙ ጋዜጦች ውስጥ አገልግለዋል።  

አቶ ማሞ ከባለቤታቸዉ ወይዘሮ አልማዝ ገብሩ ስድስት ልጆችና 10 የልጅ ልጆችን አፍርተዋል፡፡

አቶ ማሞን ይበልጥ ታዋቂና ተወዳጅ ያደረጋቸው በሥነ ጽሑፉ መስክ ያበረከቱት መጠነ ብዙና ዘርፈ ሰፊ የድርሰት ሥራዎቻቸው ናቸው፡፡ 53 መጻሕፍት ያሳተሙ ሲሆን፣ 54ኛው ‹‹ጣጣኛው›› ልብወለድ በሕትመት ላይ ነው፡፡ ሥራዎቻቸው በስለላ፣ በታሪክ፣ በልብለወድና በተውኔት ላይ ያተኮሩ ናቸው፡፡ ከነዚህ ውስጥ የሚከተሉት ይገኛሉ።

    




#Article 124: ከበደ ሚካኤል (188 words)


ከበደ ሚካኤል (1909-1991) በደብረ ብርሃን ከተማ ኣካባቢ፣ ገርም ገብርኤል አጥቢያ ጥቅምት ፳፫ ቀን ፲፱፻፱ ዓ.ም.ተወለዱ። ወደ አዲስ አበባ እንደ መጡ መጀመሪያ በአሊአንስ ኢቲዮ-ፍራንሴዝ በኋላም በላዛሪስት ሚሲዮን ትምህርታቸውን ተከታተሉ። የሼክስፒርን ሮሜዎና ዡልየትን ማክቤዝን በመተርጎም እውቅናን ለማትረፍ ችለዋል።
ሌሎች ታዋቂ የትርጉም ሰራዎች መሃል፦

ከበደ ሚካኤል 30 ገደማ መፃሕፍትን ፅፈዋል።
ከበደ ሚካእል ካበረከቷቸው የቴአትር ስራዎች

ይገኙባቸዋል።

ከበደ ሚካኤል በርካታ የስነ ጽሁፍ ስራዎች ባለቤት በመሆናቸው በተለይም ለልጆች ትምህርት አዘል ጽሁፎችን የግጥም የፈጠራ ስራዎችን ቅኔዎችን በስፋት በማበርክታቸው በኢትዮጵያ የስነጽሁፍ መድረክ ገናና ከሆኑት ደራሲዎች አንዱ ናቸው። ከነዚህም መሃል፦

ሊጠቀሱ ይችላሉ።

የሰዎች ስነ ምግባር ላይ የማተኮርና ምክር አዘል መልእክቶችን የማስተላለፍ ዝንባሌአቸው በአብዛኛው ስራቸው ላይ ይንጸባረቃል።

ዘመናዊት ኢትዮጵያን ለማደርጀት በተደረገው ትግል በግንባር ቀደምትነት የተሳተፉ እኒህ ፈላስማ፥ ባለቅኔ፥ ጸሐፌ-ተውኔት፥ ደራሲና አንጋፋ ጋዜጠኛ ፥ 'የቀለም ሰው' በሀገራችን የመጀመሪያ የነበረውን የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሽልማት ድርጅት በቀዳሚነት የተቀበሉ ሲሆን፣ አዲስ ትውልድ ላፈራ ስብእናቸው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥቅምት ፳፮ ቀን ፲፱፻፺ ዓ.ም. በሥነ ጽሑፍ የክብር ዶክቶሬት ዲግሪ ሸልሟቸዋል። በተረፈም ከፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ሶቭየት ህብረትና ሜክሲኮ ሽልማትን ተቀብለዋል።

በተረፈ የትምህርት ሚኒስትር ዳይረክተር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተከታይ ዳይሬክተር (፲፱፵፪)፣ የብሄራዊ መጻህፍት ቤት ዳይረክተር (፲፱፵፬)ና የካቢኔ ሚንስትር ሆነው አገልግለዋል።

ክቡር ዶክቶር ከበደ ሚካኤል፥ ኢትዮጵያዊ 'የቀለም ሰው' ኅዳር ፫ ቀን ፲፱፻፺፩ ዓ.ም. በሰማንያ ሁለት ዓመታቸው አረፉ።




#Article 125: ቮላፒውክ (160 words)


ቮላፒውክ (Volapük) ሰው ሠራሽ ቋንቋ ነው። የተፈጠረው በ1872 ዓ.ም. ሮማ ካቶሊክ ቄስ በሆነው በዮሐን ማርቲን ሽላየር በባደን ጀርመን ነበር። ሽላየር አንድ ዓለም አቀፍ ቋንቋ እንዲፈጥር እግዚአብሐር በሕልም እንዳዘዘው አመነ። ከዚያ በኋላ የቮላፒውክ ጉባኤ በጀርመን አገር በ1876 እና በ1879 ተደርጎ እንደገና ጉባኤ በፓሪስ ፈረንሳይ በ1881 ይፈጸም ነበር። በዛ ጊዜ 283 ክለቦች 25 መጽሔቶችና 316 መጻሕፍት ስለ ቮላፒውክ ነበሩ።

የቮላፒውክ ቃላት የተለቀሙ በብዛት ከእንግሊዝኛ ሲሆን አንዳንድ ቃላት ደግሞ ከፈረንሳይኛ እና ከጀርመንኛ ተወሰዱ። ነገር ግን ቃሎቹ በጣም ተቀየሩ። ለምሳሌ 'ቮላፒውክ' የሚለው ስም የተለቀመው ከእንግሊዝኛ ቃላት world /ወርልድ/ (ዓለም) እና speak /ስፒክ/ (ንግግር) ሆኖ /ወርልድ/ ወደ vol ቮል፤ /ስፒክ/ ወደ pük /ፒውክ/ ተቀየረ። ስዋሰው ደግሞ እንደ አውሮጳ ቋንቋዎች ስዋሰው ይመስላል። 

ምሳሌ፦

ይህ ቋንቋ ለጥቂት ጊዜ ዘበናይ ሆኖ ቀረ። ነገር ግን በ1879 ሌላ ሰው ሰራሽ ቋንቋ ኤስፔራንቶ ስለ ተፈጠረ የቮላፒውክ ተነጋሪዎች ቁጥር እጅግ ተቀነሰ። በ1923 ዓ.ም. ሰዋሰው ታደሰ፤ ዳሩ ግን በአዶልፍ ሂትለር ዘመን ደግሞ በጀርመን ስለ ተከለከለ ቋንቋው ከዚያ በኋላ ሊከናውን አልቻለም። ዛሬ በዓለም ላይ ከ 20 እስከ 30 ሰዎች ይችሉታል። 

አባታችን ሆይ ጸሎት፦

አጠራሩ፦




#Article 126: ስዕል (175 words)


ስዕል ማለት በስሌዳ ላይ በቀለምም ይሁን በጠመኔ አለዚያም በርሳስና በሌላ ነገር ተስርቶ በዓይን በማየት የሚገነዘቡት ጥበብ ነው። ለዓይንና ለመንፈስ ከሚስጠው አርካታ ሌላ ፡ ያንድን ህብረተስብ ብሎም የኪነ ጥበቡን ስው ዓመለካከት ይጠቁማል ተብሎ ስለሚታመን በዘመናዊ ዓለም የተለየ እንክብካቤ የተስጠው የስው ልጅ ጥበባዊ ተግባር ነው። የዚህ አይነት ጥበብ የሚስራው ደገሞ ስዓሊ ይባላል።

የአዲስ አበባ ሥነ ጥበብ ት/በት የመጀመሪያው ርዕስ መምህር የነበረው አለ ፈለገ ስላም ስለ ስዕል ትምህርት ስያብራራ: «የስዕል ትምህርት የስውን -የእንስሳን -ያገርን -የደመናን - በጠቅላላው የሥነ ፍጥረትን መልክና ባሕርይ አጥኝ ሁኖ የራሱን ስሜት በግሉ እየፈጠረ በቀለምና በልዩ ልዩ መሳሪያዎች ከጠፍጣፋ ነገር ላይ ስርቶ ማውጣትን፥ በሐውልት ትምህርት ደግሞ አንደ ስዕሉ የተዘረዘረውን ሓሳብ ከጠፍጣፋ ነገር ላይ በመስራት ፈንታ ጠንካራ ከሆነ አካል ላይ በድንጋይ፥ በአንጨት፥ በዝሆን ጥርስ ወይም በነሐስ ቅርጽና መልክ ጻልቶ ማውጣት ነው።» በማለት ግለጸ።

ስመጥር ገብረ ክርስቶስ ደስታ ደግሞ ፡ «በዘመናዊ አቅድ ስዕል ራሱ ሐሳብ ነው። የኣንድ ነገር ሁኔታ የአንድ ነገር ትርጉምና ስሜት ነው...። ዛሪ ስው ራሱን ብቻ መመልከት ትቶ ዓለም ከብዙ ርቀት ከብዙ በኩል ሲታይ ምን ኣይነት ስሜት አንደሚስጥ - አለማዊ ዘላለማዊ የሆነውን ነገር በመተርጎም - በዓይን የሚታይ፥ የቀለም፥ የመስመርና የቅርጽ ሙዚቃ ለመፍጠር ይጥራል።» በማለት ተናግሯል።




#Article 127: ወልደያ (268 words)


ወልደያ ወይንም ወልዲያ ከደሴ ሰሜን 75 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ከላሊበላ ደግሞ በደቡብ ምስራቅ ያለ  በኢትዮጵያ የአማራ ክልል ከተማ ሲሆን በሰሜን ወሎና በወልዲያ ወረዳ ይገኛል።  ከኢኮኖሚ አንጻር ለሕንጻ ስራ የሚያገለግል የኖራ ምርት በአካባቢው በትንሹ መካሄዱ በታሪክ ይጠቀሳል። 

ከተማው በታሪካዊ ቦታወች የተከበበ ሲሆን በ1834ዓ.ም.  ወልደያን ጎብኝቶ የነበረው ሚስዮኑ ጆዓን ሉዊግ ክራፍ ደጅአዝማች ፋሪስ አሊጋዝ እና ወንድሙ ብሩ አሊጋዝ መምሪያቸውን በዚሁ ቦታ አድርገው እንደነበር ዘግቦት ይግኛል። ሁለቱ ወንድማማቾች በዚያን ወቅት ወረ ይመኑን ለመውጋት ተንቀሳቅሰው እንደነበር ይገልጻል፡፡። 

በ1880ዎቹ  ወልደያ ለዝሆን አደን ተስማሚ ስለነበር በታሪክ ተጠቃሽነት አለው። ከ1880ዎቹ እስከ 1950ዎቹ ወልደያ የየጁ አውራጃ ማዕከል ነበር።  በዚህ ወቅት፣ የወልደያ ሆስፒታል በ1929 ዓ.ም በኮንተራክተሩ M.C.M. Pollera ተገነባ። ሆስፒታሉ ሰፊ ቦታ የያዘና ለሰራተኞች ዘመናዊ መኖሪያ ቤት ያለውም ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ሆሰፒታሉ ለከተማው ነዋሪና ለተጎራባች ከተሞች (ላሊበላ፣ አላማጣ፡አፋር፣ ጎንደር) ከፍተኛ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከተማዋ ከፍተኛ የመሰረተ ልማት ግንባታ የሚታይባት ስትሆን በሶስት አቅጣጫ የሚነሱት አውራ መንገዶቹዋም በአስፓልት ኮንክሪት የተሰሩ ናቸው፡፡ የ ፪፬ ሰዓት የ ሀይድሮ ኤሌክትሪክ ፓዎር የምታገኝ ሲሆን በቅርቡ ደግሞ አንድ ዘመናዊ ስታዲዮም ለመስራት የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል፡፡ በከተማዋ ውስጥ ባጃጅ ታክሲዎች በአሁኑ ጊዜ ዋነኞቹ የህዝብ ትራንስፖርት መንገዶች ናቸው፡፡

በ  ከመሬት መቀማት ጋር በተነሳ   የቀዳማዊ ወያኒ አመጽ ተብሎ በሚታወቀው የ1940 አመጽ ከተማው ላይ  በየጁወች ጥቃት ሲደረስ፣ እስር ቤቱ ተከፍቶ እሰረኞች ተለቀቁ።  ሆኖም አመጹ የተሳካ አልነበረም  አለም አቀፍ ሃብታም በመሆኑ የሚታወቀው መሀመድ አላሙዲ በ1950ወቹ ለ10 አመት በወልደያ እንዳደገ ይጠቀሳል። ጥቅምት 8-9፣ 1980 ከተማዋ በደርግ አውሮፕላን ብትደበደብም የሞተ ሰው ግን አልተዘገበም።

ከዚህ በተረፈ ወልደያ ላይ የሚገኙት አኖማ ማርያም (በዛፎች ተሸሽጎ ዋሻ ውስጥ የተደበቀ ቤ/ክርስቲያን)  እና ወልደያ ገብርኤል ለአካባቢው ታዋቂነትን ይሰጣሉ። ገነተ ማርያምም ከወልደያ ብዙ ሳይርቅ ይገኛል።

በ 2007 በተደረገው አጠቃላይ የህዝብ ቆጠራ፣ የከተማዋ የህዝብ ብዛት 46,139 ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 23,000 ወንዶችና 23,139 ሴቶች ናቸው።




#Article 128: ደብረ ብርሃን (263 words)


ደብረ ብርሃን በሸዋ ክፍለ ሀገር የጅሩ ሸዋ ሜዳ ተጉለትና ቡልጋ አውራጃ ዋና ከተማ ናት።
ከተማዋ የሰሜን ሸዋ ዞን (አውራጃ) አስተዳደር ርዕሰ ከተማ ከመሆኗ ባሻገር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስም ዋና ጽሕፈት ቤት እዚሁ ይገኛል።

በ፲፱፻፺፰ ዓ/ም ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን እንደተመነው ደብረ ብርሃን ከተማ የ፷፯ ሺህ ፪፻፵፫ ሰው መኖሪያ ስትሆን ከነሱም ፴፬ ሺህ ፶፭ ወንዶችና ፴፫ ሺህ ፻፹፰ ሴቶች ይገኙባታል ይላል።

በሌላ ገለልተኛ የግምት ትመና ደግሞ ከተማዋ የ፶፯ ሺህ ፯፻፹ ሕዝብ መኖሪያ እንደሆነች ተገምቷል። የከተማዋ አቀማመጥ በ ላይ ነው።

ደብረ ብርሃን ከአዲስ አበባ ፻፴ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በደሴ መስመር ላይ የምትገኝ ስሆን ፱ የአስተዳደር ቀበሌዎችም አሏት። የአየር ንብረቷ ደጋማ ነው። የተቆረቆረችውና ስያሜዋን ያገኘችው ደግሞ በ፲፬፻፵፮ ዓ/ም አካባቢ በዓፄ ዘርአ ያዕቆብ (፲፬፻፴፬-፲፬፻፷፰) ነበር። ከተማዋ ድሮ የንጉሡ የግራ በአልቴሃት (ግራ በአልቴሃት ከንጉሡ ሦሥት ሚስቶች የአንደኛዋ የክብር ስም ነው) ርስት ነበረች። በ፲፬፻፵ዎቹ መጀመሪያ አጤው ከእንደግብጣን ወጨጫ ተራራ ማለትም ከአዲስ አበባ በስተምዕራብ ከነበረው ያባታቸው አጤ ዳዊት መናገሻ ሥፍራ ተነስተው ሲጓዙ በአካባቢው ውበት ስለተደሰቱ የድንኳን ከተማቸውን ከተሙባት። በኋላም ቤተ መንግሥት አሳንፀውና ባለወርቅ ጉልላት የነበረውን የሥላሴ ቤተ ክርስቲያን አሰርተው ቆረቆሯት።

ዓፄ ዘርአ ያዕቆብ ከንግሥና ዘመናቸው ፲፬ ዓመታት የሚሆነውን በደብረ ብርሃን ከተማ እንዳሳለፉና አብዛኛዎቹን የሃይማኖትና የፍልስፍና ድርሰቶቻቸውን የፃፉት በዚሁ ከተማ መሆኑ ይነገራል። 
በዘመኑም ደብረ ብርሃን ከፍተኛ የትምህርት ማዕከል የነበረች ሲሆን በንጉሡ ትእዛዝ በርካታ የሃይማኖት መፃሕፍት የትርጉም ሥራ ተከናውኖባታል።

በዓፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት የኣዲስ ኣበባ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሲጣበቡ ለሸዋ
ጠቅላይ ግዛት ተማሪዎች እንዲያገልግል ኃይለ ማርያም ማሞ ፪ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ደብረ ብርሃን ተሠራ።
ለመጀሪያዎቹ ስድስት ዓመታት ለተማሪዎቹም መጀመሪያ በየወሩ ፳ ብር በኋላም ፲፭ ብር እየተፈልላቸው ነበር የተማሩት። ከምሩቃኖቹም መካከል ዶ/ር ኣበራ ሞላ ታላቅ ወንድማቸው ዶክተር በቀለ ሞላና ታናሽ ወንድማቸው ጌታቸው ሞላ ይገኙበታል።




#Article 129: ደብረ ማርቆስ (169 words)


ደብረ ማርቆስ በኢትዮጵያ በአማራ ብሔራዊ ክልል የምትገኝ ሲሆን የምስራቅ ጎጃም ዞን ዋና ከተማ ናት። እንዲሁም ከተማዋ የ ጉዛምን  ወረዳ አስተዳደር መቀመጫ ናት። 
በ1998 ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን እንደተመነው የ85,597 ሰው መኖሪያ ሲሆን ከነሱም 43,229 ወንዶችና 42,368 ሴቶች ይገኙበታል።
መገኛ

የደብረማርቆስ ከተማ የምትገኘው በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምስራቅ ጎጃም ከአዲስ አበባ በ 300 ኪ.ሜ ከባህር ዳር ደግሞ 253 ኪ.ሜ ፣ በ 37021’ ሰሜን ላቲቲውድ እና 37º 43’ ምስራቅ ሎንግቲውድ ነው፡፡

አመሰራረት

ደብረማረቆስ ከተማ የጎጃም ገዥ በነበሩት ደጃዝማቸ ተድላ ጓሉ በ1845 ዓም የተቆረቆረች ሲሆን የከተማዋም መጠሪያ መንቆረር ይባል ነበር፡፡ በ 1872 ዓም ወደ ሥልጣን የመጡት ንጉስ ተክለሃይማኖት ካሁኑ ቅዱስ ማርቆስ ቤተክርስቲያን መመስረት ጋር ተያይዞ የከተማዋ ስያሜ መንቆረር መባሉ ቀርቶ ደብረ ማረቆስ እንዲሆን አዋጅ በማስነገራቸው የከተማዋ መጠሪያ ሊሆን በቃ፡፡ ደብረማርቆሰ በክልሉ ከሚገኙ የሪፎርም ከተሞች አንዷ ስትሆን ከተማዋ በስሯ 6 ቀበሌዎችና ማዘጋጃ ቤት ያሉት የከተማ አስተዳደር አላት፡፡ በ2002 ዓ.ም የተዘጋጀ የተቀናጀ ልማት ፕላን አላት፡፡

በሌላ ገለልተኛ ትምና ደግሞ የ60,796 ሰው መኖሪያ ተደርጎ ተገምቷል:: የከተማው አቀማመጥ በ ላይ ነው። ደብረ ማርቆስ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የመሰረተ ልማት እየተሟላላት ነው። ከተማዋ አዲስ ድረገጽ ከፍታለች።




#Article 130: ማዖሪ ቋንቋ (246 words)


ማዖሪ ቋንቋ (Māori ወይም Te Reo Māori /ቴ ሬዖ ማዖሪ/፣ በአጭሩ Te Reo «ቋንቋው») ከኒው ዚላንድ መደበኛ ቋንቋዎች አንዱ ነው። የምሥራቅ ፖሊኔዚያ ደሴቶች ቋንቋ ቤተሠብ አባል ሲሆን የታሂቲ እና የሃዋይኢ እንዲሁም የሳሞዓ እና የቶንጋ ቋንቋዎች ዘመድ ነው። የተናጋሪዎቹ ቁጥር 100,000 የሚያሕል ነው።

ኒው ዚላንድ አሁን ሦስት መደበኛ ቋንቋዎች ያሉት ማዖሪ፣ እንግሊዝኛና የኒው ዚላንድ እጅ ቋንቋ ናቸው። ስለዚህ አብዛኛው የመንግሥት ዘርፎች ሁለት ስሞች አላቸው፤ ለምሳሌ የውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር Department of Internal Affairs (/ዴፓርትሜንት ኦቭ ኢንተርናል አፈይርዝ/) በእንግሊዝኛ፣ ደግሞም Te Tari Taiwhenua (/ቴ ታሪ ታይፌኑዋ/) በማዖሪ ተብሎ ይታወቃል። ከመጋቢት 1996 ዓ.ም. ጀምሮ የማዖሪ ቴሌቪዥን አገልግሎት በመንግስት እርዳታ ኖሯል።

ማዖሪ ወደ ኒውዚላንድ ያመጡት ፖሊኔዝያውያን ሰዎች ከሌሎች ደሴቶች የደረሱ ምናልባት በታንኳ ነበር። ከ1860ዎቹ በኋላ ግን እንግሊዞች በኒው ዚላንድ በሠፈሩበት ጊዜ እንግሊዝኛ አመጡና ትምርት ቤቶች ሲከፈቱ ከ1880ዎቹ የማዖሪ ጥቅም በትምህርት ቤት ውስጥ ተከለከለ። በዚህ ብዙዎች የማዖሪ ሕዝብ እንግሊዝኛ በግዴታ ተማሩ። ነገር ግን እቤት ውስጥ፥ በአምልኮት፥ በፖለቲካ ስብሰባ ወዘተ. የማዖሪ ቋንቋ መናገሩ ፈጽሞ አልተቋረጠም። ከዚያ በላይ አንዳንድ የማዖሪ ጋዜጣም ሆነ መጽሐፍ ይታተም ነበር። በ1980ዎቹ 20 ከመቶ ማዖሪዎች ብቻ እንደ ኗሪ ቋንቋ ይችሉት ነበር። በዚያን ጊዜ ቋንቋው ለዘለቄታ እንዳይጠፋ አዲስ የማዖሪ ቋንቋ እንቅስቃሴ ተጀመረና የማዖሪ ትምህርት ቤቶች ተከፈቱ።

ማዖሪ የሚጻፍበት በላቲን ጽሕፈት አይነት አልፋቤት ሲሆን ፊደሎች እንዲህ 20 ናቸው፦

A Ā E Ē H I Ī K M N O Ō P R T U Ū W NG እና WH

ሁላቸው እንደ ተለመደ ድምጾች አላቸው 'WH' የሚያሰማው ድምጽ ግን እንደ 'ፍ' ይመስላል።

የአብዛኛው ስሞች ቁጥር የሚታይበት ዘዴ የተወሰነ መስተጻምር በመለወጡ ነው። ለነጠላ ቁጥር መስተጻምሩ te 'ቴ' ሲሆን ለብዙ ቁጥር nga 'ንጋ' ይሆናል። ስለዚህ፦




#Article 131: ማኅበረ ቅዱሳን (359 words)


ማኅበረ ቅዱሳን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃና መምሪያ ስር የሚገኝ የአገልግሎት ማኅበር ነው። ማኅበረ ቅዱሳን እግዚአብሔር ያከበራቸው የሐዋርያት የነቢያት የጻድቃን የሰማዕታት በአጠቃላይ የቅዱሳን ገድል ትሩፋትና አማላጅነት የሚዘከርበት በመሆኑ ይህን ስያሜውን አግኝቶል።

ስለ ማኅበሩ ብዙ ለማወቅ መረጃ መረቡን  ይጎብኙ። እንድሁም የህትመት ዉጤቶቹን ሐመር መጽሄትንና ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣን ያንብቡ። ከሰሜን አሜሪካ የሚያስተላልፈውንም የሬዲዮ ፕሮግራም  መከታተል ይችላሉ።

ሃይማኖታዊ አገልግሎት ለመስጠት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ስር የተቋቋመ የአገልግሎት ማኅበር ስለሆነ ማኅበሩ እንደ ተቋም የሚሰጠውም አገልግሎት ሃይማኖታዊ ነው፡፡ ለየትኛውም የፖለቲካ ዓይነትና አደረጃጀት የሚያግዝ /የሚሠራ/ እንዲሆን መቼም ቢሆን ፍላጐቱ የለንም፡፡ በማኅበሩ መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ አምስት እንደተቀመጠው «ማኅበሩ በማንኛውም የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ምንም ዓይነት ጣልቃ ገብነት አይኖረውም» ይላል፡፡ የዚህን አንቀጽ ይዘት ተግባራዊ ለማድረግ እንዲቻል በማኅበሩ ያሉ የተወሰኑ አካላት በሓላፊነት ላይ እያሉ የማንኛውም የፖለቲካ አባል እንዳይሆኑ በ1998 ዓ.ም የሥራ አመራር ጉባኤያችን ወስኗል፡፡ በውሳኔውም መሠረት የሥራ አመራር ጉባኤ አባላት፣ የሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ አባላት፣ የማኅበሩ መደበኛ መምህራን፣ የኤዲቶሪያል ቦርድ ጽ/ቤት አባላት፣ የኦዲትና ኤንስፔክሽን አገልግሎት ጽ/ቤት አባላት፣ ጋዜጠኞች፣ የማዕከላት ሰብሳቢዎች በሓላፊነት ላይ ያሉ መደበኛ አገልጋዮች የማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል አይሆኑም፡፡

ይህ ማለት ግን ለፖለቲከኞች በማኅበሩ የማገልገል ዕድል አይኖራቸውም ማለት አይደለም፡፡ ለፖለቲካ ዓላማቸው ማኅበሩን መጠቀም ግን አይችሉም፡፡ ስለዚህ የትኛውንም የማኅበሩን አባል በግሉ የ«ሀ» ወይም የ«ለ» ፓርቲ ደጋፊ፣ አባል ወይም አመራር እንዲሆን ወይም እዳይሆን ምንም ዓይነት ተቋማዊ ተጽዕኖ በማኅበሩ የሚፈጠርበት ዕድል የለም፡፡ ይህ ግን ሀገርን በመገንባት ረገድ ለአጠቃላዩ ማኅበረሰብ ትርጉም ያለው ልማታዊ ተግባራትን የማከናውን ዓላማና እንቅስቃሴ የለውም ማለት አይደለም፡፡ እንደሚታወቀው ቤተ ክርስቲያን በታሪኳ ያላት የሀገራዊ ልማት ተሳትፎ ከፍተኛ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ቀጣይነት እንዲኖረው ክርስቲያን ምሁራንና ወጣቶች ባላቸው አቅም ሁሉ ይሳተፋሉ፡፡ የልማት ተሳትፎአቸው ለሀገርና ለትውልድ እንዲጠቅም፣ ቤተክርስቲያንም ያላትን ድርሻ እድትወጣ በማሰብ ነው፡፡ ብዙዎቹ ልማታዊ ተግባሮቻችን ደግሞ በቀጥታ የቤተክርስቲያናችንን ጥቅም የሚያስጠብቁ በመሆናቸው እንቅስቃሴያችን ለሌላ ትርጉም በሚጋለጥ መልኩ የሚደረግ ነው የሚል እምነት የለንም፡፡
ማኅበራችን ቅዱስ ሲኖዶስ በሰጠው መተዳደሪያ ደንብ ላይ ተመርኩዞ አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ሁሉ ባለው የፖለቲካ ሥርዓት ከሚቋቋመው መንግሥት ጋር መሥራት ሃይማኖታዊም ሕገ መንግሥታዊም ግዴታው ነው፡፡ ከዚህ ባለፈ ግን ማኅበሩ እንደተቋም የትኛውንም የፖለቲካ አስተሳሰብ /Ideology/ በመደገፍ ወይም በመቃውም ከፖርቲዎች ጋር ግንኙነት ስለሌለው /ስለማይኖረው/ ለማንም ስጋት ወይም ዕድል ልንሆን አንችልም፡፡ በዚህ ደረጃ ፈርጆን የሚነሣ አካል ካለ ግን ለመፈረጅ ያበቁትን የመረጃ ምንጮች እንዲመረምር በዚሁ አጋጣሚ ሳልጠቁም አላልፍም፡፡
ማኅበሩ የቤተ ክርስቲያንን ትውፊት፣ዶግማና ቀኖና የጠበቁ ስዕሎች፣ስብከቶች ፣ትምህርቶች ፣ዶክመንታሪ ፊልሞች በ ያገኛሉ።
መተዳደሪያ ደንቡ በቅዱስ ሲኖዶስ ተሻሽሎ በ1994 ዓ.ም. ጸድቆ ተሠጥቶታል።።




#Article 132: ብርሃኑ ነጋ (105 words)


ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ 1958 እ.ኤ.አ. በደብረ ዘይት ከተማ ተወለዱ። እድሜያቸውም 17 ዓመት እንደሞላ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የከፍተኛ ትምህርት መከታተል ጀመሩ። በመጀመሪያ ዓመት የዩኒቨርስቲ ቆይታቸው በወቅቱ ከነበሩ ተማሪዎች ጋር በመሆን ዲሞክራሲና የስብኣዊ መብት ይከበር ሲሉ፡ ይታገሉ ከነበሩ ወጣት የአብዮቱ የበኩር ልጆች ጋር ትግላቸውን ጀመሩ። የኢህአፓ ታጋይ ሆነው ሜዳ ገቡ። ኢህአፓ አስቸጋሪ ሁኔታ ሲገጥመው በጀብሃ እርዳታ ወደ አሜሪካ ሄደው ትምህርታቸውን ቀጠሉ። በ1983 ኢህአደግ ኢትዮጵያን ሲቆጣጠር ከኢህአደግ ጋር ለመስራት የገቡ ሰው ነበሩ።

ዶ/ር ብርሃኑ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል አስተማሪ ነበሩ።  እስከ ሐምሌ 1999 ድረስ በቃሊቲ እስር ቤት ታስረው ነበር። ከሐምሌ 13 ቀን 1999 ዓ.ም. ጀምሮ መንግሥት ባደረገው ይቅርታ መሠረት ከእስር ተለቀዋል። ከተፈቱ በኋላ ወደ አሜሪካ ሄደዋል። 




#Article 133: ኤላም (975 words)


ኤላም ጥንታዊ ሃገር ነበር። ዛሬ ደቡብ-ምዕራብ ፋርስ በሆነ አቅራቢያ ተገኘ። መነሻው በዋና ከተማው በሱስን (ሹሻን) እና በካሩን ወንዝ ሸለቆ ከታሪክ መዝገብ መጀመርያ ሲሆን እስከ 547 ክ.በ. ድረስ ቆየ። ከሱመር እና ከአካድ (የዛሬ ኢራቅ) ወደ ምስራቅ የሆነ አገር ነበር። የኤላም መንግሥት ለፋርስ ከወደቀ በኋላ ቢሆንም የኤላም ቋንቋ በፋርስ አሐይመንድ መንግሥት በመደብኝነት ቆይቶ ነበር። ይህ ቋንቋ የፋርስኛ ዘመድ ሳይሆን ምናልባት ለደቡብ ሕንድ ድራቪዲያን ቋንቋዎች የተዛመደ ይሆናል።

እስከ ዛሬም ድረስ በፋርስ አገር ውስጥ ኢላም ክፍላገር ከጥንታዊው አገር ተሰይሞ ይገኛል።

ኤላማውያን የራሳቸውን ሀገር ስም ሃልታምቲ ብለው ሰይመውት ሲሆን ለጎርቤቶቻቸው ለአካዳውያን «ኤላምቱ» በመባል ታወቁ። 'ኤላም' ማለት 'ደጋ' ሊሆን ይቻላል። ከዚህ በላይ በብሉይ ኪዳን (ዕብራይስጥ መጽሐፍ ቅዱስ) አገሩ 'ኤላም' ተብሏል፤ ስሙም ከኖኅ ልጅ ሴም ልጅ ኤላም ነው።

የኤላም መጀመርያ ከተማ ሱስን ወይም ሹሻን ነበር። አንዳንዴም የሱመር አለቆች ወርረው አገሩን ይገዙ ነበር። በሱመር ነገሥታት መዝገብ ዘንድ የኪሽ ንጉሥ ኤንመባራገሲ (2384 ዓክልበ. ግድም) እንዲሁም የላጋሽ ንጉሥ ኤአናቱም (2200 ዓክልበ.) እና የአዳብ ንጉሥ ሉጋል-አኔ-ሙንዱ (2150 ዓክልበ.) ኤላምን አሸነፉት። በሌሎች ጊዜያት ኤላማውያንም ከተሞች ለምሳሌ የሐማዚ ወይም የአዋን (አቫን) ነገስታት በፈንታቸው ሱመርን ይገዙ ነበር። በአዋን ነገሥታት ዘመን የአካድ ንጉሥ ታላቁ ሳርጎን ኤላምን አሸንፎ (2075 ዓክልበ.) ከመግዛቱ በላይ በኤላም ውስጥ አካድኛን ይፋዊ ቋንቋ አደረገበት። ሆኖም ከሻርካሊሻሪ ዘመን በኋላ በ2013 ዓክልበ ግድም የአካድ መንግሥት በጉታውያን ወረራ ተሰብሮ ኤላም እንደገና ነጻ ወጣና አካድኛን ተወ። የሹሻን አገረ ገዥ የሆነ ኩቲክ-ኢንሹሺናክ ያንጊዜ የአዋን ንጉሥ ሆነና አዲስ ኤላማዊ ጽሕፈት አገባ። ኩቲክ-ኢንሹሺናክ አንሻንንና ሲማሽኪን ወደ ግዛቱ ጨመረ፤ እንኳን በ1986 ዓክልበ. ግድም እርሱ የአካድን ቅሬታ ያዘ። ነገር ግን በ1979 ዓክልበ. ግድም  የኡር ንጉሥ ኡር-ናሙ አሸነፈውና የሲማሽኪ ሥርወ መንግሥት በኤላም ተነሣ። 

በዚህ ወቅት ከመስጴጦምያ ጋር ሰላምና ጦርነት ተፈራረቀና እንኳን ገደማ የኡር ንጉሥ ሹ-ሲን ሴት ልጁን ለአንሻን መስፍን በትዳር ሰጠ። ነገር ግን የሱመር ኃይል ደክሞ ይጀምርና በ1879 ዓክልበ. ግድም፤ በሺማሽኪ ንጉስ በኪንዳታ መሪነት ኤላማውያን ከሹሻን ሕዝብ ጋር ኡር ከተማን አጠፉና ንጉሣቸውን የሹ-ሲን ልጅ ኢቢ-ሲንን ማረኩት። ከዚህ በኋላ ግን የኢሲን ከተማ ንጉሶች ኤላማውያን ከኡር አስወጥተው እንደገና ሰርተውት ኤላማውያን የበዘበዙትን ጣኦታቸውን ናና አስመለሱ። 

የሚከተለው መንግሥት 'ኤፓርቲ' ይባላል። ደግሞ ከነገስታት ማዕረግ 'ሱካልማህ' ይባላል። በ1858 ዓክልበ. ግድም የመሠረተው ንጉሥ 2 ኤፓርቲ ነበር። በዚህ ጊዜ ሹሻን በኤላም ስልጣን ብትሆንም የመስጴጦምያ ኃያላት እንደ ላርሳ ምንጊዜ ሊይዙት ሞከሩ። በ1745 ዓክልበ. ገደማ ከሹሻን ወደ ስሜን በሆነ ከተማ የነገሠ ሌላ ኤላማዊ ንጉሥ ኩዱር-ማቡግ ልጁን ዋራድ-ሲን በላርሳ ዙፋን ላይ አስቀመጠ። የዋራድ-ሲን ወንድም ሪም-ሲን ተከተለውና በብዛት መስጴጦምያን አሸነፈ። 

በዚህ ወቅት በኤፓርቲ መንግሥት ታዋቂ ከሆኑ ነገሥታት መኃል፤ ሺሩክዱቅ የባቢሎንን ሥልጣን ለመቃወም ከሌሎች አገሮች ጋር ስምምነት አደረገ። ሲዌ-ፓላር-ቁፓክ የመስጴጦምያ ነገሥታት እንደ ማሪ ንጉስ ዝምሪ-ሊም እንዲሁም የባቢሎን ንጉስ ሃሙራቢ 'አባት' ብለው ይጠሩት ነበር። ኩዱር-ናሑንተ የአካድ መቅደሶች በዘበዘ። ነገር ግን የኤላም ተጽእኖ በመስጴጦምያ አልቆየም። በ1675 ዓክልበ. ገደማ ሃሙራቢ ኤላማውያን አስወጥቶ የላርሳ ንጉሥ ሪም-ሲን ገለበጠውና መስጴጦምያን በሙሉ ገዛ። ሃሙራቢ የዘፍጥረት 14 አምራፌል ሲሆን ዋራድ-ሲን ወይም ሪም-ሲን አርዮክ እንደ ነበር ቢታስብም ዛሬ ብዙ ሊቃውንት ይህን ሃሳብ አይቀብሉም። በዚህ ምዕራፍ የተጠቀሰው ኤላማዊ ንጉስ ኮሎዶጎምር (በግሪኩ 'ኮዶሎጎሞር') ግን እንኳን ትክክለኛ ኤላማዊ ስም ('ኩዱር-ላጋማር') እንዳለው ይመስላል፤ ላጋማር የአረመኔ እምነታቸው ጣኦት ስም ነበርና።

ካሳውያን በ1507 ዓክልበ. ገደማ ባቢሎንን ካሸነፉ በኋላ ታሪካዊ ምንጮች አይበዙምና ስለ ኤፓርቲ መንግሥት መጨረሻ ዘመን ብዙ አይታወቅም።

ከክርስቶስ በፊት ከ1500 ዓመት ጀምሮ በአንሻን ከተማ ዙርያ አዳዲስ ሥርወ መንግሥታት ተነሡ። የንገስታት ማዕረግ 'የአንሻንና የሱስን ንጉሥ' ተብሎ ነበር። መጀመርያው 1500-1400 የኪዲኑ ሥርወ መንግሥት ሲሆን የሚከተለው 1400-1210 የኢጊሃልኪ ሥርወ መንግሥት ነበር። ከኢጊሃልኪ 10 ነገሥታት አንዳንዱ ካሣዊት ልዕልትን ያገባ ነበር። በ1330 ክ.በ. ገደማ የካሳውያን ንጉስ 2 ኩሪጋልዙ ለጊዜው ኤላምን ወረረ። ከዚያም በ1240 ክ.በ. ገደማ ሌላ ካሳዊ ንጉስ 4 ካሽቲሊያሽ ከኤላም ጋር ሲዋግ አላከናወነም። የኤላም ንጉሥ ኪዲን-ሑትራን በ1232 ክ.በ. የካሳውያን ንጉሥ ኤንሊል-ናዲን-ሹሚ አሸንፎ በ1230 ክ.በ. ደግሞ የካሳውያን ንጉስ አዳድ-ሹማ-ኢዲና አሸነፈ። 

የሚከተለው ሥርወ መንግሥት የሹትሩክ ነገሥታት 1210-1100 ያሕል ገዙ። 2ኛው የሹትሩክ ንጉስ ሹትሩክ-ናሑንተ በ1184 ክ.በ. ካሳውይያንን በባቢሎን ሲዋጋ የሃሙራቢ ሕገጋት የተጻፈበትን ድንጋይ ከመማረኩ በላይ የማርዱክና የማኒሽቱሹ ጣኦታትና የናራም-ሲን ሐውልት ወደ ሱስን ማረከባቸው። በ1166 ሹትሩክ-ናሑንተ ካሳውያንን በፍጹም ድል አደረጋቸው። ነገር ግን በ1130 ሱስን ለባቢሎን ንጉሥ ለ1 ናቡከደነጾር ወደቀና የኤላም ንጉሥ ሑተሉሽ-ኢንሹሺናክ ወደ አንሻን ሸሸ። ከሱ በኋላ የኤላም ታሪክ ለጥቂት መቶ ዘመን አይገኝም።

ከዚህ ዘመን እስከ 800 ክ.በ. ድረስ ስለ ኤላም ብዙ አይታወቀም። ቢያንስ አንሻን የኤላም ከተማ ሆኖ ቀረ። ኤላም ከባቢሎን ጋር በአሦር ላይ ስምምነት ያደርግ ነበር። የባቢሎን ንጉሥ ማር-ቢቲ-አፕላ-ኡሹር (992-987) ከኤላም ትውልድ እንደ ነበር ይታመናል። ኤላማውያን ከባቢሎን ንጉሥ ከማርዱክ-በላሱ-ኢቅቢ ጋራ ጦርነት በአሦር ንጉስ በ5ኛ ሻምሺ-አዳድ (831-819) ላይ አደረጉ። በዚያን ጊዜ ገዳማ ከኤላም ወደ ስሜን የማዳይ (ሜዶን) ሕዝብ በስሜን ፋርስና ዘመዶቹ ፋርሳውያን በኡርምያህ ሐይቅ ዙሪያ ተነሡ። 

ንጉሥ ሑምባኒጋሽ (751-725) ከባቢሎን ንጉሥ ከመሮዳክ ባልዳን ጋራ በአሦር ንጉስ በ2ኛ ሳርጎን ላይ ስምምነት እንዳደረገ ይታወቃል። ከሱ የተከተለው ንጉሥ 2ኛ ሹትሩክ-ናሑንተ በ718ና በ716 ክ.በ. በሳርጎን ሠራዊት እጅ ድል ሆነ። የሳርጎን ልጅ ሰናክሬም መሮዳክ-ባላዳንን ገልብጦ የራሱን ልጅ አሹር-ናዲን-ሹሚ በባቢሎን ዙፋን ላይ በ708 ክ.በ. ንጉስ አደረገው። 

ሹትሩክ-ናሑንተ በወንድሙ ሐሉሹ ተገድሎ ይህ ሐሉሻ አሹር-ናዲን-ሹሚንና ባቢሎን በ702 ክ.በ. ማረከው። ሐሉሻ ግን በኩትር-ናሑንተ እጅ ተገደለ። ኩትር-ናሑንተ ዙፋኑን ለቅቆ በኡ ፈንታ የነገሠ ሑማ-መናኑ እንደገና ከአሦር ጋር ተዋገ። ሰናክሬም ግን በ697 ክ.በ. ባቢሎንን አጠፋው። በሰናክሬም ልጅ በአስራዶን ዘመን አንድ ኤላማዊ አገረ ገዥ በደቡብ መስጴጦምያ አመፃ አድርጎ ወደ ኤላም ሸሽቶ የኤላም ንጉስ ግን ገደለው። የአስራዶን ልጅ አስናፈር በ661 ክ.በ. ሱስንን ድል አድርጎ ወረራት። በዚህ አመት ደግሞ እስኩታውያን ሜዶንን ስለወረሩ የፋርስ ነገዶች ከዚያ ወደ አንሻን ፈልሶ ንጉሳቸው ተይስፐስ ያንጊዜ አንሻንን ማረከው። ሆኖም ለጊዜው የኤላም ነገሥታት ማዕረግ 'የአንሻንና የሱስን ንጉስ' ተብሎ ቆየ።

ከዚያ በአሦር ውስጥ የብሄራዊ ጦርነት ጊዜ ስለተከተለ እንዲሁም በኤላም የብሔራዊ ጦርነት ዘመን ተነሣ። በመጨረሻ ግን አስናፈር በ648 ክ.በ. ኤላምን በሙሉ ሲያጠፋ እንኳን እርሻቸውን በጨው ዘራ። 

ከዚያ በኋላ የኤላም ኅይል ደክሞ በብዙ ትንንሽ መንግሥታት ተከፋፈለ። በመጨረሻ የፋርሶች አሐይመኒድ ነገሥታት በ546 ክ.በ. ሱሳንን ያዙት።

የኤላም መንግሥት ቢጠፋም ተጽእኖው በፋርስ መንግሥት ቀረ። ኤላምኛ ከፋርስ ሶስት ይፋዊ ቋንቋዎች አንዱ ነበር። ኤላምኛ ደግሞ የሐዋርያት ሥራ 2:9 እንደሚመስክር በ1ኛ ክፍለ ዘመን በጴንጤቆስጤ ከተሰሙት ልሳናት አንዱ ነበር።

ኤላምኛ ለጎረቤቶቹ ለሰናዓርኛም ሆነ ለሕንዳዊ-አውሮፓዊ ቋንቋዎች ወይም ለሴማዊ ቋንቋዎች ቤተሰቦች የተዛመደ አልነበረም። በኋለኛ ዘመን የተጻፈበት ከአካድኛ ባለ-ማዕዘን (ኩኔይፎርም) ጽሕፈት በተለመደ ጽሕፈት ሲሆን ከሁሉ ጥንታዊ የሆኑት ሰነዶች ግን ከዚህ በተለየ ማሥመርያ ኤላማዊ ጽሕፈት ነው የተቀረጹት። ባለፈው አመት ውስጥ ለዚህም ተመሳሳይ ጽሕፈት በጂሮፍት ፋርስ ተገኝቷል። ከዚህ በፊት ቅድመ-ኤላማዊ ጽሕፈት የሚባል የስዕል ጽሕፈት ነበረ። ይህ ግን ኤላምኛ ለመጻፍ መጠቀሙ እርግጠኛ አይደለም። 

አንዳንድ የቋንቋ ሊቃውንት እንደሚያምኑ ኤላምኛ የዛሬው ደቡብ ሕንድ ድራቪዲያን ቋንቋዎች (ታሚል ተሉጉ ወዘተ.) ዘመድ ይሆናል። በተጨማሪ በዛሬ ፓኪስታን የተገኘው ጥንታዊ የሕንዶስ ወንዝ ሥልጣኔ የሃራፓ ስዕል ጽሕፈት ስለነበረው ከኤላም ጋር ግንኙነት ሊኖር ይችላል ቢሉ፥ እስከ ዛሬ ድረስ ግን ለዚህ ጽሕፈት መፍትሔ ወይም ትርጉም ስላልተገኘም አጠያያቂ ሆኖ ቀርቷል።




#Article 134: ሌፍኮዚያ (110 words)


ሌፍኮዚያ (Λευκωσία, Lefkoşa) የቆጵሮስ ዋና ከተማ ነው።

የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር 197,600 ሆኖ ይገመታል። ከተማው   ላይ ተቀምጦ ይገኛል።

ሌፍኮዚያ በጥንት ሌድራ የተባለ ከተማ-አገር ነበር። የሌድራ ንጉስ ኦናሳጎራስ ለአሦር ንጉስ አስራዶን በ680 ክ.በ. ቀረጥ እንደ ገበሩ ይመዘገባል። 300 ክ.በ. ገዳማ በግብጽ ንጉሥ 1 ፕቶሎማዮስ ልጅ በሌኮስ አዲስ ተሰርቶ ስሙ ደግሞ ሌፍኮጤያ ሆነ። በግሪክና ሮማውያን ዘመኖች ትልቅ መንደር አልነበረም። በ340 ዓ.ም. መጀመርያ ኤጲስ ቆፖሱን ትሪፊሊዮስን ባገኘው ጊዜ ስሙ ሌድሪ ወይም ሌፍኩሲያ ተባለ። 

በወደቦቹ ላይ አደጋ በአረቦች ስለ ተጣለ ሰዎችም ወደ ሌፍኮዚያ ስለ ሸሹ ከተማው በትልቅነት አደገና በ10ኛ ክፍለ ዘመን ገዳማ የደሴቱ ዋና ከተማ ሆነ። በ1184 ዓ.ም. ፈረንጆች (የመስቀል ጦርነት ሠራዊት) ያዙትና ስሙን ኒኮሲያ አሉት። ስለዚህ እስከ ዛሬ ድረስ በምዕራባውያን አገራት ቦታው 'ኒኮሲያ' ይባላል።




#Article 135: ፓሪስ (155 words)


ፓሪስ (ፈረንሳይኛ፦ /ፓሪ/ Paris) የፈረንሳይ ዋና ከተማ ነው።
የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር የአካባቢውን ኗሪ ሲጨምር 9,854,000 ሆኖ ሲገመት የራሱ የከተማው ኗሪ ቁጥር ደግሞ 2,110,400 ሆኖ ይገመታል። ከተማው  ላይ ተቀምጦ ይገኛል።

የኬልቶች ከተማ መጀመርያ «ሉኮቶኪያ» ተብሎ በስትራቦን ተመዘገበ። ፕቶሎመይ ደግሞ ከተማውን «ለውኮተኪያ» አለው።  ዩሊዩስ ቄሳር አገሩን ሲይዘው ሥፍራውን በሮማይስጥ «ሉቴቲያ» አለው። የኖረበት ጎሣ ፓሪሲ ስለ ተባሉ፣ የከተማው ስም በሙሉ «ሉቴቲያ ፓሪሶሩም» («የፓሪሲ ሉቴቲያ») ተባለ።  በኋላ ግን በዩሊዩስ ከሐዲ ዘመን በ352 ዓ.ም. ስሙ በይፋ «ፓሪስ» ሆነ። ይኸው ዩሊዩስ ለ፫ ዓመታት የሮሜ መንግሥትን ከፓሪስ ገዛ። የሷሶን ግዛት ለፍራንኮች በ478 ዓ.ም. ወድቆ ፓሪስ የፍራንኮች ዋና ከተማ በ500 ዓ.ም. ተደረገ። ከ784 እስከ 979 ዓ.ም. ድረስ ግን ዋና ከተማቸው በአሕን ሲሆን ከዚያ በኋላ መንግሥታቸው ወደ ፓሪስ ተመለሰ። 

ከ1399 እስከ 1411 ዓ.ም. ድረስ በጦርነት ዘመን የቡርጎኝ ኃያላት ከተማውን ለመያዝ ይወዳደሩ ነበር። ከዚያም እስከ 1428 ዓ.ም. ድረስ የእንግላንድ ንጉሥ ሥራዊት ፓሪስን ይይዝ ነበር። በመጨረሻ በ1428 ዓ.ም. የፈረንሳይ ንጉሥ ኃያላት ፓሪስን ነጻ አወጡ፤ ከዚያ አመት ጀምሮ እስከ ዛሬም ድረስ ፓሪስ የፈረንሳይ ዋና ከተማ ሳይቋረጥ ቆይቷል። 




#Article 136: እየሩሳሌም (124 words)


ኢየሩሳሌም (ዕብራይስጥ፡- ירושלים ፤ አረብኛ፦ القـُدْس) የእስራኤል ዋና ከተማ ናት። በእስራእል ትልቁ ከተማ ስትሆን የምትገኝው በስተምሥራቅ በኩል ነው። በ3 ሃይማኖቶች (ለአይሁድና፤ ለክርስትና እና ለእስልምና) በጣም የተቀደሰች ናት። የድሮ ታሪኮች ስለሞሏት፣ ብዙ ሰዎች ቱሪስት ሆነው መጥትው ያዩዋታል።

እስራኤል በ1949 እ.ኤ.አ. ዋና ከተማነቱን ከቴል አቪቭ ወደ ምዕራብ ኢየሩሳሌም አዛወረች። በ1967 እ.ኤ.አ. በተዋጀ ጦርነት ምሥራቅ ኢየሩሳሌምን ደግሞ ያዘች። በ1980 እ.ኤ.አ. እስራኤል ሙሉ ከተማውን ዋና ከተማዋ ሆኖ ሾመችው። ነገር ግን አብዛኛው አገራት ይህን አድራጎት ሳይቀበሉ ኤምባሲዎቻቸው እስካሁን በቴል አቪቭ ናቸው የሚገኙ። ፍልስጤም ደግሞ ዋና ከተማውን አድርጎታልና ዛሬም በጣም ተቃራኒ ጉዳይ ሆኗል። 

በ2017 እ.ኤ.አ. (2009-2010 ዓም) ሩስያ፣ አሜሪካና ጓቴማላ ለምዕራብ ኢየሩሳሌም የእስራኤል ዋና ከተማ እንዲሆን ዕውቅና ሰጡ። አንዳንድ አገራት ደግሞ ለምሥራቅ ኢየሩሳሌም የፍልስጤም ግዛት ዋና ከተማ እንዲሆን ዕውቅና ሰጡ።

የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር 695,500 ሆኖ ይገመታል። ከተማው  ላይ ተቀምጦ ይገኛል።




#Article 137: ቭየንትዬን (108 words)


ቭየንትዬን የላዎስ ዋና ከተማ ነው።

የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር (1997 ዓም.) 200,000 ሆኖ ይገመታል። ከተማው  ላይ ተቀምጦ ይገኛል።

በላዎስ አፈ ታሪክ ጵራ ላክ ጵራ ላም ዘንድ፣ መስፍን ጣታራድጣ ከአፈታሪካዊ ላዎስ መንግሥት 'ምዎንግ ኢንጣፓጣ ማሃ ናኾኔ' በሸሸ ጊዜ፣ ሰባት ራስ ባለበት ዘንዶ ትዕዛዝ ከተማውን 'ቻንጣቡሊ ሲ ሳታናኻናሁድ' ብሎት መሠረተው።  

ይሁንና የታሪክ ሊቃውንት እንደሚሉት ግን የቀድሞ ኽመር መንደር መሆኑ ይታመናል። በ1100 ዓ.ም. ያሕል፣ የላውና የጣይ ሕዝቦች አገሩን ከቻይና ወርረው በዚያ አካባቢ የተረፉት ሕመሮች አሳለቁ። በ1552 ዓ.ም. የላን ሻንግ ንጉሥ ሠጣጢራጥ ብይፋ ዋና ከተማ አደረጉት። በ1699 ዓ.ም. የላን ሻንግ መንግሥት ሲወድቅ የራሱ ከተማ-አገር ሆነ። በ1772 ዓ.ም. ተሸንፎ ለጣይላንድ ግዛት ተጨመረ። በ1885 ዓ.ም. ለፈረንሳይ ግዛት አለፈ። የፈረንሳይ ቅኝ አገሩ መቀመጫ በ1891 ዓ.ም. ሆነ።




#Article 138: ማልትኛ (331 words)


ማልትኛ የሴማዊ ቋንቋዎች ቤተሠብ አባል ነው። በሜድትራኒያን ባሕር ውስጥ በሚገኘው ደሴት አገር በማልታ ላይ ይናገራል። መንስኤው ከቅርብ ዘመዱ ከአረብኛ ነው። ከሁሉ የሚመስለው የቱኒዚያ አረብኛ ሆኖም ከማልታ ቅርብ ጊዜ ታሪክ የተነሣ ብዙ ቃላትና ድምጽ ከጣልኛ እና ከእንግሊዝኛ ወስዷል። 

ከሴማውያን ቋንቋዎች ሁሉ ማልትኛ ብቻ በላቲን አልፋቤት የተጻፈ ነው። በ1928 ዓ.ም. ማልትኛና እንግሊዝኛ የደሴቱ መደበኛ ቋንቋዎች ተደረጉ። ከዚያ ዓመት በፊት መደበኛው ቋንቋ ጣልኛ ነበር። ዛሬ የተናጋሪዎቹ ቁጥር 371,900 ነው። ከነዚህም ውስጥ በአውስትራሊያ፥ አሜሪካና ካናዳ የሚችሉት ይገኛሉ።

በማልትኛ ከሁሉ መጀመርያው ሰነድ በ1460 ዓ.ም. አካባቢ በፔትሮ ካሻሮ የተቃኘው ግጥም ካንቲሌና ነው። ይሁንና ለረጅም ዘመን ማልትኛው ስነ-ጽሑፋዊ ሳይሆን በብዛት የመነጋገርያ ቋንቋ ነበርና ጽሕፈት የተደረገው በአረብኛ በኋላም በጣልኛ ነበር። 

የማልትኛ ስዋሰው መሠረት ከአረብኛ ሲሆን ከሮማንስ ቋንቋዎች በተለይ ከሲሲልኛና ከኖርማንኛ ቀበሌኞች ጽኑእ ተጽእኖ ይገኛል። 

ቅጽል በስም ይቀደማል። እንደ አረብኛ ወይም እንደ ዕብራይስጥ መስተፃምሩ በስምና በቅጽል ይታያል። ለምሳሌ It-tifel il-kbir ኢት-ቲፈል ኢል-ክቢር = ትልቁ ልጅ። ይህ ደንብ ግን ከሮማንስ ቋንቋዎች ለተበደሩ ስሞች ወይም ቅጽሎች አይደለም። 

የስም ቁጥር የሚታይበት ዘዴ ለሮማንስና ለሴማዊ ቃላት ይለያያል። እንደተለመደ ለሴማዊ ስሞች ብዙ ቁጥር ለማመልከት -iet ወይም -ijiet (-የት, -ኢየት) ይጨመር። ለምሳሌ art፥ አርት (መሬት) = artijiet፥ አርቲየት (መሬቶች) ይሆናል። ደግሞ እንደ ሴማውያን ልሣናት ለአንዳንድ ስሞች 'ሰባራ ብዙ ቁጥር' ይገኛል፣ ለምሳሌ ktieb ክትየብ (መጽሐፍ) = kotba ኮትባ (መጻሕፍት)፣ raġel ራጀል (ሰው) = irġiel ኢርጅየል (ሰዎች)።

ለሮማንስ ስሞች ግን የብዙ ቁጥር ባዕድ መነሻ -ኢ (-i) ሊሆን ይችላል. ለምሳሌ lingwa፥ ሊንጓ (ቋንቋ) = lingwi, ሊንግዊ (ቋንቋዎች)። 

ግሦች እንደ ሌሎች ሴማውያን ቋንቋዎች ይመስላሉ። ከተናባቢዎች ሥር ይሠራሉ ማለት ነው። ለምሳሌ 'እኛ ጻፍን' በማልትኛ ktibna 'ክቲብና'፥ በአረብኛ 'ካታብና'፥ በዕብራይስጥም ካታቭኑ ይባላል። ከሮማንስ ለተበደሩ ግሦች ቢሆንም የአረብኛ ባዕድ መነሻ ይጨመራል፥ ለምሳሌ iddeċidejna (ኢደቺደይና) 'እኛ ወሰንን'።

ማልትኛ:

አጠራር:

አማርኛ:

የማልትኛ ፊደል ከላቲን አልፋቤት መጥቶ እንዲህ ነው።

A B Ċ D	E F Ġ G Għ H Ħ I Ie J K L M N O P Q R S T U V W X Ż Z

a b ċ d e f ġ g għ h ħ i ie j k l m n o p q r s t u v w x ż z

(Y, y) የሚለው ላቲን ፊደል በማልትኛ የለም።




#Article 139: ኢየሱስ (631 words)


 
ኢየሱስ (በዕብራይስጥ: ሲጻፍ ישוע ፣ ሲነበብ፡ የሹዓ፣ ትርጉሙም፡ የሚያድን ማለት ነው) የክርስትና ሃይማኖት መሰረት ነው። ክርስቶስ ማለት በግሪክ ቋንቋ Χριστός ነው፤ ይህም መሢሕ ማለት ነው (በዕብራይስጥ ማሺያሕ ወይም 'የተቀባ' ማለት ሲሆን በተጨማሪም 
 ይባላል ትርጉሙም እግዚአብሔር ከኛ ጋር ሆነ) ማለት ነው ።  

እየሱሰ በክርስትና ሃይማኖት አንድ አምላክ ከሚሆኑት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ማለትም ከሥላሴ አንዱ ወልድ እሱ ነው ፤ ይህም ወልድ ፣ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ
 
እንደ ሰው በምድር ተመላልሶ የአባቱን መንግሥት አስተምሮ ለሰው ልጅ መዳን ሲል ራሱን አሳልፎ የሰጠ በመጨረሻም ከሞት ተነስቶ መንፈስ ቅዱስ እንዲተካው አድርጎ ወደ ሰማይ አርጎ በአባቱ ቀኝ የተቀመጠ ይህን ዓለም ለመፍረድ ዳግም ምፃቱ የሚጠበቅ አምላክ እና ፈጣሪ ነው ። ስለኢየሱስ የበለጠ ለመረዳት አዲስ ኪዳንን በተለይ ወንጌልን በአራቱ ሐዋርያት ፣ በቅዱስ ማርቆስ ፣ቅዱስ ሉቃስ ፣ ቅዱስ ዮሐንስ ፣ ቅዱስ ማቴዎስ የተፃፈውን ያንብቡ ። 

እንዲሁም አንዳንድ ሃይማኖቶች ደግሞ የእግዚአብሔር መልዕክተኛ ነው ሲሉ አንዳንዶቹ ደግሞ ነቢይ ነው ብለው ያምናሉ።

የማርያም ልጅ ኢየሱስ ከሌሎች ኢየሱሶች ለመለየት ባደገበት አገር ስም በናዝሬት የናዝሬቱ ኢየሱስ ይባላል፦ ሉቃስ 18፥37።

ከዚህም በቀር «ኢያሱ» (ወይም በግዕዝ «ኢየሱስ»፣ በግሪክ «ኢዬሶውስ»፣ በዕብራይስጥም «ያህሹዓ») የተባሉት ሌሎች ግለሠቦች  ከብሉይ ኪዳን እና ከአዲስ ኪዳን ማየት ይቻላል፦

እንደ ክርስትና እምነትና ወንጌሎች ኢየሱስ ከድንግል ማርያም እና ከመንፈስ ቅዱስ በቤተ ልሔም፣ ይሁዳ ተወለደ። ሳዱላዋ ማርያምና እጮኛዋ ዮሴፍ ለሕዝብ ቁጠራ በይሁዳ ስለ ተገኙ የቤት መጻተኞች ሆነው በጋጣ ተኝተው ነበር፤ ኢየሱስም በግርግም የተኛ እንጂ አልጋ አልነበረም። ገሊላ ግን በስሜን እስራኤል ወይም ሰማርያ ቤተሠቡ የተገኙበት ኢየሱስም የታደገበት ሀገር ነበረ።

ቤተክርስቲያን ቅዱስ ብላ የምትጠቀምባቸው ፬ መጻሕፍት ወንጌሎች በማቴዎስ፣ ማርቆስ፣ ሉቃስና ዮሐንስ እንደተጻፉት የኢየሱስን ትምህርትና ከሞላ ጐደል የሕይወት ታሪኩን ይገልጻሉ።

በነዚህ ወንጌሎች መሠረት ኢየሱስ ሲያስተምር ብዙ ጥቅሶች ይገኛሉ። ለምሳሌ፦

በዚሁ ጥቅስ ኢየሱስ ዓለሙን እንደ ገለበጠ ተብሏል። በዚያን ጊዜ ይሁዳ በባዕድ አረመኔ ሕዝብ ከባድ ገዥነት ሥር ነበረችና፣ የአይሁዶች ሊቃውንት ከትንቢት የተነሣ ከሮሜ ዕጅ የሚያድናቸውን መሢሕ ይጠብቁ ነበር። ይህ አይነት ትንቢት ቢገኝም ኢየሱስ ያንጊዜ በጦርነት ስላላነሣ የአይሁድ መሪዎች ሊቀበሉት ፈቃደኛ አልነበሩም።

ደግሞ «እግዚአብሔር ምኑን ይፈልጋል?» ለሚለው ለዘመናት ፍልስፍና ጥያቄ በመመልስ ኢየሱስ በብሉይ ኪዳን ትንቢተ ኢሳይያስ ውስጥ ይህን መልስ አገኝቶ ብዙ ጊዜ ያጠቁመው ነበር፦

ለሚሰሙት ተከታዮቹ ግን አዲስ ጥያቄ ጠየቃቸው፣ እንዲህ ሲል፦

በወንጌላት በኩል እጅግ በርካታ ተመሳሳይ ትምህርቶች በቀላሉ ሊነቡ ይቻላል።

ደግሞ ይዩ፦ 

በተዋሕዶ አብያተ ክርስትያናት እምነት ትምህርት፣ የኢየሱስ ሰብአዊና መለኰታዊ ባሕርይ አንድ (ተዋሕዶ) ነው። ከካልኬዶን ጉባኤ ጀምሮ ግን በሮማ ቤተክርስትያን ትምህርት ዘንድ በሁለት ልዩ ልዩ ሰብአዊና መለኰታዊ ባሕርዮች ተለይቷል። ኢየሱስ ወልድ ሆኖ ከሥላሴ (አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ) አንዱ ክፍል በመሆኑ አምላክ ነው በማለት በንቅያ ጸሎተ ሃይማኖት ይስማማሉ። «ቃሉ ሥጋ ሆነ» ሲባል፣ ፈጣሪው ወደ ፍጥረቱ በሙሉ በመግባት ዓለሙን ለማዳን ኃይልና ፈቃድ እንዳለው ገለጸ ለማለት ነው።

ከዚህ በላይ ስለ ኢየሱስ ማንነት ብዙዎች አብያተ ክርስትያናት ከአዲስ ኪዳን ጠቅሰው እንደሚያስተምሩት የሚከተለውን እንረዳለን

ከሁለት ሺህ ዓመት በፊት በሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ አንድ እንግዳ ሰው ብቅ አለ፡፡ ይህ ሰው በአለም ውስጥ የተወለደ ቢሆንም፣ ልክ እንደማንኛውም ሰው ሰብአዊ ማንነት ቢኖረውም ተራ ሰው አልነበረም። ከድንግል ማርያም በመንፈስ ቅዱስ ተፀንሶ ወደ ምድር የመጣው፣ በሰው አምሳል የተገለጠው ራሱ እግዚአብሔር ነው፡፡ ይህ ሰው (የእግዚአብሔር ልጅ) ነው (ሉቃስ 1፡26-35)፣ (ዮሐንስ 1፡1 እና ዮሐንስ 1፡14)።

በብሉይ ኪዳን ስለሚመጣው መሢህ (ክርስቶስ) ሲተነበይ ከመጠሪያዎቹ አንዱ አማኑኤል በዕብራይስጥ  «ኢሜኑ» (ከኛ ጋር) «ኤል» (አምላክ) ወይም አምላክ ከኛ ጋራ ማለት ነው። ምድር የእግዚአብሔር መረገጫ እንደ ተባለች (ኢሳይያስ 66:1 እና ) ወደፊት «ከወንዝ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ» ለዘላለም የሚነግስ ብለው የተነበዩለት አምላክ የሚሉት እግዚአብሔር ነው።

(ዮሐ 14፡7-11)፡፡ በተጨማሪ ዮሐንስ 1፡18 ይመልከቱ።

ኢየሱስ በምድር ሕይወቱ እኛ የምንቀበለውን የሕይወት ችግሮች በሞላ አይቷል፤ ስለዚህም ሊራራልን ይችላል። (ዕብ 4፡15)፡፡ በተጨማሪ ማቴዎስ 8፡17 ይመልከቱ።

ኃጢአተኛ ሰዎች፣ ኢየሱስን እንደ ወንጀለኛ ከእንጨት በተሰራ መስቀል ላይ ቸነከሩት፡፡ ራሱን ከዚህ ማዳን ቢችልም፣ አላደረገውም፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር አለሙን የሚያድነው በእርሱ የመስቀል ላይ ሞት ነበርና፡፡ ስዚህ ኢየሱስ ስለ እኛ ሞተ! (ማር 15፡16-39 ያንብቡ) (1ጴጥ 2፡24)፡፡ በተጨማሪ ኢሳያስ 53፡5፣6 ያንብቡ፡፡

ከሦስት ቀን የመቃብር ቆይታ በኋላ እግዚአብሔር ልጁን ከሙታን መካከል አስነሳው! (ማቴዎስ 28 ያንብቡ)፡፡ ትንሳኤውም ጭምር ለእኛ ሲል ነበር፡፡ (ኤፌ 2፡4-6)፡፡ በተጨማሪ ሮሜ 6፡4 ያንብቡ፡፡

በምድር ላይ የነበረውን ሥራ በፈፀመ ጊዜ ኢየሱስ ወደአባቱ ዘንድ ወደሰማይ አረገ፡፡ ይህም ጭምር ለእኛ ነበር፡፡ ምክንያቱም አሁንና ለዘላለሙ ከእርሱ ጋር አብረን ለመኖር ወደ እግዚአብሔር መገኛ የምንሄድበት መንገድ ከፍቶልናል፡፡ (ዕብ 10፡19-22)፡፡ በተጨማሪ ዮሐንስ 14፡1-3 ይመልከቱ።
ለተጨማሪ መረጃ የሚከተለውን አድራሻ ይጎብኙ፡ 




#Article 140: ሲንጋፖር (393 words)


ሲንጋፖር ከተማ-አገር ነው። 

የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር 3,438,600 ሆኖ ይገመታል። ከተማው  ላይ ተቀምጦ ይገኛል።

የግሪክ መልክዐ ምድር አዋቂ ቶሌሚ (150 ዓ.ም. ግድም) በዚያ ሥፍራ ሳባና የተባለ የንግድ ወደብ በካርታው ላይ አሳየ። በ250 ዓ.ም. ግድም ደግሞ አንድ ቻይናዊ መዝገብ በዚያው ቦታ ፑ ልዎ ቾንግ የተባለ ደሴት ይገልጻል። በ680 ዓ.ም. ገዳማ ደሴቱ በሽሪዊጃያ መንግሥት ግዛት መካከል ሆነ። ከ1300 ዓ.ም. በፊት ተማሲክ የተባለ መንደር ነበረበት። በአንድ ትውፊት ዘንድ ሳንግ ኒላ ኡታማ የሚባል የሽሪዊጃያ መስፍን ያንጊዜ ስሙ ሲንጋፑራ («የአንበሳ ከተማ») የሚባል ከተማ በተማሲክ ደሴት ላይ ሠራ። 

በ1400 ዓ.ም. አካባቢ የሽሪዊጃያ መንግሥት ሲደክም ጎረቤቶቹ ማጃፓሂትና ሲያም ይታግሉበት ነበር። ሆኖም ሲንጋፖር ሽሪዊጃያን የተከተለው የመላካ ሡልጣንነት ማዕከል ሆነ። በ16ኛው ክፍለ ዘመን ዓ.ም. ላይ ይህ ሡልጣንነት ከፖርቱጋል ጋር ተጣለና በ1605 ዓ.ም. ፖርቱጊዞች ሲንጋፖርን አቃጠሉት። 

የነበረው ከተማ ጠፍቶ ዙሪያው በፖርቱጊዞች ይገዛ ነበር፤ ብዙም ሳያልፍ የሆላንድ ነጋዴዎች ዙሪያውን አስተዳደሩ። የሲንጋፖር ደሴት እራሱ በይፋ በጆሖር ሡልጣን ግዛት ነበር። በ1811 ዓ.ም. የእንግሊዝ አገረ ገዥ ስታምፎርድ ራፈልዝ የሆላንድ ነጋዴዎችን ላዕላይነት ለማቃወም አስቦ ፡ የጆሖር ሡልጣን ጣውንት ወንድሙን ለሡልጣንነቱ ደግፎ ፡ በደሴቱ ላይ አዲስ ከተማ ለመመሥረት ፈቃድ በዚያ አገኙ። የብሪታንያ ቅኝ አገርና ንግድ ጣቢያ ሆኖ በቶሎ አደገ፤ በ1815 ዓ.ም. ጆሖር ደሴቱን ለእንግሊዝ መንግሥት ሸጠው። በብዛት በሲንጋፖር የሰፈሩት ሰዎች ቻይናዊ ነበሩ። 

ከ1934 እስከ 1937 ዓ.ም. በ2ኛው አለማዊ ጦርነት የጃፓን ሃያላት ሲንጋፖርን በግፍ ያዙ፤ በዚህም ወቅት የከተማው ስም ሾናንቶ ተብሎ ይሉት ነበር። ከጦርነቱ በኋላ ሲንጋፖር በ1950 ዓ.ም. ራስ-ገዥ ሁኔታ ከእንግሊዝ አገኘ። በ1956 ዓ.ም. ግን በነጻ ፈቃዱ ሲንጋፖር በአዲሱ የመላይዢያ ፌዴሬሽን ውስጥ ክፍል ሆነ። ይህ ሁኔታ እስከ 1957 ዓ.ም. ብቻ ድረስ ቆየ፤ ትብብሩ ለጸጥታ ተስማሚ ስላልሆነም መላይዢያ ሲንጋፖርን ከፌዴሬሽኑ አስወጥቶ የዛኔ እስካሁን ድረስ የሲንጋፖር ሬፐብሊክ ሆነ።

በሲንጋፖር 4 ይፋዊ ልሳናት አሉ። እነርሱም መላይኛ፣ እንግሊዝኛ፣ ቻይንኛ (ፑቶንግኋ) እና ታሚልኛ ናቸው። መላይኛ ደግሞ ብሔራዊ ቋንቋ ነው። 

ሲንጋፖር አደንዛሽ የሚከለክል በጣም ጥብቅ ሕግ አለው፣ በአደንዛሽ የሚነግዱ ይሙት በቃ ሊቀበል ይቻላል። የሲንጋፖር ሕግጋት ሁሉ ጥብቅ ናቸው፤ ከባድ ቅጣቶች ይሰጣሉ። ሽንት ቤት ከመጠቀም ቀጥሎ በውሃ ጠርጎ መሄድ  እንዳይቀር ክልክል ነው። በገሃድ መትፋት የገንዘብ መቀጫ ያመጣል። ጠበንጃም ሆነ የኪስ ቢላዎ ተከለክለዋል፣ ማስቲካ ስንኳ በሕግ የተከለከለ ሥራ ነው። የሲንጋፖር መንግሥት አንዳንድ ፊልም ብቻ ይፈቅዳል፣ ብዙ ጊዜ በሃይማኖት፣ በዘርኛነት፣ ወይም በእራቁት ምክንያቶች የሚከለክሉ ፊልሞች አሉ። 

የሲንጋፖር የሚጣፈጥ አበሳሰል ብዙ አይነት የባህር ምግቦችን እንደ ሠርጠን፣ ኦይስተርና ካላማሪ (ስኩዊድ) ያጠቅልላል።  በሕንድ ሠፈሮች የአትክልት ቡፌ በሙዝ ቅጠል ላይ ተስፋፍቶ ይቀርባል።

ብዙ በዓላት በሲንጋፖር ይከብራሉ። ጣይፑሳም በተባለው በዓል ቀን ላይ አንዳንድ ሰው የሰውነት መውጋቶች ይሠራል። የቡዲስም፣ እስልምና፣ ክርስትና፣ እና የሕንድ ሀይማኖት በዓላት ሁሉ በሲንጋፖር ይከብራሉ። 

ብዙ የክላሲካል ሙዚቃ ወዳጆች በሲንጋፖር ይገኛሉ። ይህን የሚመሰክር በሕዝባዊ አጸዶች ቦታ ውስጥ ለአቀናባባሪው ሾፐን ትዝታ በተሠራው ሐውልት ነው።   




#Article 141: ሞቃዲሾ (149 words)


ሞቃዲሾ (ሶማልኛ፦ Muqdisho ሙቅዲሾ) የሶማሊያ ዋና ከተማ ነው።

የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር 1,208,800 ሆኖ ይገመታል። ከተማው  ላይ ተቀምጦ ይገኛል።

በ50 ዓም ገደማ በግሪክኛ በተጻፈው «የቀይ ባሕር ጉዞ» ዘንድ፣ ከ«በርበሮች» ነጻ ከተሞች (በሶማሊያ ስሜን ዳር) በኋላ፣ ከሶማሊያ ምዕራብ ዳር  ጀምሮ እስከ አሁን ሞዛምቢክ ድረስ ያለው ጠረፍ ወይም «አዛኒያ» ለሒምያር (የመን) ንጉሥ ካሪብ ኢል ተገዥ ነበር። በዚህም ጊዜ «የሳራፒዮን ፈሳሽ» ይጠቅሳል፣ ይህም የሞቃዲሾ ሥፍራ (ዋቢ ሸበሌ ወንዝ አፍ) እንደ ነበር ይታስባል። 

ሞቃዲሾ ከ686 ዓ.ም. ጀምሮ ታውቆአል። በዚያን ጊዜ ሡልጣን አብዱል ማሊክ ቢን ሙሪያሚ እንደራሴውን እንደሾመበት ይባላል። የወደቡም መጀመርያ ስም «ሐማር» ተባለ። ከመካከለኛ ዘመን በናዲር ብዙ መሐለቅ ከቻይና በመገኘቱ፣ ከሩቅ አገሮች ንግድ እንደ ተደረገ ይመሰክራል። የዛንዚባር ሡልጣን በ1863 ዓ.ም. ከተማውን ያዙ። እሳቸው በ1884 ዓ.ም. ለጣልያኖች አከራዩት። በ1897 ዓ.ም. ጣልያኖች በሙሉ ገዙትና የጣልያ ሶማሊያ መቀመጫ ሆነ። የእንግሊዝ ሃያላት ከጣልያ በ2ኛ አለማዊ ጦርነት በ1933 ዓ.ም. ያዙት። በኅዳር ወር 1942 ዓ.ም. ጣልያኖች እንዲመልሱ ተፈቀደ። በ1952 ዓ.ም. ሶማሊያ ነጻ አገር በሆነበት ወቅት ሞቃዲሾ የአገሩ ዋና ከተማ ሆነ።




#Article 142: ደማስቆ (131 words)


ደማስቆ (ወይም ደማስቆስ፤ አረብኛ፦ دمشق) የሶርያ ዋና ከተማ ነው።

የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር የአካባቢውን ኗሪ ሲጨምር 2,381,800 ሆኖ ሲገመት የራሱ የከተማው ኗሪ ቁጥር ደግሞ 1,861,900 ሆኖ ይገመታል። ከተማው  ላይ ተቀምጦ ይገኛል።

በአንዳንድ ሊቃውንት ዘንድ፣ ደማስቆ ከሁሉ ይልቅ ረጅሙ እድሜ ያለው ከተማ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ዘንድ በአብርሃም ዘመን ይገኝ ነበር። በፍላቪዩስ ዮሴፉስ ዘንድ በአራም ልጅ በዑፅ ተሠራ። ሚካኤል ሶርያዊው (12ኛው ክፍለ ዘመን) እና ባር ሄብራዩስ (አቡል-ፋራጅ) (13ኛው ክፍለ ዘመን) እንዳሉ ግን ዮሴፉስ ተሳተና «ሞርፎስ» ወይም «ሙሪፖስ» በተባለ ኬጢያዊ ሰው ተሠርቶ ነበር። 

ደማስቆ በኤብላ በተገኙት የኤብላ ጽላቶች (2100 ዓክልበ. ግድም) «ደማሽኪ» ተብሎ ይጠቀሳል። የሁክሶስ ሕዝብ በ17ኛ ክፍለ ዘመን ዓክልበ. ግብጽን በገዙበት ወቅት፣ ደማስቆ በአሙሩ ግዛት ውስጥ ነበር። በአማርና ደብዳቤዎች (1350 ዓክልበ. ገዳማ) ዲማስቁ ተብሎ በንጉሱ ቢርያዋዛ እንደ ተገዛ ይጻፋል። ከ1100 እስከ 740 ዓክልበ. ድረስ የአራም ከተማ-አገር ነበር። በዚያን ጊዜ የአሦር ንጉስ 3 ቴልጌልቴልፌልሶር ያዘው። 




#Article 143: ሀኖይ (130 words)


ሀኖይ (Hà Nội) የቪየትናም ዋና ከተማ ነው።

የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር የአካባቢውን ኗሪ ሲጨምር 2,543,700 ሆኖ ሲገመት የራሱ የከተማው ኗሪ ቁጥር ደግሞ 1,396,500 ሆኖ ይገመታል። ከተማው  ላይ ተቀምጦ ይገኛል።

ሃኖይ ዕጅግ ጥንታዊ ከተማ ሆኖ ባታሪክ መዝገብ ብዙ ስሞች ነበሩት። ድሮ ቻይናዎች ቬትናምን ከገዙ በፊት ከተማው ቶንግ ቢኝ ተባለ፤ በኋለኛ ዘመን ደግሞ ሎንግ ዶ ሆነ። በ858 ዓ.ም. ስሙ ዳይ ላ ሆነ። በ1002 ዓ.ም. ዋና ከተማ ሲሆን ስሙ ደግሞ ጣንግ ሎንግ ሆነ። ከ1002 እስከ 1389 ዓ.ም. ድረስ የቬትናም ዋና ከተማ ሲሆን ቆየ። በ1389 ስሙ ደግሞ ዶንግ ዶ ሆነ። በ1400 ዓ.ም. ቻይናዎች ወርረው ያዙትና ስሙን ዶንግ ጯን አሉት። በ1420 ዓ.ም. ወደ ቬትናም ሕዝብ ሲመለስ ስሙ በዚያን ጊዜ ዶንግ ኪኝ ሆነ። ከ1770 እስከ 1794 ዓ.ም. ድረስ ስሙ ባክ ጣኝ ሆነ። በ1794 ዓ.ም. እንደገና ስሙ ጣንግ ሎንግ ሆነ። በመጨረሻም በ1823 ዓ.ም. ስሙ ሃኖይ (ሃ ኖይ) ሆኗል። 




#Article 144: ሰንጠረዥ (325 words)


ሰንጠረዥ (ወይም ቼዝ) በዓለም ዙሪያ የተወደደ ጥንታዊ የገበታ ጫዋታ ነው። 

ስለ ሠንጠረዥ መጀመርያ በአብዛኛው የታሪክ ሊቃውንት የተቀበለው ሀልዮ በሕንድ አገር ከ500 ዓ.ም. ግድም አስቀድሞ እንደ ተለመደ የሚለው ነው። ሆኖም ከዚያ በፊት ግሪኮች በታላቁ እስክንድር ዘመን ወደ ሕንድ እንዳስገቡት የሚያስቡ ደራስያን ኖረዋል። በዚህ ሀሣብ በትሮያን ጦርነት ወቅት (1200 አክልበ. ያሕል) በፓላሜዴስ ተፈጠረ። እንኳን ከግሪኮች በፊት የእስኩቴስ ሰዎች እንዳወቁት የሚል አስተሳሰብ ደግሞ ሊገኝ ይቻላል። 

በሕንድ አገር በድሮ 2 ተመሳሳይ ቻቱራንጋ የተባሉት ጨዋታዎች ነበሩ፦ እነርሱም ባለ 4 እጅ ቻቱራንጋ እና ባለ 2 እጅ ቻቱራንጋ ናቸው። «ቻቱራንጋ» የሚለው ቃል በሳንስክሪት ቋንቋ ከ«ቻቱር» (አራት) ማለት 'አራት መደቦች' ነው። 

ባለ 4 እጅ ቻቱራንጋ ላይ፣ አራት ሠራዊት በአራት ሰዎች ይታዘዛሉ። እያንዳንዱ ተጫዋች 1 ንጉስ፣ 1 ዝሆን (ግንብ)፣ 1 ፈረስ፣ 1 መርከብ (ጳጳስ) እና 4 ወታደር ይቀበላል። መርከቡም በማዕዘን ጀምሮ ሁለት ቦታ ብቻ በሰያፍ ይዘልላል። ይህ ጨዋታ ከጥንት በዛህራ ይጫወት ነበር። ቁማር ግን ጽድቅ እንዳልተቆጠረበት መጠን ያለ ምንም ዛህራ ደግሞ ተጫውቷል። በአንዳንድ ደራሲ አስተሳሰብ ዘንድ፣ ይህ አይነት ቻቱራንጋ በቀዳሚ የታወቀው ነው። ነገር ግን በጽሑፍ ዘንድ የመኖሩ ማስረጃ ከ1000 ዓ.ም. ብቻ ስለሚገኝ፣ የዛሬ ታሪክ ሊቃውንት ይህን አሳብ አይቀበሉም። 

ባለ 2 እጅ ቻቱራንጋ በጽሁፍ የሚታወቅ ከ500 ዓ.ም. ገዳማ ነው። በዚህ አይነት 2 ሠራዊቶች አሉ። እንደ ዛሬ ቼዝ እያንዳንዱ ሠራዊት 2 ግንቦች፣ ፈረሶችና ጳጳሳት፤ 8ም ወታደሮች አሉት። በንግሥት ፋንታ ግን 'አማካሪ' (ጠቅላይ ሚኒስትር) የሚባል ክፍል አለ። ይህ ክፍል ደካም ነው፤ 1 ቦታ በሰያፍ ብቻ ይሄዳል። 

ከሕንድ አገር ጨዋታው በ550 ዓ.ም. ወደ ፋርስ መንግሥት እንደ ገባ የሚሉ ታሪኮች አሉ። በፋርስኛ የሳንስክሪት ስም «ቻቱራንጋ» ተለውጦ «ቻትራንግ» ሆነ። ከዚህ ትንሽ በኋላ አረቦች ወረሩና ጨዋታውን ወድደው በቋንቋቸው ስሙን «ሻትራንጅ» አደረጉት። በኋለኛ ግሪክ ቋንቋ ደግሞ የሻትራንጅ ስም ወደ «ሳንትራዝ» ተለወጠ። «ሰንጠረዥ» የሚለው የአማርኛ ቃል ከዚህ ግሪክ ቃል እንደ ተነሣ ይመስላል። 

በኢትዮጵያ ባህላዊ ሰንጠረዥ፣ ክፍል እስከሚማረክ ድረስ ተጫዋቾቹ እንደ ልባቸው (አለተራ) ይጫወታሉ። አለዚያ ጳጳሳትና ንግሥት ደካም በመሆናቸው እንደ ሻትራንጅ ይመስላል።

በዘመናዊ አውሮጳዊ ቼዝ (ከ1550 ዓ.ም. ጀምሮ) ጳጳስ እስከሚቻል ድረስ በሰያፍ ይጓዛል። ንግሥትም እስከሚቻል ድረስ በማንኛውም አግጣጫ ትሄዳለች። በተጨማሪ አንዴ ንጉስና ግንብ አንድላይ ሊዛወሩ የሚፈቅድና እንዲህ የሚመስል ልዩ ደንቦች አሉ። የ«ቼዝ» ስም ግን ከ«ቻቱራንጋ / ቻትራንግ» ሳይሆን ከፋርስኛ ቃል «ሳሕ-ማት» (የንጉሥ አደጋ) ተነሣ።




#Article 145: ራዲዮ (238 words)


ራዲዮ   ራዲዮ ሞገዶችን በመከርከም መልዕክት  ከቦታ ቦታ የሚተላለፍበት ቴክኖሎጂ ነው።   ራዲዮ ሞገድ የብርሃን አይነት ሞገድ ሲሆን ልዩነቱ የራዲዩ ሞገድ የብርሃንን ያኽል አይርገበገብም።  የራዲዮ ሞገድ  በአየርም ሆነ በወና ውስጥ  የሚጓዘው የኤሌክትሪክ መስኩን በማርገብገብና ሞገድ በመፍጠር ነው።  ይህን ሞገድ ባህርዩን በዘዴ በመቀየር (በመከርከም) መልዕክት እንዲያዝል ተደርጎ ይላካል። ለምሳሌ የራዲዮ ሞገዱን ቁመት በአንድ  ድምፅ ሞገድ ትክክል ተከርክሞ ሲጫን   ኤ.ኤም ራዲዮ ይፈጠራል።  በራዲዮ ሞገዱ ድግግሞሽ ላይ ሲጫን ደግሞኤፍ.ኤም ራዲዮ ይሆናል። በሞገዱ ቅድመት ላይ ሊጫን ይችላል፣ ሆኖም ይሄ ብዙ ጊዜ የተለመደ አይደለም።  በድምፅ ሞገድ ትክክል የተከረከመው የራዲዮ ሞገድ ኤሌክትሪክ አስተላላፊ ቁስ ሲያጋጥመው በቁሱ ውስጥ ተለዋዋጭ የኤሌክትሪክ ጅረት ይፈጥራል። ይህን ተለዋዋጭ ጅረት የሚተረጉሙ መሳሪያወች የተጫነውን ድምፅ ከራዲዩ ሞገዱ አውርደው ወደ ስፒከሩ በመላክ የራዲዮ ዝግጅት እንዲደመጥ ይሆናል።  ከድምፅ በተጨማሪ የምስል መልዕክትም ሊላክ ይችላል፣ በዚህ ወቅት የቴሌቪዥን ዝግጅት እንዲታይ ይሆናል።

የራዲዮ ቴክኖሎጂ ብዙ ተማሪወችንና ብዙ ጊዜ የወሰደ ጥረት ነው እንጂ ያንድ ሰው ድንገተኛ ፈጠራ አይደለም። ሆኖም አንድ አንድ ተማሪወች ከሌሎች በተለየ መልኩ ጉልህ አስተዋጾ ስላደረጉ በታሪክ ተጠቃሽ ናቸው፣ ከነዚህ ውስጥ ቶማስ ኤድሰን፣ ኒኮላ ቴስላ እና ጉልየልሞ ማርኮኒ ዋናዎቹ ናቸው።  በ1885 ዓ.ም. ኒኮላ ቴስላ እንዴት መልዕክትን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ያለ ሽቦ ማስተላለፍ እንዲቻል አሳየ ። ከዚያ በኋላ ተመራማሪወች፣ አንዱ ያንዱን ስራ በማሻሻል በ1887 ዓ.ም.  ማርኮኒ ያለ ሽቦ መልዕክትን ከአንድ ቦታ ወደሌላ ሩቅ ቦታ የሚያስተላልፍ ስርዓት በተጨባጭ በመገንባት (2.4 ኪሎ ሜትር) በሚቀጥለው አመት ደግሞ ከእንግሊዝ አገር ለራዲዮ ፈጠራ ፓተንት በማግኘት አሁን ድረስ ስሙ ተጠቃሽ ነው። በ1889 ማርኮኒ የመጀመሪያውን የራዲዮ ማሰራጫ በአይል ኦፍ ራይት፣ እንግሊዝ በመክፈት እንዲሁም የራዲዮን ማምረቻ ፋብሪካ በማቋቋም ስሙ ከራዲዮ ፈጠራ ጋር እንዲቆራኝ ሆነ።




#Article 146: ኤስቶኒያ (173 words)


ኤስቶኒያ በባልቲክ ባሕር ላይ የተገኘ አገር ሲሆን 1.4 ሚሊዮን ያህል ሕዝብ ይኖሩበታል። መደበኛ ቋንቋቸው ኤስቶንኛ የፊንላንድኛ ዘመድ ነው። የኤስቶኒያ ብሔር ከጥንት ጀምሮ በአገሩ ኑረዋል። እስከ 13ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ አረመኔ አገር ነበረ፤ ያንጊዜ ክርስቲያን መስቀለኞች ያዙት። በ16ኛው ክፍለ ዘመን ከፕሮቴስታንት እንቅስቃሴና ከጦርነቶች በኋላ ኤስቶኒያ ለስዊድን ሥልጣን ወጣ፣ በ1713 ዓ.ም. ወደ ሩስያ ተዛወረ። በዚህ ዘመን ሁሉ ግን እስከ 1808 ዓ.ም. ድረስ የኤስቶኒያ ሕዝብ ገበሬዎች ሆነው የጀርመን ገዢዎች ነበሩዋቸው። ጀርመኖች በ1ኛው ዓለማዊ ጦርነት ወርረው የሶቭየት ኅብረት በተነሣ ጊዜ ኤስቶኒያ ነጻ መንግሥት ሆነ። በ1932 ዓ.ም. ግን የሶቭየት ኅብረት በግፍ ጨመረው። ዩናይትድ ስቴትስ ይህንን አድራጎት መቸም አልተቀበለም። የሶቭየት ህብረት በ1983 ዓ.ም. በወደቀበት ዘመን ኤስቶኒያ ዳግመኛ ነጻ ሪፐብሊክ ሆነ። ፓርላማውና ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዲሞክራስያዊ ምርጫ ይመረጣሉ። በ1996 ዓ.ም. የአውሮፓ ኅብረት እንዲሁም የናቶ አባል ሆነ። ከ2003 ዓ.ም. ጀምሮ መደበኛ ገንዘቡ ዩሮ ሆኗል። 

ብዙ ኗሪዎች ከአገሩ በመውጣታቸው፣ የልደትም ቁጥር በቂ ባለመሆኑ የኤስቶኒያ ሕዝብ ቁጥር ከ1983 ዓ.ም. ጀምሮ በየዓመቱ እየተቀነሰ ሆኗል። ኤስቶኒያ በዘመናዊው መረጃ ኅብረተሠብ ከፍተኛ ሚና ወስዷል፤ የተደረጀ ኢንተርነት መንግሥት አገልግሎት አለው። ለመሆኑ አሁን ትኩስ የሆነ መስሪያ ስካይፕን የፈጠረው ድርጅት ከኤስቶኒያ ነው። ይህም ድርጅት ከ10 አመት በፊት ትኩስ የነበረውን ካዛዓ ፈጠረ። 




#Article 147: አየርላንድ ሪፐብሊክ (100 words)


በሰኔ ፪፻፱ ዓ/ም ሊዮ ቫርድከር ጠቅላይ ሚኒስትር (ቲሻሕ) በመሆኑ አይርላንድ ከሉክሳምቡርግና አሁን ከሰርቢያ ጋር በዓለም ላይ ብቸኛ በገሃድ ግብረሰዶማዊ የመንግሥት መሪ ያላቸው ሀገራት ናቸው። ከዚህም በፊት አይስላንድ (ከ2001-2005 ዓም) እና በልጅግ (ከ2004-2007 ዓም) በገሃድ ሰዶማዊ ጠቅላይ ሚኒስትሮች ነበሯቸው። ከ2001 ዓም በፊት መጨረሻው በገሃድ የሆነ ሰዶማዊ መሪ በ214 ዓም ነበር (የሮሜ መንግሥት ቄሣር ኤላጋባሉስ)። 

በ2011 አም ይሕ የአየርላንድ ግብረሰዶማዊ መሪ ወደ አፍሪካ፣ ኢትዮጵያና ላሊበላ የመንግስት ጉብኝት እያደረጉ ነው። ወንድ ከወንድ ጋር፣ ሴት ከሴት ጋር ማግባባትና መተኛት አየርላንድ የምትኮራበት የአየርላንድ ብሔራዊ ባሕል፣ ልማድና ሃይማኖት ሆኖአል።

ከ1929 ዓም ሕገ መንግሥቱ ጀምሮ የመንግሥት ሃይማኖት ተከለከለ፣ ልዩ ሁነታ ከሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በ1965 ዓም ተነቀለ።




#Article 148: አባይ ወንዝ (ናይል) (116 words)


አባይ ማለት የናይል ወንዝ ታላቁ ገባር ወንዝ ሲሆን መነሻው ኢትዮጵያ ነው። አባይ 70 በመቶ የሚሆነው የሀገሪቱን ወንዞች የውሃ ድርሽ ሲይዝ አጠቃላይ የውሃድርሻውም ቢሆን 50 በምቶ የሚጠጋ ነው። በኢትዮጵያ ከአባይ ውጭ ያሉት ወንዞች ድምር ድርሻ 30 በምቶ ነው። ስለዚህ አባይ ለግብጽና ሱዳን ዋና የወሃ ምንጭ እንደሆነው ሁሉ ለኢትዮጵያም አባይ ወሳኝ ወንዟ ነው ማለት ይቻላል።  በአሁኑ ወቅትም ኢትዮጵያ የአባይን ውሃ ፍትሃዊ በሆነ መልኩ አባይ ለሚያቋርጣቸው አገራት እንዲደርስ የተለያዩ ጥረቶችን እያደረገች ትገኛለች። በ2011 እ.ኤ.አ. የመጀመሪያ አጋማሽ ላይ፦ ኢትዮጵያ ሌሎቹን የአባይ ተፋሰስ ሃገሮች በማይጎዳ መልክ በአግባቡ የተቀየሰውን ታላቁ የህዳሴ ግድብ ተብሎ የተሰየመውን 5250 ሜጋዋት የሚያመነጭ የሃይል ማመንጫ ጣቢያ ግንባታ መጀመሯን በይፋ አስታውቃለች። ይህ ግድብ የሚገነባው በውጭ የሃብታም ሃገሮች የገንዘብ እርዳታ ሳይሆን በራሷ ህዝቦች የገንዘብ መዋጮ መሆኑን በተለያዩ አጋጣሚወች እየተገለፀ ነው።
  

 




#Article 149: ፐሽቶ (145 words)


ፕሽቶ (پښتو) በአፍጋኒስታን በምዕራብ ፓኪስታን እንዲሁም በስሜን ሕንድ አገሮች በሚኖሩት በፓሽቱን ሕዝብ የሚናገር ቋንቋ ነው። 

ከ1928 ዓ.ም. ጀምሮ ፐሽቶ ከዳሪ ፋርስኛ ጋራ ከአፍጋኒስታን ሁለት ይፋዊ መደበኛ ቋንቋ አንድ ነው። ከአፍጋኒስታን ኗሪዎች በ35 ከመቶ ወይም 22 ሚሊዮን ገደማ ሰዎች እንደሚናገር ይገመታል። 

ፐሽቶ ከአረብኛና ከቱርክኛ አያሌው ቃሎች ተበድሮዋል። በእስጅንደር ዘመን (ክ.በ. 330) ግሪኮች ይህን አገር ደረሱና አንዳንድ ሊቃውንት ከጥንታዊ ግሪክ ደግሞ የወረዱ ቃላት አሉ ብለው ይገመታሉ። በፓኪስታን ደግሞ ፐሽቶ የሚናገሩ 11-14 ከመቶ ወይም 13 ሚሊዮን ሰዎች ፐሽቶ እንደሚችሉ ይታመናል። በጠቅላላ 40-50 ሚሊዮን ያሕል ፐሽቶ ተናጋሪዎች አሉ።

ፕሽቶ በሕንዳዊ-አውሮፓዊ ቋንቋዎች ቤተሠብ ውስጥ ሲካተት በዚያ ላይ በኢራናውያን ቋንቋዎች ዘርፍ ውስጥ ይደመራል።

ፐሽቶ እንደ አማርኛ ግሡ በዕረፍተ ነገሩ መጨረሻ የሚሳክበት ቋንቋ ነው። ቅጽል ከስሙ ይቀድማል። ስምና ቅጽል የተባይና የአንስታይ ጾታዎች፥ ነጠላና ብዙ ቁጥር፥ ሳቢና ተሳቢ አይነቶች አሉዋቸው። መስተጻምር የለም።

እስልምና ከተነሣ ጀምሮ ፐሽቶ የሚጻፍበት በአረብኛ ጽሕፈት አይነት ሆኗል. አንዳንድ ልዩ ድምጾች ስልላሉት ግን ተጨማሪ ምልክቶች ይኖራሉ። ፊደሉን በሙሉ ለመመልከት  ይሂዱ።




#Article 150: ጥንታዊ እንግሊዝኛ (214 words)


ጥንታዊ እንግሊዝኛ (Englisc /ኧንግሊሽ/) በእንግሊዝ አገር ከ440 ዓ.ም. ገደማ እስከ 1100 ዓ.ም. ያሕል የተናገረ ቋንቋ ነበር። ዛሬ ጀርመንና ዴንማርክ ከተባሉት አገሮች ፈልሰው በእንግሊዝ በተስፈሩት ሕዝብ የተናገሩበት ሲሆን የዘመናዊ እንግሊዝኛ ቀድሞ አይነት ነው። ሆኖም በቃላትም ሆነ በስዋሰው ከዘመናዊ እንግሊዝኛ በጣም ይለያል። ቅርብ ዘመዶቹ ጥንታዊ ፍሪዝኛ እና ጥንታዊ ሴክስኛ ናቸው። 

ጥንታዊ እንግሊዝኛ በርካታ ተመሳሳይ ቀበሌኞች ነበሩት። በተለይ በስሜን እንግሊዝ የኖሩት የአንገሎች መነጋገርያ በደቡብ ከኖሩት ከሴክሶች ትንሽ ተለያየ። 

ከ800 ዓ.ም. ገደማ ጀምሮ ስሜኑ በቫይኪንጎች ስለተወረረ በንጉስ አልፍሬድ ጊዜ የሴክሶች ቀበሌኛ ይፋዊ ሁኔታ አገኘ። ቢሆንም የቫይኪንጎች ቋንቋ ኖርስኛ ከጥንታዊ እንግሊዝኛ ጋር ዝምድና ነበረውና ከኖርስኛ አያሌው ቃላት ወደ እንግሊዝኛ ገቡ። ለምሳሌ የእንግሊዝኛ ቃላት sky /ስካይ/ (ሰማይ) leg /ለግ/ (እግር) እና they /ዘይ/ (እነሱ) የደረሱ ከኖርስኛ ነበር። በእንግሊዝ ኗሪዎች ቋንቋ (በጥንታዊ እንግሊዝኛ) እነዚህ ቃላት 'ሄዮቮን'፣ 'ሽያንካ' እና 'ሂዬ' ሆነው ነበር። 

የተማሩ ሰዎች (መምህራን ወይም ቄሶች) በብዛት የሮማይስጥ ዕውቀት ስለነበራቸው ደግሞ ከሮማይስጥ ተጽእኖ አንዳንድ ቃላት የዛኔ ወደ እንግሊዝኛ ገቡ። ንጉሥ አልፍሬድ እራሳቸው ብዙ መጻሕፍት ከሮማይስጥ አስተረጎሙ።

ኖርማኖች እንግሊዝን በ1059 ከወረሩ ጀምሮ እንግሊዝኛ ከትምህርት ቤት ስለ ተከለከለ በየጥቂቱ ባሕርዩ እጅግ ተለወጠ።

በጥንታዊ እንግሊዝኛ እያንዳንዱ ስም የተወሰነ ጾታ (ወንድ፣ ሴት ወይም ግዑዝ) ነበረው። ለምሳሌ sēo sunne /ሴዮ ሱነ/ (ፀሐይቱ) አንስታይ፣ se mōna /ሴ ሞና/ (ጨረቃው) ተባዕታይ፣ þæt wæter /ዛት ዋተር/ (ውኃው) ግዑዝ ነበር።

ቋንቋው መጀመርያ ፉሶርክ በተባለው የሩን ፊደል ሲጻፍ ክርስትና ከተቀበለ በኋላ ግን በላቲን አልፋቤት ሊጻፍ ጀመረ። አንዳንድ ተጨማሪ ፈደላት እንዲህ ነበሩ:




#Article 151: ሰርጌይ ብሪን (208 words)


ሰርጌይ ሚካይሎቪች ብሪን (እንግሊዘኛ: Sergey Mikhailovich Brin፤ ሩስኛ: Сергей (/ሰርገይ/) Михайлович Брин) (ኦገስት 21, 1973 እ.ኤ.አ. ተወለደ) ሩሲያዊ-አሜሪካዊ ሲሆን ጉግልን በመፍጠሩ ይታወቃል።

በሩሲያ የተወለደ ሲሆን፥ ብሪን ከላሪ ፔጅ ጋር ጉግልን ከመጀመሩ በፊት ኮምፒዩተር ሳይንስና ሒሳብ አጥንቷል። ብሪን ባሁኑ ጊዜ የጉግል ቴክኖሎጂ ፕሬዝዳንት በመሆኑ ወደ 14.1 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚገመት ገንዘብ አለው። ይህም ከዓለም 26ኛ እና ከአሜሪካ 12ኛው ሀብታም ሰው ያደርገዋል።

ሰርጌይ በሞስኮ፣ ሩሲያ ለየይሁዳ ቤተሰብ ተወለደ። 6 ዓመቱ ሲሆን ሰርጌይና ቤተሰቡ ወደ አሜሪካ መጡ። አባቱ ሚካኤል በሜሪላንድ ዩኒቨርስቲ ማቲማቲሻን ሆኖ እስክ ዛሬ ድረስ ያስተምራል። የስርጂ እናት ዩጂኒያ ብሪን ማቲማቲሻንና ሲቭል ኢንጅነር ሆና ለናሳ ትሰራለች። ሳሙኤል የሚባል ታናሽ ወንድምም አለው።

ሰርጌይ በኮምፒዩተር ዕድገት ጊዜ በማደጉ የኮምፒዩተር ፍላጎቱ ከልጅነቱ ነው የጀመረው። መጀመሪያው ያገኘው ኮምፒዩተር አንድ ኮሞዶር 64 ሲሆን ይህንንም ከአባቱ ዘጠነኛው ልደት በዓሉ ላይ ነው ያገኘው። በሒሳብና ኮምፒዩተር ያለውን ተስዕጦም ገና ትንሸ እያለ ነው ያሳየው።

የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በፔንት ብራንች ሞንቴሶሪ ትምህርት ቤት የወሰደ ሲሆን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደግሞ በኤላኖር ሩዝቬልት ትምህርት ቤት አጠናቋል። ቤተስቡም የሒሳብ ዕውቀቱንና ሩሲያኛው በማዳበር ረድተውቷል። በሴፕቴምብር 1990 እ.ኤ.አ.፣ ሰርጌይ ሒሳብና ኮምፒዩተር ሳይንስ ለማጥናት ሜሪላንድ ዩኒቨርስቲ፣ ኮሌጅ ፓርክ ገባ። በሜይ 1993 እ.ኤ.አ. የባችለር ሳይንስ ካማግኘቱ በኅላ በስኮላርሺፕ ኮምፒዩተር ሳይንስን ለማጥናት ወደ ስታንፎርድ ዩኒቨርስቲ ሄደ። ከዛም ከታሰበው ጊዜ በፊት በኦገስት 1995 እ.ኤ.አ. የማስተርስ ዲግሪውን ተቀበለ። ባሁኑ ጊዜ ግን የፒ.ኤች.ዲ. ጥናቱን ላልተወስነ ጊዜ አቋርጦ ጉግል ውስጥ እየሰራ ይገኛል።




#Article 152: እስልምና (1116 words)


 እስላም

  ሙስሊሙን አሊያም ሙስሊሚን ነው ፣ ሙስሊማ አንስታይ ሲሆን የርሱ ብዙ ቁጥር ሙስሊማት ነው። ኢስላም إِسْلَٰم ደግሞ ዲኑ ሲሆን 8 ጊዜ ተወስቷል። ወጅህ وَجَّهْ ሁለንተናን አሊያም ህላዌን የሚያሳይ ሲሆን የቃል ትርጉሙ *ፊት* ማለት ነው፣ አንድ ሰው ሁለንተናውን ለአላህ ሲሰጥ ታዛዥ፣ ተገዥ፣ አምላኪ ይባላል፣ ይህ በአረቢኛ *ሙስሊም* pማለት ነው፦

የኢስላም አስኳሉ ተህሊል تهليل‎,ነው፣ ተህሊል ማለትም “ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ”لا اله الاّ الله ነው፣ “ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ” ማለት *ከአንዱ አላህ በስተቀት ሌላ አምላክ የለም* ማለት ነው፣ “ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ” ሁለት ማዕዘናት አለው፣ አንዱ *ነፍይ* ሲሆን ሁለተኛው *ኢሥባት* ነው፣ ነፍይ ማለት ላ-ኢላሀ*ሌላ አምላክ የለም* ስንል ጣኦታትን ውድቅ ማድረግን ሲያመለክት ኢሥባት ደግሞ ኢልለሏህ*ከአንዱ አላህ በስተቀት* ስንል አንዱን አምላክ እያረጋገጥን ነው፣ ይህ ተህሊል *ጠንካራን ዘለበት* ይባላል፦

ሙስሊም ማለት እንግዲህ ይህ ነው፣ አንዱን አምላክ በብቸኝነት ከሌሎች ጣኦታት ለይቶ የሚያመልክ ማለት ነው፣ በዚህ ሂሳብ ሁሉም ነቢያት ሙስሊሞች ናቸው፣ ሙስሊሞች አልነበሩም ማለት አንዱ አምላክ አያመልኩም ማለት ነው፣ ነገር ግን ቁርአን ሁሉም ነቢያት አንዱን አምላክ የሚያመልኩ ነበሩ ይለናል፦

ነጥብ አንድ
ነቢያት

አላህ ጥንት ለነበሩት ነቢያት ወህይ የሚያወርድላቸው የነበረው “ላ ኢላሃ ኢልላ አና” لَا إِلَٰهَ إِلَّا أَنَا *ከኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም* የሚል ነው፦

ወደ ሰዎች ሲልካቸውም *ማ ለኩም ሚን ኢላሂ ገይሩሁ* مَا لَكُمْ مِنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ *ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የላችሁም* ብለው እንዲናገሩ ነው፦

ይህን መረዳት ይዘን ሁሉም ነቢያት አንዱን አምላክ አላህን የሚያመልኩ ነበሩ በአረቢኛ ሙስሊሞች ነበሩ ማለት ነው፣ ችግራችሁ ቋንቋ ከሆነ ሙስሊም የሚለውን አማርኛው ታዛዦች ብሎ ይፈታዋል፦

አላህ የነቢያችንን ኡማ ሙስሊሞችን ነው ብሎ የተናገረው የጥንቶቹን በተናገረበት ስሌት ነው፦

አላህ ነቢያትን ሲልክ በማህበረሰቡ ሊግባባበት በሚችል ቋንቋ ነው፣ በራሳቸው ቋንቋ ሁሉንም ያለው *ሙስሊም* ማለትም ታዛዢዎች፣ አምላኪዎች፣ ተገዢዎች ነው፣ ሙስሊሞች አይደሉም ብሎ መቃወም አንዱን አምላክ አያመልኩም፣ ጣኦታውያን ነበሩ እንደማለት ነው፣ ስለዚህ ኢስላም በነቢያችን የተጀመረ ሳይሆን የተጠናቀቀ የአላህ ዲን ነው፦

ነጥብ ሁለት
የነቢያት አምላክ

አላህ ጥንት ነቢያቶች የሚያመልኩት የነቢያት አምላክ መሆኑን የምናውቀው ከጥንቶቹ ነቢያት ጋር የነበረውን መስተጋብር ለመግለጽ ቁልና قُلْنَا *አልን* ፣ አርሰልና أَرْسَلْنَا*ላክን*፣ አውሃይና أَوْحَيْنَا *አወረድን* በማለት ጥንትም ነቢያትን ሲልክ የነበረው፣ ግልጠተ-መለኮት*Revelation* ሲያወርድ የነበረውና በተለያየ መንገድ ሲያናግራቸው የነበረው እርሱ መሆኑን ይገልጻል፦

የኢስላም መሰረቶች

አርካኑል ኢስላም أركان الإسلام *የኢስላም መሰረቶች* አምስት ናቸው፣ እነዚህም፦ ሸሃዳ الشهادة‎፣ ሶላት صلاة‎ ፣ ሰውምصوم‎ ፣ ዘካزكاة እና ሃጅ حج ናቸው።
ሰሂህ ቡሃሪ ቅጽ 1, መጽሃፍ 2, ቁጥር 8: ይመልከቱ፦

حَدَّثَنَا عُبَيْدُ اللَّهِ بْنُ مُوسَى، قَالَ أَخْبَرَنَا حَنْظَلَةُ بْنُ أَبِي سُفْيَانَ، عَنْ عِكْرِمَةَ بْنِ خَالِدٍ، عَنِ ابْنِ عُمَرَ ـ رضى الله عنهما قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ بُنِيَ الإِسْلاَمُ عَلَى خَمْسٍ شَهَادَةِ أَنْ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَأَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ اللَّهِ، وَإِقَامِ الصَّلاَةِ، وَإِيتَاءِ الزَّكَاةِ، وَالْحَجِّ، وَصَوْمِ رَمَضَانَ

ኢስላም የነቢያት ሃይማኖት ከሆነ ነቢያችን የመሰረቱት ሳይሆን ከጥንት ነቢያት የመጣ አስተምህሮት ነው፣ እነዚህን የኢስላም መሰረቶች የጥንቶቹ ነቢያት ድርጊት መሆኑን አንድ በአንድ እንመልከት፦

ሸሃዳ الشهادةምስክርነት ሲሆን ከአላህ በቀር አምላክ አለመኖሩን በቀውል የሚደረግ የኢባዳ ክፍል ነው፣ ይህንን ምስክርነት ሰዎች በእያንዳንዱ ነብይ ዘመን በዘመኑ የነበረውን ነብይ መልእክተኛ አድርገው ይቀበላሉ፦

በተመሳሳይ መልኩ አላህ ለነቢያችን *እርሱ እንጂ ሌላ አምላክ የለም* *የአላህ መልክተኛ* ነኝ በል ብሏቸዋል፦

በአላህና በመልክተኞቹም አምኖ ምስክርነት መስጠት የኢስላም ማዕዘን ነው፣ ለዛ ነው *ከአላህ በቀር አምላክ የለም ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ ነው* لا إله إلا الله محمد رسول الله ብለን የምንመሰክረው፦

ሶላት صلاة‎ *ጸሎት* ከኢስላም መሰረቶች አንዱ ነው፣ ሁሉም ነቢያት ሶላት ነበራቸው ምናልባት ይዘቱ ይለያይ ይሆናል፣ በቀን አምስት ጊዜ ላይሆን ይችል ይሆናል እንጂ ሶላት ከነቢያችን በፊት በነበሩት ነቢያት ነበር፦

ሰውምصوم‎ ጾም በቀድሞቹ ነቢያት የተሰጠ መመሪያ ነው፣ ምናልባት በዘጠነኛው ወር በረመዳን አይሁን እንጂ ጾም ነበረ፦

ዘካزكاة ምጽዋት በቀድሞቹ ነቢያት የተሰጠ መመሪያ ነው፣ ምናልባት ከመቶ ሁለት ነጥብ አምስት አይሁን እንጂ ምጽዋት ነበረ፦

ሚሽነሪዎች ስለራሳቸው ዲን በቅጡ ስላልተረዱ ሙስሊሞች ስነ-አመክኖአዊ ጥያቄዎች ስንጠይቃቸው እርርና ምርር ብለው ከመንጨርጨርና ከመንተክተክ ውጪ ምላሽ አይሰጡም፣ ከዚያም አልፎ ከኢስላም ድንቅና ብርቅ መሰረቶች አንዱ የሆነውን ሃጅ ከፓጋን የተቀዳ ነው ሲሉ በመሰለኝ ሲተቹ ይታያል፣ እግር እራስን ሊያክ አይችልም፣ ምን ከኢስላም የተሻለ ነገር ተይዞ ነው ኢስላምን ሊያኩ የተነሱት? እስቲ ይህንን ሃጅ እናስተንትን፣ ሃጅ حج የሚለው ቃል ሃጅጀ حَآجَّ *ጎበኘ* ከሚል የመጣ ሲሆህ *ጉብኝት*“pilgrimage” ማለት ነው፣ ሃጅ የተጀመረው በነቢያችን አሊያም በሙሽሪኮች ሳይሆን በጥንቱ ነብይ ኢብራሂም ዘመን ነው፣ ይህን አምላካችን አላህ ሲናገር እንዲህ ይላል፦

አላህ ሰዎች እንዲጎበኙት ያዘዘው ቤት የራሱ ጥንታዊ ቤት ነው፦

አላህ በነቢያችን ያዘዘው ጉብኝት የጥንቱን ትዕዛዝ ዋቢና ታሳቢ ያደረገ ነው፦

ሃጅ ምንጩ መለኮታዊ እንጂ ፓጋናዊ እንደሆነ የሚያሳይ የቁርአን፣ የሃዲስ፣ የታሪክ መረጃ የለም፣ ለመሆኑ የአረቦችስ ታሪክ ከኢስላማዊ ምንጭ ሌላ ኖሮስ ነው እንዴ ለመተቸት የተበቃው? ሙሽሪኮች የጥንቱን ነብይ የኢብራሂምን አምልኮ ከጣኦት ጋር ቀላቅለው ማምለክ መጀመራቸውን የሚተርከው ኢስላማዊ ምንጭ ነው፣ መመዘንም ያለበት በዚሁ ምንጭ ነው፣ እስቲ የሚተቹትን የሃጅ ስርዓቶች እንመልከት፦

ነጥብ አንድ
ጠዋፍ

ጠዋፍ طواف, የሚለው ቃል ጣፈ طَافَ *ዞረ* ከሚል ቃል የመጣ ሲሆን *መዞር* ማለት ነው፣ ይህንንም ያዘዘው አምላካችን አላህ ለጥንቱ ነብይ ለኢብራሂም ነው

ነጥብ ሁለት
ኢህራም

ኢህራም إحرام ግላዊ ፍላጎትን በመተው በኢህክላስ ወደ አላህ የመቅረብ ውሳኔና ተግባር ነው፦

አሲም አነስን ስለ ሶፋና መርዋ ሲጠይቀው አነስ ከመዲና የሆነ ሰሃቢይ ስለሆነ ግንዛቤው ስላልነበረውን እንዲህ ይላል፦

ኢማም ቡሃሪ ቅጽ2 መጽሃፍ 26 ቁጥር 710

حَدَّثَنَا مُحَمَّدُ بْنُ يُوسُفَ، حَدَّثَنَا سُفْيَانُ، عَنْ عَاصِمِ بْنِ سُلَيْمَانَ، قَالَ سَأَلْتُ أَنَسَ بْنَ مَالِكٍ ـ رضى الله عنه ـ عَنِ الصَّفَا، وَالْمَرْوَةِ،. فَقَالَ كُنَّا نَرَى أَنَّهُمَا مِنْ أَمْرِ الْجَاهِلِيَّةِ، فَلَمَّا كَانَ الإِسْلاَمُ أَمْسَكْنَا عَنْهُمَا، فَأَنْزَلَ اللَّهُ تَعَالَى {إِنَّ الصَّفَا وَالْمَرْوَةَ } إِلَى قَوْلِهِ {أَنْ يَطَّوَّفَ بِهِمَا}

አሲም ኢብኑ ሱለይማን እንደተረከው፦ እኔ አነስ ኢብኑ ማሊክን ስለ ሶፋና መርዋ ጠየኩት፣ እርሱም መለሰልኝ ኢስላም ከመምጣቱ በፊት በዘመነ መሃይማኑ ጊዜ የነበረ ስርአት አድርገን እናስብ ነበር፣ ግን ኢስላም በመጣ ጊዜ በዚያ መዞርን አቆምን፣ ከዚያም አላህ እንዲህ የሚለውን አንቀጽ አወረደ፦

ሙሽሪኮች ሶፋና መርዋ መካከል ማናት የምትባለውን ጣኦት አስገብተው ያመልኩ ነበር፣ ይህን የተረዱት የመዲና ሰዎች ኢህራም የማናት ስም ይመስላቸው ነበር፣ ይህንን ጉዳይ እሜቴ አይሻ ሲናገሩ፦

ኢማም ቡሃሪ ቅጽ 6 መጽሃፍ 60 ቁጥር 384

وَةُ قَالَتْ عَائِشَةُ نَزَلَتْ فِي الأَنْصَارِ كَانُوا هُمْ وَغَسَّانُ قَبْلَ أَنْ يُسْلِمُوا يُهِلُّونَ لِمَنَاةَ. مِثْلَهُ. وَقَالَ مَعْمَرٌ عَنِ الزُّهْرِيِّ عَنْ عُرْوَةَ عَنْ عَائِشَةَ كَانَ رِجَالٌ مِنَ الأَنْصَارِ مِمَّنْ كَانَ يُهِلُّ لِمَنَاةَ ـ وَمَنَاةُ صَنَمٌ بَيْنَ مَكَّةَ وَالْمَدِينَةِ

አይሻ በመጨመር፦ ይህ አንቀጽ የወረደው ከአንሷር ጋር የሚገናኝ ነው፣ እነርሱ ወደ ኢስላም ከመግባታቸው በፊት ኢህራም የማናት ስም ነው ብለው ያስቡ ነበር።

ተቺዎች ይህንን ሃዲስ ይዘው ነው ሃጅ፣ ጠዋፍ፣ ኢህራም፣ ሶፋና መርዋ የፓጋን ነው የሚሉት፣ ጥቅሱ የሚያወራው ደግሞ ሌላ ጉዳይ ነው፣ ለመተቸው ምንጩ ኢስላማዊ እስከሆነ ድረስ መልሱም ኢስላማዊ ምንጭ ነውና መቀበል አለባችሁ፣ ከሃጅ ጋር በተያያዘ መልኩ የሚደረጉ ጠጉርና ጥፍር መቆረጥና ዕድፍን ማስወገድ ለኢብራሂም የተሰጠ ትዕዛዝ ነው፦

ማጠቃለያ

ኢስላም የነቢያት ሃይማኖት ነው፣ ይህን የነቢያት አስተምሮት ሙሽሪኮች ከጊዜ በኋላ ከጣኦታት ጋር ደባልቀውታል፣ ያን ጊዜ የመሃይምነቱ ጊዜ ተጀመረ፣ የነቢያቱ አምላክ አላህ ነቢያችንን በማስነሳት የጥንቱን የኢብራሂምን አስተምህሮት አመጣ፣ ሙሽሪኮች የሚሰሩትን ነገር አላህ በቃሉ ሲናገር፦

አላህ የዓለማቱ ጌታ መሆኑን ቢረዱም አላህም ከፈጠረው ከአዝመራና ከግመል፣ ከከብት፣ ከፍየልም ለጣኦቶቻቸው ድርሻን አደረጉ፡፡ ይህን ያደረጉበት 360 ጣኦቶቻቸው ወደ አላህ ያቃርቡናል ብለው ነው፣ ይህን አድራጎታቸው የቂያማ ቀን ዋጋቸውን ያገኛሉ፦

ኢማም ቡሃሪ ቅጽ 9 መጽሃፍ 83ቁጥር 21

 حَدَّثَنَا أَبُو الْيَمَانِ، أَخْبَرَنَا شُعَيْبٌ، عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ أَبِي حُسَيْنٍ، حَدَّثَنَا نَافِعُ بْنُ جُبَيْرٍ، عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ “ أَبْغَضُ النَّاسِ إِلَى اللَّهِ ثَلاَثَةٌ مُلْحِدٌ فِي الْحَرَمِ، وَمُبْتَغٍ فِي الإِسْلاَمِ سُنَّةَ الْجَاهِلِيَّةِ، وَمُطَّلِبُ دَمِ امْرِئٍ بِغَيْرِ حَقٍّ لِيُهَرِيقَ دَمَهُ ”

አላህ ዘንድ ሶስት ከተጠሉት ሰዎች መካከል አንዱ፦ በዘመነ መሃይማኑ ጊዜ የነበረውን ልማድ ቢስላም ውስጥ ማስገባት ነው፣
ስለዚህ የሃጅ ስርዓት የጥንቱ ነብይ የኢብራሂም ሃይማኖት እንጂ የጣኦታውያን ነው ማለት እውር ድንብ የሆነ ጸለምተኛ ሙግት ነው።

ወሰላሙ አለይኩም




#Article 153: ሃይማኖት (132 words)


ሃይማኖት አንድ ሕብረተሠብ የሚያምንባቸው ጽኑ እምነቶች መሠረት ነው። በዓለም ውስጥ በርካታ ልዩ ልዩ ሃይማኖቶች አሉ። 

ዋና ዓለማዊ ሃይማናቶች ክርስትና፣ እስልምና፣ አይሁድና፣ የሕንዱ ሃይማኖት እና ቡዲስም ናቸው። እነዚህ ሃይማኖቶች በአንዳንድ አገር በይፋ የመንግሥት ሃይማኖት ሁኔታ አላቸው። ከነዚህ መጀመርያ ሦስቱ.  ክርስትና፣ እስልምናና አይሁድና፣ ሁላቸው ከአብርሐም ስለ ተነሡ፣ «አብርሃማዊ ሃይማኖቶች» ተብለዋል። ሒንዱኢዝምና ቡዲስም ግን ከሕንድ ተነሡና «ሕንዳዊ» ወይም «ዳርማዊ ሃይማኖቶች» ተብለዋል። 

ሌሎች ሃይማኖቶች በአሁኑ ሰዓት በየትም አገር የመንግሥት ሃይማኖት ባይሆኑም፣ ባለፉት ዘመናት በታሪክ መንግሥታት ይኖራቸው ነበር፦ በተለይ ዛርጡሽና፣ ጃይኒስም፣ ሲኪስም፣ ዳዊስም፣ የኮንግ-ፉጸ ትምህርት፣ ሺንቶና የተለያዩ ኗሪ ወይም አረመኔ ሃይማኖቶች የቀድሞ መንግሥታት ነበሯቸው፤ የጠፉት ሃይማኖቶች ማኒኪስም እና አሪያኒስም ደግሞ የቀድሞ መንግስታት ነበሯቸው።

በተጨማሪ መቸም መንግስት ያልነበረላቸው በርካታ ሌሎች አነስተኛ ሃይማኖቶች ወይም እምነቶች አሉ ወይም በታሪክ ተገኝተዋል።

በአንዳንድ አስተሳሰብ ማርክሲስም-ሌኒኒስም በሃይማኖት ፈንታ የአንዳንድ መንግሥት ፍልስፍና፣ ትምህርት ወይም ርዕዮተ ዓለም በመሆኑ በውኑ እንደ አንድ ሃይማኖት መቆጠሩ ተገቢ ነው።




#Article 154: ዋርካ (ድረገጽ) (125 words)


ዋርካ ሳይበር ኢትዮጵያ በመባል የሚታወቀው ድረገጽ የአማርኛ ቋንቋ የውይይት መድረክ ድረ ገጽ ነው። ይህ ድረገጽ ኢትዮጵያውያን በራሳቸው ፊደል መወያየት ይችሉ ዘንድ በሁለት ወንድማማች ኢትዮጵያዊያን በሰኔ 1992ተፈጥሮ ዛሬ ሁሉንም ኢትዮጵያዊያን በስፋት እያገለገለ ያለ ዌብሳይት ሆኖአል።

ይሁን እንጂ ድረገጹ እንደሚለው ከግንቦት 1998 ጀምሮ ፥ የኢትዮጵያ መንግሥት ድረገጽን ስለአገደው በአገር ውስጥ እንዳይሰራ ወይም እንዳይታይ አግዷል። ሆኖም የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ብርሃኑ ሃይሉ ስዋርካ/ሳይበር ኢትዮጵያና ስለሌሎቹም ስለታገዱ ፖለቲካ ነክ ድረገጾች ጉዳይ ተጠይቀው ምንም የተከለከለ ድረገጽ የለም የማይታዩበት ምክንያትም አይታወቅም በማለት በተደጋጋሚ አስተባብለዋል። ዋርካ ወይም ሳይበር ኢትዮጵያ በምዕራቡና በዓለም ዙሪያ ለሚኖረው ኢትዮጵያዊያን ሕብረተሰብ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ ወይም የዕለት ከዕለት ኑሮ ስለ ፖለቲካ ወይም ስለ ባሕል እና ስነ-ጽሑፍ፣ ስነ-ጥበብ፣ ኪነ-ጥበብ፣ ፍቅር፣ ሃይማኖት እንዲሁም ወቅታዊ ጉዳዮችን ሊያወያዩ የሚችሉ በጣም ጠቃሚ መድረኮች ስላሉት መፍትሔ ያጡለትን ጉዳዮች በውይይት መፍትሔ እንደዳስገኘለት ከተጠቃሚዎች የተገኘ መረጃ ያረጋግጣል።




#Article 155: ሄርበርት ሁቨር (630 words)


 ሄርበርት ሁቨር (1866 - 1957 ዓ.ም.) ከ1921 እስከ 1925 ዓ.ም. ድረስ 31ኛ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ነበሩ።

የሁቨር ቤተሠብ ከስዊስና ጀርመን ትውልድ ሲሆን ሃይማኖቱ የክዌከር ('የሚንቀጠቀጡ' ማለት ነው) ቤተ ክርስቲያን ነበረ። ወላጆቹ በልጅነቱ ጊዜ ካረፉ አንስቶ ድሃ አደግ ሆነና ከአጎቱ ጋር አደገ። በስታንፎርድ ዩኒቨርሲቴ መጀመርያ ክፍል በመሆኑ ትምህርቱ በነጻ ተቀበለ። ከዚያ በላይ የዩኒቬርሲቴው የቤስባልና የፉትቦል ቡድኖች አለቃ ሆነ። በ1887 ዓ.ም. የጂዮሎጂ ዲግሪ ይዘው ተመረቁ። ለ20 ዓመት የማዕደን ሊቅ ሲሆኑ እንኳን በአውስትራልያና በእንግሊዝ በማዕደን ዘርፍ የሠሩት ሥራ ስመ ጥሩ ሆነ። 

መጀመርያው ታላቅ አለማዊ ጦርነት በ1906 ዓ.ም. በጀመረበት ወቅት ሁቨር ከራሳቸው ኪስ ለጋሥነት አውጥተው 120,000 አሜሪካውያን ቱሪስቶችና ሠራተኞችን ከአውሮፓ ወደ አገራቸው አስመለሷቸው። ከዚያ በጀርመኖች በተወረረው በቤልጅግ ውስጥ የኖሩት ረሃብተኞች ምግብ እንዲደርሳቸው ብዙ አደረጉ። በዚህ አይነት ሥራ በጦርነት ጊዜ የሁቨር ስም ጀግና እንዳለው ሁኔታ በመገኘት ላይ ሄዶ ነበር። ጦርነቱም ከተጨረሰ በኋላ ለምሥራቅ አውሮጳ ድሃ ሕዝብ እስከ ሩስያም ድረስ በረሃብ ላሉት ሰዎች ምግብ አደረሷቸው። 

በ1913 በፕሬዝዳንት ዋረን ሃርዲንግ ዘመን ሁቨር የአሜሪካ የንግድ ሚኒስትር ሆኑ። በሃርዲንግ ተከታይ በፕሬዝዳንት ካልቪን ኩሊጅ ዘመን ደግሞ እንዲህ ያለን ማዕረግ ይዘው አገለገሉ። የንግድ ሚኒስትር እየሆኑ ሃይለኛ ሰው ነበሩ። የንግድ ዘርፍና መንግሥት አንድላይ ይሠሩ የሚለውን ተስፋ በመያዛቸው በዚህ አንጻር ብዙ አደረጉ። በማዶ ባሕርና በውጭ አገር ለባለጉዳዮች ምክርና እርዳታ የሚሰጡ መሥርያ ቤቶች በማስከፈቱ የአለም አቀፍ ንግድ በጉልበት አስለሙ። በተለይም የሆሊዉድ ፊልም ማዶ ባሕር ለመግፋፋት ጉጉ ነበሩ። ዜጎችም ቤት እንዲያገነቡና የራሳቸው መሬት ባለአባት እንዲሆኑ አበረታቷቸው።

ሁቨር ደግሞ የራዲዮ ስርጭት እንዲስተዳደር የራዲዮን ጉባኤ ጠሩ። እንዲሁም ለአውሮፕላኖች አስተዳደር ጉባኤ ጠርተው በብዙ አይነት ኢንዱስትሪ ለምሳሌ ኤሌክትሪክ፥ መስኖ ወዘተ ከፍተኛ ሚና ተጫወቱ። በገዛ ገንዘባቸው የልጆች ጤንነት በትምህርት ቤቶች አጸኑ።

በ1919 ዓ.ም. የሚሲሲፒ ወንዝ በሃይል ሲጎርፍ ታላቅ አስጊ ሁኔታ ፈጠረ። በወንዙ አጠገብ ያሉት 6 ክፍላገሮች ሁቨር የአደጋ ማስታገሻ ጥረት ሊቅ እንዲሆኑ ጠየቁት። ስለዚህ ፕሬዝዳንት ኩሊጅ ላኳቸውና ቡድናቸው ብዙ ተስቦ እንደ ወባ በሽታ አስቆመ። በ1920 ዓ.ም. የዓለሙ መጀመርያው ቴሌቪዥን ስርጭት ፈተና ሲደረግ መጀመርያው ትርዒት የሁቨር ቃል ንግግር ነበረ።

ኩሊጅ ለሁለተኛ ዘመን ለማገልገል እምቢ ብለው በ1921 የፕሬዚዳንት ምርጫ ጊዜ ሁቨር የሬፑብሊካን ወገን ዕጩ ሆኑ። በተቃራኒው በዴሞክራት ወገን እጩ በአል ስሚስ ላይ በሰፊ መጠን አሸነፉ። 

ስለ ድሃነት፦ «እኛ በአሜሪካ ዛሬ ከማንም አገር ታሪክ ይልቅ በድሃነት ላይ በመጨረሻ ድል ልናደርግ ነው» ብለው ነበር።

ከዚህ ከጥቂት ወራት በኋላ የ1921 ዓ.ም. የእስቶክ ገበያ ውድቀት በመከሠቱ የአገሩ እንዲሁም የመላ አለም ምጣኔ ሀብት ወደ 'ታላቁ ጭፍግግ' በ1 አመት ውስጥ ቶሎ ወረደ። ባንኮችና ፌዴራላዊ መንግሥት ያስገኙ የገንዘብ መጠን ወደ አንድ ሢሶ ተቀነሰ። 

ስለ ውጭ ጉዳይ ፖሊሲ የክላርክ ሰነድ በ1920 ተጽፎ ሁቨር ፕሬዝዳንት እየሆኑ በ1922 ግልጽ ሆኖ ወጣ። በዚህ ሰነድ ዘንድ፥ አውሮጳ በላቲን አሜሪካ ላይ ዛቻ ካልጣለች በተቀር አሜሪካ በውጭ አገር ጥልቅ ለማለት ሕጋዊ መብት አልነበራትም የሚል ማስታወሻ ነበር። በዚያን ጊዜ አሜሪካ ሠራዊት በኒካራጓና በሃይቲ ነበራት። ስለዚህ ሁቨር ከነዚህ አገራት የሠራዊቱን ቁጥር ቀነሱ። በላቲን አሜሪካ ውስጥ የጦርነት መሣርያ እንዳይደርስ ማዕቀብ ለመጣል አሠቡ። በ1924 ጃፓን ማንቹርያን በወረረ ጊዜ አዲስ ፖሊሲ አወጡ። እሱም በግፍና በወረራ የሚገኝ የመሬት ለውጥ ሁሉ አናከብርም የሚል ነበር። 

ከታላቁ ጭፍግግ የተነሣ ብዙ ባንክ ቤቶች ስለወደቁ አንዳችም ብድር ለማግኘት ከባድ ሆነ። ብዙ ሰዎች ሥራ ፈት ሆኑ። በአውሮፓም ምጣኔ ሃብቱ ችግር ውስጥ ስለ ገባ ሁቨር ጀርመን ስለመጀመርያው ጦርነት ለፈረንሳይ ከምትከፍል ካሣ ለአንድ አመት ይቅር ትበል የሚል ዕቅድ አዋጁ። በሚከተለውም አመት የጀርመን ዕዳ በሙሉ ተሰረዘ። 

ሥራ ፈትነት ለመቀነስ፥ ከ1 እስከ 2 ሚሊዮን ድሃ ሰዎች ወደ ሜክሲኮ አስመለሱ። ሆኖም ከነዚህ መካከል 60 ከመቶ የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው ሜክሲካዊ-አሜሪካውያን ነበሩ። ደግሞ በተራ ዜጎች ላይ ቀረጥና ግብር በያይነቱ እጅግ ከፍ አደረጉባቸው። በዘመናቸው መጨረሻ በ1925 ዓ.ም. 25 ከመቶ አካለ መጠን ከደረሱት ሰዎች ሥራ ፈት ሆነው ነበር። 

በ1924 ዓ.ም. የፕሬዚዳንት ምርጫ እንደገና ሲቀርብ፥ 20 ሺህ በመጀመርያው አለማዊ ጦርነት ልምድ ያላቸው የድሮ ወታደሮች ከነቤተሰቦቻቸው በዋና ከተማው በዋሺንግቶን ዲሲ ሠፈሩ። እነሱ ጡረታቸውን እንዲያገኙ ፈልገው ነበር። ይህም ስብሰባ 'የጡረታ ሰልፍ' ተባለ። ከፖሊሶች ጋራ ከታገሉ በኋላ ፌዴራል ሠራዊት ገቡና ጡረተኞቹን በግድ በሳንጃና በእንባ አውጭ ጋዝ አስወጡአቸው። ብዙ ሰዎች ተገደሉ ብዙም መቶ ተቆሰሉ። 

በዚህ ሁሉ ምክንያት ሁቨር የተወደዱ ፕሬዚዳንት አልነበሩም። በ1925 ምርጫ ተቃራኒው ፍራንክሊን ሮዘቨልት በሰፊ መጠን አሸነፉና በሳቸው ፈንታ ፕሬዚዳንት ሆኑ።

ሁቨር ፕሬዚዳንት ከሆኑ በኋላ ረጀም ዕድሜ ነበራቸው። እስከ 1957 ዓ.ም. ድረስ ኖሩ። ከ2ኛ አለማዊ ጦርነት ቀጥሎ በ1939 ስለ ቀድሞው ልምዳቸው ፕሬዚዳንት ሃሪ ትሩማን የአውሮፓ ምግብ ፍላጎት ለመወሰን ወደ አውሮፓ ላኳቸው።




#Article 156: ፍራንክሊን ሮዘቨልት (178 words)


ፍራንክሊን ዴላኖ ሮዘቨልት (1874-1937 ዓ.ም.) የኒው ዮርክ አገረ ገዥና የአሜሪካ 32ኛ ፕሬዚዳንት ነበሩ። 

ሮዘቨልት በቀድሞ ፕሬዚዳንት ዉድሮው ዊልሶን ዘመን የባሕር ኅይል ምክትል ሚኒስትር ነበሩ። በ1913 ምርጫ የምክትል ፕሬዚዳንት ዕጩ ሆኑ። ጄምስ ኮክስም የፕሬዚዳንት ዕጩ ነበሩ። ነገር ግን ኮክስና ሮዘቨልት በዋረን ሃርዲንግና በካልቪን ኩሊጅ ተሸነፉ። ሮዘቨልት በ1920 ዓ.ም. የኒው ዮርክ አገረ ገዥ ሆኑ።

በታላቁ ጭፍግግ ሳቢያ ፕሬዚዳንት ሄርበርት ሁቨር በጣም ስላልተወደደ በ1925 ምርጫ ሮዘቨልት ሁቨርን አሸነፏቸው። ሮዘቨልት በጣም ስለተወደደ በ1929 ዓ.ም. ምርጫ ለሁለተኛ የ4 አመት ዘመን ተመለሱ። እንዲሁም በ1933 ምርጫ ለሦስተኛ ዘመንና በ1937 ምርጫ ለአራተኛ ዘመን ተመረጡ። በጠቅላላ 4 ዘመኖች ተቀበሉ። በ2ኛ አለማዊ ጦርነትም የአሜሪካ መሪ ነበሩ። ነገር ግን ፖሊዮ ከሚባል በሽታ የተነሣ አካለ ስንኩል ሆነው ባለ መንኮራኩር ወምበር ነበራቸውና በአራተኛው ዘመን መሃል ሞቱ። ምክትላቸው ሃሪ ትሩማን ወዲያው ፕሬዚዳንት ሆኑ። 

ፍራንክሊን ሮዘቨልት አራት ጊዜ በመመረጣቸው ከሁሉ ይልቅ ለረጅም ዘመን ገዙ። ከሳቸው በኋላ የመንግሥት አንደኛ ዘርፍ የሆነ የሕግ አማካሪ ቤት ወደፊት ሌላ ፕሬዚዳንት እንደሱ 3 ወይም 4 ዘመናት እንዳይቀብል አንፈልግም የሚል ድምጽ አሰሙ። ስለዚህ በ1943 ዓ.ም. የአሜሪካ መንግሥት 2ኛ ዘርፍ የሆኑት ፕሬዚዳንቶች ከ2 ጊዜ (እነሱም 8 አመታት) በላይ ሊያገለግሉ አይችሉም የሚለው የአሜሪካ ሕገ መንግሥት 22ኛ ማሻሻያ አንቀጽ ሕጋዊ ደንብ ሆነ።




#Article 157: የአሜሪካ ሕገ መንግሥት 22ኛ ማሻሻያ አንቀጽ (269 words)


የአሜሪካ ሕገ መንግሥት 22ኛ ማሻሻያ አንቀጽ (Amendment) ለአሜሪካ ፕሬዚዳንት የሚገዙበት ዘመን ቁጥር ይወስናል። እሱ «ማንም ሰው ለፕሬዚዳንት ማዕረግ ከሁለት ጊዜ በላይ አይመረጥም፤ ከሌላ ፕሬዚዳንት ዘመን ከ2 አመት በላይ የጨረሰ ሰውም ከ1 ጊዜ በላይ አይመረጥም» የሚለው የአሜሪካ ሕገ መንግሥት መለወጫ ነው። ይህ መለወጫ በ1943 ዓ.ም. ሕጋዊ ከመሆኑ በፊት በሕገ መንግሥት ዘንድ አንድ ሰው እንደ ፕሬዚዳንት በሚመረጡባቸው ዘመናት ቁጥር ምንም ወሰን አልነበረም። ከፍራንክሊን ሮዘቨልት አስቀድሞ ማንም ሰው ከ2 ጊዜ በላይ አልተመረጠም ነበር። ፍራንክሊን ሮዘቨልት ግን 4 ጊዜ ተመረጡ። ከሳቸው በኋላ ነው ሕጉ የተለወጠ።

ሕገ መንግሥት ለመለውጥ እንዳለው ሥራት የአሜሪካ ምክር ቤት በመጋቢት 15 ቀን 1939 ዓ.ም. ሃሣቡን አቅርቦ በክፍላገሮች በአስፈላጊው ቁጥር በየካቲት 20 ቀን 1943 አጸደቁትና ወዲያው ሕግ ሆነ።

No person shall be elected to the office of the President more than twice, and no person who has held the office of President, or acted as President, for more than two years of a term to which some other person was elected President shall be elected to the office of the President more than once. But this Article shall not apply to any person holding the office of President when this Article was proposed by the Congress, and shall not prevent any person who may be holding the office of President, or acting as President, during the term within which this Article becomes operative from holding the office of President or acting as President during the remainder of such term.

This article shall be inoperative unless it shall have been ratified as an amendment to the Constitution by the legislatures of three-fourths of the several States within seven years from the date of its submission to the States by the Congress.




#Article 158: የአሜሪካ ታላቅ ማኅተም (204 words)


የአሜሪካ ብሔራዊ ምልክት የአሜሪካ ታላቅ ማኅተም ይባላል። መጀመርያው የተገለጸው በ1774 ዓ.ም. ነበር። እንዲያውም በይፋ 'አርማ' ሳይሆን 'ማኅተም' ነው። ነገር ግን ይፋዊ አርማ ስለማይኖር በዘልማድ ይህ ማኅተም እንደ አርማ ይጠቀማል። በአሜሪካ ዶላር ላይ (ከ1927 ዓ.ም. ጀምሮ) እንዲሁም በአሜሪካ ፓስፖርት ላይ ይታያል።

በማኅተሙ ፊት ላይ ክንፎቹን የሚዘረጋ የመላጣ ንሥር ስዕል እሱም የአሜሪካ ምልክት ይታያል። በግራው ጥፍሩ (ከንሥሩ አንጻር) ውስጥ አሥራ ሦስት ፍላጻ ይዟል። እነርሱም ከእንግሊዝ ያመጹ የመጀመርያ 13 ክፍላገሮች ያመልክታሉ። በቀኙም ጥፍር የወይራ ቅርንጫፍ ይይዛል። ይህ 13 ቅጠልና 13 ፍሬዎች አሉበት። ፍላጻ የጦር ምልክትና ወይራ የሰላም ምልክት በመሆኑ የንሥሩ ራስ ወደሱ ቀኝ ሲዞር ስላምን ይመርጣል እንደ ማለት ነው። በመንቁራው ውስጥ ደግሞ E PLURIBUS UNUM የሚለውን መፈክር ይይዛል። ይህም በሮማይስጥ ማለት 'አንድ ከብዙ' ነው። ከራሱ በላይ 13 ከዋክብት በሰማያዊ በስተኋላ መደብ አለ። እኚህ ከዋክብት የዳዊት ኮከብ ይሠራሉ። በፍርምባው ላይ የሚሸክመው ጋሻ እንደ አሜሪካ ሰንደቅ አለማ ዝንጉርጉር ነው። 

በማኅተሙ ጀርባ ላይ ያልተጨረሰ ሀረም (ፒራሚድ) ይታያል። ይህ 13 ደረጃዎች ሲኖሩት በመሠረቱ ላይ MDCCLXXVI ይላል። ይህ በሮማይስጥ ቁጥሮች ማለት '፼፯፻፸፮' ወይም 1776 ሲሆን በአውሮጳውያን አቆጣጠር የአሜሪካ ነጻነት አዋጅ የተፈረመበት አመት (1768 ዓ.ም.) ለማመልከት ነው። በሀረሙ ጫፍ ፈንታ 'የእግዚአብሔር ጥበቃ ዓይን' የሚባል ምልክት ይታያል። በዚሁ ዙሪያ «ANNUIT CŒPTIS» የሚለው መፈክር አለ፤ ይህም በሮማይስጥ 'የተጀመረው ተስማምቶታል' ለማለት ነው። በግርጌው ደግሞ «NOVUS ORDO SECLORUM» የሚል መፈክር እያለ ይህ ትርጉም 'የዘመናት አዲስ ሥርዓት' ነው።




#Article 159: ዕዝራ (214 words)


ዕዝራ (ዕብራይስጥ: עֶזְרָא) ወይም ሱቱኤል በመጽሐፈ ዕዝራ ምዕ. 7 በብሉይ ኪዳን ዘንድ በባቢሎን ምርኮ ጊዜ የአይሁድ ካህን ነበረ። የሠራያ ልጅ ሲሆን በፋርስ ንጉስ አርጤክስስ 7ኛው አመት (464 ክ.በ.) ከ5000 ከወገኖቹ ጋራ ወደ ኢየሩሳሌም ለመመለስ ፈቃድ ተቀበለ። 

ከዚህ 13 አመት በኋላ ነህምያ የከተማውን ቅጥር ሲጠግነው ዕዝራ ኦሪት በሙሉ ለሕዝብ አነበበ (መጽሐፈ ነህምያ ምዕ. 8)። 

በአይሁዳዊው ታሪክ ጸሐፊ በዮሴፉስ ዘንድ ይህ የፋርስ ንጉስ አርጤክስስ ሳይሆን አሕሻዊሮስ ነበረ።  አርጤክስስ የአሕሻዊሮስ ልጅ ሲሆን እነዚህ 2 ነገስታት ስሞች ብዙ ጊዜ በተለያዩ ቅጂዎች ተደናገሩ። ዮሴፉስ ደግሞ ዕዝራ የሞተበት ወራት ኤልያሴብ ታላቁ ካህን በሆኑበት ወቅት ገደማ እንደ ነበር ይመሰክራል።  የአሕሻዊሮስ ዘመን ከሆነ 7ኛው አመት 486 ክ.በ. ነበር። 

ዕዝራ መጽሐፈ ዕዝራንና መጽሐፈ ነህምያ ከመጻፉ በላይ በዲዩትሮካኖኒካል መጽሐፍት ክፍል የሚገኙት መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤልና መጽሐፈ ዕዝራ ካልዕ እንደ ጻፈ ይባላል።  መጽሐፈ ዕዝራ ካልዕ ለመጽሐፈ ዕዝራ በጣም ተመሳሳይ በመሆኑ በዕዝራ ካልዕ 8:1 ግን ሠራያ ሳይል በግድፈት የአዛርያስ ልጅ ይለዋል።  ዕዝራ ሱቱኤል በሚባለው ትንቢት ደግሞ በ1:1 የጻፈው ኢየሩሳሌም ከጠፋች 30 አመት በባቢሎን መሆኑን ይላል። ይህም 565 ክ.በ. ማለት ነው። በዚህ መጽሐፍ 13:44 መሠረት 24 መጻሕፍት በ40 ቀን ውስጥ ጻፈ ቢለን፥ በሌሎች ልሣናት ሕትመት ግን ስለ 94 መጻሕፍት እየተናገረ ከነዚህ መሀል ተጨማሪው 70 መጻሕፍት በምስጢር እንዲቆዩ ነበረባቸው ይላል። 

በእስልምና የዕዝራ ስም ደግሞ በቁርዓን ውስጥ (9:30) 'ዑዛዒር' ተብሎ ሲጻፍ ይገኛል። አይሁዶች ዑዛኢርን የእግዚአብሔር ልጅ በመሳሳት እንዳሉት ይላል። 

መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል ከዲዩተሮካኖኒካል ወይም አዋልድ መጻሕፍት ተቆጥሮ የሱቱኤል ትንቢት ነው።




#Article 160: አንበሳ (753 words)


አንበሳ (Panthera leo) ጡት አጥቢ የእንስሶች መደብ ውስጥ Felidae ተብሎ የሚታወቀው ቤተሰብ አባል ሲሆን ግዙፍ ድመቶች ከሚባሉት 4 አራዊት አንዱ ነው። ከነዚህም መካከል ነብር ከሚባለው ግሥላ መሳይ አውሬ ቀጥሎ በቁመቱና ክብደቱ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል። አንበሳ ዛሬ በአፍሪካ (ከነኢትዮጵያ) እና በህንድ ብቻ የሚገኝ ሲሆን በታሪክ እስያና በደቡብ አውሮፓ እንደነበርና እንደጠፋ ይታወቃል።

አንበሶች በጣም ቁጡ ሊሆኑ ይችላሉ፤ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የሙጭሊትን ያህል ገራምና ተጫዋች ይሆናሉ። ሲጠግቡ በዝግታ የሚያንኮራፉ ቢሆንም እንኳ እስከ ስምንት ኪሎ ሜትር ድረስ ሊሰማ በሚችል ኃይለኛ ድምፅ ሊያገሡ ይችላሉ። አንዳንድ ጊዜ ሰነፎችና ልፍስፍሶች ይመስሉ ይሆናል፤ ሆኖም በሚያስገርም ፍጥነት የመንቀሳቀስ ችሎታ አላቸው። የሰው ልጅ፣ አንበሳ ባለው ድፍረት ለዘላለም ሲወሳ እንዲኖር አድርጓል፤ በመሆኑም ደፋር ሰው አንበሳ ተብሎ ይጠራል። 

አንበሶች በማኅበር ከሚኖሩት የድመት ወገን የሆኑ እንስሶች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው። በትልልቅ መንጋ ተከፋፍለው የሚኖሩ ሲሆን እያንዳንዱ መንጋ ከጥቂት አባሎች አንስቶ ከ30 በላይ ሊደርስ ይችላል። አንድ መንጋ የጠበቀ ዝምድና ያላቸው በርከት ያሉ ሴት አንበሶች ይኖሩታል። አንድ ላይ ይኖራሉ፣ ያድናሉ እንዲሁም ይወልዳሉ። ዕድሜ ልካቸውን ሊዘልቅ የሚችለው ይህ የጠበቀ ትስስር ለመንጋው ጠንካራ መሠረት የሚጥል ከመሆኑም በላይ ለመንጋው ሕልውና ጥሩ ዋስትና ይሆናል። 

እያንዳንዱ መንጋ እየተዘዋወሩ የሚጠብቁና የመንጋውን የክልል ወሰን የሚያወጡ አንድ ወይም ከአንድ በላይ የሆኑ ለአካለ መጠን የደረሱ ወንድ አንበሶች ይኖሩታል። እነዚህ ዕጹብ ድንቅ የሆኑ አውሬዎች ከጥቁሩ የአፍንጫቸው ጫፍ አንስቶ እስከ ጭራቸው ጫፍ ድረስ ከሦስት ሜትር በላይ ርዝመት ያላቸው ሲሆን ከ225 ኪሎ ግራም በላይ ሊመዝኑ ይችላሉ። ቤተሰቡን በበላይነት የሚቆጣጠሩት ወንዶቹ ቢሆኑም አመራር የሚሰጡት ግን ሴቶቹ ናቸው። ወደ ጥላ ሥፍራ መሄድን ወይም አደን መጀመርን በመሳሰሉት ሁኔታዎች ብዙውን ጊዜ መንጋውን ለአንድ ዓይነት እንቅስቃሴ የሚያነሳሱት ሴቶቹ አንበሶች ናቸው። 

ሴት አንበሶች በአብዛኛው በየሁለት ዓመቱ ይወልዳሉ። ግልገሎቹ በሚወለዱበት ጊዜ ምንም ዓይነት አቅም አይኖራቸውም። ግልገሎችን ማሳደግ የሁሉም የጋራ ሥራ ነው፤ በመሆኑም ሴቶቹ አንበሶች በሙሉ በመንጋው ውስጥ ያሉትን ግልገሎች ይጠብቃሉ እንዲሁም ያጠባሉ። የግልገሎቹ ዕድገት ፈጣን ሲሆን በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ መሮጥና መቦረቅ ይጀምራሉ። ልክ እንደ ሙጭሊቶች እየተንደባለሉ ይጫወታሉ፤ ከሚያጫውቷቸው ጋር ይታገላሉ፤ እንዲሁም በረጃጅሙ ሣር ውስጥ ወዲያና ወዲህ ይዘላሉ። እያንዳንዱ የሚንቀሳቀስ ነገር ሁሉ ስሜታቸውን ይማርከዋል፤ ቢራቢሮዎችን ለመያዝ ይዘላሉ፣ ትናንሽ ነፍሳትን ያሳድዳሉ፣ ከየጭራሮና ከየሐረጉ ጋር ይታገላሉ። ይበልጥ ስሜታቸውን የሚማርከው ግን እነርሱን ለማጫወት እናታቸው ወዲያና ወዲህ የምታወናጭፈው ጭራዋ ነው። 

እያንዳንዱ መንጋ የሚኖርበት በደንብ የተከለለ ቦታ ያለው ሲሆን ይህ መኖሪያ ብዙ ስኩዌር ኪሎ ሜትር ስፋት ሊኖረው ይችላል። አንበሶች ውኃ እንደ ልብ ባለበትና ከቀትር ሐሩር የሚከላከል ጥላ በሚያገኙበት ከፍ ያለ ቦታ ላይ መኖር ይመርጣሉ። በእንዲህ ዓይነቱ ሥፍራ ከዝሆኖች፣ ከቀጭኔዎች፣ ከጎሽና ከሌሎች ሜዳማ በሆኑ ሥፍራዎች ከሚኖሩ እንስሶች ጋር በአንድነት ይኖራሉ። አንበሳ አብዛኛውን ጊዜውን በእንቅልፍ ጥቂቱን ጊዜ ደግሞ በአደንና በተዋስቦ ያሳልፋል። እንዲያውም አንበሶች በቀን ውስጥ ወደ 20 የሚጠጋውን ሰዓት የሚያሳልፉት በዕረፍት፣ በመተኛት ወይም በመቀመጥ ነው። ከባድ እንቅልፍ ተኝተው ሲታዩ ሰላማዊና ለማዳ ይመስላሉ። ይሁን እንጂ በዚህ መታለል የለብህም፤ አንበሳ እጅግ ቁጡ ከሆኑት አራዊት መካከል አንዱ ነው!

 አንበሶች በጣም ቀልጣፋና ፈጣን ቢሆኑም እንኳ በአደን ጊዜ የሚሳካላቸው 30 በመቶ ብቻ ነው። በመሆኑም አንበሶች ከተደቀኑባቸው ትልልቅ አደጋዎች አንዱ ረኃብ ነው።

ለአካለ መጠን የደረሰ አንድ አንበሳ ያለው ጥንካሬ እጅግ የሚያስገርም ነው። በቤተሰብ ደረጃ የሚያድኑ እንደ መሆናቸው መጠን ከ1,300 ኪሎ ግራም በላይ ክብደት ያላቸውን እንስሳት የመጣልና የመግደል አቅም እንዳላቸው ይነገራል። አንበሶች በመጀመሪያ ላይ በሰዓት እስከ 59 ኪሎ ሜትር ድረስ ሊሮጡ ይችላሉ፤ ሆኖም ይህ ፍጥነታቸው እስከ መጨረሻ አይዘልቅም። በዚህ ምክንያት ቀለባቸውን ለማግኘት አድብቶ የመያዝ ዘዴ ይጠቀማሉ። የማደኑን ተግባር 90 በመቶ የሚያከናውኑት ሴቶቹ አንበሶች ቢሆኑም በሚበሉበት ጊዜ ትልቁን ድርሻ የሚያገኙት ትልልቆቹ ወንድ አንበሶች ናቸው። አደን በሚጠፋበት ጊዜ አንዳንዴ አንበሶች በጣም ስለሚርባቸው ያገኙትን መብል ለራሳቸው ግልገሎች እንኳ ለማካፈል ፈቃደኛ አይሆኑም። 

ከብዙ ዓመታት በፊት ባለ ግርማ ሞገሱ አንበሳ በመላው የአፍሪካ አህጉር እንዲሁም በእስያ፣ በአውሮፓ፣ በህንድና በፍልስጤም አንዳንድ ቦታዎች ይገኝ ነበር። አዳኝ እንደመሆኑ መጠን ሰውን እየተቀናቀነ የሚኖር እንስሳ ነው። በከብቶች ላይ አደጋ የሚጥልና በሰዎች ላይ ጉዳት የሚያደርስ በመሆኑ አንበሳ ገና እንደታየ በጥይት የሚገደል ፍጡር ሆነ። የሕዝብ ቁጥር ፍንዳታ የአንበሳን መኖሪያ በእጅጉ አመናምኖታል። ዛሬ ከአፍሪካ ውጪ ባለው የዓለም ክፍል በዱር የሚኖሩት አንበሶች በጥቂት መቶዎች ብቻ የሚቆጠሩ ሆነዋል። በአሁኑ ጊዜ አንበሶች ሰው ከሚያደርስባቸው ጥቃት ሙሉ በሙሉ ተጠብቀው መኖር የሚችሉት ጥበቃ በሚደረግባቸው ክልሎች ውስጥና በዱር አራዊት መጠበቂያ ቦታዎች ብቻ ሆኗል። 

አንበሶች በሚያገሡበት ጊዜ በብዙ ኪሎ ሜትር ርቀት ሊሰማ የሚችል ከፍተኛ ድምፅ የማውጣት ልዩ ችሎታ አላቸው። አንበሳ ሲያገሣ የሚያሰማው ድምፅ “እጅግ ማራኪ ከሆኑት የተፈጥሮ ድምፆች” አንዱ እንደሆነ ይነገራል። ብዙውን ጊዜ አንበሶች በጨለማ ሰዓትና ንጋት ላይ ያገሣሉ። ወንዶቹም ሆኑ ሴቶቹ አንበሶች የሚያገሡ ሲሆን አንዳንዴም የመንጋው አባላት በአንድነት ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ያገሣሉ።

በአንበሶች ላይ ጥናት የሚያካሂዱ ሳይንቲስቶች አንበሶች የሚያገሡባቸው የተወሰኑ ምክንያቶች እንዳሉ ይናገራሉ። ወንዶቹ አንበሶች የሚኖሩበትን ክልል ድንበር ለማሳወቅ እንዲሁም ሌሎች ወንድ አንበሶች ወደ ክልላቸው እንዳይገቡ ለማስጠንቀቅ ሲሉ ያገሣሉ። 

በርቀት ወይም በጨለማ ተነጣጥለው ያሉ የአንድ መንጋ አባላት ያሉበትን ቦታ ለመጠቆም ያገሣሉ። በተጨማሪም አንድ እንስሳ ከገደሉ በኋላ ለሌሎቹ የቤተሰቡ አባላት ምግቡ ያለበትን ቦታ ለማሳወቅ ያገሣሉ። 

አንበሶች በሚያድኑበት ጊዜ የሚያድኗቸውን እንስሳት ለማስደንበር ብለው አያገሡም። ሪቻርድ ኤስቲዝ ዘ ቢሄቭየር ጋይድ ቱ አፍሪካን ማማልስ በተባለው መጽሐፋቸው ላይ “አንበሶች የሚያድኑትን እንስሳ ለማጥመድ ሲሉ ሆን ብለው እንደሚያገሡ የሚጠቁም ምንም ነገር የለም (በተሞክሮዬ እንዳየሁት በአንበሳ የሚታደኑ እንስሳት አንበሳ ለሚያሰማው የግሣት ድምፅ ብዙም ትኩረት አይሰጡም)።” 

ሲምባ በስዋሂሊ “አንበሳ” ማለት ነው። 




#Article 161: ቀጭኔ (1077 words)


ቀጭኔ በአፍሪካ የሚኖር ባለሙሉ ጣት ሸሆኔ ጡት አጥቢ አራዊት ሲሆን በምድር ከሚገኙ እንሰሳት በርዝማኔ የመጀመሪያውን ደረጃ ይዞ ይገኛል። ወንዱ ከ 4.4 እስከ 5.5 ሜትር ርዝማኔና 1,360 ኪሎግራም ክብደት ያስመዘግባል። እስካሁን በሪኮርድ የተያዘው የ 5.87ሜና የ2000ኪ.ግ ቀጭኔ ነው። ሴቶቹ በጥቁቱ አነስ ብለው ይታያሉ።

እነዚህን ፍጥረታት በአራዊት ማቆያ ቦታዎች አንገታቸውን ከታጠሩበት አጥር በላይ ወጣ አድርገው የተመለከተ ሰው በአፍሪካ ቁጥቋጦዎች ነፃ ሆነው ሲሮጡ ያላቸውን ውበትና ግርማ መገመት ያስቸግራል። የቀጭኔ እንቅስቃሴ ትልቅ ግርማ ያለውና እንደ ውኃ ሙላት የሚፈስ ነው። በገላጣው የግጦሽ መስክ ላይ በሚጋልቡበት ጊዜ ቁመናቸው ትንሽ እንቅፋት ቢነካቸው ወድቀው የሚሰባበሩ ያስመስላቸዋል። ይሁን እንጂ እስከ 1, 300 ኪሎ ግራም የሚደርስ ክብደት ያላቸው ወንድ ቀጭኔዎች ቀልጣፋና ምንም የማያደናቅፋቸው ሯጭ ከመሆናቸውም በላይ በሰዓት እስከ 60 ኪሎ ሜትር ሊሮጡ ይችላሉ።

ይህች አስደናቂ ፍጡር የምትገኘው በአፍሪካ ብቻ ነው። እርጋታዋና ሰላማዊ ተፈጥሮዋ ዓይን ይስባል። የቀጭኔ ፊት በዓይነቱ ልዩ የሆነና ቆንጆ ሊባል የሚችል ሲሆን ረዥምና ጠባብ ጆሮዎች፣ ሁለት ትናንሽ ቀንዶች እንዲሁም ጠቆር ያለ ለስላሳ ጠጉር አላት። ዓይኖቿ በጣም ትላልቅና ጥቁር ሲሆኑ ረዣዥም በሆኑ ቅንድቦች ይጠበቃሉ። ቀጭኔ ያን በመሰለ ከፍታ ላይ ሆና ሩቅ ስትመለከት ፊቷ ላይ የየዋህነት ገጽታ ይታይባታል።

በጥንት ዘመናት ቀጭኔ ባላት አስደሳች ቁመና እንዲሁም ጨዋ፣ ዓይነ አፋርና ሰላማዊ ባሕርይ ያላት በመሆኑ በጣም ተወዳጅና ትልቅ ግምት የሚሰጣት ነበረች። በብሔራት መካከል ሰላምና በጎ ፈቃድ መኖሩን ለማመልከት የቀጭኔ ግልገሎች ለነገሥታትና ለገዥዎች በገጸ በረከትነት ይሰጡ ነበር። ጥንታዊ በሆኑት የአፍሪካ አለቶች ላይ ቀለማቸው የደበዘዘ የቀጭኔ ሥዕሎች እስከ ዛሬ ይታያል። 

ከእንስሳት ሁሉ ቀጭኔን በቁመት የሚወዳደር የለም። ሙሉ ዕድሜ ላይ የደረሱ ወንድ ቀጭኔዎች ከእግራቸው ኮቴ አንስቶ እስከ ቀንዳቸው ድረስ ከ5.5 ሜትር የሚበልጥ ርዝመት አላቸው። በግብፃውያን ጥንታዊ ሥዕላዊ የአጻጻፍ ዘዴ ቀጭኔ በረዥም ቁመቷና አርቆ በመመልከት ችሎታዋ ምክንያት “መተንበይ” የሚለውን ግሥ ትወክል ነበር።

ቀጭኔ በአፍሪካ መስኮች በሚሰማሩት የሜዳ አህዮች፣ ሰጎኖች፣ አጋዘኖችና ሌሎች እንስሳት መካከል ስትቆም እንደ ማማ ሆና ትታያለች። ቁመቷና አርቆ የማየት ችሎታዋ ማንኛውንም አደጋ ገና ከሩቅ ለማወቅ ያስችላታል። ስለዚህ የቀጭኔ መኖር ለሌሎች እንስሳት የመረጋጋት ስሜት እንደሚፈጥር ጥርጥር የለውም። 

ቀጭኔ ከዝሆን በስተቀር ማንኛውም ሌላ እንስሳ ሊደርስ በማይችልበት ከፍታ ላይ የሚገኙ ረዣዥም ቀንበጠቦችን ለመብላት የሚያስችል አስደናቂ አፈጣጠር አላት። ልዩ የሆነ የመቆንጠጥ ችሎታ ያለው የላይኛው ከንፈሯና እንደተፈገለው የሚተጣጠፍ ችሎታ ያለው ምላሷ ሹል በሆኑ እሾሆች የታጠሩ ቅጠሎችን ለመቀንጠብ ያስችሏታል።

ቀጭኔዎች በቀን እስከ 34 ኪሎ ግራም የሚመዝን ዕፅዋት መመገብ ይችላሉ። የተለያዩ ዕፅዋትን የሚበሉ ቢሆኑም ይበልጥ የሚመርጡት በአፍሪካ ሜዳዎች የሚገኙትን እሾሃማ ግራሮች ነው። አንድ ወንድ ቀጭኔ ምግብ ለመፈለግ ምላሱን እስከ 42 ሳንቲ ሜትር መዘርጋት ይችላል። የቀጭኔ አንገት በጣም አስደናቂ የሆነ የመተጣጠፍ ችሎታ አለው። ይህም ላይኛዎቹን የዛፍ ቅርንጫፎች ለመቀንጠብ በምታደርገው እንቅስቃሴ ረዥሙን ራሷን እንደ ልቧ ለማዘንበልና ለማዟዟር ያስችላታል።

ለቀጭኔ ወደ ላይ መንጠራራት በጣም ቀላል ነገር ሲሆን ተጎንብሶ ውኃ መጠጣት ግን ይከብዳታል። ወደ ውኃ ጉድጓድ በምትቀርብበት ጊዜ የፊት እግሮቿን ቀስ በቀስ ከፍታ ካራራቀቻቸው በኋላ ወደ ውኃው ለመድረስ እንድትችል ሁለት ጉልበቶቿን አጠፍ ታደርጋለች። ቀጭኔዋ እንዲህ ባለው አመቺ ባልሆነ ሁኔታ እያለች ረዥም አንገቷን እስከ መጨረሻ ትዘረጋለች። ደግነቱ ግን ከምትመገባቸው ቅጠላ ቅጠሎች በቂ እርጥበት ስለምታገኝ ቶሎ ቶሎ መጠጣት አያስፈልጋትም።

የቀጭኔ አንገትና ትከሻ የቅጠል ቅርፅ ባላቸውና ቀጫጭን በሆኑ ነጭ መስመሮች ያጌጠ ነው። ቀለማቸው የተለያየ ሲሆን ከወርቃማ ዳለቻ አንስቶ እስከ ቡናማ እንዲያውም ጠቆር እስካለ ቀለም ይደርሳል። የቀጭኔ ዕድሜ እየገፋ በሄደ መጠን ቀለሟም እየጠቆረ ይሄዳል። 

ቀጭኔዎች ከ2 እስከ 50 የሚደርሱ አባላት ባሉት መንጋዎች ተደራጅተው አንድ ላይ የሚኖሩ ማኅበራዊ ፍጥረታት ናቸው። አንዲት ነፍሰ ጡር ቀጭኔ ልጅዋን ከ420 እስከ 468 ለሚደርሱ እርግዝና ቀናት ከተሸከመች በኋላ ሁለት ሜትር ቁመት ያለው ግልገል ትወልዳለች። ግልገሏ በምትወለድበት ጊዜ ራስዋን ታስቀድምና ከሁለት ሜትር ከፍታ ላይ ወደ መሬት ትወረወራለች። ይሁን እንጂ በ15 ደቂቃ ውስጥ ምንም ዓይነት ጉዳት ሳይደርስባት እየተውተረተረች ትነሳና ጡት ለመጥባት ዝግጁ ትሆናለች። ከሁለት ወይም ከሦስት ሳምንት በኋላ በደመ ነፍስ ተመርታ የግራር ቀንበጦችን መለቃቀም ስለምትጀምር ብዙም ሳትቆይ ረዥም እርምጃ ያላትን እናትዋን ተከትላ ለመሄድ የሚያስችል ጉልበት ታገኛለች።

አንዲት የቀጭኔ ግልገል በጣም ውብ መልክ ሲኖራት የወላጆችዋ አነስተኛ ግልባጭ ነች። ቁመቷ ከቀጭኔ ርዝመት ጋር ሲወዳደር አጭር ብትሆንም ከብዙ ሰዎች ቁመት ግን ትበልጣለች። በእናቷ ጥንቃቄ የተሞላበት ጥበቃ ተማምና አላንዳች መሸበር አካባቢዋን የምትማትረው ግልገል ላያት ሁሉ ልዩ መስህብ አላት።

ግልገል ቀጭኔዎች በተወለዱበት ወራት በግልገል መዋያ ተሰባስበው ሙሉውን ቀን ዕረፍት በማድረግ፣ በመጫወትና በአካባቢያቸው የሚሆነውን ነገር በመመልከት ጊዜያቸውን ያሳልፋሉ። የቀጭኔ ግልገል ለማመን በሚያዳግት ፍጥነት ያድ⁠ጋል። በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ አንድ ሜትር የሚያክል ቁመት ሲጨምር በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ደግሞ በእጥፍ ያድጋል። በአንድ ሳምንት ብቻ 23 ሳንቲ ሜትር ያህል ሊያድግ ይችላል! እናትዬው ለልጅዋ ከፍተኛ ጥበቃ የምታደርግ ሲሆን ልጅዋ የተወሰነ ርቀት እንድትዘዋወር ብትፈቅድላትም ሩቅ የማየት ችሎታ ስላላት በዓይኗ ትከታተላታለች።

ቀጭኔ ግዙፍ አካል፣ ከፍተኛ ፍጥነት፣ ቅልጥፍናና የማየት ችሎታ ስላላት ከአንበሳ በቀር የሚያጠቃት ጠላት የለም። ቢሆንም ይህችን የምታምር ፍጥረት የሰውን ያህል በብዛት አድኖ የገደለ የለም። ቀጭኔ በሚያምር ቆዳዋ፣ በሚጣፍጥ ሥጋዋና አንዳንዶች ምትሐታዊ ኃይል አለው በሚሉት ረዥምና ጥቁር ጭራዋ ምክንያት እጅግ ተፈላጊ ስለሆነች በአሁኑ ጊዜ የዚህች ሰላማዊ ፍጡር የወደፊት ሕልውና ስጋት ላይ ወድቋል። በአንድ ወቅት በብዙ የአፍሪካ አካባቢዎች እንደ ልብ ትታይ የነበረችው ቀጭኔ በአሁኑ ጊዜ የምትገኘው በቂ ጥበቃ በሚደረግላት ፓርኮች ብቻ ሆኗል። 

[የግርጌ ማስታወሻ]

በአፍሪካ ገላጣ ምድር ላይ በሰፊው ተሰራጭተው የሚታዩት ትናንሽ ዓለታማ ኮረብቶች ኮፕጀስ ይባላሉ።

የቀጭኔ አካላዊ ቅርጽና ግዝፈት ችግሮች ማስከተሉ አይቀርም ብሎ የሚያስብ ይኖር ይሆናል። በጣም ትልቅ ቁመትና ረዥም አንገት ስላላት የተስተካከለ የደም ዝውውር እንዲኖራትና ወደ ሁሉም የአካሏ ክፍሎች ደም እንዲደርስ ማድረግ የማይቻል ነገር ሊመስል ይችላል። ለምሳሌ ያህል ቀጭኔ አንገቷን ወደ መሬት ስታጎነብስ በስበት ኃይል ምክንያት ብዙ ደም ወደ ጭንቅላቷ ፈስሶ አንጎሏን ማጥለቅለቅ ነበረበት። ራሷን ቀና በምታደርግበት ጊዜ ደግሞ ደሟ በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ልቧ ተመልሶ ራሷን እስከ መሳት ሊያደርሳት ይገባ ነበር። ይሁን እንጂ ይህ ነገር አይደርስም። ለምን?

የቀጭኔ የደም ዝውውር ሥርዓት በዓይነቱ ልዩ ለሆነው ለዚህች እንስሳ ቅርጽና መጠን እንዲያገለግል ሆኖ በታላቅ ጥበብ የተሠራ ነው። ልቧ ራሱ በጣም ትልቅ ሲሆን ደሙን ሦስት ሜትር ተኩል ገደማ ርቆ እስከሚገኘው እስከ አንጎላ ለመግፋት የሚያስችል አቅም አለው። በደቂቃ እስከ 170 ጊዜ የሚመታውና 7 ሳንቲ ሜትር ያህል ውፍረት ባለው ጡንቻ የተገነባው የቀጭኔ ልብ ከሰው የደም ግፊት በሦስት እጥፍ የሚበልጥ ግፊት ያመነጫል። ወደ አንጎል የሚሄደውን ደም የሚሸከመው ካሮቲድ የተባለው የደም ቧንቧና ከአንጎል ወደ ልብ የሚመለሰውን ደም የሚሸከመው ጀጉላር የተባለው የደም ቧንቧ እንዲህ ያለውን ከፍተኛ ግፊት መቋቋም የሚያስችል መጠን ሊኖራቸው ይገባል። በእርግጥም እነዚህ የደም ቧንቧዎች ከ2.5 ሳንቲ ሜትር በላይ ስፋት ያላቸው ከመሆኑም በላይ ጠንካራና የመለጠጥ ችሎታ ባላቸው ሕዋሳት የተገነቡ በመሆናቸው ከፍተኛ ጥንካሬና የመለመጥ ችሎታ አላቸው።

ቀጭኔ ከጭንቅላቷ ጎንበስ በምትልበት ጊዜ ወደ አንጎሏ የሚሄደውን የደም ፍሰት የሚቆጣጠሩ ልዩ መቆጣጠሪያዎች አሏት። አንጎልና አንገት በሚገናኙበት ቦታ ላይ ትልቁ ካሮቲድ የደም ቧንቧ ሬቴ ሚራቢሌ ተብሎ ከሚጠራ አስደናቂ የሆነ መረብ መሰል አካል ይገናኛል። በከፍተኛ ኃይል ተገፍትሮ የመጣው ደም እዚህ ጋር ሲደርስ በጣም በርካታ ወደሆኑ ትናንሽ የደም ሥሮች እንዲገባ ስለሚደረግ የደሙ ግፊት ተስተካክሎ በአንጎል ላይ ጉዳት የማያስከትል ይሆናል። ቀጭኔዋ ራስዋን ጎንበስ በምታደርግበት ጊዜ ይህ በዓይነቱ ልዩ የሆነው መረብ ይለጠጣል፤ ራሷን ቀና በምታደርግበት ጊዜ ደግሞ ይኮማተራል። ይህም የስበት ኃይል የሚያሳድረው ተጽዕኖ ሚዛኑን የጠበቀ እንዲሆን ማድረግና የደም ግፊቷ በእጅጉ ቀንሶ ራሷን የምትስትበት ሁኔታ እንዳይፈጠር ለመከላከል ይረዳታል።

የሳይንስ ሊቃውንት በጣም አስደናቂ ርዝመት ያለው የቀጭኔ አንገት ያሉት አከርካሪዎች ቁጥር ከአይጥ ወይም ከብዙዎቹ አጥቢ እንስሳ ጋር እኩል መሆኑን ሲያውቁ በጣም ተደንቀዋል! ይሁን እንጂ የቀጭኔ አከርካሪዎች በጣም ረዣዥሞችና እርስ በርሳቸው ልዩ በሆነ ሁኔታ የተሰካኩ በመሆናቸው እንደ ልብ ሊተጣጠፉ ይችላሉ። ቀጭኔ አንገቷን መጠምዘዝና ማጠፍ ስለምትችል ሁሉንም የአካሏን ክፍሎች ለመላስም ሆነ ረዣዥም የዛፍ ቅርንጫፎች ላይ ለመድረስ ትችላለች። 




#Article 162: ዛዛኪኛ (199 words)


ዛዛኪኛ (Zazaki, Zazaish) በምስራቅ ቱርክ አገር በዛዛ ሕዝብ የሚናገር ቋንቋ ነው። የቱርክኛ ዘመድ ሳይሆን ከፋርስኛና ከኩርድኛ ጋር በሕንዳዊ-አውሮፓዊ ቋንቋዎች ቤተሠብና በሕንዳዊ-ኢራናዊ ንዑስ-ቤተሠብ ውስጥ ይገኛል። በተለይ የሚመስለው በስሜን ፋርስ አገር በካስፒያን ባሕር አጠገብ የሚገኘው ጊላኪኛ ነው።

የተናጋሪዎች ቁጥር ከ1.5 እስከ 2.5 ሚሊዮን እንደሚበዛ ይታመናል።

ሦስት ዋንኛ የዛዛኪኛ ቀበሌኞች አሉ:

በዛዛኪኛ መጀመርያ የተጻፉት አረፍተ ነገሮች በ1842 ዓ.ም. በቋንቋ ሊቅ ፒተር ለርች የተከመቹ ነበር። ሌላ ሁለት ቁም ነገር ሰነድች አህማደ ሐሲ በ1891 ዓ.ም. እና ኡስማን ኤፌንዲዮ ባብጅ በ1925 ዓ.ም. የጻፉት ሃይማኖታዊ ጽሑፎች (ማውሊድ) በአረብኛ ፊደል ቀረቡ። 

ዛዛኪኛ በላቲን አልፋቤት መጻፍ የጀመረበት ወቅት በ1970ዎቹ በስዊድን በፈረንሳይና በጀርመን በተበተኑት ተናጋሪዎች በኩል ነበር። ከዚህ ተከትሎ አንዳንድ መጽሔትና መጽሐፍ በቱርክ አገርና በተለይ በኢስታንቡል ይታተም ጀመር። ከዚህ የተነሣ የዛዛ ወጣቶች ለእናት ቋንቋቸው አዲስ ትኩረት ይዘዋል። ከዚህ በላይ ቱርክ በአውሮፓ ኅብረት አባልነት ለማግኘት ስታስብ በሀገሩ በሚገኙ ትንንሽ ቋንቋዎች ላይ የነበሩትን ገደቦች አነሣችላቸው። ስለዚህ አሁን በቱርክ መንግሥት ማሰራጫ ድርጅት ላይ የዛዛኪኛ ቴሌቪዥንና ራዲዮ መደብ በየዓርቡ ተሰጥቷል።

The language differs from most Persian dialects in that it contains archaic strains of Hurrian; it has this in common with the languages Auramani (Hawrami or Gorani) and Bajelani, and these languages are put together in the Zaza-Gorani language group, but also Goran-Zazaistan by those who want emphasize their distinctness from the Kurds.




#Article 163: ላዲኖ (126 words)


ላዲኖ (Dzhudezmo) ከይሁዳዊ-ሮማንስ ቋንቋዎች አንዱ ነው። በእስፓንያ ውስጥ የኖሩት አይሁዶች የተናገሩት ቋንቋ በመሆኑ በተለይ ጥንታዊ እስፓንኛን ይመስላል። 

ጽሑፍ

El djudeo-espanyol o ladino es la lingua avlada por los sefardim, djudios ekspulsados de Espanya en 1492. Es una lingua derivada del espanyol i avlada por 150.000 personas en komunitas en Israel, Turkia, antika Yugoslavia, Gresia, Maruecos, entre otros.

አጠራር

ኤል ጁዴዮ-ኤስፓንዮል ኦ ላዲኖ ኤስ ላ ሊንጓ አቭላዳ ፖር ሎስ ሰፋርዲም, ጁዲዮስ እክስፑልሳዶስ ዴ ኤስፓንያ ኤን 1492። ኤስ ኡና ሌንጓ ደሪቫዳ ዴል ኤስፓንዮል ኢ አቭላዳ ፖር 150,000 ፔርሶናስ ኤን ኮሙኒታስ ኤን ኢስራኤል, ቱርኪያ, አንቲካ ዩጎስላቭያ, ግሬሲአ, ማሩዌኮስ, ኤንትሬ ኦትሮስ።

ትርጉም

አይሁዳዊ እስፓንኛ ወይም ላዲኖ በ1484 ዓ.ም. ከእስጳንያ በተባረሩት አይሁዶች በሴፋርዲም የተናገረ ቋንቋ ነው። ከስፓንኛ የወጣ ቋንቋ ነውና በእስራኤል በቱርክ በቀድሞው ዩጎስላቭያ በግሪክ በሞሮኮና በሌሎች ኅብረተሠቦች 150,000 ስዎች ይችሉታል። 




#Article 164: ዊጉርኛ (213 words)


ኡይጉርኛ (ئۇيغۇرچە‎ / Uyƣurqə / Уйғурчә) በቻይና የሚናገር የቱርኪክ ቋንቋዎች አባል ነው። እንደ ዘመዱ ዑዝበክኛ የተወለደው ከጫጋታይ ቱርክኛ ነበረ።

በድሮ (700 ዓ.ም. ገደማ) የጥንታዊ ኡይጉርኛ ፊደል ከሶግዲያን ፊደል ተለውጦ ይጠቀም ነበር። ደግሞ የኡይጉር መንግሥት የኦርኮን ጽሕፈት ይጠቀም ነበር። ኡይጉርኛ በቻይና የተጻፈበት ጽሕፈት ከ10ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የአረብኛ ፊደል ሲሆን በ1961 ዓ.ም. የቻይና መንግሥት የላቲን ፊደልን አይነት አወጣለት። በ1975 ዓ.ም. ግን የአረብኛ ፊደል ተመለሰለት። በተጨማሪ በቀድሞው ሶቭየት ኅብረት ውስጥ የሚኖሩ ኡይጉሮች በቂርሎስ ፊደል አይነት ይጽፋሉ። 

በአረብኛ ፊደል:ھەممە ئادەم زاتىدىنلا ئەركىن، ئىززەت-ھۆرمەت ۋە ھوقۇقتا بابباراۋەر بولۇپ تۇغۇلغان. ئۇلار ئەقىلغە ۋە ۋىجدانغا ئىگە ھەمدە بىر-بىرىگە قېرىنداشلىق مۇناسىۋىتىگە 
خاس روھ بىلەن مۇئامىلە قىلىشى كېرەك

በላቲን ፊደል (ከ1961 እስከ 1977 ይጠቀም ነበር): H̡əmmə adəm zatidinla ərkin, izzət-h̡ɵrmət wə hok̡uk̡ta babbarawər bolup tuƣulƣan. Ular ək̡ilƣə wə wijdanƣa igə h̡əmdə bir-birigə k̡erindaxlik̡ munasiwitigə hax roh bilən mu’amilə k̡ilixi kerək.

በቂርሎስ ፊደል (ከቻይና ውጭ ይጠቀማል)፦ Һәммә адәм затидинла әркин, иззәт-һөрмәт вә һоқуқта баббаравәр болуп туғулған. Улар әқилғә вә виджданға игә һәмдә бир-биригә қериндашлиқ мунасивитигә хаш рох билән му’амилә қилиши керәк.

በግዕዝ ፊደል፦ ሀመ አደም ዛቲዲንላ አርኪን፥ ኢዘት-ሄርመት ወ ሖቁቅታ ባባራወር ቦሉፕ ቱኁልኃን። ኡላር አቂልኅ ወ ዊጅዳንኃ ኢገ ሀምደ ቢር-ቢሪገ ቀሪንዳሽሊቅ ሙናሲዊቲገ ሓሽ ሮሕ ቢላን ሙአሚለ ቂሊሺ ከረክ።

ትርጉም፦ «የሰው ልጅ ሁሉ ሲወለድ ነጻና በክብርና በመብትም እኩልነት ያለው ነው። የተፈጥሮ የማስተዋልና ኅሊናው ስላለው አንዱ ሌላውን በወንድማማችነት መንፈስ መመልከት ይገባዋል።» (ከተመድ መብቶች ጽሑፍ)




#Article 165: ኖቪያል (147 words)


ኖቪያል (Novial) በኦቶ የስፐርሰን በ1920 ዓ.ም. የተፈጠረ ሰው ሠራሽ ቋንቋ ነው። ቃላቱ በተለይ ከጀርመንኛና ከሮማንስ ቋንቋዎች የተመሠረተ ነው። የስፐርሰን በ1935 ዓ.ም. ሲሞቱ ሀሣቡ በሥራ እንዳይውል ተደረገ። በ1980ዎቹ ግን ከኢንተርኔት የተነሣ አዲስ ትኩረት ተሰጥቶታል። እንደ ኤስፔራንቶ ፈጣሪ ዛምንሆፍ ሳይሆኑ የዴንማርክ ዜጋ የሆኑ አቶ የስፐርሰን ባለሙያ የቋንቋ ሊቅ ነበር። በሌሎች ሠው ሠራሽ ቋንቋዎች የተገኘው ቅጥ የሌለው ዘዴ አልወደዱም። ስለዚህ በቋንቋ ጥናት መርሆች ላይ የተመሠረተ ቋንቋ ለመፍጠር ጣሩ።

አገናዛቢ -n, -en (ን, -ኤን) ለተውላጠ ስም በመጨመር ይመለከታል። 

ፕሮቴክቴ - መጠበቅ
ሜ ፕሮቴክቴ - እጠብቃለሁ
ሜ ዲድ ፕሮቴክቴ / ሜ ፕሮቴክቴድ - ጠበቅሁ
ሜ ሃ ፕሮቴክቴ - ጠብቄያለሁ
ሜ ሃድ ፕሮቴክቴ - ጠብቄ ነበር
ሜ ሳል ፕሮቴክቴ - ወደፊት እጠብቃለሁ
ሜ ሳል ሃ ፕሮቴክቴ - ወደፊት እጠብቅ ነበር
ሜ ሳሌድ ፕሮቴክቴ - ልጠብቅ ነበር
ሜ ቩድ ፕሮቴክቴ - እጠብቅ ነበር
ሌት ኑስ ፕሮቴክቴ - እንጠብቅ
ፕሮቴክቴ! - ጠብቅ!
ሌት ሎ ፕሮቴክቴ! - ይጠብቅ! 
ፕሮቴክቴንት - ጠባቂ
ፕሮተክቴት - የተጠበቀ

የጌታ ጸሎት:-




#Article 166: ቀቿ (101 words)


ቀቿ (Qhichwa Simi / Runa Shimi / Runa Simi) በደቡብ አሜሪካ በ10 ሚሊዮን ሰዎች የሚናገር ቋንቋ ነው። በጥንታዊ ኢንካ መንግሥት መደበኛ ቋንቋ ነበረ። ዛሬም በቦሊቪያ ፔሩና አንዳንድ አውራጃ በኤክዋዶር መደበኛ ሁኔታ አለው። አይማራ የሚባለው ሌላ ደቡብ-አሜሪካዊ ቋንቋ ዘመድ ነው።

እስፓንያውያን ከወረሩ አስቀድሞ በሰፊ ይሰማ ሲሆን በዚያን ጊዜ ምንም ጽሕፈት አልነበረውም። ይሁንና መቆጣጠር ሲባጎዎች በማሰር ዘዴ ነበር የተፈጸመ። ዛሬ የሚጻፈው በላቲን ፊደል ነው።

በቀችዋ ሦስት አናባቢዎች ብቻ አሉ እነሱም አ ኢ ኡ ናቸው። 
 
ቁጥሮች:- huk (1), iskay (2), kimsa (3), tawa (4), pichqa (5), suqta (6), qanchis (7), pusaq (8), isqun (9), chunka (10)

አብዛኛው አረፍተ ነገር የ'እርግጠኛነት ምልክት' ባዕድ መድረሻ አለው። 




#Article 167: አሦር (624 words)


አሦር (አሹር) ማለት በጥንታዊ ዘመን በላይኛ ጤግሮስ ወንዝ አጠገብ የተገኘ ከተማና አካባቢው ነበረ። በኋለኛ ጊዜ የአሦር መንግሥት ሃይለኛ ሆኖ መላ መሬት እስከ ግብጽ ድረስ ገዛ። በጥንታዊ አሦር ከተማና በጤግሮስ አጠገብ ያሉትም ተራሮች እስከ ዛሬው አርሜንያ ድረስ 'የአሦር ተራሮች' ይሰየሙ ነበር። 

በኦሪት ዘፍጥረት መሠረት አሦር (አሹር) ከኖኅ ልጅ ሴም ልጆች አንዱ ሲሆን፥ ከሰናዖር ወጥቶ አንዳንድ ከተማ ሠራ። በአሦራውያንም እምነት ዘንድ 'አሹር' ከተማውን የመሠረተው አምላክ ስም ነበረ።

ከቅድመኛው ዘመን አውራጃው ሹቡር ተብሎ ከሰናዖር (ሹመር)፣ ማሪ ወይም ከአካድ ይገዛ ነበር። ሹቡር በታላቁ ሳርጎን መንግሥት ውስጥ ክፍል ሆኖ ጉታውያን እስከ አጠፉት ድረስ ቆየ። በኋላ እስከ 1879 ዓክልበ. ግ. ከኡር 3ኛ ሥርወ መንግሥት ይቆጣጠር ነበር። የዑር መንግሥት ሲወድቅ የአሦር ከተማ ነገሥታት ሊሙ ስሞች ይመዘገባሉ።  

በዚህ ወቅት አሦር ከተማ-አገር ብቻ ነበረ። ሆኖም አሦራውያን የብረታብረት ንግዳቸውን ለማስፋፋት በማሰብ አንዳንድ ቅኝ-ከተማ (ካሩም) በሐቲ (ዛሬው ቱርክ) ውስጥ መሠረቱ። ከነዚህም ዋነኛው ካነሽ የተባለው ከተማ ነበር። 

በ1720 ዓክልበ. ግ. አሞራዊው ንጉሥ 1 ሻምሺ-አዳድ አገሩን ከነአሦር ከተማ አቀና። ልጁን  1 እሽመ-ዳጋን (1688-1678 ዓክልበ.) በአሦር ላይ ሾመው። ነገር ግን የባቢሎን ንጉስ ሃሙራቢ ድል አድርጎት ዙሪያው ወደ ባቢሎን መንግሥት ተሳለፈ። ከትንሹ እስያ ይካሄድ የነበረው የብረታብረት ንግድ በዚያን ጊዜ ተቋረጠ። ለሚከተለው መቶ አመት አሦር ለባቢሎን ተገዥ ነበር። 

በ1507 ዓክልበ. ግ. ባቢሎን ለካሣውያን ከወደቀ በኋላ፥ አሦር በሚታኒ መንግሥት (ሑራውያን) በ1441 ዓክልበ.ግ. ይሸነፍ ነበር። ሚታኒ በኬጢያውያን ግፊት ሲወድቅ ግን የአሦር ንጉስ አሹር-ኡባሊት ነጻነቱን አዋጀ (1366 ዓክልበ. ያህል)። ከዚህ በላይ ይህ አሹር-ኡባሊት የራሱን ልጅ ኩሪጋልዙን በባቢሎን ዙፋን ላይ አሾመው። 

በ1290 ዓክልበ. የአሦር ንጉስ 1 አዳድ-ኒራሪ የሚታኒን መንግሥት አሸነፈ። የአዳድ-ኒራሪ ተከታይ 1 ስልምናሶር መንግሥቱን በከጢያውያን አግጣጫ እስከ ከርከሚሽ ድረስ አስፋፋ። የስልምናሶርም ልጅ 1 ቱኩልቲ-ኒኑርታ እንኳን በባቢሎን ላይ ገዛ። ሆኖም በቅርብ ጊዜ ባቢሎን በአሦር ላይ አመጽ ታደርግ ነበር። 

በ1200 ዓክልበ.. አካባቢ የኬጢያውያን መንግሥት በሙሽኪ (ፍሩጋውያን) ግፊት ስለ ወደቀ፥ ባቢሎንና አሦር ለአሞራውያን መሬት ተወዳዳሪዎች ሆኑ። የአሦር ንጉስ 1 አሹር-ረሽ-ኢሺ በዚህ አቅራቢያ በ1140 ዓክልበ. በባቢሎንን ንጉሥ 1 ናቡከደነጾር ላይ አሸነፈ።

የአሹር-ረሽ-ኢሺ ልጅ 1 ቴልጌልቴልፌልሶር የመንግሥቱን ጠረፍ በጣም አስፋፋ። ከርከሚሽን ከመማረኩ በላይ በሙሽኪ ላይ እስከ ጥቁር ባሕር ድረስ ዘመቻ አደረገ። ደግሞ እስከ ሜድትራኒያን ባሕር ድረስ ሲዘረጋ ፊንቄን (ሊባኖስ) ያዘ። 

ከ1 ቴልጌልቴልፌልሶር በኋላ ከጎረቤቶቹ ከአራማውያንና ከኡራርቱ የተነሣ የአሦር ኅይል ደክሞ ነበር። በ920 ዓክልበ. ግን 2 አዳድ ኒራሪ ንጉሥ ሆሞ የአሦር ሃይል ታደሰ። ደግሞ ወደ ስሜን የኖሩትን ሕዝቦች በሙሉ በሰፈራ አፈለሳቸው። ይሁንና መንግሥቱ ከአቦር ወንዝ ወደ ምዕራብ አልዘረጋም። 

ንጉስ አሹር-ናሲር-ፓል ከ890 ዓክልበ. ጀምሮ ነግሦ ያለ ምኅረት ጠረፎቹም አስፋፋ። ከአቦርና ከኤፍራጥስ መካከል ያሉትን አራማውያን ድል አድርጎ በሜድትራኒያን ሲደርስ ፊንቄን ቀረጠ። ካልሁንም ዋና ከተማው እንዲሆን አደረገው። 

 
በልጁ 3 ስልምናሶር 34 አመት ዘመን (865-831 ዓክልበ.) አሦር በየአመቱ ለጦርነት ሠለፈ። ባቢሎን ተወርሮ ተቀረጠ። የሶርያ (አራም-ደማስቆ) ንጉስ ወልደ አዴር (አድርአዛር) ከእስራኤል ንጉስ አክዓብ ጋራ በቃርቃር ፍልሚያ ስልምናሶርን አጋጠመው። ስልምናሶርም ፊንቄንና የእስራኤል ንጉስ ኢዩን አስቀረጠ። በዋና ከተማው በካልሁ የተገኘው ጥቁር ሐውልት ስለ 3 ስልምናሶር ዘመን ድርጊቶች ይመሰክራል ። ከዚህ ቀጥሎ የአሦር አቅም ለመቶ አመት እንደገና ይደክም ጀመር። ሆኖም ንጉሱ 3 አዳድ-ኒራሪ (818-790 ዓክልበ.) ስርያን ማረከ ሜዶንንም ወረረ።

በ755 ዓክልበ. አሦር በብሔራዊ ጦርነት ተይዞ ባቢሎን በንጉሱ ናቦፖላሣር መሪነት እንደገና ነጻነቱን አዋጀ። በሚከተለው አመት ፎሐ (ፑሉ) የሚባል አለቃ የአሦር መንግሥት ቀምቶ 3 ቴልጌልቴልፌልሶር ተብሎ ንጉስ ሆነ። እሱ በዘመኑ ባቢሎንን ዳግመኛ ቀርጦ ኡራርቱን፤ ሜዶንንና ኬጢያውያንን ድል አድርጎ ሠራዊቱን ወደ ሶርያ ወደ ፊንቄም አዞረ። አርፋድን በ 748 ዓክልበ. አጠፋ፤ ሐማትንም ያዘ። በ746 ዓክልበ. ፊልሥጥኤም ወርሮ የእስራኤልን ንጉስ ምናሔምን 1000 መክሊት ብር አስገበረ። በኋላ (740 ዓክልበ.) የእስራኤል ንጉስ ፋቁሔ ከሶርያ (አራም) ንጉስ ረአሶን ጋራ አደጋ በይሁዳ ላይ ሲጣሉ የይሁዳ ንጉሥ አካዝ የመቅደሱን ወርቅ ሰጥቶ ከቴልጌልቴልፌልሶር እርዳታ ጠየቀ። ከዚያ ቴልጌልቴልፌልሶርም ደማስቆን አጠፍቶ የሶርያ ሕዝብና የእስራኤል ግማሽ ሕዝብ በምርኮት ወደ ሌላ አገሮች ሰደዳቸው። 

በ737 ክ.በ. ቴልጌልቴልፌልሶር ወደ ባቢሎን ወርዶ ንጉሱን ናቡ-ሙኪን-ዜሪ ማረከና እራሱ 'የባቢሎን ንጉስ ፑሉ' ተብሎ ዘውዱን ተጫነ።

በ735 ክ.በ. ልጁ 5 ስልምናሶር ተከተለው። እሱ የመንግሥቱን ግዛት በየአውራጃው እያካፈለ፣ ተገዥ አገሮች ቀረጥ አንሰጥም ብለው አመጸኛ በሆኑበት ወቅት፣ አሦራዊ አገረ ገዥ አደረገባቸው። የእስራኤል ንጉሥ ሆሴዕ ግን በ733 ክ.በ. ግብርን ባቋረጠ ጊዜ የግብጽ ጠባቂነት አገኘ። ስለዚህ ስልምናሶር ወርሮ ከሦስት አመት ትግል በኋላ ሰማርያን ያዘና የእስራኤልን ቅሬታ ወደ ሌላ አገሮች ሰደዳቸው።

በ730 ክ.በ. ስልምናሶር ሰማርያን እየከበባት ድንገት ከሞተ በኋላ ሻለቃው 2 ሳርጎን ዙፋኑን ያዘ። 




#Article 168: መንግስቱ ለማ (254 words)


መንግሥቱ ለማ (1924-1988) በጣሊያን ወረራ ዋዜማ በሀረር ሀደሬ ጢቆ መካነ ሥላሴ ተወልዶ ከቆሎ ተማሪነት ተነስቶ የለንደን ስኩል ኦፍ ኢኮኖሚክስ ደቀመዝሙርነት እስከመሆን በቅቶ የቅኔ ቤት ሊቅነት ሳይበቃው የአማርኛ ሥነ ጽሑፍ ቀደምቶች መሃከል ለመደብለቅ የበቃ ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው ድንቅ ገጣምያን/ፀሃፌ ተውኔቶች አንዱ ነው። አባቱ አለቃ ለማ ኃይሉ ወልደ-ታሪክ (ታሪክ የእናታቸው ስም ነው - ምናልባት በኢትዮጵያ ታሪክ የእናታቸውን ስም ከስማቸው አስተባብረው በመጻፍ የመጀመሪያው ሳይሆኑ አይቀሩም) ታዋቂ የቤተክርስቲያን ሊቅ የነበሩ ሲሆን በመጀመሪያ ላይ የመንግስቱን የአስኳላ (በወቅቱ ዘመናዊ ትምህርት የሚጠራው እንዲህ ነበር) ትምህርት ባይወዱለትም ጣሊያኖቹ ልጁን የማያስተምር ሰው ሁሉ ይቀጡ ስለነበር ለማስተማር ተገደዋል። ሁዋላ ላይ ግን እሳቸው አዲስ አበባ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ትእዛዝ ተቀይረው መጥተው እሱ የኮተቤ ተማሪ ከሆነና የትምህርት ውጤቱም እስደሳች ሲሆን የቀድሞ ቅዋሜያቸውን ሳያላሉት አልቀሩም።

መንግስቱ በእንግሊዝ አገር ወደ ስድስት አመት ቢቆይም ትምህርቱን ሳያጠናቅቅ ነው በ1956 ዓ.ም ወደ አገሩ ለመመለስ የበቃው። ይሁን እና በቆይታው ከብዙ የእንግሊዝ ደራስያን ጋር ለመተዋወቅ በቅቷል። በተለይም ከጆርጅ በርናርድ ሾው ጋር ወዳጆች እንደነበሩ ይነገራል።

መንግሥቱ ወደ አዲስ አበባ ከተመለሰ በሁዋላ የተሰማራው ወደ መንግስት ሥራ ሲሆን በህንድ አገር ዲፕሎማት ሆኖ ከሄደ በሁዋላ ምናልባትም በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን ዘመናዊ ኮሜድ ተውኔት «ጠልፎ በኪሴን ደርሷል:: ከዚያ በሁዋላ የደረሳቸው እነ «ያላቻ ጋብቻ»፣ «ጸረ-ኮሎኒያሊስት»፣ «ባለካባና ባለዳባ» የመንግስቱን ስም በኢትዮጵያ የስነ-ጽሁፍ ታሪክ ውስጥ ቀዳሚ ተጠቃሽ ካደረጉት ስራዎቹ መካከል ናቸው። በተጨማሪም «The bear» የተሰኘውን እና የታዋቂው የሩሲያ ደራሲ አንቷን ቼኾቭ ተውኔት የሆነውን «ዳንዴዎ ጨቡዴ» በሚል የተረጎመ ሲሆን የጄ.ቢ. ፕሪስትሊን «The Inspector Calls»ን ተርጉሞ ለመድረክ አብቅቷል።

መንግስቱ ከተውኔቱ በተጨማሪም በስነ-ግጥም የተዋጣለት እንደነበር ስራዎቹ ይመሰክራሉ። «የግጥም ጉባኤ» የተሰኘው ስብስብ መንግስቱ የግጥም መክሊት የተቸረው ደራሲ እንደነበር ይመሰክራል። 

መንግሥቱ ደራሲም ብቻ አልነበረም፤ በተማሪዎቹ የተወደደ መምህር በሳል ተመራማሪ ለባህሉ እና ለቋንቋው ሙት የነበረ ከኢትዮጵያ ብርቅዬዎች አንዱ ነው።




#Article 169: ሊኦፖልድ ሴዳር ሴንጎር (117 words)


ሊኦፖልድ ሴዳር ሴንጎር (1906-2001) የሴኔጋል የመጀመሪያው መራሄ መንግስት በመሆን ከ1960 እስከ 1980 ድረስ ያገለገሉ፣ ኔግሪቲዩድ የሚባለው ፍልስፍና ዋነኛ አቀንቃኝ የነበሩ እና በግጥሞቹም አድናቆትን ያተረፉ አፍሪካዊ የሥነጽሁፍ ሰው ናቸው። 

ሴንጎር የሴኔጋል ዋና ከተማ ከሆነችው ዳካር 70 ማይልስ ያህል በምትርቅ እና ጆአል ላ ፖርቱጊዝ (ጆአል ፖርቱጊዛዊቱዋ) በምትባል ትንሽ የአሳ አጥማጆች መንደር በ1906 ተወለዱ። አባታችው ነጋዴ ከሆኑ ሴሬር ከሚባሉ ጎሳ የተወለዱ ሲሆን እናታቸው ግን ፔውል ከተባለ የሙስሊም ዘላን አርብቶአደሮች ጎሳ የተወለዱ ሴት ናቸው። ሴንጎር ኋላ ላይ ሲጽፉ «ተወልጄ ያደኩት በአፍሪካ መኸል፣ የጎሳዎች እና ዘሮች መገናኛ ላይ ነው» ብለዋል።

በ12 ዓመታችው የካቶሊክ ሚሲዮን ትምህርት ቤት ተመዝግበው ትምህርታቸውን የጀመሩ ሲሆን ከዛ በኋላ በሌሎች ትምህርት ቤቶችም በመማር በ1928 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አጠናቀዋል። ከዚያም ፓሪስ ከሚገኘው ሊሴ ፓሪ ለግራንድ ከተባለው ትምህርት ቤት በ1931 ተመርቀዋል።




#Article 170: ቺኑዋ አቼቤ (147 words)


በሙሉ ስሙ ሲጠራ አልበርት ቺኑዋሉሞጉ አቼቤ ይሰኛል። ምናልባትም ናይጄሪያ ካሉዋት ምርጥ ፀሃፍት ዝርዝር ውስጥ በአንደኛ ደረጃ የሚሰለፍ ሳይሆን አይቀርም። በ1930 እ.ኤ.አ. ኦጊዲ በተባለች የናይጄሪያ ግዛት ከአዜያህ ኦካፎ እና ከጃኔት አቼቤ ተወለድ። በ1953 እ.ኤ.አ. ከለንደን ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ዲግሪውን አግኝቷል።

ለአቼቤ ድንቅ ሥራ የተባለለት Things Fall Apart 50 ወደሚሆኑ የአለም ቁዋንቁዋዎች የተተርጎመ ሲሆን ወደ 10,000,000 ቅጂዎች እንደተሸጡለት ይነገራል። አቼቤ ከአፍሪካ ፀሃፍት ሁሉ ሥራው በበዙ ቁዋንቁዋዎች በመተርጎም ክብረ ወሰኑን እንደያዘ ነው። ብዙዎችም ይኸው ድርሰቱ በአለም እስከዛሬ ከተደረሱ ምርጥ ልበ-ወለዶች መካከል እንደሆነ ይስማማሉ። 
አቼቤ ከ30 ከሚበልጡ ዩኒበርስቲዎች የክብር ዶክትሬት የተቀበለ ሲሆን ብዙ ሽልማቶችንም ከተለያዩ ድርጅቶች አግኝቷል። ይሁንና እስከ አሁን ድረስ የኖቤል ሽልማት ለማግኘት አልታደለም። ይኸውም በብዙው ጽሁፉ የመራቡን አለም ዘረኛነት የሚተች በመሆኑ እንደሆነ ይነገራል። 

በ1990 ዓ.ም በደረሰበት የመኪና አደጋ ምክንያት ከወገቡ በታች መንቀሳቀስ የተሳነው ሲሆን ኒው ዮርክ ውስጥ በሚገኘው የባርድ ኮሌጅ የቋንቋና ሥነ-ፅሁፍ ፕሮፌሰር ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል።

ልብ-ወለድ ድርሰቶች

አጫጭር ታሪኮች

የግጥም መድብል

መጣጥፎች፣ ሂስ እና ፖለቲካዊ አስተያየቶች 

የህጻናት መጻህፍት




#Article 171: ናጊብ ማህፉዝ (162 words)


ናጊብ ማህፉዝ በ1988 እ.ኤ.አ. በስነ-ጽሁፍ የኖቤል ሽልማትን የተቀዳጀ ግብጻዊ ደራሲ ነው።

ማህፉዝ ካይሮ ውስጥ ገማልያ በተባለው ሰፈር ዲሴምበር 11፣ 1911 እ.ኤ.አ. ተወለድ። የመጠሪያ ስሙን የወረሰው ሲወለድ አዋላጅ ሃኪም ከነበሩት ከፕሮፌሰር ናጊብ ማህፉዝ ፓሻ ነው። ማህፉዝ ለረጅም ዘመን በመንግስት መስሪያቤቶች ውስጥ ያገለገል ሲሆን በስነ-ጽሁፉም ዘርፍ 34 ወጥ ልብ-ወለዶች፣ ከ350 የሚዘሉ አጫጭር ታሪኮች፣ ከደርዘን በላይ የሲኒማ ድርሰቶች፣ እና አምስት ተውኔቶችን አበርክቷል።

በ1971 ያሳተመው «ጭውውት በአባይ ወንዝ ላይ» (Chitchat on the Nile) የተሰኘው ድርሰቱ ተወዳጅነትን ካተረፉለት ስራዎቹ መካከል ሲሆን የገማል አብድል ናስር አገዛዝ በግብጽ ማህበረሰብ ላይ ያደረሰውን ዝቅጠት የሚተች ነው። 

ማህፉዝ የአንዋር ሳዳት መንግስት ደጋፊነቱ የታወቀ ሲሆን ግብጽ ከእስራኤል መንግስት ጋር በካምፕ ዴቪድ ያደረገችው የሰላም ስምምነት ደጋፊም ስለነበር ድርሰቶቹ ለብዙ ዓመታት በአረብ አገራት ታግደው ቆይተው እገዳው የተነሳላቸው የኖቤል ሽልማትን እንዳሸነፈ ከተሰማ በኋላ ነው።

ማህፉዝ የኖቤልን ሽልማት ለመቀበል ለግብጽም ሆነ ለአረቡ ዓለም የመጀመሪያው ሲሆን በስነ-ጽሁፍ የኖቤል ተሸላሚ ከሆኑት ሰዎች ሁሉ የረጅም እድሜ ባለቤት በመሆን ሶስተኛ ደረጃን የያዘ ሰው ነው።

ማህፉዝ ኦገስት 30 ቀን፣ 2006 አርፎ ቀብሩ በኦገስት 31 ቀን ካይሮ ውስጥ በሚገኘው የአል ረሽዳን መስጊድ ተፈጽሟል። 




#Article 172: አማ አታ አዪዶ (104 words)


ክሪስቲና አማ አታ አዪዶ  በማርች 23፣ 1942 እ.ኤ.አ. ጋና ውስጥ ተወለደች። ትምህርቷን በዌስሊ የልጃገረዶች ትምህርት ቤት፣ በመቀጠልም በጋና  ዩኒቨርስቲ ተከታትላ በ1964 ዓ.ም በእንግሊዝኛ ቋንቋ የመጀመሪያ ዲግሪዋን ተቀብላለች። የመጀመሪያ የድርሰት ስራዋ የሆነውን «The Dilemma of a Ghost»ን በዚያ ዓመት ለማጠናቀቅ የበቃች ሲሆን ይሄው ድርሰቷ በሎንግማን አሳታሚ ድርጅት አማካይነት በቀጣዩ ዓመት ታትሞላታል።

አዪዶ በልብ-ወለድ ደራሲነት ብቻ አይደለም እውቅናን ያተረፈችው፤ በጸሃፌ-ተውኔትነት እና ገጣሚነትም እንጂ። ጽሁፎቿ በአብዛኛው የዘመኑ የአፍሪካ ሴቶች ስላላቸው ሚና እና የምእራባዊው ባህል ስለሚያሳድርባቸው ኢርቱእ ተጽኖ ላይ የሚያተኩሩ ናቸው።

አዪዶ በ1982 የጋና የትምህርት ሚኒስትር ሆና ብትሾምም በስራው ላይ የቆየችው ለ18 ወራት ያህል ብቻ ነው። በአሁኑ ወቅት በብራውን ዩኒቨርስቲ የአፍሪካ ጥናት ክፍል ውስጥ ተጋባዥ ፕሮፌሰር በመሆን ትሰራለች።

 




#Article 173: ፖርቱጋል (485 words)


ፖርቱጋል ወይም ፖርቹጋል (ፖርቱጊዝኛ፦ Portugal /ፑርቱጋል/) በኤውሮፓ ውስጥ የሚገኝ ሀገር ነው። የፖርቹጋል መንግሥት በምዕራብና በደቡብ ከአትላንቲክ ውቅያኖስ፤ በምሥራቅና በሰሜን ከኤስፓኝ መንግሥት ጋር ይዋሰናል።

የፖርቱጋል ስም ከአንድ ሮማይስጥ ወደብ ስም /ፖርቱስ ካሌ/ («የካሌ ወደብ»፣ የአሁንም ፖርቱ) መጥቷል። የ«ካሌ» ትርጉም እዚህ ቢካራከርም ዋናው አስተሳሰብ ከጋሊስያ (የእስፓንያ ክፍላገር) እና ከጥንቱ ጋላይኪ ወገን (ኬልቶች) ጋር እንደ ተዘመደ የሚለው ነው። በየጥቂቱ የሮማይስጥ አጠራር /ፖርቱስ ካሌ/ ወደ /ፖርቱካሌ/ (400 ዓም ግ.)፣ እና /ፖርቱጋሌ/ (600 ዓም ግ.) ተለወጠ፣ ከ800 ዓም ግ. በኋላ ለመላው አውራጃ ይጠቀም ጀመር። «ፖርቱጋል» (Portugal) የሚለው አጻጻፍ ከ1000 ዓም ግድም ጀምሮ ሲገኝ፣ በአማርኛ ደግሞ የአገሩ ስም እንደ እንግሊዝኛው አጠራር እንደ ፖርቹጋል ሊጻፍ ይችላል። የብርቱካን ፍራፍሬ፣ ዛፍ፣ ቀለም ስም ደግሞ ከፖርቱጋል ስም ደርሶልናል።

የፖርቹጋል የጥንት ስም ሉዚታኒ ነው። በመጀመሪያም በአገሪቱ የነበሩት ሕዝቦች ሴልቶ ኢቤሪክ የሚባሉ የህንዶ-ኤውሮፓዊ ወገን ሆነው በኋላ ወደ ላቲንነት በልማድና በኑሮ በሃይማኖትም የተለወጡ ናቸው። የፖርቱጋል ሕዝብ በጀርመንና በኖርማንዲ በሮማውያንና በዐረቦች ሞሪ (ማውሪታኒ) ከሚባሉ በአፍሪካ ሰሜን ሕዝብና በዕብራውያንም የተቀያየጠ ነው። ነገር ግን እነዚህ ሁሉ ባንድነት ሰፊ ዘመን በሮማ መንግሥት ስለ ተገዙ በዘርም በልማድም አብዛኛውም ወደ ላቲንነት ተለውጠዋል። የሮማ መንግሥት ከወደቀ በኋላ በአምስተኛውና በስምንተኛው መቶ ዓመተ ምሕረት መካከል በነበረው ጊዜ ውስጥ እየተከታተለ ቢዚጎትና ስቤብ የሚባሉ የጀርመኖች ቀጥሎም የዐረቦች ወረራ ደርሶባቸዋል። በአስረኛው መቶ ዓ.ም. ግን አስቱሪዩ የሚባሉት የክርስቲያን ወገኖች እስላሞቹን አጥፍተው ሊስቦን ገብተው ገዥ ሆነው መንግሥታቸውን አቋቋሙ። ከዚያ ከ፲፪ እስከ ፲፬ መቶ ዓ.ም ድረስ ቤተ መንግሥቱን የቡርጎኝ ሥርወ መንግሥት ሲገዛው ቆይቶ በኋላ ሔቢዝ ለተባለው ቤተ መንግሥት አሳለፈው። በነዚህ መሪነት ጊዜ ይኸውም ማለት በ፲፬ኛውና በ፲፭ኛው መቶ ዓመተ ምሕረት ላይ የፖርቱጋል መንግሥት ከሌላው ሁሉ ይልቁንም በባሕርና በመርከብ ኃይል ሆነ።

በዚህ በ፲፭ኛው መቶ ዓ.ም. ላይ የቱርክ፣ የመስኮብ፤ የጀርመን፤ የእንግሊዝ፤ የፈረንሳይና የኤስፓኝ መንግሥታት እንደ ኃያላን መንግሥታት መቆጠራቸው አልቀረም። ነገር ግን ከነዚህ ሁሉ የፖርቱጋል መንግሥት በሌላው እንኳን ባይሆን በመርከብና አገር በመያዝ ከቀሩት ይበልጥ ነበር። የቀሩት የኤውሮፓ መንግሥታት እዚያው ወሰናቸው ላይ ገዥነታቸውን ለማጽደቅ እርስ በርሳቸው ሲጨቃጨቁ የፖርቱጋል መንግሥት ግን ደኅና ደኅና መርከቦችን አዘጋጅቶ እየላከ ከመንግሥቱና ከኤውሮፓ ርቆ የሚገኘውን የአሜሪካን፤ የእስያን፤ የአፍሪካን አገሮች ያስመረምር ነበር። መርማሪዎቹም እነቫስኮ ደጋማ፤ እነፔሬዝ፤ እነአንድራድ፤ እነካብራል በመርከብ እየሄዱ ለመከላከል ጉልበት የሌለውንና በጠባዩ ሀብት ያለበትን አገር መርምረው ሲመለሱ መንግሥቱ ወታደር በመርከብ እየላከ ብዙ አገር ያዘ።

በሚያዝያ ፳፩ ቀን ፲፭፻ እ.ኤ.አ. ፔድሮ አልቫሬዝ ካብራል የተባለው የፖርቱጋል መኮንን በትልቅ መርከብ ሄዶ ይን ጊዜ ለቀረው ዓለም ያልታወቀውን የብራዚልን አገር አስገበረና በፖርቱጋል መንግሥት ስም ቅኝ አገር አደረገው። ከዚያም አገር በተገኘው ወርቅ መንግሥቱ ሀብታም ሆነ። እንደዚሁም የመጀመሪያ የንጉሥ እንደራሴ የተባለው ፍራንቼስኮ ዳልሜዳ ወደ ህንድ አገር ሄዶ አገሩን ያዘ። ከተማውንም በጎአ አድርጎ ህንድንም የፖርቱጋል የቄሣር ግዛት አደረገና አገር ገዥውም የንጉሥ እንደራሴ ይባል ጀመር። ከዚያም በትልቁ ውቅያኖስ ውስጥ የሚገኙትን ደሴቶች ኑቤል ጉኔንና ዛሬ ፊሊፒን የሚባለውን አገር በየጊዜው በጦር ኃይል አስገበራቸው። 

በዚሁ አኳኋን ወደ ኢትዮጵያም እነኮቪልሐኦ ቀደም ብለው በዓፄ እስክንድር ዘመን መጥተው እንደመረመሩትና የኢትዮጵያ መንግሥት በዚያ ጊዜ በነሱ አጠራር የቄሱ የዮሐንስ መንግሥት አለ ብለው አውርተው እንደነበረ ሌላ የፖርቱጋል የጦር መርከብ በአፍሪካ ድንበር በቀይ ባሕር ላይም እየተመላለሰ አስቀድሞ ከያዙት ከቱርኮችና ከግብጾች እየተዋጋ አንድ ጊዜም እየተሸነፈ አንድ ጊዜም እያሸነፈ ብዙ ጊዜ ተመላለሰ። በዚህ ሁሉ ምክንያት የፖርቱጋል መንግሥት ታላቅነት በሌላው ዓለም እንደ ታወቀ እንደዚሁም ፩ኛ ትልቅ መንግሥት መሆኑ ፪ኛ ክርስቲያን መሆኑ ኢትዮጵያ ባሉት የውጭ አገር ሰዎች አፍ እየተነገረ ዝናው በኢትዮጵያ ቤተ መንግሥት ዘንድ መሰማት ቻለ።




#Article 174: ግሪክ (አገር) (204 words)


ግሪክ ወደ ሜዴቴሪኒያን ባሕር የተዘረጋ አንድ ትንሽ አገር ነው። ከምሥራቅ ወደ ትንሽ እስያ፤ ከምዕራብ ወደ ኢጣሊያ አገር ከሁለቱም ወገን ርቀቱ ትክክል ነው። ግሪክ በሰሜን ወገን ከመቄዶንያ ይዋሰናል። ግሪክ ኣብዛኛው በባሕር የታጠረ ነው።

በደቡብና በምሥራቅ ወገን አያሌ ደሴቶች አሉ። ከእነርሱም በአያሌዎቹ መንደሮችና ከተሞች ተሠርተውባቸዋል። አንዱ አንቲፖሮስ ይባላል። በእዚህም ስፍራ ያለው ታላቅ ያጌጠ ዋሻ የታወቀ ስመ ጥሩ ነው።
እኩሌቶቹም የግሪክ ደሴቶች ከባሕር ወደ ውጪ እየተወረወሩ የወጡ ይመስላሉ። እኩሌቶቹም ከጥንት ጀምረው ይታዩ የነበሩት ያሉበት አይታወቅም ጠፍተዋል። ይህ እንግዳ ነገር እንዲህ እንዲሆን ያደረገው ከባሕር በታች የተነሳው እሳተ ገሞራ ነው።

በደቡብ ግሪክ ወገን ባሉት ደሴቶች አየሩ በአሜሪካ እንዳለው እንደ ቨርጂኒያ ግዛት አየር ቀላል ነው። በዚህ አገር ብዙ አይነት ፍሬ ሁሉ ሞልቶዋል። በሰሜን በኩል ደግሞ አየሩ ቅዝቃዜ ያለበት ነው።

በየጠረፉ የመርከብ መቋሚያዎች ወደቦች ይገኛሉ። ብዙዎቹ የአገሩ ሰዎችም መርከበኞች ናቸው። በደኑም ፓይን (ጥድ) የተባለው ጠንካራ ዛፍ ይገኛል። በላይኛው አውራጃ ኦክ የተባለው ዛፍ ይገኛል። ወደታች ባለው ክፍልም ቸስትነትና ዋልነት የሚባሉት ዕንጨቶች ይገኛሉ።

በዚህ ስፍራ የሚገኘው ዋናው ነገር ደረቅ ፍራፍሬ፣ ዘቢብ፣ ጥጥ፣ ሐር ጠጉር፣ ሩዝ፣ ትንባሆና በቆሎ ነው። የእጅ ሥራ ጥቂት ነው። በቤት የተለመደ ሥራ እንደ ጥጥ እንደ ጠጉር እንደ ሐር የመሰለ ነገር ነው። ቀለም ማግባት ወይም መቀባት በጣም የተለመደ ከሆነ ብዙ ጊዜው ሆነው።

ከዛፎች ፍሬ ዋነኛው ወይራ ሲሆን በብዛት ይተከላል። ወይን፣ በኽረ? ሎሚ፣ በለስ፣ አልሞንድ (ለውዝ)፣ ተምር፣ ሴትሮን፣ ፓሜግራኔት (ሮማን)፣ ኩሬንትም ይበቅላሉ።




#Article 175: ኅዳር ፲፱ (209 words)


ኅዳር ፲፱ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፸፱ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ  ፪፻፹፯ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፹፮  ቀናት ይቀራሉ።
  

፲፭፻፲፫ ዓ.ም. በፈርዲናንድ ማጄላን መሪነት የተቀናጁ ሦሥት የፖርቱጋል መርከቦች በደቡብ አሜሪካ ደቡባዊ ጫፍ የባሕር መስመር አልፈው ከአትላንቲክ ውቅያኖስ ወደ ሰላማዊ ውቅያኖስ በመሸጋገር የመጀመሪያዎቹ አውሮፓውያን ሆኑ።

፲፰፻፴፮ ዓ.ም. በሐዋይ ደሴቶች የነጻነት ዕለት ነው። የብሪታንያ እና የፈረንሳይ መንግሥታት የሐዋይን ደሴቶች ንጉዛት (ንጉሣዊ + ግዛት)ሉዐላዊነት አወቁ፣ አከበሩ። 

፲፱፻፭ ዓ.ም. አልባኒያ ከኦቶማን ግዛትነት ነጻነቷን አወጀች። 

፲፱፻፴፮ ዓ.ም. የአሜሪካው ፕሬዚደንት ፍራንክሊን ሩዝቬልት፣ የብሪታንያው ጠቅላይ ሚኒስቴር ዊንስተን ቸርቺል እና የሶቪዬት ሕብረት መሪ ጆሴፍ ስታሊን ኢራን ዋና ከተማ ቴህራን ላይ ተገናኝተው ከናዚ ጀርመን ጋር ለሚያካሂዱት ጦርነት የሕብረት ስልት አውጥተው፣ ተስማምተው ተለያዩ።  

፲፱፻፶፩ ዓ.ም.  ቅኝ ግዛቶች የነበሩት ቻድ፣ የኮንጎ ሪፑብሊክ እና ጋቦን በፈረንሳይ ቤተሰብ ስር እራሳቸውን ማስተዳደር ጀመሩ።

፲፱፻፶፫ ዓ.ም. ሞሪታንያ ከፈረንሳይ ቅኝ ግዛትነት ነጻነቷን ተቀዳጀች።

፲፱፻፷፰ ዓ.ም. የፖርቱጋል ቅኝ ግዛት የነበረችው ምሥራቅ ጢሞር፣ ገዥዋ ስትተዋት የራሷን ነጻነት አወጀች። ከዘጠኝ ቀናት በኋላ ግን በኢንዶኔዚያ ሠራዊቶች ተወራ የኢንዶኔዚያ ሃያ ሰባተኛ አውራጃ ሆነች።

፲፱፻፹፫ ዓ.ም. በብሪታንያ “ኮንሰርቫቲቭ” የቀኝ ፖለቲካዊ ቡድን መሪ የነበረችው ማርጋሬት ታቸር ከመሪነቷ ካስወገዷት በኋላ የጠቅላይ ሚኒስቴርነቱን ስልጣን ለአገሪቷ ንግሥት ዳግማዊት ኤልሳቤጥ አስረከበች።  ከአሥራ አምሥት ደቂቃ በኋላ ንግሥቲቱ አዲሱን የ”ኮንሰርቫቲቭ” ቡድን መሪ ጆን ሜጀርን አቅርባ፣ አዲስ አስተዳደር በጠቅላይ ሚኒስቴርነት እንዲመራ ሾመችው።




#Article 176: ፐርል በክ (228 words)


ፐርል በክ በስነ-ጽሁፍ የኖቤል ተሸላሚ (1938) ለመሆን የበቃች አሜሪካዊት ደራሲ ናት። በክ ጁን 26 ቀን 1982 ዓ.ም በምእራብ ቨርጂኒያ ሂልዝቦሮ በተባለ ቦታ ተወለደች። ወላጆቿ ፕሬስብቴርያዊ ሚሲዮኖች የነበሩ ሲሆን ብዙውን የሚሲዮን ስራቸውን በቻይና ነው ያሳለፉት። በዚሁ የተነሳ በክ ከልጅነቷ ጀምሮ እንግሊዝኛን ብቻ ሳይሆን ቻይንኛንም አቀላጥፋ ትናገር ነበር።

ትምህርቷን በ1914 እንዳጠናቀቀች ወደ ቻይና ነው ያቀናችው። በ1915 የወደፊት ባሏ ከሚሆነውን ከጆን ሎሲንግ በክ ጋር ተገናነች። በ1917 ጋብቻቸውን ከፈጸሙ በኋላ ኑሯቸውን ናንሹ በተባለችው የገጠራማዋ አንህዌ ግዛት አደረጉ። በዚሁ ቆይታዋ ነው ወደፊት የሥነ-ጽሁፍ ስራዋ ጉልላት ለመሆን የበቃውን ስሙር መሬት (The Good Earth) ለተባለው መጽሃፏ የሚሆናትን መረጃ የሰበሰበችው።

በክ ጽሁፎቿን ማሳተም የጀመረችው ከ1920ዎቹ ጀምራ ሲሆን አጫጭር ስራዎቿ The Nation፣ The Chinese Recorder፣ Asia እና The Atlantic Monthly በተሰኙ መጽሄቶች ታትመውላታል። የመጀመሪያው ወጥ ልብ-ወለድ ድርሰቷ (East Wind, West Wind) በ1930 በጆን ዴይ ኩባንያ ታትሟል። የጆን ዴይ ኩባንያ አሳታሚ የነበረው ሪቻርድ ዋልሽ ኋላ ላይ (1935) የፐርል በክ ሁለተኛ ባሏ ለመሆን በቅቷል።

በ1931 ጆን ዴይ ኩባንያ የፐርል በክን ሁለተኛ ወጥ ልብ-ወለድ ድርስት የሆነውን ስሙር መሬትን አሳተመ። ይኸው ሥራዋ በተከታታይ በ1931 እና በ1932 ዓ.ም በገበያ ላይ አንደኛ ተፈላጊ ሆኖ ለመዝለቅ የቻለ ሲሆን ለሷም በ1935 ዓ.ም የፑሊትዘር ሽልማት እና የሃዌልስ ሜዳልያ አስገኝቶላታል። ስሙር መሬት በ1937 ዓ.ም በኤም.ጂ.ኤም አማካይነት በፊልም መልክ ተቀናብሮ ለተመልካች ቀርቧል። ከዛ በተከታታይ ሌሎች ድርሰቶችን ለአንባቢ አቅርባለች። በክ በ1938 ዓ.ም በስነ-ጽሁፍ የኖቤል ሽልማትን በመቀበል የመጀመሪያዋ (ሴት) አሜሪካዊት ሆናለች። 

ፐርል በክ በ1973 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ስትለይ ከ70 በላይ ስራዎቿ ታትመውላታል። መቃብሯም ፔንሲልቬንያ ውስጥ በክስ በተባለው ቀበሌ ይገኛል።




#Article 177: ማርክ ትዌይን (204 words)


ሳሙኤል ላንግሆርን ክሌመንስ (እንግሊዘኛ: Samuel Langhorne Clemens) ወይም በብእር ስሙ ማርክ ትዌይን አሜሪካ ካፈራቻቸው ድንቅ ጸሃፍት መካካል የሚመደብ ደራሲ ነው። ትዌይን በኖቬምበር 1835 ዓ.ም. ሚዙሪ በተባለችው የአሜሪካ ግዛት ተወለደ። 18 ዓመት እስኪሞላው ድረስ ከቤተሰቦቹ ጋር የኖረው ሃኒባል በተባለች እና ሚሲሲፒ ላይ በተቆረቆረች ትንሽ ከተማ-አከል ቦታ ነው። አባቱ በ1847 ሲሞት ትዌይን ትምህርቱን በማቋረጥ በማተሚያ ቤት ውስጥ በሰልጣኝነት ተቀጠረ። ይህን ስራውን በ1857 በመተው የእንፋሎት ጀልባ ነጂ በመሆን መስራት ጀመረ። በዚሁ ስራ በቆየባቸው አመታት ነው ኋላ ላይ አድናቆትን ላተረፉለት የስነ-ጽሁፍ ስራዎቹ የሚሆኑትን እውቀቶች ለማሰባሰብ የበቃው። እሱ ራሱም እንዳለው በዚሁ ስራ ላይ ነው ማንኛውንም በልብ-ወለድ፣ በግለ-ታሪክም ሆነ በታሪክ ላይ ሊገኙ የሚችሉ የሰው ባህርያትን ሊያጠና የበቃው። 

በ1861 እ.ኤ.አ. የአሜሪካ የእርስ-በርስ ጦርነት በመቀስቀሱ ምክንያት ማንኛውም አይነት የመርከብ ላይ ጉዞ ሲስተጓጎል ትዌይንም ስራውን ለመልቀቅ ተገዷል። ከዚህ በኋላም በውትድርና ወዶ-ገብነት፣ በወርቅ ማእድን ፈላጊነት፣ በጋዜጠኝነት ወዘተ ስረቷል። 

በ1869 ዓ.ም የመጀመሪያ ዋነኛ ስራው የሆነውን The Innocents Abroad ለማሳተም በቃ። ይኽ ድርሰት ክሌመንስ ራሱ በአውሮፓ እና በእየሩሳሌም ባካሄዳቸው ጉብኝቶች ላይ የተመሰረተ ነው። በ1870 ዓ.ም ኦሊቭያ ላንግዶንን በማግባት ኑሮውን ኮኔቲከት በተባለችው ግዛት አድርጓ በዛው ለ17 ዓመታት ኖሯል። በነዚህ 17 ዓመታት ነው አድናቆት ያተረፉለት ስራዎቹን ማለትም Roughing It፣ The Adventures of Tom Sawyer፣ Life on the Mississippi፣ እና ከሁኡ የላቀ የተባለለት ድርሰቱን The Adventures of Huckleberry Finnን ያሳተመው።

ትዌይን በ1910 ዓ.ም አርፎ ሬዲንግ፣ ኮኔቲከት ውስጥ በድኑ አርፏል።




#Article 178: ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር (314 words)


ስብሐት (ስብሐት ለአብ) ገብረ እግዚአብሔር (ሚያዝያ 27 [1928]ዓ.ም. - ሰኞ፣ ቀን
 [ትግራይ] ጠቅላይ ግዛት፣ አድዋ አውራጃ፣ እርባ ገረድ በተባለች መንደር ከአባቱ ከቄስ ገብረ እግዚአብሔር ዮሐንስ እና ከወይዘሮ መአዛ ወልደ መድኅን  ተወለደ። ትምህርቱን በስዊድን ሚሲዮን፣ እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተከታትሎ በትምህርት አስተዳደር የመጀመሪያ ዲግሪውን ተቀብሏል። በአስፋ ወሰን ትምህርት ቤት በእንግሊዝኛ መምህርነት ለ2 ዓመት አገልግሏል። በመቀጠልም ከየተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፤ ሳየንስ እና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ባገኘው የትምህርት እድል አማካይነት ወደ ፈረንሳይ (ኤክስ አን ፕሮቫንስ) በመሄድ ከ1962-1964 ቆይቷል። የሄደበትን ትምህርት አጠናቆ ምስክር ወረቀት ባይቀበልም ቆይታው ከአውሮፓ ባህል እና ስነ-ጽሁፍ እንዲተዋወቅ በጣም እንደረዳው ይናገራል። ወደ ፈረንሳይኛ «Les Nuits d'Addis-Abeba» ተብሎ በፍራንሲስ ፋልሴቶ የተተረጎመውን የልብ-ወለድ ድርስቱን «ሌቱም አይነጋልኝ»ን ብዙውን ለመጻፍ የበቃው እዚያው በፈረንሳይ እንደሆነም ይናገራል። ይኸው ድርሰቱም ወደ ፈረንሳይኛ ቋንቋ የተተረጎመ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ልብ-ወለድ ነው።

ስብሐት ወደ አዲስ አበባ ከተመለሰ በኋላ በመነን መጽሄት የዝግጅት ክፍል ውስጥ ሰርቷል። በ1966 ዓ.ም. ወታደራዊው ደርግ ስልጣን ከያዘ በኋላ ኩራዝ አሳታሚ ድርጅት ሲቋቋም በአርታኢነት ተቀጥሮ ሰርቷል። በመንግሥት ትእዛዝም ከሌሎች ሰዎች ጋር በመሆን የካርል ማርክስ ሥራ የሆነውን ካፒታልን (Das Capital) ከእንግሊዝኛ ወደ አማርኛ በመመለስ ሥራ ላይ ተሳትፏል።

ብዙዎቹ የስብሐት ሥራዎች በተጻፉበት ጊዜ ለመታተም ባይታደሉም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የህትመትን ብርሃን ለማየት በቅተዋል። ጽሁፎቹ ረዘም ላለ ጊዜ ሳይታተሙ ለመቆየታቸው ዋነኛው ምክንያቱ ስብሐት በመጽሐፉ የሚጠቀማቸው ቃላት ብዙዎቹ በኢትዮጵያ ባህል ያደገ አንባቢን አይን የሚያስፈጥጡ፣ ጆሮ የሚያስይዙ በመሆናቸው ነው። በገበያ ላይ በቅርብ የወጡት ድርሰቶቹ ከመጀመሪያ ቅጂያቸው ብዙ ለውጥ እና የአርትኦት ሥራ የተደረገባቸው እንደሆኑ ይነገራል። ስለዚሁ ጉዳይ ለአዲስ ላይቭ በሰጠው ቃለመጠይቅ ላይ ሲናገር «በጨለማ ያልተደረገውን ነገር አንድም የጻፍኩት የለም... ያለውን እንዳለ ነው የምጽፈው» ብሏል። ይህንኑም ከኤሚል ዞላ የአጻጻፍ ዘይቤ የወሰደው እንደሆነ ይናገራል። 

ስብሐት ገብረእግዚአብሔር ደራሲ፣ አርታኢ፣ ጋዜጠኛ ብቻ አይደለም - የልብ-ወለድ ድርሰት ገጸባህርይም ነው። ደራሲው የተሰኘው የበአሉ ግርማ ልብ-ወለድ በስብሐት ህይወት ላይ ተመስርቶ የተጻፈ ነው። ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር የ2 ወንዶች እና የ3 ሴቶች አባት ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ነው።

አምስት ስድስት ሰባት እና ሌሎችም ታሪኰች
ትኩሳት

ሌቱም አይነጋልኝ
የፍቅር ሻማዎች
ስምንተኛው ጋጋታ
እነሆ ጀግና
ዛዙ(ትርጉም)
እግረ-መንገድ (1፣2)

አዲስ ዘመን
የኢትዮጵያ ሄራልድ
መነን መጽሔት
ቁም ነገር
ለዛ
ምእራፍ
እፎይታ
አዲስ አድማስ




#Article 179: አዲስ ዘመን (ጋዜጣ) (359 words)


አዲስ ዘመን ጋዜጣ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ሥር የምተዳደር ነዉ ፣ በየዕለቱ የሚታተም ብሔራዊ ጋዜጣ ነው። አዲስ ዘመን በአሁኑ ጊዜ ከ ፵ በላይ ጋዜጠኞች ያሉት ሲሆን የጋዜጣው  መጠን ‘መካከለኛ’ /በርሊነር/ (31.5 cm × 47 cm (12.4 in × 18.5 in) ) ሆኖ የፊትና ጀርባ ገፆችን በሙሉ  ቀለም  ያቀርባል። ይህ ጋዜጣ የአገሪቱ ብቸኛው ዕለታዊ ጋዜጣ ሲሆን የመንግሥትን አቋም የሚያንፀባርቅ እና በየዕለቱ የተለያዩ ልማታዊ ዜናዎችን ይዞ ይወጣል።

ከአምሥት ዓመት የኢጣልያ ወረራ በኋላ የኢትዮጵያ ነፃነት መመለሱን ተከትሎ ንጉሠ ነገሥቱ ዙፋናቸው እንደ ተረከቡ ካከናወኗቸው ፖለቲካዊና አስተዳደራዊ ተግባራት አንዱ የመገናኛ ብዙኀን በማደራጀትና በማቋቋም ላይ ያተኮረ ነበር። በዚህም መሠረት አዲስ ዘመን ጋዜጣ ቅዳሜ፣ ግንቦት ፴ ቀን ፲፱፻፴፫ ዓ/ም በይፋ ሥራ ጀመረ። 

ንጉሠ ነገሥቱ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ከጠላት ወረራ በኋላ ሚያዝያ ፳፯ ቀን ፲፱፻፴፫ ዓ/ም በድል አድራጊነት አዲስ አበባ ሲገቡ ባደረጉት ንግግር የመግቢያው አንቀጽ፦

የጋዜጣውም ሥያሜ  «ይህ ቀን ለአዲሲቱ ኢትዮጵያ የአዲስ ታሪክ ዘመን መክፈቻ ነው» ማለታቸውን መሠረት ያደርጋል።

የጋዜጣው ድረ-ገጽ ስለጋዜጣው ታሪክ ሲዘግብ፤«የመጀመሪያ ዕትም ባለሁለት ገፅ፣  አርበ ጠባብ /ታብሎይድ/» (43.2 cm X 27.9 cm (17 in X 11 in)) እንደነበረና ስርጭቱም ፲ሺ ቅጂ እንደነበር ይገልጽና፤በዚሁ የመጀመሪያ ዕትም ርዕሰ አንቀጽ «የአዲስ ዘመን ጋዜጣ መጀመር በሚል ርዕስ ባስነበበው ጽሑፍ ‹ይህ አዲስ ዘመን ተብሎ የተሰየመው ጋዜጣ ከዛሬ ጀምሮ ወደፊት ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የነፃነቱን ሥራ ይሠራ ዘንድ ተመሠረተ› በማለት የተቋቋመበትን ዓላማ ያስረዳል» ይለናል።  ቀጥሎም ያንኑ የመጀመሪያውን ርዕሰ አንቀጽ በመጥቀስ፤ «‹ይህ ጋዜጣ የፕሮፖጋንዳ ጋዜጣ ሳይሆን እውነትን፣ አገልግሎትን፣ ረዳትነትን መሰረት አድርጐ ለአዲሲቱ ኢትዮጵያ በአዲስ ሥራ ተመርቶ እንዲረዳ የቆመ ነው› ቢልም ‹አገልግሎት ስንል የኢትዮጵያን ነፃነት ሲመሰስ ራሳቸውን መስዋዕት አድርገው፤ የነበራቸውን ጥቅም ሁሉ አስወግደው፤ ለሕዝባቸውና ለአገራቸው ሲሉ የሰው አቅም ሊሸከመው የማይችለውን ድካም ተቀብለው፤ ማናቸውም ሰው ሊያደርገው ያልቻለውን በኢትዮጵያ ሕይወት ውስጥ እስከ ዛሬ ያልታየውን ሥራ ከፍፃሜ ላደረሱ ለንጉሠ ነገሥታችንና ላቆሙት መንግሥት የሚያገለግል እንዲሆነ ነው።› በማለትም በዋነኝነት የተቋቋመበትን ዓላማ በግልፅ ይተነትናል።» የሚል ዘገባ እንደነበር የጋዜጣው ድረ-ገጽ አስቀምጦታል። 

አዲስ ዘመን ከተጀመረበት ጊዜ እስከ ታኅሣሥ ወር ፲፱፻፶፩ ዓ/ም ድረስ በየሳምንቱ፤በአርበ-ጠባብ፣ በመካከለኛና በአርበ-ሰፊ /ብሮድሺት/ (74.9cm X 59.7cm (291⁄2 in X 231⁄2  in)) መጠን ሲታተም ከቆየ በኋላ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በ፲፱፻፶ ዓ/ም ያቋቋመው የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን፣ ጽሕፈት ቤቱን አዲስ አበባ ላይ ማድረጉን ምክንያት በማድረግ  የጋዜጣው ዕትመት በሳምንት ወደ ስድስት ቀን ተሸጋግሯል።

ከመስከረም ፩ ቀን ፲፱፻፺፫ ዓ/ም ጀምሮ ደግሞ ጋዜጣው ከሰኞ እስከ እሑድ በሳምንት ሰባት ቀናት ወደመታተምከተሸጋገር በኋላ የጋዜጣው መጠን ከታኅሣሥ ፫ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ጀምሮ ወደ መካከለኛ ጋዜጣነት /በርሊነር/ ዝቅ ብሏል።




#Article 180: አባሲዶች (133 words)


አባሲዶች የሚባሉት የአረቡን ክፍለ ዓለም ከ742-1250 ዓ.ም. የገዙት የነገሥታት ቤተሰቦች ናቸው። እነዚሁም ባግዳድ (የአሁኗ ኢራቅ ዋና ከተማ) ላይ ተቀምጠው ይገዙ የነበሩት የሱኒ እምነት ክፍል አራማጆች ሲሆኑ ኡማያዶችን ከስልጣን ያስወገዱት ናቸው። ዘራቸው (እንዲሁም መጠሪያቸው) የነብዩ መሃመድ አጎት ከነበረው ከአባስ ኢብን አብደል ሙጣሊብ እንደወረደ ይተረካል። 

በ742 ካሊፍነቱን ከተቆናጠጡ በኋላ የመንግስታቸውን መቀመጫ ከደማስቆ (የአሁኗ ሶርያ ዋና ከተማ) ወደ ባግዳድ አዙረው ለ2 መቶ አመታት ያህል የአረቡን ክፍለ አለም ለመግዛት በቅተዋል። ይሁንና ኋላ ላይ የኦቶማን ቱርኮች መንግሥት እየጠነከረ በመምጣቱ ግዛቶቻቸውን ሁሉ እያጡ ሄደዋል። በመጨረሻም በ1250 ሁላጉ ካሃን የተባለው የሞንጎሎች መሪ ባግዳድን ሲበዘብዝ የመንግስታቸው ፍጻሜ ለመሆን በቅቷል። የነዚሁ የአባሲዶች ዘር የሆኑ አል አባሲ የሚሰኙ ጎሳዎች በኢራቅ ውስጥ ከቲክሪት ከተማ ወደ ሰሜን ምስራቅ ሲል በሚገኙ አካባቢዎች አሁንም ሰፍረው ይገኛሉ።

አንድ ሺ ከአንድ ሌሊቶች በተሰኘው የተረቶች መድብል ውስጥ ታሪኩ የሚነገርለት ሃሩን አል ረሺድ (በ757 ተወልዶ ከ778-800 ነግሷል) ዘሩ ከአባሲዶች የሚደመር ነው።




#Article 181: ዓረብኛ (162 words)


ዓረብኛ (العربية) ፡ የሴማዊ ፡ ቋንቋዎች ፡ ቤተሠብ ፡ አባል ፡ ሆኖ ፡ የዕብራይስጥ ፡ የአረማያ ፡ እንዲሁም ፡ የአማርኛ ፡ ቅርብ ፡ ዘመድ ፡ ነው። ፪ ፻ ፶ (250) ፡ ሚሊዮን ፡ የሚያሕሉ ፡ ሰዎች ፡ እንደ ፡ እናት ፡ ቋንቋ ፡ ይናገሩታል። ከዚህም ፡ በላይ ፡ በጣም ፡ ብዙ ፡ ሰዎች ፡ እንደ ፡ ፪ኛ ፡ ቋንቋ ፡ ተምረውታል። የሚጻፈው ፡ በዓረብኛ ፡ ፊደል ፡ ነው። በዓረብ ፡ አለም ፡ ውስጥ ፡ አያሌ ፡ ቀበሌኞች ፡ ይገኛሉ። 

ቋንቋው ፡ በእስልምና ፡ ታላቅ ፡ ሚና ፡ አጫውቷል። እስላሞች ፡ አላህ ፡ ለሙሐማድ ፡ ቁርዓንን ፡ ሲገልጽ ፡ በዓረብኛ ፡ እንደ ፡ ሆነ ፡ ስለሚያምኑ ፡ እንደ ፡ ቅዱስ ፡ ቋንቋ ፡ ይቆጥሩታል። አብዛኛው ፡ ዓረብኛ ፡ ተናጋሪዎች ፡ ሙስሊሞች ፡ ናቸው። 

ዛሬ ፡ በምዕራብ ፡ ዓለም ፡ ደግሞ ፡ ብዙ ፡ ሰዎች ፡ አረብኛ ፡ እያጠኑ ፡ ነው። በታሪክ ፡ ከፍተኛ ፡ ሚና ፡ በማጫወቱ ፡ መጠን ፤ ብዙ ፡ የዓረብኛ ፡ ቃላት ፡ ወደ ፡ ሌሎች ፡ ቋንቋዎች ፡ ገብተዋል።




#Article 182: ፍዮዶር ዶስቶየቭስኪ (354 words)


ፍዮዶር ሚኸየሎቪች ዶስቶየቭስኪ ከሩስያ ምርጥ ደራስያን መካከል የሚቆጠር እና በአለም የሥነ-ጽሁፍ መድረክ አሻራውን ትቶ ለማለፍ የቻለ ሰው ነው። ከሱ በኋላ የተነሰ የአውሮጳ ጸሃፍያን፣ ፈላስፋወችና ስነ ልቡና ተመራማሪወች፣ ከፍሬድሪች ኒሺ እስከ ሲግመን ፍሮይድ፣ ከፍራንዝ ካፍካ እስከ ዣን ፖል ሳርት ድረስ ጉልህ የስነ-ሰብእ እና የስነ-ልቦና መርማሪነቱን መስክረውለታል።

ዶስቶየቭስኪ በሩስያ ዋና ከተማ ሞስኮ (መስኮብ) ውስጥ እ.ኤ.አ በኦክቶበር 30፣ 1821 ተወለደ። አባቱ ቀድሞ የጦር ሰራዊቱ ሃኪም የነበረ ሲሆን በጣም ጠጪ እና ጢሰኞቹም ላይ ግፍን ያበዛ እንደነበር ይወሳል። ይህም በመሆኑ ይመስላል በገዛ ጭሰኞቹ እጅ ህይወቱ ሊያልፍ የበቃው። 

ዶስቶየቭስኪ በ1837 ዓ.ም በቅዱስ ፒተርስበርግ የጦር ምህንድስና አካዳሚ ተመዝግቦ ትምህርቱን በመከታተል በመኮንንነት ተመርቋል። አንድ አመት ያህል በመንግሥት ሥራ ላይ ከቆየ በኋላ ሙሉ ግዜውን በስነ-ጽሁፍ ላይ ለማዋል ሲል ከሥራው ተሰናብቷል።

የበኩር ድርሰቱ የሆነው Poor Folk በ1846 ሲታተም ወዲያው አድናቆትን ቢያስገኝለትም ብዙም ሳይቆይ በ1849 ዓ.ም የሩስያውን ንጉሥ ዛር ኒኮላስ ቀዳማዊን በመቃወም ወንጀል ተከሶ ወደ ዘብጥያ በመውረዱ የሥነ-ጽሁፍ ሥራው ሊቋረጥ በቅቷል። በተከሰሰበትም ወንጀል የሞት ፍርድ ተፈርዶበት በጥይት ተደብድቦ ሊገደል ወደ መግደያው ከተወሰደ በኋላ ፍርዱ ተለውጦለት ወደ ሳይቤርያ በግዞት እንዲሄድ ተደርጓል። ኦምስክ በተባለች የሳይቤርያ ከተማ ከከባድ የጉልበት ሥራ ጋር ለ4 ዓመታት ያህል ታስሮ በሌላ የሳይቤርያ ግዛት እንዲሁ ለተጨማሪ 6 ዓመታት በውትድርና እንዲያገለግል ከተደረገ በኋላ ተለቆ ወደ ቅዱስ ፒተርስበርግ ለመመለስ በቅቷል። ከሞት አፋፍ ያመለጠበት ሁኔታ በስነ-ልቦናው ላይ ያሳደረው ተጽእኖ በስነ-ጽሁፉም ላይ የተንጸባረቀ ሲሆን The Idiot የተሰኘው ድርሰቱ በዚሁ ላይ የተመሰረተ ነበር።

ወደ ቅዱስ ፒተርስበርግ ከተመለሰ በኋላ የበፊት ተወዳጅነቱን ለማስመለስ አፍታም አልወሰደበት። በ1862 ያሳተመው Notes from the Dead House፣ እንዲሁም ከሁለት አመት በኋላ ያሳተመው Notes from the Underground በጣም አድናቆትን ያተረፉ የሥነ-ጽሁፍ ትርፋቶቹ ሲሆኑ በመቀጠልም Crime and Punishment የተሰኘውን ልብ-ወለድ ድርሰቱን በ1866፣ The Gamblerን በ1867፣ The Idiotን በ1869፣ እንዲሁም Demonsን በ1872 አሳትሟል። የስራዎቹ ሁሉ ቁንጮ የሆነው The Brothers Karamazov በ1880 ታትሟል። በተለይ The Gambler የተሰኘውን ድርሰቱን በ26 ቀናት ውስጥ ጽፎ እንዳጠናቀቀ ይነገራል።

በስነ-ጽሁፉ ስኬትን በስኬት ላይ የደረበው ዶስቶየቭስኪ በግል ህይወቱ ግን ደስታን ለማጣጣም አልታደለም። ከልጅነቱ ጀምሮ የተጠናወተው የሚጥል በሽታ፣ በትዳሩ ደስታን ማጣት፣ እንዲሁም የገንዘብ እጦት (ቁማርተኛ ከመሆኑ ጋር ተዳብሎ) ህይወቱን ስቆቃ የተመላው አድርጎበታል።

በህይወቱ የመጨረሻ ዘመናት ወደ ወግ አጥባቂነት እና ሃይማኖተኛነት እያዘነበለ ይሄደው ዶስቶየቭስኪ የኑባሬ ፍልስፍና (Existentialism) ቀደምት ከሆኑት ውስጥ እንደነበር ብዙዎች ይስማማሉ። ዶስቶየቭስኪ ህይወቱ በ1882 ስታልፍ ከ52000 በላይ ሰዎች በቀብሩ ስነ-ስርዓት ላይ ተገኝተው የመጨረሻውን ስንብት አድርገውለታል። አጽሙም በቅዱስ ፒተርስበርግ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የአሌክሳንደር ኔቭስኪ ገዳም ውስጥ አርፏል።




#Article 183: ደበበ እሸቱ (200 words)


ደበበ እሸቱ (1936 ዓ.ም. ተወልደው) ስመ ጥሩ ተዋናይ ሲሆኑ በእሁኑ ጊዜ የቅንጅት ቃል አቀባይ ሆነዋል። ከፊልሞቻቸው ሚናዎች መሃል በዓለም ከሁሉ የታወቀው በShaft in Africa (1973 እ.ኤ.አ.) እንደ 'ዋሳ' ነበረ። ዘሰይለር ፍሮም ጂብራልታር፤ ዘግሬቭ ዲገር፤ እና ሌሎችም

ትምህርታቸውን በተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ጨርሰው ወደ ደብረ ብርሃን መምህራን ማሰልጠኛ ት/ቤት ገቡ። ነገር ግን በ1953 ዓ.ም. በመንግሥቱ ነዋይ እና በገርማሜ ነዋይ መሪነት በተካሄደው የመንግሥት ግልበጣ ሽብር ወቅት ትምህርታቸውን አቋርጠው ወደ ኢሉባቦር ታስረው ከ1 አመት በላይ እዚያ ቆዩ። 

መጀመሪያ በቴያትር የታዩት በመንግስቱ ለማ በተጻፈው ያላቻ ጋብቻ ሲሆን ከዚያ በአንዳንድ እንግሊዝኛ ትርኢት (The game of chesse, 'Waiting for Godot') እንዲሁም በራዲዮም ሆነ በቴሌቪዥን ተጫወቱ። 

ከዚያ በኋላ በሀንጋሪ አገር ከወጋየሁ ነጋቱ ጋራ ቴያትር አጠኑና ወደ አገራቸው ተመልሰው ደበበ 'ንጉሥ ሄሮድያስ' በተባለ ድራማ የአርእስቱ ሚና ተጫወቱ።

ከዚህ በላይ በሀገር ፍቅር ቴያትር እንደ ዋነኛ ዳይረክተር፣ በመረጃ ሚኒስቴር እንደ ጋዜጠኛ፣ እና ከስብሃት ገብረ እግዚአብሄር ጋር በቁም ነገር መጽሔትበባለቤትነትና  አዘጋጂነት  አገልግለዋል።

ለአፍሪካዊ ቴያትር ስላደረጉት አስተዋጽኦአቸው ሽልማት በ1991 ዓ.ም. ከቦስቶን ከተማ እና በ1994 ከአትላንታ ከተማ በአሜሪካ ተቀበሉ። ከዚህ በላይ በ1994 ዓ.ም. የጣይቱ ሽልማት ተቀባይ ነበሩ።

የ30 አመት ሚስታቸው ው/ሮ አልማዝ እና እሳቸው 4 ልጆች አሏቸ ከሴት ልጆቹም 2ቱ በ1 ቀን ውስጥ በ1995 ዓ.ም. ለባሎቻቸው ተዳሩ። 

በቅርብ ጊዜ ከፖለቲካ ነክ ሚናቸው የተነሣ እቶ ደበበ ከ1998 እስከ 1999 ዓ.ም. ድረስ የቃላቲ እስረኛ ነበሩ።




#Article 184: ተስፋዬ ሳህሉ (364 words)


ተስፋዬ ሳህሉ (1924 እ.ኤ.አ. ተወልደው) በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ላይ ስመጥርና የተወደዱ ተዋናይና በተለይም የሕፃናትና የልጆች ተረተኛ ናቸው።  ፕሮግራማቸው የልጆች ጊዜ ከ1965 እ.ኤ.አ. ጀመሮ ታይቷል። ከዚያ ጀምሮ አባባ ተስፋዬ ተብለው አዲስ ስማቸውን ተቀበሉ። በ1998 ዓ.ም. ከ42 አመታት አገልግሎት በኋላ ከሥራቸው ተለቀቁ።
በተወለዱ በ፱፬ አመታቸው ሃምሌ ፪፬ ፪፻፱ ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል። በትዳር ሕይወታቸውም ከባለቤታቸው ደብሪቱ አይታገድ ጋር አንድ ልጅ ያፈሩ ሲሆን አምስት የልጅ ልጆችንም አይተዋል።

አቶ ተስፋዬ ከአባታቸው ኤጀርሳ በዳኔ እና ከእናታቸው ዮንዢ ወርቅ በለጤ ሰኔ ፳፣ ፲፱፻፲፮ ዓ.ም በቀድሞ ባሌ ክፍለ ሃገር ከዶ የተሰኘ አካባቢ ተወለዱ። አምስት ዓመት ሲሞላቸው አባታቸው ወደ ጎባ የተጓዙ ሲሆን ጎባ ላይ ቄስ ትምህርት ቤት ገብተው የትምህርት ጅማሯቸው ተጠነሰሰ።  ወላጆቻቸው ለስራ የተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች በመዘዋወራቸው አባባ ተስፋዬ በጊኒር ከዛም በሐረርም የፈረንሳዮች ትምህርት ቤት ገብተው ትምህርታቸውን ተከታትለዋል።  በ፲፬ አመታቸው ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ትምህርታቸውን በኮከበ ፅባህ ትምህርት ቤት መከታተል ጀመሩ።

የአዲስ አበባ መስተዳደር ባህል እና ቲያትር አዳራሽ ማስታወቂያ ካወጣ በኋላ በተዋናይነት ማገልገል የጀመሩት አቶ ተስፋዬ በወቅቱ የሴት ተዋንያኖች ባለመኖራቸው የሴቶችንም ገጸባህሪ ወክለው ይጫወቱ ነበር። ‘ሀ ሁ በስድስት ወር’ ፣ ‘ኤዲፐስ ንጉስ’፣ ‘አሉላ አባነጋ’፣ ‘ዳዊትና ኦርዮን’፣ ‘ኦቴሎ’፣ ‘አስቀያሚዋ ልጃገረድ’ና ‘ስነ ስቅለት’ ተስፋዬ ሳህሉ ከተጫወቷቸው ተውኔቶች ዉስጥ የሚጠቀሱ ሲሆን ‘ብጥልህሳ’፣’ ነው ለካ’ ፣ ‘ጠላ ሻጯ’ በድርሰት ያበረከቷቸው ተውኔቶች ሲሆኑ አራት የተረት መጻሕፍት ለልጆች አድርሰዋል።

በ፲፱፻፶፯ ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሲቋቋም የልጆች ጊዜ የተሰኝ ፕሮግራም እንዲኖር ሃሳቡን አቅርቦ በማፀደቅ የራሳቸውን የአቀራረብ መንገድና የፈጠራ ችሎታ በመጠቀም ለመላው የኢትዮጲያ ህዝብ ያስተዋወቃቸውን ዝግጅታቸውን ለ፵፪ ዓመታት በአባትነት ስሜት አቅርበዋል። ለልጆች የሚሆኑ የተዋዙ ተረቶችን፣ ጨዋታዎችን እና አስተማሪ ዝግጅቶችን የሚያቀርቡት አባባ ተስፋዬ ያበረከቱት መተኪያ የሌለው አስተዋጾ ብዙዎች ያነሱታል። 

አባባ ተስፋዬ ከ፲ በላይ የሆኑ ሙያዎች ባለቤት የነበሩ ሲሆን ከነዚህም መካከል ተዋናይ፣ ድምጻዊ፣ የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋች፣ የውዝዋዜ አሰልጣኝ፣ የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ፣ ደራሲ (የልጆች ተረት)፣ ተረት ተናጋሪ፣ የዜማና ግጥም ደራሲ፣ የምትሃት ባለሙያ ይጠቀሳሉ። በገና፣ መሰንቆ፣ ክራር፣ አኮርዲዮን፣ ትራምፔት፣ ትርምቦን እና ጃስ የሙዚቃ መሳሪያዎችን የሚጫወቱ ሲሆን ከዛም በተጨማሪ አማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ እንግሊዝኛ፣ ጣልያንኛና ፈረንሳይኛ ቋንቋን ተናጋሪ መሆናቸውም ተነግሯል።

አባባ ተስፋዬ በኢትዮጲያ ቴሌቪዢን የልጆች ጊዜ ፕሮግራም ላይ የሚያቀርቡትን ተረት ሲጀምሩ የሚናገሩአት ታዋቂ ንግግር ደህና ናችሁ ልጆች የዛሬ አበባዎች የነገ ፍሬዎች እንደምን አላችሁ ልጆች። አያችሁ ልጆች የኢትዮጲያ ቴሌቭዥን የልጆች ጊዜ ዝግጅት ክፍል እናንተን ለማስደሰት ልክ በሰአቱ ይገኛል። እናንተስ ዝግጁ ናችሁ? አዎዎ አባባ ተስፋዬ ሸንተረሩን አቋርጠው ዳገቱን ወጥተው ቁልቁለቱን ወርደው በጓሮ በኩል ከተፍ ሲሉ እናንተ ደሞ ቆማችኋል አይደል? አዎዎ በቃ አሁን ተቀመጡ እንዳትጋፉ ታዲያ ትንንሾች ወደፊት ትልልቆች ወደኋላ አዎዎ።




#Article 185: ዮፍታሄ ንጉሤ (124 words)


ግራ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሤ (፲፰፻፺፯ ዓ.ም. በደብረ ኤልያስ ቀበሌ፣ ጎጃም ተወልደው ሰኔ ፴ ቀን በ፲፱፻፴፯ ዓ.ም. አረፉ) ስመ ጥር ኢትዮጵያዊ ደራሲ ነበሩ። እኚህ ታላቅ ደራሲ በርካታ ድርሰቶችን የጻፉ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች አብዛኛዎቹ ለሕትመት አልበቁም።

የመጀመርያውን የኢትዮጵያ ሕዝብ መዝሙር “ኢትዮጵያ ሆይ ደስ ይበልሽ በአምላክሽ ኃይል በንጉሥሽ” የሚለውን የደረሱት ቀኝጌታ ዮፍታሔ ንጉሤ፤ ስለአገር ፍቅርና ጀግንነት የሚያወሱ በርካታ ድራማዎችና መዝሙሮችን የደረሱ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል “አፋጀሽኝ”፣ “እለቄጥሩ” ወይም “ጎበዝ አየን” ይገኙበታል። ከድል በኋላ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ከ፲፱፻፴፭ ዓ/ም እስከ ሕልፈታቸው ድረስ አገልግለዋል። የኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር እና የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት በመታባበር ጳጉሜ ፪ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም በአዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አዳራሽ የተመረቁትን እና የቀኝ-ጌታ ዮፍታሄ ንጉሤን እንዲሁም የደራስያን፤- ነጋድራስአፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ፣ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ እና አቶ ፲፱፻፳፫ ዓ/ም)




#Article 186: ስንዱ ገብሩ (839 words)


ወይዘሮ ስንዱ ገብሩየመጀመሪያዋ ሴት የፓርላማ ተመራጭ፣ የጦር አርበኛ፣ ፀሐፊ- ተውኔት፣ ደራሲ፣ የመጀመሪያዋ ሴት ዲፕሎማት የነበሩት እና ሚያዝያ ፲፪ ቀን ፳፻፩ ዓ/ም በ፺፫ ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩን የክብርት ዶክቶር፣ ወይዘሮ ስንዱ ገብሩን ማንነት የሚዘክር “ዝክረ - ስንዱ ገበሬ”፣ በሚል ዝግጅት በእቴጌ መነን ትምህርት ቤት በኢትየጽያ የሴቶች ማኅበራት ቅንጅት (ኢሴማቅ)፣ ከኢትዮጵያ ሴት ደራሲያን ማኅበር፣ ከኢትዮጵያ ሴት መገናኛ ብዙኀን ማኅበር፣ ከኢትዮጵያ ሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበረና፣ ከጾታዊ ጥቃት መከላከያ ማኅበር ጋር በትብብር የተዘጋጀ ዝክር ተከናውኗል። 
 

ወይዘሮ ስንዱ ገብሩ በሸዋ ክፍለ ሀገር በመናገሻ አውራጃ በአዲስ ዓለም ከተማ ጥር ፮ ቀን ፲፱፻፰ ዓ/ም ተወለዱ። አባታቸው ታዋቂው ዲፕሎማት፣ የመጀመሪያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል ፕሬዘደንት፤ ጣሊያኖች ከኢትዮጵያ ከወጡ በኋላ ደግሞ የምክር ቤቱ ፕሬዘደንት የነበሩት በዳግማዊ ምኒልክ ሹመትም የመጀመሪያው የጎንደር ከተማ አስተዳዳሪ የነበሩት ከንቲባ ገብሩ ደስታ ሲሆኑ ታናሽ እህታቸው ደግሞ የውብዳር ገብሩ (አሁን ታዋቂዋ ሙዚቀኛ እማሆይ ጽጌ ማርያም) ናቸው። 

ዕድሜያቸው ለትምህርት በደረሰበት ወቅት እቤታቸው አስተማሪ ተቀጥሮላቸው የአማርኛን ትምህረት ከፊደል መቁጠር እስከ ዳዊት መድገም በቤታቸው ተማሩ። ከዚያም ወደ አዲስ አበባ ሄደው በስዊድን ሚሲዮን ትምህርት ቤት በመግባት እስከ ስምንተኛ ክፍል ተምረዋል። 

ከንቲባ ገብሩ ወጣቷን ስንዱ ገብሩን እያስከተሉ ወደ ቤተ መንግሥትም ሆነ ሌላ ሥፍራዎች ይወስዷቸው እንደነበረና ከጊዜው አልጋ ወራሽ ተፈሪ መኮንንም ጋር እንዳስተዋዋቋቸው ተዘግቧል። አልጋ ወራሹም የወጣቷን ብልህነትና ትጋት በማድነቅ ወደ ፈረንጅ አገር ተልከው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ባዘዙት መሠረት ወይዘሮ ስንዱ   በ፲፱፻፳፩ ዓ/ም (ፊታውራሪ አመዴ በ፲፱፻፲፱ ዓ/ም ይላሉ) ወደ ስዊስ ለትምህርት ቢሄዱም ኑሮው ስላልተመቻቸውና ትምህርት ይሰጥበት የነበረውን የጀርመንኛ ቋንቋ ስላልወደዱት ወደ ፈረንሳይ አቅንተው ትምህርታቸውን ቀጠሉ። በመጨረሻም በስዊስ እና በፈረንሳይ ሁለት ትምህርት ቤቶች በመዘዋወር በዲፕሎማ ተመረቁ። እዛው የሕግ ትምህርት ለመቀጠል ጀምረው የነበረ ቢሆንም፤ ፍላጎታቸው ወደ ሥነ-ጽሑፍ በማዘንበሉ በአጠቃላይ ለአምስት ዓመታት እዛው ተምረው ወደ ሀገራቸው ተመለሱ። 

ወደ ሀገራቸው እንደተመለሱም በአዲስ አበባ በቅዱስ ጊዮርጊስ ትምህርት ቤት ውስጥ የፈረንሳይኛ ቋንቋን፣ ሀይጅን፣ ቁጥርንና የአማርኛ ድርሰት አጻጻፍን ማስተማር ጀመሩ። በዚህ ሁኔታ አንድ ዓመት እንደቆዩ ለብላታ ሎሬንሶ ታዕዛዝ ተዳሩና ባለቤታቸው የሐረርጌ ክፍለሀገር አስተዳዳሪ ሆነው በመሾማቸው ወደዚያው ከባለቤታቸው ጋር አቀኑ። ከአንድ ዓመት ተኩል በኋላም ብላታ ሎሬንሶ የፍርድ ቤት ሹምና የዜና ስርጭት ኃላፊ ሆነው በመሾማቸው ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ አብረዋቸው ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ።

ፋሺስቶች ኢትዮጵያን በወረሩ ጊዜ ንጉሠ ነገሥቱ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ወደ እንግሊዝ ሀገር ሲሰደዱ ብላታ ሎሬንሶ ታዕዛዝም  አብረው ከጃንሆይ ጋር ሄዱ። ወይዘሮ ስንዱ ግን ከቤተሰቦቻቸው ጋር እና ሆለታ ውስጥ ከሚገኙ ወደ መቶ የሚጠጉ የጦር መኮንኖች ጋር ተቀላቅለው ፋሺስቶችን ለመፋለም ወደ ቦሬ ሄዱ። እዚያም የመትረየስ አተኳኮስ ትምህርት ተማሩ።  ወደ ነቀምት በመሄድም ሕዝብን እየሰበሰቡ ስለ ነፃነት ማስተማሩን ተያያዙት። በዚህ ወቅት በባንዳዎች ጠቋሚነት በፋሽስት እጅ ከመውደቅ ለጥቂት አምልጠው ጎሬ ላይ ከልዑል ራስ እምሩ ጦር ጋር ተቀላቀሉ። ከዚያም በጦርነቱ የሚጎዱ አርበኞችን ለማከም የሚሆን ቀይ መስቀል ለማቋቋም መፈለጋቸውን ለራስ እምሩ አማክረው በተሰጣቸው ፭ መቶ ብር አቋቁመው አርበኞችን መርዳት ጀመሩ። ወዲያው ግን እርሳቸው ተቀላቅለውት የነበረው የጥቁር አንበሳ ጦር ሲመታ በጣልያን ሠራዊት እጅ ተማርከው በእስር ወደ አዲስ አበባ አመጧቸውና የቁም እስረኛ ሆኑ።
 
የካቲት ፲፪ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓ/ም ግራዚያኒን ለመግደል በተደረገው ሙከራ ወንድማቸው መሸሻ ገብሩ አሉበት በመባል ይታሰሱ ስለነበር ወንድማቸውን ከአደጋ ለማዳን ሲሞክሩ በድጋሚ በፋሺስቶች እጅ ወደቁ። በወቅቱ ግራዚያኒ ይኖርበት የነበረው የገነተ ልዑል ቤተ መንግሥት ውስጥ ታሰሩ። ቀጥሎም ወደ አስመራ፣ ከዚያ ወደ ምጽዋ ተወሰዱ። ከምጽዋ ወደብ ሦስት መቶ ወንዶችና ስምንት ሴቶች (እማሆይ ጽጌ ማርያምን ጭምር) ሆነው በመርከብ “አዚናራ” ወደተባለች የኢጣሊያኖች እስር ቤት ተወስደው ዘጠኝ ወራት ታሰሩ። 
 
ከእስር በኋላም ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ በእንደዚህ ያለ ተግባር ላይ እንዳይሰማሩ ከፍተኛ ማስጠንቀቂያ ቢሰጣቸውም፤ ማስፈራሪያው ሳይበግራቸው አርበኞችን በግጥም፣ በወኔ ቀስቃሽ ጽሑፎች በማበረታታት፣ መረጃ በማቀበል፣ መሣሪያ በማዳረስ የጀግንነት ተግባር ፈጽመዋል። 

ከድል በኋላ ወይዘሮ ስንዱ ለሁለት ዓመታት ደሴ ከተማ የሚገኘው የወይዘሮ ስኂን ትምህርት ቤት አስተዳዳሪ በመሆን፣ በኋላም ወደ አዲስ አበባ ተመልሰውም የእቴጌ መነን ትምህርት ቤት ምክትል ርዕሰ መምህርነት፣ ከዚያም የመጀመሪያዋ ሴት ርዕሰ መምህር ሆነው አገልግለዋል። በእቴጌ መነን ትምህርት ቤት በነበሩበት ወቅት፤ “ኮከብ ያለው ያበራል ገና”፣ “የየካቲት ቀኖች”፣ “የኑሮ ስህተት” የሚሉ ትያትሮችን ሠርተው አቅርበዋል። 
 

ከ፲፱፻፵፰ ዓ/ም  እስከ ፲፱፻፶፪ ዓ/ም ድረስ የመጀመሪያዋ የሴት የሕግ መምሪያ ምክር ቤት አባልና የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ምክትል ሊቀ መንበር ሆነው አገልግለዋል። በዚህ ምክር ቤት አባል በነበሩበት ጊዜ ብቸኛዋ ሴት ከመሆናቸውም ባሻገር የሴቶች እኩልነት በማይከበርበት ጊዜ እና “የወንድ ዓለም” በገነነበት የታሪክ ምዕራፍ የሴቶችን ሰብዓዊ መብት ለማስከበርና እኩልነትን በሕግ ለማስተማመን ብዙ የታገሉ ሴት ነበሩ። ስለዚህ ጊዜ ሁኔታዎች ምስክርነት ከሰጡት በከፊሉ፦

 ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ፤ የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር የቦርድ ሰብሳቢ። 

 ወይዘሮ ሳባ ገብረ መድኅን፣ የኢትዮጵያ ሴቶች ማኅበራት ቅንጅት ዳይሬክተር። 

እራሳቸውም በጊዜው የዚሁ ሸንጎ አባል የነበሩት ፊታውራሪ አመዴ ለማ ደግሞ ስለዚህ ጉዳይ ትዝታቸውን ሲያካፍሉን፦ 

 ብለው ተናደው ይሄን ተናግረው ወጡ። ይላሉ 

ሌላው የዚህ ሸንጎ አባልና ለብዙ ዘመናት የወይዘሮ ስንዱ ጓደና የነበሩት  አቶ ጠንክር ተድላ፦ ሴቶችን በተመለከተ ጉዳይ ባል ከሚስቱ እውቀት ውጭ ከ አምሥት መቶ ብር በላይ እንዳይበደር የሚል ሃሣብ አቅርበው በጋለ ስሜት እንደተከራከሩና ውጤቱም ይህ ቁም ነገር ሕግ ለመሆን የበቃ መሆኑን ይመሰክራሉ።

ሌላው ብዙ የተሟገቱበትና ውጤታማ የሆኑበት ጉዳይ በጊዜው ቀርቦ የነበረው ‘እንደ ፈረንጆች’ ተለምዶ የኢትዮጵያም ሴቶች ባል ሲያገቡ የባላቸውን አባት ስም እንዲጠቀሙበት የሚል ያልተሳካ የሕግ ረቂቅ ነበር።

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀልና ቀይ ጨረቃ ማኅበር ፕሬዝዳንት፣ የሕዝባዊ ኑሮ እድገት ዋና ፀሐፊነትና አስተዳዳሪነት፣ በምዕራብ ጀርመን ለሦስት ዓመት የትምህርት አታሼ በመሆን አገልግለዋል። ወይዘሮ ስንዱ ከአሥር በላይ የግጥምና ልብ ወለድ መጻሕፍት የጻፉ ሲሆኑ ሠላሳ ሁለት ጽሑፎቻቸው  በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ] ይገኛሉ። 
 

የመጀመሪያዋ የሴት ፓርላማ አባል፣ የሴት የሰብዓዊ መብት ተሟጋች፣ ጀግናና ፀረ-ፋሺስት አርበኛ፣ ፀሐፊ ተውኔት፣የመጽሐፍ ደራሲ፣ እና የመጀመሪያዋ የሴት ዲፕሎማት ስንዱ ገብሩ (የክቡር ዶክተር) ሰኞ ሚያዝያ ፲፪ ቀን ፳፻፩ ዓ/ም በተወለዱ በ ፺፫ ዓመታቸው ሕይወታቸው አልፎ በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ተቀብረዋል።

ወይዘሮ ስንዱ ገብሩ ላበረከቷቸው አስተዋጽዖዎች  የወርቅ ሜዳሊያ፣ የንግሥት ሣባ የወርቅ ኒሻን፣ የቀይ መስቀል የወርቅ ሜዳሊያ እና በኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ዘመን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ተሰጥቷቸዋል።




#Article 187: አርባ ልጆች (111 words)


አርባ ልጆች የተባሉት በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የቱርክ መንግስት አርመናውያን ላይ ጭፍጨፋ ባካሄደበት ወቅት ወላጆቻቸውን በማጣት እና ከጭፍጨፋው ለማምለጥ ተሰደው በእየሩሳሌም የአርመን ገዳም ውስጥ ሲኖሩ ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ (ያኔ አልጋወራሽ ራስ ተፈሪ) አግኝተው ወደ ኢትዮጵያ አምጥተው ያሳደጉዋቸው 40 አርመናውያን ልጆች ናቸው። በልጆቹ የሙዚቃ ችሎታ የተደመሙት አፄ ኃይለሥላሴ በእየሩሳሌም የአርመን ፓትርያርክን ፍቃድ ካገኙ በኋላ ልጆቹን ወደ ኢትዮጵያ ወስደው ተጨማሪ የሙዚቃ ስልጠና እንዲያገኙ አድርገዋል። ልጆቹ በሴፕቴምበር 6፣ 1924 እ.ኤ.አ. ዓ.ም. ከሙዚቃ ባንዱ መሪ ከኬቮርክ ናልባንድያን ጋር ኢትዮጵያ የደረሱ ሲሆን እነዚሁ ልጆች ናቸው በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን የሙዚቃ ጓድ (የንጉሱ የሙዚቃ ጓድ የተባለውን) ያቋቋሙት። ኬቮርክ ናልባንዲያን ማርሽ ተፈሪ የተሰኘውን እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ መዝሙር ሆኖ እስከ እ.ኤ.አ. 1930-1974 ያገለገለውን ሙዚቃ (ግጥሙ የዮፍታሄ ንጉሴ ነው) የደረሰ ነው።




#Article 188: አማርኛ ልብ ወለድ መፃህፍት (247 words)


Mndnew mefthew ylal bejoroye yesekahut ye ermiyas asfaw zefen hulem guzo sguaz zefen eyadametu meguaz lmde honual zare ye betu sm mazewaweriya ken slehone wede kality eyegesegesku nw brdu betam kebad nw yekalitin muket ferche beshemiz nbr yewetahut lerase yezenetku ymeslegnal mnale rihana zare ke 18 belkuanda adrga atena tera bthed eyalku asbalew hulem szent misemagn smet nw.
ye atobis tera taxi atche be piyasa gebaw gashaw ena efremn agegnehuachew gashaw alayegnm nbr yetaxi sikefl endemegderder bye temelesku ayy gashaw yedro tsegur korache nbr beljnete 2 birr yetsegur mekorecha bematabet seat getu yemibal gorebetachn ena zemedoche bemetu seat eza eyehedku nbr mkoretew ahun sew ketro esu lela bota eyesera mehonun semche nbr atobis tera dershem swerd amesggne weredku ke ephrem gar abren werden selam tebabaln esu ye saris taxi endemiyz negrogn ene demo yekality taxi yzhe menged jemerku yhe sfr ahun yedro 06 eskimeslegn tenkke akewale ahun gotera dershalew mengedu des ylal temari lemeshager eyefera zebra lay dngrgr ylewal arogit yemengst serategnoch beza sewnetachew eskehodachew yemiders suri tatkew borchachew fitachewn shefno beza hil chama lidefu ymeslalu beye tgagatgu taxi lemeyaz yekomu sewoch borsachewn tatkew begrachew ykuatnalu tsdat serategnoch kemengedu tgtg antsebaraki lebsew mengedun yatsedalu mnale yenesun lfat ayten banakoshsh bye asbalew gn leseatu endehon ygebagnal bcha ayne wst slegebuna slasazenugn yh eznet keayne sitefu abro ytefana enenm endelelaw sew ehonalew yetsehaywa brhan kemengedu tsdat kefokochu mamar kezafochu wedehuala mewenchef gar tedemro lela bota lela sew yehonku meselegn hule eza sfr mikemet eza bet mitegnaw fuad almeslh eskilegn.




#Article 189: መኪና (826 words)


መኪና የሚለው ቃል 'macchina' ከሚለው የጣሊያንኛ ቃል የተወረሰ ቃል ሲሆን፣ (ወይም አውቶሞቢል፣ ተሽከርካሪ) ከሥፍራ ወደ ሥፍራ በመንኮራኩር ላይ በሞቶር የሚነዳ ተንቀሳቃሽ አይነት ነው። ስዎችም ሆነ ዕቃ በመንገዶች ላይ ለማዛወር ይጠቀማል። በ1999 ዓ.ም.፣ በመላ ዓለም ውስጥ የመኪናዎች ቁጥር 800 ሚሊዮን ያህል ነበር። በተለምዶ «መኪና» የሚለው ስም የሚሰጠው ከዶቅዶቄ ትልቅ፣ ከካሚዎንም ወይም ከአውቶቡስ ትንሽ ለሆነ ባለሞቶር ተሽከርካሪ ነው፤ አንዳንዴ ግን ቀላል ካሚዎኖች ከመኪናዎች ጋር መመደብ ይቻላል። በአማካኝ ለመኪናዎች የተሳፋሪዎች ቁጥር ችሎታ 5 ሰዎች ቢሆን፣ በየአይነቱ ግን ከ1 እስከ 9 መቀመጫዎች ድረስ በመገኘት ይለያያል። 

 
በቤንዚን የሚሄድ ተግባራዊ መኪና መጀመርያ በጀርመን ሰዎች በ1877 ዓ.ም. ተፈጠረ። ከዚያ በፊት ግን በእንፋሎትም ሆነ በኤሌክትሪክ የሚነዱ መኪናዎች ይገኙ ነበር። 

መጀመርያ በእንፋሎት የሚነዳ ተሽከርካሪ የታቀደው በኢየሱሳዊው ሚሲዮን ቄስ በቻይና፣ የቤልጅግ ኗሪ ፈርዲናንድ ፈርቢስት በ1664 ዓ.ም. ነበር። እሱ በጻፈው መግለጫ መሠረት፣ ይህ ተሽከርካሪ ለቻይና ንጉሥ ካንግሺ ለጨዋታ እንዲሆን ጥቃቅን ምሳሌ ብቻ ነበር፤ እቅዱም በተግባር ከተሠራ ኖሮ አይታወቅም። 
 
ከዚያ በኋላ፣ በ1761 ዓ.ም. የፈረንሳይ ሠራዊት መድፎችን ለመሸክምና ለማዛወር የጠቀመ የንፋሎት ጋሪ በኒኮላ-ዦሴፍ ኩንዮ ተፈጠረ። በመጀመርያ የፈረንሳይ መንግሥት ትኩረት በዚህ ፍጥረት ተሳበና በ1763 ዓ.ም. ሁለተኛ እንፋሎት ጋሪ ተሠራ። ዳሩ ግን ለረጅም ጊዜ እንፋሎት ማስገኘት ስላልቻለ ተግባራዊው ዋጋ ጥቂት በመሆኑ፣ ወደ ማከመቻ ሥፍራ ተላከ። የመድፍ አለቃ ሙሴ ሮላንድ እንደገና በ1792 ዓ.ም. አገኘው፣ ነገር ግን ናፖሌዎን ለዚህ ጉድ ምንም ፍላጎት አልነበረውምና ሃሣቡ ለጊዜው ተረሳ።

 
በዚሁም መካከል፤ በ1776 ዓ.ም. የስኮትላንድ ሰው ዊሊያም ሙርዶክ ባለ ሦስት መንኮራኩር የእንፋሎት ሠረገላ ሠራ። ጊዜውን ባለማግኘቱ ግን ሥራው መቋረጥ ነበረበት። 

 
ከዚያ በ1793 ዓ.ም. የሙርዶክ ጎረቤት የነበረ ሌላው የብሪታንያ ኗሪ ሪቻርድ ትሬቪሲክ የራሱን እንፋሎት ሠረገላ ሠራ። በ1795 ዓ.ም. ደግሞ «የለንደን እንፋሎት ሠረገላ» ፈጠረ፤ ይህም መኪና ለ10 ማይል በለንደን መንገዶች ላይ ስምንት ሰዎችን ወሰደ፤ ጉዞውም ከሰዓት በላይ ፈጀ። ሆኖም በኋላ ጊዜ በአጋጣሚ ግጭት ተጋጠመና ፈጠራው ለጊዜው ጠፋ። ብዙ ጊዜ ሳያልፍ ሌሎች ሰዎች አዳዲስ አይነቶች የእንፋሎት ተሽከርካሪዎች ሠሩ። 

በ1799 ዓ.ም. ደግሞ ውስጣዊ ፈነዳ ኤንጂን በስዊስ አገር ተፈጠረ፤ በመጀመርያው ይህን ፈጠራ ያካሄደው ጋዝ ሃይድሮጅን ብቻ ነበረ። በ1818 ዓ.ም. ሱሙኤል ብራውን በዚህ አይነት መሣርያ አንዱን ጋሪ በለንደን ኮረብታ ላይ እንዲወጣ አደረገ፤ የሙከራው ከፍተኛ ዋጋ ግን ተግባራዊ ፈጠራ እንዳይሆን ከለከለ። 

ከዚህ ትንሽ በኋላ፣ በ1820 ዓ.ም. የሀንጋሪ ሰው አንዮስ የድሊክ ለመጀመርያው ጊዜ በኤሌክትሪክ ሞቶር የሚሮጥ ትንሽ የተሽከርካሪ ምሳሌ ሠራ። እንዲሁም በአሜሪካ በ1826 ዓ.ም. እና በሆላንድ በ1827 ዓ.ም. ተመሳሳይ ባለ ኤሌክትሪክ ሞቶር ናሙናዎች ተሠሩ። በቅርብ ጊዜ ከዚያ ቀጥሎ፣ የስኮትላንድ ሰዎች መጀመርያው ሙሉ-መጠን ኤሌክትሪክ መኪና ለመሥራት ተከናወኑ። በሚከተሉት አሥርታት ላይ (1830ዎች-1840ዎች ዓ.ም.)፣ የእንፋሎት መኪና እና የኤሌክትሪክ መኪና ቀስ በቀስ በአውሮጳና በአሜሪካ መንገዶች ላይ ይታዩ ጀመር፤ እንደ ወትሮ ከቆየው ከባለ ፈረስ-ጋሪው ትራፊክ አጠገብ አነስተኛ ፈንታ ብቻ ወሰዱ እንጂ በዚያው ዘመን እኚህ አዳዲስ ፈጠራዎች እጅግ ብርቅ ዕይታ ሆነው ቀሩ። በተጨማሪ፣ በአገር ቤት መንገድ በሩቅ ጉዞ ለመሔድ ባለመቻላቸውና በጣም ውድ በመሆናቸው፣ ተግባራዊ ጥቅማቸው በከተማዎች ውስጥ ብቻ፣ በተለይም ለሀብታሞች ወይም እንደ ሕዝባዊ መጓጓዣ (እንደ ታክሲ) ነበር። ለፈረሶች አስደንጋጭ ሥራዎች እንደ ሆኑ መጠን፣ የእንግሊዝ መንግሥት መጀመርያ በ1853 ዓ.ም. የፍጥነት ወሰን በዚህ አይነት ትራፊክ ጣለ፤ ይህም ወሰን በከተማ 5 ማይል (8 ኪ/ሜ) በየሰአቱ ብቻ ነበረ። በ1857 ዓ.ም. የእንግሊዝ መንግሥት ባወጣ ሕግ ወሰኑን እንደገና ወደ 2 ማይል (3 ኪ/ሜ) በየሰአቱ ቀነሰው፤ ከዚህም በላይ ቀይ ባንዲራ የያዘ እግር መንገደኛ በጋሪው ፊት እንዲቀድመው ተገደደ። ስለዚህ «ፈረስ የለሽ ጋሪዎች» ከለንደን መንገዶች ለ30 ዓመታት ያህል ከማጥፋት ሁሉ ትንሽ ቀሩ። በመነጻጸር በፈረንሳይና በአሜሪካ አገራት በሕግ ቢታገሡም፣ ገና አልፎ አልፎ ብቻ የሚታዩ ድንቆች ይሆኑ ነበር። 

 
በዚሁም መካከል፣ በ1855 ዓ.ም. የቤልጅግ ሰው ኤቲየን ለኗር በሃይድሮጅን ጋዝ ውስጣዊ ፈነዳ ኤንጂን የሚነዳ መኪና ወይም «ሂፖሞቢል» ፈጠረ። በሙከራው ጉዞ 11 ማይል በፓሪስ መንገዶች በ3 ሰአቶች ጨረሰ። ለኗር 350 ያህል ሂፖሞቢሎችን ሸጠ። 

 

በ1862 ዓ.ም. የኦስትሪያ ሰው ሲግፍሪድ ማርኩስ ትንሽ ጋሪ በቤንዚን ውስጣዊ ፈነዳ ኤንጂን ሠራ። እንዲያውም ይህ ድርጊት የቤንዚን መኪና ፈጣሪ ያደርገዋል፤ ዳሩ ግን በ2ኛው ዓለማዊ ጦርነት ጊዜ ናዚ ባለሥልጣናት ይህን ዒላማ ከጀርመን መዝገቦች አስወገዱ፤ ይህም አቶ ማርኩስ ከአይሁዳዊ ዘር ስለነበር ነው። 

 
በማርኩስ ፈንታ በቤንዚን የሚሮጠውን ዘመናዊ መኪና የመፍጠር ክብር የሚሰጠው ለካርል ቤንዝ ሆነ። በ1877 ዓ.ም. በማንሃይም ጀርመን አገር መጀመርያ ቤንዝ ሞቶር-ጋሪ ሠራ። በ1880 ዓ.ም. ይህን ሞዴል በጀርመንና በፈረንሳይ በገበያው ላይ ይሸጥ ጀመር። በዚያም አመት የካርል ቤንዝ ሚስት ቤርጣ ቤንዝ ለመጀመርያው ጊዜ ለረጅም ጉዞ (106 ኪ/ሜ) በዚህ አይነት መኪና ሄደች። ከዚህ ትንሽ በኋላ በ1881 ዓ.ም. ሌላው ጀርመናዊ ጎትሊብ ዳይምለር የራሱን መጀመርያ ቤንዚን አውቶሞቢል ሠራ። 

በዚሁ ወቅት፣ በርካታ ሰዎች በኤውሮጳም ሆነ በአሜሪካ የቤንዚን መኪና መሥራት ንግድ ሞከሩ። በ1881 ዓ.ም. በፈረንሳይ አንድ የመኪና መሥሪያ ድርጅት (ፓንሃርድና ሌቫሦር) ቆሞ ነበር፤ እንዲሁም በ1885 ዓ.ም. በአሜሪካ ነበር (ዱርዬ ሞቶር-ጋሪ ድርጅት)። ከ1892 ዓ.ም. ጀምሮ፣ አሜሪካና ፈረንሳይ አገራት ሁለቱ በጅምላ በገፍ ምርት መኪናን ለመስራት ዝግጁ ነበሩ። ሄንሪ ፎርድ በዚያው ዓመት የዲትሮይት አውቶሞቢል ድርጅት መሠረተ። በቶሎ ግን በ1894 ዓ.ም. ፋብሪካው የቆመው ኦልድስ የሞቶር ተሽከርካሪ ድርጅት አንደኛውን ሥፍራ ወሰደ። በዓመቱም ውስጥ አያሌ ሌሎች ተወዳዳሪዎች ድርጅቶች ለአሜሪካ መንገዶች ብዙ ሺህ መኪናዎች ሠሩ፤ እነርሱም ዊንቶን ሞቶር ጋሪዎች፣ ፎርድ ሞቶሮች፣ ካዲላክና ቶማስ ቢ ጄፍሪ ድርጅት ነበሩ። በ1895 ዓ.ም. መጨረሻ፣ 9000 ያህል የቤንዚን መኪናዎች በአሜሪካ ነበሩ። በዚሁ ሰአት በአሜሪካ ከተገኙት መኪናዎች መካከል 40 ከመቶ የእንፋሎት አይነት ሲሆኑ፣ 38 ከመቶ የኤሌክትሪክ አይነትና 22 ከመቶ ብቻ የቤንዚን አይነት ነበሩ። ከ10 አመታት በኋላ ግን የቤንዚን መኪና ከሌሎቹ አይነቶች ይልቅ የተወደደው ዘዴ ሆነው ነበር። ይህም የሆነባቸው ሳቢያዎች ሁለት ናቸው፤ አንደኛው የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ በዚያን ጊዜ ቻርጅ ሳይደረግለት ከ1 ሳአት በላይ ሊጠቀም ስላልቻለ ነው፤ ለአጭር ጉዞዎች ብቻ ተስማሚ ነበሩ። ሁለተኛው፤ በቂ የፔትሮሌዩም ዘይት ምንጮጭ በመገኘታቸው ቤንዚን ርካሽ የነዳጅ አይነት ሆነ። ከዚህ በላይ ከ1904 ዓ.ም. ጀምሮ የቤንዚን መኪና አጀማመር ዘዴ እጅግ ከለለ። ስለዚህ ጥቂት አመታት ስያልፍ የእንፋሎት መኪናና የኤሌክትሪክ መኪና ጥቅም ለጊዜው ተረሳ። 




#Article 190: ዝሆን (188 words)


ዝሆን ከባዮሎጂ ዘመድ Elephantidae («የዝሆን አስተኔ») እንዲሁም ከክፍለመደብ Proboscidea («ባለ ኩምቢዎች») ብቸኛው ኗሪ አባሎች ናቸው። የዝሆን መደብ 3 የተላያዩ ኗሪ ዝርያዎችን ያቀፈ ነው። እነሱም የአፍሪካ የነጭ ሳር ዝሆን፣ የአፍሪካ የጫካ ዝሆን (እንከ ቅርብ የአፍሪካ ዝሆን ሲባል የነበረው) እና የኤዢያ ዝሆን (ወይ የህንድ ዝሆን የሚባለው) ናቸው። ከዝሆን ጭምር አንዳንድ በጥንት የጠፉት ነባር ዝርያዎች በተለይም Mammoth ማሞጥ ወይም ቀንደ መሬት በዝሆን አስተኔ ውስጥ ተመድበዋል።

ዝሆን ማማል (ወይም ጡት አጥቢ እንስሳ) ሲሆን፣ በምድር ከሚገኙ እንሥሣት በሙሉ ግዙፉ እንሳሳ ነው። ሴት ዝሆን ከእንስሶች በሙሉ የርግዘት ግዜት ረጅሙ ሲሆን 22 ወራት ይፈጃል። አንድ ዝሆን ሲውለድ 120 ኪ.ግ. መአከለኛ ክብደት አለው። ዝሆን እስካ 70 አመታት እድሜ ሊያስቆጥር ይችላል። እስካሁን የተመዘገበው ታላቁ ዝሆን 12 000 ኪ.ግ. ያስቆጠረ ሲሆን ርዝመቱ ደግሞ 4.2 ሜ በመድረስ ከመሀከለኛው የዝሆኖች ቁመት 1 ሜትር በላይ አስቆጥረዋል።

ዝሆኖች በሚኖሩበት ስፍራ በሰው ልጆች እንቅስቃሴ ምክኒያት እየተጎዱ መጥተው ቨ እ.አ.ኤ 1.3 ሚሊዪን ይቆጠሩ የነበሩ በ 1989 ወደ 600 000 ዝቅ በለው ተገኝተዋል። ዛሬ ከ 440 000 እስከ 660 000 ሆነው ይተመናሉ።

ባለፈው ክፍለ ዘመን በእስያ አንዳንድ ዝሆኖች በኩምቢያቸው ማለፊያ ስዕል ለመሳል በቂ አዕምሮና ሥነ ውበት እንዳላቸው አሳይተዋል። ይም በበርካታ ዩቱብ ቪዴዎች ሊታይ ይቻላል። የፈጠሩት ትርዒቶች ዝሆን፣ ዛፍ፣ አበባ፣ ሣር እና በላቲን ፊደል ፊርማቸው አለባቸው። 




#Article 191: ኤሪዱ (248 words)


ኤሪዱ (ወይም ኤሪዱግ / ኡሩዱግ፣ ከሱመርኛ ኤሪ-ዱጋ «ጥሩ ከተማ») ከዑር ወደ ደቡብ-ምዕራብ 7 ማይል የራቀ ጥንታዊ ከተማ ነበረ።  በሱመር በመስጴጦምያ በመስጊዶች ዙሪያ ከተመሠረቱት ከተሞች አንዱ ሲሆን ከሁላቸው ወደ ደቡብ ተገኘች።  

በሱመራውያን ነገሥታት ዝርዝር ዘንድ፣ ኤሪዱ የዓለሙ መጀመርያ ከተማ ነበረ። እንዲህ ሲል፦ 

በሱመር አፈ ታሪክ ዘንድ፣ ከማየ አይህ ቀድሞ ከተሠሩት 5ቱ ከተሞች አንዱ እንደ ነበር ተባለ።  ለመሆኑ በሥነ-ቅርስ ረገድ የሱመር መጀመርያ ከተማ ሆኖ ይመስላል።  ሲገነባ ኤፍራጥስ ወንዝ ወደ ፋርስ ባሕር ወሽመጥ ወደብ በሚፈስስበት ስፍራ እንደሆነ ቢታሥብም ዛሬ ግን በአሸዋ ጥርቅም ምክንያት ባሕሩ ከቦታው በጣም ይርቃል። 

የኤንኪ (አምላክ ወይም ጣኦት) ቤተ መቅደስ በኤሪዱ 'ኤ-አብዙ' ተባለ። የኤንኪ ሚስት የኒንሁርሳግ ቤተ መቅደስ 'ኤ-ሳጊላ' ደግሞ በአካባቢው ነበረ።   

መምህርዋ ኬት ፊልደን እንደምትለው፣ «ከ2050 ክ.በ. ገዳማ በፊት ከተማው ዝቅ ብሎ መኖርያ እንደሆነ ትንሽ ምልክት ብቻ አለ። ንጉስ አማር-ሲን (2055-2047 ክ.በ. ገዳማ)  ካልጨረሰው መስጊድ በታች 18 የጡብ ቤተ መቅደሶች አሉ።»

በኋላ ዘመን በአሦር ቤተ መንግሥት ልዩ ህኪሞች ስለ በሽታ ጠንቆች ህክምና ለማወቅ የኤሪዱ ጥንታዊ ጥበብ መማር ነበረባቸው።  

በሱመራውያን ነገሥታት ዝርዝር በኩል፣ ኤሪዱ የመጀመርያ ነገሥታት ከተማ ተብሎ እንዲህ ይቀጥላል፦

(የነገሥታት ዝርዝሩ ከጥፋት ውኃ በፊት ለገዙት ነገሥታት እጅግ ረጅም ዘመን ይሰጣቸዋል።)  

ስለ ኢናና (የኡሩክ ከተማ ሴት አምላክ) ደግሞ አንዳንድ ትውፊት ይተረክ ነበር። የሥልጣኔ ስጦታ ለመቀበል ወደ ኤሪዱ መጓዝ እንደ ነበረባት ተባለ። ኤንኪ በመጀመርያ የሥልጣኑን ምንጭ ለመመለስ ቢሞክርም፣ ኋላ ግን ኡሩክ የአገሩ መሃል መሆኑ ተስማማው።  

አንዳንድ የባቢሎን ጽሕፈት ደግሞ አምላካቸው ማርዱክ ኤሪዱን እንደ 'መጀመርያ ቅዱስ ከተማና የአማልክት መኖርያ' ሆኖ እንደ ፈጠረው ይላል።   

የመምህር ዴቪድ ሮህል ኅልዮ በጣም ትኩረት ይስባል። በሱ አሳብ ዘንድ፣ ኤሪዱ ከዑር ወደ ደቡብ መጀመርያይቱ ባቢሎን ነበረችና የባቢሎን ግንብ ሥፍራ በኋለኛው ባቢሎን ሳይሆን እዚህ እንደተገኘ ያምናል። ምክንያቶቹም፦ 




#Article 192: ኤንመርካርና የአራታ ንጉስ (486 words)


ኤንመርካርና የአራታ ንጉስ በጣም ጥንታዊ የሱመርኛ ትውፊት ነው። በታሪካዊ ሁኔታ ምናልባት በ3ኛ ሺህ ዘመን ክ.በ. ድርጊቶች ላይ የተመሰረተ ሊሆን ይቻላል። ከ'ኡኑግ-ኩላባ' (ኦሬክ ወይም ኡሩክ) ንጉስ ከኤንመርካርና ስሙ ካልታወቀ ከአራታ ንጉስ መከከል ስለተደረገው ውድድር ከሚገልጹ ሰነዶች አንዱ ነው።  

በሰነዱ መጀመርያ ክፍል የሚከተለው መረጃ ይሰጣል፦ «በዚያ ጥንታዊ ዘመን፣ ዕድሉ በተወሰነ ጊዜ፣ ታላላቆቹ መሳፍንት የ'ኡኑግ-ኩላባ' ኤ-አና ራሱን ከፍ እንዲያድርግ ፈቀዱ። በዚያን ጊዜ ብዛትና የዓሳ ጎርፍ፣ መልካም ገብስ የሚያመጣውም ዝናብ በ'ኡኑግ-ኩላባ' ተጨመሩ። የድልሙን አገር ገና ሳይኖር፣ የ'ኡኑግ-ኩላባ' ኤ-አና በደንብ ተመሰረተ።» 

ኤ-አና ማለት 'የአገራት ሁሉ እመቤት' ለሆነች ለኢናና ክብር በኡሩክ የተሠራ መስጊድ ነበረ። እንዲሁም የአራታ ጌታ በኢናና ስም ራሳቸውን በዘውድ ቢጫኑም፣ ይህ ማድረጋቸው ግን በኡሩክ እንዳላት ጡብ መስጊድዋ ደስ አላሰኛትም።

እንዲህ 'ኢናና ከብሩኅ ተራራ በቅዱስ ልብዋ የተመረጠችው' ኤንመርካር ከዚያ አራታ እንዲገዛለት እናና እንድትፈቅደው ይጠይቃታል። የአራታ ሕዝብም የወርቅና የዕንቁ ግብር እንዲያቀርቡ፣ ከፈተኛው የአብዙ መቅደስ በኤሪዱ፣ የኤ-አና መቅደስም በኡሩክ ይሠራ ዘንድ፣ ይጠይቃታል። እንግዲህ የኢናና ምክር ለኤንመርካር አንድ ልዩ ተልእኮ የሱስንና የአንሻን ተራሮች አሻግሮ ከአራታ ንጉስ ግብርነታቸውንና ተገዥነታቸውን ለማስፈልግ ወደ አራታ እንዲልከው ነው።  

ይህ ምክር ለኤንመርካር ተስማምቶት ተልእኮውን ይልካል። መልእክተኛውን ሲልከው ደግሞ ግብሩን ካልላኩለት በቀር አራታን ለማጥፋትና ሕዝቡን ለመበትን የሚል ዛቻ ይሰጣቸዋል እንዲህ ሲለው፦ «ኢናናም በማዕበሉ በጩኸት የተነሣችበት እንደ አጥፊው ጎርፍ ጥፋት እኔም ደግሞ የጎርፍ ጥፋት በዚያ እንዳላድርግ...»። ከዚያ በላይ ለመልእክተኛው 'የኑዲሙድ መዝሙር' ይሰጣል፤ ይህም ኤንኪ የተባለው አምላክ ኗሪ ያለባቸው አገሮች ሁሉ ወደ አንድ ቋንቋ እንዲመልሳቸው ይለምናል። (በሌላ ትርጉም ግን ኤንኪ የአገሮች ቋንቋ እንዲያደባለቅ ይላል።) እነዚህ አገሮች ስሞች ሹባር፣ ሐማዚ፣ ሱመር፣ ኡሪ-ኪ (የአካድ ዙሪያ) እና የማርቱ አገር ይባላሉ።   

መልእክተኛው በአራታ ይደርስና ይህን መልእክት ለንጉሡ ተናግሮ ለጌታው ለኤንመርካር መልሳቸውን ይጠይቃቸዋል።  የአራታ ንጉሥ መልሰው ለኡሩክ እጅ መስጠት ከቶ አይቻልም ይላሉ፣ ምክንያቱም ኢናና እራሷ ለማዕረጋቸውና ለሥልጣናቸው መርጣቸዋለችና። ተልእኮው ግን ወዲያው እናና በኡሩክ ንግሥት ሆና እንደ ተቀባች ከዚያም በላይ አራታ ለኡሩክ እንዲሰግድ ለማድረግ ቃልዋን እንደ ሰጠች ይገልጽላቸዋል። 

በዚህ ዜና ጭፍግግ ገብተው በመጨረሻ የአራታ ንጉስ መልሳቸውን ይሰጣሉ፦ የኡሩክ ሠራዊት ለሳቸው እኩል ስላልሆነ ከኡሩክ ጋር ጦርነት ለማድረግ የተዘጋጁ ቢሆኑም፤ ኤንመርካር ግን የትልቅ መጠን ገብስ ወደ አራታ ቢልክላቸውና ኢናና እራሷ አራታን እንደ ተወች ብታስረዳው የዛኔ እጃቸውን ይሰጡታል ይላሉ።

ተልእኮ ይህን መልስ ይዞ ወደ ኤንመርካር ተመለሰና በማግሥቱ ኤንመርካር እንዲያውም ገብሱን ወደ አራታ ይልካል። ደግሞ ተልእኮውን በተጨማሪ ዕንቁ ለመጠይቅ ይልከዋል።

የአራታ ንጉስ ግን እምቢ ብለው በዚያ ፈንታ ኤንመርካር እራሱ ዕንቁ ወደሳቸው እንዲልክ ይጠይቃል። ኤንመርካር ይህን ሰምቶ ለአሥር አመት የተጌጠ በትር ያዘጋጃል። ከዚያ በኋላ ይህን ወደ አራታ በመልእክተኛው እጅ ይልካል። ይህ የአራታን ንጉሥ ያስፈራል፤ አሁን ኢናና በእውነት እንደ ተወቻቸው ያያሉና። ነገር ግን ጥያቄውን ለመወሰን ከሁለቱ ከተሞች ሁለት ጎበዞች አንድ በአንድ ላይ እንዲታገሉ የሚል ሀሣብ ያቀርባሉ። የኡሩክም ጌታ ይህን ሀሣብ ሲቀበል በተጨማሪ እንዳያጠፋቸው የአራታ ሕዝብ ለከፍተኛው መቅደሱ ዕንቁና ወርቅ እንዲገብሩ ይጠይቃል። መልእክተኛው በቃሉ ብዛት ለማስታወስ ተቸግሮት ኤንመርካር በዚያን ጊዜ ጽሕፈት ይፈጥራል። ስለዚህ ተልእኮው ጽሕፈቱን ይዞ እንደገና 'ሰባቱን ተራሮች' ይሻገራልና ለአራታ ንጉስ ያቀርበዋል። የአራታ ንጉስ ጽሕፈቱን ለማንበብ ሲሞከሩም ኢሽኩር (የአውሎ-ንፋስ አምላክ) ስንዴና ሽምብራ ለማብቀል ዶፋ ዝናብ ይሰጣል። ይህ ስንዴና ሽምብራ ወደ ንጉሥ ሲያመጡ፣ እሳቸው ኢናና የአራታን ቅድምትነት እንዳልተወች ያስረዳል ብለው ኅይለኛ ጎበዛቸውን ጠሩ።

ከዚህ በኋላ የሰነዱ ሸክላ ብዙ ቀዳዳ ስላለበት በቀላል አይታነብምና የሚከተለው ታሪክ ግልጽ አይደለም። በመጨረቫ ግን ኤንመርካር እንዳሸናፈ ምናልባትም ኢናና በአራታ ዙፋን ላይ እንዳስቀመጠችው ይመስላል። የአራታም ሕዝብ ግብራቸውን ለኤ-አና እና ለከፍተኛ አብዙ ግንብ ያቀርባሉ። 




#Article 193: ሱሳ (392 words)


ሱሳ (ፋርስኛ፦ شوش /ሹሽ/፤ ዕብራይስጥ፦ שושן /ሹሻን/፤ ጥንታዊ ግሪክ፦ Σέλεύχεια /ሰለውከያ/፤ ሮማይስጥ፦ Seleucia ad Eulaeum /ሰለውኪያ አድ ኤውላዩም/) በኢራን በ የሚገኝ እጅግ ጥንታዊ ከተማ ነው። በ1997 ዓ.ም. 64,960 ገደማ ሰዎች ይኖሩበት ነበር። 

ሱሳ በድሮ ጊዜ የኤላም መንግሥት ዋና ከተማ ነበረ። በዓለሙ ከሁሉ ጥንታዊ ከተሞች አንድ ነው። በኤላምኛ ከተማው ሹሻን ተባለ። በሱመርኛ መዝገቦች ይታወቃል። ለምሳሌ ኤንመርካርና የአራታ ንጉስ በተባለው ትውፊት ለኡሩክ አምላክ ለኢናና እጅ የሰጠ ቦታ ይባላል። 

በመጽሐፍ ቅዱስ ሱሳ (ወይም 'ሱሳ ግንብ') በተለይ በመጽሐፈ አስቴር ሲጠቀስ ደግሞ አንዴ በመጽሐፈ ነህምያ አንዴም በመጽሐፈ ዳንኤል ስሙ ይገኛል። ዳንኤልና ነህምያ ሁለቱ በ6ኛ ክፍለ ዘመን ዓክልበ. በባቢሎን ምርኮ ጊዜ በሱሳ ይኖሩ ነበር። አስቴርም እዚያ ንግሥት ሆና አይሁዶች ከእልቂጥ እንዲያመልጡ ቻለች። ከዚህ በላይ የነቢዩ ዳንኤል መቃብር በከተማው አካባቢ እንዳለ ይታመናል። 

ሱሳ እንደገና በመጽሐፈ ኩፋሌ ይጠቀሳል። በቁ. 9፡10 እና 9፡16 መሠረት በሴምና በበኩሩ በኤላም ርስት ውስጥ ካሉት ቦታዎች አንድ ነው ይላል። በተጨማሪም በምዕ. 8፡34 'ሱስን' የኤላም ልጅ ይባላል።

ሱሳ በአዋን ሥርወ መንግሥት ሥር እንደ ተመሠረተ ይመስላል። በ2075 ዓክልበ. ገደማ ሱሳ በታላቁ ሳርጎን ወደ አካድ መንግሥት ተጨመረ። በአካድ ውስጥ የክፍላገሩ ዋና ከተማ ሆኖ ቀረ። በ2013 ገደማ ግን ኤላማዊው አገረ ገዡ ኩቲክ-ኢንሹሺናክ በአመጽ ተነሥቶ ነጻ አወጣው። በ1888 ዓክልበ. የኡር ንጉሥ ኢቢ-ሲን ሱሳን አሸነፈው። እንዲህ የኡር መንግስት በኤላማውያን እጅ እስከ ወደቀ ድረስ እስከ 1879 ቆየ። ያንጊዜ ሱሳ ዳግመኛ የኤላም ዋና ከተማ ሆነ። 

በ1640 ዓክልበ. የባቢሎን ንጉሥ ሳምሱ-ኢሉና ሱሳን አጠፋው። በ1184 ዓክልበ. በንጉሳቸው ሹትሩክ-ናሑንተ መሪነት ኤላማውያን የባቢሎን ንጉስ የሐሙራቢ ሕገጋት የተቀረጹበት ጽላት በዝብዘው ወደ ሱሳ በምርኮ ወሰዱት። እዚያም በ1894 ዓ.ም. በሥነ-ቅርስ ይገኝ ነበር። ይሁንና የባቢሎን ንጉስ 1 ናቦከደነጾር ከአምሳ አመት ያሕል በኋላ ሱሳን በሱ ተራ ለመበዝበዝ በቃ። 

በ655 አመት ከክርስቶስ በፊት የአሦር ንጉስ አስናፈር በጦርነት ከተማውን ፈጽሞ አጠፋ። በኋላ በ545 ክ.በ. የፋርስ ንጉሥ ታላቁ ቂሮስ ከተማውን ማረከ። በቂሮስም ልጅ በካምቡሴስ ዘመን ዋና ከተማው ከፓሳርጋዳስ እስከ ሱሳ ተዛወረ።

በ339 ክ.በ. የመቄዶን ንጉሥ ታላቁ እስክንድር ከፋርስ መንግሥት ጋር ሱሳን አሸነፈው። ከሱ በኋላ ሱሳ ለሴሌውቅያ መንግሥት ስለ ታደለ ስሙ ሰለውከያ ሆነ። ከመቶ አመት በኋላ የጳርቴ መንግሥት ነጻነቱን ከሴሌውቅያ አገኝቶ ሱሳና ካሲፍያ ሁለቱ ዋና ከተሞቹ ሆኑ። የሮማ ንጉስ ትራያን በ108 ዓ.ም. ሱሳን ይዞ በአመጽ ምክንያት ቶሎ መመለስ ነበረበት። ይህም ሮማውያን ከሁሉ ወደ ምሥራቅ የደረሱበት ወቅት ነበረ። 

የእስላም ሰራዊቶች በ630 ዓ.ም. ፋርስን በወረሩበት ጊዜ ሱሳ እንደገና በጥፋት ላይ ተጣለ። በሌላ ዘመን በ1210 ዓ.ም. በወራሪ ሞንጎሎች እጅ በፍጹም ጠፋች።

ሱሳ ወይም ሹሽ ዛሬ በፋርስ ውስጥ በሑዚስታን ክፍላገር ይገኛል።

ሥፍራው በሥነ ቅርስ ረገድ አይነተኛ ቢሆንም በቅርቡ የሕገ ወጥ ቆፈራ ትልቅ ችግር ሆኖአል። 

ከቅርሶቹም በላይ ሱሳ ስለነቢዩም ድንኤል ስመ ጥሩ ሆኖ የሺዓ እስላም ወገንም ሆነ የፋርስ አይሁዶች መቃብሩን በጣም ያከብሩታሉ። 




#Article 194: ሐማዚ (197 words)


ሐማዚ ምናልባት በ2420 ዓክልበ. ገዳማ የነበረ መንግሥት ሲሆን በምዕራብ ዛግሮስ ተራሮች ከኤላምና ከአሦር መካከል እንደተገኘ ይታሥባል።  

ሐማዚ ለሥነ-ቅርስ ጥናት መጀመርያ የታወቀው በዚህ ቦታ ላይ የኪሽ ንጉሥ ኡቱግ ወይም ኡሁብ ድል የሚመዝገብ በጥንታዊ ባለ-ማዕዘን (ኩኔይፎርም) ጽሕፈት የተጻፈ ጽላት ሲገኝ ነበር።  

ሌላ ጥንታዊ ጥቅስ ደግሞ ኤንመርካርና የአራታ ንጉስ በተባለ አፈ ታሪክ ተገኝቷል። እዚህ ኡሩክና ኤሪዱ ግንቦች በተሠሩ ጊዜ ስለ ልሣናት መደባለቅ የተለያዩ አገራት ሲዘረዘሩ በመዝሙር ይጠቀሳል። በዚሁ ዝርዝር፣ ሐማዚ ብቻ «ባለ ብዙ ልሳናት» የሚል ስያሜ ይሠጣል። የሚከተለው ጽሑፍ ኤንመርካርና ኤንሱህከሽዳና እንደሚለው፣ ሐማዚ ከጠፋ በኋላ የሐማዚው ጠንቋይ ኡርጂሪኑና ወደ አራታ ፈልሶ፣ ከዚያ የአራታ ንጉሥ ኡሩክን ለማሸነፍ በኤንመርካር ላይ ልኮት አልተከናወነም።

በሱመር ነገሥታት ዝርዝር መሠረት የሐማዚ ንጉሥ ሀዳኒሽ ኪሽን ካሸነፈ በኋላ (2243 ዓክልበ. ግ.) በሱመር ላይ ላየኛነት ያዘ። እሱ ግን በተራው በ2215 ዓክልበ. ግ. በኡሩክ ንጉስ በኤንሻኩሻና ድል ሆነ። 

በኤብላ ከተማ በሶርያ በተገኘ የሸክላ ጽላት ላይ አንድ ዲፕሎማቲካዊ መልእክት ከኤብላ ንጉስ ኢርካብ-ዳሙ (2110 ዓክልበ. ግ.) ወደ ሐማዚ ንጉስ ዚዚ ከብዙ ዕንጨት ጋር ተላከ። እንደ ወንድም ሆኖ ሰላምታ ሰጥቶ በምላሽ ወታድር እንዲልክለት ይጠይቀዋል።

በአዲስ ሱመራዊ ኡር መንግሥት ጊዜ በንጉስ አማር-ሲን ዘመን (1918-1909 ዓክልበ.) ሐማዚ ከጠቅላይ ግዛቶቹ አንድ ነበር። በዚህ ዘመን የአገረ ገዥ ስሞች ኡር-ኢሽኩር እና የናምሃኒ ልጅ ሉ-ናና ይታወቃሉ። የኡር መንግሥት ሊወድቅ ሲል (1879 ዓክልበ. ገዳማ) ጠቅላይ ግዛቱን የኢሲን አለቃ ኢሽቢ-ኤራ ወረረው።




#Article 195: ኔዘርላንድ (248 words)


ሆላንድ (ወይም ኔዘርላንድ ኔዘርላንድስ ኔደርላንድ፤ ሆላንድኛ፡ Nederland /ነድርላንት/) በአውሮጳ ውስጥ የሚገኝ አገር ነው።

ኔዘርላንድ ብዙ ጊዜ «ሆላንድ» ሲባል፣ ይኸው ስያሜ በትክክል ግን የአንዱ ትልቅ ክፍላገር ስም ብቻ ነው። በሆላንድኛ፣ የ«ነድርላንት» ትርጒም  «ታችኛ አገር» ሲሆን በብዙዎች ቋንቋዎች ያለው ስም ከዚህ ነው። የ«ሆላንድ» ትርጒም ደግሞ ከጥንታዊ ሆላንድኛ «ሆልት-ላንት» ማለት «እንጨት አገር» መጣ። 

የሥራ ቋንቋ ሆላንድኛ በምዕራብ ጀርመናዊ ቋንቋዎች መካከል ይቆጠራል፤ እንዲሁም በግዛቱ ውስጥ የሚነገረው ሌላ ቋንቋ ፍሪዝኛ በቅርብ ይዛመዳል። 

በሆላንድ ብዙ መስኖ፣ ቦይ ይታያል፣ ሕዝባዊ መጓጓዣ አገልግሎቱ ማለፊያ ነው። ብዙ ሕዝብ በብስክሌት ይጓዛሉ፣ ብዙ ጊዜም ይዘንባል። ብዙ ሰዎች በቡና ሱቅ ፊት ትቀምጠው ቡና ሲጠጡ ይታያሉ። ልማዳዊ አበሳሰሉ በጣም የተቀመመ አይደለም። ብዙ ታዋቂ አይቦች (ፍሮማጆ) ለምሳሌ ጉዳ ፍሮማጆ፣ ከኔዘርላንድ አሉ።

ሁለት በዓለም ዝነኛ የሆኑ የሆላንድ ሰዎች ሬምብራንት፣ የ17ኛው ክፍለ ዘመን ሰዓሊ፣ እና ቪንሰንት ቫን ጎ፣ የ19ኛው ክፍለ ዘመን ሰዓሊ፣ ናቸው። 1600ዎቹ የኔዘርላንድ ወርቃማ ዘመን ተብሏል። 

ክሪኬት የተባለው የኳስ ጨዋታ ደግሞ በሆላንድ እንደሚወድድ እንደሚጫወትም በተረፈው ዓለም ብዙ ጊዜ አይታስብም። በመላው አገር የክሪኬት ቡድኖችና ብሔራዊ አሸናፊነት ውድድር አላቸው። ሆኖም እግር ኳስ፣ ፈጣን ተሽካካሪ ጫማ ስፖርት፣ እና ሆኪ (ገና የመሰለ ጨዋታ) ደግሞ ዋና ተወዳጅ መሠረት አላቸው። 

በሆላንድ ገና፣ የክርስቶስ ልደት፣ በተለመደው ቀን ይከበራል፣ ቅዱስ ኒኮላስ ግን (ሳንታ ክሎዝ ወይም በሆላንድኛ /ስንተርክላስ/) የሚከበርበት ቀን በኅዳር 25 ወይም ከገና በፊት አንድ ወር ያህል ነው። 

አራስ ልጅ ለሚጎበኙ ሰዎች ብስኩትና የእንሶስላ ዘር በስኳር ማቅረብ ሌላ የሆላንድ ባህላዊ ልማድ ነው። ለፋሲካ በዓል ደመራዎች ይነደዳሉ፣ የንጉሡ ልደት በዓል በሚያዝያ ፲፱ ቀን ሲከበር፣ ነጋዴዎች ብርቱካን ልብስ ለብሰው በከተሞች መሃል ገበያ ያደርጋሉ።

የኔዘርላንድ መንግሥት ከኔዘርላንድ በአውሮጳ ጭምር በካሪቢያን ባህር ውስጥ ሌሎች ጥገኛ ግዛቶች አሉት፦ አሩባ፣ ኩረሳው፣ ስንት-ማርትንና ካሪቢያን ኔዘርላንድ ደሴቶች ናቸው።




#Article 196: ቡና (195 words)


ቡና የተክል አይነትና ከዚህ ተክል ቡን የሚባል መጠጥ የሚወጣው ነው። መጀመርያ የታወቀው በኢትዮጵያ ሲሆን ምናልባት በዚህ የተነሳ ቡና በተለያዩ የዓለም ቋንቋዎች ከፋ ከሚለው ስም ጋር ተቀራራቢ የሆነ ስሞች ተስጥተውት ይገኛል (ለምሳሌ እንግሊዝኛ፦ coffee /ኮፊ/ በፈረንሳይኛ ካፌ (café)በዳች ኮፊ (koffie) በእብራይስጥኛ ካፈ (ka-feh) በስዊድንኛ ካፈ (kaffe) ወዘተ ) ምናልባት ከድሮው የከፋ መንግሥት በተዛመደ መልኩ ሊሆን ይችላል። በአንድ ትውፊት መሠረት በመጀመርያ ያገኘው ሰው ካልዲ የተባለ አንድ ኢትዮጵያዊ እረኛ ፍየሎቹ ፍሬውን በልተው ሲጨፍሩ ስለተመለከተ ነበር።

የቡና የስነ ፍጥረት ስሙ Coffea arabica  (ኮፊ ኣራቢካ) ሲሆን የዚህ የኢትዮጵያ ቡና ዘር በጣዕሙ ጥሩነት የተነሳ በጣም ተወዳጅ ነው። 

በደራሲው ዊሊያም ኡከርስ መጽሐፍ 'ኦል አባውት ኮፊ' (ስለ ቡና ኅልዮ/ምንነት) እንደተገለጸው ቡና ወደ የመን የገባው በአክሱም ዘመነመንግሥት  በ517 ዓ.ም. አካባቢ ነበር።
የፋርስ ሃኪም አል-ራዚ (857-917 ዓ.ም. የኖሩ) ተክሉን «ቡንቹም» ብሎ ምናልባት በታሪክ አንደኛው ስለ ቡና መግለጫ የመዘገበው ጸሐፊ ይሆናል። ሌላ እብን-ሲና(972-1029 ዓ.ም.)የተባለ ፋርስ ሀኪም ደግሞ  ስለ «ቡንቹም» ጥቅም ጽፏል። የሞሮኮ ደርቡሽ ሼክ አቡል-ሀሳን አሽ-ሻዲሊ (1167-1250 ዓ.ም.) በአሰብ ዙሪያ ሲጓዝ ኗሪዎች ስለ ቡና መጠጥ እንደገለጹለት ይነገራል። የአደን ሙፍቲ ሼክ ጃማል-አል-ዲን አል-ዳባኒ በ1446 ዓ.ም. ገደማ ለመጀመሪያ ጊዜ መጠጡን እንዳስገባ ተመዝግቧል። በ1449 ዓ.ም. መጀመርያው ቡና ቤት «ኪቫ ሃን» በኢስታንቡል ቱርክ ተከፈተ። 

ሆኖም በ1503 ዓ.ም. የማካህ ይማሞች ቡና ቤት ስላልወደዱ መጠጡን ሃራም (እርም) አሉት

    ለጠቅላላ እዉቀት፦1ኛ(አቦል)
                2ተኛ(ሲና/ቶና)
                3ተኛ(በረካ)




#Article 197: አቤ ጉበኛ (116 words)


አቤ ጉበኛ (፲፱፻፳፭ ዓ/ም በባሕር-ዳር አካባቢ፣ ይስማላ ጎጃም ተወልደው - ፲፱፻፸፪ ዓ/ም አዲስ አበባ ላይ አረፉ።                                                               ባለቅኔ፤ ደራሲና ገጣሚ የነበሩት አቤ ጉበኛ በስድስት ዓመት ፊደል ቆጥረው ንባብ ከተማሩ በኋላ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርት ሲከታተሉ ቆዩ። ከዚያም ወደ ደንጎላ ሄደው በቢትወደድ መንገሻ ጀምበሬ ትምህርት ቤት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን አጠናቀው ወደ አዲስ አበባ በመምጣት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አጠናቀዋል።

አቤ ጉበኛ የመጀመሪያ ሥራቸው በማስታወቂያ ሚኒስቴር ሲሆን ቀጥሎም በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ተቀጥረው በመንግሥት ሥራ ለስድስት ዓመታት ያህል ካገለገሉ በኋላ ሕይወታቸውን በአብዛኛው የገፉት በደራሲነት ነው። በ1967 እ.ኤ.አ. በአዮዋ ክፍለ-ሀገር ወደ ዓለም አቀፍ የጽሑፍ ህብረት ፕሮግራም (International Writing Fellowship Program) ሄዱ። 

ከሥራዎቻቸው በከፊሉ፦

የአቤ ጉበኛ ቤተሰቦች ይስማላ ጊወርጊስ ኮረንች ባታ ጎጥ በመምትባል ቦታ ይኖራሉ
የአቤጉበኛ ትንሽ ወንድም ጌትነት አዛለ ይባላል፡፡




#Article 198: የመንግሥት ሃይማኖት (1528 words)


የመንግሥት ሃይማኖት በአንድ መንግሥት ዘንድ የተመሠረተ ሃይማኖት ወይም ይፋዊ እምነት ነው። ይህ ሲባል ግን የተመሠረተው ሃይማኖት መሪዎች የመንግሥቱ መሪዎች አይደሉም፤ እንደዚህ ከሆነ ግን ያው መንግስት «Theocracy» ይባል ነበር። 'የተመሠረተው ሃይማኖት' ማለት በመንግሥት የተደገፈው እምነት ወይም ትምህርት የሚመለከት ነው።

መንግሥት ሃይማኖቱን እስከ ምን ደረጃ ድረስ እንደሚደግፈው በየአገሩ ይለያያል። ከቃል ድገፋ ብቻ እስከ ገንዘባዊ እርዳታ ድረስ ሊሆን ይችላል። በአንዳንድ አገር ውስጥ የሌሎቹ ሃይማኖቶች ተከታዮች ነጻነት ቢያገኙም በሌላ አገር በኩል ግን ሌላ ሃይማኖት ሁሉ ይከለከላል። ወይም ተከታዮቹ ይሳድዳሉ። 

በአውሮፓ ውስጥ የካቶሊክና የፕሮቴስታንት አብያተ ክርስትያናት በ16ኛ ክፍለ ዘመን ሲወዳደሩና ሲተጋገሉ፤ መንግሥታት የመሪዎቻቸውን ምርጫ ተከተሉ፤ ይህም መርኅ በአውግስቡርግ ውል (1547 ዓ.ም.) ጸደቀ። የእንግሊዝ ንጉሥ በ1525 ዓ.ም. የፕሮቴስታንት እምነት ስለ አጸደቀ፤ በፓፓ ፈንታ የእንግሊዝ ቤተ ክርስቲያን ላይኛ መሪ እሱ ሆነ። በስኮትላንድ ግን በመቃወም የስኮትላንድ ቤተ ክርስቲያን ይፋዊ ሆነ።

አንዳንዴ፣ አንድ አገር ወይም ክፍለሀገር ልዩ ልዩ ሃይማኖቶች በገንዘብ ይደግፋል። ለምሳሌ በፈረንሳይ ውስጥ በአልሳስ-ሞዘል ጠቅላይ-ግዛት እንዲሁም በጀርመን አገር እንዲህ ይደረጋል።

በአንዳንድ ኮሙኒስት አገር በተለይ በቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ፤ መንግስት አንዳንድ ሃይማኖት ድርጅት ብቻ ይፈቀዳልና ሌሎቹ አይፈቀዱም። እንደነዚህ ባሉት አገሮች የተመረጠው ትምህርት ወይም እምነት የማርክስ ወይም የማው ጸ-ቱንግ ጽሑፎች ይሆናል።

ከመመሠረት መነቀል (Disestablishment) ማለት አንድ ሃይማኖት ወይም ቤተ ክርስቲያን የመንግስት አካል ከመሆን የሚቋረጥበት ሂደት ነው። ለምሳሌ በእንግሊዝ አገር በመጨረሻ 19ኛ ክፍለ ዘመን እንዲህ ለማድረግ የታገለ እንቅስቃሴ ቢኖርም አልተከናወነምና መቸም አልሆነም። በአይርላንድ ግን የአይርላንድ ቤተ ክርስቲያን በ1863 ዓ.ም. ከመመሠረት ተነቀለ። በ1912 ዓ.ም. ደግሞ በዌልስ ውስጥ የእንግሊዝ ቤተ ክርስቲያን ከመመሠረት ተነቀለ።

በአሜሪካ ሕገ መንግሥት (1ኛ የሕግ መለወጫ፣ 1783 ዓ.ም.) መሠረት ምንም ሃይማኖት እንዳይመሠረት በግልጽ ይከለከላል። ከዚህም ጋር መንግስት በሃይማኖቶች ጉዳይ ጥልቅ ከማለት ይከለከላል። ሆኖም የተወሰነ ክፍላገር መንግሥት የተመሠረተ ሃይማኖት ከመኖር አይከለክልም። ለምሳሌ ኮነቲከት እስከ 1810 ዓ.ም. ድረስ ይፋዊ ቤተ ክርስቲያን ነበረው፤ ማሳቹሰትስም እስከ 1825 ዓ.ም. ድረስ ይፋዊ ቤተ ክርስቲያን ነበረው።

ዛሬ የአሜሪካ ክፍላገሮች ሁሉ ለኗሪዎቻቸው የሃይማኖት ነጻነት ያረጋግጣሉ። ከነዚህም መካከል 8ቱ እነሱም አርካንሳው፣ ሜሪላንድ፣ ማሳቹሰትስ፣ ስሜን ካሮላይና፣ ፔንስልቬኒያ፣ ደቡብ ካሮላይና፣ ተነሲና ቴክሳስ፤ እምነተ ቢስ ሰው ከመሾም ቢከለክሉም ይህ አይነት ሕግ ግን አሁን (ከ1953 ዓ.ም. ጀምሮ) ተግባራዊ ሆኖ አይቆጠረም።

የሚከተሉት መንግስታት የክርስትና ቤተ ክርስቲያን ዓይነት በየአይነቱ መሠርተዋል።

እነዚህ አገራት ወይም ክፍላገራት የሮማ ካቶሊክ ሃይማኖት በይፋ አላችው።

እነዚህ መንግሥታት የምስራቅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አይነት በይፋ አሏቸው።

እነዚህ መንግሥታት የሉተራን ቤተክርስቲያን አይነት በይፋ አላቸው።

ይህ መንግሥት የአንግሊካን ቤተክርስቲያን አይነት በይፋ አለው።

እነዚህ መንግሥታት የተሐድሶ ቤተክርስቲያን አይነት በይፋ አላቸው።

እነዚህ መንግሥታት 'ጥንታዊ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን' የተባለው አይነት በይፋ አላቸው።

(በነዚህም 3 ውስጥ የሮማ ካቶሊክና የተሐድሶ አይነቶች አብረው ይፋዊ ናቸው)

የሚከተሉት መንግስታት የእስልምና ዓይነት በይፋ መሠርተዋል።

የሚከተሉት መንግስታት የቡዳ ሃይማኖት ዓይነት በይፋ መሠርተዋል።

ከአገራት ኔፓል ብቻ የሕንዱ ሃይማኖትን በኦፊሴል ይዞ ነበር። በ1998 ዓ.ም ግን፣ በአመጻዎች ችግር ምክንያት ይህ ሁኔታ ተለውጦ እምነቱ ከመመሰረት ተነቀለ።

በእስራኤል ሕገጋት መሠረት አገሩ 'የአይሁድ አገር' ይባላል። ይሁንና 'አይሁድ' የሚለው ቃል ሃይማኖት ብቻ ሳይሆን አንድ ዘር ወይም ወገን ማለት ደግሞ ሊሆን ይችላል። ስለዚህ አይሁድና ምን ማለት እንደሚሆን ለአገሩ ክርክር ሆኗል። አሁን እስራኤል አንዳንድ ተቋም በተለይም የኦርቶዶክስ አይሁድ ተቅዋማት ይደግፋል፤ ከዚህም በላይ የኦርቶዶክስ አይሁድ፣ የእስላም፤ የክርስቲያንና የድሩዝ ችሎቶች ይፈቅዳል።

በጥንት ሱመር መንግሥታት የመንግስት ሃይማኖት ጽንሰ ሀሣብ ይታወቅ ነበር። እያንዳንዱ ከተማ-አገር ወይም ሕዝብ የራሱን አማልክት ወይም ጣኦት ይኖሩት ነበር። የድሮ ሱመር አለቆች ብዙ ጊዜ የከተማቸውን አምላክ ያገለገሉ ቄሶች ማዕረግ ደግሞ ነበራቸው። በኋላ ዘመን እንዲሁም የባቢሎንና የአሦር መንግሥታት ሃይማኖት አረመኔ ነበር።

የጥንታዊ ግብጽ መንግሥት ሃይማኖት እንደ መስጴጦምያ ባሕል በብዙ አማልክትና ጣኦት ያመነ አረመኔነት ነበር። ንጉሥ ወይም ፈርዖን በመጀመርያ እንደ አምላካቸው ሔሩ ትስብዕት ይቆጠር ነበር፣ በኋላ ሌሎችም አማልክት ከዘመን ወደ ዘመን ይመርጡ ነበር። ከ1357 እስከ 1338 ዓክልበ ድረስ የፀሐይ ጣዖት አተን አምልኮት ብቻ ወይም ሞኖቴይስም የግብጽ መንግሥት ሃይማኖት ሆነ፤ ከዚያ ወደ በፊቱ ፖሊቴይስም እምነት ተመለሰ።

የእስራኤል አስተያየት ከጎረቤቶቿ ከባብሎን ከግብጽና ከግሪክ ባህሎች እጅግ ተለየ። ቅዱስ መጻሕፍታቸው እንደሚገልጹ፣ እምነታቸው በአንድ አምላክ ድርጊቶች በታሪካዊ ዜና መዋዕል ውስጥ የጸና እንጂ እንደ ጎረቤቶቿ በልዩ ልዩ አማልክት አፈ-ታሪካዊ ዠብዱዎችና ውድድሮች አልተመሠረተም ነበር። እነዚህ መጻሕፍት የዛሬው ብሉይ ኪዳን (ታናክ) ናቸው።

ሰዎቹ በብዙ አማልክት ቢያምኑም እያንዳንዱ ጥንታዊ ግሪክ ከተማ የገዛ ዐቃቤ አምላኩ ነበረው። እንዲሁም የአቴና አምላክ አቴና ነበረች፤ የስፓርታም አርቴሚስ፣ የዴሎስ አፖሎ፣ የኦሊምፒያ ዜውስ ነበሩ።

ከጥንት ጀምሮ በሮማውያን አረመኔ እምነት ገዢዎቹ የሲቢሊን መጻሕፍትን እንደ ቅዱሳን ጽሑፎች ለትንቢቱ ይመከሩ ነበር። 

በሮማ መንግሥት ከአውግስጦስ ጀምሮ ላይኛ ቄስ የተባለው ቄሳር ወይም ንጉሡ ነበረ። ብዙ ጊዜ ንጉሡ በትእቢቱ ብዛት እኔ አምላክ ነኝ በግልጽ ያዋጅ ነበር። በአንዳንድ ወቅት ደግሞ ለንጉሡ ካልጸለዩ ይሙት በቃ በሕዝብ ላይ ደረሰባቸው። በዚህ ዘመን ብዙ ክርስቲያኖችና አይሁዶች ለሮማ ንጉስ አንጸለይም ብለው ተገደሉ።

በ303 ዓ.ም. ንጉሡ ጋሌሪዎስ አልጋ ላይ ወድቆ ትንሽ ሊያርፍ ሲል በመንግሥቱ ግዛት ውስጥ ላሉት ክርስቲያኖች ሁሉ ይቅርታ ሰጠ። ከዚህ በፊት የክርስትናን ሃይማኖት ለማጥፋት በሙሉ ሞክሮ ነበር። ከዚያ ሁለት የጋርዮሽ ቄሣሮች 1ኛ ቆስጠንጢኖስ እና ሊቂኒዎስ በ305 ዓ.ም. የሚላኖ አዋጅን አወጡ። ይህ ህግ ለሰው ሁሉ የሃይማኖት ነጻነት በማረጋገጥ የክርስቲያኖች መሬት ያለ ገደብ እንዲመልስላቸው የሚያዝዝ ነበር።

በ317 ዓ.ም. ቆስጠንጢኖስ የኒቂያ ጉባኤ ጠሩ። ቢባልም ለብዙ አመታት ከዚህ በኋላ በጥምቀት እንዳልገቡ መገንዘብ ይረዳል። አሁን ክርስትና በሮማ ውስጥ በይፋ የመንግሥት ሃይማኖት ባይሆን በብዙዎች ሕዝብ በግልጽ ይከተል ጀመር። በዚህ ዘመን አካባቢ ግን የሮማ መንግሥት ጎረቤቶች የነበሩት የአክሱም መንግሥትና አርሜኒያ ከነገስታታቸው ጥምቀት አንስቶ በይፋ ወደ ክርስትና ገብተው ነበር። 

ለጥቂት ጊዜ ከ353 እስከ 355 ዓ.ም. ድረስ የሮማ ንጉሥ ዩሊያኖስ ከሐዲ መንግሥቱን ወደ ድሮ አረመኔ እምነት መለሠው። ተከታዩ ግን ክርስቲያን በመሆኑ አገሩን ወደ ክርስትና ፕሮግራም መለሰ።

በመጨረቫ በ372 ዓ.ም. የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በንጉሡ 1ኛ ቴዎዶስዮስ አዋጅ መሠረት የሮማ መንግስት ሃይማኖት በይፋ ተደረገ።

የሳሳኒድ መንግሥት (218-643 ዓ.ም.) ይፋዊ ሃይማኖት የዞራስተር (ዛራጡሽትራ) ሃይማኖት ነበር። ፋርስ ከ643 ዓም ጀምሮ እስላማዊ ሲሆን በስሜን በቀድሞው ሂርካኒያ በኋላ ታባሪስታን በተባለው ክፍላገር በጥቃቅን መንግሥታት መኃል፣ የዞራስተር እምነት እስከ 1399 ዓም ድረስ በይፋ ተቀጠለ።

አዲያቤኔ የተባለ በስሜን ሜስጶጦምያ የነበረ ሌላ ትንሽ መንግስት ደግሞ በ26 ዓ.ም. አይሁድናን ተቀበለ። ጎረቤታቸውም በሶርያ የተገኘው የኦስሮኤና መንግሥት በዚያን ጊዜ ክርስትናን እንደ ተቀበለ ይባላል።

በሕንድ አገር የሠፈሩት ሕዝቦች በብዛት ድራቪዳውያንና አርያኖች ሲሆኑ፣ እነዚህም መጀመርያ የየራሳቸውን እምነቶች ቢኖራቸውም፣ ሁለቱ በታሪክ ላይ ከመቀላቀላቸው የተነሣ አንድላይ የሂንዱ ሃይማኖት ሠርተዋል። በሕንድ አገሮች ከጥንት ጀምሮ የቄሳውንት መደብ ወይም ብራህማኖች የተከበሩ ባለሥልጣናት ነበሩ። 

በኋለኛ ዘመን የአንዳንድ ብሔር ገዢ ለአዳዲስ ሃይማኖቶች ቡዲስምና ጃይኒስም ተከታዮች ሆኑ። በጎታማ ቡዳ ሕይወት ዘመን የማጋዳ መንግሥት ንጉሥ ቢምቢሳራ (550-500 ዓክልበ. ግድም የገዛ) የቡዳ ምእመን እንደሆነ ይባላል፤ ሆኖም በጃይኒስም ዘንድ ይሄው ንጉሥ የጃይኖች አስተማሪ የማሃቪራ ተከታይ ነበር እንጂ። የማጋዳ ገዦች ከዚያ ወይም ቡዲስም ወይም ጃይኒስም እንደ ደገፉ ግልጽ ባይሆንም፣  በሚከተለው ማውርያ መንግሥት ንጉሦቹ መጀመርያ (ከ330 ዓክልበ. ጀምሮ) የሕንዱ (ብራህማኒስም) ደጋፊዎች ይመስላሉ። መጀመርያው ማውርያ ንጉሥ ቻንድራጉፕታ የጃይን ተከታይ እንደ ሆነ ዙፋኑን ለልጁ ቢንዱሳራ ተወ፤ ቢንዱሳራ ግን አጂቪካ የተባለውን የሕንዱ ፍልስፍና ደጋፊ ነበር። በቢንዱሳራ ልጅ አሾካ ዘመን የአሾካ አዋጆች ከ264 ዓክልበ. ጀምሮ ቡዲስምን በሕንድ የመንግሥት ሃይማኖት አደረገው። ነገር ግን ከ232- 210 ዓክልበ. የገዙት ተከታዮቹ እንደገና የጃይኒስም ደጋፊዎች ነበሩ። ከ193 ዓክልበ. በሚከተለው ሹንጋ መንግሥት ግዛቱ ከቡዲስም ወደ ሒንዱ ሃይማኖት ተመለሠ። በዚህ ዘመን ደግሞ የካሊንጋ ገዢዎች በተለይም ኻራቬላ (100 ዓክልበ. ግድም) የጃይኒስም ደጋፊዎች እንደ ነበሩ ይመስላል።

በኋላ በሕንድ ከነበሩት የጃይኒስም መንግሥታት፣ ምዕራብ ጋንጋ ከ300-1000 ዓም ግድም፣ ካናውጅ 740-825 ዓም ግድም፣ ራሽትራኩታ 806-870 ዓም፣ ሆይሳላ 1018-1100 ዓም፣ እና ጉጃራት ከ1144-1164 ዓም ይጠቀሳሉ። 

እንደገና በስሜን ከ598 እስከ 637 ዓም በሕንድ የገዛ ንጉሥ ሃርሻ ቡዲስምን ደገፈ። ከዚያ ከ742 እስከ 1150 ዓም ግድም የቆየው የፓላ መንግሥት ደግሞ ቡዲስት ነበረ። ይህ በሕንድ መጨረሻው ቡዲስት መንግሥት ነበር።

ከ1183 ዓም ጀምሮ እስላም መንግሥታት በጥልቅ ወደ ሕንድ አገር ወርረው በተለይ የደልሂ ሡልታናት (1198-1518 ዓም) እና የሙጋል መንግሥት (1518-1849 ዓም) በሠፊው በሕንድ ገዙ። ከ1666-1810 ዓም  የገዛው የማራጣ መንግሥት የሒንዱ መንግሥት ነበረ።   በተጨማሪ ከ1791 እስከ 1841 ዓም ድረስ በፑንጃብ አካባቢ የኖረው ሲኽ መንግሥት በአዲሱ ሲኽ ሃይማኖት ተጀመረ።  በ1800ዎቹ  ዓም እነዚህ ሁሉ በእንግሊዞች ተሸንፈው ሕንድ አገር ለጊዜው የዩናይትድ ኪንግደም ቅኝ አገር ነበረች፤ ከ1939 ዓም ጀምሮ ነጻንቱን አገኝቶ በይፋ የመንግሥት ሃይማኖት ባይኖርም የሂንዱ ሃይማኖት ይደገፋል።

በጥንታዊው ዘመን የቻይና እምነት የወላጆችና አያቶች አምልኮትና ሻማኒስም ነበረ። ፈላስፋው ኮንፉክዩስ (ወይም ኮንግፉጸ፣ 559-487 ዓክልበ.) የመሠረተው እምነት  ወይም ፍልስፍና ከ148 ዓክልበ. ጀምሮ በይፋ በሃን ሥርወ መንግሥት ተከተለ።  ወደ ማዕረግ ለመሾም ዕጩዎቹ በዚህ እምነት መጻሕፍት ይፈተኑ ነበር። 

በዚህ መንግሥት መጨረሻ (212 ዓ.ም.) ከተከተሉት ተወዳዳሪ ክፍላገራት መሃል፣ አንዳንዱ የሌላ ቻይናዊ ሃይማኖት የዳዊስም ደጋፊ ነበረ፤ በተለይ ከ207 እስከ 252 ዓም የነበረው ወይ መንግሥትና ከ416 እስከ 444 ዓም ድረስ ስሜን ወይ በይፋ ዳዊስት መንግሥታት ነበሩ። ከዚያ በኋላ ግን ስሜን ወይ ወደ ቡዲስም ተለወጠ። በደቡቡ ቻይና ደግሞ ንጉሦች ዉ ልያንግ ከ509-541 ዓም እና ዉ ቸን 549-551 ዓም በተለይ ቡዲስቶች ነበሩ።  መላው ቻይና በ571 ዓም በሱዊ ሥርወ መንግሥት እንደገና ሲዋሀድ የመንግሥት ሃይማኖት ቡዲስም ሆነ። የሚከተለው ታንግ ሥርወ ነግሥት ግን ከ610-682 እና ከ697-899 ዓም ወደ ዳዊስም ተመለሠ፤ ከ682-697 ዓም የገዛች ንግሥት ግን ቡዲስት ነበረች።

ከዚህ በኋላ በልያው ሥርወ መንግሥት 899-1117 ዓም፣ ጂን ሥርወ መንግሥት 1107-1226 ዓም፣ በምዕራብ ሥያ 1030-1219 ዓም እና የሞንጎሎች ንጉሥ ኩብላይ ኻን በመሠረተው ይዋን ሥርወ መንግሥት ውስጥ (1261-1360 ዓም) ቡዲስም እንደገና የመንግሥት ሃይማኖት ሆነ። ከ1360 እስከ 1903 ዓም ድረስ የነበሩት መንግሥታት እንደገና የኮንፉክዩስን ትምህርት ደገፉ፤ ከ1903 ዓም ጀምሮ እስካሁን የነበሩትም ከተመሠረተ ሃይማኖት ተነቅለዋል።

በቲቤት፣ የቲቤት መንግሥት ጥንታዊው ኗሪ እምነት «ቦን» የሚባል ሃይማኖት ሲሆን፣ በተለይ ከ610-642 ዓም፣ ከ753-832 ዓም እና ከ950 ዓም ጀምሮ ቡዲስት ነበር።

የጃፓን ድሮ መንግሥት ሃይማኖት ሺንቶ ሲባል በ579 ዓም የጃፓን መንግሥት ቡዲስም ደግሞ ተቀበለ። ሁለቱ ሃይማኖቶች ሲደገፉ በብዙ ታሪካዊ ረገዶች ይቀላቅሉ ነበር። ከ1860 እስከ 1937 ዓም ግን የመንግሥት ሃይማኖት ሺንቶ ብቻ ተደረገ፤ የቡዲስም ተጽእኖ ለማስወገድ እርምጃ ወሰደ። ከ1937 ዓም ጀምሮ የምንግሥት ሃይማኖት ባይኖርም፣ ሺንቶና ቡዲስም እስካሁን በሕዝቡ ዘንድ ዋና እምነቶች ሆነው ቆይተዋል።

በ1959 ዓ.ም. የአልባኒያ መንግስት በይፋ ከሃዲነት «የመንግስት ሃይማኖት» አደረገና ሃይማኖቶች ሁሉ ከለከለ። ይህ ሁኔታ እስከ 1983 ዓ.ም. ድረስ ቆየ። 

የፊንላንድ ብሔራዊ ቤተክርስቲያን እስከ 1801 ዓ.ም. ድረስ የስዊድን ቤተክርስቲያን ነበረ። ከ1801 እስከ 1909 ዓ.ም. ድረስ ፊንላንድ የሩስያ ቅኝ አገር ስትሆን የተለየ የፊንላንድ ወንጌላዊ ሉተራን ቤተክርስቲያን በሩሲያ መንግስት በፊንላንድ ተመሰረተ። በ1911 ዓ.ም. ሕገ መንግሥት መሠረት ከፊንላንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጋር የጋርዮሽ ብሔራዊ ቤተክርስቲያን ነው። 

በፈረንሳይ ውስጥ በ1793 ዓ.ም. ስምምነት መሠረት የሮማ ካቶሊክ፣ የካልቪናዊ፣ የሉተራንም ቤተክርስቲያኖች እንዲሁም አይሁድና ሁሉ በመንግሥት የተደገፉ ሆኑ። በ1897 ዓ.ም. መንግሥት ከሃይማኖት ግን ተለየ። 

በሀንጋሪ የ1840 ሕገ መንግሥት መሠረት አምስት የጋርዮሽ አብያተ ክርስቲያናት ተመሰረቱ፤ እነሱም የሮማ ካቶሊክ፣ የካልቪናዊ፣ የሉተራን፣ የምስራቅ ኦርቶዶክስና የዩኒታሪያን ቤተክርስቲያኖች ናቸው። በ1887 ዓ.ም. አይሁድና ስድስተኛ የተምሰረተ እምነት ሆነ። በ1940 ዓ.ም. ግን የሀንጋሪ መንግሥት ሃይማኖቶቹን ሁሉ መለየት ተወ።




#Article 199: ግብረ ስጋ ግንኙነት (2515 words)


ግብረ ስጋ ግንኙነት ወይም ሩካቤ ስጋ ማለት በሴትና በወንድ መካከል ለስሜት እርካታ የሚደረግ ግንኙነት ወይም ፍቅር መሥራት ነው። ይህም ለመባዛት ወይም ለመዋለድ አስፈላጊ ከመሆኑ በላይ የወሲብን እርካታዊ ፍላጎት ለማሟላት ሊሆን ይችላል። 

በሥነ ሕይወት ዘርፍ ሲታይ ወሲብ፣ የእንስትን (ሴትን) እና የተባእትን (ወንድን) ዘር በማዋሃድ ወይንም በማዳቀል፣ የፍጡራን ዝርያ (species)፣ ከአሮጌ ወደ አዲስ እየታደስ፡ በቅጥልጣይ ረገድ ለረዥም ጊዜ እንዲቆይ የሚያስችል፣ ተፈጥሮ የቸረችው ተፈጥሯዊ ተግባር ነው።  በእያንዳንዱ የፍጡር ዝርያ ተባእትና እንስት ፆታዎች ይገኛሉ። እነዚህ ፆታዎች በየራሳቸው ዘርን ማስተላልፍ የሚችሉብት ልዮ የማዳቀያ ህዋሳትን በአካላቸው ወስጥ ይሠራሉ ወይንም ያዘጋጃሉ።  እነዚህ ልዮ ህዋሳት 'ጋሜት' (gametes) በመባል ይታወቃሉ። እነዚህ ልዩ ህዋሳት በአካልቸው ተመሳሳይ (በተለይ isogametes በመባል የሚታወቁት) ሊሆኑ ቢችሉም፣ ነገር ግን በአብዛኛው ጊዜ ከተባእትና እንስት የሚገኙት የዘር ህዋሳት በቅርፃቸውም ሆነ በአኳኋናቸው ይለያያሉ።  የወንዱ የዘር ህዋስ፣ ም'ጥን ያለና በትንሽ ይዘት ብዙ ዘራዊ ምልክቶችን ማጨቅ እንዲችል ሆኖ የተሠራ ሲሆን፣ ይህንንም ይዞ ረጅም ርቀት መጓዝ እንዲችል የፈሳሽ ውስጥ ተስለክላኪነት ባህርይ ወይንም ችሎታ አለው።  የሴቷ ልዩ ህዋስ፣ ከወንዱ ህዋስ ጋር ሲስተያይ በአካሉ አንጋፋ ሲሆን፣ ይህ የሆነበትም ምክንያት ተንቀሳቃሽ ሳይሆን የረጋ ከመሆኑም ሌላ፣  ከተባእት ዘር ጋር ከተገናኘ በኋላ በውስጡ ለሚፈጠረው ሽል አስፈላጊውን የማፋፊያ ንጥረ ነገር መያዝ ስላለበት ነው። 

የአንድ ፍጡር ፆታ የሚታወቀው በሚፈጥረው የዘር ህዋሥ አይነት ነው። ተባእት ፍጡራን የተባእትን የዘር ህዋሥ (spermatozoa, or sperm) ሲፈጥሩ፣ እንሥት ፍጡራን የእንሥትን የዘር ህዋሥ (ova, or egg cells) ይፈጥራሉ።  
የተወሰኑ ዝርያዎች፣  የተባእትንም የእንስትንም የዘር ህዋሥ ከአንድ ግላዊ አካል የሚያፈልቁ ሆነው ይገኛሉ።  እነዚህ ፍናፍንት (hermaphroditic) በመባል ይታወቃሉ።

አብዛኛውን ጊዜ የአንድ ዝርያ ተቃራኒ ፆታዎች፣ የተለያየ የአካል ቅርፅና የባህርይ ገጽታ ይታይባቸዋል።  ይህ ልዩነት ሁለቱ ፆታዎች ያለባቸውን የእርባታ ኃላፊነትና የሚያስከትለውን አካላዊ ተፅእኖ ያንፀባርቃል።

ይህ ተግባር፣ ከላይ እንደተጠቀሰው፣ የእንስትና የተባእትን ዘር በማዋኃድ ወይንም በማዳቀል፣ ፍጡራን ዝርያ (Species)፣በተዋልዶ ከአሮጌ ወደ አዲስ እየተታደስ፡ በቅጥልጣይ ረገድ ለረዥም ጊዜ እንዲቆይ የሚያስችል፣ ተፈጥሯዊ ተግባር ነው። በዘር ሀዋሣት ውህደት ወቅት ክሮሞሶም (Chromosomes) ከአንዱ ለጋሽ (ወላጅ) ወደሌላው ይተላለፋል። እያንዳንዱ ተሣታፊ ህዋሥ የለጋሾችን ግማሽ ክሮሞሶም ይይዛል።  ግማሽ የአባት፣ ግማሽ የእናት ክሮሞሶሞች ተገናኛተው ይዋሃዳሉ ማለት ነው።  ተወራሽ የዘር ምልክቶች፣ ዲ-አክሲ-ሪቦ-ኒውክሊክ አሲድ ወይንም ዲ-ኤን-ኤ (deoxyribonucleic acid (DNA)) በመባል በሚታወቀው፣ በክሮሞሶሞች ውስጥ የሚገኝ ንጥረ ነገር ውስጥ ሰፍረው ይገኛሉ።  ይህ ውህደት ክግማሽ የአባት፣ ክግማሽ የእናት ክፍል የተስራ የክሮሞሶም ጥማድ ይፈጥራል።  ክሮሞሶሞች በጥንድ ሆነው በሚገኙበት ጊዜ ዳይፕሎይድ (diploid) ይባላሉ። ክሮሞሶሞች በአሃዳዊ ህላዌ ጊዜ ሃፕሎይድ (haploid) ይባላሉ።  ዳይፕሎይድ የሃፕሎይድ ህዋስን (ጋሜት (gametes)) መፍጠር ይችላሉ።  ይህ የሃፕሎይድ ጥንሰሳ ሂደት ሚዮሲስ (meiosis) በመባል ይታወቃል። ሚዮሲስ የሚባለው ሂደት የክሮሞሶማዊ ቅልቅል (chromosomal crossover) ሁኔታን ሊፈጥርም ይችላል።  ይህ ሁኔታ መሳ በሆኑ ክሮሞሶምች መካከል የሚፈፀም ሲሆን፣ የክሮሞሶሙ ዲ-ኤን-ኤ ከባቢ ተቆርሶ ከሁለተኛው ክሮሞሶም ዲ-ኤን-ኤ ከባቢ ጋር ይዋሃዳል። ተራፊዎቹ ዲ-ኤን-ኤ እርስ በርሳቸው ባኳያቸው ይዋሃዳሉ።  ውጤቱም በባህርይ ከበኩር ዳይፕሎይድ የተለየ አዲስ ዳይፕሎይድ መፍጠር ነው።  ይህ የክሮሞሶም ቅልቅል ሂደት ከለጋሽ ወላጆች በተፈጥሮ ባህሪው የተለየ አዲስ ዝርያ (Species) ይከስታል።

በብዙ ፍጡራን የርቢ ሂደት ውስጥ የሀፕሎይድ ክስተት፣ ጋሜት በመፍጠር ላይ ብቻ ያተኮረ ነው።  በዚህ ሁኔታ የሚገኙት ጋሜት እርስ በርሳቸው በመቀላቀል ዳይፕሎይድ መከሰት እንደሚችሉ ሆነው የተዘጋጁ ናቸው።  እንዲሁም በሌሎች ፍጡራን ርቢ ጊዜ ጋሜት ራሳቸውን በመክፈል አዲስና ልዩ ልዩ የአካል ህዋሣትን መፍጠር ይችላሉ። እነዚህ በዚህ ሁኔታ የሚፈጠሩ የአካል ህዋሣት ሃፕሎይድ ክሮሞሶም ይኖሯቸዋል።  በሁለቱም በኩል የሚገኙት ጋሜት በውጭ አካላቸው ተመሣሣይነት ያሳያሉ። ሆኖም ግን በአካላቸው የማይመሳሰሉ ጋሜት ይገኛሉ።  በተለምዶ ተለቅ ያሉት ጋሜት የእንስት ህዋስ (ovum, or egg cell) ሲሆኑ፣ አነስ ያሉት ደግሞ የተባእት ህዋስ (spermatozoon, or sperm cell) ናቸው።  በአካል መጠን ተልቅ ያለ ጋሜት የሚያመነጭ ግለፍጡር የእንስትነትን ፆታ ይይዛል፣ እንዲሁም አነስ ያለ ጋሜት የሚያመንጭ ግለፍጡር የተባእትን ፆታ ይይዛል።   ሁለቱንም አይነት ጋሜት በአካሉ ውስጥ የሚያመነጭ ግለፍጡር ፍናፍንት (hermaphrodite) ይባላል።  በአንዳንድ ሁኔታ hermaphrodite ራሳቸውን በራሳቸው በማዳቀል፣ ያላንዳች ወሲባዊ ጓደኛ አዲስ አካል (ፅንሥ) መፍጠር ይቸላሉ ። 

አብዛኞቹ የወሲባዊ ተራቢ እንስሳት እንድሜያቸውን የሚያሳልፉት በዳይፕሎይድነት ነው። በነዚህ እንሥሣት ውስጥ የሃፕሎይድ መኖር ጋሜትን ለመከሰት ብቻ የተዋሰነ ነው።  የእንስሳት ጋሜት የእንስትና የተባእት ህላዌ አልቸው። እነዚሀም የተባእት ህዋስ እና የእንሥት ህዋስ (spermatozoa and egg cells) የሚባሉት ናቸው። ጋሜት  በእንስቷ አካል ውስጥ በመዳቀል (በመዋኃድ) ከወላጅ ለጋሾች ዘር የተዋጣና፣ የታደስ አዲስ ፍጡር ወይንም ፅንስ (embryo) ይፈጥራሉ። 

የወንዱ ጋሜት፣ የተባእት የዘር ህዋሥ (spermatozoan) በወንዱ ቆለጥ ወስጥ የሚጠነሰስ ሆኖ፣ በመጠኑ አነስተኛና በፈሳሽ ውስጥ ለመስለክለክ የሚያስችለው ጭራ አለው። ይህ የዘር ህዋስ ከሌሎች የአካል ህዋሳት ጋር ሲነፃፀር አብዝኛዎቹ መደበኛ ህዋሳዊ ክፍሎች የተሟጠጡበትና፣ ለፅንሥ ምስረታ ብቻ የሚያስፈልጉ ነግሮችን የያዘ ህዋስ ነው።  የህዋሱ አካላዊ ቅርፅ፣ በፈሳሽ ውስጥ በፍጥነትና በቀላሉ እንዲጓዝ የተገነባ ነው። 

የእንስት የዘር ህዋስ ፍሬያዊ ወይንም የእንቁላል ህዋስ ሲሆን በእንስቷ ማህፀን ውስጥ፣ እንቁላል እጢ ወይንም እንቁልጢ(ovaries) በሚባሉ ቦታዎች ውስጥ የሚጠነሰስ ነው።  ይህ የዘር ህዋስ፣ ከተባእት የዘር ህዋስ ጋር ሲነጻጸር በአካሉ ትልቅ ሲሆን፣ የእንቁላል ወይንም የፍሬ ቅርፅ ይኖረዋል። በውስጡም ለመጸነሻ የሚያስፈልጉ የዘር ክሮሞሶሞችና፣ ጽንሱም ከተፈጠረ በኋላ አስፈልጊ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን ከሚይዙ ክሌሎች ህዋሳት ጋር የተቆራኘ ሆኖ ይገኛል ።  ሁሉም በአንድ እሽግ እንቁላል ውስጥ ይገኛሉ።  
የአጥቢ እንሥሣት ፅንስ በእንስቷ ውስጥ ለውልድ እስኪበቃ ድረስ ያድጋል። የሚያስፈልጉትን ንጥረ ነገሮችም ከእናቲቱ አካል በቀጥታ ይካፈላል።

እንሥሣት በአብዛኛው ተንቅሳቃሽ ሲሆኑ፣ የወሲባዊ ጓደኛ ወይንም አጣማጅ ይፈልጋሉ፣ ያስሳሉ።  አንዳንድ በውሃ ውስጥ ይሚኖሩ እንሥሣት ውጫዊ ድቅለት (external fertilization) የሚባለውን ይጠቀማሉ። በዚህ ጊዜ የንእንስቷ እንቁላሎችና የተባእቱ የዘር ህዋስ ውኃው ውስጥ አንድ ላይ ተለቀው እንዲቀላቀሉ ይደረጋል። በመሬት ላይ የሚኖሩ እንሥሣት ግን የወንዱን የዘር ህዋሳት ወደሴቷ ሰውነት የማስተላልፍ ዘዴ ይጠቀማሉ። ይህ ውስጣዊ ድቅለት (internal fertilization) ይባላል። 

አእዋፍ፣ አብዛኞቹ ለሠገራ፣ ለሽንት እንዲሁም ለመዳቀል የሚጠቀሙበት አንድ ብቸኛ ቀዳዳ አላችው።  ይህ ሬብ (cloaca) ይባላል። ተባእትና እንስት አእዋፍ፣ ሬባቸውን በማገናኘት ወይንም በማጣበቅ የወንዱን ነባዘር (sperm) ያስተላልፋሉ። ይህ ሬባዊ ጥብቀት (cloacal kissing) በመባል ይታወቃል። አብዛኞቹ የመሬት ላይ እንሥሣት የወንዱን ነባዘር ለማስተላለፍ ይሚጠቅም ብልት ይኖራቸዋል።  ይህ ብልት፣ ተስኪ ብልት (intromittent organ) በመባል ይታወቃል።  በሰብአውያንና በአጥቢ እንሥሣት ውስጥ ይህ ብልት፣ ቁላ ተብሎ የሚታወቀው ነው።  ይህ ብልት በእንስቷ የድቅያ ቀጣና (እምሥ) ውስጥ በመግባት የወንዱን ነባዘር ያፈሳል። ይህ ሂደት ወሲባዊ ግንኙነት (የግብረ ሥጋ ግንኙነት) ይባላል።  የወንዱ ብልት፣ የወንዱ ነባ ዘር የሚያልፍበት የራሱ ቀጣና ይኖረዋል።  የእንስት አጥቢ እንሥሣት ወሲባዊ ብልት (እምሥ) ከማህፀኗ ጋር የተገናኘ ነው።  የሴቷ ማህፀን ፅንሱን በውስጡ በማቀፍ አስፈላጊ ንጥረ ነገሮችን ከሴቷ አካል እያንቆረቆረ፣ አቅፎ ጠብቆ ለውልድ እስኪበቃ ያሳድገዋል። ይህ ሂደት እርግዝና  ይባላል። 

በተንቀሳቃሽነታቸው ምክንያት፣ የአንዳንድ እንሥሣት ድቅለት የግዳጅ ወሲብን ይከስታል።  አንዳንድ ነፍሳት ለምሳሌ፣ የእንስቷን ሆድ በመቅደድ ወሲብ ያካሂዳሉ።  ይህ እንስቷን የሚያቆስል ብቻ ሳይሆን፣ የሚያሰቃይ ነው።

እንደ እንሥሣት፣ ዕፅዋትም የእንስትና የተባእት የዘር ህዋስ (gamete) ያመነጫሉ።  ብዙ ታዋቂ የሆኑ ዕፅዋት የሚያመነጩት ተባእታይ የዘር ህዋስ በቅርፊት የታቀፈ ሆኖ በናኒ ወንዴዘር(pollen)ይባላል።  

የእፅዋት እንሥት የዘር ህዋስ በኦቭዩል ውስጥ የሚገኝ ነው። ይህ እንስታይ ህዋስ፣ በወንዱ ወንዴዘር ከተደቀለ በኋላ የእፁን ዘር (seed) ያመነጫል።  ይህ ዘር እንደ እንቁላል በውስጡ ለሚፈጠረው ፅንሥ አስፈላጊ ንጥረ ነገር ይይዛል።

 እንስት (በግራ) እና ተባእት (በቀኝ) ሆነው የሚታዩት ፍሬ መሰሎች፣ የዝግባና የመሳሰሉት ስርክ-አበብ ትልልቅ ዛፎች የሴትና የወንድና ወሲባዊ ብልቶች ናቸው 

ብዙ ዕፅዋት አ'ባቢዎች ናቸው፣ ማለትም አበቦችን ያወጣሉ። አበቦች የዕፅዋቱ ወሲባዊ ብልቶች ናቸው።  አበቦች አብዛኛውን ጊዜ ፍናፍንት (hermaphroditic) በመሆናቸው፣ የሁለቱንም ፆታዎች (የወንድና የሴት) የዘር ህዋሳት ይይዛሉ።  በአበባው መሃል ካርፔል (carpel) ይገኛሉ። ከነዚህ አንዱ ወይንም በዛ ያሉት ተጣምረው ፒስቲል (pistil) ይሰራሉ።  በፒስቲል ውስጥ የእንስት ፍሬ ወይንም ዘር ማመንጫ ኦቭዩል (ovule) ይገኛሉ። ኦቭዩል ከተባእት የዘር ሀዋስ ጋር ሲዳቀሉ ዘር (seed) ያመነጫሉ።  የአባባው ተባእት ክፍሎች ስቴምን (stamen) ይባላሉ። እነዚህ ጭራ መሰል ተርገብጋቢዎች በአባባው ዛላና (petal) በፒስቲል ውጫዊ ዙሪያ የሚገኙ ሲሆኑ፣ ጫፋቸው ላይ በውስጣቸው የተባእትን የዘር ህዋስ የሚይዙ የንፋስ በናኒዎች ወንዴዘር(pollen) ማመንጫ ክፍሎች አሏቸው። አንድ የወንዴዘር ረቂቅ በካርፔል ላይ ሲያርፍ፣ የእፁ ውስጣዊ ክፍል እንቅስቃሴ በማድረግ ረቂቁን በካርፔል ቀጣና ውስጥ በማሳለፍ ከኦቭዩል ውስጥ እንዲገባና እንዲዋሃድ ይደረጋል።  ይህ ውህደት ዘር (seed) ይፈጥራል።

ዝግባና መስል ሰርክ አበብ ዛፎች አና ዕፅዋት፣ የተባእትና የእንስትነት ህላዌ የሚይዙ ፍሬ መሰል (cone) አካሎች አሏቸው። በብዛት ሰው የሚያቃችው ፍሬ-መሰል (cone) አብዝኛውን ጊዜ ጠንካራ ሲሆኑ በውስጣቸው ኦቭዩል አሏቸው።  የተባእት ፍሬ-መሰል አነስ ያሉ ሲሆኑ በናኒ ወንዴዘር (pollen) አመንጪዎች ናቸው። እነዚህ በናኒዎች በንፋስ በንነው ከእንስቱ ፍሬ-መሰል ላይ ያርፋሉ።  አበቦች ላይ እንደሚታየው ሁኔታ፣ እንስታዊ ፍሬ-መሰል ከተባእት ወንዴዘር ጋር ከተዳቀሉ ዘር ያመነጫሉ።

እፅዋት በአንድ ቦታ የረጉ በመሆናቸው፣ ደቂቅና በናኒ ወንዴ የዘር ህዋሳትን ወደ እንስታን ክፍል ለማስተላለፍ የተለያዩ ዘዴዎችን ይጠቀማሉ።  ከነዚህ ውስጥ ለመጥቀስ ያክል፣ ሰርክ አበብ ዛፎችና የሳር አይነቶች፣ ደቂቅና ብናኝ የሆኑ የወንዴዘሮችን በማዘጋጀት በንፋስ ተሽካሚነት ወደ እንስት ክፍሎች እንዲደርሱ ያደርጋሉ።  በዚህ ጊዜ የአንድ ሳር ወይንም ዛፍ ወንዴዘር ወደጎረቤት ሳር ወይንም ዛፍ የእንስት ክፍሎች በመድረስ ሊዳቀል ይችላል።   ሌሎች እፅዋት ደግሞ ከበድ ያሉ ተጣባቂ ወንዴዘሮችን ያዘጋጃሉ።  እነዝህ እፅዋት በነፍሳት ላይ የሚመካ አቅርቦትን ይጠቀማሉ። እነዚህ እፅዋት በአበቦቻችው ውስጥ የሚያመነጩት ጣፋጭ ፍሳሽ ብዙ ነፍሳትን የሚስብ ወይንም የሚማርክ ነው።  ነፍሳቱ፣ ለምሳሌ ቢራቢሮዎችና ንቦች ይህንን ጣፋጭ ለመቅሰም ከአበባው ላይ ያርፋሉ። በዚህ ጊዜ ተጣባቂ ወንዴዘር ከነፍሳቱ እግሮች ላይ ይጣበቃሉ።  ነፋሳቱም ብናኞቹን በእግሮቻቸው በመሸከም ወደ ሌላ ተክል በመውሰድ ከእፁ እንስታዊ ክፍሎች ላይ ያደርሷቸዋል።

በተጨማሪ፣ ብዙ የአትክልት አይነቶች ወሲባዊ በማይሆን ዘዴ መስፋፋትና መባዛት ይችላሉ።  ይህ እፃዊ ተዋልዶ ይባላል። ለምሳሌ ከአንድንድ የፍራፍሬ ዛፍ (እንደ በለስ) አንድ ቅርንጫፍ ተወስዶ ከአዲስ መሬት ቢተከል፣ ይህ ቅርንጫፍ ያለ ወሲብ አዲስ 'ሕጻን' ዛፍ ሊሆን ይችላል።

አብዛኞቹ በወሲባዊ ዘዴ የሚራቡት ፈንጋይ፣ የህልውና ሂደታቸው በሃፕሎይድና ዳይፕሎይድ ደረጃ ውስጥ ያልፋል። ፈንጋይ  በአብዛኛው ፍናፍንትነትን (isogamous) የሚያሳዩና፣ ለእንስትነትና ለተባእትነት የተወሰኑ ፆታዎች የሏቸውም። የፈንጋይ ሃፕሎይድ አንዱ ከሌላው የሚያቀራርብ አካላዊ እድገት ያሳዩና፣ በመጨረሻው ሙሉ በሙሉ በመገናኘት የዘር ህዋሶቻቸውን ያዋህዳሉ።  አንድአንድ ጊዜ ይህ ውህደት ሙሉ በሙሉ በአካል የተስተካከለ ሳይሆን የተዛባ (asymmetric) ነው። በዚህ ወቅት፣ ህዋሳዊ ክሮሞሶም ብቻ የሚያቀርበውና አስፈላጊ ንጥረነገሮችን የማያዋጣው ሃፕሎይድ ተባእት ሊባል ይችላል የሚል የሚመጥን ሃሳብ ማቅረብ ይቻላል።

የአንድአንድ ፈንጋይ ወሲባዊ ሂደት፣ (ለምሳሌ እርሾ ውስጥ የሚገኙት) የወንድና የሴትነት ተዋናይነትን የሚይዙ ጥንዶችን ይፈጥራል።  የእርሾ ፈንጋይ አንዱ ሃፕሎይድ ከተመሳሳይ ሃፕሎይድ ጋር አይዋሃድም። ይህም ማለት የመምረጥ ዝንባሌ እያሳየ ከራሱ ተቃራኒ የሆነ ሃፕሎይድ ጋር ብቻ ይዋሃዳል።  የዚህ ጥምረት ተዋንያን የወንድነትና የሴትነት ህላዊ አላቸው ለማለት ይቻላል።

የአንዳንድ ፈንጋይ ወሲባዊ ሂደት ዕፅ መስል አካላዊ ደረጃዎችን ይፈጥራል።  ላምሳሌ የጅብ ጥላ (mushroom) በመባል የሚታወቀው፣ የፈንጋይ ወሲባዊ ሂደት ክፍል ነው።  የጅብ ጥላ የሚፈጠረው፣ የዳይፕሎይድ ክስተት በፍጥነት የመከፋፈል ሂደት ውስጥ ሲያልፍ ነው። ይህ ክፍፍል ወይንም ሚዮሲስ የሃፕሎይድ ስፖር (spores) ይፈጥራል።  እነዚህ የመብነን እድላቸውን ለማብዛት ከመሬት ወጥተው ያድጋሉ ወይንም ይረዝማሉ።  ይህ ሂደት ጥላ መስል ቅርፅ ይይዛል።

ወሲባዊ እርባታ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከሰተው ከአንድ ቢሊዮን አመታት በፊት እንደሆነ ይገመታል።  የወሲብ ክስተት አሃዳዊ  ህዋስነት ካላቸው ዩክሮይት(eukaryotes)ከሚባሉ ደቂቅ ህላውያን የመነጨ ነው።  የወሲባዊ እርባታ ክስተት እንዲሁም እስክጊዜያችን የመዝለቁ ጉዳይ አከራካሪና እልባት ያልተገኘለት ጉዳይ ነው።  አንዳንድ መጣኝ መላምቶች የሚከተሉትን ይመስላሉ፤  ወሲብ ፅንሶቹ የተለያየ ዘራዊ ባህርይ እንዲኖራቸው ያግዛል፣ ወሲብ ጠቃሚ የዘር ገፅታዎች እንዲሰራጩ ይረዳል፣ ወሲብ የማይጠቅሙ ገፅታዎች እንዳይሰራጩ ይረዳል፣ የሚሉት ይገኙበታል። 

ወሲባዊ እርባታ ዩክሮይት ብቻ የሚጠቀሙበት ዘዴ ነው።  ዩክሮይት፣ በውስጣቸው ማዕከላዊ (nucleus)እና ከባቢ (mitochondria)ያሏቸው ህዋሳት ናቸው።  ከእንሰሳት በተጨማሪ፣ ዕፅዋት እና ፈንጋይ እንዲሁም ሌሎች ዩክሮይት (ምሣሌ፣ የወባ ነቀዝ) ወሲባዊ እርባታን ይጠቀማሉ። አንዳንድ ደቂቅ ህላውያን ለምሳሌ ባክቴርያ አካላዊ ውህደት (conjugation)የሚባለውን ድቀላ ይጠቀማሉ። ይህ ድቀላ ወሲባዊ ባይሆንም የዘር ምልክቶች እንዲዳቀሉና አዲስ ፅንስ እንዲፈጠር ይረዳል። 

ወሲባዊ እርባታን ወይንም ወሲባዊ ድቅለትን ያረጋግጣል ተብሎ የሚታመነው ክስተት የጋሜት ልዩነትና የድቀላው አሃዳዊነት ናቸው። በአንድ ዝርያ የተለያዩ ጋሜት መኖራቸው እንደ ወሲባዊ ድቅለት ቢቆጠርም፣ በህብረ ህዋስ እንሥሣት ውስጥ ሳልሳዊ ጋሜት ስለመኖሩ የሚታወቅ ነገር የለም።

የሰብእን ሥነ ፍጥረታዊ እርባታ በተመረኮዘ ወደፊት ራሱን የቻለ አምድ ይዘጋጃል።  ለጊዜው ይህ ርዕስ ተንገዋሏል።

በፍጡራን ውስጥ መደበኛው የፆታ አይነት ፍናፍንት (hermaphrodites) የሚባለው ለምሳሌ የቅንቡርስና የአብዛኞቹ እፅዋት ይዘት ነው። በዚህ የፆታ አይነት አንድ ግላዊ ፍጡር ሁለቱንም ተቃራኒ የፆታ አይነቶች ማለትም የተባእትና የእንስትን የዘር ህዋሳት ያመንጫል።  ሆኖም ግን ብዙ ዝርያዎች በፆታችው አኃዳዊ የሆኑ ግላውያንን ያዘጋጃሉ።  ማለትም እነዚህ ግላውያን የዝርያውን እንስታዊ ብቻ ወይንም ተባእታዊ ብቻ ፆታ ይይዛሉ።  የአንድን ግላዊ ፍጡር ፆታ የሚወስነው ሥነፍጥረታዊ ሂደት፣ ፆታ መወሰኛ (sex determination)በመባል ይታወቃል።

የተወሰኑ ፍጡራን ለምሳሌ እንደቀይ ትል ያሉት ፆታዎቻቸው የፍናፍንትነትና የተባእት ይዘት አላቸው።  ይህ ዘዴ አንድሮዳዮሲ
(androdioecy)ይባላል።

አንዳንድ ጊዜ በአንድ ፅንስ እድገት ሂደት ጊዜ ሽሉ በሴትነትና በወንድንት ማእከል ውስጥ ያለ ይሆናል።  ይህ ሁኔታ ድብልቅ ፆታ (intersex) ሲባል፣ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ግላዊ ፍጡራን ፍናፍንት ሊባሉ ይችላሉ። ሆኖም ግን እንዚህ ፍጡራን ያልተለመዱ ናቸው ምክንያቱም በሴትነትም ሆነ በወንድንት ሙሉ በሙሉ ያልዳበሩ በመሆናቸው ነው። 

በዘረ መልአዊ መወሰኛ ዘይቤ፣ የአንድ ግላዊ ፆታ የሚወሰነው በሚወርሰው 
የዘርምል (genome)ነው።  የዘረ መልአዊ ፆታ መወሰኛ ዘይቤ በተዛባ ሁኔታ የሚወረስ፣ የክሮሞሶማዊ ውህደት ላይ የተመረኮዘ ነው። እነዚህ ክሮሞሶሞች በውስጣቸው የፆታን ክስተት የሚወስኑ የዘር ምልክቶች ይይዛሉ። የፅንሱ ፆታ የሚወሰነው ባሉት የፆታ ክሮሞሶም አይነቶች ወይንም በሚገኙት ክሮሞሶሞች ብዛት ነው።  የዘረ መልአዊ ፆታ ውሳኔ በክሮሞሶማዊ ውቅረት ላይ የተመረኮዘ ስለሆነ፣ አብዛኛውን ጊዜ የሚፀነሱት የተባእትና የእንስት ፅንሶች ቁጥር በብዛት አኳያ ሲታይ ተመጣጣኝ ነው። 

ሰብዓውያንና ሌሎች አጥቢ እንስሳት  የ 'XY' የፆታ መወሰኛ ዘዴን ይጠቀማሉ።  'Y' ክሮሞሶም የወንድ ፅንስ እንዲፈጠር የሚያግዙ ማነሳሻ ነገሮችን ይይዛል።  የ 'Y' ክሮሞሶም በሌለ ጊዜ በመደበኝነት የሚከሰተው ፅንስ እንስት ይሆናል።  ስለዚህ 'XX' ኣጥቢ እንሥሣት እንስት ሲሆኑ 'XY' የሆኑት ደግሞ ተባዕት ናቸው። የ 'XY' ፆታ መወሰኛ ዘይቤ በሌሎች ፍጡራን ለምሣሌ በዝንቦችና በእፅዋት ውስጥ ይገኛል።  አንዳንድ ጊዜ፣ ለምሳሌ በዝንቦች ውስጥ የፆታ ወሳኝ የሚሆነው የ  'Y' ሳይሆን  የ'X' ክሮሞሶም ነው። 

አእዋፍ  የ'ZW' ፆታ መወሰኛ ዘይቤ ሲኖራቸው ከላይ ከተጠቀሰው የተገላቢጦሽ ሁኔታ ይታይባቸዋል።  የ'W' ክሮሞሶም የእንስትን ፅንስ መ'ከሰት የሚያነሳሱ ነገሮችን ሲይዝ መደበኛው ፆታ ግን ወንድ ነው።  በዚህ ሁኔታ ZZ ግላውያን ተባእታን ሲሆኑ፣  'ZW' ደግሞ እንስታን ናቸው።  ብዙ በራሪዎች፣ ቢራቢሮዎችን ጨምሮ የ'ZW' የፆታ መወሰኛ ዘዴን ይከተላሉ።  ባየናቸው የ 'XY' እና 'ZW' ፆታ መወሰኛ ዘይቤዎች ውስጥ የፆታ መወሰኛው ክሮሞሶም በአካሉ በአብዛኛው አናሳ ሲሆን የፆታ መወስኛና ማነሳሻ ምልክቶችን ከመያዙ በስተቀር ሌሎች ነገሮች በውስጡ በብዛት አይኖሩም።  

ሌሎች ነፍሳት ደግሞ የሚከተሉት የፆታ መወሰኛ ዘይቤ ባላቸው የክሮሞሶም ብዛት ላይ የተመረኮዘ ነው። ይህ XX/XO ፆታ መወሰኛ ዘይቤ ይባላል።  'O' የፆታ መወሰኛ ክሮሞሶም አለመኖርን ያመላክታል።  በነኝህ ፍጡራን ውስጥ ያሉት ክሮሞሶም ዳይፕሎይድ ሲሆኑ፣ ሆኖም ግን አንዳንዶቹ አንድ ወይንም ሁለት 'X' ክሮሞሶም ሊወርሱ ይችላሉ። በፌንጣዎች ለምሳሌ አንድ 'X' ክሮሞሶም የሚወርሰው ፅንስ ወንድ ሲሆን፣ ሁለቱን የሚወርሰው ደግሞ ሴት ይሆናል። nematode C. elegans በሚባሉት ትሎች ውስጥ አብዛኞቹ ራስ በራስ ተዳቃዮች 'XX' ፍናፍንቶች ሲሆኑ አልፎ ደግሞ በክሮሞሶም ውርሰት ውዝግብ ምክንያት 'X' ክሮሞሶም ብቻ ያላቸው ግላውያን ሊፈጠሩ ይችላሉ።  እነኝህ 'XO' ግላውያን ተራቢ ተባእት ይሆናሉ። (ከሚፀንሷቸው ፅንስ ግማሾቹ ተባእት ይሆናሉ።)

ሌሎች ነፍሳት፣ ለምሳሌ ንቦችና ጉንዳኖች haplodiploid የሚባለውን የፆታ መወሰኛ ዘይቤ ይጠቀማሉ።  በዚህ ጊዜ ዳይፕሎይድ የሆኑት ግላውያን በአብዛኛው እንስት ሲሆኑ፣  ሃፕሎይድ ይሆኑት (ከተደቀለ እንቁላል የሚያድጉት) ደግሞ ተባእት ናቸው።  ይህ የፆታ መወሰኛ ዘይቤ፣ በቁጥር ረገድ ወዳንዱ ፆታ ዝንባሌ ላለው የፆታ ስርጭት ይዳ'ርጋል።  የህ የሚሆንበት ምክንያት የፅንሱ ፆታ የሚወሰነው በድቅለት ጊዜ እንጂ በሚዮሲስ ጊዜ በሚከሰተው ክሮሞሶማዊ ይዘት አለመሆኑ ነው።

በዘረ መልአዊ የፆታ ውሳኔ የማይጠቀሙ፣ ነገር ግን የከባቢ ተፈጥሮን ፀባዮች የሚመረኮዝ ፆታዊ ውሳኔ ያላቸው ብዙ ፍጡራን አሉ።  ብዙ ደመ ቀዝቃዛ፣ ገበሎ-አስተኔ (reptile)ፍጡራን የከባቢ ሙቀት ላይ የተመረኮዘ የፆታ መወሰኛ ዘዴ ይጠቀማሉ። ፅንሱ በእድገቱ ጊዜ የሚሰማው ከባቢ ሙቀት የሽሉን ፆታ ይወስናል።   ለምሳሌ በአንዳንድ የኤሊ አይነቶች ውስጥ ፅንሱ በእርግዝና ጊዜ ከባቢው ቀዝቀዝ ያለ ከሆነ ሽሉ ተባእት ይሆናል። ይህ የፆታ መወሰኛ ሙቀት መጠን ወሰናዊ ዝልቀቱ ከ1-2°C አያልፍም። 

ብዙ የአሳ ዘሮች በህልውናቸው ዘመን ፆታ የመለወጥ ፀባይ ይታይባቸዋል።  ይህ ክስተት የቅደም ተከተል ፍናፍንትነት (sequential hermaphroditism) ይባላል።  በአንዳንድ የአሳ አይነቶች በአካሉ አንጋፋ የሆነው ግለፍጡር እንስት ሲሆን፣ አናሳ የሆነው ደግሞ ተባእት ይሆናል።  በሌሎች የአሳ አይነቶች ለምሳሌ 'wrasses' የዚህ የተገላቢጦሽ ሁኔታ ይታያል፣ ማለትም ግላውያኑ በወጣትነታቸው እንስት ሆነው ያድጉና ሲተልቁ የተባእትነትን ፆታ ይይዛሉ።  እነዚህ ቅደም-ተከተላዊ ፍናፍንትነትን የሚከተሉት ፍጡራን የሁለቱንም ፆታዎች የዘር ህዋስ ወይንም ጋሜት በህይወት ዘመናቸው ጊዜ ማመንጨት ቢችሉም፣ በአንድ በተወሰነ ጊዜ ግን ወይ ሴቶች ናቸው ወይ ወንዶች ናቸው። 

በአንዳንድ ትላልቅ ዛፎች በተለይ ፈርን (ferns)ተብለው በሚታወቁት ውስጥ መደበኛው ፆታ ፍናፍንትነት ነው፣ ሆኖም በቅድሚያ የፍናፍንትን ተክል ያበቀለ አፈር ላይ የሚያድጉት ግላውያን በሚያገኙዋቸው ትርፍራፊ ንጥረነገሮች ተፅዕኖ ምክንያት የተባእትነትን ፆታ ይዘው ያድጋሉ።

ብዙ እንሥሣት በመልክም ሆነ በመጠን ልዩነት ያሳያሉ። ይህ ክስተት ፆታዊ የአካል ልዩነት (sexual dimorphism)በመባል ይታወቃል።  ፆታዊ የአካል ልዩነት ከወሲባዊ ምርጫ (sexual selection)- ተመሣሣይ ፆታ ያላቸው ግላውያን ከተቃራኒ ፆታ ጋር ለመዳራት የሚያደርጉት ፉክክር- ጋር የተቆራኘ ነው።  የአጋዘን ቀንድ ላምሣሌ፣ ወንዶቹ ከሴቶቹ ጋር የመዳራት እድል ለማግኘት ለሚያደርጉት ፍልሚያ ያሚያገለግል ነው።  በአብዛኛው ዝርያ፣ የወንድ ፆታ አባሎች ከሴቶቹ በአካል ይገዝፋሉ።  በአጥቢ እንሥሣት ውስጥ ክፍተኛ ፆታዊ የአካል ልዩነት ከአለ ከዚሁ ጋር ተያይዞ አንድ ወንድ ብቻውን ከብዙ ሴቶች ጋር የመዳራት ሁኔታ ይታያል። ይህም የሚሆነው በአካባቢው በሚገኙት ግላውያን ወንዶች መካከል በሚከስተው የጋለ የድሪያ መብት ማረጋገጫ ፍልሚያ ምክንያት ነው። 

በሌሎች እንሥሣት፣ ነፍሳትንና አሦችን ጨምሮ፣ ሴቶቹ በአካል ከወዶቹ የሚገዝፉበትም ክስተት አለ።  ይህ ሁኔታ የድቀላ እንቁላልን ከማዘጋጀት ጋር የተያያዘ ነው ለማለት ይቻላል። ቀድም ሲል እንደተወሳው የእንስትን የዘር ቅንቁላል ወይንም ፍሬ ማዘጋጀት፣የተባእትን የዘር ህዋስ ከማዘጋጅት ይልቅ ብዙ የንጥረነገር ቅምር ይጠይቃል። በአካል የገዘፉ እንስታን ብዙ የዘር እንቁላል መሥራት ይችላሉ። አንዳንድ ጊዜ ይህ ፆታዊ የአካል ልዩነት እጅግ የበዛ ከመሆኑ የተነሳ ወንዶቹ የሴቶቹ ጥገኛ በመሆን ብቻ ተወስነው እንዲቀሩ ያደርጋል። 

በአእዋፍ ውስጥ ወንዶቹ በአብዛኛው በህብረቀለም የተዋቡ (ለምሣሌ እንደ ተባእት የገነት ወፍ) ሆነው ይታያሉ።  ይህ ሁኔታ አንዳንድ ፍጡራንን ለኑሮ በጂ ያልሁነ ሁኔታ ላይ ይጥላቸዋል የሚል አመለካከት አለ። (ለምሣሌ ህብራዊ ቀለም አንድን ወፍ ለአጥቂዎች በግልፅ እንዲታይ ያደርገዋል) ከዚህ በተፃፃሪነት ደግሞ የስንኩልነት ዘይቤ (handicap principle)የሚባል አመለካከት አለ።  ይህ አመለካከት ወንዱ ወፍ ራሱን ለአጥቂዎች አጋልጦ በማሳየቱ፣ ነገዳዊ ጥንካሬውንና ድፍረቱን ለሴቶቹ ይገልፃል ይላል። 

ሰብአዊ ፍጡራን፣  ወንዶቹ አጠቃላይ የሰውነት ግዝፈትና የሰውነት ፀጉር በመያዝ እንዲሁም ሴቶቹ ተለቅ ያሉ ጡቶችን በማውጣት፣ ሰፋ ያሉ ዳሌዎችን በመያዝና ከፍ ያለ የውስጥ ሰውነት ቅባታዊ ይዘት በማፍለቅ የፆታ አካልዊ ልዩነትን ያሳያሉ።




#Article 200: ኤድስ (1260 words)


ኤድስ አኳየርድ ኢምዩኖደፊሸንሲ ሲንድረም የኤችአይቪየመጨረሻ ደረጃ ነው። ኤችአይቪ ያለበት ሰው ኤድስ ደረጃ ላይ ለመድረስ ብዙ አመታት እንደሚወስድ ጥናት ታረጋግጣል። ኤድስ በኤችአይቪ ሳቢያ የሚመፈጠረው የሰውንት የመከላከያ መዳከም ሲሆን ለተለያዩ በሽታዎች የሚያጋልጥ ደረጃ ነው። አንድ ሰው በኤድስ ሞተ የሚባለው አባባል የተሳሳተ ሆኖ ሳለ በተለያዩ በሽታዎች ተጠቅቶ ነው ወደ ሞት ደረጃ ላይ አንድ ሰው ሊደርስ የሚቻለው። እንዲሁም ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች የፀረ-ኤችአይቪ መዳኒቶችን ሳይጅምሩ የኤድስ ደረጃ ሳይ ሳይርስ ብዙ አመት ሊኖሩ ይችላል። አንድ ሰው የኤድስ ደረጃ ላይ ደረሰ ማለት የሚቻለው የኤችአይቪ ቫይርስ የበሽታ መከላከያ ሃይል ተቁዋማትን ደምስሶ እና ሰውነታችን ከማንኛውም በሽታ የመቁዋቁዋሚያ ሃይሉን በማሳጣት ለተለያዩ ኢንፈክሽኖች ይጋለጣል። 
የሲዲፎር በመባል የሚታውቀውን በነጭ ደም ሴል ውስጥ የሚገኘውን የሴል ቁጥር (cd4 count) ከ200 በታች በማድረስ የቫይረሱ መጠን በደም ውስጥ እንዲጨምር በማድረግ ለሕይወት ኣደገኛ እና ምቹ ግዝ ተባቂ በመባል የሚታውቁትን በሸታዎች ኦፓርቸንሰቲክ እንፈክሽስ (Opportunistic infections) OIs. በመፍጠር የኤድስ ደረጃ ላይ እንዲደርስ ያደርጋል። አንድ ሰው አንድ ወይም ሁለት ኢንፌክሽኖች ሲኖሩበት እና በጣም ዝቅያለ የሲዲፎር ሴል ቁጥር 350 cells/mm3 ወይም በታች ሲሆን እና የቫይረሱ ብዛት (viral load) ከ 1,000 copies/mL በላይ ከሆነ የኤድስ ደረጃ ላይ ደረሰ ሊባል ይችላል።

የበለጠ መረጃ ለማግኘት ዋና ግጽ ላይ ይመልከቱኤችአይቪ

ኤችአይቪ ህዩመን ኢምዩኖደፊሸንሲ ቫይረስ Human Immunodeficiency Virus (HIV) በመባል የሚታውቅ ቫይረስ ነው። ኤችአይቪ ቫይረስ የሰውነትን የበሽታ መከላከያ በተለይ የነጭ ደም ሴሎችን በማጥቃት በቀላሉ ሰውነት ለበሽታ እንዲጋለጥ የሚያረግ ቫይረስ ነው። ኤችአይቪ ያለባቸው ሰዎች የበሽታው ምልክት ስይታይባቸው ለብዙ አመታት መኖር ይችላሉ። ቫይረሱ በሰውነታ ውስጥ እስከ አስር ዓመት በመቆየት ምንም ሳይታውቅ እና ምንም አይነት ይህመም ምልክት ሳይታይበት በመኖር እና አለማውቅ ከአንድ ሰው ወደሌላ ሰው ሊተላለፍ የሚችል አደገኛ ቫይረስ ነው።

ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ የኤድስ ታማሚዎች መኖራችው የተረጋገጠው በ1978 ዓ/ም ነው። በአሁኑ ሰአት በኢትዮጵያ ውስጥ 1.3 ሚሊዮን በላይ የሚቆጠሩ ሰዎች ከኤችአይቪ ቫይርስ ጋር አብረው ይኖራሉ።
ኤችአይቪ የሚያመለክት የደም ናሙና የተገኘው በሁለት የደም ናሙናዎችይ ላይ ብቻ ነበር። እነዚህም ከታህሳስ 1976 ዓ.ም እስከ 1977 ዓ.ም ባለው ጊዜ ከተሰበሰቡ የደም ናሙና የተገኘ በመሆኑ ኤችአይቪ ኢትዬጵያ ውስጥ የተገኘው 1976 ዓ.ም ነው።

ከአካል የሚወጡ ፈሳሾች ላይ ሁሉ ኤችአይቪን ማግኝት የሚቻል ቢሆንም መደበኛ ኤችአይቪ ምርመራ በደም ናሙና ላይ የሚደረግ የኤችአይቪ-1/2 አንቲ ባዲ ምርመራ ነው።

እስታሁን የተሰሩትን የአንቲባዲ ምርመራ አይነቶችን በሁለት ከፍል ማየት ይቻላል።

ኤላይዛ መሰረት አርገው የሚከናወኑ

ኤላይዛ አይ.ኤፍ.ኤ 
ኤላይዛ-ዌስተርን ብሎት

ፈጣን የኤችአይቪ ምርመራ ማለት ለቫይረሱ የተዘጋጀ አንቲ ቦዲ በደም ውስጥ መኖሩንና አለመኖሩን የሚያመልክት የምርመራ አይነት ነው። በፈጣን የምርመራ ዘዴ ውጤቱን ከ10-60 ደቂቃዎች ውስጥ ማውቅ የሚያስችል የመመርመሪያ ዘዴ ነው።

ምልክቶች HIV

በኢትዮጵያ ውስጥ በአሁን ሰዓት የኤችእይቪ/ኤድስ ትምህርት በመስፋፋቱ ጥሩ የሆነ ለውጦች በማየት ላይ እንገኛለን። ከቫይረሱ ጋር ለሚኖሩም ሆነ ቫይረሱ እንደሌለባቸው የሚያቁም ሆን የማያቁም የቫይረሱ መስፋፋት ለመግታት የማያቋርጥ ትምህርት ያስፈልጋል። 
አንድ ሰው ስለኤችእይቪ/ኤድስ ዐውቀቱ ካለው አንደኛ ቫይረሱ እንዳይስፋፋ ይረዳል
ሁለተኛ ሰዎችን ከመገለልም ሆነ ከማግለል የሚመጣውን ትልቅ ጥፋት ለመታገል ይረዳል። ከቫይረሱ የበለጠ ሕብረተሰባችን ጎድቶ የነበረ እና አሁንም በመጉዳት ላይ ያለው ይህ አግሎ ነው። እያንዳዱ ገለሰብ ስለኤችእይቪ/ኤድስ ያለው እውቀት ከፍተኛ ከሆነ ከመግላል እና ከመገለል የሚመጣውን መሽማቀቅ እና ጭንቀት መቆጣጠር ከቻልን ማለት ተልቅ ለውጥ እናመጣለን ማለት ነው።
ሕብረተሰባችንም ቢሆን ከቫይርሱ ጋር የሚኖሩትን ሰዎች ማግለል እንደሎለብን መረዳት ይኖርበታል። ይሄን ስንል ማግለል የለብንም ብሎ መስበክ ወይም መናገር ብቻ ሳይሆን በዕለት ዕለት ኑሮአችን ላይ በተግባር ማዋል እንዳለብን መረዳት በጣም ጠቃሚ ነው። ይህ የሰውን የማግለል ባህሪ እኛን የአበሻን የጎዳና በመጉዳት ላይ ያለ ስለሆንም ይህ ጎጂ-ባሕል ማስወገድ አለብን።
በኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ይኸንን ዝምታ የሰበሩ ልንረሳቸው እና ሁሌ ልናስትውሳቸው የሚገቡ እራሳቸውን አውጥተው ከቫይረሱ ጋር እንድሚኖሩ ያስተማሩ እና የብዙ ወጣቶችን ሕይወት ያተረፍ የመጀመሪያው የተስፋ ጎህ ኢትዮጵያማህበር መስራቾች ናቸው።

ኤድስ በሽታ እንደጀመረ በታማሚዎች ላይ ይታዩ የነበሩት የበሽታ ምልክቶችን በማየት የሰውነት የበሽታ መከላከያ አቅም ከመዳከም ጋር ተያያይዘው የሚመጡ ምልክቶች ሊሆኑ እንደሚችሉ ከመገመት በስተቀር ብዙም የሚታውቅ ነገር አልነበረ፤። ከምን እንደመጣና በምን እንደሚተላለፍ አይታወቅም ነበር። በኋላም በተለያዪ የምርምሮች ዘርፎች ተጠናክረው በመቀጠላቸው የኤድስ በሽታን የሚያመጣው ቫይረስ ለይቶ በማወቅ ተሕዋሱንም በላቦራቶሪ ለይቶ ማውጣት ተችሏል። ይህ የኤድስ በሽታ መንስዔ ተዋሕሳትም በኋላ ላይ ኤችአይቪ የሚለውን ስያሜ አግኝቶዋል ሪትሮ ቫይረስ ከሚባል ተሕዋስ ምድብ ወስጥ መሆኑ ተረጋግጥዋል።

ኤድስ ወይም Acquired Immune Deficiency Syndrome (AIDS) በመባል የታወቀው በሽታ የሚመጣው ህዩመን ኢምዩኖደፊሸንሲ ቫይረስ Human Immunodeficiency Virus (ኤችአይቪ HIV) በሚባል ጀርም ነው። በሽታው የሰውነትን የበሽታ መከላከያ በተለይ ነጭ ሴሎችን በማጥፋት ለቀላል በሽታዎች ለሕይወት ኣስጊ የመሆን ዕድል በመስጠት የሚገድል ነው። የሚተላለፈው ቫይረሱ ያለበት ሰው የተጠቀመበትን ያልፀዳ መርፌ በመጠቀም ወይም ኣስፈላጊዎቹ ጥንቃቄዎች ሳይደረጉ በሚፈጸሙ የተለያዩ የግብረ ሥጋ ግንኙነቶች ነው። ኤድስን የሚያመጣው ሕይወት ያለው ጥገኛ ጠንቅ በኃይለኛ የማጉሊያ መሣሪያዎች ይታያል። ቫይረሱ ሰውነት ውስጥ እያለ እስከ ፰ ዓመታት የማይታመሙና በሽታውን የሚያስተላልፉ ጤነኛ ሰዎች ኣሉ።

የኤድስ በሽታ ሲጀምር ሰውነት ወይም ኣካላችን በቀላሉ የሚከላከላቸው ጀርሞች እንደፈለጋቸው በመባዛት ለሕይወት ኣደገኛ ሆነው ይገኛሉ። ለምሳሌ ያህል ጤነኛ መድን በነበረን ጊዜ ከማይተናኮሉን ባክቴሪያዎች ኣንዱ ኒሞንያ ያስከትላል። የቆዳ ካንሰር (Kaposi's Sarcoma) እና የኣንጎል በሽታም ሊኖሩ ይችላሉ። AIDS-related complex (ARC) ወይም ኣርክ የሚባሉ ምልክቶችም ሊመጡ ይችላሉ። ከእነዚህም መካከል የንፍፊት ማበጥ፣ የማይለቁ ትኩሳቶች፣ ድካምና ተቅማጥ፣ ክብደት መቀንስ (ከ፲ በ፻ በላይ)፣ ደረቅ ሳልና ከባድ የእንቅልፍ ላብ ይገኙበታል። ትረሽ (Thrush) እና ሽንግልስ (Shingles) የሚባሉ በሽታዎችም ሊኖሩ ይችላሉ።

ኤድስ እንዳይዝ የምንከላከልበት የክትባት ዘዴ የለም። በሽታው ከያዘም በኋላ የሚፈውስ መድኃኒት የለም። በኣሁኑ ጊዜ ያለን መከላከያ በበሽታው እንዳንያዝ ኣስፈላጊዎቹን ጥንቃቄዎች ማድረግ ብቻ ነው። በሽታው እንዴት እንደሚተላለፍ በምርምር የተደገፉ መረጃዎችን በመከታተል ተረድቶ ቫይረሶቹ እንዳይሰራጩ ትክክለኛዎቹን ጥንቃቄዎች መከተልና ለሌሎችም ማስተማር የያንዳንዳችን ኃላፊነት መሆን ይገባል። ኤድስ ኣሰቃቂና ኣደገኛ በሽታ ቢሆንም እንደጉንፋን በቀላሉ የሚተላለፍ ስላልሆነ ልንከላከለው የምንችለው በሽታ ነው። ስለ በሽታው በሰፊው ማወቅ ባንፈልግ እንኳን በበሽታው እንዳንያዝ እንዴት እንደምንከላከል መረዳትና ወደ ሌሎች እንዳይተላለፍ እንዴት እንደምንጠነቀቅ ማወቅ እንደሚጠቅሙ ተረጋግጧል።

ኤድስ ቀስ በቀስ እየተስፋፋ የመጣው ከ1970 ዓ.ም. ወዲህ ሲሆን እስከ 1985 እ.ኤ.አ. ድረስ የተበከለ ደም በመወጋትና በመሳሰሉት ብዙ ሰዎች ያለቅብጠታቸው በበሽታው ተይዘዋል። ከ1988 ወዲህ ግን ኤድስ ሲይዝ ነጭ ሴል የሚሠራውን ኣንቲቦዲ (Antibody) በመመርመር የኤድስ ቫይረስ እንዳጋጠመን የሚጣራበት ፈጣን የምርመራ ዘዴ ስለተሠራ በተለይ የደም ማነስን ለመከላከል ሆስፒታል ከሚሰጠን ደም በመተላለፍ ሊይዝ የሚችለው ኤድስ ወደ መጣፋቱ ደርሷል።

ኤድስ በሚከተሉት ሁኔታዎች ሊተላለፍ ይችላል።

ከኤድስ በሽታ ለመከላከል የሚከተሉትን እርምጃዎች መውሰድ ይጠቅማል።

በተጨማሪም የሚከተሉት ታውቀዋል።

የኣንድ ሰው ደም ወደ ሌላው (በብዛት) ሊተላለፍባቸው የሚችልባቸውን ቍሳቁስ ለሌላ ከማዋስ መቆጠብ። ለምሳሌ ያህል የጺም መላጭያ፣ ጥርስ ብሩሽና መፋቂያ የመሳሰሉትን ኣለመዋዋስ። ደም መበካከልን ሊያስከትሉ የሚችሉ ባህሎች ከኣሉ ማረም ወይም እንዲጠፉ ማበረታታት።

የኤድስ ቫይረስ ሊኖርባቸው የሚችሉ ደምና የመሳሰሉትን ጓንት (እና እንዳስላጊነቱም ማስክ) ሳያደርጉ ኣለመነካካት።

ስለበሽታው ለማያውቁ ማሰማትና ለልጆች ማስተማር እንዲሁም ኤድስ ያለባቸውን በሚቻለን ሁሉ የመርዳት ኃላፊነትና በየጊዜው የሚገኙትን የምርምር ውጤቶች ለማወቅ መሞከርና ይኸንኑ ዕውቀት ማሰራጨት ኣለብን።

የኤድስ ቫይረስ ደካማ በመሆኑ ከኣካል ውጭ ለረዥም ጊዜ ኣይኖርም። (እንደ ዕቃው ዓይነት የተነካኩትን ለዓሥር ደቂቃዎች ማፍላት ወይም ኣንድ በመቶ ብሊች ባለው ውሃ መዘፍዘፍ ቫይረሶቹን ሊገድል ይችል ይሆናል።

ኣንድን ሰው የበሽታው ቫይረስ እንዳላጋጠመው በተለያዩ (ተደጋጋሚ) የደም ምርመራዎች ማጣራት ይቻላል። (ኣስቀድሞም የኣካባቢውን የኤድስ ሕግ ማወቅ ጠቃሚ ነው።)

ኤድስ በመጨባበጥና በመሳሳም እንዲሁም በሽንትና በሰገራ፣ በወባ ትንኝና ቁንጫን በመሳሰሉት ደም መጣጮች ኣይላለፍም ተብሏል።

የኤድስ ቫይረስ (እራሱን ስለሚቀያይር ጥሩ ዓይነት) የመከላከያ ክትባት በቅርቡ ላይሠራ እንሚችል ተተምኗል። የቫይረስ በሽታዎችንም ማዳን በጣም ከባድ ስለሆነ (የኤድስም ቫይረስ ከሰው ጂን ጋር ስለሚካለስ) ፈዋሽ መድኃኒት በቅርቡ መገኘቱ ያጠራጥራል ይባላል። እስከዚያው ድረስ ግን በሽታው በየኣገሩ (ኢትዮጵያ ጭምር) መስፋፋቱን ስለቀጠለ ለሞት ከመማቀቅ ኣስቀድሞ ማወቅ የሚሻል ይመስለኛል። ቫይረሱ (ለረዥም ጊዜ) ከነበረባቸው መካከል ፺፱ በ፻ በበሽታው ተይዘዋል።

AZT (ኤዚቲ) እና የመሳሰሉት መድኃኒቶች ቫይረሱ እንዳይባዛ በመከላከል በሽታው እንዳይገድል ጊዜ ለመግዛት ይጠቅማሉ ይባላል።

የኤድስ መኖር ካጠራጠረ በጥሩ ጤንነት ለመኖር መሞከርና መድንን ከሚያዳክሙ መቆጠብ እንደሚራዱ ተገምቷል።

በሽታው በመካከላችን ስለኣለ በኣለማወቅና በጥንቃቄ ጉድለት በኤድስ ብንያዝ ጥፋቱና ፀፀቱ የራሳችን ይመስለኛል። እስከ (1991) በዩናይትድ እስቴትስ ውስጥ የኤድስ ቫይረስ ከተገኘባቸው ፪፻፸ሺህ ሰዎች መካከል ፩፻ሺህ (፩00, 000) በበሽታው ሞተዋል። በዓለም ላይም (፩፶፬ ኣገሮች) ኣንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በኤድስ በሽታ ተይዘዋል። (ሕዝቡም መጠንቀቅ ካልጀመረ በቫይረሱ የሚበከለው ሰው ቍጥር በየዓመቱ እጥፍ እየሆነ ሊቀጥል እንደሚችልና ለማስታመምም ብዙ ቢሊዮን ዶላርስ እንደሚያስፈልግ ተገምቷል።) ግብረ ሰዶም የሚያዘወትሩና ድረግ የሚወጉ ሰዎች በሽታ ነው እየተባለ ቸል ሲባል ቆይቶ ኣሁን የሁላችንም ጠር መሆኑ ስለተደሰረበት የሚፈለግብንን ብናከናውንና (ከመንግሥታትም ጋር) ብንተባበር በሽታውን መቆጣጠር ይቻል ይሆናል። ፈንጣጣን (እና ደስታ በሽታዎች) ከዓለም ለማጥፋት ከጠቀሙን መካከል ክትባትና የሕዝቡ ትብብር ዋናዎቹ ናቸው። ስለ ግብረ ሥጋ ግንኙነት ማውራት ለማንኛውም ሕብረተሰብ ኣሳፋሪ ቢሆንም ኤድስ ያመጣብን ዱብ-ዕዳ የሕይወት ጉዳይ ስለሆነ መወያየት መጀመር ኣለብን።

ይህ ጽሑፍ የተጻፈው የሕክምና ዕርዳታ ለመስጠት ኣይደለም። በበለጠ ለመረዳት ሓኪሞቻችሁን ኣማክሩ። በ1988 እ.ኤ.አ. ለእያንዳንዱ የዩናይትድ እስቴትስ ቤተሰብ Understanding AIDS የተባለ ፰ ገጽ ጽሑፍ ከU.S. Department of Health and Human Services ሲላክ ወደ አማርኛ በነፃ በዶ/ር ኣበራ ሞላ ተተርጕሞና ተሰራጭቶ ነበር። የእዚህ የ፲፱፻፹፫ ዓ.ም. ጽሑፍ  መነሻ ይኸው የHHS Publication No. (CDC) HHS 88-8404 ጽሑፍ ነው። 




#Article 201: ኤችአይቪ (658 words)


ኤችአይቪ (እንግሊዘኛ: Human Immunodeficiency Virus (HIV) ህዩመን ኢምዩኖደፊሸንሲ ቫይረስ) በመባል የሚታውቅ ቫይረስ ነው። ኤችአይቪ ቫይረስ የሰውነትን የበሽታ መከላከያ በተለይ የነጭ ደም ሴሎችን (ህዋሳትን) በማጥቃት በቀላሉ ሰውነት ለበሽታ እንዲጋለጥ የሚያደርግ ቫይረስ ነው። ኤችአይቪ ያለባቸው ሰዎች የበሽታው ምልክት ሳይታይባቸው ለብዙ ዓመታት መኖር ይችላሉ። ቫይረሱ በሰውነታ ውስጥ እስከ አስር ዓመት በመቆየት ምንም ሳይታውቅ እና ምንም አይነት የህመም ምልክት ሳይታይበት በመኖር እና አለማውቅ ከአንድ ሰው ወደሌላ ሰው ሊተላለፍ የሚችል አደገኛ ቫይረስ ነው።

ኤችአይቪ የሚያጠቃው የሰውነት የነጭ የደም ሴሎችን የሰውነት የበሽታ የመከላከያ ተቁዋማትን ነው። የሲዲፎር በመባል የሚታውቀውን የሰውነት የነጭ የደም ሴል ቁጥሩን (cd4 count) ከ 200 በታች በማድረግ የቫይረሱ መጠን በደም ውስጥ እንዲጨምር በማድረግ ለሕይወት ኣደገኛ እና ምቹ ጊዜ ተባቂ በመባል የሚታውቁትን በሸታዎች (ኦፓርቹንስቲክ ኢንፈክሽስ Opportunistic infections) OIs. በመፍጠር ኤድስ ደረጃ ላይ እንዲደርስ ያደርጋል። 

ኤድስ ማለትም ኣኳየርድ ኢምዩኖደፊሸንሲ ሲንድረም ሲሆን ኤድስ ኤችእይቪ የማያማጣው የመጨረሻ ደረጃ ነው። ኤችአይቪ ያለበት ሰው ኤድስ ደረጃ ላይ ለመድረስ ብዙ ዓመታት ይወስድበታል። እንዲሁም መድኃኒቱንም ሳይጅምር ኤድስ ደረጃ ሳይደርስ ብዙ ዓመታት ሊቆይ ይችላል። አንድ ሰው የኤድስ ደረጃ ላይ ደረሰ ማለት የኤችአይቪ ቫይርስ የበሽታ መከላከያ ሃይል ተቁዋማትን ደምስሶ እና ሰውነታችን ከማንኛውም በሽታ የመቋቋም ኃይሉን በማሳጣት ለተለያዩ ኢንፈክሽኖች ይጋለጣል። አንድ ሰው አንድ ወይም ሁለት ኢንፌክሽኖች ሲኖሩበት እና በጣም ዝቅያለ የቲ-ሴል ቁጥር ሲኖረው ያሰው የኤድስ ደረጃ ደረሰ ሊያስብለው ይችላል።

ሳይንቲስቶች የኤችአይቪን ቫይረስ አመጣጥ እንደጠቆሙት ከሆነ ከዌስት አፍሪካ ከሚገኝው ቺፓንዝ ዝርያ የመጣ መሆኑን አሳወቀዋል። ይህውም ሊሆን የቻለው የሰው ልጅ ቺፓንዚን ለምግብነት በሚይድንበት ጊዜ በሚደረገው የደም ንክኪ መሰርት ቫይርሱ ሊተላለፈ እንደቻለና። ከብዙ አመት በሃላም ቀስ በቀስ ወደ መላው አለም ሊስፋፋ እንደቻለ ገልጽዋል
ኤችአይቪ ቀስ በቀስ እየተስፋፋ የመጣው ከ1978 (፲፱፻፸ ዓ.ም.) ወዲህ ነው። በአሁኑ ሰአት በኢትዮጵያ ውስጥ 1.3 ሚሊዮን በላይ የሚቆጠሩ ሰዎች ከኤችአይቪ ቫይርስ ጋር አብረው ይኖራሉ። በዓለም ላይም ከ 25 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች በኤድስ በሚመጣ በሸታ ተይዘው ሞተዋል። ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዬጵያ ውስጥ የኤድስ ታማሚዎች መኖራችው የተረጋገጠው በ1978 ዓ/ም ነው። በ2006ዓ/ም ወደ 2.9 ሚሊዮን የሚጠጉ ወንዶች፤ ሴቶች እና ሕጻናትም ሕይወታቸውን አተዋል። ኤችአይቪ ከተያዙት ውስጥ ከግማሸ በላይ የሚገምቱት ሲሞቱ 39.5 ሚሊዮን የሚሆኑ ከቫይርሱ ጋር በመኖር ይገኛሉ። በቅርቡ በUNAIDS/WHO እንደተዘገበው 4.3 ሚሊዮን የሚጠጉ አዲስ ሰዎች በኤችአይቪ እንደተያዙ ይገልጻል።

ከኤችአይቪ ቫይረስ ለመከላከል የሚከተሉትን እርምጃዎች መውሰድ ይጠቅማል 

እርግጠኛ ዕራስን ለማወቅ ግዴታ መልሱ የሚገኘው የኤችአይቪ ምርመራ በማድረግ ብቻ ነው። ስለዚህ ዕራሶን የሚጠራጠሩ ከሆነ ተመርመሩ። ተመርምረው ውጤቶን ከቫይረሱ ነፃ መሆኖ ቢነገሮትም
የውሽት ውጤት የሚባል (ዊንዶ ፔሬድ የሚባል) ነገር ስላለ ከ 3-6 ወር በሃላ እርግጠኛ ለመሆን ደግመው መመርመር ይገባል። ይህን ሲያረጉ ግን አሁንም ኮንዶም መጠቀሞን
አይርሱ።

ኤችአይቪ ቀስ በቀስ እየተስፋፋ የመጣው ከ1978 (፲፱፻፸ ዓ.ም.) ወዲህ ሲሆን እስከ 1985 ድረስ የተበከለ ደም ናሙና በመወጋትና በመሳሰሉት ብዙ ሰዎች ይዚህ ሰለባ በመሆን ብዙ ሰዎች ተይዘዋል። ከ1988 ወዲህ ግን ኤችአይቪ ሲኖር ደም ውስጥ ነጭ ሴል የሚሠራውን ኣንቲቦዲ (Antibody) በመመርመር ኤችአይቪ ቫይረስ እንዳለ እና እንደሌለ የሚጣራበት ፈጣን የምርመራ ዘዴ ስለተሠራ በሆስፒታል ከሚሰጠን ደም መተላለፉ ቀርትዋል።

ከአካል የሚወጡ ፈሳሾች ላይ ሁሉ ኤችአይቪን ማግኝት የሚቻል ቢሆንም መደበኛ የኤችአይቪ ምርመራ በደም ናሙና ላይ የሚደረግ የኤችአይቪ-1/2 አንቲ ባዲ ምርመራ ነው።

እስታሁን የተሰሩትን የአንቲባዲ ምርመራ አይነቶችን በሁለት ከፍል ማየት ይቻላል።

ኤላይዛ መሰረት አርገው የሚከናወኑ 

ፈጣን ምርመራዎች የሚባሉት ተመርተው በገበያላይ የቀርቡ ወደ 60 የሚቆጠሩ መመርመሪያዎች ሲኖሩ በሶስት ዋና ዋና ቴክኒኮች ላይ የተመረኮዙ ናችው። 

እነዚህ መመርመሪያዎች እያንዳንዳቸው ለምርመራ ማከናወኛነት በምንጠቀምበት ጊዜ ምንም አይነት ተጨማሪ ኪሚካል አያስፈልጋቸውም።

ለመጠቀምም ጊዜ የማይፈጅና ዋጋውም ተመጣጣኝ ነው።
አስተማማጝነታቸውም ከኤላይዛር ጋር የሚስተካከል ነው።

ፈጣን የኤችአይቪ ምርመራ ማለት ለቫይረሱ የተዘጋጀ አንቲ ቦዲ በደም ውስጥ መኖሩንና አለመኖሩን የሚያመልክት የምርመራ አይነት ነው። በፈጣን የምርመራ ዘዴ ውጤቱን ከ10-60 ደቂቃዎች ውስጥ ማውቅ የሚያስችል የመመርመሪያ ዘዴ ነው።

በአሁኑ ጊዘ በኤችአይቪ ዙሪያ ላይ በዙ መረጃዎች የሚገኘበት ግዘ ስለሆነ ከኤች·አይ·ቪ ቫይረስ ጋር ተስማምቶ ለመኖርይቻላል። በአሁን ሰአት ኤችአይቪን እንደማንኛውም አይንት ቫይረስ አይቶ ጤናን እየጠበኩና መንፈስን ሳያስጨንቁ ተረጋግቶ መኖር ይቻላሉ። 

ኤችአይቪ እንዳይዘን የምንከላከልበት ክትባት በአሁኑ ሰአት የለም። ኤችአይቪ ከያዘም በኋላ የሚፈውስ መድኃኒት የለም። ነገር ግን ከኤች·አይ·ቪ ቫይረስ ጋር ተስማምቶ ለመኖር የቻላለ። በአሁኑ ጊዜ ፀረ-ኤችአይቪ መዳኒቶች ከፈተኛውን አስታውጾ በማድረግ ላይ የገኛሉ። ኤችአይቪ ያለበት ሰው በትክክል የፀረ-የኤችአይቪ መዳኒቶቹን በመውሰድ እንደማንኛውም ሰው መኖር ይችላል። ቫይርሱ ያለባቸው ሰዎች መውለድ ሲፈልጉ ተገቢውን የህክምና አገልግሎት ከጤና ባለሙያቸው ጋር በመነጋገር ጤነኛ ልጀ መውለስ ይችላሉ። ኤችአይቪ ያለባት እናትከማርገዝዋ በፊት ማወቅ የሚገባትን ቅድመ ተከተሎች መከተል ይኖርባታል። 

ኤችአይቪ እንዴት እንደሚተላለፍ መረጃዎችን በመከታተል ቫይረሱ እንዳይሰራጭ ትክክለኛዎቹን ጥንቃቄዎች መከተልና ለሌሎችም ማስተማር የያንዳንዳችን ኃላፊነት መሆን አለበት። ኤችአይቪ እንዴት እንደሚተላለፈ ግንዛቤዎች እንዴት እንደምንከላከል መረዳትና ወደ ሌሎች እንዳይተላለፍ እንዴት መጠንቀቅ እንዳለብን ማወቅ በጣም ጠቃሚ ነው።




#Article 202: ዕብራይስጥ (125 words)


ዕብራይስጥ የእስራኤል ብሔራዊ ቋንቋ ሲሆን ከሴማዊ ቋንቋዎች እንደ አማርኛ ወይም ዓረብኛ አንዱ ነው .

የታችኞቹ ፊደላት ደግሞ ሶፈት ይባላሉ። ማለትም በጽሁፍ በመጨረሻ ላይ የሚገኙ ለማለት ነው.ለምሳሌ כולך חורף פרטים להתכונן («ሁላችሁ ዝርዝሩን ለማዘጋጀት በጋ አላችሁ») እነዚህ ፊደላት ናቸው።
א ב ג ד ה ו ז ח ט י כ ל מ נ ס ע פ צ ק ר ש ת 
ך ם ן ף ץ

ዘመናዊ ዕብራይስጥ እነዚህ ተናባቢዎች፦
א ב ג ד ה ו ז ח ט י כ ל מ נ ס ע פ צ ק ר ש ת እና כ מ נ פ צ በቃላት መጨረሻ ላይ ሲመጡ ወደ ך ם ן ף ץ ይቀየራሉ። ሶፊት 
የዕብራይስ አናባቢዎች ኒኩድ ይባላሉ። በፊደላቱ ላይ ነጠብጣቦችን ወይም ጭረቶችን በማስቀመጥ ይጻፋሉ።

ዕብራይስጥ የሚፃፈው ከቀኝ ወደግራ ነው።  

 
 
 




#Article 203: ጫት (292 words)


ጫት ወይንም በርጫ፡ በርጫ   በምስራቅ አፍሪካና በየመን የተለመደ ቅጠል ነው። የጫትን ቅጠል በማኘክ 'ምርቃና' የሚባል ቃሚዎቹ ተወዳጅ ስሜት ነው የሚሉት ላይ መድረስ ይቻላል። ይህ የሚሆነው ጫት ውስጥ ያሉት ንጥረ ነግሮች ኣንጎል ላይ በሚፈጥሩት ለውጥ ሲሆን የጫት ወይም ጅማ የስነ ፍጥረት ስሙ በእንግሊዝኛ Catha edulis ነው።  ጫት የተገኘው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ይባላል።   

የጫት ዝርያዎች በኤትዮጵያ ወስጥ በተለያዪ ክፍለ ሃገራት ይገኛል። እንደየአገሩም የጫት (የተክሉ) ዓይነት እና በወስጡ ያለው ንጥረ ነገር ጥንካሬ (የምርቃና ሃይል) ይለያያል። በሃረር እና በአካባቢው የሚገኝ የጫት ዓይነት  (ዓወዳይ) የሚባል ሲሆን  ቅርንጫፎቹ ረጃጅም ቅጠሉ ደግሞ ሰፋ ያለ (ከሌሎች የጫት ዓይነቶች ጋር ሲተያይ) በወንዶ ገነት አካባቢ የሚገኘው ደግሞ 'ወንዶ ገነት' የሚባል ሲሆን የማስከር (የምርቃና) ሃይሉ ከዓወዳይ  እንደሚበልጥ  ይነገራል። የተክሉ ዓይነት፡ ቅርንጫፎቹ ቀጫጭን እና አጫጭር፣ ቅጠሉም ቀጠን ብሎ ዓወዳይን  ያህል ወዝ የሌለው። ጫት በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልላት በተለያየ አይነት መልኩ በመቃም ላይ ይገኛል። ለአብነትም በአማራ ክልል ውስጥ በጎንደር ባህርዳርና አካባቢዎቹ የጫት አቃቃምም ሆነ አሰፋፈሩ ከሌላው የኢትዮጵያ ክፍል በፍፁም ይለያል ይኅውም በሌላው የሀገራችን ክፍል ጫት ከነ ገረባው ወይም እንጨቱ በአነስተኛ ፕላስቲክ ተደርጎ ሲሸጥ በጎንደር ባህርዳርና አካባቢዎቹ ግን የጫቱ ቅጠል ሊቃም ከሚችል የጫቱ ለስላሳ የግንድ ክፍል ጋር ተቀንጥሶ በሚዛን ከ25 ግራም ጀምሮ እስከ ብዙ ኪሎዎች ይሸጣል። ብዙ ጊዜ ጫት መቃም ከጥቅሙ ጉዳቱ ቢብስም አንዳንድ ጥናቶች ግን ጫት ልክ እንደመድሀኒትም ያገለግላል ይላሉ። ጫት አትኩሮትን ሙሉ በሙሉ ሰርቆ ትውስታን በመንጠቅ ህይወትን አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ከሚከታት Attention Deflict Disorder ከተባለው በሽታ ነፃ እንደሚያወጣ ይነገራል።

ዩናይትድ እስቴትስ በጫት መጠቀም ክልክል ነው።

ዛፉ እስክ 7 ሜትር ወይም አንዳንዴ 15-20 ሜትር ይቆማል። 

የአረብኛው ስሙ /ጛአት/ ሲሆን የዚህም በፊደል ቁጥር ድምር 501 ሲሆን፣ ጫት 501 ልዩ ልዩ እርጉሞች እንዳሉበት በአንዳንድ አጓጉል እምነት ተገኝቷል። 

ሥሩ በአንዳንድ ቦታ ለግሪፕ (ኢንፍሉዌንዛ)፣ ለሆድ ወይም ደረት ችግሮች ተጠቅሟል። 

የቅጠሉ አደንዛዥ ውጤት ከድካም ወይም ከረሃብ ያስታግሣል። 

ጫትና ጌሾ በእኩል መጠኖች ጥራት ያለ ጠጅ ይሠራል። ይህ ጥራት ከ፰ ቀን በኋላ ግን ይጠፋል።

የጫት ቅጠልና የእንጭብር ሥር ተድቅቀው በቅቤ ለአስማ መሳል ይጠጣል።

  




#Article 204: «የሰብዓዊ መብት አቀፋዊ መግለጽ» (405 words)


ስለሰብአዊ መብቶች ለማስተማር የሚረዱ አንዳንድ ዘዴዎች።

በዩኔስኮ ተዘጋጅቶ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ኮሚሽን ተተረጎመ

እያንዳንዱ፡ ሰው፡ የኀብረ፡ ሰብ፡ አባል፡ እንደመሆኑ፡ በኀብረ፡ ሰብ፡ ደህንነቱ፡ እንዲጠበቅ፡ መብት፡ አለው። እንዲሁም፡ በብሔራዊ፡ ጥረትና፡ በኢንተርናሽናል፡ መተባበር፡ አማካይነትና፡ በእያንዳንዱ፡ መንግስት፡ ድርጅትም፡ የሀብት፡ ምንጮች፡ መሰረት፡ ለክብሩና፡ ለሰብዓዊ፡ አቅሙ፡ ነጻ፡ እድገት፡ የግድ፡ አስፈላጊ፡ የሆኑት፡ የኤኮኖሚ፡ የማኀበራዊ፡ ኑሮና፡ የባህል፡ መብቶች፡ በተግባር፡ እንዲገለጹለት፡ መብት፡ አለው።

፩/፡ እያንዳንዱ፡ ሰው፡ የመሥራት፡ የሥራ፡ ነጻ፡ ምርጫና፡ ለሥራም፡ ትክክለኛና፡ ተስማሚ፡ የአሠራር፡ ሁኔታዎችና፡ ሥራም፡ እንዳያጣ፡ መብት፡ አለው።

፪/፡ እያንዳንዱ፡ ሰው፡ያላንዳች፡ ልዩነት፡ ማድረግ፡ ለአንድ፡ ዓይነት፡ ሥራ፡ እኩል፡ የሆነ፡ ደመወዝ፡ የማግኘት፡ መብት፡ አለው።

፫/፡ በሥራ፡ ላይ፡ ያለ፡ ሰው፡ ለእራሱና፡ ለቤተሰቡ፡ ለሰብዓዊ፡ ክብር፡ ተገቢ፡ የሆነ፡ ኑሮን፡ የሚያስገኝለትና፡ ካስፈለገም፡ በሌሎች፡ የኀብረሰብ፡ ደህንነት፡ መጠበቂያ፡ ዘዴዎች፡ የተደገፈ፡ ትክክለኛና፡ ተስማሚ፡ ዋጋውን፡ የማግኘት፡ መብት፡ አለው።

፬/፡ እያንዳንዱ፡ ሰው፡ ጥቅሞቹን፡ ለማስከበር፡ የሙያ፡ ማኀበሮችን፡ ለማቋቋምና፡ ማኀበርተኛ፡ ለመሆን፡ መብት፡ አለው።

እያንዳንዱ፡ ሰው፡ የዕረፍትና፡ የመዝናናት፡ እንዲሁም፡ በአግባብ፡ የተወሰኑ፡ የሥራ፡ ሰዓቶች፡ እንዲኖሩትና፡ በየጊዜው፡ የዕረፍት፡ ጊዜያትን፡ ከደመወዝ፡ ጋር፡ የማግኘት፡ መብት፡ አለው።

፩/፡ እያንዳንዱ፡ ሰው፡ ለእራሱና፡ ለቤተሰቡ፡ ጤንነትና፡ ደህንነት፡ ምግብ፣ ልብስ፣ ቤትና፡ ሕክምና፡ አስፈላጊ፡ የማኀበራዊ፡ ኑሮ፡ አገልግሎቶችም፡ ጭምር፡ የሚበቃ፡ የኑሮ፡ ደረጃ፡ ለማግኘት፡ መብት፡ አለው። ሥራ፡ ሳይቀጠር፡ ቢቀር፡ ቢታመም፡ ለመሥራት፡ ባይችል፡ ባል፡ ወይም፡ ሚስት፡ ቢሞት፡ ቢያረጅ፡ ወይም፡ ከቁጥጥሩ፡ ውጭ፡ በሆኑ፡ ምክንያቶች፡ መሰናከል፡ ቢገጥመው፡ ደህንነቱ፡ እንዲጠበቅለት፡ መብት፡ አለው።

፪/፡ ወላድነትና፡ ሕጻንነት፡ ልዩ፡ ጥንቃቄና፡ እርዳታ፡ የማግኘት፡ መብት፡ አላቸው፤ በጋብቻ፡ ወይም፡ ያለጋብቻ፡ የሚወለዱ፡ ሕጻናትም፡ የተመሳሳይ፡ የደህንነታቸው፡ መጠበቅ፡ መብት፡ አላቸው።

፩/፡ እያንዳንዱ፡ ሰው፡ የመማር፡ መብት፡ አለው። ትምህርት፡ ቢያንስ፡ ቢያንስ፡ በአንደኛ፡ ደረጃና፡ መሰረታዊ፡ ደረጃዎች፡ በነጻ፡ ሊሆን፡ ይገባል። የአንደኛ፡ ደረጃ፡ ትምህርት፡ መማር፡ ግዴታ፡ ነው። የቴክኒክና፡ የልዩ፡ ልዩ፡ ሙያ፡ ትምህርት፡ በጠቅላላው፡ የከፍተኛ፡ ደረጃ፡ ደግሞ፡ በችሎታ፡ መሠረት፡ ለሁሉም፡ እኩል፡ መሰጠት፡ አለበት።

፪/፡ ትምህርት፡ ለእያንዳንዱ፡ ሰው፡ ሁኔታ፡ ማሻሻያና፡ ለሰብዓዊ፡ መብቶችም፡ መሠረታዊ፡ ነጻነቶች፡ ክብር፡ ማዳበርያ፡ የሚውል፡ መሆን፡ አለበት። እንዲሁም፡ የተለያየ፡ ዘር፡ ወይም፡ ሃይማኖት፡ ባሏቸው፡ ሕዝቦች፡ መካከል፡ ሁሉ፡ መግባባትን፡ ተቻችሎ፡ የመኖርንና፡ የመተባበርን፡ መንፈስ፡ የሚያጠነክርና፡ የተባበሩት፡ መንግሥታት፡ ድርጅት፡ ሰላምን፡ ለመጠበቅ፡ የሚፈጽማቸው፡ ተግባሮች፡ እንዲስፋፋ፡ የሚያበረታቱ፡ መሆን፡ አለበት።

፫/፡ ወላጆች፡ ለልጆቻቸው፡ ለመስጠት፡ የሚፈልጉትን፡ ትምህርት፡ ለመምረጥ፡ የቅድሚያ፡ መብት፡ አላችው።፡

፩/፡ እያንዳንዱ፡ ሰው፡ በኀብረ፡ ሰቡ፡ የባህል፡ ኑሮ፡ በነጻ፡ መካፈልና፡ በኪነ፡ ጥበብ፡ ለመጠቀም፡ በሳይንስ፡ እርምጃና፡ በጥቅሞቹም፡ ለመሳተፍ፡ መብት፡ አለው።

፪/፡ እያንዳንዱ፡ ሰው፡ ከደረሰው፡ ማንኛውም፡ የሳይንስ፡ የድርሰትና፡ የኪነ፡ ጥበብ፡ ሥራ፡ የሚያገኘው፡ የሞራሉንና፡ የሃብት፡ ጥቅሞች፡ እንዲከበሩለት፡ መብት፡ አለው።

እያንዳንዱ፡ ሰው፡ በዚህ፡ ውሳን፡ ውስጥ፡ የተዘረዘሩት፡ መብቶችና፡ ነጻነቶች፡ በሙሉ፡ በተግባር፡ እንዲውሉ፡ ለሚደረግባቸው፡ የኀብረሰብና፡ የኢንተርናሽናል፡ ሥርዓት፡ የመጠቀም፡ መብት፡ አለው።

፩/፡ እያንዳንዱ፡ ሰው፡ የራሱ፡ ነጻነትና፡ ሙሉ፡ መሻሻል፡ በሚያገኝበት፡ ኀብረሰብ፡ ውስጥ፡ የሚፈጽማቸው፡ ግዴታዎች፡ ይኖሩበታል።

፪/፡ እያንዳንዱ፡ ሰው፡ በመብቶቹ፡ በነጻነቶቹ፡ በሚጠቀምበት፡ ጊዜ፡ የሚታገደው፡ የሌሎችን፡ መብቶችና፡ ነጻነቶች፡ በሚገባ፡ ለማሰከበር፡ ብቻ፡ በተደነገጉ፡ ሕጎችና፡ የግብረ፡ ገብነትን፡ የጠቅላላውን፡ ሕዝብ፡ ፀጥታና፡ ደህንነት፡ በዴሞክራቲክ፡ ማኀበራዊ፡ ኑሮ፡ ትክክለኛ፡ የሆነው፡ ተፈላጊ፡ ጉዳይ፡ ለማርካት፡ በተወሰነው፡ ብቻ፡ ነው።

፫/፡ እነዚህ፡ መብቶችና፡ ነፃነቶች፡ በማንኛውም፡ ሁኔታ፡ የተባበሩት፡ መንግሥታት፡ ድርጅት፡ መሰረት፡ ዓላማዎች፡ ተቃራኒ፡ በሆነ፡ መንገድ፡ ሊፈጸሙ፡ አይገባቸውም።




#Article 205: ሹቡር (163 words)


ሹቡር (ሱመርኛ፡ ሱቢር፣ ሱባር፣ ሹባር፣ ሹቡር፤ አካድኛ፦ ሱባርቱ፣ ሹባርቱም፣ ሱባርቱም፣ ሹባሪ) ከሰናዖር ወደ ስሜን በጤግሮስ ወንዝ ላይ የተቀመጠ አገር ነበረ። ይህም ስም በጥንታዊ አማርና ደብዳቤዎችና በኡጋሪት መዝገቦች 'ሽብር' ተጽፎ ተገኝቷል።  

ከሁሉ ጥንታዊ በሆነ ዘመን፣ ከሰናዖር (ሱመር) ዙሪያ ሌሎቹ '4 ሩቦች' 'ማርቱ' (አሞራውያን)፣ 'ሱባርቱ'፣ ኤላምና 'ኡሪ -ኪ' (አካድ) ነበሩ። እንዲሁም ኤንመርካርና የአራታ ንጉስ በተባለው ሱመራዊ አፈ ታሪክ፣ ልሣናት የተደባለቁባቸው አገሮች ሹባር፣ ሐማዚ፣ ሱመር፣ ኡሪ-ኪ (የአካድ ዙሪያ) እና የማርቱ አገር ይባላሉ።

ሱባርቱ በአዳብ ንጉስ ሉጋል-አኔ-ሙንዱ መንግሥት ውስጥ አንድ ክፍል ነበረ፤ በኋላ ዘመን የአካድ ንጉስ ታላቁ ሳርጎን በሱባር ላይ አንዳንድ ዘመቻ ያደርግ ነበርና ተከታዩ ናራም-ሲን ከገዛቸው አገራት መካከል ቆጠሩት። የኢሲን ንጉስ ኢሽቢ-ኤራ እና የባቢሎን ንጉስ ሃሙራቢ ደግሞ በሱባር ላይ እንዳሸነፉት ይታመናል።

በአዲሱ የባቢሎን መንግሥት ዘመን በናቦፖላሣር፣ በ2 ናቡከደነጾርና በናቡናኢድ ዘመናት 'ሱባርቱ' ለአሦር በጠቅላላ ዘይቤ ነበር። እንኳን በፋርስ ንጉስ በካምቦሥሥ ዘመን 'ሱባርቱ' የሚለው ስም ይጠቀም ነበር።

ከሊቃውንት ብዙዎች 'ሱባርቱ' ለአሦር ቤት ጥንታዊ ስም እንደ ነበር ይቀበላሉ። ሆኖም ከዚያ አገር ትንሽ ወደ ምሥራቅ፣ ስሜን ወይም ምዕራብ እንደ ነበር የሚሉ ሃሳቦች አሉ። አንዳንድም ጸሐፊ ከሑራውያን ጋር ግኙነት እንደነበራቸው ብሏል።




#Article 206: ሙሉቀን መለሰ (102 words)


ሙሉቀን መለስ (፲፱፻፬፭ ዓ.ም. ተወለደ) የኢትዮጵያ ሙዚቃ ወርቃማ ዘመን ዘፋኖች መሃል አንዱ ነው። 1960 ና 1970ዎቹ በርካታ ዘመናዊ ዘፋኞች የታዩበት ወቅት ነበር። ሙሉቀን መለስን ለየት የሚያደርው ቢኖር ባሀላዊውን ከዘመናዊው በማዋሃድ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ለማሳደግ ያደረገው ጥረት ነው። 

ሙሉቀን መለስ ባሁኑ ጊዜ በአሜሪካን አገር በዋሽንግተን ዲሲ ሙሉ ጊዜ የፕሮቴስታንት ሃይማኖት አገልጋይ ሲሆን ያለውን ድንቅ ችሎታ ላመነበትና ለሚያምንበት ሃይማኖት አውሎ አሁንም እጹብ ድንቅ ድምጽ ካላቸው የመንፈሳዊ ዘማሪዎችም አንዱ ነው። 

ሙሉቀን መለሰ በ፲፱፻፶፰ ዓ.ም. ገና የ፲፫ ዓመት ልጅ እያለ ድምጻዊነት ሙያውን በፈጣን ኦርኬስትራ በመጀመር በ፲፱፻፷ ዓ.ም. ወደ ፖሊስ ኦርኬስትራ ክፍል ገብቶ ዝነኛነቱን አሳውቋል። ሙሉቀን በሙዚቃ ዓለም በነበረበት ጊዜ በርካታ ዜማዎች የተጫወተ ሲሆን ዜማዎቹም በሸክላ ተቀርጸው ወጥተዋል።




#Article 207: አካድ (143 words)


 አካድ (ሱመርኛ፡ አጋደ፤ መጽሐፍ ቅዱስ፡ አርካድ) በመስጴጦምያ የተገኘ ጥንታዊ ከተማ ነበረ።  ቦታው በኤፍራጥስ ወንዝ ላይ ከሲፓርና ከኪሽ መካከል እንደ ነበር ቢታሠብም ፍርስራሹ ግን እስካሁን ድረስ አልተገኘም።  ዙሪያው በሱመርኛ 'ኡሪ-ኪ' ወይም 'ኪ-ኡሪ' ተባለ። 

በሱመራውያን ነገሥታት ዝርዝር መሠረት አካድ (አጋደ) የገነባው ታላቁ ሳርጎን ነበረ። ሆኖም ከተማው ከሳርጎን ቀድሞ በኡሩክ ንጉሦች ኤንሻኩሻና እና ሉጋል-ዛገሢ ዘመናት እንደተገኘ ከጽሕፈቶች ይታወቃል። በመጽሐፍ ቅዱስም (ዘፍ. 10፡10) ዘንድ ናምሩድ ከሠሩት ከተሞች 1ዱ መሆኑ ይቆጠራል። ከዚህ በላይ ኤንመርካርና የአራታ ንጉስ በተባለው ሱመራዊ አፈ ታሪክ፣ ልሣናት የተደባለቁባቸው አገሮች ሹባር፣ ሐማዚ፣ ሱመር፣ ኡሪ-ኪ (የአካድ ዙሪያ) እና የማርቱ አገር በመባላቸው፤ ይህም የአካድን ጥንታዊነት ይመሰክራል።  እንደገና በብዙ ጥንታዊ መዝገቦች፣ ከሰናዖር (ሱመር) ዙሪያ ሌሎቹ '4 ሩቦች' ሲዘረዘሩ እነርሱ 'ማርቱ' (አሞራውያን)፣ 'ሹባር' (አሦር?)፣ ኤላምና 'ኡሪ-ኪ' (አካድ) ናቸው።

ከአካድ ንጉሥ ከሳርጎን ዘመን ጀምሮ የአካዳዊ መንግሥት ዋና ከተማ ሆኖ ከ2077 እስከ 2010 ዓክልበ. ገደማ ገዛ።  አካድኛ አንድ ሴማዊ ቋንቋ ነበርና ይህ ቋንቋ በአካዳዊ መንግሥት ጊዜ በመስጴጦምያም ሆነ በኤላም ይፋዊ ሆነ።




#Article 208: ሊኑክስ (203 words)


ሊኑክስ የሚባለው ቴክኖሎጂ የኮምፒውተር ዉስጠ-አካልን የሚቆጣጠር (ስርአተ ክውና) ዩኒክስን የሚመስል ሶፍትዌር ነው። ነገር ግን ብዙ ጊዜ ሰዎች ሊኒክስ ብለው የሚጠሩት ከዩኒክስ የሚባለው ኦፕሬቲንግ ሲስተም የተወለዱትን ኦፕሬቲንግ ሲስተሞችን ነው። 

ሊኑክስ በነፃ ከሚገኙ ሶፍትዌሮች ግንባር ቀደም ተብሎ ሊጠቀስ የሚችል ነው። የምንጭ ኮድንም ማለትም ሊኑክስ የተጻፈበትን ኮድ ተጠቃሚው ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ሊቀይረው፣ ሊጠቀመው ብሎም እንደገና ሊያሰራጨው ይችላል። የሊኑክስ ከርነል ለመጀመሪያ ጊዜ በ17 ሴፕቴምበር 1991 እ.ኤ.አ. ለህዝብ ቀረበ። ይኸውም ለኢንቴል x86 ፒሲ አርክቴክቱር የተሰራው ነበር። ከዚሀም በተጨማሪ ከርነሉ ጠቃሚ ስርአተ ክወና እንዲሆን ከጂኤንዩ ፕሮጀክት በላይብራሪዎችና በሲስተም ዩቲሊቲዎች የታገዝ ነበር። ቆይቶም ጂኤንዩ/ሊኑክስ የሚለውን ስም ተሰጥቶታል። ሊኑክስ በአመዛኙ በሰርቨሮች ውስጥ ባለው ጥቅም ይታወቃል በመሆኑም ከአይቢኤም፣ ሰን ማይክሮሲስተምስ፣ ዴል፣ ሄውሌት ፓካርድና ኖቬልን ከመሳስሉ ድርጅቶች እርዳታን ሲያገኝ ቆይቶአል። ከዚሀም በተጨማሪ ሊኑክስ በተለያዪ የኮምፕዩተር ቁሥ አካላት ላይ ማለትም ሃርድ ዌር፣ በዴስክ ቶፕ ኮምፒዩተሮች ላይ፣ በምጡቅ ኮምፒዩተርዎች ማለትም ሱፐር ኮምፒዩትር ላይ ፣ በኢምቤድድ መሳሪያዎች፣ በሞባይል ስልክዎችና በራውተርዎች እንደ ስርአተ ክወና ሆኖ ያገለግላል።

ሊኑክስ በአሁኑ ሰአት ለተለያየ ጥቅም በአካታች ውስጥ ገብቶ ማለትም «ፓኬጅድ ሆኖ» በስርጭት ላይ ይግኛል። በዚህም ምክንያት ከርነሉ በጥቂቱ ተቀያይሮ እንገኘዋለን።

ሊኒክስን የፈጠረው ሊኑስ ቶርቫልድስ የሚባል የፊንላንድ ዜጋ ነው። የዩኒክስ ስርአተ ክወና የተጸነሰውና የተገበረው በ1960 እ.ኤ.አ. ከዛም በ1970 እ.ኤ.አ. ተለቀቀ። በሰፊው መገኘቱና እንዲሁም ተጓጓዥንቱ ማለትም ፖርተብሊቲው በተለያዩ የትምህርትና የንግድ ተቋምት እንዲራባ፣ እንዲቀየር ብሎም በሌሎች ስርአት ክወናዎች ላይ የዲዛይን ተጽኖ እንዲያመጣ አስችሎታል።




#Article 209: ደርግ (793 words)


ደርግ  ከሰኔ 21፣ 1966 እስከ 1979 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሰፍኖ የነበር የወታደራዊ አገዛዝ ስርዓት አይነት ነበር። ደርግ የሚለው ቃል ከግዕዝ የተወሰደ ሲሆን ትርጓሜውም  ቡድን ወይንም ኮሚቴ ማለት ነው። ይህን ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ ለስርዓቱ መገለጫነት የተጠቀመው ግለሰብ ሻለቃ ናደው ዘካሪያስ ሲባል ይሄውም ሰኔ 21፣ 1966 ዓ.ም. ነበር።  በዚህ ወቅት፣  በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው የአራተኛ እግረኛ ክፍለ ጦር መምሪያ  ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ መለዮ ለባሾች በየካቲት ወር ስለፈነዳው አብዮት ከሰኔ 19 ጀምሮ ውይይት የሚያካሂዱበት ጊዜ የነበር ሲሆን፤ ሻለቃ ናደው የዚህ ኮሚቴ ማስታወቂያ ጉዳይ ሠራተኛ ነበር። ደርግ በዚህ ሁኔታ በዝቅተኛ መኮንኖች (ከኮሎኔል ማዕረግ በታች) ከተመሰረተ በኋላ በዚያው ቀን ሻለቃ መንግስቱ ኃይለማርያም የደርግ ሊቀመንበር በመሆን ተመርጦ እስከ ስርዓቱ ማብቂያ (1979) ድረስ በዚያ ስልጣን አገልግሏል።

የታኅሣሥ ግርግር ተብሎ በሚታወቀውና በ1953 ዓ.ም. የተካሄደው  የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ  ከከሸፈ በኋላ የቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ዘውዳዊ መንግስት የተለያዩ ማሻሻያ ለውጦችን ለስርዓቱ አስተዋወቀ። አብዛኛዎቹ ማሻሻያዎች መፈንቅለ መንግስቱን እንዲደግፉ ለሚጠረጠሩ የጦርና የፖሊስ ሃይሎች የመሬት ስጦታ በማድረግ ላይ ያተኮረ ነበር።   ስለሆነም የአገሪቱ መሰረታዊ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ሁኔታ በቋሚ ሁኔታ ሊሻሻል አልቻለም። 

በ1958ዓ.ም. የባለ ርስቱን መደብ ጉልበት ለመቀነስ በማሰብ የዘውዱ ሥርዓት አዲስ አይነት የመሬት ግብር ለማስተዋወቅ ሞከረ። ሆኖም ፓርላማው ሙሉ በሙሉ ውድቅ አደረገው። በምትኩ፣ በሚቀጥለው ዓመት የእርሻ ውጤቶች ግብር ለፓርላማ ቀርቦ ጸደቀ። ምንም እንኳ የጸደቀው ግብር መንግስት ካቀረበው በጣም የተለወጠ ቢሆንም፣ በባለርስቱ መደብ አመጽ ማስነሳቱ አልቀረም። በተለይ በጎጃም ባለርስቶች በተነሳ አመጽ ምክንያት የሁለት አመት ወታደራዊ ዘመቻ በጎጃም ተደርጎ አመጹን ለማሸነፍ ስላልተቻለ መንግስት ወታደሩን ከጎጃም በማውጣት ግብሩን ሙሉ በሙሉ መሰርዝ ግድ አለው። እንዲያውም ወደኋላ፣ እስከ 1932ዓ.ም. የነበር የግብር እዳ በሙሉ ተሰረዘ። የጎጃሙ ሽንፈት ሌሎች ለውጥን የሚቃወሙ ክፍሎች እንዲያምጹ ከማበረታቱም በላይ ስርዓቱን ለሌላ አጣብቂኝ ዳረገው።  

ለውጥን እሚቃወሙ ኃይሎች በሚያምጹበት በዚያው ወቅት፣  በተቃራኒው ለውጥን የሚፈልጉ ተማሪዎች፣ ገበሬዎችና፣ የሰራተኞች ማህበራት ባንጻሩ የኑሮ ውድነትን፣ ጉቦንና፣ የመሬት ሥርዓቱን በመቃዎም ማደም ጀመሩ። ይህ የተወሳሰበ ሁኔታ በእድሜ እየገፉ የሄዱት ንጉሱ ፊታቸውን ወደ ውጭ ጉዳይ እንዲያዞሩና የአገሪቱን የውስጥ ጉዳይ በጠቅላይ ሚንስትራቸው አክሊሉ ሃብተወልድ ጫንቃ ላይ እንዲያስቀምጡ አደረጋቸው።  

ሥርዓቱ በሁለት ተጻራሪ አጣብቂኞች ውስጥ ገብቶ ባለበት በዚህ ወቅት በተፈጠረ የርሃብ፣ የኑሮ ውድነት፣ ሙስናና አጠቃላይ ቅሬታ የ1966ቱ አብዮት እንዲፈነዳ ግድ ሆነ። አብዮቱን ሀ ብሎ የጀመረው የወታደሩ መደብ ሲሆን፣ ጥር፣1966 ዓ.ም. ነገሌ፣ ሲዳሞ ላይ ሰፍሮ የነበረው የምድር ጦር ሠራዊት  አዛዥ መኮንኖቻቸውን ሲያግቱ  ይጀምራል።  ጉዳዩ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በሚኖሩ የሰራዊቱ ክፍሎች ድጋፍን በማግኘቱ በወታደሩ መደብ ከመዛመቱም ባሻገር ወደ ተቀረው ዜጋም በመዝለል በመጋባቱ በብዙ ከተማዎች አመጽ መነሳት ጀመረ።

የዘውዱ መንግስት ለዚህ መልስ ይሆናል ብሎ ያስበውን ብዙ ጥቃቅን ለውጦችን አድርጓል፤ ለምሳሌ አክሊሉ ሃብተወልድን አንስቶ እንዳልካቸው መኮንንን ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጓል፣ ለወታደሩ ልዩ ደመዎዝ ጭማሪ አድርጓል፣ ሊተገበር የነበር የትምህርት ስርዓት ማሻሻያ ለውጥን በተነሳበት ተቃውሞ ምክንያት አስቁሟል፣ የካቲት ወር ላይ እንዲሁ የመልስቱን ሕገ መንግስት ለማሻሻል ሞክሯል። ምንም እንኳ እኒህ ለውጦች ውጥረቱን ቢያረግቡም፣ በኋላ ላይ በኮሎኔል አለም ዘውድ የሚመራ የዘውዱ ተቆርቋሪ ቡድን  የእንዳልካቸውን አስተዳደር ለመጥቀም በማሰብ ብዙ የአየር ኃይል መኮንኖችን ለእስር ዳረገ። በዚህ ሁኔታ የተበሳጨውና ተከፋፍሎ የነበረው የጦር ሠራዊቱ ክፍል፣ ኮ/ል አለም ዘውድ ከሚመራው ቡድን በማፈንገጥ በአንድ ልብ አመጽ ጀመረ። ሻለቃና ከሻለቃ በታች የሆኑት እነዚህ መኮንኖች በተለያዩ ስፍራዎች የሚገኙ የአገሪቱ ሰራዊት ሶስት ሶስት ተወካዮች ወደ አዲስ አበባ እንዲልኩ በማድረግ፣እርስ በርሳቸው በመሰባሰብ፣ ደርግን መሰረቱ።

ኮ/ል አለም ዘውድ  የዘውዱ ተቆርቋሪ እንደሆነ ከታመነበት በኋላ በኮ/ል አጥናፉ አባተ የሚመራ፣ ባብዛኛው ከሆለታ ጦር ማሰልጠኛ የተመረቀ ቡድንና ጥቂት የሐረር መኮንኖች ማስለጠኛ ምሩቆች ሁነው  አክራሪ አብዮተኛ ቡድን መስርተው  ከአለም ዘውድ ቡድን ተገንጥለው ወጡ። ይህ ቡድን በኮሚቴ በመዋቀር በአገሪቱ ከሚገኙ 42 የጦር ክፍሎች ሦስት ሦስት ወኪሎች ወደ አዲስ አበባ እንዲመጡ ካደረገ በኋላ ከሰኔ '66 ጀምሮ መደበኛ ስብስባ በማድረግ ደርግ እንዲቋቋም አደረገ።  በአነጋገር ጥንካሬው፣ ውሳኔ ለመወሰን ባለምፍራቱና ባለማመንታቱ ታዋቂነት ያተረፈው መንግስቱ ኃይለማርያም  ኢትዮጵያ ትቅደም የሚለውን መፈክር ካስተዋወቀ በኋላ በጣም ተቀባይነትን በማግኘቱ የዚሁ ኮሚቴ ሊቀመንበር ሆኖ ተመረጠ። ኢትዮጵያ ትቅደም የሚለውን መፈክር ባስተዋወቀበት ንግግሩ ኮሚቴው ኢትዮጵያን  ከመበታተን አደጋ ለማዳን የቆመ ኃይል አድርጎ በማቅረብ ለተዘበራረቀው አብዮት አቅጣጫ ከመስጠቱም በተጨማሪ  የአገሪቱን አንድነት ለማስጠበቅ የሚችል ሃይል ይሄው ኮሚቴ እንደሆነ በማሳየት ለኮሚቴው የሃገር ጠባቂነትን አላማ ለማሰጠት ችሎ ነበር።

መንግስቱ፣ ምንም እንኳ በወታደሩ ዘንድ ተቀባይነት ቢያገኝም፣ በመላው ሃገሪቱ ዘንድ ሙሉ ተቀባይነትን ማግኘት እንደማይችል ስለተረዳ ለዚህ ተግባር እንዲረዳው ጄኔራል አማን አንዶምን የስርዓቱ መሪ እንዲሆን በመጋበዝ የጊዜያዊው አስተዳደር ደርግ መሪ እንዲሆን አደረገ። ቀጥሎም ለዓፄ ኃይለሥላሴ 5 ጥያቄዎችን በማቅረብ ንጉሱ አምስቱንም ስለፈቀዱ የደርግ ሃይል በቅጽበት እንዲያድግ አደረገ።  

በመቀጠል፣ በሃይል የጎለበተው ደርግ ጠቅላይ ሚንስትር እንዳልካቸው  ከስልጣን እንዲነሱ አድርጎ ሚካኤል እምሩን ተካ። አማን አንዶም መከላከያ ሚንስትር ሆነው ከተሾሙ በኋላ እንዳልካቸውና የርሳቸው ደጋፊዎች እንዲታሰሩ ተደረገ። በዚህ መልኩ ቀስ ብሎ ይካሄድ የነበረው ለውጥ ፍጥነት ጨመረ። መንግስቱ፣ ንጉሱ እራሳቸውን በቀጥታ መጋፈጥ ስላልፈለገ ቀስ በቀስ የኃይላቻውን መዋቅር በማፈራረስ፣ የክብር ዘበኛን መሪ በማሳሰር፣ በኋላም የጆናታን ዲምብሊን የወሎ ረሃብ ቪዲዮ በቴሌቪዥን በማቅረብ ንጉሱ ተጠያቂ መሆናቸውን በማሳየት፣ ሙሉው ስራ ከተሰራ በኋላ ያለምንም ችግር ንጉሱን ከስልጣን ማስወገድ ቻለ።

ንጉሱ ከስልጣን ከተነሱ በኋላ ጄኔራል አማን አንዶም የጊዚያዊ ወታደራዊ ደርግ ዋና ሊቀመንበር ሆኖ በመሾም፣ አዲሱ ስርዓት  መስከረም፣ 1967 ተጀመረ። ደርግ በዚህ አኳሃን ስልጣን ላይ እንደወጣ አዲስ ረቆ የነብረውን ህገ መንግሥት እና የነበረውን ፓርላማ ወዲያው ሰረዘ። የአማን ተግባር በተለይ ለአለም ፈገግ የሚል መልክ ማሳየትና እጅ መጨበጥ ነበርና ከሁለት ወር በኋላ መንግስቱ አስገድሎት ሌላ አሻንጉሊት መሪ ተፈሪ በንቲ በሥፍራው አስቆመ። 

የተመሰረተው በጥቂት ዝቅተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ሲሆን ደርግ የአጼ ኃይለ ስላሴ መንግስትን ገርሦ በምትኩ ወታደራዊ ጁንታ በመመስረት ስሙን በመቀያየር አገዛዙ ለ17 ዓመታት ኢትዮጵያን አስተዳድሮአል። የተመሠረተበትም ቀን ሰኔ 20 1966 ነው

ደግሞ ይዩ፦




#Article 210: ጄራልድ ፎርድ (106 words)


ጄራልድ ሩዶልፍ ፎርድ፣ ጁንየር (እንግሊዝኛ፦ Gerald Rudolph Ford, Jr.፤ 
 1905 ዓ.ም. - ታኅሣሥ 17 ቀን 1999 ዓ.ም.) ከ1966 ዓ.ም. እስከ 1969 ዓ.ም. ድረስ የአሜሪካ አገር 38ኛው ፕሬዝዳንት ነበሩ። ከዚያ በፊት ከ1965 ዓ.ም. እስከ 1966 ዓ.ም. ድረስ የአገሩ ምትክል-ፕሬዚዳንት ነበሩ። በአሜሪካ ሕገ መንግሥት 25ኛ ማሻሻያ መሠረት ምትክል-ፕሬዚዳንት መጀመርያው የሆነው እሳቸው ነበሩ። ከዚያ በኋላ በ 1966 ዓ.ም. ፕሬዚዳንቱ ሪቻርድ ኒክሰን ማዕረጋቸውን በተዉ ጊዜ በሳቸው ፈንታ አዲስ ፕሬዚዳንት ሆኑ። ከአሜሪካ ፕሬዚዳንቶች መካከል 5ኛው ያለ ሕዝብ ምርጫ የተመረጡ ሲሆኑ፣ እንደ ፕሬዚዳንት ወይም እንደ ምትክል-ፕሬዚዳንት መቸም ያልተመረጡት ፕሬዚዳንት እሳቸው ብቻ ሆነዋል። በዋተርጌት ቀውስ ጊዜ በመካከሉ የኒክሶንን ፪ኛ ዘመን ፈጸሙ ብቻ እንጂ ሙሉ ዘመን ከገዙት ፕሬዚዳንቶች መካከል አይቆጠሩም።

በ93 ዓመታቸው በሞት ተለዩ።




#Article 211: የኡር-ናሙ ሕግጋት (208 words)


የኡር-ናሙ ሕገጋት እስከ ዛሬ ከተገኙት መንግሥታዊ ሕግ ሰነዶች መኃል ከሁሉ ጥንታዊ የሆነው ሰነድ ነው። ሰነዱ የተጻፈው ከክርስቶስ ልደት ከ1983 ዓመት በፊት (ኡልትራ አጭር) በሱመርኛ ቋንቋ ነበር። በመቅደሙ የኡር ንጉሥ ኡር-ናሙ ስም ቢጠቀስም አንዳንድ ሊቃውንት ግን ምናልባት የልጁ የሹልጊ ሥራ ይሆናል ብለው ያምናሉ። 

መጀመርያ የተገኘው ቅጂ በተሰበረ ጽላት በኒፑር ፍርስራሽ ሲሆን፣ በ1944 ዓ.ም. ሊቅ ሳሙኤል ክሬመር አስተረጎሙት። ሆኖም ሰባራ ክፍሎች እንደ መሆኑ ከሕጎቹ ሁሉ 5ቱ ብቻ ሊታነቡ ይችሉ ነበር። ዳሩ ግን ሌሎች ቅጂዎች በኡርና በሲፓር ከተገኙ በኋላ አሁን ከ57 ድንጋጌዎች በጠቅላላ፣ 40 ያሕል ሊታወቁ ተቻለ። 

የኡር-ናሙ ሕገጋት ከሃሙራቢ ሕጎች በ300 አመት አስቀደሙ። ሆኖም ሌሎች የሕገጋት ሰነዶች ከኡር-ናሙ ጊዜ በፊት በሱመር እንደ ኖሩ ይታወቃል። የላጋሽ ንጉሥ ኡሩካጊና የሕግ ማሻሻል እንዳወጣ የሚል ጽላት ተገኝቷልና። 

በዚህ ሰነድ ሕጎቹ «አንድ ሰው እንዲህ ቢያደርግ፣ እንዲህ ይደረግ» በሚመስል አባባል ይጻፋሉ። ይህም ዘዴ ደግሞ በኋለኛ ሕገ መንግሥታት ይታያል። ከንጉሡ («ሉ-ጋል» ወይም ታላቅ ሰው) በታች፣ ከኅብረተሠቡ 2 አይነት ማእረግ ሰዎች ነበሩ፤ እነርሱም፦ 1) «ሉ» ወይም ነጻ ሰው እና 2) «አራድ» (ባርያ) / «ጌሜ» (ገረድ) ናቸው። የ«ሉ» ወንድ ልጅ ሚስት እስከሚያገባ ድረስ «ዱሙ-ኒታ» ይባል ነበር። የሴት («ሙኑስ») ሁኔታ ከሴት ልጅ («ዱሙ-ሚ») ጀመሮ እስከ ሚስት («ዳም») ከዚያም ከባሏ እረፍት ብትኖር ኖሮ እስከ ጋለሞታ («ኑማሱ») ድረስ ይደርስ ነበር። 

መቅደሙ እንደ ኋለኛ ሕገ መንግሥታት መቅደሞች ይመሳሰላል። ስለኡር-ናሙ መንግሥት አማልክቱን ካመሰገነ በኋላ በሰፊ ምድር ላይ የእኩልነት አዋጅ ያቀርባል።

ከታወቁት ህገጋት እነዚህ አሉ፦




#Article 212: ጨው (153 words)


ጨው ማለት በጥንተ ንጥር ረገድ በተለይ NaCl (ሶዲየም ክሎሪድ) ነው። የተሠራው ከሶዲየም (Na) እና ክሎሪን (Cl) ንጥረ ነገሮች ነው። ይህ ማዕደን በምግብ ውስጥ ይበላል። ጣዕም ለመጨመር እንዲሁም የምግብን ኹኔታ ለማስጠበቅ በጣም ይጠቅማል። 

ጨው የምግብን ኹኔታ ስለሚያስቆይ፣ ሥልጣኔ በግብጽ ወዘተ. እንዲጀመር የጨው ጥቅም አይነተኛ ሚና ነበረው። ከጥቅሙ የተነሣ በ1 ወራት ውስጥ የሚበላሽ ምግብ እንግዲህ ከወራቱ በኋለ እንዲቆይ ተደረገ። ከዚህም በላይ፣ እንዲህ ያለ ምግብ በረጅም ጉዞ ላይ እንደ ሥንቅ መውሰድ ከዚያ ጀምሮ ተቻለ።

በጥንታዊ ዘመናት ጨው ዕጅግ ከፍ ያለ ዋጋ ስለነበረው በቻይና በግሪክ በመካከለኛ ምሥራቅም ሆነ በአፍሪቃ ውድ የንግድ ቅመም ሆኖ ተቆጠረ። በሜዲቴራኔያን ዙሪያ እንዲሁም በሮማ መንግሥት፣ ጨው እንደ ገንዘብ (አሞሌ) አገለገለ። ይሁንና ሰዎች ጨው ከውቅያኖስ ጨዋማ ውሃ ማስገኘት በተማሩበት ጊዜ፣ የጨው ዋጋ ተቀነሠ። የፊንቄ ሰዎች ብዙ የውቅያኖስ ውኃ በየብስ ላይ አፍስሰው ውኃው ከተነነ በኋላ ጨውን አከማችተው ይሽጡት ነበር።

አንዳንዴ ደግሞ ጨው በጦርነት ጊዜ የከተማ ሰብል ለማበላሽ በእርሻ ላይ ተበትኖ እንደ ቅጣት መሣርያ ያገልግል ነበር። ለምሳሌ የአሦር ሰዎች ይህን በጎረቤቶቻቸው ላይ እንዳደረጉ በታሪክ መዝገቦች ይባላል።




#Article 213: ጎጃም ክፍለ ሀገር (370 words)


ጎጃም በሰሜን ምራብ ኢትዮጵያ የሚገኝና በአባይ ወንዝ ተከቦ የሚገኝ ባህር ዳርን ፍኖተ ሰላምን አገው ምድርን መተከልን ፓዊ ቆላ-ደጋዳሞትን፣ አቸፈርን ደብረ ማርቆስን ሞጣና ብቸና አውርጃዎች እና በነዚ ውስጥም ከ 35 በላይ ወረዳዎችን ይዞ የሚገኝ የራሱ ስርዎ መንግስት የነበረው ከፍለ-ሃገኢ፣fር ነው። ጎጃም ውስጥ ኣሉ ከሚባሉት ከተሞች እንደ ባህርዳር ፡ ደብረ ማርቆስ ፡ፍኖተሰላም ፡ቡሬ ፡ኮሶበር ፡ ዳንግላ ፡ቻግኒ ፡ ኣዴት ፡ መራዊ ፡ ሞጣ፡ ቢቸና፡ ደጀን ይገኙበታል ፡፡
ጎጃም እንደነ በላይ ዘለቀ ያሉ ጀግኖች መፈጠሪያ እንዲሁም የ ኣባይ እና የጣና ባለቤት ናት ፡፡

ጎጃም የቅኔ ትምህርት በስፋት የሚሰጥበት ፡እንዲሁም    እንደነ የፍቅር እስከ መቃብር ደራሲ ሀዲስ አለማየሁ (ዶ ር) (1902- 1996  )ኣ.ም  ኣቤ ጉበኛ (1925 - 1972 )ኣ.ም  ዮፍታሄ  ንጉሤ(1897-1937  ) ኣ.ም የመሳሰሉ  የጥበብ ሰወችን ኣፍርታለች ፡፡  ጎጃም በጤፍ አምራችነት ከታወቁት የኢትዮጵያ ክልሎች ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል። በተለይ የአዴት ጤፍ በባህር ዳር ጎንደር ደሴ እና መቀሌ ነዋሪዎች ዘንድ በስፋት የታወቀ እና ተወዳጅም ነው። እንዲሁም በምስራቅ ጎጃም  እነብሴ  ሞጣ ዙሪያ  ወይንውሀ  እና ጎንቻ  ሲሶ ግንደወይን ዙሪያ የሚመረተው ጤፍ የአዲስ አበባን ህዝብ ገትሮ እንደያዘ ይነገራል። ጎጃም ሌሎች እንደ ገብስ ስንዴ በቆሎ ባቄላ አተር ወዘተ የሰብል አይነቶችን በማምረትም ይታወቃል።
ጎጃም የአባይ  እና ሌሎች የበርካታ ወንዞች መነሻ ነው ።ጮቄ ተራራ በዚሁ ክፍለ ሃገር ይገኛል።
ጎጃም በኣሁኑ ጊዜ ማለትም ኣገራችን የፌደራሊዝም ስርኣት ከተከተለች ወዲህ ከኣራት ኣስተዳደር ዞን ተከፍሏል ።ሥወስቱ ማለትም አዊ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም በአማራ ክልል ሲገኙ መተከል ቤሻንጉል ጉምዝ ክልል ተካቷል ።

ምዕራብ ጐጃም ዞን                §የዞኑ ዋና ከተማ፡- ፍኖተ ሰላም
                                             §የወረዳዎች ብዛት፡- 13

                                               §የከተማ አስተዳደሮች ብዛት፡- 6

                                                  oባህር ዳር 
                                                    oፍኖተ ሰላም
                                                     oመርዓዊ
                                                    oቡሬ
                                                    oመርዓዊ
                                                         oደንበ ጫ  
                                                         o   አዴት
                   

                                                            §የቀበሌዎች ብዛት፡- 370

                                                                oየገጠር፡-328

                                                                     oየከተማ፡-42

                                                      §በዞኑ ውስጥ የሚገኝ ህዝብ ብዛት፡- 2714017

                                                               ወንድ 1 364 143

                                                                                  ሴት 1 349 874
	

የወረዳው ስም    የወረዳው ዋና ከተማ                                                                                                               
                     
      

                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                           

 አዊ  ዞን                §የዞኑ ዋና ከተማ፡- እንጅባራ 
                                                   §የዞኑ ዋና ከተማ ከክልሉ ዋና ከተማ ያለው ርቀት-122 ኪ.ሜ
                                                                                                                               

                                                       §የወረዳዎች ብዛት፡- 7

                                                      §የከተማ አስተዳደሮች ብዛት፡- 3

                                                             oዳንግላ

                                                            oእንጅባራ

                                                            oቻግኒ

                                                       §የቀበሌዎች ብዛት፡- 201

                                                              oየገጠር፡- 180

                                                         oየከተማ፡- 21

                                                  §በዞኑ ውስጥ የሚገኝ ህዝብ ብዛት፡- 1058 289

                                                      oወንድ916015

                                                     oሴት142274
       
	

  
የወረዳው ስም                                  የወረዳው ዋና ከተማ

ምስራቅ ጐጃም ዞን                  
  §የዞኑ ዋና ከተማ፡- ደብረ ማርቆስ

     §የዞኑ ዋና ከተማ ከክልሉ ዋና ከተማ ያለው ርቀት፡-

               249 ኪ.ሜ

        §የወረዳዎች ብዛት፡- 16

       §የከተማ አስተዳደሮች ብዛት ፡- 4

  oደብረ ማርቆ
 oሞጣ

    oቢቸና

     oደጀን

  §የቀበሌዎች ብዛት፡- 424

    oየገጠር፡- 388

     oየከተማ፡- 36

   §በዞኑ ውስጥ የሚገኝ ህዝብ ብዛት፡- 2 152 671

 ወንድ1 066 09    ሴት1 086 577

 የወረዳው ስም                                     የወረዳው ዋና ከተማ

                                       ድጓፅዮን

                  ሰዴ 

 1.  




#Article 214: ሚካኤል (2656 words)


ሚካኤል (በዕብራይስጥ: מִיכָאֵל‎, ሲነበብ፡ ሚካኤል, ሲተረጎም፡ 'ማንነው እንደ እግዚአብሔር?'; በግሪክ: Μιχαήλ, ሲነበብ፡ Mikhaḗl; በላቲን: Michahel-ሲነበብ፡ ሚካኤል; በአረቢኛ: ميخائيل‎, ሲነበብ፡ ሚካኤል) በክርስትና በአይሁድ በእስልምና እንዲሁም በመላዕክት አማላጅነት በሚያምኑ ሃይማኖቶች የመላዕክት ሁሉ አለቃ ሊቀ መላዕክት ተብሎ ይጠራል

መላእክት ቁጥራቸው እጅግ ብዙ ቢሆንም በ ፺፱ኙ ነገደ መላእክት የተከፈሉና አለቆችም ያሏቸው ናቸው፡፡ የእነዚህ ሁሉ መላእክት አለቃ የሆነው ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡ በትህትናው ልዕልናን ያገኘው ቅዱስ ሚካኤል በእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠው ክብር ከማንኛውም መልአክ የበለጠ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ አስቀምጦታል፡፡ 
የቅዱስ ሚካኤልን ተአምራቶች ወይም ድርሳኑን ለማንበብ 

በተጨማሪም ስለ መላእክት ከመጽሐፍ ቅዱስ ለመረዳት እነዚህን ጥቅሶች ይመለከቱ

ሰውን ይረዳሉ
ዘፍ.16፡7/ ዘፍ.18፡15/ ዘጸ.23፡20/ መሳ6፡11/ 1ኛነገ.19፡5/ 2ኛነገ 6፡15/ ዳን.8፡15-19/ ዳን.3፡17/ ት.ዘካ.1፡12/ ማቴ.18፡10/ሉቃ. 1፡26/ ሉቃ.13፡6/ ዩሐ.20፡11/ ሐዋ.12፡6/ ራዕይ 12፡7/

ስግደት ይገባቸዋል
ዘፍ.19፡1-2/ ዘኁ.22፡31/ ኢያሱ 5፡12/ መሳ.13፡2/ 1ኛ ዜና 21፡1-7/ ዳን.8፡15

ሚካኤል ማለት  ማለት ነው፡፡ ይህም የእግዚአብሔርን ገናንነትና እሱን የሚመስል አምላክ እንደሌለ የሚያመለክት ነው እንደ እግዚአብሔር ያለ ቅዱስ ንጹሕ ርህሩህ ኃይል ረቂቅ ማነው መልሱ የለም ነው፡፡ ቅዱስ ሚካኤል የስሙ ዘርፍ ሆነው የሚጨመሩ መጠሪያዎች አሉት እነዚህም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠውን የባለሟልነት ክብር የሚገልጹ ናቸው፡፡ ይኸውም መልአከ ኃይል፣ መጋቤ ብሉይ፣ መልአከ ምክሩ፣…ናቸው፡፡ መልአከ ኃይል የተባለው እግዚአብሔር በሱ አማካይነት ታላላቅ ሥራዎችን በመሥራት ኃይሉን ስለገለጸ - ዲያብሎስን ከነሠራዊቱ ስላሸነፈ ነው፡፡ መጋቤ ብሉይ የተባለበት ምክንያት በብሉይ ኪዳን ውስጥ ከእግዚአብሔር እየተላከ ብዙ ታላላቅ ሥራዎችን የሠራ በመሆኑ ነው፡፡

መልአከ ምክር ወይም የእግዚአብሔር የምክሩ አበጋዝ የተባለበት ምክንያት እግዚአብሔርን በምክሩ ይረዳዋል ለማለት ሳይሆን እግዚአብሔር የሚሠራውን ሥራ ለወዳጁ ለቅዱስ ሚካኤል ይገልጽለታል በሱም አማካኝነት ይሠራል ለማለት ነው፡፡

ቅዱስ ሚካኤል በዚህ ሁሉ ልዕልና ላይ ትሕትናን ደርቦ የያዘ በጸሎቱ ተማጽኖ በተራዳኢነት አምኖ ለሚለምነው ሁሉ ፈጥኖ በመድረስ ከሠራዊተ አጋንንት ተንኰል የሚያድን መልአክ ነው፡፡ ወደ ቅዱስ መጽሐፍ ስንገባ ለቅዱስ ሚካኤል የተሰጠውን ክብርና ባለሟልነት እንዲሁም የሠራቸውን ሥራዎች እንመለከታለን፡፡ በመጀመሪያ (ኢያሱ 5÷13-15) እንዲህ ይላል፡፡ ‹‹እንዲህም ሆነ ኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ ዓይኑን አንሥቶ ተመለከተ፡፡ እነሆም የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ ሰው በፊቱ ቆሞ ነበር፡፡ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህን አለው፡፡ እርሱም አይደለሁም እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁን መጥቻለሁ አለ፡፡ ኢያሱም ወደ ምድር በግምባሩ ተደፍቶ ሰገደ፡፡ ጌታዬ ለባሪያው የሚነግረው ምንድን ነው አለው፡፡ የእግዚአብሔርም ሠራዊት አለቃ ኢያሱን አንተ የቆምህበት ሥፍራ የተቀደሰ ነውና ጫማህን በፊቱ አውልቅ አለው፡፡ ኢያሱም እንዲሁ አደረገ ይላል፡፡ ይህን ጥቅስ ልብ ብለን ብናጤነው ለሌላው ሁሉ መርህ ይሆናልና ጥቂት ለማብራራት እንሞክራለን፡፡

እንዲሁም እግዚአብሔር ራሱ ለኢያሱ ‹‹…በሕይወትህ ዕድሜ ሁሉ ማንም አይቋቋምህም ከሙሴ ጋር እንደሆነው እንዲሁ ካንተ ጋር እሆናለሁ አልጥልህም አልተውህም፡፡…›› (ኢያሱ 1÷1-9) በማለት ምን ያህል እንዳከበረው ያስረዳል፡፡ እስራኤላውያን አሞራውያንን በወጉ ጊዜ ቀኑ ስለመሸባቸው ከመደበኛው የተፈጥሮ ሕግ ውጭ ቀኑ እንደማይጨልምና መዓልቱ እንዲረዝም ኢያሱ በጸሎት ፈጣሪውን ስለጠየቀ እግዚአብሔርም ጸሎቱን ሰምቶ ቀኑን አስረዝሞ ከሰማይ በረድ አዝንሞ ጠላቶቻቸውን በማጥፋት የፈጸመውን አስደናቂ ተአምር እንዲህ ብሎ ጸፏል፡፡

ይህ የእስራኤል መሪ በእጅ የተመዘዘ ሰይፍ ይዞ የተገለጸለት ቅዱስ ሚካኤል መሆኑን አላወቀም፡፡ ከቃሉ እንደምንረዳው ከራሱ ወገን ወይም ከጠላቶቹ ወገን የሆነ አንድ ወታደር መስሎት ነበር፡፡ መልአኩ በሰው አምሳል ስለተገለጸለት አላወቀውም ነበር፡፡ ያነጋገረውም ያለ ፍርሃት ያለ ጭንቀት ያለድንጋጤ ወታደሮቹን እንደሚያነጋግር ዘና ብሎ ነው፡፡ ሆኖም ከመልአኩ የተሰጠው መልስ ታላቅ መሪና ነቢይ የሆነውን የኢያሱን አስተሳሰብ ለወጠው፡፡ ይኸውም  የሚለውን ቃል ሲሰማ ኢያሱ በፊቱ የቆመው ተራ ወታደር ሳይሆን የመላእክት ሠራዊት አለቃ ከሙሴ ሳይለይ የእስራኤልን ሕዝብ የሚጠብቅ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል መሆኑን ሲረዳ ለመልአኩ ክብር መስጠት ስለሚገባ የአክብሮት ስግደት ሰገደለት፤  በማለት በትህትና ጠየቀ፡፡ ጌታዬ አንተ ቅዱስ ሚካኤል ለኔ ለባሪያህ ለኢያሱ የምትነግረኝ ምንድነው; በማለቱ የእግዚአብሔርን ክብር ለፍጡር መስጠቱ አይደለም መላእክት ጌቶች ይባላሉ፡፡ ጌትነታቸውም የጸጋ ጌትነት ነው፡፡

ኢያሱ መልአኩን ጌታዬ ብሎ ከጠራው እኛማ ኃጢአተኞች ጌታዬ፤ ቀዱስ ሚካኤል ለኔ ለባሪያህ ጸልይልኝ መጥተህ አድነኝ…በማለት የአክብሮት (የጸጋ) ስግደት በመስገድ ብንለምነው ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ውጭ አልወጣንም፡፡ የፈጣሪን ክብር ለፍጡር አልሰጠንም፡፡ ተሳስታችኋል የሚለን ሰው ቢኖር እኛ አብነት ያደረግነው የእግዚአብሔር ወዳጅ ኢያሱን ስለሆነ ኢያሱም ተሳስተሃል ይባል፡፡ መልአኩም ኢያሱ ያቀረበለትን የአክብሮት ስግደትና ጥያቄ በመቀበል ከእግዚአብሔር የተሰጠውን መልእክት ነገረው፡፡ ኢያሱም ትእዛዙን ፈጸመ፡፡

ይህም ማለት መላእክትን ፈጥሮ የሚገዛ፣ የሚያዛቸው፣ የሚቀድሳቸው ማለት ነው፡፡ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ የሚለው ከፈጣሪ በታች በመላእክት ላይ በፈጣሪ የተሾመ ማለት ነው፡፡ መላእክት አለቆቻቸውን ያከብራሉ፤ ለእነሱም ይታዘዛሉ፡፡ ቅዱስ ሚካኤል የመላእክት ሁሉ አለቃ ስለሆነ ከትእዛዙ አይወጡም፤ ሠራዊተ መላእክት የሚያከብሩትንና የሚታዘዙለትን የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን እኛም እንደ ኢያሱ እናከብረዋለን እንታዘዘዋለን፡፡ መላእክትን ማክበርና መታዘዝ እንደሚገባ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡፡ (ዘጸ.23÷20-22) በማለት ለሙሴ ተናግሯል፡፡ ይህ ቃል ለአንድ ጊዜ ብቻ ለሙሴና ለሕዝቡ ተነግሮ ያበቃ ሳይሆን እስከዛሬና ወደፊትም የሚቀጥል ነው፡፡ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ✞✞✞ በስመ ሥላሴ ✞✞✞

እንኳን ለሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖ ወርሃዊ መታሰቢያ ክብረ በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ አደረሰን!!!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር 
ወለወላዲቱ ድንግል 
ለመስቀሉ ክቡር አሜን ። ይቆየን ጊዜ ሕዝበ እስራኤልን ፊት ፊት እየመራ ጠላቶቻቸው አሕዛብን አጥፍቶ ምድረ ርስትን ምድራዊት ኢየሩሳሌምን እንዳወረሳቸው ዛሬም ይኸው መልአክ ቅዱስ ማካኤል እስራኤል ዘነፍስ የተባልን ህዝበ ክርስቲያንን ፊት ፊት እየመራ ጠላቶቻችን ሠራዋተ አጋንንትን እያጠፋ ምድረ ርስት ወደተባለች ሰማየ ሰማያት ያገባናል፡፡ የእስራኤል ሕዝብ ታሪክ ለአዲስ ኪዳን ሕዝብ ምሳሌ ስለሆነ በታሪክነቱ ብቻ ተነግሮ የሚታለፍ አይደለም፡፡ ኦሪት ሰም ሲሆን ሐዲስ ኪዳን ደግሞ ወርቅ ነውና፡፡

ይህ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ሕዝበ እስራኤልን ከግብጽ ባርነት ያወጣ፣ በበረሃ 4ዐ ዓመት የመራቸው፣ ምድር ርስትን ያወረሳቸው መሆኑን በሌላ ስፍራ እንዲህ ይላል፡፡ ‹‹…በእስራኤል ሠራዊት ፊት ይሄድ የነበረው የእግዚአብሔር መልአክ ፈቀቅ ብሎ በኋላቸው ሄደ፤ የደመናውም ዓምድ ከፊታቸው ፊቀቅ ብሎ በኋላቸው ቆመ፡፡›› (ዘጸ.14÷15-20) በዚህ መሠረት እስራኤልን ይመራ የነበረው የእዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡ እንዲሁም በኮሬብ ተራራ እግዚአብሔር ለሙሴ ሐመልማል ከነበልባል ተዋሕዶ በተገለጸለት ጊዜ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል አልተለየም ነበር፡፡ (ዘጸ.3÷1-6፣ የሐዋ. 7÷30-34) በኦሪት የእግዚአብሔር መልአክ እየተባለ የሚጠራው አብዛኛውን ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ያስተምራሉ በድርሳነ ሚካኤልም ተጽፎ ይገኛል፡፡ (መዝ.33÷7) ‹‹የእግዚአብሔር መልአክ (ቅዱስ ሚካኤል) እግዚአብሔርን በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ያድናቸዋል (በኢሳ.37÷36) ›› የእግዚአብሔር መልአክ(ቅዱስ ሚካኤል) መጣ፡፡ ከአሞራውያንም ሰፈር መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ገደለ…›› በማለት ቅዱስ ሚካኤል ሕዝቅያስን እንዴት እንዳዳነው ተገልጿል፡፡ በአጠቃላይ ቅዱስ ሚካኤል ያልረዳው ቅዱስ የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡

በዳን.10÷13 ‹‹የፋርስ መንግሥት አለቃ ግን ሃያ አንድ ቀን ተቋቋመኝ፤ እነሆም ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ›› በማለት የቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነት ተገልጿል /ዳን.10÷21/፡፡

በዚሁ በትንቢተ ዳንኤል ም.12÷1 ላይ ‹‹በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሳል በማለት ታላቅነቱን፤ለሰው ልጆች ሁሉ በአማላጅነቱና በተራዳኢነት የሚቆም እንደሆነ በማያሻማ ቃል ተገልጿል፡፡

ከዚህም ሌላ ዲያብሎስ ከነሠራዊቱ በእግዚአብሔር ላይ ባመፀ ጊዜ ከክብሩ ያዋረደው ወደምድር የጣለው ቅዱስ ሚካኤል ቅዱሳን መላእክትን በመምራት ከዲያብሎስና ከሠራዊቱ ጋር ስላደረገው ጦርነትና ስለተቀዳጀው ድል ቅዱስ ዮሐንስ እንዲሀ በማለት ገልጾታል፡፡ ‹‹በሰማይም ሰልፍ ሆነ፤ ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ፤ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ፡፡ አልቻላቸውምም፤ ከዚያም ወዲያ በሰማይ ሥፍራ አልተገኘላቸውም፡፡ ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው፡፡ ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀድሞው እባብ ወደ ምድር ተጣለ፡፡ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ…›› (ራእ.12÷7-9) ዛሬም ቅዱስ ሚካኤል ሰዳዴ አጋንት አጋንንትን የሚያሳድድ በመሆኑ ከሰይጣንና ከሠራዊቱ መከራ እንዲያድናቸው በጸሎት ለሚለምኑት በቃል ኪዳኑ ለሚማፀኑት ሁሉ ፈጥኖ እየደረሰ ይታደጋቸዋል፡፡ በዙሪያቸው እየከተመ አጥር ቅጥር ሆኖ ይጠብቃቸዋል፡፡ ከክፉ ነገር ሁሉ ያድናቸዋል (መዝ.33÷7)፡፡

በመልእክተ ይሁዳ ቁ.9 ‹‹የመላእክት አለቃ ሚካኤል ግን ከዲያብሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ ስለ ሙሴ ሥጋ ሲነጋገር ጌታ ይገስጽህ አለው እንጂ የስድብን ፍርድ ሊናገረው አልደፈረም›› በማለት ቅዱስ ሚካአል ዲያበሎስን እንኳ እግዚአብሔር ይፍረድብህ ከማለት በቀር ሌላ ቃል አለመናገሩ ታጋሽነቱን ያሳያል፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቅዱስ ሚካኤል ለማንም ያልተሰጠ እጅግ ታላቅ የሆነ ክብር እንደተሰጠው ተጽፎ እናገኛለን፡፡ ይኸውም በዕለተ ምጽአት ጌታችን ቅዱሳን መላእክትን አስከትሎ በክበበ ትስብአት በግርማ መለኮት በሚመጣበት ጊዜ ከእግዚአብሔር ዘንድ በሙታን ላይ ሥልጣን የተሰጠው ለዚሁ ለኃያሉ መልአክ ለቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡ ይህንንም ቅዱስ ጳውሎስ በሚገባ ገልጾታል፡፡ ‹‹እነሆ አንድ ምሥጢር እነግራችኋለሁ ሁላችን አናንቀላፋም፡፡ ነገር ግን የኋለኛው መለከት ሲነፋ ሁላችን በድንገት በቅጽበተ ዓይን እንለወጣለን፤ መለከት ይነፋል፤ ሙታንም የማይበሰብሱ ሆነው ይነሣሉ፤ እኛም እንለወጣለን ይላል›› (1ቆሮ.15÷51-52) ከዚሁ ጋር በተጨማሪ ‹‹በጌታ ቃል የምንላችሁ ይህ ነውና እኛ ሕያዋን ሆነን ጌታ እስኪመጣ ድረስ የምንቀር ያንቀላፉትን አንቀድምም ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና በክርስቶስ የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ…›› (1ተሰ..4÷15-16) በማለት በዕለተ ምጽአት ምን ያህል ክብርና ጌትነት እንደሚሰጠው ይገልጽልናል፡፡

የቤተ ክርስቲያን አባቶች በየወሩ በ12 መታሰቢያውን እንድናደርግ አዘውናል፡፡ ይህንንም ያልቻለ በዓመት አራት ዐበይት በዓላትን ከቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ጀምሮ እንደተቻለ ማዝከር ይገባል፡፡ እነዚህም ኅዳር 12 ቀን ቀጥሎ ሰኔ 12 ቀን ከዚያም ነሐሴ 12 ቀንና ታኅሳስ 12 ቀን ናቸው፡፡ ከሁሉም የሚበልጠው ታላቁ በዓሉ ኅዳር 12 ቀን ነው፡፡ በዚህም ዕለት እግዚአብሔር በሰማይ ካሉ ሁሉ በላይ አድርጐ ሾመው፡፡ ስለትሕትናውና ስለ መታዘዙ ጌታውን ፈጣሪውን የከዳና የበጐ ሥራ ሁሉ ጠላት የሆነውን ሰይጣንን ድል ይነሣ ዘንድ ሥልጣን ሰጠው፡፡ በዚህ ዕለት እንዲሁ ከላይ እንደተገለጸው ቅዱስ ሚካኤል በታላቅ ክብር ሆኖ በንጉሥ ጭፍራ አምሳል ለነዌ ልጅ ለኢያሱ የታየበት ዕለት ነው፡፡

በቅዳሴያችን ‹‹ተውህቦ ምሕረት ለሚካኤል፤ ለሚካኤል ምሕረት (ይቅርታ ርኀራኄ) ተሰጠው ይላል፡፡ ነቢዩ ሄኖክም ምሕረት ለሚካኤል መሰጠቱን ገልጿል፡፡ ትሕትናውን ታዛዥነቱን አስረድቷል (ሄኖክ. 6 ቁ.5 ምዕ.10 ቁ.12) ፡፡

የሰማያውያን ሠራዊት አለቃ ለሰው ሁሉ የሚራራና ስለ ሰው ልጆች ሳያቋርጥ ወደ ፈጣሪው የሚለምን ርኀሩኀ ትሑት የሆነው ኃያሉ ቅዱስ ሚካኤል የሠራውን ሥራ የክብሩን ገናንነት ጽፈን ለመጨረስ ስለማይቻለን በዚሁ እናበቃለን፡፡ ጸሎቱ እና በረከቱ፣ ተራዳኢነቱም ሀገራችንና ሕዝባችንን ይጠብቅልን አሜን፡፡

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም።

በየካቲት ወር በአሥራ ሁለት ቀን የሚነበብ ኃያል ክቡር የሚሆን የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል ድርሳን ይህ ነው። ልመናው በረከቱ ከኛ ጋር ይኑር ለዘለዓለሙ አሜን።

ከዚህ ነገር በኋላ በዚህ አገር የሚኖር ሃይማኖቱ የፀና አንድ ድሃ ነበር። በመዓልትም በሌሊትም ይጸልይ ነበር። ቅዱስ ሚካኤልን ጌታዬ ሆይ እዘንልኝ የዕለት ምግብ የዓመት ልብስ ስጠኝ ይለው ነበር። ሰውዬው ግን ሰነፍ ነው። ከቤቱ ወደሥራ አይወጣም ልድከም አይልም የሚያውቀው ሥራ የለም። አንዲት ሰዓት ስንኳ ልሥራ አይልም። ንግድም አያውቅም።

ከዚህ በኋላ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በሕልም ተገልጦ ወደዚህ ደሃ ሰው መጣ። እንዲህም አለው።እርሻውም ቢሆን ንግድም ቢሆን ጥቂት ሥራ የማትወድ አንተ ሰነፍ ሰው በመዓልትም በሌሊትም ይቅር በለኝ እያልክ እንዴት ትለምነኛለህ።

እባርክልህ ዘንድ ወይንህ የት ነው ስንዴህ የት ነው የሠራኸው የትነው የደከምክበት የት ነው። አንተ ሰነፍ ሰው የምተሸጠው የምትገዛበት የት አለ ጌታዬ ሚካኤል እዘንልኝ እንደምን ትለኛለህ። የደከምክበት ሥራ የት አለ። የሁሉ አባት አዳምን እግዚአብሔር እንዳለው አልሰማህምን፡

በክፉ በዲያብሎስ ሽንገላ የአዘዘውን ሕግ በተላለፈ ጊዜ። ይህች የተገኘህባት ምድር ናት ወደሷም ትመለሳለህ። ሥራ በፊትህ ወዝ እንጀራህን ብላ። እሾህ አሜከላ ይብቀልብህ አላለውምን አንተ ግን አትሠራም ግን ባርክልኝ ትለኛለህ። ይህን ብሎ ወደ ሰማይ ወጣ።

በነጋ ጊዜም ይህ ድሃ ተነስቶ ሊጸልይ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔደ። ሊጸልይም በቅዱስ ሚካኤል ስም ወደ ተሠራው መቅደስ ገባ። የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ሆይ ከኔ ጋር ሁን አትለየኝ አለ። ከቤተ ክርስቲያንም በወጣ ጊዜ እግዚአብሔርን የሚፈራ ለደሆች ለችገረኞች ብዙ ምጽዋት የሚሰጥ አንድ ባለጸጋ ሰው አገኘ።

ይህ ድሃ ጌታዬ እዘንልኝ መቶ ወቄት ወርቅ ስጠኝ ሔጄ እነግድበት ራሴን እረዳበት ዘንድ ገንዘብህንም ከነወለዱ እከፍለሃለሁ አለው። ባለጸጋውም ድሃውን እኔ አላውቅህም ይህም ባይሆን ዛሬ ከዚህ ሀገር የሚዋስህ አንድ ሰው አምጣ። በኔና በአንተ መካከል ፀብ እንዳይሆን ገንዘቤን የሚመልስልኝ ዋስ ስጠኝ አለው።

ይህም ድሃ ባለጸጋውን እኔ ድጋ ነኝና የሚዋሰኝ አላገኝም። አሁንም ፈቃድህ ከሆነ ከራራህልኝም ተነስተህ እኔም አንተም ሁለታችንም የመላእክት አለቃ ወደ ሚሆነ ወደ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን እንሒድ እሱ አለቃዬ ነውና ይዋሰኛል አለው። ይህም ባለጸጋ አንተስ በቅዱስ ሚካኤል የምታምን ከሆነ እኔም አምንበታለሁና ተነሥ እንሒድ አለው።

ከዚህ በኋላ ሁለቱም ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔደው የቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ባለበት አንድነት ቆሙ። ይህም ደሃ የመላእክት አለቃ ጌታዬ ቅዱስ ሚካኤል ሆይ ስለዚህ ባለጻጋ አላመነኝምና አንተ ጌታዬ ተዋሰኝ አለው። ከዛሬ ጀምሮ በዓልህ እስከሚከበርበት ሰኔ አሥራ ሁለት ቀን ድረስ ለባለገንዘቡ ወርቁን እመልሳለሁ አለው።

ይህም ባለጸጋ ነገርክን ሰማሁ ተነስ እንሂድ ልስጥህ አለው። ይህ ነገር ለባለጸጋው ድንቅ ሆኖበታልና። ከዚህ በኋላ ከቤተ ክርስቲያን ወጥተው ሁለቱም አንድነት ወደባለጸጋው ቤት ሔዱ። ባለጸጋውም መቶ ወቄት ወርቅ ሰጠው። ድሃውም የተሰጠውን ወቄት ወርቅ ይዞ ደስ እያለው ወደቤቱ ተመለሰ ከዚህም በኋላ ወደሮም አገር ሔደ በዚያ ወርቅም ነገደና አተረፈ።

ከዚህ በኋላ ቀጠሮው የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሚካኤል በዓል የሚሆንበት ዕለት ሰኔ አሥራ ሁለት ቀን እንደደረሰና ወደ ሀገሩ ሊመለስ እንዳልቻለ በአወቀ ጊዜ ጽኑ ኀዘን አዘነ። ተቆረቀረ። በልቡናውም አስቦ እንዲህ አለ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን ዋስ ያደረግሁበት ጊዜው ደረሰ ዛሬ መድረስ አልተቻለኝም ምን ላድርግ አለ።

ያን ጊዜም የቅዱስ ሚካኤልን ተራዳኢነት የፈጣሪውንም ከሃሊነት አሰበ።ከዚህ በኋላ እጁን ወደ ሰማይ ዘርግቶ አንገቱን ወደ ላይ አቅንቶ ጸለየ። በፍጹም ልቡና በፀና ሃይማኖት ታምኖ ለባለ ዕዳው ከአምሳ ትርፍ ጋራ መቶውን ወቄት ወርቅ ይዞ በከረጢት ቋጥሮ በከረጢቱም ውስጥ የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤልን ስምና የባለጸጋውን ስም ከነሱም ጋር የእሱን ስም ጻፈ።

ከዚህ በኋላ ተነስቶ ወደ እንጥረኛ ሔዶ አንጥረኛውን የእርሳስ ሣጥን ሥራልኝ አለው። የእርሳስ ሣጥን ሠራለት። ከዚህ በኋላ ይህን ከረጢት ወስዶ ከውስጡ ጨምሮ ዘጋው።

ከዚህ በኋላ በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል በዓል ዋዜማ ቀን ወደ ወንዝ ሔደ ከባሕር ዳርም ቆሞ አቡነ ዘበሰማያት ደገመ እግዚአብሔርን ፈጽሞ አመሰገነ።

በፍጹም ሃይማኖቱም ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ሆይ እነደተዋስከኝ ባለጠጋውና እኔ የተቃጠርንበት የበዓልህ ቀን ዛሬ እንደሆነ እኔም ከሩቅ አገር እንዳለሁ ዛሬም እስክንድርያ መድረስ እንዳይቻለኝ አንተ ታውቃለህ አሁንም የባለጠጋውን ገንዘብ ከነወለዱ ለአንተ ሰጥቼሃለሁ ለባለ ዕዳዬ መልስልኝ ብሎ ጸለየ ጸሎቱንም በጨረሰ ጊዜ ሣጥኑን ከነ መክፈቻው ወደ ባሕር ወረወረው ያን ጊዜ ጊዜውን ታላቅ ዓሣ ወጥቶ ሣጥኑን ተቀብሎ ዋጠው።

ከዚህ በኋላ ያ ዓሣ በአንዲት ሌሊት የስድስት ወር ከስድስት ቀን ጎዳና ተጉዞ በነጋው ፀሐይ በወጣ ጊዜ ከእስክንድርያ ባሕር ወደብ ደረሰ። በዚች ቀን ያ ባለጸጋ ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ ሚካኤል በዓል ዓሣ ሊያሠግሩ ሔደው ከባሕር ላይ መረባቸውን ይጥሉ ዘንድ ብላቴኖቹን አዘዘ።

ያ ዓሣ ተያዘና ወደ ባለ ጸጋው ወሰዱት ባለጠጋውም ባየው ጊዜ ደስ አለው ታላቅ ነበርና። ባለጠጋውም ብላቴኖችን ይህን ዓሣ ለበዓሉ ቅዱስ ሚካኤል አመጣልኝ አላቸው። ብላቴኖችን ያን ዓሣ ጥቡት ብሎ አዘዛቸው ሆዱንም በቀደዱት ጊዜ በዓሣው ሆድ ውስጥ ይህን የዋጠውን ሣጥን አገኙት።

ያም ባለጸጋ ዕቃ ቤቱን በሀገራችን የተደረገውን በባሕርም ውስጥ የሆነውን ሁሉ ሰምተን እስክናውቅ ድረስ ይህን ሣጥን አስቀምጥ አለው። ከጥቂት ቀን በኋላ ያ ድሃ ወደ እስክንድርያ ከተማ ገባ። ባለዕዳውም አገኘውና ለምን እንዲህ አደረግህ አምኜ ገነዘቤን ብሰጥህ በጊዜው እንዴት አልሰጠኸኝም ለምንስ አልከፈልከኝም አለው።

ያም ድሃ እኔስ ለተዋሰኝ ሰጥቼው ነበር በውኑ በቀጠሮው አልሰጠህምን አለው። ዋስህን ወዴት አግኝተኸው ሰጠኸው አለው ድኀውም እኔ ሩቅ አገር ስለ አለሁ የተቃጠረንበት ቀን በደረሰ ጊዜ ወደ አንተ መድርስ ባይቻለኝ በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል በዓል ቀን መቶውን ወቄት ከአተረፍኩልህ ከአምሳ ትርፍ ጋር በከረጢት ውስጥ አድርጌ በላዩም የቅዱስ ሚካኤልን ስም የኔንና የአንተንም ስም ጽፌ በሣጥን ውስጥ አደርጌ ቆለፍኩና ያንንም ሣጥን ወስጄ በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል በዓል ዋዜማ የመላእክት አለቃ ሚካኤል ሆይ እንደተዋስከኝ አንተ ታውቃለህ እነሆ እንካ ለባለ ዕዳዬ ገንዘቡን መልሰህ ሰጥልኝ ብዬ ከባሕር ጣልኩት አለው።

ያ ድኀም ይህን ነገር በነገረው ጊዜ ባለጠጋው ከጥቂት ቀን በፊት የሆነውን ነገር አሰበና በሊቀ መላእክት በቅዱስ ሚካኤል ቀን በዓሣው ሆድ ውስጥ የተኘገውን ሣጥን አምጣ ብሎ ዕቃ ቤቱን አዘዘው። አመጣለት በእጁም ይዞ ድኀውን ሣጥኔ ነው የምትለው ይህ ነውን አለው። ባለጠጋውም አዎን ጌታዬ አለው። ፈጥኖ ከፈተው። በከረጢቱ ላይም የቅዱስ ሚካኤልን ስምና የራሱንም ስም የባለጠጋውንም ስም እንደ ተጻፈ እንደ ታተመ አገኙ። መቶ ወቄትና ትርፉንም አምሳ ወቄት በውስጡ አገኙ።

ስለዚህም ነገር ባለጸጋው የቅዱስ ሚካኤልን የተአምራቱን ገናንነት የአምላኩንም ከሀሊነት አደነቀ እግዚአብሔርንም አመሰገነ አከበረ ከፍ ከፍ አደረገ። መቶውን ወቄት ትርፉንም ይዞ ባለፀጋው ድሃውን እንዲህ አለው ወንድሜ ሆይ ሃይማኖትህ ፍጹም ነው።

በእውነት አንተ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነህ ይህን ትርፍ ከአንተ አልቀበልም አለው። ያም ባለጸጋ ከገንዘቡ አምሳውን ወቄተ ወርቅ ወስዶ ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ጽዋዕ አሠራው። ለመታሰቢያው ይሆነው ዘንድ

ሁለቱም ከዚያን ቀን ጀምሮ እስከ ዕለተ ሞታቸው ወዳጅ ሆነው በእግዚአብሔር ፍቅር ፀንተው ኖሩ። ይህም ሁሉ የሆነው በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት ነው። እኛንም በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል የጸሎት ኃይል እግዚአብሔር ይማረን ይቅር ይበለን በጥምቀት የተወለድን ሁላችንንም ይጠብቀን ለዘለዓለሙ አሜን።

እሳታዊ ባሕርይ ያለው የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ያደረገው ተአምር ይህ ነው። ልመናው አማላጅነቱ ከኛ ጋር ይሁን ለዘለዓለሙ አሜን።

ቸር እግዚአብሔርን የሚፈራ አንድ ሰው እንደነበር ተነገረ። ለድኆች ለችግረኞች ቸርነትን ያደርግ ነበር። የአዳም ልጆች ሁሉ ባለጋራ በጎ ነገርን የሚጠላ ሰይጣንም ይህን ባየ ጊዜ ቀንቶ ጽኑ ደዌ አመጣበት። ሽባ ሆነ ጽኑ ደዌ ታመመ። ይህም ሰው ደዌው ስለጸናበት ሁል ጊዜ ይጮህ ነበር።

ከደዌው ጽናት የተነሣ ከተኛበት መነሣት ተሳነው። ስለዚህም ዘመዶቹን ጎረቤቶቹን ወደመላእክት አለቃ ወደ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ከርስቲያን በሥውር ተሸክመው እንዲወስዱት ለመናቸው አንሱም ሰው ሳያውቅ በሌሊት ወሰዱት። እንደለመናቸውም የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል ሥዕል በአለበት ወስደው አስቀመጡት።

ከዚህ በኋላ ያ ሰው በፍጹም ልቡና ወደ ቅዱስ ሚካኤል ይለምን ይማለል ይማልድ ጀመር። እንዲህ እያለ ጌታዬ የመላእከት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ሆይ በእግዚአብሔር ፊት በጸሎትህ አስበኝ ከአሁንም ና እርዳኝ። ከዚህ ከአገኘኝ ጽኑ ደዌም ፈውሰኝ አድነኝ እኔ አገልጋይህ ልመናህን አምኜ መታሰቢያህን ሳደርግ ኖሬአለሁና።

ከልቅሶና ከጽኑ ዕንባ ጋረ ደረቱን እየመታ እንዲህ ሲል እኩለ ሌሊት በሆነ ጊዜ በላዩ ላይ ታላቅ ብርሃን ወጣ።የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ከብርሃኑ ውስጥ ሆኖ እንዲህ ብሎ ተናገረው። ከዚህ ደዌህ እግዚአብሔር አድኖሃልና ከዚህ ደዌህ ዳን ተነሥ እነሆ እግዚአብሔር አድኖሃል ድኅነትንም ሰጥቶሃል እንግዲህ ዳግመኛ አትበድል ኃጢኣት አትሥራ ከዚህ የበለጠ እንዳያገኝህ።

ይህንን ብሎት እጁን ዘርግቶ ሁለንተናውን ዳስሶ እግዚአብሔር ፈጽሞ አድኖሃልና ተነስተህ ሒድ አለው። ከእንቅልፉም በነቃ ጊዜ ቀንቶ በእግሩ ተነስቶ ሔደ። የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤልን ፈጣሪ እግዚአብሔርን እያመሰገነ።ከደዌው ስለ ዳነ ፈጽሞ ደስ አለው። በፍጹም ደስታ ቃል እያመሰገነ በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ፊት ሰገደ።

ሕዝቡም ሁሉ ይህን ታላቅ ተአምራት ባዩ ጊዜ የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤልን ክብር ገናንነት ፈጽመው አደነቁ። የተአምራቱን የነገሩን ምስጋና አበዙ። የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤልን ተአምር ያዩትም ለሰው ሁሉ ነገሩ። ያ የዳነው ሰውም ከቀድሞው ይልቅ በጎ ሥራን አበዛ። እስኪሞትም ድረስ በየወሩ በአሥራ ሁለት ቀን መታሰቢያ ማድረጉን አላስታጎለም።

የቸርነትና የይቅርታ መልእክተኛ በሚሆን በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት ወደ መንግሥተ ሰማያት ገባ። እኛንም የክብር ባለቤት ጌታ በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት ከኃጢኣት ሞት ያድነን ከክፉ ቀን ከመከራ ዘመን ይሠውረን። መንግስተ ሰማያትን ያውርሰን። በዚህ ዓለም በሚመጣውም ዓለም የሕይወትን ተስፋ ያድለን አሜን።

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም የካቲት አሥራ ሁለት ቀን የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል በዓል መታሰቢያ ነው። በዚች ቀን ክብር ምስጋና ይግባውና እግዚአብሔር የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን የረዓይት ወገን ወደሚሆን ወደ ሶምሶን ልኮታልና።

ሊገድሉት የፈለጉትን የፍልስጥኤምን ሰዎች ድል እስኪያደርጋቸው ድረስ ረድቶታልና። በእነሱ ላይ እግዚአብሔር ኃይል ሰጥቶት አጠፋቸው ከእነሱ በአንዲት ቀን በአህያ መንጋጋ ሺህ ሰው ገደለ። ውሃ ጠምቶት ሊሞት በደረሰ ጊዜም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ታይቶ አፀናው ከአህያ መንጋጋ አጥንትም ውሃ አወጣለት ጠጥቶም ከውሃ ጥም ዳነ።

የፍልስጥኤም ሰዎች ድል በሆኑ ጊዜ ከሚስቱ ጋር ተማክረው ዓይኑን አጥፍተው ወደ ጣኦታቸው ቤት ወሰዱት። የእግዚአብሔር መልእክተኛ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ታየው ተነጋገረው ኃይልንም ሰጠውና ሁሉንም አጠፋቸው ስለዚህ ነገር የቤተ ክርስቲያን መምህራን በየወሩ በአሥራ ሁለት ቀን የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል መታሰቢያ እናደርግ ዘንድ። አዝዘውናል።




#Article 215: ናምሩድ (1151 words)


በመጽሐፍ ቅዱስ እንዲሁም በአፈ ታሪክ፣ ናምሩድ (ዕብራይስጥ נִמְרוֹד /ኒምሮድ/) የኩሽ ልጅ፣ የካም ልጅ ልጅ እና የኖህ ልጅ-ልጅ-ልጅ ሲሆን የሰናዖር ንጉሥና 'በእግዚአብሔር ፊት ኃያል አዳኝ' ይባላል። በመጽሐፍ ቅዱስ ስሙ የሚገኘው በኦሪት ዘፍጥረት 10፣ በዜና መዋዕልና በትንቢተ ሚክያስ ብቻ ነው። እነዚህ መጻሕፍት ስለ ናምሩድ ብዙ ባይነገሩንም፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ስለሱ ያሉት ትውፊቶች ግን በርካታ ናቸው። ከነዚህም ትውፊቶች መካከል ከሁሉ የታወቀው የባቢሎን ግንብ እንዲገነባ ያዘዘ መሆኑ ነው። 

መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 1፡10 ከዚህ በላይ ምንም አይጨምርም። ትንቢተ ሚክያስም 5፡6፦ «የአሦርንም አገር በሰይፍ፥ የናምሩድንም አገር በመግቢያው ውስጥ ያፈርሳሉ» ያለው ነው።

በእብራይስጥ ትርጉም ኦሪት ዘፍጥረት 10፡11-12 ዘንድ ነነዌንና በነነዌ ዙሪያ ሌሎች ከተሞች የሠራው የሴም ልጅ አሦር ወይም ናምሩድ መሆኑ ግልጽ አይደለም። ስለዚህ በአንዳንድ ትርጉም ዘንድ በአሦር አገር ያሉትን ከተሞች የሠራው ደግሞ ናምሩድ ነበረ።

በመጽሐፈ ኩፋሌ 8፡39 የኤቦር ሚስት አዙራድ «የአብሮድ ልጅ ናት» ሲል በግሪኩ ደግሞ በ«አብሮድ» ፈንታ «ነብሮድ» አለው፤ ይህም በግሪክ መጽሐፍ ቅዱስ «ናምሩድ» ማለት ነው። ናምሩድ የኤቦር አማትና የፋሌክ ቅድማያት ከሆነ፣ እንግዲህ አብርሃምና አይሁዶች ሁሉ ኢየሱስ ቢሆንም ከናምሩድ ከኩሽና ከካም ትንሽ ተወላጅነት አለባቸው ማለት ነው።

በዘፍጥረት በብዙ ጥንታዊ ግዕዝ ቅጂዎች የናምሩድ ስም ኑቤርድ ወይም ኑቤር ተጽፎ ይታያል፤ ይህም ከግሪኩ አጻጻፍ ነብሮድ የደረሰ ይሆናል። አንድ ግዕዝ ቅጂ ግን «ናምሩድ» አለው፤ ይህም ከአረብኛው አጻጻፍ ታረመ።

በአይሁድ ልማዶች ዘንድ በተለይ በታልሙድ እንደሚገኘው ናምሩድ የባቢሎን ግንብ እንዲሠራ ያዘዘው ነው። በአንዳንድም የአይሁዶች ምንጭ ዘንድ፣ ከአብርሃም ጋር የታገለው የባቢሎን ንጉስ አምራፌል (ዘፍ. 14፡1) እና ናምሩድ አንድ ናቸው። ፕሲውዶ-ፊሎ የሚባል የአይሁድ መጽሐፍ (70 ዓ.ም. ያህል ተጽፎ) እንደሚለው፣ ናምሩድ የነገደ ካም አለቃ ሲሆን፣ እንዲሁ ዮቅጣን የነገደ ሴም አለቃ፣ የያዋንም ልጅ ዶዳኒም (ሮድኢ) ልጅ ፌኔክ የነገደ ያፌት አለቃ ሆኑ። 

በ1ኛ ክፍለ-ዘመን የአይሁድ ታሪክ ጸሐፊ ፍላቪዩስ ዮሴፉስ ስለ ናምሩድ እንዲህ ብሎ ጻፈ፦

ብዙዎቹም የናምሩድን ውሳኔ እንዲከተሉ፣ ለእግዚአብሔርም መገዛት እንደ ቦቅቧቃነት እንዲቆጠሩ በጣም ተዘጋጁ። ግንብም ሠሩ፤ ምንም ጣር አላስቀሩም ወይም በምንም ረገድ ስራቸውን ቸል አላሉም። በስራው ላይ በተደረጉ እጆች ብዛት ምክንያት፣ ማንም ሳይጠብቀው ቶሎ ቶሎ እጅግ ከፍ ከፍ አለ፤ ሆኖም ውፍረቱ በጣም ግዙፍ በመሆኑ፣ ታላቅ ከፍታው ከርቀት ሲታይ ከእውኑ ያነሰው ይመስል ነበር። ውኃ እንዳይዘልቀው የተሠራው በዝፍት ከተመረገ ከተቃጠለ ጡብ ነበር። እግዚአብሔርም እንዲህ ያለ አእምሮ እንደ አደረጉ ባየ ጊዜ፣ በሙሉ እንዲያጠፋቸው አላሰበም፤ በቀድሞ ሐጢአተኞች ጥፋት ጥበበኛ አልሆኑምና፤ ነገር ግን ትርምስ አደረገባቸው፣ የተለያዩም ልሣናት አስገኘባቸው፣ በቋንቋዎች ብዛት ሳቢያ እርስ በርስ እንዳይግባቡ። ግንቡን ያገነቡበት ሥፍራ አሁን ባቢሎን ይባላል፤ ምክንያቱም አስቀድሞ በቀላል የገባቸው ቋንቋ ተደናገረና፤ አይሁዶች 'ባቤል' በሚለው ቃል 'ድብልቅ' ማለታቸው ነውና…»

ኪታብ አል-ማጋል የተባለው ጥንታዊ አረብኛ መጽሐፍ (ከ'ቄሌምንጦስ መጻሕፍት' መሃል) እንደሚለው፤ ናምሩድ ሐዳኒዩንን፣ እላሳርን፣ ሴለውቅያን፣ ክቴሲፎን፣ ሩሂን፣ አትራፓተነን፣ ተላሎንንና ሌሎችን ከተሞች ሠራ። የፋሌቅ ዕድሜ 50 አመት ሲሆን ናምሩድ ኒሲቢስን፣ ራሃን (ኤደሣ) እና ካራንን ሠርቶ ከዚህ በላይ የራግው ዕድሜ 163 አመት በሆነበት ወቅት ናምሩድ የዓለም ንጉስ ሆኖ ለ69 አመታት ነገሠ። በተጨማሪ ናምሩድ 'ጥቁር ጨርቅና ዘወድ በሰማይ አይቶ ሸማኔውን ሳሳንን ጠርቶ እሱ በእንቁ ሠሮቶት በራሱ ላይ ጫነው። እሱ መጀመርያ ዘውድ የጫነው ንጉስ ነበረ። ስለዚህ ነገር ምንም የማያውቁ ሰዎች ዘውድ ከሰማይ ወረደለት አሉ።' በኋላ መጽሐፉ ናምሩድ የእሳትና የጣኦት አምልኮት መሠርቶ ለ3 አመት የአስማት ትምህርት ከኖህ 4ኛ ልጅ ከ'ቡኒተር' እንደ ተቀበለ ይላል።

በጽርዕ የተጻፈው በዓተ መዛግብት (350 ዓ.ም.) ስለ ናምሩድ ተመሳሳይ ታሪክ አለው፤ ነገር ግን ናምሩድ ኒሲቢስን፣ ኤደሣንና ካራንን የሠራው የራግው ዕድሜ 50 አመት ሲሆን ነው፤ የናምሩድም ዘመን የጀመረው የራግው ዕድሜ 130 በሆነበት ወቅት ይባላል። በዚህ መጽሐፍ ደግሞ የሸማኔው ስም 'ሲሳን'፣ የኖህም አራተኛ ልጅ ስም 'ዮንቶን' ይባላል።

ቅዱስ ሄሮኒሙስ 380 ዓ.ም. ገዳማ በጻፉት ጽሕፈት እብራይስጥ ጥያቄዎች ስለ ኦሪት ዘፍጥረት እንደሚሉ፣ ናምሩድ በባቤል ከነገሠ በኋላ «ደግሞ የነገሠባቸው በኦሬክ እሱም ኤደሣ፤ በአርካድ እሱም አሁን ኒሲቢስ፣ በሐላኔ [ካልኔ] እሱም ስሙ ከተቀየረ በኋላ ስለ ንጉስ ሴሌውቆስ 'ሴሌውቅያ' አሁንም እንዲያውም 'ክተሲፎን' የሚባሉ ከተሞች ናቸው» ነገር ግን ይህ ልማዳዊ መታወቂያ በዘመናዊ ሊቃውንት አይቀበለም፤ የናምሩድ ከተሞች በሶርያ ሳይሆኑ ሁላቸው በሱመር ይገኛሉ ባዮች ናቸውና።

በግዕዝ የተጻፈው መጽሐፈ አዳምና ሕይዋን (ምናልባት ከ5ኛ ክፍለዘመን የታወቀ) ደግሞ ለበዓተ መዛግብት ተመሳሳይ ታሪክ አለው፤ በዚህ ግን የዘውዱ ሠሪ ስም 'ሳንጣል'፤ ናምሩድንም ያስተማረው የኖህ 4ኛ ልጅ ስም 'ባርውን' ይባላል። 

በአይሁድ መጽሐፍ ፒርኬ ዴ-ረቢ ኤልኤዘር (826 ዓ.ም. ያህል) ዘንድ፣ ናምሩድ ከአባቱ ከኩሽ የአዳምና የሕይዋን ልብሶች ወረሰ። እኚህም ልብሶች የማይሸነፍ አደረጉት ይላል። ከዚያ የናምሩድ ወገን ነገደ ያፌትን ድል በማድረግ ላዕላይ ገዚነት ተቀበለ። በኋላ ዔሳው (የአብርሃም ልጅ-ልጅ) ናምሩድን ገደለው። ይህ ተረት እንደገና ከ1618 ዓ.ም. በሚታወቀው «ያሻር መጽሐፍ» በሚባለው ሚድራሽ ይገኛል። ከዚህ በላይ የናምሩድ ልጅ ማርዶን በክፋት ከአባቱ እንደበለጠ ይጨምራል። 

በ9ኛ መቶ ዘመን 'የነቢያትና የነገሥታት ታሪክ' የጻፉት የእስላም ጸሓፊ ሙሐመድ እብን ጃሪር አል-ታባሪ ይህን የመሰለ ተረት ያቀርባል ። በዚህ መሠረት ናምሩድ ግንቡን በባቢል (ባቢሎን) አስገንቦ አላህ አጠፋውና የሰው ልጅ ቋንቋ ከዚያ ቀድሞ የሶርያ (አራማያ) ሲሆን የዛኔ ወደ 72 ልሣናት ይደባለቃል። ከዚያ በላይ ደግሞ በ13ኛ መቶ ዘመን የጻፉት ሌላ የእስላም ታሪከኛ አቡ አል-ፊዳ ይህን መሰል ታሪክ ሲያወራ የአብርሃም ቅድመ-አያት ዔቦር ግንቡን ለመሥራት እምቢ ስላለ የፊተኛው ቋንቋ ዕብራይስጥ እንዲቀርለት ተፈቀደ ብሎ ይጽፋል።

በሀንጋሪ አፈ ታሪክ ደግሞ የሀንጋሪ ሰዎች አባቶች ወንድማማች 'ሁኖር' እና 'ማጎር' ሲሆኑ እነኚህ የታና ልጅ መንሮጥ እና የሚስቱ የኤነሕ መንታዎች ይባላሉ። በአንዳንድ ትውፊት ይህ መንሮጥ የኩሽ ልጅ ናምሩድ እንደ ነበር ይባላል። ጥቂት ደራሲዎች የ'ታና' እና የ'ኩሽ' ስሞች ከታሪካዊ ሱመራዊ የኪሽ ንጉሥ ኤታና ጋር እንዲሁም ከኩሻን መንግሥት (እስኩቴስ) አባት 'ኩሽ-ታና' ጋር ያለውን ተመሳሳይነት አጠቁመዋል። ሆኖም በአንድ መጽሐፍ ዘንድ የሁኖርና የማጎር አባት የኤነሕም ባል ናምሩድ ሳይሆን የኖህ ልጅ ያፌት ነበረ።

በአርሜኒያ አፈ ታሪክ ዘንድ፣ የአርሜኒያ ሕዝብ መስራች ሐይክ ናምሩድን በቫን ሐይቅ አጠገብ በተካሔደ ፍልሚያ አሸንፎት ነበር።

በዩናይትድ ስቴትስ በሚገኘው በሞርሞን ሃይማኖት መጻሕፍት ዘንድ፣ ልሣናት በተደባለቁበት ጊዜ የ'ያሬድ' ወገኖች መጀመርያውን ቋንቋ ጠብቀው በስሜን ቅርብ ወደ ሆነ፣ ስለ አዳኙም 'ናምሩድ' ወደ ተባለ ሸለቆ እንዲጓዙ ታዘዘ።

በመጽሐፍ ቅዱስ ስለ ናምሩድና አብርሃም ምንም ግንኙነት የለም። እንዲያውም ከሁለቱ መካከል 7 ትውልዶች አሉ። ይሁንና በሐሣዊ ፊሎ ጽሕፈት; በተልሙድም፣ በመካከለኛው ዘመን ረቢዎች ጽሕፈቶች እና በዛሬም አይሁዶች ልማድ ዘንድ፤ ናምሩድና አብርሃም በአንድ ጊዜ የኖሩ ጠላቶች ያደርጋቸዋል። 
በዚሁ ትውፊት፣ አብርሃም ናምሩድን ስለ ጣኦት አምልኮት ይገሥጸዋል። በቤተ እሥራኤል ጽሕፈት ትዕዛዘ ሰንበት ተመሳሳይ እምነት ይተረካል። እዚህ ግን ናምሩድ የከነዓን ንጉሥ ይባላል። 

በኢብራሂም (አብርሃም) እና ባልተሰየመ ንጉሥ መሃል ያለው ተመሳሳይ ክርክር ደግሞ በእስልምና ቁርዓን ይገኛል። በአይሁድ ምንጮች መሠረት፣ የእስላም ሊቃውንት ይህ ንጉሥ ናምሩድ ነበር ይላሉ። ናምሩድ የፈላጭ ቁራጭና የክፋት አራያ ሆኖ በእብራይስጥ 'ናምሩድ ክፉው' (נמרוד הרשע) በአረብኛም 'ናምሩድ አል-ጃባር' (አምባገነን) ይሠየማል።

የታሪክም ሆነ የአፈታሪክ ሊቃውንት ለረጅም ዘመን የናምሩድን መታወቂያ ለመገመት ሙከራዎች አድርገዋል። 

የከለዳውያን ጸሐፊ ቤሮስስ በ3ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. እንደ ጻፉ፣ ከማየ አይኅ በኋላ መጀመርያው ንጉሥ የከላውዴዎን ንጉሥ «ኤወኮዮስ» እንደ ነበር መሠከረ። ስለዚህ በ4ኛው ክፍለ ዘመን ዓ.ም. በክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ አውሳብዮስ አስተያየት ይህ ኤወኮዮስና ናምሩድ አንድ ነበሩ። ከዚህም ጋር በ200 ዓ.ም. ግድም የጻፉት ክላውዲዩስ አይሊያኑስ እንዳለው፣ «ኤወኮሮስ» የባቢሎን ንጉሥና የ«ጊልጋሞስ» አያት ይባላል። የዛሬው ሊቃውንት እምደሚያስቡ፣ የዚህ «ኤወኮሮስ / ኤወኮዮስ» መታወቂያ በተጨማሪ ከኩኔይፎርም ሰነዶች ከታወቀው ከኡሩክ (ኦሬክ) ጥንታዊ መስራች ከኤንመርካር ጋር አንድ ላይ ነው። በጥንታዊ ጽሑፍ ኤንመርካርና የአራታ ንጉሥ ዘንድ፣ ኤንመርካር የግንብ መቅደስ በኡሩክ (ኦሬክ) እና በኤሪዱ (ባቢሎን እንደመሰለው) ሠርተው ነበር። «ባቢሎን» ማለት የኤሪዱ መጠሪያ እንደ ነበር የሚል ማስረጃ በሌሎችም ጥናቶች አለ።

ሌሎች ሊቃውንት ለናምሩድ የተለያዩ መታወቂያዎች አቅርበዋል። የ4ኛው ሮማ ፓፓ ቅሌምንጦስ በጻፉት ደብዳቤ መሠረት፣ ናምሩድ የፋርስ ሃይማኖት ሰባኪ ዞራስተር (ዛራጡሽትራ) ነበረ ። ደግሞ የባቢሎን አምላክ ሜሮዳክ አፈ ታሪክ ከናምሩድ ሕይወት እንደ ተወሰደ ተብሎአል። ሌሎች ሃሣብ ናምሩድ በዕውኑ የአሦር ንጉሥ 1ኛ ቱኩልቲ-ኒኑርታ  ነበር ይላል። አሌክሳንድር ሂስሎፕ በ19ኛ ክፍለ ዘመን የጻፈው በግሪክ አፈ ታሪክ ዘንድ የመስጴጦምያ ንጉስና የሴሚራሚስ ባል ኒኑስ ተመሳሳይነት አየ። 

በሱመራውያን ነገሥታት ዝርዝር የአካድ መስራች ታላቁ ሳርጎን ስለሆነ እንዲሁም በባቢሎን ዜና መዋእል ስነድ (ABC 19:51) ሳርጎን የባቤል መስራች ስለ ሆነ፣ አንድ ሃልዮ ሳርጎንንና ናምሩድን አንድ ያደርጋቸዋል። ነገር ግን ሌሎች ጽሕፈቶች አካድ ከሳርጎን አስቀድሞ በኤንሻኩሻና እና በሉጋልዛገሢ ዘመናት እንደ ነበር ስለሚመሰክር ይህ ሃሳብ ተጠይቋል። በተጨማሪ ሌላ ሰነድ (ABC 20:18-19) ሳርጎን ባቢሎንን ወደ አካድ ዙሪያ እንዳዛወረው ይላል።




#Article 216: ወሎ (297 words)


ወሎ  (Wollo) በሰሜን ምስራቅ የኢትዮጵያ ክፍል የሚገኝ ታሪካዊ አውራጃ እና ክፍለ ሀገር ሲሆን ዋና ከተማዋ ደሴ ነው። ከ1700ዓም በፊት ከፊል የወሎ አካል  ስሙ   አምሐራ  የነበረ ሲሆን  17ኛው ክፍለ ዘመን የኦሮሞ መስፋፋትን ተከትሎ በአከባቢዉ  በፊት አምሐራ ተብሎ የሚጠራውን አካባቢ ጨምሮ  ወሎ በሚባል ሰፊ ግዛት አካታች በሆነ ስያሜ  እና ማንነት  መጠራት ጀመረ ። ወሎ እንዳሁኑ በስፋት ከመዋሀዱ በፊት በቀድሞ ካርታዎች አምሐራ በሚል ስያሜ በሰሜን በሽሎ ወንዝ፣ በደቡብ ጃማ ወንዝ፣ በምእራብ አባይና በምስራቅ አፋር ያዋስኑት ነበር።
የወሎ ድንበር በየዘመኑ የመስፋት እና የመጥበብ ሁኔታዎች የሚታይበት ሲሆን በአንዳንድ የታሪክ አጋጣሚዎች እስከ አሰብ ድረስ ይሰፋ ነበር፡፡ ከጣልያን ጦርነት ቀጥሎ በ1933 ዓ.ም. አዛቦ፣ ላስታ፣ ራያ፣ ዋግ እና የጁ ይፋዊ የወሎ ግዛቶች ሆኑ። ወሎ እጅግ ሰፊ የሚባል ጠቅላይ ግዛት የነበረ ሲሆን በስፋቱም ከሀረርጌ፣ ከባሌ እና ከሲዳሞ በመቀጠል በአራተኛ ደረጃ ላይ የቀመጣል ስፋቱም 79,4002 ስኩየር ኪሎሜትር ነበር፡፡

በ1987 ዓ.ም. ኢህአዴግ የደርግን ስረአት በሀይል በመጣል አገሪቱን ከተቆጣጠረ በኋላ ባወጣው ሕገ መንግሥት መሠረት፣ ወሎ የሚባል ራስገዝ የአውራጃ አስተዳደር በማስቀረት ግዛቱን በአፋር ክልል፣ ትግራይ ክልል፣ እና አማራ ክልል እንዲከፈል ተደረገ። ከዚህ የወሎ ግዛት መበታተን ጀምሮ የወሎ መዲና የሆነችው ደሴ ብዙ የልማት ዝቅተት አጋጥሟታል፣ መንገዶቿ ፈራርሰዋል፣ ከተማዋም  ከመቶ አመት በላይ ስም ያላት ብትሆንም አስርት አመታት እድሜ ባላቸው ከተሞች ተበልጣ በመታየቷ የወሎ ህዝብን አንገት ያስደፋ ጉዳይ እንደሆነ ዘልቋል። አንዳንድ ምሁራን የወሎን የቁልቁለት ጉዞ ከተለያዩ የታሪክ አጋጣሚዎች ጋር ለማያያዝ ቢሞክሩም ሁሉንም የሚያሳምን አይመስልም። ከታሪክ አጋጣሚዎች በላይ የወሎ እና የደሴ ከተማ ስመ ገናናነትን ውሀ የቸለሰበት ጉዳይ ህዝቡ አንድ ሆኖ በወሎየነት መንፈስ አለመሰለፉና የራሱን ታሪክ ጠንቅቆ ባለመረዳቱ ነው ይባላል። ምንም እንኳ የወሎ ህዝብ ስመገናናነት እንደ ድሮው ባይሆንም አሁን ላይ ባለው የእርስበርስ መስተጋብር፣ ባህል፣ ወግ፣ የሀይማኖት መቻቻል እና የሀሳብ አሸናፊነት ትልቅ ልዕልና እንዳለው በማሳየት ላይ ይገኛል።

ወሎ የክርስትናና እስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ተከባብረውና ተዋደው በጋራ የሚኖሩበት የመቻቻል ተምሳሌት የሆኑ ህዝቦች መገኛ ድንቅ አካባቢ ነው።

ከሀይማኖቱ ውጭ ካለ ሌላ እምነት ተከታይ ህዝብ ጋር በሰላም በመኖርም ለአለም ምሳሌ የሆነ ህዝብ ነው። ወሎ እጅግ ውብ የሆኑ ልጃገረዶች መፍለቂያ ነው።




#Article 217: ሱመር (496 words)


ሱመር (አካድኛ፦ ሹመር፣ ግብጽኛ፦ ሳንጋር፣ ዕብራይስጥ፦ ሰናዖር) በጥንታዊ መካከለኛ ምሥራቅ አለም በቅድሚያ ሥልጣኔ የሚባል ኹኔታ የደረሰለት አገር ነበር። ዘመኑ ከታሪካዊ መዝገቦች መነሻ ጀምሮ ይታወቃል። 'ሱመራዊ' ማለት ሱመርኛ የቻሉ ወገኖች ሁሉ ነው። ከጥንታዊ ግብፅ እና ከሕንዶስ ወንዝ ሸለቆ ሥልጣኔ ጋራ ከሁሉ መጀመርያ ሥልጣኔ ካሳዩት አገሮች አንዱ ነው ይባላል። 

ሹመሩ የሚለው ስም በጎረቤቶቻቸው በአካድ ሰዎችም ሲጠራ ሕዝቡ ለራሳቸው የነበራቸው ስም ሳግ-ጊ-ጋ (ጥቁር ራስ ያላቸው) ነበር። አገራቸውንም ኪ-ኤን-ጊር ይሉት ነበር። በተረፈ በኬጢያውያን መዝገቦች አገሩ ሳንሃር፣ በግብጽ አማርና ደብዳቤዎች ሳንጋር፣ በመጽሐፍ ቅዱስም ሰናዖር ይባላል።

ጽሕፈት በመፍጠሩ የታሪክ መጋረጃ ሲከፈት፣ ሱመራውያን በደቡብ መስጴጦምያ (ከጤግሮስና ኤፍራጥስ ወንዞች መኃል፣ የዛሬው ኢራቅ) ይገኙ ነበር። 

ጥንታዊው የሱመራውያን ነገሥታት ዝርዝር የያንዳንዱን ከተማ ሥርወ መንግሥት ይዘርዝራል። ከነዚህም በመግቢያው ያላቸው ነገሥታት ከማየ አይህ በፊት እንደ ነገሡ ይላል። እነዚህ ስሞች ትውፊታዊ ሊሆኑ ይችላል። ከሌላ አፈ ታሪክ ምንጭ የታወቀው በዝርዝሩ የተገኘ ስም የኪሽ ንጉሥ ኤታና ነው። ከዚያ በኋላ የኡሩክ መጀመርያ ነገሥታት ኤንመርካር፣ ሉጋልባንዳ፣ ዱሙዚድና ጊልጋመሽ ሁላቸው ከሌሎች ትውፊቶች ይታወቃሉ። ከሥነ ቅርስ የታወቀው መጀመርያ ስም ኤላምን ያሸነፈው የኪሽ ንጉሥ ኤንመባራገሲ ነው። እሱ ደግሞ የጊልጋሜሽ ትውፊት በተባለ ጽሑፍ ስለሚገኝ ይህ ለጊልጋሜሽ ታሪካዊ ሕልውና ምናልባትነት መስጠቱ ይታመናል። 

ከዚህ በኋላ የኡር ንጉስ መስ-አኔ-ፓዳ ኡሩክንና ኪሽንም አሸንፎ «የኪሽ ንጉሥ» የሚልን ስያሜ ወሰደ። በሚከተለውም ዘመን የሱመር ላዕላይነት ከኡር ወደ አዋን (ኤላም)፣ ከአዋንም ወደ ኪሽ፣ ከኪሽም ወደ ሐማዚ በመፈራረቅ ይዛወር እንደ ነበር መዘገቦች ይሉናል። 

የኡሩክ ንጉሥ ኤንሻኩሻና ሐማዚን፣ አካድን፣ ኪሽንና ኒፑርን በማሸነፉ መጀመርያ 'የሱመርና የአካድ ንጉሥ' የተባለ ነበረ። ከዚህ ቀጥሎ የላጋሽ ንጉሥ ኤ-አና-ቱም ሱመርን ሁሉ ኤላምንም በከፊል አሸነፈ። ከተገኙ ጽላቶች መሠረት፣ የሱ መንግሥት አደራረግ ተገዥ ወገኖችን ማስፈራራትና ግፍ መሆኑን ልንገምት እንችላለን። እሱ እንደ ሞተ፣ ግዛቱ ለጊዜው በየከተማው ተከፋፈለ። 

በኋላ የአዳብ ንጉሥ ሉጋል-አኔ-ሙንዱ በዘመቻ እስከ ሜዲቴራኔያን እና እስከ ጣውሮስ ተራሮች (ትንሹ እስያ) ና እስከ ዛግሮስ ተራራዎች (ፋርስ) ድረስ እንዳቀና ይመዘገባል። ይህም ማርቱ፣ ሊባኖስ፣ ሹቡር፣ ኤላምና ጉታውያን የጠቀለለ ነው። የሱም ግዛት በመሞቱ እንደ ከተሞቹ ብዛት ተሰባበረ። 

ላዕላይነቱ አሁን እንደ «ቅዱስ የሮማ መንግሥት ንጉስ» የመሰለ ማዕረግ ሆኖ ነበር። ከከተማ-አገሮቹ የማሪ ንጉስ ማዕረጉን ከያዘ፣ ከዚህ ወደ አክሻክ ንጉሥ ተዛወረ። የአክሻክ ንጉስ ፑዙር-ኒራሕ ክፉ ሆኖ፣ የሱመር ቄሳውንት መንግሥቱን ለአንዲት ሴት ባለ ጠጅ ቤት ለኩግ-ባው ንግሥት ሆና እንዳሸለሙላት የሚል ሰነድ አለ። በዚህም ዘመን በላጋሽ፣ ከአንድ ክፉ ንጉሥ ሉጋላንዳ በኋላ፣ የላጋሽ ንጉሥ ኡሩካጊና የራሱን ሕገጋት አውጥቶ ለድኆች ማሻሻል አደረገ፤ በተጨማሪ 1 ሚስት ቀድሞ ብዙ ባሎችን የምታገባበትን ልማድ ከለከለ።

በኡሩካጊና ዘመን መጨረሻ፣ የኡማ ንጉሥ ሉጋል-ዛገ-ሲ ላጋሽን አገለበጠውና ዋና ከተማውን በኡሩክ አድርጎ መንግስቱን ከፋርስ ወሽመጥ እስከ ሜዲቴራኔያን ድረስ እንደ አስፋፋ በጽላቶች ተቀርጿል።

ከሉጋል-ዛገ-ሲ ላይኛነቱን የያዘ ሱመራዊ ሰው ሳይሆን የአካድ ንጉሥ ታላቁ ሳርጎን ነበር። የአካድ ሰዎች ሴማዊ ቋንቋ፣ አካድኛ ይናገሩ ነበር። ቋንቋቸውን በሱመር እንዲሁም በኤላም ይፋዊ በግድ አደረጉ። በጽላት ዜና መዋዕል መዝገቦች መሠረት፣ ሳርጎን የባቢሎንን ሥፍራ ወደ አካድ ዙሪያ አዛወረ።

የአካድ መንግሥት በጉታውያን ዕጅ ከወደቀ በኋላ የላጋሽ ንጉሥ ጉዴአ ተነሣ። ከዚያ በኋላ የኡር ንጉስ ኡር-ናሙ ላጋሽን አሸንፎ ላይኛነቱን ያዘ። እሱ በተለይ የኡር-ናሙ ሕገጋት ስለ ተባለው ፍትኅ ይታወሳል። በዚህ ወቅት ብዙ ሴማዊ ቋንቋ ያላችው አሞራውያን ወገኖች ወደ መስጴጦምያ ስለ ገቡ፣ የሱመርኛ ጥቅም ቀስ በቀስ ቀነሰ። ሆኖም ሱመርኛ በትምህርት ቤትና በሃይማኖት ረገድ ይቀጠል ነበር። 

ይህ የኡር መንግሥት እስከ 1879 ዓክልበ. ግድም (ኡልትራ አጭር አቆጣጠር)  ኤላማውያን እስከ ወረሩት ድረስ ቆየ። የዚያ ውጤት አሞራውያን ለራሳቸው ከተሞች ያዙና የሱመር ሃይል ጠፋ። ከነዚህ ከተሞች መካከል ባቢሎን በንጉስዋ ሃሙራቢ ወቅት ላይኛነቱን ለረጅም ወራት መሰረተች።




#Article 218: ሐይክ (255 words)


ሐይክ (አርሜንኛ፦ Հայկ) በአርሜኒያ አፈ ታሪክ ውስጥ የአርሜናዊ ህዝብ መስራች ነበረ። የሱ አፈታሪክ በታሪክ ጸሐፊው ሙሴ ሖሬናዊ 5ኛ ክፍለ ዘመን መጽሐፍ የአርሜኒያ ታሪክ በተለይ የሚገኘው ነው። 

በሙሴ ሖሬናዊ ዘንድ ሐይክ  የያፌት ልጅ ጋሜር ልጅ የቶርጎም (ቴርጋማ) ልጅ ነው። ሐይክ ደግሞ የሐይካዙኒ ሥርወ መንግሥት መስራች ይባላል። በታሪክ ጸሐፊው ጇንሸር ዘንድ፣ ሐይክ 'የሰባት ወንድማማች መስፍን ሆኖ፣ መጀመርያ ዓለሙን በሙሉ እንደ ንጉሥ ለነገሠው ለረጅሙ ሰው ለናምሩድ ያገልግል ነበር'።  

'ሐይክ' ደግሞ በአርሜንኛ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም የኦሪዮን ከዋክብት ስም ነው። (ኢዮብ 38፡31)

በሙሴ ሖሬናዎ መሠረት፣ በባቢሎን እየኖረ የቶርጎማ ልጅ ሐይክ ልጁን አርማኔያክን ከወለደ በኋላ፣ ትዕቢተኛው ቲታናዊው ቤል (እሱም ሙሴ እንደሚለው ናምሩድ ነው) እራሱን የአለም ሁሉ ንጉሥ ስላደረገ፣ ሐይክ ከቤተሠቦቹ ከ300ም ሰዎች ጋራ ወደ አራራት አገር ፈልሶ ሐይካሸን የተባለ መንደር ይመሠረታል። በመንገዱ ላይ ለልጅ-ልጁ ለካድሞስ አንድ ሠፈር ይተወዋል። ሐይክ ወደ ባቢሎን እንዲመልስ ግድ እንዳለው የሚል መልእክት ለማቅረብ ቤል ከልጆቹ አንዱን ወደ ሐይክ ልኮ እሱ ግን እምቢ ይለዋል። ከዚያ ቤል ከግዙፍ ሠራዊቱ ጋራ በሱ ላይ ቢዘምትም ካድሞስ ግን ስለመቅረቡን ሐይክን ያሳውቀዋል። ሐይክ የራሱን ሠራዊት በቫን ሐይቅ ዳርቻ ሰብስቦ የቤል ባርዮች እንዳንሆን ወይም ቤልን አሸንፈን መግደል ወይም በሙከራው መሞት አለብን ብሎ ይላቸዋል።

ከዚያ በኋላ ሐይክ የቤልን ሠራዊት በአንድ ተራራ ላይ ያገኛቸዋል። ሙሴም ይህን ተራራ በዳስታከርት ሥፍራ እንደሚገኝ ይላል። ቤል እራሱ በሠራዊቱ ፊት ይታያል። በፍልሚያው መኅል ሄይክ በእድለኛ ፍላጻ ቤልን ገድሎ ሠራዊቱ ተደናገረና ድል ሆነ።

በሌሎች ደራሲዎችም ዘንድ፣ ይህ ፍልሚያ በቫን ሐይቅ ደቡብ-ምሥራቅ በጁላመርክ ዙሪያ በበድዩጻዝናማርት ከክርስቶስ በፊት በ2501 አመታት ነበረ።

'ሐይካበርድ' የተሰየመ አምባ በውጊያው ሥፍራ ላይ መሠርቶ ስሙ 'ሐይካሸን' የተባለ መንደር ይሠራል። የፍልሚያው አገር 'ሐይክ' ይለዋል፤ የዛሬም አርሜኒያ ስም 'ሃያስታን' የአርሜኒያም ሕዝብ 'ሃይ' ይባላል። እንዲሁም በጥንት በኬጢያውያን ጽሕፈቶች በዙሪያው ሐየሣ የተባለ ብሔር ነበረ።




#Article 219: ትርኪ ተራራ (132 words)


ትርኪ ተራራ በቱልሳ አካባቢ ኦክላሆማ ክፍላገር አሜሪካ ውስጥ ከአርካንሳው ወንዝ አጠገብ የሚገኝ ሲሆን እንዲያውም ተራራ ሳይሆን ትልቅ ኮረብታ ነው። በዚያ ላይ በተገኙት ድንጋዮች ላይ ያሉት ምልክቶች 'የጥንታዊ አሜሪካ መዝገቦች' ተብለዋል። በአንድ ዋሻ ውስጥ የተቀረጹት ስዕሎችና ምልክቶች ከውቅያኖስ ማዶ የመጡት መርከበኞች ሥራ መሆናቸውን አንዳንድ ምሁር ያምናል።

በዋሻው የሚታይ አንዱ ምልክት የላቲን አልፋቤት ፊደላት «PIA» ይመስላል። ከዚህ በላይ አንዳንድ መስመር ሊታይ ይችላል። አወዛጋቢው ምሁር ባሪ ፌል ይህን «PIA» የሚለውን ቃል ከ«A»-ኡ ቅርጽ የተነሣ እጅግ ጥንታዊ መሆኑን ገመተ። በሱ አስተሳሰብ በከነዓን ቋንቋ የተጻፈው 'ፓያ' ወይም 'ነጭ' ለማለት ነው። መስመሮቹ ደግሞ የኦጋም ፊደል መስለውት በጎይደሊክ ቋንቋ 'ጒን' ወይም 'ነጭ' እንደሚል ያምናል። በሁለት ቋንቋዎች የተጻፈ ቃል ማለቱ ይሆናል። 

ይህ ሥፍራ ልክ በጋዲር ('የሄራክሌስ ዓምዶች' ወይም የዛሬው ካዲዝ) ኬክሮስ ላይ (36 N) ይገኛል። በመጽሐፈ ኩፋሌ መሠረት ከጋዲር ወደ ምዕራብ የሚሄድ መስመር የሞሳሕ ያፌት ርስት ከከነዓን ካም ርስት ይለያል።




#Article 220: ግዕዝ (688 words)


ግዕዝ ፡ በአፍሪካ ቀንድ ፡ በኢትዮጵያና ፡ በኤርትራ ፡ በጥንት ፡ የተመሠረተና ፡ ሲያገለግል ፡ የቆየ ፡ ቋንቋ ነው። የግዕዝ ፡ አመጣጥ ፡ በግምት ፡ የዛሬ ፡ ፫ ፡ ሺህ ፡ ዓመት ፡ ከየመን ፡ እና ፡ ደቡብ ፡ አረቢያ ፡ በመነሣትና ፡ ቀይ ፡ ባሕርን ፡ በመሻገር ፡ በኤርትራ ፡ እና፡ ሰሜን ፡ ኢትዮጵያ ፡ ውስጥ ፡ ከሰፈሩ ፡ የተለያዩ ፡ የሳባውያን ፡ ነገዶች ፡ ቋንቋና ፡ በጊዜው ፡ ሰሜን ፡ ኢትዮጵያ ፡ ይነገሩ ፡ በነበሩ ፡ ቋንቋዎች ፡ ዘገምተኛ ፡ ውኅደት ፡ ነው። በአክሱም ፡ መንግሥትና ፡ በኢትዮጵያ ፡ መንግሥት ፡ መደበኛ ፡ ቋንቋ ፡ ነበር።

ግዕዝ ፡ ከአማርኛና ፡ ሌሎች ፡ ኢትዮ-ሴማዊ ፡ ቋንቋዎች ፡ ጋር ፡ ሲወዳደር ፡ «ንጹሕ» ፡ ሴማዊ ፡ ቋንቋ ፡ ነው። ግዕዝ ፡ እስከ ፡ ፲ኛው ፡ ክፍለ-ዘመን ፡ መጀመሪያ ፡ ድረስ ፡ ዋነኛ ፡ የመግባቢያ ፡ ቋንቋና ፡ ልሳነ ፡ ንጉሥ ፡ ነበር። ከ ፲፫ኛው ፡ ክፍለ ፡ ዘመን ፡ ጀምሮ ፡ ግን ፡ ሙሉ ፡ በሙሉ ፡ መነገር ፡ አቁሞ ፡ በሰሜን ፡ ኢትዮጵያ ፡ በትግርኛ ፡ እንዲሁም ፡ በማዕከላዊው ፡ ክፍል ፡ ደግሞ ፡ በአማርኛ ፡ ተተካ። ዛሬ ፡ በኢትዮጵያ ፡ ኦርቶዶክስ ፡ ተዋሕዶ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ ሥነ-ስርዓት ፡ እንዲሁም ፡ በኤርትራ ፡ ኦርቶዶክስ ፡ ተዋሕዶ ፡ ቤተክርስቲያን ፣ በኢትዮጵያ ፡ ካቶሊክ ፡ ቤተክርስቲያን እና ፡ በቤተ-እስራኤል ፡ ሥነ-ስርዓቶች ፡ ይሰማል። በሰሜን፡ ኤርትራ ፡ የሚገኘ ፡ ትግረ ፡ የሚባል ፡ ቋንቋ ፡ ከሁላቸዉ፡ የሰሜን ፡ኢትዮጵያ ፡ቋንቋዎች፡ ለግእዝ ፡ በቅርብ ፡ ይዛመዳል ፡ እና። ትግረ ፡ ፸ በመቶ ፡ ግእዝ ፡ ነዉ ፡ እና ፡ በመቀጠል ፡ ትግርኛ ፡ እና ኣማርኛ። 

ቋንቋው ፡ የሴማዊ ፡ ቋንቋዎች ፡ አባል ፡ እየሆነ ፡ በደቡብ ፡ ሴማዊ ፡ ቅርንጫፍ ፡ ውስጥ ፡ ይካተታል። ደቡብ ፡ ሴማዊ ፡ በመባሉ ፡ ግዕዝ ፡ የሣባ ፡ ቋንቋ ፡ ቅርብ ፡ ዘመድ ፡ ነው። ግዕዝ ፡ የተጻፈው ፡ በግዕዝ ፡ ፊደል ፡ አቡጊዳ ፡ ነው። ይህም ፡ ፊደል ፡ ደግሞ ፡ ዛሬ ፡ ለአማርኛ ፣ ለትግርኛ ፡ እና ፡ ለሌሎችም ፡ ቋንቋዎች ፡ ይጠቀማል። በመላውም ፡ የአፍሪቃ ፡ አህጉር ፡ ውስጥ ፡ የመጀመሪያውና ፡ ብቸኛ ፡ አፍሪቃዊ ፡ የራሱን ፡ ፊደላት ፡ የያዘ ፡ ቋንቋ ፡ ሲሆን ፣ በዓለምም ፡ ላይ ፡ ዋናና ፡ የስልጣኔ ፡ አራማጅ ፡ ከሚባሉት ፡ ቋንቋዎች ፡ አንዱ ፡ ነው። 

በግዕዝ ፡ ጽሕፈት ፡ ፳፮ ፡ ፊደላት ፡ ብቻ ፡ ይጠቀሙ ፡ ነበር ፤ እነርሱም፦

ሀ ፣ ለ ፣ ሐ ፣ መ ፣ ሠ ፣ ረ ፣ ሰ ፣ ቀ ፣ በ ፣ ተ ፣ ኀ ፣ ነ ፣ አ ፣ ከ ፣ ወ ፣ ዐ ፣ ዘ ፣ የ ፣ ደ ፣ ገ ፣ ጠ ፣ ጰ ፣ ጸ ፣ ፀ ፣ ፈ ፣ ፐ

ናቸው። 

ሊቁ ፡ ሪቻርድ ፓንኩርስት ፡ እንደሚጽፍ ፣ አንድ ፡ ተማሪ ፡ በመጀመርያው ፡ አመት ፡ ፊደሉን ፡ ከተማረ ፡ በኋለ ፣ በሚከተለው ፡ አመት ፡ መጀመሪያይቱ ፡ የሐዋርያው ፡ የዮሐንስ ፡ መልእክትን ፡ ከአዲስ ፡ ኪዳን ፡ በግዕዝ ፡ ከትዝታ ፡ ለመጻፍ ፡ መማር ፡ ነበረበት። በሦስተኛው ፡ ደረጃ ፡ የሐዋርያት ፡ ሥራ ፡ በአራተኛውም ፡ መዝሙረ ፡ ዳዊት ፡ በግዕዝ ፡ ማስታወስ ፡ ነበረበት። ይህንን ፡ ከጨረሰ ፡ ታላቅ ፡ ግብዣ ፡ ይደረግና ፡ ልጁ ፡ ጸሐፊ ፡ ይሆን ፡ ነበር።

በብሪቲሽ ፡ ቤተ-መጻሕፍት ፡ (የእንግሊዝ ፡ አገር ፡ ብሔራዊ ፡ ቤተ-መጻሕፍት) ፡ ውስጥ ፡ ፰፻ ፡ የሚያሕሉ ፡ የድሮ ፡ ግዕዝ ፡ ብራናዎች ፡ አሉ። 

በኢ.ኦ.ተ.ቤ. ፡ ትምህርቶች ፡ ዘንድ ፣ ግዕዝ ፡ የአዳምና ፡ የሕይዋን ፡ ቋንቋ ፡ ነበር። ፊደሉን ፡ የፈጠረው ፡ ከማየ አይኅ ፡ አስቀድሞ ፡ የሴት ፡ ልጅ ፡ ሄኖስ ፡ ነበረ። ከባቢሎን ፡ ግንብ ፡ ውድቀት ፡ በኳላ ፣ ከአርፋክስድ ፡ ወገን ፡ የዮቅጣን ፡ ልጆች ፡ ቋንቋውን ፡ እንደ ፡ ጠበቁት ፡ ይባላል። የዮቅጣን ፡ ልጅ ፡ ሣባ ፡ ነገዶች ፡ ከዚያ ፡ ቀይ ፡ ባሕርን ፡ አሻግረው ፡ ወደ ፡ ዛሬው ፡ ኢትዮጵያ ፡ ያስገቡት ፡ ይታመናል። እንዲሁም ፡ ካዕብ ፡ እስከ ፡ ሳብዕ ፡ (አናባቢዎችን ፡ ለመለየት) ፡ ወደ ፡ ፊደል ፡ የተጨመረበት ፡ ወቅት ፡ በንጉሥ ፡ ኤዛና ፡ ዘመን ፡ እንደ ፡ ነበር ፡ ይባላል።

 

የቱ

ሄኖክ ፡ መጀመርያ ፡ ቃሎች ፡ በጽሕፈት ፡ በግዕዝ ፡ የጻፈ ፡ እንደ ፡ ነበር ፡ ስለሚባል ፣ ይህ ፡ ቃል ፡ በማንኛውም ፡ የሰው ፡ ልጅ ፡ ቋንቋ ፡ ከሁሉ ፡ አስቀድሞ ፡ የተጻፈ ፡ መሆኑ ፡ በብዙዎች ፡ የኢትዮጵያ ፡ ሊቃውንት ፡ ይታመናል።




#Article 221: ሁኖርና ማጎር (137 words)


ሁኖርና ማጎር በሀንጋሪ አፈ ታሪክ ዘንድ የሁኖችና የሀንጋራውያን (ማውጃሮች) ቅድማያቶች ናቸው። 

በአንዳንድ መጻሕፍት መሠረት (ለምሳሌ የመካከለኛ ዘመን ላቲን ዜና መዋዕል ጌስታ ሁኖሩም ኤት ሁንጋሮሩም)፤ መንታ መሳፍንት ሁኖርና ማጎር የ'ታና' ልጅ 'መንሮት'ና የሚስቱ 'ኤነሕ' ልጆች ነበሩ። ይህ 'መንሮት' 200 አመታት ከማየ አይህ በኋላ በባቢሎን ሥልጣን እንደያዘ ሲባል መታወቂያው ደግሞ የኩሽ ልጅ ናምሩድ መሆኑ ይተረካል። መንታዎቹም በፋርስ አገር ተወልደው በአዞቭ ባሕር አጠገብ ለ5 አመት ሲቆዩ አንድ ቀን ነጭ አጋዘንን በማደን ላይ ሒደው ከአላኖች አለቃ 'ዱር' ሴት ልጆች መካከል ለራሳቸው ሚስቶችን አገኝተው እንደወሰዱ ወደ እስኩቴስም እንደ ሄዱ ይባላል።  የሁኖር ተወላጆች ሁኖች፣ የማጎርም ልጆች ማውጃሮች እንደሆኑ ይገለጻል።

ጥቂት ደራስያን ደግሞ 'ታና' ወይም 'ኩሽ' ከሱመራዊው ኪሽ ንጉሥ ኤታና ጋር ተመሳሳይነቱን አጠቁመዋል። ከዚህ በላይ የኩሻን መንግሥት (እስኩቴስ) ቅድማያት 'ኩሽ-ታና' በአፈ ታሪክ አጠቁመዋል።

በመካከለኛው ዘመን መጽሐፍ ክሮኒኮን ፒክቱም መሠረት ግን፣ ይህ 'ማጎር' እንዲያውም ማጎግ ሲሆን፣ እሱና ሁኖር የናምሩድ ልጆች ሳይሆኑ የያፌት ልጆች (በኤነሕ) ናቸው።




#Article 222: የጄኖቫ ቅዱስ መልክ (214 words)


የጄኖቫ ቅዱስ መልክ በጄኖቫ፣ ጣልያን በተገኘው ቅዱስ በርተሎሜዎስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚገኝ ስዕል ነው። ይህ ስዕል የኢየሱስ ክርስቶስ መልክ ለመግለጽ እንደታሠበ ይታመናል። 

በአንድ ትውፊት ዘንድ፣ ኢየሱስ በሕይወቱ ስብከት ሳለ የኦስሮኤኔ (በሶርያ) ንጉሥ 5 አብጋር በበሽታ ታምመው ኢየሱስ መጥቶ እንዲፈውሳቸው አንድን መልእክተኛ (ሐናን) ወደ ኢየሩሳሌም ልከው ነበር። ኢየሱስ ወደ ከተማው ወደ ኤደሣ ለመሔድ ጊዜ ስላልነበረው፣ ባንድ ጨርቅ ላይ መልኩን በተአምር አሳተመና ሐናን ስዕሉን ይዞ ወደ ንጉሡ እንዲሔድ ላከው። እንዲህም ሆኖ አብጋር ይህን ስዕል አይተው ከበሽታቸው ተፈወሱና ወዲያው ምዕመን ሆኑ። ስዕሉ ደግሞ በተአምር በመፈጠሩ 'ያለ እጅ የተሠራው' ተብሏል።

በጥንታዊ ታሪክ መጻሕፍት መሠረት ይህ ታምራዊ መልክ ያለበት ስዕል እስከ 936 ዓ.ም. በኤደሣ ቆይቶ በዚያ አመት ወደ ቢዛንታይን ዋና ከተማ ወደ ቊስጥንጥንያ ተዛወረ። እዚህም ፈረንጆች (መስቀለኞች) ከተማውን እስከ ዘረፉት አመት እስከ 1196 ድረስ እንዳደረ ይባላል።  ከዚያ በኋላ ምን እንደሆነበት ባይታወቀም ብዙ ቅጂዎች ስለተደረጉበት በአውሮጳ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ አንዳንድ ቅጂ ዕውነተኛው መልኩ እንዳሉ የሚል ልማድ አለ።  እንግዲህ በጄኖቫ ብቻ ሳይሆን በቫቲካን ከተማ ሮማ ተመሳሳይ ስዕል ቢገኝ እሱ እውነተኛው መሆኑ የሚያምኑ አሉ። 

በጄኖቫ ያለው ስዕል መገኛ የጄኖቫ ዶጄ (መስፍን) ሌዮናርዶ ሞንታልዶ በ1376 ዓ.ም. ለበርተሎሜዎስ ቤተክርስቲያን  እንዳወረሰው ይባላል። በተጨማሪ ሞንታልዶ ያገኘው፣ የቢዛንታይን ንጉሥ 5 ዮሐንስን ቱርኮች በወረሩበት ዘመን እርዳታ ስለ ሰጠ፣ ዮሐንስ ስዕሉን ስለ ወሮታው በምላሽ እንደ ሠጡት ይታመናል። 

የጣልያዊት ሊቅ ኮለት ዱፎር ቦዞ በ1961 ዓ.ም. ብዙ ልዩ ትንትና አድርጋ፣ የጄኖቫ ስዕል በሳንቃ ላይ የተለጠፈ ጨርቅ ከወርቃም ከፈፍ በታች መሆኑን ገለጠች።




#Article 223: ወላይታ (370 words)


ወላይታ በቀድሞ ሲዳሞ ጠቅላይ ግዛት ባሁኑ ደቡብ ክልል የሚገኝ ና የራሱ የሆነ ቋንቋና ባህል ያለው ሕዝብ ሲሆን ከሲዳማ፡ ከከምባታ፡ ከሃዲያና ተመሳሳይ ቋንቋ ከሚናገሩ ከኩሎ ኮንታ ከጎፋና ጋሞ ሕዝብ ጋር ይዋሰናል።
ወላይታ ህዝቡ በጣም የተደባለቀ ሲሆን በከተማ አከባቢ ልቆ የሚገኝ ኃይማኖት ኦርቶዶክስ ይሁን እንጂ በጠቅላላ አውራጃው ፕሮቴስታንትና እስልምና እምነት እየተስፋፋ ነው። 

የወላይታ ዞን አስራ ሁለት ወረዳዎች አሉት። እነሱም፦ 1ኛ - ዳሞት ጋሌ ዋና ከተማው ቦዲቲ፡  2ኛ -ዳሞት ወይዴ ዋና ከተማው፦ በደሳ፡ 3ኛ -ቦሎሶ ሶሬ ዋና ከተማው አረካ፡ 4ኛ -ሁምቦ ዋና ከተማው ጠበላ፡ 5ኛ - ኦፋ ዋና ከተማው ገሱባ፡ 6ኛ- ሶዶ ዙሪያ ዋና ከተማው ሶዶ፡  7ኛ- ኮይሻ ዋና ከተማው በሌ፡ 8ኛ- ቦሎሶ ቦምበ ዋና ከተማው ቦምበ እድገት፡ 9ኛ-ዳሞት ሶሬ ዋና ከተማው ጉኑኖ፡ 10ኛ- ዱጉና ፋንጎ ዋና ከተማው ቢጣና፡ 11ኛ ዳሞት ፉላሳ ዋና ከተማው ሻንቶ፡ እና 12ኛ ኪንዶ ዲዳዬ ዋና ከተማው ሀላለ ናቸው። 

ወላይታ ከደቡብ ካሉት አከባቢዎች በትምህርት፡ በልማትና በማህበራዊ ሁኔታዎች ልቆ ሊገኝበት የቻለበት ሁኔታዎች ይታያል። ይህም የሆነበት ምክንያት በቀደማዊ ኃ/ስላሴ ዘመነ መንግስት ምዕራባዊያን በብዛት ገብተው የአከባቢውን ሕዝብ ከመጽሓፍ ቅዱስ ጋር የቀለም ትምህርት አጣምረው ስለሰጡ እድሉን በመጠኑም ቢሆን በመጠቀማቸውና በየጊዜው በአከባቢው የሚመደቡ አስተዳዳሪዎች ጠንካራ በመሆናቸው ነው ይባላል። 

በቀድሞ ዘመን በወላይታ በርካታ ምሁራን ብቅ ብቅ ብለው ነበር። ከነዚህም ምሁራን በደቡብ ኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው ዶክተርና የጦር ጄኔራል ለመሆኑ የበቁ ብ/ጄኔራል ዶ/ር ጋጋ ኤልጆ በአብይነት ሲጠቀሱ ፦ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ካንገት በላይ ስፔሻሊስት ዶ/ር ታዲዮስ ሙንኤ; ኢትዮጵያ ካሏት ጥቂት የፕላስቲክ ቀዶ ጥገና ባለሙያዎች አንዱ የሆኑት ዶ/ር ቀለሙ ደስታ ፡አሜሪካን አገር በዩኒቨርስቲ ኦፍ ፍሎሪዳ ታዋቂ ሓኪምና ረዳት ፕሮፌስር የሆኑ ዶ/ር ይስሓቅ ዳልኬ ናቸው። ዶ/ር ይስሓቅ በትምህርት ውጤታቸው ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ልቀው በመገኘታቸው ከአጼ ኃይለስላሴ እጅ የወርቅ ሰዓት የተሸለሙ 2ኛው የወላይታ ተወላጅ ሲሆኑ ዳዊት ጦሼ ደግሞ የመጀመሪያው ናቸው።   

የወላይታ ታሪክ ሲወሳ የወላይታ የልማት ሰው በሚል የሚታወቁ ወ/ሰማዕት ስም ሁሌም አብሮ ይወሳል። ደ/ች ወ/ሰማዕት በአስተዳዳሪነት በቆዩበት በአጼ ኃ/ስላሴ ዘመነ መንግስት ብዙ የልማት ስራዎችን አከናውነዋል። ከሰሯቸው አበይት ስራዎቻቸውም ፦ 

ደ/ች ወ/ሰማዕት በወቅቱ ማንም ወጣት የሆነ መንገድ ዳር ቆሞ ሲያወራ ካዩ ይበሳጩ እንደነበርና ከመኪናቸው ወርደው ስራ እንዲሰሩ ወይም ት/ቤት እንዲሄዱ ይመክሩም እንደነበር ይነገርላቸዋል።

ደ/ች ወ/ሰማዕት በሰብዓዊ መብት ረገድ ግን ጨቋኝ: ህዝብን የማያከብር: ግብረ-ገብነት የጎደለው ሰው ነው:: ገዥ መደብ ነኝ እያለ የወላይታ አባቶቻችን ሲያሰቃይ ነበሩ:: በ ወ/ሰማዕት ተመቶ የሞቱ ወላይታ አባቶችም እንዳሉ የ ቦጋለ ዋለሉ ቤተሠብ ይናገራሉ::

ባሁኑ ጊዜ ባገር ውስጥና ከአገር ውጭ በተሳተፉበት የሙያ ዘርፍ ሁሉ ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር አንቱታን የተጎናጸፉ የወላይታ ተወላጆች ብዛት በርካታ ነው።

ወላይታ የኢትዮጵያ ብሔር ነው።

ዶ/ር ተመስገን ላንቴራ




#Article 224: ሌቱም አይነጋልኝ (179 words)


ሌቱም አይነጋልኝ በውቤ በረሃ በ ፲፱፻፶፯ ዓ.ም. ተጀምሮ በፈረንሳይ አገር ኤክስ አን ፕሮቫንስ የተፈጸመ መጽሐፍ ነው።
 
ደራሲው ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር መጽሐፉ እንዲታተም እሱ ደንታ ባይኖረውም...በመጽሐፉ ውስጥ እንደጠቀሰው «እኔ 'ኮ ያደረብኝ ለዘብተኛ ልዝብ ዛር በበቂ ደሞዝና 'ትርፍ' ስኣት 
እያምበሻበሸ ስላበረታታኝ ፃፍኩ'ንጂ፤ ይታተም አይታተም ደንታ አልነበረኝም።»

ወዳጆቹ ቢሞክሩም በመንግስት ሳንሱር «ለአንባቢያን የማይገቡ ግልጽ የወሲብ ቃላቶች አሉበት» በሚል ምክንያት እየታገደ ለሃያ አምስት ዓመታት በአንባቢዎቹ እጆች በእጅ እየተገለበጠ ሲነበብ ኖሯል።

በአሁኑ ሰዓት በመጀመሪያ እነዚያ ወሲባዊ ቃላቶችን «ለስለስ» ባሉ ቃላቶች በመተካት ለአንባቢያን እንዲደርስ መጽሐፉ ታትሞ ለገብያ የቀረበ ሲሆን በመቀጠልም በአገራችን አቆጣጠር በ1999 ያንኑ መጽሐፍ ደራሲው የተጠቀመባቸውን ቃላቶች ትክክለኛ ግልባጭ የያዘ «ሌቱም አይነጋልኝ...እንደ ወረደ» ለአንባቢያን ቀርቧል።

ስብሐትም እዚሁ ዕትም ላይ «እንግዲህ አንባብያን ሆይ፤ በገዛ ታሪኬ፤ በገዛ ሦስት ሺ ዘመን ያገሬ ክርስትና፤ በገዛ ውቤ በረሀዬ፤ የኖርኩትን፤ ያየሁትን፤ የሰማሁትን፤ በተቻለኝ አቅምና በታደልኩት የትረካ ተሰጥዎ ለአራዳዎችም ለፋራዎችም ያገሬ ልጆች (ያውም ከሊቅ እስከ ደቂቅ!) ለምን አላበረክትላቸውም? አራዳዎቹም አብረውኝ ደስ ይላቸዋል፤ ፋራዎቹም ድብርታቸው ይብስባቸውና አንጀቴ ቅቤ ይጠጣል፤ ቀኑ የፆም ቢሆንም፤ እና እኔ የቄስ ልጅ፤ የደብተራ የልጅ ልጅ በመሆኔ የምኮራ ብሆንም።
ያውም መብቴ በህገ መንግስት እየተጠበቀልኝ! ለሁላችሁም እንሆ በረከት!» እያለ ይኼንን የሚይስቅ፤ የሚያዝናና እና የ'ውቤ በርህን' የ፲፱፻፶ዎች ታሪክ 'የሚያስተምረን' መጽሐፍ አቅርቦልናል።




#Article 225: ቋንቋ (108 words)


ቋንቋ የድምጽ፣ የምልክት ወይም የምስል ቅንብር ሆኖ ለማሰብ ወይም የታሰበን ሃሳብ ለሌላ ለማስተላለፍ የሚረዳ መሳሪያ ነው። በአጭሩ ቋንቋ የምልክቶች ስርዓትና እኒህን ምልክቶች ለማቀናበር የሚያስፈልጉ ህጎች ጥንቅር ነው። ቋንቋዎችን ለመፈረጅ እንዲሁም ለመክፈል የሚያስችሉ መስፈርቶችን ለማስቀመጥ ባለው ችግር ምክንያት በአሁኑ ሰዓት በርግጠኝነት ስንት ቋንቋ በዓለም ላይ እንዳለ ማወቅ አስቸጋሪ ነው። እንደ ተለያየ መስፈርት ግምት ከ3000 እስክ 7000 ቋንቋዎች በአለም ላይ እንዳሉ ስምምነት አለ። 

የሰው ልጅ ቋንቋ በተፈጥሮ የሚገኝ ሲሆን ህጻናት ቋንቋን በደመ ነፍስ ይማራሉ። በተፈጥሮ የሚገኙ የሰው ልጅ ቋንቋዎች ከድምጽና ከየሰውነት ክፍሎች ምልክት ይፈጠራሉ። በሺሆች የሚቆጠሩ የሰው ልጆች ቋንቋዎች ቢኖሩም የሁሉም የጋራ የሆኑ ቋሚ ጸባዮች አሏቸው። እኒህ ቋሚ ጸባዮች በሁሉም የተፈጥሮ ቋንቋውች ሠርጸው የሚገኙ እንጂ ላንዱ ሰርተው ላንዱ የማይሰሩ አይደሉም። 




#Article 226: ጃቫ (252 words)


ጃቫ (Java) ስነ ፍርገማ በቅርብ ታዋቂነትንና ተቃባይነትን እያገኘ ከመጡ ፍርገማ ቋንቋዎች አንዱ ነው። ጃቫ ተመራጭ ካደረጉት ዋና ባሀሪዎቹ አንዱ በፕላትፎርም አለመወሰኑ ነው። ይሀም ማለት በጃቫ የተጻፈ ትግበራ (አፕሊኬሽን) የጃቫ ቨርቹአል ማሽን ባለበት ሁሉ መሮጥ መቻሉ ነው። ስለዚህ በጃቫ ስራአት የሚጻፍ ኮድ በመጀመሪያ ኮምፓይል ከተደረገ በኋላ ኮምፓይለሩ አዲስ ዶክመንት ይፈጥራል። ይህም ማለት ኮምፓይለሩ የሚፈጥረው አዲስ ዶክመንት በጃቫ ባይት ኮድ ሲሆን የሚተገበረው (ኢምፕልመንት የሚደረገው) በያቫ ቨርቹዋል ማሽን ነው። እናም ጃቫን ከነሌሎቹ የሚለየው ምንም አይነት ቁስ ሳይጨመር ሌላ ማሽን በመጠቀም ፋንታ በሶፍትዌር ብቻ መስራት መቻሉ ነው። ስለዚህ የሶፍትዌሩ ስም ጃቫ ቨርቹአል ማሽን ነው። 

  

ጃቫን ለመምረጥ ሌላው ዋናው ምክንያት በነጻ መገኘቱ ነው። ስለሆነም ጃቫን ከሚከተለው ሊንክ  ወይም ማስፈርጠሪያ ላይ ዳውንሎድ ማድረግ ይቻላል፤
ጃቫን ኢንስቶል ካደረጉ በኋላ ተጨማሪ መሳሪያ (ኢንቲግሬትድ ዴቨሎፕመንት ቱል) መጠቀም ይቻላል። ይህም በኮማንድ ላይን ከመጠቀም የቀለለ ነው። ይሁን እንጂ ብዙ አይነት አይ.ዲ.ኢ. (IDE) ስላለ የእያንዳንዱ አጠቃቀም ከሌላው አይነት ይለያል። በብዛት የሚታወቀው አይ.ዲ.ኢ ኔትቢንስ 5.5 ይባላል። ኔትቢንስን ከሚከተለው ሊንክ ላይ ማግኘት ይቻላል፤

በእጅ ታይፕ በማድረግ የጃቫን ጥሬ ኮድ ፋይል ካስገባን በኋላ ጥሬ ኮዱን በጃቫ ኮምፓይለር ኮምፓይል ይደረጋል፤ ይህም ማለት በእጅ የተጻፈው ምንጭ ኮድ ከስህተት ነጻ መሆኑንና ለማሽን በሚገባ ቋንቋ በትክክል መተርጎሙን ማረጋገጥ ነው። ኮምፓይል የተደረገው ባይትኮድ በማንኛውም ጃቫ ቨርቹአል ማሽን ላይ መሮጥ ይችላል።

የጃቫ ምንጭ ኮድ በHelloWorld.java መልክ መቀመጥ ይኖርበታል። ይህም የጃቫ ምንጭ ፋይል ነው። በጃቫ ምንጭ ፋይል ውስጥ ክላስ ይቀመጣል። ክላስ የፕሮግራሙን ቁራጭ ያመለክታል። ወይም አንድ ክላስ ብቻውን ፕሮግራም ሊሆን ይችላል። HelloWorld የሚለው ቃል በተጠቀሰው ምንጭ ፋይል ውስጥ (ማለትም በ HelloWorld.java ውስጥ) የክላሱን ስም ያመለክታል። በክላስ ውስጥ ሜተድ (method) የሚባል ነገር ይቀመጣል። አንድ ክላስ ብዙ ሜተዶች ሊኖሩት ይችላሉ። በሜተድ ውስጥ ስቴትመንቶች ይቀመጣሉ ማለት ነው።




#Article 227: አርፋክስድ (303 words)


 

አርፋክስድ (ዕብራይስጥ፦ אַרְפַּכְשָׁד /አርፓክሻድ/፣ አረብኛ፦ أرفخشذ /አርፋሕሻድ/) በኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 10 ዘንድ የሴም ልጅና የቃይንም አባት ነው። (በዕብራይስጥ ትርጉም ግን የቃይንም ስም የለምና በቀጥታ የሳላ አባት ነው።) 

በመጽሐፈ ኩፋሌ 8፡15 አማርኛ ትርጉም የሴም ልጆች ኤላም፣ «አቡር»ና አርፋክስድ ከማየ አይህ ፬ኛ አመት በኋላ ተወለዱ ሲል፣ በሌሎቹ ትርጉሞች (እንደ ግሪክ፣ ሶርያ) ግን ኩፋሌ ከዘፍጥረት ጋር በመስማማት በ«አቡር» ፈንታ «አሹር» (አሦር) አለው (ዘፍ. 10፡22)፤ አርፋክስድም በማየ አይህ ፪ኛ አመት እንደ ተወለደ (ዘፍ. 11፡10) ይላል። 

በኩፋሌ 8፡34 መሠረት አርፋክስድ ሚስቱን የኤላም ልጅ ሱስን ልጅ ራሱአያ አገባትና ልጁን ቃይናምን ወለደች። ቃይናም መጻሕፍት ከአባቱ ከአርፋክስድ እንደ ተማረ ይጨምራል። 

በኦሪት ዘፍጥረት 11 ዘንድ፣ አርፋክስድ ቃይንምን ሲወልድ ዕድሜው 135 አመት ሆኖ ከዚያ 400 አመት በጠቅላላ 535 አመታት ኖረ። እነዚህም ቁጥሮች ከግሪኩ ትርጉም ተገኙ። በእብራይስጥ ትርጉም ግን ሳላን ሲወልድ ዕድሜው 35 አመት ሆኖ ከዚያ 403 አመት በጠቅላላም 438 አመታት ኖረ ይላል። ሳምራዊው ትርጉም እንደገና ሦስተኛ ድምር ይሰጣል፦ ዕድሜው 135 ሆኖ ሣላን ወልዶ ከዚያ 303 አመት ኖሮ በጠቅላላ 438 አመት ነው። በኩፋሌ ዘንድ ደግሞ አርፋክስድ በአመተ አለም 1310 ተወልዶ ቃይናምን በ1375 አ.አ. ወለደ። 

በኩፋሌ 9፡18 መሠረት የአርፋክስድ ክፍለ ምድር ከላውዴዎንን ሁሉ እስከ «ኤርትራ ባህር» (ቀይ ባሕር) ድረስ ይጠቅልላል። ክፍሉ በምሥራቅ በኤፍራጥስ ወንዝ ይወሰናል። በውስጡም የሲና ወሽመጥና አማና አገር ይገኛሉ። በሌላ ትርጉም ሊባኖስ ደግሞ ትጠቀሳለች። በ9፡26 ደግሞ የ«ክማቱሪ ደሴቶች» በአርፋክስድ ክፍል ውስጥ መሆናቸውን ይወስናል፤ በ9:10 «የከፍቱር ደሴቶች» ተብለው በሴም ዕጣ መሆናቸውን ያረጋግጣል። ፕሮፌሰር ቻርልስ ይህ ማለት የቀፍቶሪም ደሴቶች (ምናልባት ቆጵሮስና ቀርጤስ) ይሆናል በማመን ጽፈዋል። 

አብራም (በኋላ አብርሃም) ከአርፋክስድ ወገን በከለዳውያን ዑር ተወለደ። በኩፋሌ 10፡24 ይህ በኬሴድ ልጅ በዑር ተሠርቶ ነበር። የሥነ ቅርስ ሊቅ ሌዮናርድ ዉሊ ይህን ከተማ በዑር ሱመር በኤፍራጥስ ምዕራብ ዳርቻ ላይ እንደ ነበር አመነ፤ የቀድሞው አይሁድና አረብ ልማድ ግን «የከላውዴዎን ኡር» በሶርያ እንደ ተገኘ ይላል። 

አርፋክስድ የከለዳውያን ወገን አባት ብቻ ሳይሆን፣ በተጨማሪ የዮቅጣን፣ የእስማኤልና የያዕቆብ ቅድማያት በመሆኑ አረብ፣ ሣባ እና እስራኤል ሁሉ ከአርፋክስድ ወገን እንደተወለዱ ይባላል።

ሌላ አርፋክስድ የሚባል የሜዶን ንጉሥ በመጽሐፈ ዮዲት ሲገኝ ይህ ለታሪካዊው ሜዶን ንጉስ ስም «ሗክሻጥራ» የተሳተ ይሆናል።




#Article 228: የኅሊና ነፃነት (340 words)


የኅሊና ነፃነት ማለት ማንኛውም ግለሠብ ምንምን ሀሣብ፣ እምነት ወይም አስተያየት በጽናት ለመያዝ የሚረጋገጥበት ነጻነት ነው። የሌላ ሰዎች እምነት ምንም ቢሆንም፣ ይህ ነጻነት ለየግለሠቡ ጽኑእ ሆኖ ይቆጠራል። 

የኅሊና ነጻነት ለሰዎች ለመከልከል ቢሞከር ኖሮ ይህ የሰው ልጆች መሠረታዊ መብት (ሰው ለራሱ ለማሰብ) እንደ መከልከል ይቆጠራል። 

የኅሊና ነጻነት ፍሬ ነገር እያንዳንዱ ግለሠብ ለራሱ የቱን እምነት ለመምረጥ ስለሚሰጥ፣ 'የሃይማኖት ነጻነት' ጽንሰ ሐሳብ ከዚህ ጋር ተያይዟል። በአንዳንድ ህብረተሠብ ወይም መንግሥት በተግባር የሃይማኖት ነጻነት ወይም የእምነት ነጻነት ባይከበርም፣ በሌሎች ህብረተሠብ ወይም ሕገ መንግሥታት ግን በተለይ በምእራቡ አለም ይህ ነጻነት በታሪክ እጅግ ተከብሯል። ለምሳሌ በአሜሪካ ሕገ መንግሥት 1ኛ ማሻሻያ አንቀጽ መሠረት ሃይማኖት ወይም ንግግር የሚከለክል ሕግ እንደማይጸና ይረጋገጣል። ዛሬ በአለም ዙሪያ ደግሞ አብዛኛው ሕገ መንግሥታት የእምነት ነጻነት የሚያረጋግጡ ናቸው። በ1948 ዓ.ም. በኢትዮጵያ የወጣ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 40 አባባል እንዲህ ነው፦

እንዲሁም በአንቀጽ ፲፱ ዘንድ፣

አንድ ተራ ሰው ልጅ ሌሎቹ ሁሉ በእውነት ምን ምኑን እንደሚያሥቡ ለማወቅ ስንኳ ይሁንና ለማስተዳደር በፍጹም አለመቻሉ ግልጽ ስለሚሆን፣ ይህ ኹኔታ የህሊና ነጻነትን ለመከልከል ለሚያስቡ ሰዎች ጽኑ መሰናከል ነው። 

የሰውን ሀሣብ ለማስተዳደር በፍጹም እንደማይቻል መጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፈ መክብብ 8፡8 እንዲህ ያስተምራል፦

ተመሳሳይ አስተያየት በኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርት ይገኛል። እዚህ የባልንጀሮቻቸውን ስሜት ለማስተዳደር በከንቱ የሚጣሩ ሰዎች «በገበያ የሚቀመጡትን ልጆች»ን ያስመስላቸዋል፤ ደስታ በእምቢልታ ልቅሶም በሙሾ ለማስገኘት ይሞክራሉና ባለመቻላቸው በቅሬታ ይጮሃሉ። (ማቴ. 11፡16)። ጽንሰ ሃሳቡ እንደገና በቅዱስ ጳውሎስ የተለማ ሲታይ ውሏል። («አርነቴ {ኤለውጠሪያ} በሌላ ሰው ሕሊና {ሱነይዴሰዮስ} የሚፈረድ ኧረ ስለ ምንድር ነው?» 1 ቆሮ. 10፡29)

በሰው ጭንቅላት ውስጥ ምን እንደሚታሠብ ለመወሰን የሚሞክሩ ድንጋጌዎች በታሪክ አጠያያቂ ሆነዋል። ለምሳሌ የእንግሊዝ ንግሥት 1 ኤልሳቤጥ (16ኛው ክፍለ ዘመን) እንዲህ አይነት ሕግ በሠረዙት ጊዜ፣ 'በሰዎች ነፍስና ግል ሀሣብ ላይ መስኮት ለመስራት አልወድም' ብለዋል። 

የኅሊና ነጻነት ለዴሞክራሲ መሠረታዊ መርኅ ሲባል፣ የኅሊና ነጻነት የሚከለከልበት ሙከራ የፈላጭ ቁራጭ ወይም አምባገነን መንግሥት ባኅርይ ሆነዋል። አፈና፣ ማሳደድ፣ መጽሐፍ መቃጠል፣ ወይም ፕሮፓጋንዳ ሁሉ የንግግር ነጻነት ሲወስኑ ይህ ሁናቴ ለኅሊና ነጻነት ጤነኛ አይደለም። ለምሳሌ በሂትለር ዘመን በጀርመን ባለሥልጣናቱ ያልወደዱት ብዙ መጻሕፍት ተቃጥለው ነበር። ዛሬም ባንዳንድ አገራት ውስጥ የንግግር ነጻነት ለመቆጣጠር ሲያስቡ በኢንተርኔት ላይ ማገጃ የሚጣሉ መንግሥታት አሉ። በአንዳንድ ክርክር ዘንድ ደግሞ፣ አደንዛዥ ዕጽ የተለወጠ ሀሣብ ሊፈጥር ስለሚችል፣ እንግዲህ ሕገ ወጥ መሆኑ የኅሊና ነጻነት እንደ መከልከል ሊባል ይችላል።

በመጋቢት 2006 ዓ.ም. የሚከተሉት አገራት ፌስቡክ፣ ትዊተር ወይም ዩ ቱብ ላይ ማገጃ ጥለዋል፦




#Article 229: ዳግማዊ ምኒልክ (2281 words)


ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ (ነሐሴ ፲፪ ቀን ፲፰፻፴፮ እስከ ታኅሣሥ ፫ ቀን ፲፱፻፮ ዓ.ም.) ከ፲፰፻፶፯ እስከ ፲፰፻፹፪ ዓ/ም የሸዋ ንጉሥ ከዚያም ከ፲፰፻፹፪ እስከ ፲፱፻፮ ዓ/ም የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ነበሩ።

  
ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ፤ ግንቦት ፲ ቀን ፲፱፻፩ ዓ.ም.

ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ከአባታችው ከሸዋው ንጉሥ ኃይለ መለኮት ሣህለ ሥላሴና ከእናታቸው ወይዘሮ እጅጋየሁ ለማ አድያም ቅዳሜ ነሐሴ ፲፪ ቀን ፲፰፻፴፮ ዓ.ም. ደብረ ብርሃን አካባቢ አንጎለላ ከሚባል ሥፍራ ተወልደው፤ በአንጎለላ መቅደላ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ክርስትና ተነሱ። 

አያታቸው ንጉሥ ሣህለ ሥላሴ የልጁን መወለድ ሲሰሙ “ምን ይልህ ሸዋ” በሉት ብለው ስም አወጡ። እሳቸው “…ምኒልክ በሚል ስም የሚነግሥ ንጉሥ ኢትዮጵያን ታላቅ ያደርጋታል” የሚል ትንቢት ስለነበር ‘ምኒልክ’ የኔ ስም ነው ብለው ነበር። ሆኖም፣ በህልማቸው ከልጁ ጋር አብረው ቆመው ከሳቸው ጥላ የልጁ ጥላ በልጦ፤ በእግር የረገጡትን መሬት ሲያለካኩ እሳቸው ከረገጡት ልጁ የረገጠው ረዝሞ አዩ። ከዚህ በኋላ “ምኒልክ የኔ ስም አይደለም። የሱ ነው። ስሙን ምኒልክ በሉት” ብለው አዘዙ ይላል ጳውሎስ ኞኞ “አጤ ምኒልክ” በተባለው መጽሐፉ (ገጽ ፲፪) 

ምኒልክ እስከ ሰባት ዓመታቸው ድረስ መንዝ ውስጥ ጠምቄ በሚባል አምባ ከእናታቸው ዘንድ አደጉ።አያታቸው ንጉሥ ሣህለ ሥላሴ ሲሞቱ የሸዋውን አልጋ የምኒልክ አባት ንጉሥ ኃይለ መለኮት ሣህለ ሥላሴ ወረሱ። 

ዓፄ ተዎድሮስ በጥቅምት ወር ፲፰፻፵፰ ዓ/ም ትግራይንና ወሎን አስገብረው፣ አቤቶ ምኒልክ ገና የአሥራ ሁለት ዓመት ልጅ ሳሉ፤ የድፍን አማራንና የወሎን ጦር አስከትተው የሸዋውን ንጉሥ ኃይለ መለኮትን ለማስገበር ሸዋ ገቡ። ሁለቱ መሪዎች ጦርነት ለመግጠም ተዘጋችተው ሲጠባበቁ ንጉሥ ኃይለ መለኮት ባደረባቸው ሕመም ጥቅምት ፴ ቀን አረፉ። በዚህ ጊዜ የሸዋ መኳንንት ሕጻኑን ምኒልክን ከጠላት እጅ እንዳይወድቅባቸው ይዘው ሸሹ፤ ዳሩ ግን ዓፄ ቴዎድሮስ እንደሚከታተሏቸው ስላወቁ ኅዳር ፴ ቀን ፲፰፵፰ ዓ/ም የልጅ ምኒልክ ሠራዊትና የዓፄ ቴዎድሮስ ሠራዊት በረከት ላይ ገጥሞ የምኒልክ ሹማምንት እነአቶ በዛብህ፣ እነአቶ አንዳርጋቸው ሁሉ ተያዙ። ልጅ ምኒልክም ለቴዎድሮስ ገባ።

ዓፄ ቴዎድሮስ ለሳቸው ያልገቡ ብዙ የሸዋ መኳንንት ስለነበሩ ይወስዱብኛል በሚል ፍርሀት ምኒልክን በሰንሰለት አሳሰሯቸው። ንጉሠ ነገሥቱ ግን ምኒልክ በመታሠሩ ሲያለቅስ እንዳደር ሲሰሙ አዝነው ሰንሰለቱን እንዲፈቱላቸው አዘዙ። በጥር ወር ፲፰፻፵፱ ዓ/ም መቅደላ ገብተው በቁም እሥር ይቀመጡ እንጂ ከቴዎድሮስ ልጅ ከመሸሻ ጋር አብረው አደጉ። ወዲያውም የደጃዝማችነት ማዕረግ ተሹመው በጥር ወር ፲፰፻፶፮ ዓ.ም የዓፄ ቴዎድሮስን ልጅ ወይዘሮ አልጣሽን አገቡ። በዚህ ሁኔታ እድሜያቸው ፳፪ ዓመታቸው ድረስ ለ አሥር ዓመታት ዓፄ ቴዎድሮስ ግቢ ኖሩ።

ዓፄ ቴዎድሮስ ምኒልክን እንደልጃቸው ያዩዋቸው እንደነበረና በታላቅ ጥንቃቄም እንዳስተማሯቸው እንደ ኢጣልያዊው ጉሌልሞ ማሳያ፤ ዓለቃ ወልደ ማርያም እና ዓለቃ ገብረ ሥላሴ የመሳሰሉ መስክረዋል። ምኒልክም ቴዎድሮስን እንደአባት ይወዷቸው እንደነበር ይገለጻል። በኋለኛው ጊዜ ዓፄ ቴዎድሮስ መሞታቸውን ሲሰሙ ንጉሥ ምኒልክ በጣም ማዘናቸውንና የመንግሥት ሐዘንም ማወጃቸው ተዘግቧል።

ደጃዝማች ምኒልክ መቅደላ ላይ ከባድ ዝናብ ጥሎ ባደረበት ሰኔ ፳፬ ቀን ፲፰፻፶፯ ዓ/ም በ’ቆቂት በር’ ከሃያ ተከታዮቻቸው እና ከእናታቸው ከወይዘሮ እጅጋየሁ ጋር አምልጠው ወደአባታቸው ወዳጅ ወደ ወሎዋ ገዥ ወይዘሮ ወርቂት አመሩ። ሆኖም ወይዘሮ ወርቂት በቴዎድሮስ እጅ ወድቆ የነበረውን ልጃቸውን አመዴ አሊ ሊበንን ማስፈቻ ይሆነኛል በሚል ምኒልክን እና ተከታዮቻቸውን በእስር ይዘዋቸው ነበር።

ወይዘሮ ወርቂት ዓፄ ቴዎድሮስ ልጃቸውን አስደብድበው ገደል ከተቱት የሚል ወሬ ሲሰሙ ቦሩ ሜዳ ላይ ምኒልክን ተቀብለው፣ “የሸዋ ሰው አውራህ መጥቷልና ደስ ይበልህ፣ ተቀበል” ብለው አዋጅ አስነግረው፣ አጃቢ አድርገው በመለከትና እምቢልታ አሳጅበው ከሸዋ ድንበር ድረስ ላኳቸው።

ሸዋን ‘ንጉሥ ነኝ’ እያሉ ይገዙ የነበሩት አቶ በዛብህ የምኒልክን ወደመሀል ሸዋ መግፋት ሲሰሙ ለመውጋት ጋዲሎ ከተባለ ሥፍራ ተሠልፈው ሲጠባበቁ፣ አንዲት ሴት

 ማነው ብላችሁ ነው ጦራችሁ መሾሉ 
 ማነው ብላችሁ ነው ካራችሁ መሳሉ፣ 
 የጌታችሁ ልጅ ነው ኧረ በስማም በሉ» 
 ብላ ገጠመች።  

ውጊያው ጋዲሎ ላይ ነሐሴ ፲፮ ቀን ተፋፍሞ ሳለ ከአቶ በዛብህ ጋር ተሠልፈው የነበሩት የሸዋ መኳንንት “በጌታችን በኃይለ መለኮት ልጅ ላይ አንተኩስም” ብለው ወደምኒልክ ዞሩ። አቶ በዛብህም ሸሽተው አፍቀራ ገቡ፤ ድሉም የምኒልክ ሆኖ ምሥራቅ ምስራቁን ተጉዘው በድል አድራጊነት አባቶቻቸው ከተማ አንኮበር ገቡ። ንጉሥ ምኒልክም በአንኮበር ጥቂት ወራት ከተቀመጡ በኋላ ወደ ደብረ ብርሃን ወርደው አዲሱን ከተማቸውን ልቼን እያሠሩ ተቀመጡ።

ተቃራኒያቸውን አቶ በዛብህን ጋዲሎ ላይ ድል ካደረጉ በኋላ፣ ንጉሥ ምኒልክ ታማኞት የሸዋ መኳንንትን በሚሠበስቡበትና በሚያዳብሩበት ጊዜ ትኩረታቸውን ዓፄ ቴዎድሮስ አሲዘው በመርሐ ቤቴ አውራጃ በደጃዝማች ወልደ ሚካኤል ሥር ያስጠብቋቸው የነበሩትን አጎታቸውን መርዕድ አዝማች ኃይለ ሚካኤልን ነጻ ለማውጣት ግንቦት ፳፩ ቀን ፲፰፻፶፱ ዓ/ም ከልቼ ዘመቱ። ያላንዳች ተኩስ አጎታቸውን ካስለቀቁ በኋላ ወደ ልቼ ተመልሰው መርዕድ አዝማቹ የቡልጋን ግዛት ተሰጣቸው።

በሚያዝያ ፯ቀን ፲፰፻፷ ዓ/ም ዓፄ ቴዎድሮስ የእንግሊዝን ጦር መቅደላ ላይ ገጥመው መሞታቸው ሲሰማ ንጉሥ ምኒልክ ወደ ወሎ ዘምተው ባላባቶቹን አስገብረው፣ ወረይሉን ቆርቁረው ወደ ሸዋ ተመለሱ። በኋላም አንደኛው የወሎ ባላባት መሐመድ አሊ (በኋላ ንጉሥ ሚካኤል) ገቡላቸውና ይማሙ ብለው ወሎን በሙሉ ሰጧቸው። ለመተማመኛም የወይዘሮ ባፈናን ልጅ ወይዘሮ ማናለብሽን ልጅ ዳሩላቸው።

የትግራይ ደጃዝማች ካሳ (በኋላ ዓፄ ዮሐንስ ሐምሌ ፬ ቀን ፲፰፻፷፬ ዓ/ም የቴዎድሮስን ተከታይ ዓፄ ተክለ ጊዮርጊስን ተዋግተው ድል ስላደረጉ ዮሐንስ ፬ኛ ተብለው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ሆኑ።

ምኒልክ እና ዮሐንስ ከመጀመሪያው ጀምሮ ለንጉሠ ነገሥትነት ሥልጣን ተወዳዳሪዎች ሲሆኑ ጠባያቸው የተለያየ እና እርስ በርስ የማይተማመኑ ነበሩ። ዓፄ ዮሐንስ ሟቹን ንጉሠ ነገሥት ቴዎድሮስን ሊወጋ የመጣውን የእንግሊዝ ሠራዊት በመርዳት ከሸኚ እና ስንቅ ጋር በግዛታቸው እንዲያልፍ በማድረጋቸው ወሮታውን ከድሉ በኋላ በዘመናዊ መሣሪያ፤ መድፍ እና ጥይት አበልጽጓቸው ሲሄድ በጊዜው ከነበሩት መሪዎች ሁሉ የላቀ ኃይል ለማግኘትና ያስከተለውንም የንጉሠ ነገሥትነት ዘውድ እጃቸው ለማስገባት አመቸላቸው።

ንጉሥ ምኒልክ ደግሞ ጊዜያቸው እስኪደርስ፤ ኃይላቸውን በዘመናዊ መሣሪያዎች እስከሚያዳብሩና ለንጉሠ ነገሥትነቱ ሥልጣን እስከሚዘጋጁ ድረስ ግዛታቸውን በደቡብ እና በምዕራብ አቅጣጫ እያስፋፉ በዘዴ ለንጉሠ ነገሥት ዮሐንስ ታማኝና የበታች መስለው መኖርን ያዙ።

በሁለቱ መሀል ግንኙነታቸው መካረር የጀመረው ዓፄ ዮሐንስ የንጉሥ ምኒልክን ገባር የበጌ ምድሩን ገዥ ራስ ወልደ ማርያምን ለማሳመን ከዘመቱ በኋላ ጎጃምን አሳምነው ወደ ሸዋ ለመምጣት ዘቢጥ ላይ ሲደርሱ ከወደኋላ የቱርክ ጦር መጣ የሚባል ወሬ ስለሰሙ ወደትግራይ ተመለሱ። ይማም አባ ዋጠውም (ንጉሥ ሚካኤል) ምኒልክን ከድተው ወደ ዓፄ ዮሐንስ ሲገቡ ምኒልክ ገስግሰው የጁ ላይ ደርሰውባቸው እጃቸውን ይዘው አስረው ወደሸዋ ሰደዷቸው፡

ምኒልክ ወዲያው መልሳቸውን በጎጃም አድርገው በጌ ምድር ዘመቱና ደብረ ታቦር ላይ ሳሉ ዓፄ ዮሐንስ መምጣታቸውን ሲሰሙ እንደገና ወደ ጎጃም ተሻገሩ። ወዲያውም ወደሸዋ ተመለሱ። ይሄኔ ነው ወይዘሮ ባፈና ምኒልክን ከድተው ካማቻቸው ከይማሙ መሐመድ አሊ ጋር ተማምለው ወደዓፄ ዮሐንስ መላላክ ጀምረው ነበር።እንዲሁም አጎታቸው የቡልጋው ገዥ መርዕድ አዝማች ኃይለ ሚካኤልም ሸፍተው አንኮበርን ይዘው ነበር። 

መርዕድ አዝማቹ ሚጣቅ አፋፍ ላይ ሲያዙ ወይዘሮ ባፈና ደግሞ መርሐ ቤቴ ላይ ኮላሽ አምባ እምቢላው ሥፍራ ላይ የተከተሏቸው ወታደሮች አሠሯቸው። ንጉሡ ይማሙ መሐመድ አሊን ለመያዝ በግስጋሴ ተከታትለው ሲደርሱበት አምልጦ በመሄዱ ተናደው ከተማውን ደሴን አቃጠሉት።

ዓፄ ዮሐንስ ደብረ ታቦር ላይ ሳሉ ከሸዋ ከሦስት ወገን መልእክት ይደርሳቸው ነበር። 

በአንዱ ወገን አቤቶ መሸሻ ሰይፉ እርስዎ ከመጡ በሸዋ የኔ ወገን ነውና የሚበዛው ከንጉሥ ምኒልክ ምንም የሚሰጉበት ነገር የለም ብሎ ልኮላቸዋል።

በሁለተኛው ወገን ደግሞ የ’ሁለት ልደት’ ኃይማኖት ወገኖች እርስዎ መጥተው የማርቆስን ኃይማኖት ቢያቀኑልን ነው እንጂ ንጉሥ ምኒልክ በአዳል በኩል አባ ማትያስ የሚባሉ ጳጳስ አስመጥተው ከ’ሦስት ልደት’ ወገኖች ጋር ተፋቅረዋል እያሉ ይልኩባቸው ነበር።

በሦስተኛው ወገን ከወይዘሮ ባፈና እና ከመርዕድ አዝማች ኃይሌ ጋር የመከሩ ሰዎች ቶሎ ካልደረሱልን ንጉሥ ምኒልክ ያጠፉናል እያሉ ልከውባቸው ነበር።

ዓፄ ዮሐንስ እንግዲህ በነኝህ ተነሳስተው ወደሸዋ ለመዝመት ቆረጡ። ምኒልክም በጥቅምት ወር ፲፰፻፸ ዓ/ም ላይ ወደወሎ ሲሻገሩ መሐመድ አሊ ሸሽተው ወደ ዓፄ ዮሐንስ ገቡ። ይማሙ አባ ዋጠው ግን ከምኒልክ ጋር ታርቀው ስለገቡ የወሎን ግዛት መልሰው ሰጧቸው። ወዲያውም በምስጢር ወደ ዓፄ ዮሐንስ መኳንንቶች እየተላላኩ የንጉሠ ነገሥቱን አሳብ በርግጥ ደሩበት። እነኚሁም መኳንንት ዓፄ ዮሐንስን መክረው በረግም መንገድ እንዲጓዙ ሲያደርጓቸው ምኒልክ ወደ መርሐ ቤቴ ወርደው መሸሻ ሰይፉን መውጋት ጀመሩ። ዳሩ ግን እዚያ ከመሸሻ ሰይፉ ጋር ሲዋጉ ንጉሠ ነገሥቱ ደርሰው አገሬን የጠፉብኛል በሚል ዕርቅ ለማድረግ መነኮሳት ልከውበት እሱንም ወይዘሮ ባፈናንም አስታረቋቸውና ሁሉም ወደ ልቼ ገቡ።

የሁለቱ ነገሥታት አለመግባባት እየተገለጠና እየሰፋ ሲሄድ አንዳንድ መነኮሳት የክርስቲያን ወገን ለምን ይፈሳል በሚል ተነሳስተው ሁለቱን ለማስታረቅ ተነሡ። ሆኖም ዓፄ ዮሐንስ የዕርቅ ወዝ እያሳዩ ወደፊት እየገሰገሱ ያለፉበትን አገር ሁሉ እያጠፉ ቀኝና ግራ እየወረሩ ከብቱን እየማረኩ ስለነበር ንጉሥ ምኒልክም ተናደው በአንጎለላ ሠራዊታቸውን ሁሉ ሰብስበው ሰልፍና ግባት አሳዩ። 

ሆኖም ምኒልክ ዕርቅን ይፈልጉ ስለነበር መነኮሳትና ሊቃውንቶችን ሰብስበው ወደ ንጉሠ ነገሥቱ ላኩ። ዕርቁንም በተመለከተ የተነደፈው ውል ሁለት ነገሮችን ብቻ የተመለከተ ሲሆን፣ እንኚህም፦

(ሀ) ንጉሥ ምኒልክ ወደ ዓፄ ዮሐንስ ሄደው ላይገቡና ላይገናኙ፤ በዓፄ ዮሐንስም ላይ ጠላት ቢነሳ ንጉሥ ምኒልክ የጦር አብጋዛቸውን እየላኩ ሊረዱ እንጂ ራሳቸው ወደ ዘመቻ ላይሄዱ

(ለ) በኃይማኖት አንድ ሊሆኑና አባ ማስያስ የሚባሉትን የካቶሊክ ጳጳስ ካገራቸው አስወጥተው ሊሰዱ ነው።

አስታራቂዎቹ ገና ወደ ንጉሥ ምኒልክ ተመልሰው የእርቁን ድርድር ሳይናገሩና ሳያስወድዱ የዓፄ ዮሐንስ ሠራዊት ‘ጭሬ ደን’ የተባለውን ወንዝ ተሻገረ። በዚህ ጊዜ የንጉሥ ምኒልክ ሠራዊት፣ በተልይም የፈረስ ዘበኛው ፈንድቶ ወጥቶ ጦርነት ተጋጠሙና ከሁለቱም ወገን ብዙ ሰው ሞተ። ከዚህ በኋላ ዓፄ ዮሐንስ “ከወንድሜ ከንጉሥ ምኒልክ ጋራ ታርቄያለሁና ከንግዲህ ወዲህ አገር ያጠፋህ ከብት የዘርፍክ ወታደር ትቀጣለህ”” የሚል አዋጅ አስነገሩ።

ሁለቱ ነገሥታት ከታረቁ በኋላ በ’ሁለት ልደት’ እምነትና በ’ሦስት ልደት’ እምነት የኃይማኖት ጉባዔ እንዲደረግ ስለተስማሙበት በግንቦት ወር ፲፰፻፸ ዓ/ም ቦሩ ሜዳ ላይ ሁለቱም ነገሥታት ቀኝና ግራ በተዘረጋላቸው ዙፋን ተቀመጡ።

ከሁለት ልደት ወገን አፈ ጉባዔው መልአከ ብርሃን ወልደ ዮሐንስ፤ ከሦስት ልደት ወገን ደግሞ ዓለቃ ወልደ ሐና ሆነው ቆሙ። ሁለቱም ወገኖች በየተራቸው ጥያቄ እያመጡ ከተከራከሩ በኋላ ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስተኛ ልደት አለው የሚል ከቅዱሳት መፃሕፍት ምስክር ስላልተገኘ ሁለት ልደት አለው የሚለው ወገን ረታ። በኢሁም በጉባዔው ያለው ሁሉ ኃይማኖቴ ሁለት ልደት ነው እያለ ከዚያው ሳይወጣ ተገዘተ። ከደብረ ሊባኖስ ተይዘው የመጡት ዋልድቤ እንግዳ እና ዘራምቤ እንግዳ ተክለ አልፋ የሚባሉት ሦስት ልደት አለው የሚለውን እምነታችንን አንተውም ስላሉ ሦስቱንም ምላሳቸውን በመቁረጥ ሲቀጧቸው ዋልድቤ እንግዳ ያን ጊዜውን ሞቱ። ዙራምቤ እንግዳና ተክለ አልፋ ግን ከቦሩ ሜዳ ጉባዔ በኋላ ብዙ ዘመን ኑረው ሞቱ።

ንጉሠ ነገሥቱ ወዲያው በዚያው ዓመተ ምሕረት እስላምና ያልተጠመቀ ሁሉ እንዲጠመቅ የሚያስገድድ አዋጅ አሳውጀው በኢትዮጵያ ያለ እስላም ሁሉ አስከፉ። ጉልበት ያለውና በኃይማኖቱ የጸናውም ወደ መተማ እየተሰደድ ከደርቡሾች ጋር ተቀላቀለ። ሌላው ወደሐረር ወደ ዋቤ እና ወደ ጅማ ተሰደደ።

የወሎውም ባላባት ይማሙ መሐመድ አሊ በዚሁ አዋጅ መሠረት በዓፄ ዮሐንስ ክርስትና ተነስተው ስማቸው ሚካኤል ተባለ። ንጉሥ ምኒልክም ክዚህ መልስ ወረይሉ ሲደርሱ ኡለተኛውን የወሎ ባላባት ይማሙ አባ ዋጠውን ክርስትና ናስተው ስማቸው ኃይለ ማርያም አስብለው የወሎን እስላም ለማስተማርና ወደ ክርስትና ለመመለስ መምሕር አካለ ወልድን ሾመው በሰኔ ወር መጨረሻ በ፲፰፻፸፪ ዓ/ም ወደ ሸዋ ተመለሱ።

በንዲህ ዓይነት ሁኔታ ንጉሥ ምኒልክ ጊዜያቸው እስኪደርስ፤ ኃይላቸውን በዘመናዊ መሣሪያዎች እስከሚያዳብሩና ለንጉሠ ነገሥትነቱ ሥልጣን እስከሚዘጋጁ ድረስ ግዛታቸውን በደቡብ እና በምዕራብ አቅጣጫ እያስፋፉ በዘዴ ለንጉሠ ነገሥት ዮሐንስ ታማኝና የበታች መስለው መኖርን ያዙ።

ዓፄ ዮሐንስም የምኒልክን ‘ሰሎሞናዊ’ ሥልጣን ለመበረዝና ኃይላቸውንም የሚቃረን ኃይል ለመመሥረት ባቀዱት ሤራ መሠረት ከዚያ በፊት በአገሪቱ ታሪክ ያልነበረውን “የጎጃም የንጉሥ ስርዓት በመፍጠር ገዚውን ራስ አዳልን ለማንገስ ወሰኑ። ስለዚህም ጉዳይ ወደምኒልክ የጻፉት ደብዳቤ የሁለቱን ሁኔታ ሲያሳይ ዮሐንስ ምኒልክን በአክብሮት የሚያይዋቸው ቢሆንም ንጉሠ ነገሥቱ የራስ በራስ መተማመን እንደሚያንሳቸውና የመጨረሻው አንቀጽ ደግሞ ምኒልክንም እንደማያምኗቸው ያሳያል።

 
ራስ አዳልን በጥምቀት ዕለት የምሾመው የማንግሠው ነኝ። ሲሆን ቢሰላ አብረን ሁነን መሾም ይገባነ ነበር። ቀኑ የሚያጥር የማያዳርስ እንደሆነ አንድ ደህና ሰው ሁኔታውን ሁሉ የሚያይ ገስግሶ ለጥምቀት እንዲገባ ይሁን። እኔ ይህን ማለቴ ንጉሠ ነገሥት ተብዬ እኮራለሁ ብዬ አይደለም። አንድ ጊዜ ስሙም ወጥቶልኛል። የ እግዚአብሔር ኃይማኖቴ እንዲጸናና እንዲሰፋ አሕዛቦች እንዲጠፉ ብዬ ነው። ደግሞ ይህን ጉዳይ ካደርግነ በኋላ ወደ አምናችን የምመጣ ነኝና መምጣቱ የሚቸግር እንደሆነ ከዚያው እንድንገናኝ ይሁን።

የኢጣልያ ንጉሥ አምና በረከት ሰዶልኝ ነበር። ዕቃውን አኑኦ ሰዎቹን መልሶ ወሰዳቸው። ፍቅር ጀምሮ ሰዎቹን መልሶ መውሰዱ ብልሃቱ ጠፍቶብኛል። የዚህ ነገር ወደእርስዎ ይገኛል ይሆንን?
ተጽሕፈ በአምባጨራ ከተማ። አመ ሰሙኑ ለታሕሣሥ ወር በ፲ወ፰፻፸ወ፫ ዓ/ም»

ዓፄ ዮሐንስ በተለያየ ጊዜ፣ ባንድ በኩል የምስር (ግብጽ) ሠራዊት በግዛታቸው በምጽዋ በኩል፤ ባንድ በኩል ደርቡሾች በሌላ በኩል ደግሞ የእንግሊዝን ድጋፍ የያዙት ኢጣልያኖች ከአሰብ በቶሎ አልፈው ቤይሉል የሚባለውን የባሕር ጠረፍ ያዙ። ከነኚህ የውጭ ቀማኞች ጋር ክፉኛ ፍልሚያ ይዘው አንዳንዴ ሲያሸንፉ አንዳንዴም ሲገፏቸው ኖሩ። 

በ፲፰፻፹፩ ዓ/ም ደምቢያ ሣር ውሐ ላይ ደርቡሾች ከንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ጋር ገጥመው አሸንፈው የፈጁትን የኢትዮጵያን የክርስቲያን አጽም አይተው እጅግ አዘኑ። ከዚያም ወደመተማ ገሠገሡ። አሳባቸው መተማን አጥፍተው ወደ ትልቁ ከተማ ኦምዱርማን ለመሄድ ነበር። መጋቢት ፩ ቀን ፲፰፻፹፩ ዓ/ም ቅዳሜ ጦርነት ገጥመው የከተማውን ቅጥር ጥሰው ከገቡ በኋላ በጠመንጃ ጥይት ተመተው ቆሰሉ። ወሬውም ያንጊዜውን በየሠልፉ ውስጥ ሲሰማ መኳንንቱም ወታደሩም ከቅጥሩ ውስጥ እየወጡ መሸሽ ጀመሩ። በማግሥቱ እሑድ መጋቢት ፪ ቀን አረፉ። ደርቡሾቹም የንጉሠ ነገሥቱን ሬሳ ከማረኩ በኋላ ራሳቸውን ቆርጠው በእንጨት ላይ ሰክተው ገበያ ለገበያ መንደር ለመንደር እያዞሩ ሲያሳዩ ዋሉ።

ንጉሥ ምኒልክም ዓፄ ዮሐንስ ወደመተማ ሲዘምቱ ምናልባት ድል የሆኑ እንደሆነ ደርቡሽ ተከታትሎ ወጥቶ በጌ ምድርን እንዳያጠፋና ሕዝበ ክርስቲያኑንም እንዳይገድል በወሎና በበጌ ምድር ወሰን ሆነው ለመጠባበቅ ሲሉ ቀውት የሚባል ሥፍራ መጋቢት ፲፯ ቀን ሲገቡ የንጉሠ ነገሥቱን መሞት አረዷቸው። ለአራት ቀናትም በኀዘን ሰነበቱ። 

ጳውሎስ ኞኞ “አጤ ምኒልክ” በተባለው መጽሐፉ የንግሡን ስራት ሲተነትን፤
ከዚያም መልስ የንግሥ በዓሉ ስርዓት እየተዘጋጀ ከርመው ጥቅምት ፳፭ ቀን ፲፰፻፹፪ ዓ/ም በእንጦጦ ርዕሰ አድባራት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በተፈጸመው ስርዓት በጳጳሱ አቡነ ማቴዎስ እጅ የወርቅ ሰይፍ ታጥቀው፤ በወርቅ ሽቦ የታሸቡ ሁለት ጦሮች ጨብጠው፤ የወርቅ ዘንግ ከተሰጣቸው በኋላ ቅብዐ መንግሥቱን ተቀብተው፣ “ሞአ አንበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ፤ ዳግማዊ ምኒልክ ሥዩመ እግዚአብሔር ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ” ተብለው የወርቅ ዘውድ ተደፋላቸው። 

የቅዳሴውም ስርዓት ከተፈጸመ በኋላ ዓፄ ምኒልክ በውጭ አገር በአምስት ሺ ብር የተሠራ ካባቸውን ለብሰው፣ ባለወርቅ ጥላ ተይዞላቸው ዘውዳቸውን ደፍተው የወርቅ ዘንግ ይዘው የወርቅ ጫማ አድርገው ካህናቱ ከፊትና ከኋላ እያጠኑ በራሶችና ደጃዝማቾች ታጅበው ከቤተ ክርስቲያኑ ብቅ አሉ። እጅግ በጣም በዝቶ የተሰበሰበው ሕዝብም የዘንባባ ዝንጣፊ እየያዘ “ሺህ ዓመት ያንግሥዎ” እያለ ደስታውን በእልልታና በሁካታ ገለጠ።(ገጽ ፻) ይልና “ከቤተ መንግሥታቸው ውስጥ ከተዘጋጀው የግብር ማብሊያ ዳስ ገብተው ከተዘጋጀላቸው ዙፋን ላይ ሲቀመጡ ፻፩ ጊዜ መድፍ ተተኮሰ። ከመድፎቹ መተኮስ ጋርም ጠቅላላው ሠራዊት የያዘውን ጠመንጃ በተኮሰ ጊዜ የጭሱ ብዛት እንደ ደመና ሆነ።” ብሎ አስፍሮታል።

ታሪከ ዘመን ዘዳግማዊ ምኒልክ የተባለውን መፅሃፍ በዳግማዊ ምኒልክ ዘመን፤ የኢትዮጵያ መንግሥት የጽሕፈት ሚኒስተር በነበሩት በፀሓፌ ትእዛዝ ገብረ ስላሴ ወልደ አረጋይ በአማርኛ የተፃፈ የዳግማዊ ምኒልክ ታሪክ ነው። መጽሐፉ በ288 ገፆች የተደጎሰና በተለያዩ ፎቶዎች የተደገፈ ሲሆን ፥ የተለያዩ ታሪካዊ ክስተቶችና ጸሓፊዉ የአይን እማኝ የነበሩበት ስለአድዋ ጦርነት ዝግጅትና ክናዋኔ በሰፊዉና በዝርዝር መረጃ የሚዳስስ ነዉ፡፡

መኪና ስልክ ዘመናዊ ትምህርት ቤት እና ሌሎችም በጣም ብዙ ስራዎች ሰርተዋል።

አቶ ተክለጻድቅ መኩርያ ስለ ዕምዬ ምኒልክ ዜና ዕረፍት፣ «ዐፄ ምኒልክና የኢትዮጵያ አንድነት» መጽሐፍ ላይ ካሠፈሩት ሀተታ የሚከተለው ይገኝበታል።

ንጉሠ ነገሥት በ፲፱፻ ዓ/ም የጀመራቸው በሽታ እየጸና ሔዶ በመጨረሻ ሰውነታቸው ዝሎ፣ አንደበታቸው ተዘግቶ እንደቆየ በታኅሣሥ ፫ ቀን ፲፱፻፮ ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። የሸዋ ንጉሥ (፲፰፻፶፯-፲፰፻፹፩) በኋላም፣ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት (፲፰፻፹፪-፲፱፻፮) በነበሩበት ዘመን ሁሉ ክፉውን በክፉ ሳይሆን፣ ክፉውን በደግነት እየመለሱ ጥፋትን ሁሉ በትዕግሥት እያሸነፉ፣ አገር የሚሰፋበትን ልማት የሚዳብርበትን፣ ሕዝብ ዕረፍትና ሰላም የሚያገኝበትን ከማሰብና ከመፈጸም አልተቆጠቡም። የአውሮፓን ኃያል መንግሥት በጦር ሜዳ በማሸነፍ ኢትዮጵያን በዓለም እንድትደነቅ አድርገዋል።

የዳግማዊ አፄ ምኒልክን ዜና ዕረፍት በወቅቱ ለመደበቅ ቢሞከርም ወሬው ካንዱ ወደሌላው እየተላለፈ ነገሩን የተረዳው ሁሉ፣ «እምዬ ጌታዬ፣ እምዬ አባቴ» እያለ በየቤቱ ያለቅስ ነበር። ከአልቃሾቹ አንዱ፣ «ፈረስ በቅሎ ስጠኝ ብዬ አለምንህም አምና ነበር እንጂ ዘንድሮ የለህም፤» አለ ይባላል። በንጉሠ ነገሥቱም ሞት ዋናዎቹ ሐዘንተኞች ባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱ፣ ልጃቸው ወይዘሮ ዘውዲቱና ብዙ መኳንንት አሉ። በልቅሶውም ጊዜ እቴጌ ጣይቱ፣ ‹‹ነጋሪት ማስመታት፣ እምቢልታ ማስነፋት ነበረ ሥራችን፣ ሰው መሆን አይቀርም ደረሰ ተራችን›› ብለው ገጠሙ ይባላል።

ከልጅ ኢያሱ ቀጥለው ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ወለቱ ለምኒልክ ተብለው የነገሡት ልጃቸው ወይዘሮ ዘውዲቱ የሚከተለውን ሙሾ አወረዱ። ሙሾውም በ«ዐፄ ምኒልክና የኢትዮጵያ አንድነት» መጽሐፍ ላይ እንዲህ ተከትቧል

ይመስለኝ ነበረ ይኼ የማይፈርስ። 
ሠላሳ ሦስት ዘመን የበላንበቱ የጠጣንበቱ፣ 
የትሣሥ ባታ ለት ተፈታ ወይ ቤቱ። 
ብትታመም ልጅህ እጅግ ጨነቀኝ፣ ብትሞትስ አልሞትም እኔ ብልጥ ነኝ። 
ወልደውኛል እንጂ እኔ አልወለድሁዎ፣ አንዠቴን ተብትበው ምነው መሔድዎ። 
አሳዳጊ አላንተ አላውቅም እናት፣ ምነዋ ሞግዚቴ እንዲህ ያል ክዳት። 
ቀድሞ የምናየው የለመድነው ቀርቶ፣ እንግዳ ሞት አየሁ ካባቴ ቤት ገብቶ። 
እጅግ አዝኛለሁ አላቅሽኝ አገሬ፣ የሁሉ አባት ሞቶ ተጐዳችሁ ዛሬ። 
ትንሽ ትልቅ አይል ለሁሉ መስጠት፣ ከጧት እስከ ማታ ያለመሰልቸት። 
ድርቅ ሆኗል አሉ ዘንድሮ አገራችሁ፣ ዝናሙ ሲጠፋ ምነው ዝም አላችሁ። 
አሻግሬ ሳየው እንዲያ በሰው ላይ 
መከራም እንደሰው ይለመዳል ወይ።»




#Article 230: ልድያ (453 words)


ልድያ (አሦርኛ፦ ሉዱ፤ ዕብራይስጥ፦ לוד /ሉድ/፣ ግሪክ፦ Λυδία /ሉዲያ/) በምዕራብ ትንሹ እስያ የተገኘ ታሪካዊ አውራጃና መንግሥት ነበር። 

በታወቀበት ዘመን ዋና ከተማው ሰርዴስ ሆነ። በአንድ ወቅት የትንሹ እስያ ምዕራብ ክፍል በሙሉ የሉድያ ግዛት ነበረ። በኋለ ዘመን ደግሞ ልድያ የሮማ መንግሥት ጠቅላይ ግዛት ነበረ። መሐለቅ መጀመርያ የተፈጠረው በልድያ ክ.በ. 660 አመት ያሕል እንደ ነበረ ይታመናል። 

የታሪካዊው ልድያ ጠረፎች በዘመናት ላይ ይለያዩ ነበር። በመጀመርያ በሚስያ፣ በካርያ፣ በፍርግያና በዮንያ ይወሰን ነበር። በኋላ፣ የንጉሦች አልያቴስና ቅሮይሶስ ሠልፎች ልድያን ሲያስፋፏት፣ ከሉቅያ በቀር ትንሹን እስያ ከሃሊስ ወንዝ ምዕራብ በሙሉ ገዙ። ከፋርስ ወረራ ቀጥሎ ማያንድሮስ ወንዝ በፋርስ መንግሥት የክፍላገሩ ደቡብ ጠረፍ ሆነ። በሮማ መንግሥት ውስጥ ደግሞ የልድያ ጠቅላይ ግዛት በአንድ በኩል ከሚስያና ከካርያ መካከል በሌላውም በኩል ከፍርግያና ከአይጋዮስ ባሕር መካከል ያለው አገር ሁሉ ነበረ።

ቋንቋቸው ሉድኛ በሕንዳዊ-አውሮፓዊ ቋንቋዎች ቤተሠብ ሲሆን በዚሁም ቤተሠብ ውስጥ የአናቶላዊ ቅርንጫፍ አባል ነበር። ስለዚህ የሉዊኛና የኬጥኛ ቅርብ ዘመድ ነው።. ሉድኛም በመጨረሻ እስከ 1ኛ ክፍለ ዘመን ከክርስቶስ በፊት ድረስ እንደ መነጋገርያ ሆኖ ቆየ። 

የልድያ መንግሥት መጀመርያ የተነሣ የኬጥያውያን መንግሥት በ1180 ክ.በ. ገደማ ከወደቀበት ወቅት በኋላ ነበረ። 

ቀድሞ በኬጥያውያን መንግሥት ዘመን፣ የአገሩ ስም አርፃዋ ሲሆን ይህ ሉዊኛ የሚናገር አገር ነበር። ይሁንና ክሁሉ ጥንታዊ በሆኑት ኬጥያውያን ሰነዶች የአገሩ ስም «ሉዊያ» ይባላል። በግሪክ ምንጮች ዘንድ ግን፣ የልድያ መንግሥት መጀመርያ ስም ማዮንያ ተባለ፤ ሆሜርም (ዒልያድ ii. 865; v. 43, xi. 431) የልድያን ነዋሪዎች ማዮናውያን (Μαίονες) ይላቸዋል። ሆሜር ደግሞ ዋና ከተማቸውን 'ሰርዴስ' ሳይሆን 'ሁዴ' ይለዋል (ኢልያድ xx. 385)። ሆኖም 'ሁዴ' ምናልባት ሰርዴስ የቆመበት ሠፈር ስም ሊሆን ይቻላል.። ኋላም፣ ሄሮዶቶስ (ታሪኮች i. 7) እንደሚነግረው፣ መዮናውያን ስለ ንጉሳቸው ስለ አቲስ ልጅ ሉዶስ (Λυδός) ስም አዲስ ስያሜያቸውን 'ልድያውያን' (ግሪክ፡ Λυδοί /ሉዶይ/) ተቀበሉ። ይህም የሆነ ከአፈታሪካዊው ሄራክሌስ ሥርወ መንግሥት በፊት እንደ ነበር ይላል። እንደዚህም ሕዝቡ በዕብራይስጥ ሉዲም (לודים) ሲባሉ፣ ምክንያቱም በጥንት ከሉድ ሴም (ዘፍ. 10) እንደ ተወለዱ መሆኑ ይታመናል። በመጽሐፈ ኩፋሌ ምዕ. 9 መሠረት እንደገና የሉድ ርስት ከ'አሦር ተራሮች' ወደ ምዕራብ እስከ 'ታላቁ ባህር' ድረስ ይሠጣል፤ ይህም ማለት የትንሹ እስያ ልሳነ ምድር በሙሉ ነው።

ትልቁ ፕሊኒ (የተፈጥሮ ታሪክ 5:30) እና ሄሮክሌስ እንደ ጻፉት፣ ማዮንያ የተባለ መንደር ለረጅም ዘመን በዙሪያው ይገኝ ነበር።

ሄሮዶቶስ ደግሞ (1.94) የኤትሩስካውያን ሥልጣኔ (በዛሬው ጣልያን) በልድያውያን ሠፈረኞች እንደተመሠረተ በሉዶስም ወንድም በቲሬኖስ እንደ ተመሩ የሞለውን ትውፊት ይጠቅሳል። ነገር ግን የሃሊካርናሦስ ዲዮኒስዮስ ይህን ታሪክ አልተቀበለም፣ የኤትሩስካውያን ባሕልና ቋንቋ ከልዳውያን እጅግ ይለያይ ነበርና።

በፓክቶሎስ ወንዝ የተገኘው የወርቅ ዝቃጅ የልድያ መጨረሻ ንጉስ ቅሮይሶስ ሀብት ምንጭ ሆነ። በአንድ ትውፊት ዘንድ መንስኤው የፍርግያ ንጉስ ሚዳስ 'የወርቅ ዕጆቹን' በውኆቹ ውስጥ ስለ ታጠቡ ነበር።

የፈተና ደንጊያ የተባለው ፈጠራ ዕውቀት በልድያ ከተስፋፋ በኋላ፣ የልድያ ሰዎች ወዲያው ለብረታብረታቸው መደበኛ ጥረት ለማረጋገጥ ቻሉ። ይህ ቀላል መሣርያ ለግሪኮችም «የልድያ ደንጊያ» በመባል ታወቀ። ከዚያ በፊት ከጥንት ጀምሮ ወርቅና ብር በክብደት (ሰቀል) ለሸቀጥ ቢጠቅምም (ለምሳሌ በካሩም)፣ ብዙ ጊዜ ከሌሎች የብረት አይነቶች ጋር ተቀላቅሎ ነበር። አሁን የልድያ ንጉሥ ማሕተም የጥረቱ ማረጋገጫ ሆነ፤ በዚህም አዲስ የመሐለቅ ገበያ መጀመርያ መመሠረት ቻለ።

በሄሮዶቶስ ታሪክ መሠረት፣ ልዳውያን ከሁሉ በፊት የወርቅና የብር መሐለቅ የተጠቀሙት ሰዎች ነበሩ፤ እንዲሁም ቋሚ ሱቆችን መጀመርያ የገነቡት ሕዝብ መሆናቸውን ይመሠክራል




#Article 231: አሞራውያን (257 words)


አሞራውያን (ሱመርኛ፦ ማርቱ ፤ አካድኛ፦ አሙሩ፤ ግብጽኛ፦ አማር፣ ዕብራይስጥ፦ אמורי /አሞሪ/) በጥንት ከኤፍራጥስ ወንዝ ወደ ምዕራብ የኖረ ሕዝብ ነበረ። 

የአካድ ንጉሥ ናራም-ሲን ስሜን ሶርያን 2040 ዓክልበ. ገደማ ወርሮ ዘመተባቸው፤ ልጁም ሻር-ካሊ-ሻሪ እንዲህ አደረገ። በኡር መንግሥት ዘመን በአንዳንድ ሰነድ አሞራውያን እንደ ዘላኖች ይሰደባሉ። ለምሳሌ፦

በኡር መንግሥት ጊዜ፣ አሞራውያን በአገሩ ውስጥ በጣም በመብዛታቸው ምክንያት፣ እንደገና እነሱን ለመከልከል ንጉሶቹ እንደ ሹ-ሲን ከጤግሮስና ከኤፍራጥስ መኃል አዲስ ታላቅ ግድግዳ ሠርተው ነበር።

የኡር መንግሥት በኤላም እጅ በ1879 ዓክልበ. ገደማ በወደቀበት ጊዜ በመንግሥቱ ውስጥ የኖሩት ብዙ አሞራውያን የራሳቸውን መንግሥታት አቆሙ። «የአሞራውያን መንግሥታት ዘመን» በመስጴጦምያ ታሪክ ከ1879 እስከ 1507 አመታት ከክርስቶስ ልደት በፊት ነው። ዋናዎቹ አሞራውያን ሥርወ መንግሥታት በማሪ፣ በያምሐድ በቃትና፣ በአሦር (በአሞራዊው 1 ሻምሺ-አዳድ ገዥነት)፣ በኢሲን፣ በላርሳና በባቢሎን ተነሡ።

ስለ ቋንቋቸው የሴማዊ ቋንቋዎች ቤተሠብ አባል ከመሆኑና ከጥቂት ስሞች በቀር ምንም ዕውቀት አሁን የለንም። በተለይ በማሪ ጽላቶች (1800-1750 ክ.በ. ገዳማ) መካከል የተገኘ የአንዳንድ አሞራዊ ጽሑፍ በአካድኛ ተጻፈ።

'የአሞራውያን ዘመን' መጨረሻ ኬጥያውያን ባቢሎንን በ1507 ክ.በ. ገዳማ (ኡልትራ አጭር አቆጣጠር) ሲያሸንፉት ነበር። ከዚያ ጀምሮ አዳዲስ ወገኖች - በተለይም ካሣውያንና ሚታኒ - በመስጴጦምያ ተነሡ። ከዚያ በኋላ አሙሩ ሲጠቀስ ማለቱ ስሜን ከነዓን እስከ ቃዴስ ብቻ ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን ውስጥ 'አሞራውያን' በከነዓን ምድር የኖረ ሕዝብ ነው። በኦሪት ዘፍጥረት 10፡16 መሠረት የከነዓን ካም ልጆች ናቸው። በብዙ ጥቅሶች 'አሞራውያን' እና 'ከነዓናውያን' የሚሉት ስሞች የሚለዋወጡ ያሕል ናቸው።

ከጨው ባሕርና ከዮርዳኖስ ወንዝ ምዕራብ ከሆኑት ተራሮች ጀምሮ እስከ ኬብሮን ድረስ ያለው አገር ከነገለዓድና ባሳን ጋር ነበራቸው። ኢያሱ እስራኤላውያንን ዮርዳኖስን አሻግሮ ወደ ከነዓን ሳይመራቸው ሙሴ ከአሞራውያን ንጉሦች ከዐግና ከሴዎን ሠራዊት ጋር ታግሎ አሸነፋቸው። እንዲሁም አሞራውያን በግብፅ በተገኙ አማርና ደብዳቤዎች ዘንድ የጢሮስ፤ የሲዶናና የሌሎች ከተሞች ጠላት ሆኑ። በሳሙኤል ዘመን ግን በእስራኤልና በአሞራውያን መካከል ሰላም ነበረ።




#Article 232: አምልኮ (502 words)


ዘዳግም 6፥13 አምላክህን ያህዌህን ፍራ እርሱንም #አምልክ תַעֲבֹ֑ד በስሙም ማል።
ዘዳግም 10፥20 አምላክህን ያህዌህን ፍራ፥ እርሱንም #አምልክ תַעֲבֹ֑ד ከእርሱም ተጣበቅ፥ በስሙም ማል።
ዘዳግም 13፥4 አምላካችሁን ያህዌህን ተከተሉ፥ እርሱንም ፍሩ፥ ትእዛዙንም ጠብቁ፥ ቃሉንም ስሙ፥ እርሱንም תַעֲבֹ֑ד፥ ከእርሱም ጋር ተጣበቁ።
ኢያሱ 24፥14 አሁንም ያህዌህን ፍሩ፥ በፍጹምም በእውነተኛም ልብ #አምልኩት תַעֲבֹ֑ד አባቶቻችሁም በወንዝ ማዶ በግብፅም ውስጥ ያመለኩአቸውን አማልክት ከእናንተ አርቁ፥ ያህዌህንም አምልኩ תַעֲבֹ֑ד ።
ሳሙኤል ቀዳማዊ 12፥20 ሳሙኤልም ሕዝቡን አለ። አትፍሩ በእውነት ይህን ክፋት ሁሉ አደረጋችሁ ነገር ግን ያህዌህን በፍጹም ልባችሁ #አምልኩት תַעֲבֹ֑ד እንጂ ያህዌህን ከመከተል ፈቀቅ አትበሉ።
ሳሙኤል ቀዳማዊ 7፥3 ሳሙኤልም የእስራኤልን ቤት ሁሉ። በሙሉ ልባችሁ ወደ ያህዌህ ከተመለሳችሁ እንግዶችን አማልክትና አስታሮትን ከመካከላችሁ አርቁ፥ ልባችሁንም ወደ ያህዌህ አቅኑ፥ እርሱንም ብቻ #አምልኩ תַעֲבֹ֑ד… ብሎ ተናገራቸው።
ማቴዎስ 4፥10 ያን ጊዜ ኢየሱስ፦ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ #አምልክ λατρεύσεις ተብሎ ተጽፎአልና አለው።

ልብ አድርግ አንድ ማንነት ብቻ ያለው አንድ አምላክ መሆኑን ለማመልከት “እርሱን” ብቻ አምልክ በሚል በገላጭ”adjective” የተጠፈነገ ነጠላ ተውላጠ ስም እንጂ “እነርሱ” የሚል የለም፤ ታዲያ ሶስት ማንነቶች ያሉባቸውን ምስልና ሃውልት አበይት በሚባሉት በኦርቶዶክስ፣ በካቶሊክ እና በአንግሊካን አብያተ-ክርስቲያናት ለምን ይሰገዳል፣ እጣን ይጨሳት፣ ይሸረገዳል፣ ይጎባደዳል? ይህ የጣኦት አምልኮ ካልሆነ ምን እንበለው? ወገኖቻችን፦ “ለስእልና ለሃውልት የአምልኮ ስግደት ሳይሆን የፀጋ ስግደት ነው የምናደርሰው” ይላሉ፤ እርግጥ ነው የአክብሮት ስግደት ባይብል ላይ ለመላእክትና ለሰዎች አይተናል፤ ግን የት ቦታ ነው ለማይሰማና ለማይለማ ምስልና ሃውልት ስገዱ የተባለው? ከዚያ ይልቅ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ፤ አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም ተብሏል፦
ዘጸአት 20፥4 በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ፤ #አትስገድላቸው፥ #አታምልካቸውምም፤

የሚገርመ የአገራችን ሰዎች እንዲህ ይፀልያሉ፦ “ዓለምን ለማዳን ሲል ኢየሱስ ክርስቶስ “ለ”ተሰቀለበት መስቀልም እስገዳለው” የዘወትር ጸሎት

ኢሳይያስ 44፥17 #የቀረውንም #እንጨት አምላክ አድርጎ ምስል ይቀርጽበታል፤ በፊቱም ተጐንብሶ #ይሰግዳል ወደ እርሱም #እየጸለየ፦ አምላኬ ነህና አድነኝ ይላል።
ኢሳይያስ 45፥20 እናንተ ከአሕዛብ ወገን ሆናችሁ ያመለጣችሁ፥ ተሰብስባችሁ ኑ በአንድነትም ቅረቡ፤ #የተቀረጸውን #የምስላቸውን #እንጨት የሚሸከሙና ያድን ዘንድ ወደማይችል አምላክ #የሚጸልዩ እውቀት የላቸውም።
ኤርምያስ 10፥2-5 ያህዌህ እንዲህ ይላል፦ “የአሕዛብን መንገድ አትማሩ ከሰማይ ምልክትም አትፍሩ፤ አሕዛብ ይፈሩታልና። “የአሕዛብ ልማድ” ከንቱ ነውና፤ ዛፍ ከዱር ይቈረጣል፥ በሠራተኛም እጅ በመጥረቢያ ይሠራል። በብርና በወርቅ ያስጌጡታል፥ እንዳይናወጥም በችንካርና በመዶሻ ይቸነክሩታል። እንደ #ተቀረጸ ዓምድ ናቸው እነርሱም አይናገሩም፤ መራመድም አይቻላቸውማን ይሸከሙአቸዋል። ክፉ መሥራትም አይቻላቸውምና፥ ደግምም መልካም ይሠሩ ዘንድ አይችሉምና አትፍሩአቸው።

የሥላሴ፣ የመላእክት፣ የቅዱሳን ምስልና ሃውልት ክፉ መሥራትም አይቻላቸውም፤ ደግምም መልካም ይሠሩ ዘንድ አይችሉም፤ ካልቻሉ ለምን ይሰገድላቸዋል? ይህ የእኛ የሙስሊሞች ጥያቄአችን ብቻ ነው እንጂ ነቀፌታ ወይም መዘርጠጥ አይደለም፤ አላህ ከእርሱ ሌላ ሰዎች የሚያመልኩአቸውን ጣዖታት አትስደቡ ብሎናል፤ ምክንያቱም ድንበርን በማለፍ ያለእውቀት አላህን ይሰድባሉና፦

ለናሙና ያክል እነዚህ መልእክተኞች፦
ኑሕ

ሁድ

ሷሊህ

ኢብራሂምን

ሹዐይብ

ሙሳ

ዒሳ

ነብያችን

ቁርአን ሲሶው የሚናገረው ስለ ኢባዳ ነው፣ ይህ የቁርአን አንድ ሶስተኛው የአምልኮ ጭብጥ በቀድሞዎቹ መጻሐፍት ውስጥ የተወሳ ነው፣ ለቀድሞቹ ነቢያት የመጣው የተውሂድ ትምህርት ነው በቁርአን ውስጥ የመጣው፣ በፊት ለነበሩት መልክተኞች የተባለው “አምልኩኝ” ሲሆን በነብያችን የተባለው ይህ ነው፤ ይህ ለእሳቸው እና ከእሳቸው በፊት የነበረው የተውሒድ መገሰጫ ነው፦

Or, have they taken gods besides Him? Say: Bring your proof; this is the reminder of those with me and the reminder of those before me. Nay! most of them do not know the truth, so they turn aside. Shakir translation

በቀድሞዎቹ መጻሐፍት ውስጥ ፈጣሪ “ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ” ብሎ የተናገረ አምላክ ዛሬም በዘመናች እኔን ብቻ አምልኩ ብሎ በተከበረው ቃሉ ይናገራል፦




#Article 233: መጽሐፈ ሄኖክ (309 words)


መጽሐፈ ሄኖክ ጥንት የተጻፈ የመጽሐፍ ቅዱስ ዲዩትሮካኖኒካል መጽሓፍ ነው። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ዘንድ ይህም በሰዎች ቃላት በግዕዝ በያሮድ ልጅ በሄኖክ ከማየ አይህ አስቀድሞ ተጽፎ ነበር።

በመጽሓፉ ሄኖክ ከእግዚአብሔር ብዙ ራዕዮች ሲያይ ይናገራል። ደቂቀ ሴት (ትጉሃን) በአመጻቸው ጽናት ከቃየል ልጆች ጋራ አብረው እንዲዋሀዱ ከደብረ ቅዱስ በወረዱበት ጊዜ ሄኖክ እንደ ገሠጻቸው ይላል። የከለሱት ልጆቻቸውም በቁመት አብልጠው ረጃጅሞች እንደተባሉ እነዚህም አባቶቻቸውንና ምድሪቱን እንደ በደሉ ይላል። በሠሩት እጅግ ክፉ ሥራ ምክንያት የጥፋት ውኃ እንደሚደርሰባቸው ፈጽሞም እንደሚያሰምጣቸው የሚል የትንቢትም መጽሓፍ ነው። ይህም ትንቢት ኖህ በኖረበት ዘመን የተፈጸመ እንደነበረ የሚያምኑ ኣሉ። 

በተጨማሪም ሄኖክ ወደ ሰማያት ተወስዶ የሰማይ ቦታዎችን ያሳዩታል። ከዚህ በላይ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ብዙ ይነበያል፤ ያኔ ጻድቃን ሺ ልጆችን ይወልዳሉና በሰላም በደስታ እንደሚኖሩ የሚል ትንቢት ነው። በዚህ መሠረት የመሢህ፣ የሙታን ትንሣኤ እና የዕለተ ደይን ትንቢቶች መጀመርያ ከሄኖክ ወይም ከአዳም ዘመን ጀምሮ ተገለጹ።

መጽሐፉ በሙላቱ የታወቀው በግዕዙ ትርጉም ብቻ ሲሆን፣ የተጻፈበት ቋንቋ፡ በተለይም በኢትዮጵያ መምህራን ዘንድ፡ ግዕዝ መሆኑ ይታመናል። ከዚህም ውጭ አንዳንድ ፍርስራሽ ብራና ቅጂዎች በሙት ባሕር ብራናዎች (በቁምራን ዋሾች) መካከል በአረማይስጥ ቋንቋ በ1950ዎቹ በመገኘታቸው፣ በምዕራባውያን ሊቃውንት ዘንድ መጀመርያ የተቀነባበረበት ልሳን ግዕዝ ሳይሆን አረማይስጥ ይሆናል የሚሉ አሉ። ከዚህም በላይ አንዳንድ የግሪክኛ ወይም የሮማይስጥ ምንባቦች በከፊል ተርፈዋል።

ለምስጋና የሚተጉ የከበሩ የመላእክት ስማችው ይህ ነው። 

ከከበሩ ከመላእክት አንዱ ቅዱስ ዑርኤል በመብረቅ በነጐድጓድ የተሾመ ነው። 

በስው ቁስል የተሾመ ከከበሩ ከመላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው። 
                                                                              
ዲያብሎስን የሚበቀለው አጋንንትንም የሚበቀላችው ከከበሩ ከመላእክት አንዱ ቅዱስ ራጉኤል ነው። 

ለሰው ባደረገው በጎነት ላይ ለሕዝቡ ታዛዥ ነውና ከከበሩ ከመላእክት አንዱ ሚካኤል ነው።

አእምሯቸውን ባጡ ሰዎችም ላይ የተሾመ ከከበሩ ከመላእክት አንዱ ሠረቃኤል ነው።

በባቦች ላይ በጎነትም ባሉ ጻድቃን ላይ በኪሩቤልም ላይ የተሾመ ከከበሩ ከመላእክት አንዱ ገብርኤል ነው። -- ሄኖክ 6፡1-7

የይሁዳ መልእክት፡ 
፡1፡14-15 ከአዳም ጀምሮ ሰባተኛ የሆነ ሄኖክ። እነሆ፥ ጌታ በሁሉ ላይ እንዲፈርድ፥ በኃጢአተኝነትም ስላደረጉት ስለ ኃጢአተኛ ሥራቸው ሁሉ ዓመፀኞችም ኃጢአተኞች በእርሱ ላይ ስለ ተናገሩ ስለ ጭከና ነገር ሁሉ ኃጢአተኞችን ሁሉ እንዲወቅስ ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋር መጥቶአል ብሎ ለእነዚህ ደግሞ ትንቢት ተናገረ።

ስዕል:3-apoch-3-cr.pdf|thumb|left|300px| የሚያዩት ገጽ ላይ ወይም እዚህ ላይ   በመጫን የመጽሐፉን  ገጾች   ማንበብ ይችላላሉ|page=4




#Article 234: ክርስትና (706 words)


ክርስትና በኢየሱስ ክርስቶስ (1ኛ ክፍለዘመን ዓ.ም.) ሕይወትና ትምህርት የተመሠረተ እምነት ነው። 

የክርስትና መጀመርያ የሚተረክበት አዲስ ኪዳን በተለይም ወንጌልና የሐዋርያት ሥራ ነው። የቅሌምንጦስ ስነ ጽሑፍ እንደሚለው ረቢ ኢየሱስ  በይሁዳ ክፍላገር ገና ሲያስተምር፣ ደቀ መዝሙሩ ባርናባስ በሮሜ ከተማ አደባባይ ቆሞ ኢየሱስ መሲኅ መሆኑን አዋጀ፤ ይህ ታሪክ ግን አሁን በምዕራባውያን መምኅሮች ዘንድ አጠያያቂ ሆኗልና በሰፊ አይታወቅም። በሌላ ልማድ ኢየሱስ ለኦስሮኤና ንጉሥ ለ5ኛው አብጋር ደብዳቤ ጻፈ፣ ታዓምራዊ መልክም እንደ ላካቸው ይባላል (የጄኖቫ ቅዱስ መልክን ይዩ።) 

በወንጌል መሠረት ኢየሱስ ከተሰቀለ በኋላ፣ እንደገና በሕይወት ከመቃብር ተነሥቶ ለደቂቀ መዝሙሮቹ እንደገና ታይቶ ከዚያ ወደ ሰማይ ዓረገ። ከዚህ በኋላ የአይሁድ ጉባኤ ጴጥሮስንና ሌሎችን ሐዋርያት አስገረፋቸው፣ በኢየሱስ ስም እንዳያስተምሩ ከለከሉዋቸው። ጴጥሮስ ግን፦ «ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል» ብሎ መለሳቸው (የሐዋርያት ሥራ 5:29)። 

የኢየሱስ ወንድም ያዕቆብ በኢየሩሳሌም የቤተክርስቲያን መጀመርያ መሪ ሆኑ። ከትንሽ በኋላ አይሁድ ያልሆኑ አሕዛብ ምዕመናን እንዲሆኑ ፈቀደ፣ ግርዘት ወይም ሌሎች የሕገ ሙሴ ከባድ ደንቦች አላስገደዳቸውም፣ ነገር ግን ከሕገ ሙሴ «ለጣዖት ከተሠዋ፣ ከደምም፣ ከተናቀም (ከመብላት)፣ ከዝሙትም ትርቁ ዘንድ» አስገደዳቸው (የሐዋርያት ሥራ 15)።  ከዚያ በተለይ በቅዱስ ጳውሎስ ስብከት ምክንያት ክርስትና ወንጌልም በቶሎ በሮማ መንግሥት እስከ ሮሜ ከተማ ድረስ ተስፋፋ።  በተጨማሪ ልዩ ልዩ ሐዋርያት ወንጌሉን እስከ አክሱም መንግሥትና እስከ ሕንድ ድረስ ቶሎ ወሰዱ። 

በ41 ዓም የሮሜ ቄሣር ክላውዴዎስ «አይሁዶችን» ከሮሜ ከተማ ባሳደዳቸው ዘመን፣ ብዙዎቹ ክርስቲያኖች እንደ ነበሩ ይመስላል። ክርስቲያኖች በሮሜ መንግሥት ብዙ ጊዜ እስከ 303 አም ድረስ ከቄሣሮቹ መከራዎች ቢያገኙም፣ ሃይማኖቱ ግን ምንጊዜም እየተበዛ ነበር። 

የአይሁዶች ትምህርት ግን በረቢ አኪቫ በን ዮሴፍ መሪነት በሌላ አቅጣቻ ሄዶ አዋልድ መጻሕፍት ከብሉይ ኪዳን አጠፉና ተልሙድ በተባለ ጽሑፍ አዳዲስ ትምህርቶችን ፈጠሩ። ስለዚህ የሮሜ ንጉሥ ቤስጳስያን የኢየሩሳሌምን ቤተ መቅደስ በ62 ዓም ካጠፋ በኋላ፣ አይሁድና እና ክርስትና እንደተለያዩ ሃይማኖቶች ተቆጥረዋል። 

በ303 ዓም ክርስትና በሮሜ መንግሥት በጋሌሪዎስ ዘመን ሕጋዊ ሆነ። የሚቀጠለው ቄሳር ቆስጠንጢኖስ  በመጋቢት 10 ቀን 313 ዓ.ም. በአዋጅ እሑድ ለሮማ ዜጎች ሁሉ ስለ ጣኦቱ አፖሎ የእረፍት ቀን እንዲሆንላቸው አዘዘ። በኋላ በ317 ዓም እርሱ የንቅያ ጉባኤ ጠራ፣ በዚህ ጉባኤ በዚያን ጊዜ በዕብራይስጥ የተገኙት ጸሐፍት ብቻ (አዋልድ መጻሕፍት ሳይሆኑ) በብሉይ ኪዳን እንዲቀበሉ ተስማሙ። ከጥቂት ዓመታት በኋላ ቆስጠንጢኖስ እራሱ ተጠመቀ። ከዚያስ የሮሜ ቤተ ክርስቲያን የአይሁዶችን «አጭር» ብሉይ ኪዳን የሚያጸድቀው ምንም ቢሆንም፣ እንደ አስርቱ ቃላት ሰንበት በቅዳሜ የከበሩት ሁሉ እንደ «አይሁዳውያን» ሀራ ጤቆች በአውሮጳ ይቆጠሩ ጀመር።

በዚህ ዘመን ያህል ብዙ ሌሎች ተወዳዳሪ ትምህርቶች በሮሜ መንግሥት ይሄዱ ነበር፣ በተለይም፦

ስለዚህ የንቅያ ጉባኤ የንቅያ ጸሎተ ሃይማኖት ወሰነ።  በዚህ ውስጥ ኢየሱስ ወልድ፣ ከአብ ጋራ አንድ ባሕርይ አለው ይላል። በ372 ዓም በተሰሎንቄ ዐዋጅ ቄሣሩ ጤዎዶስዮስ ይህን እምነት በሮሜ ግዛት ውስጥ የመንግሥት ሃይማኖት አደረገው፤ ብዙ የአረመኔ መቅደሶች ተፈረሱ። በሚከተለው ዓመት በ373 ዓም ፩ኛው የቁስጥንጥንያ ጉባኤ የጸሎተ ሃይማኖቱን ይፋዊ ቃላት ትንሽ ቀየሩ፤ በተለይም ስለ መንፈስ ቅዱስ ባሕርይና መለኰታዊነት በይበልጥ የሚገልጹ ቃላት ተጨመሩ።

ከዚያ የተነሣ ወደፊት ቄሣሮች በማንም ሰዓት ጉባኤ በመጥራት ይፋዊ የመንግሥት ሃይማኖት ቀይረው በፍጹም ሊያባልሹት ይቻላል የሚል ጭንቀት ነበር። በተለይ ኢየሱስ «ከአብ ጋር አንድ ባሕርይ አለው» ቢልም፣ ሆኖም ሁለት ልዩ ልዩ ጸባዮች አሉት የሚሉ አስተማሪዎች ሲቀርቡ፣ ይህ ኢየሱስ በሁለት ልዩ ልዩ ጸባዮች ተለይቷል ማለታቸው ወደፊት ቄሣሮቹ በተንኮላቸው ብዛት የመለኮታዊነቱን ጸባይ በይፋ አስለይተው ወደፊትም አንዱን ጸባይ መካድ ይችላሉና የሃይማኖት ጽሑፉን እንደገና ቀይረው 'ተራ ሰው ብቻ መሆኑ የሮሜ ይፋዊ እምነት ነው' ማለት ይችላሉ የሚል ጭንቀት ተነሣ። የንቅያ (ቁስጥንጥንያ የ373 ዓም) ጸሎተ ሃይማኖት ግን እስካሁን ድረስ ምንም ቃል ሳይቀየር በአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ (ካቶሊክ፣ ተዋሕዶ፣ ኦርቶዶክስ እና ፕሮቴስታንት) ይደገፋል። 

ኢየሱስ አንድ «ተዋሕዶ» ጸባይ (ሰውና አምላክ) ያመነበት ወገን እንዲህ ካልሆነ ፈጣሪ ወደ ፍጥረቱ በፍጹምነት ተዋሕዶ ካልገባ በቀር የሰውን ልጅ አያድንም ነበር ባዮች ነበሩ። ነገር ግን የኢየሱስ «ሁለት ጸባዮች» ትምህርት ወዳጅ ወገን በመጨረሻ በፓፓ ኬልቄዶን ጉባኤ (443 አም) ስለ ተቀበለ፣ የሮሜ ፓፓ ከሌሎቹ ጳጳሳት (የእስክንድርያ፣ የአንጾኪያ ጳጳሳት) ተለያየ። እስካሁንም ድረስ ተዋሕዶ የተባሉት አብያተ ክርስቲያናት መጀመርያ ፫ቱ ጉባኤዎች (ንቅያ፣ ቁስጥንጥንያ፣ ኤፌሶን) ብቻ የሚቀበሉ ናቸው እንጂ የኬልቄዶን ጉባኤ አይቀበሉም።  

እስከ 777 ዓም ድረስ በጥምቀት ሥርዓት ወደ ክርስትና የገቡት በጠቅላላ በፈቃደኝነትና በሰላም ነበር። ከነዚህ መካከል ብዙ ሕዝቦች ክርስትናን ተቀበሉ (የክርስትና መስፋፋት ይዩ።) በ777 ዓም ግን የፍራንኮች ንጉሥ ካሮሉስ ማግኑስ የሳክሶኖች ብሔር (በጀርመን የቀሩትን ሕዝብ) በግድና በዛቻ አስጠመቁዋቸው።  ጀርመኖች ደግሞ በበኩላቸው ዞረው የባልቲክ ቋንቋ ተናጋሪ ነገዶችን (በተለይ ላትቪያ፣ ሊትዌኒያ እና የቀድሞው ፕሩሳውያን) በጨካኝ ጦሮች አስጠመቁዋቸውና እንደ ባርዮች ያህል አደረጉዋቸው።  ከነዚዎች ጉዳዮች በስተቀር ግን በክርስትና ታሪክ በአጠቃላይ አብዛኞቹ ብሔሮች የገቡት በሰላምና በፈቃደኝነት ሆኖዋል።  

ኢየሱስ የሰበከው በተለይ በአረማይስጥና በዕብራይስጥ እንደ ነበር ይታመናል። ግሪክኛ ደግሞ በዙሪያው በሰፊ ይነገር ነበርና የአዲስ ኪዳን መጀመርያ የምናውቀው ቅጂ ግሪክኛ ነው። በሉቃስና ዮሐንስ ወንጌላት ዘንድ በመስቀል የተጻፉት ልሳናት ዕብራይስጥ፣ ግሪክኛና ሮማይስጥ ስለ ሆኑ እነዚህም ለዚያው ይከበራሉ። አዲስ ኪዳን በኋላ የተተረጎመባቸው ሌሎች ልሳናት ደግሞ እንደ ክቡራን ቋንቋዎች ተቆጠሩ፤ ግዕዝ፣ ቅብጥኛ፣ አርሜንኛ፣ ጥንታዊ ስላቭኛ እና ሌሎች በአብያተ ክርስትያናት መደበኛ ሆኑ። በአሁኑ ጊዜ አዲስ ኪዳን ወይም ቢያንስ ወንጌል በብዙ ሺህ የሰው ልጅ ቋንቋዎች ተተርጎመዋል።




#Article 235: የኖህ ልጆች (765 words)


የኖህ ልጆች በመጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 10 ይዘርዘራሉ። 

በአዚህ መጽሐፍ ዘንድ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ ከኖህ 3 ልጆች ከሴም ካምና ያፌትና ከሚስቶቻቸው ተወልደዋል ይባላል። ይህም በአውሮፓ ውስጥ በብዙዎቹ እስከ 19ኛ ክፍለ ዘመን ድረስ እንደ ታሪካዊ ዕውነት ይቆጠር ነበር። እስከ ዛሬም ድረስ በብዙ አይሁድ፣ እስላምና ክርስቲያን አማኞች ዘንድ ዕውነተኛ ታሪክ ሆኖ ይታመናል።

የሴማውያን አባት ይባላል። 

አፍሪካውያን እንግዲህ በጥንት የካም ልጆች ተባሉ። እስከ ዛሬ ኩሻውያን ወይም ኩሺቲክ ሕዝቦች ሲገኙ በምዕራብ አፍሪቃ የሚገኙት ዮሩባ ሕዝብ የትውልዳቸውን ሐረግ እስከ ካም ድረስ ያደርሱታል። ከ9ኛው መቶ ዘመን ጀምሮ አንድ አይሁድ የስዋሰው መምህር ይሁዳ እብን ቁራይሽ እንደ አስረዳ የኩሺቲክና የሴሚቲክ ቋንቋ ቤተሠቦች ዝምድናን ያሳያሉ። ዛሬ የቋንቋ ጥናት ሊቃውንት እነዚህን ልሳናት ከግብጽኛ፣ በርበርኛ፣ ቻዲክ፣ እና ኦሞቲክ ቤተሠቦች ጋራ በአንድ ታላቅ አፍሮ-እስያዊ ቋንቋዎች ቤተሰብ ውስጥ ይጨምራሉ። በተጨማሪ በደቡባዊ አፍሪካ ያሉት ቤተሠቦች (እንደ ባንቱ) ከነዚህ የተለዩ ናቸው።

በአንዳንድ የድሮ እና ዘመናዊ አስተያየቶች ዘንድ የያፌት ስም ከሮማውያን አምላክ ዩፒተር ጋር ግንኙነት እንዳለው የሚል ክርክር አቅርበዋል። ከዚህ በላይ ከግሪኩ አፈ ታሪካዊ ቅድማያት ከያፔቶስ ጋር ወይም ከሕንድ አፈ ታሪክ ሰው ከፕራ-ጃፓቲ ጋር ግንኙነት እንደ ነበራቸው የሚሉ ጽፈዋል።

በ1ኛ ክፍለ ዘመን የጻፈው ሮማዊ-አይሁድ ታሪከኛ ፍላዊዩስ ዮሴፉስ (ዮሴፍ ቤን-ማቲትያሁ) የአይሁዶች ጥንቶች በሚለው መጽሐፍ ውስጥ (1፣ 6) በዘፍጥረት 10 ላሉት ስሞች በየቀገኑ ለማስታወቅ ከሞከሩት አንድ ነው። እሱ የጻፋቸው መታወቂያዎች ለተከታተሉት ደራሲዎች መሠረት ሆነው እንዲህ ነበሩ፦

የቅዱስ አቡሊዴስ ዜና መዋዕል (226 ዓ.ም.) በብዙ ሮማይስጥና ግሪክ ቅጂዎች ሲገኝ በኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 10 ላሉት ስሞች በየሕዝቡ መታወቂያ ለመስጠት እንደገና ይሞክራል። አንዳንዴ ከዮሴፉስ ውጤት ጋር ተመሳሳይ ቢሆን ልዩነቶቹ ግን ሰፊ ናቸው፣ እነሱም፦ 

የ346 ዓ.ም. ዜና መዋዕል፣ በክርስቲያን ጸሐፊ ኤጲፋንዮስ ዘሳላሚስ የተጻፈው መጽሐፍ ፓናርዮን (367 ዓ.ም. ገደማ)፣ የፋሲካ ዜና መዋዕል (619 ዓ.ም.)፣ የጅዮርጅያ ታሪከኛ ሙሴ ካጋንካትቫትሲ (7ኛው ክፍለ ዘመን) የጻፈው የአልባንያ ታሪክ እና ዮሐንስ ስኩሊትዜስ የጻፈው የታሪኮች መደምደምያ (1049 ዓ.ም.) ሁሉ የአቡሊዴስን መታወቂያዎች የከተላሉ። 

 

በ382 ዓ.ም. ገዳማ የጻፉት ቅዱስ ሄሮኒሙስ (ጀሮም) በጻፉት ጽሕፈት ዕብራይስጥ ጥያቄዎች በዘፍጥረት የዮሴፉስን መታወቂያዎች በአዲስ ዝርዝር አወጣ። የሄሮኒሙስ ዝርዝር በተግባር እንደ ዮሴፉስ ዝርዝር ይመስላል፤ እነዚህ ልዩነቶች ግን አሉ፦

ጳጳሱና መምኅሩ ኢሲዶሬ ዘሰቪሌ 600 ዓ.ም. ገደማ በጻፉት ኤቲሚሎጊያይ የሄሮኒሙስን መታወቂያዎች ሁሉ ይደግማል፣ ከነዚህ ጥቃቅን ልዩነቶች በቀር፦:

የኢሲዶሬ መታወቅያዎች ለያፌት ልጆች እንደገና በሂስቶሪያ ብሪቶኑም ይገኛሉ። የኢሲዶሬ መታወቂያዎች ደግሞ ለብዙ ኋለኞች መካከለኛ ዘመን መምህራን መሠረት ሆኑ።

በዘፍጥረት 10 የሚገኘው ትውልድ መጽሐፍ፣ የልጆቹ ስሞች 70 ወይም 72 አገሮችና ቋንቋዎች ሆኑ። ይህ እምነት ለረጅም ዘመን ሳይጠየቅ ተቀበለ። ነገር ግን በቅርቡ ክፍለ ዘመናት የቋንቋ ጥናት ሲመሠረት አዳዲስ ጥያቄዎች በአውሮፓ ተፈጠሩ። ጥያቄዎች የተነሡባቸው ዋን ምክንያቶች፦

ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ኖኅ ከሴም ካምና ያፌት ጭምር ሌላ ልጅ እንደ ተወለደለት የሚናገሩ ልዩ ልዩ ታሪኮች ይገኛሉ። በነዚህ ምንጮች ዘንድ ተጨማሪው ልጅ የሚወለደው ወይም ከማየ አይህ በፊት፣ ወይም በኋላ (ወይም በውሃው ጊዜ እራሱ) በመሆን ይለያል። 

በቁራን ሱራ «ሁድ» ዘንድ (11፡42-43) በመርከቡ እንዳይሣፈር እምቢ ያለ ሌላ ወንድ ልጅ ለ ኖኅ ነበረው። በመርከቡ በመሣፈር ፈንታ እሱ በተራራ ወጣና ሰመጠ። አንዳንድ የእስልምና ጸሐፊ ስሙ ወይም ያም ወይም ከነዓን እንደ ነበር ጽፏል። 

በአይርላንድ አፈ ታሪክ ዘንድ፣ በመርከቡ ለመሣፈር ያልተፈቀደ ቢጥ የተባለ ሌላ ወንድ ልጅ ለኖኅ ነበረው። በዚህ ታሪክ መሠረት ቢጥ ከዚያ በኋላ ወደ አይርላንድ ከነቤተሠቡ (በጠቅላላ 54 ሰዎች) ቢፈልሱም፣ ሁላቸው በማየ አይኅ ግን ሰጠሙ። 

በ9ኛው መቶ ዘመን ዓ.ም. በተጻፈ የአንግሎ-ሳክሰን ዜና መዋዕል ዘንድ፣ ሼይፍ የዌሰክሽ ሥርወ መንግሥት ቅድማያት ሲባል በመርከቡ ላይ የተወለደ የኖህ አራተኛ ወንድ ልጅ መሆኑ ይነገራል። በ1112 ዓ.ም. ገደማ ዊልያም ኦፍ ማልምዝቡሪ የእንግሊዝ ነገሥታት ትውልድ ጽፎ ግን ይህ ሼይፍ በመርከቡ ላይ ከተወለደው ከኖህ አራተኛው ወንድ ልጅ ከስትሬፊዩስ ዘር እንደ ነበር ብሏል። 

ኪታብ አል-ማጋል የተባለው ጥንታዊ አረብኛ መጽሐፍ (ከ«ቄሌምንጦስ መጻሕፍት» መሃል) እንደሚለው የኖህ አራተኛ ወንድ ልጅ ቡኒተር ከማየ አይኅ ቀጥሎ ተወልዶ ሥነ ፈለክም ፈጥሮ የናምሩድ አስተማሪ ሆነ። ለዚህ ተመሳሳይ ታሪኮች ለኖህ አራተኛ ልጅ የተለያዩ አጠራሮች ሲሰጡት ይታያል። ከነዚህም ጥንታዊው የግዕዝ ሰነድ መጽሐፈ አዳምና ሕይዋን (ስሙ ባርዊን ሆኖ)፤ ጥንታዊው የጽርዕ ሰነድ የመዝገቦች ዋሻ (ዮንቶን)፤ ፕሲውዶ- ('ሐሰተኛ') ሜቶድዮስ በተባለው ሰነድ (ዮኒቱስ)፣ በጽርዕ በ1213 ዓ.ም. የተጻፈው መጽሐፈ ንቡ (ዮናቶን)፤ በዕብራይስጥ በ12ኛው-14ኛው መቶ ዘመን አካባቢ የተጻፈው የይረሕምኤል ዜና መዋዕል (ዮኒጠስ)፣ እና በበርካታ አርሜንኛ ራዕዮች ውስጥ ማኒቶን ይባላል። ከዚህም በላይ ስለ ኖህ 4ኛ ወንድ ልጅ ተመሳሳይ ታሪኮች በጸሐፊዎቹ ጴጥሮስ ኮሜስቶር በ1152 ዓ.ም. ገደማ (ዮኒጡስ)፣ ጎድፍሬይ ዘቪቴርቦ 1177 ዓ.ም. (ኢሆኒቱስ)፤ ሚካኤል ሶርያዊው 1188 ዓ.ም. (ማኒቶን)፤ አቡ ሳሊኅ አርመናዊው 1200 ዓ.ም. ገደማ (አቡ ናይጡር)፤ ያዕቆብ ቫን ማይርላንት 1232 ገደማ (ዮኒቱስ)፤ አብርሃም ዛኩቶ 1496 ዓ.ም. (ዮኒኮ) እና ይሒኤል ቤን ሰሎሞን ሃይልፕሪን 1689 ዓ.ም. ገደማ (ዩኒኩ)።

ማርቲን ዘኦፓቫ (1240 ዓ.ም. ገደማ)፣ የሚራቢሊያ ዑርቢስ ሮማይ ኋለኛ ቅጂዎች፣ እና የጆቫኒ ዲ ማሪንዮላ ክሮኒኮን ቦሄሞሩም (1347 ዓ.ም.) ሁላቸው ሲስማሙ፣ ወደ ጣልያን አገር ፈልሶ ሥነ ፈለክን ፈጥሮ ናምሩድንም ያስተማረው የኖህ አራተኛ ወንድ ልጅ ያኑስ ነበረ (የሮማ አረመኔው አምላክ 'ያኑስ' ሆነ ለማለት ነው)። 

በመነኩሴው አኒዮ ዳ ቪቴርቦ ዘንድ (1490 ዓ.ም.)፣ በግሪኮች ዘመን (~300 ዓክልበ) በባቢሎን የጻፈው ታሪከኛ ቤሮሶስ ለኖኅ ከማየ አይኅ በኋላ 30 ልጆች እንደ ተወለዱለት ጽፎ ነበር። ከነዚህም መካከል ቱዊስኮን፣ ጵሮሜጤዎስ፣ ያፔቶስ፣ ማክሮስ፣ «16 ቲታኖች»፣ ክራኖስ፣ ግራናዎስ፣ ውቅያኖስ እና ቲፌዮስ የተባሉ ወንድ ልጆች በስም ይጠቀሳሉ። ደግሞ የኖኅ ሴት ልጆች አራክሳ «ታላቂቱ»፣ ሬጊና፣ ፓንዶራ፣ ክራና እና ጤቲስ ይባላሉ። ነገር ግን አኒዮ ያገኘው ሰነድ የቤሮሶስ ሳይሆን ሐሰተኛ መሆኑ ዛሬ አይጠረጠርም።




#Article 236: ከነዓን (ጥንታዊ አገር) (1909 words)


ከነዓን ጥንታዊ አገር ሲሆን ዛሬ በእስራኤልና በሊባኖስ አካባቢ ያሉትን አካባቢዎች ያጠቃልል ነበር። በመጽሐፍ ቅዱስ ዘንድ እግዚአብሔር ይህን አገር ለአብርሃም ልጆች በቃል ኪዳን ሰጠ። 

ቅድመ-ታሪክ ከማናቸውም መዝገቦች በፊት የሆነ ጊዜ ነውና እዚህ በተለይ ብዙ አስተያየቶች ስላሉ የከነዓን ቅድመ ታሪክ ተከራካሪ ሆኗል። በብዙ ምዕራብ ሥነ ቅርስ ሊቃውንት ዘንድ ኢያሪኮ ከሁሉ አስቀድሞ የተሠፈረው ቦታ ሲሆን በ9000 ዓክልበ. እንደ ተሠራ ይላሉ። ይህን ዕድሜ ለማረጋገጥ ግልጽ አይሆንም። የግብጽ ጥንታዊ መንግሥት ፈርዖኖች (1-6ኛ ሥርወ መንግሥታት)  አቅራቢያውን ሰትጨት እንዳሉት ይመስላል፤ አንዳንድ ሰረኾች (የፈርዖን አርማዎች) በተለይም የናርመር ሰረኽ (ከ3100 ዓክልበ. ግድም) እዚያ ተገኝተዋል።

አገሩ በኋላ «ከነዓን» እና «ማር-ቱ» ተብሎ ታሪኩ ከተለያዩ ምንጮች ሊሰበሰብ ይችላል።

በኦሪት ዘፍጥረት አገሩ ስለ መሥራቹ ከነዓን (የካም ልጅ) ተሰየመ።  በመጽሐፈ ኩፋሌ ዘንድ፣ ካምና ሌሎች ልጆቹ ኩሽ፣ ምጽራይምና ፉጥ ከሰናዖር ወደ አፍሪካ በተጓዙበት ጊዜ ከነዓን ግን ሥምምነታቸውን ጥሶ በአርፋክስድ ርስት በዚያው አገር ተቀመጠ። በሱመር አፈ ታሪክ ደግሞ የአሞራውያን ምድር ወይም «ማርቱ» ከኤፍራጥስ ወንዝ ምዕራብ ያለው አገር ሲሆን በዚህ ሰዓት ያሕል (2425 ዓክልበ. ግድም)  የሱመር መጀመርያው ንጉሥ ኤንመርካር በማርቱ ላይ ግድግዳ እንዳሠራ ይጠቅሳል። 

ከ2390 ዓክልበ. በፊት ከተሞች በጌባልና ሲዶን (በፊንቄ) ተሠሩ፣ መርከበኞቻቸውም በባሕርና በውቅያኖስ ላይ በመጓዝ አንጋፋዎች ሆኑ። ሌሎችም ከተሞች በሐማትና አርቃ ተሠሩ። በ2345 ዓክልበ. ግ. በኤፍራጥስ ላይ የማሪ መጀመርያ ንጉሥ ጋንሱድ ይጠቀሳል፤ ይህም ከተማ ለማር-ቱ (ሶርያ) እና ለመስጴጦምያ የንግድ ማዕከል ሆነ።  በስተ ደቡብ የሲዲም ሸለቆ (ሰዶም ወዘተ.) ምናልባት 2235 ዓክልበ. ተሰፈረ።

ከ2210 ዓክልበ. በኋላ ከግብጽ የመኮትኮቻ ጥቅም በከነዓን ይስፋፋ ጀመር።  በዚህ ዘመን ደግሞ የላጋሽ ንጉሥ ሉማ ከ2200 እስከ 2195 ዓክልበ. ድረስ ማሪን ይዞ ነበር፣ በማረፉ ግን ማሪ ወዲያው እንደገና ነጻ ሆነ። እንዲሁም ከ2175 ዓክልበ. ጀምሮ ከመስጴጦምያ የማረሻ ጥቅም በከነዓን ይስፋፋ ጀመር።

በ2150 ዓክልበ. ግ. በኋላ ለትንሽ ጊዘ አስጊ ሁኔታ (ጦርነት ወይም ረሃብ) በከነዓን ስለ ደረሰ፣ አንዳንድ ብሔር ወደ ውጭ እንደ ፈለሰ ይመስላል። ከነዚህም መካከል የሲኒ እና የሰማሪዎን ነገዶች በኋላ በኩሽ መንግሥት እንደ ደረሱ በኢትዮጵያ መዝገቦች ይጻፋል።  

በ2125 ዓክልበ. ግ. በስሜኑ በሶርያ ተዋዳዳሪ የኤብላና የማሪ ግዛቶች ይበረቱ ጀመር። ከዚህ ትንሽ በኋላ (2122 ዓክልበ.) የሱመር (አዳብ) ንጉሥ ሉጋል-አኔ-ሙንዱ በደቡብ ያለውን ምድር እስከ ዮርዳኖስ ወንዝ ድረስ ያዘ።  በመጽሐፈ ኩፋሌ አቆጣጠር አብርሃምና ሣራ ወደ ከነዓን የፈለሱ በ2118 ዓክልበ. ሲሆን የሰናዖር ንጉሥ አምራፌልን ዘመን ያሳስባል። ያንጊዜ ኬብሮንና ደማስቆ ከተሞች፣ በኋላም ሐቲ አገር ወደ ስሜኑ በኬጥያውያን ተሠፈሩ። በ2115 ዓክልበ. ረሃብ በከነዓን ስለ ሆነ አብርሃምና ሣራ ወደ ግብጽ ወረዱ፤ እንዲሁም በ2110 ዓክልበ. የቅማንት አባት ከነዓናዊው አይነር ወደ ኩሽ እንደ ፈለሰ ይዘገባል። በ2108 ዓክልበ. ሰዶምና ሌሎቹ የሲዲም ከተሞች ከአምራፌል አገዛዝ አመጹ፣  በሚከተለውም  አመት የአምራፌል ሃያላት መጥተው የአብርሃም ሥራዊት ግን አጠፋቸው። በዚህ ጊዜ በሱመር ታሪክ ሉጋል-አኔ-ሙንዱ ወድቆ የሱመር ላዕላይነት ለጊዜው ወደ ማሪ እንዳለፈ ይመስላል።  የሰዶም ጥፋት በኩፋሌ አቆጣጠር በኋላ በ2092 ዓክልበ. ከእሳት ደረሰ። በ2080 ዓክልበ. ግድም ሳሌም (ኢየሩሳሌም) ተመሠረተ።

በ2074 ዓክልበ. (ኡልትራ አጭር አቆጣጠር) የአካድ ንጉሥ ታላቁ ሳርጎን ኤብላን አጠፋና በስሜኑ ሶርያን ያዘ። ከ፲ አመት በኋላ ሳርጎን ባረፈ ጊዜ ግን ሶርያ እንደገና ነጻ ሆነ፣ ያንጊዜ ወደ ግብጽ ተጽእኖ ተዛወረ። የሶርያና በተለይም የሊባኖስ ግንኙነት ከግብጽ ጋራ ምንጊዜም በመርከብ ይካሄድ ነበር። 

በ2036 ዓክልበ. ደግሞ የሳርጎን ተከታይ ናራም-ሲን በሶርያና ሊባኖስ አካባቢ ዘመተ፤ እርሱም ከ፮ አመት በኋላ አርፎ አገሩ እንደገና ነጻ ሆነ።   በአንድንድ ዜና መዋዕል ዘንድ ኢያሪኮ በዚህ ወቅት ያህል ተሰፈረ። 

በ2021 ዓክልበ. የአካድ ንጉሥ ሻርካሊሻሪ እንደገና በአሞራውያን ላይ በሶርያ ዘመተ።  በዚህም ወቅት ያህል ነባታያውያን ከእስማይል ልጆች በደቡባዊ በረሃ ማዶ ተመሠረቱ።

ከአካድ መንግሥት በኋላ የግብጽ ተጽእኖ እንደገና ወደ ሶርያና ሊባኖስ ተመለሠ።

ከኩፋሌ አቆጣጠር ያዕቆብ ለዔሳው ስለ ረሃብ ምስር ወጡን የሼጠበት አመት 1991 ዓክልበ.፣ ይስሐቅም ወደ ጌራራ ፍልስጥኤማውያን ንጉሥ አቢሜሌክ የሄደበት አመት 1990 ዓክልበ. ሆነ። 

በአንድ ግብጻዊ ጽሑፍ «የሲኑሄ ታሪክ» ዘንድ፣ የ1 ሰኑስረት አለቃ ሲኑሄ በ1972 ዓክልበ. አካባቢ በረጨኑ (ስሜን ከነዓን ወይም ሶርያ) ይዘመት ነበር። በኋላ በተከታዩ 2 አመነምሃት ዘመን በ1932-1930 ሥራዊቱ በሶርያና ሊባኖስ እንደ ዘመተ ይዘገባል። የብርጭቆ መሥራት ኢንዱስትሪ የተጀመረው በፊንቄ በዚህ ወቅት ያህል እንደ ነበረ ይመስላል። 

በደቡቡ ግን በዚሁ ወቅት የያዕቆብ (እስራኤል) ሥራዊት ይበረታ ነበር።   በ1928 ዓክልበ. የሴኬም ንጉሥ ኤሞርን አጠፉ፣ በ1923 ዓክልበ. አሞራውያን አሸነፉ፣ በ1909 ዓክልበ. የዔሳው ስራዊት (ኤዶምያስን) አሸነፉ። 

አሞራውያንም በዚህ ሰዓት በመስጴጦምያ ውስጥ ይበዙ ጀመር። በ1899 ዓክልበ. ታላቁ ረሃብ በደረሰ ጊዜ፣ አሞራውያን የኢሲን መንግስት በሱመር መሠረቱ፣ የያዕቆብም ቤተሠብ ከከነዓን ወደ ጌሤም ወረዱ።  

ዕብራውያን በጌሤም እየኖሩ የግብጽ ፈርዖን 3 ሰኑስረት በ1884 ዓክልበ. ምድያም፣ ሴኬምና ረጨኑ ወርሮ ያዘና የከነዓን ምድር ለጊዜው  ወደ ግብጽ መንግሥት ተጨመረ።  ይህም ሰኑስረት እስካረፈበት ጊዜ እስከ 1859 ዓክልበ. ድረስ ቆየ፣ ያንጊዜ ከነዓን እንደገና ከግብጽ ነጻ ሆነ።

አሁን ከዕብራውያን በላይ በርካታ ሌሎች ከነዓናዊ ያልሆኑት ህዝቦች በአካባቢያቸው ተገኙ፦ ፍልስጥኤማውያን እንደ ከነአናዊ አልተቆጠሩም፣ እንዲሁም ኤዶምያስ፣ ምድያም፣ ነባታያውያን፣ ሞአብ፣ አሞን፣ አማሌቅ የተባሉት አገሮች ሁላቸው ከሴማውያንና ከዕብራውያን ዘመዶች ተነሡ።

ከሰኑስረት በኋላ፣ ከነዓን እንደገና ነጻ ከተማ አገሮች ሆነ። አሞራውያን አለቆች በመስጴጦምያ ጉዳይ ጥልቅ እያሉ፣ ዕብራውያን በጌሤም፣ የአሦርም ካሩም በሐቲ ነጋዴዎች የሆኑበት ወቅት ነበር። 

በዚህ ዘመን ያሕል (ምናልባት ከ1800-1400 ዓክልበ. ግድም) በጌባል (ቢብሎስ) ከተማ እስካሁን ሊነበብ የማይቻለው የጌባል ጽሕፈት ከግብጽ ሃይሮግሊፎች እንደ ተለማ ይታስባል።  

በጌሤም ዕብራውያን ከ1821 እስከ 1742 ዓክልበ. ድረስ የየራሳቸውን 14ኛው ሥርወ መንግሥት የነበራቸው ይመስላል።  በ1808 ዓክልበ. ግን የግብጽ ፈርዖን ከከነዓን ንጉሥ መምካሮን ጋር ጦርነት ስላደረገ የግብጽ በሮች እንደ ተዘጉ በኩፋሌ ይዘገባል። ከከነአን ስለደረሱ  ዕብራውያንም  ከዚህ በኋላ በጥርጣሬ ይታዩ ጀመር። ከ1742 ዓክልበ. በኋላ በጌሤም የነበሩት ወደ ባርነት ተገደዱ።

ከዚያ በኋላ በሶርያ ከተማ ሐለብ ዙሪያ የያምኻድ መንግሥት ተነሣ።  የያሚና ልጆች ወይም «ብኔ-ያሚና» (የቀኝ ልጆች) የተባለ ብሔር ከያምሓድ ቢደገፍም፣ የማሪ ነገሥታት ከ1720-1690 ዓክልበ. ይዘመቱባቸው ነበር።  

ዕብራውያን ከግብጽ በጸአት አምልጠው በ1661 ዓክልበ. ግ. የግብጽ ሃይል እጅግ ደክሞ ወዲያው ሌሎች አሞራውያን «ሂክሶስ» ግብጽን ወርረው እንደ ገቡ ይመስላል። በኦሪት መሠረት፣  ከ፵ ዓመት በኋላ ዕብራውያን በሙሴ መሪነት ከዮርዳኖስ ምዕራብ የተገኙት አሞራውያን ነገሥታት ሴዎንንና ዐግን አሸነፉዋቸው፤ በኋላም በኢያሱ ወልደ ነዌ መሪነት ከዮርዳኖስ ምሥራቅ የነበሩትን ከነዓናውያን አሸነፉዋቸው። በያህዌ ትዕዛዝ ሀገሩ ለአብርሃምና ለአርፋክስድ ሰጥቶ ስለሆነና ስለከነዓናውያን አስቀያሚ መረንነት እንደ ነበር በኦሪትም ይገልጻል። ከነዓናውያን ግን በጥቂት ሥፍራዎች ቀሩ፣ እስራኤልም በበረታ ጊዜ ለዕብራውያን አገልጋዮች ሆኑ።

የዕብራውያን ወረራ በከነዓን በተለይ በመጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ ይገለጻል። መጀመርያ ኢያሪኮንና ጋይን ያዙ፣ ከዚያም ገባዖን ተገዛላቸው። አምስት የአሞራውያን ነገሥታት፦ የኢየሩሳሌም ንጉስ አዶኒጼዴቅ፣  የኬብሮን ንጉሥ ሆሃም፣ የየርሙት ንጉሥ ጲርአም፣ የለኪሶ ንጉሥ ያፊዓ፣ የኦዶላም ንጉሥ ዳቤር ለመቃወም ተሰብስበው ኢያሱ አጠፋቸውና ደቡቡን ከነዓን ሁሉ ያዘ። ትልቅ ተዓምራት እንደ ተደረጉ ይጻፋል። ካሌብ ኬብሮን የተሰጠው ከጸአት 45 ዓመት በኋላ (ኢያሱ 14:10) ወይም በ1616 ዓክልበ. ነበር። ከዚያ የአሶር (ሐጾር) ንጉስ ኢያቢስና የማዶን ንጉሥ ዮባብ በስሜን ተቃወሙት፣ ኢያሱም አሸነፋቸውና ሐጾርን አቃጠለ።  ከኢያሱ ዘመቻዎች በኋላ የከነዓን ሰዎች በአንዳንድ ቦታዎች በተለይ በፍልስጥኤምና በፊንቄ አካባቢ ቀሩ። 

ወደ ስሜኑ በሶርያ የያምኻድ ንጉሥ እርካብቱም (1587-1575) ከ«ሃቢሩ ወገን አለቃ «ሰሙማ» ስምምነት እንዳደረገ ይዘገባል። ከዚህ ጀምሮ «ሃቢሩ / አፒሩ» የተባለው ወገን በከነዓን ምድር ሃይለኛ ወገን እንደ ነበሩ በብዙ መዝገቦችና ሰነዶች በእርግጥ ይታወቃል።  ሆኖም የመጽሐፍ ቅዱስ ታማኝነት ለምዕራባውያንና ለአይሁዳውያን ሊቃውንት እጅግ ተከራካሪ በመሆኑ ምክንያት፣ ስለዚህ የ«ሃቢሩ»  መታወቂያ ከዕብራውያን ጋር አንድ አይሆንም፣ ይህም እንግዲህ ከግድ አጋጣሚ መሆን አለበት የሚሉ ናቸው። በ1550 ዓክልበ. ግድም የሶርያ ሑራውያን ቲኩናኒ ከተማ ንጉሥ ቱኒፕ-ተሹፕ በሥራዊቱ የተገኙት ሃቢሩ ስሞች በቲኩናኒ ፕሪዝም ላይ ሲዘረዝር፣ ብዙዎቹ ሑርኛ፣ የተረፉትም ሴማዊ ስሞች ነበሩዋቸው። 

በ62 ዓም ገደማ የተጻፈው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥንታዊነት የተባለው መጽሐፍ ብቻ ከኢያሱ ዘመን ቀጥሎ ስለ ፈረዱት ቄኔዝና ዜቡል 82 ዓመታት ይዘርዝራሉ። በ1548 ዓክልበ. አዲሱ ግብጻዊ ፈርዖን 1 አሕሞስ ሂክሶስን አባርረው ሂክሶስ በደቡብ ሻሩሔንን ከስሜዖን ርስት ያዙ። አሕሞስ ከብቦት ከ6 ዓመት በኋላ ሻሩሔንን አጠፋ። በ1537 ዓክልበ. ደግሞ የአሕሞስ ባሕር ሃይል በጌባል፣ ፊንቄ አካባቢ እንደዘመቱ ይመስላል። በዚህም ዘመን የኬጥያውያን መንግሥት ከስሜን ወደ ሶርያ ገብተው በ1531 ዓክልበ. ሐለብን ይዘው የያምኻድን መንግሥት አስጨረሱ። በኋላ ፈርዖኑ 1 ቱትሞስ በ1513 ዓክልበ. ግድም በሶርያ ሑራውያን (ናሐሪን) ላይ እስከ ኤፍራጥስ ድረስ እንደ ዘመተ ይመስላል። ተከታዩም 2 ቱትሞስ ደግሞ (1500 ዓክልበ. ግድም) «ሻሱ» በተባለ ወገን ላይ በከነዓን ይዘምት ነበር። እነዚህም «ሻሱ» (ማለት «ዘላኖች») በግብጽ መዝገቦች ከ1500-1200 ዓክልበ. ያሕል ሲገኙ፣ «ሃቢሩ» ያልሆነ ሌላ የተለየ ወገን ናቸው፤ መታወቂያቸውም ተከራካሪ ሆኗል። ከኤዶምያስና ከዙሪያው እንደ ወጡ ቢመስልም፣ እኚህ «ሻሱ» በውነት የአይሁድ አባቶች እንደ ሆኑ የሚሉ አስተሳስቦች ይኖራሉ።  

በ1506 ዓክልበ. ግድም የመስጴጦምያ (ዕብራይስት፦ አራም-ናሐራይም) ንጉሥ ኲሰርሰቴም ወርሮ እስራኤልን ገዛ። በዚሁ ዘመን ደቡብ መስጴጦምያ ወይም ባቢሎን ለካሣውያን ወገን እየወደቀ፣ በስሜኑ መስጴጦምያና ሶርያ ደግሞ ሑራውያን የተባሉት ነገዶች በሚታኒ ገዥነት ወደቁ፣ አገራቸውም በተጫማሪ «ናሓሪን» («ሁለቱ ወንዞች») ይባል ነበር። የሚታኒ መጀመርያ ንጉሥ ኪርታ ሲባል እርሱ ከሶርያ በላይ ምናልባት መላውን ከነዓን ያስተዳደር ነበር። ያም ሆነ ይህ ከ8 ዓመታት በኋላ (1497 ዓክልበ.) ጎቶንያል የናሓራይም ሥራዊት እንዳሸነፈና የእስራኤል ፈራጅ እንደ ሆነ በመጽሐፈ መሳፍንት እናንባለን። በ1473 ዓክልበ. ግድም በሶርያ «ሃቢሩ» ከሐለብ መስፍን ኢድሪሚ ጋር ተባብረው አላላኽን ለመያዝ እንደ ረዱት ይታወቃል።

ከነዓናውያን በባሕር ዳርና በመጊዶ አካባቢ ቀርተው ነበር (መሳፍንት 1:27)። በ1465 ዓክልበ፣ ፈርዖኑ 3 ቱትሞስ በባሕር ዳር ላይ ገስግሦ የመጊዶ እና የቃዴስ አሞራውያን ነገሥታትን በታላቁ መጊዶ ውግያ ድል አደረጋቸው። ሃቢሩ ፍላጻ ወርዋሪዎች በፈርዖኑ ሥራዊት እንደ ተገኙ ይዘገባል።  በሚከተሉት አመታት እስከ 1437 ዓክልበ ያህል ድረስ የግብጽ ሥራዊት ሶርያን ከሚታኒ መንግሥት ያዙ። በደቡብም፣ በመሳፍንት መሠረት ሞአባውያን (ከአሞንና አማሌቅ ብሔሮች ተባብረው) በእስራኤላውያን ላይ ከ1457 እስከ 1439 ዓክልበ ድረስ ወይም ፈራጁ ናዖድ የሞአብን ንጉሥ ዔግሎምን እስካሸነፈው ድረስ ገዝተው ነበር። የ3 ቱትሞስ ተከታይ 2 አመንሆተፕ እንዲሁም እስከ 1426 ዓክልበ ድረስ በሚታኒ ላይ በሶርያ ዘምቶ፣ በዚያው ዓመት ስምምነት ተደረገና በታላቅ አገራት ግብጽ፣ ሚታኒ፣ ባቢሎንና ኬጥያውያን መካከል ዲፕሎማስያዊ ግንኙነቶች ተመሠረቱ።

ናዖድ ሞዓባውያንን ካሸነፈ በኋላ እስራኤላውያን ለ80 ዓመት ወይም 1439-1359 አክልበ. ድረስ ነጻ ነበሩ።  በዚያ ዘመን ወደ መጨረሻ ሴመጋር 600 ፍልስጥኤማውያን በበሬ መውጊያ እንደ ገደላቸው በመሳፍንት 3:31 ይዘገባል፤ ስለዚያ ወቅት ከዚህ በላይ አይነግረንም። ከ1400 ዓክልበ. ገደማ ጀምሮ በሶርያ ባሕር ዳር ላይ የነበረው ትልቅ ከተማ ኡጋሪት ሰዎች ለሴማዊ ቋንቋቸው የራሳቸውን አልፋቤት ፈጠሩ፣ እስከ 1200 ዓክልበ. ድረስ ይጻፍ ነበር። ይህ የኡጋሪት አልፋቤት እንደ ኩኔይፎርም መሰለ፣ የፊደሎቹም በሁለት ቅደም ተከተሎች እንደ ግዕዝ (አ፣ በ፣ ገ፣ ደ) ወይም (ሀ፣ ለ፣ ሐ፣ መ) መሰሉ። (ሌላው ኩኔይፎርም ያልሆነ «ቅድመ-ከነዓናዊ» የተባለው ፊደል ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት የተደረጀ ሲሆን ከ1200 ዓክልበ. በፊት ብዙ አልታየም፤ ይህ ግን ከ1050 ዓክልበ. ጀምሮ የፊንቄ አልፋቤት ስለ ወለደ በዚያ ለአውሮፓ ዘመናዊ አልፋቤቶች ሁሉ  ወላጅ ሆነ።)

ከ1369 እስከ 1339 ዓክልበ. ድረስ ደግሞ በግብጽ የተገኙት የአማርና ደብዳቤዎች ዘመን ነው። ብዙዎቹ ደብዳቤዎቹ በአካድኛ (ኩኔይፎርም) ከከነዓን ገዦች ወደ ፈርዖኖች 3 አመንሆተፕና አኸናተን ተጽፈው፣ የሃቢሩ ወገን በከተሞቻቸው ላይ እንደ ታገሉ ይመስክራሉ።  በስሜኑ፣ አንዳንድ ሃቢሩ ከአሞራውያን አለቆች አብዲ-አሺርታና ልጁ አዙሩ ጋር ተባብረው የሊባኖስን ጠረፍ ከኡጋሪት ወደ ደቡብ እስከ ሲዶና ድረስ እየቃሙ ነበር።  ወደ ደቡብም፣ ሃቢሩ ወገኖች ከሴኬም ንጉስ ላባያ ጋር ተባብረው ለጊዜው ሐጾርን ይዘው ብዙ ከነዓናዊ ከተሞች ከነመጊዶና ኢየሩሳሌም ለፈርዖን እርዳታ ይለምኑ ነበር። ከዚህም ወቅት ጀምሮ «አሕላሙ» (የአራም ሕዝብ) በሶርያ ገብተው ብዙ ጊዜ ይጠቀሱ ጀመር። በ1359 ዓክልበ.  መጽሐፈ መሳፍንት እንዳለን፣ የሐጾር ንጉሥ ያቢስ (ያቢን ወይም እብኒ) እና አለቃው ሲሰራ 900 ሠረገላዎችን ይዘው እስራኤልን አሸነፉ፣ ለሃያ ዓመት ገዙአቸው። በ1339 ዓክልበ. ነቢይቱ ዲቦራና ባራክም እንደገና ያቢስን ድል አደረጉት።

በዚህም «አማርና ደብዳቤዎች ዘመን» ኬጥያውያን እንደገና ወደ ደቡብ ገፍተው ከ1357 ዓም ጀምሮ ሚታኒ ይገዛላቸው ነበር። አሦራውያንም ያንጊዜ እንደገና ነጻ ሆነው ይበረቱ ጀመር፤ ከ1327 ዓክልበ. በኋላ ሚታኒ ለነርሱ ይወድቅ ጀመር። ተወዳዳሪ የግብጽና የኬጥያውያን ነገሥታት ብዙ ጊዜ በሶርያ ይዘመቱ ነበር፤ በመጨረሻ በትልቁ የቃዴስ ውግያ በ1282 ዓክልበ. ኬጥያውያን የፈርዖኑን 2 ራምሴስ ስራዊት ድል አደረጉ። በ1266 ዓክልበ. ራምሴስ ከኬጥያውያን መንግሥት ጋር ዘላቂ ስምምነት ተዋዋለ። ከ1299 እስከ 1292 ዓክልበ. ድረስ ግን ዕብራውያን ለምድያምና አማሌቅ ሰዎች ተገዝተው ሰብላቸውን እንደቀሙ በመሳፍንት እናብባለን። ከዚያ ጊዴዎን የተባለው ፈራጅ ምድያምን አሸንፎ ነገስታቸውን ዛብሄልንና ስልማናን ገደላቸው፤ እስከ 1252 ዓክልበ. ድረስ ፈራጅ ሆነ።  የግብጽም ሰነዶች በዚሁ ዘመን ያህል አሸር የተባለውን ዕብራውያን ነገድ በዙሪያው ጠቅሰዋል።

ከጊዴዎን በኋላ በመሳፍንት ዘንድ አቢሜሌክ ለሦስት አመት (1252-1249 ዓክልበ.) በእስራኤል ላይ ንጉሥ ሆነ። የራሱ ከተማ ሴኬም ስለ አመጸበት አጠፋው። ከእርሱ ቀጥሎ ቶላ 1249-1226 ዓክልበ. ፈራጅ ሆነ ይለናል፤ ከዚያም ኢያዕር 1226-1204 ዓክልበ. ፈራጅ ሆነ።  የኢያዕር ልጆቹ 30 ከተሞች በገለዓድ አካባቢ አስተዳደሩ ይለናል። በ1215 ዓክልበ. ግድም ግን የራምሴስ ተከታይ መርነፕታህ እንደ ዘገበ የእስራኤልን ስም በንቀት ሥፍራ ጠቅሶ «የእስራኤል ዘር ጠፍቷል» በማለት የመርነፕታህ ጽላት አስቀረጸ። 

የመርነፕታህ ተከታይ 2 ሴቲ 1205 ዓክልበ. ግድም የመዳብ ማዕድንና የአረመኔ ጣኦት መቅደስ በኤዶምያስ አበጀ።    ከ1204-1186 ዓክልበ. እስራኤላውያን በገለዓድ ሆነው ለአሞንና ለፍልስጥኤም ሰዎች ተገዙ።  የአሞን ንጉሥ ስም አይሰጠም፤ በዚህ ዘመን በግብጽ ላይ ንግሥት ትዎስረት እያለች በአንዱ ፓፒሩስ ሰነድ ዘንድ «የርሱ» ወይም «ሱ» የተባለ አለቃ መላውን ከነዓን ይገዛ ነበር።  በዚህም ጊዜ «የባሕር ሕዝቦች» የተባሉት ወገኖች አናቶሊያን እስከ ስሜን ሶርያ ድረስ ወርረው የኬጥያውያን መንግሥት እንዳጠፉ ይታስባል፣ በሦስት ራምሴስ ዘመን በግብጽ ላይ ጥቃት አደረጉ፣ በከነዓንና በፍልስጥኤም ደግሞ እንደ ሰፈሩ ይታስባል።   

በ1186 ዓክልበ. ዮፍታሔ የአሞንን ንጉሥ አሸነፈ፣ ነገደ ኤፍሬምንም አሸነፈ፣ በገለዓድ (እስራኤል) እስከ 1180 ዓክልበ. ፈረደ፣ ከዚያም ኢብጻን 1180-1173 ዓክልበ.፣ ኤሎም 1173-1163 ዓክልበ.፣ ዓብዶን 1163-1155 ዓክልበ በዕብራውያን ላይ ፈረዱ።  ግብጽም እስከ 1155 ዓክልበ ድረስ ያሕል ኢዮጴን በፍልስጥኤም ያስተዳድር ነበር።  በ1155 ዓክልበ. ግን ፍልስጥኤም በርቶ እስራኤልንም ይገዛ ጀመር።

በ1135 ዓክልበ. በፍልስጥኤማውያን ሥር እየቆዩ ሶምሶን የእስራኤላውያን አለቃ ሆነ። ከ1122 ዓክልበ. ጀምሮ የአሦር መንግሥት በአራም ላይ በሶርያም እስከ ሊባኖስ ድረስ ይዘምቱ ጀመር።  በ1115 ዓክልበ. ኤሊ የእስራኤል ፈራጅ ሆነ። በ1076 ዓክልበ. ፍልስጥኤማውያን ታቦትን ማረኩ፤ በሚከተለው አመት ግን ሳሙኤል አስመለሰው። በ1055 ዓክልበ. ሳሙኤል ሳኦል የእስራኤል ንጉሥ እንዲሆን አደረገ።




#Article 237: ኣበራ ሞላ (29204 words)


ዶ/ር አበራ ሞላ (መጋቢት ፳፬ ቀን ፲፱፻፵ ዓ.ም.) ሸዋ ጠቅላይ ግዛት፣ መናገሻ ኣውራጃ፣ ሰንዳፋ ከተማ የተወለዱ ኮምፕዩተሮችና የእጅ ስልኮች በግዕዝ ፊደል እንዲጽፉ የፈጠሩ  ኢትዮጵያዊ ሳይንቲስት ናቸው። 

ዶክተር ኣበራ ሞላ የታወቁባቸው ዋናዎቹ  ጉዳዮች የሚከተሉት ናቸው። የመድንን ማነስ በማስወገድ ከዓለም የእንስሳት ሓኪሞች ኣንዱ ታዋቂ ምሁር፣ የግዕዝ ፊደልንና ሥነ ጽሑፍ በኮምፕዩተርና የእጅ ስልክ ውስጥ በኣለውም መጠቀም እንዲቻል የኣደረጉ ሰባት የዩናይትድ እስቴትስና ኢትዮጵያ ፓተንቶች ብቻቸውን የኣሏቸው የግኝት ሊቅና የኣክሱም ሓውልት ከሮም ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ ጣልያንን በማስገደድ ወሳኙን እርምጃ የወሰዱ ኣርበኛ ናቸው።                        ዶክተሩ የግዕዝ ኣልቦ ኣኃዝ ቀለሞችና የግዕዝ ኣሥር ቤት ኣኃዛዊ ቍጥሮች ፈጣሪም ናቸው።    የግዕዝ ፊደል ሳይቆራረጥ፣ ሳይቀነስና ሳይበላለጥ ዩኒኮድ እንዲገባ የሰጡና ለመብቱ የተሟገቱለት ኣሸናፊ ናቸው። ፣  ዶ/ር ኣበራ ሞላ ከታዋቂ የዓለም ሳይንቲስቶች ኣንዱ ናቸው።   ኢትዮጵያውያን ኢንተርኔት ላይ በዓማርኛ በነፃ ፒሲና ማክ ኮምፕዩተሮች ውስጥ እንዲከትቡ በድረገጽ ለግሰዋል። 

ዶ/ር አበራ በኮምፕዩተር ግዕዝ ፊደልን መጠቀም እንዲቻል ያደረጉ ምሁር ናቸው። ይሀንንም ያደረጉት የዓማርኛውን የጽሕፈት መሣሪያ (ታይፕራይተር) ለሚያውቁት ቀላል እንዲሆን በ“a”፣ “b”፣ “c”፣ “d” ምትክ “ሀ”፣ “ጠ”፣ “ሸ”፣ “ዘ” እና እንግሊዝኛ ለሚያውቁ በ“A”፣ “B”፣ “C”፣ “D” ምትክ “አ”፣ “በ”፣ “ቸ”፣ “ደ” ቀለሞችን በመመደብ ዓይነት ሠላሳ ሰባቱን የግዕዝ ቤት ኆኄያት ለ፴፯ የኮምፕዩተር መርገጫዎች ስሞችም በማድረግ ነበር። ስምንቱን የፊደል ቤቶች ወይም እንዚራን ስምንት ፎንቶች ላይ በተኗቸው። በእዚህ ዘዴ በእጅ ጽሑፍና ማተሚያ ቤቶች ብቻ ይታተሙ የነበሩት የግዕዝ (Ethiopic) ፊደላት ለመጀመሪያ ጊዜ በኮምፕዩተር ተከተቡ። እ.ኤ.ኣ. በ1982 ከባለቤታቸው ወንድሞች ኣንዱ የሆነው ግሩም ከተማ ድህረ-ምረቃ ከሚማርበት ዴንቨር ዩኒቨርሲቲ መጥቶ ፊደል መሥሪያ ስለተለቀቀ ከኣንድ ዓረብ ጓደኛዬ ጋር ፊደሉን ለመሥራት ስንታገል ዋልን ብሎ ለዶ/ር ኣበራ ቢነግር ለዓማርኛ ፊደል ያላቸውን የልጅነት ፍቅር ቀስቅሶባቸው ፊደል መሥራት ከቻልክ ለምን የዓማርኛውን ኣትሞክርም ኣሉት። ሃያ ሰባት 27 የዓረብ ቀለሞችን በሚያስሠራው መሥራትን በመቶዎች የሚቆጠሩትን ፊደሎቻችንን መሥራት ኣንድ ኣይደለም ከተባባሉ በኋላ ወደፊት በዓማርኛ የሚሠራ ኮምፕዩተር እስኪሠራ ሺዎች ለእንግሊዝኛ የተሠሩን ፕሮግራሞችን ኢትዮጵያውያን  እንድንጠቀምባቸው ቃላት ማተሚያዎችን በኣማራጭነት ማቅረብ እንዲቻል ዶክተሩ ኣብሻ የሚባለውን ኩባንያ ኣቋቋሙ። ፊደል መሥራት በመጀመር እ.ኤ.ኣ. ፍላጎታቸውን ኣሟሉ። መጀመሪያ መሥራት የሚቻለውም የኣማርኛ ታይፕራይተር ዓይነቱን ቅጥልጥል ፊደል እንደኣማርኛው ታይፕራይተር በኣንድ የላቲን 
ፊደል ምትክ መተካት ስለነበረ ያንን ስለኣልፈለጉ እንጂ ቅጥልጥሉንም ከማንም በፊትም ሊሠሩበት ይችሉ ነበር። ተሠርቶበታልም። እየኣንድኣንዱ ቀለም ኣንድ-ወጥ የሆነውን የማተሚያ ቤቶች ዓይነት ትክክለኛ የግዕዝ ፊደላችንን ለመጀመሪያ ጊዜ በማቅረብና 
እየኣንድኣንዱም በሁለት መርገጫዎች እንዲከተብ በመፍጠር ግዕዝ ከማተሚያ ቤቶች ወደ ኮምፕዩተር እንዲገባ ኣደረጉ።  ሞዴት (ModEth) በመባል የታወቀውን የቃላት ማተሚያ የማይክሮሶፍትን ዶስ በመጠቀም በ፲፱፻፹ ዓ.ም. ኣሜሪካ ውስጥ ለገበያ ኣቀረቡ። ጊዜውም ኮምፕዩተሮችና ማተሚያዎች በቂ ኃይል ማግኘት የጀመሩበት ነበር። ግዕዝ በኮምፕዩተር እንዲከተብ የፈጠሩበትን ዘዴ በዩናይትድ እስቴትስ ፓተንት መጠበቅ እንዲችሉ ቢያመለክቱም በእዚያን ጊዜ ኢትዮጵያ የፓተንት ሕግ ስለኣልነበራት የሳይንስና ቴክኖሎጂ መረጃ ማዕከል (ኢትዮጵያ) ሕጉ ሲወጣ ጉዳዩ ይታያል በማለት ስለወሰነ  ፓተንት ኣልወጣለትም ነበር።

ግዕዝ ድምጻዊ ፊደል ስለሆነ እየኣንድኣንዱን “ሀሁሂ” ቀለም በ“ABC” ምትክ  እየደረደሩ ማተም ከ፲፱፻ ዓ.ም. ገደማ ጀምሮ ኢትዮጵያ ውስጥ የኣሉ ማተሚያ ቤቶች ሊጠቀሙበት ችለዋል።   በቀለሞቹ ብዛት የተነሳ ግን የእንግሊዝኛውን የጽሕፈት መሣሪያ ለዓማርኛ እንኳን መጠቀም ኣልተቻለም። ከዳግማዊ ምኒልክ ጀምሮ  ብዙ ኢትዮጵያውያን ሊቆች፣ ሚኒስትሮችና ደራስያን የእንግሊዝኛውን የታይፕ መጻፊያ ለዓማርኛ መክተቢያ እንዲያገለግል ወደ ሰማንያ ዓመታት ግድም ሲመራመሩ ቆይተው ባይሳካላቸውም  ዶ/ር ኣበራ ጥረቶቻቸውን በኮምፕዩተር ኣሳክተዋል። ስለ ዓማርኛ የጽሕፈት መኪና ምርምሩም የዋቢው ዝርዝር ውስጥ ከተካተቱት ኣባ ተክለ ማርያም ሰምሃራይ፣ ክቡር ዶ/ር ሃዲስ ኣለማየሁ፣ ኣቶ ዓለሙ ኃብተ ሚካኤል፣ ኢንጂነር ኣያና ብሩ፣ ዶ/ር ዓለመ ወርቅ፣ ኣለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፣ ክቡር ኣቶ ኣበበ ኣረጋይ፣ ክቡር ራስ ዕምሩ ኃይለ ሥላሴ፣ ዶ/ር ሉባክ፣ ኣቶ ዘውዴ ገብረ መድኅን፣ ብላታ መርስዔ ሃዘን ወልደ ቂርቆስ፣ ፀሓፊ ትዕዛዝ ወልደ ጊዮርጊስ ወልደ ዮሐንስ፣ ክቡር ኣቶ ሚሊዮን ነቅንቅ፣ ኣቶ ስይፉ ፈለቀ፣ ክቡር ዶ/ር ከበደ ሚካኤል፣ ኣቶ ሳሙኤል ተረፈ፣ ሌላ እነ ኮሎኔል ታምራት ይገዙ፣ መንግስቱ ለማ፣ ኣቶ ብርሃኑ ድንቄ፣ ብላታ ዘውዴ በላይነህ፣ የኔታ ኣስረስ የኔሰው፣ ተክለማርያም ኃይሌ፣ ሼክ በክሪ ሳጳሎ እና ዶ/ር ፍቅሬ ዮሴፍንም  ያጠቃልላል።  ይህ ድካማቸው በመጨረሻ ሊሳካ የቻለው ግን ዶክተሩ ምንም ቀለም ሳይቀንሱ ወይም መልካቸውን ሳይቀይሩ የጥንቱንና ትክክለኛ የግዕዝ ቀለሞች  በኮምፕዩተር እንዲቀርቡ ስለኣደረጉ ነው።   የእነዚህ ምሁራን በታይፕ መሣሪያ ሙከራዎች የመጠቀም ዓላማዎች ባይሳኩላቸውም ዶክተሩ በእዚያው የፊደል ገበታ ምኞታቸውን ኣሳክተውላቸዋል።   በተጨማሪም የቢለን፣ ጉራጌ እና ሳሆ ምሁራን የቋንቋ ፊደሎቻቸውን እንዲጨምሩላቸው ናሙና ጽሑፎችን ልከውላቸዋል። ከእዚሁ ጋር በማያያዝ እየኣንድኣንዱ ቀለም በሁለት መርገጫዎች እንዲከተብ ኣዲስ የኣከታተብ ዘዴ ፈጥረው ኣዳዲስ የፊደል ገበታዎችን ኣቅርበዋል። ለእየኣንድኣንዱ የግዕዝ ቤት ቀለምም እንደ እንግሊዝኛው ቍልፎች የእየእራሱ ቍልፍና የቍልፍ ስም መድበዋል። በእነዚህ የተነሳ የግዕዝን ፊደል የእንግሊዝኛው ወይም የኣማርኛ የታይፕ መጻፊያ መጻፍ ስለኣልቻለና ሳይጽፈው ኮምፕዩተር ለመጀመሪያ ጊዜ ደርሶለታል።   ዶ/ር ኣበራ ኮምፕዩተራይዝ የኣደረጉት የግዕዝ ፊደል ኢትዮጵያውያን ለብዙ ሺህ ዓመታት በእጃቸው ሲጽፉትና  ከ፲፱፻፬ ዓ.ም. ገደማ ጀምሮ በማተሚያ መሣሪያዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ሲጠቀሙብት የነበረውን ፊደል ነው።        ግዕዝ በማተሚያ መሣሪያዎች ከኢትዮጵያ ውጪም ታትሟል። የግዕዝ ፊደል በብራናና የመሳሰሉት ላይ  ሲጻፍ ቆይቶ በጉተንበርግ የፊደል መልቀሚያ ማተሚያ መሣሪያ ፈጠራ ከ፲፭፻፮ ዓ.ም. ጀምሮ በማተሚያ መሣሪያ ሲጠቀም ቆይቶ ከ፲፱፻፹ ጀምሮ በዶክተሩ ግኝት በኮምፕዩተርና በኋላም በእጅ ስልክ መጠቀም ስለተቻለ ሕዝቡ በዓማርኛና ሌሎች ቋንቋዎች የእራሱ ኣታሚ ሆኗል። 

የግዕዝን ቀለም (Glyph) በኮምፕዩተር በቀላሉና በቀልጣፋ ዘዴ ማቅረብ ስለቻሉ ሕዝቡ ከማተሚያ ቤቶች በተሻለ ሁኔታ በፊደሉ መሥራት ችሏል። በእዚህም የተነሳ ሕዝቡ መጽሓፍትንና የመሳሰሉትን ለማሳተም በየማተሚያ ቤቶች ወረፋ ከመጠበቅና ከመንግሥት እገዳ ተርፎ የእራሱ ኣታሚ ሆኗል።   ዘዴውም በዓማርኛ ሳይወሰን ለሁሉም የግዕዝ ቀለሞች መክተቢያና ማተሚያ ከሌሎች የዓለም ፊደላት እኩልና ጎን በሚገባ ሥራ ላይ እየዋለ ነው።  ይህ የዓማርኛ ውክፔዲያ ገጽ እንደ ሌሎች ትክክለኛ የዓለም ባለ ፊደል ቋንቋዎች ገጾች የቀረበውም በእዚሁ በግዕዝ የዩኒኮድ መደብ ቀለሞች ነው።  ሌላው የትግርኛ ውክፔዲያ ገጽ ነው። የዶ/ር ኣበራ ግኝቶች  (Ethiopic Character Entry - July 16, 2009 ሕትመት) በግዕዝ ሳይወሰኑ ለኣንድኣንድ የዓለም ፊደሎች ኣዳዲስ ኣጠቃቀሞችና ግኝቶች ስለጠቀመ ስምንት የዩናይትድ እስቴትስ ፓተንቶች ውስጥና ሦስት የፓተንት ማመልከቻዎች ውስጥ (Citing Patents) ተጠቅሷል።     ቊጥሮቻቸውም ፣ 8645825፣ 8700653፣ 8706750፣ 8762356፣ 8812733፣ 9715111፣ 9723061፣ 9733724፣ 20110173558፣ 20160042059 እና 2963525A1 ናቸው።  እነዚህ ኢትዮጵያን የሚያኮሩ ሥራዎችም ናቸው።

ዶ/ር ኣበራ ሞላ ዩናይትድ እስቴትስ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ  በኩል ስለ ኢትዮጵያ ፊደል ግኝታቸው ጉዳይ ፓተንት ማመልከቻ እ.ኤ.ኣ. ፌብሩዋሪ 15 1990 ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን የኣቀረቡት በኮምፕዩተር  የተጻፈ የዓማርኛ ደብዳቤ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያው ባይሆንም ታሪካዊ ነበር። ኮሚሽነር ኣበበ ሙሉነህ በዶ/ር ኣበራ በኮምፕዩተር ለተጻፈው ደብዳቤ መልሱን የጻፉት በአማርኛ የጽሕፈት መሣሪያ በተጻፈ ደብዳቤ ነበር።  ዶክተሩ ታህሳስ ፲፩ ቀን ፲፱፻፹፩ ዓ.ም. (December 19, 1988 ለኮሚሽነሩ የጻፉት ደብዳቤም ኣለ። በኣሁኑ ጊዜ በኮምፕዩተር፣  የእጅ ስልኮችና  በመሳሰሉት በግዕዝ ፊደል እየቀረቡ የኣሉት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ስለሆኑ የዶክተሩ ሕልምና ምኞት ከተሳኩ ቆይቷል።     መጋቢት ፳፱ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. የዩናይትድ እስቴትስ መንግሥት ቊጥሩ 9,000,957 የሆነ የመጀመሪያውን የግዕዝ ፓተንት ወይም የግኝቱ ባለቤትነት መብት ማመልከቻውን ከኣስገቡበት ከሰባት ዓመታት በኋላ ለዶ/ር ኣበራ ሞላ ሰጥቷል።  ዕውቅናው እንዲታወቅ U.S. Patent No. 9,000,957 የእሚል ማሳወቂያ ግኝቱን ከሚጠቀሙት ዘዴዎች ጋር መቅረብ እንደእሚገባው ሕጉ ይደነግጋል። የፓተንቱም መገኘት የግዕዝ ፊደል በትክክለኛ ሳይንስና ቴክኖሎጂ እየተደገፈ የማደጉ ምስክርነት ነው።   ይኸው የኢትዮጵያም ፓተንት ለዶክተሩ በሦስት ወራት ውስጥ እንደሚሰጥ የኢትዮጵያ ኣእምሯዊ ንብረት ጽሕፈት ቤት ጥቅምት ፳፱ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም. ደብዳቤ ጽፏል። በቅርቡም ቍጥሩ 9,733,724  የሆነ ሁለተኛው ፓተንት ግዕዝን በእጅ ስልክ መጠቀም እንዲቻል በመፍጠራቸው በዩናይትድ እስቴትስ መንግሥት ለዶ/ር ኣበራ ሞላ ተሰጥቷል። የእነዚህ ፓተንቶች የኢትዮጵያዊ ሳይንቲስት መሆኑ ጥቅሞች ለብዙዎቹ የኣልገባቸው ይመስላል። ዶ/ር ኣበራ ሞላ የፓተንትን ጥቅም ቀደም ብለው በኣሏቸው ፓተንቶች ምክንያት በማወቃቸው ግዕዝን ዲጂታይዝ በማድረግ ሌሎች ኢትዮጵያውያንን በቴክኖሎጂው እንዳይቀደሙ በማድረግ በፊደሉና እንደ ዓማርኛ በኣሉ ቋንቋዎቻቸው ላይ መብታቸው እንዳይወሰድ የኣደረጉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ባለውለታ ሳይንቲስት ናቸው። እስከ ፳፻፲፩ ዓ.ም. ለዶ/ር ኣበራ ሞላ ብቻቸውን የተሰጧቸው የግዕዝ ፓተንቶች ሰባት ደርሰዋል። ይኸንንም USPTO Patent Search ሄዶ Aberra Molla በመፈለግ ማጣራት በሳይንስ ዓለም የተለመደ ነው። ግዕዝን በኮምፕዩተር መክተብ ኣስቸጋሪ በመሆኑ በብቸኛው ምርምራቸው ገፍተውበት ተሳክቶላቸዋል።

ከልጃቸው ብሩክ ጋር የመጀመሪያውን የግዕዝ የእስክሪንና የማተሚያ ቀለሞች ለመሥራት ኣንድ ዓመት ግድም ነበር የወሰደው።  የፊደሉም ችሎታ በማደግ መጀመሪያ ፖስትእስክሪፕት ከእዚያም በ፲፱፻፹፩ ዓ.ም. ትሩታይፕ  በኋላም ተንቀሳቃሽ (Embedable) ሆኗል። ግዕዝ ወደ ኮምፕዩተር ሲገባ የስምንት እንግሊዝኛ ሥፍራዎችን በማስለቀቅ ዓይነት ኣንዱኑ ቦታ በየተራ በመጋራት ነበር። በዩኒኮድ መፈጠር የተነሳ ዶ/ር  ኣበራ ኮምፕዩተራይዝ የኣደረጉት እየኣንድኣንዱ ቀለም የእራሱን ስፍራ ኣግኝቷል። Aberra Molla ከዓለም ፊደል ሠሪዎች ኣንዱ ናቸው።  ብዙዎቹ የግዕዝ ቀለሞች በዓለም የፊደላት መደብ ዕውቅና ከኣገኙበት ከ፲፱፻፹፫ ዓ.ም.  ግድም ወዲህ ግን የዕውቀት ክምችት እንዲስፋፋ በቀለሞቹ እንደመጠቀም ዛሬም ኋላቀር በሆነው የኣማርኛ የታይፕ መጻፊያው ዓይነት ቅጥልጥል የኣማርኛ ፊደላት እየጻፉ ኢትዮጵያንና እራሳቸውን ወደኋላ እየጎተቱ ያሉትን እየተቃወሙ ነው።  ትክክለኛዎቹና ሁሉም የግዕዝ ቀለሞች የዩኒኮድ መደብ ውስጥ እንዲገቡ ዶክተሩ ትልቅ ትግልና ኣስተዋጽዖም ኣድርገዋል። ለምሳሌ ያህል በመጀመሪያ ዙር ዶክተሩ ኮምፕዩተራይዝ የኣደረጉት እንጂ የታይፕራይተሩ ፊደል ግዕዝ እንዳልሆነ ተገልጿል።  ይኸን  ግዕዝ የኣልሆነ ቊርጥራጭ የኣማርኛ ታይፕራተር ዓይነት ፊደል የግዕዝ ፊደል ስለኣልሆነ በሁለተኛ ዙር ተቃውመው ኣስጥለዋል።   የዶክተሩ ሦስተኛ ዙር ተቃውሞ  የዓማርኛውን የማተሚያ ቤት ፊደላት ለዩኒኮድ  እ.ኤ.ኣ. በ1992 የቀነጠሱትን  እና የኣናሳ ተጠቃሚዎች ፊደላት በቍርጥራጭ ፊደላት እንዲተኩ  እ.ኤ.ኣ. በ1993 የፈለጉትንና የኣማርኛ ፊደላት ቅነሳ ውስጥ የገቡትንም ያጠቃላል።   ዶክተሩ ዲጂታይዝ የኣደረጉት የግዕዝ ፊደል የኢትዮጵያ ማተሚያ ቤቶች ሲጠቀሙባቸው በነበሩት ፊደላት ሲታተሙ ስለነበሩና ስለሆኑ ዛሬ ወደ ፒ.ዲ.ኤፍ (P.D.F.) የተቀየሩትን ጭምር ያለ ችግር ማንበብ ተችሏል።

ፊደሉንም ለማሟላትና ከሌሎች ፊደላት እኩል እንዲራመዱ በየጊዜው ጽፈዋል። ለምሳሌ ያህል እነ “ሀ”፣ “ሐ”፣ “ኀ”፣ “አ”፣ እና “ዐ” የተሳሳቱ ድምፆች ተሰጣቸው እንጂ በዶ/ር ኣበራ ገለጻ የእየራዕቦቻቸው ሞክሼዎች ስለኣልሆኑ ለማጥፋት ማዘጋጀት ቀርቶ ድምፆቻቸውን ተረክበው መብታቸው መከበር ኣለበት ነው። ዕውቀቱም ከዩኒቨርሲቲ ወደ ሕዝቡ መድረስ ኣለበት።  ይህ ትግርኛውንም ይመለከታል። ዓማርኛ፣ ቤንችና ጉሙዝ የቋንቋ ዋና ክፍሎች የ“ጨ” ቀለሞች፣ እንዚራንና ዘመዶች ቀለበቶች ሦስት ሳይሆኑ ሁለት ናቸው። የ“ሀ” ትክክለኛ ድምጽ ወደ “ኸ” የቀረበ ቢሆንም “ኸ”ም የዓማርኛ ሞክሼ የሚባለው ዓይነት ቀለም ስለኣልሆነ ነው ግዕዝ ኮምፕዩተራይዝ ሲደረግ የምልክት መርገጫዎች ላይ የመርገጫ ስም የተሰጠው። የ“አ” ድምጽ  በስሕተት “ኧረ” የሚለው ቃል ምሳሌ ውስጥ ስንጠቀምበት የነበረ ድምጽ ስለሆነ ለ“ኧ” ስምንተኛው የ“አ” ቤት ፊደል ድምፁን ዶክተሩ መልሰው ኣስረክበውታል። [“ኧረ”] መከተብ ያለበት በ“አረ” ነው። ምክንያቱም የስምንተኛው ድምጽ ቀለም የሚሠ'ራው ግዕዙ ወይም ራብዑ ላይ መስመር በመጨመር ስለሆነና የ“አ” ቤት ስምንተኛ ቀለም የማይኖርበት ምክንያት ስለሌለ ነው። ይህ የዓይኑ “ዐ” ባለመስመር “ዓ”ንም ሊመለከት ይችላል። “ኧ” የስምንተኛው የ“አ” ቤት ቀለም ስለሆነ ስምንተኛውን የ“አ” ቤት ድምጽ (ወደ “እዋ” የቀረበውን) ለ“ኧ” ፊደል መስጠቱ ተገቢ ይመስላል።  የ“የ”ም ስምንተኛ ድምጽ ቀለም ኣለ። የ“ሀ”ም አንዲሁ። ግዕዝ ድምፃዊ ፊደል (Syllabic) ስለሆነ “ሀ” እና “ሃ” ወይም “አ” እና “ኣ” ድምጽ ስለማይጋሩ ነው ዶክተሩ ስማቸውን “ኣበራ” እንጂ “አበራ” በማለት የማይጽፉት።   ከምክንያቶቹ ኣንዱ የግዕዝ ቤቶቹ ቅርሶች ሲጠሩ እንደራብዖቹ ኣፍ በሰፊው ስለማያስከፍቱ ነው። 

ለግዕዝ የሚያስፈልጉትን በመጨማመር ከፈጠሯቸው የግዕዝ ምልክቶች መካከል “መብት”፣ “ንግድ”፣ “ተመዝግቧል”፣ “ብር”፣ “ሣንቲም”፣ “ማጥበቂያ”፣ “ማላልያ” እና “ኣልቦ” ኣኃዝ ይገኙበታል። የማጥበቂያ ምልክትን ዓማርኛ ለጥቂት ምዕት ዓመታት የተጠቀመ ስለሆነ ዶክተሩ የኣቀረቡት ከኮምፕዩተሩ ቴክኖሎጂ ጋር እንዲሄድ ኣዲስ ቅርጽና ስፍራ በመስጠት ነው። ዕውቅናም እንዲያገኙ ደራሲዎች እንዲጠቀሙባቸው ለዓመታት ከማቅረብ ሌላ ፓተንቶቻቸው ውስጥ ጽፈዋቸዋል።  የኮምፕዩተር 42 እንግሊዝኛ ቁጥሮችና ምልክቶች ከግዕዙ ጋር ያቀረቡት ዶክተሩ ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ሲያደርጉ ለግዕዝ ሥራ እንዲያገለግሉ ወስነው ከግዕዙ ቀለሞች ጋር በተመጣጠነ መልክ መሥራት ስለጀመሩ ኮምፕዩተር ገበታ ላይ ያሉት ኣጠቃቀም ለግዕዝም እንዲያገለግል ነው። ለምሳሌ ያህል “+”፣ “-”፣ “*” እና “/” የመደመር፣ መቀነስ፣ ማባዛትና ማካፈል የግዕዝ የሢሳብ ምልክቶችና ማስሊያዎችም ናቸው። በእጅ ጽሑፍና ማተሚያ ቤቶች ብቻ ይቀርብ የነበረው የግዕዝ ፊደል  ኮምፕዩተራይዝድ ስለሆነ ኣጠቃቀሙ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ፲፱፻፹ ዓ.ም. ገደማ ለሕዝብ ቀርቧል። ከእዚያም ወዲህ ፊደሉ የዩኒኮድ የዓለም ፊደላት መደብ ውስጥ ስለገባ እየኣንድኣንዱ ቀለም የእራሱ ስፍራና ቍጥር (ኮድ) ኣለው።  በእዚህም የተነሳ የግዕዝ ፊደል እንደሌሎች የዓለም ፊደላት የዩኒኮድ መደብ ውስጥ ገብቷል። 

ግዕዝ በዩኒኮድ ዕውቅና ስለ ኣገኘና ወደ ፲፫ የተለያዩ የቋንቋ ቀለሞች ስለኣሉት የሁሉም የግዕዝ ፊደል ተጠቃሚ ብሔሮች መብቶች በእኩልነት መጠ'በቅ እንደኣለባቸው ዶክተሩ ያምናሉ።  ስለዚህ ሁሉንም የግዕዝ ቀለሞች የማያስተናግድ ወይንም ለማስተናገድ ችሎታ የሌለው ዘዴ መቅረብ ስለሌለበት ተጠያቂው ኣቅራቢው ብቻ ሳይሆን ተጠቃሚው ምሁርም ነው። በግዕዝ ቀለሞች ብዛት የተነሳ በግዕዝ መሥራት ቢያስቸግርም ከቴክኖሎጂው ጋር መጓዝ ስለቀጠለ ለእንግሊዝኛው የተሠሩትን ለግዕዝ መጠቀም እንዲቻልና ግዕዝ የሚፈልገውንም ለመሥራት መትጋት ይጠበቅብናል። የተሳሳቱ ነገሮችን ማስተካከልና በትክክል መጠቀም ጠቃሚ ናቸው። ዶክተሩ የተጠቀሙበት የሁለተኛው ፊደል መነሻ ተወዳጁና ለረዥም ዘመናት ጥቅም ላይ ሲውል የነበረው የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ኣንደኛው የሞኖታይፕ የፊደል መልቀሚያ መሥሪያ ፊደልና የተስፋ ገብረሥላሴ ማተሚያ ቤት ፲፱፻፲፯ ዓ.ም. ቁምፊ (Typeface) ናቸው። የቀለማቱም መልኮች ከዩኒኮዱ ጋር ኣንድ ዓይነትና መደበኛ የኢትዮጵያ  ፊደላት ናቸው።  ውብ ቀለሞቻችንን በወጉና በማዕረጉ መጠቀም ተችሏል። ዶክተሩ ይኸን በመደበኛነት ከ፲፱፻፹፩ ዓ.ም. ጀምሮ እየተጠቀሙበት ነው። በማያምር፣ የተሳሳተና የከሳ ፊደል የተጻፈ ጽሑፍ ማንበብ ኣያጓጓም። 

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እነ ማይክሮሶፍት (Microsoft)፣ ጉግል (Google)ና ኣፕል (Apple) የተለያዩ የግዕዝ ፊደላት ማቅረብ ጀምረዋል። ምንም እንኳን የተለያዩ ቁምፊዎች መኖር ተፈላጊ ቢሆኑም ኣስቀያሚውንና የተሳሳቱትን በዝምታ ማሳለፍ ሕዝቡ ተስማምቶበታል ማለት ነው። በኣሁኑ ጊዜ ብዙ ደራስያን መጻሕፍትን በተሳሳቱ ፊደላት እያሳተሙ ስሕተቶችን እያስፋፉ ስለሆነ ሊነገራቸው ይገባል።  ወደፊት በትክክለኛ የግዕዝ ፊደሎቻችን የተከተቡትን ጥንታዊ ቀለሞቻችንን ዶክተሩ ኮምፕዩተራይዝ ወደኣደረጉት ትክክለኛ የዘመናዊው ማተሚያ ቤቶች ቀለሞች መቀየር ቢቻልም ዛሬ በኣለማወቅ በተሳሳቱ ቀለሞች ኣዳዲስ ስሕተቶችን ማስተዋወቅ ኣስፈላጊ ኣይደለም። 

የግዕዝ ፊደል ውስጥ ለሌሉ ድምጾች ኣዳዲስ ቀለሞች መፍጠር ሊያስፈልጉ ይችላሉ። ይህ ፊደላችን ለሌሎች ቋንቋዎችም እንዲጠቅሙ ያስችላል። 
 
በየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርቶች ዘንድ ግዕዝ የኣዳም እና የሔዋን ቋንቋ ነበር፤ ፊደሉን የፈጠረው ከማየ ኣይኅ ኣስቀድሞ የሴት ልጅ ሄኖስ ነበረ፤   በሌላ በኩልም ኢትዮጵያዊው የግዕዝ ፊደል የዓለም ፊደላት ምንጭ ነው ይባላል።      የኢትዮጵያ ነገሥታት ዝርዝሮችና የግዛት ዓመታት እዚህ ኣሉ።   ሌሎችም መረጃዎች ኣሉ።    በግዕዝ ቋንቋ ብዙ እልፍ ድርሳናትና ምስጢራት ተከትበዋል።  የግዕዙ ፊደል እድሜ ከላቲኑ የበለጠ ነው።   (ጥንታዊቷ ግብጽ ከ5100 ዓመታት በፊት በኢትዮጵያውያን የተቈረቈረች ናት ይባላል።) የግብፆችን ጽሑፍ ከኢትዮጵያ የተወሰደ መኾኑንና የሮማና የሌሎች ፈላስፎችም የተጠቀሙባቸው መጻሕፍት ከግብጽ መጽሓፎች የተወሰዱ እንደኾኑ ማረጋገጥ ተችሏል። በጽሑፍ ሰፍረው ከሚገኙ አንዳንድ መረጃዎችም በመመሥረት የጽሑፍ ፊደል በኢትዮጵያውያን የተጀመረ መኾኑን መገመት ይቻላል። የሥነ ፈለክ (Astronomy) ጥናትን የጀመሩት ኢትዮጵያውያን ስለመኾናቸው ማስረጃዎች ይናገራሉ። ሌሎች ሃገራት የሓውልትንና የግንባታ ሥነ ጥበብን የተማሩት በጥንት ኢትዮጵያውያን ነው።   ኢትዮጵያ የሥልጣኔ ምንጭ ነች የሚሉም ኣሉ። 
የላቲን ኤቢሲዲ ካፒታል ፊደላት የግዕዙን ፩፪፫፬ የመሰሉት እኛ ከግሪኮቹ ወስደን ኣይደለም።  በኢትዮጵያ ታሪክ ጽሑፍ በግሃ ድንጋይ ተጠቅሞ በድጋይ ላይ ከመጻፍ ቅጠልን ቀጥቅጦ በመጭመቅ በብራና ላይ ወደ መጻፍ ሽግግር የተደረገው በንጉሥ ሰብታህ (2545-2515 ዓ.ዓ.?) ዘመነ መንግሥት መሆኑ ተጽፏል።  ይህ ከ5000 ዓመታት ግድም በፊት መሆኑ ነው። ኢትዮጵያ ከዛሬ ሰባት ሺህ አመታት በፊት በዳዕማት የፅሁፍ ትምህርት መስጠት መጀመሯን ለሚያውቅ ሰው በወቅቱ ኣገራችን ደርሳበት የነበረውን የሥልጣኔ ደረጃ መገመት ኣያዳግተውም፡፡ 

ምንም እንኳን ከ“A” እስከ “Z” የኣሉት የኮምፕዩተሩ መርገጫዎች (Keys) ለእንግሊዝኛው ፊደላት ስምና መርገጫ እንዲሆኑ ቢሠሩም  ፴፯ቱን መርገጫዎች ለ፴፯ቱ የግዕዝ ቤት ቀለሞች ማለትም ለ“ሀ”፣ “ለ”፣ “ሐ”፣ “መ”፣ “ሠ”፣ “ረ”፣ “ሰ”፣ “ሸ”፣ “ቀ”፣ “ቐ”፣ “በ”፣ “ቨ”፣ “ተ”፣ “ቸ”፣ “ኀ”፣ “ነ”፣ “ኘ”፣ “አ”፣ “ከ’፣ “ኸ”፣ “ወ”፣ “ዐ”፣ “ዘ”፣ “ዠ”፣ “የ”፣ “ደ”፣ “ዸ”፣ “ጀ”፣ “ገ”፣ “ጘ”፣ “ጠ”፣ “ጨ”፣ “ጰ”፣ “ጸ”፣ “ፀ”፣ “ፈ” እና “ፐ” ስምና ቍልፎች እንዲሆኑ ኣድርገዋል። ግዕዝ በኮምፕዩተር እንዲጠቀም ሲፈጥሩ እየኣንድኣንዱ ቀለም የሚከተበው በሁለት መርገጫዎች ነበር። ለሚፈልጉትም የቍልፍ መለጠፊያዎች ነበሩት። እየኣንድኣንዱ የግዕዝ ቀለም ስም የሚከተበው እንደ እንግሊዝኛው ዝቅ (Shift) መርገጫን በመጠቀም ነው። በኣሁኑ ጊዜ እየኣንድኣንዱን ቀለም በኣንድና ሁለት መርገጫዎች መክተብ የሚያስችል ኣብሻ (ABSHA) የሚባል ዘዴ ስለፈጠሩ ዓማርኛውን በእንግሊዝኛ ፎነቲክ እስፔሊንግ እንጽፋለን በማለትና ያም ስለኣልተሳካ እስከ ኣራት መርገጫዎች መጠቀም እንደማያስፈልግ ተደርሶበታል።  ምክንያቱም ዓማርኛው በኣራት ቢከተብም የኣናሳ ተጠቃሚዎች ቋንቋዎችን በእዚሁ እስፔሊንግ ዘዴ ለመክተብ እስከ ስምንት መርገጫዎችን መጠቀም ስለሚያስፈልግ ነው።   እንግሊዝኛ የእራሱ ችግሮች የኣሉት ፊደል ነው።  

ላቲን (Latin) “ቸ” ቀለምን የሚከትበው በ“CH” ሲሆን “ቸ” ቀለም ቢኖረው ኖሮ ትክክለኛ ኣጠቃቀም ስለሆነ ኣንድ መርገጫ ይሰ'ጠው ነበር። የላቲን ቊልፎች ለሃያ ስድስቱ ቀለሞች የተመደቡት ለእየኣንዳንዳቸው እንጂ በዋየልነትና ኮንሰናንትነት የሥራ ክፍፍል ኣይደለም። በሌላ ኣነጋገር የ“E” መርገጫ ለ“E” የእንግሊዝኛ ፊደል የተመደበው “E” ቀለም ስለሆነ እንጂ ዋየል ስለሆነ ኣይደለም። የዶክተር ኣበራ ግኝት ይኸን መሠረታዊ ኣጠቃቀም በማገናዘብ የላቲኑንና የግዕዙን ኣቀራረብ በማዋሃድ የዋየል መርገጫዎችን የፊደልነትና የዋየልነት ኣሠራር ለግዕዝ ተጠቅሞበታል።   ምክንያቱም ግዕዝ ድምፃዊ ፊደል ስለሆነ እንዚራኖቹን በዋየል መዘርዘር ሃያ ስድስቱን የላቲን ቀለሞች በዋየል ከመዘርዘር ጋር የተቀራረበ ስለሆነ ነው። በእዚሁ መሰረት 37ቱ የግዕዝ ቤቶች እንደ 26ቱ የላቲን ቤቶች የእየእራሳቸው መርገጫዎች ከተሰጣቸው በኋላ በዋየልነት እንዲያገለግሉ ለሁለተኛ ሥራ የተመደቡት የዋየል መርገጫዎችና ተጨማሪ መርገጫዎች የእንዚራን መቀየሪያዎች ሆነዋል። ግኝቱ ከእነዚህም ኣልፎ ለዋየል መርገጫዎች ሦስተኛ ኣዲስ ኣጠቃቀም ሥራ ላይ ኣውሏል። 

ለእንግሊዝኛው የኮምፕዩተር መርገጫና ኣከታተብ ዘዴ እንዲመች የግዕዝ ፊደላት ከ“A” እስከ “Z” ያሉት ፳፮ ቁልፎችን እንዲጋሩ ማድረግን ዶክተሩ ይቃወማሉ። ምክንያቱም ከ“ኤ” (“A”) እስከ “ዚ” (“Z”) የኣሉት የላቲን ቍልፎችን ፊደሉ በኣንድኣንድ መርገጫዎች በመጠቀም እንግሊዝኛውን እንዲከትብ የተሠራ እንጂ ከእዚያ በላይ ብዛት ከኣለው የግዕዝ ፊደል ኣጠቃቀም ጋር ግንኙነት ስለሌለው የግዕዙ ኣጠቃቀም ውስጥ ጣልቃ በመግባት ወሳኝ መሆን ስለማይገ'ባው ነው። ላቲን 26 ሳድሳን ሆህያቱን የሚከትበው ለእየኣንድኣንዱ ኣንድ መርገጫ በመጠቀም ሲሆን ለካፒታል (Capital) ቀለሞቹ ሁለት መርገጫዎችን ይጠቀማል። የዶክተሩን ትክክለኛ ግኝትና ኣመዳደብ እናሻሽላለን ብለው የዝቅ (Shift) መርገጫዎችን ከሳድሳኑ ጋር ግንኙነት ለሌላቸው የግዕዝ ኆኄያት (ምሳሌ፦ “ጥ” በ“ዝቅ” “ት” ) የመደቡ ግዕዙን ለእስፔሊንግ ጣጣ ለመዳረግ የሚፈልጉትንና ቀለማቱን በብዙ መርገጫዎች የሚከትቡትን ይቃወማሉ። ምክንያቱም ዶክተሩ በፈጠሩት ዘዴ ሁሉንም ቀለሞች ከኣንድ ገበታ በኣንድና ሁለት መርገጫዎች ብቻ በኮምፕዩተሮችና የእጅ ስልኮች መክተብ ስለተቻለና እየተሻሻለም ስለሆነ ነው። 

እነ “ዠ” እና “ጰ” ቀለሞች ራቅ የኣሉ መርገጫዎች ላይ የተመደቡት ብዙ ቃላትና ተጠቃሚዎች ስለሌሏቸው ነው።  ግዕዙን በ26 የላቲን ፊደላት መጻፍ መሞከር ግዕዙ በላቲን መርገጫዎች እንዲጠቀም ማስገደድ ነው። የኢትዮጵያ ሳይንቲስቶች ለግዕዝ የሚበጀውን መሥራትና መፍጠር እንጂ ሌላ ፊደል ላይ ማተኰር ኣስፈላጊ ኣይደለም። ምክንያቱም በዘዴው ዓማርኛውን እስከ ኣምስት መርገጫዎች በመጠቀም መክተብ ቢቻልም የሌሎች ቋንቋዎች ሲጨመሩ ከእዚያ በላይ መርገጫዎችን መጠቀም ስለሚያስከትሉ ነው። ዶክተሩ ለፊደላቱ መደበኛ ስፍራዎች ሲመድቡ ወደ ቀኝ ዳር የተመደቡት ብዙ ተጠቃሚዎች የሌላቸው ናቸው። እንዲህም ሆኖ በጥናት ላይ የተመረኰዘ ማሻሻል ማቅረብ ይቻላል። ለምሳሌ ያህል ኣንድ የኢትዮጵያ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤት የግዕዝ መርገጫዎች መደብ ኣቅርቧል። መደብ የሚያወጡት ግን ሥራውን የፈጠሩት ናቸው። ግዕዝን በላቲን ፊደል ገበታ መክተብ ኣስቸጋሪነት የቀረበ ጽሑፍ ኣለ።

ግዕዝ (Ge'ez) ወደ ኮምፕዩተር ሲገባ የስምንት እንግሊዝኛ ሥፍራዎችን በማስለቀቅ ዓይነት ኣንድውኑ ቦታ በየተራ በመጋራት ነበር። በዩኒኮድ (Unicode) መፈጠር የተነሳ ግዕዝ ኣሥራ ሁለተኛው ገበታ ላይ ተመድቦ እየኣንድኣንዱ ቀለም የእራሱን ስፍራ ኣግኝቷል። ጥንትም ቢሆን እየኣንድኣንዱ ቀለም የግሉ የሆነ ከ1 እስከ 5600 ቍጥር ነበረው።    በተጨማሪም ትክክለኛዎቹና ሁሉም የግዕዝ ቀለሞች ዩኒኮድ የዓለም ፊደላት መደብ እንዲገቡ በማቅረብና በመጻፍ ዶክተሩ ትልቅ ኣስተዋጽዖ ኣድርገዋል። ይህ ሊሆን የቻለውም የዓለም ፊደላትን ዩኒኮድ የተባለ የፊደላት መደብ ውስጥ ሁሉም የዓለም ቀለሞች ዕውቅና እንዲያገኙ በ፲፱፻፹፫ ዓ.ም. ለተቋቋመ ድርጅት ሁለተኛውን የግዕዝ ፊደል ከሠሩበት የኮሎራዶ ኩባንያ በኩል ዶክተሩ ኮምፕዩተራይዝ ያደረጉትንና ያቀረቡትን ብዙ መቶዎች ትክክለኛ ቀለሞች    በማስጣል  ሌሎች ዓማርኛ ፊደል የኣልሆነውንና ዓማርኛን የማያስጽፈውን ኢንጂነር ኣያና ብሩ የሠሩትን ዓይነት የዓማርኛ የጽሕፈት መኪና ቅጥልጥል ፊደል ተሳስተው ዓማርኛና ግዕዝ ነው ብለው ስለኣቀረቡ ነበር። እነዚህ  መቶ ሃያ ስምንት ስፍራዎች ይበቃሉ በማለት ለዩኒኮድ ኣቅርበው የነበረውን በመቃወምና ጽፈው በ፲፱፻፹፬ ዓ.ም. ኣስጥለዋል።  በኋላም 106 ፊደላትና 97 ቍርጥራጮችን የኣልሆኑትን ኢትዮፒክ እየኣሉ 256 የፊደል ስፍራዎች እንደማይበቋቸው እንኳን የኣልዓወቁትን ተቃውመዋል። ይኽንንም በማድረጋቸውና ኢትዮጵያውያን በፊደላቸውና ቋንቋዎቿቸው በኮምፕዩተር እንዲጠቀሙ ስለፈጠሩ ለግዕዝና ኢትዮጵያ ባለውለታ መሆናቸው ከመጻፉ ሌላ “የግዕዝ ኣባት” የሚል የቅጽል ስም ተሰጥቷቸዋል።         
     በሁለተኛ ዙር ይህ የፊደል መቀጠል ጥፋት እንደገና ተደግሞ  364 ብቻ ግዕዝ፣ ዓማርኛ፣ ትግርኛና ኦሮምኛ ቀለሞችን ያጠቃለለ ለዩኒኮድ በሌሎች ስለቀረቡ ዶክተሩ በድጋሚ ተቃውመዋል። ይኸንንም ተቃውመው የጻፉት ፊደል ስለበዛና የግዕዝ በቶቹ ወደ ፴፯ ስለደረሱ የኣናሳ ተጠቃሚዎች ቋንቋዎች ቀለሞች በቅጥልጥሎች እንዲጻፉ ሌሎች ስለወሰኑ ነበር።   በሦስተኛ ዙር ማሻሻያዎችም ከ55 በላይ የጉራጌ፣ ኣገው/ቢለንና የመሳሰሉት የኣናሳ ተጠቃሚዎች ቋንቋዎች የግዕዝ ቀለሞች ዕውቅና እንዲያገኙ ቢጽፉምና  በትብብር ቢሳካም ሌሎች በጀመሩት ጠንቅ ግዕዝ ኣራት ስፍራዎች ተበትኖ ለዩኒኮድ ቀርቧል።        ዶ/ር ኣበራ ለግዕዝ መብት ባይቆሙለት ኖሮ     የኣማርኛ መጻፊያው መኪና ኣስቸጋሪ ኣከታተብና የኣልተሟላ ቁርጥራጭ ፊደል ተሻሽሎም ቢሆን ስሕተቱ እንደሚቀጥል ጽፈውም የዩኒኮድ ፊደል ሆኖ ኢትዮጵያ ከማትወጣበት ዘላቂ ችግር ውስጥ ከመውደቅ ኣትድንም ነበር።   ምንም እንኳን ዶክተሩ ሞዴት ውስጥ ጭምር ያቀረቧቸው ኣናሳ ቊጥር የኣላቸው ብሔሮች ቀለሞች ዩኒኮድ መደብ ውስጥ በመጨረሻው ቢገቡም    ዶክተሩ ለግዕዝ ፊደል እንዲያገለግሉ የፈጠሯቸውና ብዙዎች ከ፳ ዓመታት በላይ የተጠቀሙባቸው የግዕዝ ኣልቦ፣ ቊጥራዊ ኣኃዞችና ኣዳዲስ ምልክቶች ገና ኣልገቡም። ለምሳሌ ያህል የሚፈልጉት የማጥበቂያ ምልክትና ሌሎችም ከፊደሉ በኋላ እንጂ ከላይ ብቻ እንዲገቡ ዶክተሩ ኣይፈልጉም። ያም ሆነ ይህ ዛሬ በኮምፕዩተር፣ የእጅ ስልክና የመሳሰሉት መሣሪያዎች ውስጥ የምንጠቀምበት የዩኒኮድ ፊደል ዶክተር ኣበራ ሞላ ኮምፕዩተራይዝ የኣደረጉትም የግዕዝ ፊደላቸውና ፊደላችን ነው። ይህ ፊደል ኢትዮጵያውያን ለብዙ ዘመናት በብራናና በወረቀት ሲከትቡ የነበረውና ደራስያን በየማተሚያ ቤቶች ኣያሌ መጽሓፍትን የጻፉበት ነው።  

የኣማርኛ የታይፕርይተር ኣማርኛ እንዳልሆነ ዩኒኮድንና ሌሎች ኢትዮጵያውያንን ኣሳምነው ዶክተሩ ኮምፕዩተራይዝ የኣደርጉት የግዕዝ ፊደላቸው የዩኒኮድ ፊደል ሆኗል። እንዲህም ሆኖ የቅጥልጥል ፊደላቸው ውድቅ ከሆነባቸውና መጻፊያ ሠርተው ከተካሰሩት መካከል ኣንዱ ተቀይሞ ዛሬም የታይፕራይተሩን ፊደል ኮምፕዩተራይዝ ከኣደረጉት ኣንዱ ነው ተብሎ ዕውቅና ቢሰጠውም እንኳን በሓሰት ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ኣደረግሁ የሚል ኣለ። በሳይንስ ዓለም ውሸት ትልቅ ነውር ነው።  የዓማርኛ የጽሕፈት መኪና በሚል ርዕስ ከእዚህ በታች የቀረቡትን ከ፴፭ በላይ እንከኖች ማንበብ ይቻላል። 

በኣሁኑ ጊዜ ግዕዝ በዩኒኮድ ዕውቅና ያገኙትን የቢለን፣ ባስኬቶ፣ ቤንች፣ ምኢን፣ ሙርሲ፣ ሱሪ፣ ትግረ፣ ትግርኛ፣ ኣገው፣ ኣውንጂ፣ ኦሮምኛ፣ ዓማርኛ፣ ዲዚ፣ ዳውሮ፣ ጉሙዝ፣ ጉራጌ፣ ጋሞ ጎፋ እና ግዕዝ ቋንቋዎች የሚጋሯቸውን ቀለሞችና ሌሎች ያጠቃልላል። ከእነዚህ መካከል የቢለን፣ ባስኬቶ፣ ምኢን፣ ትግረ፣ ትግርኛ፣ ኣገው፣ ኦሮምኛ፣ ዓማርኛ፣ ዳውሮ፣ ጉሙዝ፣ ጉራጌ፣ ጋሞ ጎፋ እና ግዕዝ በዩኒኮድ የቋንቋዎች ፊደላት ስሞች አንዲሆኑ በዶክተሩ ተለይተዋል። በፊደሉ ከሚጠቀሙ ቋንቋዎች መካከል ሓረሪ ኣንዱ ነው። መጽሓፍ ቅዱስ ሙሉዉን ወይም በከፊል ከ፲፭፻፲፫ ዓ.ም. ጀምሮ በግዕዝ ቀለሞች በማተሚያ ቤቶች  ከታተሙባቸው ቋንቋዎች መካከል ሃዲያ፣ ሲዳሞ፣ ከንባታ፣ ኦሮሞ፣ ወላይታ እና ጌዴኦ ይገኙበታል።   የግዕዝ ፊደል ኢትዮጵያዊው ሊቅ ኦነሲሞስ ነሲብ የኦሮምኛውን መጫፈ ቁልቁሉ ሲጽፉ የፈጠሩትን ዸ ቀለምና እንዚራኖቹን ይጨምራል።  ዶክተሩ ኮምፕዩተራይዝ ያደረጉት ትክክለኛውና በሳይንሳዊ ግኝትና ኣርበኝነት ከኣጥፊዎች ያቆዩልንና የግዕዝ ቀለሞቻችን የተለያዩ መልኮች እዚህ ኣጓዳኝ መዝገበ ቃላት ማየት ይቻላል። እንደ ኤውሮጳ ኣቆጣጠር በ1991 Ethiopian Research Council የሚባል በ1934 ኣሜሪካ ውስጥ (በእነ ዶ/ር መላኩ በያን) የተቋቋመ ድርጅት ዶክተሩ ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ በማድረግና ለጀመሩት የግዕዝ ፊደል ሕዳሴ የዕውቅና ሽልማት ሰጥቷቸዋል።   ሽልማቱም “...for computerizing Ethiopic and revolutionizing the Geez script” ይላል።

ምንም እንኳን ለኣማርኛው የጽሕፈት መኪና ሲባል ቀለሞቹ እንዲቀነሱ የተለያዩ ሓሳቦች ቀደም ብለው ቢቀርቡም  ትክክለኛዎቹ ፊደላት ወደ ኮምፕዩተርና ወደ ዩኒኮድ የዓለም መደብ በዶክተሩ ሲገቡ ሞክሼዎች እንዲቀሩ ስለኣልተባለ ትክክለኛ ሥራ ተሠርቷል።  ምክንያቱም የዶክተሩ ዓላማ የግዕዝን ፊደል ወደ ኮምፕዩተር ማስገባት እንጂ የዓማርኛውን የታይፕራይተር ፊደል ወደ ኮምፕዩተር ማስገባት ስለኣልሆነና ሥራቸው የታይፕራይተሩን ችግር ከመፍታት ሌላ የማተሚያ ቤቶች ሠራተኞችንም ድካም የሚቀንስ መሆኑን ስለዓወቁ ነው። በኋላም ይህ ውጤት ሊገኝ የቻለው ግን በግማሽ የዓማርኛ ፊደል እንዲጻፍ መደብ ኣውጥተናል የኣሉትንና ፊደል ስለበዛ የኣናሳ ተጠቃሚዎች ቋንቋዎች ቀለሞች ቅርጾቻቸውን እንደጠበቁ ማስገባት ቀርቶ በቅጥልጥል ነገሮች ይሥሩ የኣሉትን ጥቂት ኢትዮጵያውያን ዶክተሩ ከተቃወሙና ሁሉም ቀለሞች ቅርጾቻቸውን ጠብቀው እንዲቆዩ ከኣሳመኑ በኋላ ነበር።  እንዲህም ሆኖ ለድረገጽ መሥሪያ 225 ፊደሎችን ኣንድ የተራዘመ ለእንግሊዝኛ የተሠራ መደብ (Extended ASCII) ስለሚችል በእዚያ ልክ የዓማርኛውን ቀለሞች መርጠው በቂ ናቸው በማለት ለኣንዱ ዕውቅና ስለሰጡ   ዶክተሩ ለሦስተኛ ጊዜ ተቃውመው በማስጣል ኣሸንፈዋል። የሚያሳዝነው ግን እነዚሁ ሰዎች ግዕዝና ዩኒኮድ ምን እንደሆነ ዋቢ ኣድርገው እ.ኤ.ኣ. 1995 ሲጠቀሙበት የነበሩትን የዶክተሩን ቀለሞች እንኳን ያስገቡት ግዕዝን ኤክስቴንድድ (Ethiopic Extended) ብለው ለኣራተኛ ጊዜ ከስሕተቶቻቸው ሲነቁ ነበር።  እንዲህም ሆኖ ደራስያን በሚፈልጉት ቀለሞች ዓማርኛውን የመክተብ መብት ቢኖራቸውም ቀለማቱ በዩኒኮድ ዕውቅና ስለኣገኙ ፊደል መቀነስና መቀንጠስ ያስፈልጋል የሚባለው ክርክር በዶክተሩ ኣሸናፊነት ኣክትሟል። ቴክኖሎጂው በሁሉም የግዕዝ ቀለሞች እንድንጠቀም ችሎታ ስለሰጠን በተቀነሱ ወይም ሞክሼዎች በሌሏቸው መሥራትን ዶክተሩ ኣይደግፉም። ምክንያቱም ወደፊትም ኮምፕዩተሩ ትክክለኛዎቹን ኆኄያት መርጦ ስለሚያቀርብ ለመሳሳት ዕድሉ ስለማይኖር መቀነስ ደካማ ጊዜያዊ ኣማራጭ እንጂ ግዴታ መሆን ስለሌለበት ነው። በተጨማሪም ፊደል መቀነስ ከታይፕራይተር ጋር በተያያዘ የመጣ ደካማ አስተሳሰብ በዶክተሩ ግኝቶች የተነሳ ቀርተዋል። በግዕዝ ፊደል የሚጠቀሙ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ብዛት ወደ 45 ይደርሳል ይባላል።  በቅርቡ መጠቀም ከጀመሩት መካከል ማሌ እና ዲሜ ቋንቋዎቻችን ይገኙበታል።

ግዕዝ ወደ ዩኒኮድ ሲገባ ኣስተዋጽዖ ከኣደረጉት መካከል ዶ/ር ፒ. ማክክሉር፣ ኢ/ር ጆ. ቤከር፣ ኢ/ር ሎይድ ኣንድርሰን፣ ኢ/ር ግሌን ኣዳምስ፣ ዶ/ር በቀለ ሞላ፣ ጌታቸው ሞላ፣ ኢ/ር ፍሰሓ ኣጥላው፣ ኢ/ር ታከለ ኣድነው፣ ኢ/ር ፀሓይ ደመቀ፣ ዶ/ር ይጥና ፍርድይወቅ፣ ኢ/ር ግሩም ከተማ፣ ኢ/ር ቴዎድሮስ ኪዳኔ፣ ዶ/ር ሳሙኤል ክንዴ፣ ኢ/ር ተረፈ ራስወርቅ፣ ኢ/ር ተሻገር ተስፋዬ፣ ኢ/ር ታደሰ ፀጋዬ፡ ኢ/ር ማቲዎስ ወርቁ፣ ኢ/ር ኣባስ ዓለምነህ፣ ኢ/ር ዳንኤል ያዕቆብ፣ ኢ/ር ዮናስ ፍሰሓ፣ ዶ/ር ኣርዓያ ኣምሳሉ፣ ማይክል ኤቨርሰን፣ ኢ/ር ዳዊት ብርሃኑ፣ ኢ/ር ኤፍሬም ተክሌ፣ ኢ/ር እስክንድር ሳህሌ፣ ኢ/ር ዮናኤል ተክሉ እና የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኤጀንሲ ይገኙበታል። እነዚህ ውጭ ኣገር የኣሉ ኢትዮጵያውያን ኣገራቸው ችሎታውን በኣልነበራት ጊዜ ኃላፊነታችውን በትብብር የተወጡና ታሪክ የሠሩ ባለውለታ ጀግናዎች ናቸው። ይህ ዝርዝር ያላካተታቸውን ማሟላት ይቻላል።  

ዶክተሩ ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ኣድርገው ለዩኒኮድ ከኣቀረቡ በኋላ ችግር የፈጠሩባቸው የተለያዩ ዓይነቶች ሰዎች ነበሩ።  ይህ የሚቀርበው ከረዥም ስሕቶቻችው መማር ኣቅቷቸው ዛሬም ሰውን ከማውናበድ በኣለመቆጠባቸው ሲሆን እንደኣስፈላጊነቱ ወደፊት ስማቸው  ይዘረዘራል።   ምሳሌ፦  

የዩኒኮድ የዓለም ቀለሞች መደብ ውስጥ  የግዕዝ ፊደላችን ፲፪ኛው (1200) መደብ ላይ ይጀምራል።  የዩኒኮድ መደብ ውስጥ “ፘ” “ፙ”ን ስለቀደመ ማስተካከል ይኖርብናል። የኣሽሙር (ስላቅ፣ ቀልድ፣ ፌዝና መፀት) ምልክትም ተረስቶ የዩኒኮድ መደብ ውስጥ ኣልገባም።

በዶክተሩ ሳይንሳዊ ሥራ ተሸንፈው ፊደል መቀነስና መቀንጠስ ትተው በኋላ ተቆርቋሪ የሆኑ ኣሉ። ቀንና ደራሲ የሌሏቸው በተለይ በእንግሊዝኛ የቀረቡ ጽሑፎች ኣቀራረባቸው ግዕዙን ለማዳከም ስለሆነ ኣንባቢው መገንዘብ ይኖርበታል። ፊደሉ ለሌሎች ቋንቋዎች እንዲተርፍ መጨመር ያስፈልገው ይሆናል። ወደፊት ዩኒኮድ ውስጥ መግባት የኣለባቸው ወንበር የሌላቸውን ኣሥሩን የዶክተሩን ኣኃዞች፣ ሥዕላቸው እዚህ የቀረቡ የፈጠሯቸውን ስምንት ምልክቶችና ነቍጥን ይጨምራል። 

ዶ/ር ኣበራ ሞላ የግዕዝ ፊደል፣ ገበታና ኣከታተብ ፈጣሪ ከመሆናቸው ሌላ ፊደሉንም ወደ ትሩታይፕ በመቀየር የመጀመሪያው ናቸው። የሠሩትንም የግዕዝ ፊደል ለዩኒኮድም ሰጥተዋል። የፈጠሯቸው የተለያዩ የግዕዝ ፊደላት ሆኑ ኣከታተቦችና ገበታዎች ለተለያዩ ቍርጥራጮች፣ የግዕዝ ቀለሞችና የዩኒኮድ ፊደላት ጭምር ነው።

ዶ/ር ኣበራ ለመጀመሪያ ጊዜ ግዕዝ በኮምፕዩተር እንዲከተብ በሞዴት ሲፈጥሩ እየኣንድኣንዱ ቀለም የትኛው ቍልፍ ላይ መመደብ እንዳለበትም ወስነዋል።   ከእዚያም ወዲህ ኣመዳደቦቹ እንዳስፈላጊነታቸው በኢትዮወርድ (EthioWord)   እና ግዕዝኤዲት (GeezEdit) ተሻሽለው ቀርበዋል። 
 
ግዕዝ ወደ ኮምፕዩተር ለመጀመሪያ ጊዜ ሲገባ ወይንም ግዕዝ በኮምፕዩተር እንዲሠራ ሲፈጥሩ ኣዳዲስ ነገሮችን ፈጥረዋል። እነዚህም ኣንደኛ ፊደላቱ ኮምፕዩተር ላይ እንዲታዩና ሲታተሙም ወረቀት ላይ እንዲታዩ እየኣንድኣንዱን ቀለም ለኮምፕዩተሩ እስክሪንና ለተለያዩ የማተሚያ መሣሪያዎች መሥራት። እየኣንድኣንዱ የግዕዝ ቤት በፈንክሽን (Function key) መርገጫ በኣንደኝነት እንዲቀርብ ሆኖ ቀለማቱ እንዚራን በሁለተኛው መርገጫ ኣማካኝነት ቀረቡ።  ሁለተኛው ለፊደላቱ ገበታዎችና ገጽታ (Layout) በመፍጠር የትኛው ቀለም የትኛው ቍልፍ ላይ እንደሚመደብ መወሰን። ሦስተኛው እየኣንድኣንዱ ቀለም ከሁለት መርገጫዎች በላይ ሳያስፈገልገው እንዲከተብ የመክተቢያ ዘዴ መፍጠር። ለምሳሌ ያህል በሁለት መርገጫዎች የሚከተብ ቀለም የሚታየው ሁለተኛው መርገጫ ከተረገጠ በኋላ ሊሆን ይችላል። ኣራተኛው የግዕዝ ፊደል ለዘመናት ሲጠቀምበት እንደቆየው የፊደሉ ተጠቃሚ ቋንቋዎች የሚከተቡት በግዕዝ ፊደል ነው። (በሌላ ኣነጋገር ኣብዛኛው ፈረንጅ እንደሚመስለው ፊደሉ በላቲን ፊደል ተጽፎ ወደ ግዕዝ ኣይቀየርም ማለት ነው። የፊደሉ ዋና ጥቅሞች ለመጻፍና ኣንድን የግዕዝ ጽሑፍ ለማየት ነው።) ኣምስተኛው ግዕዝ መሣሪያውን በሚገባ እንዲጠቀም ኣስፈላጊ የሆኑትን ኣዳዲስ ነገሮች መጨመር፣ መፍጠር፣ ማስተዋወቅና መጠበቅ ነበሩ። 

 
  ለምሳሌ ያህል ፊደላቱ ከተበተኑበት ስምንት ፎንቶች ሌላ ድርብርብ ሆነው ከቀረቡት ሌሎች ፊደላት ኣንዱ የሞዴት መጻፊያ ፎንት መነሻ ዓማርኛ በብዛት የሚጠቀምበት ሳድሳኑ በቀዳሚነትና በብዛት ሁለተኛ የሆኑት የግዕዝ ቤት ቀለሞች በዝቅ መርገጫዎች እንዲከተቡ ቀርበዋል። ለስድስተኛ ምሳሌ ያህል የኮምፕዩተር የእንግሊዝኛ ምልክቶች ኣጠቃቀም ለግዕዙም እንዲያገለግል በተመጣጣኝ ቀለሞች ቀርበዋል። የእንግሊዝኛው ኣመዳደብ የተመረጠው የቍልፎች መለጠፊያዎች በሰባተኛነት ቢሠ’ሩም ግዴታ በመሆን እንዳያስፈልጉና  ኣከታተቡን ወደ እንግሊዝኛው QWERTY (ቅውኽርትይ) ገበታ ለማቀራረብ ነበር። በኮምፕዩተር ዘመን ግዕዝን ብቻውን ማቅረብ በቂ ስለኣልሆነ ግዕዙ የቀረበው በዘጠኝነት ከእንግሊዝኛ ፊደሎች ጋር ነው። ስለዚህ እንደ ግዕዝኤዲት ዩኒኮድ የኣሉት የሞዴት፣ ኢትዮወርድ እና ግዕዝኤዲት ፊደሎቻችን የእየእራሳቸው የእንግሊዝኛና የግዕዝ ፊደሎች ኣሏቸው። በዘጠኝነት ሕዝቡ እራሱን ኣከታተቦች እንዲያስተምር ጠቅሟል። በኣሥረኝነት የተጠቃሚዎች ቋንቋዎች ብዛት ተመጣጥነዋል፣ ስሕተቶችና ግድፈቶች እንዲታረሙና ወደ ዘመናዊ ኣሠራር እንዲሻሻሉ ሓሳቦች ቀርበዋል። በኣሥራ ኣንደኝነት ኣንድን ጽሑፍ በኣልተቀጠሉት የታይፕራይተር ገበታና በእንግሊዝኛ ዓይነት ኣቀማመጥ በሁለቱም ኣከታተብ መጻፍና ማሻሻል ቀርቶ በእንግሊዝኛው ዓይነት ብቻ እንዲሠራ ኣድርገዋል። በኣሥራ ሁለተኝነት ኣሠራሩም ለዘመናት የተለመዱትን የእንግሊዝኛ ዘዴዎችና ኣጠቃቀሞች ለግዕዙም በማድረግ ከኮምፕዩተር ወደ እጅ ስልኮች እንዲዘልቅ ሆኗል። የዶክተሩ ግኝት ለግዕዝ ብቻ ስለኣልሆነ እንግሊዝኛውንም ይመለከታል። በኣሥራ ሦስተኝነት ኣንድን ጽሑፍ ታይፕራይተርና በእንግሊዝኛው ኣጻጻፋቸው የተለያዩ ሰዎች እንዲከትቡና አንዲያሻሽሏቸው ኣስችለዋል። በመጨረሻም ዶክተሩ በፊደል ቅነሳ ባይስማሙም ለሚፈልጉት የተቀነሱትን የፊደል ገበታ ኣቅርበዋል። በኣሥራ ኣራተኛነት የዜሮ ኣኃዝ በሕንዶች ከሺህ ዓመታት ግድም ተገኝቶ ቀስ በቀስ ዓለም ሲጠቀምበት ኢትዮጵያውያን ምንም ሳያደርጉ ቆይተው በመጨረሻው የኣረቡን መጠቀም ስለጀመሩ ዶክተሩ ለመጀመሪያ ጊዜ የግዕዝን ኣልቦዎች ፈጥረው ፊደሉ ከኮምፕዩተር ቴክኖሎጂ ጋር የሚሄድ ኣኃዛዊ ኣድርገውታል። 

እንዲህም ሆኖ ግዕዝን በኮምፕዩተር መጠቀም ፊደሉን ማቅረብ የሚመስሏቸው ኣሉ። የላቲንም ሆነ የግዕዙ ፊደል መሣሪያው ላይ ከሌለ ሳጥን የመሰሉ ነገሮች ይታያሉ። ፓተንት የሚሰጠውም ለፊደሉ ወይም ፊደሉን ለሠራው ኣይደለም። የዶክተሩን ፊደላት መርገጫዎች ስፍራ ቀይሮ ማቅረብ ሕዝቡን ለማወናበድ እንጂ ኣዲስ ግኝት ወይም ገበታ ኣይደለም። የዶክተሩን ፈር ቀዳጅ ሥራ በተለያዩ ደካማ ገልባጮች መተካት ቢሞከርም ብቸኛውና ትክክለኛ በመሆን ከ፴፪ ዓመታት በላይ ማገልገሉን ቀጥሏል። ዶክተሩ መክተቢያዎቹን ወደ ኣንድ ሲያሻሽሉት ገልባጮች ከሁለት በላይ መርገጫዎችን በመጠቀም ያልተሟሉና ያልተከተቡ ጽሑፎችን በማቀረብ ሕዝቡን በማጃጃል ገፍተውበታል። 

በኮምፕዩተር የግዕዝ ፊደል የመጀመሪያውን መብት ያገኘበት የዩናይትድ እስቴትስ ኮፒራይት ወይም መብት ምሳሌ ሞዴት (የኢትዮጵያ ቃላት ማተሚያ) በዶ/ር ኣበራ ሞላ፣ የመብት ቍጥር TX0003337637 ፲፱፻፹፪ ዓ.ም. እዚህ ኣለ። 

ዶ/ር ኣበራ ሞላ እየኣንድኣንዱ የግዕዝ ቀለም በሁለት መርገጫዎች እንዲከተብ የፈጠሩትን ዘዴ በኢትዮጵያ ኋላ ቀርነት የተነሳ መብታቸውን ማስጠበቅ ስለኣልቻሉ የተለያዩ ኣከታተቦች መቅረብ ቢቀጥሉም ለዊንዶውስ  እና ማክ  ያቀረቡትንም በቅርቡ ወደ ኣይፎን እና ዓይፓድ ወስደውታል።  የእንግሊዝኛው ኣመዳደብ የተመረጠው መለጠፊያ እንዳያስፈልግና ኣከታተቡን በፓተንት በተጠበቀው ወደ እንግሊዝኛው QWERTY (ቅውኽርትይ) ገበታ ለማቀራረብ ነው። ሁለቱም ቋንቋዎች የሚጠቀሙበትን መርገጫዎች በመጋራት ሕዝቡ በሁለቱም ፊደላት በኣንድና ሁለት መርገጫዎች የተጠቀመው ለብዙ ዓመታት ሥራ ላይ ውሏል። በዶክተሩ ግኝት ሁሉንም የግዕዝ ቀለሞች ከኣንድ ገበታ በኣንድና ሁለት መርገጫዎች ብቻ መክተብ ተችሏል። ለላቲን ቀለሞች የተሠሩት መርገጫዎች ከኣሥር እጅ በላይ ብዛት ለኣላቸው የግዕዝ ቀለሞች ሥራ ላይ ውለዋል።  በዶክተሩ ዲጂታይዝድ (Digitized) የሆነው የጥንቱ የግዕዝ ፊደል የውጭ ኣገሮችና የኢትዮጵያ ማተሚያ ቤቶች ከመቶ ዓመታት በላይ የተጠቀሙበትም ፊደል ነው። 

መርገጫዎችን በጣቶች በመንካት መጻፍ ያስቻለውን የላቲን ቀለሞች የእጅ ጽሑፍ መሣሪያ ኣከታተብ ወደ ኮምፕዩተርና ጮሌ የእጅ ስልኮች በተሻሻለው ዓይነት ለግዕዝ ቀለምም ይኸው ትክክለኛና ሳይንሳዊ ኣጠቃቀም ለግዕዝ ሥን ጽሑፍ ሥራ ላይ ውሏል። የእዚህ ገጽ ኣንዱ ዓላማ ሕዝቡ ስለ ቴክኖሎጂው እንዲያውቅና እንዳይታለል ሲሆን ጥቂቱ በወሬ እየተፈታ ጊዜውን እንዳያባክን መረጃ መጠየቅም እንዲጀምር ነው። በሳይንስ ኣሠራር ኣንድ ነገር ተሻሻለ የሚባለው በሂሳብ ተመዝኖ (Statistical Analysis)  ብልጫ ወይም ልዩነት ሲያሳይ (Significance) እንጂ ኣንድኣንዶቹ እንደሚፈልጉት በተራቀቀ መሣሪያ በመጠቀም ወደኋላ ለመመለስ ኣይደለም። በዶክተሩ ኣከታተብ ህ እንዲሁ በኣንድ መርገጫ ብቻ ይከተባል። ሀ በዝቅ h ወይም h መዝለያ ሲጻፍ ሁ በhu፣ ሂ በhi፣ ሃ በha፣ ሄ በhe እና ሆ በho ይከተባሉ። የስምንተኛ ቤት ቀለሞች በ\፣ . ወይም 8 ይከተባሉ። በኮምፕዩተር ኣከታተብ ወግ የመጀመሪያዎቹ የላቲን ቀለሞች ወይም ካፒታሎቹ (Capitals) የቁልፉም ስም ስለሆኑ የሚከተቡት በዝቅ መርገጫ ነው። በእንግሊዝኛው ኣያያዝ H (ኤች) የመርገጫው ስም የሆነው በዝቅ h (ኤች)  እንደተከተበው የግዕዙም ሀ የመርገጫ ስም በዝቅ ህ ወይም ሀ እንዲከተብ ተደርጓል። ስለዚህ የሀ መርገጫ የሀ ቍልፍ ስምም ነው። በእዚሁ ኣያያዝ እንግሊዝኛ ለ94 ቀለሞቹ የሚጠቀምበትን ኣከታተብ የግዕዝ ፊደል ሁሉንም ቀለሞቹን እንዲጠቀምበት ሆኗል።     ሠላሳ ሰባቱ የግዕዝ ቤት ቀለሞች እንደላቲኑ 26 የእራሳቸው ቁልፎች ስለኣሏቸው ለትምህትና ገለጻም ጠቀሜታ ኣላቸው። ስለዚህ ማንኛውንም የግዕዝ ቀለም በማዳበል በሦስት መርገጫዎች መክተብ ጊዜና ጉልበት ማባከን ነው። ማንኛውንም የግዕዝ ቀለም በማዳበል በሦስት መርገጫዎች መክተብም ግዕዝ የእራሱ ገበታ እንዳይኖረው ነው። ማንኛውንም የዓማርኛ ቀለም በስድስት መርገጫዎች መክተብ ጊዜና ጉልበት ማባከን ነው። ምሳሌ ፄ። ዓማርኛውን በብዙ መርገጫዎች መክተብ ሌሎችን ከእዚያ በላይ መጠቀም ያስከትላል። ኣንዳንዶቹ በዘዴዎቻቸው የእራሳቸውን ቋንቋዎች በሦስት መርገጫዎች መክተብ እንጂ ፊደሉን ለሚጠቀሙ 80 የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ዘዴዎቻቸው እንደማይጠቅሙ የተገነዘቡ ኣይመስልም።

ኣመልካች ጣቶችን የ“ፈ” እና “ጀ” መርገጫዎች ላይ በማድረግ “ፋ” በትንሿ ጣትና “ፌ” በግራ ቀለበት ጣት ይከተባሉ። “ጁ” በቀኝ ኣመልካች፣ “ጂ” በመካከለው፣ “ጆ” በቀኝ ቀለበት እና “ጇ” በትንሿ ጣት ይከተባሉ። ይኸም በየተራ እንደ “fa”፣ “fe”፣ “ju”፣ “ji” ፣ “jo” እና “j\” እንደሚከተቡት መሆኑ ነው።  ይህ በእንዲህ እንዳለ የግዕዝ ፊደል የእራሱ ገበታ ቢኖረው ስለማይጠቅመው በእንግሊዝኛ፣ ፈረንሳይኛ ወይም ኣረብኛ የፊደል ገበታ ቢጠቀም ይሻለዋል በማለት ግዕዝ በእንግሊዝኛ እስፔሊንግ እንዲከተብ የሚፈልጉ ኣሉ። ላቲን ፊደሉን የሚከትበው በፊደሉ ነው። ግዕዝ ፊደሉን በላቲን ፊደል እስፔሊንግ ከA እስከ Z በኣሉት ይከተብ ማለት ለፊደሉና ኢትዮጵያውያን ስድብ ነው። ምክንያቱም ለእየኣንድኣንዱ የእንግሊዝኛ ቀለሙ የተሠሩት 26 መርገጫዎች ለ37 የግዕዝ ቀለሞች የተሠሩ ስለኣልሆኑ 26 መርገጫዎች ለላቲን መክተቢያዎች እንጂ ለግዕዙ ኣልተሠሩም። ግዕዝን በእንግሊዝኛ እስፔሊንግ መክተብ እንግሊዝኛ ቋንቋዎችንንና ፊደሎቹን ለማዳበር ስለሚጠቅም ኣንድኣንድ የውጭ ኣገር ሰዎችና ኢትዮጵያውያን ኣጎብጓቢዎች ይወዷቸዋል። በእንግሊዝኛ እስፔሊንግ ዓማርኛና ግዕዝን መክተብ እንዳስቸገረ ቢጻፍም የማይቀየሩ ኣሉ። ግዕዝን በ26 መርገጫዎች መክተብ መሞከር ከእስፔሊንግ ጣጣ ኣልፎ ላቲን ውስጥ የሌለውን ፊደልን በእስፔሊንግ የመጻፍ ኣዲስ ችግር ግዕዝ ላይ ይፈጥራል። የላቲን ፊደል ተጠቃሚዎችን ለእስፔሊንግ ፊደል ችግር ውስጥ ከጣላቸው ኣንዱ ምክንያት የፊደላቱ ቍጥር ማነስ ነው። ግዕዝ ድምጻዊና የተስፋፋ ፊደል ስለሆነ የላቲንን ችግር ለግዕዝ ማካፈል ኣያስፈልግም። ለምሳሌ ያህል ትግርኛውን ቜ በስድስት መርገጫዎች የሚያስከትቡ ኣሉ። ከእዚህም ሌላ ያልተሟሉና ስለሆነ ሁሉንም የግዕዝ ቀለሞች የማያስከትቡ ኣሉ። ወደ ኦሮምኛው የላቲን ቁቤ ኣከታተብ በቀረበ ኣንድን ድምጽ በብዙ መርገጫዎች የሚያስከትቡ ኣሉ። 

ግዕዝ ብዙ የድምጽ ቤቶች በኣሉት ቀለሞች ሲጠቀም እንግሊዝኛ ኣንድ ዓይነት ድምጽ ብቻ በኣለው ፊደል ነው የሚጠቀመው። የእንግሊዝኛው ፊደል ድምጽ በግዕዝ የሳድሱ ድምጽ ዓይነት ነው። በእንግሊዝኛ የኮምፕዩተር ገበታ ሳድሳኑ ድምጾች በኣንድ መርገጫ እንደሚከተቡት ሁሉ የግዕዙም ሳድሳን በኣንድ ይከተባሉ። በእንግሊዝኛ ካፒታል ፊደሎቹ የቁልፎቹ ስምም (ምሳሌ፦ Capital “M”) ስለሆኑ በዝቅ መርገጫዎች እንደሚከተቡት በግዕዝም የመርገጫዎቹን ስሞች የግዕዝ ቤት ፊደላት (ምሳሌ፦ የግዕዝ ቤቱ “መ”) የቁልፎቹ ስምም በዝቅ መርገጫዎች እንዲከተቡ ዶክተሩ ወስነዋል። በተጨማሪም በዓማርኛ 40 በመቶ የሚሆኑት ቃላት ሳድሳኑ ስለሆኑና ይህ በብዛት ኣንደኛ ስለሚያደርጋቸው እነሱን አንደላቲኑ እያንዳቸውን በኣንድ መርገጫ መክተብ ተገቢ ነው። ሌሎቹ ሰባት እንዚራን ወደ 60 በመቶ ናቸው። በእንግሊዝኛው እንደሚደረገው የኮምፕዩተሩ ኣከታተብ ወደ እጅ ስልክ እንደዞረው ለግዕዙም ሆኗል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ወጉንና ሥርዓቱን ሳይጠብቁ የፊደሎቹን ቦታዎች እየቀያየሩ ለኮምፕዩተርና ለእጅ ስልክ የተለያዩ፣ የኣልተሟላና የማይጽፉ ኣከታተቦች በብዙ መርገጫዎች የሚያቀርቡ ኣሉ። ለምሳሌ ያህል ይህ የዊኪፔዲያ ገጽ “ቊ”  እና “ቌ”  የዓማርኛ ቀለሞችን ኣያስመርጥም። የዶክተሩን ሥራ መገልበጥ እንጂ ኣስተሳሰብ የኣልገባቸው ሳድሳኑን በሁለት መርገጫዎች የሚያስከትቡና የሚከትቡ እንዲሁም ኣንብበው ከመረዳት ይልቅ በወሬ የሚነዱ ተወናባጆች ኣሉ። በብዛት ኣንደኛ የሆኑትን የግዕዝ ሳድሳን ቀለሞች በዶክተሩ ፈጠራ በኣንድ መርገጫዎች ከመክተብ ይልቅ በሁለት መክተብ ጅልነት ነው። (ምሳሌ፦ ጥን በዝቅ T ።) የእንደዚህ ዓይነቶቹ ችግሮች መነሻዎች ስለጉዳዩ የሚያውቁት የዶክተሩን በፓተንቶች የተጠበትን ዘዴዎች ከመደገፍና እዚህ እንደሚደረገው ከማስተማር ይልቅ መገልበጥ፣ መስረቅ ወይም ዝምታን የመረጡ በብዛት ስለኣሉ ነው። እነዚህ እራሳቸውንና ግዕዝን መበደላቸውንም የማይገባቸውም ኣሉ።  የዶክተሩ ግዕዝ ኣጠቃቀም ፊደላቱን ከኣንድ እስከ ስምንት በላይ ፎንቶች በመበታተንና እንዳሉ ከመጠቀም ሌላ በዋየሎች፣ ፈንክሽን፣ ኣኃዞችና ምልክቶች ቍልፎች ማቅለምንና መለዋወጥንም ይመለከታል።  እንደታይፕራይተሩ ዘዴ ኣንድ የፊደል ገበታ ለግዕዝ ስለማይበቃ ከኣንድ በላይ ገበታዎች ላይ የተበተኑትን በኣንድ የተጻፈውን በሌላ መርገጫ ቀይሮ ማቅረብን ይጨምራል።  ዶክተሩ የተጠቀሙበት ፕሮግራም ዓይነት ለገበያ የቀረበ ሲሆን (እ.ኤ.ኣ. በ1983) ዘዴዎቻቸው ከኢትዮጵያውያን ይልቅ የገልባጮችና የእውሸት የግዕዝ ሌጀንዶች (Legends) ሲሳይ ሆኗል። ኢትዮጵያ የፓተንት ሕግ እንደሌላት ሳያውቁና ከዓወቁ በኋላ የዶክተሩን ዘዴዎች ገልብጠው የተለያዩ ፕሮግራሞች ውስጥ ሲሸጡና ሲበትኑ የነበሩ ከተጠቀሙባቸው ፕሮግራሞች መካከል ወርድእስታር፣ ወርድና ወርድፐርፌክት ይገኙበታል። የኢትዮወርድን ኢትዮፒክ ዶት ስም ቀይሮ ሲሸጥ ከነበረ ኣንስቶ ዘዴውን እንደኣዲስ ነገር ለኮምፕዩተር፣ ለእጅ ስልክና ፓተንት ማመልከቻ የኣቀረቡ ኣሉ። የዶክተሩ ፓተንት ግዕዝን በኣንድና ሁለት መርገጫዎች መክተብን ያጠቃልላል።

ከእዚህ ሌላ በእንስሳት ሕክምና ሙያቸውም  በተለይ በኢምዩን ደፊሸንሲ ፓተንቶችና በኣበረከቱት Immune Deficiency Patent 4,501,816   2,127,963  ፈውስ  ይታወቃሉ።      በኣደረጉት ምርምርና ውጤት ኢምዩን ደፊሸንሲን በማስወገድ  በየዓመቱ ሲጠፉ የነበሩትን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕይወትን  እ.ኤ.ኣ. ከ፲፱፻፸፰ ወዲህ ማትረፍ ተችሏል።   ከሰው ልጅ እናቶችና ከኣንዳንድ የጦጣና ውሻ ዝርያዎች በስተቀር የሌሎች እንስሳት ማህጸኖች ኢምዩኖግሎቡሊን (Immunoglobulin) የሚባለውን የበሽታ መከላከያ ፕሮቲን ለጽንሶቻቸው በእርግዝና ጊዜ ኣያስተላልፉም። ኣጥቢ እንስሳት በእርግዝና ጊዜ በኣካባቢው ለሚገኙት በሽታዎች መከላከያዎች በእንገርነት ያከማቹላቸውና ኣራሶቻቸው እንደተወለዱ ጡት ሲጠቡ የበሽታ መከላከያዎቹ ፕሮቲኖች ሳይለወጡ ከኣንጀት ወደ ደም በመግባት ለጥቂት ሳምንታት ከበሽታዎች ይከላከሉሏቸዋል። ኣራሶቹ እንገሩን ሳያገኙ ከቆዩ ግን ወደ ደም መግባታቸውና መከላከያነታቸው ቀርቶ እንደ ተራ ፕሮቲን ምግብ ብቻ ይሆናል።  ስለዚህ እንደ ጥጆች የኣሉት ሲወለዱ የኤድስ ቫይረስ የበሽታ መከላከያቸውን እንደጨረሰ ሰው ምንም መከላከያ ስለሌላቸውና ኣካባቢው ያሉትን የበሽታ ጀርሞች እየቀማመሱ በተለያዩ በሽታዎች የእራሳቸውን መከላከያ መሥራት እስከሚጀምሩ ድረስ እየተጠቁ ኣብዛኛዎቹ ይታመማሉ፣ ወደ ኣሥር ከመቶም  ይሞታሉ። ታክመው የሚድኑትም ኣይጠረቁም።    በኮሎራዶ እሰቴት ዩኒቨርሲቲ (Colorado State University) የዶ/ር ኣበራ የድህረ ዶክትራል ምርምር ይኸን ችግር ለመቋቋም መፍትሔ ፍለጋ ጋር የተያያዘ ነበር።      

ከላይ እንደተገለጸው በዶ/ር ኣበራ ሞላ ግኝት እስከ 50 ከመቶ  ለዘመናት ጠንቅ ሆኖ የቆየውን መድኃኒት የሌለውን የእንስሳትን ኤድስ ዓይነት ሁኔታ (Failure of Passive Transfer / FTP) መቆጣጠርና ማስወገድ ተቻለ።      ጥጆች የእናቶቻቸውን ጡት በመጥባት ወይም በጡጦ ከሚሰጣቸው እንገር በቂ የበሽታ መከላከያ ማግኘታቸው ኣስተማማኝ ኣይደለም።  ኣንዱም ምክንያት የጥጃ ወተት ኣንጀት ይዘት ሁለት ሊትሮች ብቻ ስለሆነ ነው። በእዚህ የተነሳ እንደኣካባቢው ቆሻሻነት ለተቅማጥ፣ የሳንባ ምችና ሌሎች በሽታዎች እየተጋለጡ ገበሬውን የሚያካስሩት እንደተወለዱ በቂ መድኅን የኣላገኙት ዋናዎቹ ናቸው። እንገር ውስጥ የኣለውን የበሽታ መከላከያ ፕሮቲን ጥጃው እንደተወለደ ከተሰጠው እንገሩ ጨጓራ ሳይገባ ከወተት ኣንጀት ወደ እንጀት በመሄድ ሳይለወጥ ደም ውስጥ ይገባል። የእንቦሳ ጨጓራ እንደሚሠራና እንገር ውስጥ የኣሉት የበሽታ መከላከያዎች ወደ ደም እንደሚገቡ በምርምር በማረጋገጥ የመድኅን ማነስን (Passive Immune Deficiency) ለመጀመሪያ ጊዜ ዶክተሩ ማስወገድ ቻሉ። ምርምራቸውን ጨርሰው ያቀረቡትን መፍትሔ ሁሉም ዓውቀውት ቢጠቀሙበት የመድኅን ማነስ ወደ ኣልቦ (ዜሮ) ከመቶ ግድም ሊወርድ ይችላል።      
         ምክንያቱም ጥጃው እንደተወለደ እንገሩን ማግኘቱ የበሽታ መከላከያው ወደ ደም በብዛት የሚገባበት ጊዜ ከመሆኑም ሌላ የበሽታ መከላከሉን ሥራ ስለሚጀምርና ብዙ ደቂቃዎች ሳይወስድ እንገሩን በብዛት መስጠት ስለተቻለ ነው። እነዚህን ማሳካትና እንገሩ በቂ መከላከያ ፕሮቲን እንዳለው ማረጋገጥ ተጨማሪ ጥቅሞች ናቸው። ጥጆች እንደተውለዱ ወደ ጋለን የሚጠጋ ጥሩና ንፁህ እንገር እንደመጋት ባይጠቅምም ገበሬውም የእንገሩን ጥሩነት የሚያጣራበት የእንገር መመርመሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ ወይም ተወልዶ የተገኘ ጥጃ በቂ መድኅን እንዳገኘ የሚያጣራበት የደም መመርመሪያ ኣስፈላጊ ሆኖ ስለኣገኙት ኣዲስ የምርመራ ዘዴዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ፈጠሩለት። ኢምዩኖግሎቡሊን የሚባል ኣካል እራሱን የሚከላከልበት ፕሮቲን በብቃት መኖር ኣስፈላጊ ስለሆነ መ’መ’ርመር ኣለበት በማለት ኣዲስ ኣስተሳሰብ ከማስተዋውቅ ሌላ ለእንገርና ደም ቀላል መመዘኛዎች ፈጠሩ። በቂ የመከላከያ ፕሮቲን የኣለውን እንገር መጋት ፈውስ እንደሆነ በሳይንስ መጽሔቶችም ኣቀረቡ።  የኣጋጋት ቪድዮዎች እዚህ ኣሉ።       በዘዴው እየተጠቀሙ የኣሉት ቀስ በቀስ እየጨመሩ ስለሆነ በእየዓመቱ ብዙ ሚሊዮን ሕይወት ማዳን ቀጥሏል።    በኣሁኑ ጊዜ የዶክተሩን ግኝት በመከተል በተለይ የዩናይትድ እስቴትስ ትላልቅ እርሻዎች ውስጥ ለእየኣንድኣንዱ ጥጃ እንደተወለደ በቱቦው እንገር ይሰጣል።   
    የእንገር ጥቅም በምርምር ከተረጋገጠበት እ.ኤ.ኣ. 1922 ወዲህ  በመስኩ ትልቅ ኣስተዋጽዖ የዶክተሩ የ1977 ምርምራዊ ሥራ    ሳይሆን ኣይቀርም። ምክንያቱም የእንገር ጥቅሙ ቢታወቅም ሁሉም ጥጃዎች እንዲያገኙት ስለኣልተቻለ ችግሩ ቀጥሎ ነበር።  
      ከዶክተሩ ምርምር በፊት ጥጆች ሳር መቀንጠስ እስኪጀምሩ ድረስ ጨጓራ ስለማይሠራ በስሕተት እንኳን እንገር እዚያ ቢገባ ይጎዳቸዋል የሚባል ኣጉል እምነት በዓለም ላይ ነበር። ኣሜሪካ 65,000 የእንስሳት ሓኪሞችና 92 ሚሊዮን የቀንድ ከብቶች ኣሏት።  የዶክተሩ ዘዴ ለተለያዩ ለማዳና የዱር እንስሳት ጥቅም ላይ መዋሉ ለኣርባ ዓመታት እያደገ ቀጥሏል። ዩናይትድ እስቴትስ ውስጥ በእየዓመቱ ከሚወለዱት 40 ሚሊዮን ጥጃዎች 4 ሚሊዮን የሚሆኑት በመድኅን ማነስ ሊሞቱ ይችሉ የነበሩት በዶክተሩ ግኝት በኣለፉት ኣርባ ዓመታት ሊተርፉ ችለዋል። በተጨማሪም ፵ በመቶ ጥጃዎች ሕክምና እንዳያስፈልጋቸው ሆኗል። በዓለም ላይ የኣሉ የቀንድ ከብቶች ኣንድ ቢሊዮን ስለሆኑ ቢያንስ ኣሥር በመቶ በዘዴያቸው ቢተርፍ ግምቱን ማስላት ይቻላል።  

ሌላው በረከታቸው ኣዲስ የሕክምና ዘዴ ሓኪሞችና ገበሬዎች እንዲጠቀሙባቸው የቱቦዎቹን ቀላልና ቀልጣፋ የሕክምና መንገድ ወይም ኣሰጣጥ (ጨጓራ ስለሚሠራ) (New medical route) ማግኘታቸው ነው። ከዶክተሩ ግኝት በፊት ጥጆች ሲታመሙ ሓኪም ቤት ተወስደው መድኃኒት የሚሰጣችው በመርፌ ነበር። በዶክተሩ ግኝት የተነሳ ገበሬው በቱቦው መድኃኒትና ፈሳሽ መስጠት ስለሚችል ወጪና ጊዜ ተቆጥበዋል።  

ዶክተሩ የመድኅንን ማነስ በማስወገድ ከዓለም የእንስሳት ሓኪሞች ኣንዱ ታዋቂ ምሁር ናቸው። የግዕዝ ፊደል በኮምፕዩተርና የእጅ ስልክ ውስጥ በኣለውም መጠቀም እንዲቻል የፈጠሩ ሊቅና የኣክሱም ሓውልት ከሮም ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ ጣልያንን በማስፈራራት ወሳኙን እርምጃ የወሰዱ ኣርበኛ ናቸው።  ከእዚሁ ጋር የተያያዘ በኮምፕዩተር ኣዳዲስ ኣከታተቦችን፣ የፊደል ኣመዳደቦችና ገበታዎች ፈጥረዋል። ኮምፕዩተራይዝ የኣደረጉት ፊደላቸውም የዩኒኮድ ፊደል ሆኗል። በተጨማሪም በሳይንቲስትነት፣ ተመራማሪነትና ሥራ ፈጣሪነት ለኣበረከቱት ዕውቅና የምንሰጠው በታላቅ ኩራት ነው። የኣበረከትነውም ዕውቅና በማሕበረሰቡ የዲሬክተሮች ቦርድና በሁሉም ኢትዮጵያውያን ስም ወሰን ከሌለው ምስጋና፣ ፍቅርና ኣድናቆት ጋር ነው።  የኢትዮጵያ ቅርስና ውርስ ማሕበረሰብ በሰሜን ኣሜሪካ ዶክተሩን የበዓሉም የክብር እንግዳ ኣድርጓል። ከእዚህ በላይ የቀረበውን የተናገሩት የኢትዮጵያ ቅርስና ውርስ ማሕበረሰብ በሰሜን ኣሜሪካ ፕሬዚደንት ኣቶ የሺጥላ ኣርኣያ ድርጅቱ ሰባተኛውን ዓመታዊ በዓል ኅዳር ፲ ቀን ፳፻፲ ዓ.ም.  ሲልቨር እስፕሪንግ፣ ሜሪላንድ ሲያከብር ስለዶክተሩ የተናገሩት ነበር።  

ጥጆች ወተት ሲጠቡ ወተቱ ትንሽ ይዘት የኣለው ወተት ኣንጀት ውስጥ በቀጥታ ስለሚገባ ወደ ሦስት ሳምንታት እድሜ ሞልቷቸው ሳር መቀንጠስ እስከሚጀምሩ ድረስ ጨጓራ (Rumen)፣ ኣይነበጎ (Reticulum) እና ሽንፍላ (Omasum) ሥራቸውን ኣይሠሩም የሚል እምነት በዓለም ስለነበረ ኣልጠባ ያሉትን እስቶማክ ቲዩብ በሚባል ቱቦ መጋትም ኣይጠቅምም የሚባል እምነት ነበር። ምክንያቱም እንቦሳዎች ወተት ሲጠቡ በተፈጥሮ ኢሶፋጂያል ግሩቭ የሚባል የጉሮሮ እጥፋት በኩል ወተቱ በኣቋራጭ ከጉሮሮ ወደ ወተት ኣንጀት (Abomasum) ስለሚገባ ነው።   በኣፍ በሚገባ የጨጓራ ቱቦ ውስጥ በደቂቃ ጨጓራ ውስጥ የተንቆረቆረ ኣንድ ጋለን ያህል እንገር ወደ ኣንጀት ሄዶ ደም እንደሚገባ በምርምር በማረጋገጥ በመድኅን ማነስ (ፓሲቭ ኢምዩን ደፊሸንሲ / Passive Immune Deficiency) መነሻነት ሲከሰቱ የነበሩ ችግሮች (እ.ኤ.ኣ. በ፲፱፻፳፪ ቢደረስበትም)  በዶ/ር ኣበራ ሞላ ለመጀመሪያ ጊዜ እ.ኤ.ኣ. በ፲፱፻፸፯ ተወግደዋል። መረጃውም 182 ገጾች በኣለው መጽሓፋቸው በእንግሊዝኛ ቀርቧል።       ከእዚያም ወዲህ ምርምራቸው በሌሎች ምርምሮች ተረጋግጠዋል።            በእዚህ የተነሳ እንገር (Colostrum) ባለማግኘት ሊሞቱና ሊታመሙ የሚችሉትን እስቶማክ ቲዩብ ወይም ኤሶፋጊያል ቲዩብ በሚባሉ ቱቦዎች በመጠቀም እንገሩን ጥጃው እንደተወለደ በመስጠት ሕይወቱን ማዳን ተችሏል።  እንቦሳውም እንገሩን ቶሎ ከኣላገኘ ጀርሞችም ከሆድ እቃ በቀጥታ ወደ ደም ስለሚገቡ ኣደጋው ስለሚጨምር እንገሩን ጥጃው እንደተወለደ ከኣላገኘ ወደ ደም መግባቱም ቀስ በቀስ ስለሚቀር ጊዜና የእንገሩ መጠን ወሳኞች ናቸው። የእንቦሳ ጨጓራ እንደሚሠራ ለመጀመሪያ ጊዜ በማረጋገጥ የጥጃውን ትብብር ሳይጠይቅ በምርምራቸው የእንገር መጠንንና ጊዜውን ሰው እንዲወስን ሆነ። ስለዚህ ኣልጠባ ያለን ጥጃ ዝም ብሎ መመልከትና መበሳጨት ቀርቶ ወተት ኣንጀት የማይችለውን እንገር ጨጓራ ውስጥ በማስቀመጥ ጥጃው እራሱን እንዲረዳ ኣደረጉ። ከብዙ ላሞች ተሰብስቦ ተደባልቆ የተፈረዘ እንገር በክብደት መጠን እየተለካ በቱቦ በኣንድ ደቂቃ ለጥጆች እንደተወልዱ የተሰጠው ኣንድ ጋለን ያህል እንገር በ፳፬ ሰዓታት ውስጥ በቂ መድኅን ደሙ ውስጥ እንዳስገኘና እንገሩን በፈቃዳቸው እያረፉ ብዙ ሰዓታት ሳይፈጁ ከጠቡት ጋር እኩል መሆኑን ኣረጋገጡ። የዶ/ር ኣበራ የምርምርው ውጤት ትልቅ ፈውስ ሊሆን የቻለው ጊዜ፣ ይዘትና መጠንን በኣንዴ በማካተት ስለገላገለ ነው።  የጊዜ ጥቅም ጥጃው እንደተወለደ የተሰጠውን ወደ ደሙ ስለሚያስገባ ሲሆን በእዚህ ጊዜም ወደ ደም እንደመድኅኑ የሚገቡትን ጀርሞች ለመቅደምም ነው። እንገሩም ከኣንጀት ወደ ደም የሚገባው ጥጆች እንደተወዱ ሲሆን ቀስ በቀስ እየቀነሰ በ24 ሰዓታት ውስጥ መተላለፉ ይዘጋበታል። በቱቦው ወደ ጋለን እንገር መስጠት ስለሚቻል በቂ መድኅን እንደተወለዱ መስጠቱ የበሽታ መከላከዎች በብዛት ወደ ደም ስለሚገቡ ነው።  ስለዚህ ጥጃው እንደተወለደ መስጠቱ እንጂ መቆየቱ እንገር ማባከን ነው። ጥጃው ቢጠባም ወተት ኣንጀት በቂ ይዘት ስለሌለው የሚፈለገውን ያህል ሊጠባም ስለማይችል ጨጓራ እንደሚሠራ ስለኣረጋገጡ ኣንድ ጋለን እንደተወለደ በቱቦው መስጠት ስለቻሉ እንገሩ ውስጥ በቂ የመድኅን መጠን እንዳለ የሚጣራበት ኣስፈላጊ ነው በማለት ቀላል የምርመራ ዘዴ ለመጀመሪያ ጊዜ ፈጠሩ። ምክንያቱም የሁሉም ላሞች እንገር የበሽታ መከላከያ ፕሮቲኖች መጠን እኩል ስለኣልሆነ ነው። በተጨማሪም ሬፍራክቶሜትር የሚባል መሣሪያ የእንገርን መድኅን መጠን ለመገመት እንደሚጠቅም የምርመራ ጽሑፍ ጻፉ።     ግን ኣንድ ጥጃ በቂ መድኅን የሚኖረው እንደተወለደ ኣንድ ጋለን እንገር ስለኣገኘ ብቻ ሳይሆን በቂ ኢምዩኖግሎቡሊን ስለኣገኘ ስለሆነ እንገሩ ውስጥ በቂ እንዳለ ገበሬው ከላሟ ሳይለይ በኣንድ ደቂቃ እንገሩን መርምሮ የሚያጣራበት የምርመራ ዘዴ ፈጥረውና ኣስፈላጊነት ኣስተዋወቁ። የሥጋ ላሞች ግን ስለማይታለቡ ያንኑ የምርመራ ዘዴ የጥጆችን ደም በመውሰድ ገበሬው ሜዳ እንዳለ በኣንድ ደቂቃ ጥጃው በቂ መድኅን እንዳገኘ እንዲያጣራና ከኣላገኘ ቱቦውን በመጠቀም ማረም እንደሚቻል ኣቀረቡ። እንገሩን በሚገባ ለመጠቀም በኣካባቢው ለኣሉት በሽታዎች ላሞቹን በመክተብ ጥጆቹ ትክክለኛ መከላከያውን ከእንገሩ ያገኛሉ። (ዶክተሩ በተለይ የቫይረስ በሽታዎች ኣዳዲስና የተለመዱ መክተቢያዎችን የመሥራት የብዙ ዓመታት ልምድ ኣላቸው።)  የምርምር ውጤቶቻቸውም ጥቅም በሌሎች ሲረጋገጡ ኣርባ ዓመታት ሊሞሉ ነው።            
 
እዚህ ላይ ሊታወቅ የሚገባው ግን መድኅን ስለሌለ የግዴታ ይሞ'ታል ማለት ኣለመሆኑንና (ኤድስ ያለበት ሁሉ እንደማይሞት ዓይነት) ሲጠባ የታየ ጥጃ ሁሉ በቂ መድኅን ኣገኘ ማለት ኣለመሆኑን ነው። የእንገሩ ጥቅም በኣካባቢው ቆሻሻነት፣ ጥጆቹ ጀርሞቹን ስለሚበሉና የበሽታዎች መኖር ናቸው። ሲጠባ የታየም ይሁን ያልታየ ጥጃ ጊዜ እንዳያልፍበት ደሙን በመመርመር የመድኅኑ መጠን እንዲጣራበት የእንገር መድኅን መመርመሪያ ኣዲሱን ዘዴያቸው ለጥጃውም ደም መመርመሪያ እንዲያገለግል ኣደረጉ።  ምርመራዎቹም ኣስፈላጊ ሆነው ስለኣገኙዋቸው መፍትሔውን ፈጥረው ኣቀረቡ። ስለ ምርምር፣ ግኝቶቻቸውና ኣስተዋጽዖ ከታዋቂ የዓለም የእንስሳት ሓኪሞች ኣንዱ ከመሆናቸውም ሌላ     በሽታን መከላከል ሲቻል በማከም ብቻ ስለማያምኑም የኣሜሪካና እንግሊዝ ፓተንቶች (የባለቤትነት መታወቂያ) ኣግኝተዋል። የግኝቶቻቸው ጥቅሞች  እዚህ በተጠቃቀሱት የተወሰኑ ኣይደሉም፦ ምሳሌ 4,501,816 ፓተንታቸው ሌሎች ፓተንቶችን ጠቅሟል።   በዶ/ር ኣበራ የምርምር ውጤት ዘዴ የተነሳ በኣሁኑ ጊዜ እየኣንድኣንዱ ጥጃ እንደተወለደ እንገር በቱቦው የሚሰጠው ትላላቅ እርሻዎች ውስጥ ብቻ ኣይደለም።  
 
      ብዙ ትላልቅ እርሻዎች ውስጥ ጥጆች በተወለዱ በሁለት ሰዓታት ውስጥ የሆድ ቱቦን በመጠቀም እንገር ይሰጣቸዋል።  
 የእንገር ብዛት ብቻ ሳይሆን ጥራቱንም ማወቅ ኣስፈላጊ ሆኖ ስለኣገኙት መመርመሪያ ዘዴ ፈጥረውለት ዘዴውም ወደ መሣሪያ ተቀይሮ የእንገርን ኢምዩኖግሎቡሊን መጠን መገመት የገበሬዎች የዘወትር ሥራ ሆኗል። እንገር ሌሎች ጥቅሞችም ኣሉት። ለምሳሌ ያህል እንደተወለዱ በቂ መድኅን የኣገኙ ጥጆች ሲያድጉ ብዙ ወተት ይሰጣሉ።  ኣሜሪካ ውስጥ ብቻ በእየዓመቱ ወደ 39 ሚሊዮን ጥጆች ስለሚወለዱ  የተለያዩ እንስሳት ሳይቆጠሩ   ምን ያህል ሕይወት እንደተረፈ ግምቱን ለኣንባቢ መተው ይሻላል። የዶክተሩን ዘዴ ዓለም እየተጠቀመበት   ኣሜሪካ ውስጥ ብቻ ብዙ ቢሊየን ዶላሮች ሲይስተርፉ ኣርባ ዓመታት ሊሞሉ ነው።  የኣንድ ጥጃ ዋጋ 70 ፓውንድ ቢሆንና በየዓመቱ በዓለም ላይ የሚያልቁትን ጥጃዎች ብቻ መቶ ሚሊዮን በማትረፍ የዶ/ሩ ምርምር ሥራ ዋጋ በኣለፉት 40 ዓመታት ብዙ ቢሊዮን ነው።   ሌላ ምሳሌ ለመጥቀስም ያህል የእንገር መድኅን መጠን ሬፍራክቶሜትር (Refractometer) በሚባል መሣሪያ መገመት እንደሚቻል የጻፉትም  ከ፴፮ ዓመታት በኋላ ዋቢ እየሆነና መጥቀሙ ነው።            ዘዴዎቻቸውም እንደኣስፈላጊነታቸው ለተለያዩ ለማዳና የዱር እንስሳት ጥቅም ሥራ ላይ እየዋሉ ናቸው። ዶክተሩ በተማሩበት የሕክምና መስክ ብዙ ሚሊዮኖች ሕይወቶች ማትረፍ ስለቻሉ ፈጣሪናን የረዷቸውን ያልረሱ ደስተኛ ናቸው። የላም እንገር ለሰው ሕክምናም እየጠቀመ ነው።  

የምርምር ግኝታቸውም ጥጆች ሲታመሙም ኣዲስ የመድኃኒት፣ ምግብና ፈሳሽ መስጫ ዘዴ ሆኖ ተገኝቷል።  ለምሳሌ ያህል የእንቦሳ ተቅማጥ እንደ ስው ኮለራ (Cholera) ብዙ ጥቃት የሚያደርሰው ከኣካል ውስጥ ውሃ እየተመጠጠ ስለሚያልቅ ስለሆነ ውሃውን ለመተካት ጥጆቹን ሓኪም ቤት መውሰድና ማሳከም ገበሬውን ብዙ ወጪ ያስወጣ ነበር። ከዶክተሩ ግኝት በኋላ ግን ትክክለኛውን የጨውና ስኳር መጠን ያለውን ንፁህ ውሃውን በቱቦው ማጠጣት ስለሚቻል ወጪ ቀንሷል።    ዶክተሩ ለሕክምና ሞያቸው  ካበረከቷቸው ኣንዱ ይኸን ኣዲስ የሕክምና ዘዴ ማቅረባቸው ነው። ከእዚያም ወዲህ ጥቅሙ ቢጋነንም  የእንገር ንግድ ኣዳዲስ የዓለም ገበሬዎችና ኣምራቾቹ የገቢ ምንጭና የመድኅን የሕክምና ዘዴ ከመሆኑ ሌላ የሰው እናት እንገርና ወተትም ኣጠቃቀምም ተሻሽሏል።    የምርምር ውጤታቸውም ጤናማ እንስሳትን ለማሳደግ መራዳትና  ሓኪሞችንም ከመጥቀም ሌላ   ለሌሎች እንስሳትም ሥራ ላይ ውሏል። ምሳሌ -         

እንግሊዝን የ፲፮ ቢሊዮን ዶላር ያካሰረውን የላም ጉንፋን ወረርሽኝ (Foot-and-mouth-disease) ከኣስቆሙትና ከኣጠፉት ኣንዱ በመሆናቸው ዶክተሩ  ሁለት የጀግንነት ሽልማት ከዩናይትድ እስቴትስ መንግሥት ተሰጥቷቸዋል።  በሽታው ኢትዮጵያ ውስጥ ኣለ።   ኢትዮጵያውያን ሥጋ ለውጭ ኣገሮች በመሸጥ ብቻ ብዙ ቢሊዮን ብር ገቢ ሊያገኙ ስለሚችሉ መጀመሪያ ኣደገኛ የእንስሳት በሽታዎችን ማጥፋት ይጠበቅባቸዋል።   እንደ በሽታውም ዓይነት ክትባት ትልቅ መሣሪያ ነው። የሰው ልጅ በመተባበር የሰውን ፈንጣጣ (Smallpox) እና የቀንድ ከብትን ደስታ (Rinderpest) በሽታዎች ክትባትን በዋናነት በመጠቀም ከዓለም ኣጥፍቷል። ዶ/ር ኣበራ ኣዳዲስና የተለመዱ ክትባቶችን ኣምርተዋል፦ Equine Encephalitis , Equine Influenza , IBR  Vesicular Stomatitis , BVD   Orf  ጥቂት ምሳሌዎች ናቸው። የወፍ ኢንፍሉኤንዛና የመሳሰሉ በሽታዎች ሕዝቡ በሚገባ ማወቅና መዘጋጀት ይኖርበታል።  

ኤድስ (Acquired Immune Deficiency Syndrome / AIDS / ኣኳየርድ ኢምዩን ደፊሸንሲ ሲይንድሮም) በዓለም ላይ መሰራጨት እንደጀመረ ኤችኣይቪ (Human Immunodeficiency Virus)ን ክትባት እንደማይከላከለው በጊዜው ከሚያውቁት ሳይንቲስቶችና የበሽታ መከላከያ ክትባት ሠሪዎች ኣንዱ በመሆናቸው በሽታው ኢትዮጵያ ውስጥ ሊያስከትል ከሚችለው ጉዳት ለመከላከል ሕዝቡን ለማስተማር ባለ ኣራት ገጾች የመጀመሪያው የሆነውን ገለጻ በዓማርኛ ስለ ኤድስ በ፲፱፻፹፩ ዓ.ም. ተርጕመው  እና ጽፈው   በገዛ ገንዘባቸው እያባዙና እየኣደሉ ቆይተው በኋላም በኢትዮጵያ ሪቪው መጽሔት ኣትመዋል። በእዚያን ጊዜ ስለ ግብረሥጋ ግንኙነትና ኮንዶም የሚጠቅሰውና እንዲሁም የታመሙትን መርዳት ይገባል የሚለው ጽሑፋቸው ከጊዜው ደካማ ኣስተሳሰብ የቀደመ ስለሆነ ተገቢውን ተቀባይነት ሳያገኝ ቸል ተብሎ የታለፈበት ጊዜ ስለነበረ በሽታውን በምርምር በተረጋገጡ ዕውቀትና ትምህርት መከላከል  ስለኣልተቻለ ከፍተኛ ጉዳት ኣድርሷል። ይኸንኑ ጽሑፍ ሕዝቡ እንዲያነብበት GeezEdit Amharic P  የሚባል የኮምፕዩተር ፊደላቸውን በ፲፱፻፹፯ ዓ.ም. በነፃ የሰጡት ስጦታ ኣሁንም ኢንተርኔት ላይ ስለኣለ ኣንዳንዶቹ ኣልደረሱበትም እንጂ ደርሰውላቸው ነበር። ጽሑፉ ሲጻፍ ኤች ኣይ ቪ ቫይረስ የተገኘባቸው የዓለም ሕዝቦች ኣንድ ሚሊዮን ሆኖ ሳለ እስካሁን በበሽታው ሳቢያ የሞቱ ሰዎች ቍጥር ፴፮ ሚሊዮን ደርሷል።  በ፳፻፰ ዓ.ም. 36 ሚሊዮን ያህል ሕዝቦች ቫይረሱ ኣለባቸው። 

ሰሞኑን ኃምሳ ሁለት ከመቶ ዩናይትድ እስቴትስ ውስጥ የኣሉ ኢትዮጵያውያን ኤድስ ኣለባቸው የሚባል ወሬ እየተናፈሰ ነበር።  ለምሳሌ ያህል መቶ ሰዎች ተመርምረው ኃምሳ ሁለቱ ኢትዮጵያውያን ውስጥ ኤድስ ቢኖርባቸው ዩናይትድ እስቴትስ ከኣለው ወደ ሚሊዮን ከሚጠጋ ሕዝብ ኣምስት መቶ ሃያ ሺህው ኤድስ ኣለው ማለት ኣይደለም። እነዚህ ሁለቱ ኣነጋገሮች የተለያዩ ናቸው። የወሬው ትክክል ኣለመሆንና መረጃው ከዶ/ር ገበየሁ ተፈሪ ጋር በምናላቸው ስማቸው ቃለምልልስ እዚህ ቀርቧል።   ኣንድ ሌላ ትንሽ ጥናትም እንደሚያሳየው ኢትዮጵያ ውስጥ ቫይረሱ ከተገኘባቸው መካከል ከመቶው 28 እንዳለባቸው ኣያውቁም።  ይህ ከመቶ 28 ኢትዮጵያውያን ውስጥ ቫይረሱ ኣለባቸው  ማለት ኣይደለም።

ከቅርብ በረከትም በግዕዝኤዲት ኦንላይን (Free Typing GeezEdit Amharic Online) 
GeezEdit, ዓማርኛ  ሕዝቡ በነፃ በዓማርኛ ዊንዶውስ እና ማክ ኮምፕዩተሮች ውስጥ መጻፍና የዓለም ድረገጾችንና የመሳሰሉትን (ኢንተርኔት) በዓማርኛ መፈለግ እንዲችል ኣበርክተዋል። (Amharic) ፣ ጉግል በዓማርኛና እንግሊዝኛ፣   ያሁ እና ቢንግ በዓማርኛ መፈለጊያም ይገኙብታል።  ቪድዮም እዚህ ኣለ።  እነዚህ የኣንድ ሰው ብቻ ሥራዎች ስለኣልሆኑ ለሚመለከታቸው ሁሉ ምስጋና ይድረስልን። 

የድረገጹ ፩ኛ ጥቅም ሌላ መክተቢያና እንደ ማይክሮሶፍት ወርድ  ወይም ፔጅስ  የመሳሰሉ ፕሮግራሞችን (ተጠቃሚው ተመዝግቦ እየኣንድኣንዱን 
በብዙ ሺህ ብር መግዛት ስለማይችል በእራሱ ፊደል መጠቀም እንዳይቸግረው) ኣማራጭ በማበርከት በዊንዶውስ እና ማክ ኮምፕዩተሮች በዓማርኛ ለመጻፍ ነው። ከእዚያ ጽሑፉ ኮፒ ተደርጎ ሌላ ሥፍራ ይለጠፋል።  የግዕዝ ፊደል ተጠቃሚዎች ጽሑፎቻችንንና የመሳሰሉትን ወደ ኢንተርኔት ማስገባትና እነዚህኑ ፈልገን ማግኘት ካልቻልን የሚከተለው ኋላ ቀርነት ቀላል ላይሆን ይችላል። ፪ኛው ኢንተርኔትን በዓማርኛና እንግሊዝኛ ወይም ቀላቅሎ ለመፈለግ በኮምፕዩተር ያገኘነውን ኣዲስ ኣጠቃቀም በሚገባ እንድንጠቀምበት ነው። ይህ ቃላትን ጽሑፍ ውስጥ ለመፈለግና ለመተካትም ይጠቅማል። ሕዝቡ በቀላሉ መጻፍ ስለሚችል በሰለጠነበት የጽሑፍ ኣሠራር እንዲቀጥሉ ሲሆን ፫ኛው ጥቅም ኣንድ የዓማርኛ ጽሑፍ በቀለሙ የተጻፈ መሆኑን ለማረጋገጥና እንደኣስፈላጊነቱ ለማረም ነው። በግዕዝ ቀለም ያልተጻፈ ጽሑፍ ኮፒ ተደርጎ ገጹ ላይ ሲለጠፍ ዝብርቅርቅ እንግሊዝኛ ሆኖ ይታያል። ፬ተኛ ጥቅም ኣንዳንድ ምሁራን እንደ “ዝሆን”፣ “ኣኣ”፣ “ክኅሎት”፣ “ድድ የመሳሰሉትን የዓማርኛ ቃላት የማያስጽፉ ድረገጾችንና የመሳሰሉትን ለመጻፊያ ከማቅረብ እንዲቆጠቡ ነው። ኣንዳንዶቹ “ኵ”ን ኣጥፍተው በ“ክው” እንደ እንግሊዝኛ እስፔሊንግ መክተብና ወጪ መጨመር ቢፈልጉም “ኵ”ን መጻፍ የማይችሉ ኣሉ። ሥዕልን በሥእል መተካትም ችግር ኣለው። ከእነዚሁ መካከል የእነ “ሐ” እና “ኀ” ቤቶች ቀለሞችን የ“ሀ” ሞክሼዎች ስለሆኑ መቀነስ እየፈለጉ ኣንዳንዶቹ “ትህትና”፣ “ትስስር”፣ “ግግር” እና “ትዝታ” የመሳሰሉትን ቃላት መክተብ ስለማይችሉ ዓማርኛውን በእንግሊዝኛ ለመክተብ ሲባል ቃላቱን ማጥፋት ይፈልጋሉ። እነዚህ ምሳሌዎች ያለተቃውሞ ለብዙ ዓመታት ኣሉ። ይህ ገጹን እየተጠቀሙ የኣሉ ኢትዮጵያውያን ምሁራን ለዓማርኛ ፊደልና ቋንቋ መጥፋት ደንታ እንደሌላቸው የሚያሳይ ኣሳፋሪ መረጃ ነው። ኣንዳንዶቹ ግዕዝኤዲት በሁለት መርገጫዎች የሚያስከትበውን “ስስ” ቃል የሚከትቡት በሰባት መርገጫዎች ሲሆን “ፄ” ቀለምን ለመክተብ እስፔሊንጉን ማስታወስና ስድስት መርገጫዎች መጠቀም ቢያስፈልግም ሁሉንም የዓማርኛ ፊደላት ባዶ ስፍራ እየጨመሩ እንኳን ኣያስከትቡም። ዓማርኛውን መክተብ ሳይችሉ ሌሎች ቋንቋዎችን የጨመሩ ኣሉ። ምክንያቱም ከግዕዝ ቋንቋ ቀለሞች በሰተቀር ሌሎቹ ከዓማርኛው ቀለሞች በላይ ብዛት ስለኣላቸው ነው። ግዕዝ በዩኒኮድ ዕውቅና እንዳገኘ እያወቁ ዛሬም በእየዓይነቱ የፊደል ቁርጥራጭ የሚያቀርቡም ኣሉ።

፭ተኛው ጥቅም ሞክሼዎችን የማይወዱ ደራስያን ከሚወዷቸው ጋር እያምታቱ በተገኘው እንዳይጠቀሙ ይራዳል። “ሀ” የ“ሃ” እንዲሁም “አ” የ“ኣ” ሞክሼዎች የሚመስሏቸው ኣሉ። “ኳ” እራሱን የቻለ ሞክሼ የሌለው ቀለም ነውና ጊዜና ስፍራ ማባከን ስለሆነ በ“ኩዋ” ወይም “ክዋ” መዘርዘርም ፊደል ለመቀነስ በታይፕ መጻፊያ ዘመን በኣማራጭነት የቀረበና ያኔም ቢሆን ተቀባይነት የኣላገኘ ኣሁንም ቢሆን ጊዜው ያለፈበት ኋላ ቀር ኣስተሳሰብና የማያስፈልግ ግድፈት ነው። የዓማርኛ የጽሕፈት መኪና “ኳ”ን ሲከትብ የነበረው “ካ” ቀኝ እግር ስር መሥመር በመጨመር በኣሌለና የተሳሳተ ቀለም በመጠቀም ነበር። የዓማርኛ የጽሕፈት መኪና “ቋ”ን ሲከትብ የነበረው “ቀ” እግር ስር መሥመር በመጨመር በኣሌለና የተሳሳተ ቀለም በመጠቀም ነበር። ፮. በነፃ እየታደሉ በኣሉ የማያዛልቁ ኣከታተቦች ሕዝብ መታለሉ እንዳይቀጥልና እየተነገረውም እነዚያን ለምዶ በኋላ በትክክለኛ ሳይንሳዊ ኣከታተብ መጠቀም ተቸገርኩ እንዳይል ግዕዝኤዲት ይራዳል። ምክንያቱም በተገኘው መክተቢያ ተምሮ በኋላ በግዕዝኤዲት ለመሥራት ሲሞከር ሌላውን ኣጠቃቀም ለመተው ኣስቸጋሪ ስለሚሆንና ምንም ዓይነት ኣከታተብ ለማያውቅ ግዕዝኤዲትን መማር ቀላል ስለሆነ ነው። በተጨማሪም ዓማርኛውን በቍልፎቹ ብቻ መክተብ ስለኣልቻሉ ቀለሞቹን ከ“ሀ” እስከ “ፖ” ደርድረው በማውስ ቀስት በመጠቆም እንዲከተቡ ማድረግ ኣያስፈልግም። ፯. ዓማርኛውን በላቲን ቀለሞች መክተብ ኣስፈላጊ ሳይሆን በተገኘው የእንግሊዝኛ እስፔሊንግ እየጻፉ ያሉትን ኣንዳንድ ጉራማይሌ ምሁራን በሚገባ በሚያውቁት ዓማርኛ ፊደልና ቋንቋቸው እንዲጽፉና እንዲያነቡ ያገለግላል። እንግሊዝኛ እስፔሊንግ ከባድ ነገር በመሆኑ ዓማርኛ እንግሊዝኛውን ሊጠቅም ስለሚችል በእንግሊዝኛ ማድበስበስ የለብንም።  ግዕዝ ድምፃዊ ፊደል ስለሆነ ለመነበብም ሆነ ለመከተብ እስፔሊንግ ስለማያስፈልገው ሕዝቡ ዓማርኛውን በላቲን እስፔሊንግ እንዲከትብ በብዙ መርገጫዎች ማስቀጥቀጥም ሳይስፋፋ ዓማርኛውን በዓማርኛ ፊደል ለመክተብ ግዕዝኤዲት ይጠቅማል። ለምሳሌ ይህል “ያመት” የሚለውን ቃል በ“yamet” እየጻፉ እንግለዝኛ ቃሉ በማወስ ቀስት እንዲመረጥ ወይም የባዶ ስፍራ ቍልፍ ሲነካ እንግሊዝኛውን ወደ ኣማርኛ በመቀየር “ያመት”ን እንድንጽፍ የሚገልጉ ፈረንጆች ኣሉ። እነሱ እንግሊዝኛውን የሚጽፉት ከኣንዱ ፊደል ወደ ሌላ በመቀየር ወይም ቃላትን በማውስ ቀስት በመልቀም ስለኣልሆነ ለዓማርኛ ተጠቃሚው እንዳልተጨነቁ ያሳያል። የ“ጰ” የዓማርኛ Latin (ቁቤ) ኣነባበብና ኣከታተብ ካፒታል “ፒ” (P) ነው ሲባል ተከርሞ    በቅርቡ ወደ “ፒ” (“p”) እና ነቍጥ (“.”) ተቀይሯል ይባላል። ቴክኖሎጂውን ለዓማርኛ መፍጠር እንጂ ዓማርኛውን ለቴክኖሎጂው ኣያስፈልግም። ለላቲን ከተሠራ ቴክኖሎጂ ጋር እንዲሄድና በዓማርኛው ኪሳራ ላቲኑን ለማዳበር ሲሞከር የላቲን ተናጋሪዎች ባይናገሩ ባይገርምም የግዕዝ ፊደል ተጠቃሚዎች በዝምታ እንደማይቀበሉት ዶክተሩ ኣሳይተዋል። ፰. ግዕዝኤዲት የዓማርኛና እንግሊዝኛ መክተቢያ ነው።  ፈረንጆች ቋንቋዎቻቸውን በግዕዝ ፊደል እንዲከትቡ ኢትዮጵያውያን ኣልጠየቁም። ኢትዮጵያውያን ቋንቋዎቻቸውን በላቲን ፊደል እንዲከትቡ የሚፈልጉ ጥቂት ፈረንጆችና ኢትዮጵያውያን ግን ኣሉ። ኣንዳንድ ኢትዮጵያውያንም ነገር ስለተማታባቸው ቋንቋዎቹን መቀላቀልም ስለጀመሩ ዓማርኛውንም ሆነ እንግሊዝኛውን በሚገባ የማይናገርና የማይጽፍ ትውልድ እንዳይፈጥሩ ግዕዝኤዲት ይራዳል።  

፱. ኢትዮጵያ ለብዙ ሺህ ዘመናት ከነፃነትዋ ጋር ጠብቃ ያቆየቻቸው ቋንቋዎችዋና የተሟሉት ቀለምዎችዋ ዛሬም በእኩልነት እየኣንድኣንዱ ቀለምዋ በኣንድና ሁለት መርገጫዎች ብቻ እንዲከተብ ተደርጎ ተከባብሮና ተጋብቶ የኖረው ሕዝብ ፍላጎትና እኩልነት በኣብሻ ሥርዓት ቴክኖሎጂ ምሳሌ በግዕዝኤዲት ቀርቧል።  የኣንዳንዶቹን ኣንድ ቋንቋ ቀለሞች በኣራት መርገጫዎች የሌላውን በስድስት መክተብ ወይም እንደሌሉ መርሳት የለም። ፲. የምሁራንና ቴክኖሎጂ ፈጣሪዎች ሥራና ጥቅም ለኣለ ችግር መፍትሔ መፍጠር ነውና ዶ/ር ኣበራ ለእነዚያ የሚጠቅሙ ሠርተዋል። ኣንዳንድ የግዕዝ ተመራማሪዎች ግን በተሳሳተ ዓላማቸው ፊደሉ ለላቲን ፊደልና ገበታ እንዲስማማ መክተቢያ ሴራ መፍጠር ስለሆነ ግዕዝኤዲት ሳይንሳዊ ዓላማን በመሳት እንዳይቀጥሉ ትክክለኛውን ኣስተሳሰብ ያስገነዝባል። በቅርቡ ኣንድ የግኝታቸው ትክክለኛ ኣከታተብ የገባቸው ኢትዮጵያዊ “ዶ/ር አበራ ምሥጋና ይግባውና የአማርኛ ጽሑፍ ትየባ ፍጥነቴ ከእንግሊዝኛው አያንስም” በማለት ጽፈዋል። ፲፩. ግዕዝኤዲት በዓማርኛና እንግሊዝኛ ኣከታተብ ለመማር ይጠቅማል። በዓማርኛ በብዛት የምንጠቀምባቸው ቀለሞች ሳድሳን ስለሆኑ በኣንድ መርገጫ ይከተባሉ። ሳድሳን ዓማርኛ ጽሑፍ ውስጥ በብዛት ኣንደኛ ስለሆኑ ሳድሳንን በሁለት መርገጫዎች መክተብ በማያስፈልግ ድካም እራስን መበደል ነው። በብዛት ኣጠቃቀም ሁለተኛ የሆኑት ለሁለቱ ዝቅ መርገጫዎች ተመድበዋል። ለግዕዝ ተጠቃሚዎች ኢንተርኔት ላይ በነፃ ለመማርያ የቀረቡ እንግሊዝኛ ኣከታተብ መለማመጃዎችን በመጠቀም ያለኣስተማሪ በፍጥነት መክተብ መማር ይቻላል።  “አ”፣ “ሰ”፣ “ደ” እና “ፈ” በግራ እጅ ጣቶች “ጀ”፣ “ከ”፣ “ለ” እና “ጠ” በቀኝ እጅ ጣቶች ይከተባሉ። ምሳሌ     ፲፪. ዶ/ር ኣበራ ኮምፕዩተራይዝ ያደረጉትና የታገሉለት ግዕዝ በዩኒኮድ ዕውቅና ስለኣገኘ የዓማርኛ የጽሕፈት መኪና ቅጥልጥል ፊደል እንዲቀር ቢጻፍም ዓማርኛ ነው ብለው ሲያቀርቡ የነበሩና ዛሬም የሚያቀርቡ ኣሉ።  ግዕዝኤዲት የሚሠራው በትክክለኛ የግዕዝ ፊደላት ስለሆነ ልዩነቱን የማያውቁ እንዳይታለሉ ይጠቅማል። በትክክለኛ የግዕዝ ቀለሞች የተጻፉ ብዙ መጽሓፍት ምሳሌዎች እዚህ ኣሉ። 

፲፫. የግዕዝና ላቲን ኣከታተብ ግንኙነት የላቸውም። በጥቂት የላቲን ቀለሞች እስፔሊንግ ብዙ የሆኑትን የግዕዝ ቀለሞች መክተብ መሞከር ላቲኑን ለመጥቀም ወይም ግዕዝን ለማዳከም ካልሆነ ጥቅም የለውም። ግዕዙን በላቲን እስፔሊንግ መክተብ ኣለባችሁ ብሎ ኢትዮጵያውያንን ያስገደደ የለም። በላቲን “b” እና “o” ሲረገጡ “bo” ይታያሉ። በግዕዝ “bo” ሲረገጡ “ቦ” ቀለምን ሊያስከትቡ ይችላሉ። “bo” ማለት “ቦ” ኣይደለም። እንዲሁም “ቦ” “bo” ኣይደለም። በ”ቦ” ምትክ “bo” እየጻፉ የዓማርኛውን ቀለም ትተው ዓማርኛውን በላቲን ፊደል የሚጽፉ ተጠቃሚዎች ቍጥር እየጨመረ ነው።   ይህ የዓማርኛ ቁቤ (Qubee) ስለሆነ ፊደሉንና ቋንቋውን ሊያዳክማቸው ይችላል።    በዓማርኛ “ቾ”ን በሁለት መርገጫዎች ከመክተብ በ“cho” በሦስት መክተብ ኣያፈጥንም። ተጨማሪ ምሳሌ ከኣስፈለገ ኣንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ዓማርኛ በላቲን ፊደል እንዲጻፍና በኣጻጻፉም በግዕዝ ፊደል ምትክ በላቲን ፊደል ጽፎ ያቀረበው ጽሑፍ በዓማርኛው በዓማርኛና ዓማርኛው በእንግሊዝኛ እዚህ  ኣለ። ዓማርኛን በላቲን ፊደል መጻፍና ማንበብ በኣንድ በኩል ዓማርኛንና ፊደሉን ማዳከም ሲሆን በሌላ በኩል ደካማና ኣክሳሪ የላቲንን ፊደል በዓማርኛው ፊደል መተካትን ለማስፋፋት ይመስላል። ይኸን ኣጠቃቀም ዶክተሩ ከሚቃወሙባቸው ምክንያቶች መካከል ዓማርኛን በላቲን ቀለሞች መክተብ ከዓማርኛው ቀለሞች የበዙ ቀለሞችን መጠቀምን ስለሚያስከትል ነው። የላቲን እስፔሊንግ ለቃላት እንጂ የግዕዝን ፊደላት ለመክተብ ኣይደለም። “የኢትዮጵያ ዘመን ኣቆጣጠር” የሚለውን ርዕስ በ15 የግዕዝ ቀለሞች ማስፈር ሲቻል “yeityoPya yezemen aqoTaTer” በሚለው 28 መርገጫዎችን በመጠቀም በ24 የላቲን ቀለሞች መተካት ድርብርብ መካሰር ነው። (ይህ ዘዴ ባዶ ስፍራ ቃላት መካከል እያስገቡ በዓማርኛም ሆነ እንግሊዝኛ የሌለ ኣከታተብን ማስተዋወቅን ቢያስከትልም ይኸንን ኣከታተብ የሚደግፉና እያስፋፉ ያሉ ጥቂት ኣይደሉም።) ግዕዝኤዲት የሚከትበውም ከእዚያ በኣነሱ መርገጫዎች ነው። ሙሉ ጽሑፉን በላቲን ፊደል ከመጻፍ ይልቅ በዓማርኛ ፊደል ማስፈር ብዛቱን ወደ 64.7 በመቶ ዝቅ ያደርገዋል። ይህ ውጤት በደካማ ኣከታተብ ዓማርኛና እንግሊዝኛውን ፊደላት ስናወዳድር ነው። በግዕዝኤዲት ኣከታተብ ይኸው ጽሑፍ በዓማርኛ የሚከተበው በኣነሱ መርገጫዎች ስለሆነ ከኣብሻ ኣከታተብ የተሻለ ኣከታተብ በኣሁኑ ጊዜ የለም። ይህ ለዓማርኛው ሲሆን ሌሎች የግዕዝ ፊደላት ሲጨመሩ ለእስፔሊንጉ ተጨማሪ መርገጫዎች ለሌላው ዘዴ ስለሚያስፈልጉ ግዕዝኤዲት ተወዳዳሪ የለውም። ለምሳሌ ያህል በሌላ ዘዴው እስፔሊንግ የዓማርኛው “ፄ” የሚከተበው በስድስት መርገጫዎች ስለሆነ ለጉሙዙ “ጼ” መክተቢያ ስምንት መርገጫዎችን መጠቀም ያስፈልጋል። ስለዚህ ትርፉ እጅ ማሳመም ነው።  ግዕዝኤዲት የዓማርኛውን ሆነ የጉሙዙን የሚከትበው በሁለት መርገጫዎች ነው። በሁለት መርገጫዎች መከተብ የሚችልን ኣንድ የግዕዝ ቀለም ከሦስት እንከ ስምንት መርገጫዎች በመጠቀም መክተብ የዓለም መሳቂያና መሳለቂያ እንዳንሆን ያሰጋል። በትክክለኛ ኣከታተብ ላይ ያልተመረኰዙ ኣዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ኣገሪቷን ወደኋላ ሊጎትቱ ይችላል።  ፲፬. የተቆራረጡ የኣማርኛ የጽሕፈት መሣሪያ ዓይነት ቀለሞችንና ያልተቆራረጡ ኣንድ የላቲን ፊደል የሚችለውን ቀለሞች እየመረጡና በሌሎች ዘዴዎች ሕዝቡን ሲያጉላሉ ከነበሩት ይገላግላል። ፲፭. ላቲን ለቀለሞቹ መክተቢያ የማይጠቀምበትን ከግዕዝ መጠየቅ ኣያስፈልግም፦ ምሳሌ በማውስ መክተብ። ምክንያቱም ግዕዝኤዲት ባይኖር ኖሮ ግዕዝ ሌሎች ችግሮች ውስጥ ሊወድቅ ይችል እንደነበረ ከእዚህ በላይ የተዘረዘሩት ሊቀሰቅሱን ይገባል። በእዚህ በተራቀቀው የኮምፕዩተር ዘመን የግዕዝ ፊደል በሳይንስና ቴክኖሎጂ  ተደግፎ ማደግ ያለበት ጊዜ ነው። ለምሳሌ ያህል ነፃው የግዕዝኤዲት መክተቢያው ገጽ እንደሚሸጡት የዊንዶውስና የኣይፎን ኣከታተብ ዘዴዎች ቀላል ኣይደለም። ፲፮. ቴክኖሎጂውና ሳይንሱ ስለቀረበለት በተለይ ኣንዳኣዳንዱ ስለጉዳዩ በሚገባ ዓውቆ ኣልገባኝም ከእሚል የፊደሉን መብት እንዲያከብርና እንዲያስከብር ነው።

፲፯. የእንግሊዝኛው የቅውኽርትይ (QWERTY) የኮምፕዩተር የፊደል ገበታ ወደ እጅ ስልክ ዞሯል። የግዕዙም እንደዚያው በግዕዝኤዲት ቀርበዋል።  ኣዲስ ኣሠራር በእጅ ስልክ ማስተዋወቅ ስለተጀመር ሕዝቡ ሁለተኛ ዙር መታለል ውስጥ እንዳይገባ ግዕዝኤዲት ይራዳል። ፓተንት እየተጠበቀ ወይም Patent Pending የሚለው ማሳሰቢያ ነፃው ግዕዝኤዲት ላይ ያለውና እዚህም ስለሚሸጠው ዓይነት ገለጻም ውስጥ የተጠቀሰው ሌላ ሰው በተሰጠው ወይንም በተሸጠለት እንዲጠቀም እንጂ ዘዴውን መገልበጥ ትክክል እንዳልሆነና በሕጉ መሠረት እንደሚያስቀጣም ለማስጠንቀቅ ነው። የግኝታቸውን እንግሊዝኛ ገለጻ በቍጥሩ US20090179778  ወይም በሚከተለው ማያያዣ  ማግኘት ይቻላል። ግኝቱ መጀመሪያ የቀረበውና የኣተመው የዩናይት እስቴትስ መንግሥት ስለሆነ ከኢትዮጵያው ቅድሚያ ኣለው። ፲፰. የነፃ መክተቢያውን ፊደል ወደ እንግሊዝኛ ቀይሮ ለእንግሊዝኛ ቃላት ማቀነባበሪያም መጠቀም ይቻላል። ፲፱. ኢትዮጵያ የእራሳቸው የጥንት ፊደላት ከኣላቸው ጥቂት ኣገሮች ኣንዷ በመሆንዋ ይህ ለሕዝብዋ ትልቅ ኩራት ነው። ዋጋው ውድ ነው ተብሎ ሶፍትዌር በሕገወጥ የኮፕ ቅጂ መጠቀም ኢትዮጵያ ውስጥ ተስፋፍቷል ይባላል። ኣብዛኛው ኢትዮጵያዊ ልክ እንደእንግሊዝኛው ኮምፕዩተሩን የሚጠቀመብት ለተራ ጽሑፍ ነው። ሕዝቡ ኢንተርኔት እስከኣለው በነፃው ግዕዝኤዲት  መጠቀም ስለሚችል መኃይምነት ሊኖር ኣይገባም። ግዕዝኤዲት በነፃ በዶክተሩ ስለተሰጠ ሕዝቡ ስፍትዌርም ከኣልፈለገ መግዛት ስለሌለበት እንደኣንዳንዶቹ የኣልከፈለበትን ሶፍትዌር ማባዛት የለባቸውም። ምክንያቱም በዓማርኛ ለመጻፍ የሚያስፈልጉት ኮምፕዩተርና ኢንተርኔት ብቻ ስለሆኑ ነው።  ፳. በኣለፉት ጥቂት ዓመታት ኢትዮጵያን እየጎዱ የኣሉ ከመንደር ኣስተሳሰብ መላቀቅ ኣቅቷቸው የዶክተሩን ሥራዎች ማስተዋወቅ ሲገባቸው ሲደብቁ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ዋናዎቹ ናቸው። ምሳሌ በተሰረቀ ሶፍትዌር ስማቸውን በየዲስኩ የሚጽፉ የሚያተኩሩት ስለተሰረቁባው ዘፈኖች እንጂ ስሞቻቸውን ስለጻፉባቸው የተሰረቁ የዓማርኛ ሶፍርትዌር ማሰብ የማይችሉ በመሆናቸው ነው።

ስለ ኢትዮጵያ የዘመን ኣቈጣጠር ኢንተርኔት ላይ የተጻፈ ከጥቂት ዓረፍተ ነገሮች በስተቀር ስለኣልነበሩ ዶክተሩ በ፲፱፻፺፬ ያቀረቡት በተወዳጅነቱም ብዙ ድረገጾች ላይ ቀርቧል።  
                      ከእዚያም ወዲህ የኢትዮጵያ ዘመን ኣቈጣጠር ተገቢውን ዕውቅና ቢያገኝም ዛሬም በስሕተት የጁልያን (Julian) ካለንደር ነው የእሚሉ ኣሉ። 

ኢትዮጵያውያን ስለ ሄኖክ ዘመን ኣቈጣጠርም ያውቃሉ።  የሄኖክ ዓመት 364 ቀናት ነበሩት።  የኢትዮጵያ መጽሓፍ ቅዱስ ውስጥ መጽሓፈ ሄኖክ ምዕራፍ ፲፰ ቍጥር ፲፩ ስለ 364 የዓመት ቀናት ይናገራል። 

ኢትዮጵያውያን ሲወርድ ሲወራረድ የመጣውን የነገሥታት የስም ዝርዝር ለብዙ ሺህ ዓመታት ከክርስቶስ ልደት በፊት 4,400 ዓመት በመጀመር ኣቆይተውልናል። ይህ ከ1,000 ዓመተ ዓለም ግድም ጀምሮ መሆኑ ነው። ይህ ኢትዮጵያውያን የእራሳቸው የዘመን መቍጠሪያ እንደነበራቸው የሚያመለክት ኣንድ ማስረጃ ነው።   የግብጽና የሌሎችም እዚህ ኣለ። የጥንት ኢትዮጵያውያን የከዋክብትን ሳይንስ ፈጥረውና ስም ሰጥተዋቸው ለግብጻውያን ኣስተላለፉ ይባላል።  የግሪክ ፊደል ከግብጹ ዴሞቲክ የተወሰደ ነው ይባላል። 

የኢትዮጵያ ዘመን ኣቈጣጠር (Ethiopian calendar) የጁልያን ዘመን ኣቈጣጠር ኣይደለም። ጁልየስ ሲዘር ባለ 10 ወራትና 300 ቀናት የነበረውን የሮማውያን ካላንደር ትቶ 365.25 ቀናት የኣለውን ካለንደር ወስዷል። በኣሁኑ ጊዜ በጁልያንና በጎርጎርዮስ ካለንደሮች መካከል ያለው የ13 ቀናት ልዩነት ሲሆን የዓመታቱ ቍጥሮች ግን (2017) ልዩ ኣይደሉም። በ525 ዓ.ም. ዲኖስዮስ ኤክሲጅዮስ (Dionysius Exiguus) የሚባል የሩስያ መነኩሴ የሮማው ጳጳስ መልዕክተኛም በመሆን የፋሲካን በዓል ኣወሳሰን ከግብጻውያን እንዲማር ተልኮ ነበር። እንደሚመስለኝና ኣንዳንድ ፀሓፊዎችም እንደሚሉት ኤክሲጅዮስ በ525 ዓ.ም. 532 ዓመትን ሳይጠቀም ኣልቀረም። ዲኖስየስ ኣኖ ዶሚኒ (Anno Domini ወይም ኤ.ዲ.) የሚባለውን ካለንደር በጃንዋሪ 1፣ 1 ኤ.ዲ. እንዲጀምር በ525 ቢወስንም በኋላም ፀሓፊዎች ጁልያን (ዩልዮስ) ካለንደር የኣሉት የግብጾችንና የኢትዮጵያን ዘመን መቊጠርያዎች ስለማይመለከት እራሱን የቻለ ካለንደር ሆኖ ቆይቷል። ኤክሲጅዮስ ወደኋላ በመቍጠር ሲጀምር ይመስለኛል ኣዲሱ ካለንደር ላይ ሰባት ዓመታት ግድም የጨመረበት ይላሉ ዶክተር ኣበራ ሞላ። የዓመታቱም ቍጥር ከግብጽ ይልቅ ወደ ኢትዮጵያ የቀረበ ነው። ምክንያቱም የግብጻውያን ዓመተ ሰማዕታት ኣንድ ብሎ በ፪፻፸፮ ዓ.ም. የጀመረ ስለሆነ ነው።  ጨረቃ መሬትን ስትዞርና መሬት ፀሓይን ስትዞር የሚወስዱት 532 ዓመታት (19 X 28) ተደጋጋሚነታቸው የታወቁ ናቸው በማለት ዶክተሩ ጽፈዋል።     ኣሁን ያለነው ፲፭ኛው የ፭፻፴፪ ዓመታት ዙር ውስጥ ነው። የዲኖስዮስ ጁልያን ካላንደር ስሕተት እንደነበረው የቫቲካኑ ጳጳስ በቅርቡ በመጽሓፋቸው ስለኣሰፈሩ ዶክተሩም ኣመስግነዋቸዋል።    ምክንያቱም የዩልዮስ ቀለንጦስ ተጠቃሚዎች የኢትዮጵያው ላይ ሰባት ዓመታት ግድም ቢጨመሩም የእኛው ወደ ትክክለኛው የቀረበ ሳይሆን ኣልቀረም። 
ከግዕዙ ሲነጻጸር የጎርጎርዮስ ቀለንጦስ ተጠቃሚዎች የሦስተኛውን ሺህ መጀመሪያ የኣከበሩት ሰባት ዓመታት ግድም ቀድመው ነው። ኢትዮጵያውያን በዓላትንና ኣጽዋማትን ሲያከብሩ የቆዩት 532 ዓመታትን የሚሸፍነውን ኣንድ ትልቅ ጠንጠረዥ ደጋግሞ በመጠቀም ነው። ኢትዮጵያውያን ሚሌንየሙን ዋሽንግተን ዲ.ሲ. ሲያከብሩ ዶክተሩ ተጋብዘው ይኽንኑ የቀለንጦስዎቹን ታሪክ ኣቅርበዋል።    

ከኣንድ ዓመተ ዓለም ጀምሮ መስከረም ኣንድ ቀን ምን ዕለት እንደዋለ ወይም እንደሚውል ማስላት ስለሚቻል የኢትዮጵያ ዘመን ኣቈጣጠር ለሌሎች ቀለንጦሶዎችም ማነጻጸሪያ ሊያገለግል ይችላል። ለምሳሌ ያህል በ፲፱፻፺፬ ዓ.ም. መስከረም ፩ ቀን ምን ዕለት እንደዋለ ለማወቅ 7494 ዓመተ ዓለም ላይ 1873 ደምሮ በሰባት ማካፈል ነው። ቀሪው ኣንድ ከሆነ ዕለቱ ማክሰኞ ነው። (1873 የተገኘው 5500 ዘመነ ብሉይንና 1994 ዓመተ ምሕረትን ደምሮ በኣራት በማካፈል ነው።) 

የኢትዮጵያና የጎርጎርዮስ ዘመን የዕለት ልዩነቶች በጥቂት ቀናት መለያየት እየጨመረ ይቀጥላል። ይህ በጎርጎርዮስ የሠግር ዓመታት ኣወሳሰን የተፈጠረ ልዩነት ነው። የጎርጎርሳውያን ሠግር በ፬፻ ዓመታት ፺፯ ብቻ እንዲሆን እ.ኤ.ኣ. በ፲፭፻፹፪ ስለወሰኑ የቀናቱ ኣመዳደብ በእየ ፬፻ ዓመታት ሦስት ሦስት ቀናት እየቀነሰ መለያየቱ ይቀጥላል። የጁልያን ካለንደር ላይ ዲኖስዮስ ሰባት ዓመታት ግድም ሲጨምር ጎርጎርዮስ ፲ ቀናት ቀንሷል። በእነዚህ የሮማውያን ለውጦችም ሳትስማማ ኢትዮጵያ ካለንደሯን እንደጠበቀች ቆይታለች። በኣሁኑ ጊዜ ኣንድ ዕለትን ከኢትዮጵያ ወደ ጎርጎርሳውያን ወይም ከጎርጎርሳውያን ወደ ኢትዮጵያ ኣቈጣጠር የሚመነዝሩ ድረገጾች ኣሉ።    የቀለንጦስዎቹም ዕውቅና ጨምሯል።      ዓለማችን ከኣንድ ስፍራ ጀምራ ፀሓይን እየዞረች ተመልሳ እዚያ ገደማ የምትደርሰው በተለያዩ ዕለታት ስለሆነ ካለንደሮች ትክክል ኣይደሉም። የኢትዮጵያ ዕለት የሚጀምረው ጠዋት ነው። ስለ ጵጉሜን 7 የሚጽፉም ኣሉ።  ይህ በየስድስት መቶ ዓመታት የሚከሰተው በየዓመቱ የተጨመሩትን ደቂቃዎች ለመቀነስ ስለሚመስል ትክክል ሳይሆን ኣይቀርም ይላሉ ዶክተሩ። 

በዶክተሩ የጽሑፍ ገለጻና ምክንያት የተባበሩት መንግሥታት ማሕበር እና የኣፍሪቃ ሕብረት ከመስከረም ፩፣ ፳፻ ዓ.ም. እስከ መስከረም ፩፣ ፳፻፩ ዓ.ም. የኣለውን የኢትዮጵያ ዓመት ሚሌንየሙን በማክበር ዕውቅና (Commemoration) ሰጥተዋል።  
 ሦስተኛው የኢትዮጵያ ሺህ ዘመን የጀመረው መስከረም ፩ ቀን ፳፻፩ ዓ.ም. (September 11, 2008) ሲሆን መስከረም ፩ ቀን ፳፻ ዓ.ም. የሁለተኛው ሺህ የመጨረሻው የ2,000 ዓመት እንቁጣጣሽ እንጂ የሚሌንየሙ መጀመሪያ ኣልነበረም።    

ኢትዮጵያውያን  ካለንደራቸውን እንዲተዉ የተሞከሩት ስለኣልሠሩ ጽሑፎቹ ደራሲና ቀናት ወደሌላቸው እየተቀየሩ ነው።   

የኢትዮጵያ ዕለት የሚጀምረው ጠዋት ሲሆን የዩሊዮሱ እኩለ ሌሊት ላይ ነው። ስለዚህ ልዩነቶቹን ለማስላት ስድስት ሰዓታት መጨመር ወይም መቀነስ ያስፈልጋል።

የኢትዮጵያ ቋንቋዎች በ፲፱፻፺፪ ወይም Languages of Ethiopia, 1999 የሚል ድረገጽ SIL ያቀረበውን በመተርጐም ከእነካርታው በዶ/ር ኣበራ ቀርቦ ነበር።  
እነዚህም፦ 1. ኣሪ 2. ኣፋር 3. ኣላባ 4. ዐማርኛ 5. ኣንፊሎ 6. ኣኝዋክ 7. ኣርቦሬ 8. ኣርጎባ 9. ኣውንጅ 10. ባይሶ 11. ባምቤሺ 12. ባስኬቶ 14. ቤንች 15. በርታ 17. ቢራሌ 18. ኦሮምኛ (ቦረና-ኣርሲ-ጉጂ) 19. ቦሮ 20. ቡርጂ 21. ቡሳ 22. ጫራ 23. ደሳነች 24. ዲሜ 25. ደራሻ 26. ዲዚ 27. ዶርዜ 28. ጉራጌ 29. ጋሞ-ጎፋ-ዳውሮ 30. ጋንዛ 31. ጋዋዳ 32. ጌዴኦ 34. ጉሙዝ 35. ሃዲያ 36. ሃመር ባና 37. ሆዞ 38. ካቻማ-ጋርጁሌ 39. ካሲፖ-ባለሲ 40. ካፊቾ 41. ከንባታ 42. ካሮ 43. ኮሞ 44. ኮንሶ 45. ኩረት 47. ኩንፈል 48. ክዋማ 49. ክዌጉ 50. ሊቢዶ 51. ማጃንግ 52. ማሌ 53. ምኢን 54. ሜሎ 55. መስመስ 56. ሙርሌ 57. ሙርሲ 59. ናዪ 60. ጉራጌ (ሶዶ) 61. ኑአር 62. ንያንጋቶም 63. ኦፑኦ 64. ኦይዳ 65. ቆቱ (ኦሮምኛ) 66. ሳሆ 67. ሰዘ 68. ሻቦ 69. ሻካቾ 70. ሼኮ 71. ሲዳሞ 72. ሱማሌ 73. ሱሪ 75. ትግርኛ 76. ፃማይ 77. ኡዱክ 78. ጉራጌ (ምዕራብ) 79. ኦሮምኛ (ምዕራብ-መካከለኛ) 80. ኣገው (ምዕራብ) 81. ወላይታ 82. ጫምታንግ 83. የምሳ 84. ዛይ 85. ዛይሴ-ዘርጉላ ናቸው።  
 በኣጭሩ ኢትዮጵያ ሰማንያ ቋንቋዎች ኣሏት ማለት ይቻላል። 

ሌሎች ዝርዝሮችም እዚህ    ኣሉ። 

እዚህ ዝርዝር ውስጥ የግዕዝ ቋንቋ ኣልተካተተም።  የግዕዝ ቋንቋና  ግዕዝ ፊደል  እንዳይምታቱ መጠንቀቅ ያስፈልጋል። እስከኣሁን በኣብዛኛዎቹ የግዕዝ ፊደል ቀለሞቻችን ተጠቃሚ ቋንቋዎች ብዙ ጽሑፎች ስለኣልተጻፉ ብዙ የቃላት ክምችቶችም የሉም። 

በኣሁኑ ጊዜ ውጪ ኣገር የኣሉ ኢትዮጵያውያንን በዓማርኛ ማስተናገድ ተጀምሯል።  በዓማርኛ ለማንበብ “Amharic” የሚለውን መምረጥ ያስፈልጋል። ወደፊት በሌሎቹም የግዕዝ ፊደል ተጠቃሚ ቋንቋዎች መስተናገድ እንዲጀመር በየቋንቋዎቹ መጻፍ መስፋፋት ጠቃሚ ሳይሆን ኣይቀርም። በሁሉም ቋንቋዎቻችን በግዕዝ ፊደል መክተብ እንዲቻል ቀለሞቹ ዩኒኮድ ውስጥ ገብተው መክተቢያዎቹ በዶክተሩ ስለተዘጋጁ ባለመጠቀም ለሚዳከሙ ቋንቋዎች ተጠያቂዎቹ የየቋንቋዎቹ ተጠቃሚዎች ናቸው። ዕውቀት እየበዛና እየገዘፈ ወደ ኢንተርኔት ስለገባ የሚፈለገውን በቀላሉ ማግኘት ተችሏል። ይህ በተለያዩ ቋንቋዎቻችንም እንዲኖር መጻፍ ያስፈልጋል። ቃላትና ጽሑፎች በብዛት ሲኖሩ ወደ መተርጐም ይኬዳል።  በኢትዮጵያ ከ80 በላይ የአፍ መፍቻ ቋንቋዎች እንዳሉ፣ ከእነዚህም መካከል ወደ 51 የሚጠጉት ቋንቋዎች በመጀመርያ ደረጃና በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች ለሚሰጡ ትምህርቶች በመማርያነት እንደሚያገለግሉ ናቸው፡፡   

ከተለያዩ የፊደል ዓይነቶች ዶክተሩ ስሙን ለጥቂቶቹ የሰጡት ሥራ ለማቅለል ነው። ለምሳሌ ያህል የቤንች ገበታ ሲመረጥ የሚጠቀሙበት ቋንቋዎች ብዙ ናቸው። ምሳሌ ኣዊንጊ። የ“ዸ” ፊደል እርባታዎች ለኦሮሞ የተሰጡት ዶክተሩ ፊደሉን ቀድመው ስለዓወቁና መረጃዎቹ ስለቀደሙ እንጂ ይኸው ፊደል የሳሆ ቋንቋን ድምጽ ስለሚወክልና የሳሆም ምሁራን ፊደሉን እንዲጨምሩላቸው ስለላኩላቸው ፊደሉ የሳሆም ነው።

የኣንድኣንድ የቦታዎች ስሞችም እየተለዋወጡ ስለሆነ ጥንቃቄ ያስፈልጋል። ምሳሌ በረራ 

ከግዕዝ በፊት የደኣማቱ ቅድመ-ግዕዝ (Proto-Ethiopic) ፊደል ነበር።  ግዕዝ (Ethiopic) የሚለው ቃል ሁለት ትርጕሞች ኣሉት። ኣንደኛው የግዕዝ ቋንቋ ስም ሲሆን ሌላው የፊደሉ (Script)  ነው። የግዕዝን ፊደል የሚጠቀሙት የተለያዩ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች የእየራሳቸው የሆኑ ቀለሞች ኣሏቸው። የግዕዝ ቋንቋ ፊደሉን ብቻውን ሲጠቀም ቆይቶ ሌሎች ቋንቋዎች የእየራሳቸው የሆኑ ቀለማትን ጨምረውበት ተስፋፍቷል ይባላል።  ዓማርኛ፣ ትግርኛና ኦሮምኛ ብዙ ቀለሞች ከመቶ ዓመታት በላይ ቢጋሩም ሁሉም የእየራሳቸው ብቻ የሆኑ ቀለማት ኣሏቸው። ቢሆንም ግዕዝ የሁሉም ተጠቃሚ ቋንቋዎች የፊደል ስምም ነው። ከእነዚህም መካከል ብዙ ተጠቃሚዎች የኣሉት የዓማርኛ  ፊደል ነው። የዓማርኛው ፊደልም በቅርቡ የተጨመረለትን የ“ቨ” ቤት ጨምሮ ከ፸ በላይ የግዕዝ ቋንቋ የሌለውን እነ “ሸ”፣ “ቸ”፣ “ኘ”፣ “ጀ”፣ “ጨ”፣ “ኸ”፣ “ዠ” እና ሌሎችንም ቀለማት ያካትታል። (ይህ ገለጻ ዓማርኛ የኣልሆነውን የታይፕራይተር ፊደል ስለማይመለከት ቅጥልጥል ፊደሉም ግዕዝ ኣይደለም።) ስለዚህ ዓማርኛ የሚጠቀመው በእራሱ ፊደል ነው። ይህ ኣገላለጽ የሌሎች ቋንቋዎች ፊደላትንም ይመለከታል። ለምሳሌ ያህል ሁሉም የዓማርኛ ቀለሞች የትግርኛው ውስጥ እንደሌሉት ሁሉም የትግርኛ ቀለሞች (ለምሳሌ “ቐ”) ዓማርኛው ውስጥ የሉም። ኣንዳንድ ሰዎች በስሕተት ዓማርኛ የእራሱ ፊደል የለውም ይላሉ። ዓማርኛ የእራሱ ፊደል (Amharic Alphabet) የኣለው ቋንቋ  ነው። የግዕዝም ቋንቋ የእራሱ ፊደል ኣለው። የግዕዝ ቋንቋ ፊደላት የዓማርኛው ውስጥ ሲኖሩ ሁሉም የዓማርኛ ፊደላት የግዕዙ ቋንቋ ፊደላት ውስጥ የሉም። የግዕዝ ወይም Ethiopic የተለያዩ ቋንቋዎች የሚጠቀሙበት የፊደሉም ስም ሲሆን ለተለያዩ ቋንቋዎች ተጨማሪ ቀለሞች ተጨምረዋል። ኦሮሞም የእራሱ የግዕዝ ፊደል ኣለው። እንዲሁም ሁሉም የኦሮሞ ፊደላት (ምሳሌ “ዸ”) የዓማርኛው ውስጥ የሉም። የኤርትራው ቢለንና የጎጃሙ ኣገው ቋንቋዎች ፊደላት ቀለሞች ኣንድ ዓይነት ናቸው። ጉራጌኛ ሰባቱንም ቤቶች ያጠቃልላል። 

የኣብዛኛዎቹ ኣዳዲስ ተጠቃሚ ቋንቋዎች ፊደሎች ዓማርኛው ላይ የተጨመሩ ናቸው። በእዚህም የተነሳ የቀለሞቹ መልኮች እየጨመሩ ቢሆንም ኮምፕዩተራይዝድ ስለሆኑ ማወቁ እየቀለለ ነው። ተጠቃሚው የሚፈልገውን ቋንቋ በመምረጥ በቋንቋው ቀለሞች ብቻ መጠቀም ተችሏል። በላቲን (Latin) ፊደል እንደሚጠቀሙት እንደእነ እንግሊዝኛ፣ ጀርመንኛና እስፓንኛ ፊደላት    በመባል እንደሚታወቁት ሁሉ በግዕዝ ፊደል የሚጠቀሙትም የትግርኛ፣  ዓማርኛ፣  ግዕዝ፣  ኦሮምኛ  ሌሎችም ፊደላት በመባል በፊደል ስማቸው ተከፋፍለዋል። ኣንድኣንድ ምሁራን በስሕተት ዓማርኛና ትግርኛ የእራሳቸው ፊደላት የላቸውም ይላሉ። ይህ እንግሊዝኛና እስፓንኛ የእራሳቸው ፊደላት የላቸውም እንደማለት የተሳሳተ ነው። ከእዚህ ጎን የኣለው ሥዕል እንደሚያሳየው ፊደላቱን በቋንቋ ቀለሞች (Character sets) የመከፋፈሉ ጥቅም ኣጻጻፍ ለማቅለልም ሲሆን በሁሉም የግዕዝ ቀለሞች ለመጠቀም “Ethiopic ግዕዝ” የሚለውን መምረጥ እንደሚቻል ለማሳየት ነው። Ethiopic (ኢትዮፒክ) በእንግሊዝኛ ግዕዝ ነው። በግዕዝ ቋንቋ ፊደላት ለመጠቀም ግዕዝ ቋንቋ የሚለውን መምረጥ ያስፈልጋል። በኣንድ ምሳሌ ቋንቋ የተሰየሙትንም ብዙ ቋንቋዎች ሊጠቀሙባቸውም ይችላሉ። ምሳሌ፦ ኣዊንጂ፣ ዲዚ። ወደፊትም ገበታውን በእየኣንድኣንዱ ቋንቋ ለየብቻ ማቅረብ ያስፈልጋል። ምክንያቱም ወደፊት እየኣንድኣንዱ ቋንቋ በእራሱ ሰዋሰው፣ መዝገበ ቃላት፣ ማረሚያና የመሳሰሉት መጠቀም ስለኣለብን ሳይንሱንና ቴክኖሎጅውን በጀመርንበት በኣሁኑ ጊዜ ለየብቻቸው ማዳበር ስለሚያስፈልገን ነው። ይህ እንግሊዝኛና ፈረንሳይኛ ተቀላቅለው በላቲን ፊደላት እንደማይቀርቡት ዓይነት መሆኑ ነው። ለጥቂቶቹም መደበኛ ቅርጽ የተሰጣቸው ፊደላቱ በቋንቋ ስሞቻቸው ወደ ዩኒኮድ ሲገቡ ነበር። (በግዕዝኤዲት ኣጠቃቀም እንግሊዝኛ ለመቀላቀል የ“ቍጥጥር” (“Ctrl”) እና “ኣማራጭ” (“Alt”) ቁልፎች መጫን ያስፈልጋል።) በዶክተሩ ፓተንቶች የተጠቀሱት የግዕዝ ቀለሞች ብዛት  ዊኪፔዲያ ውስጥ  ከተጠቀሱት የበለጡ ናቸው። 

ዶክተሩ ግን በግላቸው በዓማርኛ ፊደል መቀነስ ከማይስማሙባቸው ምክንያቶች ኣንዱን ለመጥቀስ ያህል ኣንድኣንድ የኣናሳ የግዕዝ ቀለሞች ተጠቃሚ ቋንቋዎች ቀለማት የተሠሩት ይቀነሱ የተባሉትን በመጠቀም ስለሆነ ነው።  ሞክሼዎች ይቀነሱ የተባለው የኣናሳ ተጠቃሚዎች ቋንቋዎች ፊደሉ በዛ ብለው ቅር እንዳይላቸው ነው የሚባልም ወሬ ኣለ። በእዚህ የተነሳ ጸሎቱ “ጸ” የፀሓዩ “ፀ” ሞክሼ ከሆነ የጉሙዙ “ጸ” ሞክሼውን መመርኰዝ ኣልነበረበትም። “ጿ” ቀለም ያለውን ጸሎቱ “ጸ” ሞክሼ ነው ተብሎ ተዘልሎ የምኢኑ ዘጠነኛ እንዚር ፀሓዩ ላይ ስለቀረበ ዶክተሩ ለፀሓዩ ስምንተኛ ቀለም ኣቅርበዋል። ምክንያቱም በዶክተሩ ኣስተሳስብ ፊደል መቀነስ የሚፈልጉ ፊደል እንዳይቀነስ የሚፈልጉትን መብት መንካት የለባቸውም። “ኳ”ን ኣጥፍቶ “ክዋ” ወይም “ኩዋ” እንደ “ኳ” ይነበቡ ማለት ብቻ በቂ ኣይደለም። ምክንያቱም ግዕዝ ድምፃዊ ፊደል ስለሆነ ነው። “ሀ” እና “አ” የእየራዕቦቻቸው ሞክሼዎች መስለዋቸው ከኣናሳ ቋንቋዎች ቀለሞች ውስጥ ሊያጠፏቸው የሚፈልጉም ኣሉ። ይኸን ልዩነት በኣለማወቅ የዩኒኮድ ፊደላችንም ላይ ችግር የፈጠሩ ኣሉ።  ስለዚህ የሚሻሻሉ ነገሮች ጥናት ላይ ቢመረኰዙ ኣይከፉም። ሞክሼ የተባሉት ቀለሞች የእየእራሳቸው ጥቅሞች ኣሏቸው። ምሳሌ፦ መሳሳትና መሣሣትን በማጥበቂያ ወይም በማላልያ ምልክት ከመለየት የቃላቱን ኣመጣጦች ማወቅ ለዕውቀቱም ሆነ ለኮምፕዩተሩ ሳይበጅ ኣይቀርም። 

በጊዜውም የኮምፕዩተር ክፍል ባይኖርም ፲፪ የሞዴት ፕሮግራሞች የኢትዮጵያ ኮምፕዩተሮችና ሶፍትዌር ለኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርሲቲ (በፕሮፌሰር ዓለማየሁ በኩል) በ፲፱፻፺፪ ዓ.ም. በነፃ ኣበርክቶ ነበር። ኦሮምኛን በግዕዝ ፊደሉ መክተብ ያስቸግራል በተባለበት ጊዜ ለቀረቡት ኣንድኣንድ ምክንያቶች ዶክተሩ መፍትሔ ነበራቸው።  ኦሮምኛን ከግዕዝ ይልቅ በላቲን ፊደል መጻፍ ይሻላል ተብሎ የቀረቡት ዘጠኝ ምክንያቶች ደካማዎች ነበሩ። ለምሳሌ ያህል በኣንደኝነት የቀረበው ምክንያት ላቲን 26 ቀለሞች ሲኖሩት የግዕዙ 189 ናቸው ይላል። የላቲን “ኤ” ፊደል ዓይነቶች 27 ሲሆኑ ከእነዚህ ስምንቱ “aàáâãäåæ” ናቸው። “ብላ” በግዕዝ ፊደል “ኛዹ” ተብሎ በኦሮምኛ ሲጻፍ የሚወስደው ስፍራ ሁለት ብቻ ሲሆን እየኣንድኣንዱን ቀለም ለመክተብ ኣንድ ስከንድ ቢወስድ በላቲን ፊደል በእንግሊዝኛ “nyaadhuu”፣ በፈረንሳይ “gnaadhuu”፣ እና በእስፓኝም ፊደል ኣያታርፉም። በሌላ በኩል ኣንድኣንድ ኦሮሞዎች ወደ ላቲን የዞሩት በግዕዝ ፊደል እንዳይጠቀሙ ስለተከለከሉም ነው ይባላል።   

የግዕዝ ፊደልና ተጠቃሚ ቋንቋዎቹ ጥቃት እየደረሰባቸው ነው።    ለምሳሌ ያህል ውክፔዲያ ስለ እንግሊዝኛ ፊደል  ገጽ ሲኖረው ስለ ዓማርኛ ቋንቋ እንጂ  በእንግሊዝኛ ስለ ዓማርኛ ፊደል ወይም የኣማርኛ የጽሕፈት መኪና ገጽ የለውም። በጽሑፍ የሌለ ነገር እንደሌለ ይቆጠራል ነው የሚባለው። በዓማርኛ ፊደል  በነፃ መጻፊያ እዚህ  ኣለ። የተሟሉ የዓማርኛ መክተቢያዎች ኣሉ።    ስለዚህ ኣሁን በግዕዝ ፊደላችን በትክክለኛው ኣጠቃቀም በተለያዩ ቋንቋዎቻችን በሕጋዊ ሁኔታ በተገዙ ሶፍትዌር በመጻፍ ጽሑፎች ወደ ኮምፕዩተርና ኢንተርኔት የሚገቡበት ጊዜ ነው። በቅርቡም ሕዝብ ለብዙ ዘመናት የተጠቀመበት ዓማርኛ ብሔራዊነቱ ቀርቶ የሥራ ቋንቋ በመሆን በእንግሊዝኛ እንዲተካ ተደርጓል ይባላል። ኢትዮጵያ የእንግሊዝ ቅኝ ኣገር ስለኣልሆነች ባይሆን ዓማርኛው ላይ እንግሊዝኛን መጨመር (Grandfathering) እንጂ መተካቱን ዶክተሩ ይቃወማሉ። ተማረ የሚባለው ኣንድአንድ ኢትዮጵያዊ እያተኮር የኣለው ከጻፈልኝ ምን ኣለበት እየኣለ በተገኘው ሶፍትዌር ይጽፋል እንጂ ሁሉንም የዓማርኛ ቀለሞች እንኳን ከትቦ የሚጠቀምበት የመክተብ ችሎታ እንዳለው ማጣራቱ ኣጠራጣሪ ነው። “ባለፈው አንድ ዩኒቨርሲቲ ሄጄ አንድ ጓደኛዬ የነገረኝ አሳዛኝ ነገር ነበር። የአማርኛ መምህር ለመቅጠር የተሰጠው ፈተና ዩ፣ ዪ፣ ዬ እና ዮን መጻፍ ነበር። በጣም የሚገርመው ግን ከተፈተኑት ኣምስት የሁለተኛ ዲግሪ ያላቸው መምህራን ኣንዱ ብቻ አሟልቶ ጽፏቸዋል። ወደፊት አማርኛን ማንበብና መጻፍ የሚችል ሰው ለማግኘት ሥዕለት ሳያስፈልግ አይቀርም።” ይላል እዚህ  የኣለ ኣንድ ጽሑፍ። ለእዚህ ችግር የአማርኛ የጽሕፈት መኪናም ኣስተዋጽዖ ሳይኖረው እንዳልቀረ የኮሚሽነር ኣበበ ሙሉነህን የ፲፱፻፹፪ ዓ.ም. ደብዳቤ ውስጥ የኣሉት የ“የ” እንዚራን መቀጠያዎች ያሳያሉ።  (“ኢትዮጵያ”፣ “ዩናይትድ” እና “ኮምፒዩተር” የሚሉት ቃላት የተጻፉባቸው የ“የ” መቀጠያዎች መለየት ኣስቸጋሪ ነው። የአማርኛ የእጅ ጽሑፍ መጻፊያ “ዮ”ን መጻፍ የኣልቻለ ቢመስልም ስሕተቱ የፀሐፊው ሳይሆን ኣይቀርም። )

የትግርኛ ቀለሞቻችንን ለኣለመጠቀምና ቀስ በቀስ ለማጥፋት ያቀለሟቸውንም ዶክተሩ ተቃውመዋል።    ለምሳሌም ያህል በአማርኛ የ“ሀ” ድምጽ ወደ “ኸ” የቀረበ ነው አንጂ “ሀ” የ“ሃ” ሞክሼ ኣይደለም። የ“ሀ” እና “ኸ” ድምፆች ኣንድ ባይሆኑም “ሀ” እና “ሃ” ኣንድ መሆን የለባቸውም። “ሐ”፣ “ኀ”፣ እና “ዀ”ም ኣሉ። የተለያዩ ቋንቋዎች ብቻ የሚጠቀሙባቸው ቀለሞችና ድምፆች ኣሉ። ምሳሌ የጉራግኛው “ⷐ”። ይኸ ለምሳሌ ያህል የቀረበ የጉራጌ ፊደል እንደ ግዕዝኤዲት ዩኒኮድ ዓይነት የተሟላ የግዕዝ ፊደል ለሌላቸው ኣይታይም። 

የሁሉም የግዕዝ ፊደል ተጠቃሚ ቋንቋዎች ተለይተው መታወቅ እንደየፍላጎቱ ለማዳበር ይጠቅማል።   ለምሳሌ ያህል ኦሮምኛ ከቴክኖሎጅው ጋር እንዲጓዝ እነኢትዮስዊትን ማዳበር ያስፈልጋል። ግዕዝ ትክክለኛ ፊደል ስለሆነ ወደፊት ሌሎች ዓለማት ስንሄድ ይዘናቸው የምንሄድ ስለሆኑና ከዋክብትን ስለሚጎበኙ በኣቋራጭ ኣንሸወድ። በግዕዝ በሚገባ ለመጠቀም ወጪ ማውጣትና ለመክፈል መዘጋጀት እንጂ   ለላቲን የተሠሩ ፕሮግራሞችና መሣሪያዎች ሲባል ፊደል መቀነስ  ላይ ማተኮርን ዶክተሩ ይቃወማሉ። 

የግዕዝ ፊደል መክተቢያዎች ሁሉንም ቀለሞች የማስተናገድ ችሎታ ሊኖራቸው ይገባል። በዓማርኛ ብቻ የሚያስጽፈውን ግዕዝ ማለትም ተገቢ ኣይደለም። የዓማርኛ ከታቢም በሌሎች ፊደላት መኖር እንዳይዘናጋ ዓማርኛው ብቻ ተመርጦ እንዲከተብበት ኣማራጭ ሊኖር ይገባል። ፊደላትን በተለያዩ ቋንቋዎች ማቅረብ ለትርጕምና የተለያዩ ሥራዎች ማዳበር ይጠቅማል። ለምሳሌ ያህል ኦነሲሞስ ነሲብ በሁሉም የግዕዝ ቀለሞች ኣልተጠቀሙም።

ኢትዮጵያንና ጠቅላላ ዕውቀት የሚመለከቱ ጉዳዮች  በተለይ Ethiopic.com በእየጊዜው የቀረቡ ኣሉ። ለምሳሌ ያህል፣ ስመ እጸዋት፣     የኢትዮጵያ ዘመን ኣቈጣጠር፣ ፣        ስመ በሽታ፣  የግዕዝ ፊደል፣    ስመ ኣኃዝ፣    የኢትዮጵያ እንስሳት ስመ አንሰሳት፣   የግዕዝ ስምና ኣኃዝ   
ስመ ምልክቶች፣ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች፣ ኣንዳንድ የፊደል ስሕተቶች፣     ግልጽ ደብዳቤ ለቫቲካን ጳጳስ ቤነዲክት ፲፮ተኛ    እና Amharic Glossary ምሳሌዎች ናቸው።  ሌላ ምሳሌ ለመጥቀስ ያህል የኢትዮጵያ ሚሌንየም መከበር ያለበት መስከረም ፩ ቀን ፳፻፩ ዓ.ም. እንጂ መስከረም ፩ ቀን ፳፻ ዓ.ም. መሆን እንደኣሌለበት ኣንድ ድረገጽ ላይ ዶክተሩ ጽፈውና ኣሳምነው የኢትዮጵያ ምክር ቤት ከሰኔ ፩ ቀን ፲፱፻፺፱ ዓ.ም. እስከ መስከረም ፩ ቀን ፳፻ ዓ.ም. እንዲከበር የተደነገገው ስሕተት ተደርሶበት ሚሌንየሙ ዓመቱን ሙሉ እንዲከበር ተደርጓል።    የኢትዮጵያ ስመ እጽዋት ምንጭ የዶ/ር ኣበራ ሞላ ሥራ ነው።   

በተጨማሪም ዶክተሩ በየጊዜው የሞዴት፣ ኢትዮወርድና ግዕዝኤዲት ኣማርኛና እንግሊዝኛ መመሪያዎችን ለመክተብና ማቀነባበሪያ ከተጠቀሙባቸውና የሌሎችም ሥራዎች ሌላ ብዙ መጽሓፍት ከ፲፱፻፹፫ ዓ.ም. ጀምሮ ከጻፉባቸው ታዋቂ ደራስያን መካከል ዶ/ር ዓለሙ ቢፍቱ እና ዶ/ር ለይኩን ብርሃኑ ይገኙበታል። እነዚህ በዓማርኛው ፊደል መጽሓፎቻቸውን ኣሜሪካ የጻፉና ያሳተሙ ደራስያን ዶክተሩን በመጥቀስ ኣመስግነዋል። ዶ/ር በቀለ ሞላ እና ጌታቸው ሞላ ዋሽንግተን ዲ.ሲ. ውስጥ ፈጣን ማተሚያ ቤት  የመጀመሪያው የሆነውን ግዕዝ ማተሚያ በ፲፱፻፹፱ ዓ.ም. ኣቋቁመው ብዙ መጽሓፍትና ጽሑፍ-ነክ ሥራዎች በሶፍትዌር ታትመዋል። ዶ/ር በቀለም ተመስግነዋል። ዶክተር ኣበራም የግዕዝ ፊደል የረዥም ጊዜ ተጠቃሚ ናቸው።  
      ለኣሥር ዓመታት ያህልም የ“Ethiopian Review”  (ኤልያስ ክፍሌ) “ላንዳፍታ”  (መኮንን ገሠሠ) መጽሔቶች ተባባሪ ኣዘጋጅ ነበሩ። ዶክተሩ ዲጂታይዝ በኣደረጉት ግዕዝ በተለያዩ ርዕሶች ኢንተርኔት ላይ የተለያዩ ጽሑፎችን ኣቅርበዋል።  

የዶክተሩ ሥራዎች የተለያዩ መጽሓፍትና መጽሔቶች ውስጥም ተጠቅሰዋል። ምሳሌ፦ History of Mathematics in Africa, AMUCHMA 25 Years (ገጽ 526)
  Encyclopedia of Time, (ገጽ 128)      
  ዶክተሩንም ስለ ሥራዎቻቸው የኣመስገኑ ብዙዎች ናቸው።    ቪድዮዎችና ሌሎችም ኣሉ።             ይህ “ኣበራ ሞላ” የውክፔዲያ (Wikipedia) ገጽም በብዛት ከሚነበቡት ኣንዱ ነው።  የዓማርኛና እንግሊዝኛ ቅልቅል ጽሑፎች ምሳሌ እዚህ ኣለ።  ዶክተሩ ይኸን የዓማርኛ ዊኪፔዲያ ገጽ ከኣቀረቡት ፀሓፊዎች ኣራተኛ ናቸው።  
ገጹም በትልቅነት ኣንደኛ ነው።  ሌላ ምሳሌ ለመጥቀስ ያህል የአማርኛ ዊክፔዲያ ስመ እጽዋትና  ስም አንስሳት  መነሻዎች የዶክተሩ ጽሑፎች ናቸው።

ዶክተሩ ከታዋቂ ሰዎች ኣንዱ ናቸው።  በኣከናወኗቸው የተለያዩ ሥራዎች ጥቅሞቻቸው የተነኩ ጥቂት ሰዎች ስለእሳቸው የተጻፉ የእንግሊዝኛ ጽሑፍችን የሚሠርዙ ቢኖሩም ኣልተሳካላቸውም።     

ዶክተሩ (Dr. Aberra Molla) ከ564 በላይ የሆኑትን የግዕዝ ዩኒኮድ ቀለሞች ማንኛቸውንም በኣንድና ሁለት መርገጫዎች ብቻ እንዲከተቡ ለፈጠሩት ቀልጣፋና ግሩም ኣዲስ ዘዴ መረጃ Ethiopic Character Entry ፔንዲንግ ፓተንት (Pending Patent) እዚህ  ወይም እዚህ   ማንበብ ይቻላል። ኣብሻ (ABSHA) በመባል በታወቀው በእዚህ ኣዲስ የመክተቢያ ዘዴ ወይም ሥርዓት ሕዝቡ በነፃ በአማርኛ መጻፍና የዓለም ድረገጾችንና የመሳሰሉትን (ኢንተርኔት) በአማርኛ መፈለግ እንዲችል (ፍሪታይፒንግ.ግዕዝኤዲት.ኮም) የሚባል ድረገጽ በ፳፻፪ ዓ.ም. ኣበርክተዋል። ከእዚያም ወዲህ ብዙ መቶ ሺህ ሰዎች ተጠቅመውበታል። በኣብሻ ሥርዓት ብዛቱ ከ፭፻ በላይ ከሆነው የግዕዝ ፊደል፣ ምልክት፣ ኣኃዝና ማዜሚያ ሌላ ኮምፕዩተሩ የሚጠቀምባቸውን የእንግሊዝኛ ቊጥሮችና ምልክቶችን ግዕዝ በኣንድና ሁለት መርገጫዎች ተጠቅሞባቸው መክተቢያዎቹ ተርፈዋል። በኣንድና ሁለት መርገጫዎች የእንግሊዝኛውን ቀለሞች እንዲከትብ የተሠራው የኮምፕዩተር የፊደል ገበታ ግዕዝን ወደ እንግሊዝኛው ዓይነት ኣከታተብ በቀረበ ዘዴ እንዲከትብ ሠርተዋል። በእዚህ ዘዴ ግዕዝ የእንግሊዝኛ እስፔሊንግ ጣጣ ውስጥ ሳይገባ የእንግሊዝኛውን የኮምፕዩተር ገበታ በመጋራት፣ በማዋሃድና ለብቻውም እንዲጠቀም ሆኗል። ይኸንንም ያደረጉት በፓተንት ማመልከቻቸው እንደጠቀሱት ግዕዝን በቀላሉና በቀለጠፈ ዘዴ መክተብ የሚያስችል ዘዴ ስለኣልነበረ ነው። 

ነፃውና የሚሸጠው ግዕዝኤዲት ሶፍትዌር የተሸፈኑት በኣንድ የባለቤትነት መታወቂያ ስለሆነ ማስጠንቀቂያው ለሁለቱም ነው። ፓተንቱ ቢኖርም ባይኖርም ከፈጠሩት ዘዴ የተሻለ በኣሁኑ ጊዜ ስለሌለ ማንኛውምን ቀለም በሁለት መርገጫዎች መክተብም ያስችላል። ለምሳሌ ያህል በፈጠሩት ኣዲስ ዘዴ ኮምፕዩተሩ በኣለው 47 መርገጫዎች የግዕዝ ሳድሳንና ኣኃዞች በኣንድ ኣንድ መርገጫዎች ሲከተቡ ሌሎች ከ400 በላይ የሆኑት የግዕዝ ቀለሞች እያንዳንዳቸው በሁለት መርገጫዎች ይከተባሉ።  ስለዚህ በእዚህ ዘዴ መፈጠር የተነሳ ቀለሞችን በሁለትና ከእዚያ በላይ መርገጫዎች በመጠቀም ወይንም የግዕዝን ቀለም ላቲን በማይጠቀምበት ኣዲስና ኋላ ቀር ዘዴ እንደላቲን ቃላት በእስፔሊንግ መክተብ ኣያስፈልግም። ይህ በእንዲህ እንዳለ ዓማርኛውን  በኣራት መርገጫዎች የሚያስከትቡ ዘዴዎችንና የኮምፕዩተር ፕሮግራሞች በነፃ በማደል እያዘናጉ በማለማመድ ላይ የኣሉም ኣሉ። ይህ ሁሉንም የግዕዝ ቀለሞች በኣራት መርገጫዎች ስለማያስከትብና ሊያዛልቅ ስለማይችል ዓማርኛውንም ሆነ እንግሊዝኛውን ሳይጠቅም ሁለቱንም ከሌሎች የግዕዝ ፊደል ተጠቃሚዎች እንዳያጣላና እንዳያስተዛዝብ ዶክተሩ የፈጠሩት ይራዳል። ቸልተኝነት ከቀጠለ ግን የግዕዝ ፊደል ተጠቃሚዎች ኣናሳ እንዳይሆኑ ሳያስተውሉ በተገኘው በመጠቀም ይሀን ወሳኝ ጊዜ ከማባከን መጠንቀቅ ያስፈልጋል። ግዕዝኤዲት የሚከትበው እንደ እንግሊዝኛው ኣከታተብ በኣንድና ሁለት መርገጫዎች ቢመስልም ከእንግሊዝኛው በተሻለ፣ በረቀቀ፣ ኃይለኛና ኣዲስ ዘዴ ስለሆነ ፊደላችንን በዓለም ላይ ለማስፋፋትና በድምፃዊነቱ ጥቅም ላይ ለማዋል በሚገባ ተዘጋጅቷል። ሥራውም ሳይንስን የተመረኰዘ ነው። የግዕዝ ፊደል የረዥም ጊዜ ተናጋሪዎችና ጸሓፊዎች የኣሉት ሲሆን ድምጽን እንዲወክል የተሠራውን የእንግሊዝኛውን ዓለም-ኣቀፍ ድምፃዊ ፊደል (International Phonetic Alphabet) ሊረዳ ይችላል።   በኣሁኑ ጊዜ ግዕዝ በዩኒኮድ ዕውቅና ያገኙትን የቢለን፣ ቤንች፣ ምኢን፣ ሙርሲ፣ ሱሪ፣ ትግረ፣ ትግርኛ፣ ኣገው፣ ኣውንጂ፣ ኦሮምኛ፣ ዓማርኛ፣ ዲዚ፣ ዳውሮ፣ ጉሙዝ፣ ጉራጌ፣ ጋሞ ጎፋ እና ግዕዝ ቋንቋዎች የሚጋሯቸውን ቀለሞችና ሌሎችንም ያስከትባል። ይህ የውክፔዲያ ገጽም የተጻፈውና የቀረበው በግዕዝ ፊደል ነው። 

ግዕዝኤዲት.ኮም  (Geezedit.com)  የኮሎራዶው ኣብሻ/የኢትዮጵያ ኮምፕዩተሮችና ሶፍትዌር ኩባንያ ሌላ የእሳቸውና ባለቤታቸው ወ/ሮ ሠናይት ከተማ ድረገጽ ነው። የሁሉም ስም ግዕዝኤዲት ቢሆንም የነፃው ኃይልና ኣጠቃቀም የተወሰነ ነው። ዶክተሩም እንዴት የግዕዝ ፊደል ለኮምፕዩተሮች፣ የእጅ ስልኮችና ለመሳሰሉት መቅረብ እንደሚቻል በሳይንሳዊ ምርምር የደረሱበትን ለገበያና በነፃ ከማድረስ ኣልፈው ለፊደሉ መብት ታግለው ስለተሳካላቸው በምርምሩ በመቀጠል ትክክለኛ መደብ ፈጥረዋል።   
 እየተሻሻለም ነው። ስለዚህ እየኣንድኣንዱን ቀለም በሁለት መርገጫዎች መክተብን ጨምሮ ከኣሁን ወዲያ መጠቀም ኣስፈላጊ ኣይደለም። ሕዝቡም ይሀን ተገንዝቦ ሳይንስ በፈጠረው የተራቀቀ መሣሪያ በሳይንሳዊ ወጉና በማዕረጉ መጠቀም እንጂ ለተለያዩ ዓላማዎችና በነፃ የሚቀርቡት ኋላቀር ኣከታተቦች ኣንዳንዱን እያበላሹት እንደሆነ መገንዘብ ይገባል። 

ግዕዝ በኮምፕዩተር እንዲሠራ ኣዲስ ግኝት ሲቀርብ በኮምፕዩተር ዘመን ብቻውን ማሠራት በቂ ስለኣልሆነ ሞዴት የግዕዝና የእንግሊዝኛ ማተሚያ ነበር። የኮምፕዩተር ኣጠቃቀም ከዶስ ወደ ዊንዶውስ ሲዞር ዶክተሩ ኢትዮወርድን በማቅረብ ለመጀመሪያ ጊዜ ግዕዝ ዊንዶውስን እንዲጠቀም ኃይል ኣገኘ። የኢትዮወርድ ኢትዮኤዲትም ሌሎች ጥቂት የዊንዶውስ ፕሮግራሞችም ውስጥ ይሠራ ነበር፦ ምሳሌ ወርድፐርፌክትና ኳርክኤክስፕሬስ።  በግዕዝኤዲት ኮምፕዩተር በግዕዝ እንዲጠቀም ሆነ። ግዕዝ ወደ እጅ ስልክ ሲገባም የግሉ የማቀነባበሪያ (የግዕዝኤዲት) ገበታ ኖሮት ስልኩን በፊደሉና ከላቲን ጋር በመጋራት እንዲሠራ ኣደረጉ።  

የግዕዝኤዲት ኣከታተብ ትክክለኛና ሳይንሳዊ ከመሆኑም ሌላ ሁሉም የግዕዝ ቀለሞች በእኩልነት ተስተናግደዋል። የግዕዝ ፊደል ተጠቃሚዎች ቀለሞቻቸውን በወጉና በቀላሉ እንዲጠቀሙ ኣስችሏል። ባለፉት ጥቂት ዓመታት የዶክተሩ ፓተንት ማመልከቻ 20090179778  በሚከተሉት የኣሜሪካ ፓተንቶች ተጠቅሷል፦  8,381,119 ፣ 8,645,825 ፣ 8,706,750 ፣ 8,700,653 ፣ 8,762,356 ፣ 8,812,733  ከጠቃሾቹም የፓተንቶች ባለመብት ዋነኛው ጉግል  ነው። ይህ ለኢትዮጵያም ክብር ነው።

ስለ ዶክተሩ ሥራ የኣስተዋወቁና የኣመሰገኑ ከኢትዮጵያውያን ማሕበሮች እስከ ዩኒቨርሲቲ ዩኒየን የኣሉ ቢኖሩም    
ስለ ሥራዎቻቸው የኣልሰሙም ኣሉ።  

በቅርቡ ከኣንድ ኣንባቢ ስለ ዓማርኛና እንግሊዝኛ ኣጻጻፎች ጥያቄ ለግዕዝኤዲት ፌስቡክ (GeezEdit Facebook) (ቀርቦ ነበር። [23] ጽሑፍን በግዕዝ ፊደል መጻፍ ያታርፋል። ኣንድን ገጽ በዓማርኛ ወይም እንግሊዝኛ ጽሑፎች ለመሙላት ዓማርኛውን የበለጠ ጊዜ ይወስድበታል። ምክንያቱም ዓማርኛ ቃላቱን ሲጽፍ ከእንግሊዝኛው በኣንድ ሦስተኛ ግድም በኣነሰ ስፍራ ስለሚያሰፍረው ነው። በእንግሊዝኛ ሦስት ገጾች ለሚያስፈልጉት በዓማርኛው ሁለት ገጾች ገደማ ይበቁታል። ይኸም የሆነበት ግዕዝ ድምፃዊ ፊደል ሲሆን ላቲን ፊደላዊ በመሆኑ ነው። እንግሊዝኛው የሚጻፈው በኣንድና ሁለት መርገጫዎች ሲሆን ግዕዝ ወደ ኮምፕዩተር ሲገባ በሁለት መርገጫዎች ስለተከተበ እንግሊዝኛው ብልጫ የኣለው ይመስል ነበር። በቅርቡ ግን በዶ/ር ኣበራ ሞላ ግኝት ግዕዝን በኣንድና ሁለት መርገጫዎች መክተብ ስለተቻለ ኣከታተቡ ከእንግሊዝኛው ጋር እኩል ቢመስልም በላጭ ሆኗል። እንግሊዝኛ 47 መርገጫዎች የኣሉትን ኮምፕዩተር ከዝቅ (Shift) መርገጫዎች ጋር በመጠቀም 94 ቀለሞችን ያስከትባል። ግዕዝኤዲት (GeezEdit) የዝቅ መርገጫዎችን ሳይጠቀም ወደ 500 የግዕዝ ቀለሞችን ያስከትባል። ከላይ በቀረቡት ምክንያቶች ስፍራዎች ስለሚያስቀንስ ኣንድን ጽሑፍ ወረቀት ላይና በኮምፕዩተሮች ለማቅረብ ዓማርኛው ያታርፋል ማለት ይቻላል። ለምሳሌ ያህል “ዘ ኲክ ብራውን ፎክስ ጀምፕስ ኦቨር ዘ ሌይዚ ዶግ።” በዓማርኛ በ36 መርገጫዎች ተጽፎ 24 ስፍራዎች ይወስዳል።  “The quick brown fox jumps over the lazy dog.” በእንግሊዝኛ በ37 መርገጫዎች ተጽፎ 36 ስፍራዎች ይወስዳል።  [24] ይህ የእጅ ስልኮችንም (Smartphones) ኣጠቃቀም ይመለከታል። ስለዚህ ማንኛውንም የግዕዝ ቀለም በሦስት መርገጫዎች መክተብ ጊዜና ስፍራ ያስባክናል።  ከላይ የኣሉት ሦስት ምሳሌዎች እንደሚያሳዩት በኣነሰ የኆኄያት ግድፈቶች (Spelling / አስፔሊንግ) እና ስፍራዎች (Space) ማስከተብ ብልጫዎች የነበረው የግዕዝ ፊደል በዶ/ር ኣበራ ግኝት የተነሳ የግዕዝ ፊደል ሓሳብን በኣነሰ ጊዜ (Time)፣ መርገጫዎች (Keystrokes) እና ገበታ (Keyboard) በማስከተብ ብልጫዎቹ ወደ ኣምስት ዓይነቶች ከፍ ብለዋል።  ግዕዝ በእራሱ ፊደል እራሱን በዶክተሩ ግኝት ሲከትብ ከእንግሊዝኛው እስፔሊንግ ኣከታተብ የተሻለ ስለሆነ ግዕዝን በእንግሊዝኛ ፊደል እስፔሊንግ የሚያቀርቡትን ኣለመቃወም ሕዝቡን በማጃጃል ቀጥሎበታል። 

ግዕዝን ወደ ኮምፕዩተርና ጮሌ ስልክ ሲያስገቡ ፊደሉ የኣገኘውን ኣዲስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ በሚገባ እንዲጠቀም ዶክተሩ አቅርበዋል፣ አስተምረዋልም። ይህ መሻሻል ስለኣለበት በየጊዜው መከታተል ያስፈልጋል።

ስለ ዶ/ር አበራ ሞላ 
  እና የአክሱም  
 
 ሐውልት ከጣልያን ማስመለስ ጉዳይ ያውቁ ኖሯል? 
 
 
 Aksum 
 Obelisk of Axum 
  ጣልያኖች በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ከኣክሱም የዘረፉትን  የኣክሱም ሓውልት  እንዲመልሱ በ፲፱፻፵ ዓ.ም. የተባበሩት መንግሥታት ወስኖ ኢትዮጵያ እና ጣልያንም በጉዳዩ ተስማምተው ነበር። የተስማሙትም ጣልያን በኣሥራ ስምንት ወራት በወጪዋ ሓውልቱን ኢትዮጵያ መልሳ ኣክሱም እንድትተክል ነበር። ይህ ስለኣልተፈጸመ በፍርዱ መሠረትሓውልቱ  እንዲመለስ ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ፣ ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም እና ኣቶ መለስ ዜናዊ ጠይቀው ጣልያን ለመመለስ ፈቃደኛ ኣልነበረችም።  የሰውንም ልመና ስለኣልሰሙ ብስጭቱ ቀጠለ።    

በኋላም የተተከለበት ሮም ከተማ እንዳለ መብረቅ እንደመታው እንዲመለስ ኣቶ መለስ ዜናዊ ቢጠይቁም ሊያናግሯቸው እንኳን ፈቃደኞች ስለኣልሆኑና  
 
 ጣልያኖች ስለኣልመለሱት 
 የኢትዮጵያ ወዳጆች ሓውልቱ እንዲመለስ የተቻላቸውን ሁሉ እንዲያደርጉ ግንቦት ፳፭ ቀን ፲፱፻፺፬ ዓ.ም. በሮም ንግግራቸው መጠየቃቸው ይታወሳል።   የሮም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞም ነበር። ቀደም ብሎም የኣንዳንድ ታዋቂ የዓለም ሰዎች፣ ኢትዮጵያውያንና የኣክሱም ሕዝብ 
 
 
 
 
 
   የጥያቄ ፊርማ ጣልያኖችን ከኣለማስጨነቁም ሌላ  ሓውልቱ ከተመለሰ ሥልጣኔን እለቃለሁ የኣሉም የጣልያን ባለሥልጣንም ነበሩ። 
 ለኣለመመለስ ከቀረቡት ሰበቦች ሓውልቱ ጣልያን ኣገር ስለቆየ ጣልያናዊ ሆኗል፣ 
 
 ቀደም ብሎ ፈቅዶት የነበረውን ገንዘብ የለንም በማለት፣   ሓውልቱ ስለኣረጀ ኢትዮጵያ ሲደርስ ይሰባበራል፣ በኣካባቢው ጦርነት ኣለ፣ በገንዘቡ ኣክሱም ያለውን ትልቁን የኣክሱም ሓውልት እንትከልበት፣ 
 መመለስ የሚችለው ኣይሮፕላን ጦርነት ላይ ነው፣ ዓፄ ኃይለሥላሴ ሓውልቱን በስጦታ ለሮም ከተማ ሰጥተዋል 
 ነበሩበት። 
  
  ኢትዮጵያም ሓውልቱን ከፈለገች ለጣልያን መክፈል ኣለባት የኣሉም የጣልያን ኣክራሪ እንደነበሩ በኋላም ተደርሶበታል። 
   

ሓውልቱን መብረቅ ከመታው በኋላ ዶ/ር ኣበራም በግላቸው ለዩናይትድ እስቴትስ ፕሬዚደንት፣ ጥቂት ሴነተሮችና የኮንግረስ ወኪሎች እንዲረዱ የጻፉት ደብዳቤ መልስ ሳያገኝ ቀረ። በመጨረሻም ርዝመቱ 79 ጫማዎችና ክብደቱ 160 ቶን የሆነው ከ፲፯፻ ዓመታት በላይ ዕድሜ ያለው የኣክሱም ሓውልት ሦስት ቁርጥራጮች ተደርጎ መጋዘን የተቀመጠው 
 የትም ኣይሄድም ተብሎ በማዘናጋት ኣጀንዳ ቆየ።  ወደ ኢትዮጵያ እንዳይመለስ ኣሜሪካ ኣውሮፕላንና ጣልያን ገንዝብ ከለከሉ የሚለውን የጦቢያ የካቲት ፳፭ ቀን ፲፱፻፺፮ ዓ.ም. (March 4, 2004) ጽሑፍ 
 
 የዓዩትና የፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክኸርስት በዩናይትድ እስቴትስ መማረር  ያላስደሰታቸው ዶ/ር ኣበራ ሞላ ቅር ኣላቸው። በእዚህም የተነሳ ሓውልቱን በትናንሹ ኣስቆርጦ ገንዘብ ከዓለም ሕዝቦች ላይ በኢንተርኔት ማሰባሰብ እንደሚችሉ ኣዲስ ኣበባ ለሚገኘው የጣልያን ኤምባሲ በኢሜይል የካቲት ፳፰ ቀን ፲፱፻፺፮ ዓ.ም. ከዓሳወቁ በኋላ 
 ኣጣብቂኝ ውስጥ የገባው የጣልያን መንግሥት ወጪውን ከፍሎ ሓውልቱን እቦታው እንደሚተክለው ገለጸላቸው። በተጨማሪም ሌላ የጣልያን ኤምባሲ ባለሥልጣን የሆኑ ዶክተር ሰርቦ ሓውልቱን ለማስጫን ተስማሚ ኣውሮፕላን እያፈላለግን ነው ብለው መጋቢት ፫ ቀን ፲፱፻፺፮ ዓ.ም. (March 12, 2004) ለዶ/ር ኣበራ ኢሜይል ላኩ። ይኸንንም ለሓውልቱ መመለስ ለኣያሌ ዓመታት ሲታገሉ ለነበሩት ፕሮፌሰር ገልጸው ሓውልቱን መብረቅ ከመታው በኋላ ሊረዱዋቸው ስለጀመሩ በኢሜይል ይጻጻፉ ስለነበረ ላኩላቸው። ፕሮፌሰር ፓንክኸርስትም የዶክተሩን ሓሳብ ከሰሙ በኋላ የታችኛውን ሁለት ማስቆረጥም እንደሚያስፈልግና ገንዘብ ሊዋጣ እንደሚችል ጣልያኖችን ማሳወቅ እንዲከፍሉ ሊያስገድዳቸው ሳይችል እንደማይቀር ደግፈው ኣስታውቀዋቸው ነበር። ግንኙነት ስለኣልነበራቸው ለኢትዮጵያ ባለሥልጣኖች ግን ሳያሳውቁ   
 ኣንዳንዶቹን ጽሑፎች ኢትዮፒክ.ኮም ድረገጻቸው ላይ ቢያስቀምጡም ብዙዎቹ ስለኣላነበቡት ጣልያን ወጪውን ለምን ለመክፈል እንደተስማማች ቢጻፍም በጊዜውና እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ሳይታወቅ የቆየ ይመስላል። 
  
 
 
 ለኢትዮጵያ መንግሥት ግን ጣልያኖች ገንዘቡን እንደሚከፍሉ  እስከ ሓምሌ ፺፮ ዓ.ም. ድረስ ያላሳወቁ  
  
 ይመስላል።   ጣልያኖች ቃላቸውን ደጋግመው ስለኣጠፉ እንደሚመልሱ የተስማሙበትንና የዶክተሩን ጉዳይ በሚገባ የሚያውቁት ፕሮፌሰር ፓንክኸርስትም ታግሰዋል። 
 ስለ ገንዘብና ኣይሮፕላን መጥፋት ጣልያኖች ሲያወሩ መቆየታቸውን ዘ ጋርድያን ጋዜጣ (The Guardian, July 16, 2004) የኣተመው ኣንድ ምሳሌ ነው።   በእዚህም ጊዜ (ሰኔ፣ ፺፮) ለሓውልቱ የብረት ማቀፊያ ተሠራለት።

በመጨረሻም ሓውልቱ በ፺፰ ሲመለስ እንኳን ደስ ያለዎት የሚል የምስጋና ኢ.ሜይል ዶክተሩ ስለጉዳዩ ለዓመታት ለታገሉት ፕሮፌሰር ላኩ። ኤምባሲውም ዶ/ር ኣበራን ድንጋይ ከምታመላልስ ለረሃብተኛው ሕዝብ በገንዘቡ እህል ግዛበት ያለበትን ኢሜይል ኣስታውሰዋቸው ሓውልቱ ኢትዮጵያ ሲደርስ ፕሮፌሰሩ ደረሰኝ ብለው ከኣቀረቡት የእንግሊዝኛ ኢ.ሜይሎች መካከል የዶክተሩ ኣንዱ ነበር።   ኣሜሪካኖችም የሓውልቱን ቁርጥራጮች ትክክለኛ መጠን ለማወቅ ተጠይቀው ያወጡትን ወጪና የኣክሱም ኣይሮፕላን ማረፊያ ችሎታ ያጠኑበትን ገንዘብ ጣልያኖች ኣልከፈሉንም ብለዋል።  በእዚህ ኣኳኋን ወደ ስምንት ሚሊዮን ዶላር የጣልያን መንግሥት ወጪ  ሓውልቱ በሩስያ ኣንቶኖቭ ኣይሮፕላን ከጣልያን ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ 
 በየተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት መኃንዲሶች እርዳታና ሥራ (ኢንጂነር ክሮቺ) 
 ኣክሱም ተተክሎ ነሓሴ ፳፱ ቀን ፳፻ ዓ.ም. ተመርቋል።  
 ቪድዮዎችም እዚህ 
 
 
 ኣሉ። 

ዓፄ ኃይለሥላሴ ሓውልቱን ጣልያኖች ከኣክሱም ሲወስዱትም ከመቃወማቸውም ሌላ ለብዙ ኣሥርት ዓመታት ሓውልቱ እንዲመለስ በሮም የኢትዮጵያ ኣምባሳደሮችና በየተባበሩት መንግሥታት የኢትዮጵያ ወኪሎች ጠይቀዋል። 
 የኣክሱም ሓውልት ከሮም ወደ ኣክሱም እንዲመለስ በዓፄ ኃይለሥላሴ ዘመን መንግሥት የኢትዮጵያ ምክር ቤት ጠይቆ ነበር። 

ፕ/ር ፓንክኸርስት የኣክሱም ሓውልት ለኢትዮጵያ እንዳልተመለስ ለኣንድ የጣልያን ጋዜጣ በ፲፱፻፹፬ ዓ.ም. የጻፉትን የኣነበቡ ብሩኖ ኢምፔሪያሊ ለኣንድ ጋዜጣ የድጋፍ ደብዳቤ ጻፉ። የተጻፈውን የኣነበቡ ቪንሴንዞ ፍራንካቪግሊያ፣ ጁይሴፔ ኢንፍራንካ እና ኣልበርቶ ሮሲ የተባሉ ምሁራን ሓውልቱ እንዲመለስ ለጣልያን መንግሥት ደብዳቤ ከጻፉ በኋላ ፕሮፌሰሩም ይኸን ድጋፍ እንደሰሙ ኢትዮጵያውያን ፊርማ እንዲያሰባስቡ ጠየቁ። በእዚህም በመተባበር ከ500 ፊርማዎች በላይ በማሰባሰብ ከተሳተፉት መካከል ኣሰፋ ገብረማርያም፣ ልጅ ሚካኤል ዕምሩ፣ ሺፈራው በቀለ፣ ክሎውድ ሰምነር፣ ደኒስ ጀራርድ፣ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም፣ ክቡር ደጃዝማች ዘውዴ ገብረሥላሴ፣ ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድኅን፣ ተክለጻዲቅ መኩሪያ፣ ተፈራ ደግፌ፣ ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ፣ ፕ/ር ኣቻምየለህ ደበላ፣ ፕ/ር ኣሸናፊ ከበደ፣ ካሳሁን ቸኮል፣ ሃሪ ችሃብራና ራስተፈሪያን ነበሩበት። በዓመቱም ፕሮፌሰሩን የጨመረ ፲ ሰዎች የኣሉት የኣስመላሽ ኮሚቴ ተቋቋመ። ፕ/ር ፓንክኸርስት ስለ ጉዳዩ ካነሱበትና ሌሎችም በእየጊዜው ሲጽፉ ሓውልቱን ለማስመለስ ከ፲፱፻፹፭ ዓ.ም. ጀምሮ የኣምስት ዓመታት የኣስተዋጽዖ ዝርዝር ውስጥ የሚከተሉት ኣሉበት። 
 
 የኣዲስ ኣበባ ምክር ቤት፣ 
 የኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የጥያቄ ፊርማ፣ ፕ/ር እስቲቨን ሩበንሰን፣ ፕ/ር ደኒስ ማክ እስሚዝ፣ ኣቡነ ጳውሎስ ፭ተኛ፣ ዶ/ር ሳሊም ኣህመድ ሳሊም፣ ፕ/ር ፓስካል ጄ. ኢምፐራቶ፣ ፕ/ር ፍረደሪክ ጋምስት፣ ፕ/ር ኖርማ ኮምራዳ፣ ራጌሽዋር ሲንግ፣ ባማን ኣሊፍ፣ ዶ/ር ነቪል እስሚዝ፣ ሲይልቭያ ኤይሊንግ፣ ግለንዳ ጃክሰን፣ ኣቶ ገብሩ ኣሥራት፣ ፊታውራሪ ኣመዴ ለማ፣ ፊታውራሪ ኣበባየሁ ኣድማስ፣ ቀኛዝማች ቢያዝን ወንድወሰን፣ ሻምበል ምሩጽ ይፍጠር፣ ሻለቃ ዻራርቱ ቱሉ፣ ዶ/ር ፈቃዱ ገዳሙ፣ ልዑልሥላሌ ተማሙ፣ ኢንጂነር ታደለ ብጡል፣ ተስፋዬ ዘለለው፣ ሚስስ ዊንዞፕ ቦዝወል፣ ኣንጀሎ ደል ቦካ፣ ዶናልድ ክረሜይ፣ ጆን እስፔንሰር፣ ዴቪድ በክስተን፣ ኣልበርቶ እስባክቺ፣ ሰይድ ሳማታር፣ ቪራጅ ጉፕታ፣ ፕ/ር ሃጋይ አርሊች፣ ሪቻርድ ግሪንፊልድ፣ ፒተር ጋረትሰን፣ ዩሪ ኮቢስቻኖቭ፣ ማርያ ራይት፣ ካትሱዮሺ ፋኩይ፣ ጃክ ጎትሌ፣ ፕ/ር ኢማኑኤል ሴሚ፣ ሮጀር ሽናይደር፣ ፕ/ር ክሪስቶፈር ክላፋም፣ ፕ/ር ፍረድሪክ ሃሊደይ፣ ፖውል ብሪትዝኪ፣ ኣሊ ማዝሩይ፣ ቶማስ ፓከንሃም፣ ኮህን ለጉም፣ ኬረን ዳልተን፣ ሆዜ ጃፊ፣ ፕ/ር ዊሊያም ዲያኪን፣ ዶ/ር ኪርስተን ፒደርሰን፣ ካትርይን ባርድ፣ ዶ/ር ረይደልፍ ሞልቬር፣ ኣይቫን ኣድለር፣ ዊልፍረድ ተሲገር፣ ግራሃም ሃንኮክ፣ ሰር በርናርድ ብሬይን፣ ሉትዝ ቤከር፣ ሮደሪክ ግሪየርሰን፣ ሪታ ማርሌይ፣ ጀርሜን ግሪር፣ ሲሮ ታደኦ፣ ኒኮላ ደማርኮ፣ ፕ/ር ኤፍሬም ይስሃቅ፣ ፕ/ር ሥዩም ገብረእግዚኣብሔር፣ ዶ/ር ጌታቸው ኃይሌ፣ ፕ/ር ኣሸናፊ ከበደ፣ ዶ/ር ካሳሁን ቸኮል፣ ዶ/ር ኣስፋወሰን ኣስራቴ፣ ልጅ ዘውዴ ኃይለማርያም፣ ሳሙኤል ፈረንጅ፣ ሪቻርድ ባልፍ፣ ሃሪ ካህን፣ ዶ/ር ካሳይ በጋሻው፣ ሪታ ፓንክኸርስት፣ ክቡር ደጃዝማች ዘውዴ ገብረሥላሴ፣ ኣርቲስት ኣፈወርቅ ተክሌ፣ ሴጉን ኦሉሶላ እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ይገኙበታል። 

ሰለ ሓውልቱ ጉዳይ በየጊዜው በመጻፍ ከተራዱትም ውስጥ “ኢትዮፒያን ሪቪው” (ኤልያስ ክፍሌ)፣ “ኢትዮፕያን ሬጂስተር” (ግርማ በቀለ)፣ “ኢትዮፕያን ኮመንቴተር”፣ “ኣዲስ ትሪብዩን” እና “ቤዛ” ተጠቅሰዋል። ሓውልቱ እንዲመለስ እስከ ፲፱፻፺ ዓ.ም. እንቅስቃሴውን በመቀጠል ከተዘረዘሩት  መካከል የሚከተሉት ኣሉበት። 
 የኣክሱም ሓውልት ኣስመላሽ ኮሚቴ፣ የኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ፣ ኣቶ ኃብተኣብ ባይሩ፣ ፕ/ር ሳሙኤል ኣሰፋ፣ ኣቶ ዳዊት ዮሓንስ፣ የኢትዮጵያ ፓርላማ፣ ፕ/ር ባሕሩ ዘውዴ፣ ማርኮ ቪጎኒ፣ የትግራይ ክልል ፓርላማ፣ ቶኒ ሂኬይ፣ ናፍታለም ኪሮስ፣ እስቲፈን ቤል፣ ኣልበርቶ ኢምፔሪያሊ፣ የሮም ኢትዮጵያውን፣ ጃራ ኃይለማርያም፣ ክቡር ኣቶ ወልደሚካኤል ጫሙ፣ ክቡር ኣቶ ሥዩም መስፍን፣ ፕ/ር ፍራንካቪግሊያ፣ በላይ ግደይ፣ ዶ/ር ተቀዳ ዓለሙ፣ ፕ/ር እንድርያስ እሸቴ  ፣ ፕ/ር ኣበበ ከበደ   ፣ ክቡር ኣቶ ተሾመ ቶጋ፣ ጆርጅዮ ክሮቺ፣ የታዋቂ ኢትዮጵያውያን ፊርማ፣ ፲፬ሺህ ፊርማ የፈረሙ የኣክሱም ሕዝብና ብዙ ሺህ ፊርማ ያለው በዓለም ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያና ሌሎች የጥያቄ ፊርማ (ፔቲሽን)፣ የጥቂት ኣፍሪቃ ኣገሮች ኣምባሳደሮች ደብዳቤዎችና ሌሎችንም ጠቅሷል። ስለ ፊርማውም በማሰማት የቢቢሲ ሬድዮና ቴሌቪዥን፣ የካናዳ ሬድዮ፣ የእንንግሊዝ፣ የጣልያንና ኣንዳንድ የዓለም ጋዜጣዎች ትኩረት በመስጠት ረድተዋል። ኣንድ ቪድዮም ተሠርቶ ነበር። ለእዚህ ጉዳይ ከተረባረቡት መካከልም ብርሃኑ ተሰማ፣ ልዑልስገድ ተማሞ፣ ቢያዝን ወንድወሰን፣ ኣበባየሁ ኣዳማ፣ ኣፍሮሜት (AFROMET)፣ ኣሉላ ፓንክኸርስት፣ ታጋስ ኪንግ፣ ቶኒ ሂኪ፣ ሬናቶ ኢምፔሪያሊ፣ ጌይል ዋርደን እና ኣንድሩ ሎውረንስ ነበሩ። እዚህ የቀረበው በስም የተጠቀሱትን ብቻ ስለሆነ ወደፊት ማሟላትና ስለ እየኣንድኣንዳቸውም በስማቸው መጻፍ ይቻላል። ከእዚህ ሁሉ ድካም በኋላ ጣልያኖች ሓውልቱን እንደሚመልሱ ቃል ገብተው በ፲፱፻፺ ዓ.ም. ይመለሳል ተብሎ (ኢትዮጵያም ፕሮፌሰር ፓንክኸርስት የኣሉበት የኣክሱም ሓውልት ኣስመላሽ ኮሚቴ በ፲፱፻፹፭ ዓ.ም. ተቋቁሞም ስለነበረ (በ1988 ዓ.ም. ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በተጻፈ ደብዳቤ ለማስታወቂያና ባህል ሚኒስቴር ሐውልቱን ለማስመለስ የሚረዳ ብሔራዊ ኣስተባባሪ ኣካል እንዲቋቋም በተጠየቀው መሠረት፣ ሓውልት ኣስመላሽ ብሔራዊ ኮሚቴም ተቋቁሞ ነበር።) 
 ) የጣልያን ፕሬዚደንት ኢትዮጵያን ሲጎበኙ ይቅርታ ከጠየቁም በኋላ የመመለሱ ጉዳዩ በወሬ ቀረ።  
   
  ይህ የኢትዮጵያና የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትሮች ስለ ሓውልቱ መመለስ ከተፈራረሙና ቴምብር ሁሉ ከተሠራ በኋላ ነበር። በመጨረሻም በዶ/ር ኣበበ ከበደ የኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ተማሪዎች ኔትወርክ  
 በኩል ለጣልያን ጠቅላይ ሚኒስቴር በእንግሊዝኛና ጣልያንኛ የተጻፈው የልመና ደብዳቤ (14 June 2001) መልስ ሳያገኝ ቆይቶ በዓመቱ ግድም ሓውልቱን መብረቅ መታው። ሓውልቱን መብረቅ ሳይመታው ከስድስት ወራት ቀደም ብሎ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስርት ለጣልያኑ ኣቻቸው በነበሩት ውለታዎች መሠረት ሓውልቱ እንዲመለስ ደብዳቤ ጽፈው መልስ እንኳን ተነፈጋቸው። 

እንዲህም ሆኖ ሓውልቱ እንዲመለስ የደገፉ ጣልያኖች ነበሩ። የጣልያን መንግሥት ግን ለመመለስ ፈቃደኛ ስለኣልነበረ ተስፋ ተቆርጦ ነበር።  የሓውልቱ መመለስ ጉዳይ እንደገና ያንሰራራው ጣልያኖች ሓውልቱን ሮም ሲተክሉት ብረት ኣስገቡበት እንጂ ከመብረቅ ስለኣልተከላከሉት ግንቦት ፲፯ ቀን ፲፱፻፺፬ ዓ.ም. (May 28, 2002)  መብረቅ ከመታውና ከላይ በኩል ተሰብሮና ከተጎዳ በኋላ ነበር።  
  ምክንያቱም ሌላ መብረቅ ቢመታው ሓውልት መሆኑ ቀርቶ የድንጋይ ክምር ሊሆን ስለሚችል ከልመና ያለፈ ኣስቸኳይ እርምጃ በኣንዳችን መወሰድ ስለነበረበት ነው ዶክተሩ በግላቸውና በብቸኝነት በጉዳዩ የገቡበት። የሚያሳዝነው ግን ሓውልቱን መብረቅ ከመታውም በኋላ እንኳን ለኢትዮጵያ እንዳይመለስ ተቋውሞ መቀጠል ነበር።  
 

ከእዚህ በላይ ለተዘረዘሩትና ሌሎችም ለኢትዮጵያ ስለ ኣደረጉት ኣስተዋጽዖ በተለይ ለፕሮፌሰር ፓንክኸርስት እግዜር ውለታቸውን ይመልስልን።  
 ጣልያኖች የኣድዋን ድል ለመበቀልና  ኢትዮጵያ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጣልያንን ለሁለተኛ ጊዜ ስለ ኣሸነፈች ተበሳጭተው ሓውልቱ ላይ ቢንጠላጠሉም    ከኣክሱም የወሰዱትን ሓውልት ሌላ ትውልድ ኣስመልሷል። 
 
     
 ታሪኩ እንዳይጠፋ ኣንድ ቦታ መጻፍ ተገቢ ነው።   ሓውልቱም ግዙፍ፣ ታዋቂና ተደናቂ በተባበሩት መንግሥታት የተመዘገበ የዓለም ቅርስ  እንጂ ጉራም ኣይደለም። 
 ይህ ሲደረግም በየተባበሩት መንግሥታት ስምምነት መሠረት ይኸን ትልቅ ቅርሷን 
 ለማስመለስ ለዓመታት ስትታገል ኢትዮጵያን የረዳት መንግሥት ኣልነበረም። 
  የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት እንኳን ሓውልቱን መብረቅ ከመታው በኋላ ለኢትዮጵያ ይመለስ ኣላለም።   ማንም ኣያስገድደንም ብለው የዓለም ሕዝቦች ላይ ሲቀልዱ የነበሩትን ጣልያኖች 
 ኣንድ ሰው ሊያስመልሰውና እንደሚዋረዱ ኣስጠንቅቆ ሓውልቱን በማስገደድ ከማስመለስ በስተጀርባ ትምህርትነትም ኣሉት።  ጣልያኖች የኣክሱምን ሓውልት ዘርፈው ከ፷፱ ዓመታት በኋላ በ፲፱፻፺፰ ዓ.ም. የመለሱት በዶክተሩ እንዳይዋረዱ ተገድደው እንጂ ወደ'ው ኣይደለም። 
 ጣልያኖች በዶክተሩ ያለጉራ የተሰጣቸውን በጎ ፈቃድ  ተጠቅመው ሓውልቱን ቢመልሱም በፈቃዳችን መለስን ብለው ሸንግለዋል።  
   
  ምክንያቱም በፈቃድ ለመመለስ ብዙ ኣሥርት ዓመታት መፍጀት ባላስፈለገ ነበር። በፈቃድ ለመመለስ ቆራርጠው ድንጋያችሁን ውሰዱ በኣላሉ ነበር።  በፈቃድ ለመመለስ ቆራርጠው ከኣስቀመጡበት ሮም ከተማ ለዘለዓለሙ የትም ኣይሄድም በኣላሉ ነበር። ከእዚያም ወዲህ ከዘረፏቸው መካከል እንኳን በፈቃዳቸው ተለምነውም ለኢትዮጵያ የመለሱት ሌላ ቅርስ የለም።  

የኢትዮጵያ መሪዎች 
 ሥልጣን ላይ ሲያተኵሩ ግፍ የሠሩባት ለፍርድ ሳይቀርቡና በቢሊዮን ዶላሮች ሊቈጠር የሚችል ካሳ ጣልያንን ኣልኣስከፈሉም። 
  (ሆኖም ሓውልቱ ሮም ሲነቀልና ኢትዮጵያም ሲተከል ጣልያኖች ከኢትዮጵያውያን ጋር ተባብረዋል።) 
 ግን፤ ይባስ ብለው ጣልያኖች በ፳፻፬ ዓ.ም. ለግፈኛው ግራዚያኒ ሓውልት ስለሠሩ ከታሪክ መማር ሳይጠቅመን ኣይቀርም። 
  
   
  
 የቫቲካን ካቶሊክ ጳጳሶችም ከፋሺስት ጋር በመተባበር ወረራውን ቄሶቻቸው ስለባረኩና ስለሌሎች ጥፋቶችም ይቅርታ መጠየቅ እንኳን ከብዷቸዋል።  በእዚህ ጉዳይ ለሃገር በመቈርቈር ኢትዮጵያ ፍትሕ እንድታገኝ የሚታገሉ ኣሉ፦ ኪዳኔ ዓለማየሁ።  የኣሁኖቹም መሪዎች ስልጣን ላይ እየኣሉ ጣልያን ለግራዚያኒን የሠራችውን ሓውልት እስክታፈርስ 
 
 (እንደእነ ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም የኣሉትን ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን ከማሰር ይልቅ 
) ዲፕሎማቲክ ግንኙነት ማቋረጥ ያንስባቸዋል።

በ፳፻፮ ዓ.ም. ጄፍ ፒይርስ (Jeff Pearce) የሚባሉ ታዋቂ ካናዲያዊ ደራሲ ስለ ኢትዮጵያውያን ጀግንነትና ጣልያንን በድጋሚ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት በማሸነፍ ዓለምን እንደቀየሯት በጻፉት Prevail (ISBN: 978-1-62914-528-0 አና ISBN: 978-1-63220-096-9) መጽሓፋቸው የኢትዮጵያን በደል የማይረሱ ዛሬም እንዳሉ በማሳሰብ ስለ ኣክሱም ሓውልት ወደ ኢትዮጵያ መመለስ ሲያሰፍሩ ዶክተሩን (Dr. Aberra Molla) ገጽ 552 ላይ ጠቅሰዋል። “Besides Richard Pankhurst, who spearheaded the fight, there was Ethiopian-American scientist, Dr. Aberra Molla. There was...” በማለት ጽፈዋል። የፒይርስን መጽሓፍ መግቢያ የጻፉት ፓንክኸርስት ናቸው። 
  
 
 
 
 
 
  
 ስለ ዶክተሩ ኣስተዋጽዖ የኣሰሙም ጥቂቶች ኣሉ።  
 
  ኢትዮጵያን-ኣሜሪካን ፎረም ዶክተሩን የ2013 የዓመቱ ሰው በማለት ዕውቅና ሲሰጣቸው ከኣቀረባቸው ሥራዎቻቸው ኣንዱ ጣልያን የኣክሱምን ሓውልት በወጪዋ ስለኣልመለሰች እሳቸው ገንዘቡን ከዓለም ሕዝቦች በማሰባሰብ ሓውልቱን በትናንሹ ኣስቆርጠው ወደ ኢትዮጵያ ሊያስወስዱ እንደሚችሉ ከኣስፈራሩ በኋላ መሳካቱን ጠቅሷል። 
 በሓምሌ ፳፻፰ ዓ.ም. ዶክተር ኣበራ ንግግር እንዲያደርጉ የተጋበዙበት የዝነኛው ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ተቋም የግብዣ ደብዳቤ ትርጕም እንደሚከተለው ነበር። “ዓማርኛን ዲጂታይዝ በማድረግዎ ተወዳዳሪ የሌለው ዘመናዊ እድገት ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲኖር ኣድርገዋል፣ እንዲሁም ተጽንእዎ ባህላዊ ቅርሶችን ወደ ማስጠበቅ ዘልቆ የኣክሱምን ሓውልት ወደ ትግራይ ሲያስመልሱ በጉዳዩ ባይገቡበት ኖሮ ይህ የኢትዮጵያ ቅርስ ላይመለስ ይችል ነበር” ይላል። 
 የኢትዮጵያን ቅርሶች በማስከበርና በጥሩ ዓርዓያነት እ.ኤ.ኣ. በ2016 ሽልማት ተሰጥቷቸዋል። በቅርቡም በፕሮፌሰር ፓንክኸርስት ከእዚህ ዓለም በሞት መለየት የተነሳ ሓውልቱን ኣስመልክቶ ከሰይፉ ብሻው ጋር የተደረገ ቃለምልልስ እዚህ ኣለ። 
 ቀደም ብሎም (፳፻፯) ከኢሳት ሲሳይ ኣጌና ጋር በተደረገው ቃለ ምልልስ ስለ ኣክሱም ሓውልት ኣስተዋፅዖዋቸው እዚህ   ነበር። ዶክተሩ ከብዙ ዓመታት ቆይታ በኋላ ኢትዮጵያ ሄደው ሳለ የኣክሱምን ሓውልት ጎብኝተዋል። በኅዳር ፳፻፲ የኢትዮጵያ ቅርስና ውርስ ማሕበረሰብ በሰሜን ኣሜሪካ የዕውቅና ሽልማት ለዶ/ር ኣበራ ሞላ ሲሰጥ 
ከጠቀሳቸው ኣንዱ የኣክሱም ሓውልት ከሮም ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ ጣልያንን በማስፈራራት ወሳኙን እርምጃ የወሰዱ ኣርበኛ መሆናቸውን ነበር።  

በግንቦት 2008 ዓ.ም. በኣገራዊ የዕውቅናና የሽልማት ፕሮግራም ኣዲስ ኣበባ ሲደረግ ሟቹን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ጨምሮ ሌሎች 250 ሰዎችና ለሓውልቱ መመለስ ጥረት ያደረጉ የኣስመላሽ ብሔራዊ ኮሚቴ አባላትና ባለሃብቶችን የኣካበተ ነበር።  ለጥረቱ ሽልማት መሰጠት ያስፈለገው ኣንዳቸው ኣሜሪካ መጥተው ሓውልቱን ኣስመለስኩ ሲሉ ማን እንዳስመለሰ ከተነገራቸው በኋላ ነበር።

ስለ ዓማርኛ የጽሕፈት መኪና በዓማርኛም ሆነ በእንግሊዝኛ የተጻፉ ኢንተርኔት ላይ ብዙ የሉም። በእንግሊዝኛው እንደሚደረገው ኢትዮጵያውያን ፊደላቸውን በመጻፊያ መኪና መሣሪያ (Amharic typewriter / አማርኛ ታይፕራይተር)  ለመጠቀም ተመራምረው ከደረሱበት ዘዴ ፊደላቱን ቆራርጦ መቀጠል (Ligature) የኢ/ር ኣያና ብሩ የ፲፱፻፳፭ ዓ.ም. (እ..ኤ.ኣ. 1932) ገደማ ግኝት ሥራ ላይ ውሏል።  በእዚህ የተነሳ ኢንጂነሩ ለኢትዮጵያ ባለውለታ ሊቅ ናቸው። ከመቶ በታች መርገጫዎች የኣሉት የእንግሊዝኛ የመጻፊያ መሣሪያ ከሁለት መቶ በላይ ለሆኑት የዓማርኛ ቀለሞች እንዲብቃቃ ፊደላቱን ቆራርጦ መቀጠል ኣስፈለገ። “ሀ”፣ “ለ”፣ “ሐ”፣ “መ” እና “ሠ” ኣሉ እንጂ “ሁ”፣ “ሉ”፣ “ሑ”፣ “ሙ” እና “ሡ” ስለሌሉ የመቀነስ ምልክትን የመሰለ “-” ከሌላ መርገጫ በመክተብ “ሀ”፣ “ለ”፣ “ሐ”፣ “መ” እና “ሠ” ጎን በማስቀመጥ ቅጥሎቹ ካዕቦቹን ስለሚመስሉ ተመልካቹ እንዲቀበላቸው ሆነ። ኣንዱን መቀጠያ ብዙ ቀለሞች ሊጋሩት ስለሚችሉ የሁሉም ቀለሞች በኣለመኖር የተነሳ መርገጫዎች መቆጠብ ተቻለ። “ሃ” እና “ማ’ እንጂ “ሂ”፣ “ሚ”፣ “ሄ” እና “ሜ” ስለሌሉ “ሃ” እና “ማ” እግሮች ጎን መስመር ወይም ቀለበት በማስቀመጥ እነዚያን በሚመስሉ ቅጥሎች እንድንጠቀም ሆነ። እነ “ቻ”ን የመሰሉ ቀለሞች ከታችና ከላይ ከሁለት መርገጫዎች “ተ” ላይ በሚቀጠሉ ነገሮች ስፍራው ወደኋላ እየተመለሰ ሦስት ነገሮች ኣንድ ፊደል እንዲመስል ተሠሩ። ስፍራ ስለኣነሰ እንደነ “ኳ” ያሉ ቀለሞች “ካ” ስር በተቀመጠ መስመር በሚሠሩ ኣዳዲስ ቀለሞች ተተኩ። የ“ላ”ን ግራ እግር ማሳጠር ስለኣልተቻለ “ለ” ቀኝ እግር ላይ ከመስመር በታች በወረደ መቀጠያ የ“ለ” ቀኝ እግር ረዝሞ ያልተለመደ መልክ ይዞ ቀረበ። በመቀጠል ሊሠሩ ለማይችሉ ቀለሞች የእራሳቸው ስፍራ ሲሰጣቸው ቦታ ስለኣልበቃ ካልገቡት መካከል የዓማርኛ ኣራት ነጥብ ኣሉበት።  ስለዚህ የዓማርኛ የጽሕፈት መኪና የተመረኮዘውና ኣከታተቡ የተንፏቀቀ ፊደል በኣንድ የእንግሊዝኛ ገበታ ምትክ መቀጠል ላይ ነው። የዓማርኛ ቀለም ግን እየኣንድኣንዱ እራሱን የቻለ ስለሆነና ኣንድ የእንግሊዝኛ የፊደል ገበታ ስለማይበቃው የዓማርኛ የጽሕፈት መኪና ፊደል ዓማርኛ ኣይደለም።  ፊደላት ለኮምፕዩተር ሲሠሩ ተለያይተው እንዲቀርቡ ሲደረግ የታይፕራይተሮቹ ግን እንዲነካኩ ተንፏቅቀው የተሠሩ ስለሆኑ ቦታዎቻቸውን የኣልጠበቁም ናቸው። ይህ ሁሉ ሲደረግ እንደእነ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት የመሳሰሉት ሲጠቀሙ የነበሩት በትክክለኛዎቹ የግዕዝ ቀለሞች ነበር። የዓማርኛ የጽሕፈት መኪና   በዓፄ ኃይለሥላሴ ዘመን ተጀምሮ በደርግ ዘመን የኣበቃ የ፶ ዓመታት ግድም ዕድሜ የነበረው ቴክኖሎጂ ነው። የኣማርኛ ታይፕራይተር የሠሩ ሌሎችም ኣሉ።  የኣማርኛ ታይፕራይተር ቴክኖሎጂ ያበቃለትም ዶክተር ኣበራ ሞላ የግዕዝን ፊደል ኮምፕዩተራይዝ ኣድርገው እ.ኤ.ኣ. በ1987 ሞዴትን ለገበያ ኣሜሪካ ውስጥ ስለኣቀረቡ ነበር።

የዓማርኛ ፊደል የመክተቢያ ገበታና ዘዴ ስለ ኣልነበሩት ዶክተሩ ፊደሉን ወደ ኮምፕዩተር ሲያስገቡ ዘዴዎቹን ለመጀሪያ ጊዜ ከመፍጠር ሌላ  የዓማርኛ የመጻፊያ መኪና ቅጥልጥል ፊደልና ኣከታተቡ ወደ ኮምፕዩተር እንዳይገባ ጽፈዋል።  ኣንዳንዶቹም የቆዩና ኣዳዲስ ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው። 
፩ኛ. የዓማርኛ ፊደላት ኮምፕዩተራይዝድ ስለሆኑ ዓማርኛ ያልሆኑ ፊደላት መኖር ዋጋ የለውም። በእንግሊዝኛው የጽሕፈት መኪና በዓማርኛ ለመጠቀም የተሠራው ዘዴ ጊዜው ያለፈበት ቴክኖሎጂ ነው። እንኳን ዓማርኛውን የማይጽፍ የጽሕፈት መኪና በሚገባ እንግሊዝኛውን የሚጽፈው የእንግሊኛ የጽሕፈት መኪና ዋጋ ኣጥቶ ሙዚየም ገብቷል። ስለዚህ የኮምፕዩተር ኣከታተብ ማሰልጠኛዎች የኣማርኛ ታይፕራይተር ኣከታተብ ማስተማር መተው ይጠበቅባቸዋል። ፪ኛ. የእንግሊዝኛው የመጻፊያ መኪና የተሠራው ለእየኣንድኣንዱ የላቲን ፊደል መክተቢያና የመርገጫ ስም በመመደብ ሲሆን የዓማርኛው የመጻፊያ መኪና እነዚያን የሉትም። ዶክተሩ ለግዕዙ መክተቢያና የመርገጫ ስም ለመጀመሪያ ጊዜ ለኮምፕዩተር ፈጥረውለታል። ፫ኛ. የዓማርኛ የመኪና ፊደላት የሚሠሩት ለተወሰነ መጠን ተስተካክለው ወረቀት ላይ እንዲሰፍሩ ነው። በኮምፕዩተር ግን ኣንዱን መጠን መጨመርና መቀነስ ይቻላል። የመኪና ፊደላት ቁርጥራጮች መጠን ሲለወጥ ቅጥሎቹ ይደበቃሉ ወይም ክፍተታቸው ይጨምራል። የገጹ ስፋት ሲጠ'ብ ወይም ሲሰፋ ቅጥሎቹ ብቻቸውን ወደ ኣዲስ መስመር ሊዞሩ ይችላሉ። ቅጥሎቹ ስለሚበጣጠሱ ማሕተምን የመሳሰሉ ነገሮች ኣያሠሩም። ስለዚህ ቅጥልጥል የመኪና ቀለሞች የትክክለኛው ፊደል ተጠጊ እንጂ እራሳቸውን ችለው ሁሉንም ሥራዎች ስለማያሠሩ ኣስፈላጊ ኣይደሉም ብለው ዶክተሩ ጽፈዋል። በቅጥሎች ተንቀሳቃሽ የሚገላበጡ የሲኒማ፣ ቴሌቪዥና ቪድዮ ፊደላት ሊሠሩባቸው ኣይችልም። ፬ኛ. የላቲኑ የመጻፊያ መኪና እየኣንድኣንዱን ቀለም የሚከትበው በኣንድና ሁለት መርገጫዎች ሲሆን የዓማርኛው መኪና ከእዚያ በላይ መርጫዎችን ይጠይቃል። ስለዚህ ዓማርኛ ሳያስጽፍ ብዙ መርገጫዎችን መነካካት በሚያስፈልግ ዘዴ ግዕዝ ኮምፕዩተራይዝድ ሆኖ ከቀረበ ከ፴ ዓመታት በኋላ ዛሬም በ፳፻፱ ዓ.ም. መቀጣጠል ጥቅም የለውም።  በኣብሻ ሥርዓት የተከተበውን ትክክለኛ ቀለም ለመሰረዝም ኣንድ መርገጫ በቂ ነው። ለኣስቀጣይና ተቀጣይ ግን ኣንድ መሰረዣ በቂ ኣይደለም። 

፭ኛ. ወረቀት ላይ ሲሰፍሩም ሆነ የኮምፕዩተር እስክሪን ወይም መዝገብ ኣብዛኛዎቹ የዓማርኛ መኪና ፊደላት ከኣንድ በላይ ስፍራና ኮድ ይጠይቃሉ።  ይህ ወጪ ያስጨምራል። የግዕዝና የላቲን የኮምፕዩተር ፊደላት እያንዳንዳቸው የሚያስፈልጓቸው ኣንድ ስፍራ ብቻ ነው። ፮ኛ. የፊደል ዋና ዓይነቶች ሁለት ናቸው። ኣንደኛው የሁሉም ቀለሞች ስፋት እኩል (Fixed) ሲሆን ሌላው የተለያዩ (Proportional) ስፋቶች ያለው ነው። በቅጥልጥል የዓማርኛ የመጻፊያ መኪና ቁርጥራጮች ስፋታቸው እኩል የሆኑ ቀለሞች መሥራት ኣይቻልም። በእንግሊዝኛና ዶክተሩ ኮምፕዩተራይዝ በኣደረጉት ግዕዝ ቀለሞች ሁለቱንም ዓይነቶች መሥራት ይቻላል። ፯ኛ. ስፍራ ስለኣነሰ የግዕዝ ኣኃዞች ቀርተው የእንግሊዝኛው ቍጥሮች ብቻ የዓማርኛው ኣኃዛት ሆነው በዓማርኛው የጽሕፈት መኪና ቀርበዋል። ይህ ለግዕዙ ኣኃዞች መዳከም ኣንዱ ምክንያት ሆኗል። ግዕዝን ዲጂታይዝ ከማድረግ ሌላ ኣኃዞቹን ለማሟላት ዶክተሩ የግዕዝ ኣልቦ ሠርተው በማሰተዋወቅ ቊጥሮቹን ኣሟልተዋል።    ስለዚህ በኣማርኛ የጽሕፈት መኪና ድክመትና በግዕዝ ኣልቦ ኣለመኖር የተዳከሙት ኣኃዞቻችንን ኣሁን መጠቀም ይጠበቅብናል። በዶክተሩ ግኝት የተነሳ የግዕዝ ኣኃዞች ሠላሳ ናቸው። 

፰ኛ. ለዓማርኛ የጽሕፈት መሣሪያ እንዲስማማ ተብሎ ፊደል መቀነስና መቀንጠስ ተለምዶ ዶክተሩ ሁሉንም ቀለሞች ኮምፕዩተራይዝ ከኣደረጉ በኋላም መቀነስና መቀንጠስ እንደማያስፈልግ ግንዛቤ ማስጨበጥ ማስቸገሩ ቀጥሏል።  ለምሳሌ ያህል “ኳ”ን በ“ኩዋ” ማንበብ የሚፈልጉ ሲኖሩ ፊደሉን ኣጥፍተው በ“ካ” እና መቀጠያው ሲጠቀሙ የከረሙ ስለኣላዋጣቸው የቆራረጡትን እንደመተው መልሰው በመቀጠል የኣሌለ መልከ-ጥፉ ኣዳዲስ ቀለሞች በመጨመር እያስለመዱ ናቸው። ኳ እራሱን የቻለ መስመር ላይ የሚያርፍ ቀለም ነው። ካ ላይ በተቀጠለ መስመር ተሠርቶ በኣዲስ ቅርጽነት የተሠራው የተሳሳተ ፊደል ነው። ለምሳሌ ያህል የጡን መቀጠያ ለኩ የሰጠ ኣለ። የማተሚያ ቤቶች መደበኛው ፊደል ተቆራርጦ ሲቀርብ ቅጥልጥል ዓማርኛ ያልሆነ ፊደል ይኸን  ይመስላል።
ለኣንዳንቹም ይኸን ፊደል ከኣልተቀጠሉት የማተሚያ ቤቶች ቀለሞች መለየት ስለተሳናቸው ኣሁንም እየተወናበዱ ነው። ምክንያቱም የዓማርኛ የጽሕፈት መሣሪያ እንደ ቋ የኣሉትን ቀለሞች ስለሌሉት ከቀ እና መስመር በመቀጠል ሲያቀርቡ የነበሩትን እንደ ኣዲስ ፊደል የዩኒኮድ ፊደል መደብ እያቀረቡ ግዕዝ ያልሆኑ ነገሮችን በማሰራጨት ሰውን እያስቸገሩ ናቸው። የየን እንዚራን ለማይለዩ ኣንዳኣንድ ምሁራን ሁለት ዓይነት ቋ፣ ኋ፣ ኳ እና ጓ ዓይነት ቀለሞች ማቅረብ የሚጎዳ እንጂ የሚጠቅም ኣይደለም። ትክክለኛዎቹ የግዕዝ ቋ፣ ኋ፣ ኳ እና ጓ የእየእራሳቸው መልኮች ያሏቸው መስመር ላይ የሚያርፉ ቀለሞች ናቸው። በተጨማሪም ትክክለኛዎቹን ቀለሞች የሚያዩት የዶክተሩን ፊደል ወይም ትክክለኛዎቹን ያሏቸው እንጂ በተሳሳቱ ቀለሞች የሚያዩት የተሳሳቱትን ስለሆነ መወናበዳቸውን ላይረዱ ይችላሉ። 

፱ኛ. ከሚያስገርሙት ነገሮች መካከል ኣንዱን ለመጥቀስ ያህል 128 ስፍራዎች ይበቃሉ ብለው ሌሎች ለዩኒኮድ ሲያቀርቡ (ገልባጮች እንጂ) ከዶክተሩ በስተቀር ለዓማርኛ እንኳን እንደማይበቃ የሚያስተውሉና የሚጽፉ ምሁራን መጥፋት ነበር። በኋላም ቢሆን ቅጥልጥሎቹ እንደማያዋጡ ገባቸው እንጂ ሞዴት ፕሮግራም ውስጥ ጭምር የኣሉት የኣናሳ ተጠቃሚዎች የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ቀለሞች በቅጥልጥል እንዲሠሩ ስለፈለጉ የዩኒኮድ መደብ ውስጥ እንዳይገቡ በ፲፱፻፹፱ ዓ.ም. ሌሎች ኣስወግደዋቸው ነበር።  ፲ኛ. የኣማርኛ የጽሕፈት መኪና መሣሪያዎች ቁርጥራጮች፣ ኣከታተቦቻቸውና ኣመዳደቦች የተለያዩ ስለሆኑ ኣይናበቡም። ፲፩ኛ. የጽሕፈት መጻፊያ መሣሪያ ዓላማ በዓማርኛም ሆነ እንግሊዝኛ ፊደል ለመክተብ ነበር። ዓማርኛ የሚያስጽፍ የጽሕፈት መሣሪያ ግን ስለሌለ የኣማርኛ የጽሕፈት መኪና ዓላማ ቁርጥራጮችን ለመቀጣጠል ነው።  ግዕዝ ኮምፕዩተራይዝድ ስለሆነ መቀጣጠል ኣስፈላጊ ኣይደለም። ምክንያቱም እየኣንድኣንዱ የግዕዝ ኆኄ እራሱን የቻለ ቀለም እንጂ ቅጥልጥል ፊደል ኣይደለም። ፲፪ኛ. ቁርጥራጮቹ የተመደቡባቸው ስፍራዎች መደበኛ ስለኣልሆኑ ፕሮግራም በተቀየረ ቍጥር ለደራሲው እንኳን ላይነበቡ ይችላሉ። 

፲፫ኛ. ጽሑፉ የተጻፈበት ቁርጥራጮች ከሌሉ ጽሑፉ ኣይነበብም።  በግዕዝ ዩኒኮድ የተጻፈ ጽሑፍ ኮምፕዩተሩ ወይም የእጅ ስልክ ላይ በኣለው ኣንዱ የዩኒኮድ ፊደል ይነበባል። ጽሑፉን ኣቅልሞ ወደ ሌላ የግዕዝ ፊደል መልክ መቀየር ይቻላል። የታይፕ ቈርጥራጮች ዓማርኛ እንኳን ስለኣልሆኑ ወደ ዩኒኮድ ፊደል ሲቀየሩ ዝብርቅርቅ የላቲን ፊደል ይሆናሉ። ፲፬ኛ. ዶክተሩ ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ሲያደርጉ ፴፪ የላቲን ምልክቶችንና ሌሎችንም ለግዕዝ ኣውርሰዋል። የኣማርኛ የጽሕፈት መኪና መሣሪያዎች እንኳን ሌሎች የላቲን ምልክቶች መጨመር ሁሉንም ቀለሞች በመቀጣጠል በኣማርኛ እንኳን ኣያሠሩም። ፲፭ኛ. ኣንድን ጽሑፍ ለማረም ወይም ለማሻሻል የተጻፈበትን ኣከታተብ ዘዴ ዕውቅናና የመጻፊያው ኮምፕዩተሩ ላይ መኖርን ይጠይቃል። በነፃውና በሚሸጠው ግዕዝኤዲት ሲጻፍ የፊደል ገበታው እየታየ በመልቀም እንኳን መክተብ ይቻላል። በዩኒኮድ ፊደል የተጻፉትን በነፃው ግዕዝኤዲት ድረገጽ ላይ በመለጠፍ ማረምና ማሻሻል ይቻላል። በታይፕራይተር የተጻፉ ጽሑፎች ነፃው ግዕዝኤዲት ድረገጽ ላይ ሲለጠፉ ዝብርቅርቅ የእንግሊዝኛ ፊደል ሆነው ስለሚታዩ ማረምና ማሻሻል ኣይቻልም። ፲፮ኛ. የግዕዝ ሀሁሂ ቀለሞች እንደ እንግሊዝኛው ABC ስለሆኑ ትክክለኛና የተወስኑ መልኮች ስለኣሏቸው ፊደል የቈጠረ ሁሉ ያውቃቸዋል። ከኣስቀያሚ ቆብ፣ ሠረዞችና ቀለበቶች ሲሠሩ የነበሩት የኣማርኛ የጽሕፈት መኪና ቀለሞች ቀርተው ትክክለኛውን የማተሚያ ቤት ቀለሞች ወይንም ዶክተሩ ኮምፕዩተራይዝ ያደገረጉትን ቀለሞች መቆራረጥ ስለተጀመረ መለየት እያስቸገረ ነው። 

፲፯. የዓማርኛ የጽሕፈት መኪና ኣፍቃርያን በጀመሩት ሳይንሳዊ ያልሆነ ግትርነት ኣንድ ስፍራ የዩኒኮድ መደብ ውስጥ ሊቀርብ ይችል የነበረው የግዕዝ ቀለም ኣራት የተለያዩ ስፍራዎች ተበትኗል። ፲፰. የዓማርኛ ሞክሼዎች ይቀነሱ የሚለው ኃሳብ የመጣው ለኣማርኛው የጽሕፈት መሣሪያ ሲባልም ስለነበረ ያልተቀነሱትን ቀለማት ብቻ ማስተማር የቆዩ ጽሑፎችን ማንበብ የማይችል ትውልድ ሊያስከትል ይችላል። የግዕዝ ኣኃዛት የዓማርኛ የጽሕፈት መኪና ውስጥ ስለኣልነበሩ በኣሁኑ ጊዜ የዓማርኛ ኣኃዞችን የማይለዩ ምሁራን ኣሉ። ፲፱. የኣማርኛ የጽሕፈት መኪና ኣጻጻፍ ኣንድኣንዱን ቀለም ለመክተብ እስከ ኣራት መርገጫዎችን መጠቀም ስለሚያስከትል ትርፉ እጅ ማሳመም ነው ተብሎ ወደ ፲፱፻፺ ዓ.ም. ግድም ተጽፏል።  ፳. የዓማርኛ የጽሕፈት መኪና በኣንድ የእንግሊዝኛ የፊደል ገበታ ምትክ እንዲያገለግል የተሠራው ጊዜው ያለፈበት ቴክኖሎጂና ያልተሟላ ከመሆኑም ሌላ ሊሻሻልም የማይችል ስለሆነ ቀርቷል። ዩኒኮድ የተፈጠረው ብዙ መርገጫዎች ላይ የተበተኑትን ዶክተሩ ኮምፕዩተራዝ ያደረጉት የግዕዝ ቀለሞች የእየራሳቸው ኮዶች እንዲኖራቸው እንጂ ለቅጥልጥሎች ኣይደለም። ቅጥልጥልና ግማሽ ፊደሎችን ዩኒኮድ ኣያውቅም። የእንግሊዝኛ የመጻፊያ መሣሪያ እንግሊዝኛ ቀለሞችን ስለሚያጽፍ የእንግሊዝኛ የኮምፕዩተር ገበታ ሆኗል። የኣማርኛ የጽሕፈት መኪና ዓማርኛ ስለኣልጻፈና ስለማያጽፍ የዓማርኛ የኮምፕዩተር ገበታ መሆን የለበትም። ኣልሆነምም። ይህ የተዘረዘሩትንም ለማክ (Macintosh) ኮምፕዩተሮች የቀረቡትንም ያጠቃልላል።   

፳፩. የአማርኛ ታይፕራይተር ኮምፕዩተራይዝ ከተደረገ በኋላ ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ኣደረግን ከኣሉት ኣንዳንዶቹ ጥፋታቸውን ማረም ስለተቸገሩ እንዳይዋረዱ ዝም ስለተባሉ ኤክስቴንድድ ኣስኪ የሚችለው ስፍራ ላይ ቁርጥራጮችን ኣቅርበው ተጠቃሚውን ከሃያ ዓመታት በኋላም ማታለል መቀጠላቸው በየቃለምልልሶቹ ቀርበዋል።   ትክክለኛ የግዕዝ ፊደል መስለዋቸው በተቀጣጠሉ ፊደላት የተለያዩ ጽሑፎችና መጽሓፍት ሲጽፉ የከረሙ መታለላቸው ሲገባቸው የተበሳጩና እርዱን የኣሉን ኣሉ።   በትክክለኛ ፊደላችን የተጻፉትን ወደፊት በተለያዩ ዓይነቶች ማቅረብ ስለሚቻል መጽሓፎችንም በኢንተርኔት መሸጥና ማንበብ ይቻላል፦ ምሳሌ ፒ.ዲ.ኤፍ.(PDF)። ፳፫. በኣማርኛ የጽሕፈት መሣሪያ ዓማርኛ ብሬል መጻፍ ኣስቸጋሪ ነው።  ፳፬. ኢንጂነር ተረፈ ራስወርቅ በቅጥልቅል የዓማርኛ ፊደል የሚሠራ የመጀመሪያውን ቴሌክስ መሣሪያ የፈጠሩ ኢትዮጵያዊ ሊቅ ናቸው።  ዓማርኛ ያልሆነውን የቅጥልጥቅል ፊደልና የኢትዮጵያን ፊደላት የማይለዩ ኢንጂነሩ የኣልኣሠሩትን በፊደሉ ኣሠሩ የእሚል ጽሑፍ እዚህ ኣለ።  ኣንድኣንድ ደራስያን ስለ ሳይንስ ከመጻፋቸው በፊት መረጃዎችን መመልከት ቢጀምሩና ቢያቀርቡ ሳይጠቅም ኣይቀርም። ምክንያቱም ኮምፕዩተር የኢትዮጵያን ፊደላትና ኣኃዞች የተረከበው በኮምፕዩተር ዘመን ከማተሚያ ቤቶች እንጂ ችሎታውን ከኣልነበረው የቴሌክስ መሣሪያና ዘመን ኣልነበረም። አንዲሁም ኮምፕዩተር የኢትዮጵያን ፊደላትና ኣኃዞች የተረከበው በኮምፕዩተር ዘመን ከማተሚያ ቤቶች እንጂ ችሎታውን ከኣልነበረው የኣማርኛ የጽሕፈት መሣሪያና ዘመን ኣልነበረም።

፳፭. የኣማርኛ ታይፕራይተርና ለኮምፕዩተር የተሠራው ፊደሉ እንኳን ግዕዝን ኣማርኛ ቀለሞች ኣላስከተበም። በኣንድ የእንግሊዝኛ መደብ (Character set) ምትክ የተሠራውን የኣማርኛ የጽሕፈት መኪናና የኮምፕዩተር ቅጥልጥል ፊደል በሓሰት ግዕዝ (Ethiopic) ነው በማለት ሰውን የሚያወናብዱ ኣሉ። ኣንድ የእንግሊዝኛ ፊደል ሥፍራ ለኣማርኛ ስለማይበቃ ሳይንስን ኣለመደገፍና እነዚህን ኣለመቃወም ግዕዙን እያበላሸው ነው። ፳፮. ግዕዝን ዲጂታይዝ ወይም ኮምፕዩተራይዝ ማድረግ ሳይንስ እንጂ ልብወለድ ኣይደለም። የኣማርኛውን ታይፕራይተር ፊደል ዲጂታይዝ ኣድርጎ ግዕዝን (Ethiopic) ዲጂታይዝ ኣደረግሁ  የሚለውን በዝምታ ማሳለፍ ቦዘኔ ምሁራን ሳይንስን ወደ ልብወለድ እንዲቀይሩ እያበረታታ ነው። የታይፕራይተር ቁርጥራጮችን ኣቅርቦ ከማተሚያ ቤት ኣዲስ ዘመን ጋዜጣ ፊደላት ዓይነቶች ጋር ተመሳሳይ ናቸው የሚለውን ወሬኛ ወይም ሶን ፊደል ለመጻፍ የሰ ግራ እግር ላይ መሰመር ጨምሮ የሰን ቀኝ እግር ኣሳጠርኩ የሚለውን ወይም የግዕዝ ፓተንት ሳይኖርው ኣለኝ የሚለውን የኣለመረጃ የሚያሳልፍ ጋዜጠኛ መተቸት ካልቻልን ፊደላችን ከኩራታችን ምንጭች ኣንዱ መሆኑ ቀርቶ የዓለም መሳቂያና መሳለቂያ ሊያደርገን ይችላል። ይህ ለኢትዮጵያ የሚጠቅሙ ሥራዎች የሠሩ ኢትዮጵያውያን እንዳይታወቁ የሚሰርዙትን እያበተረታታ ነው።  ሶፍትዌር የሚሠሩ ሠራተኞች እንደማንኛውም ሥራ ለጊዜዎቻቸውና ውጤቶቻቸው መከፈል ስለኣለባቸው ዶክተሩ በነፃ ማደል ኣልቻሉም። ገልባጮች ቀን፣ ፀሓፊና መረጃ በሌላቸው ልብ ወለዶች Legends እና Pioneers ተብለውበታል። ፳፯. የአማርኛ የታይፕራይተር ፊደል የግዕዝ ፊደል ኣይደለም። የማተሚያ ቤቶቻችን ፊደልም ኣይደለም። የእውሸት የዓማርኛ (Fake Amharic) ፊደል እንጂ የዓማርኛም ፊደል ኣይደለም። መጽሓፍትም ሲታተሙ የነበሩት በግዕዝ ፊደል በማተሚያ ቤቶች ነበር። ኣሁንም ቢሆን በድሮው የማተሚያዎቹ ዓይነት ወይም ዶክተሩ ኮምፕዩተራይዝ በኣደረጉት የዩኒኮድ የዓማርኛ ፊደል ነው። የታይፕራይተርንና በቅርቡም ተቈራርጠው ሲቀጣጠሉ የነበሩትን የማተሚያውን ፊደላት የማይለዩና ሁለቱ ኣንድ የሚመስሏቸው ኣሉ። የግዕዝ ዩኒኮድ ፊደል ከአማርኛው የታይፕራይተር ነገሮች ጋርም ግንኙነት የለውም።  የአማርኛውን ታይፕራይተር ፊደል ግዕዝ እያሉ ስለጉዳዩ ያልሰሙትን ማታለልና ኣዳዲስ የታይፕራይተር ቁርጥራጮች ፊደላትን በመሥራት ጊዜዎቻቸው እየተባከነባቸው የኣሉ ኣሉ።  ኦሮምኛም የእራሱ የግዕዝ ፊደል ስለኣለው ችግር ቢኖር እንኳን መፍትሔ ይፈጠርለታል እንጂ መቀጣጠል ኣስፈላጊ ኣይደለም። ፳፰. የኣማርኛ ታይፕራይተር እንደ ማተሚያ ቤቶች ፊደሎቻችን የግዕዝን ዜሮ ሳያውቁ የኣረብኛውን ኣልቦ በመውረስ እንዘልቅ ነበር።

፳፱. ከአማርኛ የጽሕፈት መኪና ኣጠቃቀምና ኣስተሳሰብ መላቀቅ ተቸግረው የግዕዝን ኣራት ነጥብ (ዓቢይ ነጥብ) በሁለት የላቲን ሁለት ነጥብ እየከተቡ የዓማርኛውን የዩኒኮድ ጽሑፍ እያበላሹ የኣሉት ደራስያን ቍጥር ብዙ ነው። የእዚህ ስሕተት ምንጭ የግዕዝን ኣራት ነጥብ የሌለው የአማርኛ የጽሕፍት መሣሪያ የአማርኛ ቁቤ ኣጠቃቀም ነው። በኮምፕዩተሮችና የእጅ ስልኮች ኣጠቃቀም ሁለት ባለ ሁለት ነጥቦች ጎን ለጎን ስለተቀመጡ የዓረፍተ ነገሮች መዝጊያ የሆነው የኣራት ነጥብ ምልክት ኣይደሉም። ለምሳሌ ያህል በግዕዝኤዲት ኣራት ነጥብ የሚከተበው በ“ዝቅ” (“Shift”) እና “፫” (“3”) ቊልፎች መርገጫዎች ነው። ፴. ለተለያዩ የፊደል መጠኖች ለእየብቻቸው የሚገጣጠሙ ቀለሞችን መሥራት ኣድካሚና የማያዛልቅ ሥራ ነው። ለኣሥራ ሁለት ፖይንት የተሠራው ፊደል መጠን ሲለወጥ ፊደላቱ ይበላሻሉ። የአማርኛው ታይፕራይተር የእራሱ ፊደል ስለሌለው እንደግዕዝኤዲት ዩኒኮድ ዓይነት የኣለውን ፊደል እየቆራረጡ በመቀጠል ሰዉን ሲያወንናብዱ ቆይተዋል። ምክንያቱም ገልባጮች ኣስቀያሚ መቀጣጠያዎቻቸውን መቀጣጠል (Ligation) ትተው ይኸን የማተሚያ ቤቱም ትክክለኛ ፊደል ቈራርጠው መቀጠል ስለጀመሩ ነው። የሚያቀርቡትም ጥቂት ዓይነቶች የፊደል መጠኖች ብቻ በመሆኑ ፊደላቱን ለማሳደግ ወይም ለማሳነስ ሲፈለግ ይዛነፋሉ። (ምሳሌ- ፊደል ሶፍትዌር) ፴፩. ለመቀጠል ሲባል ኣስቀጣዮች በወጉ ስለማይሠ'ሩ ስፍራዎቻቸውን የለቀቁ ቀለሞች ናቸው። በእዚህ የተነሳ የታይፕ ፊደላት የተዛነፉና ክፍተቶች የበዙባቸው ናቸው። ፴፪. እ.ኤ.ኣ. በ1987 በአማርኛ የእጅ ጽሑፍ ፊደል በኮምፕዩተር የተጻፉ ገጾች ምሳሌ እዚህ ሰምና ወርቅ መጽሔት የገጾቹ ሥዕሎች አሉ። 

፴፫. የአማርኛን ታይፕራይተር የፈጠራ ቀለሞች Ethiopic ወይም ግዕዝ እያሉ የሚያወናብዱና የሚተባበሩዋቸው ጋዜጠኞች ኣሉ። ዶክተሩን የታይፕራይተር ኣፍቃርያን ኣሸንፈው ቢሆን ኖሮ ግዕዝን ኣንድ የፊደል ገበታ ላይ በኣሉት ሥፍራዎች መጠቀም ስለማይቻል ትርፉ ውርደት ይሆን ነበር። ፴፬. የአማርኛን ታይፕራይተር የፈጠራ ቀለሞች እንደ ዓማርኛው የኦሮሞውንም የግዕዝ ፊደል ስለኣልጻፉ ኣንድኣንድ ኦሮሞዎች በላቲን ፊደል እንዲጠቀሙ ኣንዱ ምክንያት ሆኗል። ፴፭. በፊደል ቆራጮች ለዩኒኮድ እዚህ  የቀረበው ሥራ ላይ ያልዋለው የማተሚያ ቤቱ ፊደል ኣቀራረብ ለይስሙላ ብቻ ነበር። ምክንያቱም ስምንት በኣሥራ ስድስት ማለትም 128 ሥፍራዎች በቂ ኣይደሉም። የኣማርኛ ታይፕራይተር ወደ ኮምፕዩተር የገባው በኣስቀያሚ ቀጫጭን ቁርጥራጮች እንጂ በእነዚህ የተቆራረጡ ትክክለኛ የግዕዝ ቀለሞች ቍርጥራጮች ኣልነበረም። የትክክለኛ የግዕዝ ቀለሞችን ቍርጥራጮችንም ግዕዝ ነው ማለትም ቅጥፈት እንጂ ሳይንስ ኣይደለም። በኣስቀያሚ ቀጫጭን ቁርጥራጮች አማርኛ የጽሕፈት መኪና ፊደሎች ምን አንደሚመስሉ አዚህ  የኣለውን የኢትዮጵያ መዝሙር ገጽ ማየት ይቻላል። ሌላ ምሳሌ አዚህ ጎን የኣለው የ፲፱፻፹፪ ዓ. ም. የኣቶ ኣበበ ሙሉነህ ደብዳቤ ሥዕል ነው።  ፴፮. ፊደል ቀናሾችና ቀንጣሾች ኣስቀያሚዎቹን የታይፕራይተር ፊደል ትተው የዶክተሩን ዓይነት ትክክለኛ ቀለሞች መቀንጠስ ጀምረው ሁሉንም የግዕዝ ፊደላትና መጻፊያ ስለሌላቸው ያልቀነጠሷቸውን ከሌላ በመውሰድ ኣንባቢውን በማታለል ቀጥለውበታል። ለምሳሌ ያህል የኣቶ ዘውዴ ረታ “የኤርትራ ጉዳይ” መጽሓፍ ርዕስ የውጭውና የውስጡ “ጉ” ቀለም መልኮች የተለያዩ ናቸው። ኣንድኣንዱቹም ሲቀጥሉ የነበሩትን “ኳ”ን የመሰለ “ካ” እና መስመር ወይም “ቋ”ን የመሰለ “ቀ” እና መስመር መልሶ በቅርቡ በመቀጠል የዩኒኮድ ሥፍራ ላይ ጭምር በማቅረብ የተሳሳቱ ቀለሞችን በማስተዋወቅ ፊደሉን የማያስተውለውን ምሁር የሌለ ፊደልን ግዕዝ (Ethiopic) ነው እያሉት በማወናበዱ ገፍተውበታል። እንኳን 128 ቀርቶ 256 የኣንድ የእንግሊዝኛ ፊደል ተራዝሞም (Extended  ASCII) ስፍራዎቹ ስለማይበቁ በቅጥልጥል የግዕዝ ፊደላችንን መጻፍ ስለማይቻል ዶክተር ኣበራ ሞላ ባይኖሩ ኖሮ ኣንድኣንድ ውሸታሞች የግዕዝ ፊደልን በተለመደው ሓሰታቸውና ዩኒኮድንም በመጠቀም ገድለውት ነበር። 

፴፯. የኣማርኛ የታይፕራይተር ፊደል የተሠራውና በኮምፕዩተር የተሠራለትም ዓይነት በኣንድ የእንግሊዝኛ ASCII ፊደል ምትክ የቀረቡ የእውሸት ነገሮች ነው። ዶክተሩ ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ የኣደረጉት ለመጀመሪያ ጊዜ የግዕዝ ፊደላቱን በስምንት የእንግሊዝኛ ASCII ፊደላት ምትክ በመጠቀምና በመበተን ነው። ፴፰. የኣማርኛ ታይፕራይተር ትክክለኛዎቹን ፊደላት ስለሌሏቸው የሚቀጣጠለው ፊደል ትክክለኛ ላይሆን ይችል ነበር። ለምሳሌ ያህል የግዕዝ “ጯ” ፊደል ኣንድ ወጥ የግዕዝ ቤቱ ሦስተኛው እግር ላይ የተቀረጸ መስመር ያለው ሲሆን ፊደሉን በሚገባ የማያስተውሉ፣ ታይፕራይተር ተጠቃሚዎችና ተማሪዎቻቸው ፊደሉ የሚሠራው “ጫ” ስር መስመር በመጨመር የሚመስሏቸው ኣሉ።  ፴፱. ዶክተሩ ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ እንደኣደረጉ የማያውቁ ዓዋቂዎችም ኣሉ።   ፵. ኣንድኣንዶቹም የታይፕራይተር ቅርጾች ወይም ሌሎችንም የሚከተቡት ከሁለት በላይ መርገጫዎችን በመጠቀም ነው።  

፵፩. ኣንድኣንድ ሰዎች ዶክተሩ የሠሯቸውን የተሟላውን የዓማርኛ የታይፕራይተር ፊደል መልክ ስላላሳዩ የሚገርማቸው ኣሉ። ዶክተሩ ፊደሉን የሠሩት ፊደል የሌላቸው ሰዎች ስለ ኤድስ የጻፉትን ዓይነት ጽሑፍ በነፃ እንዲያነቡበት የለቀቁት ሲሆን GeezEdit Amharic P የሚል ስም የሰጡትን ያልተሟላ ወደ AmharicQ በመቀየር የሚያድሉ ሌባዎችም ስለበዙ ነው።  

ዶ/ር ኣበራ ሞላ ዕድል በኣገኙ ቍጥር ችሎታቸውን ለሌሎች ከማስተማርና ስለሚያውቁት ከማስረዳት ኣይቆጠቡም። ለምሳሌ ያህል በ፳፻፭ ዓ.ም. ከኣንድ የዋሽንግተን ዲ.ሲ. የዓማርኛ ሬድዮ ጣቢያ ጋር ስለ ጥሬ ሥጋ (Raw meat) ገለጻ ኣድርገው ነበር። ኢትዮጵያውያን ጥሬ ሥጋ ከሚበሉ ሕዝቦች መካከል ስለሆኑ   ኣትብሉ ማለት ብቻ ትክክል ስለኣልሆነ የሚያዋጣው በምርምር የተደገፉ መረጃዎችን ማቅረብ ነው።     በኣሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚደረገው ከብት በየቦታው እየታረደ ይበላ ስለነበረ ዩናይትድ እስቴትስ (ኣሜሪካ) ውስጥ እንዲቀር ተወስኖ በ፲፰፻፺፱ ዓ.ም. ፌዴራል ድንጋጌ የኣልተመረመረና ንጹህ ያልሆነ ሥጋ ለሕዝብ ማቅረብ ክልክል ነው።  ሕጉን ኣለማወቅ መከላከያ ኣይደለም። ሥጋው የተመረመረ ለመሆኑ ማሕተሙን ማየት ያስፈልጋል። እንዲህም ሆኖ ኣንድ ሰው የእራሱን እንሰሳ ኣሳድጎና ኣርዶ ሳያስመረምር ቤተሰቡን ብቻ የማብላት መብት ኣለው። 

ጥሬ ሥጋ ጀርሞች ኣሉት። ስለዚህ የሚከተሉትንም ማወቅ ጠቃሚ ነው።  ፩. ኣንድ እንሰሳ ሲታረድና ቆዳው ሲገፈፍ ጀርሞች በተለያዩ ሁኔታዎች ሥጋው ውጭ ላይ ስለሚቀሩ ያንን ማስወገድ ኣይቻልም። ቆዳ ሲገፈፍ ቢላው እንዲጸዳ ሙቅ ውሃ ውስጥ እየተነከረ ነው። ፪. እንደ ባክቴሪያ የኣሉ ጀርሞች በእየ20 ደቂቃዎች ሁለት በመሆን ይራባሉ። ይኸን እርባታ ቅዝቃዜ ያዘገየዋል። ስለዚህ እንሰሳው እንደታረደ ሥጋው ጥቅም ላይ ከኣልዋለ ሁልጊዜ መቀዝቀዝ ወይም መፈረጅ (ፍሪጅ ውስጥ መቀመጥ) ኣለበት። ለብዙ ጊዜ መቀመጥ ከኣለበት ሥጋው ከውሃ በረዶ ቅዝቃዜ በኣነሰ ወይም መፈረዝ (ፍሪዘር መግባት) ኣለበት። ፫. ኣንድ እንሰሳ ከመታረዱ በፊትና ከታረደ በኋላ በእንስሳት ሓኪም መታየት ኣለበት። ሓኪም ከሌለ ረዳት ሓኪሞች ወይም በሥጋ ምርመራ የሰለጠኑ ኣይተው ኣጠራጣሪውን ለእንስሳት ሓኪም የሚያቆዩበት መዘጋጀት ኣለበት። ምክንያቱም ሓኪሞች ብቻ የሚያውቋቸው ከእንስሳት ወደ ሰዎች የሚተላለፉ ብዙ በሽታዎች ስለኣሉ ነው።      
፬. ሥጋ ውስጡ ንጹህ ነው። 

፭. እንጨት ልሙጥ ስለኣልሆነ ለጀርሞች መደበቂያ ስለሚያገለግል ለብዙ ሰዎች የሚቀርብ ሥጋ ሲዘጋጅ መክተፊያ፣ የቢላው እጀታና ማቅረቢያው እንጨት ባይሆን ይመረጣል። ፮. የኮሶ በሽታ ሰውን የሚይዘው ያልተመረመረ ጥሬ ሥጋ በመብላት ነው። የኮሶ በሽታ ያለበት ሰው በየሜዳው ሰገራ ሲወጣ ከብቶች የኮሶውን እንቁላል ከሳር ጋር በመብላት ይበከላሉ።  የኮሶ ትላምነት የኋላ-ቀር ሕዝብ የሰው በሽታ እንጂ የከብት በሽታ ኣይደለም። ፯. ሥጋ ጀርሞች ስለኣሉት ሲዘጋጅ ሳይበስሉ ከእሚበሉ እንደሰላጣ የኣሉ ምግቦች ጋር መነ'ካካት የለበትም። ፍሪጅ ውስጥም ሥጋን ከታች ማስቀመጥ ጠቃሚ ነው። ፰. ሥጋ የኣለው የበሰለ ለብዙ ሰዎች የሚቀርብ ምግብ ጀርሞች እንዳያድጉበት እንደሞቀ እንዲቆይ ከኣልተደረገ በሁለት ሰዓታት ውስጥ ከኣልተበላ ወደ ማቀዝቀዣ ማግባት ጠቃሚ ነው። ማቀዝቀዣ ያልሞቀ ምግብ ማቀዝቀዣ ነው። 

፱. የበሰሉ ሥጋ-ነክ ምግቦችን ማቀዝቀዣ (ፍሪጅ) ውስጥም በንጽሕና ማስቀመጥ ጠቃሚ ነው። ምክንያቱም እንደ ሊስቴሪያ (Listeria) የኣሉ ባክቴሪያዎች ማቀዝቀዣም ውስጥ ስለሚያድጉ ነው።  ፲. ሥጋን ማብሰል የኮሶውን እንቁላል ይገድላል። የኮሶ ትል (Taenia saginata) እንቁላል ያለበትን ጥሬ የከብት ሥጋ ለሁለት ሳምንታት ፍሪዝ ማድረግም ይገድላቸዋል። ፲፩. ኣልፎ ኣልፎ ሥጋ እየበሉ ስለታመሙ ሰዎች ይሰማል።    ፲፪. ኣንድ ሰው በኮሶ በሽታ ከተያዘ በኣንድ ጊዜ የሚኖረው ኣንድ የኮሶ ትል ብቻ ነው።  

፲፫. ጥሬ ሥጋ ውስጥ የኣሉ ጀርሞች ኣደገኝነት ሕጻናትና በቂ መድኅን የሌላቸው እንደኤድስ በሽተኞችና ኣዛውንት ላይ የበረቱ ናቸው። ፲፬. ለትላልቅ ድግሶች በስለው ፍሪዝ የተደረጉ ሥጋ-ነክ ምግቦችን ለማብሰል ከበረዶነታቸው እንዲሟሙ እንደ እቃው ትልቅነት እስከ ሦስት ዕለታት (፸፪ ሰዓታት) ሊያስፈልጉ ይችላሉ። ፲፭. ጥሬ ሥጋን የተመለከተው ሕግ ሌሎች እንስሳትንም ይመለከታል። ፲፮. ኣንድ ከብት ለምግብነት እንዲያልፍ ወይም እንዲወድቅ የመወስን ሥልጣን የኣላቸው የእንስሳት ሓኪሞች ብቻ ናቸው። 

፲፯. የሚሰራጭ ካንሰር የኣለበት እንሰሳ ለምግብነት ኣያልፍም። የኣልተሰራጨ ካንሰር በማየት የሚያውቁና የሚጠረጥሩ ሓኪሞች ናቸው። ፲፰. ጥሬ የኣሳማ ሥጋ ከመብላት ሰው የሚኖረው የኮሶ በሽታ ኣደገኝነት የከፋ ነው።  
፲፱. ጥሬ ሥጋ መብላትና ጥሬ ኣሳ (ሱሺ) መብላት ኣንድ ኣይደለም። ፳. ኣንድ ጀርም ሰውና የተለያዩ እንስሳት ውስጥ የተለያዩ በሽታዎች ሊያመጣ ይችላል። ለምሳሌ ያህል ኣባሰንጋ (Anthrax) ኣእዋፍን ኣይተናኰልም። 

፳፩. ኮሮናቫይረስ (Coronavirus)  ከጥሬ ሥጋ እንደሚተላለፍ ወይም እንደማይተላለፍ መረጃው ስለሌለ ሥጋን በጥንቃቄ መያዝና ኣብስሎ መብላት ይመከራል።      በነገራችን ላይ ኮሮናቫይረስ እንጂ ኮሮና ወይም ኮሮና ቫይረስ የሚባል ቫይረስ የለም። በእንግሊዝኛም ስሙ coronavirus ነው። 

የእጅ ወይም ተንቀሳቃሽ ስልክ ለእንግሊዝኛ ኣጠቃቀም ከተሠራ ፵ ዓመታት ቢያልፉም    ለዓማርኛ ሥራ ላይ ማዋል ይቻላል።  ግዕዝኤዲት ለኣፕል ኣይፎን 6 (iPhone 6 GeezEdit app)  ከኣፕሮባቲክስ (Approbatics) ቀርቦላችኋል።  

 በኣፕል ኣይፓድም (iPad) ያስከትባል። ከኣይፎን 4ኤስ (iPhone 4s) ወዲህ ለተሠሩትም ኣዲሱን የኣይኦኤስ 8 (iOS 8) ሥርዓት በማስገባት ማሻሻል (Upgrade) በዓማርኛው መጠቀም ያስችላል። GeezEdit (Amharic Typing) ከኣፕ ሱቅ (App Store) ወይም ኣይቲዩንስ (iTunes) ወደ ኣይፎን 6 የእጅ ስልካችን ስናስገባ Allow Full Access የሚለው ከፊደል ገበታዎች ኃይል ጋር ያሉትን ልዩ ጥቅሞች ለመጠቀም የሚያስፈልግ ስለሆነ ለጊዜው መዝለል ይቻላል። እንዲህም ሆኖ ኣፕል እንጂ የኢትዮጵያ ኮምፕዩተሮችና ሶፍትዌር የገዥዎችን ክሬዲት ካርድና ኣድራሻ ኣያውቅም። ይህ ለኣዲሱ የኣፕል የእጅ ስልክ የተለያዩ ቍሳቍሶች ውስጥ እንዲሠራ የቀረበው ቁስ ኣከታተብ የባለቤትነት መብቱ ለዶክተሩ ሊሰጥ እየተጠበቀ ባለው ኣብሻ ዘዴ ለዊዶውስና ማክ ኮምፕሩዩተሮች መክተቢያ በነፃ ከተሰጠውና ከሚሸጠው ግዕዝኤዲት ጋር ኣንድ ዓይነት ነው። ለተወስነ ጊዜ ዋጋው ዶላር ፩.፱፱ (1.99) ነው። ቁሱ ተወዳጁን የግዕዝኤዲት ዩኒኮድ (GeezEdit Unicode) የዓማርኛውን ፊደል ይጨምራል። የግዕዝ ፊደል ያላቸው የኣንድሮይድ ስልኮችም ከኣይፎን የተላከላቸውን ማስነበብ ይችላሉ። የፊደል ገበታው ለጊዜው ለዓማርኛ ብቻ ቢሆንም ሁሉንም የግዕዝ ቀለሞች ማለትም ፣ ፣  እና  ከኣንድ ገበታ እንዲያስከትብ የተሠራ ነው። እየተሻሻለ ስለሆነም የሌሎች ቋንቋዎቻችን መክተቢያዎች እንደኣስፈላጊነታቸው ወደፊት ይከፈታሉ።

ከኣፕል ሱቅ GeezEdit App ቁስ ከተገዛ በኋላ ኣዶው ስር Amharic Typing የሚል ስሙ ይታያል። ከእዚያ Settings፣ General፣ Keyboard፣ Keyboards በኩል Amharic Typing ገበታውን መጫንና
ወደ Settings ከእዚያ General ተመልሶ በProfile በኩል GeezEdit Font ፊደሉን በInstall ማስገባት ያስፈልጋል። GeezEdit ሲከፈት የሚታየው እንግሊዝኛ ስለሆነ ለዓማርኛው የዓለም ካርታ ያለበትን ኣዶ መጫን ነው። ተጭኖ መቆየትም “Amharic Typing” “ኣማርኛ” የሚለው የፊደል ገበታ እንዲመረጥ ያቀርባል። ለኣጻጻፉ “Help”  የሚለውን በኣማርኛ ወይም እንግሊዝኛ/English ማንበብ ይጠቅማል። ግዕዝኤዲት ኣንዴ ከተጫነ ጽሑፍ የሚያስፈልጉበት ቦታዎች ሁሉ ከእንግሊዝኛው ገበታ ስር በዓማርኛ ለመጻፍ ዝግጁ ስለሆነ የሚያስፈልገው ገበታውን መክፈት ብቻ ነው። የግዕዝኤዲት ገጽ ላይ ከትቦና ኮፒ ኣድርጎ ሌሎች ስፍራዎች መለጠፍ ሌላ ዘዴ ነው። በግዕዝኤዲት የተጻፈን የዓማርኛ ጽሑፍ በፋይል መልክ ለማስቀመጥ ወደ “ኖትስ”  (“Notes”) መገልበጥ ወይንም ኖትስ ውስጥ መክተብ ጠቃሚ ናቸው። 

ቀደም ብሎም ለእጅ ስልክ ዓማርኛውን ለመጀመሪያ ጊዜ ማቅረባቸው ቢታወስም ዓማርኛ ከዓለም ቋንቋዎች መደብ እንዲገባ ኣፕል (Apple) ገበታችንን እንድናስገባ ስለወሰነና የመጀመሪያው ኩባንያ በመሆኑ ምስጋና ይገባዋል። የግዕዝኤዲት ቁስ የተለያዩ የኣይፎን 6 የእጅ ስልክ ፕሮግራሞች ውስጥ እንድንሠራ ኣዲስ ችሎታ ኣስገኝቷል። ቴክስት (Text)፣ ኢ-ሜይል (Email)፣ ትዊተር (Tweeter) እና በመሳሰሉት ተደሰቱ። በኣሁኑ ጊዜ ኣንዳንድ ድረገጾችና ጽሑፎች ግን ላይነበቡ የሚችሉት በሌሎች ምክንያቶች ሲሆን ችግር የሌላቸው ድረገጾች ምሳሌ እዚህ  ኣለ። ለምሳሌ ያህል እንደነፃው የግዕዝኤዲት ገጻችን  የመሳሰሉት በኮምፕዩተር የሚነበቡት በኣዶቢ ፍላሽ ስለሆነና ኣፕል ፍላሽን ስለማያስገባ ድረገጹ ባይነበብ ችግሩ የግዕዝኤዲት ኣይደለም። ወጪና ጊዜ ያስጨምራል እንጂ ለኣንዳንዳቹም ተግዳሮት መፍቻ ዘዴዎች ኣሉ። ኣንዳንድ ፕሮግራሞችም በእንግሊዝኛ እንጂ በዩኒኮድ ፊደላት የመጠቀም ኃይል ገና የላቸውም። ምሳሌ ለመጥቀስ ያህል ፌስቡክን በድረገጽነት ማንበብ የዓማርኛውን ቀለሞች በኣለማቅረብ ሳጥን ስለሚያደርጋቸው በፌስቡክ ቁስ (Facebook App) መጠቀም ያስፈልጋል። ኣይኦኤስ ፰.፫ እነዚህን ችግሮች ስለኣስወገደ ግዕዝ ብዙ ፕሮግራሞች ውስጥ ይሠራል። ከጉግል፣ ቢንግ፣ ያሁ፣ ሳፋሪ የመሳሰሉት ሌላ ይኸን የዓማርኛ ውክፔድያ ገጽ ያስነብባል፣ ያስከትባልም። ለተጨማሪ መረጃ የግዕዝኤዲት ፌስብክ ገጽ መከታተል ይጠቅማል። የፌስቡክ ኣጓዳኙም እዚህ  ኣለ።

በኣይፓድና ኣይፎን ግዕዝኤዲትን ለመጠቀም ለጊዜው እንግሊዝኛውን በቋንቋነት በLanguage  Region በኩል ትቶ ኣማርኛን ኣንደኛ ማድረግ ይሻላል። ኣንድኣንድ ፕሮግራሞች የተሠሩት ለእንግሊዝኛው ብቻ ስለሆነ በሚገባ ከኣልሠሩ ወደ እንግሊኛ መመለስ ያስፈልጋል። ኣይፎንና ኣይፓድ ለኣለው ግዕዝኤዲት ዩኒኮድ ፊደል ጨምሮ የሚከፈለው $1.99 ለሦስቱም ነው። የኮምፕዩተሩና የስልኩ ግዕዝኤዲት ኣከታተብና ፋይሎች ኣንድ ከመሆናቸው ሌላ ይናበባሉ። 

ከእዚህ በፊት መጻፊያ ጠፍቶ በእንግሊዝኛ ፊደል ዓማርኛውን ፓልቶክ (Paltalk) በመሳሰሉ ድረገጾች ውስጥ ሲጽፉ የነበሩትን ነፃው የግዕዝኤዲት ድረገጽ መገላገሉ ይታወሳል። ከእዚህ በፊት መጻፊያ ጠፍቶ በእንግሊዝኛ ፊደል ዓማርኛውን ሲጽፉ ወይም ለጄልብሬክ ሲከፍሉ የነበሩትን ግዕዝኤዲት ገላግሏል። ከእንግዲህ ወዲያ ማንኛውንም የግዕዝ ቀለም በሦስት መርገጫዎች መክተብና ቴክኖሎጂን በሚ'ገባና ሳይንሳዊ ባልሆነ ዘዴ መጠቀም ኣስፈላጊ ኣይደለም። ይኸን በፔንዲንግ ፓተንት የተጠበቀ ትክክለኛ ቴክኖሎጂ ላልሰሙት እንድታሰሙና እንድታሳዩ እናበረታታለን። ስለ ቁሱ እዚህ የተጻፈው ጥቂት ሰዎች ግዕዝኤዲትን ከገዙ በኋላ ገበታውንና ፊደሉን ሳያስገቡ መጻፍ እየሞከሩ ስለተቸገሩም ነው።   “Amharic Typing” የሚለው ባለ ሰንደቅ ዓላማ ካርታችን ያለበት ኣዶ ከታየ በኋላ ያንን መንካት እንደተራ ቁስ ግዕዝኤዲትን ኣይከፍትም። በቁሱ ለመጠቀም የፊደል ገበታውና ፊደሉ በሴቲንግስ (Settings) በኩል መግባት ኣለባቸው።  የእንግሊዝኛው የፊደል ገበታ ከታየ በኋላ የዓለም ካርታው ያለበትን ኣዶ መንካት ወይም ተጭኖ መቆየት የዓማርኛውን የፊደል ገበታ ያቀርባል። በቅርቡ ወደ ኣይኦኤስ 10 ሲሻሻል የቁሱን ክፍል 1.3 በማድረግ ስሙም GeezEdit Amharic ተብሏል። ማሻሺያውም (Upgrade) ነፃ ነው።

የእንግሊዝኛው የኮምፕዩተር ኣከታተብ የእጅ ስልክ ኣጠቃቀምም ሆኗል። ግዕዝም ለኮምፕዩተር ሲጠቀምበት የነበረው ኣከታተብ ዓይነት ወደ እጅ ስልክ በዶ/ር ኣበራ ግኝት ገብቷል።  የተለመደው የእንግሊዝኛና የግዕዙ ገበታ መርገጫዎች እየታዩ ለሁለቱም ፊደላት እንዲያገለግሉ የፈጠሩት ጥቅም ቀጥሏል።  ኮምፕዩተርና የእጅ ስልክ የሚጠቀሙት የግዕዝ ዩኒኮዱን ፊደል ስለሆነ ውበቱን እንደጠበቀ ሁሉም መሣሪያዎች ይናበቡበታል። በእጅ ስልክ በኣንድ ጣት ከመክተብ ስልኩን ወደጎን ኣዙሮ በኣውራ ጣቶች መክተብ ያፈጥናል። በእዚህ የተነሳ ላቲን ለቀለሞቹ መክተቢያ የማይጠቀምበትን ከግዕዝ መጠየቅ ለእስማርት (ጮሌ) ስልኮችም ኣያስፈልግም። የግዕዝ ኣከታተብ ፈጣሪ ፓተንት (የግኝት ባለቤት) ከዶ/ር ኣበራ ሞላ ጋር ቃለ ምልልስ (ኢቢኤስ / EBS Tube) ቪድዮ እዚህ  ኣለ። ለኮምፕዩተር የቀረቡት የላቲን ምልክቶችም ለግዕዝ ፊደል እንዲጠቅሙ በእጅ ስልክም ሥራ ላይ ውለዋል። 

የእጅ ስልኩ ገበታና ፊደል ከተበተነ በኋላ መክተብ ሲያስፈልግ የመጻፊያው ስፍራ ሲነካ የመክተቢያ ገበታ (GeezEdit Amharic) ይቀርባል። በዓማርኛ ለመክተብ የሚያስፈልገው የዓለም ካርታ ያለበትን በመንካት ገበታውን ወደ ዓማርኛ መለወጥ ነው። ለላቲን ኮምፕዩተር ኣከታተብ የተፈጠረው QWERTY ገበታ ለላቲን የእጅ ስልክ እንደሆነው ሁሉ የግዕዙም ቀወኸረተየ የኮምፕዩተር መደበኛ ገበታ የእጅ ስልክም የግዕዝ ገበታ ሆኗል።  ለስልክ የተገዛው ለኣይፓድም ጭምር ነው። ጽሑፍን ለማስቀመጥ  Notes ውስጥ መጻፍ ያስፈጋል። ዊንዶውስና ኣፕል የሚጠቀሙት በግዕዝኤዲት ዩኒኮድ (GeezEdit Unicode) ፊደል ነው።  

ይህ በእንዲህ እንዳለ ለኮምፕዩተር ለዓመታት ሲቀርቡ የነበሩት ዓይነት የማያዛልቁ ኣከታተቦች ለእጅ ስልኮች መቅረብ ስለጀመሩ ሕዝቡ በኣዲስ ዙር መታለል እንዳይቀጥል መጠንቀቅ ያስፈልጋል። ለእዚህም የሚከተሉትን እንድንዘረዝር ተገድደናል። ፩. ግዕዝ ወደ ኮምፕዩተር ሲገባ እየኣንድኣንዱ የግዕዝ ቀለም የተከተበው በሁለት መርገጫዎች ነበር። ይህ ተሻሽሎ በኣንድና በሁለት መርገጫዎች እንዲከተብ ሆኗል። እንደእንግሊዝኛው የኮምፕዩተሩ ኣጠቃቀም ለእጅ ስልኩም ቀርቧል። ኣጠቃቀሞቹም ይቀጥላሉ። ፪. ይህ በሳይንስ የተደገፈ ኣጠቃቀም ይቀጥላል እንጂ ጥልቅ እየተባለ ለእጅ ስልክ ኣዲስ ኣጠቃቀም ኣይሠ'ራም ወይም ችግር ኣለበት ተብሎ ወደቀረው ኋላቀር ኣከታተብ መመለስ ኣስፈላጊ ኣይደለም። ፫. የኣማርኛ ታይፕ መቀጣጠያው ኣሠራር የትክክለኛ ኣማርኛ ፊደል መጻፊያ ኣልነበረም። የታይፕራይተሩ ኣጠቃቀም ሁለት ነጥብ ምልክት ለባዶ ስፍራነትና ሁለቱ፣ ሁለት ነጥቦችን በኣራት ነጥብ ምልክት ምትክነት መጠቀም ከመሣሪያው ኣጠቃቀም ችግሮች ጋር በተያያዙ የቁጠባ ኣሠራሮች የመጡ ነበሩ። ወረቀት ላይ ብቻ ሰፍረው የምናያቸው የጽሕፈት መሣሪያ ኣጠቃቀም ውጤቶች ከኮምዩተሩና የእጅ ስልክ ኣጠቃቀሞች ጋር ኣንድ ዓይነት ኣይደሉም። ዶክተሩ ኮምፕዩተራይዝ የኣደረጉት የግዕዝ ፊደል ኣንዱን ምልክት ለሁለቱም ኣይጠቀምም፤ ኣልተጠቀመምም። ፬. የላቲንን የኮለን (Colon) ሁለት ነጥብ ምልክት ዶክተሩ እንደሌሎቹ ለግዕዝ ኣጠቃቀም ቢያወርሱም ኣጠቃቀሞቻቸውን ማወቅ የተጠቃሚው ኃላፊነት ነው። ኮለን የግዕዝ ሁለት ነጥብ የባዶ ስፍራ ምልክት እንዳልሆነው ሁሉ የግዕዝ ሁለት ነጥብ ምልክትም ኮለን ኣይደለም። ሁለት፣ ሁለት ነጥቦችም ሆኑ ሁለት ኮለኖች የግዕዝ ኣራት ነጥብ ምልክት ኣይደሉም። የእዚህ ገጽ ኣንዱ ዓላማ ኣዳዲስ ጥፋቶች በቴክኖሎጂ እየተደገፉ እንዳይስፋፉ ነው።  

፭. የዓማርኛን ጽሑፍ ለማስቀመጥ ኖትስ (Notes) ቁስ ውስጥ መጻፍ ያስፈልጋል። ፮. የግዕዝ ፊደል የእጅ ስልክ ትክክለኛ ሳይንሳዊ ቴክኖሎጂ ኣጠቃቀሞች ዘዴዎቹን ለፈጠሩት ለዶ/ር ኣበራ ሞላ ቍጥራቸው 9000957፣ 9733724፣ 10067574 እና 10133362 በሆኑ የዩናይትድ እስቴትስ ፓተንቶች ተሰጥተዋል። ፯. ኮምፕዩተሮችና የእጅ ስልኮች የሚጠቀሙት ግዕዝኤዲት የኢትዮጵያ ኮምፕዩተሮችና ሶፍትዌር ፕሮግራሞች ኣንድ ዓይነት በሆነው የግዕዝ ፊደሉ ነው። ስለዚህ የቴክኖሎጅው ተጠቃሚዎች የተላኩላቸውን ኢሜይል የመሳሰሉ ጽሑፎች በኮምፕዩተሮችና የእጅ ስልኮች የሚመለከቱት በግዕዝኤዲት ፊደል ነው። ፊደሉን ለሌላቸው ግን መሣሪያዎቹ ላይ በኣሉ ፊደላት ይቀርባሉ። ፰. ኣንድኣንድ የግዕዝኤዲት ተጠቃሚዎች ፊደሉ በኣስቀያሚና የተሳሳተ የግዕዝ ፊደል ተቀየረብን የኣሉ ኣሉ። ይህ በቅርቡ ኣፕል መጠቀም በጀመረው ፊደሉ ኣጠቃቀም የመጣ ችግር ነው።

በእዚህ ርዕስ (Errors) ዶክተሩ ከዓመታት በፊት ያቀረቡትን ብዙ ኣንባቢዎች ስለኣላዩት ኣልታረሙም።    እዚህ ውክፔዲያ ገጽ ላይ የቀረቡት ውጤት ማምጣት ስለጀመሩ ተሻሽለው ቀርበዋል። ወደፊት ኮምፕዩተሩ በግዕዝ ፊደል የቀረቡትን ያነባ'ል፣ ያሰማናል፣ ያርማል፣ ይተረጕማል፣ ወዘተርፈ።  ስለዚህ ዶክተሩ ኣርቆ በማስብ ስሕተቶችና ግድፈቶች ወደ ኮምፕዩተር ሳይገቡ እንዲታረሙ ከመጻፍ ኣልተቆጠቡም።   

፩. እንደ ኤውሮጳ ኣቆጣጠር ማጠር ያለበት በ“እ.ኤ.ኣ.” እንጂ “እ.ኤ.ኣ” ማድረግ ከሚገባው በታች ማሳጠር ነው። ኣንድ ሰው በስሕተት የተጠቀመበትን ኣሠራር ሌሎቻችን በሚገባ ሳናስተውል መከተል የለብንም። “ኣ” ጎን ነጥብ ከኣሌለ “ኣ” ብቻውን እንዳለ ቃል መቆጠሩ ስለሆነና ኣጠቃቀሙም ትክክል ስለኣልሆነ ቋንቋ ሲበላሽ ዝም ብሎ መመክልከት ተገቢ ነው? ፪. “ዓመተ ምሕረት” ማጠር ያለበት በ“ዓ.ም.” እንጂ “ዓ/ም” ያሳስታል። የእዝባር ጥቅም እንደ “ወይዘሮ” የሚጻፉትን ቃላት በ“ወ/ሮ ለማሳጠር እንጂ ሁለት ቃላትን ለማሳጠር ኣይመስልም። ፫. የ“ሊቅ” ብዙ “ሊቆች” ወይም “ሊቃውንት” እንጂ “ሊቃውንቶች” የሉንም። እዚህ ላይ በተለይ ከግዕዝ የመጡ ቃላት ላይ መጠንቀቅ ሳይጠቅም ኣይቀርም። ኣባላት፣ መምህራን፣ መኳንንት የመሳሰሉ ቃላት የብዙ ቍጥሮች ናቸው። ስለዚህ ኣባላቶች፣ መምህራኖች፣ መኳንንቶች፣ ቃላቶች የሚባሉ የብዙ ብዙ ስለሆኑ እንዲህ የኣሉ የዓማርኛ ቃላት የሉም። ፬. ሞክሼ ቀለሞች የተለያዩ ጥቅሞች የኣሏቸው ለግዕዝ ቋንቋ እንጂ ለዓማርኛ ኣይደለም የሚባለው ትክክል ኣይደለም። 

፭. ዌብ (Web) ድር፣ ዌብፔጅ (Webpage) ድረገጽ ወይም ገጸድር ነው። ድህረገጽ ከገጽ በኋላ ስለሆነ ትክክል ኣይደለም። ይህ ስሕተት ምን ያህል እንደተስፋፋ ለማስተዋል ድህረገጽ፣ ድኅረገጽ እና ድሕረገጽ ቃላትን ኢንተርኔት ላይ በመፈለግ ስህተቶቹን መመልከት ይቻላል። ድሕር ማለት ኋላ ነው። Website ድረገጽ ነው። ስለዚህ ድሕረገጽ ወይም ድኅረገጽ Website ኣይደለም።  ፮. የ“ው” ድምጽ ሳድስ እንጂ ካዕቡ “ዉ” ስለኣልሆነ “ነው” መከተብ ያለበት በሳድሱ “ው” ነው። ዓማርኛ “ዉ” ቀለምን የሚጠቀምባቸው ብዙ ቃላት ስለሌሉት መጠንቀቅ ጠቃሚ ነው። በ“ዉ” ቀለም ከመጠቀም ልዩነቱ ላልገባቸው “ዉ”ን ኣለመጠቀም ያዋጣል። ፯. “ጊዜ” እንጂ “ግዜ” ዓማርኛ ኣይደለም።  ፰. ኣንዳንድ ደራስያን “እ” ቀለምን መቀነስ ይወዳሉ። “ተእኛ” እና “ተኛ” እንዲሁም “የእርሷ” እና “የርሷ” የተለያዩ ናቸው። 

፱. ኣራት ነጥብ (“።”) እራሱን የቻለ ኣንድ የግዕዝ የምልክት ቀለም ነው። ኣንዳንድ ደራስያን ምልክቱን ከሁለት ባለሁለት ነጥቦች (ነቊጦች) ወይንም በእንግሊዝኛ ኮለን (“Colon”) መክተብ ስለጀመሩ ይህ ትክክል ከኣለመሆኑም ሌላ ኣስፈላጊ ያልሆኑ ሁለት መርገጫዎች በማስጨመር ጊዜና ስፍራ የሚያስባክን ግድፈት ነው። ከሁለት ቀለሞች የተሠሩትን ለመሠረዝም ሁለት መሠረዣዎች ያስፈልጋሉ። ኣራት ነጥቦች የሌሉት ጽሑፍም ችግር ውስጥ ሊወድቅ ይችላል። ፲. ዶክተሩ የእንግሊዝኛው ኮለን ለግዕዝ እንዲጠቅም ያደረጉት በኮለንነት ስለሆነ የግሉ የዩኒኮድ ቊጥር ከኣለው ባለሁለት ነጥብ (ወይም ነቊጥ) የባዶ ስፍራ የግዕዝ ምልክታችን ጋርም ኣንድ ኣይደለም። ኣራት ነጥብን ከሁለት ባለ ሁለት ነጥቦች (“፡”) በኮምፕዩተር መክተብም ግድፈት ነው። ምክንያቱም ይህ ኣሠራር ኣራት ነጥቦች ከሌሉት የኣማርኛ የታይፕ መጻፊያ የመጣ የኣሠራር ችግር ስለሆነ  እንጂ ሁለት ባለ ሁለት ነጥቦች ኣራት ነጥቦች የሚሆኑበት ኣከታተብ ወደ ኮምፕዩተር እንዳይገባ ዶክተሩ ከተከላከሉት ኣንዱ የጎደለ ኣጠቃቀም ነው።  በሞዴት፣ ኢትዮወርድ፣ ግዕዝኤዲት በኮምፕዩተርና ግዕዝኤዲት በእጅ ስልክ የግዕዝ ኣራት ነጥብ ምልክት የተከተበውና እየተከተበ የኣለው በሁለት መርገጫዎች (“ዝቅ 3”) ነው። በግዕዝ ዩኒኮድ መደብ ውስጥ እንደሚታየው  እና እዚህ ጎን ላይ የኣለው ሥዕል እንደሚያሳየው ሁለት ነጥብና ኣራት ነጥብ የተለያዩ ናቸው። ሁለት ሁለት ነጥብና ኣራት ነጥብ የተለያዩ ናቸው። ኢትዮጵያውያንም ኣራት ነጥብን በማያስከትብ ፕሮግራም መጠቀም የለባቸውም። ፲፩. የመጽሓፎች ይዘት (Contents) እና ማውጫ (Index) የተለያዩ ናቸው። ፲፪. የኣንዳንዶች ስሕተቶች ምንጮች የተሳሳቱ ፊደላት ወይም መክተቢያዎች ናቸው፦ ምሳሌ “ቍጥር”ን በ“ቁጥር” መጻፍ።

፲፫. “ው”ን አንጂ “ዉ”ን የሚጠቀሙ ብዙ የዓማርኛ ቃላት የሉም። በቅርቡ ግን በኣለማወቅ በ“ው” ቀለም ምትክ “ዉ”ን በግድፈት የሚጠቀሙ ፀሓፊዎች እየበዙ ነውና ቢታሰብበት ኣይከፋም። መዝገበ ቃላትም ጠቃሚዎች ናቸው። (እንግሊዝኛ አማርኛ መዝገበ ቃላት 1972)።  “ው”ን በትክክል ከ40 በላይ ቃላት ውስጥ የተጠቀመ ጽሑፍ ምሳሌ እዚህ ኣለ።  “ው”ን በስሕተት ከ400 በላይ ቃላት ውስጥ የተጠቀመ ጽሑፍ ምሳሌ እዚህ ኣለ።   ፲፬. የግዕዙ “ሀ” ድምጽ  ወደ “ኸ” የቀረበ ነው። “አ” እና “ኣ” ድምጽ  ኣይጋሩም።      ፲፭. ኣንዳንድ ፀሓፊዎች በነጠላ ሰረዝ (“፣”) ምትክ ኮማ (“,”) (Comma) በኣራት ነጥብ (“።”) ምትክ ፔርየድ (“.”) (Period) መጠቀም ስለጀመሩ ፊደሉንና ቋንቋውን እያበላሿቸው ናቸው። ፲፭. ኣንዳንድ ምሁራን ስለማያስተውሉ ሁሉንም የዓማርኛ ቃላት መክተብ በማይችሉ እየተጠቀሙ የሚያወሩትን መጻፍ ኣይችሉም። የግዕዝ ፊደል ታዋቂነት የኣለ እስፔሊንግ ስሕተት ድምጽን በማስፈር ትክክክለኛ ድምፃዊ ፊደል መሆኑ ነው። ፲፮. ማንኛውንም የግዕዝ ቀለም በሦስት መርገጫዎች መክተብ ጊዜና ጉልበት ማባከን ነው። (Typing any Ethiopic glyph with three keystrokes is a waste of time and effort.) ምክንያቱም የዶክተሩ ኣሠራር እንግሊዝኛውን ከኣጋጠመው ችግር ጭምር ለማላቀቅ እንጂ ለግዕዙ የእንግሊዝኛውን ችግር ለማካፈል ስለኣልሆነ ነው። ፲፯. ኣንድኣንድ ፀሓፊዎች የተሳሳቱ ቅርጾች ያሏቸውን ቀለሞች እየተጠቀሙ ስሕተቶችን እያስፋፉ ናቸው። ለምሳሌ ያህል የ“ኩ” እና የ“ቡ” መቀጠያዎች ኣንድ ዓይነት ኣይደሉም። ኮምፕዩተርና የእጅ ስልክ ላይ የኣሉ ፊደላት የተሳሳቱ ከሆኑ መሳሳቱ ስለማይታወቅ የተሳሳቱ ቀለሞች ተለምደው መቸገርና ማስቸገር ኣይቀርም። እነ “ቋ”፣ “ኋ”፣ “ኳ” እና “ጓ” እራሳቸውን የቻሉ መስመር ላይ የሚያርፉ ቀለሞች እንጂ እነ “ቀ”፣ “ኃ”፣ “ካ” እና “ጋ” ስር በተጋደሙ መስመሮች የሚቀርቡ ኣዳዲስ የታይፕራይተር የእውሸት ፈጠራዎች ተቀጣጥለው እንደ ኣዳዲስ ቀለሞች ማቅረብ ተገቢ ኣይደለም። የየ”ን እንዚራን መለየት ለኣቃታቸው ኣንድኣንድ ምሁራን የኣሌሉ ቀለሞችን መልኮች ማስተዋወቅ ኣይበጅም።  ስለዚህ የግዕዝን ፊደል ከመለገስ መለየቱ ቢቀድም ሳይሻል ኣይቀርም። ፲፰. መስከረምና ሰፕቴምበር ብዙ ቀናት ይጋራሉ እንጂ ኣንድ ኣይደሉም። መስከረም 1 ሰፕቴምበር 1  ወይም September 1 ኣይደለም። ፲፱. ሁለት ዓመታት ወይም ዓመቶች እንጂ ሁለት ዓመት በማለት መጻፍ ስሕተት ነው። ፳. በግዕዝ ጽሑፍ ውስጥ ኣራት ነጥብና የመሳሰሉት (በቀለማት እንጂ) በባዶ ስፍራ መቀደም የለባቸውም። ምክንያቱም ግዕዝ ከእጅ ጽሑፍና የማተሚያ ቤቶች  ኣጠቃቀም ወደ ኮምፕዩተር ሲሻሻል መለ'የት የሚገባቸውን ዶክተሩ ስለኣቀረቡ ነው። 

፳፩. የግዕዝ ፊደል የኦሮምኛው ፊደል ውስጥ ያለውን የግዕዙን “ዸ” እና ሰባት እንዚራን ቀለሞቹን ያጠቃልላል። ስለዚህ እንደ “በዻዻ” የኣሉትን ቃላት በ“በዳዳ” ወይም “ዻራርቱን በ“ደራርቱ” መክተብ ግድፈት ነው። የኦሮምኛው ፊደል የዶክተሩ ሞዴት፣ ኢትዮወርድ፣ ግዕዝኤዲትና ሌሎች ፕሮግራሞች ውስጥ ቀርበው የሚፈልጓቸው ተጠቅመውባቸዋል። ፳፪. ሁሉንም ቀለማት የሌሉት ወይም የማይከትቡ ዓማርኛ እየተባሉ ሲቀርቡ ኣለተቃውሞ መቀበል ነውር ነው። ምክንያቱም ይህ ለፊደሉና ለሰዋሰው የኣለመጨነቅን ስለሚያሳይና የፀሓፊዎችን ችሎታ ጥያቄ ውስጥ ስለሚያስገባ ነው። ፳፫. ዓማርኛ “መጠጥ” እና “መጠጥ ኣደረገ” የሚለውን በማጥበቅ መለየት ኣይችልም የሚሉ ኣሉ።   “መጠጥ” እና “መጠጥ ኣደረገ” ሁለት ትርጕሞች ያሏቸው ቃላት እንጂ በማጥበቅ የሚለዩ ኣይደሉም። ፳፬. በኮምፕዩተር ሁለት ነጥብ “፡” የግዕዝ የባዶ ስፍራን ምልክት ነጥብ በሌለው የባዶ ስፍራ የእንግሊዝኛው ኣጠቃቀም ጋር ደርበው ዓማርኛውን የሚያቀርቡ ኣሉ። ከሁለቱ ዘዴዎች ኣንዱን መምረጥ እንጂ ሁለቱንም መውደድ ኣያዋጣም።

፳፭. ኣንዳንድ ሰዎች ዓማርኛ የእራሱ ፊደል የለውም ይላሉ። ዓማርኛ የእራሱ ፊደል (Amharic Alphabet) የኣለው ቋንቋ ነው።  የግዕዝም ቋንቋ የእራሱ ፊደል ኣለው። የግዕዝ ቋንቋ ፊደላት የዓማርኛው ውስጥ ሲኖሩ ሁሉም የዓማርኛ ፊደላት የግዕዙ ቋንቋ ፊደላት ውስጥ የሉም። ግዕዝ ወይም Ethiopic የተለያዩ ቋንቋዎች የሚጠቀሙበት የፊደሉም ስም ሲሆን ለተለያዩ ቋንቋዎች ተጨማሪ ቀለሞች ተጨምረዋል። ፳፮. የኣማርኛ የታይፕራይተር ፊደል የግዕዝ ፊደል ኣይደለም። የእውሸት (Fake) ወይም የፈጠራ የዓማርኛ ፊደል እንጂ የዓማርኛም ፊደል ኣይደለም። መጽሓፍትም ሲታተሙ የነበሩት በግዕዝ ፊደል በማተሚያ ቤቶች ትክክለኛ ቀለሞች ነበር። ኣሁንም ቢሆን በድሮው ዓይነት ወይም ዶክተሩ ኮምፕዩተራይዝ በኣደረጉት መነሻው ይህ ፊደል በሆነው የዩኒኮድ የግዕዝ ፊደል ዓይነት ነው።  የታይፕራይተርንና የማተሚያውን ፊደላት የማይለዩና ሁለቱ ኣንድ የሚመስሏቸው ኣሉ። ፳፰. በወልጋዳ፣ የተሳሳቱና ከሲታ ቀለማት ተጽፈው የሚቀርቡ ጽሑፎችና መጻሕፍት እየበዙ ነው። የፊደል መልክ ከኣላማረ ለማንበብም ኣያጓጓም። ጥሩ የግዕዝ ፊደል ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት “ነጋሪት ጋዜጣ”ን ሲያትምበት የነበረው ፊደል ነው። ብዙ መጻሕፍትም ታትመውበታል። 

፳፱. ግዕዝ ኮምፕዩተራይድ ስለሆነ በኮምፕዩተር የሚቀርቡት በዓለም ዙሪያ ሊታዩ ስለሚችሉ ጥንቃቄ ያስፈልጋል። ዓማርኛውን በላቲን ፊደል የሚጽፉ ኣሉ። ግዕዝ ድምጻዊ ስለሆነ የተለያዩ ቋንቋዎችን ያስከትባል። እንግሊዝኛ ውስጥ የኣሉ ኣንድኣንድ ችግሮችም የሉትም።  ፴. ግዕዝን በኣንድና ሁለት መርገጫዎች መክተብ ስለተቻለ ኣከታተቡ ከእንግሊዝኛው ጋር እኩል ሆኗል። ስለዚህ ማንኛውንም የግዕዝ ቀለም በሦስት መርገጫዎች መክተብ ያካስራል። ይህ የእጅ ስልኮችንም (Smartphones) ኣጠቃቀም ይመለከታል። ፴፩. ከላይ የተጠቀሱት ስሕተቶች ጥቂቶቹ ትግርኛንም ያጠቃልላሉ። ፴፪. ግዕዝ ኮምፕዩተራይዝድ ሆኖ ለኮምፕዩተሮችና የእጅ ስልኮች ቀርቧል። ወጉንና ሕጉን ጠብቆ መጠቀም የእራስንና የፈጣሪዎችን መብት መጠበቅ ነው። በተሰረቁ፣ በማይጽፉና የኣልተሟሉ ሶፍትዌሮች መጠቀም ለእራስና ለሌላው መብት ኣለመጨነቅን ያሳያል። ለጽሑፍ ጥቅም የሚያስፈልጉ ነፃ ሶፍትዌሮች ስለኣሉ ከእንደግዕዝኤዲት ዓይነት በስተቀር መግዛት ግዴታ ኣይደለም። 

፴፫. ትክክለኛ ሰዋስው፣ የተሟሉ ቀለሞች፣ ትክክለኛ ቅርጾች እና የመሳሰሉትን በኣሌላቸው መጠቀም ለቋንቋው መዳከም ምክንያቶች እንዳይሆኑ መጠንቀቅ ኣስፈላጊዎች ናቸው። ስሕተቶች ሲደጋገሙ ሊለመዱ ይችላል።  ዶክተሩ ከሰዋስው ተሳሳቶች ኣንዱ ናቸው። ፴፬. ስለ ግዕዝና ዓማርኛ ፊደላት ሲጻፍ ስለ ግዕዝ ቋንቋ የሚመስሏቸው ኣሉና ይታሰብበት። ፴፭. ፊደላችን ለኣፍሪቃውያንና ሌሎችም  እንዲተርፍ በወጉ መጠቀምና መንከባከብ ይጠቅማል።  ፴፮. ዓማርኛ በግዕዙ ዐ የማይጻ'ፈው ቀለሙ ድምጹን ስለማይወክል ነው። 

፴፯. ብዙ ስሕተቶችና ግድፈቶች የኣሉትን ጽሑፍ በዋቢነት ለመጠቀም ኣያስተማምንም። ምክንያቱም ደራሲው ኣስፈላጊዎቹን ጥንቃቄዎች ኣለማድረጉን ስለሚያሳይ ኣለመግዛት ወይም መተቸት ሳይሻል ኣይቀርም። ለምሳሌ ያህል ነው እና ነህ የመሳሰሉትን ቃላት ነዉ  እና ነክ የሚሉ ኣሉ። ኢትዮጵያን በትክክል መጻፍ የማይችሉ ፊደል በሚገባ ኣልቈጠሩም ወይም ረስተዋል ማለት ኣይደለምን? ፴፰. የኣንድኣንዶቹ ስሕተቶች ምንጮች ማተሚያ ቤቶች ናቸው። ለምሳሌ ያህል ቀደም የኣሉ ጽሑፎች ውስጥ የፏ ፊደል መስመሩ የኣለው ከላይ ሆኖ ሳለ የኣዳዲሶቹ ከታች ነው። ቀደም የኣለውን ምልክት ዶክተሩ ሲጠቀሙ የተሳሳቱ የሚመስሏቸው ኣሉ። ይኸንኑ መቀጠያ ከግዕዝ ወግ ውጪ ፍ ላይ ተደርጎ በቅርቡ የቀረበ ፊደልም ኣለ። ማተሚያ ቤቶች በትክክለኛዎቹ ቀለሞች ከመቶ ዓመታት በላይ የተጠቀሙ ስለሆኑ መሪዎች እንጂ ተከታይ መሆን የለባቸውም። ፴፰. ዓማርኛ ማጥበቂያ ኣይጠቀምም የሚሉ ፈረንጆችም ኣሉ። በዓማርኛ ፊደል ሲደረብ እንደእንግሊዝኛው ኣይጠብቅም።  ፴፱. ኣንዳንድ የዓማርኛ ተጠቃሚዎች ዓማርኛ ሞክሼዎ ድምጾች የሉትም የሚሉ ኣሉ። ኣባይና ዓባይ ኣንድ ኣለመሆናቸው በቅርቡ ከወንድሜ ጋር ስከራከር የዓባይ ጉዳይ የባ መጥበቅና ኣለመጥበቅ ነው በማለት ስላሳመነኝ ምርምሮች ኣስፈላጊ ናቸው። ፵. ዶክተሩ ለመንግሥት የኣቀረቡት የፓተንት ማመልከቻ በወጉ ጥበቃ ሳይደረግለት መንግሥትና ኣብዛኛው ሕዝብ ከዶክተሩ በተሰረቁ የግዕዝ ቴክኖሎጂ ሲጠቀም ቆይቷል። ኣሁን ለውጥ መጥቷል ስለተባለ ሁሉም ሌቦች መስረቅ ማቆም ይገባቸዋል። ሌብነት ተለምዶ የዶክሩን ሥራዎች የሚደብቁም ኣሉ። ፵፩. ይህ ጽሑፍ ብዙ ዓይነት ግድፈቶች ኣሉት፦ ለምሳሌ ያህል ኣራት ነጥብ የለውም፣ በሳድሱ “ው”  ምትክ ካዕቡን “ዉ”  ተጠቅሟል፣ ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ፣ ኢትዪጵያ እና ኢትዩጵያ በማለት ኣቅርቧል። 

የዓማርኛ ሞክሼ በተለያዩ ቀለሞች የተወከሉ ኣንድ ዓይነት ድምጽ ኣሏቸው የሚባሉ ኆኄያት ናቸው ይባላል። ሞክሼዎች ቢያንሱ ሁለት ሰዎች ስለሆኑ ስሞች ተጋሩ እንጂ ኣንድ ስለኣልሆኑ ኣንዱ ሞክሼ ሌላውን ሊሆን ኣይችልም። ስለዚህ የዓማርኛ ቀለሞች ሞክሼዎች ስለሆኑ ኣንዱን በሌላው መተካት ይቻላል የሚባለ4ው ኣስተሳሰብ ትክክል ኣይደለም። የኣማርኛ ሞክሼዎች ናቸው የሚባሉት የእየእራሳቸው ቅርጾች፣ ድምፆችና ስሞች ስለኣሏቸው ሞክሼዎች ኣይደሉም።  ምሳሌ “ዓይን” የሚጻፈው በዓይኑ “ዐ” ነው። 

የዓማርኛ ሞክሼዎችን ማስወገድ በሚከተሉት ምክንያቶች ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል። ፩. ሞክሼዎች ኣንድ ስለኣልሆኑ ኣንድ ናቸው ብሎ ኣንዱን ማንሳትና ሌላውን መጣል ከመነሻውም የተሳሳተ ኣስተሳሰብ ነው። ፪. የእነዚህ ሞክሼዎች ፊደላት ድምጾች እስከ ፲፭፻፴ ዓ.ም. ድረስ ማለትም እስከ ዓፄ ልብነ ድንግል ዘመነ መንግሥት ድረስ ተለይቶ ሲነገር ነበር።  ሞክሼ ቀለሞች ይቀነሱ የተባለው ኃሳብ የመጣው በታይፕ መኪና ዘመን መርገጫዎቹ ስለኣነሱ ነበር። የኣማርኛ የጽሑፍ መሣሪያ ዓማርኛ ስለኣልጻፈና ግዕዝ በዶክተር ኣበራ ዲጂታይዝድ ስለሆነ የታይፕ መሣሪያውና ቅጥልጥል ቅርጾቹ ቀርተዋል። ኣሁን ሁሉም ቀለሞች ዲጂታይዝድ ስለሆኑ የዱሮ ችግሮችም መፍትሔ ኣግኝተዋል። መፍትሔ የፈጠሩትን ማመስገንና ሥራዎቻቸውን ማስተዋወቅ የጥቂቱ ብቻ መሆን የለበትም። ፫. የኣማርኛ ታይፕራይተር ፊደል የዩኒኮድ ፊደል እንዲሆን የሞከሩት በሳይንሳዊ መረጃ ተሸንፈው ቀርተው ትክክለኛዎቹ የግዕዝ ቀለሞች የዩኒኮድ መደብ ውስጥ ገብተዋል። ይህ ከሆነ በኋላ ስዉ የሚያውቃቸው ቀለሞች ይቀነሱ ማለት የተማረውን ማስቸገር ስለሆነ ተገቢ ኣይደለም። ምክንያቱም እየኣንድኣንዱ ቀለም የሚከተበው በሁለት መርገጫዎች ስለሆነ በኋላም ከኣንድ መርገጫ የተረፉት ኣብላጫዎቹ የግዕዝ ቀለሞች የሚከተቡት በሁለት መርገጫዎች ስለሆነ የሞክሼዎች መኖር የፈጠረው ችግር የለም። ኣንዳንዶቹ ሞክሼዎችን የሚከትቡት ከኣንድ የመርገጫ ቍልፍ ስለሆነ ኣንድኣንዱን ሞክሼዎች የሚከትቡት ብዙ መርገጫዎችን በመጠቀም ነው። ሞክሼዎችን የሚጠሉት የማያዋጣው መክተቢያዎቻቸውን ለመጥቀም ሊሆን ይችላል። ይህ በተለይ የዓማርኛውን ቀለሞች በእንግሊዝኛ እስፔሊንግ መክተብ የሚፈልጉትን ይመለከታል። ፬. በስመ ሞክሼና መሻሻል ሞክሼዎች የኣልሆኑትን መቀነስ የፈለጉ ኣሉ። ምሳሌ፦ “ጐ”ን በ“ግወ” መተካት። ይህ ድምፃዊ ፊደላችንን ወደ ኣክሳሪው ፊደላዊ ፊደል በመቀየር ያዳክመዋል። የፊደል ጥቅም ቋንቋን ለመግለጽ እንጂ ለፊደል ኣጠቃቀም ሲባል ቋንቋን መቀየር ወይም መቀነስ ኣይደለም።  

፭. የሞክሼዎቹ ማንነት በጥናት ላይ የተመረኰዘ ኣይደለም። ለምሳሌ ያህል መንትያ እንጂ ሞክሼዎች ኣይደሉም የሚሉ ኣሉ።  ፮. ሞክሼዎችን መቀነስ ጥቅም ቢኖረው ኖሮ የ“ከ ቤት ድምጽን የሚጋሩትን “C” (“ሲ”)፣ “K” (“ኬ”) እና “Q” (“ኪው”) (ምሳሌ “Cake” እና “Queen” ወይም “ኬክ” እና “ኲን”) የላቲን ቀለሞች ተጠቃሚዎቻቸው ሊቀንሷቸውና ሦስቱንም በ“C” ብቻ መጠቀም በመረጡ ነበር። ይህ ኣስቸጋሪነቱን ለማመልከት የቀረበ ምሳሌ ነው። ፈረንጆች ለእነዚህ ቀለሞቻቸው የተለያዩ መርገጫዎች ቢመድቡም ለእነ “ሐ”፣ “ኀ”፣ “ኸ”፣ የግሎቻቸው መርገጫዎች መመደብ ኣይገባም የሚሉ ኣሉ። ዶክተሩ ይገ‘ባል በማለት ይኸን ኣይደግፉም። ፯. ሞክሼዎች እንዲጠፉ ከመቸኰል ልዩነታቸውንና ጥቅሞቻቸውን ማስተማር ከምሁራን ይጠበቃል። ምሳሌ፦      ኣለ። ፰. ሞክሼዎች የሌሉት ጽሑፍ ተለምዶ ሞክሼዎቹ ሊረሱ ይችላሉ። ሞክሼዎችን የማያውቋቸው ምሁራን የቆዩ ጽሑፎችን በሚገባ ላያውቁና ትርጕሞቻቸውን ላይረዱ ይችላሉ። ዶክተሩ የሠሩት የማጥበቂያና የማላልያ ቀለሞችም ላይጠቅሙ ይችላሉ። በቍጥሮቹ በኣለመጠቀም የተነሳ የግዕዝን ኣኃዞች የማይለዩ ምሁራን ኣሉ ይባላል። 

፱. ምክሼዎችን የማይወዱ ጥቅሞቻቸውን መማር የማይፈልጉ ሊሆኑ ይችላሉ። የማይጽፉና ያልተሟሉ መክተቢያዎች የሚያቀርቡ ስለኣሉ ዘላቂ ችግሮችን ሲፈጥሩ ዛሬ መታገስ ኣስፈላጊ ኣይደለም። (የሞክሼዎች ኣለመኖር የፊደላቱን ቊጥሮች በማስቀነስ ኣከታተብ ቢያቀል'ም ኣማራጭ እንጂ ግዴታ መሆን የለበትም ባይ ናቸው ዶክተሩ። ምክንያቱም ኣማራጭነቱ አንደማያዋጣ ኣቅርቦ ማሳመን ስለሚቻል ነው።) ፲. ወደፊት በኮምፕዩተር እንድንራቀቅ ትክክለኛዎቹንና ሳይንሳዊ መሠረቶችን ስለፈጠርን ከሞክሼዎች መኖር ይልቅ ኣለመኖር ሊጎዳ ይችላል። ወደፊት ኮምፕዩተር ስለሚያስተካክለው የሞክሼዎች ኣጠቃቀም ችግር ስለማይሆን የሚያስቸግሩት ቀለሞቹን የማያውቁት ሊሆኑ ይችላሉ። ጥቂት የኣናሳ ተናጋሪዎች ቋንቋዎች ቀለሞች የተሠሩት ሞክሼዎች የተባሉትን በመጠቀም ስለሆነ ሌሎች ኢትዮጵያውያን የሚያውቋቸውን የዓማርኛ ቀለሞች የማያውቁ ዓማርኛ ተናጋሪዎች መኖር ዓማርኛ ቋንቋንና ፊደሉን ይጎዷቸዋል እንጂ ኣይጠቅሙም። ስለዚህ በስመ ሞክሼ ዓማርኛውን ማዳከም ለዓለም ሕዝቦች ጭምር ጉዳት ነው። ፲፩. ኣንድ ጽሑፍ ሞክሼዎች በተባሉትም ይሁን በሌሎቹ ቢጻፍ ልዩነቶቻቸውን ለማያውቁ የሚፈጥሯቸው ችግሮች የሉም። ፲፪. ዓማርኛ የግዕዝ ቋንቋ ፊደል ላይ የሚያስፈልጉትን ኣዳዲስ ቀለሞች ጨመረ እንጂ የግዕዝን ፊደል ኣልቀነሰም። የግዕዝ ፊደል መክተቢያ ሁሉንም ቀለሞቹን ማስተናገድ የቴክኖሎጂው መጀመሪያ ነው። የኮምፕዩተር ቴክኖሎጂው የገላገለው የግዕዝን ቀለም ለዘመናት ሲለቅሙ የነበሩትን የኢትዮጵያ ማተሚያ ቤቶች ሠራተኞች ጭምር ነው። ይህ ጉዳይ የአማርኛ የታይፕ መጻፊያውን ኣይመለከትም። 

፲፫. የትግርኛ ቀለሞች በዓማርኛው ላይ ተጨማሪ ኣሏቸው እንጂ የተቀራረቡ ናቸው። የትግርኛ ፊደል ውስጥ የሌሉ ጥቂት የዓማርኛ ቀለሞች ኣሉ። ኣንዳንድ ፀሓፊዎች ግን ከትግርኛ ቀለሞች ውስጥ እነ “ሀ”፣ “ሐ”፣ “ኀ”፣ “አ” እና “ዐ” የራብኦቻቸው ሞክሼዎች መስለዋቸው ተሳስተው ሊቀንሷቸው ኣጥቊረዋቸዋል።   እንደ ዶ/ር ኣበራ ሞላ ገለጻ ግን ኆኄያቱ ሞክሼዎች ስለኣልሆኑ መብታቸው መከበር ኣለበት ነው።  ይኸንንምና የ“ሠንና የ“ፀ እንዚራን የኣጠቃለለውን ሞክሼነት በዓማርኛና በእንግሊዝኛ ተቃውመዋል።  ፲፬. ሞክሼነት ልብወለድ እንጂ ሳይንስ ኣይደለም። ዶክተሩ ዲጂታይዝ ያደረጉትና የእየኣንድኣንዱ ግዕዝ ቀለም መብት ተጠብቆ ዩኒኮድ ውስጥ እንዲገባ የታገሉት ሳይንስንና ታሪክን በመመርኰዝ ነው።  ፲፭. የግዕዝ ፊደል ተጠቃሚዎች በፊደላቸው ሲጠቀሙ ብዛቱ ኣላስቸገራቸውም። ብዛት ችግር የሆነው መርገጫዎች ስለኣነሱ ስለሆነ የምሁራን ዓላማ ለችግሮቹ መፍትሔ መፍጠር እንጂ ለጊዜያዊ ችግርና መርገጫዎች ሲባል ፊደል መቀነስ መፍትሔ ኣይደለም። የታይፕራይተር ፊደል ቀናሾችና ቀንጣሾች ቢሳካላቸው ኖሮ ሞክሼዎቹ ስለማይኖሩ ዶክተሩ መፍትሔ ለመፍጠር ይቸገሩ ነበር። እንዲህም ሆኖ የታይፕራይተሩን ቍርጥራጮች ኣንዱ ግዕዝ ነው ብሎ ሲያወናብድ ዶክተሩን በመደገፍ የተማሩበት የኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርሲቲም ይሁን የፊደሉ መብት ተከራካሪ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በኣለፉት ፴ ዓመታት ስለ ዶክተሩ ሥራዎችም ይሁን ሁሉም የግዕዝ ቀለሞች ዩኒኮድ እንዲገቡ ስለታገሉት ትንፍሽ ኣላሉም። ፲፮. ስር የሰደደን ነገር መቀየር ኣስቸጋሪ ነው።   

፲፯. በስመ ሞክሼ ቋንቋው እየተበላሸ ነው። ለምሳሌ ያህል “ቍጥር”፣ “ሽኵቻ”፣ “ጫጕላ”፣ “ጓጕቷል”ን የመሳሰሉ ትክክለኛ ቃላት እንዳይኖሩ ሊሆን ነው። ያም ካልሆነ እንደላቲኑ ኣስተሳሰብ ሁለት ቀለሞች በኣንድነት ኣንዲነበብ የማድረግን ባዕድ አጠቃቀም ያስከትላል። ፲፰. “ጸ” እና እንዚራኖቹ የ“ፀ” እና እንዚራኖቹ ሞክሼዎች ናቸው ተብለው ቀርተው ዩኒኮድ የሚያውቀው “ጿ” በሞክሼ ስም እንዲወገድ ተፈልጓል። ስምንተኛው የ“ፀ” ድምጽ ብስሕተት ስለሌለና ዩኒኮድ ስለማያውቀው ዩኒኮድ ውስጥ እንደማስገባት ዝም ማለት በስመ ሞክሼ ፊደሉን ለማበላሸት እንጂ ለመቀነስ ብቻ እንዳልሆነ ያመለክታል። ምክንያቱም ለኣንድኣንዶቹ ሁለቱም “ጿዎች ሞክሼዎች ስለሆኑ ነው። “ጸሎት” እና “ፀሓይ” ውስጥ “ጸ” እና “ፀ” ሲነገሩ ኣፋችን ውስጥ ምላስ የሚያርፈው በተለያዩ ስፍራዎች ነው። ፲፱. ትግርኛ እንደ ዓማርኛው የግዕዝ ቋንቋ ፊደል ላይ የሚያስፈልጉትን ኣዳዲስ ቀለሞች ጨምሯል። ግዕዝና ትግርኛ የሞክሼ ችግር የለባቸውም ይባላል። የሞክሼዎችን ችግር ዓማርኛ ላይ ማጥበቅ ለምን ኣስፈለገ? ፳. ኣንድኣንድ ሰዎች ሞክሼዎች የግዕዙን ድምጽ በዓማርኛ ኣጥተዋል ይላሉ።   የሞክሼዎች ጉዳይ ግን የቃላት ኣመጣጥንና በቀለም የትርጕማንን መለያየት ጭምር ያመለክታል።  ምሳሌ፦ ዓይኑ “ዐ” የጠበቀ ነው  ።  ትክክለኛ ኣጠቃቀሞችንም ለመከተል መዝገበ ቃላት ኣሉ። “ፀ”ም የጠበቀ ነው።  ትክክለኛዎቹን የኣማርኛ ኆኄያት የተከተለው ኣፄ ኃይለ ሥላሴ በ፲፱፻፷፪ ዓ.ም. የኣሳተሙት መጽሓፍ ቅዱስ ኣስተማማኝ ነው ይባላል።  

፳፩. ቅዱስ ኦነሲሞስ ነሲብ “መጫፈ ቁልቁሉ”ን በግዕዝ ፊደል በ፲፰፻፺፪ በኦሮምኛ ጽፈው ሲያሳትሙ በኋላ ሞክሼዎች ከተባሉት ኣንድኣንዳንዶቹን ኣስወግደዋል። “ፍቅር እስከ መቃብር”  67 ሞክሼዎች ቀለሞች በሌሉት አማርኛ በክቡር ዶ/ር ሓዲስ ዓለማየሁ በ፲፱፻፶፪ ታትሟል። (ይህ የሆነው የኢትዮጵያ ማተሚያ ቤቶች ሞክሼ የተባሉትን ቀለሞች እየኣሉት ነው።) የኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማእከል  ግዕዝ ኮምፕዩተራይዝድ ከሆነ በኋላ በታይፕራይተር ዓይነት ቅጥልጥል ፊደል “ኣማርኛ መዝገበ ቃላት” ሞክሼዎች የተባሉትን በሌሉት ቀለሞች በ፲፱፻፺፫ ኣትሟል። ስለ ሞክሼዎች በምሳሌ ቀረቡ እንጂ ደራሲዎቹ በሥራዎቻቸው ታላላቅ የኣገር ባለውለታዎች ናቸው። ፳፪. ዶ/ር ኣበራ ሞላ “ኧ” ስምንተኛው የ“አ” ቤት ፊደል መሆኑን በ፲፱፻፺፬ ዓ.ም. ጽሑፋቸው እስከኣመለከቱበት  ጊዜ ድረስ ብዙዎቹ የኣላወቁት ይመስላል። ሓዲስ ዓለማየሁ “ኧ” የእራሱ እንዚራን እንዳለው ቈጥረው በስሕተት ስድስት እንዚራኑን ጭምር ቀንሼዋለሁ ብለዋል።  የኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርሲቲም ኧ”ን ጥቅም ላይ ኣላዋልኩም ቢልም “ኧ”ን በስምንተኝነት ሳይጠቀምበት ጥሎታል። “አ” እና “ኧ” ሞክሼዎች ስለኣልሆኑ መጽሓፎቻቸው ውስጥ የማይመለከታቸው የሞክሼዎች ኣጠቃቀምና ውይይት ውስጥ ሁለቱም በስሕተት ጣልቃ ኣስገብተዋቸዋል። እነዚህ የኣለ በቂ ምርምር በስመ ሞክሼ የቀረቡ ጉዳዮች የኣለፉትን ችግሮች እያስወገዱ የኣሉትን የዶክተሩን ሥራዎች ኣክብደዋቸዋል። ሓዲስ የ“ኧ”ን ግዕዞች ብቻ ይዤ እርባታቸውን ጥያለሁ ቢሉም “ኧ” የግዕዝ ቤት ቀለም ኣይደለም። የ“ኸ”ን ግዕዝ ብቻ ይዤ እርባታቸውን ጥያለሁ ቢሉም “ኸ”ን ከእንዚራኖቹ ጋር ጥለዋል ማለት ይቻላል። ምክንያቱም ሓዲስ “ኹ”ን የጣሉት የ“ሁ” ሞክሼያቸው በመሆኑ ኸም የሀ ሞክሼያቸው ስለሆነ እንደሌሎቹ መጣ'ል ነበረበት። ዩኒቨርሲቲውም ነባር የፊደል ገበታው ውስጥ “ኧ”ን እንደ ግዕዝ ቤት ወስዶ እርባታዎቹን በጥያቄ ምልክቶች ኣቅርቧቸዋል። ፳፫. “ሀ” እና “ሃ” እንዲሁም “አ” እና “ኣ” ሞክሼዎች ኣይደሉም። እነዚህን ቀለሞች በስመ ሞክሼ ተሳስቶ በማስወገድ ማግደፍና ኣንዱን ቀለም ጥሎ ሌላውን ማንሳት ትክክል ኣይደለም። ይህ በስመ ሞክሼ ፊደል መቀነሰ ሳይሆን ፊደል ማስወገድ ነው። ለምሳሌ ያህል የሓዲስ መጽሓፍ ውስጥ ራብዖቹ “ሃ” እና “ኣ” የሉም። ሓዲስ መጽሓፋቸው ውስጥ በ“ሃ” ምትክ “ሀ”ን እና በ“ኣ” ቀለም ምትክ “አ”ን በስሕተት ተጠቅመዋል። እነዚህን ስሕተቶች ለማስወገድ በኣሁኑ ጊዜም አንደኣስፈላጊነቱ በ“ሀ” ምትክ “ሃ” እና በ“አ” ምትክ “ኣ”ን መጻፍ ትክክል መሆኑን ለኣንድኣንዶቹ ማስገንዘብ ኣስቸግሯል። ምክንያቱም መመራመር በማይችሉባቸው ጊዜያት የተማሯቸውን ስሕተቶች ከኣደጉም በኋላ በምርምር ለማሳመንና ለማስተካከል ሲሞከር የሚያስቸግሩ ስለኣሉ ነው። ምሳሌ፦ “ኣበራ” አንጂ “አበራ” ትክክል ኣይደለም። በተጨማሪም ፊደል ቀናሾችና ቀንጣሾች ወደዱም ኣልወደዱም ዶክተሩ ኣሸንፈው ሁሉም የግዕዝ ቀለሞች የዩኒኮድ መደብ ውስጥ ስለገቡ በእነዚህ ስሕተቶችና ግድፈቶች መቀጠል ኣስፈላጊ ኣይደሉም። ወደፊት ኮምፕዩተር ትክክለኛዎቹን ስለሚያቀረብ ዛሬ ሥራ ከማበላሸት ይልቅ መማር ሳይጠቅም ኣይቀርም። ፳፬. ዶክተሩ ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ሲያደርጉ የምልክት መርገጫ ላይ ወደዳር ከመደቧቸው መካከል “ኸ” ኣንዱ ነበር። ሓዲስ የ“ኸ” እና “ኧ” ግዕዞቻቸውን  ብቻ ይዤ እርባታዎቹን ጥያለሁ ሲሉ “ኸ” ወደ ግዕዙ “ሀ” ድምጽ የቀረበና “ኧ” (እንደ “Earth” “አርዝ”) የግዕዙ “አ” ድምጽ  መሆኑን የተገነዘቡ ኣይመስልም። በሌላ በኩል ስማቸውን “ሀዲስ” እንጂ “ሃዲስ” ኣለማለታቸውና “ኸ” ኣራተኛ የ“ሀ” ሞክሼያቸው መሆኑን ስለኣልጠቀሱም የተቸገሩበት ይመስላል። ስለዚህ በሓዲስ ኣስተሳሰብ “ኸ” እና “ኧ” ለየት የኣሉ ቀለሞች ብቻ ተደርገው በስሕተት የተወሰዱ ናቸው ማለትም ይቻላል። የ“ኸ” ጉዳይ ኣንድኣንድ ፈረንጆችንም ግራ ያጋባ ይመስላል። ለምሳሌ ያህል የ“ኧ” ድምጽ  ወደ “እዋ” የቀረበ ስምንተኛ የ“አ” ቤት ቀለም በመሆኑ በተለምዶ “ኧረ” የሚለው ቃል ኣጻጻፍና ኣነባብ የተሳሳቱ ስለሆኑ ትክክለኛው “አረ” ነው። ስሕተቱ የ“አ”ን ድምጽ እንጂ የፊደሉን መልክ ኣይመለከትም። ምሳሌም እዚህ ኣለ።  የስሕተቱ ምንጭ “አ” እና “ኣ” እንደሞክሼ ተወስደው የግዕዙ “አ” ሥራ ስለጐደለ ለ“ኧ” የተሰጠው ሳይሆን ኣይቀርም ይላሉ ዶክተሩ።

፳፭. ሊቁ ኣለቃ ኪዳነወልድ ክፍሌ ኣንድኣንድ ፀሓፊዎች ሲጠነቀቁ ብዙዎቹ አዐ፣ ሀሐኀ፣ ሰሠ፣ እና ጸፀ ፪ እና ፫ የሆኑበት ምክንያት ምን እንደሆነ ኣያስቡም ብለው የጥንቱ “አበገደ” ፊደል ኣኃዛዊ ስለሆነ “ጐ” ሰባ ቍጥርን ይወክላል ይላሉ። ፳፮. ሞክሼዎችን ለማስወገድ በተጀመረው ዘመቻ ሳቢያ የማያስፈልጉ ቀለሞች ዓማርኛ ቃላት ውስጥ ብቅ እያሉ የቋንቋውን የኮምፕዩተሮችና የእጅ ስልኮች ጽሑፎች ማበላሸት ቀጥሏል። ፳፯. የዓማርኛ ፊደልን መጻፍ የኣልቻለው የጽሕፈት መሣሪያ ሳይጽፈው ተዘልሎ ኮምፕዩተር ደርሶለታል። ትክክለኛዎቹን ኆኄያት ከመማር ይልቅ መቀነስ የሚፈልጉትን ቴክኖሎጂ ስለሚደርስላቸው የሞክሼዎች ተግዳሮት ዘላቂ ኣይደሉም። በፊደሉ ብዛት የተነሳ መጻፍ ያስቸግራል ሲሉ የነበሩት መፍትሔ ከተፈጠረለት ፴ ዓመታት እንደኣለፉ የኣልሰሙ ይመስላል።  “The quick brown fox jumps over the lazy dog.” የሚለውን የእንግሊዝኛ ዓረፍተ ነገር “ዘ ኲክ ብራውን ፎክስ ጀምፕስ ኦቨር ዘ ሌይዚ ዶግ።” ብሎ ሞክሼውን ሳይቀንሱ ጭምር በዓማርኛ መጻፍ ያታርፋል። ለምሳሌ ያህልም የኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርሲቲው ማዕከል ሞክሼዎች እንዲቀነሱ ስለወሰነና “ኲ” በ“ኩ” አንዲተካ ስለፈለገ ቀለሙ ስለማይኖር “ኲክ” (quick) የሚለው ቃል በዓማርኛ እንዲጻፍ የሚፈልገው “ኩክ” በማለት ነው። ከላይ የቀረበውን 36 ሥፍራዎች የወሰደውን የእንግሊዝኛ ዓረፍተ ነገር በግዕዝ 24 ሥፍራዎች መጻፍ ስለሚቻል ሞክሼዎችን የማስቀረት ጉዳት አንጂ ጥቅም ኣያሳይም። ጽሑፍን በፊደላዊ (Alphabetic) ፊደል ከመጻፍ ይልቅ በግዕዙ ድምጻዊ (Phonetic) ፊደል መጻፍ የወረቀትንና የኮምፕዩተር ጽሑፎች ማስቀመጫ ስፍራዎችን ስለሚቆጥብ ጽሑፎችን በላቲን ፊደል ለሚጽፉ ኢትዮጵያውያንም ትምህርት ነው። ምክንያቱም ዓረፍተ ነገሩን በኦሮምኛ ቁቤም ሆነ በአማርኛ ቁቤ መክተብም ኣያታርፍም። ፳፰. ዕውቀትን መቀነስ ሞክሼዎችን እንደመቀነስ ስንፍና እንጂ ጉብዝና ኣይደለም። ኢትዮጵያውያን ሞክሼ የተባሉትን ሳይቀንሱ ለረዥም ዘመናት በእጃቸውና ማተሚያ ቤቶች ሲጠቀሙ ቆይተው ታይፕራይተርን የኣዩ ለመቀነስ ታግለው ኣልተሳካላቸውም። ነገር በቀለለበት በእዚህ ዘመን እየኣንድኣንዱ ፀሓፊ በቀላሉ ኣታሚ በሆነበት ጊዜ ስለ ፊደል ማስተማር እንጂ መቀነስ ምሁራዊ ተግባር ኣይደለም። “መሳሳት” (“ርህሩህ ወይም ስስ መሆን”) እና “መሣሣት” (“ትክክል ኣለመሆን”) ኣንድ የኣልሆኑት  በዓማርኛ ድምጽ መጥፋት ኣይደለም። ኣንዳንዶቹ ፊደል መቀነስ የሚፈልጉት ለዓማርኛው ከኣላቸው ጥላቻ ወይም ኣጎብጋቢነት ሊሆን ይችላል። የፊደላቱን መልኮች ከመቀየር ኣንስቶ ግዕዙን በላቲን ፊደል መተካት የሚፈልጉ ኣሉ። “ተደጋግሞ የሚነሳውም የቱርክ (ኣረብኛ) ፊደሏን ትታ የላቲን ፊደልን መቀበሏና የጃፓን ፊደሏን ሳትቀይር በሥልጣኔ የመገስገሷ ታሪካዊ ተሞክሮ ነው። የእኛ ኣገር የብሔር ፖለቲከኞችና ኣመራራቸው የቱርኩ ልምድ ይሻለናል ብሎ ከወሰነ፣ ይኼው ሁለት አሥርት ዓመታት ገደማ ተቆጠሩ” ይላል ይህ  ጽሑፍ። የዓማርኛውን ፊደል ትተው ቋንቋውን በላቲን ፊደል የሚጽፉ ባይጠፉም፤ ግኝቶቻቸው ከግዕዝ ኣልፈው ለላቲኑ ስለጠቀሙ ዶክተሩ በሥራና ተቃውሞ ቀድመዋቸዋል። 

፳፱. ግዕዝ በማተሚያ፣ የኮምፕዩተርና የእጅ ስልክ ቴክኖሎጂዎች በሚገባ እየተጠቀመ ነው። እንደሰዉ ብዛት ግን ብዙ ጽሑፎች በኮምፕዩተርና የእጅ ስልኮች ተጽፈው ኣልተቀመጡም። በኣንድ የፊደል ዓይነት መጻፍ የኣልቻለን ሕዝብ ሞክሼዎች በኣሉትና በሌሉት ጻፍ ማለት ተገቢ ኣይመስልም። ምክንያቱም ኣዲስ ነገር ከጥንቱ ጋር ይቀርባል እንጂ ስለማይተካው ነው። ፴. የግዕዝ ቋንቋ ቀለሞች የዓማርኛ ቋንቋ ፊደል መነሻ ቢሆኑም የተለያዩ ሰዎች የተለያዩ ቀለሞችን ሞክሼዎች ናቸው በማለት ከዓማርኛ ሲቀንሷቸው ተስተውሏል። እነሱ የኣሰቡት ቢሳካላቸው እነ “Quick”፣ “Which”፣ “Qwench”፣ “Guie”፣ “Kwikset”ን የመሳሰሉት ቃላት በእንግሊዝኛ እንጂ በዓማርኛ መጻፍ ላይቻል ነው። እንደእነዚህ ዓይነት ምሁራን ለማያውቋቸው የግዕዝ ፊደል ተጠቃሚ ቋንቋዎች ቀርቶ ለሚያውቁት ዓማርኛ ደንታ የሌላቸው ሳይሆኑ ኣይቀሩም። ፴፩. በስመ ሞክሼ ፊደሉን መቀነስ የጀመሩት ጥቂት ዓማርኛ ተጠቃሚዎች ናቸው። የግዕዝ ፊደል ኣንዱ ትልቅ ችሎታ ለኣዳዲስ ድምጾች ኣዳዲስ ቀለሞች መፍጠር መቻሉ ነው። ፴፪. ዓማርኛ ፊደላቱን ከግዕዝ ቢወስድም ለቋንቋው የማያስፈልጉትን ሞክሼዎች መጣል ነበረበት የሚሉ ኣሉ። ዓማርኛ የሚጥላቸው ሞክሼዎች የሉም። እንግሊዞች ፊደላቸውን ለማሻሻል ሞክረው ኣልተሳካላቸውም እየተባለ ዓማርኛው መሻሻል ኣለበት ማለት ምንድን ነው?  

፴፫. የግዕዝ ፊደል ውስጥ ለሌሉ ድምጾች ኣዳዲስ ቀለሞች መፍጠር ሊያስፈልጉ ይችላሉ። ይህ ፊደላችን ለሌሎች ቋንቋዎችና ፊደላትም እንዲጠቅም ያስችላል። ዓማርኛ ከግዕዝ የወረሳቸውን ቃላት እየተጠቀመ እየኣደገ ነው። ፊደላቱ እንዳይቀነሱ ከሚፈልጉት ኣንዱ ዶ/ር ኣምሳሉ ኣክሊሉ ናቸው።  ይህ በእንዲህ እንዳለ ግዕዝ ውስጥ የኣሉት በተናጠል እየቀጠሉ ሞክሼዎች የሚሆኑት ዓማርኛ ስለሆኑ የሚመስላቸው ኣሉ። ይህ እውነት ኣይደለም። ፴፬. ኢትዮጵያውያን ቀለሞቻቸውን ሳይቀንሱ በብራናና ማተሚያ ቤቶች ብዙ ደክመው በሚገባ ተጠቅመውባቸው ኣቆይተውናል። ይኸንኑ ፍላጎት ዶክተሩ በኮምፕዩተር ከማሳካት ሌላ ለዩኒኮድ ኣቅርበው የፊደሉ ፍላጎት ተሟልቷል። የግዕዝን ፊደል ሳይጽፍ የእንግሊዝኛውን የታይፕ መሣሪያ ዓማርኛን እንደጻፈ መቍጠርና ይኸንኑ በኮምፕዩተር መጠቀም እራስን ማታለል ነው። ፊደል መቀነስና መቀንጠስ ከታይራይተር ጋር ጊዜው የኣለፈበት ኣስተሳሰብ ነው። ፴፭. በኣንድ በኩል ፊደል በዛ እያሉ በሌላ በኩል የሚጠብቅና የሚላሉ ቃላት ችግር ፈጥረዋል የሚሉ ኣሉ።  የፊደል ቀናሾች ስንፍና  ወደ ኮምፕዩተርና የእጅ ስልክ ስለገባና ኣንድኣንዱን ሰው ከሚገባው በላይ ቸልተኝነት ስለተጠናወተው መቀስቀስ ኣስቸግራል። ስለ ቴክኖሎጂ ኣንብቦ ከመረዳት ይልቅ በወሬ የተገኘውን ሶፍትዌር እየተጠቀመ ፊደል ሲጎድልበት መጠየቅ የማይችል ሆኗል። ፴፮. በተቀነሱ ቀለሞች የሚጠቀሙ ደራስያን ጽሑፎች ኢንተርኔት ላይ ተፈልገው ላይገኙ ስለሚችሉ እራሳቸውና ሥራዎቻቸውን ከጥቅም ውጪ እያደረጉ ናቸው። 

፴፯. ሁለተኛው የሞክሼዎች ጥቅም ዓማርኛ ከሌሎች ሴማዊ ቋንቋዎች ጋር ያለውን ዝምድና ስለሚያመላክቱ ነው።   የዓማርኛ ሞክሼዎችን ለመለየት ከቃላቱ ብቻ ፍንጭ ማግኘት ስለሚቻል ምሳሌዎችን ከመሸምደድ ይልቅ መረዳት ሳይጠቅም ኣይቀርም ይላሉ ዶክተሩ። ለምሳሌ ያህል “ፀሓይ የሚለ ቃል ውስጥ “ፀ የጠበቀ ስለሆነ ፀሓዩን “ፀ መጠቀም ይጠቅማል። “ንሥርና “ንስርን ለመለየት የቋንቋው ተናጋሪ በድምጽ ስለሚለያቸው “ንስርን ከእሳቱ “ሰ ጋር በማያያዝ ኣገባቡን መለየት ይቻላል። ሌላ ምሳሌ “ምሥር እና “ምስር ሲሆን የጠበቀው እንደንጉሡ “ሠ” ባለ ንጉሡ “ሠ” “ምሥር መሆኑ ነው።  “ምሥር”ን ኣጥፍቶ እንደ “ምስ'ር” መጻፍ ሥፍራና መርገጫዎች በማስጨመር ያካስራል። “ምስር” እንዲሁ ወይም (Default) ያልጠበቀ ሲሆን “ምሥር” እንደ ዓይኑ “ዐ” የጠበቀ ስለሆነ ኣነጋገሩን ከፊደሉ ማገናኘት ሳይጠቅም ኣይቀርም። የሞክሼዎች ኣጠቃቀም ኃይማኖታዊ ነው የሚሉም ኣሉ።  ዓይንና ዓመት የጠበቁ ናቸው ቢባል የወንዙን ስም በኣባይ የሚጽፉ ኣሉ።  ስለዚህ እነዚህ ነገሮች ጥናት ያስፈልጋቸዋል። ለምሳሌ ያህል ኣባይ እና ዓባይን በድምጽ መለየት ይቻላል እንዳይባል የሚጠብቀውና የሚላላው ባ ቀለም ስለሆነ ነው። ፴፰. የሞክሼ ተብዬዎቹ መኖር ዓማርኛውን ኣዳበረው እንጂ ኣልጎዳውም። ይህ ፊደሉን የሚጠቀሙ ሌሎች ቋንቋዎችንም ሊመለከት ይችላል። የላቲን ፊደል ስለኣስቸገረ ፈረንጆች ኣዳዲስ ፊደላት እየፈጠሩ እያሻሻሉት ነው። ፴፱. የሞክሼ ፊደል ጉዳይ ጊዜው የኣለፈበት ክርክር ነው። በኮምፕዩተር ዘመን ቴክኖሎጅው ችግሮቻችንን ስለሚፈታ ፊደል ለመቀነስ መከራከር ግዕዛዊ ኣይደለም። ትክክለኛዎች ቀለሞች ከሌሉ ወደፊት ኮምፕዩተሩን ማናገር ቀላል ኣይሆንም። ሞክሼዎችን በሚፈልጉና በማይፈልጉ መካከል የሚፈጠሩት ችግሮች ሰዉ ላይ ሥራ ያበዛሉ። ፵. ኆኄያትን መጠበቅ ቅኔ ላይ ትንሽ ችግር ሊፈጥር ይችላል።  

፵፩. በቅርቡ በግዕዝ ፊደል መብዛት የተነሳ መዝገበ ቃላትን መጠቀም ኣስቸገረ በማለት ፊደል እንዲቀነስ የሚል መጽሓፍ ተጽፏል።  ይህ ጊዜው ያለፈበት ኣስተያየት ነው። ወደፊት ኣንድ የሚፈለግን ቃል ጽፎ ኮምፕዩተር ካለበት ያወጣዋል እንጂ መጽሓፍ ማገላበጥ ኣያስፈልግም።  ፵፪. መጥበቅና ኣለመጥበቅ ከሞክሼዎች ጋር እንዳይምታቱ መጠንቀቅ ያስፈልጋል።
  
በሌላ በኩል የዓማርኛን ሞክሼዎች መወገድ የሚፈልጉ ምክንያቶች ቢኖሯቸውም  ኣንዳንዶቹ ከላይ ተጠቃቅሰዋል። ፩. ስድስት ዓይነቶች “ሀ”ዎች ቢኖሩም በሃሌታው “ሀ” እና እንዚራኖቹ ብንጠቀም የእነ “ሐ”፣ “ኀ”፣ “ኈ”፣ “ኸ” እና “ዀ” እንዚራኖች ጭምር ድምፆች ኣንድ ዓይነት በመሆናቸውና ዓማርኛ ውስጥ ስለጠፉም ስለማያስፈልጉ የቀለሞች ቍጥር ይቀንሳል ነው። ፪. ሞክሼዎች ቢቀነሱ ግዕዝን ለመክተብ በሁሉም ቍልፎች መጠቀም ኣያስፈልግም የሚሉ ኣይጠፉም። ፫. የኣለነው ዓለም እየሰለጠነና ነገሮች እየቀለሉ በኣሉበት ዘመን ስለሆነ መቀነስ የምንችላቸው ስለኣሉ መጓተት ኣያስፈልግም የሚሉ ኣሉ። ፬. በግዕዝ ፊደል የሚጠቀሙ የተለያዩ ቋንቋዎች ድምፆችን የሚወክሉት ኣዳዲስ ቀለሞች ተሠርተው ሥራ ላይ ስለዋሉ የማያስፈልጓቸውን ሞክሼዎች ማስወገጃ ጊዜው ኣሁን ነው የሚሉ ኣይጠፉም።

ፓተንት (Patent) ኣንድ ሰው ጥቅም ያለው ኣዲስ ነገር ወይም ግኝት ሲያቀርብ ከመንግሥት ለተወሰነ ጊዜ የሚሰጥ የባለቤትነት መታወቂያ ነው። በፓተንት የተጠበቀን ግኝት ያለባለቤቱ ፈቃድ መሥራት፣ መጠቀምና መሸጥ ክልክል ነው። ምሳሌ፦ እ.ኤ.ኣ. በ1878 የ“ቅውኽርትይ”ን (QWERTY) የእንግሊዝኛ የታይፕ መሣሪያ ለፈጠረው ክሪስቶፈር ሾልስ ቍጥሩ 207,559 የሆነ የዩናይትድ እስቴትስ ፓተንት ሲሰጠው የእጅ ስልክ በ1973 ለፈጠረው ማርቲን ኩፐር ቍጥሩ 3,906,166 የሆነ የኣሜሪካ ፓተንት ተሰጥቷል። በ2015 ግዕዝ በኮምፕዩተር ለተከተበበት ግኝት ቍጥሩ 9,000,957  የሆነ ለዶክተር ኣበራ ሞላ በዩናይትድ እስቴትስ መንግሥት የባለቤትነት መታወቂያ መጋቢት ፳፱ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ተሰጥቷል። የፓተንቱ ስም፣ ቍጥር፣ ፈጣሪና የተሰጠበት ቀን ይታተማል።  (የኢትዮጵያም ፓተንት ለዶክተሩ በሦስት ወራት ውስጥ እንደሚሰጥ ጥቅምት ፳፱ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም. ተጽፏል።)  ይህ ኣብሻ በሚል ስም የታወቀው ግኝት ግዕዝ በኮምፕዩተርና ከመሳሰሉት ከኣንድ ገበታ በኣንድና ሁለት መርገጫዎች እንዲከተብ የኣስቻለ መደብ ነው። ለግዕዝ ፊደልም የመጀመሪያው ፓተንት ነው።   ፓተንት ለፈጣሪው የሚሰጠው ዕውቀቱን ለሕዝብ ስለኣሳወቀ ሌሎች ያለፈጣሪው ፈቃድ እንዳይጠቀሙበት መከላከያ ሲሆን የመለያ ቊጥር ይሰጠዋል። ኣንድ ሰው ፓተንት ኣለኝ ሲል በስሙ ወይንም በፓተንቱ ቍጥር በመፈለግ ማረጋገጥ ይቻላል። ምሳሌ እዚህ፦  የግዕዝ ፓተንት ተሰጠ ማለትም ኣሜሪካ ግኝቱን ኣጣርቶ ለዓለም በማሳወቅ ስለግኝቱ ኣተመ እንጂ ፊደሉ ለኣሜሪካ ተሰጠ ማለት ኣይደለም። የግዕዝ ፊደል ቴክኖሎጂ በፓተንት የተጠበቀ ስለሆነ የግኝቱን ፈጣሪ መብት ማክበርና ማስከበር ከሕዝቡና መንግሥት ይጠበቃል።

የግዕዝ ፊደል ሁለተኛ የዩናይትድ እስቴትስ የባለቤትነት ማሳወቂያ በቅርቡ ኣግኝቷል።  ዶክተር ኣበራ ሞላ ቍጥሩ ዘጠኝ ሚሊዮን ሰባት መቶ ሰላሳ ሦስት ሺህ ሰባት መቶ ሰላሳ ሁለት የሆነ ኣዲስ የዩናይትድ እስቴትስ የባለቤትነት ማሳወቂያ (ፓተንት) ሚያዝያ ፯ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. ተሰጣቸው። ይህ ኮምፕዩተሮች፣ የእጅ ስልኮችና ተመሳሳይ መሣሪያዎች ውስጥ የእንግሊዝኛ ፊደላት ከሚከትቡበት ኣንዳንድ ዘዴዎች ጋር የተቀራረበ ነው።

በቅርቡ ኣንድ የኤውሮጳ ኩባንያ ከጤፍ ኣጠቃቀም ጋር የተያያዘ ፓተንት ስለኣገኘ ኢትዮጵያውያን ኣልተደሰቱም።   ዶ/ር ኣበራ ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ኣድርገው በፓተንቶች ባይጠብቋቸው ኖሮ ኢትዮጵያ ከማትወጣበት ጣጣ ትገባ እንደነበረ በሚገባ የተረዱ ምሁራን ኣሉ። የዶክተሩን ግዙፍ ውለታዎች ከግማሽ ደርዘን በላይ የሆኑ ድርጅቶች በሽልማት ሲያበረታቷቸው  የኢትዮጵያን ቅርስ፣ ፊደልና ቋንቋዎች በኣዳዲስ ቴክኖሎጂ እንደጠበቁ ዛሬም ያልተገነዘቡ ኣሉ። የዶክተሩ ድካም ኣንዱ ምክንያት የኢትዮጵያውያን በፊደላቸው የመጠቀም መብት እንዳይወሰድባቸው ነው። 

ኣንድ ፓተንት የኣለው ፈጣሪ በፈጠራው ላይጠቀም ወይም ውጤቱን ላይሸጥ ይችላል። ቴክኖሎጂ ዓለምን ስለኣቀራረበና በፍጥንት እያደገ ስለሆነ ፓተንት ማግኘት ቀላል ነገር ኣይደለም። በፓተንት የሚጠበቅ ግኝት መጀመሪያ ለመንግሥት እንጂ ለሕዝብ መቅረብ የለበትም። በግዕዝ ፊደል ለብዙ ሺህ ዓመታት ስንጠቀም ስለነበረ ኣጠቃቀሙም ሆነ ፊደሉ ኣዲስ ነገር ኣይደለም። ዶክተሩ የፓተንትን ጥቅም ቀደም ብለው ያውቁ ስለነበረ ቴክኖሎጂው እንደጀመረ በመረዳትና በማበልጸግ የሠሩት በሌሎች እንዳንቀደም ነበር። ቴክኖሎጂውንም የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር እንደሚጋሩም በኢትዮጵያ ኤምባሲ በኩል ለመንግሥት በጽሑፍ ቢገለጽም ስላልተባበሩ መብታቸውን ለማስጠብቅ ወደ ኣሜሪካ መንግሥት ስለተመለሱ ኣሜሪካም የኢትዮጵያ ባለውለታ ናት።  ዶ/ር ኣበራ የግዕዝ ፓተንት ኣገኙ ማለት ሰዉ በፊደሉ እንዳይጠቀም ተደረገ ማለት ኣይደለም።

ሌላ የፓተንት ጥቅም ሌሎች ዓዋቂዎች ቀደም የኣሉትን እየጠቃቀሱ በማሻሻል ኣዳዲስ ፈጠራዎችን እንዲፈጥሩ ነው። የፓተንቶች በሌሎች መጠቀስ ለግኝቱ ፈጣሪ፣ ኩባንያና ኣገርም ክብር ነው። ለምሳሌ ያህል የዶ/ር ኣበራ ፈጠራዎች ከደርዘን በላይ የዓለም ፓተንቶችና ማመልከቻዎች ውስጥ ተጠቅሰዋል። የፓተንት መረጃዎችም ውስጥ ከግኝቱ ጋር የተያያዙ ጠቃሚ ሥራዎች በፈጣሪዎቹና መርማሪዎች ይጠቀሳሉ።  በዶ/ር ኣበራ ሞላ ስምና በብቸኝነት እስከኣሁን (እ.ኤ.ኣ. 2018) የተሰጡዋቸው ፓተንቶች ቍጥር 9 ደርሰዋል። በኣሜሪካ ፓተንት የሚሰጠው ሰው ነዋሪነት (Citizen) እንጂ ዜግነት (Nationality) ኣይመዘገብም። ቍጥሩ 10,067,574 የሆነ ሦስተኛ የዩናይትድ እስቴትስ የግዕዝ ፓተንት በቅርቡ ለዶክተሩ ተሰጥቷል።  በቅርቡም ኣራተኛ የዩናይትድ እስቴትስና ሦስት የኢትዮጵያ ፓተንቶች ለዶክተሩ ተስጥተዋል። 

ዶክተር ኣበራ ሌሎች ፓተንቶች እንዳሏቸው ቀደም ብሎ ተጠቅሷል።   እንዶድ ትላትልን እንደሚገድል በደረሱበት ትልቅ ኣስተዋጽዖዋቸው የኣሜሪካ ፓተንት በማግኘት የታወቁት ሌላው ኢትዮጵያዊ ዶ/ር ኣክሊሉ ለማ ናቸው። የኣሜሪካ ፓተንቶች ያሏቸው ኢትዮጵያውያንም እነዚህ ብቻ ኣይደሉም። የመጀመሪያው የዩናይትድ እስቴትስ ፓተንት ከተሰጠበት 1790 ኤ.ዲ. ጀምሮ የኣሉት  ኢንተርኔት ላይ ይገኛሉ። ፓተንቶቹ ለቀለሞቹ ስለሆኑ ዶክተሩ መብቱን ያስከበሩት ለኢትዮጵያና ኤርትራ ፊደላት ነው። የዶ/ር ኣበራ ሞላ ፓተንቶች የኣማርኛ ታይፕራይተርን ስለማይመለከቱ ከእነሱ ጋር ግንኙነት የላቸውም።

የፓተንትና ኮፒራይት መብቶች የተለያዩ ናቸው። ለምሳሌ ያህል የዶክተሩ የሞዴት የዩናይትድ እስቴትስ ኮፒራይት መብት እዚህ ኣለ።  የግዕዝ ፊደል ከተለያዩ መብቶች ጋር በተያያዙ ተጠቃሚዎቹ እንዲጠቀሙ የመብት (Copyright)፣ ንግድ ምልክት (Trademark)፣ ተመዝግቧል ምልክት (Registered)፣ የመሳሰሉትን ፈጥረው በፓተንታቸውም ስለኣስተዋወቁ በዓማርኛ መጠቀም ተጀምሯል። የግዕዝ ፊደል የእጅ ስልክ ትክክለኛ ሳይንሳዊ ቴክኖሎጂ ኣጠቃቀሞች ዘዴዎቹን ለፈጠሩት ለዶ/ር ኣበራ ሞላ ቍጥራቸው 9000957፣ 9733724፣ 10067574 እና 10133362 በሆኑ የዩናይትድ እስቴትስ ፓተንቶች ተሰጥተዋል።

ግዕዝን ዲጂታይዝ ሲያደርጉ ዶ/ር ኣበራ ሞላ ለዓለም ከኣበረከቷቸው ግኝቶች መካከል የግዕዝ ኣልቦ ወይም ዜሮ ቍጥር ምልክት (Ethiopic Zero Symbol) መፍጠር ኣንዱ ነበር።    በእዚህ ግኝት የተነሳ አንደጥቂት ባለ ኣኃዝ የዓለም ፊደላት ግዕዝ ኣዲስ ባለ ኣሥር ቤት (Base Ten) የኣኃዝ ቀለሞች ኣሉት።     እነዚህም ኣዲሱ የኣልቦ ኣኃዝ ምልክትና የሚከተሉት ከኣንድ እስከ ዘጠኝ የኣሉት የግዕዝ ቍጥራዊ ኣኃዞች ናቸው። የዘጠኙ ቍጥሮች መልኮች ከፊደላውያኑ ጋር ኣንድ ዓይነቶች ቢሆኑም የኣሥሮቹ ቍጥራዊ ኣኃዞች ዶክተሩ ኮምፕዩተራይዝ የኣደረጓቸውን ሃያ የግዕዝ ቍጥሮችና በኋላም በዩኒኮድ ዕውቅና ያገኙትን የእነዚህኑ ሃያ ፊደላዊ ቍጥሮቻችን መብቶችና ኣጠቃቀሞች ኣይመለከትም። ኣዲሶቹ ኣሥር ቍጥራዊ ኣኃዞች የዱሮዎቹ ሃያ ቍጥሮች ላይ የተጨመሩ ሆነው በኣጠቃቀማቸው የተለያዩ ናቸው። ግዕዝ ወደ ዩኒኮድ ከመግባቱ በፊት ዘጠኞቹና  ኣልቦ በቊጥራዊ ኣኃዝነት ከኣራተኛው ፊደል በዶክተሩ  የግዕዝ መክተቢያዎች ሥራ ላይ ውለዋል። የግዕዝ ኣልቦ ኣኃዝ ከሞዴት 480 ቀለሞች ኣንዱ መሆኑና መርገጫው እዚህ ኣሉ።   

የኣልቦ ኣኃዝ ዋና ጥቅሞች ሁለት ናቸው። ኣንደኛው በቍጥርነት (Numeric) ሲሆን ሌላው ስፍራ በመያዝ (Positional) ነው። የግዕዝ ኣልቦና ቍጥሮች ኣስፈላጊ ናቸው። ፩. ኣልቦ የታወቀ ቍጥር ስለሆነ የግዕዝ ፊደል ተጠቃሚዎች በፊደላቸው የማያውቁበት ምክንያት የለም። ፪. የኣልቦ ስፍራ መያዝ ጥቅም በእንግሊዝኛው ዜሮ ለማስረዳት ያህል 2016 እና 201 ሲጻፉ በየተራ (Respectively) ምዕትና ዓሠርቱ ቤቶች ውስጥ ቍጥሮች እንደሌሉ ለማሳየት ነው። 2016 ከ201 የሚለየው በዜሮ ስፍራ ኣያያዝም ነው። ፫. እንደ ግዕዝ የኣሉ የጥንት ፊደላት የኣልቦ ጉዳይ በሚገባ ስለኣልገባቸው የቍጥር ምልክቶችን ከኣንድ ጀምረዋል።   የዜሮ ምልክት ጥቅም በሕንዶች ተደርሶበት ከሺህ ዓመታት በላይ ሥራ ላይ ቢውልም ኢትዮጵያውያን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ሳይጠቀሙበት ቆይተዋል።  የማተሚያ መሣሪያ ኢትዮጵያ ውስጥ ለግዕዝ ጥቅም ላይ በዋለባቸው መቶ ዓመታት ውስጥና ከአዚያ በፊትም የእንግሊዝኛውን (ኣረብኛ) ዜሮ ተጠቅመዋል። ፬. ግዕዝ ወደ ኮምፕዩተር ሲገባ ኣንድኣንዶቹ ቍጥሮቹ የቀረቡት በፊደልነት ስለሆነ ኮምፕዩተር ሁሉንም የግዕዝን ቍጥሮች በኣኃዝነት ኣያውቃቸውም። ፊደሉ በኮምፕዩተሮችንና ተመሳሳይ መሣሪያዎች በሚገባ እንዲጠቀም የጎደለበት የኣልቦ ኣኃዝ ተሠርቶ ከዘጠኞቹ ኣኃዞች ጋር ተገቢ ሥፍራዎች ውስጥ መቅረብ ይኖርባቸዋል። ስለዚህ ኣዲስ ኣሥር ቍጥሮች ስለተጨመሩ ፊደሉ ሠላሳ ኣኃዞች ኣሉት። ዶክተሩ የኣልቦን ቍጥር መልክ የኣቀረቡትም ኣሁን ኣይደለም።   የግዕዝ ኣልቦ ሞዴት፣ ኢትዮወርድና ግዕዝኤዲት ፕሮግራሞች ኣራተኛው ፊደል ውስጥ ቀርበዋል። ኣዲሶቹ ኣሥር የግዕዝ ኣኃዛት ሥራ ላይ የሚውሉት በተግባር የእንግሊዝኛው ኣሥር ቍጥሮች ኣማራጭ በመሆን ነው። የኣዲሶቹ ኣሥር ቍጥሮች ኣጠቃቀም ከሃያዎቹ የተለየ ስለሆነ መለየት እንዲቻል ኣዲሶቹን “ኣበራ” ማለት ይቻላል። ኣዲሶቹን በቅርጽም መለየት እንዲቻል ትንሽ ለውጥ ማድረግ ሳይጠቅም ኣይቀርም፦ ምሳሌ ወንበሮቻቸውን ማንሳት። 

፭. ግዕዝ ወደ ኮምፕዩተር ሲገባ ከዶ/ሩ ኣሥር ኣኃዛት በስተቀር ኣሥራ ኣንዶቹ የቀረቡት በፊደልነት ነበር። ከኣሥር እስከ መቶ የኣሉትንም የመደቡት የሰባተኛው ፊደል ኣኃዞች መርገጫዎች ላይ በፊደልነት ነበር። ይህ ስንጠቀምባቸው የነበሩትን ፳ የግዕዝ ቊጥሮች ኣጠቃቀሞችንም ኣልቀየረም። በኋላም ሃያዎቹ ወደ ዩኒኮድ የገቡት በፊደልነት ነበር።  ፮. የግዕዝ ኣልቦ ኣኃዝ ሥፍራው የቍጥሮች መካከል በመሆን ነው። ከዜሮው በላይ በኣሉት ቍጥሮች ልክ ከዜሮ በታችም ኣሉ። ፯. ዶክተሩ የግዕዝን ዜሮ ፈጥረው የጨመሩት ቍጥሮቹ ኣልቦን ስለሌላቸው እንደሮማ (Roman) ኣኃዛት ለሂሳብ ሥራ ኣይጠቅሙም ተብለው እንዳይዳከሙም ነው። ፮. ኮምፕዩተር የሂሳብና የጽሕፈት መሣሪያ በመሆኑ ግዕዝ ዜሮ ቍጥርን ስለሌለው ፈጥረውለት ዶክተሩና ሞዴት፣ ኢትዮወርድና ግዕዝኤዲት ፕሮግራሞቻቸውን የገዙ ሲጠቀሙበት ቆይተዋል። የቍጥሮችን ስፍራዎች ዩኒኮድ ለእንግሊዝኛ ስለመደበ ግዕዝ ወደ ዩኒኮድ ሲገባ የግዕዝን ኣኃዞች ከላቲኑ ጋር መጠቀም ስለኣልተቻለ የፊደላት ስፍራዎች ተሰጥተዋቸዋል። የግዕዝን ኣልቦ የኣለው የግዕዝ ኣሥር ቊጥራዊ ኣኃዛት ስፍራዎቹን ከእንግሊዝኛ ጋር መጋራት ይችላሉ። ፯. የግዕዝ ዜሮ ስለሌለ የጥንት ኢትዮጵያውያን ሂሳብ ኣያውቁም ወይም ኣይችሉም ማለትም ኣይደለም። የመደመር፣ መቀነስ፣ ማባዛትና ማካፈል ዘዴዎች ምሳሌዎች እዚህ ኣሉ።    
  ፰. የግዕዝ ፊደል ኣልቦ ቍጥርን ኣልነበረውም እንጂ ኣስተሳሰቡን ኣልተጠቀምበትም ማለት ኣይደለም። ኣንድ ስንዝር ሲለካ የመነሻው የኣውራ ጣት ስፍራ በቍጥር ሲገለጽ ኣልቦ ነው። የኣልቦ ኣጠቃቀሞች ዘመን መቍጠሪያችን፣ ኮከብ ቆጠራና ሌሎችም ውስጥ ኣሉ። 

፱. በግዕዝ ኣልቦ ምልክት መፈጠር የተነሳ ኢትዮጵያ ለዓለም ኣዲስ የቍጥር ኣኃዝ ኣበርክታለች። በግኝቱ መጠቀምና ማስተዋወቅ የኢትዮጵያውያን ኃላፊነት ነው። ከሠላሳ ዓመታት በላይ ሥራ ላይ የዋለ ኣኃዝና ፓተንቶችም ውስጥ የቀረበ በመሆኑ ከማተሚያ ቤት ጎደሎ ፊደሉና የታይፕራተር ቅነሳ ኣስተሳሰብ መላቀቅ ያስፈልጋል። ፲. ዶ/ሩ የግዕዝን ኣልቦ ምልክትና ኣጠቃቀም ስለኣቀረቡ የግዕዝን ሃያ ኣኃዞች የኣጠፉ የሚመስሏቸው ኣሉ። ፲፩. ኣንድኣንድ ሰዎች ፊደሉ እንከን የሌለው የእግዚኣብሔር ስጦታ ነውና ኣትነካኩት ይላሉ። የዶክተሩ ገለጻ ሳይንስ  እንጂ እምነት ኣይደለም። ፲፪. ዶክተሩ የግዕዝን ኣልቦ ከኣቀረቡ ከኣሥር ዓመታት በኋላ ለእኔም ታየኝ የእሚል ኣንድ ኢትዮጵያዊ ዩናይትድ እስቴትስ ኣለ።

፲፫. በኣሁኑ ጊዜ ነፃው፣ የሚሸጠውና የቁሱ ግዕዝኤዲት ውስጥ የኣሉት የግዕዝ ኣልቦና ቍጥሮች በኣኃዝነት ኣይሠሩም። የኣልቦውም ኣቀማመጥ ጊዜያዊ ነው። ፲፬. ኣልቦ ለረቀቁ የሂሳብ ሥራዎችም ኣስፈላጊ ነው። ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፊዚክስ ስማር ኣልቦ ኣልቦ መሆኑን ማረጋገጤን ኣስታውሳለሁ።  ፲፭. ግዕዝ ኣገር በቀል ፊደል ሆኖ ሳለ ለቅኝ ተገዥዎቻው ተሰጥተዋል።   ግዕዝ የኣልቦን ኣኃዝ የኣልነበረው ከኣምስት ግኝቶቹ ኣንዱ ኣኃዝነት ስለነበረ ሳይሆን ኣይቀርም። ፲፮. የጥንት ግብጻውያን በኣኃዞቻቸው ማባዛትን ከኢትዮጵያውያን ሳያገኙ ኣልቀሩም።   

፲፯. ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ኣደረግን የሚሉትን ኣንድኣንድ ዋሾዎች ከኣሳጧቸው መካከል የግዕዝ ኣልቦ ኣለመኖሯቸው ኣንዱ ነው። ምክንያቱም በታይፕራይተር ኣጠቃቀም ሥራ ላይ ማዋል የሚቻለው የላቲኑን ኣኃዞች ብቻ ስለሆነ የዶክተሩን የኣልቦ ኣኃዝ ኣስተሳሰብ ኣልደገፉም። ፲፰. በነገራችን ላይ የመጀመሪያዎቹ የላቲን ካፒታል ቀለሞች የግዕዙን ኣኃዞች የመሰሉት ኣንድኣንዶቹ ቀንና ደራሲ በሌለው ጽሑፍ ሊያሳምኑን በመፈለግ ምንጩ የግሪክ ሳይሆን ኣይቀርም እንደሚሉት ሳይሆን  ገልባጮቹ ግሪኮች ሳይሆኑ እንዳልቀረ መረጃ ኣለ። እዚሁ ጽሑፍ ውስጥ መጨረሻ ላይ መቀየሪያ ተብለው የቀረቡ ኣሉ። ሥራው ጥሩ ሆኖ ሳለ የቀረበው የኣረብኛን የኮምፕዩተር ቍጥሮች ወደ ግዕዝና ግዕዙን ወደ ኣረብኛው ያስቀይራል ተብሎ ነው። ዩኒኮድ ውስጥ የኣሉት የግዕዝ ቍጥሮች ፊደል እንጂ በኮምፕዩተር ወግና ኣሠራር ቍጥሮች ስለኣልሆኑ ለኮምፕዩተር ሂሳብ ሥራ የተዘጋጀ ኣለመሆኑ መታወቅ ኣለበት። ኣሁን በኣለው ወግና ኣሠራር ኮምፕዩተር በግዕዝ ኣኃዞች እንዲጠቀም ዶክተሩ ከብዙ ዓመታት በፊት የፈጠሩት የተሻለና ዘለቄታ የኣለው ዘዴ ነው። ፲፱. ግዕዝ ኮምፕዩተራይዝ ከተደረገ በኋላ ለትላልቆቹ ኣኋዞች የተለያዩ ቀለሞች መፍጠር የሞከሩ ኣሉ። ምሳሌ  ። ቍጥሮችን ከኣልቦ እስከ ዘጠኝ በኣሉ ቀለሞች መጠቀም ሳይንሳዊ ነው። ስለዚህ ኣዲስ ተጨማሪ የግዕዝ ኣኋዞችን መፍጠርን ዶክተሩ ኣያበረታቱም።  በእዚህ ኣጋጣሚ ዶክተሩ ማሳሰብ የሚፈልጉት ኣንድኣንድ ፀሓፊዎች ከሌሎች የኣገኙትን ዋቢ ኣድርጎ የማቅረብ ጥቅምና ኣስፈላጊነት መገንዘብ ነው። ዋቢ የሌለውን ጽሑፍ በዋቢነት መጠቀም ኣስቸጋሪ ነው። ፳. ኣልቦን ጨምሮ የእንግሊዝኛውን የኣኃዞች ኣጠቃቀም በተለይም ኣኃዞች በቃላት ሲገለጹ ጠንቅቆ ማወቅ ለትርጕም ጠቃሚ ነው።   

፳፩.  በዓማርኛ የጽሕፈት ሥርዓት ውስጥ የሒሳብ ምልክቶች ኣለመገኘታቸው ችግር ነው የሚሉ ኣሉ።   ከሒሳብ ምልክቶቹ ይልቅ የግዕዝ ኣልቦ ኣኃዝ ምልክት ኣለመኖር ነበር ችግሩ።  ምንም እንኳ የዜሮ ምልክት በቊጥሩ ስርዓት ውስጥ ባይኖርም፣ የዜሮ ጽንሰ ሐሳብ ግን ለብዙ መቶ ዓመታት አልቦ በሚለው ቃል ውስጥ ተካቶ እናያለን፣ በተለይ የማካፈል ስሌት ውጤቶች ውስጥ።  ፳፪. የዶክተሩ ኣሥር ኣዳዲስ የግዕዝ ቍጥራዊ (Numeric) ኣኃዞች ከኣንድ እስከ ዘጠኝ ከኣሉት የዩኒኮድ መደብ ውስጥ የገቡት ዘጠኙ ጥንታዊ ፊደላዊ (Alpahbetic) ኣኃዞች እንዲለዩ በቅርቡ ዶክተሩ መቀመጫዎቻቸውን ኣንስተዋል። ይህ ከግዕዝ ቀለሞች ጠባይም ጋር የሚሄድ ነው። ምክንያቱም ቍጥራዊና ፊደላዊ ኣኃዞች ቅርጾች መጋራት ስለሌለባቸውም ነው። ኣልቦው ጥቅም ላይ እንዲውል ዶክተሩ ከ1 እስከ 9 ተጨማሪም ኣኃዞች በመጨመር የግዕዝን ቍጥሮች ብዛት ከ፳ ወደ ፴ ከፍ ቢያደርጉም ኣሥሮቹን በቊጥርኝት በመቀጠል አንድንጠቀም ኣድርገዋቸዋል። ዶክተሩ ከዩኒኮድ በፊት የፈጠሩት የኣልቦ ቍጥራዊ ኣኃዝ መቀመጫ የኣለው ቀለም ሲሆን ከዩኒኮድ በኋላ በቅርቡ የጨመሯቸው ከኣልቦ እስከ ዘጠኝ የኣሉት መቀመጫ የሌላቸው ኣዳዲስ ኣሥር ቍጥራዊ ኣኃዛት ናቸው። ስለዚህ የዶክተሩ ኣልቦ ኣኃዞች ሁለት ዓይነቶች ናቸው። ሕዝቡ በኣማራጭነት እንዲጠቀምበት የሚፈልጉትም በኣዲሶቹ ኣሥሮቹ ቊጥራዊ ኣኃዞች ነው። እነዚህ ግኝቶችና ኣጠቃቀሞቻቸው በፓተንት ማመልከቻቸውም ተጠቅሰዋል። ዶ/ሩ GeezEdit Amharic P ፊደል ውስጥ የኣቀረቡት የግዕዝ ኣልቦ ዩኒኮዱ ውስጥ እንደኣሉት ኣኃዞች ፊደላዊ ነው። ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ሲያደርጉ ዶክተሩ ከኣረቡ ሌላ ለኣሥሩ ኣኃዛዊ ቍጥሮች ከሰባት በላይ ምርጫዎች ሲኖራቸው ታይፕራይተሩ በኣንድ የእንግሊዝኛ ፊደል ምትክ የቀረበ ቴክኖሎጂ ስለሆነ ለኣንድም ግዕዛዊ ኣኃዝ ስፍራ ኣልነበነውም። የኣማርኛ ታይፕራይተር ኮምፕዩተራይዝድ ሲደረግ ለፊደላት የነበረው 128 ስፍራዎች ብቻ ስለነበሩና ለኣማርኛም በቂ ቦታዎች ስለኣልነበሩት ግዕዝን በታይፕራተር ዲጂታይዝ ኣደረግን የሚሉት ፊደሉንና መጻፊያውን የኣልነበራቸው ዋሾዎች ጭምር ናቸው።   ፳፫. ለግዕዙ ግኝት ቀለም ቅርፅ የተጠቀሙት በእንግሊዝኛ እዝባራዊ ኣልቦ (Slashed zero) የሚባለውን ነው።  ከላቲኑ “o” (“ኦ”) ቀለም እንዲለይ የላቲኑም ኣልቦ ጠበብና ረዘም የተደረገ ስለሆነ ቅርፁ ወደ የግዕዝ ኣራት ቍጥር (“፬”)፣ ዓይኑ “ዐ” እና ፀሓዩ “ፀ” የቀረበ ስለሆነ እንዳያምታቱ ነው።  ስለ ዶክተሩ ኣልቦ ኣኃዝ ፈጠራ እስከኣሁንም ከኣልሰሙት መካከል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ይገኙበታል።  ፳፬. የግዕዝ ቍጥሮች ዩኒኮድ ውስጥ የኣሉት በፊደልነት ቢሆንም እንጠቀምባቸው።  ሃያዎቹ የግዕዝ ኣኃዞች ፩/1 ፪/2 ፫/3 ፬/4 ፭/5 ፮/6 ፯/7 ፰/8 ፱/9 ፲/10 ፳/20 ፴/30 ፵/40 ፶/50 ፷/60 ፸/70 ፹/80 ፺/90 ፻/100 ፼/10,000 ናቸው። ምሳሌ፦  ሰኔ 28 ቀን 2012 ዓ.ም. ሰኔ ፳፰ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም.።

የግዕዝ ፊደል ምልክቶቹንም (Symbols) ያጠቃልላል። በኮምፕዩተር ዘመንም ግዕዝ መሣሪያዎቹንና የእጅ ስልክ የመሳሰሉትን በሚገባ እንዲጠቀም ዶክተሩ የላቲኑን ምልክቶች በማውረስ ተጠቅመውባቸዋል። ከእነዚህም ዋናዎቹ ቍልፎች የኣሏቸው 32 ምልክቶች ናቸው። የኮምፕዩተር 42 እንግሊዝኛ ቁጥሮችና ምልክቶች ከግዕዙ ጋር ያቀረቡት ዶክተሩ ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ሲያደርጉ ለግዕዝ ሥራ እንዲያገለግሉ ወስነው ከግዕዙ ቀለሞች ጋር በተመጣጠነ መልክ መሥራት ስለጀመሩ ኮምፕዩተር ገበታ ላይ ያሉት ኣጠቃቀሞች ለግዕዝም እንዲያገለግሉ ነው። ለምሳሌ ያህል “+”፣ “-”፣ “*” እና “/” የመደመር፣ መቀነስ፣ ማባዛትና ማካፈል የግዕዝ የሂሳብ ምልክቶችና ማስሊያዎችም ናቸው። የግዕዝ ምልክቶች ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ የፈጠሯቸውን ኣሥር የዜማ ምልክቶች ያጠቃልላል።  ምልክቶቹን ከቀለሞች በላይ መክተብ ከኣስቸገረ ከቀኝ ጎኖቻቸው መክተብ ይቻላል። 

እንዲህም ሆኖ የላቲኑን ምልክቶች በግዕዝነት ስንጠቀምባቸው መከተል የኣለብን ኣጠቃቀሞች ኣሉ። ፩. የእንግሊዝኛው የፊደል ገበታ ላይ የኣለው የላቲንን የኮለን (Colon) ምልክት ኮምፕዩተሩ የሚያውቀው በኮለንነት እንጂ መልኩ የግዕዝን ሁለት ነጥብ ምልክት (“፡”) ስለመሰለ በነጥብነት ኣይደለም። ግዕዝ የእራሱ ኮድ የኣለው በኣለ ሁለት ነጥብ የባዶ ስፍራ ምልክት ስለኣለው ኮለንን በባዶ ስፍራ ምትክ መጠቀም ትክክል ኣይደለም። ፪. ሁለት፣ ሁለት ነጥቦች (“፡፡”) (Ethiopic Spaces) የኣራት ነጥብ ምልክት (“።”) (Period) ኣይደሉም። ስለዚህ ሁለት፣ ሁለት ነጥቦች በኣራት ነጥብ ምትክ መጠቀም ትክክል ኣይደለም። ፫. ሁለት ኮለኖችም (Colons) (“::”) የኣራት ነጥብ ምልክት (“።”) ኣይደሉም። ስለዚህ ሁለት ኮለኖችም በኣራት ነጥብ ምትክ መጠቀም ትክክል ኣይደለም። ሁለት፣ ሁለት ነጥቦች በዓማርኛ የመኪና መጻፊያ (ታይፕራይተር) ዘመን በኣራት ነጥብነት ስንጠቀምባቸው የነበረው ዓላማው ጽሑፉን ወረቀት ላይ ኣስፍሮ ማንበብ ብቻ ስለነበረ ነው። በኮምፕዩተር ግን የቀለሙ ኮድ ወይም ቍጥር ስለሚሰፍር ኣጠቃቀሞቹ የተለያዩ ናቸው። ይህን ኣጠቃቀም ኣለማወቅ ኣራት ነጥብ የሌላቸው 
ጽሑፎችን ያስከትላል። ኣራት ነጥብ የሌሏቸው ጽሑፎችን መተርጐምም ያስቸግራል። ሌሎች የተግዳሮት ምንጮች የዶክተሩን የመርገጫዎች ኣመዳደብ እናሻሽላለን ብለው የላቲኑን የምልክት መርገጫዎች ለግዕዝም ተመሳሳይ ኣጠቃቀሞች የኣቀረቡትንም በመጠኑ ይመለከታል። ስለዚህ ኣንድኣንድ ኢትዮጵያውያን ዓማርኛውን ኣራት ነጥብ በሌለው ከመጻፍ እንዲቆጠቡና ኣራት ነጥብ በሌለውም መጻፊያ እየጻፉ ጊዜያቸውን ከማባከን ቢቆጠቡ ይጠቅማል። ፬. ስለ ኣራት ነጥብ የተሳሳተ ኣጠቃቀም ተጨማሪ መረጃ የሁለት ነጥቦቹ ሁለት እየተከፈሉ ግማሾቹ ወደ ኣዲስ መስመር መዞር ነው።  

፭.  በኮምፕዩተሮችና የእጅ ስልኮች ኣጠቃቀም ምልክቶች በቀለማት እንጂ በባዶ ስፍራዎች መቀደም የለባቸውም። ፮. ዶክተሩ በእንግሊዝኛው የንግድ ምልክት (“TM”) ምትክ የግዕዝ የንግድ ምልክት (“ንም”) ምልክት ፈጥረው ሲጠቀሙበት ቆይተዋል።  ፯. ጮሌ ስልኮችን ወደጎን ኣዙሮ መጠቀም ያፈጥናል።  በተለይ ይኸን ኣጠቃቀም እንደእንግሊዝኛው ለማቀላጠፍ ለሳድሳን መዝጊያ ዶክተሩ የ”ዠ“ን መርገጫ ለግራ ኣውራ ጣት እንዲጠቅምም ኣድርገዋል። ፰. የግዕዝ የነቁጥ ምልክት ተረስቶ ዩኒኮድ ውስጥ ስለኣልገባ መጨመር ይኖርብናል። ምክንያቱም ምልክቱ ከሌሎች የቁምፊው ቀለሞች ጋር እንዲሄድ መሠራት ስለኣለበት ነው። 

፱.  ኣሥሩ የያሬድ ምልክቶች ብዙ ሰዎች ከኣሏቸው የዶክተሩ ግዕዝኤዲት ዩኒኮድ ፊደል ውስጥ ኣሉ። እያንዳንዱም የሚከተበው በሁለት መርገጫዎች ነው። ፲. በተሳሳቱ ኣራት ነጥቦች የተጻፉ ኣስተማማኝ የኣልሆነ ጽሑፎች ኣሉ።  ከእዚህ ጽሑፍ ኣንድ ሁለት ኣንቀጾችን ኮፒ ተደርገው ገጽ ላይ ቢለጠፉ ችግሮቹን መመልከት ይቻላል።

ግዕዝ በዶክተር ኣበራ ሞላ ኮምፕዩተራይዝድ ሆኖ ለዓማርኛ ተመድበው ከተረፉት ሦስት መርገጫዎች ኣንዱ ለኦሮሞ (Oromo) ሲሆን ሌላው ለትግርኛ ተሰጥቶ የቀረው ለኣገው/ቢለን ሥራ ላይ ውለዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በ፲፱፻፹፫ ዓ.ም. የመንግሥት ለውጥ ጊዜ የኣንድ ድርጅት ኦሮሞ ምሁራን ተሰብስበው ከግዕዙ ይልቅ ላቲን ይበጀናል በማለት ግዕዙን (Ethiopic Oromo syllabary) ስለተዉት የሚከተሉትን መጋራት ሳይጠቅም ኣይቀርም።  (ለኦሮሞው “ዸ” ፊደል የላቲኑ የመቀነስ ምልክት መርገጫ በዶክተሩ መመደቡን እዚህ ከቀኝ ጎን ከኣሉት ሥዕሎች “ModEth 1989 ሞዴት የፊደል ገበታ ፬፣ ፲፱፻፹፪ ዓ.ም.” የሚለውን ማስተዋል ይጠቅማል።  ) ቁቤ ኦሮምኛን በላቲን ፊደል የመክተቢያ ዘዴ ነው።

፩. ጥንትም ቢሆን ፊደላት በእጅ ጽሑፍ ሲጻፉ ላቲን ከግዕዙ በፍጥነት የተከተበበት ጊዜ ኣልነበረም። ምክንያቱም ግዕዝ ኣንድን ድምጽ በኣንድ ቀለም ሲያሰፍር ለኣብዛኛው የላቲን ድምጾች ሁለት ቀለሞች ስለሚያስፈልጉት ነው።  

፪. የላቲንና ግዕዝ ቀለሞች (ኦሮምኛውን ግዕዝ ጨምሮ) በማተሚያ መሣሪያዎች ሲከተቡ የሁለቱም ቀለሞች መረጣዎች ኣጠቃቀሞች እኩል ነበር። በእዚህ ዘዴ በግዕዝ ቋንቋ በ1513፣  /0/] ኦሮምኛ ዓማርኛ መተርጐሚያ (Lexicon) በ1850 ግድም በኣቶ ሓብተ ሥላሴ ታትሟል።  መጽሓፍ ቅዱስን ወደ ኦሮምኛ የመተርጐሙንም ሥራ በማስፋፋት ከሌሎች የቋንቋው ተናጋሪዎች ጋር (ዋሬ፣ ሩፎ፣ ሾለን፣ ጀገን እና ገብረሚካኤል) በመተባበር ሙሉውን ኣዲስ ኪዳን ወደ ኦሮምኛ ተርጕመው በሰኔ 1862 ዓ.ም. ኣገባደዱ። ይህም ትርጕማቸው ለኦሮምኛ ሥነጽሑፍ የመጀመሪያው ኣዲስ ኪዳን መሆኑ ነው። ከጥቂት ዓመታት በኋላም ሚስዮኑ ክራጵፍ (J.L. Krapf) በ፲፰፻፸፩ ዓ.ም. በራሱ ስም ያሳተመው ይህንኑ የነኣለቃ ዘነብን ፲፰፻፷፪ ዓ.ም. ሥራ “ቁልቁሎታ መጻፎታ ከኩ ሐረዋ” ነበር።  ኣለቃ ዘነብ ወደ ፲፰፻፸ ዓ.ም. ግድም የ“ኦሮምኛና ኣገውኛ መዝገበ ቃላት” ጽፈዋል ይባላል። የኣስቴር ጋኖን የትርጕም መጽሓፍ በመጠቀም በ፲፰፻፹፯ ዓ.ም. የታተመም የኦሮምኛ ሓዲስ ኪዳን፣  መጫፈ ቁልቁሉ በ፲፰፻፺፱ እ.ኤ.ኣ. (፲፰፻፺፪ ዓ.ም.) በቅዱስ ኦነሲሞስ ነሲብ፣     እና ከእዚያም ወዲህ እንደነ በሪሳ የኣሉ ጋዜጣዎች በግዕዝ ፊደል በኦሮምኛ ታትመዋል። መጫፈ ቁልቁሉ ለመጀመሪያ ጊዜ በግዕዝ ፊደል በኦሮምኛ ቋንቋ የተጻፈ የምዕራብያኑ King James Version) መጽሓፍ ቅዱስ ትርጕም ነው። ቀደም ብሎም በግዕዝ ፊደል በኦሮምኛ ከቀረቡት መረጃዎች ኣንዱ ጀምስ ብሩስ የወሰደው የ1790 የኦሮምኛ ትርጕምና የኢዘንበርግ ጽሑፍም ኣሉ።  

፫. በዶክተሩ ኮምፕዩተራይዝድ የሆነው ግዕዝ እ.ኤ.ኣ. በ1987 ለገበያ ቀርቦ በማተሚያ ቤቶች ፊደላት (ሞዴት ፕሮግራም) መክተብ ስለተጀመረ ምሁራን ደስ ሊላቸውና ሳይንሱንና ቴክኖሎጅውን ማወቅና ማስተዋወቅ በተገባ ነበር። ይህ በኣለመደረጉ እ.ኤ.ኣ. በ1992  በፕሮፌሰር ጥላሁን ጋሜታ ወደ ላቲን ለማዞር ከቀረቡት የኣማርኛ የጽሕፈት መኪናን የሚመለከቱት ጊዜ ለኣለፈባቸውና ኮምፕዩተርን የማይመለከቱ ምክንያቶች መልሶችም ነበሩ።    ስለዚህ በግዕዝ ፊደል በማተሚያ ፊደላት ሲጻፉ የነበሩት በኮምፕዩተር ስለቀረቡ ቴክኖሎጂው ስለተሻሻለና ስለቀለለ ጉዳዩ ይመለከተናል የኣሉት የኦሮሞ ምሁራን ሊደሰቱ የሚገባ እንጂ ወደ ላቲን የሚያስዞር ኣዲስ ምክንያት ኣልነበረም። በጊዜውም በፕሮፌሰር ባዬ ይማም በዓማርኛ መልስ ቀርቦ ፕሮፌሰር ሚንጋ ነጋሽና ፕሮፌሰር ሳሙኤል ክንዴ ወደ እንግሊዝኛ ተርጕመውታል።  ለምሳሌ ያህል ወደ ላቲን የተዞረው ብዙ የግዕዝ ፊደላትን ከማስተማር የኣነሱትን ላቲን ማስተማር ይቀልላል የሚሉ ኣሉ። የላቲኑ ፊደል በቍጥር ማነስ ዕድሜ ልክ እስፔሊንግ ማጥናትንና ኣለመጨረስን ኣስከትሏል። የግዕዝ ፊደላት ቤቶች፣ ቅርጾችና ድምጾች በወጉ የተሠሩ ውብና ግሩም ፈጠራዎች ናቸው። ለምሳሌ ያህል የካዕብ ቤት ፊደላትን ድምጾች ለማሰማት ከንፈሮችን ማሞጥሞጥ ሲያስፈልግ በቅርጽ ከግዕዙ የሚለዩት ከቀኝ ጎን መሥመር በማስጨመር ነው። የስምንተኛው ቤት ድምጾች የሚጻፉት ከግዕዙ ወይም ራብዕ ግርጌ ወይም ኣናት ላይ መስመር በመጨመር ዓይነት ነው።  

፬. ላቲን የእራሱ ችግሮች የኣሉት ፊደል ነው።     በዶክተሩ ግኝት እየኣንድኣንዱን የግዕዝ ቀለም በሁለት መርገጫዎች መክተብ ተችሏል። ላቲን ይኸን እየኣንዳንዱን የግዕዝ ቀለም በሁለት መርገጫዎች የመክተብ ችሎታ ስለሌለው ግዕዝን በግዕዝ ፊደል መክተብ ብልጫ ኣገኘ። ስለዚህ ኦሮምኛን በላቲን ፊደል መክተብ (ቁቤ) መሻሻል ኣይደለም። 

፭. የኦሮምኛው የግዕዝ ፊደል ከሌሎቹ የግዕዝ ቀለሞች ጋር በዶክተሩ ኮምፕዩተራይዝድ ስለሆነ  ለኣለፉት ፴፪ ዓመታት በኮምፕዩተር ቀርቦ በኋላም በዩኒኮድ ዕውቅና ቢያገኝም  ሁሉም ባይሆኑ ኦሮሞዎች ግዕዙን እርግፍ ኣድርገው ጥለው ወደ ላቲኑ ስለዞሩ የተፈጠሩት ችግሮች ቀጥለዋል። ለምሳሌ ያህል ላቲን እራሱን የሚገልጸው የኮምፕዩተሩ ገበታ ላይ በኣሉት ቀለሞች ብቻ ኣይደለም። 

፮. በእጅ የጽሕፈት መሣሪያ ዘመን ታይፕራይተር ዓማርኛንና ኦሮምኛን ለማስጻፍ ስለኣልቻለ ላቲን ብልጫ ነበረው። የዶክተሩ ግኝት ለእውሸቱ (የፈጠራ) የታይፕራይተር የኣማርኛ ነገሮችና ለትክክለኛዎቹ የማተሚያ ቤቶች ፊደላት ኣጠቃቀሞች እጅግ ትልቅ ፈውስ (Breakthrough) ነበር። የታይፕራይተር ፊደል ለታይፕራይተር ሲባል የተሠራ በፍፁም ትክክለኛ በኣለመሆኑና ለብዙ ምዕት ዓመታትም በእጅ ስንጽፈው የነበረው ከኣለመሆኑም ሌላ የማተሚያ ቤት ፊደላችንም ስለኣልሆነ ከቁርጥራጮች የሚሠራውን ብጥስጥስ ዶ/ር ኣበራ የእውሸት ፊደል ይሉታል። ስለ ታይፕራይተሩ ድክመት ዶክተሩ እ.ኤ.ኣ. በ1991   ስለኣቀረቡ መሣሪያው ወደ ቁቤ ለመዞር ምክንያት መሆን ኣልነበረበትም። በታይፕራይተር በመቀጣጠል “ዸ”ን እና እርባታዎቹን መጻፍም ከአማርኛው የተለየ ችግር ኣልነበረውም። ቀደም ብሎም የኢትዮጵያ ማተሚያ ቤቶች ሲጠቀሙቸው የነበሩት የኦሮሞ የግዕዝ ቀለሞች እየኣሉና ከእዚያም ወዲህ በኮምፕዩተር የኦሮምኛው የግዕዝ ፊደል በዶክተሩ መከተብ መቻልና የተጠቃሚዎች መኖር ግንዛቤ ውስጥ ሳይገቡ በንቀት ብዙ ዓመታት ባክነዋል። ቴክኖሎጂ የችግር መፍቻ እንጂ ከችግር መሸሽያ ኣይደለም። ለቴክኖሎጂ ተብሎ ፊደል መቀየርና መቀነስም ነውር ነው። ለምሳሌ ያህል እንደ እንግሊዝኛው ላቲን ዓይነቶቹ የተጻፉት ቃላት የማይነበቡበት (ለምሳሌ ይህል Write) ሳይቀነሱ ኣሉ።

፯. ቁቤ በላቲን ዋየሎች ከሚጠቀምባቸው በተሻለ ኦሮምኛ በግዕዙ ሊጠቀም ይችላል። ኦሮምኛን በፊደል ለመክተብ ከላቲኑ ቁቤ የግዕዝ ፊደል ይጠቅማል።    

፰. መጽሓፍ ቅዱስ በከፊል እ.ኤ.ኣ. በ1841 በኦሮሞ ቋንቋ በግዕዝ ፊደል ተጽፏል።   እንዲሁም እ.ኤ.ኣ. በ1875 የኦሮሞ ሓዲስ ኪዳን በግዕዝ ፊደል ታትሟል።   

፱. በልሳነ ግእዝና በኣፋን ኦሮሞ (ግእዚፊ ኣፋን ኦሮሞቲን - Giiiziifi Afaan Oromootiin) የተዘጋጀው መጽሓፈ ቅዳሴ - ክታበ ቅዳሴ - Kitaaba Qiddaasee መጋቢት 10 ቀን 2008 ዓ.ም. በኢሊሌ ሆቴል ተመርቋል። የትርጐማና የኣርትኦት ሥራው 10 ዓመታት የወሰደው ባለ ሦስት ዓምዱ ክታበ ቅዳሴ፦ የመጀመርያው ረድፍ በግእዝ ቋንቋ፣ ሁለተኛው ረድፍ በኦሮምኛ ሆኖ በግእዝ ፊደል፣ ሦስተኛው ረድፍ በኦሮምኛ ሆኖ በቁቤ ፊደል ተጽፏል ይላል ሪፖርተር ጋዜጣ።  ይህ የግዕዝ ፊደል ኦሮምኛን ኣይጽፍም ለሚሉት ማፈሪያ ነው። ስለዚህ ጥቂት የኦሮሞ ምሁራን ግዕዝ ኦሮምኛን ኣይጽፍም በማለት ከጀመሩት የእውሸት ዘመቻዎቻቸውና ሕዝቡን ከማጣላትና ከመለያየት መቆጠብ ይኖርባቸዋል። ከእነዚህ ተርጓሚዎች ሌላ ለግዕዝ እድገት የሠሩ የኦሮሞ ሊቃውንት ኣሉን።   

፲. መጽሓፍ ቅዱስ ሙሉዉን ወይም በከፊል ከ፲፭፻፮ ዓ.ም. ጀምሮ በግዕዝ ቀለሞች በማተሚያ ቤቶች ከታተሙባቸው ቋንቋዎች መካከል የግዕዝ ቋንቋ (ግዕዝኛ)፣ ዓማርኛ፣ ትግርኛ፣ ኦሮምኛ፣      ሃዲያ፣  ሲዳሞ፣  ከንባታ፣  ወላይታ  እና ጌዴኦ  ይገኙበታል። መጽሓፍ ቅዱስ በሌሎች የኢትዮጵያ ቋንቋዎችም ተተርጕሟል። ለምሳሌ ጋሞ ጎፋና ዳውሮ።  ስለዚህ ለዓመታት በማተሚያ ቤቶች የግዕዝ ፊደላት ሲከተብ የነበረው ኦሮምኛ ኮምፕዩተራይዝድ ሆኖ ዛሬ ሥራ ላይ እየዋለ ግዕዝ ኦሮምኛን ኣይጽፍም ማለት ሳይንስ ኣይደለም።  

፲፩. በኣነሱ የኆኄያት ግድፈቶች (Spellings / እስፔሊንጎች) እና ስፍራዎች (Spaces) ማስከተብ ብልጫዎች የነበረው የግዕዝ ፊደል በዶ/ር ኣበራ ግኝቶች የተነሳ የግዕዝ ፊደል ሓሳብን በኣነሱ ጊዜያት (Times)፣ መርገጫዎች (Keystrokes) እና ገበታዎች (Keyboards) በኮምፕዩተሮችና የእጅ ስልኮች በማስከተብ ብልጫዎቹ ወደ ኣምስት ዓይነቶች ከፍ ብለዋል። ለምሳሌ ያህል “ዘ ኲክ ብራውን ፎክስ ጃምፕስ ኦቨር ዘ ሌይዚ ዶግ።” የሚለውን ዓረፍተ ነገር ላቲን በ36 ቀለሞችና በቁቤ በ45 ቀለሞች ከመክተብ ይልቅ በግዕዝ ፊደል በ24 ቀለሞች መክተብ የተሻለ ነው። ስለዚህ ግዕዝ እንኳን ከላቲኑ ቁቤ ከላቲኑ እንግሊዝኛ የተሻለ ነው።  

፲፪. የቁቤ ሥርዓት እ.ኤ.ኣ. በ1992 ገደማ የተመሠረተው ኣንዱ ቀለም ኣንድን ድምጽ በመወከል ነው ተብሏል። የላቲንም ሆነ የቁቤ ቀለሞች ኣንድን ድምጽ በኣንድ ቀለም ከሚወክለው የግዕዝ ፊደል ጋር የመወዳደር ችሎታ የላቸውም። ላቲን ኣንድኣንድ ድምጾችን የሚከትበው በሁለት ቀለሞች ስለሆነ ሁሉም ቀለሞች ለየብቻቸው ኣንድ ድምጽ እንዲወክሉ እንኳን ተደርጎ መጠቀም ኣይቻልም። ለምሳሌ ያህል “d” እና “h” የ“ዽ” እስፔሊንግ ስለሆኑ “ዲ” እና “ኤች”ን በሁለት ቀለምነት ጎን ለጎን ኣስቀምጦ በ“d” እና “h” ድምጽ ሰጪነት መጠቀም ኣይቻልም። ይህ ምሳሌ የሚያሳየው ቁቤ የተመሠረተው በጥቂት የኦሮሞ ምሁራን ማምታታትም ላይ መመርኰዙን ነው። ሌላ ምሳሌ ግዕዝ ዋየልና ማጥበቂያ (Long Vowels / Germination) የለውም የሚባለው ነው።
 ለግዕዝ ዋየል ስለማያስፈልገውና ስለሌለው ዋየል ባያስፈልገውም መዘርዘር ይቻላል። ኣንድ ቀለም የሚበቃውን የግዕዝ ማጥበቂያ ትቶ ለኣልተሟላ ማጥበቅ ሲባል ወደ ላቲን ዋየሎች መዞር ኣያታርፍም። ለላቲን የሚያስፈልጉትን ረዣዥም ዋየሎች ግዕዝ ስለሌለው ኦሮምኛን በላቲን ለመክተብ መረጥን ለሚሉት ሰበቡ ሳይንሳዊ ስለኣልሆነና ግዕዝ ሥርዓተ ንባብ (ማንሳት፣ መጣል፣ ማጥበቅ፣ ማላላት፣ ማናበብ፣ አለማናበብ፣ መዋጥና መቍጠር) ስለኣለው  ሊታሰብበት ይገባል ይላሉ ዶክተር ኣበራ። የግዕዝ ፊደል በብዛቱ እየተወቀሰ ከእዚያ በበዙ ቀለምች መተካት ትክክል አይደለም። ቁቤ ሁሉንም የላቲን ዋየሎችንና እንዚራን (Accents) ኣልተጠቀመም። ጥናት ላይ ተመርኵዞም ኦሮምኛ ሁሉንም የዓማርኛ ቀለሞች የኣለመጠቀምም መብት ኣለው። የተለያዩ ምክንያቶች በማቅረብ የግዕዝ ፊደል ኦሮምኛን ኣይጽፍም የኣሉትን እንደተሳሳቱ ሳይጠቅሱ ኣሁንም መጥቀስ ስለጉዳዩ ኣሁንም የሚጽፉት ጥቂት ምሁራን እራሳቸውን ማረም እንዳልቻሉ ያሳያል።   የ“መ” እና “ማ”ን እስፔሊንግ “ma” እና “maa” ማድረግ መካሰር ነው። ወደ ላቲን የተዞረው ያለበቂ ጥናትና ሕዝቡ ሳያውቅና ሳይመርጥ በእውሸት ሕዝብ መረጠው ተብሎ ነው። 

፲፫. ማንኛውንም የኦሮሞ ፊደል በሦስት መርገጫዎች መክተብ ነውር ነው። ማንኛውንም የኦሮምኛ ድምጽ በሦስት መርገጫዎች መክተብ ነውር ነው። ምክንያቱም ግዕዝ በኮምፕዩተር ኣይጻፍም ተብሎ የኣማርኛ ታይፕራይተር ማጓጓዝ እንደችግር በቀረበበት ጊዜ እየኣንድኣንዱ የኦሮምኛ የግዕዝ ቀለም በኮምፕዩተር በሁለት መርገጫዎች በዶክተሩ እየተከተበ ነበር። ምንም እንኳን ግዕዝ እንከን የማይወጣለት ፊደል ነው ማለት ባይቻልም ለኣንድ ድምጽ ኣንድ ቀለም ለመመደብና ኣንድን ቀለም ለኣንድ ድምጽ ለመመደብ የተፈጠረ ነው ማለት ይቻላል። ግዕዝ በኮምፕዩተር እየተጻፈ በፊደላዊ ፊደል በላቲን ኦሮምኛውን በበዙ መርገጫዎች መክተብ ኣሁንም ሳይንሳዊና የተሻለ ነው ማለት ለቴክኖሎጂ ሲባል እራስን ዝቅ ማድረግና ኣርቆ ኣለማስተዋል ነው።  

፲፬. ጥቂት የኦሮሞ ምሁራን ዓማርኛ የማጥበቂያ ምልክት የለውም የሚሏቸውን ስሕተቶች ቀጥለውበታል። ዓማርኛ መጥበቅ የኣለበትን ቃል ከማይጠብቀው የሚለይበት ዘዴዎች ኣሉት። ከእነዚህ ኣንዱ ከሚጠብቀው ቀለም ኣናት በላይ ኣንድ ነጥብ መክተብ ሲሆን ምሳሌውም በ፲፮፻፺ ዓ.ም. ላቲንና ዓማርኛ መተርጐሚያ መጽሓፍ ውስጥ ታትሟል።  ለምሳሌ ያህል “ላላ‘” እና  “አላላ‘” ገጽ 1 እና “መነ‘ሣት” ገጽ 50 ላይ ቀርበዋል።   ይኸንንም ኣጠቃቀም ሓዲስ ዓለማየሁ  [በ“ፍቅር እስከ መቃብር” መጽሓፋቸው ኣስፋፍተውታል።  

፲፭. የቁቤ ዋየሎች “ኤ”፣ “ኢ”፣ “ኣይ”፣ “ኦ” እና “ዩ” (“a”፣ “e”፣ “i”፣ “o” እና “u”) ስለሆኑ በቁቤ “ክታበ”ን ከ“ኪታባ” የመለየትና ማጥበቅ/ማላላት ችግሮች ቢኖሩትም ስለ ቁቤ ማጥበቅ፣ ማላላት፣ ማስረዘምና ማሳጠር የሚጽፉም ኣሉ። ይህ በኣዲስ ፊደልነት የቀረበውንም በብዛት ከግዕዝ ፊደል የበለጠውንም  ይመለከታል። ግዕዝ ሰባት እንዚራን ሲኖረው ኦሮምኛ 10 ያስፈልጉታል የተባለው ትክክል ከኣለመሆኑም ሌላ ቍጥሩን ወደ 13 መጨመርም ስለኣላዋጣም ኣልቀጠለም።  ትክክለኛው የግዕዝ ኣጻጻፍ “ኣፋን” እንጂ “አፋን” ኣይደለም። 

፲፮. ይህ ግዕዝና ኦሮምኛ ሳይንሳዊ ጽሑፍ ስለ ፊደላቱ እንጂ ቋንቋዎቹን ኣይመለከትም። የኦሮሞ ቋንቋችን መዳከም ስለሌለበት ስለ ፊደል ስንወያይ ሰለ ቋንቋና ሰለኣልፈጠርናቸው ኦሮሞነት መቀላቀል ሳይንስ ኣይደለም። የኦሮምኛው የግዕዝ ፊደል ከሌሎቹ የግዕዝ ቀለሞች ጋር በዶክተሩ ኮምፕዩተራይዝድ ስለሆነ ለኣለፉት ፴፪ ዓመታት በኮምፕዩተር ቀርቦ  በኋላም በዩኒኮድ፣ ዩናይትድ እስቴትስና የኢትዮጵያ መንግሥታት ዕውቅና ቢያገኝም ዛሬም ሶፍትዌር ውስጥ የሉም ብለው የሚጽፉ ኣሉ። ምሳሌ፦ “በዻኔ”  

፲፯. እነ “ሸ”፣ “ቸ”፣ “ኘ”፣ “ዸ”፣ “ጠ”፣ “ጨ”፣ “ጰ”፣ እንዚራኖቹንና ሌሎች ቀለሞች የኣሉትን ለኦሮምኛ የሚያስፈልጉትን ቀለሞች ትቶ እነዚህን ወደ የሌሉት የላቲን ፊደል መዞር ሳይንስ ኣይደለም።  የእነ“ጨ”፣ “ⶸ” እና “ꬠ” እንዚራን በቁቤ መለየት ቀላል ኣይሆንም።  

፲፰. የኦሮምኛ ድምጾችንና እርባታዎችን የሚወክል የፊደል ገበታ (ከኣማርኛ ታይፕራይተር፣ ዓረብኛና ላቲን) ለጊዜው የተሻለው ላቲን ነው በማለት በስሕተት የቁቤ ኣጻጻፍ ሥራ ላይ ዋለ። ይህ ለዓማርኛው በኣለመደረጉ ዶክተሩ በመፍትሔው የደረሱለት ለኦሮምኛው ፊደል ጭምርም ነበርና  ነውም። ምክንያቱም ዓማርኛና ኦሮምኛ በትክክለኛው የግዕዝ ፊደል ለብዙ ምዕት ዓመታት ተጠቅመውበታል።  የጄምስ ብሩስና ሌሎች መረጃዎችም ኣሉ።  ስለዚህ ዓማርኛውንም ሆነ ሌሎችን ቋንቋዎቻችንን ለማይጽፈው የዓማርኛ ታይፕራይተር ሲባል ፊደሉን የተዉት ቋንቋዎች በኣንድኣንድ ተናጋሪዎች ስሕተት እንጂ በግዕዝ ፊደል ሲጠቀሙ በነበሩ ኢትዮጵያውያን ስሕተት ኣልነበረም።  

፲፱. በዶክተሩ ግኝቶች ከ“አ” እና “ኸ” መርገጫዎች ፲፬ የግዕዝ ቀለሞች እየተከተቡ ናቸው።    

፳. ቁቤ በ“a”፣ “e”፣ “i”፣ “o” እና “u” በተጠቀመው ዓይነት በ“ኣ”፣ “ኤ”፣ “ኢ”፣ “ኦ” እና “ኡ” የግዕዝ ቀለሞች መጠቀም ይችል ነበር። ኣንድኣንድ ኦሮሞዎች “ቢራ” በላቲን ኦሮምኛ biirraa ተብሎ የሚጻፈው ግዕዝ ስለማይችለውም ነው ይላሉ። በ“biirraa” ምትክ “ብኢኢርርኣኣ” ተብሎ በግዕዝ ፊደል መጻፍ ይቻላል። ስለዚህ ቁቤ የተመሠረተው ሳይንሳዊ ጥቅም ላይ ኣይደለም። “ቢ” እና “ራ” ቀለሞችን ዓማርኛ በኣራት ዓይነቶች ማለትም “ቢራ”፣ “ቢ'ራ”፣ “ቢራ'” እና “ቢ'ራ'” መጠቀም ይችላል። “ብኢርኣ” ወይም “ቢርራ”ም ኣለ። ለምሳሌ ያህል “ለቆ” የሚለውን ቃል “ለቅቆ” ወይም “ለቆ'” ዓይነቶች መክተብና ማላልያና ማጥበቂያዎች መጨመርም ይቻላል። ቁቤ ዋየሎችን ከመደራረብ በ“ዓ”፣ “ዔ”፣ “ዒ”፣ “ዖ” እና “ዑ” የግዕዝ ቀለሞች ኣጠቃቀም ምሳሌዎች ጊዜ፣ ሥፍራና ጉልበት መቆጠብ ይችል ነበር። ከኣምስት የላቲን ዋየሎች የግዕዙ “አ”፣ “ዐ” እና ሰባት እንዚራኖቻቸው የተሻለ ገላጮችና ሥፍራ ቆጣቢዎች ናችው። 

፳፩. ኣንድኣንድ የኦሮሞ ምሁራን ግዕዝ የኦሮምኛ ቃላትን ኣይጽፍም በማለቱ በኣለማወቅ በስሕተቱ ገፍተውበታል። ጎዸቱ፣ ቶኮፋዸ፣ ዹፌ፣ ዹጉማ፣ ጀዺ፣ ዻባ፣ ዻራርቱ፣ ባዻዻ፣ ዻዻ፣ ጄዼ፣ ዼራ፣ ዽባፍ፣ ዽባ፣ ነንዾከዼስ፣ ዿ የእንዚራኑ ምሳሌዎች ናቸው። ዓማርኛው ላይ የተጨመሩት ስምንቱ የኦሮሞ ቀለሞች “ዸ”፣ “ዹ”፣ “ዺ”፣ “ዻ”፣ “ዼ”፣ “ዽ”፣ “ዾ” እና “ዿ” ናቸው። የኦሮሞውም ላይ የተጨመረ የምኢን የግዕዝ “ⶍ” ቀለምም ኣለ። 

፳፪. ጥቂት የኦሮሞ ምሁራን “ዻ” የግዕዝ ኦሮምኛ ቀለም በኣንድ ቀለም በሁለት መርገጫዎች ከመክተብ ይልቅ “dha” በማለት በሦስት ቀለሞችና በሦስት መርገጫዎች በኦሮምኛ መክተብ የተሻለ ሳይንስ ይመስላቸዋል። ኣንድኣንድ የግዕዝ ቀለሞችን በላቲን ለመለየት ሦስትና ከሦስት በላይ ቀለሞችን መደርደር ያስፈልጋል። ግዕዝ ለኣዳዲስ ድምጾች ፊደል ሲፈጥር ቁቤ ለኣለው ፊደል ሌላ ድምጽና እስፔሊንግ በመጨመር መሻሻል ስለሚፈልግ ችግሩን ያባብሳል። ግዕዝን በላቲን እስፔሊንግ ለመጻፍ የሞከሩትም ጥቂቶቹን እስከኣሁን የኣዋጣቸው የሕዝቡ ስለቴክኖሎጂው በሚገ'ባ ኣለመረዳት ነው። 

፳፫. በሚገባ ሳይታሰብበት የግዕዝ ቀለሞች በላጭነትና ጥቅሞች ሳይገለጹ ታልፈዋል። ምሳሌ፦ ግዕዝ ችግር የለውም ማለት ሳይሆን የላቲንን ቃላት እስፔሊንጎች ዕድሜ ልክ ቢማሩትም ማስታወስ ኣይቻልም። በእዚህ ላይ “ኦሮሞ” የሚለው ቃል እስፔሊንግ በላቲን “Oromo” በኦሮምኛ ቁቤ የኣለ በቂ ምክንያት “Oromoo” ነው።   የቁቤ ላቲንና የላቲንን እንግሊዝኛ ተደራራቢ እስፔሊንጎች ማስታወስ ኣስቸጋሪነት የተነሳ ትክክለኛዎቹን ማስተማርና ማስታወስ ሳያስቸግር ኣይቀርም። ግዕዝ ኣዳዲስ ቀለሞችን እየፈጠረ ሲያድግ ቁቤ በኣሉት የላቲን ቀለሞች ላይ እስፔሊንግ መጨመር ስለኣለበት ለሁሉም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች እየጠቀመ ማደጉ ኣጠራጣሪ ነው። ምክንያቱም በሁሉም የግዕዝ ቀለሞቻችን ለመክተብ ከቁቤው የበዙ ልዩ የፊደል መክተቢያ እስፔሊንጎች  መማር ሊያስፈልግ ነው። ስለዚህ ቁቤ የኣናሳ ተጠቃሚዎች በመሆን ኦሮምኛን፣ ኦሮሞውንና ኢትዮጵያን ሊያቈረቍዝ ይችላል። 

፳፬. በኣጠቃቀም የላቲን ፊደል ከግዕዝ ሳድሳን ቀለሞች ጋር ኣንድ ዓይነት ነው። ግዕዝ እንዚራኑን በኣንድኣንድ ቀለሞች ሲወክል ላቲን ዋየሎቹን ሳድሳኑ ጎን ማስከተብ ስለኣለበት ከሰባት ጊዜ በላይ እጥፍ ስፍራዎችን ያስባክናል። ይኸንን የግዕዝ ምሳሌ የ“ገ” 11 እንዚራን በላቲን ጠብቆና ሳይጠብቅ በመክተብ ልዩነቱን መመልከት ይቻላል።

፳፭. ጥቂት የኦሮሞ ምሁራን በስሕተት ኦሮምኛ 10 እንዚራን ሲያስፈልገው ግዕዝ ሰባት ብቻ ኣለው ይላሉ። ላቲን ኣምስት ዋየሎች ኣሉት ተብሎ ኣምስቱኑ ዋየሎች እየደራረቡ ኦሮምኛ ኣሥር ዋየሎች ኣሉት ማለት 
ኦሮምኛውን መሳደብ ነው። ዋየል መደራረብም ትርፉ ስፍራ ማባከን ነው። የላቲን ዋየሎች ኣምስት ናቸው ቢባል እንኳን ለኦሮምኛ ኣምስት ዋየሎች በቂ ኣይደሉም። የቁቤ ዋየሎች ኣምስት ከሆኑ ከኣምስት በላይ እንዚራን ለኣላቸው የግዕዝ ቀለሞች ለመጠቀም ከላቲኑ ቁቤ የበዙ የእስፔሊንግ ችግሮች ይፈጥራሉ።  ለምሳሌ ያህል “ዸ”ን በስምንት ዋየሎቹ ለመክተብ ለቁቤ ላቲን ከ20 በላይ ቀለሞች ሲያስፈልጉት ለግዕዙ ፯ በቂ ናቸው።  

፳፮. ጥቂት የኦሮሞ ምሁራን በስሕተት ላቲን 26 ቀለሞች ሲኖሩት  የግዕዙ ብዙ ናቸው ይላሉ። የላቲን a ዓይነቶች ከ26 በላይ ናቸው። ዋናዎቹ 26 የላቲን ቀለሞች እንደግዕዙ 37 የተሟሉ ኣይደሉም። የግዕዝ ፊደላት በ37 የግዕዝ ቤት ተከፋፍለው እንዚራኖቹ በድምጽና በቅርጽ በወጉ የተደረደሩ ስለሆነ ሕጻናትን ማስተማር እንደ “abcd” ቢሆንም የግዕዝ ተማሪ የሚማረው እስፔሊንግ እንዳያስታውስ እንጂ ዕድሜ ልኩን እስፔሊንጎች እንዲፈልግ ኣይደለም። ለምሳሌ ያህል የካዕብ ቤቶቹ ቀለሞች የሚከተቡት በግዕዞቹ ላይ ከቀኝ ጎን መስመር በመጨመር ሲሆን ድምጾቻቸው እንዲሰሙ ከንፈሮችን ማሞጥሞጥ ያስፈልጋል። ላቲን እራሱን ለማሻሻል ኣዳዲስ ፊደላትን እየቀረጸ ሲሆን ቁቤ ሊጠቀምባቸው ኣልተዘጋጀም። የቻይና ሥዕላዊ   ፊደላት ብዙ ሺህ ናቸው።    

፳፯. ግዕዝ በእጅ ኣይጻፍ ይመስል ስለላቲኑ የእጅ ጽሑፍ (Cursive) የሚያነሱም ኣሉ። ዶክተሩ ኦሮምኛን በግዕዝ ፊደል በኮምፕዩተር ለመክተብ የሚያስፈልጉትን ከሠሩ በኋላ ለ24 ተነባቢና 10 ዋየሎቹ የኦሮምኛ ፊደላቱ 34 ቀለሞችን መፍጠር ስለሚያስቸግርና ኣስፈላጊ ኣይደለም ተብሎ ወደ ላቲን ዞርን ከቀረቡት ምክንያቶች ኣንዱ ነበር።  

፳፰. ግዕዝ እንደኦሮምኛና ሲዳምኛ የኣሉትን (ኩሻዊ) ቋንቋዎችን   ጥሩ ኣድርጎ ኣይጽፍም የሚለው ወይም የግዕዝ ኣንድን ድምጽ በኣንድ ቀለም መወከል እንደችግር ተቆጥሮ ወደ ላቲን ለመዞር የቀረቡት ምክንያቶች ወደ እውነት የተጠጉ ኣልነበሩም። ግዕዝ ለኣንድ ድምጽ ኣንድ ቀለምና ኣንድን ቀለም ለኣንድ ድምጽ በማድረግ የተራቀቀ ፊደል ነው። 

፳፱. በግዕዝና በላቲን የሚጠቀሙ ኢትዮጵያውያን ስለማይግባቡ በየእለቱ እየተራራቁ ናቸው። ኣንድ ሕዝብ  በተለያዩ ፊደላትና ቋንቋዎች እንዲጠቀም ማስገደድ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ነበር። ኦሮሞው ዓማርኛና ፊደሉን እንዳይማር ተወስኖ የፌዴራል ሥራ እንዳያገኝ ሆኗል። 

፴. ኣይርላንዳዊው በርናርድ ሿው ግዕዝን ዓውቆ ቢሆን ኖሮ ላቲን ቦታ ኣይኖረውም ነበር የሚል ጽሑፍ በሰይፉ ኣዳነች ቢሻው እዚህ ቀርቧል።  የላቲን ፊደል ለእየኣንድኣንዱ ድምጽ ኣንድ ቀለም እንዲኖረው ተመኝተው ነበር። ላቲን የኣልተሟላና ኣክሳሪ ፊደል መሆኑንም ሿው ገልጸዋል።  ስለዚህ ባለቤቱ የጠላውን ኦሮሞው ኣዲስ ኣግበስባሽ መሆን የለበትም። 

፴፩. ላቲን ማወቅ ኦሮሞዎችን ከፊደሉ ተጠቃሚዎች ያቀራርባል ተብሎ እንደምክንያት ቀርቧል። ኢትዮጵያውያን የላቲንን ፊደል ስለሚማሩ ኣልተጎዱም። 

፴፪. በግዕዝ እንደኣስፈላጊነቱ መጠቀም እንዲቻል የማላልያ (Stretch) ምልክት ለመጀመሪያ ጊዜ ስለፈጠሩ የዶክተሩ ፓተንትም ውስጥ ተጠቅሷል።  የዩኒኮድ ግዕዝ መደብም ውስጥ ኣለ። ግዕዝ ኣንድን ቀለም ባለማጥብቅ፣ በማጥበቅና በማላላት ያስከትባል ይላሉ ዶክተሩ።  ቁቤ የሚረዝሙ ድምጸ ልሳናትን የሚወክልበት ምልክት የለውም። ኤ (a) ሾርት ዋየል እና ኤኤ (aa) ሎንግ ዋየል ናቸው ተብለው ዋየል፣ ማጥበቂያና ማላሊያም ሊሆኑ ኣይችሉም። ስለዚህ ላቲን ከግዕዙ ጋር ሲወዳደር ለቋንቋው የሚያስፈልጉትን እንዚራን በመቀነስ ኦሮምኛውን ጎዳው እንጂ ኣልጠቀመውም።  የኦሮምኛን “ዽ” ድምጽ “dh” እንጂ ግዕዝ ኣትጽፈውም በማለት ማታለል የኦሮሞው ትግል ምክንያትም ይሁን ውጤት ኣይደለም።

፴፫. ኣንዳኣንድ የኦሮሞ ምሁራን ላቲንም ሆነ ቁቤ ከውጪ የተገኙ ናቸው በማለት ግዕዝ የሳባ ፊደል ነው ማለቱን ኣክርረውበታል። ግዕዝ ኢትዮጵያዊ ፊደል ነው። 
  

፴፬. ዶክተሩ ለግዕዝና እንግሊዝኛ ፊደል የሚጠቅሙ ግኝቶችን በማቅረቡ ገፍተውበታል።  የቁቤ ተከታዮች የኦሮሞ ምሁራን ላቲን እራሱን የኣሻሻለበትን ዘዴዎች እንኳን ሳይጠቀሙ ከግዕዙ ኣጠቃቀም እራሳቸውን ስለኣገለሉ ኢትዮጵያንና ዓለምን በመስኩ እንዳይጠቅሙ እየተደረገ ነው። 

፴፭. በዓማርኛ “መሣሣትና “መሳሳት፣ “ዓለማቀፍና “ኣለማቀፍ እንዲሁም “ኣባይና “ዓባይ ኣንድ ኣይደሉም። 

፴፮. የግዕዝ ፊደል የኦሮምኛው ፊደል ውስጥ ያለውን “ዸ” እና ሰባት እንዚራን ቀለሞቹን ያጠቃልላል።  ስለዚህ እንደ “በዻዻ” የኣሉትን ቃላት በ“በዳዳ” ወይም “ዻራርቱን በ“ደራርቱ” መክተብ ግድፈት ነው። የ“ዸ” እንዚራን የግዕዝ ፊደላት ውስጥ መኖርን በመካድ ኣንድኣንድ የኦሮሞ ምሁራን ኦሮሞውን ሲያጃጅሉት ፴ ዓመታት ኣልፈዋል። ለምሳሌ ያህል “በዻዻ” የሚለውን ሦስት ድምጾች የኣሉትን ቃል በሦስት ቀለሞች በስድስት መርገጫዎች በግዕዝ ከመክተብ ይልቅ በላቲን በስምንት ቀለሞች በዘጠኝ መርገጫዎች መክተብ ዓይነት የተሻለ መሆኑን ሕዝቡ መርጧል የሚሉ ኣሉ።  

፴፯. ኦሮምኛን በግዕዝ ፊደል ማስተማር እንዲጀመር ሓሳብ ቀርቧል።        ይህ ሌሎች ኦሮምኛውን እንዲማሩም ያበረታታል።  

፴፰. ጥቂት የኦሮሞ ምሁራን በምክንያቶች ስለተሸነፉ ስሕተቶቹን ተቀብለው እንደመታረም ኣዳዲስ ምክንያቶችን እያቀረቡ በማወናበዱ ቀጥለውብታል። ለምሳሌ ያህል የኣማርኛ ታይፕራይተርም ይሁን የግዕዝ ማተሚያ ቤቶች የኣረቡን ኣኃዞች ሲጠቀሙባቸው ስለነበረ እንደኣዲስ ነገር ግዕዝ የኣልቦ ኣኃዝ ስለሌለው ፊደሉ ለሂሳብ ኣይጠቅምም ብለው ወደ ላቲን ለመዞር እንደምክንያት ማቅረብ የሚሞክሩ ኣሉ። ቁቤ ወደ ላቲን የዞረው በኣኃዞቹ ምክንያት ስለኣልነበረና ዶክተሩ ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ሲያደርጉ የግዕዝ ዜሮ ቀለምን ፈጥረው ስለነበረ ቁቤ ተቀባይነት እንዲያገኝ ሊመሠረት የሚፈለ'ገው በኣዲስ ቅጥፈት ላይ መሆን የለበትም።    

፴፱. በቅርቡ በኣንድ ፀሓፊ “ተማሪ” የሚለውን ቃል በግዕዝ ቀለሞች ለማስቀመጥ ኣሥራ ሁለት ባይትስ (Bytes) ሲያስፈልገው በቁቤ “tamaarii” ስምንት ባይትስ ይበቃዋል በማለት የላቲንን ብልጫ ለማሳየት ተሞክሯል። ሁለቱም የሚወስዱት ስምንት ባይትስ ነው። (ይህ ቀለሞቹ ፊታችን በኮምፕዩተር እስክሪን ወይም ወረቀት ላይ ሲታዩ ማለት ኣይደለም።)  

፵. ግዕዙ ላይ ከተጨመሩት የተለዩ የእራሳቸው ፊደላት ከኣሏቸው 13 የፊደል ዓይነቶች ሌላ ወደፊት ለኣፍሪቃና ሌሎች ቋንቋዎች ኣዳዲስ ፊደላት ሲጨመሩ በየስሞቻቸው ይቀርባሉ። በፊደሉ መጠቀምንና ኣለመጠቀምን ዶክተሩ ኣያስገድዱም። 

፵፩. “የኦሮሞ ሊቃውንት ባደረጉት ጥናት መሠረት ለኦሮምኛ የሚስማማውን ፊደል (ላቲንን) መርጠውለታል፤ ይህ ያለቀ፥ የደቀቀ ጉዳይ ነው፤ ኦሮሞ ያልሆኑትን የሚገዳቸው ጉዳይ አይደለም። ጉዳዩ የሚገድደው ኦሮሞዎችን ብቻ ከሆነና ኦሮሞዎች ከተስማሙበት በጥላቻ ላይ የተመሠረተ ምርጫ ሊያደርጉ ይችላሉ። ኦሮምኛ ብሔራዊ ቋንቋ እንዲሆን ከታሰበ ግን፥ ጉዳዩ ብሔራዊ እንጂ ኦሮሞዎች ብቻቸውን የሚወስኑበት የኦሮሞዎች ጉልማ ሊሆን አይችልም። ጥያቄውም ከሌሎቹ ቋንቋዎች ይልቅ በኦሮምኛ ላይ የሚነሣው በዚህ ምክንያት ነው።” ይላሉ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ።  ግዕዝ ለኦሮምኛ እንደሚበጅ የሚቀርቡ ጽሑፎች ቀጥለዋል።             የፖለቲካን ችግር ሳይንስ ማድረግ መሞከር ተገቢ ኣይደለም። 

፵፪. ኣንድኣዳንድ ሰዎች “ዱ” ፊደል ሆኖ ቀለበቱ መካከል መስመር የኣለውን ቀለም የኦሮምኛው የግዕዝ ፊደል ነው ይላሉ። ይህ ስሕተት ነው። እነዚያ የጋሞ ጎፋ፣ ዳውሮና ባስኬቶ ፊደላት ናቸው። 

፵፫. በግዕዝ ፊደል ድምጽን ከፍና ዝቅ ማድረግ (Tone) ለመለየት የሚያስችሉ ምልክቶችን መፍጠር ይቻላል። ይህ ለኦሮምኛው ኣስፈላጊ ኣይደለም። ዶ/ር ኣማረ ተግባሩ ኃይሌ ፊዳ በሚለው በ፳፻፲ ዓ.ም. በታተመው መጽሓፋቸው ገጽ 101 ላይ የግዕዙ ፊደል ድክመቶቹን ለማስወገድ የሚያስችል ቅጥያዎች ከተደረጉለት ኣፋን ኦሮሞውን በግዕዝ ፊደል መጻፍ እንደሚቻል መናገራቸውን መመስከር እችላለሁ ይላሉ።

ይህ ጽሑፍ ዓማርኛን የተመለከተ ስለ ፊደሉ  (እንደ ኦሮምኛው) የዶክተሩ ኣስተዋጽዖ እንጂ ስለ ቋንቋው ኣይደለም። ስለ ቋንቋው በየሺሓሳብ ኣበራ እዚህ      ጥሩ ቀርቧል። 

የግዕዝን ፊደል በኮምፕዩተር መጠቀም ኣዲስ ቴክኖሎጂ ስለሆነ የተጠቃሚው መሠረታዊ ሕጎችንና ወጎችን ማወቅ ኣስፍላጊ ናቸው። ቴክኖሎጂ ጠቃሚ ነው።  እነዚህ ታውቀው በኢትዮጵያውያን ትጋት ብዙ ሚሊዮን ጽሑፎች በኣለፉት ፴፪ ዓመታት ቀርበዋል። የፊደሉ እድገት ለወዳጆቹ ትልቅ እርካታ ነው። ለምሳሌ ያህል ዶ/ር ዓለሙ ቢፍቱ በሞዴት፣ ዶ/ር ለይኩን ብርሃኑ በኢትዮወርድ መጽሓፎች ጽፈው ኣሳትመዋል።  በቅርቡም ዶ/ር ኣክሊሉ ሃብቴ ግዕዝኤዲትንና ግዕዝኤዲት ዩኒኮድ ፊደሉን ተጠቅመዋል።  የመጀመሪያው የግዕዝ ትሩታይፕ ፊደላችን እንደኣስፈላጊነቱ እየታረመ የዩኒኮድ ፊደል የሆነው ትክክከኛ ቅርጾች እዚህ ጎን ከኣለው የኣቶ ኣብርሃም ያየህ የ፲፱፻፺፪ ዓ.ም. መጽሓፍ ማሳሰቢያ ገጽ ሥዕል መመልከት ይቻላል። በዶክተሩ ፈጠራ ምክንያት መጽሓፎቻቸውን ጽፈው ለማሳተም የቻሉ ብዙ ኢትዮጵያውያን ኣሉ። ከእነዚህም መካከል እ.ኤ.ኣ. በ1994 የዶክተሩን ፕሮግራም በመጠቀም ከ25 ዓመታት በኋላ ምስጋና የለገሷቸው ኣንዱ ዶ/ር ኣማረ ተግባሩ ናቸው።  [ የዶ/ር ኣበራ ሞላ እና ጋሼ አበራ ሞላ (ስለሺ ደምሴ) ግንኙነትም እዚህ ኣለ።  

ይህ በእንዲህ እንዳለ  በኣለማወቅ በተለይ ዓማርኛ ላይ ብዙ ችግሮች የኣደረሱ ኣሉ። ከግዕዝ ፊደል ተጠቃሚዎች ዓማርኛ ዋነኛውና ወሳኝ ነው። 

፩. የኮምፕዩተር፣ እጅ ስልክና የመሳሰሉት የቴክኖሎጂ ግኝቶች በብዙ ቢሊዮን ዶላር ወጪ፣ በብዙ ሰዎች ድካም፣ ፓተንቶችና ምርምሮች የተገኙ ስለሆኑ ሶፍትዌር እንደማንኛውም ነገር የሚገዙ እንጂ ኣንዳንዶቹ እንደሚያደርጉት ሰርቆ መጠቀም ነውር ነው። ብዙ ኢትዮጵያውን እነዚህን ሁሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ሳንከፍልባቸው በማግኘታችን  እንደማመስገንና ለግዕዝ የሚያስፈልጉትን ገዝቶ  ከመጠቀም ይልቅ ፊደሉ የእራሱ ገበታ እንዳይኖረው የሚፈልጉትን ጭምር ዓውቀውም ሆነ ሳያውቁ እየረዱ ናቸው። ፪. የግዕዝ መክተቢያ ሁሉንም ተጠቃሚ ቋንቋዎች ለማስተናገድ የሚችል መሆን ይኖርበታል። ችሎታውን ከኣለው ለዓማርኛው ብቻ ማቅረብ ሲቻል ዓማርኛ ብቻ የሚያስጽፍ ግን ዓማርኛውን ኣደጋ ላይ የሚጥል ነው። ለምሳሌ ያህል “ቜ”ን በ6 መርገጫዎች የሚከትብና “ⷄ”ን ለመክተብ ከ6 በላይ ተጨማሪ መርገጫዎች የሚያስፈልጉት ኣለ። እየኣንድኣንዱን ቀለም በሁለት መርገጫዎች መክተብ ሲቻል የ“ጬ”፣ “ⶼ”፣ “ꬤ” እና “ⶐ” ኣከታተብ ለመለየት የመክተቢያ እስፔሊንግ ማስታወስ ወይም መዝገብ (መዝገበ ፊደል) ያስፈልጋል። ፫. ዓማርኛ የማያስጽፍ መጻፊያ ይጽፋል ተብሎ ኢንተርኔት ላይ ለዓመታት ተቀምጧል። በዶክተሩም የፓተንት ማመልከቻዎች ቀርበዋል። ይኸን የሚያስተውልና የሚቃወም የተማረ ኢትዮጵያዊ ኣለመኖር የሚያሳዝንና የሚያሳፍር ነውና ይታሰብበት። ምሳሌ፦ “ትዝታ”፣ “ድድ”፣  “ህህ”፣  እና “ሏ”ን የማያስጽፉ ኣሉ። ምክንያቱም ሕዝቡ ትናንሽ ችግሮችን እየተመለከተ መቃወም ከኣልቻለ እራሱን ከከባድ ችግሮች ለመከላከል ኣለመዘጋጀቱን ስለሚያሳይ ነው።   ይኸን ኣጻጻፍ የወደዱ ከመቶ ሺህ በላይ ተጠቃሚ ኢትዮጵያውያንን ምን እንደነካቸው ማስገረም ቀጥሏል። ምክንያቱም ጥቂት የኦሮሞ ምሁራን ግዕዙን ለመጥላት መጥላት ምክንያት ሊሆን ሲችል የኣንድኣንድ የዓማርኛ ፊደል ተጠቃሚዎች በኣምታታቾች መጃጃል ምክንያቱ ኣልተገኘም። ላቲን እስፔሊንግ የሚጠቀመው ለቃላት ሲሆን የኣንድኣንድ ኢትዮጵያውያን ፊደሎቻቸው ቃላት ይመስሉ በላቲን እስፔሊንግ መክተብ ምን ይባላል? ፬. ኣንድኣንድ ኢትዮጵያውያን ለብዙ ዓመታት ዓማርኛውን በእንግሊዝኛ ፊደል በተገኘው እስፔሊንግ ሲጽፉ ቆይተዋል።  እንደ ፓልቶክ የኣሉ ፕሮግራሞች ምሳሌዎች ናቸው። በፓልቶክ ለመሳተፍ ከተቻለ እንደ ግዕዝኤዲት የኣሉትንም የዓማርኛ መክተቢያ መጠቀም ስለሚቻል ኣንድኣንድ ዓማርኛ ተናጋሪዎች ዓማርኛውን በኣለመጠቀም እያዳከሙት ናቸው። በዓማርኛ እያወሩ በላቲን መጻፍ ከቀጠለ ነገ ዓማርኛውን መጻፍ የሚችሉ ላይኖሩ ይችላሉ። ይህ የብዙ ሺህ ዓመታት ታሪክ ከኣለው ሕዝብ ትውልድ ኣይጠበቅም።   

፭. ኣንድ የዓማርኛ ጽሑፍ ቀርቦ ውይይት ሲጀመር ኣስተያየት በእንግሊዝኛ የሚሰጡ ኣሉ። በእንግሊዝኛ የሚጽፉት ዓማርኛውን ለማዳከም ሊሆን ስለሚችል በተለይ ስማቸውን እየደበቁና እየተሳደቡ የኣሉትን የድረገጾቹ ኣቅራቢዎች ማንሳት ይገባቸዋል። ፮. ኣንድ የዓማርኛ ጽሑፍ ቀርቦ ውይይት ሲጀመር ኣስተያየት በእንግሊዝኛ የሚሰጡ ምሁራን ኣሉ። በዓማርኛ መጻፍ የማይችሉት ስለጉዳዮቹም ላይገባቸው ስለሚችል በኣለማስተዋል ዓማርኛውን እያዳከሙ ናቸው። ዓማርኛ የሚያነቡ እንጂ የማይጽፉ የቋንቋው ምሁራን በእንግሊዝኛ ሲጽፉ ኣንባቢዎቹንም ላይገባቸው ይችላል። ፯. ኣንድኣንድ ምሁራን ዶክተሩ እየተጠቀሙበት የኣለውን ፊደል ስለሌላቸው ስለቅርጾቹ የሚያነቡትን ባይረ'ዱ ኣያስገርምም። ምክንያቱም ጽሑፉን የሚጽፉትና የሚያነቡት መሣሪያው ላይ በኣለ ፊደል ስለሆነ ነው። ለምሳሌ ያህል ሦስት ቀለበቶች የኣሉት ኃምሱ እንጂ ግዕዙ “ጨ” ኣይደለም።  ስለዚህ ኣንድ ኣንባቢ ወይም ፀሓፊ ሦስት ቀለበቶች የኣለውን ግዕዝ “ጨ” ከኣየ የሚጠቀመው በተሳሳተ ፊደል ነው። ፰. በኮምፕዩተር ዘመን ስለኣለን ጽሑፎችን ለማቅረብ ወርቃማ ጊዜ ውስጥ ነን። ሶፍትዌራችንን እየገዙ የኣሉት ዓማርኛ ተናጋሪዎች ስለሆኑ እናመሰግናለን።   

፱. በግዕዝ ኮምፕዩተር መክተቢያ ከኮምፕዩተሩ ጋር ስለማይመጣ መክተቢያ መግዛት ያስፈልጋል። የኮምፕዩተርም ዋና ጥቅም የተጻፈን ነገር ማስቀመጥ ስለሆነ ማስቀመጥ ጠቃሚ ነው። በተጨማሪም ኣንድን ጽሑፍ እንደፌስቡክ ከኣሉ ገጾች ውስጥ ወስዶ ማስቀመጥ ብቻ በቂ ኣይደለም። በቋንቋዎቻችን የተጻፉ መረጃዎች እንደሌሎች ቋንቋዎች በብዛት እንዲኖሩ በእጥፍ ብዛት መጻፍና ማስቀመጥ ይጠበቅብናል። በኣለፉት ጥቂት ዓመታት ብዙ ጽሑፎች በኢትዮጵያውያን ትጋት ስለቀረቡ በኮምፕዩተር እንግሊዝኛውን ወደ ዓማርኛና ዓማርኛውን ወደ እንግሊዝኛ መተርጐም ተጀምሯል። ፲. የዓማርኛ ትክክለኛዎቹ ኆኄያት ዓማርኛ ናቸው። ሌሎች ምሳሌዎችም “ኃይል”፣ “ሕዝብ” እና “ዓቢይ” ናቸው። ለምሳሌ ያህል “አቢይ”፣ “ኣቢይ”፣ “ዐቢይ”፣ ወይም “ዓብይ” ትክክል ኣይመስለኝም ይላሉ ዶክተሩ።  ምሳሌ  የፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ባሕረ ሓሳብ መጽሓፍ ገጽ 47 እና 48 ስለ ዓቢይ ጾምና ዓቢይ ቀመር ቀርበዋል። ፲፩. በኣጠቃላይ በኣለፉት 45 ዓመታት የኢትዮጵያውያን የዕውቀትና የዓማርኛ ቋንቋዎች ችሎታዎች ኣቆልቍለዋል። በተለይ በእዚህ ዕድሜ ክልል ውስጥ የኣሉ ምሁራን ዓማርኛ ሲናገሩ እንግሊዝኛ  እንዳይቀላቅሉ ሊያስተውሉ ይገባል። ፲፪. ኣንድኣንድ ዓማርኛ ተናጋሪዎች “Torture” በሚለው ቃል ምትክ “Torch” የሚለውን ይጠቀማሉ። መዝገበ ቃላት መጠቀም ሳይጠቅም ኣይቀርም።   ፊደል በሚገባ ስለ ኣልቆጠሩ በ“ነው” ምትክ “ነዉ ይጠቀማሉ። 

፲፫. ኣንድኣንድ ዓማርኛ ፀሓፊዎች በነጠላ ሰረዝ ምትክ የላቲኑን ኮማ (Comma) እንዲሁም በድርብ ሰረዝ ምትክ የላቲኑን ሰሚ ኮለን (Semi-colon) መጠቀም ስለጀመሩ ዶክተሩ እየተቃወሙ ናቸው። ፲፬. ኣንድኣንድ ዓማርኛ ፀሓፊዎች መጽሓፎች ሲያሳትሙ ገጾቹን ለየብቻቸው እያተሙ ይጠርዛሉ። የመጽሓፍና መጽሔት ገጾች ሲታጠፉ ቍጥሮቹና ርዕሶቹ መሣሣም ይገባቸዋል። ለምሳሌ ያህል ገጽ ኣንድ ከግራ ግርጌ ግራ ማዕዘን ላይ ከሆነ ገጽ ሁለት ከቀኝ ግርጌ ቀኝ ማዕዘን ላይ መሆን ይኖርበታል። ፲፭. ኣንድኣንድ ምሁራን ለዓማርኛ ቃለ ምልልስ ሲቀርቡ በዓማርኛ መናገር እንዳለባቸው ኣስቀድሞ ማስጠንቀቅ ያስፈልጋል። እንግሊዝኛ እየቀላቀሉ የሚያስቸግሩትን በማረም የኣሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ጥሩ ሥራ ይዟል። ፲፮. ኣንድኣንድ ኢትዮጵያውያን ዓማርኛውን ኣራት ነጥብ በሌለው ከመጻፍ እንዲቆጠቡና ኣራት ነጥብ በሌለውም መጻፊያ እየጻፉ ጊዜያቸውን ከማባከን ቢቆጠቡ ይጠቅማል። 

፲፯. ኣንድኣንድ ፀሓፊዎች ሞክሼዎች የሚሏቸውን ቀለሞች በሌሏቸው ዓማርኛውን እየጻፉ ችግሮች እየፈጠሩ ናቸው። ለምሳሌ ያህል “መሳሳት“ና “መሣሣት ኣንድ ኣይደሉም። “ምሥር“ አና “ምስር“ ኣንድ ኣይደሉም። ፲፰. ኣንድ የግዕዝ ፊደል በሁለት መርገጫዎች እንደተከተበ ከዶክተሩ ፈጠራ ጋር ከነማስረጃዎቹ ከቀረቡ ፴፪ ዓመታት ኣልፈዋል። ማንኛውንም የግዕዝ ፊደል ዛሬ በሦስትና ከእዚያ በላይ መርገጫዎች መክተብ ከተማረ ሕዝብ ኣይጠበቅም። ኣንድን የዓማርኛ ቀለም በ5 መርገጫዎች መክተብ ኣንድኣንዶቹን የሌሎች ቋንቋዎች ቀለሞች ለመክተብ እስከ ስምንት መርገጫዎች መጠቀም ያስፈልጋል። ፊደል ለመክተብ ቃላት ይመስል እስፔሊንግ ማስታወስ የለብንም። ፲፱. ኣንድ የግዕዝ ፊደል በኣንድ ወይም ሁለት መርገጫዎች ከተከተበ በኋላ ልክ እንደላቲኑ ሌላ ፊደል ኣጠገቡ ስለተከተበ ኣይቀየርም። ሌላ ፊደል ወይም መርገጫ የሚቀይረው ከሆነ መጀመሪያውኑ ቀለሙ ኣልተከተበም ማለት ነው። እነዚህ ከነማስረጃዎቹ ከቀረቡ በኋላ በእንደዚህ ዓይነት መክተቢያዎች መጠቀምና የኣልተጻፉትን ማንበብ ሊያበቃ ይገባል። ፳. ኢትዮጵያ የእራሳቸው ፊደል ከኣሏቸው ጥንታዊ ጥቂት ኣገራት ኣንዷ ሆና ሳለ እንደሌሎቹ ቴክኖሎጅውን ማሳደግ ሲገባ የሶፍትዌር መብት በሚገባ የማይከበርባት ኣገር ሆናለች። ይህ የኢትዮጵያን እድገት ማቀጨጩን ይቀጥላል። የሌላውን መብት የማያከብርን መንግሥትና ሕዝብ ማሰልጠንና መብት ማስጠበቅ ኣስቸጋሪ ነው። 

፳፩. ዓማርኛ የተናጋሪዎቹ የነበረና የሁሉም ኢትዮጵያውያን የጽሑፍ ቋንቋ የሆነ ነው።  ፳፪. በኣሁኑ ጊዜ ዓማርኛ ኢንተርኔት ላይ ብዙ እድገት እያሳየ ነው። እንደነ ጉግልና ፌስቡክ የኣሉ ድርጅቶች ሥራዎቻቸውን በዓማርኛ ሲያቀርቡ ኢትዮጵያውያን እየተራዱ ከኣሉት መካከል ናቸው። ይህ ጥሩ ሥራ ሆኖ ሳለ በቂ ዕውቀት የሌሏቸው እየገቡበት ስሕተቶችን እያስፋፉ ናቸው። ለምሳሌ ያህል “Days” የሚለውን ቃል “ቀናቶች” በማለት የሚያቀርቡ ኣሉ። ትርጕሙ “ቀናት” ወይም “ቀኖች” እንጂ “ቀናቶች” የሚባል ነገር የለም። ፳፫. ግዕዝ ለመጀመሪያ ጊዜ በኮምፕዩተር በዶ/ር ኣበራ ግኝት እስከሚቀርብ ድረስ ቴክኖሎጂው ስለኣልነበረም ከእርሳቸው ዘዴም ውጪ በግዕዝ መጻፍ ኣይቻልም ነበር። ዝምታው ስለቀጠለ ቴክኖሎጅውን ቀድመው ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ኣደረግን የሚሉ ዋሾዎችም ኣሉ። ፳፬. የግዕዝ ፊደል ሌሎች እንዲጠቀሙበት ቀለሞች እንደመጨመር በስሕተት ዓማርኛው ኣይፈልጋቸውም እያሉ በተቀነሱ ፊደላት የሚጠቀሙ ኣሉ። ባለቤቱ የኣላከበረውን ፊደል ጎረቤት ኣይፈልገውም። 

፳፭. የግዕዝ ፊደል ለሁሉም ተጠቃሚ ቋንቋዎች የሚያስፈልጉትን በኣንድና ሁለት መርገጫዎች በዶክተሩ ግኝት መክተብ ተችሏል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የተቀነሱ የዓማርኛ ፊደላትን እንኳን ከሦስትና ከእዚያም በላይ መርገጫዎች የሚከትቡ የእንግሊዝኛ እስፔሊንግ የመክተቢያ ዘዴዎች የኣለተቃውሞ እየተስፋፉ ናቸው። እነዚህ ኣከታተቦች ሌሎች የኣናሳ ተጠቃሚዎች ቋንቋዎች ቀለሞች በበዙ መርገጫዎች እንዲከተቡ ያስገድዳሉ።  ዓማርኛ በበዙ መርገጫዎች በሌሎቹ ቋንቋዎች ምትክ ለመጠቀም ከኣልተዘጋጀ በዘዴዎቹ መጠቀም የለበትም። ፳፮. ኦሮምኛን በላቲን መክተብ (ቁቤ) ከኣሰከተሉት ችግሮች ኣንዱ የማያስፈልጉ ብዙ መርገጫዎችን መነካካት ነው። ዓማርኛን በላቲን እስፔሊንግ መክተብ ተቀራራቢ ችግሮችን ስለሚፈጥር የዘዴው የግዕዝ ተጠቃሚዎች ሌሎችን በእዚህ ለመውቀስ ብቃት የላቸውም። ፳፯. የግዕዝ ፊደል አንዲቀነስ የሚያቀነቅኑ ኣሉ።  ፳፰. ኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ የኣላት ኣገር መሆኗ እየተረሳ ወሬና ፖለቲካ ላይ ማተኰር በዝቷል።  
በግዕዝ እንዲከትብ የኣደረገለትን ለማመስገንም የማያውቅ ሕዝብ ወደመሆኑ ስለተጠጋ ፈጣሪን ማመስገን ኣይጎዳም። ግዕዝ ኮምፕዩተራይዝድ ሆኖ በኮምፕዩተሮችና የእጅ ስልኮች እየተጠቀምንበት ይህን ግኝት የፈጠሩልን ዶ/ር ኣበራ ሞላ  መሆናቸውን የማያውቁ ብዙ ናቸው። ፈረንጁ ኣዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ፈጥረው ዓለምን በቴክኖሎጂ የቀየሩትን ፓተንቶች የኣሏቸውን እነ ቶማስ ኤዲሶን፣ ግራሃም ቤል ፣ እስቲቭ ጆብስ  ፣ ቢል ጌትስ  የመሳሰሉትን ሲያከብርና ሲያበረታታ ኢትዮጵያዊውን ሳይንቲስት ሶፍትዌሩን በፓተንቶች ጠብቀው ሲያቀርቡ  ለመግዛትና ሥራውን ለማስተዋወቅ እንኳን የሚፈልጉ ብዙ ኣይደሉም።  በኮምፕዩተር መጻፍ ኣለመቻል የዘመኑ መኃይምነት ነው። 

፳፱. ኣንድ ደራሲ ስለኣንድ ነገር ሲጽፍ የእራሱ ሥራ ከኣልሆነ ዋቢ ማቅረብ ተገቢ ነው። ዋቢ የሌለው ሥራ የደራሲው ብቻ ነው ማለት ነው። ፴. ኣንድ ደራሲ ትክክለኛ የቃላት ቀለሞችን ከዘነጋ መዝገበ ቃላት መመልከት ጠቃሚ ነው። ምሳሌ፦  መዝገበ ቃላት እያሉ  ፊደል በሚገባ የኣልቈጠሩ ጸፀሓፊዎችን በመከተል በ “ው”  እንጂ በ “ዉ”  የማይጻፉትን እየጻፉ ቋንቋ ማበላሸት ከኣንድኣንድ የተማሩ ሰዎች ኣይጠበቅም። መኃይም የማይሠራውን ስሕተት የተማረው ሲሠራው ኣሳፋሪ ነው። ለምሳሌ ያህል እዚህ ጽሑፍ ውስጥ ከ፬፻ በላይ ግድፈቶች ኣሉ።  አዚህ ውስጥ የለም።  ፴፩. “ፊደላቱ የሚሰጡትን ድምጽና ትርጉም ኣውቆ የኣንዱ ፊደል መውጣት መሻሻል ለረዥም ዘመናት የተጻፉ መጻሕፍት የሓሳብ፣ የትርጕም፣ የቅርስ ጥፋት እንደሚያመጡ ማወቅ ይሻል። ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ የኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ዳግም ጥያቄ በማያስነሳ መልኩ ትክክለኛውን ነገር ሊያስቀምጡና ጥናት በማጥናት ምላሻቸውን ሊሰጡ ይገባል። ከእዚህም በላይ ደግሞ ባለድርሻ የሆነችው ቅደስት ቤተ ክርስትያን ምላሿን ማሳወቅ እንደሚገባት የጥያቄው መብዛት ኣፋጣኝ እንደሆነ ያመላክታል”  ይላል ማኅበረ ቅዱሳን።  
እንዲህም ሆኖ ጽሑፋቸውን በዓማርኛ እንዲጽፉ ያስቻላቸውን እግዜር ይስጥልኝ ለማለት እንኳን የዶክተሩን ስም ሰምተው ላያውቁ ይችላሉ። ፴፪. በተሳሳተ መክተቢያ የተጻፈ በመሆኑ ኣስተማማኝ የኣልሆነ ጽሑፍ ምሳሌ እዚህ ኣለ።  ከእዚህ ጽሑፍ ኣንድ ሁለት ኣንቀጾችን ኮፒ ተደርገው ገጽ ላይ ቢለጠፉ ችግሮቹን መመልከት ይቻላል። 

፴፫. ግዕዝ በዶክተሩ ኮምፕዩተራይዝድ ሆኖ ተገቢውን ዕውቅና ኣግኝቷል። የማይጽፉና የኣልተሟሉ መክተቢያዎች እየተጠቀሙ ኣንድኣንድ የዓማርኛ ምሁራን እራሳቸውን እያዋረዱ ናቸው። ለምሳሌ ያህል ያልተሟሉ የመክተቢያ ዘዴዎች ኣሉ። ሕዝቡን እያወናበዱ የኣሉት ወደ ኦሮምኛው የላቲን ቁቤ ኣከታተብ ዓይነት በብዙ መርገጫዎች የሚያስከትቡ ኣሉ። ፴፬. ኣንድኣንድ የዓማርኛ ደራስያን በተሳሳቱ መጻፊያዎችና ፊደላት እየተጠቀሙ እራሳቸውን እየጎዱ ናቸው። በጊዜ መንቃት ስለኣልቻሉ ኣንድኣንዶቹ እንደኦሮሞዎቹ መጃጃልን እያስፋፉ ናቸው። ፴፭. በቂ የኢንተርኔት ኣገልግሎት ኢትዮጵያ ውስጥ ስለሌለ የዶክተሩን ሥራዎች የማያውቁ በተወሰነው ዕውቀታቸው የሚያቀርቧቸው ኢትዮጵያን እየጎዱ ስለሆነ ኣንባቢው ይሀን ከግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።  ምሳሌዎች፦ ይህ  ስለ  እና  ያልሰማ ይመስላል። ስለ ጋብርኤላ፣ ስለ ዶ/ር ኣየለና ካማራ የዶ/ሩ ሥራዎች ውስጥ ተጠቅሰው ስለኣሉ ከሁሉም ቀድሞ የነበሩትን ሥራዎች ኣንዳቸውም ኣልጠቀሱም። በዶክተሩ 
በተፈጠረው ቴክኖሎጂ እየተጠቀመ የማያመስግነው ቍጥር ስፍር ስለሌለው ከተለመደው መደበቅ ታልፎ ስድብ ተጀምሯል። ፴፮. የዓማርኛውን ፊደል ከ“ሀ”  እስከ “ፐ”  በቃል የማይደረድሩ ምሁራን ኣሉ ይባላል።  ይህ ኣሳፋሪ ነውና ይታሰብበት።

ስለ ፊደል ቅነሳ እዚህ ገጽ በየቦታው የቀረቡ ቢኖሩም እንደገና ማንሳቱ ኣይጎዳም። 

፩. የግዕዝ ፊደል ከ1513 ዓ.ም. ጀምሮ እስከኣሁን ድረስ በማተሚያ መሣሪያዎች በሚገባ እየተጠቀመ ስለሆነ የብቃት ችግር የለውም። መጽሓፍት በማተሚያ ቤቶች ሲታተሙ ስሕተቶቹ ብዙ ኣልነበሩም። ፊደል መቀነስ የተጀመውረው በሚሲዮናውያን ነው።   በዐፄ በካፋ ዘመነ መንግሥት ሃሌታውን “ሀ” ከሐመሩ “ሐ” ንጉሡን “ሠ” ከእሳቱ “ሰ” ፥ ጻድቁን “ጸ” ከፀሐዩ “ፀ” ለይቶ በሥፍራቸው ያልጻፈ፤ ፊደል አዛውሮ የተገኘ ጸሐፊ እጁን ይቆረጥ እንደ ነበረ የጽሑፍ መረጃዎች ይጠቁማሉ።  ፪. የመቀነሱም ነገር ብዙዎቹ ሲከራከሩ እንደነበሩት ዓማርኛውን ብቻ የተመለከተ ኣይደለም። ፫. ከዳግማዊ ምኒልክ ጀምሮ ብዙ ኢትዮጵያውያን ሊቆች፣ ሚኒስትሮችና ደራስያን የእንግሊዝኛውን የታይፕ መጻፊያ ለዓማርኛ መክተቢያ እንዲያገለግል ወደ ሰማንያ ዓመታት ግድም ሲመራመሩ ቆይተው ኣልተሳካላቸውም። 
፬. ኢ/ር ኣያና ብሩና ኢ/ር ተረፈ ራስወርቅ የዓማርኛውን ፊደላት በመቀነስና ቆርጦ በመቀጠል ኣማርኛ በመሰሉ የፈጠራ ቅርጾች የኣቀረቧቸው ሥራ ላይ ውለዋል። እነዚህ ቍርጥራጮች ግን የዓማርኛ ፊደሎች ኣይደሉም። ለእነዚህ ከመቶ በኣነሱ መቀጣጠያዎች የሚሠሩ የፈጠራ የኣማርኛ ነገሮች የሚያስፈልጋቸው ኣንድ የእንግሊዝኛ የፊደል ገበታ ስለሆነ በኣንዱ ገበታ ምትክ ብቻ የቀረቡ ናቸው። የዓማርኛ ቀለሞች ብዛት ከ200 በላይ ስለሆነ 100 ስፍራዎች ኣይበቁትም።

፭. ኆኄያቸውን የጠበቁ የግዕዝና ዓማርኛ ጽሑፎች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለብዙ ዘመናት ተጽፈዋል። ፮. በእጅ ጽሑፍም ወረቀት ላይ መክተብ ለኢትዮጵያ ሕዝብና የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ጠቅሟል።  ፯. ፊደል መቀነስ ትኩረት የኣገኘው “ፍቅር እስከ መቃብር” መጽሓፍ በተቀነሱ ፊደላት በ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. ከታተመ በኋላ ነበር። እዚህ ላይ ተደርቦ ለታይፕራይተር ቴክኖሎጂ እንዲመች የፊደል ቅነሳ ክርክር ተጀምሮ በመጨረሻው ውድቅ ሆነ። ፰. የኢትዮጵያ ቋንቋዎች መርሐ ልሳን [ኣካዴሚ] በ1973 ዓ.ም. ካወጣው የአጻጻፍ ሥርዓት ውሳኔ በስተቀር ሌላ ወሳኝ ጥናት ባለመደረጉ፣ ለዚህ ጉዳይ ተጠያቂ ሊሆን የሚችሉ መምህራንንም ስለዚህ ጉዳይ ሆን ብሎ ያስተማራቸው ሰው ባለመኖሩ እነሱ ራሳቸው በዘፈቀደ ስለሚጽፉ ተማሪዎቻቸውም የነሱን ፈለግ በመከተል በዘፈቀደ ይጽፋሉ፤ የሚሉት ዶ/ር አምሳሉ አክሊሉ የአማርኛን ሞክሼን ሆሄያት ጠንቅቆ ያለመጻፍ ችግርና መፍትሔ የሚባል መጽሓፍም ጽፈዋል። ሃሌታው “ሀ”፣ ሓመሩ “ሐ”፣ ብዙኃኑ “ኀ”፣ ንጉሡ “ሠ”፣ እሳቱ “ሰ”፣ ኣልፋው “አ”፣  “ዓይኑ” “ዐ”፣ ጸሎቱ “ጸ”፣ ፀሐዩ “ፀ” የተባሉትን በማጥበቅና በማላላት ብቻ ለመግለጽ ኣስቸጋሪ ነው። 

እንደ ዶ/ር ኣምሳሉ ተፈራ ኣገላለጽ ከፊደላት ጋር የሚከሰቱ ችግሮችን ኣስመልክቶም በዓማርኛ ፊደል ገበታ ላይ ተመሳሳይ ድምጽ ያላቸው ስለሚገኙ፤ በኣጻጻፍ ረገድ በርካታ ልዩነቶች መኖራቸው፤ ራብዕ ድምፅ ያላቸው ከግዕዙ ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው ፊደላት መኖራቸው፤ ሳድስና ሳልስን እያቀያየሩ መጠቀም፣ ዲቃላዎችንና ፍንጽቅ ፈደላትን በዝርዝር የመጠቀም ዝንባሌ፣ በመሠረታዊ ቃሉ ላይ የሌለውን ቃል መጨመር፣ የኣናባቢዎች ቅጥል ኣለመለየት ችግሩን ይበልጥ እንዳሰፋው ጠቁመዋል።  (የእነዚህም ምሳሌዎች በቅደም ተከተል “ሀ እና “ኀ፤ “ሃገር እና “ኣገር፣ “አ እና “ኣ፣ “ግዜ እና “ጊዜ፣ “ፏፏቴንን በ“ፍዋፍዋቴ፣ “ኈን በ“ሆ፣ “መምህራንን በ“መምህራኖች እና “ዮን በ“ዬ ዓይነቶች ናቸው በማለት በኣጠቃላይ ግን ችግሩ ከፊደሉ ሳይሆን ከተጠቃሚው ነው ይላሉ ዶ/ር ኣበራ።) ይህ ችግር በምሁራን ዘንድ ሞክሼ ቃላት ይቀነሱ፤ አይቀነሱ የሚለው ሐሳብ ዛሬም ድረስ እያከራከረ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ኣማራጮችንም በተመለከተ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ኣካዳሚ በ1973 ዓ.ም. ተመሳሳይ ድምፅ ያላቸው ፊደሎች ከገበታው ላይ ተቀንሰው በኣንድ ፊደል ብቻ ይወከሉ የሚል ሲሆን፣ የቤተ ክሕነት ሊቃውንት ኣቋም ደግሞ ፊደላት የፈጣሪን ቸርነት የሚገልጹ እና ከእሱ የተገኙ ስለሆኑ ሁሉም ጠንቅቆ ሊጽፋቸው ይገባል እንጂ በፍጹም ሊቀነሱ አይገባም ነው። ፊደላቱ በሙሉ መንፈሳዊ፣ ተፈጥሯዊና ሙያዊ ትርጓሜ ስላላቸው ያንን ያጣሉ በማለት ዶ/ር አምሳሉ ተፈራ ይገልጻሉ።  የኣብነት (ቄስ) ትምህርት ቤቶች ትኩርት መነፈግንም የሚጠቅሱ ኣሉ።  

፱. ከ1980 ዓ.ም. ወዲህም እነዚሁ ቀለሞች በዶ/ር ኣበራ ወደ ኮምፕዩተር ስለገቡ የግዕዝ ፊደላችንን የኣጋጠመው ችግር የለም። ይህ በእንዲህ እንዳለ የኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማዕከል በተቀነሱና በተቀነጠሱ ፊደላት “ኣማርኛ መዝገበ ቃላት” በ፲፱፻፺፫ ዓ.ም. እንዲሁም “ክብረ ነገስት ግእዝና ኣማርኛ” መጽሓፍት በ፲፱፻፺፬ ዓ.ም. ኣትሟል። በመጽሓፎቹ ርዕሶች “ኣማርኛ”፣ “ነገስት”ና “ግእዝ” ተብለው የቀረቡት “ዓ”፣ “ሥ” እና “ዕ” ከተቀነሱት ቀለሞቻቸው ውስጥ የተካተቱ በመሆናቸው ነው። እነዚህ ቍርጥራጮች ግን የዓማርኛ ፊደሎች ኣይደሉም። ክርክሩ በኣይቀነስ ባዮች ምክንያታዊ ኣሸናፊነት ማለቅ ሲገባው እንደቀጠለ ኣለ።    
  
    ይህ ሁሉ ሲደረግ የዩኒኮድ ዓማርኛ ቀለሞች ኣልተቀነሱም። ፲. ለብዙ መቶ ዓመታት በውጭ ኣገራትና ኢትዮጵያ ውስጥ በግዕዝ ፊደላችን ሲጠቀሙ የነበሩ ማተሚያ ቤቶች ፊደል ሲቀንሱ ኣልሰማንም።
፲፩. ይህ የተዛባ የቅነሳ ኣጠቃቀም የመንግሥትም ፍላጎት ይመስላል። ምክንያቱም የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዓይነት ተቋማት ፊደል መቀጠሉን ተዉት እንጂ በመቀነሱ ስለቀጠሉበት ነው። የግዕዝ ፊደል ትክክለኛ ኣጠቃቀም እያለ በተቀነሱና በተቈራረጡ ነገሮች መጠቀም መቀጠል በኮምፕዩተር ዘመን የሚያስከትለው ኪሳራ ቀላል ኣይደለም። ለምሳሌ ያህል በታይፕራይተር ዘመንና ይኸንኑ መሣሪያ ኮምፕዩተራይዝ የኣደረጉት ኣራት ነጥብን ሲከትቡ የነበሩት ሁለት ባለ ሁለት ነጥቦችን በመጠቀም ነበር። ዶ/ር ኣበራ ግን ለኣራት ነጥብ ከመነሻውም ኣንድ ስፍራ ስለመደቡለት ከዩኒኮድ በፊትም ይሁን በኋላ ፊደሉ የእራሱ የኮምፕዩተር ቍጥር ወይም ኮድ ኣለው።  ጥቂት ኣዳዲስ ፊደል ቀናሾች ወይም የግዕዝ መክተቢያ ኣቅራቢዎች ኣራት ነጥብን ከሁለት ባለ ሁለት ቀለሞች ማስከተብ ስለጀመሩ ጽሑፎቹ ኣራት ነጥብ የላቸውም። በኣሁኑ ጊዜ በብዙ ሚሊዮን የሚቈጠሩ ኢንተርኔት ላይ የኣሉ ኣራት ነጥብ የሌላቸው ጽሑፎች ማለቂያ የሌላቸው ናቸው። (የማለቂያን ቅኔነት የሚገባቸው ያውቁታል።) እነዚህን ስሕተቶች እየተከታተሉ ማረም ኣስቸጋሪ ስለሆነ ስሕተቶቹ እንዳይቀጥሉ ሁላችንም መረባረብ ይኖርብናል። ሁለት ነጥቦች መካክል ተገብቶ ሁለቱን ብቻ በኣንድ መርገጫ መሰረዝ ከተቻለ መክተቢያውን ሆነ ፊደሉን ኣለመጠቀም ያዋጣል። ኣራት ነጥብ በሌላቸው ቀለሞች የተጻፉ ብዙ መጽሓፍትም ስለኣሉ ሰዉ በኣወናባጆች ወደኋላ እየተመለሰ ነው። ይህ የምልክት ቅነሳ ያስከተለው ችግር ነው። የግዕዝ ፊደላችን እንደ ቻይናው ሥዕሎች የሚሳሉበት ስለኣልሆነ  በሺዎች የሚቈጠሩ ኣይደለም።  ፲፪. ፊደል መቀነስ ፊደላችን ላይ የተቃጣ ዘመቻ ነው።   

፲፫. ቀደም ብለው በዶክተሩ ለዩኒኮድ የተለገሰውን ፊደል  ኣስጥለው የተቈራረጡ የአማርኛ ፊደል  ለዩኒኮድ የኣቀረቡት ተሸንፈዋል። ቀደም ብለው በዶክተሩ ለዩኒኮድ የተለገሰውን ፊደል ኣስጥለው የተቀነሱ ፊደላትን  ለመቀጣጠል ለዩኒኮድ ለማቅረብ የኣቀዱት በሁለተኛ ዙር ጥፋት የኣቀዱትም ተሸንፈዋል። ይህ ሁሉ ሲሆን ቀደም ብሎ ለአማርኛ ታይፕራይተር ሲባል ፊደል ይቀነስ የተባለውን ክርክር የቀጠሉበት ስለ ዶክተር ኣበራ ሥራ ያልሰሙት እንደእነ የኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርሲቲ ተቋም የኣሉት ነበሩ።  ወደፊት ኮምፕዩተሩ ዓረፍተ ነገርን በማረም ትክክለኛውን ሆኄ እንዲያስቀምጥ እናደርጋለን።  መጻፍ የማይፈግጉ ለኮምፕዩተሩ ነግረውት ይጽፋል። ፲፬. ቋንቋን በቁዋንቁዋ መጻፍ ኮምፕዩተሩ ቀለሞቹን የሚያስቀምጥባቸውን ሥፍራዎች ከማስጨመር ሌላ ወረቀትንና ጊዜ ያስባክናል። ቋንቋን ቁዋንቁዋ በሚመስል ድምጽ ማንበብ እንኳን የፊደሉና የዓማርኛ ቋንቋ ሥርዓት ኣይደሉም። ቁዋ እንደ ቋ እንዲጻፍና እንዲነበብ ማስገድድ የኣምባገነኖች ፍላጎት እንጂ  የፊደሉና የቋንቋው ኣይደሉም። ፲፭. ዶክተር ኣበራ ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ኣድርገው ፓተንቶች ሲያገኙባቸው ቴክኖሎጅው በዓዋቂዎች ተጠንቶና ተፈትሾ ነው። ከእዚሁ ጋር የተያያዙ ኣዳዲስ ኣጠቃቀሞች ለግዕዙ ቀርበዋል። ለምሳሌ ያህል ቋንቋ የሚለው ቃል እንዲፈለግ ለኢንተርኔት ሲቀርብ ብዙ ቃላቱን የያዙ ጽሑፎችን ማግኘት ሲቻል ቃሉን በቁዋንቁዋ የሚጽፉ ከኣሉ ፍለጋው ሁለቴ እንዲደረግ ያስገድዳል። ስለዚህ ለታይፕራይተር ሲባል የቀረበ ክርክር ከኋላቀር መሣሪያው ጋር መቅረት ኣለበት። ዶ/ር ኣበራ ሞላ ከታዋቂ የዓለም ሳይንቲስቶች ኣንዱ ናቸው። 

ቁምፊ (Typeface) ኣንድ ዓይነት ቅርጽ የኣሏቸው የፊደል ቀለም (Font) ቤተሰብ ነው። 

ድንጋይ፣ ብራናና ወረቀት ላይ በእጅ ሲጻፉ የነበሩት የግዕዝ ቀለሞች በማተሚያ መሣሪያዎች እ.ኤ.ኣ. ከ1513 ጀምሮ ሲጠቀሙ ቆይተዋል።    በ፲፱፻፳፭ ዓ. ም. ግድም የጽሕፈት መሣሪያ ተፈጥሮ ለቢሮ ሥራዎች ጠቅሟል። ግዕዝ ወደ ኮምፕዩተር ሳይገባ ለኢትዮጵያ ጽሑፍ መበልጸግ ትልቁን ድርሻ የኣበረከተው የማተሚያ መሣሪያ ሳይሆን ኣልቀረም። የግዕዝ ወደ ኮምፕዩተርና የእጅ ስልክ በፊደሉ መግባት በተለይ የዓማርኛ ጽሑፎችን እንዲስፋፉ ጠቅሟል። ፊደሉ ከቴክኖሎጅው ጋር እንዲራመድ መገንዘብ ስለኣለብን ኣንድኣንድ ነጥቦች ከእዚህ በታች ቀርበዋል። 

፩. ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ሲያደርጉ ዶክተሩ የቁምፊውን መጠን በግምት ኣስቀመጡት እንጂ መደብ ኣላወጡለትም። ፪. በኣሁኑ ጊዜ ሕዝቡ በግዕዝ ፊደል በብዛት መጽሓፍት እየጻፈ ስለሆነ እየተደሰትን ነው። ሆኖም ጽሑፎች እየታተሙባቸው የኣሉት ቁምፊዎች መልኮች የተለያዩና ኣብዛኛዎቹ የተሳሳቱ ስለሆኑ መጠንቀቅ ያስፈልጋል። ከግዕዝኤዲት ፕሮግራሞች ጋር እየተሸጠ የኣለው የዶ/ር ኣበራ ሞላ ግዕዝኤዲት ዩኒኮድ (GeezEdit Unicode) ቁምፊ ወደ ትክክለኛው የቀረበ ነው።  ይኸን ቁምፊ ከተጠቀሙበት መካከል ዶ/ር ኣክሊሉ ሃብቴ በ፳፻፱ ዓ.ም. ያሳተሙት ባለ 629 ገጾች የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ታሪክ መጽሓፍ ኣንዱ ነው።  በፊደሉ ለብዙ ዓመታት እየተጠቀሙበት የኣሉት የኣቶ ኣብርሃ በላይ ኢትዮሚዲያ ገጾችም ኣሉ።  በ፳፻፲፩ ዓ.ም. ሰይፉ ኣዳነች ብሻው በግዕዝኤዲት ፕሮግራም በመጠቀም የምኒልክ ጥላ መጽሓፍ ጽፈዋል። በጽሑፋቸውም ዶክተር ኣበራ ስለ ሆኄያት መልኮች በተለይ የጨ ባለሁለት እግርነት እውነታ ተቀብለዋል። ፫. መጽሓፍ በኮምፕዩተር ሲታተም ቁምፊውን ኣስቀድሞ መወሰን ይጠቅማል። ምክንያቱም በኣንድኣንድ ኣስቀያሚና የተሳሳቱ የፊደል መልኮች የተጻፉ ጽሑፎች ማንበብ ኣያጓጓም።  ፬. ኣንድ የግዕዝ ዩኒኮድ ቁምፊ ሁሉንም የግዕዝ ቀለሞች እንደኣሉት ማጣራት የደራሲው ሥራ ነው። ምክንያቱም ዶክተሩ ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ኣድርገው የማተሚያ ቤቶቹን ኃላፊነት ለደራሲዎች ስለሰጡ ኣዲሱን ቴክኖሎጂ መማር ኣስፈላጊ ስለሆነ ነው።

፭. ኣንድ በግዕዝ ዩኒኮድ ቁምፊ የሚጠቀም ደራሲ ሁሉንም የግዕዝ ቀለሞች መክተብ መቻሉን ማጣራት የደራሲ ሥራ ነው። ምክንያቱም ዶክተሩ ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ኣድርገው የማተሚያ ቤቶቹን ኃላፊነት ለደራሲዎች ስለሰጡ ኣዲሱን ቴክኖሎጂ መማር ኣስፈላጊ ስለሆነ ነው። ፮. ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ሲያደርጉ ዶክተሩ በመደበኛነት (Standard) የተጠቀሙት የኢትዮጵያ ቍጥር ፩ ፊደል ነው። እ.ኤ.ኣ. በ1988 በዶክተሩ ከፖስትእስክሪፕት (Postscript) ፊደላቸው የተሠራ የመጀመሪያው ትሩታይፕ (TrueType) የግዕዝ ፊደልና ፊደላቸው ነው። ለሥራቸው መሳካት የኮሎራዶው ኩባንያዎች ከዶክተሩ ባለውለታዎች ዋነኞቹ ናቸው። ይህ እነ ብርሃንና ሰላምና የመሰሉ የኢትዮጵያ ማተሚያ ቤቶች ሲጠቀሙበት የነበረው ቁምፊ ወደ ታይምስ ሮማን (Times Roman) የእንግሊዝኛ ቁምፊ የቀረበና ተመሳሳይ ቢሆንም ከላቲኑ ጋር ሲወዳደር የግዕዝ ፊደል ተለቅና ደመቅ የኣለ ነው።  ኣብዛኛዎቹ የዓማርኛና እንግሊዝኛ መጽሓፍት ሲጻፉ የነበሩት በእነዚህ ቁምፊዎች ነበር። ይህ የግዕዝ ቁምፊ መልክ ወደጎን ቀጠን ብሎ ወደታች የወፈረ ነው። በማተሚያ ቤቶቹና ግዕዝኤዲት ዩኒኮድ ሲታተሙ የነበሩት መጽሓፎች የፊደል መጠን (Points) ከ10 እስከ 12 ነበር። ፰. ኣንድ የግዕዝ ቁምፊ ቢያንስ ከኣንድ ተመጣጣኝ የእንግሊዝኛ ቁምፊ ጋር መቅረብ ይኖርበታል። 

፱. ኮምፕዩተሮችና የእጅ ስልኮች ላይ በቀላሉ ማየት እንዲቻል የሚቀርቡ ጽሑፎች ደቦልቦል በኣሉ ቁምፊዎች ነው። እነዚህን ለመጽሓፎችና ለመሳሰሉት መጠቀም ኣስፈላጊ ኣይደለም። ምክንያቱም ትላልቅ ስለሆኑ በዛ የኣሉ ስፍራዎችንና ወረቀቶችን ስለሚያስባክኑና ጥቅማቸው ለኅትመት ስለኣልሆነ  ነው። ፲. ኣንዳኣንድ ሰዎች ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ማድረግ ፊደሉን መሥራትና ማቅረብ ይመስላቸዋል። ይህ ከኣለማወቅ የመጣ ስሕተት ነው።  በፓተንት የሚጠበቀው ኣዲስ የሆነውና ፊደሉን በኮምፕዩተር መጠቀም የኣስቻለውን ቀደም ብሎ ያልነበረውን ዘዴ ነው እንጂ ከዘዴው ጋር ለሚቀርቡት ፊደላት ኣይደለም።  ፲፩. ኣንዳኣንድ ሰዎች ግዕዝን ኣሜሪካ ፓተንት ማድረግ ፓተንቱን ወይም ፊደሉን ለኣሜሪካ መስጠት ይመስላቸዋል። ይህ ከኣለማወቅ የመጣ የፈጠራ ወሬ ነው። ፲፪. ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ኣድርገው ከትክክለኛው ቁምፊ ጋር ዶክተሩ ከኣቀረቡ በኋላ ከአማርኛው ቅጥልጥል ፊደል እስከኣልተሟሉና የተሳሳቱ ቀለሞች የኣሉዋቸውን ቁምፊዎች በነፃና በሽያጭ የሚያቀርቡ ኣሉ።  ይኸንን መረዳትና ማስተዋል የተጠቃሚው ኃላፊነት ሲሆን ኣንባቢው ስሕተቶችን እያየ ዝም ማለቱ ደረጃቸው ለኣዘቀጡ በኮምፕዩተር ለቀረቡ ጽሑፎች ኣስተዋጽዖ እያበረከተ ነው። 

፲፫. ኣንድ ኣንባቢ ኮምፕዩተር፣ የእጅ ስልክና የመሳሰሉት ላይ የሚመለከተው የግዕዝ ዩኒኮድ ፊደል መሣሪያው ላይ በኣለው ፊደል ነው። ፊደሉ ትክክል ከኣልሆነ ትክክል ኣለመሆኑንንም ላይረዳ ይችላል። ለምሳሌ ያህል የጨ ቀለበቶች ሁለት ናቸው ሲባልና ቢያነብ ባለ ሁለት ቀለበቶች ትክክለኛ ፊደል ከሌለው ፊደሉን የሚያነበው ሦስት ቀለበቶች በኣሉት የተሳሳተ ፊደል ነው። የዶክተሩ የግዕዝ ቁምፊ ከኣሥር ዓመታት በላይ እዚህ የዩናይትድ እስቴትስ ፓተንትና ማመልከቻው ውስጥ ኣሉ።  ፲፬. ኣንድ በቅርቡ የተለቀቀ ቁምፊ ውስጥ የዓይኑ ዓ ፊደል መልክ ወደ ኣረቡ ዘጠኝ (9) የቀረበ ሲሆን የሌላው ፃ መስመሩ የኣለው በዓ ክብ ውስጥ ነው። ፲፭. ዶክተር ኣበራ ሞላ ከዓለም ፊደል ሠሪዎች ኣንዱ ናቸው።  ፲፮. በማተሚያ ቤቶች ከታተሙ የግዕዝ ቁምፊዎች የሚከተሉት ይገኙበታል።  

፲፯. በተሳሳተ ፊደል የተጻፈ በመሆኑ ኣስተማማኝ የኣልሆነ ጽሑፍ ምሳሌ እዚህ ኣለ።  ከእዚህ ጽሑፍ ኣንድ ሁለት ኣንቀጾች ኮፒ ተደርገው ገጽ ላይ ቢለጠፉ ችግሮቹን መመልከት ይቻላል። ፲፰. ኣንድ ቆንጆ የቁም ፊደል አጣጣል እዚህ ኣለ።  ፲፱. በግዕዝ ፊደል ወግ ስምንተኛው ፊደል የሚቀርበው ግዕዙ ወይም ራብዑ ላይ መስመር በመጨመር ነው ። ፏ የተሠራው መስመሩን ፋ ኣንገት ላይ በመጨመር ነው። በኣሁኑ ጊዜ ብዙዎቹ ቅጣዩን በስሕተት ከታች ሲያቀርቡ ኣንዱ በቅርቡ ፍ ላይ ኣድርጎታል። መሳሳታቸውን ከቆዩ ጽሑፎች ውስጥ ማየት ይቻላል። እንዲህ ዓይነቶችን ስሕተቶች ስር ሳይሰዱ ማረም ከኣልተቻለ ዛሬ ኣበበን እሞታታለሁ እንጂ በአበበ ከኣልሆነ ኣልጽፍም እንደሚሉት ጥቂቶቹ በኋላ በትምህርት ማቃናት ሊያስቸግር ይችላል። ፳. ኣንድ የግዕዝ ቁምፊ ቢያንስ ኣንድ ኣብሮት የኣለ የእንግሊዝኛ ፊደል ጋር መቅረብ ይኖርበታል። ስለዚህ ለሰው የሚቀርበው የላቲን ፊደልም እንደግዕዙ የፊደል ሠሪው መሆን ይገባዋል።  የግዕዙና የላቲኑም ፊደላት ቅርጾች የተቀራረቡ መሆን ይኖርባቸዋል። 

፳፩. ዩኒኮድ ለፊደላቱ መደብ ሰጠ እንጂ ፊደል ኣላቀረበም። የግዕዙ ፊደል ኮምፕዩተርና የእጅ ስልክ ላይ ከሌለ የግዕዝ ፊደል ኣይታይም። የሚታየውም እንደፊደሉ ሊለያይ ይችላል። ስለዚህ ኣንድ ተጠቃሚ የሚጠቀምበትን መሣሪያ ላይ ያለውን የፊደል ስምና መልክ ማወቅ ኣለበት። ፳፪. ኣንድ የግዕዝ ፊደል ተጠቃሚ ሁሉንም የግዕዝ ቀለሞች ቅርጾች ማወቅ ይጠበቅበታል። በኣሁኑ ጊዜ ግን ሁሉንም የዓማርኛ ቀለሞች እንኳን የማይለዩ ኣሉ። ፳፫. ከእዚህ በፊት ተዉ እያልናቸው በታይፕራይተር ዓይነት ፊደል ተታልለው መጽሓፍት ሲጽፉ ከርመው የተበሳጩ ኣሉ። ኣሁንም በተሣሣቱ የዩኒኮድ ፊደሎችና የዓማርኛ መጻፊያዎች እየተጠቀሙ እራሳቸውንና ዓማርኛውን እየጎዱ የኣሉ ኣሉና ይታሰብበት። ፳፬. የግዕዝ ፊደል ቅርጾችና ምንነት ምሳሌዎች የሚከተሉት ናቸው።  

፳፭. የግዕዝ ኣኃዞች እያንዳንዳቸው ከላይና ከታች ሰረዞች ኣሏቸው። የኮምፕዩተሩ እስክሪን ላይ የሚታየውና የሚታተመው ኣንድ ፊደል ነው። የፊደሉ መጠን በኣነሰ ቍጥር ጥራቱ እየቀነሰ መስመሮቹ ኣንድ መስለው ይታያሉ። ፊደሉ የዶክተሩ GeezEdit Unicode ከሆነ ጽሑፉን ከእዚህ ውስዶ ወርድ ላይ ለጥፎ በማሳደግ ማረጋገጥ ይቻላል። እንዲህም ሆኖ ቍጥሮቹ ጎን ለጎን ሲሆኑ ሰረዞቹ እንዲገናኙ የተሠሩና የሚቀጣጠሉ በነፃ የሚታደሉ የተሣሣቱ ፊደሎች ኣሉ። ለእዚህ ነው በነፃ የሚታደሉትን ሁሉ መጠቀም የማያዋጣው። ፳፮. ኣንድን የግዕዝ ፊደል ጽሑፍ እንደወርድ የኣሉ ቁሶች ውስጥ ኣቅልሞ GeezEdit Unicode የሚለውን ፊደል በመምረጥ ወደ ፊደሉ መቀየር ይቻላል። ይህ እንግሊዝኛውንም ወደ ግዕዝኤዲት ዩኒኮድ ፊደል ያስቀይራል። ፳፯. ለዊንደውስንና ኣይፎን የሚሸጡት ግዕዝኤዲት ፕሮግራሞች የሚጠቀሙት ኣንድ ዓይነት በሆነው ግዕዝኤዲት ዩኒኮድ ፊደል ነው። ይህ ፊደል እ.ኤ.ኣ. በ1989 ግድም ለዩኒኮድ የተለገሰው የመጀመሪያ የግዕዝ ትሩታይፕ ፊደል ነው።

 

 

 
 
 

 

 
 
 

 
 
 
 
 

 

 




#Article 238: የለጥ ቅዱስ ጊዮርጊስ (381 words)


 
የለጥ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት፤ በከሰም ወረዳ ውስጥ የሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ነው።
   
ማረጋገጫ ጽሑፍ ባይገኝም፤ አፈ ታሪኩ፣ የጊዮርጊስ ታቦት በቡልጋ የለጥ የተተከለው በዓጼ ዮሐንስ ዘመን ነው ይላል። እስከ ፲፱፻፵፫ ዓ.ም. ድረስ የቤተ ክርስቲያኑ ሕንጻ ክብ የሳር ክዳን ሕንጻ እንደነበር ይነገራል። እስከ እዚያም ዘመን የሰማእቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ታቦት ከድንግል ማርያም፣ ቅዱስ ፋሲለደስ እና መድሃኔ ዓለም ታቦታት ሌላ 13 ታቦታት እዚያው እሳር ክዳን ቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ እንደነበሩ ይነገራል።

በ ፲፱፻፵፫  ዓ.ም ንቦች ጣሪያው ውስጥ ሰፍረው ኖሮ ከሳር ክዳኑ ውስጥ ሲገቡ ሲወጡ ይታዩ ነበር። የጊዜውም ካህናት በምስጢር ይሸራረሩኩና ማሩን በድብቅ ለመቁረጥ ይስማማሉ፣ ከዕለታት አንድ ቀን በምሽት ፍም ይዘው ሳር ክዳኑ ላይ ይወጡና ማሩን ቆርጠው ይወርዳሉ፣ ያልተገነዘቡት ግን ፍሙ ለካ እጣራው ወራጅ ላይ ወድቆ ኖሮ አንድ ሳምንት ሙሉ ካፈጋ በኋላ ተያይዞ ቤተ ክርስቲያኑን ያቃጥለዋል። ቤቱ ሲቃጠል የዋንዛ ዋልታው እመንበሩ ላይ ይወድቃና ታቦቱን ሸፍኖ ቀብሮ ያድነዋል። በየለጥ አካባቢ ሀዘንና ትካዜ ሰፈረ፣ ሕዝቡ ታቦታቱን ሲፈልግ ሰንብቶ በዚያ ጊዜ ከነበሩት አሥራ ሰባት ታቦታት ውስጥ የጊዮርጊስ ታቦትና የማሪያም፣ የመድሃኔዓለም፤ የፋሲለደስ ታቦታት ብቻ ሳይቃጠሉ ድነው ተገኙ ይላሉ ቄስ ሰርጸወልድ ተሰማ። 

ይኸኔ ልዩ ስሟ ቡሄ አምባ በምትባለው የየለጥ መንደር በ ፲፱፻፯ ዓ.ም ተወልደው በአምስቱ የኢጣሊያ ዘመን በአርበኝነት ተሰማርተው ሀገራቸውን ያገለገሉት ደጃዝማች ኪዳኔ ወልደመድኅን ቤተ ክርስቲያኑን እንዲያሰሩላቸው ጠይቀዋቸው ደጃዝማች ኪዳኔም ቤተ ክርስቲያኑን አሰርተው ከጨረሱ በኋላ ሕንጻው አሰራሩ ቅሬታ ስላሰማቸው አስፈርሰው እንደገና አሰርተው ታቦቱን ሚያዝያ ፳፫ ቀን ፲፱፻፵፱) ዓ.ም አዲሱ ቤተ ክርስቲያን ሊያስገቡ ቻሉ። ይኼ ቤተ ክርስቲያን በዘማናዊ መልክ በአራት ማእዘን ተሰርቶ በአካባቢው ቡልጋ ውስጥ በቆርቆሮ የተሰራ የመጀመሪያው ሕንጻ ነበር።  

በ ፲፱፻፺፭ ዓ.ም ለሚያዝያ ጊዮርጊስ በዓል በተደረገው የሕንጻ ምርመራ ቤተ ክርስቲያኑ አርጅቶ ተሰናጣጥቆ፣ ተበላሽቶ ስለነበር ሕንጻውን አፍርሶ እንደገና በዘማናዊ መልክ ለማሠራት ተወሰነ። 
ለዚኽም ሥራ:- 

አዲሱ ቤተ ክርስቲያን ባለ ስምንት ማእዘን ሕንጻ ሲሆን፤ የመሬቱን ገደላማነት በመጠቀም ግምጃ ቤትና ቢሮ የሚሆን ምድር ቤት ተሠርቶለታል። ሕንጻው ሙሉ በሙሉ በድንጋይ የተገነባ ሲሆን፤ ጣራውን በዘመናዊ ሸክላ መሰል ቆርቆሮ ተደፍኗል። ከአካባቢውም ጋር በቀለም እንዲዋሃድ አረንጓዴ ቀለም ተመርጧል። ደጃዝማች ኪዳኔ ያሠሩት ቤተ ክርስቲያን ተገጥመው የነበሩት የሙገሬ ጽድ መዝጊያና መስኮቶች ከታደሱ በኋላ አዲሱ ቤተ ክርስቲያን ሕንጻ ተመልሰው ሊገጠሙ ችለዋል። ሥራው በሁለት ዓመት ተኩል ተጠናቆ ቅዳሜ ጥቅምት ፳፫ ቀን ፳፻ ዓ.ም ታቦታቱን አዲሱ ቤተ ክርስቲያን አስገብተናል። በዚህም ዕለት ጸበሉን አስባረክን። 

ኢትዮጵያዊ የገጠር ሕዝብ በአንድነት የጋራ ኃይማኖቱን፤ ባህሉንም ሆነ ሰብዓዊ ሕይወቱን የሚኖረው በኃይማኖቱ ማስተናገጃ ቤት ነው። እነሆ በጋራ የዚህን ገጠር ሕዝብ የለጤ እና ሕዝበ ክርስቲያን አስብሎ የሚያስጠራውን የየለጥ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በቅድሚያ ተሠርቶለታል፤ ከዚህ በኋል ትምህርት ቤት፤ ክሊኒክ፤ ወዘተ. ሊከተል ይችላል። ይኼንንና የመሳሰሉትንም ተግባራት ለማስፈጸም እግዚአብሔር ፈቃዱ ይኹን።




#Article 239: ደጃዝማች ኪዳኔ ወልደመድኅን (1282 words)


ኪዳኔ ወልደመድኅን ዓርብ ሌሊት ሐምሌ ፪ ቀን ፲፱፻፯ ዓ.ም ቡልጋ በከሰም ወረዳ፤ የለጥ ቀበሌ፤ ልዩ ስሙ ቡሄ አምባ በሚባለው ሥፍራ ላይ ከናታቸው ከወይዘሮ አስካለ ደጀን እና ከአባታቸው ከቀኛዝማች ወልደመድኅን አዩደረስ ተወልደው ነሐሴ ፲ ቀን በጥምቀት ስም ኪዳነ ማርያም ተሰይመው የለጥ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ክርስትና ተነሱ። አባታችው ቀኛዝማች ወልደመድኅን ትውልድ ሃገራቸው ወበሪ ሲሆን፤ በዘመኑ የታወቁ ስመጥሩ ጠበቃ ነበሩ። ከወይዘሮ አስካለም ጋር የተገናኙት ሁለቱም እወረዳው ፍርድ ቤት ኮረማሽ ለየጉዳያቸው ሄደው እንደነበር ይነገራል።   ኪዳነማርያምም እስከ ፲፪ ዓመት እድሜያቸው እዚያው ቡሄ አምባ ከአያታቸው አቶ ደጀን ደብሩ ቤት እንዳደጉና የቄስ ትምህርት ቤት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን እንደተከታተሉ ተጽፏል።  ከዚህ በኋላ አባታቸው ቤት እያደጉ የአማርኛና የግእዝ ትምህርት አጠናቀዋል። 

አካለ መጠን ሲደርሱ በ፲፰ዓ መታቸው በ፲፱፻፳፭ ዓ.ም. አዲስ አበባ በክብር ዘበኛ ደንብ ተቀጥረው ወዲያው በንጉሠ ነገሥቱ ትዕዛዝ ከስድሳ ዘጠኝ አዲስ ወታደሮች ጋር ባሌ ተመድበው እስከ ፲፱፻፳፯ ዓ.ም ድረስ በተራ ወታደርነት ከዚያም በ ሃምሳ ዓለቃና በባሻነት ማእረግ ሲያገለግሉ ከቆዩ በኋላ ኢጣሊያ ኢትዮጵያን ሊወር ሲመጣ በ፲፱፻፳፰ ዓ.ም በምስራቅ ደቡብ በደጃዝማች በየነ መርድ እና በጄነራል አስፋው ወልደ ጊዮርጊስ መሪነት፤ የመጀመሪያ ልጃቸው ዓለማየሁ በተወለደ በዘጠኝ ቀኑ፤ ጥቅምት ፲፩ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓ.ም ከጎባ ወደ ኦጋዴን ዘመቱ። 

በዚህ ጦር ግንባር ፱ ወራት ለበሽሊንዲ፤  ዋቢ ሸበሌ፤ እና የመሳሰሉ ሥፍራዎች  ከ እነ ባላምባራስ አየለ ወልደማርያም ጋር ሆነው ጠላትን ሲከላከሉ ከርመው ወደ ጎባ ተመለሱ።  ከሰኔ ፲፱፻፳፰ ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሚያዚያ ፳፫ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓ.ም ከአሩሲ፤ ከሲዳሞ፤ ከሐረርና ኦጋዴን ወደ ጎባ በሃይል የመጣውን የጠላት ጦር በራሳቸው መሪነት  ሲዋጉ ከርመው፤ መጨረሻ ላይ ተማም ከሚባለው ሥፍራ ላይ በተካሄደው ጦርነት ላይ ማምለጥ በማይቻልበት ኹኔታ በጠላት እጅ ወደቀው ተማረኩ። ጠላትም ለአምስት ወራት በጽኑ እሥራት ከያዛቸው በኋላ፤ በጥር ወር ፲፱፻፴ ዓ.ም ጣሊያን መሳሪያ አስታጥቆ በሽፍን መኪና ከጎባ ወሊሶ አምጥቶ እስር ላይ አዋላቸው። ባሻ ኪዳኔም እዚሁ እስር ቤት እያሉ አብረዋቸው ከታሰሩት መሀል በምስጢር ቃለ መሃላ በመስጠት መቶ ሰዎች አሳብረው እዚያ ያለውን የጠላት ጦር ፈጅተው ለመሸፈት ከወሰኑ በኋላ ወደ ባላምባራስ (በኋላ ደጃዝማች) ገረሱ ዱኪ የሚላክ ሰው በማፈላለግ ላይ እያሉ ጠላት ሰምቶ ኖሮ አጥብቆ ይከታታላቸው ጀመር። ይኼን ሲገነዘቡ ነገሩን አብርደው ሲጠባበቁ ወደ ባላምባራስ ገረሱ የላኩት ብሩ የሚባለው መልክተኛ ጥር ፲፭ ቀን ፲፱፻፴ ዓ.ም በጠላት እጅ ተይዞ ቀኑን ሙሉ ሲመረመር ዋለ።  ባሻ ኪዳኔም በዚያው ዕልት ከምሽቱ ፪ ሰዐት ሲሆን በቃለ መሃላ ያደራጇቸውን ሰዎች በያሉበት እየሄዱ ከነመሳሪያቸው እየሰበሰቡ ሲያከማቹ የጠላትም ዘቦች ነቅተው በተንቀቅ ተሰልፈው ይጠብቋቸው ጀመር።  ባሻ ኪዳኔ ግን ወገኖቻቸውን ሸልሉ ብለው ሲያሸልሉ የጠላት ዘቦች ተደናግጠው እንዲያውም 'እነሱ ሳይተኩሱ አትተኩሱ' የሚል ትእዛዝ አስተላልፈው ይጠባበቃሉ። ባሻ ኪዳኔም በዚህ ጊዜ ቃለ መሓላ ከሰጧቸው ፻ ሰዎች ውስጥ ፶፭ ወታደር ከነመሳሪያው፤ አራት ድግን መትረየስ፤ አስር ሣጥን ጥይት፤ ስድስት ሽጉጥ ከጠላት እጅ ነጥቀው እየተታኮሱ ሲወጡ የጠላት ኃይል ሃያ ወታደርና አንድ መትረየስ ከ ሁለት ሣጥን ጥይት ጋር ብቻ ገንጥሎ ሲያስቀርባቸው የተረፈውን መሳሪያና ወታደሮች ጋር ድል አድርገው ሸፈቱ።  ወዲያውም ኩሳ ኪዳነምሕረት ከሚባል ሥፍራ ላይ ከባላምባራስ ገረሱ ጋር ተገናኙ። 

ከባላምባራስ ገረሱ ጋር ከተቀላቀሉ በኋላም በደንዲ፤ በሶዶ፤ በበዳቄሮ እና በመሳስሉ ሥፍራዎች አርበኝነታቸውን እስከ ጥቅምት ፲፱፻፴፩ ዓ.ም ድረስ ሲያካሂዱ ከቆዮ በኋላ በዳቄሮ ከሚባለው ሥፍራ ላይ ከ ዱካ ዳኦስታና ከ ጄነራል ናዚ ተልኬያለሁ የሚለው ሙሴ ቀስተኛ(ሴባስቲያኖ ካስታኛ) (Sebastiano Castagna) የሚባለው ሰላይ ከሦሥት ባላባቶች ጋራ መጣ። አርበኞቹም ቀደም ሲል በ፲፱፻፴ ዓ.ም ይኼው ሰላይ ወደ ባላምባራስ አበበ አረጋይ ዘንድ ሄዶ የጦሩን ኃይል ከአየ በኋላ ብዙ አርበኛ እንዳስፈጀ ሰምተው ስለነበር እነሱንም እንደዚሁ ለማስፈጀት እንደመጣ ስለተገንዘቡት ባሻ ኪዳኔ ወልደመድኅን በመውዜር ጠመንጃ ሲመቱት 'ማማ ሚያ፤ ኢጣልያ ለዘለዓለም ትኑር ለኢጣሊያ ስል ሞትኩላት' ብሎ ሲናገር በሽጉጥ ራሱን መትተው ከገደሉት በኋላ የለበሰውን ሙሉ ገበርዲን ልብስና ካፖርት እንዲሁም የ ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ን ስዕል ያለበትን የብር ሰዐትና በቅሎውን ከነኮርቻው ማረኩት። እሱም እንደተገደለ አብረውት መጥተው የነበሩት ባላባቶች ለጄነራል ናዚ አስታውቀው ኖሮ ያያ አምሥት ባታሊዮን ወታደርና ሃያ ስምንት አውሮፕላን ወደበዳቄሮ ዘምቶ ተርታውን ለሦሥት ቀን ሲከላከሉ ከቆዩ በኋላ አርበኞቹ ተሸንፈው ጠላትም የሙሴ ቀስተኛን እሬሳ አንስቶ ወሰደ። አርበኞቹም ከዚያ ሥፍራ ሸሽተው ሶዶ ላይ እንደገና ልስምንት ቀን ተዋጉ። 

ባሻ ኪዳኔ ከባላምባራስ ገረሱ ጋር ከሙሴ ቀስተኛ የተማረከውን አላስረክብም በማለታቸውና በሌላም ምክንያቶች ባለመስማማታቸው፤ በኅዳር ወር ፲፱፻፴፩ ዓ.ም. አባሎቻቸውን አስከትለው ወደ ትውልድ አገራቸው ወደቡልጋ ተጉዘው በአሥራ ሁለት ቀናቸውም ቡልጋ ገቡ። እዚሁም ከፊታውራሪ ኃይለማርያም ማናህሌ እና ከፊታውራሪ ተረፈ ማናህሌ ጋር ተቀላቅለው እስከ መጋቢት ፲፱፻፴፩ ዓ.ም. ድረስ በውሽንግር፤ ጨፌ ዶንሳ ምሽግ፤ ነጭ ድንጋይ ምሽግ፤ ልዝብ ድንጋይ ከተባሉ ቦታዎች ላይ ከጠላት ኃይል ጋር ሲዋጉ ከርመው በመጋቢት ወር በሃገሩ ላይ ገብቶ በነበረው የ እንቅጥቅጥ በሽታ በጽኑ ታመው ከልዝብ ድንጋይ ምሽግና ቤቶች ነጭ ድንጋይ ጦስኝ ምሽግ ከወደምስራቅ ኮረማሽ መካከል ታመው ተኙ:: ወዲያው በሰኔ ወር ሦሥት አምባ ላይ ሰፍረው ሳሉ ጠላት በሦስት አምባ፤ በወይን አምባ እና በጦስኝ በኩል ወርዶ ሲከባቸው ባሻ ኪዳኔ ገመምተኛ ስለነበሩ መሮጥ አቅቷቸው ‘ተማረክ’ እያለ የከበባቸውን የጠላት ጦር እየተከላለከሉ ጫካ ገቡ የጠላትም ወታደሮች የገቡበት ጠፍቶባቸው ሲፈልጉ ባሻ ኪዳኔ ጎርፍ በጀለጣት ዛፍ ተንጠልጥለው ደፍጠው ሲጠባበቁ ጠላት ጫካውን በእሳት ነበልባል ግራና ቀኙን ሲያቃጥልው እሳቸው ያሉባት ሳትቃጠል ሊተርፉ ቻሉ። ከሦስት ቀንም በኋላ ጠላት ለቆ ሲሄድ ባሻ ኪዳኔ ከጅረት ወርደው ውሃ ሲጠጡ ደክመው ወድቀው ሳሉ ወንድማቸውና ሌሎች ሲፈልጓቸው በጥይት ያሉበትን አሳወቋቸውና መጥተው በቃሬዛ አዛውሯቸው፡ 

ከዚህ በኋላ ክረምቱን ቡልጋ ውስጥ በነጭ ድንጋይ፤ ፍልፍል አፈር፤ ጦስኝ ምሽግ፤ በመስኖ ከነደጃዝማች ኃብተ ሥላሴ በላይነህ፤ ከነፊታውራሪ በለጠ ሳሴና ፊታውራሪ አጎናፍር ሌሎችም ስመጥሩ የቡልጋ ልጆች ጋር ሆነው ጠላትን ሲያጠቁና ሲከላከሉ ቆይተው በመስከረም ፲፱፻፴፪ ዓ.ም በሰገሌ በኩል ተጉዘው ገሊላ ከሚባል ሥፍራ ላይ ከራስ አበበ አረጋይ ጋር ሲቀላቀሉ ባሻ ኪዳኔ የግራዝማችነት ማዕረግ ተሾሙ። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ከ”ጊዲዮን ፎርስ” (Gideon Force) ጋር ወደጎጃምና ወደጎንደር እስከዘመቱ ፲፱፻፴፫ ዓ.ም ድረስ ከራስ አበበ ጋር ጠላትን በየቦታው ሲዋጉ በአርበኝነት ቆዩ። ከብዙ ከተለያዩ ውጊያዎችና ጀብዱዎች በኋላ በየካቲት ፲፱፻፴፫ ዓ.ም መሶቢት ከሚባለው ቦታ ላይ በመሪነት የጠላትን ጦር ድል አድርገው ወደዋናው ሰራዊት ከተቀላቀሉ በኋላ ራስ አበበ የቀኛዝማችነት ማዕረግ ሾሟቸው። 

ቀኛዝማች ኪዳኔ በ፲፱፻፴፫ ዓ.ም ዳውንት፤ ተንታ፤ ደብረታቦር ላይ የሰፈረውን የጣሊያን ወታደሮች ከጓደኞቻቸው ጋር እየማረኩ በመስከረም ፲፱፻፴፬ ዓ.ም ጉማራ ላይ ከፍ ያለ ውጊያ አድርገው ጠላትን ድል አደረጉ። 

ኅዳር ፲፪ ቀን ፲፱፻፴፬ ዓ.ም ከጎንደር ወደ ቁልቋል በር ላለው የጠላት ጦር ስንቅ ሊያቀብል ከባድ መኪና፤ ታንክና መድፍ ጭኖ የመጣውን ኃይል ገጥመውት አሸንፏቸው ስንቁን አቀብሎ ሲመለስ እንደገና አጥቅተው ብዙ ባንዳዎች ገደሉ። 

ኅዳር ፲፰ ቀን ፲፱፻፴፬ ዓ.ም ጎንደር ከተማ ውስጥ ጄነራል ናሲ ከብዙ ሺህ ሰራዊት ጋር አካባቢውን በሽቦ አጥሮ በሽቦው ውስጥና ውጭ ፈንጂ ቦንብ ከምሱሩን ነቅሎ ቀብሮበት ሳለ፡ በእንግሊዛዊው ማጆር ዳግላስ መሪነት ቀኛዝማች ኪዳኔ ይኼንኑ የተቀበረ ቦንብ በመቀስ እየቆረጡ ሌሊቱን ተጉዘው ምሽጉ ሲደርሱ ከበው ሲነጋ ተኩስ ተከፈተ። ጠላትም ከከፍተኛ ተራራ ላይ ወደታች ወደነ ቀኛዝማች ኪዳኔ በቦንባርድና ከባድ መትረየስ ሲያጠቃቸው በተራራው ሥር ሥር አድርገው ወደ ጎንደር ከተማ የሚወስደውን መንገድ ላይ ሲደርሱ ከጎንደር ከተማ የሚመጡ አስመስለው ከኋላው በጨበጣ የጅ ቦንብ እየጣሉ ብዙ ወታደሮች ፈጁ። እንዲሁም ሦስት ቦንባርድና ስድስት የውሐ መትረየስ ማርከው ምሽጉን አስለቅቀው ከያዙ በኋላ ጀነራል ናሲ ወዳለበት ወደጎንደር ቀጠሉ። ጎንደርም ሲገቡ በአሶ ቤተክርስቲያን ምሽግ በኩል ፋሲል ግንብ ምሽግ ሲደርሱ ምሽጉን ለመድፈር የጅ ቦንብ ምሽጉ ላይ በብዛት ሲጥሉ ጠላት ተሸንፎ የሰላም ባንዲራ አውጣ። በዚህ ጊዜ ቀኛዝማች የጠላትን ወታደሮች ለመማረክ ሲጠጉ የነቀሉትን የጅ ቦንብ እረስተውት ኪሳቸው ከተቱ። ወዲያው አራት መቶ ሰማንያ አራት (፬፻፹፬) ነጮች በጃቸው ተማርከው በከተማው የሚገኙትን የዓረብ ተወላጆች ሱቅና ገንዘብ እንዳይዘረፍ በወታደር አስጠብቀው ከምሽቱ ሁለት ሰዐት ላይ ተማራኪዎቹን ለ ማጆር ዳግላስ አስረክበው እረፍት ሲያደርጉ ቀን በ ዘጠኝ ሰዐት ገደማ የነቀሉት ቦንብ ከምሽቱ ሁለት ሰዐት ላይ ከኪሳቸው ላስቲኩ ተነቅሎ ሳይፈነዳ ተወርውሮ ሲጣል ፈነዳ።

የጎንደርም ጦርነት ኅዳር ፲፱ ቀን ፲፱፻፴፬ ዓ.ም ተፈጽሞ ባራት ቀኑ አልጋወራሹ መጥተው ወዲያው ከሳቸው ጋር ወደወሎ ጠቅላይ ግዛት እንዲሄዱ ተደርጎ እዚያው ብዙ ወታደርና መሳሪያ ለመከላከያ ሚኒስቴር አስረከቡ።

የካቲት ፲፰ ቀን ፲፱፻፴፬ ዓ.ም የፊታውራሪነት ማእረግ ተሰጥተው መጀመሪያ በ ወረዳ አስተዳዳሪነት ከዚያም በ፲፱፻፴፮ ዓ.ም የየጁ፤ የዋድላ ደላንታ፤ የመቂት፤ የሸደሃና የዳውንት ብሔራዊ ጦር አዛዥና የጠቅላይ ግዛቱ ጦር አማካሪ ከዚያም እስከ ፲፱፻፵፫ ዓ.ም ድረስ በወሎና በከፋ ውስጥ አውራጃ አስተዳዳሪነት ተመድበው ሲያገለግሉ ቆዩ።

ከፋ ውስጥ እንደተሾሙ (፲፱፻፵፫ ዓ.ም) ከጠቅላይ ገዢው ጋር ባለመስማማታቸው ተሽረው ንጉሠ ነገሥቱ ከስልጣን እስከወረዱ ድረስ በእስራትና በግዞት ሐያ ሦስት ዓመት ሙሉ ለሃገሩ እንዳልተጋደለ፣ በአርበኝነት ደሙን እንዳላፈሰሰ፣ ለኢትዮጵያ ነጻነት መስዋዕት እንዳልሆነ ተቆጥረው፣ ንጉሠ ነገሥቱ ለቅርብ ሎሌአቸው አድልተው ደጃዝማች ኪዳኔን ከሀገር አገልግሎት አስወገዷቸው። 

ንጉሠ ነገሥቱ ከስልጣን ከወረዱ በኋላ ክቡር ደጃዝማች ኪዳኔ በመላ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ሊቀመንበርነት ተመርጠው ሲያገለግሉ ከቆዩ በኋላ ሃገራቸውንንና  ማኅበሩን ወክለው ሮማ ላይ በተካኼደው የዓለም አቀፍ ጸረ ኑክሊየር መሣሪያ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ሲጓዙ መስኮብ (Moscow) ላይ ጥቅምት ፱ ቀን ፲፱፻፸፪ ዓ.ም. በተወለዱ በስልሳ አራት ዓመታቸው አረፉ። ቀብራቸውም መንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ጥቅምት ፲፭ ቀን ፲፱፻፸፪ ዓ.ም. ተከናውኗል።

ክቡር ደጃዝማች ኪዳኔ ወልደመድኅን በ ፲፱፻፵፱ ዓ.ም. በተወለዱበት አጥቢያ በቡልጋ የየለጥ ቅዱስ ጊዮርጊስን ቤተ ክርስቲያን በግል ያሠሩ ሲሆን፤ በ ፲፱፻፷፬ ዓ.ም .ከልደት እስከ ሞት የተባለች አጭር ኃይማኖታዊ፤ መንፈሳዊና የፍልስፍና መጽሐፍ ደርሰው አሳትመዋል።

በጠቅላላው ፲ ኒሻኖችን ተሸልመዋል።




#Article 240: ንግሥት ዘውዲቱ (740 words)


ግርማዊት ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ቅዳሜ ሚያዝያ ፳፪ ቀን ፲፰፻፷፰ ዓ.ም  ከሸዋ ንጉሥ ምኒልክና ከወረኢሉ ተወላጅ ከወይዘሮ አብቺው በተጉለትና ቡልጋ አውራጃ ጅሩ እነዋሪ  ከተማ ተወለዱ። ሐምሌ ፲፩ ቀን ሰኞ ሥርዓተ ጥምቀት ተፈጽሞላቸው፣ የክርስትና ስማቸው አስካለ ማርያም ተባለ። ግርማዊት ንግሥተ ነገሥት ዘውዲቱ ለዳግማዊ ምኒልክ ሦስተኛ ልጅ ሲሆኑ ከልጅ ኢያሱ ቀጥለው መኳንንትና ሕዝቡ መክሮና ዘክሮ በምርጫ በኢትዮጵያ ዙፋን ላይ የተቀመጡ ብቸኛዋ ንግሥት ናቸው።

አባታቸው የሸዋው ንጉሥ ምኒልክ (በኋላ ዳግማዊ ዐፄ) ዘውዲቱ የስድስት ዓመት ሕጻን እንደነበሩ ለአሥራ ሁለት ዓመቱ የዐፄ ዮሐንስ ልጅ ለአርአያ ሥላሴ ዳሩዋቸው። ጋብቻቸውም ጥቅምት ፲፫ ቀን ፲፰፻፸፭ ዓ.ም. በተክሊልና በቁርባን ተፈጸመ፡ የሠርጉም ማማርና የሽልማቱ ብዛት ሊነገር አይቻልም። ልጅ ኢያሱ መስከረም ፲፯ ቀን ፲፱፻፱ ዓ.ም ከስልጣን ሲወርዱ፤ መኳንንቱና ሕዝቡ መክሮና ዘክሮ በምርጫ ወይዘሮ ዘውዲቱን ግርማዊት ንግሥተ ነገሥት፤ ራስ ተፈሪ መኮንንን አልጋ ወራሽ እና ባለሙሉ ሥልጣን እንደራሴ እንዲሆኑ ወስነው መስከረም ፳፩ ቀን ግርማዊት ዘውዲቱ፣ ንግሥተ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ተብለው ነገሡ። በመኳንንቱም ምክር መሠረት ጳጳሱና እጨጌ ወልደጊዮርጊስ ኢያሱን የተከተልክ፣ ያነገሥናትን ዘውዲቱንና ራስ ተፈሪን የከዳህ፣ ውግዝ ከመአርዮስ እያሉ በአዋጅ አወገዙ፡ 

ከዚህ በኋላ በጥቅምት የሰገሌ ጦርነት ከተደረገ በኋላ የዘውድ በዓሉ የካቲት ፬ ቀን ፲፱፻፱ ዓ.ም እንዲሆን ታዞ፣ ለዘውዱ በዓል በኢትዮጵያ አዋሳኝ ያሉት የእንግሊዝ ሱዳንና የእንግሊዝ ሱማሌ ገዥዎች፤ የፈረንሳይ ሱማሌ ገዥ እና በኢትዮጵያም ታላላቅ ራሶች እንዲሁም የየአውራጃው ገዥዎች በተገኙበት በዕለተ እሑድ አባታቸው ባሠሩት በትልቁ ደብር በመናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በሊቀ ጳጳሱ በአቡነ ማቴዎስ እጅ ቅብዐ መንግስት ተቀብተው የንጉሠ ነገሥቱን ዘውድ ጫኑ። ከዚህም በኋላ እንደ ሥርዓተ ንግሡ ሕግ፤ ንግሥተ ነገሥት ዘውዲቱ በአባታቸው ዙፋን ተቀምጠው መንገሣቸውን፤ ደጃዝማች ተፈሪም ራስ ተብለው አልጋ ወራሽና ባለሙሉ ሥልጣን እንደራሴ መሆናቸውን በቤተ ክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ በተሰበሰበው ሕዝብ ፊት አዋጅ ተነገረ። 

የንግሥተ ነገሥታትን ሥልጣን ለማሳወቅ ሲባል ራስ ወልደ ጊዮርጊስ የካቲት ፲፩ ቀን ራስ ወልደ ጊዮርጊስን ንጉሠ ጎንደር ብለው አንግሠው ዘውድ ደፉላቸው። እንደዚሁም መስከረም ፳፯ ቀን 1921 ዓ.ም. ብዙ መኳንንትና መሣፍንት፤ ሊቃውንትና ጳጳሳት ባሉበት የኢትዮጵያ መንግሥት አልጋ ወራሽ ራስ ተፈሪ መኮንንን አዲስ አበባ መካነ ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን፣ ንጉሥ ተፈሪ ተብለው ዘውድ ተጫነላቸው።

ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ በነገሡ በአሥራ ሦሥት ዓመት ተኩል በ፶፬ ዓመት ዕድሜያቸው ረቡዕ መጋቢት ፳፬ ቀን ፲፱፻፳፪ ዓ.ም በ ፰ ሰዓት ዐረፉ። የሞታቸው ዜና እንደተሰማም በከተማው የሐዘን ጥላ አጠላበት። አባታቸው ዐፄ ምኒልክ በተቀበሩበት በታዕካ ነገሥት በዓታ ቤተ ክርስቲያን ተቀበሩ።

የዓለም መንግሥታት ማኅበር (ሊግ ኦፍ ኔሽንስ) ጠቅላላው ጉባዔ በ28 ሴፕቴምበር በ1923 እ.ኤ.አ. (መስከረም 17 1916 ዓ.ም.) ስብሰባውን ቀጠሉና የስድስተኛውን ኮሚሲዮን ማስታወቂያ ተደግፎ ኢትዮጵያ ማኅበርተኛ እንድትሆን ፈቃዱ መሆኑን አስታወቀ። በዚህ ጊዜ ዋናው መልእክተኛ ደጃዝማች ናደው የደስታ ስሜታቸውን ለመግለጥ ንግግር ማድረጊያው ስፍራ ላይ ቆመው የሚከተለውን ዲስኩር ተናገሩ፡፡

ክቡራን ሆይ፤

ጠቅላላው ጉባኤ በበጎ ፈቃደኝነትና በትክክለኛ ፈራጅነት፣ በጥልቅ አስተሳሰብ መርምሮ ወደ ማኅበሩ ስለመግባት ያቀረብነውን ጥያቄ ስለ ተቀበለው፣ የኢትዮጵያ መልእክተኞች በግርማዊት ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱና በልዑል ራስ ተፈሪ መኰንን የኢትዮጵያ መንግሥት አልጋ ወራሽና ባለ ሙሉ ሥልጣን እንደራሴ ስም፣ እንዲሁም በመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ስም ምስጋና ያቀርባሉ።

የሰውን ልጅ ወንድማማችነት የመመሥረት ዓላማ ባለው ውሳኔያችሁ የተሰማንንም ልባዊ ደስታ እንድገልጽላችሁ ይፈቀድልኝ ዘንድ እለምናለሁ። ኢትዮጵያ ባለፈው የጀግንነት ታሪክና በከፍተኛ ሥልጣኔዋ የምትኮራ አገር መሆንዋ፣ የዘመናዊ ድርጅቶች ከሚያስገኙላትም ፍሬ ተካፋይ ለመሆን ብርቱ ጥረትና ሙሉ ፈቃደኛነት እንዳላት የታወቀ ነው።

መንግሥታችንም ይህን ጥረት ወደ መልካም ግብ ለማድረስ የዓለም መንግሥታትን አንድነትና ኅብረት የሚያስፈልግ መሆኑን በጥብቅ ያምንበታል።

ልዑል አልጋ ወራሽ ራስ ተፈሪ መጋቢት ፲፮ ቀን ፲፱፻፲፮ ዓ.ም በግርማዊት ንግሥት ዘውዲቱ ፈቃድ ስለ ባሮች ነፃነት አንድ ደንብ አወጡ። ደንቡ «ስለ ባሮች አስተዳደርና ነፃነት የቆመ ደንብ» የሚል አርእስት ተሰጥቶትና እንደ መጽሐፍ ሆኖ በልዑል አልጋ ወራሽ ማተሚያ ቤት ታትሞ ወጣ። መጽሐፉ ባለ 10 ገጽ ሲሆን የደንቡ ቃል በ45 ቁጥሮች ተመድቧል፡፡

ይህ መጽሐፍ ለሕዝብ ይሸጥ ነበርና መጽሐፉን ገዝቶ ያነበበው አብዛኛው ሰው «የሥልጣኔ እርምጃ ነው» እያለ አልጋ ወራሽን አመሰገነ።

ባለብዙ ባሮች የሆኑት ሰዎች ግን በልባቸው ቅሬታ ገብቶ አዘኑ። ለምሳሌ የጦር ሚኒስትሩ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ በዚያው ሰሞን የልባቸውን ቅርታ በጨዋታ ላይ ሲናገሩ «እንግዲህ ምን አለ አልታየ ወርቅ (ሚስታቸው) ወደ ወንዝ እየወረደች ውሀ መቅዳት ነው፣ እኔም እንጨት እየፈለጥሁ አቀርብላታለሁ» አሉ እየተባለ ሲወራላቸው ከረመ፡፡

ከእንግሊዝ አገር የመጣው የአፄ ቴዎድሮስ ዘውድ ሐምሌ 4 ቀን 1917 ዓ.ም ቅዳሜ ለግርማዊት ንግሥት ዘውዲቱ ተመለሰ። በዚህም ጊዜ የተፈጸመው ሥነ ሥርዓት እንደሚከተለው ነበር፤

ከጧቱ በ4 ሰዓት የግቢ ሚኒስትር ደጃዝማች ወልደ ገብርኤል በሻህ በጦር ልብስ ያጌጡ ጭፍሮች አስከትለውና በአራት ፈረሶች የሚሳብ ሠረገላ አሲዘው ከአቶ ሣህሌ ፀዳሉ ጋር ወደ እንግሊዝ ሌጋሲዮን ሄዱ። የእንግሊዝ መንግሥት ሚኒስትር ሚስተር ቻርልስ ቤንቲንክም ዘውዱን በሠረገላው ላይ አስቀመጡትና ሁሉም ዘውዱን አጅበው ወደ ቤተ መንግሥት መጡ።

ግርማዊት ንግሥት ዘውዲቱና ልዑል አልጋ ወራሽ በቤተ መንግሥታቸው ውስጥ በተለይ በተሰናዳው ስፍራ ከመኳንንት ጋር ተቀምጠው ይጠብቁ ነበር። የግቢ ዘበኞችም በግቢው ውስጥ በቀኝና በግራ ተሰልፈው ነበርና ሠረገላው በሰልፉ መካከል አልፎ ከመንግሥት ፊት ደረሰ። እዚያም አንድ ጠረጴዛ ተዘጋጅቶ ነበርና ሚስተር ቤንቲንክ ዘውዱን ከሠረገላው አውርደው በጠረጴዛው ላይ አስቀመጡትና ከዚህ ቀጥሎ ያለውን ቃል ተናገሩ፤

ግርማዊት ሆይ በንግሥት ቪክቶሪያ መንግሥት በ1860 ዓ.ም ከመቅደላ የተወሰደውን የአፄ ቴዎድሮስን ዘውድ የታላቂቱ ብሪታንያና የአየርላንድ፣ ከባሕር ማዶ ያሉት ግዛቶች ንጉሥና የህንድ ንጉሠ ነገሥት በሆኑት በግርማዊ ጌታዬ በንጉሡ ትዕዛዝ ለግርማዊት ንግሥት በማክበር እመለስሁ።

(መርስዔ ኀዘን ወ/ቂርቆስ፣ የሐያኛ ክፍለ ዘመን መባቻ፣ 2000)




#Article 241: የኢትዮጵያ አየር መንገድ (344 words)


                                         

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መሥሪያ ቤቱ በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ የሆነ የኢትዮጵያ ብሔራዊ አየር መንገድ ድርጅት ነው። አየር መንገዱ ከቀድሞው ትራንስ ወርልድ ኤይርዌይስ/ Transworld Airways (TWA) ጋር በጋራ የተመሠረተ ሲሆን አስተዳደሩ በአሜሪካኖች እጅ ነበር፤ ድርጅቱ ታኅሣሥ ፳፩ ቀን ፲፱፻፴፰ ዓ/ም ተመሥርቶ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓለም አቀፍ በረራውን መጋቢት ፴ ቀን ፲፱፻፴፰ ዓ/ም ከአዲስ አበባ ተነሥቶ ካይሮ ድረስ አከናወነ። 

አየር መንገዱ ሲመሠረት ከአሜሪካ ወታደራዊ ኃይል የተገዙና በሁለተኛው ዓለም ጦርነት ያገለገሉ አምስት ዲ.ሲ. ፫ (DC 3-C47) አውሮፕላኖች ነበሩት። በዓለም ዙሪያ በአፍሪካ፤ በእስያ፤ በአውሮፓ እና በአሜሪካ ክፍለ አህጉራት ወደ ፶ የመንገደኛና የጭነት አገልግሎት ሲሰጥ፤ በሀገር ውስጥ ደግሞ በአሁኑ ጊዜ ፲፮ መድረሻዎችን ያገለግላል። ዋና የጣቢያው ማዕከል በአዲስ አበባ የሚገኘው ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ነው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የራሱ የአውሮፕላን አብራሪዎች ማሰልጠኛ ትምሕርት ቤት ሲኖረው የግል አብራሪ እና የንግድ አውሮፕላን አብራሪ ፈቃድ በመስጠት የሀገር ልጆችንም ሆነ የውጭ ዜጎችን በማሰልጠን እስከ አርባ ዓመት ልምድ አለው። እንዲሁም ለብዙ የአፍሪካ ሀገር ብሔራዊ አየር መንገዶችና የግል አውሮፕላኖች የጥገና አገልግሎት ይሰጣል።

አየር መንገዱ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ ፌደራላዊ መንግሥት የተያዘ የኢትዮጵያውያን ሀብት ሲሆን፤ በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ ለሽያጭ እና ለግዢ እንዲሁም ለብድር አመቺ እንዲሆን ተብሎ በአየር መንገዱ ሙሉ ቁጥጥር ሥር በኬይማን ደሴቶች የተመሠረተ ድርጅት ባለቤት ነው። 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ለመንገደኞች አገልግሎት አዲሱንና ዘመናዊውን የቦይንግ ፯፻፹፯ (Boeing 787) ድሪምላይነር አውሮፕላን በማዘዝና ጥቅም ላይ በማዋል ከአፍሪካ የመጀመሪያው አየር መንገድ ሊሆን ነው። የታዘዙትን አሥር ቦይንግ ፯፻፹፯ ድሪምላይነር (Boeing 787 Dreamliner) አውሮፕላኖች እ.አ.አ. በ2009 መጨረሻ ላይ እንደሚረከብና ጥቅም ላይ እንደሚያውል ይጠበቃል። ከዚህ በተጨማሪ አየር መንገዱ 8 ቕ400 አውሮፕላኖች ከቦምባርዲየር (Bombardier ለሀገር ውስጥ መንገደኞት አገልግሎት አዟል።

በ፲፱፻፹፱ ዓ.ም. ዓለማየሁ በቀለ በላይነህ፣ ማትያስ ሰሎሞን በላይ እና ሱልጣን አሊ ሁሴን የተባሉ ሦስት ኢትዮጵያውያን፣ ከአዲስ አበባ ተነስቶ በናይሮቢ በኩል ወደ ቦምቤይ በረራ ላይ የነበረውን የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ በረራ ቁ. ፱፻፷፩ በዓየር ላይ ጠለፉ። በጠላፊዎቹም ትእዛዝ ወደ አውስትራሊያ ሲያመራ ነዳጅ በመጨረሱ ምክንያት በረራው በሕንድ ውቅያኖስ ላይ ወደምትገኘው የቆሞሮስ ደሴት ተጠግቶ ከደሴቷ ግማሽ ኪሎሜትር ውቅያኖሱ ላይ ሊያርፍ ሲሞክር የዓየር ተሽከርካሪው ተሰባብሮ ፈነዳ። ከመንገደኖቹም ውስጥ፣ ጠላፊዎቹን ጨምሮ መቶ ሃያ ሦሥት ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ። ከሞቱት መንገደኞች አንዱ፣ ኬንያዊው የፎቶ-ጋዜጠኛ ሞሐመድ አሚን ነበር።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ፬፻፱ ጥር ፲፯ ቀን ፳፻፪ ዓ/ም ከቤይሩት በተነሳ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ባልታወቀ አደጋ ምክንያት በሜድትራኒያን ባሕር ላይ ውድቆ የሰመጠ በረራ ነበር።




#Article 242: አይሳክ ኒውተን (194 words)


ሰር አይሳክ ኒውተን ከጃንዩዌሪ 4 ቀን 1663 እ.ኤ.አ. እስከ ማርች 31 ቀን 1727 እ.ኤ.አ. የኖረ እንግሊዛዊ የፊዚክስ፤ የሒሳብ፤ የስነ ክዋክብት፤ የስነ መለኮት፤ የተፈጥሮአዊ ፍልስፍና እና ጥንት የነበረው የአልኬሚ ምሁር ነበረ። ምናልባትም ኒውተን በጣም ከሚታወቅባቸው ነገሮች ውስጥ ሶስቱ የኒውተን ሥነ-እንቅስቃሴ ህጎች ፤ የኒውተን የግስበት ቀመር፤ ካልኩለስ ለተባለውን የሒሳብ ክፍል መጀመር (ይህን ክብር ከጀርመናዊው ምሁር ከጎትፍሪድ ሌብኒትዝ ጋር ይጋሩታል)፤ ስለ ብርሃንና ስለሚይዛቸው ቀለማት ያገኘው ግኝት ይጠቀሳሉ። በተጨማሪም ኒውተን የእንቅስቃሴ ህጎችን በመጠቀም የፕላኒቶች (ፈለገ ሰማያት) እንቅስቃሴ በነዚሁ ህጎች እንደሚመሩ በማሳየት እና የሌላ ምሁር የጃናንስ ኬፕለር የፕላኒቶች እንቅስቃሴ ህግ ጋር እንደሚጣጣም በማሳየት ፤ በፊት ይታመንበት የነበረውን መሬት የሁሉም ነገሮች ማዕከል ናት የሚባለውን ሐሳብ ትክክል እንዳልሆነ በሳይንሳዊ መንገድ አሳይቷል።

ሰር አይሳክ ኒውተን በ፬ኛ ቀን ፩፮፬፪ አመተ ምህረት ተወለደ። አባቱ ከመወለዱ በፊት በመሞቱ እናቱ ከሌላ ባል ጋር ኮበለለች። ስለዚህ ከአያቱ ጋር መደግ ጀመረ።  ከ ፩፪ እስከ ፩፬ አመት ድረስ ኒውተን በግራንተም ግራመር ት/ቤት ውስጥ ተማረ። ኒውተን ገበሬ መሆን ባለመፈለጉ ወደ ተሪኒቲ ኮሌጅ ካምበሪጅ ገባ። ዲግሪውን በ፩፮፭፱ ጨረሰ። ነገር ግን በ፩፮፮፮ በነበረው ወረርሽ ምክንያት ከኮሌጁ መሰደድ ነበረበት። በቀጣዩ አመት ተመለሰ። 
በቀጣዮቹ አመታት ስለ ሥነ-እንቅስቃሴ ህጎች፣ ካልኩለስ እናም ስለ ነጭ ብርሃን እና ስለሚይዛቸው ቀለማት ያገኘው ግኝት ይጠቀሳሉ። በማርች ፫፩ ቀን ፩፯፪፯ ከዚህ አመት በሞት ተለየ ኒውተን ራሳቸውን በቀላሉ ከሚገልጹ ተመራማሪዎች አንዱ ነበር።።

  




#Article 243: የዶሮ ጉንፋን (146 words)


የዶሮ ጉንፋን ወይም ኤቭያን ፍሉ (Avian Flu) ኢትዮጵያን እንደ ማንኛውም ኣገር ያሰጋታል። ይህ የወፍ ኢንፍሉኤንዛ ወይም የዶሮ ጉንፋን እያጠቃ ያለው ኣንዳንድ የሩቅ ምሥራቅ እስያ ኣገሮችን ቢሆንም ወደ ኤውሮፓና ኣፍሪቃ መስፋፋት ጀምሯል። እስካሁን (፳፻ ዓ.ም.) በሽታው የገደላቸው ሰዎች ብዛት ከ300 ያነሱ ሲሆን በሽታውን ለመቆጣጠር ከ150 ሚሊዮን ዶሮዎች በላይ ተፈጅተዋል። 

ያለውም ዋና ስጋት ቫይረሱ ከታመመ ዶሮ ሰው ጭምር ስለሚይዝና እራሱንም መቀያየር ስለሚችል ቀስ በቀስ ጉንፋኑ ከሰው ወደ ሰው የመተላለፍ ችሎታ ኣፍርቶ ሕዝብ እንዳይፈጅ ነው። ከዚህ በፊት ኢንፍሎኤንዛ በመደጋገም በዓለም ላይ ብዙ ሚሊዮን ሕዝቦች ገድሏል። ስለዚህ ስለበሽታው ሕዝቡ በሚገባ ማወቅና መዘጋጀት ኣለበት። በሽታው ኣንድ ቦታ ያሉትን ዶሮዎች በ48 ሰዓታት ሊፈጅ ይችላል። ኣንዳንድ ኣእዋፍ ወደተለያዩ ኣገሮች ስለሚበሩ በሽታውን መከላከል ቀላል ባይሆንም የመከላከያ ክትባት ኣለ። ለሰው መድኃኒትና መከላከያ የመሥራትም ጥድፊያ ቀጥሏል። በብዛት የሞቱ ኣእዋፍ ሲታዩ ለባለሥልጥኖች መንገር እንጂ ኣለመነካካትና ድመቶች እንዳይበሏቸው መከላከል ያስፈልጋል። በሽታው ካለበት ኣገር ዶሮን ኣለማስገባትና የጓሮ ዶሮን ኩስ ማጸዳዳት ጠቃሚ ናቸው። ዶሮንና እንቁላልን ለመብላት በሚገባ ማብሰል ቫይረሱን ይገድለዋል።




#Article 244: ሶፊያ ሮታሩ (104 words)


ሶፊያ ሮታሩ (ሞልዶቭኛ፦ Sofia Mihailovna Rotaru-Evdokimenko /ሶፊያ ሚሃይሎቭና ሮታሩ-ኤቭዶኪመንኮ/ ፤ ዩክራይንኛ፦ Софія Ротару) ሩሳዊት፣ ኡክራይናዊት፣ ሞልዶቫዊት እና ቀድሞ ሶቭየት ዘፋኝ፣ ሙዚቀኛ፣ ጭፍረኛ፣ ተዋናይና ደራሲ ነች። ስለ ድምጿና በምሥራቅ አውሮፓ በተለይ ትታወቃለች። 

በዜና ማሰራጫ በኩል «የዘመናዊ ሙዚቃ ንግሥት» ተብላ ተሰይማለች። በ1986 እ.ኤ.አ. ስመ ጥሩ ማእረግ «የሶቭየት ህብረት ሕዝብ ዛፋኝ» የተቀበለች መጀመርያ ዘመናዊ ሴት ዘፋኝ ሆነች፤ በ2000 እ.ኤ.አ. ደግሞ የ20ኛው ክለ ዘመን ዘፋኝ ተባለች። 

ዛሬ ሶፊያ ሮታሩ የዩክሬን ዜጋ ሆና በክሪሜያና በያልታ ክብር ኗሪ ነች። ዋና መኖርያዋ ያልታ ሲሆን ደግሞ ቤቶች በመስኮብ፣ ክዬቭና ባደን-ባደን አሏት። በርካታ ከፈትኛ ሽልማቶችም አሏት፤ ከነዚህም መካከል የዩክሬን ሶቭዬት ሪፐብሊክ ክብር ዘፋኝ፣ የዩክሬን ሕዝብ ዘፋኝ፣ የሞልዳቪያ ሶቭዬት ሪበብሊክ ሕዝብ ዘፋኝ፣ ወዘተ ናቸው። 




#Article 245: ጳውሎስ ኞኞ (256 words)


ደራሲ ጳውሎስ ኞኞ ኅዳር 11 ቀን 1926 ዓ.ም ቁልቢ አካባቢ ተወለደው ድሬዳዋ ከተማ አደጉ። በጣሊያን ወረራ ምክንያት ትምህርታቸውን ከ4ኛ ክፍል በላይ ለመቀጠል አልቻሉም ነበር። ብልህ አዕምሮና የፈጠራ ችሎታ የነበራቸው ሰው ስለነበሩ፤ በልጅነታችው የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ጣሊያንን ሲገድሉ ወይንም ሲማርኩ ሥዕል በመሣል ያሳዩ ነበር። ጳውሎስ ካላቸው የጽሑፍ ጥማት የተነሳ የ«ድምጽ ጋዜጣ» አዘጋጅ በመሆን የብዕር ድምጻቸውን ያሰሙ ነበር። ጋዜጦች ላይ ከጽሑፍ አቅራቢነት እስከ አዘጋጅነት ለበርካታ ዓመታት ሠርተዋል። በተለይ «አንድ ጥያቄ አለኝ» በሚለው የአዲስ ዘመን ጋዜጣ አምዳቸው ላይ ብዙ ታዋቂነትን አግኝተዋል።  አቶ ጳውሎስ ኞኞ ከ1955 ዓ.ም ጀምሮ ለኢትዮጵያ ስነ ጽሑፍ ዕድገት የነበራቸውን ተሰጥኦ በአግባቡ በሥራ ላይ ያዋሉ እውቅ ጋዜጠኛና ደራሲ ነበሩ። እኚህ ታዋቂ ሰው በተወለዱ በ58 ዓመታቸው ሞቱ።

አቶ ጳውሎስ የጌታችው ሚስቶች በሚል ርዕስ ያሳተሟትን መጽሐፍ፤ «ከታተመችበት ወር አንሥቶ ላንድ ዓመት የመጽሐፌ መብት የግሌ ነው፡ ከአንድ ዓመት በኋል መብቱ የማንኛውም ኢትዮጵያዊ ይሁን፡ ከወሰንኩት ጊዜ በኋላ አሳትሞ ለመሸጥ የፈለገ ሁሉ ከድርሰቴ ሳይቀንስም ሆነ ሳይጨምር ሊያራባው ይችላል።  ስሜን ሳይሰርዝ 'አሳታሚውን እገሌ' ብሎ ማንም ኢትዮጵያዊ ከፈለገ እንዲያራባት የደራሲነት መብቴን ልቅቄአለሁ፡ አሳታሚው የግሉን የመግቢያ ሐተታ በስሙ ቢጽፍ እኔም ሆንኩ ወራሼ አንቃወምም።» ብለዋል

ከጋዜጠኝነታቸው ጎን ለጎን በድርሰትና በታሪክ ጸሐፊነታቸውም ፲፱ መጻሕፍት የታተመላቸው ሲሆን ሁለቱ ካረፉ በኋላ የታተሙ ናቸ። ለሕዝብ የሚሆኑ ዕውቀት ተኮር መጻሕፍት በማቅረብ ይታወቁ የነበሩት አቶ ጳውሎስ ኞኞ ካረፉ ከ፳ ዓመታት በኋላ ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ በሀገር ውስጥ የተጻጻፏቸውንና ወደውጭ አገር የላኳቸውን ደብዳቤዎች የሚያሳዩት ሁለት መጻሕፍት በአስቴር ነጋ አሳታሚ ድርጅት አማካይነት ታትመዋል።

ስለጸሐፊነት ባህሪያቸው ሲጽፉ፦ «'ይምሰል አይምሰል የጠይብ እጅ ከከሰል' እንደሚባለው እጄ እንደልማድ ሆኖበት መሞጫጨርን ይወዳል፡ ያን ሟጫራዬን ደግሜ ካነበብኩ ቀድጄ መጣል ነው፤ ይሰለቸኛል፡ እጠለዋለሁ፡ ስለዚህ አንድ ጊዜ በማርቀቅ የጻፍኳትን እንድትታተም እፈርድባታለሁ። ምናልባት አባጣ ጎባጣ ሆኖ አላስኬድ የሚል ገደላገደል ቢያጋጥማችሁ በደምዳሜ እመር እያላችሁ አላፉት።» 




#Article 246: አጥናፍሰገድ ኪዳኔ (443 words)


አጥናፍሰገድ ኪዳኔ አዲስ አበባ ዑራኤል አካባቢ ኅዳር ፲፮ ቀን ፲፱፻፵፬ ዓ.ም ተወለደ። ዕድሜው ለትምሕርት ሲደርስ ረፒ በልዕልት የሻሸወርቅ አዳሪ ትምሕርት ቤት፤ አዲስ አበባ በዳግማዊ ምኒልክ እና አስፋ ወሰን ትምሕርት ቤቶች ተምሯል።

አጥናፍሰገድ በጋዜጠኝነትና በአሳታሚነት እንድ ጦቢያ፣ ጥቁር ደም እና ታይታኒክ የተባሉ ጋዜጣዎች ላይ የሠራ ሲሆን በመጽሐፍት ረገድ ደግሞ ከዚህ በፊት በትርጉም ሥራ አምስት መጻሕፍቶችን እና አንድ ልብ ወለድ ድርሰቱን ለአንባብያን ያቀረበ ጸሐፊ ነው። 

 

አጥናፍ ሰገድ ሌዮኔ የተባለውን የመጀመሪያ ልብ ወለድ ድርሰቱን በጥቅምት ፳፻ ዓ.ም. አሳትሞ በሀገር ውስጥ፤ በብሪታኒያ እና በአሜሪካ ገበያ ላይ አውሏል። 

ሌዮኔ የተሰኘው ይህ ድርሰቱ  በወንጀል፤ በፍቅር፤ በጀብድ፤ በፖለቲካና የሀገር ፍቅር ስሜት የተሞላ ድርሰት ሲሆን፤ ቁም ነገሩ ጥንታዊ የሆኑ የኢትዮጵያ ቅርሳ ቅርሶች ቀ.ኃ.ሥ. ከሥልጣን ከወደቁበት ጊዜ ጀምሮ በአንዳንድ ራስ ወዳድ ግለሰቦች እና ባለሥልጣናት እየተሰረቁ በአውሮፓ የጥንታዊ ዕቃዎች ገበያ ላይ እንደዋሉና እየዋሉ መሆኑ ላይ ሲሆን፤ ሴራው ዓፄ ኃይለ ሥላሴቢሮ ጠረጴዛ ላይ ይቀመጥ የነበረው ከወርቅ የተሠራው የአንበሳ ቅርጽ ከፕረዚዳንቱ ቢሮ ተሰርቋል፡ ወደውጭም አውጥቶ ገበያ ላይ ለማዋል እነኛ ራስ ወዳድ ግለሰቦች ከውጭ ዜጎች ጋር ስለሚጎነጉኑት ሴራ እና በዚያውም አኳያ የሀገር ፍቅር ያላቸው አውሮፓ በስደት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ግለሰቦች ይኼ ትልቅ የሀገር ቅርስ ከኢትዮጵያ እንዳይወጣ የሚያደርጉትን ጥረት ያካትታል።  አጥናፍሰገድ፤ እግረ መንገዱን በደርግ ጊዜ ዋናው ተዋናይ 'አናርኪስት' ተብሎ ከ'አብዮት' ጥበቃ ካድሬዎች ሲሸሽ በዚያ ጊዜ ባገር ላልነበርን እና ለአዲሱ ትውልድ አንባብያን በቃላት የሚቀርጽልን ሁኔታ እውን እዚያው እንደነበርን ያህል ያደርገዋል። እኒያስ ብልሕና ተንኮለኛ ንጉሠ ነገሥት፤ ለካስ የምስጢር የስዊስ ባንክ ቁጥራቸውን የደበቁት እዚያው እተሰረቀው አንበሳ ቅርጽ ላይ ኖሯል! (አያደርጉትም ብለው ነው?)

ደራሲው አንዳንዴ ደግሞ ምርጥ እና አስቂኝ አባባሎችን በመቀላቀል አንባቢውን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻው ገጽ ድረስ ሳይጨርስ እንዳያስቀምጥ የሚያደርግ የጽሑፍ ባለችሎታ እንደሆነ ሌዮኔ ጥሩ ምስክር ነው። ለምሳሌ፤- አስፋው ሲጋሩን እያጤሰ ግሩምን ሲያዳምጥ ...የእሥራኤል አገር ጅብ የሰማው ተረት ድንገት ትዝ አለው። 'እሥራኤል አገር ነው አሉ። ሰዎች ሬሳ ተሸክመው ይሄዳሉ። ታዲያ መንገድ ላይ አያ ጅቦ ያገኛቸውና ወዴት እንደሚሄዱ ይጠይቃቸዋል። ሰዎቹም የሞተ ዘመዳቸውን ለመቅበር መሆኑን ይነግሩታል። አያ ጅቦም የሞተ ሰው መቀበሩን እንደማያውቅ ሆኖ በመደንገጥ ራሱን ይይዝና ልንቀብረው? ይላቸዋል። ሰዎቹም ግራ ተጋብተው አዎ ንልቀብረው! በማለት ይመልሱለታል። በዚህ ጊዜ አያ ጅቦ ከምትቀብሩት ለምን አትበሉትም? ይላቸዋል። በጅቡ አነጋገር የተናደዱት ሀዘነተኞች የሞተ ሰው ሲበላ የት ነው ያየኸው? ብለው ወደሱ ሲሄዱበት ቆም ይልና ...እሺ እናንተ ካልበላችሁት ለምን ለሚበላ አትሰጡትም? አላቸው። 

በሌላ ቦታ ደግሞ፤- ...የዘጠኝ ዓመቷ ሠናይት የአስራ ሦስት ዓመቱ አስፋው ቆሎ መያዙን ስታይ ወዲያው ፈገግ ብላ..አቀርቅራ በጥርሷ ጥፍሯን እየነከሰች አስፊቲ! እስቲ በናትህ ቆሎ ስጠኝ ትለዋለች። የሠናይት አራዳ መሆን ቢያስገርመውም ጥያቄውን ቸል ብሎ ለመሄድ ግን አላስቻለውም። ከዚያም ቶሎ ብሎ የግራ እጁን ሱሪ ኪሱ ውስጥ ከከተተ በኋላ የተናገርችውን እንዳልሰማ ዓይነት ቆሎ ስጠኝ?..አለ።  አስፋው ሱሪ ኪሱ ውስጥ ያቆየውን ግራ እጁን ባዶውን ካወጣ በኋላ በኩራት ስሜት በእጄ መስጠት ትቻለሁ። ከፈለግሽ መጥተሽ ከኪሴ ውሰጂ አላት። በደስታ የተዋጠችው ሠናይት ወደአስፋው እየሄደች ምን ቸገረኝ ጠራርጌ ነው የምወስድልህ! ብላ እጇን ሱሪ ኪሱ ውስጥ ከተተችው። ኪሱ ውስጥ ግን ያገኘችው የጓጓችለትን ቆሎ አልነበረም። የያዘችው ለስላሳና ጠንካራ ነገር ቆሎ ያለመሆኑን ያረጋገጠችው በድንጋጤ በድን ሆኖ የምታየው አስፋው ከት ብሎ በመሳቁ ነበር።




#Article 247: ኅሩይ ወልደሥላሴ (ብላቴን ጌታ) (284 words)


ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ በኢትዮጵያ መኻል አገር በሰሜን ሸዋ በመርሐ ቤቴ አውራጃ በታች ቤት ወረዳ ረመሸት ቀበሌ ደን አቦ ገዳም በተባለ ሥፍራ በ ፲፰፻፸፩ ዓ.ም ተወለዱ።  ሲወለዱ የተሰጣቸው ስም ገብረመስቀል ነበር።  በቤተ ክህነት ትምህርት እንጦጦ ራጉኤል ደብር መጥተው የመጻሕፍትን ትርጓሜ በዘመኑ ከነበሩት የደብሩ ሊቃውንት ዘንድ ተምረው አጠናቀዋል።  እዚህ ነው አንዱ መምህራቸው «አንተ የቀለም ቀንድ ስለሆንክና በምግባርህም የተመሰገንህ ነህና፡ ኅሩይ የተባለውን ስሜን ሸልሜያሃለሁ፡ ከንግዲህ ኅሩይ እየተባልክ ተጠራ!» አሏቸው። 

ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ ሃያ አንድ መጻሕፍትን የደረሱ ሲሆኑ፤ የመጨረሻው መጽሐፋቸው «የኢትዮጵያ ታሪክ፡ ከንግሥተ ሳባ እስከ ታላቁ የአድዋ ድል» ለመጀመሪያ ጊዜ በ ፲፱፻፺፱  ዓ.ም የልጅ ልጃቸው ወይዘሮ ሠናይት ተክለማርያም አሳተሙት። የኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር እና የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት በመተባበር ጳጉሜ ፪ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም በአዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አዳራሽ የተመረቁትን እና ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ  እንዲሁም የደራስያን፤- ቀኝ-ጌታ ዮፍታሄ ንጉሤን፤ ነጋድራስአፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ፣ እና አቶ ተመስገን ገብሬን ምስል የተቀረጸባቸውን አራት ቴምብሮችን ገበያ ላይ አውለዋል።   ደራሲው ፋሽሽት ኢጣልያ ኢትዮጵያን በወረረ ጊዜ ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ጋር አብረው ወደ እንግሊዝ አገር ስደት ላይ እንዳሉ በስልሳ ዓመታቸው መስከረም ፱ ቀን ፲፱፻፴፩ ዓ.ም. አረፉ።

ሥርዓተ ቀብራቸው መስከረም ፲ ቀን እዚያው እንግሊዝ አገር ሲፈጸም ንጉሠ ነገሥቱ የሚከተለውን ንግግር አደረጉ።

በአጭሩ ከጠባዩ ትልቅነት የሚሰማኝን ለመናገር ሳስብ ጊዜውን ሁሉ ቁም ነገር በመሥራት ማሳለፉ፤ ከራሱ ይልቅ የተቸገሩትን ለመርዳት መጣሩ፤ እውነትን፣ ፍርድንም ማክበሩና በአገር ፍቅር መቃጠሉ ትዝ ይሉኛል።

አገልጋዬና ወዳጄ ኅሩይ!
በተቻለህ ስለአገርህ ሥራህን በሚገባ ፈጽመህ በምትሰናበትበት ጊዜ ታላቅ ነህ ሳልልህ ብቀር ሥራዎችህ ቀድመውኝ ይናገራሉ።
በክፉ አድራጊዎች የሚገፋ የዓለምን ፀጥታ የሚያናውጥ ነፋስ ምንም ቢያንገላታህና በታላቅ ፈተና ላይ ቢጥልህም ሊያሸንፍ አልቻለም። ታላቅና ቸር በሆነው ጌታ በተመደበው ሕግ ግን መታዘዝ ግድ ሆነብህ። ይህም ለያንዳንዳችን የሚደርሰን ዕድል ነው። አንተም እስከ መጨረሻ ከታገልክ በኋላ ዛሬ ደከመህ፣ አንቀላፋህም።  በሥጋ ብትለየንም ስምህና ሥራህ በመካከላችን ይኖራሉ።

ኅሩይ! እግዚአብሔር ሲያስበን አጥንቶችህና መንፈስህ የሚሰፍሩበትን ቦታ እስኪያዩና ከአባቶችህ እስኪቀላቀሉ ድረስ በእንግድነት በመጣህበት በዚህ ሥፍራ በሰላም ዕረፍ።» 




#Article 248: በዓሉ ግርማ (174 words)


ደራሲ በዓሉ ግርማ በኢላባቡር ክፍለ ሀገር ሱጴ በምትባል ሥፍራ በ1928 ዓ.ም. ተወለዱ። ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በልዕልት ዘነበወርቅ ትምሕርት ቤት ፤ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በጄኔራል ዊንጌት ትምህርት ቤት አጠናቀዋል።  ከዚያም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፖሊቲካል ሳይንስ እና ኢንተርናሽናል ሪሌሽንስ የ ቢ.ኤ. ዲግሪ ያገኙ ሲሆን፤ በዚሁ ተመሳሳይ መስክ ከአውሮፓ የማስተርስ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል።

ደራሲ በዓሉ ግርማ በተለይ በልብ ወለድ እና በፈጠራ የሥነ ጽሑፍ ሥራዎች ከታወቁት የኢትዮጵያ የዘመኑ ደራሲዎች መካከል ተወዳጅነትና ዝናን ያተረፉ ዕውቅ ደራሲ ነበሩ። ከጻፏቸው በርካታ ድርሰቶቻቸው ውስጥ «ከአድማስ ባሻገር»  የተሰኘው መጽሐፋቸው በሩስኛ ቋንቋ ተተርጉሞ በቀድሞዋ የሶቪየት ሶሽያሊስት ሪፑብሊኮች ኅብረት ቀርቧል። በተጨማሪም በጋዜጠኝነት ሙያም ስማቸውን ያስጠሩ፤ ሙያቸውንም ያስከበሩ ደራሲ ነበሩ። «የዛሬይቱ ኢትዮጵያ» ጋዜጣ፤ የመነን መጽሔት፤ የአዲስ ረፖርተር መጽሔት፤ የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ በመሆን ከመሥራታቸውም ባሻገር፤ ብዙ ወጣት ጋዜጦችን ለማፍራት ጥረት አድርገዋል።  አዲስ ሪፖርተር የተባለውን መጽሔትም ደረጃው ከፍ እንዲልና በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲገመገም አድርገዋል። በጋዜጠኝነት ሙያቸው በኢትዮጵያ ራዲዮ ሠርተዋል። 

ደራሲ በዓሉ ግርማ ለኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱና ብዙ ሥራዎችን ያቀረቡ ሲሆን፤ የመጨረሻው መጽሐፋቸው «ኦሮማይ» በመባል ይታወቃል። ይኼውም መጽሐፍ በወቅቱ በነበረው የደርግ መንግሥት ሊደገፍ ባለመቻሉ በ1976 ዓ.ም. ለደራሲው ሕይወት መጥፋት መንስኤ ሊሆን በቅቷል። 




#Article 249: ማኅተመ ሥላሴ ወልደ መስቀል (203 words)


ብላቴን ጌታ ማኅተመ ሥላሴ ወልደ መስቀል በ፲፰፻፺፯ ዓ.ም. በሰሜን ሸዋ ቡልጋ  ውስጥ የተወለዱ ታዋቂ የሥነ ጽሑፍ ሰው ከመኾናቸው ባሻገር፤ በፈረንሳይ አገር የግብርና ትምሕርት ያጠናቀቁ ኢትዮጵያዊ ነበሩ።  በ ስልጣንም መጀመሪያ የ ልዑል አልጋወራሽ መርድ አዝማች አስፋ ወሰን ፀሐፊ፤ የእርሻ ሚኒስቴር ምክትልና ዋና ሚንስትር፤ የገንዘብ ሚኒስትር፤ የሕዝብ አገልግሎት ሚኒስትር እንዲሁም የዘውድ አማካሪ በመሆን አገራቸውን አገልግለዋል። 

በታሪክ ፊት ከፍተኛ ግምት የሚሰጠውና አጠቃላዩን የኢትዮጵያን ሕዝብ ኢኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ የሚዘክረውን «ዝክረ ነገር» የተሰኘውን መጽሐፍ በ ፲፱፻፵፪ ዓ.ም. ለህትመት አብቅተዋል። እኚህ ታላቅ የሥነ ጽሑፍ ሰው፤ በታሪክና ባህል፤ በትምህርተ ጥበባት እና በመንፈሳዊ ግንባራት አሥራ አምስት መጻሕፍትን አበርክተዋል።  እነዚህም መጻሕፍት

አንደኛ ክፍል፦ ታሪክና ባህል

ሁለተኛ ክፍል፦ ትምሕርተ ጥበባት

ሦስተኛ ክፍል፦ አንክሮ ለእግዚአብሔር፤ ተዘክሮ ለነፍስ (መንፈሳዊ)

ብላቴን ጌታ ማኅተመ ሥላሴ ቋንቋችን ባህላችንን፤ ልማዳችንን እና መንፈሳችንን የሚይስተጋባ አንዱ ትውልድ የሚከተለውን ትውልድ የማስተማርና ይኼን ቅርሳችንን የማስተላለፍ ኃላፊነት እንዳለበት ሲገልጹ እንዲህ ብለዋል። «ወላጆች ለልጆቻቸው በየጊዜው አንዳንድ ግጥም እየሰጡ ሠምና ወርቁን እንዲለዩ፤ በውስጡ ተሸፍኖ የሚገኘውን ድርብ ምስጢር መርምረው ተጨንቀውና ተጠበው እንዲያወጡና እንዲያስፋፉትም ቢያደርጓቸው የሚገኘው ፍሬ አስደሳች ይሆናል። ወጣቶቹ የሚሰለቹ ቢሆን እንኳ ኮሶ እየመረረ ካልተዋጠ ፈውስን አይሰጥምና እየተከታተሉ ማሠራቱ ዋጋ አለው፤ ይጠቅማልም።»

እንዲሁም፦ «እኛ ኢትዮጵያውያን አገራችን ጥንታዊት መሆኗን ሥልጣኔም በመሻት ዐዋቆችና አስተዋዮች አባቶቻችን በብዙ የደከሙ መሆናቸውን በመገንዘብ ላገራችን ወጣቶችም ሆነ ወይም ለውጭ አገር ሰዎች እውነተኛውንና ምስክርም ሊሆን የሚገባውን ሁሉ እየሰበሰብን ማዘጋጀት፤ ለመጭውም ትውልድ እንዲተላለፍ ማድረግ አለብን።»




#Article 250: ተስፋዬ ገብረአብ (173 words)


   ተስፈዬ ገብረአብ የበርካታ መፅሀፍት ደራሲ ነው።ሆኖም ግን ከብዙሀኑ የአማርኛ አንባቢ ጋር በስፋት ያስተዋወቀው ማስታወሻዎቹ ናቸው፤ እነሱም የጋዜጠኛው፣ የደራሲው እና የስደተኛው ማስታወሻ የተሰኙ ትረካዎቹ ናቸው። 

ያልተመለሰው ባቡር እና የቢሾፍቱ ቆሪጦች
      እነዚህ ሁለት መፅሃፍትን እራሱ ተስፋዬ ገብረአብ፣ ችሎታዬን ያገየሁባቸው የሚላቸው ስራዎቹ ናቸው። ምንም እንኳ በአንዳንድ ሃያሲያን ለመተቸት ቢበቃም።
የቡርቃ ዝምታ
     የቡርቃ ዝምታ በ1992 ዓም የታተመ መፅሀፍ ነው። መፅሀፉን ብዙዎች ጠብ አጫሪ ነው ብለው ቢተቹትም በቅን ልቦና ከተነበበ ግን አስተማሪና ታላቅ እውቀት አስጨባጭ እነደሆነ ይነገርለታል።
ማስታወሻዎች
   ማስታወሻ በሚል ርዐስ ያሳተማቸው 3 መፅሀፍት ሲሆኑ፤ እነሱም የጋዜጠኛው ማስታወሻ (2000) ፣ የደራሲው ማስታወሻ (2000) እና የስደተኛው ማስታወሻ (2006) ናቸው። በነዚህ 3 መፅሀፍት የተበታተኑ ፅሁፎችና መረጃዎችን አንድ ወጥ በሆነ የጋራ ጉዳይ ዙሪያ ማስተሳሰር ችሏል። ፅሁፊቹ አብዛኛው ትኩረታቸው በጊዜው ፓለቲካ ቢሆንም ፣ የፃፈበት ስነፅሁፋዊ ክህሎት ግን ከተለመዱት ፓለቲካዊ ፅሁፎች አብዝቶ የተለየ ነው። በመንግስት ስልጣን ላይ ስላሳለፈው ህይወትም ያወጋናል። ከስራም አልፎ በማህበራዊ ጉዳዮችና በልጅነት የደብረዘይት አስተዳደጉ ዙሪያም ሰፋ ያሉ ወጎች ታጭቀዋል። ከዛም አልፎ ከመንግስት ሀላፊዎች በደረሰበት ጫና ሀገሩን ለመልቀቅ በተገደደበት ሁኔታ ላይ ሳለ ፤ከኬንያ አስከ ደቡብ አፍሪካ ከዛም አሜርካ እና በተለያዩ የአውሮፓ ሀገሮች ስላሳለፈው የስደተኝነት ህይወት ቀልብን በሚስብ መልኩ ፅፏል።

ያሳተማቸው መፅሃፍት




#Article 251: ፀረ-ኤችአይቪ መዳኒቶች (105 words)


ፀረ-ኤችአይቪ መድኃኒቶች ወይም Antiretroviral Therapy (ART) drugs የኤችአይቪ ቫይረስ በሰውንት ውስጥ እንዳይባዛ የሚከላከል መድኃኒት ነው። ኤችአይቪ እንዳለበት አንድ ሰው ካረጋገጠ በጥሩ ጤንነት ለመኖር መድኃኒቶቹን በትክክል እየወሰደ እና የተመጣጠነ ምግብ እየተመገበ እራሱን በመጠበቅ 
መኖር ይቻለል። ተመርምሮ እራስን ማወቅ ብዙ ጠቀሜታ አለው። የኤችአይቪ መድኃኒት ቶሎ መጀመሩና ቆይቶ መጀመሩ እራሱ ለጤና ትልቅ ልዩነት ስላለው አውቆ ተገቢውን እርምጃ መውሰዱ በጣም ትልቅ አዋቂነት ነው።
አንድ ሰው የፀረ-ኤችአይቪ መድኃኒቶች ለመጀመር በቂ የሚያደርጉት ዋነኛ እርምጃዎች cd4 count less than 350 cells/mm3 (updated 2008)የሲዲፎር ሴል ቁጥር 350 cells/mm3 ወይም በታች ሲሆን ኤችአይቪ መድኃኒት መጀመር ይገባል።

አላለቀም ይቀጥላል።

ትርጉም በአበሻ ኬር ( Source: CDC Questions and Answers on HIV/AIDS )
 written by Abesha Care




#Article 252: ኤችአይቪ ያለባት እናት (186 words)


ኤችአይቪ ቫይረስ ያለባት እናት የኤችአይቪ መድሃኒት መውሰድ ተገቢ የሚሆንበት ምክንያት (mother-to-child transmission) በፅንስ ጊዜ ኤችአይቪ ቫይረስ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ ለመከላከል ነው። ኤችአይቪ ከአናት ወደልጅ አንዳይተላለፍ የሚወሰዱ የሕክምና የመዳኒት አይነቶች በዝርዝር ከታች ተገልፃል።

አንድ እናት እርጉዝ ከሆነች ወይም ለማርገዝ የምታስብ ከሆነ የራስዋንና የልጅዋን ጤና ለመጠበቅ ስትል የኤችአይቪ መዳኒት መውሰድ ጥቅሙን እና ጉዳቱን መረዳት ይኖርባታል።
አንዳንድ የፀረ-ኤችአይቪ መዳኒቶች እንደ ሳስቲቫ (such as Sustiva) አይነት በፍጹም መወሰድ የለበትም ምክንያቱም በፅንስ ጊዜ የተበላሽ ፅንስ ስለሚፈጠር በተለይ በመጀመሪያ እርግዝና አካባቢ ከተውሰደ በጣም እደገኛ ነው። አንድ እናት ከማረገዝዋ በፊትም ሆነ በእርግዝናዋ ጊዜ ከዶክተርዋ ጋር በቅርብ በመነጋገር ለእናትና ለልጅዋ ተስማሚ የሆነውን መድሐኒት አብረው መወሰን ይኖርባቸዋል።

ነፍስጡር እናት ከምትወስዳቸው የኤችአይቪ መድሃኒት ውስጥ AZT ሶስቱ ክፍሎች (three-part AZT (also known as Retrovir, zidovudine, or ZDV) መኖር የገባል ኤችአይቪ ቫይረስ ከናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ በጣም ትልቅ አስተዋጾኦ የሚያደርግ መዳኒት ነው።

የኤችአይቪ መድሐኒት በመውስድ ላይ የምትገኝ እናት ከዶክተርዋ ጋር ካለማቁዋረጥ በመነጋገር ጥቅሙንና ጉዳቱን በመረዳት መዳኒቱን በትክክል በመውሰድ የመዳኒቱን መጠን በትክክል አስተካክሎ መውሰድ ጠቃሚ ነው።

ከታች የተዘረዘሩት መዳኒቶች በነፍስጡር እናት መወሰድ የሌለባቸው ናቸው፦

ኤችአይቪ ያለባት እናት ከውሊድ በሃላ ሕጻኑን ማጣባት እንደሌለባት መከንዝብ አለባት
ኤችአይቪ ቫይረስ ከናት ወደልጅ በእናት ጡት አማካኘነት ሊተላለፈ ይችላል።

አበሻ ኬር የበጎ አድራጎት ድርጅት




#Article 253: ዘውዱ ጌታቸው (215 words)


ዘዉዱ ጌታቸው (አዲስ አበባ 1952 -አዲስ አበባ ታኅሣሥ 18 ቀን 1997 ዓ.ም)፣ ኤች.አይ.ቪ|ኤድስን በሚመለከት ፀጥታና ዝምታ በሰፈነበት ወቅት ራሱ ከቫይረሱ ጋር እንደሚኖር ይፋ በማዉጣት  «ትውልድ ይዳን በእኛ ይብቃ» ! ብሎ ኤች.አይ.ቪ|ኤድስን ለመዋጋት የተነሳ ኢትዮጵያዊ ጀግና ነበረ።  ዘውዱ ጌታቸው የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን በመስፍን ሀረር ትምህርት ቤት ፤ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደግሞ በተፈሪ መኰንን ትምህርት ቤት ተምሮ ካጠናቀቀ በኋላ በአዲስ አበባ ዮኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ፋክልቲ በመግባት የከፍተኛ ደረጃ ትምህርቱንም አጠናቋል። በአሰላ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመምህርነት እንዲሁም በዚላ፥ በበርታ፥ በሱርና፥ በሶጀት ኮንስትራክሽን ድርጅቶች በመካኒክነት ሠርቷል።

ራሱ ከቫይረሱ ጋር እንደሚኖር ይፋ አውጥቶ በማሳወቁ ምክንያት ይደርስበት የነበረውን አድልኦና ማግለል በቆራጥነት በመፋለም ዛሬ ኤች.አይ.ቪ|ኤድስን በሚመለከት ኢትዮጵያ ውስጥ ለተገኙ አዎንታዊ ለውጦች ከፍ ያለ ድርሻ አበርክቷል። ዘውዱ ጌታቸው በአገርና በአለም አቀፍ ደረጃ ተስፋ ጎህን በመወከል  የኤች.አይ.ቪ|ኤድስ ችግር በአገራችን እያደረሰ ያለውን እዉነታ በመናገርና ለበሽታዉ መንግስት ትኩረት እንዲሰጥ ጥሯል። በተጨማሪም «ተስፋ ብርሃን በኤድስ ወላጅ አልባ ሕፃናትና ወጣቶች ማህበር»ንም በመመስረት ኤች.አይ.ቪ|ኤድስን የሚያስከትለውን ሰብዓዊና ማህበራዊ ቀውስ በመታገል አያሌ ታዳጊዎችን ከመበተን አድኗል።
ከ1996 ዓ.ም ጀምሮ በኤች.አይ.ቪ ምክንያት በስራ ቦታ የሚደርሰውን አድልኦና ማግለል ይበልጥ ለመታገል ወደ ማህበር ለመምጣት ያልደፈሩትን ወገኖች በስልክና በሌሎች የመገናኛ አውታሮች የምክር አገልግሎት ለመስጠትና ከኤች.አይ.ቪ|ኤድስ ጋር የሚኖሩ ወገኖች ሰብአዊ መብት እንዲከበር ይበልጥ ለመታገል «አዲስ ምዕራፍ» የተባለ ድርጅት አቋቁሟል። እስከ ሕልፈተ ሕይወቱ ድረስ ሠርቷል። ዘውዱ ጌታቸው ባደረበት ሕመም ምክንያት በተለያዩ ሆስፒታሎች በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ በተወለደ በ45 ዓመቱ ታህሣሥ 18 ቀን 1997 ዓ.ም. ከዚህ አለም በሞት ተለይቱዋል።




#Article 254: ንዋይ ደበበ (115 words)


ንዋይ ደበበ (፲፱፻፶፫ ዓ.ም. ተወለደ) አንጋፋ ኢትዮጵያዊ ድምፃዊና የዘፈን ግጥም ደራሲ ነው።

ንዋይ ደበበ በጋሞጎፋ ክፍለ ሀገር በገለብና ሀመርባኮ አውራጃ በሀመር ወረዳ በ፲፱፻፶፫ ዓ.ም. ተወለደ። በተወለደበት አካባቢ ትምህርቱን እስከ ፬ኛ ክፍል ከተማረ በኋላ በ፲፱፻፷፫ ዓ.ም. ወደ አሰላ በመሄድ እዚያው እየተማረ ሳለ በአስተማሪውና በት/ቤት ጓደኞቹ ዘንድ አድናቆትን እያገኘ መጣ። በኋላም ላይ ንዋይ በቤተሰቦቹ የሥራ ዝውውር ምክንያት ወደ ሲዳሞ ሄዶ አርባምንጭ ከነማና በወላይታ ሶዶ የቀበሌ ኪነት ውስጥ ድምፃዊ ሊሆን ችሏል። ከዚያም ወደ አዲስ አበባ በመሄድ በ፲፱፻፸፯ ዓ.ም. የመጀመሪያ ካሴቱን ለማሳተም ችሏል። ንዋይ ከድምፃዊነቱ በተጨማሪም የዘፈን ግጥሞችና የዜማዎች ደራሲ በመሆኑ አገራችን ካሏት ጥቂትና ልዩ ድምጻዊያን አንዱ ነው። ንዋይ ደበበ ከታዋቂ ዘፈኖቹ አንዱ «የጥቅምት አበባ» የተባለው ሲሆን ዜማውንና ግጥሙን የደረሰው ገና የ8ኛ ክፍል ተማሪ በነበረ ጊዜ እንደሆነ ይናገራል።

ዜማዎች፦




#Article 255: አንሻን (269 words)


አንሻን (ፋርስኛ: انشان ፣ ዘመናዊ ታል-ኢ ማልያን ኢራን) በዛግሮስ ተራሮች የተገኘ () ጥንታዊ የኤላም ዋና ከተማ ነበረ። 

በ1965 ዓ.ም. ከሥነ ቅርስ ምርመራዎች የተነሣ ሥፍራው ታል-ኢ ማልያን መሆኑ ታወቀ። ከዚያው አመት አስቀድሞ ቦታው ከዚያ ወደ ምዕራብ በመካከለኛ ዛግሮስ ሰንሰለት እንደ ነበር ይገመት ነበር።

ይህ ኤላማዊ ከተማ እጅግ ጥንታዊ መሆኑ አይጠራጠርም፤ በጥንታዊው ሱመርኛ አፈ ታሪክ ኤንመርካርና የአራታ ንጉሥ መሠረት ከኡሩክ ወደ አራታ በሚወስድ መንገድ ላይ ይገኝ ነበር፤ ይህም መጻፍ የተለማበት ዘመን ያሕል እንደ ነበር ይባላል። በአንዳንድ ዘመን አንሻን ከሌሎች ትልልቅ የኤላም ከተሞች ጋራ ሲወዳደር የብዙ ኤላማዊ ስርወ መንግሥታት ምንጭ ሆነ። 

የአካድ ንጉሥ ማኒሽቱሹ አንሻንን እንዳሸነፈ ብሎ አስመዘገበ። በተከታዮቹ ሥር ግን የአካድ መንግስት በደከመበት ወራት (2013 ዓክልበ.)፣ የሱሳ ኗሪው አገረ ገዥ ኩቲክ-ኢንሹሺናክ እሱም የአዋን ሥርወ መንግሥት ተወላጅ ነጻነቱን ከአካድ አዋጀና አንሻንን ማረከ። (አንዳንድ ሊቃውንት ደግሞ 'አዋን'ና 'አንሻን' አንድ ቦታ እንደ ነበር የሚል ግምት አቅርቧል።) ከዚህ ቀጥሎ የላጋሽ ንጉሥ ጉዴኣ አንሻንን እንዳሸነፈ የሚል መዝገብ ቀረጸ። የኋለኛ ኡር ነገሥታት ሹልጊና ሹ-ሲን ደግሞ በአንሻን ላይ የራሳቸው አገረ ገዦች እንደነበሯቸው በጽላት ላይ ተጽፎ ይገኛል። ሆኖም የነሱ ተከታይ ኢቢ-ሲን በዘመኑ በሙሉ አመጽ በአንሻን ለመስበር ይታገል ነበር፤ በመጨረሻም ኤላማውያን በ1879 ዓክልበ. ገዳማ ዑርን በዝብዘው የናና ጣኦትና ኢቢ-ሲንም እራሱ እስከ አንሻን ድረስ ተማረኩ።

ከ15ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. ጀምሮ የኤላም ነገሥታት በሱሳ «የአንሻንና የሱሳ ንጉሥ» የሚል ማዕረግ ይጠቅማቸው ነበር። በአካድኛ መዝገቦች ግን እነዚህ ስሞች ተገልብጠው «የሱሳና የአንሻን ንጉሥ» ተብሎ ይጻፋል። በመካከለኛ ኤላማዊ ዘመን አንሻንና ሱሳ በአንድ ግዛት እንደ ተወሐዱ ይመስላል። ይህም ስያሜ የወሰደው መጨረሻው ኤላማዊ ንጉሥ 2ኛ ሹትሩክ-ናሑንተ (700 ዓክልበ. ያሕል የነገሠ) ነበረ።

በ650 ዓክልበ. ገደማ አንሻን በፋርስ ነገድ አለቃ ተይስፐስ ተይዞ ከዚያ እሱ «የአንዛን ንጉሥ» ተባለ። በሚከተለው መቶ አመት የኤልማውያን መንግሥት ሲደከም፣ አንሻን ጥቃቅን አገር ነበር፤ ከ550 ዓክልበ. ገደማ የፋርሳውያን አሐይመኒድ ሥርወ መንግሥት ከአንሻን ተነሥቶ የፋርስ መንግሥት ያስፋፉ ጀመር። 




#Article 256: አራም (የሴም ልጅ) (163 words)


አራም ሴም (ዕብራይስጥ፦ אֲרָם) በመጽሐፍ ቅዱስ ኦሪት ዘፍጥረት (ምዕ. 10) መሠረት የኖህ ልጅ ሴም ከወለዱት ልጆች አንድ ሲሆን የዑፅ፣ ሁል፣ ጌቴርና ሞሶሕ አባት ይባላል። 

በጥንቱ ታሪክ ጸሐፊዎች ዘንድ፣ ይህ አራም የስሜን መስጴጦምያና የሶርያ ሕዝብ የአራማውያን አባት ነበር። በኤብላ ጽላቶች ላይ (2300-2100 ዓክልበ. ግድም) «አራሙ» እና «አርሚ» የሚሉ ስያሜዎች ይገኛሉ፤ «አርሚ» የሐላብ (አሌፖ) ስም ነበር። በ2034 ዓክልበ. ያሕል በአካድ ንጉሥ ናራም-ሲን በስሜን ተራሮች በተደረገው ዘመቻ «የአራም አለቃ ዱቡል» እንደማረከው ይመዘገባል።  የአራም ሕዝብ ወይም አገር ደግሞ በማሪ ጽላቶች (1900 ዓክልበ. ግድም) እና በኡጋሪት ጽላቶች (1300 ዓክልበ. ግድም) ታይተዋል። ሆኖም እነዚህ ስያሜዎች ትርጉሞች ለሊቃውንት ክርክር ሆነዋል፤ የአራም ሕዝብ መኖሩ ከ1100 ዓክልበ. ጀምሮ በእርግጥ ይታወቃል።  

በመጽሐፈ ኩፋሌ (9፡19) መሠረት፣ የኖህ ልጆች ምድሪቱን ሲያከፋፈሉ የአራም ልጆች የወረሱት ርስት ከኤፍራጥስና ከጤግሮስ ወንዞች መካከል ያለው አገር ሁሉ ያጠቅልል ነበር። ይሁንና በታሪካዊው ዘመን አራማውያን በተለይ በዚያ አቅራቢያ ስሜን ሠፍረው ነበር።

በብሉይ ኪዳን የተጠቀሰው ካራንንም ከተማ የጠቀለለው ሀገር «አራም-ናሐራይን» (የሁለት ወንዞች አራም) እንዲሁም በአካባቢው የተገኙት አራም-ደማስቆና አራም-ረሆብ በአራም ልጆች እንደ ተመሰረቱ ይታመናል።

ደግሞ የሴም ልጅ አራም በማንዳያውያን ሃይማኖት እንደ ነቢይ ሆኖ ይከብራል።




#Article 257: ከኤች·አይ·ቪ ቫይረስ ጋር ተስማምቶ ለመኖር (1020 words)


ከኤች.አይ.ቪ ቫይረስ ጋር መኖር ማለት ቫይረሱ በደሙ ውስጥ እንዳለ የተረዳ ሰው ራሱን አረጋግቶና ችግሩን እንደማንኛዉም የጤና ችግር በማየት ቫይረሱ የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነሰ እና ለመከላከል በሕክምና፣ በአመጋገብ፣ እንዲሁም በባህርይ ላይ አስፈላጊ የሆኑ ለውጦችን በማምጣት ጥሩ ሕይወት መኖር ማለት ነው። አንድ ሰው ኤች·አይ·ቪ አለበት ማለት አሁኑኑ ታሞ ይተኛል ወይም በቅርቡ ሕይወቱ ያልፋል ማለት አለመሆኑን ማወቅ ተገቢ ነው። ከኤች.አይ.ቪ ጋር የሚኖሩ ሰዎች የእድሜ ማራዘሚያ መድሀኒቶችን (ፀረ-ኤችአይቪ መዳኒቶች) በመጠቀም ለረጅም ዓመታት ጤናማ ሆነው ለመኖር ይችላሉ። አንዳንድ ሰዎች የበሽታዉ ምልክት ጨርሶ ሳይታይባቸው ከ15 ዓመት በላይ ከቫይረሱ ጋር መኖር እንደሚችሉ አንዳንድ ጥናቶችም ያመለክታሉ። ኤች·አይ·ቪ ቫይረስ በደም ውስጥ በመኖሩ ምክንያት ሊሰማ የሚችለዉን ስሜት አውነታውን መቀበል መቻል በጣም አስፈላጊ ነው። ጥሩ ያልሆኑትን ስሜቶች ለማስወገድ የሚከተሉትን ምክሮች መቀበልና መተግበርም ተገቢ ነው።

ከኤች·አይ·ቪ ቫይረስ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ቫይረሱ እንዳለባቸዉ አውቀው ከጥቂት ጊዜ በኋላ ያሉበትን የጤና ሁኔታ ተቀብለው ራሳቸውን በማረጋጋት ወደፊት በተሻለ መንገድ ለመኖር ምን ማድረግ እንዳለባቸው ማሰብ ይጀምራሉ። እራሰን አረጋግቶ ለመኖር ከዚ በታች የተጠቀሱት ጠቃሚ መመሪያዎች በዝርዝር ጠንቅቆ ማወቅ አጥጋቢ የሆነ የፀባይ እና የአኗኗር ለውጥ ለማምጣት ይረዳል፦

ከኤች.አይ.ቪ ጋር ኑሮን በሠላም ለረጅም እድሜ መምራት እንደሚቻል መገንዘብ አስፈላጊ ነው። እንዲሁም ከኤች.አይ.ቪ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ህጋዊ መብታቸውን የሚያከብሩ ህግጋት እንዲደነግጉ ድጋፍን በመስጠት የራስን አስተዋፅኦ በማድረግ ተስፋን እውን ማድረግ። በተጨማሪም የዕለት ዜናዎችን በመከታተል፣ባለሞያዎችን ወይንም አማካሪዎችን በመጠየቅ በኤች.አይ.ቪ ላይ ያሉ አዳዲስ የህክምና እና የመድሀኒት ግኝቶችን መከታተልና ማወቅ ተስፋን ይሰጣል።  ስለ ኤች.አይ.ቪ ዕውቀትን ማዳበርና ይበልጥ ማወቅ ራስን በደንብ ለመንከባከብ ይረዳል። አንድ ከኤች.አይ.ቪ ጋር የሚኖር ሰው ልጆች ካሉት ህመም ሲጠና ልጆችን የሚንከባከብ ሰው ቀድሞ ማዘጋጀት ያስፈልጋል።

ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ክትባት ወይም ፈዋሽ መድኀኒት ባይገኝለትም ምርምሩና ሙከራዉ እንደቀጠለ ነው። የዕድሜ ማራዘሚያ መድሃኒቶች (ፀረ-ኤችአይቪ መዳኒቶች) ቫይረሱ በደም ውስጥ የሚያደርገውን የስርጭት ፍጥነት ለመግታትና ለማስቆም የሚወሰዱ መድሃኒቶች ናቸው። በሰውነት ዉስጥ የሚገኘውን የኤች.አይ.ቪ ቁጥር መቀነስ ይችላሉ፤ መድሃኒቶቹ ቫይረሱን ከናካቴው ማጥፋት አይችሉም። መድሃኒቶቹን ያለ ህኪም ትዕዛዘና ፍቃድ መውሰድ በጤንነት ላይ ትልቅ ችግር ያስከትላል። የመድሃኒቶቹ ተጠቃሚ ሰው አንድ በቅርብ ሆኖ የሚከታተለው ብቃት ያለው የህክምና ባለሙያ ያስፈልገዋል። 

የተመጣጠነ ምግብ መመገብ ሰውነታችንን እና የሰውነት የመከላከያ አቅማችንን እንደሚያጠነክር ሁሉ በቀላሉ ለበሽታ እንዳንጋለጥም ይጠቅመናል። ከኤች·አይ·ቪ ጋር የሚኖሩ ስዎች በምግብ እና ውኀ ውስጥ ለሚገኙ በሽታን ወይም ህመምን ሊያስከትሉ ለሚችሉ ጀርሞች በቀላሉ የተጋለጡ በመሆናቸዉ፤ በቤት ውስጥም ሆነ ከቤት ውጭ ሲመግቡ ንጽህናውን የጠበቀ የአመጋገብ ሥርዓት መከተልና የሚጠጣው ውሃ ንጹሀ መሆኑን ማረጋግጥም በጣም ጠቃሚ ነው።  ከኤች·አይ·ቪ ጋር የሚኖሩ ስዎች የተለያዩ ዓይነት ምግቦችን በመመገብ ያልተፈለገ የሰውነት ክብደት መቀነሰን ለመከላከል እና ጡንቻዎቻቸዉ እንደጠነከሩ እንዲቆዩ የሰውነት እንቅስቃሴ ማድረግ አለባቸው። 
ሁሉም የምግብ ዓይነቶች የተለያዩ ጥቅሞች አላቸዉ። የተለያዩ የምግብ ዓይነቶች በሚከተለው መሰረታዊ ምድቦች ተከፋፍለው ሊታዩ ይችላሉ።

የሰዉነትን የመከላከል አቅም ለማጎልበት፦

ዉኃ ለሰውነታቻን ከሚያሰፈልጉን ነገሮች አንዱ ነው። በየቀኑ ቢያንስ 8 ብርጭቆ ዉሃ መጠጣት ጠቃሚ ነው። የምንጠጣው ዉሃ ንፁህ መሆን አለበት። ከኤች. አይ.ቪ ጋር የሚኖር ሰው እንደ ተስቦ፣ ኮሌራ፣ ቢልሀርዚያ እና ጃርዲያ ለመሳሰሉት በተበከለ ውኃ አማካኝነት በሚተላለፉ በሽታዎች የተጋለጠ ስለሆነ በቀጥታ የህይቅ ወይም የምንጭ ውኃ ከመጠጣት ፈልቶ የቀዘቀዘ ውኃ መጠጣት በጣም አስፈላጊ ነው።

ሰዉነታችንን በጤንነት ለማቆየትና ቫይረሱ በጤና ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ጉዳት ለመቀነስ ቫይታሚን ኤ፣ ቢ6፣ ቢ12፣ ሲ፣ ዚንክ፣ አይረን፣ ኮፐር፣ ማንጋኒዝ፣ ማግኒዥየም እና ሴሊኒየም ጨዉ የመሳሰሉትን ሁሉ መመገብ ይጠቅማል።
የሰዉነትን የተፈጥሮ በሽታን የመከላከል አቅም በማጎልበት ረገድ ቫይታሚን ኤ፣ ሲ፣ ኢ፣ እና ከማዕድናትም ዚንክ በጣም ጠቃሚዎች ናቸው። እነዚህ የምግብ ንጥረ-ነገሮች በተፈጥሮ ከተለያዪ ምግቦች ዉስጥ ይገኛሉ።

አንዳንድ ጊዜ የተመጣጠነ ምግብ ባለመመገባችን ምክንያት የሚከተለውን ክፍተት ለማካካስ በፋብሪካ የተዘጋጁ ቫይታሚኖችን እንወስድ ይሆናል። ቅድሚያ መስጠት የሚገባን የተመጣጠነ ምግብ በመመገብ ተፈላጊ የሆኑትን የምግብ ንጥረ ነገሮች ማግኘት ቢሆንም የቫይታሚን እንክብሎችን መውሰድ አስፈላጊ የሚሆንባቸው ጊዜያት አሉ። በግምት ብዙ ቫይታሚኖችን መውሰድ ጤንነትን ስለሚያቃውስ የቫይታሚን እንክብ በሚወሰድበት ጊዜ በህክምና ባለሞያ ትዕዛዝ መሰረት መሆን አለበት። 

ከኤች·አይ·ቪ ጋር የሚኖሩ ሰዎች በምግብ ምክንያት ለሚመጡ በሽታዎች የተጋለጡ ናቸዉ። አንዳንድ ጎጂ የሆኑ ጀርሞች ከጥሬ ስጋ፣ ምግቡን ከሚያዘጋጁ ሰዎች ወይም አብረዉ እንጀራ ከሚበሉ ሰዎች አፍና እጅ ንክኪ ሊሸጋገሩና የምንመገበውም ሊበከል ይችላል። ከኤች·አይ·ቪ ቫይረስ ጋር የሚኖር ሰው በምግብ መመረዝ ሲታመም ለማዳን በጣም ከባድ ከመሆኑ ሌላ በሽታው በተደጋጋሚ ሊመላለስበት ይችላል። እንደ ኮሶ፣ ወስፋት እና አሜባ የመሳሰሉት በሽታዎች ከፍተኛ የጤና ችግርን እንዲሁም ሞትን ሊያስከትሉ ይችላሉ። ከነዚ በሽታዎች አብዛኛዎቹ በቀጥታ በበሽታዎቹ ከተያዘ ሰው የሚተላለፉ ቢሆንም ባልበሰለ ወይም ንጽህናው ባልተጠበቀ ምግብ፣ በነፍሳት (ተባዮች) በተበከለ ምግብ፣ የምግብ አያያዝ ሥርዓትና ደንብን ባልተከተለ ሰው ተዘጋጅቶ በሚቀርብ ምግብ አማካይነት ሊተላለፉ ይችላሉ። ምግብን በደምብ ማብሰል ባክቴርያና ጀርሞች እንዲሞቱ ይረዳል። ከኤች·አይ·ቪ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ጥሬ ሥጋ ወይም ጥሬ ክትፎም ሆነ ለብለብ ክትፎ ባይመገቡ ይመረጣል። በተጨማሪም ከቤት ውጭ በሆቴሎችና ቡና ቤቶች ውስጥ መመገብ ምግቡ እንዴት እንደተዘጋጀ ስለማይታወቅ ለህመም ሊያጋልጥ ይችላል። ከተቻለ ከቤት ውጭ አለመመገብ፤ ካልሆነም ምግቡ እንዴት እንደተዘጋጀ እና ጥሬ የሆኑ የምግብ ውህዶች ማለትም ያልበሰለ ሥጋ፣ እንቁላል ወይም አትክልት የሌለበት መሆኑን ጠይቆ ማረጋገጥ ያስፈልጋል። 

ዕፅም  ሆነ አልኮል በብዛት መውሰድ የሰውነትን የተፈጥሮ በሽታን የመከላከል አቅም ያዳክማል። ጤናማ ሆኖ ለመኖርም ሆነ ጤንነትን ለመንከባከብ አልኮልንም ሆነ ዕፅን መጠቀምን እስከመጨረሻው መተው አማራጭ መንገድ ቢሆንም ይህንን ሁሉም ሰው በቀላሉ ሊያደርገው አይችልም። የሚወሰደው የሲጋራ፣ የዕፅ ወይም የአልኮል መጠንን በተቻለ መጠን መቀነስ ጤንነትን በተሻለ ሁኔታ ለመጠበቅም ይረዳል። 

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የተሻለ ጢና እንዲኖር ከመርዳቱ ሌላ የመጨነቅ፣ እና የድካም ስሜትን ይቀንሳል። የአካል ብቃት እንቅስቃሴው ራስን ዘና የሚያደርግና የልብን ምት እንዲጪምር ተደርጎ መሠራት አለበት እንጂ እስኪደክሙ መሆን የለበትም። ተገቢውን የየአካል ብቃት እንቅስቃሴ መጠን ለማወቅ ቢቻል የስፖርት ባለሞያዎችን አስቀድሞ ማማከር የተሻለ ነው። በየቀኑ ከ30 እስከ 60 ደቂቃ ያህል በእግር መጓዝ የተሻለ ጤና እንዲኖረን ከሚረዱት የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች አንዱ ነው።

አንድ ከኤች·አይ·ቪ ጋር የሚኖር ሰው ስለራሱ ጤና በተመለከተ መብቱ የተሰጠዉ ለራሱ በመሆኑ ለፈለገው ሰው መንገር፣ ካልፈለገ ደግሞ ያለመናገርም ውሳኔው በእጁ ነው። ነገር ግን ከዚህ ጋር በተያያዘ መዘንጋት የሌለበት ጉዳይ አለ። በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ላይ የሰፈረ ድንጋጌ አንድ ሰው የሌላውን ሰው ጤንነት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ሆን ብሎ ይሁን በቸልተኝነት የሚጎዳ ተግባር ከፈጸመ እንደሚቀጣ ያስረዳል። ስለዚህ ከወሲብ ጓደኛ ጋር በሚኖር ግንኙነት ቫይረሱ ወደዛ ጓደኛ እንዳይተላለፍ ኮንዶም መጠቀም ያስፈልጋል ። ይህ ከሆነ ከኤች·አይ·ቪ ነፃ የሆነውን ወዳጅ ከቫይረሱ ለመጠበቅ ይረዳል። ከኤች·አይ·ቪ ጋር ነዋሪ መሆንን ለወሲብ/ፍቅር  ጓደኛዎ አንዳንድ ጊዜ በቀጥታ ሌላ ጊዜ ደግሞ በተዘዋዋሪ መናገር ይቻላል። ለምሳሌ ስለቅድመ ወሲብ ጥንቃቄ ወይም ስለ ኤች·አይ·ቪ እና መተላለፊያ መንገዶች በማንሳት መነጋገር ይቻላል። 

አንዲት ሴት ኤች·አይ·ቪ በደሟ ውስጥ ቢኖርም እንኳን ልጆች ማፍራት ትችላለች። ተገቢውን ጥንቃቄ እና የህክምና ክትትል ካደረገች ከኤች·አይ·ቪ ነፃ የሆነ ጤነኛ ልጅ ሊኖራት ይችላል። ይሁን እንጂ ለኤች·አይ·ቪ የሚጋለጥም ልጅ ሊኖር ይችላል።
ልጅ ለመውለድ እቅድ ካለ የሚከተሉትን ነጥቦች ልብ ማለት እና የህክምና ባለሞያን ማማከር ያስፈልጋል

ከኤች·አይ·ቪ ጋር መኖር ከማንኛውም ሰብአዊ ፍጡር አያሳንሰም። ኤች·አይ·ቪ በደም ውስጥ በመኖሩ በሰብአዊ ፍጡርነት ሊኖር የሚገባውን መብት ሊያጓድል የሚችል አንድም ምክንያት የለም። ይህም ማለት ከኤች·አይ·ቪ ጋር የሚኖር ማንኛውም ሰው እንደሌሎች

ከኤች·አይ·ቪ ጋር በሚኖሩ ሰዎች ላይ የሚደረግ መድልዎ ዋና ዋና መንስኤዎች አሉት፦ እነዚህም

በሥራ ቦታ ላይ ስለሚደርስ መድልዎ ማወቅ፦ አንድ ሰው ከኤች·አይ·ቪ ጋር በመኖሩ ምክንያት መገለል ወይም አድልዎ ከደረሰበት ከቀጣሪው ጋር በመነጋገር ወይም በፍርድ ቤት በመክሰስ ፍትህ የማግኘት መብት አለው። ሕግም ከለላና ጥበቃ ያደርግለታል። የኢፌዴሪ የኤች·አይ·ቪ/ኤድስ ፖሊሲ ማግለልና አድልዎን በግልጽ ይከለክላል።




#Article 258: አለቃ አያሌው ታምሩ (524 words)


አለቃ አያሌው ታምሩ ከአባታቸው ከአቶ ታምሩ የተመኝና ከእናታቸው ከወይዘሮ አሞኘሽ አምባዬ፤ በጎጃም ክፍለ ሀገር በብቸና አውራጃ በእነማይ ወረዳ በታላቁ ደብር ወገዳም በደብረ ድማኅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ልዩ ስሙ ቤተ ንጉሥ 
በተባለ ቦታ መጋቢት ፳፫ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓመተ ምሕረት በዕለተ ሆሣዕና ተወለዱ። ዕድሜአቸው ለትምህርት ሳይደርስ ገና የሦስት ዓመት ተኩል ሕፃን ሳሉ በፈንጣጣ ሕመም ምክንያት የዐይናቸውን ብርሃን አጥተዋል። የስምንት ዓመት ዕድሜ ልጅ ሳሉ በዓለ ተክለ አልፋን ለማክበር ከአባታቸው ጋር ወደ ዲማ እንደ ሄዱ በዚያው ትምህርታቸውን ለመቀጠል ቀሩ።  ከዚህ ጊዜ ጀምሮም በቅርብ ቤተ ዘመድ እየተረዱ ለአንድ ዓመት ያህል ሲማሩ ከቈዩ በኋላ አባታቸው ስላረፉ ኑሮአቸው በትምህርት ቤት ብቻ ስለ ተወሰነ ከቤተ ሰብእ ጋር የነበራቸው ግንኙነት እየቀነሰ መጣ። ይህም ሁኔታ የሚፈልጉትን ትምህርት በአንድ ልብ ለመቀጠል ግድ ሆኖባቸዋል። 

በዚሁ መሠረት በ፲፭ ዓመት ዕድሜአቸው የቅኔ መምህር ለመሆን በቅተዋል። ስለ ዐይናቸው ብርሃንና ስለ ትምህርታቸው፤ «ምልጃ ዕርቅና ሰላም፤» በተባለው መጽሐፋቸው ገጽ ፬ ላይ እንዲህ ሲሉ ገለጸዋል። «ይህ ሁሉ የተገኘው ገና በልጅነት ዕድሜዬ፤ በቅዱስ ሐዋርያ ያዕቆብ እንደ ተነገረው የምመራበት፣ የምኖረበት በወሰድከው በዐይኔ ፈንታ ዕውቀት ስጠኝ ብዬ የለመንኩት አምላኬ፤ «ለምኑ ይሰጣችኋል፤ ሹ ታገኛላችሁ፤ በር ምቱ ይከፈትላችኋል፤ ለሚወደኝ እኔ ራሴን እገልጥለታለሁ፤»
ሲል በሰጠው ተስፋና በለገሰኝ የአእምሮ ምጽዋት መሆኑን ስለምረዳ ነው፤» ብለዋል።

ክቡር አለቃ አያሌው ታምሩ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት፥ ትምህርት፥ ሥርዐትና አስተዳደር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተለወጠና እየተበላሸ መሄዱ በእጅጉ ያሳዝናቸው ስለ ነበር፤ የቤተ ክርስቲያኒቱ የሊቃውንት ጉባኤ ዋና ሰብሳቢ እንደ መሆናቸው መጠን፤ ጥፋቱ እንዲታረም ብዙ አቤቱታና ተማጽኖ ጉዳዩ ወደሚመለከተው ወደ ቤተ ክርስቲያኒቱ ቅዱስ ሲኖዶስ፤ ሲኖዶሱን በመሠረተና በሚመራው በመንፈስ ቅዱስ ስም ተማጽነው ቢያቀርቡም ሲኖዶሱ ጉዳዩን ለማፈን ከመሞከር በስተቀር ምንም እርምጃ ሳይወስድ ቀርቷል። እሳቸውም ያቀረቡት ጥያቄ መፍትሔ ባለማግኘቱ ጉዳዩን ለሚመለከተው ለኢተዮጵያ ሕዝበ ክርስቲያን ለማሳወቅና፤ በቤተ ክርስቲያን ላይ ዐመፅ የሚፈጽሙትን ፓትርያርኩንና የእሳቸው ተባባሪ የሆኑ ጳጳሳትን ባላቸው ከፍተኛ ኀላፊነተና ሥልጣነ ክህነት በሥልጣነ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፥ በሥልጣነ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ለማውገዝ ተገደዋል። ከዚህም በተጨማሪ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናት በጸሎተ ቅዳሴ ጊዜ
የዐመፀኛውን ፓትርያርክ ስም እንዳይጠሩ ውግዘት አስተላልፈዋል። ምእመናንም ከዐመፀኞች ካህናት ምንም ዐይነት አገልገሎት ማገኘት የማይችሉ መሆናቸውን ተገንዝበው ሕይወታቸውን በጥንቃቄ እንዲመሩ አሳስበዋል። በዚህም ምክንያት ከ፶ ዓመት በላይ ካገለገሉበት የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በሐሰት ክስና የእምነት ክሕደት ቃላቸውን ባልሰጡበት ሁኔታ ያለ ምንም ጡረታ ከሥራ ገበታቸው ላይ በግፍ እንዲነሡ በመደረጉ ከሚያዝያ ወር ፲፱፻፹፰ ዓመተ ምሕረት ጀምሮ እስከ ዕለተ ዕረፍታቸው በመኖሪያ ቤታቸው ተወስነው ኖረዋል። በነዚህ ዓመታትም በየዕለቱ ለጸሎት ባዘጋጇት አነስተኛ ክፍል በመገኘት ወደ ልዑል እግዚአብሔር በመጸለይና በማልቀስ ይተጉ ነበር። ምእመናንም በተኲላ እንዳይነጠቁ በተለያዩ ጋዜጦች ትምህርትና ማበረታቻ ሲሰጡ ኖረዋል። 

የክቡር አለቃ አያሌው ታምሩ የቀብር ሥነ ሥርዐት ነሐሴ ፲፯ ቀን ፲፱፻፺፱ ዓመተ ምሕረት ብዙ ዘመን ባገለገሉበት የአዲስ አበባው ደብረ አሚን ተክለ ኃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ብዙ ሕዝብ በተገኘበት ተፈጽሟል።

ክቡር አለቃ አያሌው ታምሩ በቤተ ክርስቲያን ሥርዐት መሠረት በሥርዐተ ተክሊል ከወይዘሮ ርብቃ ልሳነ ወርቅ ጋር ሚያዝያ ፲፪ ቀን ፲፱፻፶ ዓመተ ምሕረት ጋብቻ ፈጽመው ፲፬ ልጆችና ፲፪ የልጅ ልጆች ለማፍራት ታድለዋል።
 Thaddaeus.G

በመጽሐፍ ጥራዝ አዘጋጅተውና አሳትመው ለትውልድ ያስተላለፏቸው መጻሕፍት ዘጠኝ ሲሆኑ በይዘታቸው በሁለት የተከፈሉ ናቸው። በአንደኛው ክፍል ያሉት የቤተ ክርስቲያንንና የኢተዮጵያን ማንነት ለኢትዮጵያውያን ለማስተማር የተዘጋጁ ሲሆኑ፤ በሁለተኛው ክፍል ያሉት ደግሞ ከቤተ ክርስቲያን ውስጥም ሆነ ከቤተ ክርስቲያን ውጪ ለተነሡና ለሚነሡ መናፍቃን መልስ በመስጠት የምእመናንን ልቦና ለማጽናት የሚያስችል መልእክት የሚያስተላልፉ ናቸው። ከነዚህ መጻሕፍት ውስጥ ዐምስቱ በቤተ ክህነት አገልገሎት ላይ የተዘጋጁ ሲሆኑ፤ አራቱ ደግሞ ከቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በግፍ ከታገዱበት ከ፲፱፻፹፰ ዓመተ ምሕረት በኋላ የተዘጋጁ ናቸው።

በቤተ ክህነት አገልገሎት ላይ በነበሩበት ጊዜ ያዘጋጇቸው፤ 

የተባሉት መጻሕፍት ሲሆኑ፣ ከሥራ ገበታ ከታገዱ በኋላ በመኖሪያ ቤታቸው ሆነው ያዘጋጇቸው፤ 

የተባሉት ናቸው።

የኢትዮጵያ እምነት በሶስቱ ሕግጋት




#Article 259: ኩሽ (የካም ልጅ) (174 words)


ኩሽ (ዕብራይስጥ፦כּוּשׁ) በኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 10 መሠረት ከኖህ ልጆች መካከል የካም በኩር ልጅ ነበረ። የኩሽ ልጆች ሳባ፣ ኤውላጥ፣ ሰብታ፣ ራዕማና ሰብቃታ ሲሆኑ ከዚህ በላይ የናምሩድ አባት ይባላል።

የአይሁድ ታሪክ መምህር ፍላቭዩስ ዮሴፉስ (100 ዓ.ም. ገደማ) እንደ ጻፉት፣ «ከካም አራት ልጆች፣ እድሜ የኩሽን ስም ከቶ አልጎዳምና፤ እርሱ የነገሠባቸው ኢትዮጵያውያን ዛሬውም ቢሆን በራሳቸውና በእስያም ሰዎች ሁሉ ዘንድ 'ኩሻውያን' ይባላሉና።» 

ከጥንት ጀምሮ ታሪካዊው የኩሽ መንግሥት በአሁኑ ስሜን ሱዳን እንደ ኖረ ሊጠራጠር አይችልም። ይኸው ስያሜ ከቅድመኞቹ የግብጽ መዝገቦች ከ2 መንቱሆተፕ ዘመን (ከ2092 ዓክልበ.) ግድም ጀምሮ ታውቋል። በኋለኛ ዘመን «ኩሽ»ና የግሪክ ትርጉሙ Αιθιοπία (/አይቲዮፒያ/) ከሳህራ ደቡብ ላለው ምድር በሰፊው ይጠቀም ነበር። ደግሞ በአፍሪቃ ቀንድ ዙሪያ የሚኖሩት 'ኩሺቲክ ሕዝቦች' (ሶማሌ፣ አፋር፣ ኦሮሞ፣አገው፣ቅማንት፣ስልጤ፣ጉራጌ፣ሲዳማ፣ጋሞና ሌሎች) ይህን ስም ከዚሁ ኩሽ ተቀበሉ፤ ከተወላጆቹ መሃል ተቆጥረው ነው። አብዛኛው ጊዜ ኩሺቲክ የሚባሉ የቤጃ ሕዝብም ከኩሽ የደረሰ ልዩ የትውልድ ልማድ አላቸው። 

በኢትዮጵያ ታሪካዎ ልማድ ዘንድ፣ አባቱ ካም ከሞተ በኋላ ኩሳ በኢትዮጵያ ለ50 ዓመት ነገሠ፣ ከዚያ ሃባሢ ለ40 አመት፣ ሰብታ ለ30 አመት ነገሡ።

የፋርስ እስላም ታሪክ ጸሐፊ ሙሐመድ እብን ጃሪር አል-ታባሪ በ907 ዓ.ም. እንደ ጻፈው የኩሽ ሚስት የቲራስ ልጅ ባታዊል ሴት ልጅ ቃርናቢል ስትሆን «ሀበሾችን፣ ስንዶችንና ሕንዶችን» ወለደችለት።




#Article 260: ሓሊዞናውያን (154 words)


ሓሊዞናውያን (ግሪክ፦ `Αλιζωνες) በግሪኩ ባለቅኔ ሆሜር ግጥም ኢልያድ የተገኘ መታወቂያው ግን ምስጢራዊ የሆነ ሕዝብ ነበር። በኢልያድ መሠረት በትሮያስ ጦርነት ጊዜ በትሮአስ ሠራዊት ውስጥ የዘመቱ ወገን ነበሩ። መሪዎቻቸውም ኦዲዮስና ኤፒስትሮፎስ ሲሆኑ እሊህ የመኪስቴዎስ ልጆች ተባሉ። ሆሜር እንደሚለው «ከብር ልደት አገር - ከሩቅ አሉቤ» ደርሰው ነበር። 

በኋላ ዘመን የታሪክ ጸሐፊ ስትራቦን ጉዳዩን ለመፍታት ሲሞክር «ከሩቅ አሉቤ» በማለት ፈንታ «ከሩቅ ሓሉቤ» ሆሜር መጻፍ የፈለገ ይሆናል በማለት ግመቱን አቀረበ። ስለዚህ «ሓሊዞናውያን» የሓሉባውያን ስም እንደ ነበር መሰለው። በዚህ አጋጣሚ በሓሉባውያን አገር መካከል ሓሉስ (ሓሊስ) የተባለ ወንዝ ይፈሳል። ከስትራቦን ዘመን በፊት ከ1200ም ዓክልበ. በፊት ኅይለኛ መንግሥት የነበራቸው ኬጢያውያን ደግሞ በዚያው ወንዝ ዙሪያ የብር ማዕድን ሠርተው በዚያን ጊዜ የአገሩ ስም ሓቲ ተብሎ ነበር። ይህም በዛሬው ቱርክ አገር መሃል ይስፋፋ ነበር።

ሌሎች ግሪክ ጸሓፊዎች ግን (ፕሊኒ፣ ሄካታይዎስ ወዘተ.) ሓሊዞናውያን በትንሹ እስያ ውስጥ ለትሮአስ ቅርብ በሆነ ክፍል እንደ ኖሩ ይላሉ። ሄሮዶቶስም በእስኩቴስ መካከል (በዛሬው ዩክራይን) ስለሚኖሩ «ሓሊዞናውያን» ጽፏል።

ቅዱስ አቡሊዴስም በ226 ዓ.ም. በጻፉት ዜና መዋዕል ሓሊዞናውያን የሴም ልጅ ሉድ ተወላጆች እንደ ነበሩ አመለከቱ።




#Article 261: ኑግ (132 words)


ኑግ በሮማይስጥ Guizotia abyssinica በመባል የታወቀው የእህል ዘር የሚሰጥ ተክል ዝርያ ነው። ኑግ ዩናይትድ አስቴትስ ውሱጥ ተወዳጅ የወፍ ምግብ ነው።
ይህን የዘይት እህል በብዛት የሚያመርቱ ኣገሮች ኢትዮጵያና ሕንድ ናቸው ይባላል፣ ሌሎችም አሉ።

ወፎች ስለሚወድዱት ብዙ አገሮችም ያስገቡታል። ዘሩ ወደ ሌላ አገር ሳይገባ ግን የአረም ዘሮች ስላሉበት ጉንቆል እንዳይሆኑ ለ15 ደቂቃ በከፍተኛ ሙቀት እንዲቆይ ይገደዳል።

በደቡብ ሕንድ አበሳሰል በአንዳንድ ወጥ ወይም ስጎ ውስጥ ይገኛል። 

የኑግ ዘይት፣ ቅባኑግ ደግሞ ያስገባሉ፤ በአበሳሰል በወይራ ዘይት ፈንታ ሊጠቀም ይችላል፣ ወይም ሳሙና፣ ቀለም መቀብያ በማዘጋጀት በኢንዱስትሪዎች ይጠቀማል። በተለይ በኢትዮጵያ ቅባኑግን ከማውጣት የተረፈው የዘሩ እንጐቻ ለከብት መኖ ይሰጣል። 

በኢትዮጵያ የተቆለለና የተደቀቀ ኑግ ውጥ በስኳርና በውሃ ጉንፋን ለማከም ይጠቀማል።   የተደቀቀ ኑግና ተልባ ለጥፍ በቆዳ ፋቂም ይጠቀማል።

እንዲሁም የኑግና የመተሬ ዘር ለጥፍ ለኮሶ በሽታ ይሰጣል። ቁንጭር (ሌይሽመናይሲስ) ለማከም የኑግ፣ የነጭ ሽንኩርት ልጥና የኣዞ ሓረግ ቅጠል ተደቅቀው በለጥፍ ትንሽ ሙቅ ተደርጎ ይቀባል።




#Article 262: ቤተ እስራኤል (222 words)


ቤተ እስራኤል በኢትዮጵያ ሲኖሩ የነበሩ የዘር ሃረጋቸው በመጽሐፍ ቅዱስ እንደተገለጸው የአብርሃም የያዕቆብ የይስሃቅ የዘር ሃረግ ሲሆን በኢትዮጵያ ለብዙ ዘመናት ሲኖሩ ቆየተው ከ1984 እ.ኤ.አ. ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ወደ እስራኤል ሃገር በመመለስ ላይ ይገኛሉ።

የመጀመሪዎቹ ቤተ እስራኤላዊያን ከእየሱስ ክርስቶስ ልደት 500 አመት በፊት፤ የመጀመሪያው የሰለሞን ቤተ መቅደስ ከፈረሠ በሗላ፣ ተሰደው ወደ ኢትዮጵያ እንደገቡ ታሪክ ያሳያል።እስከ 4ተኛው ክፍለ ዘመን ድረሥ በኤርትራ እና በተለይ በአክሱም ትግራይ አካባቢዎች ኑረዋል። በ4ተኛው ክፍለ ዘመን፣ በኢትዮጵያ የሀገሪቱ ሀይማኖት ክርሥትና ሁኖ በታወጀበት ወቅት፣ የክርስትና ሀይማኖትን አንቀበልም በማለታቸው፣ በአክሱሙ ንጉስ ዒዛና ከአክሱም ተባረው በወገራ፣ ደምቢያ፣ ጭልጋ፣ ጣና ሀይቅ ዳር፣ እና በሰሜኑ ተራራማ ቦታ ከሰፈሩ በሗላ፥ በህገ ኦሪት የሚመራ የራሳቸውን ስርወ መንግስት አቋቁመው ኑረዋል።ይህ ስርወ መንግስት የሰሜን መንግስታት  (kingdom of Semien,kingdom of Bete Israel) ወይም የጌድኦናዊያን ስርወ መንግስት Kingdom of Gedeon's ተብሎ ይታወቃል።ይህ የቤተ እስራኤላዊያን ስርወ መንግስት፣ ከአክሱም ስልጣኔ መንግስት እና በ13ኛው ክፍለ ዘመን ከተመሠረተው ሰሎሞናዊ ሥርወ መንግስት ጋር ብዙ የጦርነት ውጣ ውረዶችን ያሳለፈ ሲሆን፣ እስከ 16ኛው ክፍለ ዘመንም  ለመዝለቅ ችሏል።ይህ የቤተ እስራኤል ስረወ መንግስትም፣ በ10ኛው ክፍለ ዘመን ድል ቀንቶት የአክሱም ስልጣኔን ካፈራረሠ በሗላ፣ በዮዲት ጌድዖን(ዮዲት ጉዲት) መሪነት ለ40 ዓመታት ያክል ጊዜ ሰፊዋን ኢትዮጵያ  አስተዳድሯል ።

በ10ኛው ክፍለ ዘመን የነበር አንድ ኤልዳድ ሃዳኒ (Eldad Hadani) የተባለ ፃሀፊ፣ በወቅቱ ወደ አንድ ሚልዮን የሚደርስ ቤተ እሰራኤላዊ በዛሬዋ ኢትዮጵያ ይኖር እንደነበር በፅሁፎቹ አስቀምጧል።በጊዜ ሂደት አብዛኛዎቹ ፣ ክርስትናን እየተቀበሉ ቁጥራቸው እየቀነሰ በመሄዱ ዛሬ ወደ 165 ሺህ የሚሆኑ ቤተ እስራኤላዊያን በሀገረ እስራኤል ይኖራሉ።

ቤተ እስራኤል የኢትዮጵያ ብሔር ነው።




#Article 263: ዓፄ ቴዎድሮስ (6537 words)


ዳግማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ (ጥር ፮ ቀን ፲፰፻፲፩ ዓ.ም. - ሚያዝያ ፮ ቀን፲፰፻፷ ዓ.ም.) ከ፲፰፻፵፯ ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ዕለተ ሞታችው ድረስ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ነበሩ። በትውልድ ስማቸው ካሳ ኃይሉ ሲባሉ፣ በፈረስ ስማቸው አባ ታጠቅ፣ በወታደራዊ ስማቸው መይሳው ካሳ እና እንዲሁም አንድ ለናቱ ተብለው የሚታወቁ የ19ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ ወታደርና ፖለቲከኛ ነበሩ። 

ቴዎድሮስ ጥር ፮ ቀን ፲፰፻፲፩ ዓ.ም. ሻርጌ በተባለ ቦታ ቋራ ውስጥ፣ ከጎንደር ከተማ በስተ ምዕራብ ተወለዱ። የተወለዱትም አገሪቷ በባላባቶች ተከፋፍላ በምትመራበት-ዘመነ መሳፍንት በሚባለው ወቅት ነበር። አባታቸው ደጃዝማች ኃይሉ ወልደ ጊዮርጊስ የቋራ ገዢ ነበሩ። ዓፄ ቴዎድሮስ በህጻንነታቸው የቄስ ትምህርት ከቀሰሙ በኋላ፣ የአጎታቸውንና በኋላም ለጥቂት ጊዜ የጎጃሙን ጦር መሪ የጎሹ ዘውዴን ጦር ተቀላቀሉ። በዚሁ የውትድርና ዘመናቸው ከፍተኛ ችሎታን ማስመዝገብ ስለጀመሩና ዝናቸው ስለተስፋፋ በ፲፰፻፴፱ ዓ.ም. በወይዘሮ መነን ሊበን አምዴ አነሳሽነት የልጇን የራስ አሊ አሉላን ልጅ፣ ተዋበች አሊን ተዳሩ፤ እንዲሁም በደጃዝማችነት ማዕረግ የቋራ አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ። ቴዎድሮስ ግን በ፲፰፻፵፬ ዓ.ም. አጠቃላይ የዘመነ መሳፍንት ሥርዓትን በመቃወም በሰሜናዊ ባላባቶች ላይ ዘመቻ ጀመሩ። በኒህ ተከታታይ ዘመቻወች የገጠሟቸውን ባላባቶች ስላሸነፉ፣ መጀመሪያ የራስ ማዕረግን በኋላም የንጉሥ ማዕረግን በአንድ ዓመት ውስጥ ተቀዳጁ። በየጊዜው በሚያደርጉት የተሳካ ዘመቻ የዘመኑን ባላባቶች ኃይል በመሰባበር የካቲት ፫ ቀን ፲፰፻፵፯ ዓ.ም ንጉሥ ካሳ - ዳግማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ ተብለው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ሆኑ። 

ሥርዓተ ንግሡ የዘመነ መሳፍንት መቃብር በመሆን የዘመናዊ ኢትዮጵያን ታሪክ ሀ በማለት ጀመረ። ዓፄ ኃይለ ስላሴ እስከ ፈጸሙት ድረስ ኢትዮጵያን አንድ የማድረግ ሥራም በዚሁ ወቅት ተጀመረ። ዓፄ ቴዎድሮስ ሰሜናዊ ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን አንድ ለማድረግ የሞከሩት፣ አጠቃላይ በታሪክ የሚታወቀውን የኢትዮጵያ ክፍል ነበር - ለዚህም ዋቢ ወደ ወሎና ወደ ሸዋ ያደረጓቸው ዘመቻወች ይጠቀሳሉ። 

በዘመነ ንግሣቸው ዓፄ ቴዎድሮስ አገሪቱን የሚያሻሽሉ ሥርዓቶችን ለአገራቸው አስተዋውቀዋል። ከነዚህም ውስጥ፡ ባርነትን የሚያግድ አዋጅ፣ የመጀመሪያው መንገድ ግንባታ፣ የሥርዓተ ንዋይና የፖለቲካ ሥርዓቱን በማዕከላዊ መንገድ ማዋቀር፣ የባላባት የተከፋፈለ ሁሉ-በሁሉ-ጦርነት ሥርዓትን በማስቀረት ብሔራዊ ውትድርናን ማስተዋወቅ ይጠቀሳሉ። በዘመነ መሳፍንት እንደልባቸው ይፈልጡ ይቆርጡ በነበሩ ባላባቶች ዘንድ እኒህ ለውጦች እጅግ የተጠሉ ሆኑ። በ፲፰፻፶ ዓ.ም. ብዙወቹ ባላባቶች አመጽ ማነሳሳት ጀመሩ። በ፲፰፻፶፪ ዓ.ም ንጉሠ ነገሥቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ርስት የነበረውን መሬት ለገበሬወች በማከፋፈላቸው ከሃይማኖት መሪወች ጋር ተጣሉ። ይህን ተከተሎ በየቦታው አመጽ በሚነሳበት መካከል አውሮፓውያን ሚሲዮኖችም ከእንግሊዝ መንግሥት ጋር በተነሳሳ አለመግባባት ምክንያት በዓፄው ታሰሩ። 

በመጋቢት ወር ፲፰፻፷ ዓ.ም ላይ የእንግሊዝ መንግሥት በሮበርት ናፒየር የሚመራ፣ በጊዜው እጅግ ግዙፍ የተባለ ኃይልን አሰናድቶ አውሮፓውያን እስረኞችን ለማስፈታት ጦር ላከ። መጋቢት ፭ ቀን ፲፰፻፷ ዓ.ም ይህ ጦር በመቅደላ ምሽግ ላይ በሚገኘው፣ በአመጽ በተዳከመ የንጉሱ ጦር ላይ ጥቃት አደረሰ። በውጊያው መሃል ንጉሠ ነገሥቱ እጃቸውን እንዲሰጡ ቢጠየቁ እስከመጨረሻው አሻፈረኝ በማለት በሽጉጣቸው እራሳቸውን ገድለው በጀግንነት አለፉ። ዓፄ ቴዎድሮስ ያሰቡትን ለውጦች በሙሉ በተግባር ቢፈጽሙ ኖሮ በእርግጥም ታላቅና የሰለጠነ ሀገር መሪ ሊሆኑ ይችሉ እንደነበር ታሪክ ተመራማሪወች ይስማማሉ። ዕቅዳቸው በዚህ መልኩ ቢሰናከልም፣ እጅግ ድንቅ መሪ፣ የተዋጣላቸው ወታደርና የተባበረች ዘመናዊ አገር ራዕይ አብሳሪ እንደነበሩ ያሰሯቸው አውሮጳውያን ሳይቀር ሳይመሰክሩ አላለፉም።

የዙፋን ስማቸው «ቴዎድሮስ»ን የወሰዱት ከፍካሬ ኢየሱስ ከተገኘ ትንቢት ነበረ። በዚያው ትንቢት በኩል፣ በዓለም መጨረሻው ክፍለ ዘመን፣ ተወዳጁ፣ የጥንቱ ዘመን ንጉስ ቀዳማዊ ቴዎድሮስ እንደገና ተነስቶ አገሪቱን ለ፵ ዓመታት ይገዛል የሚል ነበር። ቴዎድሮስ የሚለው ስም ከግሪክ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም «ጤዎስ ዶሮስ»፣ 'የአምላክ ስጦታ' ማለት ነው።

ዓጼ ቴወድሮስ የቋራ አስተዳዳሪ የነበሩት ደጃዝማች ኃይለ ጊዮርጊስ ወልደ ጊዮርጊስ (ባጭሩ ኃይሉ ወልደ ጊዮርጊስ) ልጅ ናቸው። እናታቸው ወይዘሮ አትጠገብ ወንድበወሰን ሲባሉ አመጣጣቸውም ከጎንደር ከተማ ባላባቶች ነበር። የወይዘሮ አትጠገብ እናት ወይዘሮ ትሻል ስትባል የበጌምድር ክፍል መሳፍንት ዘር ነበረች፣ በአባቷ በኩል አያቷ ራስ ወዳጆ በዘመናቸው ከፍተኛ ተሰሚነት የነበራቸው ባላባት ነበሩ። የወይዘሮ አትጠገብ ድህነት በታሪክ መጻህፍት በተደጋጋሚ የሚጠቀስ ቢሆንም አመጣጡ እንዲህ ነበር፡ የህጻኑ ቴወድሮስ አባት ደጃች ሃይሉ ወልደ ጊዮርጊስ ከሱዳኖች ጋር በተነሳ ጦርነት በጀግንነት ሲወድቁ እናት ገና ሁለት አመት የሆነውን ልጇን ይዛ ከቋራ ወደ ጎንደር ከተማ ሄደች። በዚህ ወቅት ሁለተኛ ላታገባ በመቁረብ ልጇን ብቻዋን ማሳደግ ግድ አላት። አንዳንዶች በዚህ ምክንያት እራሷን ለማስተዳደር ኮሶ ትሸጥ ነበር ሲሉ ጸሃፊው ጳውሎስ ኞኞ ወይዘሮ አትጠገብ መቼውንም ኮሶ አትሸጥም ነበር ይላል (ኮሶ ትሸጥ ነበር የሚለው የልጁ ጠላቶች ፈጠራ ወሬ ነበር በማለት ያስረዳል)። ሆኖም ቀረ ህጻኑ ቴወድሮስ በድህነት እንዳላደገ ሁሉም የታሪክ ጸሃፊያን ይስማማሉ።

አንድ ለናቱ ቴወድሮስ በእናቱ በኩል እህትም ሆነ ወንድም አልነበረውም። የወደፊቱ አጼ ቴዎድሮስ በ፲፰፻፴፱ ዓ.ም. ተዋበች አሊ የተባለችውን የዘመነ መሳፍንት ታላቅ ባላባት፣ የራስ አሊ አሉላን፣ ልጅ አገባ። ተዋበች በጊዜው የ፲፭ ዓመት ወጣት የነበረች ሲሆን ቁንጅናዋና አስተሳሰቡዋ በጊዜው በነበሩ ሰወች ዘንድ የተደነቀ ነበር። ሁለቱ በፍቅር በመውደቃቸው ቴወድሮስ በአባቷ ራስ አሊና በአያቷ እቴጌ መነን ላይ ሲያምጽ ባሏን ትደግፍ ነበር። 

አጼ ቴወድሮስ የሚስታቸውን መታመም ከዘመቻ መልስ በ፲፰፻፵፰ ዓ.ም ላይ ከሰሙ በኋላ እቴጌ ተዋበች በ፲፰፻፶ አረፉ። በኃዘኑ ወቅት 

ብለው እንደተቀኙ በታሪክ መዛግብት ሰፍሮ ይገኛል።

ከሁለት ዓመት ሀዘን በኋላ በ፲፰፻፶፪ ዓ.ም ዓፄ ቴዎድሮስ ከሁለተኛ ሚስታቸው ጋር ተገናኙ። «ደራስጌ ቤተክርስቲያን ውስጥ ተቀምጠው ሳለ አንድ ወታደራቸው ወደ ርሳቸው ቀረበና «ጌታየ፣ አንዲት ሴት አገኘሁ፣ ፊቷም እንደ ፀሐይ የሚያበራ ነው።» ልጅቱም በኋላ ወደ ቤተመንግሥት ቀረበች፣ ስሟም ጥሩነሽ ውቤ፣ የደጃዝማች ውቤ ኃይለማርያም ልጅ ነበረች። ንጉሱም አይተዋት እውነትም ወርቅ ናት በማለት አገቧት። በዚህ ወቅት ንጉሠ ነገሥቱ አባቷን ራስ ውቤን አስረዋቸው ነበር። ራስ ውቤ የሰሜን፣ወልቃይት ፣ፀገዴ፣ትግራይ፣ ሰራየ፣ ሐማሴንና አንጎት (ሰሜን ወሎ) አስተዳዳሪ ሲሆኑ ከዓፄ ፋሲለደስ የሚወለዱ ስለነበሩ ለንጉሥነት የሚገዳደሩ ነበሩ። የጥሩወርቅ (ጥሩነሽ) እናት ደግሞ ወይዘሮ ላቂያየ የተባሉ የትግራይ መሳፍንት ዘር ነበሩ። ከኒህ ሚስታቸው ደጃዝማች ዓለማየሁ ቴዎድሮስ የተባለውን ከሁሉ በላይ የሚወዱትን፣ እርሳቸውን እንዲተካ ያጩትን ልጅ ወለዱ።
ዓፄ ቴዎድሮስ በአጠቃላይ ፬ ጊዜ ሲያገቡ ፮ ወንድና ፫ ሴት ልጆች ነበሯቸው፣ እነርሱም፦

ካሳ ኃይሉ በ1811 ዓ.ም. አባታቸው ሃይሉ ወልደ ጊዮርጊስ በሚያስተዳድሩት ቋራ፣ ከእናታቸው ወይዘሮ አትጠገብ ተወለዱ።  ቋራ በምዕራቡ ኢትዮጵያ ከሱዳን ድንበር የሚገኝ ሲሆን በዘመኑ ከሱዳኖችና ክግብፆች ዘንድ ብዙ ወረራ ይደርስበት የነበር ክፍል ነው።  ደጅ አዝማች ሃይሉ ወልደ ጊዮርጊስ ከሱዳን ጋር በተደረገ ጦርነት ሲያልፉ፣ በ1813 ዓ.ም ወይዘሮ አትጠገብ ህጻኑን ቴወድሮስ ይዘው ወደተወለዱበት ጎንደር ከተማ ተመለሱ።  
ይህም በህጻኑ ላይ የማይጠፋ የአይምሮ ጠባሳ ትቶ ያለፈ ኩነት ነበር።  ማንበብና መጻፍን በዚሁ ወቅት በሚገባ ተለማመደ።  የወደፊቱ ቴወድሮስ እጅግ ማንበብን የሚወድ ሰው ነበር፣ የኢትዮጵያን ጥንታዊና ጊዜያዊ ድርሳናትን፣ የአውሮጳን ጥንታዊ እና ጊዚያዊ ታሪክ በደንብ እንዳጠና መረጃ አለ። የሼክስፒርን ስራወችና መጽሃፍ ቅዱስን ሳይቀር እንዳጠና በጊዜው የነበሩ አውሮጳውያን ሳይመዘግቡ አላለፉም። ለነበረበት ዘመን በደንብ የተማረ ሰው ነበር።

የደምቢያ አስተዳዳሪ የነበሩት ደጃዝማች ክንፉ ምንም እንኳ ቴወድሮስን ለዘመቻ ይዘውት ቢውጡም ግዛታቸውን ከካሳ ይልቅ መኮንን ለተባለ ልጃቸው ለማውረስ በመፈለጋቸው ግንኙነታቸው የሻከረ ሆነ። በ1839 ደጃች ክንፉ ካረፉ በኋላ የክንፉ ሁለት ልጆችና ካሳ ሆነው የዳሞትና ጎጃም ገዢ በነበሩትን ደጅ አዝማች ጎሹ ዘውዴን ጦርነት ገጥመው ተሸነፉ። ልጅ ካሳ በጦርነቱ ባይማረክም ብዙ ወራት በሽሽት ከቆየ በኋላ የአሸናፊውን ደጃች ጎሹን ጦር በመጨረሻ ተቀላቀለ። ምንም እንኳ የውትድርና ብቃትን ቢያሳይም በደጃች ጎሹ ሰራዊት ውስጥ እድገትን ስላላገኘ ወደ ቋራ ተመለሰ።። ሆኖም ወይዘሮ መነን ሊበን አምዴ አጠቃላይ ደምቢያን የግሏ ርስት አድርጋ ነበር። በዚህ ምክንያት የመነን ሊብን ተወካይ ገዢወች ወጣቱን ካሳ ከቋራ እንዲለቅ ይወተውቱት ነበር። ካሳም የተነጠቀውን የአባቱን ርስት ለማስለመስ ያለው አማራጭ አመጽ በመሆኑ ወደቆላ ወርዶ ሸፈተ።

ካሳ እንደሌሎች ሽፍቶች ሳይሆን በደግነቱና በፍርድ አዋቂነቱ እራሱን ለየ። ለምሳሌ በሽፍትነት የሚያገኘውን ገንዘብ ለገበሬወች እያከፋፈለ ሞፈርና ቀንበር እንዲገዙ ይረዳ ነበር። ይህ አይዞህ ባይነትና ደግነት ለወጣቱ የፖለቲካ መሰረት ሲያስገኘው ከጊዜ ወደጊዜ ደጋፊወቹ እንዲበራከቱ አደረገ። በ12 ሰወች የተጀመረው አመጽ በጥቂት ጊዜ 300 ጦረኞችን ሰበሰበ። ተከታዮቹ እየበዙ ሲሄድ በጣም የተሳካ የጦር ስልት መከተል ጀመረ፣ ስልቱም እንዲህ ነበር፡ ያልተጠበቀ ዘመቻውን ቀን ላይ ካወጀ በኋላ ከ5 እስከ 600 ፈረሰኞቹ ጋር ሆኖ ሌሊቱን ሲጓዝ ያድርና ጠዋት ላይ ጠላቶቹ ላይ በድንገት ይደርሳል። ዱብዳው ጦርነትም በካሳ አሸናፊነት ይፈጸማል። በዚህ ሁኔታ በ1829 ዓ.ም. የካሳ ጦር ሱዳን ጠረፍ ደረሰ።
 

የካሳ ሽፍቶች በነጋዴወች ላይ የሚያካሂዱት ጥቃት በተዘዋዋሪ የእቴጌ መነንን (በጊዜው የሳልሳዊ አጼ ዮሃንስ ባለቤት) የቀረጥ ገቢ ቀነሰ። በዚህና እየጎላ በመጣው የካሳ ዝና ምክንያት የየጁ ባላባት ምን እንዲያደረጉ ግራ ገባቸው። ችላ እንዳይሉት ችሎታ አለው፣ እንዳይወጉት ጥሩ ተዋጊ ነው።  ስለሆነም ወይዘሮ መነን ለቴወድሮስ በመስፍን ማዕረግ የልጇን የራስአሊ አሉላን ጦር እንዲቀላቀል ጋበዘችው።  ካሳም ያለውን ጥንካሬ ግምት ውስጥ በማስገባት ለመነን ባቀረበው ጥያቄ መሰረት የራሱን ሰራዊት እንደያዘ የቋራ አስተዳዳሪ ሆኖ ተሰየመ። በዚያውም የራስ አሊን ልጅ ተዋበች አሊን በ1839ዓ.ም. አገባ። አዲስ ማዕረግ የተጎናጸፈውን የልጁን ባል ራስ አሊና እናቱ ወይዘሮ መነን ድሃ አደግነቱን አስመልክተው ንቀት በተሞላው መልኩ ያስተናግዱት ነበር። ከዚህ በተረፈ የመነን ርስት የሆነ ደምቢያም የቋራን ክፍሎች ስለያዘ የቋራ ገቢ በጣም አንስተኛ ነበር። በዚህና መስል ምክንያቶች በሚስቱ ድጋፍ በመነን ላይ አመፀ፣ ስሙንም አባ ታጠቅ በማለት ደምቢያን ወረረ። የቴወድሮስን ወርራ አድገኛነት ያልተረዳችው ወይዘሮ መነን በደጅ አዝማች ወንድይራድ የሚመራ አንስተኛ ሃይል አድርጋ ጦር ላከችበት። ይህ ጦር ሁለት ጊዜ በቴወድሮስ ተሸነፈ። በምስራቅ፣ በጎጃም መነንና ልጇ አሊ በጦርነት ተጠምደው ስለነበር የጎንደር ከተማን ለቀው ወደጎጃም ጦራቸውን ይዘው ዘመቱ።

የተገኘውን አጋጣሚ በመጠቀም ጥር 1840 ላይ የጎንደር ከተማን ቴወድሮስ ተቆጣጠረ። የራሱን ባለስልጣኖች በከተማው ላይ ከሾመ በኋላ ለአሊ ይገባው የነበርውን ግብር ሰበሰበ፣ ቀጥሎም ከነገስታቱ ጎተራና ከከባቢውም መንደሮች እህልን መዘበረ። ከጎጃም መልስ፣ በጣና ሃይቅ በስተሰሜን በተደረገ ጦርነት እቴጌ መነን ጭኗ ላይ ቆስላ ከባሏ ከሳልሳዊ አጼ ዮሃንስ ጋር በቴወድሮስ ታሰረች። እኒህ እሰርኞችን ለማስለቀቅ በተደረገ ውይይት ቴወድሮስ የደጅ አዝማችነትን ማዕረግ ከራስ አሊ አገኝ። እንዲሁም ደምቢያ ለቋራ ተመልሰ። በአንጻሩ ቴወድሮስ የአሊን ሰራዊት ልዋሃድ ተስማማ።

ቴወድሮስ የመጀመሪያው የዘመናዊ ጦር መሳሪያ ውጊያ የገጠመው በዚሁ በደጅ አዝማችነት ወራት ነበር። ደባርቅ ላይ ሰፍሮ የነበረውን በሙሃመድ አሊ የሚመራ የግብጽ ወራሪ ሃይል ለማጥቃት ከ16፣000 ሰራዊት ጋር መጋቢት 1840 ላይ ዘመቻ አድርጎ፣ ምንም እንኳ የርሱ ሃይሎች ቁጥር ከግብጾቹ ቢበልጥም በግብጾቹ ዲሲፕሊንና ዘመናዊ ጦር መሳሪያ ምክንያት ተሸነፈ። ይህ ጉዳይ ቴወድሮስን እጅጉን ያስደነቀ ኩነት ነበር። ከዚህ በኋላ ነበር ቴወድሮስ ዘመናዊ ጦር መሳሪያን ለማግኘትና ዘመናዊ የጦር ስልትን ለመማር ከፍተኛ ፍላጎት ያደረበት።

ቴወድሮስ ከሱዳን ጋር ለጦርነት በወጣበት ወቅት ቋራ ላይ ይዘርፉ የነበሩትን አማጺወች ሲመለስ ቀጣ። በዚህ መንገድ የቋራ ግዛቱን ካጸና እኋላ ከከባቢው ተገዳዳሪወች ይበልጥ ጠነከረ። ጥር 1840 ላይ ራስ አሊ ቴወድሮስ ወደ ደብረ ታቦር እንዲመጣ ለሁለተኛ ጊዜ ቢልኩበትም ባለመሄዱ በሁለቱ መካከል የመጀመሪያው ጥል ታየ። ከ1841- 42 ለተወሰነ ጊዜ በአገው ምድር ዘመቻ ካደረገ በኋላ ወደ ቋራ ተመለሰ። 1844 ላይ ከራስ አሊ ጋር ፊት ለፊት በመጋፈጥ ወደ ዙፋን የሚያደርገውን ጉዞ ጀመረ።

ከዚህ ዓመት በኋላ ታላላቅ የዘመነ መሳፍንት ባላባቶችን ተራ በተራ በመውጋት አሸነፋቸው። በኒህ ጦርነቶች የላቀ የውጊያ ስልትንና ጥበብን በማሳየት ወታደራዊ ብቃቱን አስመዘገበ።  በ1844 መጨረሻ አካባቢ ከራስ አሊ ጋር የገባውን ውል ሙሉ በሙሉ በማፍረስ ራስ አሊ ወደ ጎጃም ሊያደርገው በነበርው ዘመቻ እንደማይሳተፍ አስታወቀ። ራስ አሊም ለብዙ ወራት ጦር በመላክ ቴወድሮስን በቋራ ውጊያ ገጠመው 7። በስተመጨረዣ መስከረም 1845 ላይ አሊ ጎሹን የቋራ ገዢ አድርጎ በቴወድሮስ ላይ ሾመበት። ይህ አዲሱ ሹም ቴወድሮስን ለመግጠም ወደቋራ ከሰራዊቱ ጋር ተመመ።

ጥቅምት 27፣ 1845 ላይ ቴወድሮስ የድሮ አለቃውን የጎጃም ባላባት ደጅ አዝማች ጎሹ ዘውዴን በጉር አምባ ጦርነት ገጥሞ አንድ ቀን ሙሉ በተደረገ ውጊያ ደጅ አዝማች ጎሹ ስለወደቁ በቴወድሮስ አሸናፊነት ተጠናቀቀ። ይህ በጊዜው እንደ ታላቅ ድል የታየ ሲሆን ጉር አምባ ለጎንደር ከተማ በጣም የቀረበ ቦታ ስለነበር የቴወድሮስን የወደፊት ምኞት ያመላከተ ጦርነት ነበር። በዚህ ድል የተደናገጠው ራስ አሊ ምንም እንኳ ከቴወድሮስ የዕርቅን መልዕክት ቢላክለትም የጎንደር ከተማን ለቆ ወደ ደብረ ታቦር አመራ። ቴወድሮስ ብዙም ሳይቆይ የጎንደር ከተማን ያዘ። 

ራስ አሊ ደብረ ታቦር ላይ ሆኖ የየጁን፣ የወሎና የትግራይን ጦር አንድ አድርጎ ቴወድሮስን ለመውጋት ለ3ቱም ክፍሎች ጥሪ አደረገ። ጥር 1945 ላይ የትግራዩ ባላባት ደጅ አዝማች ውቤ ከራስ አሊ ጋር ትብብር እንደፈጠሩ ሰማ፡ ይህ በዘመኑ የሁለት ታላላቅ የተባሉ ሰራዊቶች ቅንጅት ነበር። መጋቢት ላይ የጠላት ጦር ወደርሱ እየመጣ እንደሆነ መረጃ በማግኘቱ ከጎንደር ከተማ 3ሰዓት የእግር ጉዞ ላይ ባለው በ ጎርጎራ ቢሸን ላይ ሰራዊቱን አሰፈረ። ሚያዚያ12፣ 1845 ላይ በዚሁ ቦታ በተደረገ ጦርነት በየጁው ደጅአዝማች ብሩ አሊጋዝ የሚመራው ጦር እንዳለ ተደመሰሰ። በዘመነ መሳፍንት ላይ ጦርነት የከፈተው ካሳ በጦርነቱ የራስ አሊንና የደጅ አዝማች ውቤን ሶስት ደጅ አዝማቾች ገደለ። ከዚህ ድል በኋላ ወደ ጎንደር ከተማ ተመልሶ የተቀሩትን ሁለቱን መሪዎች ፣ ውቤንና አሊን፣ ለመደምሰስ ይዘጋጅ ጀመር።

ግንቦት 1845 ላይ ደብረ ታቦር ላይ ዘመቻ አድርጎ ከተማይቱን መዘበረ። አማቱን ራስ አሊንም ቢያሳድደው ጎጃም ላይ መሸገ። ቀጥሎም በሰኔ29፣ 1845 ላይ አይሻል በተባለ ቦታ ጦርነት ገጥመው ቴወድሮስ ራስ አሊን አሸነፈ፣ እቴጌ መነን ሊበንንም ማረከ። የአይሻል ጦርነት በዘመኑ እጅግ በደም የጨቀየ አስክፊ ጦርነት ነበር። ብዙ ታሪክ አጥኝወች ይህ የአይሻል ጦርነት የዘመነ መሳፍንት ማብቂያ እንደሆነ ይስማማሉ። 

ከዚህ በኋላ ሁሉ በሁሉ ጦርነት የሚከፍትበትና ሃይለኛ ባላባቶች ተቀራምተው አገሪቱን የሚያስተዳድሩበት ዘመነ መሳፍንት አበቃለት። በዚህ ወቅት እንደ ጥንቱ አንድ ጠንካራ ሰው ከሌሎች ልቆ አገሪቱን የሚያስተዳድርበት ሁኔታ ተፈጠረ። ከአይሻል ጦርነት በኋላ ራስ አሊ ወደ የጁ ሸሹ፣ 1848 ላይ በዚያው በየጁ አረፉ። ከ18ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ጀመሮ የገነነው የየጁ ሃይልና የራስ አሊ ጥንካሬ አይሻል ላይ አበቃ። ከዚህ ድል በኋላ ቴወድሮስ የመላው ሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ መሪ ቢሆንም ቅሉ አጠቃላይ መሪ ለመሆን የተቀሩትን የሰሜን ባላባቶች ማሸነፍ ነበረበት። ግንቦት 1846 አምባ ጄበል ላይ ከጎርጎራ ቢሸን ጦርነት አምልጦ የነበረውን ብሩ ጎሹን ተዋግቶ በመማረክ ለሚለቀጥሉት 14 አመታት እስረኛው አደረገው። ትንሽ ቆይቶም ቴወድሮስ የላስታውን ፋሪስ አሊን ደመሰሰ።

በወቅቱ ዙፋን ላይ ለመውጣት አንድ ቀሪ እንቅፋት በቴዎድሮስ ላይ ተጋረጠ፣ እርሱም የሰሜኑ ደጃዝማች ውቤ ነበር። ከአይሻል ጦርነት በኋላ ራሱ ውቤ ከቴወድሮስ ጋር እርቅን በመሻት የተለያዩ ስጦታን ላከለት። ቴዎድሮስ በላስታና በጎጃም ቀሪ ዘመቻወችን ሲያደርግ ከኋላው በሰሜውን ውቤ ጦር እንዳይከፍትበት ሲል የውቤን ስጦታወች ተቀበለ። በዚህ ስምምነት መሰረት የቴዎድሮስ ሰራዊት ትግራይን መልቀቅ ጀመረ ሆኖም ግን አቡነ ሰላማ ከትግራይ ወደ ጎንደር እንዲመጡ አደረገ። አቡነ ሰላማ ከግብጽ የመጡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን ፓትሪያርክ ነበሩ። ደጅአዝማች ውቤ እራሳቸውን ለማንገስ ከግብጽ ያስመጧቸው ነበሩ። የቴወድሮስ አላማ አቡነ ሰላማን ከርሱ ዘንድ በማድረግ የቤተክርስቲያኗን ፈቃድ ለማግኘትና አገሪቷን እንደገና ለመገንባት ነበር። ወዲያውም ቴወድሮንና አቡነ ሰላማን የሚያግባባ አንድ አላማ ተገኘ ፡ አንዲት ጠንካራ ቤ/ክርስቲያን በአገሪቱ እንዲኖር ማድረግ። በዘመኑ ሶስት ልደት የሚባል ትምህርት ተነስቶ ይህን ሃሳብ በሚያነሱና በተዋህዶ ተከታዮች መካከል ከፍተኛ ክርክር ነበር። ይህን ክፍፍል ለማስወገድ ሐምሌ 1846 ላይ በቴዎድሮስ የሚመራ የአምባ ጫራ ጉባኤ ተጠራ። ለተዋህዶ ተቃዋሚወች ቴወድሮስ ጠየቃቸው፡ አቡነስ ሰላማን እንደመሪያችሁ ታውቁታላችሁ? እነርሱም ለስወ አዎ አሉት። ያን ጊዜ መልሶ ጠየቃቸው፡ እንኪያስ ልጆቼ ከአቡኑ የተለየ የሚያስተምሩ መናፍቅ ናቸው ። ከዚህ በኋላ ለ3 ቀን ያለምግብና መጠጥ ትቷቸው ሄደ፣ ከዚህ በኋላ ጥፋታቸውን አመኑ። ከዚህ ስምምነት በኋላ የሶስት ልደት ትምህርት ኑፋቄ ተባለና የተዋህዶ ትምህርት የአገሪቱ ብቸኛ ትምህርት ሆነ ። እኒህን ለውጦች በመፈጸሙ ከአቡነ ሰላማ ጋር ያለው ግንኙነት እጅግ ጥሩ ሆነ። በ1846 መጨረሻወቹ ቴዎድሮስ ንጉስ ተብሎ በአቡነ ስላማ ተቀባ። ቴዎድሮስና ተዋበችም ጋብቻቸውን ህጋዊ በማድረግ ቆረቡ።

የቴዎድሮስን ንጉስ መሆን ደጅአዝማች ውቤ ሊቀበለው አልቻለም። ስለሆነም ቴወድሮስን ለመውጋት ዝግጅት ማደርግ ጀመረ። በዚህ ምክንያት ቴዎድሮስ ያለመንም ችግር ሰሜንን በመውረር ከትግራይ የካቲት 9፣ 1847 የተነሳውን ውቤን ደራስጌ ላይ ገጠመው። ደራስጌ የደጅ አዝማች ውቤ ዋና ከተማ የነበር ቢሆንም በዚህ ጦርነት ተሸነፈና ተማረከ። ከሁለት ቀን በኋላ ቴወድሮስ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገሥት ተብሎ አክሊል ጫነ።

ከብዙ መራራ ትግል በኋላ የሰሜን ተፎካካሪወቹን ያስወገደው። ንጉስ ካሳ ሃይሉ የካቲት 11፣ 1847 ዓ.ም. ንጉሰ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ተብለው ዘውድ ጫኑ፣ ስማቸውም ዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ ተባለ። ስርአተ ንግሱ የተከናወነው በደራስጌ ማርያም ቤተክርስቲያን ሲሆን የዓለምን ተገልባጭ ዘይቤ በሚያሳይ መልኩ ይኸው ቤ/ክርስቲያን ደጃዝማች ውቤ ለራሳቸው ስርዓተ ንግስ ሲሉ ያስሩት ነበር፣ ስርዓተ ንግሱንም የፈጸሙት አቡነ ሰላማ ሲሆኑ እኒሁ ጳጳስ ከግብጽ በደጅ አዝማች ውቤ ለራሳቸው ንግስና የመጡ ነበሩ። 

አጼ ቴዎድሮስ በመጀመሪያወቹ የአገዛዝ ዘመናቸው ራሳቸውን ከሰሎሞናዊው ስርወ መንግስት የተለዩ እንደሆነ ለማሳየት ሞክረዋል ይህም በዘመነ መሳፍንት የደረሰው የግብረገብና ፖለቲካ መላሸቅ ምክንያት ስርወ መንግስቱ በህዝቡ ዘንድ ዋጋው ረክሶ ነበር ። በዚህ ምክንያት የአጼ ቴወድሮስ የመጀመሪያወቹ የአገዛዝ ዘመናት ከ1270ዓ.ም. ይኩኖ አምላክ ጀምሮ ሲወርድ ሲዋርድ የመጣውን የአገሪቱን አሰራር በጭንቅላቱ የደፋ ነበር። ሆኖም ግን በኋላ ላይ አጼ ቴዎድሮስ በእናታቸው የአጼፋሲለደስ ዘር እንደሆኑ ለማሳየት ሞክረዋል፣ ስለሆነም በአጠቃላይ መልኩ በአሁኑ ዘመን የሰለሞናዊ ስርወ መንግስት አካል እንደሆኑ ይጠቀሳል ። የአጼ ቴዎድሮስ ዙፋን ላይ መውጣት በ1845 በአይሻል ጦርነት ተጀምሮ የነበረውን የዘመነ መሳፍንት ስርዓተ ቀብር አጠናቋል። ብዙ ታሪክ ተመራማሪወች የካቲት11፣ 1847 የዘመናዊት ኢትዮጵያ ታሪክ ጅማሬ እንደሆነ ይስማማሉ 2። ሪቻርድ ፐንኸርስት እንደጻፈ፡የካሳ ሃይሉ ከፍ ማለት አዲሱን የኢትዮጵያ ታሪክ የከፈተ ክስተት ነበር 3። 

አጼ ቴዎድሮስ የዙፋን ስማቸውን የመረጡት ከፍካሬ እየሱስ ሲሆን ይህ መጽሃፍ የሚያትተው ስለሚመጣው አለምና በ15ኛው ክፍለ ዘመን ስለነበረው በዘመኑ ኢትዮጵያውያን ዘንድ እጅግ ተወዳጁ ስለነበር ንጉስ ቀዳማዊ አጼ ቴወድሮስ ስርዓት እንደገና በኢትዮጵያ መንሰራፋት ነበር። ይሄው የጥንቱ ንጉስ፣ ምንም እንኳ የአገዛዙ ዘመን እጅግ አጭር ቢሆንም፣ የፈጸመውም ጥሩ ተግባራት በታሪክ ጅረት ተሽርሽሮ ቢጠፋም በጥንቶቹ ኢትዮጵያውን ዘንድ ምንጊዜም የማይረሳ ተወዳጅ ንጉስ ነበር። ከሰራቸው ስራወች አንዱ ከይኩኖ አምላክ ጀምሮ ለቤተክርስቲያን ሲወርድ ሲዋርድ የመጣውን የቤተክርስቲያን መሬት ለገበሬወች ማከፋፈሉ ነበር። በፍካሬ እየሱስ መሰረት፣ ቀዳማዊ ቴዎድሮስ እንደገና ከሞት ይነሳና ፍትህና ሰላም አስፍኖ ሁሉም ከሚፈጠረው ደስታና ሰላም ተካፋይ የሚሆንበት ግዛት ያንሰራፋል የሚል ነበር ። በ1830ዎቹ የዘመነ መሳፍንት ጦርነቶች በተሰቃየው ህዝብ ዘንድ ይህ የፍካሬ እየሱስ ትንቢት ከመንደር መንደር የገነነ ነበር። 

አጼ ቴዎድሮስ፣ ይህ የአገሪቱን የታሪክ አቅጣጫ የሚቀይር የሚመጣው ንጉስ ነኝ ብለው ያምኑ እንደነበር ለማመን አይከብድም 7። በስርዓተ ንግሳቸው ላይ ባደርጉት ንግግር አገሪቷን አንድ ለማድረግና እንደገና ለመገንባት ያላቸውን ከፍተኛ ፍላጎት ገልጸዋል። የቴወድሮስን የህይወት ታሪክ የጻፈው ስቬን ሩቤንሰን አፄ ቴወድሮስ ስልጣን ላይ ሲወጡ በአይምሮአቸው ውስጥ የነበረውን ዕቅድ እንዲህ ሲል ይዘግባል፡ 

ከሁለት አመት የማያቋርጥ ዘመቻ በኋላ የነገሱት አጼ ቴወድሮስ ለማረፍ አልፈለጉም፣ እንዲያውም ዋናዋና ታላቁ ግባቸውን እውን ለማድረግ ወደ ደቡቡ ታሪካዊ የኢትዮጵያ ክፍል መዝመት ግድ አላቸው 9። የሰሜኖቹን ባላባቶች በማሸነፍ ብቻ አለመታቀባቸው በታሪክ ጸሃፊው ባህሩ ዘውዴ ዘንድ ንጉሱ ሰፋ ያለ ራዕይ እንደነበራቸው የሚያሳይ ሆኖ ተገኝቷል። የደራስጌው ስርዓተ ንግስ የዘመነ መሳፍንትን ማብቃት ሲያሳይ የሸዋውና የወሎው ዘመቻ በአንጻሩ በአጼ ምንሊክ የተጠናቀቀውን የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ ማዕከል ወደ ደቡብ ማምራት አመላካች ነበር። 

የወሎና የሸዋ በራስ መተዳደር በርግጥም ንጉሱ የነበራቸውን የማዕከላዊ አንድ ኢትዮጵያ ራዕይ አደጋ የጣለ ስለሆነ ዘመቻው ግድ የሚል ነበር ። በመጋቢት ፲፰፻፵፯ ዓ.ም በፆም ወቅት አጼ ቴዎድሮስ ወደ ወሎ ዘመቻ አደረጉ። ምንም እንኳ ይህን ዘመቻ ወሎ ውስጥ ይገኙ የነበሩት ፯ ጎሳወች ተባብረው ለማሸነፍ ቢሞክሩም የቴዎድሮስ ሰራዊት በመስከረም ፲፪ ቀን ፲፰፻፵፰ ዓ/ም መቅደላን በመቆጣጠር ድል አደርጋቸው። መቅደላ እንግዴ በኋላው ዘመን የአጼ ቴወድሮስ የመንግስት ማዕከልና ዋና ምሽግ የሆነ ነው ። የወሎ ዋና ዋና መሪወች ከተማረኩ በኋላ አመጽ እንዳያስነሱ በቴወድሮስ መቅደላ ላይ ታሰሩ። 
 
የወሎው ድል ለአጼ ቴወድሮስ ትልቅ ስልታዊ ጠቀሜታ ነበረው ምክንያቱም ወደ ሸዋ በሚያደርጉት ዘመቻ የኋላቸው ለጥቃት አይጋለጥምና። ሸዋ በዚህ ወቅት ከዘመነ መሳፍንት ትርምስ የተገላገለ ክፍል ስለነበር ከሰሜኑ ኢትዮጵያ በተለየ መልኩ ሰላም የሰፈነበትና ሃብታም ነበር። ጥቅምት 1848 ላይ በድንገት የአጼ ቴዎድሮስ ሰራዊት ከወሎ ተነስቶ ሸዋ ገባ። የንጉሰ ነገሥቱ ሰራዊት ድንገተኛ አመጣጥ የሸዋን ሰራዊት ስለከፋፈለው በጥቅምት አጋማሽ ላይ በአጼ ቴዎድሮስና ንጉሥኃይለ መለኮት ሣህለ ሥላሴ ሠራዊት መካከል በተደረገ ጦርነት የአጼው ጦር የባለወርቅ ጦርነት ተብሎ የሚታወቀውን ውጊያ ድል አደረገ። ዘመቻው ባጠቃላይ ፭ ወር የፈጀ ነበር። መንዝ ግድምና ኤፍራታ በቴዎድሮስ ስር ሲወድቁ ሌሎች የሸዋ ክፍሎች ግን በሰይፉ ሣህለ ሥላሴ፣ የንጉሥ ኃይለ መለኮት ወንድም መሪነት የቴዎድሮስን ጦር በመከላከል ቆዩ ። በራስ ዳርጌ የሚመራው የንጉሠ ነገሥቱ ጦር ህዳር 1848 ላይ በበረከት ጦርነት አሸነፈ ። በመካከሉ ኅዳር ፱ ቀን፣ ንጉሥ ኃይለ መለኮት በሕመም አረፉ። በዚህ ምክንያት የሸዋ ወታደሮች ዓላማ የንጉሡን ልጅ ምኒልክን ከቴዎድሮስ እጅ ተከላክሎ ማዳን ሆነ። ሆኖም ግን ልጅ ምኒልክ በቴዎድሮስ እጅ በመውደቁና ቴዎድሮስም እንደልጃቸው ሊያሳድጉት ቃል በመግባታቸው የካቲት ፲፰፻፵፰ ዓ/ም ላይ አንኮበር ሲገቡ በቀሳውስትና አንኮበር መሪወች ዘንድ ተቀባይነትን አገኙ። ቀጥሎም ንጉሰ ነገስቱ በጊዜው የነበረውን የሸዋ አስተዳደር በመቀየረ መርድ አዝማች በሚለው የጥንት ማዕረግ የንጉሥ ኃይለ መለኮት ወንድም የነበሩትን ኃይለ ሚካኤል የሸዋ አስተዳዳሪ አድርገው ሾሙ።

ለ፪ መቶ ክፍለ ዘመን ተከፋፍሎ የነበረውን የኢትዮጵያ ግዛት አጼ ቴዎድሮስ በ፫ አመት ዘመቻ በንዲህ መልኩ አንድ አደረጉ 11። በ፲፰፻፵፰ ዓ/ም አጋማሽ ላይ ሸዋን ጎጃምን ወሎን ትግራይንና ጎንደርን አንድ ላይ በመግዛት፣ በ፵፯ ዓመታቸው፣ የዘመነ መሳፍንት የመጨረሻ ባላባትና የአዲሱ ዘመናዊ አገር የመጀመሪያ ንጉሠ ነገሥት ለመሆን በቁ። በዚህ ወቅት የአገሪቱ ዋና ከተማ ከጎንደር ወደ ደብረ ታቦር ተዛውሮ ነበር 9።

የቴዎድሮስ መነሳት የዘመናዊ ኢትዮጵያ ታሪክ መጀመሪያ ነው፣ ለዚህም ምክንያቱ የፈጸሟቸው ለውጦች ናቸው ። ከርሳቸው በፊት ከነበሩ ነገሥታት በተለየ መልኩ ቴዎድሮስ አገሪቱን ወደ ዘመናዊ አገር ለማሻገር ያሳዩት ፍላጎት ንግሰ ነገሥት በነበሩበት ወቅት የነበራቸው ወጣትነትና። ከአደጉበት ከቋራ ነባራዊ ሁኔታ የመነጫል። ቋራ በዘመኑ ከሱዳን የማያቋርጥ ውጊያ የሚደረግበትና በዚያ የሚኖረው ህዝብ ከመካከለኛው መንግስት የሚያገኘው ምንም እርዳታ ስላልነበር ህዝቡ እጅግ የተሰቃየበት ነበር። ቀሳውስቱም ቢሆን በጎጥ ተከፋፍለው የየራሳቸው ሃይማኖታዊ ስርዓት በመተለም የተዋህዶ ቤተክርስቲያናን ከብዙ ቦታ ለመክፈል የሚገዳደሩበት ዘመን ነበር። የገጠሩም ክፍል በባላባቶች የርስ በርስ ጦርነት የተሰቃየ ነበር። የአገሪቱ ሁኔታ ንጉሰ ነገስቱ ዘመነ መሳፍንትን ለማጥፋት እንዲነንሳሱ አደረገ። በጊዜው የነበረው የእንግሊልዙ ቆንጽላ ዋልተር ፕላውዴን ንጉሰ ነገሥቱ የኢትዮጵያን ቀደምት ታላቅነት ለመመለስ ዋና አላማ እንዳላቸው ሳይመዘግብ አላለፈም፣ በፕላውዴን አስተሳሰብ ይሄ የንጉሰ ነገስቱ ዋና አነሳሽ አላማ ነበር። ከዚህ አንጻር የቴዎድሮስ የንግስና መጀመሪያ አመታቶች በብሄራዊ ፍትሕ፣ ርህራሄና የደሃ አደጎችን ህይወት በማሻሻል ላይ ያተኮረ ነበር።

ቴዎድሮስ ቀደምት የአገሪቱ መንገድ ሰሪ ነበር። በዜና መዋዕሎችና የውጭ አይን እማኞች መሰረት ቴዎድሮስ በራሱ በእጁ መንገድ በመስራት ሌሎች እንዲከተሉት ይመራ ነበር። ንጉሱ ከሌት እስከ ምሸት በራሳቸው እጅ ድንጋይ ይፈነቅሉ እንዲሁም ጎርባጣውን ክፍል ያቃኑ ነበር። በምሳሌ የሚመራው ቴዎድሮስ እርሱ እየሰራ ሌሎች ተከታዮቹ ሊበሉም ሆነ ሊያርፉ አይደፍሩም ነበር። ሌሎች መንገድ ሰሪወችንም እጅግ ይረዳ ነበር። ደብተራ ዘነብ እንዲህ ሲል ይዘግባል፡
ያነግዜም፡ንጉሱ፡ወደ፡ዋድላ፡ሄዱ። የንምሳ፡ሰው፡አቶ፡ሰንደል፡የቤተ፡ሐርን፡መንገድ፡ያበጁ፡ነበር። ከንጉሥ፡ቴዎድሮስም፡በተገናኙ፡ጊዜ። አቶ፡ሰንደል፡የሚረዳኝ፡አጣሁ።ብቻዬን፡ሆንኁ፡አሉ። ንጉሡም፡እጅግ፡ተቆጡ፡ይኽ፡ከሩቅ፡አገር፡መጥቶ፡ሲገዛ።ያገሬ፡ሰው፡እምቢ፡ሊል፡ብለው፡የዋድላውን፡ምስለኔ፡ይመር፡ጎዳናን፡ገርፈው፡አሰሩዋቸው። ለአቶ፡ሰንደልም፡ንጉሥ፡የሚቀመጡበትን፡በቅሎ፡መጣምር፡ኮርቻ፡የተጫነ፡ከነስራቱ፡ቀሚስዎን፡ሱሪዎን፡ሺ፡ብር፡አድርገው፡ሰጧቸው። ለአቶ፡ቡላዴ፡ለእንግሊዙ፡ሶስት፡መቶ፡ብር፡ሰጡ። ለንምሳ፡ሰዎች፡ለበንደርና፡ለኪንጽሌን፡ለማየር፡፮፻ብር፡ሰጧቸው። ቀሚስ፡ድርብ፡እያለበሱ፡የጨጨሆን፡ መንገድ፡ያበጁ፡ነበር።

ቴዎድሮስ ቀደምት የተንሰራፋውን የባሪያ ንግድ ስርዓት ያጠቃ ንጉስ ነበር ። በዚህ ወቅት ባሪያ መሸጥም ሆነ መለወጥ እንዲሁም ማጓጓዝን የሚያግዱ ብዙ ድንጋጌወችን ንጉሱ በማወጅ ቀደምት የባርነት ስርዓት ተቃዋሚ ንጉስ ሆነ። ለምሳሌ ጎጃም፣ ባሶ ውስጥ ባደረገው ዘመቻ በገበያው የተገኙ ባሪያወችን በነጻ ለቋል። ወሎ ውስጥ የተማረኩ ባሪያወች እንዳይሸጡ አግዷል። ሆኖም ግን ከህጉ ውጭ በኮንትሮባንድ ውስጥ ለውስጥ በአገሪቷ ዳርቻወች ባሪያ መሸጡና መለወጡ አላቆመም።

ከባህል አንጻር የአማርኛ ስነ ጽሁፍ በኒሁን ንጉሥ ዘመን ማደግና መሻሻል አሳይቷል። ከፍተኛው የመንግስት ስራ በአማርኛ ይካሄድ ነበር። ዜና መዋእላቸውን በአማርኛ ለመጀሚርያ ጊዜ ያስጻፉ ንጉሥ ነበሩ።፣ ከዚህ በፊት በግዕዝ ነበር። ከዚህ በኋላ አማርኛ የአገሪቱ ብሔራዊ ቋንቋ ሆነ።።ቴዎድሮስ ከግዕዝ ይልቅ ሰወች በሚረዱት አማርኛ መጽሃፍ ቅዱስ እንዲተረጎም አደርጉ። የመጀመሪያው የጂዖግራፊያ መጽሃፍ በአማርኛ የታተመውም በኒሁ ንጉስ ዘመን ነበር። ህዝቡ ለጋብቻ ከፍተኛ ዋጋ እንዲሰጥም በጣም ጥረት አድርገዋል፣ እራሳቸውም በአንድ ሴት በመወሰን መሪ ምሳሌ ለመሆን ሞክረዋል። ከቴዎድሮስ በፊት ይሰራበት የነበረውን ከወገብ በላይ እራቁት መሆን የአለባበስ ዘዴን በማስቀረት ሹሞች በጥሩ ሁኔታ እንዲለብሱ አድርገዋል። በአጠቃላይ ህዝቡ የሃይማኖትና የባህል ህጎችን አጥብቆ እንዲከተል ጥረት አድርገዋል።

ከአስተዳደር ስልት አንጻር ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ስላሴ እስከፈጸሙት ድረስ የነበረውን አገሪቱን በማዕከላዊ ሃይል የማስተዳደር ስራ ጀምረዋል። በአዲሱ ስርዓት መሰረት የግብር እና የፍርድ ባለስልጣናት ከማዕከላዊ መንግስት ደመወዛቸውን እንዲያገኙ ተደረገ፣ ይህም በየቦታው የነበሩ ባላባቶችን የመፍለጥ የመቁረጥ ሃይል የቀነሰ ተግባር ነበር። የሆኖ ሆኖ ንጉሡ የገዥውን መደብ ሙሉ በሙሉ አልቀየሩም፣ አንድ አንድ ገዥወች በነበሩበት እንዲቀጥሉ አድርገዋል። ለምሳሌ የትግራይ ገዥ የነበሩት ደጅ አዝማች ሰባጋዲስ ዘር የሆኑትን ካሳ ምርጫን በትግራይ ሾሙ፣ እንዲሁም የንጉስ ሳህለ ስላሴ ዘር የሆኑትን ሃይለ ሚካኤልን በመሾም በየቦታው የነበሩትን የሃይል ማዕከላት በነበሩበት እንዲጸኑ አድርገዋል። በአንዳንድ ክፍሎች የራሳቸውን ዘመዶች ስልጣን ያወጡበት ሁኔታ ይገኛል፣ ለምሳሌ ራስ እንግዳን በጎጃም። ይህ ስርዓት በመጀመሪያ እጅግ የተሳካ ነበር ምክንያቱም በዘመነ መሳፍንት እንኳ ሳይቀር ጠንካራ ባላባቶች ለንጉሳዊው ስልጣን የመገዛት ባህርይ ያሳዩ ነበርና። ከሸዋ መርዕድ አዝማች ሃይለ ሚካኤል በየጊዜው ወደ ንጉሱ የጓዙ ነበር። ትግራይ ደግሞ ለንጉሱ ዋና የገቢ ምንጭ ነበር (200፣000 ማሪያ ቴሬሳ በአመት)፣ ከበጌምድር የሚያገኙት 50፣000 ማሪያ ቴሬሳ ብቻ ነበር። ሆኖም ግን አንድ አንድ ጥቃቅን ባላባቶች አመጽ ለማስነሳት መመኮራቸው አልቀረም፣ ስለሆነም ንጉሱ ሰራዊቱን ማሻሻል እንዳለባቸው ተገነዘቡ።

ሠራዊቱ በፖለቲካው ውስጥ ባለው መሰረታዊ ተፅዕኖ ምክንያት ንጉስ ቴዎድሮስ በዚህ ክፍል ላይ ብዙ ትኩረት አድርገዋል። እራሳቸውን ከስሎሞኑ ስርወ መንግስት በመጀመሪያ የአገዛዛቸው ዘመን በማራቃቸው ብቸኛው ወደላይ የሚያወጣቸው መሰላል የውትድርና ብቃት እንደሆነ ጠንቅቀው ተረዱ። አገራዊ ሠራዊቱን ለማጠናከርና ብሔራዊ አንድነትን እውን ለማድረግ፣ ዋልተር ፕላውዴን ታላቁ ለውጥ ያለውን አጼ ቴዎድሮስ አከናወኑ 9። ይህ ታላቅ ለውጥ በ3 አብይ ክፍሎች ላይ ያተኮረ ነበር፡ ፩.መዋቅር ፪.ዲሲፕሊንና ፫.ትጥቅ ናቸው። እኒህ ለውጦች ከሞላ ጎደል የተወደዱና ለብዙ ድሎች ያበቃቸው ሲሆን ስልጣናቸውንም ለማንሰራፋት አይነተኛ ምክንያት ናቸው። እኒህ ለውጦች የአገሪቱ ዜጎች በአንጻራዊ ደህነነት እንዲኖሩ ረድተዋል 9። 

ከመዋቅር አንጻር ከዘመነ መሳፍንት ሲወርድ የመጣውን የተከፋፈለ የባላባቶች ሰራዊትን በአንድ ብሔራዊ ሰራዊት ቀይረዋል። ከተለያዩ ክፍለ ሃገሮች የመጡት ወታደሮች በንጉሠ ነገሥቱ በተዋቀረ አንድ የጦር ክፍል ስር ተደራጁ። እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ ሰራዊት የሚሰራበት የአስር አለቃ፣ የሀምሳ አለቃና መሰል ማዕረጎች የተፈጠሩት በዚሁ ዘመን ነበር። ንጉሡን የሚያጅቡትን ወታደሮች ቁጥር በመቀነስ፣ የዚህን ክፍል እዳተኝነትን ቀነሱ። ወታደሮች ከዚህ በኋላ ቋሚ ደሞዝ ተቆርጦላቸው ስለሚተዳደሩ የሰፈሩበትን ቦታ መበዝበዝ በህግ ተከለከሉ። በፊውዳሉ ስርዓት ወታደሮች በረገጡበት ቦታ ያሉ ገበሬወች ምግብና መኝታ እንዲያቀርቡ ይገደደዱ ነበር። ይህ ሁኔታ በንጉሠ ነገሥቱ አጥብቆ የተከለከለ ነበር። ይህን በሚያሳይ መልኩ ለምሳሌ አንድ ገበሬ የ12 ጫጩት እናት የሆነችን ዶሮ እንዲያርድ በንጉሱ ወታደር ይገደዳል። ድርጊቱ ንጉሱ ድረስ ቀርቦ በዳኝነት ከታየ በኋላ ወታደሩ በሞት ሲቀጣ ገብሬው ላም ተሰጥቶት እንዲሄድ ተደረገ። በዚህ ዘመን ወታደሮች ቀለብ የሚባል ገቢ ከንጉሱ የሚሰፈርላቸው ሲሆን ከዚህ ውጭ ማንም ገበሬውን ያስገደደ ወታደር ከፍተኛ ቅጣት ይቀጣ ነበር።
 
ንጉሡ በሠራዊቱ ዘንድ እንደ ብረት የጠነከረ ዲሲፕሊን ለማቋቋም ሞክረዋል። ለምሳሌ ወደ ወሎ ባደረጉት ዘመቻ ያለትዕዛዝ ጦርነት የሚገቡ ወታደሮች ያለርህራሄ ይገደሉ ነበር። በሸዋው ዘመቻ እርስ በርስ ሽኩቻ ያሳዩ ወታደሮች በሙሉ በጥይት ተደብድበዋል። ባህሩ ዘውዴ እኒህ ድርጊቶች ደም መፋሰሱ እንዲባባስ በማድረግ ብዙ ጥቅም አላመጡም ያላል። ሆኖም ወታደሩ በራሱ ፈቃድ ብዙ ጥፋት እንዳያደርግ ረድቷል።

አብዛኛው የአጼ ቴዎድሮስ ሰራዊት ጦር መሳሪያ ከጦር ሜዳ የተማረከ ነበር ። ቆይተው ግን ከአውሮጳ ቴክኖሎጂ በማስመጣት በኢትዮጵያ ምድር ላይ የመሳሪያ ማምረቻ ለማቋቋም ሞክረዋል። ለዚህ ተግባራቸው እንዲረዳ የአውሮጳ ሚስዮኖችን በጋፋት፣ ደብረታቦር ሰብስበው መሳሪያ እንዲሰሩ አደርጉ ከዚህ ትይዩ ትምህርት ቤት በማቋቋም ጥበቡን ተማሪወች እንዲቀስሙ አደረጉ። የመጀመሪያው ትክክለኛ የመሳሪያ ዝርዝር የተገኘው ከመቅደላ በአጼ ቴዎድሮስ ዘመን ነበር፡ 15 መድፎች፣ 7 አዳፍኔዎች፣ 11፣063 ጠመንጃዎች፣ 875ሽጉጦች፣ 481 ሳንጃዎችና ጥይቶችን ያጠቃልላል።

አጼ ቴዎድሮስ ያሰቡትን ለውጥ በተግባር ለመፈጸም ቋሚ የተረጋጋ የመዋዕለ ንዋይ መሰረት እንደሚያስፈልጋቸው ተገነዘቡ ። በዘመኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክርስቲያን ከሁሉ ግምባር ቀደም ሃብታም ድርጅት ነበር። አጼ ቴዎድሮስ የተዋህዶን ትምህርት ስለደገፉና አቡነ ሰላማም ይህ ጉዳይ ስላስደስታቸው በቴዎድሮስና በቤተክርስቲያን መካከል የነበረው ግንኙነት በመጀመሪያው የንጉሱ ዘመን መልካም ነበር። 17፣። በፖለቲካው አንድነት እንደሚፈልጉ ሁሉ በሃይማኖቱም አንድነትን ማየት ይፈልጉ ነበር።

በዘመኑ ቴዎድሮስ እጅግ ሃይማኖተኛና የጋብቻን አንድ ለአንድ መጽናት የሚያክብሩ፣ የቤተክርስቲያን ክፍፍልን የሚቃወሙና እንዲሁም ከክርስቶስ ውጭ እኔ ባዶ ነኝ የሚሉ መሪ ነበሩ። በዚህ ምክንያት ከቤተ ከርስቲያን ጋር የነበረው የመጀመሪያ ግንኙነት ጥሩ የነበር ቢሆንም የቴዎድሮስና የአቡነ ሰላማ (እንዲሁም መላው የቤተክርስቲያኒቱ ቀሳውስት) ግንኙነት ቀስ እያለ እየተበላሸ ሄደ፣ ለዚህም ምክንያቱ ቤተክርስቲያኒቱን ለመለወጥ ያደረጉት አንድ አንድ ተግባር ነበር። ከቤተክርስቲያን ጋር ያለው ጥል በተለይ ፈጦ የወጣው የመሬት ይዞታን ለማሻሻል ያቀዱትን ሃሳብ ባሰውቁ ጊዜ ነበር። ለምሳሌ በ1848 ዓ.ም. ቀሳውስቱን ሰብስበው እንዲህ አሏቸው፡ እኔስ ምን ልብላ፣ ወታደሮቸስ? ግማሹን መሬት የመስቀል መሬት ብላችሁ ትወስዳላችሁ፣ ግማጩን ደግሞ ሪምና ገዳም 19፣። መሬቱን ለግብር ከፋይ ገብሬወች በማከፋፈል አገሪቱ ላይ ሊያካሂዱት ላሰቡት መሻሻል ወጭ ቋሚ ገቢ ለማግኘት ነበር። 1852 ላይ የመሬት የዞታ ማሻሻሉ ስራ በከፊልም ቢሆን ተከናወነ በዚህ ወቅት የቤ/ክርስቲያን መሬት በከፊል ለገበሬወች አከፈፋሉ። ይህም በፍካሬ እየሱስ ላይ እንደተጠቀሰውና በእውን እንደነበረው ቀዳማዊ ቴዎድሮስ ስራ ነበር። በዚሁ አመት የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ከሁለት ቄሶችና ሶስት ዲያቆኖች በላይ እንዳይሆን ደነገጉ። ከዚህም በላይ ደብተራነትን ከነአካቴው ለማጥፋት እንዳሰቡ ገለጹ። ብዙ ደብሮች ከአስፈላጊ በላይ የሰው ሃይል ሲኖራቸው ነገር ግን ከግብር ነጻ ስለሆኑ የአገሪቱን ሃብት በከንቱ ያባክናሉ፣ ይህም አጼ ቴዎድሮስ አጥብቀው የተቃወሙት ስርዓት ነበር። ንጉሱ በወግ አጥባቂ ቀሳውስት ላይ ያላቸውን መጸታዊ ንቀት ሲገልጹ ዱላቸውን ከመንደር መንደር እየጎተቱ ያለ ምንም ስራ የሚያውደለድሉ  ይሏቸው ነበር። ሆኖም ቀሳውስቱ አርፈው የንጉሱ ተጠቂ መሆን አልቻሉም። በ1856 ዓ.ም. አቡነ ሰላማ እስከታሰሩ ድረስ ቤተክርስቲያኗ በአቡኑ መሪነት በንጉሱ ላይ ተቃውሞ አነሳች። የቀሳውስቱ ዋና ማጥቂያ ስልት የንጉሱን ነጣቂእንጂ ህጋዊ ንጉስ አለመሆን ማስታወስ ነበር።

አስተዳደሩ ማዕከላዊ እየሆነ በሄደ ቁጥር የሃይላቸውን መሸርሸር የተረዱት የየጎጡ ባላባቶች ጦር ማንሳት ጀመሩ። የጎጃሙ ተዳላ ጓሉ፣ የወልቃይቱ ጢሶ ጎበዜ፣ የሸዋወቹ ሰይፉ ሳህለስላሴና በዛብህ፣ የወሎዎቹ ደጃዝማች ሊበን አምዴ አመጽ አስነሱ። በዋግሹም ጎበዜ የሚመራው የላስታ ጦር ጭራሽ ጎንደርን ለጥቂት ጊዜ ለመቆጣጠር ቻለ፣ ሰሜንና ወገራም እንዲሁ ለአመጽ ተነሳሱ። በመጀመሪያዎቹ የቴዎድሮስ ዘመናት የትግራዩ ደጃዝማች ካሳ ምርጫ ከሌሎቹ ባላባቶች በተለየ መልኩ ለአዲሱ ንጉስ ክብርና ታማኝነት ያሳይ ነበር። በዚህ ወቅት የንጉሠ ነገሥቱ ጦር ሰራዊት ከሁሉ የተሻለ ስለነበር ሁሉኑም አመጽ በሃይል ለመቆጣጠር ቻለ። የንጉሱን ሰራዊት መመገብ የሰለቻቸው ገበሬወች ግን ባንጻሩ ለአመጹ መበረታታት አስተዋጾ አደረጉ። በየጊዜው የሚካሄደው ዘመቻም ለድህነትና ለህዝብ ማለቅ ከፍተኛ አስተዋጾ እያደረገ መጣ። በዚህ መካከል የአገሪቱን ብሄራዊ መከላከያ ለማጠናከር አጼው ያወጡት የግብር ስልት አዲሱን ስርዓት ከገበሬወች ዘንድ ሙሉ በሙሉ ለየው ። እኒህ ተቃውሞወች ከተራ ሰውነት ተነስተው አገሪቱን ለማሳደግና ፍትሃዊ ስርዓት ለማስፈን በሞከሩት አጼው ዘንድ አሳዛኝ ነበሩ።

በ1850ወቹ ንግሡ በዛ ያሉ አመጾችን በትግሬና በበጌምድር ለማፈን ቻሉ። ታህሳስ 1852 የሰሜኑ ክፍል አመጽ ዋና አዛዥ የነበረውን አገው ንጉሴን ወግተው ገደሉ። በ1857 መቅደላ ያደገው ወጣቱ ምኒሊክ ምንም እንኳ ንጉሱን ቢወድም ከመቅደላ አምልጦ ሸዋ በመግባት የግዛቱን ኢ-ጥገኝነት አወጀ። ጎበዝ የተሰኘው የድሮው የላስታ መሪ ልጅ የላስታ መሪ በመሆን ስልጣኑን አወጀ፣ ትግራይም እንዲሁ በካሳ ምርጫ ስር ወደቀ። ከ1858-59 ንጉሱ የጢሶ ጎበዜን ጦር በጎንደርና የተድላ ጓሉን ሃይሎች በጎጃም ለመቆጣጠር ብዙ ዘመቻወን አካሄዱ። በነዚህ ዘመቻወች ብዙ ወታደሮች ከንጉሱ እየከዱ አመለጡ። በ1859 በንጉሱ ሙሉ ቁጥጥር ስር የነበረ አካባቢ ቢኖር በጌምድር ነበር 72። ጥቅምት 1860 ላይ ቴዎድሮስ ደብረታቦርን አቃጥለው ወደ መቅደላ በመሄድ እስከ እለተ ሞታቸው ድረስ ኑሮአቸውን በዚያ አደረጉ።

አጼ ቴዎድሮስ ያቀዱት እና ለመተግብረ የፈለጉት አገር በተግባር መስራት አልቻለም። ንጉሱ የሃገራቸውን ህዝብ ምንጊዜም ላለመበደል ቢፈልጉም የፖለቲካውንና የፍትሃዊ ስርዓቱን ቅጥ ለማስተካከል አይነተኛ አማራጭ የወታደራዊ ሃይል በመሆኑ ብቻ ጦር መክፈት ግድ እንዳላቸው ሳይናገሩ አላለፉም። ከባህር ጠረፍ በርቀት የመሰረቱት መቅደላም እንደ ትግራይና ሸዋ በፍጥነት ዘመናዊ ጦር መሳሪያን ሊያገኝ አልቻለም። የንጉሱ በጣም ጠንካራ ወታደራዊ ዲሲፕሊን(ግብረ ገብ) ብዙዎቹ ወታደሮች እንዲከዱ አደረገ። ባንድ ወቅት የአጼው ሰራዊት ከመቶ ሺህ በላይ የነበር ሲሆን በ1858 ከአስር ሺህ ብዙ አይበልጥም ነበር። በቁም እስር የነበሩት አቡነ ሰላማ በ1859 ሲሞቱ አጠቃላይ ክርስቲያኑ ክፍል በቴዎድሮስ ላይ ከፍተኛ ጥላቻን አሳየ። በአገሪቱ የነበረው የተቃውሞ መጠን ከማየሉ የተነሳ አጼ ቴዎድሮስ ከደብረታቦር መቅደላ ባሰሩት መንገድ እንኳ ሳይቀር በሰላም መንቀሳቀስ አልቻሉም። በ1859 መጨረሻ ይሄው መንገድ እጅግ አደገኛ እየሆነ በመምጣቱ ንጉሰ ነገስቱ በመቅደላ ሙሉ በሙሉ ተወሰኑ።

በንጉሱና በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን መካከል የነበረው ግንኙነት እየተበላሸ ቢሄድም ከሌሎች ሃይማኖቶች ጋር የነበርው ግንኙነት የከፋ ነበር። በመጀመሪያ፣ ፕሮቴስታንቶች፣ ካቶሊኮች፣ እስላሞች፣ እና ፈላሻወች የሃይማኖት ነጻነት ተፈቅዶላቸው ይኖሩ ነበር። ሆኖም የአገሪቱ ውስጣዊ ሁኔታን መበላሸት ተከተሎ ፣ ሚሲዮኖችና ሌሎች ሃይማኖቶች ጫና እየበዛባቸው ሄደ። ንጉሰ ነገሥቱ ለአገሪቱ አዲስ አይነት ቴክኖሎጂን ለማስተዋወቅ ከነበራቸው ፍላጎት አንጻር በንግሱና በፕሮቴስታንት ሚሲዮኖች የነገረው የመጀመሪያ ግንኙነት መልካም ነበር። እንደ ካቶሊኮች የግለሰቦችን ሃይማኖት ለመቀየር ሳይሆን የቤተክርስቲያኒቱን ውስጣዊ አሰራር ለመቀየር ስለሚፈልጉ ፕሮቴስታንቶች በንጉሱ ዘንድ በጥሩ አይን ይታዩ ነበር። በ1847 ከስዊዘርላንድ የተላኩ ወጣት እጅ ጥበብ አዋቂ የፕሮቴስታንት ሚስዮኖችን ለማስተናገድ ንጉሱ ቃል ገቡ። እኒህ ሚስዮኖች በአማርኛ የታተሙ የሃይማኖት መጽሃፍትን ይዘው የመጡ ሲሆን፣ ቴዎድሮስ ግን የፈለጉት የጦር መሳሪያወችን ነበር፣ ሆኖም ቀረ ግን ንጉሱ ለኒህ ሚሲዮኖች ጥሩ አቀባበል አደረጉላቸው። በንጉሱ ፈቃድ መሰረት እኒህ ሚሲዮኖች የሰበካ ስራቸው ክርስቲያን ባልሆነው ክፍል ብቻ እንዲወስኑ ሲደረግ፣ የእጅ ጥበብ ስራቸው ግን ንጉሱ በፈለጉት መጠን ጥራት አልነበረውም።

ሚሲዮኖቹ የእጅ ጥበብ አዋቂ ቢሆኑም ንጉሱ ላሰማራቸው ስራ ግን የተለማመዱ አልነበሩም። በ1853 አካባቢ በንጉሱ አግባቢነት አንስተኛ አዳፍኔ ሰርተው ሲያቀርቡ ወዲያው መድፍ እንዲሰሩ ከንጉሱ ዘንድ ጥያቄ ቀረበላቸው። ምንም እንኳ እኒህ ነገሮች ንጉሱን ቢያስደስቱም ፕሮቴስታንቶች ሌሎች አውሮጳውያን ላይ ይደርስ ከነበረው ጭቆና ተቋዳሽ ከመሆን አልተረፉም። ለዚህ ምክንያቱ ለምሳሌ የፕሮቴስታንት ሰባኪ የነበረውን ሄንሪ ስተርን ንግሱ ላይ የሚናገራቸው በጊዜው የሚያስቆጣ ንግግር ይጠቀሳል። ለምሳሌ ሄነሪ ስተርን ባሳተመው መጽሃፉ ላይ የንጉሱ እናት በጣም ደሃ ከመሆኗ የተነሳ ኮሶ ትሸጥ ነበር ይህም በንጉሱ ዘንድ እጅግ የሚያስቆጣ ነበር። ስለሆነም ከጥቂት ጊዜ በኋላ ብዙዎቹ ሚሲዮኖች (ከሄንሪ ስተርን ጨምሮ) በመቅደላ ታሰሩ። 

በአንጻሩ ከካቶሊኮች ጋር የነበረው ግንኙነት ምንጊዜም ብልሹ ነበር፣ ለዚህም ምክንያቱ ሁለት ነበር፦ ፩) ካቶሊኮች በስሜኑ በኩል የነበራቸው ተጽዕኖ የንጉሱን ስልጣን የሚገዳደር ነበር ፪) ከፈረንሳይ ሃይል ጋር የነበራቸው የጠበቀ ግንኙነት ነበር ። ጃኮቢና ጉስቲኖ የተሰኙ ካቶሊኮች በአንድ ወገን አቡነ ሰላማ በሌላ ወገን ባስነሱት የግል ጥል ምክንያት አጼ ቴዎድሮስ ካቶሊኮቹን በ1846 ከአገር ሲያባርሩ ኢትዮጵያዊ ደጋፊወቻቸውን እንዲታሰሩ አደርጉ። በዚህ ምክንያት ካቶሊኮች፣ በተለይ ፈረንሳይ ንጉሱን ከስልጣን ለማሰወገድ መዘጋጀት ጀመሩ። አገው ንጉሴ የተሰኘው የሰሜን መሪ ንጉሱን ለመውጋት እና ዘመናዊ ጦር መሳሪያ በተለዋጭ ለማግኘት እንደሚፈልግ ሲሰማ በፓሪስ ደስታ ሆነ። አገው ንጉሴ ከካቶሊኮችና ከፈረንሳይ ባገኘው ድጋፍ መሰረት ሃይሉን በትግራይ ማጠናክር ጀመረ። ሆኖም በ1852 ላይ በጦርነት ተሸንፎ ተገደለ። አጼ ቴዎድሮስ ከመስሊሞች ጋር የነበራቸው ግንኙነት ለየት ያለ ነበር። ምንም እንኳ ሙስሊሞች ሃይማኖታቸውን በነጻነት እንዲያካሂዱ ንጉሱ ቢፈቅዱም ወደ ኦሮቶዶክስ ክርስትና እንዲለወጡ ግን ይደግፉ ነበር። የአጼ ቴዎድሮስ አባት የተገደሉት በሱዳን መስሊሞች ቢሆንም ቅሉ የሃይማኖት ነጻነታቸው ግን እንደተጠበቀ እንዲቀጥል ፍላጎታቸው ነበር። ሆኖም በአገዛዛቸው መጨረሻ ከሙስሊሞች ጋር የነበረው ግንኙነት የሻከረ ነበር፣ ለዚህ ምክንያቱ ሁለት ነበር፤ አንደኛው የኦቶማን ግዛት በቀይ ባህር መንሰራፋትና የሙስሊም ነጋዴወች ባሪያ ንግድ ነበር። ባሪያ ንግድ በንጉሠ ነገሥቱ አዋጅ መሰረት ወንጀል ነበር። ስለሆነም በሚያዚያ 1856 ዓ.ም. እስልምና በግዛቱ ሲከለከል፣ ይህን ጉዳይ በመቃወም ስራ ያቆሙ ሙስሊሞችኑን ንጉሱ ይቀጡ ነበር።

የንጉሰ ነገስቱን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት በ፫ ዋና ኩነቶች ተጽዕኖ ደርሶበታል፦

አጼ ቴዎድሮስ በግል ደረጃ ከነበራቸው የጠበቀ ሃይማኖታዊ እይታ ውጭ ስለ ዘመኑ የአውሮጳ እርስ በርስ ዲፕሎማሲያዊ ውጥረትና ግንኙነት የጠለቀ መረጃ አልነበራቸውም። የአጼ ቴዎድሮስ የዲፕሎማሲ ደብዳቤወች እንደሚያሳዩት ለንጉሱ የሃይማኖት ጉዳይ ለዲፕሎማሲው ጥረት ዋና ጉዳይ ነበር፣ ከአውሮጳውያን ጋር ትብብር በመፍጠር የግብጽን እስላማዊ ሃይል ለመመከት የነበራቸውን ፍላጎት የዚሁ ሃይማኖታዊ ዲፕሎማሲ አካል ነበር። ስለሆነም ክርስቲያን እንግሊዝ ከሙስሊም ቱርክ ጋር ወግና ክርስቲያን ሩሲያን በክሪሚያ ጦርነት እንደወጋች ሲሰሙ ለንጉሱ እጅግ እንግዳ ሁኔታ ነበር። በተረፈ የዘመኑ የአውሮጳ ቤተመንግስቶች በዘረኛነት የተሸበቡ ስለነበር ለነሱ «አንድ የአፍሪቃ ንጉስ ከተራ የጎሳ አለቃነት ባለፈ አይታይም ነበር»፤ ይህም እውነታ ለንጉሱ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት የተደበቀ ነበር።

ከውጫዊ አደጋ በተረፈ ውስጣዊ አመጽ ሲነሳም እንዲሁ ዲፕሎማሲን በመጠቀም ብሄራዊ ድጋፍ ለማግኝገት ንጉሱ ሞክረዋል4። ከአውሮጳ አገሮች የቴክኖሎጂ እና የወታደራዊ ድጋፍን መጠየቅ የዚህ ዲፕሎማሲ አካል ነበር። የፈረንሳዮች መልስ ንጉሱ የካቶሊክ ሚሲዮኖች በአገሪቱ እንዲዘዋወሩ ከፈቀዱ ድጋፉን እንደሚሰጡ ነበር፣ ሆኖም ግን ይህን ጉዳይ ንጉሱ እንደማይፈቅዱ አስቀድሞ የታወቀ ስለነበር «ድጋፍ ከመከልከል» ጋር ምንም ልዩነት አልነበረውም። ሩሲያኖች በክሪሚያ ጦርነት ተዳክመው ስለነበር ለንጉሱ ድጋፍ መላክ አልቻሉም። በዚህ ምክንያት በክሪሚያው ጦርነት መነሳት የተበሳጩት ቴዎድሮስ። በኋላ ያሰሩትን መድፍ ሴባስቶፖል በማለት ለሩሲያኖቹ ጦር ሜዳ ማስታወሻ ሰየሙ።

በዚህ ትይዩ ከሙስሊም አገሮች ጋር፣ በተለይ ከግብጽ ጋር፣ የነበረው ግንኙነት እየተበላሸ ሄደ። በ1848፣ የአሌክሳንድሪያ ፓትሪያርክ ቄርሎስ ለጥየቃ ወደኢትዮጵያ በመጡበት ጊዜ አቡነ ሰላማ፣ በንጉሱ ስም፣ ግብጽ ወታደራዊ እርዳታ እንድታደርግ ጠየቁ። የቆብጡ ፓትሪያርክም የንጉሰ ነገሥቱ አምባሳደር በካይሮ ለመሆንና ጥያቄውን ለማቅረብ ተስማሙ። ሆኖም ይህ ጉዳይ ንጉሱ ሳይሰሙ በሁለቱ የሃይማኖት መሪወች መካከል የተከናወነ ስለነበር ንጉሰ ነገሥቱ የተደረገውን ጉዳይ ሲሰሙ ሁለቱንም ግብጻውያን እስር ቤት ከተቷቸው። በዚ ሁኔታ ነገሮች ቀጥለው ፓትሪያርክ ቄርሎስ ህዳር 1849 ላይ ሲፈቱ አቡነ ሰላማ በታሰሩበት 1859 አረፉ። ከዚህ ጎን ዋድ ንምር ለተሰኘው ሱዳናዊ የማክ ንምርልጅ ንጉሰ ነገስቱ እርዳታ ያደርጉ ነበር። ይሄ ሰውና አባቱ በግብጾች ላይ የሚካሄድ ሱዳናዊ አመጽ መሪ ነበሩ። ስለሆነም የአጼ ቴዎድሮስ ድጋፍ በአካባቢው የነበርውን የግብጽን ሃይል ለመነቅነቅ ከነበረ አቅድ የመነጨ ነበር። ይሁንና ከምዕራቡ የአገሪቱ ክፍል ከሚመጣው የግብጾች ጸብ ይልቅ ቴዎድሮስን ከአውሮጳውያን ጋር ለመስራት የገፋፋቸው በምስራቅ ከቀይ ባህር የሚመነጨው የቱርኮች አደጋ ነበር።

የቴዎድሮስ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት በአብዛኞቹ አውሮጳውያን ሃይሎች ዘንድ አወንታዊ ምላሽ አለማግኘቱን ተከትሉ ንጉሱ ከእንግሊዞች ጋር የጠበቀ ግንኙነት ለመፍጠር ፈቀዱ። በተለይ ለዚህ ፍላጎት ዋና መንስኤ የነበረው ሊቀ መኩዋስ ብለው ከሰየሙት ሊቀመኳስ ጆህን ቤል እና የእንግሊዝ የመጀመሪያ ቆንጽላ በኢትዮጵያ ዋልተር ፕላውዴን ጋር የነበራቸው ቅርበት ነበር። በኒህ ሁለት ሰወች ምክንያት ንጉሱ ለብሪታንያ ከፍተኛ አድናቆትና ክብር የነበራቸው ሲሆን ነገር ግን ከእንግሊዞች ዘንድ ተገልባጭ ፍቅርና አድናቆት አልነበረም። የሆነው ሆኖ በመጨረሻ ንጉሱ የጠበቀ ግንኙነት ለመፍጠር የፈለጉት አገር ዋና ጠላታቸውና የመውደቃቸው ምክንያት ሆኖ አረፈው።

ጥቅምት 29፣ 1854 ላይ አጼ ቴዎድሮስ ሁለት ተመሳሳይ ደብዳቤወችን ለእንግሊዟ ንግስት ቪክቶሪያና ለፈረንሳዩ ናፖሊዮን ሳልሳዊ ላኩ። የደብዳቤያቸው ፍሬ ነገር የቱርኮች በኢትዮጵያ ግዛት መኖርን የሚቃወምና እነርሱን ከኢትዮጵያ ምድር ለማባረር ድጋፍ እንዲሰጡ ነበር። ደብዳቤው በ1854 የእንግሊዝ ቆንጽላ በኢትዮጵያ ተብሎ በተሾመው ካፕቴን ካሜሮን አማካኘት የተላከ ነበር። በዚሁ ደብዳቤ ንጉሠ ነገሥቱ ጆን ቤልና ዋልተር ፕላውዴን ለንጉሱ የገቡትን ቃል አስታውሶ ንግስት ቪክቶሪያ የንጉስ ታላቅ ንግስት እንደሆነችና የክርስቲያኖች ወዳጅ እንደሆነች ያስታውሳል። በዚህ ምክንያት እንግሊዝን እንደሚወዱ በደብዳቤው አስፍረዋል። ከዚህ በተጨማሪ የቱርኮች በኢትዮጵያ ባህር ወደብ ላይ መንሰራፋት በቀይ ባህርል ላይ ጉዞ እንዳያደርጉ የሚከለክልና አምባሳደርም እንዳይልኩ ያደረጋቸው መሆኑን ጠቅሰዋል።

ጥር 12፣ 1854 ላይ የቴዎድሮስ ደብዳቤ ለንድን ቢደረሰም። የታቀደውን አላማ አልፈጸመም። ለዚህ ምክንያቱ ሩሲያውያን የእንግሊዝን የህንድ ግዛት መገዳደራቸው ነበር። ስለሆነም እንግሊዝ ሩሲያን በጠላትነት ፈርጃ ክሩሲያ ጠላቶች -ከቱርኮች ጋር የጠበቀ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በማድረግ ሩሲያን አንድ ላይ የሚታገሉበት ወቅት ነበር። ስለሆነም የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ መሰሪያ ቤት ለቴዎድሮስ ደብዳቤ መልስ እንኳ ሳይጽፍ እንዲሁ በተመላሽ ደብዳቤውን ለእንግሊዝ ወኪል በህንድ ላከ። የህንዱም መስሪያ ቤት ደብዳቤውን ወደ ጎን ከማስቀመጥ ውጭ መልስ አልላከም ነበር። በዚያው አመት ሚያዚያ 1854 ካፒቴን ካሜሮን ክእንግሊዙ የውጭ ጉዳይ ጸሃፊ ኸርል ረስል በደረሰው ደብዳቤ የእንግሊዝ መንግስት የኢትዮጵያን የድጋፍ ጥያቄወች ውድቅ እንዳደረገ ተረዳ። ካሜሮን ወደ ምጽዋ በመሄድ በዚያ እንዲወስን መልዕክቱ ያዝ ነበር። በዚህ መካከል ንጉሱ ከእንግሊዝ መልስ ባለማግኘታቸው የእንግሊዝ መንግስት ሆን ብሎ ችላ እንዳላቸው እምነት አሳደረባቸው።

በታሪክ አጥኝው ሪቻርድ ፐንክኽርስት አስተሳሰብ የዚህ እምነት ምክንያት የቴዎድሮስ እንግሊዝ ግብጽን ትደግፋለች የሚል የተሳሳተ እምነት ነው ይበል እንጂ። በእርግጥም እንግሊዞች ከግብስ ጋር የንግድ ግንኙነት ለመፍጠር ሞክረው ነበር። በ1856፣ በግብጽ ቁጥጥር ስር በነበረው የሱዳን ክፍል የጥጥ ተክልን ለመትከል የሚያስችል እቅድ ለመንደፍ የእንግሊዙ ካፒቴን ካሜሮን ተጉዞ ነበር። እኒህን ነገሮች የሚከታተሉት ንጉሱ፣ ካሜሮን የግብጾቹን በሱዳን ወረራ ዕውቅና እንደሚሰጥና በግልጽም ለነሱ እንደሚያደላ ተረዱ። ህዳር 1856 ላይ ከኸርል ሩስል ጸሃፊ ጄምስ መሪይ በመጣ ደብዳቤ መሰረት ካፒቴን ካሜሮን በምጽዋ ላይ እንጂ በኢትዮጵያ እንዳልተሾመ ማስታወሻ ደረስው። ነገር ግን ይሄ ደብዳቤ ስህተት ነበር ምክንያቱም የካፒቴን ካሜሮን ሹመት የንግስቲቷ ቆንጽላ በኢትዮጵያ የሚል ነበርና።።.

እንኒህ ለውጦችን በጥሞና የሚከታተሉት አጼ ቴዎድሮስ ይህ የብሪታኒያ መንግስት ፖሊሲ በጊዜው ምጽዋን ይቆጣጠር የነበረውን የኦቶማን/ቱርክ ግዛት የሚደግፍ ሆነው አገኙት። ለቴዎድሮስ ትልቅ ትርጉም በነበረባት እየሩሳሌም ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያውያንና መኖሪያቸው በእንግሊዞች ጥበቃ ያገኝ የነበር ቢሆንም አዲስ የተሾመው የብሪታንያ ቆንጽላ ግን የኦቶማን ቱርኮች ኢትዮጵያውያንን ከሚኖሩበት ሲያባርሩ እንግሊዞቹ አልተቃወሙም ነበር። የእንግሊዝ መንግስት ኦቶማን ቱርክን ለመደገፍ መምረጡ በንጉሰ ነገስቱና በእንግሊዝ መንግስት መካከል ለተፈጠረው ጥል ዋና መነሻ ነበር። ንጉሡ ለጻፉት ደብዳቤ አንድ አመት ሙሉ መልሱን ሲጠባበቁ ቢቆዩም ምንም መልስ ባለማግኘታቸው ትዕግስታቸው ተሟጦ  ጥር 4፣ 1856 ላይ ካፒቴን ካሜሮንና ሌሎች የዲፕሎማሲው አካሎች በመቅደላ ታሰሩ። እስክዚያው ድረስ መልስ ሳይሰጡ ዝምታን የፈቀዱት እንግሊዞች በርግጥም በዚህ ጊዜ ከዝምታቸው ነቁ ። ወዲያውም ወደ ጎን የተጣለው የንጉሱ ደብዳቤ ተፈልጎ ተገኘ፣ ብዙም ሳይቆይ እንግሊዞች ደብዳቤ ላኩ ። አስቸኳይ ደብዳቤ ተጽፎ በሆሙዝ ራሳም አማክይነት ጥር 26፣ 1858 ጣና ሃይቅ አጠገብ ለንጉሱ ደረሰ። በዚሁ ደብዳቤ የእንግሊዝ መንግስት እስረኞቹ እንዲፈቱና ይህ ሲሆን እርዳታ እንደሚሰጥ አስታወቀ። በዚህ መልስ ያልረኩት ቴዎድሮስ ራሳምን እንዲሁ በመቅደላ እስር ቤት ከተቱት ።

ለሰላም መውረድ የመጨረሻው ተስፋ ነው የተባለው ሚሲዮኑ ማርትን ፍላድ በሐምሌ 1858 ከቴዎድሮስ ወደ እንግሊዝ ተላከ። ጥር 1859 ላይ ንጉሰ ነገሥቱ እስረኞቹን ፈተው ወደ ምጽዋ ከተወሰዱ በምትኩ የእንግሊዝ መንግስት ወታደራዊ እርዳታ እንደሚያደርግ ደብዳቤ ከእንግሊዝ መንግስት ደረሳቸው። በመካከሉ፣ ኢትዮጵያው ውስጥ የነበረቸው የማርቲን ፍላድ ሚስት፣ አውሮጳውያኑ እንደገና እንደታሰሩ ለባሏ አሳወቀች። ታህሳስ 185 ላይ እስረኞቹ ተፈተው ወደ ምጽዋ እንዲላኩ ፍላጎቱን አስታወቀ። በዚህ ወቅት ንጉሰ ነገሥቱ በማያባራ ዘመቻና የማያቋርጥ አመጽ ተጠምደው ስለነበር ከመቅደላ ምጽዋ ያለውን መንገድ መቆጣጠር አይችሉም ነበር። ስለሆነም ሚያዚያ 1859 ከእንግሊዝ የደረሳቸውን ዛቻ መልስ ባለመስጠት ችላ አሉት ፣ በዚህ ሁኔታ የእንግሊዝ መንግስት እስረኞቹን ለማስፈታት ዘመቻ ለማድረግ ወሰነ።

በመረጃ ልውውጥ ላይ በተነሳው ችግርና እንዲሁም እንግሊዞች ለንጉሱ የላኩት ዛቻ መልስ ባለማግኘቱ ምክንያት ነሐሴ 1859 እንግሊዞች በሮበርት ናፒየር የሚመራ 32፣000 ጦር ሰራዊት አዘመቱ። እንግሊዞቹ በዚህ ወቅት በኢትዮጵያ ስለሚሆነው ጉዳይ ጥልቅ መረጃ የነበራቸው ሲሆን በየአካባቢው እየተነሳ ስለነበር አመጽ ሙሉ ግንዛቤ ነበራቸው። የቴዎድሮስ ሰራዊት በድሮ ጊዜ ወደ 100፣000 የሚጠጋ የነበር ሲሆን በ1859 ከ5 እስከ 10፣000 በላይ አይሆንም ነበር። ንጉሰ ነገሥቱ የመጨረሻ ዘመቻቸውን ፈጽመው በጥቅምት 1860 ላይ መቅደላ ደረሱ፣ ይሄውም ከናፒየር ሰራዊት 2 ሳምንት ቀድሞ ነበር።

የእንግሊዝ ሠራዊት ያለምንም ችግር ምጽዋ ላይ ካረፈ በኋላ ከሌሎች የኢትዮጵያ ኃይሎች ለምሳሌ ካሳ ምርጫ ድጋፍ በማግኘት፣ ከተክለ ጊዮርጊስ ሐዘን በማግኘት፣ ከዳግማዊ ምኒልክ ድጋፍም ሆነ ተቃውሞ ሳይደርስበት ያለ ችግር ወደ መቅደላ ተመመ። የብሪታንያ ሠራዊት በተለይ ከፍተኛ ድጋፍ ያገኘው ከካሳ ምርጫ ሲሆን፣ በቂ የመጓጓዣና የምግብ እርዳታ ያገኙት ከኒሁ ሹም ነበር። ሚያዚያ ፲ ቀን ፲፰፻፷ ዓ/ም ላይ የመጀመሪያውና የመጨረሻው የፊት ለፊት ጦርነት በቴዎድሮስ ሰራዊትና በናፒየር ሰራዊት መካከል ተካሄደ70። ይህ ጦርነት በታሪክ የአሮጌ ጦርነት ተብሎ ሲታወቅ ከመቅደላ እግርጌ የተደረገ ውጊያ ሲሆን በዚሁ ጦርነት የኢትዮጵያ ሰራዊት ተሸንፎ አፈገፈገ 12። 

በሚቀጥለው ቀን፣ ሚያዚያ11 ላይ፣ ናፒየር ለቴዎድሮስ በጻፈው ደብዳቤ ንጉሡ እስረኞቹን ከፈቱና ለእንግሊዟ ንግሥት እጅ ከሰጡ በክብር እንደሚያዙ አሳወቃቸው። ሆኖም ንጉሰ ነገሥቱ ከኩራታቸው አንጻር ይህን አይነት መዋረድ እንደማይቀበሉ አሳወቁ። በዚህ ሁኔታ ንጉሱ አቋማቸውን በደምብ የሚያሳውቅ፣ በጊዜው ድንቅ የተባለ፣ ማንነታቸውንም በርግጥ የሚይሳይ ደብዳቤ ጻፉ። ለናፒርየር የተጻፈው ይህ ደብዳቤ አጠቃላይ የጊዜውን የኢትዮጵያ ሁኔታ የዳሰሰና ለኢትዮጵያ ህዝብ የገቡት የመጨረሻ ኪዳን ነበር።

እኒህን የጀግንነት ቃላት ካስጻፉ በኋላ ንጉሱ እራሳቸውን ሊያጠፉ ቢሞክሩም ወታደሮቻቸው ሽጉጣቸውን ከጃቸው ነጥቀው አዳኗቸው። ይህ ሁሉ ሲሆን ከእንግሊዞች ጋር የሚደረገው ድርድር አላቋረጠም፣ ንጉሰ ነገሥቱም ጥሉን በሰላም ለመፍታት ከመሞከር አልተቆጠቡም። ለፋሲካ በዓል ማክበሪያ ብለው ንጉሱ ለናፒየር ብዙ ከብቶች በስጦታ ላኩ። የእንግሊዙ ጦር አዛዥ ግን የከብት ስጦታውን አልቀበልም በማለት መልሶ ላከ። የስጦታውን አለመቀበል ንጉሱ ሲሰሙ ከመቅደላ ለመውጣት ሞከሩ ሆኖም ግን መቅደላ በእንግሊዞች ተከቦ ነበር።

በዚህ ወቅት ለብዙ ወቅት የታሰሩት ሚሲዮኖችና የፖለቲከኛ እስረኞች ተፈቱ። የተፈቱትን እስረኞች ያዩ ገለልተኛ ተመልካቾች፣ በፈረንሳይ፣ በሩሲያ፣ በሳውዲ አረቢያ፣ በሆላንድ፣ አውስትራሊያና ስፔን በእስረኞቹ መልካም ጤና በጣም ይደነቁ ነበር፣ ከእስረኞቹ አንዱም «በታስርነበት ወቅት ጥሩ ቤትና ምግብ ነበረን የምንፈራው የንጉሱን ቁጣ ነበር»።

ሚያዚያ ፮ ቀን ሦስት ሰዓት ላይ እንግሊዞች በመቅደላ ምሽግ ላይ የመጨረሻ ጥቃት አደረሱ። ንጉሱ፣ የሃይል ሚዛኑ ወደ እንግሊዞቹ ሙሉ በሙሉ አንዳጋደለ ስለተረዱ ለወታደሮቻቸው እንዲህ በማለተ ተለይተው ሄዱ ተፈጽሟል! ከርሱ እጅ ከምወድቅ ብሞት ይሻለኛል። ወዲያውም ከንግስት ቪክቶሪያ የተላከላቸውን ሽጉጥ መዘው በመጉረስ በጀግንነት አለፉ።

እንግሊዞቹ 9 ሚሊዮን ፓውንድ አውጥተው ዘመቻውን ሲያቅዱ የመቅደላን ምሽግ አፍርሰው ንጉሱን ለመማረክ ነበር። ሆኖም ምሽጉ ሲሰበር ንጉሱ ሞተው ስልተገኘ ናፒየር እጅጉን በመናደዱ ሙሉውን መቅደላ እንዲመዘብርና  የተረፈው በእሳት እንዲጋይ አደረገ። ሚያዚያ 18 ላይ እንግሊዞቹ የተከፋፈለች አገር ትተው ሄዱ፣ ወዲያም ግንቦት 1860 ላይ የላስታው ዋግሹም ጎበዜ በ60፣000 ጠንካራ ወታደሮቹ በመታገዝ ንጉሰ ነገሥት ዳግማዊ አጼ ተክለ ጊዮርጊስ በመባል ስልጣን ላይ ወጣ።

እንደ ባህሩ ዘውዴ አስተያየት የቴዎድሮስ ህይወት በ3 ቦታወች ይጠቃለላል፡ ቋራ፣ ጋፋትና መቅደላ። የመጀመሪያው የፖለቲካና ውታደራዊ መሰረትን ሲወክል፣ ሁለተኛው የዘመናዊነትን ፍላጎት ይወክላል፣ ሶስተኛው ደግሞ መጠለያንና፣ የሞት ቦታን ይወክላል። አጠቃላዩ የቴዎድሮስ ውጤት ቅይጥ ነው፣ የሚለው ባህሩ ዘውዴ፣ ለውጡ ስልትና ጭብጥ ይጎለዋል ሲል። ብዙው ለውጥ ሙሉ በሙሉ ያልተተገበረ ሙከራ ነበር ይላል። በአጠቃላይ መልኩ፣ ለውጡቹ ሊተገበሩ የሚችሉ የነበሩ በሂንም 60 ላለመተግበራቸው የተወሰኑ ምክንያቶች ነበሩ 68።የመጀመሪያው ምክንያት የኢትዮጵያ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ ሲሆን ተራራማው ምልክዓ ምድር ተገቢ የሆነ የርስ በርስ መርጃ ልውውጥን ስለሚያግድ ለውጦቹን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ለማስተዋወቅ አስቸጋሪ ነበር። ሌላው ደግሞ ታላቅ የወታደራዊ መዋቅራቸውን ወደ ፖለቲካዊ የበላይነት ለመተርጎም አለመቻላቸው ነበር። አንድ ክፍለ ዘመን ሙሉ ያለምንም መካከለኛ መንግስት የነበረን አገር በንጉሰ ነገሥቱ መልካም ፈቃድ ብቻ ለማስተካከል የማይቻል ነው። በፖለቲካ ሹመት አዲስ የገዢ መደብ ለመፍጠር የሞከሩትም ሁኔታ ከነባር ጥንታዊ ገዥወች ጋር ያጣላቸው ነበር60። ፓውል ሄንዝ እንደጻፈ ግን ምን አልባትም የተዋቀረ መንግስት እና አንስተኛ አስተዳዳሪወች ቢኖራቸው፣ ንጉሱ ያሰቡትን ለውጥና ተሃድሶ ማድረግ ይችሉ ነበር። የንጉሱ ተራማጅ ግቦች በቂ ስልትና አስፍላጊ ጥሬ ሃብት አልነበረውም 47፤ እንዲሁም ለነበሩበት ጊዜ የሚፈጥንና የሚጋጭ ነበር።
 
ታሪክ ጸሃፊወች ቴዎድሮስ ከፈጸሙት ተግባራት ይልቅ ባሳዩት አርቆ አሳቢነትና ሊፈጽሙት በሞከሩት ተግባራት ሲያነሱ 60 ሺፈራው የተባለው የታሪክ ተመራማሪ ብዙ ጊዜ ታሪክ ጸሃፊወች ከዚህ ጎን ለጎን የቴዎድሮስን ህጋዊ መሪነት ጥያቄ ስር ሲጥሉ ይታያሉ ብሏል። ታሪክ አጥኝው ፓውል ሄንዝ እንደመዘገበ ከ20ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ጀምሮ ቴዎድሮስ በኢትዮጵያን ዘንድ በጣም ታዋቂው መሪ ሆነ። ንጉሱ ከሞቱ በኋላ በትውልዶች ዘንድ ለየት ያሉ ሰው መሆናቸው እየታመነ ሄደ፣ አንድ አንድ ጊዜም በተጋነነ ሁኔታ ። በተለይ ንጉሱ እስካሁን የሚታወሱበት ዋና ምክንያት ከጊዜይቸው ቀደም ብሎ በነበራቸው የተለያዩ እቅዶች ነበር።

 
በኢትዮጵያኖች አይን ቴዎድሮስ የዘመናዊ ስልጣኔን በር ከፋች ሲሆኑ  እንደገና አንድ የሆነችና ጠንካራ ኢትዮጵያም ምልክት ናቸው። የአገሪቱን ፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ አንድነት ለመመለስ ታላቁ ምኖታቸው ነበር፣ ያገሪቱን ጥንታዊ ድንበርም ለማስመለስ እንዲሁ 60። ምንም እንኳ በጊዜያቸው ብዙወች ባይረዷቸውም አገራቸውን ለማሰልጠንም ከፍተኛ ርብርብ አድርገዋል60። በፖውል ሄንዝ አስተሳሰብ ንጉሱ ለአንድ ክፍለ ዘመን ሲበሰብስ የነበረውን መንግስት በመቅጨት ተራማጅነትን፣ አንድነትንና ስልጣኔን አስተዋውቀዋል፣ ስለሆነም የመጀመሪያው ዘመናዊና ማዕከላዊ መሪ ነበሩ። የብሄራዊ አንድነት መፍጠርን ሂደት ንጉሱ ዙፋን ላይ ከወጡ ጀምሮ አካሂደዋል። በሞቱ ጊዜ ብዙውን ህዝብ ከእንቅልፍ በመቀስቀሳቸው፣ የርሳቸው ተከታዮች ንጉሱ የጀመሩትን ስራ ሊያስፈጽሙ ችለዋል። እንደ ታሪክ አጥኝው ሃሮልድ ማርከስአስተያየት የዳግማዊ አጼ ምንሊክ ግዛት በቴዎድሮስ የተጠነሰሰውና በአጼ ዮሓንስ የታደሰውን የማዕከላዊ ግዛትን ሃሳብ ድል ያበሰረ ነበር። በመጨርሻም ሌላው አጼ ቴዎድሮስ በኢትዮጵያውያን ዘንድ የሚታወሱበት ምክንያት በከፍተኛ ጀብዱዋቸውና ከርሳቸው በላይ ከፍ ባሉ ሰራዊቶች ላይ በተቀዳጇቸው አስገራሚ ድሎች ምክንያት ነበር ። 

ከሌሎች ታላላቅ መሪወች ይልቅ የአጼ ቴዎድሮስ አሟሟት በኢትዮጵያን ዘንድ የማይረሳ ነው 39። በጀግንነት፣ እጅ አልሰጥም ብለው ማለፋቸው ለህዝቡ ቅቤ ያጠጣ ተግባር እንደነበር ታሪክ አጥኝው ብርሃኑ አበበ ይገልጻል። ስለሆነም ንጉሱ በሞቱ ጊዜ የተገጠሙት ግጥሞች እስካሁን ድረስ በብዙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ይታወቃሉ።

የቴዎድሮስ እራሳቸውን ማጥፋት በጊዜው ለነበሩና አሁን ድረስ ላሉ ሰዓሊያን ስእሎች ጥሩ ርዕስ ሆነ። የንጉሱ ሞት በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአውሮጳ ሳይቀር ለቴዎድሮስ ከፍተኛ ሃዘንና አድናቆትን አተረፈ። «ማርከው ሊወስዷቸው አቅደው የመጡትን እንግሊዞች ግብ በማኮላሸት »ቴዎድሮስም በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ቦታን አገኙ። ብዙ የልቦለድ ጸሃፊያን እና ቲያትር አዘጋጆች ለቴዎድሮስ እስካሁን ድረስ ይደርሳሉ ይጽፋሉ፣ ምሁራንም ቢሆን አሁን ድረስ ልጆቻቸውን በንጉሱ ስም ይሰይማሉ። የኢትዮጵያ ዘፋኞች፣ ዘመናዊ ዘፋኞች ሳይቀሩ የንጉሱን ስም ይጠቅሳሉ። እንደ ብርሃኑ አበበ አስተሳስብ የምርኮን ውርደት አሻፈረኝ በማለት በመሞታቸው በኢትዮጵያውያን ዘንድ ከፍተኛ ግምትን ንጉሱ እንዲያገኙ አድርጓል።




#Article 264: ምጽራይም (235 words)


ምጽራይም (ዕብራይስጥ፦ מִצְרָיִם /ሚጽራዪም/) በኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 10 መሠረት ከኖህ ልጆች መካከል የካም ሁለተኛ ልጅ ነበረ። የምጽራይምም ልጆች ሉዲም፣ ዐናሚም፣ ላህቢም፣ ነፍታሌም፣ ፈትሩሲም፣ ከስሉሂምና ቀፍቶሪም ናቸው። 

የ«ሚጽራዪም» ትርጉም በዕብራይስጥ ደግሞ ግብጽ (ምሥር) አገር ነው። እንዲሁም በአረብኛ የአገሩ ስም مصر (ምጽር) ይባላል። ስሙ ዕጅግ የቆየ መሆኑ እርግጠኛ ነው። በአካድኛ መዝገቦች የግብጽ ስም «ሙሱር»፣ «ሙስሪ»፣ በኡጋሪትም ጽላቶች «ምስርም» ተብሏል። 

አባ አውሳብዮስ በጻፉት ዜና መዋዕል ዘንድ፣ የድሮ ግብጻዊው ባለታሪክ ማኔጦን (3ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ.) ስለ ኋለኞቹ ግብጻውያን ሲጽፍ፣ ይኮሩበት የነበረው የታላቁ ጥንት ዘመን ከማየ አይህ አስቀድሞ እንዳለፈ፣ በኋላም በዚያው አገር ዳግመኛ ከሠፈረበት ከካም ልጅ ምጽራይም በውኑ እንደ ተወለዱ ጽፎ ነበር። ተመሳሳይ ታሪክ በእስላም ጸሐፊዎች በግብጻዊው እብን አብድ ኤል-ሀከም እና በፋርሳውያን አል-ታባሪና ሙሐመድ ቈንዳሚር መጻሕፍት ሲገኝ፣ ፒራሚዶች፣ እስፊንክስ ወዘተ. ሁሉ የተሠሩ ከጥፋት ውኃ በፊት በኖሩት ክፉ ዘሮች ሆኖ፣ ከዚያ በኋላ ግን አገሩ ለካም ተወላጅ ለምጽራይም (ማሣር ወይም መሥር) ተሠጠ ብለው ጻፉ።  በነዚህም ደራስያን ዘንድ የመሥር ዕድሜ እስከ 700 መቶ አመት ድረስ ደረሰ። 

በፊንቄ አፈ ታሪክ ዘንድ፣ «ሚሶር» የሚባል ሰው የታዓውቶስ አባት ሲሆን የጌባል ንጉሥ ክሮኖስ ግብጽን ለዚሁ ታዓውቶስ እንደ ሰጠ ይታመን ነበር።

በዕብራይስጥ ስዋሰው «-አዪም» የሚለው ባዕድ መድረሻ የድርብ ቁጥር ምልክት ሲሆን ስሙ 'ሁለት ምድሮች' ይመስላል፤ የዚህም ትርጉም በጥንታዊ ግብጽኛ «-ታ-ውይ» ነው። ከመጀመርያው መካከለኛ ዘመን ጀምሮ ግብጽ «-ታ-ውይ» (ሁለቱ ምድሮች ወይም «ላይኛው መንግሥት» እና «ታችኛው መንግሥት») ይባል ነበር። ይህም በ፱ኛው ሥርወ መንግሥት ፈርዖን ስም መሪብታዊ ቀቲ (2300 ዓክልበ. አካባቢ) ይታያል። 

ጸሓፊው ጊዮርጊስ ስንቄሎስ (800 ዓ.ም. አካባቢ) አስተሳሰብ ግን ምጽራይም የግብጽ ቀድሞ ዘመን መንግሥት የመሠረተው ፈርዖን መኔስ እንደ ነበረ ገመተ።




#Article 265: መጽሐፍ ቅዱስ (1117 words)


መጽሐፍ ቅዱስ ነብያት እና ታሪካውያን የጻፉት የክርስቲያኖች እምነት መጽሓፍ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በብሉይ ኪዳንና በአዲስ ኪዳን ተከፍሎ 66 መጻሕፍት ያሉት ሲሆን በአንዳንድ እምነቶች ደግሞ 83 ክፍል ብቻ ነው አሉት ብለው ያምናሉ። ከነዲዩትሮካኖኒካል መጻሕፍትም ጋራ የመጻሕፍት ቁጥር 81 ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ከመቶ 25% የአምላክ ንግግር፣ ከመቶ 25 % የነብያት ንግግር እና ከመቶ 50 % የታሪክ ጽሐፍያን ንግግር ይዟል። ነገር ግን በነብያት ውስጥም በቃሉም በታሪክም ተነገረ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ነው

በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተለመደው «ባይብል» የሚለው ቃል ከጥንቱ የኮይነ ግሪክኛ ቋንቋ የተወሰደ ሲሆን ቃሉ የተገኘበት τὰ βιβλία /ታ ቢብሊያ/ የሚለው ሀረግ «መጽሐፍቱ» ወይም «ትንንሽ መጽሐፍት» ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። የዚሁም ቃል መነሻ ከግሪኩ ስም Βύβλος /ቢውብሎስ/ (ፓፒሩስ ወይም ቄጠማ፣ የወረቀት ተክል) ሲሆን ይሄ ቃል «ፓፒሩስ» ከተነገደበት ከተማ ጌባል / ቢውብሎስ ስም መጣ።

መጽሐፍ ቅዱስ ለአይሁድና ክርስትና እምነት የእምነት መሰረት የሆኑ ትናንሽ መጽሐፍትን የያዘ አንድ ጥራዝ ነው። በተለምዶ «ብሉይ ኪዳን» በመባል የሚጠራውና በአይሁዳውያን በ24 እና በክርስቲያኖች በ39 መጽሐፍት የሚከፈለው የመጽሐፍ ቅዱስ የመጀመሪያ ክፍል በመጀመሪያ በአብዛኛው የተጻፈው በጥንታዊው የዕብራይስጥ ቋንቋ ሲሆን የተጻፉበት ዘመን ከክርስቶስ ልደት በፊት የተወሰኑ መቶ አመታት ቀደም ብሎ እንደሆነ ይነገራል። እነዚህን መጽሐፍት የጻፉት በወቅቱ የነበሩ የታመኑ አይሁዳውያን ወይም እስራኤላውያን ናቸው። የመጨረሻዎቹን 27 መጻሕፍት በግሪክኛ የጻፏቸው ክርስቲያኖች ሲሆኑ «አዲስ ኪዳን» በመባል በሰፊው ይታወቃሉ። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው ማስረጃም ሆነ በጣም ጥንታዊ የሆኑት ወጎች እንደሚጠቁሙት እነዚህ 66 መጻህፍት የተጻፉት ግብጽ ኃያል ከነበረችበት ጊዜ አንስቶ ሮም የዓለም ኃያል መንግስት እስከ ነበረችበት ዘመን ባሉት 1600 ዓመታት ውስጥ ነው።

በካቶሊክ ቤተክርስቲያን እምነት መሰረት ከ66ቱ መጽሐፍት በተጨማሪ የተካተቱ የተወሰኑ መጽሐፍት ሲኖሩ፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እነዚህ ተጨማሪ መጻሕፍት (ዲዩቴሮካኖኒካል በመባልም ይታወቃሉ) በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተካተቱትን መጻሕፍት ቁጥር ወደ 81 ያደርሱታል።በ greek እና hibrew የተፃፈው 66 ነው::

ከክርስቶስ ስብከት ቀጥሎ ምዕመናን የሆኑት ለረጅም ዘመን ተጨማሪ መጻሕፍቱን ከነመጽሐፈ ሄኖክና ኩፋሌ ያንብቡ ነበር። የአይሁድ ሰንሄድሪን ረቢዎች በ100 ዓ.ም. አካባቢ  በተለይም ረቢ አኪቫ በን ዮሴፍ እነዚህን ተጨማሪ መጻሕፍት ከዕብራይስጥ ቅጂ አጠፉ። እስካሁንም ድረስ በዕብራይስጥ ትርጉም አይታወቁም። አዲስ ኪዳን ከተጻፈ በኋላ፣ ብዙ አጠያያቂ ወንጌሎችና የሌሎች እምነቶች ጽሑፎች ደግሞ ሊሠራጩ ጀመር። ግኖስቲክ የተባለው እምነት ተከታዮች በተለይ ብዙ ሥነ ጽሑፍ ፈጠሩ፣ ይህ ግን ከኦርቶዶክስ ወንጌል የተዛቡ ትምህርቶች ነበር። በ170 ዓ.ም. በክርስትያኖች ዘንድ የቱ መጻሕፍት ትክክለኛ ቅዱሳን መጻሕፍት ናቸው? የሚል ጥያቄ ይነሣ ጀመር። መሊቶ ዘሳርዲስ የተባለ ጳጳስ በዚያን ጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም መጻሕፍት ቤት ጉዞ አድርጎ የ ዕብራውያን መጻሕፍት ምን ምን እንደ ነበሩ ዘገበ። ተጨማሪ መጻሕፍቱ ከዚያ በፊት ስለ ጠፉ አልተዘገቡም። ስለዚህ ከዚህ በቀር ምንም ያልተዘረዘሩት ብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ትክክለኛ አይሆኑም የሚል ሀሣብ በሮሜ መንግሥት ክርስቲያኖች ተነሣ። ይህም የአይሁዶች ቀኖና በንቅያ ጉባኤ (317 ዓ.ም.) በሮሜ መንግሥት ለክርስቲያኖች ጸና።

መጽሐፍ ቅዱስ የስነምግባር ጉዳዮችን በሚመለከት መመሪያ የሚሰጥ ከመሆኑም ሌላ እንደ ወንጀል፣ ረሃብና የአካባቢ መበከል ያሉት ችግሮች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መፍትሔ የሚያገኙበትን መንገድ ይገልጻል። ችግሩ ግን፣ መጽሐፍ ቅዱስ እነዚህን ጉዳዮች አስመልክቶ የሚናገረውን ነገር ብዙ ሰዎች በቁም ነገር መመልከት ትተዋል። ከዚህ ቀደም ይህ መጽሐፍ ቢያንስ በምዕራቡ ዓለም እንኳ ትልቅ ተሰሚነት ነበረው። መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው በሰዎች አማካኝነት ቢሆንም እንኳ ቀደም ባሉት ጊዜያት በሕዝበ ክርስትና ውስጥ የነበሩት አብዛኞቹ ሰዎች የአምላክ ቃል መሆኑንና መልእክቱም አምላክ በመንፈስ አነሳሽነት ያስጻፈው እንደሆነ ያምኑ ነበር።

ይሁን እንጂ ዛሬ እያንዳንዱን ነገር መጠራጠር የተለመደ ነገር ሆኗል። ሰዎች ባህላቸውን፣ የተለያዩ ጽንሰ ሐሳቦችን፣ የስነምግባር ደንቦችንና የአምላክን መኖር እንኳ ሳይቀር የጠራጠራሉ። በተለይ የመጽሐፍ ቅዱስን ጠቃሚነት በተመለከተ ጥርጣሬ ገብቷቸዋል። አብዛኞቹ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን ጊዜ ያለፈበትና አላስፈላጊ እንደሆነ አድርገው የሚያዩት ይመስላል። ከዘመናችን ምሁራን መካከል መጽሐፍ ቅዱስን እንደ አምላክ ቃል አድርገው የሚመለከቱት በጣም ጥቂት ናቸው። እንዲያውም አብዛኞቹ ሰዎች ከምሁሩ ጄምስ ባር አባባል ጋር ይስማማሉ፡- ስለ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ልማዶች ያለኝ አመለካከት የሰው ልጅ የፈጠራ ውጤት ናቸው የሚል ነው። የሰው ልጅ የራሱን እምነት ያሰፈረበት መጽሐፍ ነው።

ይህ አመለካከት ወደ አንድ ነጥብ ያመራል፦ መጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች የጻፉት ተራ መጽሐፍ ከሆነ ለሰው ልጅ ችግሮች ምንም ዓይነት ግልጽ የሆነ መልስ አይገኝም ማለት ነው። የሰው ልጆች በገዛ እጃቸው በሚያመጡት ጣጣ ከህልውና ውጭ እንዳይሆኑ ወይም በኑክሊየር ጦርነት እንዳያልቁ አቅማቸው የፈቀደውን ያህል በጭፍን መዳከር ይኖርባቸዋል ማለት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል ከሆነ ግን ይህን አስቸጋሪ ጊዜ ለማለፍ የሚያስፈልገን ዋነኛው ነገር እርሱ ይሆናል።   

የታሪክ መዝገቦች ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላሉ?

መጽሐፍ ቅዱስ በብዛት ታትሞ በመሸጥና በሰፊው በመሰራጨት ረገድ በሰው ዘር ታሪክ ውስጥ ቀዳሚውን ስፍራ ይዟል። ጊነስ ቡክ ኦቭ ወርልድ ሬኮርድስ የተባለው መጽሐፍ በ1988 እትሙ እንደገለጸው ከ1815 እስከ 1975 ባሉት ዓመታት ውስጥ ብቻ ወደ 2.5 ቢልዮን የሚገመቱ ቅጂዎች ታትመዋል። ይህ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ነው። የመጽሐፍ ቅዱስን ያህል ሊሰራጭ ይቅርና ወደዚያ ቁጥር የተጠጋ አንድም መጽሐፍ በታሪክ አልታየም።

ከዚህም በተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስን ያህል በብዙ ቋንቋዎች የተተረጎመ መጽሐፍ አይገኝም። ዛሬ መጽሐፍ ቅዱስ ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል ከ1800 በሚበልጡ የተለያዩ ቋንቋዎች ይገኛል። በኢትዮጵያ እንኳን በአማርኛ፣ ትግሪኛ፣ ኦሮምኛ፣ ወላይትኛ፣ ጉራግኛና ሌሎች ቋንቋዎች መጽሐፍ ቅዱስ በሙሉም ሆነ በከፊል ተተርጎሞ ይገናል። በአጠቃላይ ዛሬ 98 በመቶ ገደማ የሚሆነው የምድራችን ነዋሪ መጽሐፍ ቅዱስን በቋንቋው ማግኘት ይችላል።

ዘ ኒው ኢንሳይክለፒዲያ ብሪታኒካ መጽሐፍ ቅዱስን በታሪክ ዘመናት ከታዩት ጽሑፎች ሁሉ ይበልጥ ተደማጭነት ያለው የመጻህፍት ስብስብ ሲል ጠርቶታል። የ19ኛው ጀርመናዊ ባለቅኔ ሄንሪክ ሃይነ እንዲህ ብለዋል፦ ይህን ሁሉ ማስተዋል ያገኘሁት ከአንድ መጽሐፍ ነው። . . . መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብ። ቅዱስ መጽሐፍ መባሉ ይገባዋል። አምላኩን ያጣ ሰው ካለ በዚህ መጽሐፍ አማካኝነት ሊያገኘው ይችላል። በዚሁ መቶ ዘመን የኖረውና የጸረ-ባርነት እንቅስቃሴ አራማጅ የነበረው ዊልያም ኤች ሴዋርድ እንዲህ ብሏል፦ የሰው ልጅ የመሻሻል ተስፋ የተመካው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በሚሄደው የመጽሐፍ ቅዱስ ተደማጭነት ላይ ነው።

የዩናይትድ ስቴትስ 16ኛ ፕሬዚዳንት የነበሩት አብርሃም ሊንከን መጽሐፍ ቅዱስን በሚመለከት እንዲህ ብለዋል፦ አምላክ ለሰው ልጆች ከሰጠው ስጦታ ሁሉ የላቀ ስጦታ ነው። . . . መጽሐፍ ቅዱስ ባይኖር ኖሮ መልካሙንና ክፉውን ለይተን ማወቅ ባልቻልን ነበር። የብሪታንያው የህግ ሰው ሰር ዊልያም ብላክስተን ሁሉም ሰብዓዊ ሕጎች የተመሰረቱት በእነዚህ ሁለት ሕጎች ማለትም በተፈጥሮ ሕግና አምላክ ለሰው ልጆች በሰጠው ሕግ [በመጽሐፍ ቅዱስ] ላይ ነው፤ እንግዲያው ሰብዓዊ ሕጎች ከእነዚህ ሕጎች ጋር እንዲጋጩ ማድረግ አይገባም ማለት ነው። ብለው ሲናገሩ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያህል ተደማጭነት እንዳለው ጎላ አድርገው መግለጻቸው ነበር።

በአንጻሩ ደግሞ በታሪክ ዘመናት ሁሉ የመጽሐፍ ቅዱስን ያህል የከረረ ተቃውሞ የገጠመው መጽሐፍ የለም። መጽሐፍ ቅዱስ ከመካከለኛው ዘመን አንስቶ እስከ 20ኛው መቶ ዘመን ድረስ በአደባባይ ተቆልሎ እንዲቃጠል ተደርጓል። በዛሬው ዘመን እንኳ ሳይቀር መጽሐፍ ቅዱስን በማንበባቸው ወይም በማሰራጨታቸው ምክንያት የገንዘብ ቅጣት የተጣለባቸው ወይም በእስራት የተቀጡ ሰዎች አሉ። ባለፉት መቶ ዘመናት እንዲህ ያለው ወንጀል ብዙውን ጊዜ አሰቃቂ ለሆነ ድብደባ አልፎ ተርፎም ለሞት የሚዳርግ ነበር።

መጽሐፍ ቅዱስ በሰዎች ውስጥ ያሳደረው ፍቅር ከዚሁ ጎን ለጎን የሚታይ ነው። ብዙዎች የማያቋርጥ ስደት ቢደርስባቸውም መጽሐፍ ቅዱስን ማንበባቸውን ገፍተውበታል። ለምሳሌ ያህል በ16ኛው መቶ ዘመን የኖረውንና በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ተምሮ በካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ትልቅ ቦታ ያለው አስተማሪ የነበረውን ዊልያም ቲንደልን እንመልከት።

ቲንደል ለመጽሐፍ ቅዱስ ከፍተኛ ፍቅር ነበረው። ይሁን እንጂ በዘመኑ የነበሩት ሃይማኖታዊ ባለ ሥልጣናት መጽሐፍ ቅዱስ ሙት በነበረው በላቲን ቋንቋ ተወስኖ እንዲቀር ሽንጣቸውን ገትረው የሟገቱ ነበር። ቲንደል ግን የአገሩ ሶዎች መጽሐፍ ቅዱስን የማንበብ አጋጣሚ እንዲኖራቸው በማሰብ ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ ለመተርጎም ቆርጦ ተነሳ። ይህ ተግባሩ ከሕጉ ጋር የሚቃረን ስለነበር ቲንደል ጥሩ የማስተማር ስራውን ትቶ መሰደድ ግድ ሆነበት። የግሪክኛ ቅዱሳን ጽሑፎችን (አዲስ ኪዳን) እና አንዳንዶቹን የዕብራይስጥ ቅዱሳን ጽሑፎች (ብሉይ ኪዳን) ወደ አገሩ ቋንቋ ተርጉሞ እስኪጨርስ ኑሮውን በስደት ለመግፋት ተገዷል። ይሁን እንጂ በመጨረሻ በመያዙና መናፍቅ ነው ተብሎ በመወንጀሉ ተሰቅሎ እንዲሞትና በድኑም በእሳት እንዲቃጠል ተደርጓል።

ቲንደል፣ መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ ወይም ለሌሎች ሰዎች እንዲዳረስ ለማድረግ ሲሉ ብዙ መሥዋዕትነት ከከፈሉት በርካታ ሰዎች መካከል አንዱ ብቻ ነው። ከሌላው ሰው የተለየ ምንም ነገር ያልነበራቸውን ብዙ ወንዶችና ሴቶች ይህን ያህል ድፍረት እንዲኖራቸው ያነሳሳ ሌላ መጽሐፍ በታሪክ ውስጥ አልታየም። ከዚህ አንጻር መጽሐፍ ቅዱስ በእርግጥም አቻ አይገኝለትም።




#Article 266: ወላይትኛ (152 words)


ወላይትኛ በኢትዮጵያ በተጠቃሚ ብዛት በ4ኛነት የሚመደብና በደቡብ ኢትዮጵያ ውስጥ በሰፊው የሚነገር ቋንቋ ነው። ይህም ብቻ ሳይሆን የሌሎቹ ተቀራራቢ ቋንቋዎች ምንጭ ነው። ወላይትኛ ከሁሉም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች በፊት የመጀመሪያው የላቲን ፊደል መጽኃፍ ቅዱስ ታትሞበታል። ከወላይትኛ ጋር ዝምድና ያላቸው ሌሎች ቋንቋዎች ጋሞ-ጎፋ-ዳውሮ እና ኩሎና ኮንታ ናቸው። ባሁኑ ጊዜ በሥልጣን ላይ ያለው የኢሕአዴግ መንግሥት እነኚህን ተቀራራቢ ቋንቋዎች ነገር ግን 25% ትርጓሜዎቻቸው እርስ በርሳቸው በፍጹም የማይገናናኙትን  በማለት አዲስ ስያሜ በመስጠት የ1ኛ ደረጃ መማሪያ መጽሃፍ አዘጋጀ። ይሁን እንጂ  በተለይ በወላይታ ተወላጆች ዘንድ ኃይለኛ ቁጣን አስነስቶ በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ በርካታ ሰዎች ሕይወታቸውን በማጣታቸው ጉዳዩ የዓለምን ትኩረት ስቦ ነበር። 
ለምሣሌ ያህል፡  ማለት በወላይትኛ ሥራ ማለት ሲሆን በጎሙኛ ግን ግብረ ሥጋንኙነት የሚል ትርጓሜ ስላለው ለኅብረተሰቡ ያልተለመደና እጅግ አስነዋሪ ቃል ነው። በአንጻሩ ግን አብዛኛው ቃል ቢመሳሰልም በመጽኃፍ ደረጃ ታትሞ ለልጆች ትምህርት እንዲውል ገዢው መንግሥት በቂ ጥናት ስላላደረገ በቂ ግንዛቤ አልነበረውም።   
በተመሳሳይ ሁኔታ የዎላይታ ብሄራዊ ክልል ጥያቄ የህዝብ ጥያቄ ሆኖ የዞን አመራሮችና ጥቂት ግለሰቦች ነዉ በማለት ወላይተኛ ተናጋሪዎች መብት ተሟጋቾችን ጨምሮ አፈና ደርሶባቸዋል።




#Article 267: ኃይለማሪያም ደሳለኝ (746 words)


አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ በወላይታ አውራጃ በቦሎሶ ወረዳተወለዱ። የ1ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአከባቢያቸው የአየርላንድ ካቶሊክ ሚሺን ባቋቋመው ት/ቤት እንደፈጸሙ የ2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በወላይታ ሶዶ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፈጽመው በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በኢንጂነሪንግ ከተመረቁ በኋላ በአርባምንጭ ውኃ ተቋም አስተማሪ ሆነው እያገለገሉ ሳሉ የማስትሬት ዲግሪያቸውን በፊንላንድ ተምፔ ዩኒቨርስቲ በጽዳት ወይም ሳኒቴሺን አጠናቀው አገር ቤት በመመለስ በአርባምንጭ ውኃ ቴክኖሎጂ ዲን ሆነው አገልግለዋል። ከዚያም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በም/ፕሬዚዳንት፣ በፕሬዚዳንትና የኢሕአዴግ ዋና ጸሃፊ ሆነው አገልግለዋል። 

ተማሪ በነበሩ ጊዜ የደርግ ደጋፊ የነበሩት አቶ ሃይለማርያም፣ የማስተርስ ትምህርታቸውን ጨርሰው ሲመለሱ የመንግስት ለውጥ ስለነበረ፣ እሳቸውም የአቁዋም ለውጥ አርገው የገዚው መንግስት ደጋፊ መሆን ጀመሩ። የስልጣን ጥማታቸውንም ለማርካት፣ ከፖፑ በላየ ካቶሊክ እንደሞባለው፣ እሳቸውም የዘር ፖለቲካውን ከወያኔ ባለስልጣኖች በላይ ማናቸስ ጀመሩ። 

ባለቤታቸው ወይዘሮ ሮማን ተስፋዬ ከአከባቢያቸው ከወላይታ ዞን ሲሆኑ በኢኮኖሚክስና በሥራ ሃላፊነት ሁለት የማስተርስ ዲግሪ ምሩቅ ሲሆኑ ባለቤታቸው ወደ አዲስ አበባ እስከመጡበት ድረስ የደቡብ ኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ቢሮ /የባለቤታቸው/ ልዩ አማካሪና የሴቶች ጉዳይ ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል። ወ/ሮ ሮማን ከሃይስኩል እስከ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ድሕረ ምረቃ ድረስ ከባለቤታቸው ጋር አብረዋቸው በከፍተኛ ትምሕርት ዘልቀዋል። ወ/ሮ ሮማን ተስፋዬ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ድርጅት መሥርተው በኃላፊነት ከሰሩ በህዋላ ወደ ዩ.ኤን.ዲ.ፒ. ዓለም አቀፍ መሥሪያ ቤት ተዛውረው ሲሰሩ ቆይተው ከህዳር ወር ጀምሮ ሙሉ በሙሉ የቀዳሚ ወይዘሮ ቢሮ ተረክበዋል። በዚህም ሥራ መስክ የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያ ና የጎጂ ልማዶችና ባህሎች ማስወገጃ ሰሚናሮች ላይ እየተገኙ ንግግር በማድረግና ትምህርት በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ የኢሕአዴግ መንግስትና የወላይታ ሕዝብ በቋንቋ ምክንያት በተፈጠረው ውዝግብ ጊዜ የወጋጎዳ ቋንቋ የወላይታ ልጆች ተገደው እንዲማሩ ጫና አርገዋል ተብለው በሌሎች የአከባቢያቸው ጎሳዎች ዘንድ አለመወደዳቸው ጥቁር ነጥብ በታሪካቸው ጥሎ እንዳለፈ ይነገራል። እንዲሁም በደቡብ ክልል የክልል ምክትል ፕሬዚዳንት በነበሩ ጊዜ በጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ትዕዛዝ የበላይ አለቃቸውና የክልሉን ፕሬዚዳንት የነበሩትን አቶ አባተ ኪሾን ከስልጣን የሚያስወግድ ደብዳቤ በገዛ እጃቸው የጻፉና በምትካቸው ራሳቸውን ተክተዋል እየተባሉም ይተቻሉ። ይሁን እንጂ በመንግሥት ሚዲያ በኋላ እንደተነገረው አቶ አባተ ኪሾ በሙስና ምክንያት ከስልጣን መወገዳቸው ተዘግቦአል። 

በዚህም የተነሳ በጊዜው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መስተዳድር አስተዳደራቸውና እውቅናቸው እይደበዘዘ ስለመጣ የአካከባቢው ተወላጆች በተደጋጋሚ በሚቀሰቅሱት ተቃውሞች ከሥልጣናቸው ተነስተው ወዲያውኑ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢኮኖሚ አማካሪ ሆነው በታላቁ ቤተመንግሥት አከባቢ ቆይተው በ2003 በ8ኛው የኢሕአዴግ ጠቅላላ ስብሰባ ላይ የቀድሞውን ብሄረ አማር ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ መሪ አቶ አዲሱ አበበን በመተካት የኢሕአዴግ ምክትል ሊቀመንበር ለመሆን በቅተዋል። በተጨማሪም የደቡብ ክልላዊ መንግሥት የኢሕአዴግ ሊቀመንበር በመሆናቸው በፓርቲው ታሪክ የመጀመሪያው በትጥቅ ትግል ያልተሳተፉ ከፍተኛ ባለሥልጣን መሆን ብቻ ሳይሆን ከመለስ ዜናዊ ቀጥሎ ያለውን 2ኛውን ትልቅ ቦታ በጣም በአጭር ጊዜ ውስጥ ከመቆናጠጣቸውም በላይ የኢትዮጵያ 24ኛው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነዋል። 

ይህም በመሆኑ፡ ከሶስት ትላልቅ ብሄሮች ውጪ ማለትም አማራ፣ ትግሬ፣ ኦሮሞ ብሄር አባል ያልሆነ በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የደቡብ ተወላጅና ከኦርቶዶክስ እምነትተከታይ ውጪ ፕሮተስታንትየውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው እ.ኤ.አ ኦገስት 22 /2012 ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ አቶ ኃ/ማሪያም ወደ ተጠባባቂ ጠ/ሚኒስትርነት ማዕረግ ከፍ ብለው ለአንድ ወር ያህል ከቆዩ በኋላ የገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የፓርቲው ሊቀመንበርና ባለሙሉ ስም ጠ/ሚኒስትር እንዲሆኑ በመመረጣቸው እስከ 2015 ምርጫ ቀጣዩ የኢትዮጵያ መሪ በመሆን በኢትዮጵያ ታሪክ መዝገብ ላይ ስማቸውን አኑረዋል። 

የሚከተለው አስረጅ ከአይጋ ፎረም የተወሰደ ነው 

የ47 ዓመቱ አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ በደቡብ ክልል ወላይታ ዞን ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ በአረካ ከተማ ነው የተወለዱት ። የወጣትነት ዘመናቸውንም በዚህ በተወለዱበት ሰፍራ ያሳለፉ ሲሆን ፥ በ1980 ዓመተ ምህረት የባችለር ድግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በምህንድስና አግኝተዋል። ገና በወጣትነት ዘመናቸው የያኔውን የአርባምንጭ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የዛሬውን አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲን በመምህርነት አገልግለዋል ። በተቋሙ ቆይታቸው ባገኙት ነፃ የትምህርት እድልም ወደ ፊንላንድ በማቅናት ከታምፔሬ የቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በስነ ንፅህና ምህንድስና የማስተርስ ድግሪያቸውን ተከታትለዋል ። ከተመለሱም በኋላ የአርባ ምንጭ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዲን በመሆን ለ13 ዓመታት ያገለገሉ ሲሆን ፥ በነዚህ ጊዜያት ውስጥም ከአሜሪካው አዙሳ ፓስፊክ ዩኒቨርሲቲ በድርጅት አመራር የማስተርስ ድግሪ አግኝተዋል ። አቶ ሀይለማሪያመ ደሳለኝ በ1990ዎቹ መግቢያ ላይ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር /ኢህአዴግ/ አባል በመሆን በአገሪቱ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ መሳተፍ ጀምረዋል ። የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስትን በምክትል ርእሰ መስተዳደርነት ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ሀይለማሪያም በ1998 ለአራት ዓመታት የክልሉ ርእሰ መስተዳድር ሆነው ሰርተዋል ። በመቀጠልም አቶ ሀይለማሪያም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል በመሆን የተንቀሳቀሱ ሲሆን ፥ በምክር ቤቱ የመንግስት ጉዳዮች ተጠሪ ሚኒስትርም ነበሩ ። ከዚህ በተጓዳኝም በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ አማካሪም ሆነው የሰሩ ሲሆን ፥ የጠቅላይ ሚኒሰትሩ የማህበራዊ ጉዳዮች ፣ የህዝብ አደረጃጀትና ተሳትፎ ልዩ አማካሪም ሆነው የሰሩባቸው ጊዜያቶች ነበሩ ።ከ2002 አገር አቀፍ መርጫ በኋላም በድጋሚ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ሆነው የተመረጡ ሲሆን ፥ በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ካቢኔ ውስጥም በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነትና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ተሹመው በማገልገል ላይ ይግኛሉ ። በፓርቲያቸው ውስጥ ባላቸው እንቀስቃሴም የኢህአዴግ አባል በሆነው ድርጅታቸው በደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ንቅናቄ / ደኢህዴን/ ሊቀመንበር በመሆን ከ10 ዓመት ለሚበልጥ ጊዜ እየሰሩ ይገኛሉ ። የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልም ሲሆኑ ፥ ከሁለት ዓመት በፊት የድርጅቱ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ምክትል ሊቀመንበር ሆነውም ተመርጠዋል ። ከወይዘሮ ሮማን ተስፋዬ ጋር ትዳር መስርተውና ሶሳት ልጆች አፈርተው እየኖሩ የሚገኙት አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ ዛሬ የኢህአዴግ ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል። በፓርቲው አሰራርም መሰረት የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ያገለግላሉ።




#Article 268: ፍቅር (153 words)


ፍቅር ከልብ (ልቦና) ውስጥ የሚወጣ ጠንካራ የመውደድ ስሜት ነው። ፍቅር በብዙ አስተሳስቦች በኩል ልዩ ልዩ ትርጉሞች አሉት። ለምሳሌ «የሕይወት መዓዛ» ተብሏል።

በአይሁድም በክርስትናም በአንዳንድም ሌሎች ሃይማኖቶች በሚከብረው በብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ ፍቅረ ቢጽ በኦሪት ዘሌዋውያን 19፡18 ይታዘዛል፦ «ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ»... እንደገና ዘዳግም 10፡19፦ «እናንተ በግብፅ አገር ስደተኞች ነበራችሁና ስለዚህ ስደተኛውን ውደዱ።»

በመጽሐፈ ምሳሌ ደግሞ፦ «የጎመን ወጥ በፍቅር መብላት የሰባ ፍሪዳን ጥል ባለበት ዘንድ ከመብላት ይሻላል።» - (15፡17)
እናም ፍቅር ወሳኝ ነው

የፍቅር ትርጓሜ በክርስትና የሚገኘው በቆሮንቶስ ፩፣ ምዕራፍ ፲፫ ነው። ፍቅር «ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም» በማለት ያሳስበናል (፲፫፡፮)።

ክርስቲያኖች የሚቀበሉት አዲስ ኪዳን ስለ ፍቅር በርካታ ተጨማሪ ትምህርት ይጠቅሳል። ለምሳሌም፦ 

ፍቅር /love /
በእርግጥ  ስለፍቅር ብዙ ሰምተናል አይተናል  እንድሁም አንብበናል ነገር ግን በፍቅርም ዓለም የምኖር ሰው አለ ለማለት አያስደፍርም  ምክንያቱም በናፈቅር እንኳ ዘላቂ የሆነ በምክንያታዊነት የምንጠላቤት ሁነታ በሰዎች ህይወት ወይም ኑሮ ላይ ይታያልና  በአጠቃላይ 
ፍቅር ማለት ትዕግስት ነው
ፍቅር ማለት እውነት ነው
ፍቅር ማለት ባለእንጀራውን እንደራሱ መወደድ ማለት ነው




#Article 269: ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ (143 words)


መቶ አለቃ ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ከመስከረም ፳፰ ቀን ፲፱፻፺፬ ዓ/ ም ጀምሮ ለሁለት ዙር እስከ መስከረም ፳፯ ቀን ፳፻፮ ዓ/ም የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ሆነው ያገለገሉ አዛውንትና ከዘውድ ስርዓት ጀምሮ በደርግ እና በኢሕአዴግ መንግሥት የሠሩ የቀድሞ ወታደር ናቸው። መቶ አለቃ ግርማ ኦሮሚኛ፣ አማርኛ፣ አፋርኛ፣ እንግሊዘኛ፣ ጣሊያንኛ እና ፈረንሳይኛ አቀላጥፈው ይናገራሉ።

በ1917 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ተወለዱ፤ በልጅነታቸውም የቤተክህነት ትምህርት ከተማሩ በኋላ፣ በ1926 ዓ.ም. በተፈሪ መኮንን ትምሕርት ቤት ገብተው እስከ ጣልያን ወረራ ድረስ ዘመናዊ ትምህርት ተከታትለዋል፡፡

በ1930-33 ዓ.ም. ባሉት ጊዜያትም በአዲስ አበባ “ዘ ስኮላ ፕሪንሲፔ ፒዮሞንቴ” በተባለው የጣሊያኖች ትምሕርትቤት ገብተው ጣልያንኛ ቋንቋ አጥንዋል፡፡

በ1942 እና 1944 ዓ.ም. መካከለል ባሉት ጊዜያት ደግሞ በዓለም ዓቀፍ የሲቪል ማኅበር ድጋፍ በሚሰው የማሠልጠኛ መርኃግብር ፣ ከሆላንድ አገር በአስተዳደር ሙያ፣ ከስውዲን አገር በአየር ትራፊክ አስተዳደር፣ እንዲሁም ከካናዳ አገር በአየር ትራፊክ መቆጣጠር የተለያዩ የምሥክር ወረቀቶችን አግኝተዋል፡፡

መንግሥታዊ፣ አስተዳደር ተሞክሮዎቻቸው

ከመንግሥት አስተዳደር ውጪ የሆኑ ተሞክሮዎቻቸው

(ማስታወሻ፣ ሁሉም የዘመን አቆጣጠር እንደ ኢትዮጵያዊያን የዘመን አቆጣጠር ነው፡፡)




#Article 270: ፀሐይ ዮሐንስ (123 words)


ፀሐይ ዮሐንስ (፲፱፻፶፬ ዓ.ም. ተወለደ) የኢትዮጵያ ታዋቂ ዘፋኝ ሲሆን ብዙ ዘመናዊ የሙዚቃ ስራወችን  በማቅረብ ይታወቃል።

ፀሐይ ዮሐንስ በ፲፱፻፶፬ ዓ.ም. በኤርትራ ክፍለ ሀገር አሥመራ ከተማ ተወለደ። ፀሐይ ከአባቱ ጋር ወደ አዲስ አበባ መጥቶ ትምህርቱን በሚከታተልበት ወቅት የሙዚቃ ችሎታውን ለማዳበር ቻለ። የ፭ኛ ክፍል ተማሪ እያለ በአብዮቱ ወቅት ፷ ሺህ ተማሪዎች ወደ ገጠሪቱ ኢትዮጵያ ለዕድገት በሕብረት ዘምተው ሳለ «በርታ ዘመዴ ዘማቹ ጓዴ» የተሰኘው የመጀመሪያውን ሙዚቃ ለሕዝብ በማቅረብ በወቅቱ ከፍተኛ አድናቆት ተችሮታል።

ከዚያም መሀይምነትን ለማጥፋት የመሠረተ ትምህርት ዘመቻ በታወጀበት ጊዜ «ማንበብና መፃፍ» የተሰኘው ዘፈኑ በጣም ቀሽቃሽና አስተማሪ ስለነበር ፀሐይን ይበልጥ እንዲታወቅ አድርጎታል።

ከእነዚህም ማህበራዊ ሕይወትን ከሚገልፁት በተጨማሪ በ፲፱፻፸፭ ዓ.ም. ካሰማቸው ዘፈኖቹ ውስጥ «ፍንጭትዋ»፣ «ያዝ ያዝ» እና «ጡር ነው» የተሰኙት በሕዝቡ ዘንድ ውዴታን ያገኙ ነበሩ። ፀሐይ አሁንም ቢሆን የተለያዩ ዜማዎችን በመዝፈን በሕዝቡ  ዘንድ ከፍተኛ አድናቆት ያለው አርቲስት ነው። 




#Article 271: እግዚአብሔር (220 words)


እግዚአብሔር የግዕዝ ቋንቋ ቃል ሲሆን ትርጓሜውም እግዚእ ማለት ገዢ ወይም ጌታ ሲሆን፤ ብሔር ማለት ደግሞ የሰው ስብስብ ወይም አገር ማለት ነው። የተሟላ ትርጉም ፡ የብሔር ገዢ ከሁሉ በላይ የሆነ ፡ ዓለምን የፈጠረ ፡ ብቸኛ አለቃ ማለት ነው።  

የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የተጻፉት በሶስት ቋንቋዎች ሲሆን የመጀመሪያው ክፍል በዕብራይስጥና በአረማይክ እንዲሁም የኋለኛው በግሪክ መሆኑ ይታወቃል። እግዚአብሔር በሚለው የግዕዝ ቃል የተተካው ስም በዋነኞቹ እና በመጀመሪያዎቹ ቅጅዎች የፈጣሪን ስም የሚወክሉት አራት የእብራይስጥ ፊደላት (יהוה) ተጽፎ የነበረ ሲሆን አጠራራቸውም ዮድ ሄ ዋው ሄ ነው።  በቀድሞ ዘመን ተነባቢዎች ብቻ የሚጻፉ ሲሆን አናባቢዎችን የሚጨምረው አንባቢው በመሆኑ በዘመናችን የእነዚህን አራት ፊደላት ትክክለኛ አነባበብ በእርግጠኛነት የሚያውቅ የለም።  ሆኖም ወደ ትክክለኛው በእጅጉ የሚቀርቡ ሁለት የአማርኛ አጠራሮች ይገኛሉ።  እነሱም ይሖዋ እና ያህዌህ የሚሉት ሲሆኑ በ1879 የአማርኛ ትርጉም መፅሓፍ ቅዱስ አንድ ጊዜ (ይሆዋ)፣ በ1941 ትርጉም ሁለት ጊዜ (ያህዌ) አንዲሁም በአዲሱ መደበኛ ትርጉም እጅግ በርካታ ቦታ ላይ (ያህዌ) በሚል ተጽፈው ይገኛሉ።

በግዕዝ ፍልስፍና B-H-R (𐩧𐩢𐩨) የሚለው ሥር ብሔር ወይም ባሕር ከመስጠት በላይ ትርጉሙ ማናቸውም ባሕር ዓይነት፣ የዓለም፣ የሀሣብ፣ የድምጽ፣ የጠፈር፣ ወይም የመንፈስ ባሕር ቢሆን፤ ባሕሩ የባሕሩም ክፍሎች ሁሉ ወሰኖች እንዳሉባቸው በቀላል ሊገለጽ የሚችል ነው።  እንግዲህ ወሰኖቹን የሚወስነው አወሳኝ ወይም ገዢው ኃይል «ብሔሩን የሚገዛ» ወይም በግዕዝ «እግዚአብሔር» በመባል ሊታወቅ ይቻላል። ይህ ላይኛ ፈቃድ ፈጣሪው ጸባይ የሰማዩ አባታችን ሲሆን ያለ እርሱ ረድኤት ምንም አለመቻሉን የሚል ግንዛቤ ነው። ስለዚህ የማናቸውም ተቃዋሚ ወይም ጋኔን ፈቃድ ቢኖር በእግዚአብሔር ፈቃድና ትግዕስት ብቻ ነው ስንኳ ለጊዜው ሊቃወሙት የሚቻለው (ኩፋሌ 10:5-7)።




#Article 272: መንፈስ ቅዱስ (366 words)


መንፈስ ቅዱስ በክርስትና እምነት ከሥላሴ አንዱ ሲሆን የእግዚአብሔር መንፈስ ነው።
መንፈስ ቅዱስ መለኮታዊ አእምሮ ያለዉ ማንነት ስሜት እና ፍቃድ ያለዉ እንደሆነ መፃፍ ቅዱስ ይናገራል መንፈስ ቅዱስ ስሜት አለው ያዝናል ኤፍ 4:30 መንፈስ ፈጣሪ ነው.የእግዛቤሬ መንፈስ ፈጠረኝእዮ 33:4

አብዛኛውን ጊዜ “መንፈስ” ተብለው የሚተረጎሙት ሩዋሕ የተባለው የዕብራይስጥ ቃልና ፕነቭማ የተባለው የግሪክኛ ቃል ብዙ ትርጉሞች አሏቸው። ሁሉም የሚያመለክቱት ለሰው ዓይን የማይታይንና በእንቅስቃሴ ላይ የሚገኝን አንድ ኃይል ነው። የዕብራይስጡና የግሪክኛው ቃላት የሚከተሉትን ነገሮች ለማመልከት ያገለግላሉ:- (1) ነፋስን፣ (2) በምድራዊ ፍጥረታት ውስጥ የሚሠራውን አንቀሳቃሽ የሕይወት ኃይል፣ (3) ከአንድ ሰው ምሳሌያዊ ልብ የሚወጣውንና አንዳንድ ነገሮችን በሆነ መንገድ እንዲሠራ ወይም እንዲናገር የሚያደርገውን አስገዳጅ ኃይል፣ (4) ከማይታይ ቦታ የሚመጡ መግለጫዎችን (5) ሕያው የሆኑ መንፈሳዊ አካላትን (6) አንቀሳቃሽ የሆነውን የአምላክ ኃይል ወይም መንፈስ ቅዱስ።

መንፈስ ቅዱስ በመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ መሰረት የራሱ የሆነ ህልውና ያለው እና በተቃራኒው የሌለው በሚመስል መልኩ ቀርቧል። መንፈስ ቅዱስ የራሱ ህልውና ያለው አካል ነው ወይስ አይደለም የሚለው ሃሳብ ክርስቲያኖችን ለዘመናት ሲያጨቃጭቅ እንደነበረ የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ። 

በቀጥዮቹ ጥቅሶች መንፈስ ቅዱስ አጽናኝ (በግሪክኛ ጰራቅሊጦስ፣ “ረዳት”፣ “አጽናኝ”፣ “ጠበቃ” ) ‘የሚያስተምር’፣ ‘የሚመሰክር’፣ ‘የሚናገር’ እና ‘የሚሰማ’ እንደሆነ ተደርጎ ተገልጿል።

በእነዚና በመሳሰሉት ጥቅሶች ላይ በመመስረት መንፈስ ቅዱስ የተወሰነ አካልና የራሱ የሆነ ስብዕና ያለው እንደሆነ አብዛኞቹ የክርስትና እምነት ተከታዮች ያምናሉ። 

የሚከተሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች እንመልከት፦

እነዚህ ጥቅሶች እንደሚያሳዩት መንፈስ ቅዱስ ሰዎች የሚሞሉት ነገር፣ ልክ እንደ ውሃ የሚጠመቁበት፣ ወይም እንደ ዘይት የሚቀቡት እንደሆነ መረዳት ይቻላል።

አዲስ ኪዳን በተጻፈበት የጥንቱ የግሪክ ኮይነ ቋንቋ መሠረት የአንድ ነገር ፆታና ስብዕና ያለውና የሌለው መሆንን የሚያሳዩ የቃላት ክፍሎች አሉ። በዚህ መልኩ የኮይነ ቋንቋ አንድ ነገር ወይ ወንድ፣ ወይም ሴት፣ ወይም ግኡዝ ነገር ብሎ መክፈል ያስችላል። በዚህም መሰረት መንፈስ ቅዱስ እንደ ወንድ የተገለጸባቸውን ብዙ ቦታዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እናገኛለን። ይሁንና በግኡዝ ፆታም የተገለጸባቸው ጥቂት የማይባሉ ጥቅሶች አሉ። (ለምሳሌ ያህል ዮሐንስ 14:17 ላይ τὸ Πνεῦμα ('ቶ ፕኒውማ' ወይም 'መንፈሱ') የተገለጸው በግኡዝ ፆታ ነው።)

ኒው ካቶሊክ ኢንሳይክሎፔድያ እንዲህ ይላል:- “በአዲስ ኪዳን ውስጥ የሚገኙት አብዛኞቹ ጥቅሶች የአምላክን መንፈስ የሚገልጹት የተወሰነ አካል እንደሆነ ሳይሆን ረቂቅ ነገር እንደሆነ አድርገው ነው። መንፈስና የአምላክ ኃይል ተመሳሳይ እንደሆኑ ተደርጎ መገለጹ ይህንን ያስረዳል።” (1967፣ ጥራዝ 13፣ ገጽ 575) 

ያው መጽሐፍ በተጨማሪ እንዲህ ሲል ዘግቧል:- “አፖሎጂስቶች [በሁለተኛው መቶ ዘመን ይኖሩ የነበሩት በግሪክኛ ቋንቋ ይጽፉ የነበሩ ክርስቲያን ጸሐፊዎች] ስለ መንፈስ የተናገሩት በጣም ያዝ እያደረጋቸው፣ ወደፊት የሚሆነውን በመጠበቅ፣ የተወሰነ አካል እንደሌለው አድርገው ነው።”—ጥራዝ 14፣ ገጽ 296

በዚህም ምክንያት በመንፈስ ቅዱስ ምንነትና ማንነት ዙሪያ የክርስትና ኃይማኖቶች ለሁለት እንደተከፈሉ እንመለከታለን።  




#Article 273: ሰይጣን (306 words)


ሠይጣን በመጽሐፍ ቅዱስና በልዩ ልዩ ሃይማኖት ትምህርት እርኩስ መንፈስ የተጠናወተው ክፉ ኃይል ነው። 

በተዋሕዶ ሃይማኖት ዘንድ፣ የሰይጣኖች አለቃ ዲያብሎስ አመጸኛ ሆኖ እስከ ዕለተ ደይን ድረስ ይታስራል። በዕለተ ደይንም በእግዚአብሔር ምሕረት ያልዳኑ ሰዎች ሁሉ ከዲያብሎስ ጋር በገሐነመ እሳት ሊቀጡ ነው የሚል እምነት ነው። በአብያተ ክርስትያናት ውስጥ ባሉት ስዕሎች ላይ የዲያብሎስ ቅርጽ ቢታይ፣ ሁልጊዜ እጅና እግሩን ታሥሮ በእሳትም ሓይቅ ተቀምጦ በስቃዩ ጮኾ ይሆናል። 

ሰይጣን ሌላው ስሙ ዲያብሎስ ነው። ሰይጣን ከመሰይጠኑ በፊት የነበረው ስም ሳጥናኤል ሲሆን በዕብራይስጥ አዛዝኤል ይባላል። አዛዝ ማለት ጥንካሬ ማለት ሲሆን ኤል ማለት አምላክ ማለት ነው፤ አምላክ ጥንካርዬ ነው ማለት ነው። 

በዕብራይስጥ የ«ሰይጣን» ትርጉም «ተቃዋሚ» ሲሆን የእግዚአብሔርን ዕቅዶች የሚቃወም ማናቸውም መንፈስ ሊሆን ይችላል። ስለዚህ በማቴዎስ ወንጌል 16:23 እና ማርቆስ ወንጌል 8:33 ጴጥሮስ ለኢየሱስ ይህ ያልከው ስቅለትህ አይሁን! ሲለው ኢየሱስ ጴጥሮስንም «ሰይጣን» ይለዋል። አዛዜል የተባለው ከሴት (የአዳም ልጅ) ተወላጆች መካከል ያመጸ ሰው እንደ ነበር በአንዳንድ ልማዶች ይታመናል።  ያው ሰይጣን በመጽሐፈ ሄኖክ ዘንድ ፍዳውን አገኝቶታል። ከአዛዜልም በፊት በእባብ ወይም ከአዛዜልም በኋላ ወደፊት ማናቸውም ተቃዋሚ መንፈስ ወይም ሠይጣን እንዲሁም ፍዳውን ያገኛል። በማርቆስ 3:25-26 ኢየሱስ ስለ ሠይጣን እንዳስተማረ «እርስ በርስ የተለያየ ቤት» ሲለው፣ ሰይጣን በራሱ ላይ ተለያይቶ እንደ ሆነ እንጂ ክፉው በአንድ በተዋኸደ ፈቃድ እንደማይመራ ያሳያል።   

በአብርሃማዊ ትምህርቶች ዘንድ ሰው ሁሉ ወይም በኅሊና ወይም በትዕቢት እንደየመጠኑ እንዲመራ ነጻ ፈቃድ የተሰጠ ሲሆን፣ በአንዳንድ ሰዎች እምነቶች ግን አምላኩና ሠይጣኑ በእኩልነት ሃይለኛ ይሆናሉ የሚለው ሀሣብ መጀመርያ በዞራስተር ትምህርቶች እንደ ተገኘ ይባላል።  

በአብርሃማዊ ትምህርቶች ደግሞ አምላኩ እንደ ብርሃን ሲሆን፣ ሰይጣን ግን ጉድጓዶች የማይታዩበት ጥላውን ወይም ሌሊት እንደሚመርጥ ይባላል። በአረመኔ ግሪክ አገር ወይም ሮሜ መንግሥት ባሕል ግን፣ ይህን ገልብጠው ክፉው ብርሃኑን የሚያመጣ ይሆናል ስላሉ፣ የሮማይስጥ ስያሜ «ሉሲፈር» («ብርሃን አምጪ») ተቀበለ።  ይህ ርዕዮተ አለም በመጽሐፍ ቅዱስ ባይደገፍም፣ የሮማይስጥ ትርጉምና ብዙ የአውሮጳ ትርጉሞች በትንቢተ ኢሳይያስ 14:12 በ«የአጥቢያ ኮከብ» ፈንታ «ሉሲፈር» የሚለውን ስያሜ አስገብተዋል። ንባቡ በኦሪጂናሉ ዕብራይስጥ በሙሉ ሲነበብ ግን «የአጥቢያ ኮከብ» የተባለው የባቢሎን ንጉሥ ፪ ናቡከደነጾር እንደ ሆነ ግልጽ ነው። ስለዚህ ከዚሁ ጥቅስ ሰይጣናዊ መረጃ ደርሷል የሚለው ትምህርት ስሕተት ይመስላል፤ ሆኖም በአንዳንድ ሃይማኖት በተለይም በሞርሞኒስም እንደዚያ ይታመናል።   




#Article 274: ዒዛና (530 words)


ዒዛና (በግሪክ ፡ ኤይዛናስ) ፣ (ወደ ፬ኛው ክ/ዘ አጋማሽ ዓ.ም.) ፣ ከአክሱም ነገስታት ሁሉ ገናና የሆነ የመጀመሪያው ክርስትያን ንጉሥ ነበር ። ምናልባት ለአባቱ ለንጉሥ ኢላ-አሚዳ ፡ የበኩር ልጁ ሳይሆን አይቀርም ። ስለ እናቱ ሥም የሚናገር ታዓማኒ የጽሑፍ መረጃ እስካሁን ድረስ አልተገኘም ። ከሁለተኛ ደረጃ ምንጮች መሠረት ግን የእናቱ ሥም ሶፍያ ይባላል ። 

ሁለቱ ወንድሞቹ ሣይዛና እና ኃደፋ በአስተዳደር እና በውትድርና ሥራዎች ይረዱት ነበር ። በተለያዩ ጊዜያት ባደረጋቸው ተከታታይ የግዛት ማስፋፍያ ዘመቻዎች ፡ ንጉሥ ዒዛና ግዛቱን በስሜን ቤጃዎች፣ ካሡና ኖባ በተባሉ የተከዘ ቀበሌዎች ፣ በአትባራ እና በአባይ ወንዞች ፣ በምስራቅ በኩል በአግወዛት ፣ በደቡብ ስራኔ በተባለ የአፋን ምድሮች ላይ ወረራ እንደፈጸመ በግዕዝ ፣ በጥንታዊ ዐረብኛ ፣ እና በግሪክ ተጽፈው በአክሱም የተገኙ የጽሑፍ መረጃዎች ያመለክታሉ ። የግዛት ማስፋፍያ ዘመቻዎቹ ቅደም ተከተል ግን እስካሁን አከራካሪ ናቸው ።

ንጉሥ ዒዛና ከሚጠቀሱለት የአስተዳደር ባሕርያት ውስጥ፤ የተቀናቃኞችን እና የአመፀኞችን ግዛቶች ካስገበረ በኋላ በምሕረትና በበጎ አስተዳደር ሥርዓት መተካቱ ፣ የአመፀኞችን ኃይል ለመስበር የሚያደርጋቸው የርስት ነቀላና የተለዋጭ ሠፈራ እርምጃዎች ተጠቃሽ ናቸው ። የዙፋኑ ሥያሜም ፦ ዒዛና የአክሱም፣ ሒምያር ፣ ራይዳን ፣ ሳባ ፣ ሳልሄን ፣ ሲያሞ ፣ ቤጋ (ቤጃ) እና ካሡ ንጉሥ ነበር ። 

የደቡብ ዓረብያ ግዛቶች ሥም በዙፋኑ ሥያሜ መካተታቸው ከንጉሣዊ ራዕይ ወይም ምኞት የመነጩ እንጂ በእርግጥም በግዛቱ የተጠቃለሉ የባሕር ማዶ አውራጃዎች ናቸው ለማለት የሚያበቃ በቂ መረጃ የለም ። ከወርቅ፣ ከብር እና ከነሓስ በተቀረጹት ገንዘቦቹ ላይ «ዒዛና ዘሐለን ፣ የአክሱሞች ንጉስ» የሚል ጽሑፍ ይነበባል።

በንጉሥ ዒዛና ዘመን ፡ አክሱማውያን በዓለም-ዓቀፍ ንግድ ረገድ እንደ ዝሆን ጥርስ፣ ወርቅ፣ የዔሊ ክዳን ፣ ቆዳ፣ ቅመማ ቅመም ወዘተ ወደ ውጭ ይልኩ እንደነበር፤ እንዲሁም ከወደ ሕንድ የሚመጡ ሽቀጦችን በመጨመር ከግሪኮችና ከሮማዊያን ጋር የአዱሊስ ወደብን በመጠቀም የንግድ ልውውጥ ያካሂዱ እንደነበር፣ በመዲናዋም የውጪ ዜጎችን ጨምሮ፣ ነጋዴዎች እና በልዩ ልዩ የሙያ መስኮች የተስማሩ በርካታ ነዋሪዎች ይኖሩባት እንደነበር መረጃዎች ያመለክታሉ ።

በንጉሥ ዒዛና ዘመን ዋንኛው ተጠቃሽ ክስተት ክርስትናን ከፍሬምናጦስ አምኖ መቀበሉ ነው ። ሆኖም የክርስትና እምነት ወደ ኢትዮጵያ በ 4ኛው ክ/ዘ የመጀመሪያ ዓስርተ ዓመታት ውስጥ ቀደም ብሎ መግባት ጀምሮ ነበር ። በቅድመ ክርስትና ዘመኑ ፡ ንጉሥ ዒዛና አስቴር ፣ መድር ፣ ቤኄር ፣ ሜኅረም ፣ አረስ በተባሉ አማልክት ያምን እንደነበረና እራሱንም የነዚህ አማልክት ልጅ አድርጎ ይቆጥር እንደነበር በጽሑፍ የተገኙ መረጃዎች ያሳያሉ ። በኋለኛ ዘመኖቹ ደግሞ የአሃዳዊ መለኮታዊ አምላክ አማኝ ስለመሆኑ የሚመስክሩ ጽሑፎች ተገኝተዋል ። በ 1969 በተገኘ የመረጃ ሰነድ ላይ ፡ ንጉሥ ዒዛና በግልፅ ክርስትያን ስለመሆኑ ሳያሻማ ይናገራል ። በዘመኑ የተቀረፁት ሳንቲሞቹ ላይ የጨረቃና-ኮከብ የቅድመ ክርስትና ምልክቶች ቀስ በቀስ ፡ የመስቀል ምልክቶች ባላቸው ሳንቲሞች እየተተኩ ሄደዋል ። እንዲሁም የአርያኖች ንጉሥ ቆንስጣንጢኖስ (፫፻፳፱-፫፻፶፫) የላከው «ለተወደዱት ሁለት ወንድሞቼ ዒዛና እና ሳይዛና ፡ የአክሱም ነገስታት» በማለት የሚጀምረው ታሪካዊ ደብዳቤ ስለ ፍሬምናጦስ ጵጵስና እና ዕውቅና ጉዳይ በሚመለከት ግለስቡን ወደ እስክንድርያ ፓትርያርክ አትናቴዎስ ዘንድ እንዲልኩት የሚጠይቀው ይህ ደብዳቤ እንደ ተጨማሪ መረጃ የሚያገለግል ስነድ ነው ። ፍሬምናጦስን ከዚሁ ደብዳቤ መላክ ሃያ አምስት ዓመት ቀደም ብሎ በኢትዮጵያ ጳጳስ አድርጎ ሾሞ የላከው ይኸው ንጉስ አትናቴዎስ ነበር ።

በነገስታት ዝርዝር ላይ የንጉሥ ዒዛና ሥም አለመታወቁ ያስገርማል ። ሆኖም በሳንቲሞቹ ላይ ያለው ሥምይኸው «ዒዛና» የሚለው ነው ያለው ። በዘልማድ እንደሚነገረው ግን ፡ ንጉሥ አብርሃ(አበራ,ብርሃን አመጣ) እና ወንድሙ አጽብሃ(አነጋ,ጨለማን አባረረ) ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ በገባበት ዘመን ኢትዮጵያን የሚገዙ ወንድማማች ንጉሦች ነበሩ ። ምናልባት ክርስትናን በተቀበሉበት ጊዜ የወስዱት የክርስትና ሥማቸው ሊሆን ይችላል ።

ስለ ንጉሥ ዒዛና ዘመነ ንግስ ፍፃሜ ወይም ስለ አሟሟቱ የሚዘረዝር ተጨባጭ መረጃ እስካሁን አልተገኘም ። በአፈ-ታሪክ መረጃዎች መሠረት ግን ንጉሡ በምዕራብ ኢትዮጵያ አካባቢ በተደረገ ጦርነት በጀብድ ወድቆ እንደሞተ እና አስከሬኑም ወደ ምስራቅ ትግሬ መጥቶ እንደተቀበረ ይነገራል ።




#Article 275: አው ባድር (955 words)


ኣው-ባዲር፣ አው-ባድር፣ አባዲር፦ (ዑመር አርሪዳ) (በግምት ወደ ፲፫ ኛው ክ/ዘ)፦ በ ፲፫ ኛው ክ/ዘመን ውስጥ የተፃፈውና  ስለ ሐረር ጥንታዊ አፈታሪካዊ ታሪክ የሚዘክረው 'ፋዝ መዲናት ሐረር' የተባለው ያልታተመ መጽሐፍ እንደሚገልጸው አባድር (ዑመር አርሪዳ) እጅግ ከተከበሩት የሐረር ሼኽዎች ውስጥ አንዱና ዋንኛው ናቸው።  በዚሁ መጽሓፍ አገላለጽ መሠረት፡ አባድር ከሌሎች በርካታ ሼኾች ጋር በመሆን ከሂጃዝ በ፮፻፩፪ ሂጅሪያ (1216 እ.ኤ.አ) ተነስተው ሐረር ከገቡ በኋላ በአካባቢው የጎሣ እና ኃይማኖት መሪዎች ተመርጠው ዒማም ሆኑ። በቀጣዮቹ ዓመታትም፡ ከተከታዮቻቸው ጋር በመሆን የዚህ ዘመን ፖርቱጋላዊያን ወይም ጣልያኖች ይሆናሉ ተብለው በሚገመቱት የአአዋሚ ንጉሥ ካርቢናል ብ. ማኅራዋል፣ በልጁ ጁርኒያል፣ በሴት ልጁ ማርቃኒሽ(ስ) እና በወንድሙ ሣያደር ላይ በርካታ ጦርነቶችን መርተዋል። እነዚህ ጦርነቶች የተካሄዱት በሐረር ዙርያ ባሉ አካባቢዎች ነው።

አባድር በሐረር የአሚሮች ሥም ዝርዝር ውስጥም ሥማቸው ተጠቅሷል። ከዚህ አኳያ ሦስት ዘመናት ከአባድር የግዛት ዘመናት ጋር ተዛምደዋል። እነዚሀም ከ፫፻፩-፬፻፭ ሂጅሪያ (1000-1014  እ.አ.አ)፣ ቀጥሎም ከጥቂት የተቋረጡ የግዛት ዘመናት በኋላ ከ ፬፻፭-፬፻፲፩ ሂጅሪያ፣ እንዲሁም ሥማቸው እስከ አሁን ካልታወቁ ገዢዎች የሥልጣን ዘመናት በኋላ ከ፬፻፶፰-፶፱ ሂጅሪያ ባሉት ጊዘያት ውስጥ አባድር አካባቢዉን መርተዋል። አህመድ አስ-ሣሚ የተባለ ጸሓፊ ጃድዋል አስ-ሣስ ወስ-ሣሚ በተባለው መጽሓፉ የአባድርን የግዛት ዘመን ከ ፫፻፴፫-፫፻፶፫ ሂጅሪያ ያደርገዋል። ይህ ስሌት አሳማኝነቱ ያጠራጥራል፤ ምክንያቱም በአው-ባድር የዘር ሐረግ መሠረት፡ ከመጀመሪያው ከሊፋ ኣቡበከር አስ-ስዲቅ (ረዲ አላሁ አንሁ) እስከ አው-ባድር ዘመን ድረስ፡ የሓያ አምስት ትውልድ ልዩነት ሲስላ ፊት ከተጠቀስው ቁጥር ጋር ስለማይሄድ ነው። ከተገለጹት ዘመናት ውስጥ የፋዝ ዘገባ ከአሚሮች ሥም ዝርዝርና የግዛት ዘመናት እና ከአስ-ሣድ የአውባድር ዘመን ቆጠራዎች በተሻለ ከአው-ባድር የዘር ሐረግ ቆጠራ ስሌት ጋር ይቀራረባል።

በተለይም በሐረር፡  እስከዚህ ዘመን ድረስ አው-ባድርን የሚያወድሱ፣ የሚዘክሩ በርካታ ዝክሪዎች በየቀኑ ይዘከራሉ። በጥንታዊቷ የሐረር ከተማ ውስጥ፡ የሚገኘውና በአካባቢው ሕዝቦች የሚዘየረው የአው-ባድር የቀብር ሥፍራና ቤት-መስጊድ፡ እንዲሁም ቤት-አሩስ አው-ባድር፦ አው-ባድር የሐረሪ ሤት ያገቡበት ተብሎ የሚታመነው ቤት ሥፍራዎች ለአብነት ይጠቀሳሉ።  የአው-ባድር ዝናና መልካም ምግባራት ከሐረር ውጪ ባሉት የኢትዮጵያና አካባቢዋ ባሉ ሙስሊሞች ጭምር በጣም ይከበራሉ፣ ይዘከራሉ።

ከአው-ባድር (ዑመር አር-ሪዳ) ሌላ ተመሳሳይ ሥም ያላቸው ዑለማዎች በሐረር አቅራቢያ በተለያዩ ዘመናት ኖረዋል። እነኝህም ታላላቅ ዑለማዎች አባድር ሳይህ ዑስማን፣ አባድር ባያዚድ፣ እና ባዴ አባድር ናቸው። 

እኛ እርስበእርስ ስንናከስ ወይናደጋማዋ ሐረር እርስ በእርሱ ከሚበላላው ጅብ ጋር ሳይቀር ተግባብቶ የሚኖርባት ከተማ ናት፡፡
   ሐረር ከአዲስ አበባ ደቡብ ምስራቅ በአምስት መቶ ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ የምስራቅ ኢትዮጵያ ከተማ ናት። በዘመኑ የአስተዳደር መዋቅር የሃረሪ ክልል ዋና ከተማ ናት። በ1,885 ሜትር ከፍታ ላይ፣ የወይና ደጋ የአይር ጠባይ በተላበሰ ቦታ ላይ አርፋለች።  በ1987 ዓመተ ምህረቱ የህዝብ ቆጠራ መሰረት ሐረር 76,378 ሕዝብ ይኖርባታል።
ሐረር ለዘመናት ከፍተኛ የንግድ ማዕከል ሆና ስትኖር ከመሃል አገር፣ ከአፍሪካ ቀንድ እና ከአረብ አገራት ጋር በንግድ መንገዶች ስትገናኝ ከቀሪው አለም ጋር ደግሞ በቀይ ባህር ወደቦች አማካኝነት ትገናኝ ነበር።
የሐረር ጀጎል ግንብ ከ1998 ጀምሮ በዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ዝርዝር ውስጥ ይገኛል። በእስልምና ሃይማኖት 4ኛዋ የተቀደሰች ቦታ ተብላም ስትታወቅ 82 መስጊዶች፤ አንዳንዶቹ ከ10ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የነበሩ፤ እንዲሁም 102 የቀብር ቦታዎች አሉዋት
  ኣው-ባዲር፣ አው-ባድር፣ አባዲር፦ (ዑመር አርሪዳ) (በግምት ወደ ፲፫ ኛው ክ/ዘ)፦ በ ፲፫ ኛው ክ/ዘመን ውስጥ የተፃፈውና ስለ ሐረር ጥንታዊ አፈታሪካዊ ታሪክ የሚዘክረው 'ፋዝ መዲናት ሐረር' የተባለው ያልታተመ መጽሐፍ እንደሚገልጸው አባድር (ዑመር አርሪዳ) እጅግ ከተከበሩት የሐረር ሼኽዎች ውስጥ አንዱና ዋንኛው ናቸው። በዚሁ መጽሓፍ አገላለጽ መሠረት፡ አባድር ከሌሎች በርካታ ሼኾች ጋር በመሆን ከሂጃዝ በ፮፻፩፪ ሂጅሪያ (1216 እ.ኤ.አ) ተነስተው ሐረር ከገቡ በኋላ በአካባቢው የጎሣ እና ኃይማኖት መሪዎች ተመርጠው ዒማም ሆኑ። 
 የሀረር ህዝብ ታሪክ ፣ ባህል እና ማንነት ከሀረር ከተማ ጋር በእጅጉ የተቆራኘ ነው፡፡ ሀረሪዎች በረዥም ዘመን የስልጣኔ ታሪካቸው ያፈሯቸው ተንቀሳቃሽ እና የማይንቀሳቀሱ እንዲሁም የሚዳሰሱ እና የማይዳሰሱ በርካታ ቁሳዊ እና መንፈሳዊ ቅርሶች ባለቤት ናቸው፡፡ ከእነዚህ ቅርሶች መካከልም የከተማዋ ልዩ መለያ ምልክት ከመሆንም አልፎ እ.ኤ.አ በ2006 በአለም ቅርስነት የተመዘገበው የጀጎል ግንብ በቀዳሚነት ይጠቀሳል፡፡በግንቡ ውስጥም ከ82 በላይ መስኪዶች እና በርከት ያሉ የሀረሪ ባህላዊ ቤቶች ይገኛሉ፡፡
ሀረር ከፍተኛ የስልጣኔ እድገት ደረጃ ላይ በደረሰችበት በ16ኛው ክፍለ ዘመንም በምስራቅ አፍሪካ የእስልምና ሀይማኖት ትምህርት እና የንግድ ማዕከል ሆናም አገልግላለች፡፡ ይህም የበርካታ ታሪካዊ እና ባህላዊ ቅርሶች ባለቤት እንድትሆን አድርጓታል፡፡ የጀጎል ግንብ የሀረሪ ህዝብ የኪነ ህንፃ ችሎታውን የሚያስመሰክር የታሪክ እና የጥበብ መዘክር ነው፡፡ ይህ ግንብ በ16ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ በአሚር ኑርአማካኝነት እንደተገነባም ይነገራል፡፡ሐረር እንኳን ዛሬ ቀን ዘምኖ ትናንትናም ቢሆን ስንቱ ባህር አቋርጦ የከተመባት፤ ስንቱ ቅጥሯ ገብቶ ለትውልድ የተረፈ ትዝታ ያስቀመጠባት የውበትና የጥበብ መዲና ናት፡፡ የኢትዮጵያ ኢስላማዊ ኪነ ህንጻና ባህል ማንምም ሳይመስል፤ ሃይማኖታዊ መሰረቱን ሳይጥል የነገሰባት መዲና፤ ያው ጀጉልን መዞር ነው፡፡ 
በየቦታው መቆም፡፡ በየቦታው ማየት….በየቦታው መደምም…ጀጉልን ገብተው ይኖሯታል እንጂ አይጽፏትም፡፡  
 ጀጉልን ውስጥ ለውስጥ ከጀመርናት መቆሚያ የለውምና ከጊዜ እየተሻማን በበራፍ በበራፍ እንለፍ
ሀረር ከቅርስነት ባሻገር እ.ኤ.አ በ2003/4 በሰላም ፣ በመቻቻል ፣ በመፈቃቀር እና በልማት ከተማነት አለም አቀፍ ሽልማት እና እውቅናን አግኝታለች፡፡ ይህም የተለያየ እምነት ፣ ባህል እና ቋንቋ ያላቸው ህዝቦች ለዘመናት በሰላም እና በፍቅር የኖሩባት እና ዛሬም የሚኖሩባት ከተማ በመሆኗ የተቀዳጀችው ክብር እና እውቅና ነው፡፡
ሀረር ዩኔስኮ ዕውቅናን የቸራት በዓለም ቅርስ ብቻ አይደለም፡፡ ከኪነ ህንጻዎቿ ልቀት ባለፈ ህያው ሆኖ ዛሬም እየኖረ ባለው ሰዋዊ እሴት ምርጥ ነሽ ብሏታል፡፡ ፈረስ መጋላ ይሉታል ሀረሮች  ከፊት ለፊቱ የአሚር አብዱላሂ አደራሽ አለ፡፡ ሀረር መድኃኒዓለም በር ላይ፡፡ ጀጉል በሀገራችን በርካታ መስጂዶች የሚገኙባት ከተማ ናት፡፡ 
በግንብ የተከበበው ቅጥሯ ውስጥ የሚገኘው የመድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን ከተማዋ ዩኔስኮ የተባለውን ዓለም አቀፋዊ ትኩረት ስባ የመቻቻልና የሰላም ተምሳሌት የተባለ እውቅና እንድትቀበል አድርጓታል፡፡ በረዣዥም የመስጂድ ሚናራዎች የታጀበው የሀረር መድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን በ27 በድምቀት ይነግሳል፡፡ የጀጉል መንገዶች ከጁምአ ዕለት ድምቀት በተጨማሪ በተለየ 27 ነጠላ ለባሾች ከየአሉበት ወደ ቅጥሯ የሚገቡበት ሌላ ትዕይንት ያስተናግዳሉ፡፡ 
ምዕተ ዓመት የተሻገረው ይህ ቤተ ክርስቲያን ንጉሰ ነገስቱ አጼ ምኒሊክ ኢትዮጵያን በሚመሩበት ራስ መኮንን የሀረርጌ ገዢ በነበሩበት ዘመን የታነጸ ነው፡፡ ያሰሩት ራስ መኮንን ናቸው፡፡ ክቧ ቤተክርስቲያን ውብ ናት፡፡ ዛፎቿ ጥቂት ናቸው ነገር ግን ከግቢዋ ስፋት አኳያ ጥሩ አድርገው አጅበዋታል፡፡ 
ዛሬ ከሁሉም አቅጣጫ ሰው ወደ ጀጉል እያመራ ነው፡፡ ሐረር ወይም ዱክ በር ከሚባለው በሗላ በተሽከርካሪ ማለፍ አይቻልም፡፡ ይሄ አጋጣሚ ሌላ ትዕይንት ፈጥሯል፡፡ ነጠላ ያጣፉ ጧፍ የያዙናና ሂጃብ የለበሱ መንገደኞች በጋራ እየተሳሳቁ መንገዱን ሞልተውታል፡፡ እጣንና ጧፍ የዘረጉ ነዋየ ቅድሳት የሚሸጡ መንገዱን ዳርና ዳር ይዘውታል፡፡ የኔ ቢጤዎች ስለ መድሐኒያለም እያሉ ይለምናሉ፡፡ 
መላው የሐረር ህዝብ አቦ እንወድሃለን! ሀገርን ለማጥፋት ለመበታተን ቀን ከሌት የሚተጋ መንግስት መሳይ ጊዜ አንግሶት እየገዛን ቢሆንም አንተም እንደኛው በቁምም በስጋም እየሞትክ ቢሆንም አብሽሩ እኛ አንድ ሆነን ሽ የሆንን ኢትዮጵያውያንነን! 
የመጣብንን ሰይጣናዊ የጥፋት ውሃ ከአምላክ ጋር አንድ ከሆን እናከሽፈዋለን!!!  ኢትዮጵያ ማለት መንፈስ ነው፣ እሱም አንድነት ማለት ነው፡፡ ኢትዮጵያ የፍቅር ሀገር የመቻቻል ምድር ለዘላለም ትንሩልን!!!!

ኢ. ዋግነር፣ ዘ ዲክሽነሪ ኦፍ ኢትዮጵያን ባዮግራፊ፣ ገጽ 1፣ ቮልዩም 1፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የኢትዮጵያ ጥናት ኢንስቲትዩት፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ።




#Article 276: ኩላሊት (105 words)


ኩላሊት በሰዎችና በብዙ እንስሶች ውስጥ ሽንት የሚሠሩት አካላት ናቸው። 

የቃሉ «ኩላሊት» መነሻ ከግዕዝ «ኲሊት» እና በተለይ ከዚሁ ግዕዝ ቃል ብዙ ቁጥር («ኲሊያት») ነበር። 

ከ4 መቶ ዓመታት በፊት፣ ኩላሊት የኅሊና መቀመጫ መሆኑ በአውሮፓ በሰፊ ይታመን ነበር። ይህም የተነሣ ከዕብራይስጥ መጽሐፍ ቅዱስ (መዝሙር 7:9) እንዲሁም በከአዲስ ኪዳን (የዮሐንስ ራዕይ 2:23) መሠረት ነው። የዛሬ ሕክምና ሊቃውንት ግን ኩላሊት እንዲህ አይነት ሥነ ልቡናዊ ሚና እንዳለው አይቆጠሩም።
የሚያስደንቀው ግን አድሬናል ሆርሞን (ኩላዕጢ እድገንጥር) ወይም ግላንድ (ኩላትጌ ዕጢ) የሚገኘው በኩላሊት በላይኛው ክፍል ነው!!! 
ታላቅ ደስታ ወይም ድንጋጤ ሲገጥመን ሰውነታችንን መቆጣጠር እስኪያቅተው ድረስ ለዐይምሮዋችን መልክት የሚያስተላልፍ ክፍል ነው ። ብቻ ከፍተኛ ግንኙንት ከዐይምሮዋችን ጋር አለው ፤ ለምሳሌ የፋይት ኦር ፍላይት ስሜታችንን ይቆጣጠራል።




#Article 277: ዶሮ (241 words)


ዶሮ መብረር የማትችል የአእዋፍ ዘር ናት። የሰው ልጅ ካለመዳቸው እንስሳት አንዷ ዶሮ ስትሆን የሰው ልጅ ሥጋዋንና ዕንቁላሏን በመብላት ይጠቀማል።
ዶሮ ተወዳጅና በብዛት የሚገኝ

በአጠቃላይ ከ13 ቢልዮን የሚበልጡ ዶሮዎች እንዳሉ ይገመታል! እንዲሁም ሥጋው በጣም ተወዳጅ በመሆኑ በየዓመቱ ከ33 ቢልዮን ኪሎ ግራም በላይ ለምግብነት ይውላል። ከዚህም በተጨማሪ ዶሮዎች በዓለም ዙሪያ በአንድ ዓመት ውስጥ 600 ቢልዮን ገደማ እንቁላሎችን ይጥላሉ።  ዶሮ በምዕራባውያን አገሮች በብዛት የሚገኝ ሲሆን ዋጋውም ርካሽ ነው።

ዶሮ የእስያ ቀይ የዱር ጅግራ ዝርያ ነው። ሰው ዶሮን በቀላሉ ማልመድ እንደሚችል ለመረዳት ጊዜ አልፈጀበትም። ዶሮና እንቁላል ለገበያ ለማቅረብ ሲባል በሰፊው የዶሮ እርባታ የተጀመረው ከ19ኛው መቶ ዘመን በኋላ ነው።
የዶሮ ሥጋ ዛሬ በብዙዎች ዘንድ በጣም ተወዳጅ ምግብ ነው። የከተማ ነዋሪዎችን ጨምሮ በሚልዮን የሚቆጠሩ ቤተሰቦች ለራሳቸውም ሆነ ለገበያ ለማቅረብ ዶሮ ያረባሉ።  ብዙ አገሮች ለራሳቸው አገር የአየር ጠባይ የሚስማሙና ጥሩ ምርት የሚሰጡ የዶሮ ዝርያዎችን አራብተዋል። ከእነዚህ መካከል የአውስትራሊያው አውስትራሎፕ፣ መጀመሪያ በሜድትራኒያን የተገኘውና አሁን በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በብዛት ያለው ሌግሆርን፣ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የሚረቡት ኒው ሃምፕሻየር፣ ፕላይማውዝ ሮክ፣ ሮሜ አይላንድ ሬድ እንዲሁም ውያንዶቴ፤ የእንግሊዞቹ ኮርኒሽ፣ ኦርፒንግቶን እና ሱሴክስ የሚባሉት ጥቂቶቹ ናቸው።
በእርባታ ረገድ የተገኘው የተሻሻለ ሳይንሳዊ ዘዴ ዶሮ እርባታ ስኬታማ የግብርና ኢንዱስትሪ እንዲሆን አስችሎታል። የዩናይትድ ስቴትስ ገበሬዎች የዶሮ በሽታን በሳይንሳዊ መንገድ ከመቆጣጠራቸው በተጨማሪ አመጋገባቸውንና አሰፋፈራቸውን በተመለከተ ጥንቃቄ በተሞላበት ዘዴ ክትትል ያደርጋሉ። አንዳንድ ሰዎች እንዲህ ያለውን በገፍ የማርባት ዘዴ እንደ ጭካኔ ይቆጥሩታል። ይሁን እንጂ ይህ አመለካከት ገበሬዎቹ በየጊዜው ይበልጥ ውጤታማ የሆኑ የዶሮ ማራቢያ ዘዴዎችን ከመፈለግ አላገዳቸውም። ዘመናዊው ዘዴ አንድ ሰው ብቻውን ከ25, 000 እስከ 50, 000 የሚያክሉ ዶሮዎችን እንዲያረባ ያስችላል። አንድን ዶሮ ለገበያ ለማድረስ የሚወስደው ጊዜ ሦስት ወር ብቻ ነው። 




#Article 278: ታላቅ የአናባቢ መፈራረቅ (114 words)


ታላቅ የአናባቢ መፈራረቅ በ15ኛው ክፍለ ዘመን አካባቢ በእንግሊዝኛ አጠራር ላይ የደረሰ የድምጽ ለውጥ ነበር።

በዚህ ለውጥ ሳቢያ የእንግሊዝኛ ረጅም አናባቢዎች አጠራር ከሌሎች ልሳናት (እንደ እጣልኛ፣ ፈረንሳይኛ ወዘተ) እጅግ ይለያል።

ስለዚህ፦

ከዚህ ዋና ለውጦች ጭምር አንዳንድ ሌሎች ትንንሽ የድምጽ ለውጦች ደረሱ። እንዲሁም ዘመናዊ እንግሊዝኛ more /ሞር/ («ተጨማሪ») ከ6 መቶ አመታት በፊት māra /ማረ/ እንደ ነበር እርግጥኛ ነው።

ከለውጡ በፊት የላቲን ፊደል ዋና ዋና አናባቢዎች (a, e, i, o, u) እንደ ላቲን፣ እንደ ጣልኛ፣ እንደ ሌሎቹም ልሳናት «ኣ፣ ኤ፣ ኢ፣ ኦ፣ ኡ» ይሰሙ ነበር።  ከለውጡ በኋላ እነኚህ ድምጾች ረጅም ሲሆኑ ወደ «ኤ፣ ኢ፣ አይ፣ ኡ (oo)፣ አው (ou)» ተሻገሩ። ለውጡ የደረሰበት ምክንያት በ1400-1500 ዓ.ም. ግድም በእንግሊዝ የተነሣው ትውልድ ከወላጆቻቸው አነጋገር ለመለየት አዲስ ቄንጥ ስለ ፈለጉ ነው።  




#Article 279: የሺጥላ ኮከብ (116 words)


ኢትዮጵያዊው ደራሲ፤ ጋዜጠኛ አና መምሀር የሺጥላ ኮከብ መስከረም 21 ቀን 1958 በሃረርጌ ክፍለ ሃገር ተወልዶ የአንደኛ አና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በባቢሌ፤ ወተር አና ሃረር እንዲሁም የከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርቱን ደግሞ በሆሳእና ልጅ አበበ ወ/ ሰማያት ት/ቤት ተከታትሏ። ቀጥሎም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በባዮሎጂ በቢ ኤስ ሲ ዲግሪ ተመርቆ በኢሉባቦር ክፍለሃገር ሞቻ አዉራጃ እና መቱ ፤ እንዲሁም በአዲስ አበባ የከፍተኛ 12 እና በቀድሞው ተፈሪ መኮንን (እንጦጦ አጠቃላይ ) በመምሀረነት አገልገሏል።  የሺጥላ ኮከብ ዶሰኛው እና ወገግታ የተሰኙ ከፍተኛ ተነባቢነት ያላቸዉ ልቦለዶቹን ገና በወጣትነት እድሜው ያበረከተ ሲሆን በጋዜጠኛነት ህይወቱም በየካቲት መጽሄት ዋና አዘጋጅነት፤ በአዲስ ዘመን እና የ ኢትዮጵያ ሄራልድ አዘጋጅነት አገልግሏ። በተለይ ለየት ያሉ የመጣጥፍ (ኤሴይ) አቀራረቦቹ ተንኳሽ (ፕሮቮካቲቭ) እና አነጋጋሪ በመሆናቸው ይታወቃሉ። በአሁኑ ጊዜ ነዋሪነቱ በጀርመን ሃገር ነው።




#Article 280: ፋሲካ (126 words)


ፋሲካ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን መካከል የተነሳበትን የትንሳዔ ቀን ማሰብያ ዕለት ነው።

ስሙ ፋሲካ የመጣው ከአረማይክ /ፓስኻ/፣ ግሪክኛ /ፓስቃ/፣ ዕብራይስጥ /ፐሳኽ/ ሲሆን፤ የአይሁድ ፋሲካ በዓል ዕብራውያን በሙሴ መሪነት ከግብፅ ፈርዖን ግዛት በተዓምራትና በመቅሠፍቶች የወጡበትን ጊዜ ለማክበር ነበር። ይህ ታሪክ በተለይ በብሉይ ኪዳን ኦሪት ዘጸአት ይገለጻል። በተለይ በዘጸአት 12፡23 በአሥረኛው መቅሠፍት ጊዜ እግዚአብሔር ያልፋል ሲል፥ ያልፋል የሚለው ግሥ በዕብራይስጡ /ፐሳኽ/ ስለ ሆነ፣ ስሙ ፋሲካ ከዚያው ቃል ደረሰ።

በአዲስ ኪዳን ዘንድ ደግሞ ኢየሱስ ለፋሲካ በዓል አዲስ ትርጉም ሰጠው። በመጨረሻው እራት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር የበዓሉን ዝግጅት ሲጠብቅ ሥጋ ወደሙ እንደ መስዋዕቱ ሆኖ ባካፈለው ኅብስትና ወይን በኩል እንደሚገኝ አመለከተ። ኢየሱስም ተሰቅሎ ከ፫ ቀን በኋላ በእግዚአብሔር ኃይል ተነስቶ ዳግመኛ ለደቀመዛሙርቱ ታይቶ፣ በነዚህ ዘመኖች ፍፃሜ ለፍርድ ቀን በሕያዋንና በሙታን ለመፍረድ እንደሚመለስ ነገራቸው። ይህ ሁሉ አሁን በክርስትና ወይም በአብያተ ክርስቲያናት በፋሲካ በዓል የሚከበር ነው።




#Article 281: ፊልጶስ አረባዊ (194 words)


ፊልጶስ አረባዊ ከ236 እስከ 241 ዓ.ም. ድረስ የሮማ መንግሥት ንጉሠ ነገስት ነበረ።

በሮሜ ንጉሥ አሌክሳንድር ሴቬሩስ ዘመን ፊልጶስ የፕራይቶርያን ጠባቂዎች (የንጉሡ ልዩ ዘበኞች ክፍል) አባል ሆነ። በኋለኛውም ንጉሥ በ3ኛ ጎርዲያኖስ ዘመን በ235 ዓ.ም. ፊልጶስ የዘበኞች አለቃ ሆነ። ይኸው ንጉሥ ግን ልጅ ስለ ሆነ፣ ፊልጶስ እንደራሴ የሚመስል ሚና አጫወተ። ከዚህ ትንሽ በኋላ ጎርድያኖስ ሞተና ፊልጶስ በዚያን ጊዜ ንጉሥ ሆነ። በዚያው ጊዜ የሮማ ነገሥታት ሁሉ የተነሡ በሠራዊት ፈቃድነት ነበርና። 

ንጉሥ ፊልጶስ ሰላም ከፋርስ መንግሥት ጋር ካዋጀ በኋላ በጀርመናዊ ጎሣዎች ላይ ዘመቻ አደረገ። በየጊዜው ሠራዊቶቹ ጣውንት ንጉሥ በማቆም ያምጹ ነበር፤ ነገር ግን ሳይከናውኑ ቆይተዋል። በ240 ዓ.ም. የሮሜ ሺህኛው አመት በዓል አፈጸመ። ለዚህ በዓል አንድ ሺህ የጨዋታ ወታደሮች (gladiator) እና ብዙ እንስሶች መስዋዕት ሆኑ። በሚከተለው አመት ግን አንዱ ሠራዊት አለቃቸውን ዴቅዮስ ንጉሥ ሆኖ ስላቆሙት፣ ፊልጶስ ከነሱ ጋር ለመታገል ሂዶ ተገደለና ዴቅዮስ የዛኔ ንጉሥ ሆነ።

በኋለኛው ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊው አውሳብዮስ ዘንድ፣ ንጉሥ ፊልጶስ አንድ ጊዜ ፋሲካ በዓል ለማስታወስ ወደ አንድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገባ። ሳይገባም ጳጳሱ ንስሐ እንዲገባ አደረጉት ተባለ። ከዚህ በላይ በየወቅቱ በክርስትያኖች ላይ የተካሄዱት እልቂቶች በፊልጶስ ዘመን የተቋረጡ ይመስላል። ስለዚህ ይህ ንጉሥ ምናልባት የሮማ የመጀመርያው ክርስቲያን ንጉሥ ባይሆንም እንኳን የክርስትና ተቆርቋሪ ሊባል ይቻላል ባዮች አሉ። ሆኖም በዘመኑ በወጡ መሐለቆች መሠረት እምነቱን ከሮማ አረመኔ ሃይማኖት መቸም የቀየረ አይመስልም።




#Article 282: ፉጥ (259 words)


ፉጥ (ደግሞ ፉድ በኩፋሌ፤ ዕብራይስጥ፦  פוט /ፉጥ/ ግሪክ፦ Φουδ /ፉድ/) በኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 10 መሠረት የካም ልጅ ነው። 

የጥንት ሊቃውንት «ፉጥ» ጥንታዊ ሊብያውያን («ለቡ» እና «ፒቱ») እንደ ነበሩ በማለት ይስማማሉ። እነዚህ ነገዶች የግብጽ ጎረቤቶች በስተ ምዕራብ ተገኙ። ዮሴፉስ እንደ ጻፈው፦ «ፉጥ ደግሞ የሊቢያ መስራች ነበረ፣ ከራሱም ኗሪዎቹን፦ «ፉጣውያን» አላቸው፤ ደግሞ በሞሮች አገር በዚያው ስም የሚሰየም ወንዝ አለ፤ ስለዚህ ነው አብዛኞቹ ግሪክ የታሪክ ጸሐፍት ያንን ወንዝና ዙሪያውን «ፉጥ» በሚል ስያሜ የሚጠቅሱት፤ ነገር ግን አሁን ያለው ስም በለውጥ ከምጽራይም ልጅ ከሊብዮስ ተሰጠው።» ይህም 'ፉጥ ወንዝ' በፕሊኒና በፕቶሎሜዎስ መጻሕፍት ዘንድ በዛሬው ሞሮኮ ይገኝ ነበር። ፕቶሎሜዎስ ደግሞ «ፑቴያ» የተባለች ከተማ በልብያ እንዳለች ይጠቅሳል። 

በብሉይ ኪዳን ትንቢተ ናሆም 3፡9 እንዲሁም «ፉጥና ሉቢም» (ልብያ) የግብጽ ረዳቶች ይባላሉ። በሌሎች መጻሕፍት ደግሞ የፉጥ ልጆች ጦረኞች ይላቸውዋል። በትንቢተ ኤርምያስ 46፡9 እንደገና የግብጽ ረዳቶች ይላቸዋል። ትንቢተ ሕዝቅኤል ሦስት ጊዜ ይጠቅሳቸዋል፦ በ27፡10 የጢሮስ (ፊንቄ) ረዳቶች፣ በ30፡5 የግብጽ ረዳቶች፣ በ38፡5 የጎግ ረዳቶች ናቸው። በዕብራይስጥ «ፉጥ» ሲለው በሕዝቅኤል ግሪኩ ትርጉም (ከ300 ዓክልበ.) «ሊቡዌስ» ይላል። በትንቢተ እሳይያስ 66፡19 ሩቅ አገር ይባላል። 

የፋርስ ታሪክ ጸሐፊ ሙሐመድ እብን ጃሪር አል-ታባሪ (907 ዓ.ም. ገደማ) በጻፈው ልማድ ዘንድ፣ የፉጥ ሚሥት ስም ባኅት ሲሆን እስዋ የቲራስ ልጅ የባታዊል ልጅ ነበረችና 'ቅብጦቹን' ወለደችለት።  

የጥንታዊ ግብጽ መንግሥት ሰነዶች ወደ ፑንት ሀገር ስለተደረጉት ጉዞዎች ሲጽፉ፣ ይህ ቦታ ግን ሊብያ ሳይሆን በቀይ ባሕር ዳር እንደ ተገኘ ይመስላል። ሆኖም በአንዳንድ ዘመናዊ አስተሳሰብ ዘንድ ፑንት ከፉጥ ጋር ግንኙነት እንዳለው ይታስባል።

ፒዱ ወይም ፒቱ የተባለ የልብያ ነገድ በምሥር መዝገቦች በ900 ዓክልበ. ይታያል። በኋላ በቅብጥኛ ቋንቋ ልብያ «ፋያጥ» ይባል ነበር። 

የናቡከደነጾር ዜና መዋዕል በ575 ዓክልበ. በግብጽ ባደረገው ዘመቻ በ«ፑቱ ያዋን» (ኩሬኔ) ሠራዊት ላይ እንዳሸነፈ ይጠቅሳል። በዳርዮስ ዘመን፣ «ፑቲያ» (በፋርስኛ) ወይም «ፑጣ» (በአካድኛ) የተባለ ክፍላገር በሊብያ ነበረ።




#Article 283: ሉድ (131 words)


ሉድ (ዕብራይስጥ፦ לוּד) በኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 10 መሠረት የሴም ልጅ የኖህም ልጅ ልጅ ነበረ። ይህ ሉድ (የሴም ልጅ) እና ምጽራይም የወለደው ሉዲም ግን ሁለት የተለያዩ ዘሮች ሆነው ይቆጥራል።  

የሉድ ተወላጆች በዮሴፉስና በሌሎች ጸሐፍት ዘንድ የትንሹ እስያ ሀገር ልድያ (አካድኛ፦ ሉዱ) ሆኑ። ከልድያም አስቀድሞ በዚያ ዙሪያ ሉዊያ የተባለ አገር ነበር። በመጽሐፈ ኩፋሌ ድግሞ የሉድ ርስት 'የሉድ ተራሮች' (ከአራራት ወደ ምዕራብ፣ በትንሹ እስያ) ናቸው። ከዚህ በላይ የግሪክ ታሪክ ጸሐፊ ሄሮዶቶስ እንዳለ፣ ልድያ ከንጉሳቸው ከሉዶስ (Λυδός) ተሰየመች።  የአቡሊድስ ዜና መዋዕል (226 ዓ.ም. ገደማ) የሉድ ልጆች 'ላዞኔስ' ወይም 'አላዞኒ' (ሓሊዞናውያን) ሲለን፣ ስትራቦን ሐሊዞናውያን በሐሊስ ወንዝ ላይ ኖሩ በማለት አገኛቸው። ሆኖም በአቡሊድስ ዘንድ፣ «ልድያ» የተባለች አገር ከሉዲም ምጽራይም ወጣች።  

የእስላም ታሪክ ጸሃፊ ሙሐመድ እብን ጃሪር አል-ታባሪ 907 ዓ.ም. ገደማ በጻፈው ታሪክ የሉድ ሚስት የያፌት ልጅ ሻክባህ ስትሆን የፋርስና የጅዮርጅያ ዘሮች እንዲሁም ሌሎች የምሥራቅ ሕዝቦች ወለደችለት ይላል።




#Article 284: የአካዳውያን ታላቅ መፈንቀል (124 words)


የአካዳውያን ታላቅ መፈንቀል ከ1747 እስከ 1755 ዓ.ም. ድረስ የእንግሊዝ መንግሥት በአካዲያ ፈረንሳዊ ሕዝብ ላይ ብግድ የጣለው ስደት ነበር። 

ፈረንሳውያን ከ1596 ዓ.ም. ጀምሮ «አካዲ» (አካዲያ ወይም የዛሬው ኖቫ ስኮሺያ፣ ካናዳ) በተባለ አውራጃ ከኗሪ ሚግማቅ ሕዝብ ጋራ አንድላይ ይኖሩ ነበር። አገሩ ለረጅም ዘመናት የሚግማቅ መኖሪያ ምንም ቢሆንም በ1705 ዓ.ም. የፈረንሳይ ንጉሥ በአንድ የአውሮፓ ጦርነት ድል ሆኖ በኢውትረኽት ውል ስምምነት ሥር ቅኝ አገሩን (አካዲያ) ለእንግሊዝ ሀብት ሰጠ። ከዚህ ጀምሮ የእንግሊዝ መንግሥት በዙሪያው የኖሩት ሕዝቦች እንደ ገዛው ተገዦች ቆጠራቸው። በ1746 ዓ.ም. ግን እንግሊዝ እና ፈረንሳይ ወደ ጦርነት ስለ ተመለሡ፣ እንግሊዝ ከነዚህ ተገዦች የተነሣ ስለ ታማኝነታቸው ብዙ ስለ ፈራ፣ ሚግማቆቹን እየገደላቸው ከ14,000 በላይ ፈረንሳያውያንን (አካዲያውያንን) ከቤቶቻቸው ወደ ሌላ ቅኝ አገሮቹ በግፍ አሳደዳቸው። ከነዚህ ብዙዎች በሉዊዚያና ቅኝ አገር ፈልሰው እስከ ዛሬ ድረስ ካጀን («አካድየን» ወይም አካዲያዉያን) የሚባል ሕዝብ በሉዊዚያና ይገኛል። 




#Article 285: ኢሳያስ አፈወርቂ (387 words)


ኢሳይስ አፈወርቂ ኣብረሃም እስካሁን ድረስ የኤርትራ ፕሬዚዳንት ናቸው። ኢሳያስ አፈወርቅ ለረጅም አመታት ለኤርትራ ነፃነት የታገሉ መሪ ናቸው። አሁን በስልጣን ዘመናቸው አገሪቱን ለማልማት በጥቂት ደሞዝ ያገለግሉ ይገኛሉ።
የኢሳያስ አፈወርቂ አባት አቶ አፈወርቂ አባት አቶ አፈወርቅ አብርሃ ይባላሉ፤ እናቱ ወይዘሮ አዳነች በርሄ ይባላሉ።

ልጆቻቸውም፦

 

በናታቸው በኩል የኢሳያስ አጎቶች፦

የአቶ ኢሳያስ አጎት ደጃዝማች ሰለሞን አብራሃ (በጊዜው ሲጠርዋቸው በነበሩ ጋዜጦች አጠራር «ሰለሞን አብሃም») በዓጼ ሃይለ ስላሴ ዘመነ መንግሥት ማለት (በ1946 ዓ.ም.) የወሎ እንደራሴ ሆነው ያገለገሉ ናቸው። በዚያ ጊዜ መቀሌ ከተማ ውስጥ ተደራጅቶ የነበረው የባህል ቡድን አስመራን ከጎበኘ በሗላ ወደ ደሴ መጣ። እንደራሴው ደጃዝማች ሰለሞን ለክብር እንግዶቹ በተዘጋጀው የእራት ግብዣ ላይ ምስጋናቸውን ለቡድኑ ከገለጹ በሗላ እሳቸውም ትግሬ መሆናቸውን አንስተው የባህል ቡድኑ የትግራይ ባህላዊ ሙዚቃ እና ባህላዊ ውዝዋዜ ለማስፋፋት ላደረገው አስተዋጽኦ አድናቆታቸው ገለጹ።

በተጨማሪም የደጃዝማች ሰለሞን እናትም አጋሜ አውራጃ ውስጥ ተወላጅ ትግሬ መሆናቸውን እና አባታቸውም በትግራይ ክ/ሃገር ውስጥ የተምቤን ተወላጅ መሆናቸውን አንስተው ለባህል ቡድኑ ገልጸውላቸዋል።

የባሕር ሃይል ካፒቴን የሆኑት ካፒቴን መኮንን አብርሃ የእቴጌ መነን ትምሕርት ቤት ተማሪ የነበረቺው የደጃዝማች ገብራይ ልጅን አግብተው ሦስት ልጆች እንደወለዱ ይታወቃል። አቶ ሐጎስ አብርሃም ቢሆን በአዲስ አበባ የተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት የጥንት ተማሪ ሲሆን ለዚያው ተማሪ ቤት የእግር ኳስ ቡድን በረኛ ነበር፣ ሆኖም በበሽታ ምክንያት ትምህርቱን አቋርጦ ለጥቂት ጊዜ በብሔራዊ ባንክ ስራ ተቀጥሮ እየሰራ እንዳለ ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለየ ይታወቃል።

የአቶ ኢሳያስ አፈወርቂ አያቶችና ሌሎች ዘመዶቻቸውም - በሚመለከት፦
በእናቱ በኩል የኢሳያስ አፈወርቂ አያት (የእናት እናት) ወይዘሮ መድህን «በራድ» ይባላሉ። በራድ (ተብለው በቅጥያ ስም የተጠሩበት ምክንያት ወ/ሮ መደህን በጠጅ ስራ ንግድ ተሰማርተው ይኖሩ ስለነበር «ጠጅ» ባካባቢው የሚቀዳው «በራድ» ተብሎ በሚታወቀው «ማንቆርቆርያ» ስለነበር ነው። መድህን የኢሳያስ እናት የወይዘሮ አዳናች በርሄ እናት ናቸው። ኢሳያስ የልጅነት ትምህርቱ የተከታተለው በሴት አያቱ በወይዘሮ መድህን ተንከባካቢነት ነው። ወ/ሮ መድህንም በትውልዳቸው ዓድዋ ሲሆኑ፣ የፊታውራሪ ኪዳነ መስቀል አጎት ናቸው።

ፊታውራሪ ኪዳነ የአቶ የማነ ኪዳነ (የየማነ ጃማይካ) አባት ናቸው ይባላል። ይህ እውነት ከሆነ የአቶ የማነ ኪዳነ (ጃማይካ) እና አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ «በኢትዮጵያ አጠራር» ወንድማማቾች ናቸው። በአውሮጳውያኖች አጠራር ግን «የአጎት ልጆች ናቸው»። ባጭሩ አሥመራ የሚገኙ አክራሪ ጠላቶች ናቸው የሚባሉት አብዛኛዎቹ የትግራይ ዝርያ የሆኑና በተለይ ከትግራይ በጠቅላላም ከኢትዮጵያ ጋር ጠንካራ የስጋ ፣ የአጥንት እና የደም ቁርኝት ያላቸው ናቸው። የኢሳያስ አክስት (የኢሳያስ እናት እህት) ወ/ሮ ሃና ይባላሉ። የአቶ በላይ ባለቤት ናቸው። አቶ በላይ የዓድዋ ሰው ናቸው። እንደሚባለውም ልጆቻቸው ስዊድን ሃገር ውስጥ ይኖራሉ። በእናታቸው በኩል የአቶ ኢሳያስ አጎት የሆኑት ከዓድዋ ተወላጅ ከሆኑት በአሁኑ ጊዜ ጀርመን ውስጥ የሚኖሩ ወ/ሮ ዘውዴ የሚባሉትን ወልደዋል። ከላይ በተገኘው መረጃ መሰረት የአቶ ኢሳያስ ኤርትራዊነት ኤርትራ መሬት መወለዳቸው ብቻ ነው። የአቶ ኢሳያስ ባለቤትም ወ/ሮ ሳባ ሃይለ ይባላሉ። ኤርትራዊት ናቸው።
 




#Article 286: «የተከሠተው ዕድል» (152 words)


አንዳንዴም የተከሠተው እድል ደግሞ ስሜን አሜሪካ በሙሉ ከነካናዳ፣ ሜክሲኮ፣ ኩባና መካከለኛው አሜሪካ ጋራ ሁሉ እስከሚመጠት ድረስ የሚል ሰፊ ትርጉም ተሰጠው። ከዚህ በላይ ይኸው ፅንሰ ሀሣብ ሌሎችን ግዛቶች መግዛቱን ለማጽደቅ ተጠቅሞ ያውቃል። በተከሠተው ዕድል አራማጆች አስተያየት ዘንድ መስፋፋቱ ጥሩ ነገር ከመሆኑ በላይ ግልጽ (የተከሠተው) እና እርግጥኛ (ዕድል) ነው ብለው አመኑ። በመጀመርያ ዘይቤው የ19ኛው ክፍለ ዘመን ፖሊቲካዊ መፈክር ሆኖ በጊዜ ላይ ለአሜሪካ መንግሥት በአሕጉሩ ዳር እስከ ዳር መስፋፋት ተራ ታሪካዊ መግለጫ ሆነ። 

ዘይቤው መጀመርያ በተለይ በጃክሶኒያን ዴሞክራት ወገን በ1840ዎቹ አሁን ምዕራብ አሜሪካ ያለውን ማለት ኦሬጎን ግዛት፣ ቴክሳስ ሬፑብሊክና በዚያን ጊዜ ስሜን ሜክሲኮ የነበረውን በኃይል መያዙን ለመምዋገት ይጠቀም ነበር። ሁለተኛ በ1890ዎቹ በሪፐብሊካን ወገን ደጋፊዎች መሃል አሜሪካ አገር ከስሜን አሜሪካ ውጭ እንድትስፋፋ የሚያጸድቅ ሃልዮ እንዲሆን ተነሣ።

በ20ኛ ክፍለ ዘመን ዘይቤው በአሜሪካ መሪዎች ዘንድ ቶሎ ከጥቅም ወደቀ፣ ዳሩ ግን አንዳንድ ተቺዎች እንደሚያምኑ፣ ልዩ ልዩ የተከሠተው እድል ረገዶች፣ በተለይም በዓለም ዙሪያ ዴሞክራሲ ለመግፋፋትና ለመከላከል ያለው አሜሪካዊ 'ተልዕኮ' የመኖሩ እምነት፣ እስካሁን በአሜሪካ ፖሊቲካዊ ርዕዮተ ዓለም ላይ ተጽእኖ አሳድሮአል ይላሉ።




#Article 287: አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ (183 words)


አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ የሚገኝ የመጀመሪያውና ትልቁ የመንግሥት  የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ነው። አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ  በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ስምነት የኢትዮጵያን የትምህርት ፋናንና ዕርምጃን እንዲያሳይ ታኅሣሥ ፱ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓ.ም. ከመመረቁ በፊት፣ መሠረቱ በንጉሠ ነገሥቱ ጥቅምት ፳፫ ቀን ፲፱፻፵፪ ዓ.ም. ተጣለ። ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ አዲስ አበባ በመባል ይታወቅ ነበር፤ በኋላም የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርስቲ የሚል ስያሜ የነበረው ሲሆን የዘውዳዊው መንግሥት ሥርዓት ካከተመ በኋላ የተመሠረተው ወታደራዊ መንግሥት አሁን በሚጠራበት ስሙ ሰይሞታል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዋና አስተዳደሩን ሰድስት ኪሎ በሚገኘው በዋናው ግቢ ያደረገ ሲሆን በአምስት ኪሎ (የቴክኖሎጂ ፋኩለቲ-ሰሜን)፣ በአራት ኪሎ የሳይንስ ፋኩልቲ፣ በስድስት ኪሎ (የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ፋኩልቲ እንዲሁም የኢንፎርማቲክስ ፋኩልቲ)፣ በጥቁር አንበሳ (የህክምና ፋኩልቲ ) በልደታ (የቴክኖሎጂ ፋኩለቲ-ደቡብ)፣ የአዲስ አበባ ንግድ ስራ ኮሌጅ፣ የያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት፣ የጥርስ ህክምና ትምህርት ቤት፣ እንዲሁም በደብረዘይት ከተማ የእንሰሳት ህክምና ፋኩልቲን ያስተዳድራል።
አዲስ አበባ በስሩ የሚከተሉትን ፋኩልቲዎች እና ኢንስቲቲዩቶች ይዟል፦

የኢንፎርማቲክስ ፋኩልቲ በአዲስ መልክ የተመሠረተው በ1994 ዓ.ም. ሲሆን ቀድሞ ሲሳ (ስኩል ኦፍ ኢንፎርሜሽን ስተዲስ ፎር አፍሪካ) በመባል ይታወቅ ነበር። በአሁኑ ሰዓት የኢንፎርማቲክስ ፋኩልቲ በስሩ የኢንፎርሜሽን ሳይንስ ትምህርት ክፍልን እና የኮምፒዩተር ሳይንስ ትምርት ክፍልን ይዞአል። ሁለቱም የትምህርት ክፍሎች የባችለርና የማስተርስ ፕሮግራሞች አሉዋቸው።

ኢንፎርሜሽን ሳይንስ ማለት ኢንፎርሜሽን ሳይንስ ማለት ነው?




#Article 288: የኖህ መርከብ (2174 words)


የኖህ መርከብ ወይም ሐመር (ዕብራይስጥ፦ תיבת נח /ተይባት ኖዋሕ/፤ ዓረብኛ፦ سفينة نوح /ሣፊና ኑህ/) በመጽሐፍ ቅዱስ (ኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 6—9)፣ በቁርዓንም (ሱራ 11 እና 71)፣ እንዲሁም በሌሎች «አብርሐማዊ» የተባሉ ሃይማኖቶች ጽሑፍ ዘንድ፤ ኖህን፣ ቤተሠቡንም፣ ከዓለም እንስሶችም ምሳሌዎች ከማየ አይኅ ለማዳን የተሠራ ታላቅ መርከብ ነበረች። 

በዘፍጥረት የተገኘው መሠረታዊ ታሪክ እንደሚለው፣ እግዚአብሔር በሰው ልጅ ክፋት አዝኖ ብልሹውን ዓለም ለማጥፋት ወስኖ ነበር። ሆኖም ኖህ ጻድቅ ሆኖ እራሱን፣ ቤተሠቡንም የመሬት እንስሶችንና አዕዋፍንም የምታድን መርከብ እንዲገነባ አዘዘው። የጥፋት ውኃ ከዚያ ምድሩን አጥፍቶ ውሆቹ መልሰው የብስ እንደገና ታየና መርከቢቱ በአራራት ተራሮች ላይ ዐረፈች። በመጨረሻ እግዚአብሔር ከኖህና ተወላጆቹ ጋራ ቃል ኪዳን ገባ። 

ለዚህ መተረክ ብዙ ጊዜ በአብርሃማዊ ሃይማኖቶቹ በኩል ሰፊ ዝርዝሮች ተጨምረዋል። እነዚህ ዝርዝሮች ከሥነ-መለኮታዊ ትርጉሞች ጀምሮ ለተግባራዊ ጉዳዮች የሆኑ መላምታዊ ፍቾች እስከሚነኩ ድረስ ሊሆኑ ይችላሉ። በ19ኛው ክፍለ-ዘመን ላይ፣ በተለይ በምዕራብ ዓለም በብዙዎቹ የሳይንስና የሥነ ጽሑፍ ሊቃውንት አስተያየት፣ መተራረኩ አፈ ታሪክ ብቻ እንጂ በዕውኑ አይሆንም በማለት ተጠራጠሩ። ዳሩ ግን በመጽሐፍ ቅዱስ ትክክለኛነት የሚያምኑት ሰዎች እስካሁን አይነተኛና ዕውነተኛ ታሪክ መሆኑን ቆጥረውታልና እስከዚህ ቀን ድረስ ለመርከቢቱ ማረፊያ ተራራ አንዳንድ ፍለጋ ሲካሄድ ነው። 

በዘፍጥረት 6፡15 መሠረት፣ የመርከቢቱ ርዝመት 300 ክንድ፣ ወርድዋም 50 ክንድ፣ ከፍታዋም 30 ክንድ እንዲሆን ኖህ ታዘዘ። ቢሆንም በጥንት ዘመን «ክንድ» የሚባለው መስፈርያ (ዕብራይስጥ «አማህ») በየአገሩ ይለያይ ነበርና በልክ ርዝመቱ አይታወቅም። በግድም ግን አንድ ክንድ ምናልባት ግማሽ ሜትር የሚያሕል ነበር። የርዝመቱና የስፋቱ ውድር 6፡1 ሆኖ ይህ ለዛሬው መርከቦች እንኳን በጣም ጽኑና ጠቃሚ ቅርጽ ሆኗል። ደግሞ መርከቢቱ መስኮትና በር በጎኑ ነበራትና መገንባትዋ 100 አመት ፈጀ ይላል። 

በዘፍጥረት 6፡14 መሠረት ኖህ መርከቢቱን ከጎፈር ዕንጨት እንዲሠራ ታዘዘ። ይህ ቃል በዕብራይስጥ (גפר) በሌላ ስፍራ ከቶ አይታውቅም። የአይሁድ መዝገበ ዕውቀት ቃሉ ከአሦርኛ «ጊፓሩ» (መቃ) የተተረጎመ ይሆናል በሚል ሀሣብ ግመቱን አቅርቧል። በግሪክ ብሉይ ኪዳን (70 ሊቃውንት) ዘንድ «ξύλων τετραγώνων» /ክሲውሎን ተትራጎኖን/ (አራት ጎን ያለው ዕንጨት) ይላል። እንዲሁም በሮማይስጥ ትርጉም «lignis levigatis» /ሊግኒስ ሌዊጋቲስ/ (የተለመጠ ዕንጨት) አለው። በሌሎች ግመቶች ዕንጨቱ ዞጲ፣ ዝግባ ወይም አርዘ ሊባኖስ ሊሆን ቻለ። ከዚህ በላይ 6፡14 «በቅጥራን ለቅልቃት» ሲል የቅጥራን ትርጉም በዕብራይስጡ «ኮፈር» ነውና አንዳንድ ተቺዎች «ጎፈር» ለ«ኮፈር» የተሳተ ይሆናል በማለት ገመቱ። 

በዘፍጥረት የኖህ መርከብ ታሪክ መጀመርያ፡ እግዚአብሔር የሰው ልጅ ክፉ ሥራ አይቶ ሕይወት በሙሉ የሚያጠፋ ጎርፍ ለመላክ ሀሣቡን ቆጥሮአል። ነገር ግን እግዚአብሔር አንድ ጻድቅ ሰው ኖህን አግኝቶ የአዳም ዘር በርሱ እንዲኖር አስቧል። ስለዚህ እግዚአብሔር ኖህ መርከብ እንዲሠራ አዝዞ ሚስቱን፣ ሦስት ልጆቹንም (ሴም፣ ካምና ያፌት)፤ ሦስት ሚቶቻቸውንም በድምሩም 8 ሰዎችን እንዲያሣፍራቸው አለው። በተጨማሪ ከንጹሕ እንስሶች 14፣ ንጹሕ ካልሆኑትም 4 ወይም 2 ናሙናዎች እንዲያሣፍር መብላቸውንም እንዲያመጣ ታዘዘ። ሁሉም ወደ መከቢቱም ገብተው እግዚአብሔር ዘጋት ይላል። 

ዘፍጥረት እንደሚለው የኖህ ዕድሜ 600 አመታት ሲሆን በ2ኛው ወር በ17ኛው ቀን 'የታላቁ ቀላይ ምንጮች ሁሉ ተነደሉ፣ የሰማይም መስኮቶች ተከፈቱ'፤ ጎርፉ እንግዲህ ከዝናብና ከታችኛ ምንጮች አንድላይ ወጣ ማለት ነው። ውኃው ከተራሮቹ በላይ 15 ክንድ ነበረ (7፡20)፤ በምድር የሚኖር ሁሉ ሰመጠ። (በዕብራይስጥ መዝሙር 103፡8 ደግሞ፣ ውኆች በተራሮች ላይ ከቆሙ በኋላ ተራሮቹ ከፍ አሉ ቈላዎቹም ወረዱ ይላል።) ኖህና ከሱ ጋር በመርከቢቱ ላይ የነበሩ ብቻ አልሰመጡም። 

ዘፍጥረት ስለጥፋት ውኃ የተወሰኑ ቀኖች ያመልክታል። በኖህ ሕይወት 600ኛው አመት በ2ኛው ወር 17ኛው ቀን ከጀመረ በኋላ ዝናቡ ለ40 ቀን ዘነበ። ውኆቹም እንደገና ለ150 ቀን ምድርን ሸፈኑ። ዝናቡ ከጀመረ 5 ወሮች በኋላ ሐመር በአራራት ተራሮች አረፈች (8፡4)። 2.5 ወሮች ከዚህ በኋላ፡ በአሥረኛው ወር መባቻ የተራሮች ጫፎች ታዩ (8፡5)። እንደገና 3 ወር አልፈው በኖህ ሕይወት በ601ኛው አመት በመጀመርያው ቀን፣ ኖህ የምድር ፊት እንደ ደረቀ ከመርከብ አየ (8፡13)። ሁለት ወር ከዚያም በኋላ፣ በ2ኛው ወር 27ኛው ቀን፣ ምድሪቱ ድርቅ ሆነች። በዚያን ጊዜ ኖህ፣ ቤተሠቡና እንስሶቹ ሁሉ ከሐመር ወጡ። 

ማየ አይኅ በየትኛው አመት እንደ ደረሰ ለመገመት፣ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያምኑት መምህራን አብዛኛው ጊዜ የዘፍጥረት ትውልዶች በምዕራፍ 5ና 11 ያጥናሉ። በ17ኛው ክፍለ ዘመን የአይርላንድ ሊቀ ጳጳስ ጄምስ አሸር በዚህ ዘዴ በ2349 አክልበ. (እ.ኤ.አ.) እንደ ደረሰ ቆጠሩ። አንዳንድ ምዕመናን እስካሁንም ድረስ ይህን አቆጣጠር ይቀበላሉ። ነገር ግን በዕብራይስጥ (ማሶሬታዊው) ትርጉም፤ በግሪኩ ትርጉምና በሳምራዊው ትርጉም የአባቶች አመቶች ስለሚለያዩ፣ ሌላ ውጤት ማግኘት ይቻላል። በመጽሐፈ ኩፋሌ ዘንድ ማየ አይኅ በአመተ አለም 1308 ደረሰ፣ ባጋጣሚው የሳምራውያን ትርጉም ደግሞ ከኩፋሌ ጋራ በመስማማት ይህን አመት ያመለክታል። ኩፋሌው እንደሚለው የእስራኤል ልጆች ከግብጽ የወጡ በ2410 ዓመተ አለም ከሆነ፣ ከጥፋት ውኃ 1,102 አመታት በኋላ ነበር ማለት ነው። ለምሳሌ ከግብጽ የወጡ በ1661 አክልበ. ከሆነ፣ እንግዲህ ማየ አይህ በ2763 አክልበ. ሊቆጠር ይቻላል።

የክፉ ልጆችን ሁሉ ለማጥፋት የተገኙባቸው አገሮች ብቻ በውኃ መሸፍን አስፈላጊ ይሆን ነበር፤ ብዙዎች እንደሚያስቡ፣ ሰዎች ያንጊዜ ካልተገኙባቸው አሁጉራት ጭምር መላውን ዓለም መሸፈን አስፈላጊ አይመስልም።

ዘፍጥረት እንደሚተርከው፣ መርከቢቱ በአራራት ተራሮች አርፋ ተራሮችም ታይተው ኖህ ቁራን ላከና ወዲያ ወዲህ በርሮ የብስን አላገኘም ነበር። ቀጥሎም ኖህ ርግብን ሰደደና ምንም መሬት ሳታገኝ ተመለሰች። ከሳምንት በኋላ በተጨማሪ ርግቧን ልኮአት የወይራ ቅርንጫፍ ይዛ ተመለሰች። ሦስተኛ ላካትና አልተመለሰችም። 

ኖህ በዚህ መሬት ደረቅ እንደ ሆነች አውቆ፣ እግዚአብሔር ሁላቸው ከመርከብ እንዲወጡ አዘዘና ቃል ኪዳን ገባ። ይህ ቃልኪዳን ምድርን በሙሉ ዳግመኛ በውኃ ከቶ እንዳያጠፋ የኖህም ተወላጆች በመሠረታዊ ደንቦች እንዲኖሩ ነበር። የሰው ልጅ ምንም እንስሳ ከነደሙ መቸም እንዳይበሉ የሚል ትዕዛዝ ተሰጠ። ለዚህ ቃልኪዳን ምልክት እግዚአብሔር በዚያን ጊዜ ቀስተ ደመናን ፈጠረ። 

ከማየ አይህ አስቀድሞ የአንዳንድ ሰዎች ዕድሜ እስከ 1 ሺህ አመታት ድረስ ይደርስ እንደ ነበር ኦሪት ይለናል። ግን ከዚህ በኋላ የእድሜ መጠን እስከ 120 አመት ድረስ ቶሎ ይቀነስ ጀመር።

በኩፋሌ ውስጥ ኖህ እራሱ አራት መታሰቢያ በዓላት አዋጀ እነዚህም በዓላት በየአመቱ በ1ኛው፣ 4ኛው፣ 7ኛው፣ 10ኛውም ወሮች መባቻ እንዲከብሩ ትልቅ ቁም ነገር መሆናቸውን ያጠቁማል።

በአይሁድ ረቢዎች ስነ-ጽሑፍ ዘንድ (በመጀመርያ ክፍለ-ዘመናት ዓ.ም.) ኖህ ከጥፋት ውኃ 120 አመታት በፊት አርዘ ሊባኖስ ተክሎ ሐመርን ከዚህ ዕንጨት ሠራት። መላዕክት እንስሶቹን ወደ መርከቢቱ ያመሯቸው ሲሆን እግዚአብሔር ቤተሠቡን ከክፉ ሰዎች ለመጠበቅ አንበሶች አኖረ። ኖህ ቀንና ሌሊት በማገንባት ላይ ኖረ፣ ደግሞ በመርከቢቱ ላይ ሲሆን ለአመቱ አላንቀላፋም ይባላል። ራባ የተባለው ሚድራሽ እንደሚል የጎርፉ ክልል አለም አቀፍ ሳይሆን እስከ ሞሮኮ ድረስ ብቻ ሸፈነ። ታልሙድ ሳንሄድሪን ደግሞ አንበሣው ኖህን እንደ ሰለበው ይተርካል። 

በመርከብ ላይ ያሉት ሁሉ ከማርባት ቆዩ የሚል መረጃ በአይሁድ ጸሐፍት ይጨመራል። ቁራው ሲሰደድ ፈቃደኛ አልነበረም። ከሐመር ሦስት ፎቆች፣ ታቸኛው ለቆሻሻ፣ መካከለኛው ለሰዎችና ለንጹሐን እንስሶች፣ ላየኛም ለርኩስ እንስሶችና ለወፎች ነበር። (በሌላ የአይሁድ ጽሑፍ ግን ቆሻሻው በላይኛ ፎቅ ሆኖ ቀጥታ ወደ ባሕር ይጣል ነበር።) ብርቅ ድንጋይ በተዓምር ብርሃን ይሰጥ ነበር። ከኖህ ቤተሠብ 8 ሰዎች ጭምር አንድ ረጃጅም ሰው ወይም ናፊል፣ የባሳን ንጉሥ ዐግ በሐመር ከመሰጠም አመለጠ የሚል የአይሁዶች ልማድ ቢገኝም፣ ይህ ግን ለመጽሐፍ ቅዱስ ተቃራኒ ይመስላል፤ የዐግ ግዛት በኢያሱ ወልደ ነዌ ዘመን ይታወቅ ነበርና። 

በሌላ የአይሁድ ታሪክ ዘንድ የሐመር ሣንቃ በአሦር ንጉሥ ስናክሬም ተገኝቶ ጣኦት ሠራበት። በሚድራሽ አባ ጊርዮን ዘንድ፣ ሌላ የሐመር ሣንቃ ደግሞ ለሐማን (ከመጽሐፈ አስቴር) ስቅለት ተጠቀመ።

በወንጌል መሠረት ኢየሱስ መመለሱን እንደ ኖህ ዘመን አመስሎ መሠከረ። (ማቴ. 24:37-42) መጀመርያ የቤተ ክርስትያን ጸሐፍት ሐመርን እንደ ምልክት ቆጠሩት። 1 ጴጥሮስ መልእክት እንዳለ በሐመር ያመለጡት ሰዎች በጥምቀት ውኃ ለመረጡት ሰዎች ምሳሌ ናቸው። 

ቅዱስ አቡሊድስ (200 ዓ.ም. ገዳማ) አንዳንድ ልማዶች ተረኩ። በሦስት ፎቆች ታችኛው ለአውሬዎች፣ መካከለኛው ለአዕዋፍና ለከብቶች፣ ላየኛው ለሰዎች ሲሆን ማርባት ለመከልከል ወንዶች ከሴቶች በችካል ተለዩ። የአዳም አጽም፣ ወርቅ፣ ዕጣንና ከርቤ ተጫኑባት፤ ሐመርም በመስቀል ቅርጽ ሰፈፈች። የሰፈረችበት ተራራ 'ደብራ ካርዱ' «በምሥራቅ፣ የራባን ልጆች አገር፣ ምሥራቃውያንም 'ጎዳሽ'፤ ዓረባውያንና ፋርሳውያንም 'አራራት' ይሉታል» በማለት ጻፈ።.

ኦሪጊኔስ ስለ ሐመር ቅርጽ ራሱ እንደ ተቋረጠ ፒራሚድ ይመስል ነበር ብሎ ጻፈ። በሱ አስተያየት፣ በጫፉ ርዝመቱ አንድ ካሬ ክንድ ነበር፤ ይህም ክንድ ሙሴ በግብጽ ስላደገ የግብጽ ክንድ ሳይሆን አይቀርም መሰለው። ከ12ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ቅርጹ ባለ-ጣራ ሳጥን እንደ ነበር ተቆጠረ። በ15ኛው ክፍለ ዘመን አልፎንሶ ቶስታዳ፣ በ16ኛው ክፍለ ዘመን ዮሐንስ ቡቴዎ የሐመርን ቅርጽ ገለጹ።

በአይርላንድ አፈ ታሪክ፣ የኖህ አራተኛ ልጅ «ቢስ» እንዳይሣፈር አልተፈቀደም፤ ወደ አይርላንድ ከ54 ሰዎች ጋራ ሸሽቶ ሁላቸው ሰመጡ። 

ሐመር ደግሞ በመጽሐፈ ሞርሞን (መጽሐፈ ኤጠር) ትጠቀሳለች። በመጨረሻ ቀን ቅዱሳን (ሞርሞን) እምነት፣ የኖህ መታወቂያ በውነት መልአክ ገብርኤል ነበረ።

ኖህ (ኑኅ) ከእስልምና አምስት ዋና ነቢዮች አንዱ ነው። በቁርዓን መሠረት ኑኅ ጻድቅ ሆኖ ጣኦት ለሚያምኑት ክፉ ሰዎች ሰብኮ 70 ወይም 72 አሳመናቸውና በድምሩ 78 ወይም 80 ሰዎች በመርከቢቱ ላይ አብረውት አመለጡ። እነዚህ 72 ሰዎች ግን ምንም ልጅ ስላልወለዱ የዛሬ ሰው ልጆች በሙሉ ከኖህ ቤተሠብ ተነሡ። የኖህ አራተኛ ልጅ እንዳይሣፈር እምቢ ብሎ ተሰጠመ፤ ባንዳንድ ምንጭ ስሙ «ያም» ወይም «ከንዓን» ይሰጣል። 

በሱራ 11:44 ዘንድ የሠፈረችበት ሥፍራ ደብረ ጁዲ ሲሆን ይህ በተለመደው በሞሱል፣ ኢራቅ አካባቢ በጤግሮስ ወንዝ አጠገብ የሚገኝ ኮረብታ መሆኑ ይታስባል። ጸሐፊው አል-ማሱዲ (940 ዓ.ም. ያህል) እንደ ጻፈው፣ ሐመር ከኩፋ፣ ኢራቅ ተነሥቶ እስከ መካ ድረስ ሰፍፋ ካዕባን ዞረችና ወደ ደብረ ጁዲ ተመለሰች። በዚያም እስከ ሕይወቱ ዘመን ሊታይ ቻለ ብሎ ጻፈ። ያቁት አል-ሐርማዊ (1200 ዓ.ም. ዙሪያ) ኖህ በዚያ ያሠራው መስጊድ በዘመኑ እንደ ተገኘ ጻፈ። በቅርቡ ሌላ ተራራ በቱርክ አገር፣ ዱሩፒናር፣ በውኑ የደብረ ጁዲ ሥፍራ ነው የሚል ግመት አለ። 

ከመርከብ በሙሐራም ወር 10 ቀን ወጥተው ሰዎቹ በጁዲ ግርጌ «ጣማኒን» (ሰማንያ) የተባለ መንደር ሠሩ። ኑህ መርከቢቱን ቆልፏት ቁልፉን ለሴም ሰጠ። 

በሙሐመድ ዘመን የኖረው አብድ አላህ እብን አባስ በጻፈው ዘንድ፡ ኑኅ ዋንዛን ተክሎ ከ20 አመት በኋላ በቂ ዕንጨት ነበረው። 

አል-ባይዳዊ በጻፈው ታሪክ መጽሐፍ ደግሞ በሐመር ሦስት ፎቆች ታችኛው ለእንስሶች፤ መካከለኛው ለሰዎች፤ ላየኛውም ለአዕዋፍ ነበር። የአዳም ሬሳ ወንዶች ከሴቶች ለመለየት በመካከላቸው ተደረገ። ረጃጅሙ ዐግ ከውኆቹ ለማምለጥ እንደተፈቀደ የሚል ተረት ደግሞ ይገኛል። 

በፋርስ ጸሐፊ አል-ታባሪ ጽሁፍ ተጨማሪ ዝርዝር አለ። መጀመርያው የተሣፈረ ፍጡር ጉንዳን ሲሆን መጨረሻው ሠይጣን የተሣፈረበት አህያ ነበረ ይላል። ደግሞ የኢየሱስ ሐዋርያት ስለ ሐመር ለመማር በፈለጉ ጊዜ፣ ኢየሱስ እንዲመልሳቸው የኖህ ልጅ ካምን ከሙታን አንሥቶት ካም እንዲህ መሠከረላቸው፤ ቆሻሻ በበዛበት ጊዜ ኑህ በተዓምር ዐሣማዎች ከዝሆን ኩምቢ አወጣ፤ እንደገና አይጥ ያለ ፈቃድ ስለ ገባ ድመት ከአንበሣ አፍንጫ ፈጠረ አላቸው። እነዚህ ተረቶች በቁርዓን ስለማይገኙ ግን ብዙዎቹ እስላሞች አይቀብሉዋቸውም። 

እስላሞች ዛሬ ቁርአን ትክክለኛ ታሪክ ሆኖ ይቆጥሩታል። አንዳንድ ተቺዎች ለምሳሌ ሃሩን ያህያ እንደሚያስቡ፣ ማየ አይህ አለም አቅፍ ሳይሆን የኖህን አገር ብቻ ያጠፋ ነበር።

ባኃኢ እምነት የተባለው ሃይማኖት የሀመር ታሪክ እንደ ምሳሌ ይቆጥሩታል። የኖህ ተከታዮች በመንፈሳዊ ረገድ ሕያው የሆኑ፤ የሰጠሙትም በመንፈሳዊ ረገድ ሙታን የሆኑት ምሳሌ ናቸው። በባኃኢ ቅዱስ መጽሐፍ ኪታብ-ኢ-ኢቃን ዘንድ፡ ከኖህ ጋር 40 ወይም 72 ተከታዮች አመለጡ፤ ከማየ አይህ አስቀድሞ ኖህም ለ950 አመታት ያስተምር ነበር።

በኩርዲስታን ተራሮች የሚገኘው የየዚዲ ሀይማኖት ትምህርት በመጽሐፋቸው ምስሐፈ ረሽ (ጥቁሩ መጽሐፍ) ይገኛል። በዚህ በኩል የጥፋት ውኃ ሁለት ጊዜ መጣ። ከመጀመርያው ጥፋት የካም አባት ናኡሚ አመለጠ፤ መርከቡም በሞሱል ዙሪያ በዓይን ስፍኒ ተቀመጠች። ከዚህ በኋላ ሁለተኛው ጥፋት ውኃ በየዚዲዎቹ ብቻ ደረሰ፤ ከዚህም ኖህ በሌላ መርከብ አምልጦ መርከቡ ከደብረ ስንጃር በላይ በዓለት ተወግቶ ከዚያ በደብረ ጁዲ ተቀመጠች። 

በደቡብ ኢራቅ የሚኖሩ ማንዳያውያን ሃይማኖት ደግሞ ኖህንና ዮሐንስ መጠምቁን እንደ ነቢያት ሲቆጥሩ አብርሐምና ኢየሱስ ግን ሐሣዊ ናቸው ብለው ያምናሉ። ሐመር የተሠራ ከጀበል ሃሩን (ሖር ተራራ በዛሬው ዮርዳኖስ) በመጣ ሰንደል ዕንጨት ተሠራ፤ ርዝመቱ፣ ስፋቱና ቁመቱ ሁላቸው 30 ክንድ ነበሩ፤ ማረፊያው ደግሞ በግብጽ ነበር ይላሉ።

በሜስጶጦምያ ጥንታዊ ተረት ጽላቶች አንዳንድ ተመሳሳይ ታሪኮች ተገኝተዋል። እነዚህ ከሱመር፣ ከአካድ፣ ከባቢሎንና ከአሦር በኩነይፎርም ጽሕፈት ተጽፈው ይታወቃሉ። 

በሱመር አፈ ታሪክ የጊልጋመሽ ታሪክ፤ አማልክት ምድርን በውኃ ለማጥፋት ወስነው ኤንኪ ግን የሹሩፓክ ከተማ ንጉሥ ዚውሱድራን በመርከብ እንዲያመልጥ ይነግረዋል። ነገር ግን በዚህ ተረት የጥፋት ውኃ ለ7 ቀን ብቻ ነው። ጽሁፉ ቢያንስ ከ17ኛው ክፍለ ዘመን አክልበ. የተጻፈ ቢሆን በጊልጋመሽ ታሪክ የሚጠቀሱት ነገሥታት ኤንመባራገሲና አጋ በ3ኛ ሺህ አክልበ. በውኑ እንደ ነገሡ ከስነ ቅርስ ይታወቃል። 

የጊልጋመሽ ታሪክ በባቢሎን ትርጉም ተጽፎ የዚውሱድራ ስም በአካድኛ ኡትናፒሽቲም ሆኗል። ከ7 ቀን በዝናብና ከ12 ቀን በውሆቹ ላይ በኋላ፣ መርከቡ በደብረ ኒጺር ተቀመጠች፤ ከሌላ 7 ቀን በኋላ ኡትናፒሽቲም 3 ወፎች ይልካል። በመጀመርያ ርግብ ልኮ ተመለሰች፤ ሁለተኛ ጊዜ ጨረባ ትልካ ተመለሰች፤ ሦስተኛም ቁራ ግን አልመለሰም። በሌላ ትርጉም መርከብን የገነባው ሰው ስም አትራሐሲስ ይባላል። 

በ300 አክልበ. ገዳማ የባቢሎን ቄስ ቤሮሶስ አንድ ታሪክ በግሪክ ጽፎ ይህን አይነት ተረት መዘገበ። በዚህ ትርጉም መርከብ የገነባው ሰው ስም ክሲሲውጥሮስ ተባለ። መርከቡም እስከ ቤሮሶስ ዘመን በአርሜንያ ተራሮች እንደ ተገኘ ጻፈ።

በአንዳንድ ሊቃውንት አስተያየት የሜስጶጦምያ ተረት ለኦሪት ዘፍጥረት ምንጭ ነበረ፤ በሌሎች ሀሣብ ግን ሁለቱ በአንድ ድርጊት ተመነጩና ከሁለቱም የሜስጶጦምያ ተረቶች እጅግ የተዛቡ፣ የዘፍጥረት ግን ትክክለኛ የሆኑ ይመስላል።

በአለም ዙሪያ በማናቸውም አሕጉር በማናቸውም ወቅት የማየ አይህ ታሪክ ይታወቃል። ለምሳሌ በግሪክ ተረቶች ዘንድ ከጥፋት ውኃ በመርከብ ያመለጡ ዴውካሊዮንና ሚስቱ ፒውራ ነበሩ።

በሕንዱ ሃይማኖት ጽሕፈት፣ ከጥፋት ውኃ በመርከብ ያመለጠው ቅዱስ ንጉስ ማኑ ተባለ፤ እሱም የማኑስምርቲ ሕገጋት ደራሲ እንደ ነበር ታመነ። ከቤተሠቡና ከ7 ሊቃውንት ወይም 'ሪሺዎች'ና የአለም እንስሶችና አትክልት ናሙናዎች ጋራ ተጉዞ መርከቢቱ በሂማላያ ወይም በካሽሚር እንዳረፈች ይባላል። 

በርካታ ሌሎች ተመሳሳይ ተረቶች በአፍሪካ፣ በስሜን አሜሪካ፣ በደቡብ አሜሪካ፣ በአውስትራላዚያ፣ በእስያና በአውሮጳ ኗሪዎች መካከል ተገኝተዋል። ስለዚህ በጥንት የሰው ልጅ ሁሉ ወላጆች ከጥፋት ውኃ እንዳመለጡና በኦሪት ዘፍጥረት ያለው ከሁሉ ይልቅ ትክክለኛ ታሪክ ነው የሚያምኑ ብዙ ሰዎች አሉ። 

የአይሁድ ታሪክ ጸሕፊ ፍላቭዮስ ዮሴፉስ (1ኛው ክፍለ ዘመን አ.ም.) የቀድሞ አሕዛብ ጸሕፍት ቤሮሶስ፣ ሂኤሮኒሙስ ግብጻዊ፣ ምናሴዎስና የደማስቆ ኒቆላዎስ ሁላቸው ሐመር በአርሜንያ ተራሮች ትገኛለች እንዳሉ ጠቀሳቸው። እንዲሁም ረቢው ዮናታን ቤን ዑዝኤል (1ኛው ክፍለ ዘመን አ.ም.)፣ ክርስቲያን ጸሐፍት አቡሊድስ፣ የአንጾኪያ ቴዎፊሎስ (2ኛው ክፍለ ዘመን)፣ ቅዱስ ሂኤሮኒሙስና ኤጲፋንዮስ (400 ዓ.ም. ገዳማ)፤ የእስላም ጸሓፍት አል-ማሱዲ (9ኛው ክፍለ ዘመን) ሁላቸው በዘመናቸው ሐመር በአርሜንያ ወይም በኩርዲስታን ተራሮች ልትታይ ቻለች አሉ። ቅዱስ ያዕቆብ ዘኒሲቢስ ከሐመር ሥፍራ የወሰደው የእንጨት ቅርስ በአርሜንያ ኤጭምያጺን ገዳም እስከ ዛሬ ድረስ እንደሚታይ ይባላል። 

በ17ኛው ክፍለ ዘመን የሮማ ካቶሊክ ኢየሳስዊ ቄስ አታናስዮስ ኪርከር በግሪክ አፈ ታሪክ የሚገኙት ሲሬኖች የተባሉት ፍጡሮች (በከፊል ወፍ በከፊልም ሴት) በውኑ እንደሚኖሩ አስተማረ። ስለዚህ በኖህ መርከብ ልዩ ክፍል ነበራቸው ብሎ ገመተ። በዚህ ዘመን የሐመር ታሪክ ብዙ ሊቃውንት የአትክልትና የእንስሶችን ስርጭት ለማጥናት ነዳቸው። 

በ19ኛው ክፍለ-ዘመን ላይ፣ በተለይ በምዕራብ ዓለም በብዙዎቹ የሳይንስ ሊቃውንት አስተያየት፣ መተራረኩ አፈ ታሪክ ብቻ እንጂ በዕውኑ አይሆንም በማለት ተጠራጠሩ። ቢሆንም በዚህ ወቅት የኖሩ አንዳንድ መምህራን ለምሳሌ አውጉስት ዲልማን፣ ፍራንጽ ዴሊችና ፍራንሷ ለኖርማን ማየ አይኅ አፈ ታሪክ ወይም ተረት ብቻ ሳይሆን ትክክለኛ ታሪክ ነው በማለት ገመቱ። ለማስረጃ እያንዳንዱ ጥንታዊ ሥልጣኔ ለዚህ ታላቅ ፍዳ ትዝታውን ስለ ጠበቀ ነው የሚል ምስክር አቀረቡ።

ከአሜሪካ (USA) ሕዝብ 2 ሢሶ ወይም 65 ከመቶ የሚያህሉ ማየ አይህ ዕውነተኛ ታሪክ እንደሚሆን ጽኑዕ እምነት አላቸው። በመጽሐፍ ቅዱስ ትክክለኛነት የሚያምኑት ምእመናን አብዛኛው ጊዜ ጸሐፊው ሙሴ በ13ኛው ክፍለ ዘመን አክልበ. ሲሆን ማየ አይህ በ3ኛ ሺህ አክልበ. የደረሰ መቅሠፍት እንደ ሆነ ይቀበላሉ። የማየ አይህ ጥናት የጥፋት ውኃ አለም አቅፍ እንደ ነበር፣ በመሬትም ብዙ ማስረጃ እንዳለ (ለምሳሌ የባሕር እንስሳ ቅርስ በተራሮች ላይ ሲገኝ) ያስተምራል። ሆኖም አብዛኛው የዛሬውኑ ሳይንስ ሊቃውንት ይህ ጥናት ሀሣዊ ነው የምድርም ዕድሜ ብዙ ሚልዮን አመታት ነውና በማለት ተቃውመውታል። 

የሐመር ሥፍራ ማግኘት ከጥንት ጀምሮ ታስቧል። ብዙዎች ፍለጋዎች በደብረ አራራት በዛሬው ቱርክ አገር ቢሆኑም፣ እንዲያውም ዘፍጥረት «የአራራት ተራሮች» ይላል። በኩፋሌ የጫፉ ስም ሉባር ይሠጣል። ሌላ የቱርክ ጫፍ ዱሩፒናር ላይ ወይም በኢራን በደብረ ሳባላን ላይ እንደምትገኝ አንዳንድ ጀብደኞች ይላሉ። 

በ1999 አ.ም. (2007 እ.ኤ.አ.) አንድ የቱርክና የሆንግኮንግ ፍለጋ ወደ ደብረ አራራት ሂዶ በአንድ ዋሻ ውስጥ፣ ወደ ድንጋይ የተቀየረ የዕንጨት ግድግዳ እንዳገኘ ናሙናዎችም ከዚያ እንዳወረዱ ይላሉ። ይህ የሐመር ሥፍራ በደብረ አራራት ላይ ተገኝቷል ማለት ነው ይላሉ።




#Article 289: ማስሩቕ (423 words)


ማስሩቕ (መስሩቕ፣ መስሩቅ፡ 595 አ.ም ገደማ) በየመን የመጨረሻው የኢትዮጵያ ንጉሥ፣ በየመን የኢትዮጵያ ንጉሥ ኣብረሃ የመጨረሻው ልጁ ሆኖ ከታላቅ ወንድሙ ከአክሱም ቀጥሎ በየመንና አካባቢው ግዛቶች በዙፋን የተቀመጠ። እናቱ ንግስት ሪይሃና ትባላለች። ከወንድሙ ከያክሱም ጋር የአንድ አባትና እናት ልጆች ናቸው። ሪይሃና ከየመን ልዑላን ቤተሰብ የምትወለድ ስትሆን ሥሙ ዙል-ያዛን (ዱ-ያዛን) ከተባለ፣ ከሂምሪያ ንጉሣዊ ቤተሰብ አንዱ ክፍል ከሚወለድ የመጀመሪያ ባልዋ ላይ በግድ ጠልፎ ነው ንጉሥ ኣብረሃ ያገባት። የወንድማማቾቹ በእናታቸው የመናዊ መሆን ከሕዝቡ ተቀባይነት ለማግኘት ብዙም አልረዳቸውም። ከወንድሙ ከያክሱም ንግስና ዘመን ጀምሮ የኢትዮጵያውያን ወራሪ ኃይልና ዝና እያሽቆለቆለ ሄዶ በምትኩ ሥርዓት አልበኝነት፣ ተቃውሞና ጥላቻ በየመን እያየለ ሄዶ  በንጉስ ማስሩቅ ጊዜ ወደ ፍጹም የከፋ ረብሻና አለመረጋጋት ተቀይሮ ነበር። እንዲሁም ይህን ሁኔታ ለመቀልበስ ሲባል  ከባድ ጭቆና በሕዝቡ ላይ ይታይና ይደርስ ጀመር። የመኖች ከውጪ ሌላ ረዳትና ኃይል እስኪያገኙ ድረስ ግን የኢትዮጵያዉን ንጉስ ማስሩቅ ከሥልጣኑ የሚያነቃንቀው ደረጃ የደረሰ ኃይልና እንቅስቃሴ አልተገኘም።

የዘጠነኛው ክ/ዘመን ጸሃፊ ታብሪን እንደዘገበው ከሆነ ለንጉስ ማስሩቅ ውድቀት፣ ብሎም ለኢትዮጵያ የባሕር ማዶ ግዛት ማክተም አንዱና ዋንኛ ምክንያት የሆነው የገዛ ግማሽ ወንድሙ ሠይፍ ማዕዲ ካሪብ ኢብን ዱ-ያዛን ነው። ሠይፍ ማዕዲ በአብረሃም ቤት ያደገና ከቀሪው ልጆቹ እኩል እንደ ገዛ ልጁ አብረሃም ያሳደገው ልጁ ሲሆን ሠይፍ ማዕዲም ቢሆን አባቱ አብረሃም እንደሆነ ነበር የሚያውቀው። ከዕለታት አንድ ቀን በርሱና በወንድሙ ማስሩቅ መካከል በተነሳ ጭቅጭቅ ውስጥ የዱ-ያዛን ልጅ መሆኑን ይረዳል። ሠይፍ ማዕዲም ከጥንቱ የየመናዊው ንጉሣዊ ቤተሰብ የሚወለድ መሆኑንና ዙፋኑ ለርሱ የሚገባ መሆኑን አውጆ እርዳታ ለማግኘት የመንን ለቅቆ ኮበለለ።

ለሠይፍ ማዕዲ የእርዳታ ጥሪ መልስ የሰጠው የታላቋ ፋርስ ንጉሥ ቀዳማዊ ኾስሩ ኑሺርዋን፣ 800 ከሚደርሱ በሕግ ሥር ካሉ ወታደሮች ጋር ዕድሜው 80 ዓመት የደረሰውን ባለ አንድ ዓይና የጦር አበጋዝ ዋህራዝ በመርከብ ወደ የመን ላከ። በፐርሺያ ጦር ቁጥር ማነስ የተነሳ የአበሻው ንጉስ ማስሩቅ ጠላቶቹን እጅግ አናንቆ ነበር የተመለከታቸው። በዚህም የተነሳ የፐርሺያ ጦር የየመን ወደብን ከረገጠ ጀምሮ ከአንድ ወር ጊዜ በላይ ሳይዋጋቸው የመወስኛ ዕድል ሰጣቸው። እንዲያውም ለዋህራዝ ጦር የምግብና ሌላም ስንቅ ያሉበት ድረስ ለስላቅ ይልክላቸው ነበር። ይህ ያልተጠበቀ ዕድል ለፐርሺያ ጦር ጥሩ የእረፍትና የጦር ዝግጅት እንዲያደርግ ረዳው። ሠይፍም ከየመን የሂምያር መሳፍንት ቤተሰቦች ጋር እየተላላከ ደጋፊና ወገን ለመሰብሰብ አስቻለው። በመጀመሪያው ዙር ጦርነት፣ ንጉስ ማስሩቅና ዋህራዝ ሁለቱም ልጆቻቸውን በአዝማችነት ልከው የሁለቱም ልጆች በጦርነቱ ተገደሉ። በዚህ ጦርነት ላይ የፐርሺያዎች የቀስት ፍላጻ፣ በኢትዮጵያውያን ላይ ከፍተኛ ጉዳት አደረሰ። የኢትዮጵያ ጦር ከጦርና ጋሻ በስተቀር ቀስትን በወቅቱ ስላልታጠቀ፡ እራሱን ላልተመጣጠነ ጉዳት አጋለጠ። አበጋዙ ዋህራዝ በመቀጠል ይዘውት የመጡትን መርከቦች በማቃጠል፡ የሠራዊቱን የመሸሽ ዕድል አጨልሞ ፈጽሞ እንዲዋጋ አሰልፎ አዘጋጀው። ለወሳኙ ጦርነት፣ ንጉሥ ማስሩቅ እራሱ በዝሆን ላይ ተቀምጦ፣ ግምባሩ ላይ ሩቢ አድርጎ ወደ 100 ሺህ የሚገመት ሠራዊቱን እየመራ ለጦርነት ተሰለፈ። አንድ አይናው ዋህራዝ ቀስቱን ደግኖ የማስሩቅ ሩቢ ላይ በማነጣጠር የለቀቃት ፍላጻ በአፍታ ማስሩቅን ግምባሩን ነድላ ገደለችው። በዚህ የተሸበረው የኢትዮጵያ ጦር ተበታተኖ ለሽንፈት እንዲዳረግ ምክንያት ሆነ። 

በዚህ ጦርነት የተገባደደው የአክሱማዊያን የየመን ግዛት ሥልጣን፣ በፐርሺያዎች የበላይ አስተዳደርነት ተተክቶ ሙስሊሞች ወደ የመን እስከሚመጡ ድረስ ፀና።




#Article 290: መምበርቱ (305 words)


መምበርቱ (መስከረም 10 ቀን 1604 ዓ.ም. የሞቱ) ፈረንሳያውያን በአካዲያ (የዛሬው ኖቫ ስኮሺያ፣ ካናዳ) መጀመርያ በሠፈሩበት ወቅት የሚግማቅ ብሔር ሳግሞው (አለቃ) ነበሩ። መጀመርያ የገስፑጒትክ ክፍላገር ሳግሞው ሆነው፣ በኋላ የሌሎቹ 6 ሚግማቅ ክፍላገሮች ሳግሞዎች ዋና ሳግሞው እንዲሆኑ መረጡዋቸው።  

መምበርቱ ከስሜን አሜሪካ ኗሪዎች መጀመርያ የተጠመቁት በመሆናቸው በተለይ ይታወቃሉ።  በሰኔ 20 ቀን 1602 ዓ.ም. ቄሱ አቤ ዠሴ ፍሌሼ ለመተባበር ምልክት እሳቸውን ስለ ፈረንሳይ ንጉሥ 4ኛ አንሪ ስም «አንሪ» ሰይሟቸው ከቤተሠባቸው ጋር አጠመቃቸው።  

ፈረንሳያውያን መጀመርያ በደረሱ ጊዜ በ1597 ዓ.ም. ዕድሜያቸው ከ100 አመት እንደ በለጠ ተብሎዋል። በወጣትነታቸው የፈረንሳይ ዠብደኛ ዣክ ካትዬን በ1526 ዓ.ም. ጉዞ ላይ መገኛነቱን ትዝ እንዳሉ ነገሯቸው። ፈረንሳያውያን ምሽግ በመምበርቱ አገር በፖርት ሮያል ሠርተው በ1599 ዓ.ም. ሁለት ሰዎች ብቻ ትተው ወጡ። በ1602 ዓ.ም. ወደ መምበርቱ እስከተመለሱ ድረስ እሳቸው ለምሽጉና ለ2ቱ ፈረንሳውያን ሰዎች ኅላፊና ታማኝ ነበሩ።  

ከተጠመቁ አስቀድሞ «ሳግሞው» ወይም ፖለቲካዊ መሪ ከመሆናቸው በላይ፣ መምበርቱ ደግሞ «ኦትሟን» ወይም መንፈሳዊ መሪ ሆነው ነበር፤ ነገዳቸው የሕክምናና የትንቢት ችሎታ እንደነበራቸው ያመን ነበር። በዛሬው ሜን ክፍላገር የኖረው ፓሣማኰዲ (አርሙሺኳ) ብሔር ሌላውን የሚግማቅ ሳግሞው ፓኖኒያክን በ1598 ዓ.ም. ከገደሉ በኋላ፣ መምበርቱ ሥርዓተ ቀብር ሲያካሔዱለት ፈረንሳያውያን አዩ። ቂሙን ለመበቀል፣ መምበርቱ በዘመቻ በሐምሌ 1599 ዓ.ም. 500 ጎበዞችን ወደ አርሙሺኳ መንደር ወደ ሿኮወት (የዛሬ ሳኮ፣ ሜን) መሯቸው፣ ከጠላቶቻቸውም 20፣ ከነመሪዎቻቸው ኦንመሻንና ማርሻን ገደሏቸው።

ኢያሱሳዊው ቄስ ፒዬር ቢያርድ እንደ ጻፈው፣ እንደ ሌሎች የተነጩ ሚግማቅ ወንዶች ሳይሆን፣ መምበርቱ ባለ-ጺም ነበሩ። ከሌሎቹም ትልቅ ነበሩ፣ የመቶ አመት ሽማግሌ ቢሆኑም፣ ምንም ሽበት አልነበራቸውም።  አብዛኞቹ ሳግሞዎች ከአንድ ሚስት በላይ ቢያገቡም፣ መምበርቱ ግን አንዲት ሚስት ብቻ ነበረቻቸው፤ እርሷም «ማሪ» ተብላ ተጠመቀች። የበኲር ልጃቸውም ስም መምበርቱጂች ሲሆን የጥምቀት ስም «ሉዊ መምበርቱ» ተቀበለ። ሁለተኛው ወንድ ልጅ (አክቶዲን) በጥምቀት ጊዜ አልተገኘም፤ ሦስተኛውም አክቶዲጂች «ፖል መምበርቱ» ተብሎ ተጠመቀ። ደግሞ የሴት ልጃቸው ጥምቀት ስም «ማርገሪት» ነበረ። 

አባ ቢያርድ እንደ ጻፈው፣ የመምበርቱ ልጅ አክቶዲን በብርቱ በታመመ ጊዜ፣ ለማማለጃ 2 ወይም 3 ውሾች ለመሠዋት ዝግጁ ሲሆኑ፣ ቢያርድ ግን ይህ ስህተት ነው ሲላቸው አልሠዋቸውምና ወዲያው አክቶዲን ዳነ። 

ከዚህ ትንሽ በኋላ፣ በ1603-4 ዓ.ም.፣ መምበርቱ እራሳቸው ታመሙ፤ በመስከረምም ዐረፉ። በመጨረሻ ቃላቸው፣ ልጆቻቸው በክርስትና ጸንተው እንዲተጉ አስጠነቀቋቸው። 




#Article 291: ኦሊቨር ክሮምዌል (141 words)


ኦሊቨር ክሮምዌል (ሚያዝያ 30 ቀን 1591 ዓ.ም.-መስከረም 6 ቀን 1651 ዓ.ም. የኖሩ) በንጉሥ ፋንታ የእንግሊዝ አገር ጠባቂና መሪ ነበሩ። 

የእንግሊዝ ብሔራዊ ጦርነት በጀመረበት ጊዜ (1634 ዓ.ም.) ዖሊቨር ክሮምዌል የፒዩሪታን ወገን መሪ ሆነው ነበር። በተደረገው አብዮት በንጉሡ 1 ቻርልስ ይሙት በቃ ከተፈረደባቸው ቀጥሎ (1641 ዓ.ም.) አገሩ ያለ ንጉሥ መንግስት ሆኖ የእንግሊዝ ኅብረተሠብ (Commonwealth ወይም የጋራ ደኅንነት) ይባል ነበር። በ1645 ዓ.ም. የክሮምዌል ማዕረግ «ጌታ ጠባቂ» ሆነ። ሆኖም እንደ ንጉሥ ያሕል ሥልጣን ነበራቸው። የፕዩሪታን ወገኖች በጽናት የሮማ ቤተክርስቲያንና ፓፓን እንደ ተቃወሙት መጠን በዚያን ዘመን የፕሮቴስታንት ኮዝ (ምክንያት) ተግፋፋ። ከዚህ በላይ የኤጲስቆጶሳዊ ወይም የእንግሊዝ ቤተክርስቲያን (አንግሊካን) ተቃዋሚዎች ነበሩ። 

በ1650 ዓ.ም. ክሮምዌል በድንገት ከትኩሳት ታምመው በቅርቡ ዓረፉና ልጃቸው ሪቻርድ ክሮምዌል ተከታያቸው ጌታ ጠባቂ ሆነ። ሪቻርድ ግን እንደ አባቱ ኃይለኛ መሪ አልነበረምና በጥቂት ጊዜ ውስጥ (በ1651 ዓ.ም.) ከሹመቱ ወረደ። ከአንድ አመት ችግሮች በኋላ በ1652 ዓ.ም. ንጉሣዊው ወገን ወደ ሥልጣን ተመለሰና የ1 ቻርልስ ልጅ 2 ቻርልስ ዙፋኑን ያዙ።




#Article 292: ቤስጳስያን (114 words)


 ቤስጳስያን (ሮማይስጥ፦ Titus Flavius Vespasianus /ቲቱስ ፍላዊዩስ ዌስፓሲያኑስ/) (ከ2 ዓ.ም. እስከ 71 ዓ.ም. የኖሩ) ከታህሳስ ወር 62 ዓ.ም. እስከ 71 ዓ.ም. የነገሡ የሮሜ መንግሥት ቄሣር ነበረ።

በ60 ዓ.ም. ሰዶማዊው ቄሣር ኔሮን ራሱን ከገደለ ቀጥሎ፣ የሮሜ መንግሥት በብሔራዊ ጦርነት ተያዘ። በየክፍላገሩ ሠራዊቶቹ የወደዱትን አለቃ ሾመው፣ በ1 አመት ብቻ ውስጥ የሮሜ ሴናት (ሕግ አዋሳኝ ቤት) በ4 ልዩ ልዩ ነገሥታት ላይ ዘውዱን ለመጫን ተገደደ። ይህ «የአራቱ ቄሣሮች ዓመት» ይባላል። ከነዚህም፣ መጀመርያ 3ቱ ጋልባ፣ ኦቶ እና ቬቴሊውስ ሁላቸው ሰዶማውያን አለቆች ነበሩ። በመጨረቫ ግን አንድ ቀና አለቃ ቤስጳስያን አሸነፈና ከዚያ ጀምሮ ነገሠ። 

እነዚህ ነገሥታት ሁላቸው በጣም ጨካኝ አለቆች ነበሩ። ቤስጳስያን ደግሞ ኢየሩሳሌምንና መቅደሱን በልጁ ቲቱስ እጅ በማጥፋቱ ይታወቃል። በተለይ ስለ ዳዊት የሆነ አንድ ትንቢት ፈርቶ የዳዊትን ልጆች በየአገሩ አሳደዳቸው።




#Article 293: ኡሩካጊና (115 words)


ኡሩካጊና (ሱመርኛ፦ 𒌷𒅗𒄀𒈾፤ ወይም ኡሩ-ኢኒም-ጊና? 2102-2095 ዓክልበ. ገደማ የነገሠ) በሱመር ውስጥ የላጋሽ ከተማ ገዢ ንጉስ ነበረ። የሉጋላንዳ መረን ግዛት በወደቀ ጊዜ፣ ኡሩካጊና በላጋሽ ንጉስ ሆነ።

ኡሩካጊና ያዋጀው ሕገ ፍትሕ (2098 ዓክልበ. ግ.) በታሪካዊ መዝገብ እስከምናውቀው ድረስ መጀመርያው የሕገ መንግሥት ሰነድ ነው። ሰነዱ እራሱ ገና አልተገኘም፤ ነገር ግን ለዜጎቹ አንዳንድ መብት እንደ ፈቀደላቸው ይታወቃል። ለምሳሌ ለመበለትና ለደሀ አደጎች ቀረጥ እንዳስቀረላቸው ድሆችንም ከሃብታሞች አራጣ እንደጠበቃቸው ይታወቃል። ከተማውም ለሞተ ሰው መቃብር ወጪውን ለመክፈል ተገደደ። በተጨማሪ 1 ሚስት ቀድሞ ብዙ ባሎችን የምታገባበትን ልማድ (አእኑስያ ጋብቻን) ከለከለ።

አልፎ አልፎ ኡሩካጊና ከጎረቤት ከተሞቹ ጋር ተዋግቶ በመጨረሻ ግን ለኡሩክ ድል ሆነ። በዚህ ወቅት (2095 ዓክልበ. ግ.) ኡሩክ፣ ላጋሽና ሌሎቹ ከተሞች ሁሉ ለኡማ ገዢ ለሉጋል-ዛገ-ሲ ግዛት ተጨመሩ፤ ይህም በሱመር ሁሉ የገዛ መንግሥት ሆነ።   




#Article 294: ሴይንት ህሊና ደሴት (109 words)


ሴይንት ህሊና (እንግሊዝኛ፦ Saint Helena ወይም ቅድስት ሄሌና) በአትላንቲክ ውቅያኖስ የሚገኝ ደሴትና የእንግሊዝ ቅኝ (ጥገኛ) አገር ነው። ስሙ ስለ ቄሣሩ ቆስጠንጢኖስ ክርስቲያን እናት ሄሌና ተሰየመ። አሁን 4,255 ያህል ሰዎች ይኖሩበታል። ከ 2001 ዓ.ም. በፊት፣ አሰንሸን ደሴት እና ትሪስተን ደ ኩና በሴይንት ህሊና ጥገኝነት ሥር ኖረው ነበር፤ በዚያ ቀን ግን ሦስቱ ግዛቶች በሕግ እኩል ተደርገው የጠቅላላ ግዛቱ ይፋዊ ስም ከ«ሴይንት ህሊናና ጥገኞቿ» ወደ «ሴይንት ህሊና፣ አሰንሽንና ትሪስተን ደ ኩና» ተቀየረ። 

ፖርቱጊዝ በ1494 ዓ.ም. ደሴቱን መጀመርያ ባገኙት ጊዜ አንድ ኗሪ አልነበረበትም። እንግሊዞች በ1651 ዓ.ም. ሰፈሩት። ሴይንት ህሊና ከአኅጉሮች ሁሉ በጣም ሩቅ ሆኖ ለረጅም ጊዜ ለግዞት አገር ይጠቀም ነበር፤ ለምሳሌ ናፖሌዎን ተማርኮ ከ1807 ዓ.ም. እስከ 1813 ዓ.ም. ድረስ ሕይወቱን እዚህ ላይ ጨረሰ። 




#Article 295: ሐምሌ ፩ (192 words)


ሐምሌ ፩ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፩ ኛው ቀን  ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ  ፷፭ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፷፬ ቀናት ይቀራሉ።

፲፱፻፵፪ ዓ/ም  የአሜሪካ ሕብረት ፕሬዚደንት ሃሪ ኤስ ትሩማን በኮርያ ጦርነት ላይ ለተሠማራው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ማሕበር ሠራዊት ጠቅላይ አዛዥ ብለው ጄነራል ዳግላስ ማካርተርን ሰየሙ። በጦርነቱ የኢትዮጵያ ሠራዊት አባላትም በ ማሕበሩ ስር ተሳትፈዋል።

፲፱፻፶፰ ዓ/ም የቡሩንዲው ንጉሥ ምዋምቡትሳ ፬ኛ ባንጊሪሴንግ በልጃቸው በልዑል ቻርልስ ንዲዚ ተገለበጡ።

፲፱፻፸፰ ዓ/ም የቀድሞው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ እና በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የናዚ የጦር መኮንን ነበሩ የተባሉት ኩርት ቫልዳይም የአውስትሪያ ፕሬዚደንት ሆነው የቃለ መሃላ ሥርዐት ፈጸሙ።

፲፱፻፺፭ አንድ መቶ አሥራ ስድስት መንገደኞችን የጫነው የሱዳን አየር መንገድ (Boeing 737-200) አውሮፕላን ፖርት ሱዳን  በአደጋ ሲከሰከስ አንድም የተረፈ ሰው አልነበረም። 
ጥር ፲፯ ቀን ፳፻፪ ዓ/ም ሜዲተራኒያን ባሕር ላይ የሠላሳ አንድ ኢትዮጵያውያን እና የሃምሳ ዘጠኝ ሌላ ዜጎች ሕይወት የጠፋበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ 409 እንደዚሁ የ(Boeing 737-8AS) አውሮፕላን ነበር። 

፲፱፻፺፯ ዓ/ም በስኮትላንድ ግሌን ኢግልስ የተካሄደው የቡድን ስምንት (G8) ስብሰባ ለታዳጊ አገሮች እርዳታ በሃምሳ ቢሊዮን ዶላር ወይም ሃያ ስምንት ነጥብ ስምንት ቢልዮን ፓውንድ ስተርሊንግ ይጨምራል አለ። እንዲሁም ኢትዮጵያን አካቶ፣ ለአሥራ ስምንት የአፍሪቃ ድሀ አገራት ብድራቸውን እንደሚሰርዝ አስታወቀ።




#Article 296: ገደረ (223 words)


ገደረ ወይም ገደራት በግምት ከ3ኛው ክፍለ ዘመን በፊት በአክሱም የነገሰ የኢትዮጵያ ንጉሥ ነበር። የንጉሥ ገደረ ሠራዊት በደቡብ አረብ ስለመዝመቱ የሚናገሩ መረጃዎች ተገኝተዋል። ሆኖም የመንን በቁጥጥሩ ሥር አድርጎ መግዛቱን ለማረጋገጥ አያስችሉም። በሳባ ቋንቋ ተጽፎ በየመን የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ንጉስ ገደረ (ገደራት) ከሂምያር ቤተሰቦች ተቀናቃኝ ከሆነው ሓምዳ አኒድ ባላባት አል-ሃን፣ ናህፋን እና ከልጆቹ ሳይ-ሩውም፣ አውታር፣ እና ያሪም አይመን ጋር ወግኖ እንደነበርና ሆኖም ቆይቶ ወገንተኝነቱን ቀይሮ ከሂምያሮች ጎን እንደተሰለፈ ያመለክታል። የንጉስ ገደረ ዘመቻዎች ውጤቶች ባይታወቁም፡ ከሌላ ጽሑፍ በተገኘው መረጃ መሰረት፤ ናህፋን ወደ ሃበሻት (ሃበሻ) ሠራዊቱን እንዳዘመተና ከገደራት ጋር ባደረገው ውጊያ እንደቀናው መረጃው ይጠቁማል። በዚሁ ተመሳሳይ መረጃ መሰረት፡ የንጉሥ ገደረ ልጅ ባይጃ (በይጋ) በደቡብ አረብ ናይድና ዛፋር በተባሉ ቀጠናዎች ጦርነት ውስጥ እንደተሰለፈና ተሸንፎ ወደ ባሕር ጠረፍ ክልሎቹ እንዳፈገፈገ ያወሳል። የአክሱም ኃይላት ግን ዋዲ ሱርዱድ እና ዋዲ ሣሃም በተባሉት የስሜን የመን የባሕር ማዶ ቀጠናዎች እንቅስቃሴያቸውን ቀጥለው በጉራቲድ ነገስታት ኢልሳራህ ያህዱብ እና ያዚል ባይዪን በኃይል ተገፍተው እስኪለቁ ድረስ በአካባቢው ቆይተዋል። ንጉስ ገደረ በእርግጥ ደቡብ አረብን መግዛቱን የምያረጋግጥ ማረጋገጫ እስካሁን ባይገኝም የአክሱም ሠራዊት በደቡብ የመን ያደረገው ዘምቻና ቆይታ በወቅቱ በኢትዮጵያና በደቡብ አረብ ግዛቶችና ነገስታት መካከል ጠንካራ ግንኙነት እንደነበር ይረጋግጣሉ።

ዓዲ ገለሞ በተባለ በደቡብ ኤርትራ ከሚገኝ ስፍራ በቁፋሮ የተገኘው ከመዳብ በተሰራ ዘንግ ላይ የተገኘው የግዕዝ ጽሑፍ ላይ ገደረ፣ ነጋሲ አክሱም መሆኑን የሚናገር መልዕክት ይዟል። ይህ ንጉስ ገደረ ደቡብ አረብ ከዘመተው ገደረ (ገደራ) ጋር አንድ ስለመሆኑ እስካሁን ማረጋገጫ የለም። በ330 ዓመተ ዓለም አካባቢ በአካባቢው አግዱር የተባለ ንጉሥ ነግሶ እንደነበር ለምሳሌነት ማስቀመጥ ይገባል።




#Article 297: አብርሀም ሊንከን (407 words)


 አብርሀም ሊንከን (እንግሊዝኛ፦ Abraham Lincoln፣ የካቲት ፮ ቀን ፲፰፻፩ ዓ.ም. - ሚያዝያ ፰ ቀን ፲፰፻፶፯ ዓ.ም. ድረስ የኖሩ) ከ፲፰፻፶፫ ዓ.ም. እስከ ፲፰፻፶፯ ዓ.ም. ድረስ ፲፮ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ነበሩ። ፲፰፻፶፯ ዓ.ም. ከአሜሪካ የእርስ በርስ ጦርነት ፍጻሜ በኋላ ጆን ዊልክስ ቡዝ በተባለ ነፍሰ ገዳይ እጅ በጥይት ተመትተው ተገደሉ።

የአብርሀም አባት ማሀይም ገበሬ ቢሆንም፣ አብርሀም ከልጅነት ጀምሮ እራሱን በትጋት ያስተምር ነበር። በ፲፰፻፳፮ ዓ.ም. ለኢሊኖይ ክፍለ ሀገር ምክር ቤት መቀመጫ ተመረጡ። የሕግ ትምህርት በጠንካራ ትጉነት አጥንቶ የሕግ ባለሙያ ሆነ። ከ፲፰፻፳፱ ዓ.ም. ጀምሮ የባርነት ተቃዋሚ ሆነ። ከአፍሪካ የተወሰዱት ጥቁር ሕዝቦች በግብርና መሥራት እንዲገደዱ ትክክለኛ ወይም ጥሩ ሀሣብ አይደለም ብለው አመኑ። ዳሩ ግን በ1834 ብዙ ባርያዎች ባገለገሉበት ቤተሠብ ውስጥ ያደገችውን ሚስታቸውን ሜሪ ቶድን አገቡ። ሜሪ ያለ ባርያዎች ከባልዋ ጋር መኖር ትንሽ የተቸገሩ ቢሆነም ከጊዜ ብዛት ግን ለምደዉ 4 ወንድ ልጆችን በተከተሉት አመታት  ወለዱ።

በ፲፰፻፴፰ ዓ.ም. የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጄምስ ፖልክ በሜክሲኮ ላይ ጦርነት ባደረገ ጊዜ አብርሀም ሊንከን የዚህን ጦርነት ተቃዋሚ ነበሩ። በ፲፰፻፵፮ ዓ.ም. የባርነት ተቃዋሚዎች ወገን ሪፐብሊካን ፓርቲ መሥርተው አብርሀም ከፍተኛ ሚና አጫወቱ። በ፲፰፻፶፪ ዓ.ም. የፕሬዚዳንትነት ምርጫ ዘመቻ፣ እሳቸው የሪፐብሊካን ዕጩ ሆኑ። ምርጫው በተደረገበት ቀን በጥቅምት ፳፰ ቀን ፲፰፻፶፫ ዓ.ም.፣ ሊንከን አሸነፉ። 

ይህም የሆነ የሕዝቡ ብዛት በአገሩ ስሜን እየኖረ የሬፑብሊካን ደጋፊዎች ነበሩ። በስሜኑ ክፍላገሮች ደግሞ፣ ባርነት ከዚህ በፊት ተክለክሎ ነበር። በአሜሪካ ደቡብ በተገኙ ክፍላገሮች ግን ባርነት ገና የተለመደ ከመሆኑ በላይ በጥጥ የተመሠረተው የምጣኔ ሀብታቸው አስፈላጊነት መሰላቸው። ስለዚህ የባርነት ተቃዋሚ ሊንከን ፕሬዚዳንት መሆኑ በደቡብ ያሉት ክፍላገሮች ከአሜሪካ መገንጠላቸው ማለት ነበር። እንዲሁም ከምርጫው ቶሎ ተቀጥሎ ማዕረጉንም እንኳን ገና ሳይይዙ፣ ሳውዝ ካሮላይና በታኅሣሥ ፲፪ ቀን ፲፰፻፶፫ ዓ.ም. መገንጠሏን አወጀች። በጥቂት ጊዜ ውስጥ ሌሎች የደቡብ ክፍላገሮች እንዲህ አዋጁና በጥር ፳፭ ቀን ቴክሳስ ፯ኛው ሆነ። ከዚያ ቀጥሎ እነዚህ ፯ ክፍላገሮች በሞንትጎመሪ፣ አላባማ ተባብረው አዲሱ መንግሥት የአሜሪካ ኮንፌዴራት ክፍላገሮች (CSA) ተባሉ። በየካቲት ፳፮ ቀን ሊንከን የፕሬዚዳንትነቱን ማዕረግ በተቀበሉበት ቀን አገሩ በተግባር በሁለት ተከፋፍሎ ነበር። የደቡብ ፕሬዚዳንት ጄፈርሰን ዴቪስ ሆኑ። የደቡብ ክፍላገሮች ለጦርነት ተዘጋጁና ምሽጎች ከUSA ሠራዊት ሊይዙ ጀመር። በሚያዝያ ፭ ቀን ፎርት ሰምተር ምሽግ በሳውስ ካሮላይና በግፍ ስለ ተያዘ ጦርነቱ ጀመረ። ስለዚህ ሊንከን ከስሜኑ ፸፭ ሺ ሰዎች ለዘመቻ ጠሩ። ከዚህ በኋላ ሌላ አራት ደቡብ ክፍላገሮች ተገንጥለው ለCSA ተጨመሩ። የደቡብ ዋና ከተማ ለዋሺንግተን ዲሲ ቅርብ ወደ ሆነው ወደ ሪችሞንድ፣ ቪርጂንያ ተዛወረ። 

በጦርነቱ የስሜን ሠራዊት ከብዛታቸው የተነሣ በአራት ዓመት ውስጥ አሸነፉ። በዚህ ጊዜ ላይ ሊንከን ለአመጸኖቹ ባርዮች ነጻነት አዋጁ። ያላመጹ ዜጎች ባርያዎች ግን በዚያን ጊዜ ነጻ አልወጡም። በ፲፰፻፶፮ዓ.ም.ምርጫ ሊንከን በቀላል ለሁለተኛ ጊዜ ለፕሬዚዳንትነት ተመረጡ። በሚያዝያ ፪ ቀን ፲፰፻፶፯ ዓ.ም. የኮንፌደራት ሠራዊት እጁን ሰጠ። ነገር ግን ሚያዝያ ፯ ቀን የመድረክ ትርዒት ሲያዩ በነፍሰ ገዳዩ በጆን ዊልክስ ቡዝ እጅ በጥይት ተመትተው በማግሥቱ ሞቱ። ከዚህም ትንሽ በኋላ ባርነት በሕግ በሙሉ ተክለክሎ የተረፉት ባርያዎች ነጻነት አገኙ።




#Article 298: ጥቅማዊነት (128 words)


ጥቅማዊነት (እንግሊዝኛ፦ Utilitarianism /ዩቲሊቴሪየኒዝም/) በፍልስፍና ስለ ድርጊት ትክክለኛነት የሚሰፍን ግብረ-ገባዊ ኅልዮ ነው። ከሁሉ የሚሻለው ድርጊት ለአብዛኛዎቹ ደስታ ወይም ጥቅም የሚያመጣው ያው ነው የሚለው ፍልስፍና ነው። 

ጽንሰ ሃሣቡ በግሪኩ ፈላስፋ በኤጲቁሮስ ጽሑፍ ይገኛል። መርኁ ከጥንት ጀምሮ ቢታወቅም፣ በቅርቡ ዘመን ስለ ጥቅማዊነት በተለይ የጻፉት ፈላስፎች እንግሊዞች ጄርሚ ቤንታም እና ጆን ስቱዋርት ሚል ነበሩ። ቤንታም እንደ ጻፈው የተሻለው ሥራ ለብዛቱ በጎ የሚሆነው ነው። በሱ ፍልስፍና አስተያየት ሰዎች ሁሉ ለ'2 ጌቶች' እነርሱም ለደስታና ለሀዘን ሲገዙ ይኖራሉ። ስለዚህ ለሰዎች በጎ የሆነ ሥራ ማለት ደስታን ማምጣትና ማብዛት እንደ ሆነ ገመተ። አንዱ ድርጊት ለጥቂቶች ደስ ቢያስን፣ ሁለተኛውም ለብዙዎች ደስ ቢያሰኝ፣ ሁለተኛው ይመረጣል ማለት ነው። ወይም እንደገና አንዱ ድርጊት ለ10 ሰዎች፣ ሁለተኛውም ለ5 ሰዎች ብቻ ደስታ ወይም ጥቅም ካመጣ፣ መጀመርያው የበለጠው ግብረገብ ነው ብሎአል። የቤንታም ደቀ መዝሙር ጆን ስቱዋርት ሚል 'ዩቲሊቴሪያኒዝም' በሚል መጽሐፍ ለፍልስፍናው ስሙን አወረሰ።




#Article 299: አስራት ወልደየስ (1196 words)


ፕሮፈሰር አስራት ወልደየስ አዲስ አበባ ተወልደው ድሬዳዋ ያደጉ ሲሆኑ፣ ለመጀመርያ ጊዜ ፕሮፌስናል ስልጠና ያገኙ የመጀመርያው ኢትዮጵያዊ ቀዶ ጠጋኝ ነበሩ።  

ፕሮፌሰር አስራት ወያኔ ስልጣን በያዘ ጊዜ የወያኔ ተቃዋሚ በመሆን መአሀድ የመላው አማራ ሕዝብ ድርጅት መስራችና ዋና ሊቀመንብር በመሆን ታላቅ የወያኔ ተቃዋሚ ሲሆኑ ወያኔም በፍረሀት ወደ እስርቤት ካስገባቸው በሗላ  በሰሜን ሸዋ ደብረ ብርሀን፣ ጅሩ እነዋሪ፣ መንዝ፣ ተጉለትና ቡልጋ፣ አውራጃ ውስጥ እንዲሁም በመላው የአማራ ክልል የፕሮፌሰር አስራት ተከታዮች በማለት በጣም ብዙ ሕዝብ ጨፍጭፏል። 
በአሁን ሰዓትም የአማራ ብሔርተኝነት በፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ የመንፈስ ልጅነት እየተመራ ይገኛል፡፡

በመጀመሪያ ትክክል ነበሩ በኇላ አበላሹት::

ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ እና የአማራ ህዝብ ትግል!!!!!

ወንጀል አይሆንም ወይ ወገኑ ነኝ ማለት
ሀይሉ( ገሞራው)
ማሳሰቢያ

ይህ ፅሁፍ ከተፃፈ አራት አመት አልፎታል ፡፡ ነገር ግን በየአመቱ የጓደኞቼ ብዛት
ስለሚጨምር ለአዲሶቹ አባላት የተወሰነ ስለ አባታችን ፕሮፌሰር አስራት
ወልደየስ መረጃ ለመስጠት ያህል ሲሆን በዛውም የሙት አመታቸውን
ለማስታወስ ያህል ነው፡፡ ሌላው ፅሁፉን ምስጋናው አንዷለም ( መለክ ሀራ) እኔን
አስፈቅዶ  የሚለው መፅሀፉ ውስጥ አካቶታል፡፡ ግዮናዊነት
ሊወጣ ሲል ምስገጋናው ፅሁፉን በደንብ አጎልብተው እያለኝ እኔም በግሌ ከ 9-

እየፃፍኩ በነበረበት ሰአት ስለነበረ ተደራረበብኝና ትንሽ ተዘናጋሁ መፅሀፉ ሲወጣ
ግን ህዝቡም ሲወደው የተሻለ ባበረክት ኑሮ ብዬ ተቆጨሁ፡፡ ነገሩን ነው እንጂ
አሁን ላይ በጋሻው መርሻ የተፃፈ  የተባለ የፕሮፌሰር
አስራትን ትግል የሚዳስስ መፅሀፍ ስላለ አንባቢዎች በጥልቀት ያንን ቢያነቡ ስል
እመክራለሁ፡፡

እውቁ የቀዶ ጥገና መምህር ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ሀምሌ 11 1920ዓ.ም
በአዲስ አበባ የተወለዱ ሲሆን፤ በሶስት አመታቸው ቤተሰቡ በሙሉ ወደ ድሬደዋ
በመዛወሩ እድገታቸው ድሬደዋ ሊሆን ችሏል፡፡ ጣልያን ኢትዮጲያን ሲወር ገና የ8
አመት ልጅ ቢሆኑም የወረራው ወቅት ግን ለብላቴናው አስራት መጥፎ ትዝታን
ጥሎ ያለፈ ነበር:: ገና በመጀመሪያ አመት ላይ ፋሽስት ጣሊያን አያታቸውን ቀኝ
አዝማች ፅጌ ወረደን ወደ ጣልያን በምርኮ የወሰዳቸው ሲሆን፣ የ1932ቱን
የግራዚያኒ ግድያ ሙከራ ተከትሎ ከ30,000 በላይ ኢትዮጲያዊ ሲያልቁ
አባታቸው አቶ ወልደየስ አጥላየ አንዱ መስዋዕት ሆኑ፡፡ ይህንን ተከትሎም
በባላቸው ሀዘን ከፍተኛ ህመም ላይ የወደቁት እናታቸው ወዲያውኑ ሞቱባቸው፡፡

በ1933ዓ.ም ኢትዮጲያ ከጣሊያን ነፃ ስትወጣ ወደ አዲስ አበባ የመጡት
አስራት ወልደየስ በሚቀጥለው አመት ማለትም በ1934ዓ.ም በተፈሪ መኮንን
ት.ቤት ዘመናዊ የቀለም ትምህርት ጀምረዋል፡፡ በትምህርት ላይ ጥሩ አቀባበል
የነበበራቸው ይህ ምሁር በ1935ዓ.ም የፎቶ ካሜራ ተሸልመዋል፡፡ በኀላም
ከ42ቱ ምርጥ ተማሪዎች አንዱ ሆነው የውጭ የመማር እድል አግኝተዋል፡፡
በግብፅ አሌክሳንደሪያ ቪክቶሪያ ኮሌጅ በ1948ዓ.ም በቀዶ ጥገና ሙያ በጥሩ
ነጥብ ተመርቀው የወጡት ፕሮፌሰር አስራት ወደ ሌላ ለገር ለመሄድ ወለም
ዘለም ሳይሉ ደሀውን ወገናቸውን ሊያገለግሉ ወደ ሀገራቸው መጥተዋል፡፡
ለተከታታይ አምስት አመታት ህዝቡን ሲያገለግሉ ቆይተው ወደ እስኮትላንዱ
Edinburgh University specialized ለማድረግ ተመልሰው ሄደዋል፡፡
ትምህርታቸውን እንደጨረሱ ሀገር ቤት ከረጅም ግዜ ልፋት በኀላ የሙያ
አጋሮቻቸው ጋር በመሆን የመጀመሪያውን የህክምና ት.ቤት አቋቁመዋል፡፡
በሙያቸው መምህር፣ ሀኪምና የት.ቤቱ ዲን ሆነው ደሀውን ህዝባቸውን
አገልግለዋል፡፡ ለዚህም እስከ ንጉሱ የግል ሀኪምነት ድረስ ደርሰዋል፡፡

ወታደራዊው መንግስት ስልጣን እንደያዘ ንጉሱን ገሎ ለህዝብ የሰጠውን
መግለጫ professor John H. spencer ' Ethiopia at bay' በሚል
መፅለፋቸው ሁኔታውን ሲገልፁት፦  The Dergue announced that Haile
selassie has been found dead in bed and that it had
immediately summoned the former Emperor's physician Dr.
Asrat woldeyes with considerable courage, the doctor publicly
denied any such summons. He has been at home all day and
no such call ever reach him. ይህም ማለት በግርድፉ (ደርግ ንጉሱን
ገሎ ለህዝብ በሰጠው መግለጫ  ሲል ፕሮፌሰሩ ግን  ሲሉ ንግግሩን ተቃውመዋል)

በዚህ የተጀመረው ግንኙነት በኀላም የደርግ ካድሬዎች የህክምና ት.ቤቱ ላይ
ሊያሳርፉት በሚሞክሩት የሶሻሊስት ፅንሰ ሀሳብ በተደጋጋሚ ፕሮፌሰሩ ጋር
ሳያስማማቸው ኖሯል፡፡ ይህም ሆኖ ግን በ1970ወቹ መጀመሪያ አካባቢ ከሰሜን
ተገንጣዮች ጋር ያደርገው የነበረው ፍልሚያ ላይ ፕሮፌሰር አሰራት ሙያዊ
ግዴታቸውን ለመወጣት ወደ ቦታው አቅንተው ነበር፡፡

ምሁር በአይኔ አልይ የሚለው ይህ መንግስት ገና ከጅማሮው ነበር ፕሮፌሰሩሠ
ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ የጀመረው፡፡ በወቅቱ በመንግስት ቁጥጥር ስር
ይታተሙ በነበሩ ጋዜጦች( እፎይታ፣ ማለዳ፣ አዲስ ዘመን፣ አቢዮታዊ
ዲሞክራሲ...) ፕሮፌሰሩ ከደርግ ጋር ሆነው እንደወጉት አድርገው መፃፍ ጀመሩ፤
በወቅቱ ፕሮፌሰሩ ሲጠየቁ ግን፦  እኔ የህዝብ ልጅ ነኝ በሙያየ ከንጉሱ እስከ
መንግስቱ ሀ/ ማርያም ቤተቦች፤ ከድሀ ገበሬ አስከ ወታደር የሙያው ስነምግባር
በሚጠብቅ ሁኔታ አገልግያለሁ። እነሱ እንደሚሉትም ሳይሆን ምፅዋ ላይ
የኢትዮጲያ ወታደር ወይም የተገንጣይ ሳንል አክመናል፡፡ አሁንም ቢሆን እርዳታየ
ካስፈለጋቸው ለእነሱም ለማገልገል ችግር የለብኝም፡፡ ነበር ያሉት፡፡

ፕሮፌሰር አስራትን ለየት የሚያደርጋቸው ስብእና በሙያው እንዳሉ ሌሎች
አጋሮቻቸው፤ የራሳቸው የግል ህክምና ተቋም ገንብተው ገንዘብ ለመሰብሰብ
አንድም ቀን ያልሞከሩ ሲሆን፤ ህይወታቸውን በሙሉ ለህዝብ ችግር አሳልፈው
የሰጡ ነበሩ፡፡

እዚሀህ ላይ ብዙዎች የሚጠይቁት ጥያቄ ዋናው ይህ ትልቅ ምሁር እንዴት ወደ
ዘር ፖለቲካ ሊገቡ ቻሉ? የሚለው ነው። ለዚህም ራሳቸውን ጨምሮ ብዙ
ፀሀፊዎች እንደሚያስቀምጡት የተለያዩ ምክንያተቶች አሉ ከእነሱም ውስጥ፦

ሀ. በሰኔ መጨረሻ 1983ዓ.ም በአውሮፓውያን እና አሜሪካ አቀናባሪነት
የተደረገው national peace conference ፕሮፌሰሩ አዲስ አበባ
ዩኒቨርስቲ ወክሎ የታደመው ቡድን አባል ሆነው ተሰብስበው ነበር፡፡ በዚህ
ስብሰባ ላይ የተለያዩ ዘሮችን የወከሉ ቡድኖች ሲኖሩ በህዝብብዛቱ ሁለተኛ
የሆነውን አማራን የወከለው ቡድን የለም ነበር፡፡ የስብሰባው ዋነኛ አጀንዳም
'ስለተጨቆኑ ብሄር ብሄረሰቦች ...ምናምን ' ሲሆን ጨቋኝ ሆኖ የቀረበው ቡድን
ደግሞ አማራው ነበር፡፡ ይህ ነገር መንግስት በሚቆጣጠራቸው ሚዲያ ሳይቀር
አማራው ደርግና የአፄው ስርአት ላጠፉት ጥፋቶች ሁሉ እንደ ዋና ባለቤት ተደርጎ
ተወሰደ፤ ቋንቋው ቆሻሻ ቋንቋ/ dirty language/ ወይም እንደ ኦነግ አጠራር
( Afan Ajawa) ተብሎ ይጠራ ጀመር፡፡ በግልፅም የመንግስት አካል የነበረው
የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስተር ታምራት ላይኔ ሳይቀር ኤርትራ ሄዶ በአማራው ስም

ይቅርታ እጠይቃለሁ የሚል ሰንፋጭ ንግግር አድርጎ መጣ፡፡ ይህ ሁሉ በሬ
ወለደ ፕሮፓጋንዳ ፍሬ አፍርቶ ወደ ተግባር ተለወጠ፡፡

ለ. ይህንን የቃላት ጦርነት ወደ ተግባር ለመለወጥ ሁለም ታጣቂ ሀይሎች
ተንቀሳቅሰዋል፡፡ ኦነግ፣ ኦህዲድ/ ኢህአዲግ/... በበደኖ 154 ሰው፣ ጊራዋ፣
ኩርፋ ጨሌ፣ ለንጋ፣ ኬርሳ፣ ሶካ፣ ደደር፣ ሂርና፣ ቁኒ፣ መስላ፣ ጋሊቲ፣ ደባ የቸባሉ
አካባቢዎች ከ 1000 ሰው በላይ፤ አርባ ጉጉ ላይ ከሞተው ውጭ ከ32,000
በላይ ሰው ከመኖሪያው ተፈናቅሏል ፡፡ አርሲ ነገሌ 60 ሰው፣ ወለጋ ከ200 ሰው
በላይ እንደ ዱር እንስሳ ታድነው ተገለዋል፡፡ ይህ ከብዘ በጥቂቱ ነው፡፡ ሴቶችን
መድፈር፣ ፅንሳቸውንን በጩቤ እያወጡ ማሳየት ዋና መዝናኛቸው ነበር፡፡ ይህ
ሁላ ሲሆን ወያኔ/ህወሀት/ ዳር ቆሞ ለኦነግ እና ሌሎቸች መሳሪያ እያስታጠቀ
ያልታጠቁ ንፁህ ገበሬ አማሮችን አስጨፈጨፈ። የሚገርመው በቀደመ ስሙ
ኢህዲን የጥምቀት ስሙ ብአዲን የሚባለው ድኩማን ድርጅት ይህ ሁሉ
ጭፍጨፋ ሲካሄድ አንድም ተቃውሞ አላደረገም፡፡ ከበአዲን ይልቅ # የኢሳ_
ሶማሌ_ጎሳዎች ለመንግስት ባስገቡት ደብዳቤ እንደገለፁት ይህ በኦነግ እና
ኦህዲድ አማካኝነት የሚደረግ ንፁሀን ጭፍጨፋ ማስቆም ካልቻላችሁ እኛ
ጣልቃ ገብተን እናስቆማለን የሚል የወንድማዊ እና ታሪክ የማይረሳው ስራ
ሰርተውልናል፡፡

እንግዲህ ከላይ የጠቀስናቸው ምክንያቶች እና ሌሎችም ተጨምረው ናቸው
ፕሮፌሰሩን መአህድን ጥር ወር 1984ዓ.ም ሊያቋቁሙ ያስቻላቸው፡፡ መአህድ
( መላው አማራ ህዝባዊ ድርጅት) ገና ከጅማሮው በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች
ፅህፈት ቤት የከፈተ ሲሆን፡፡ በተለያየ መንገድ ተፅዕኖ ማድረግ ጀመረ፡፡ በህዳር
ወር 1985ዓ.ም ደብረ ብርሃን ላይ ያደረገው ህዝባዊ ስብሰባ ድርጅቱን
በመንግስት ደህንነቶች ክትትል ስር እንዳይወጣ አደረገው፡፡ መአህድን እንደፈሩት
የሚያስታውቀው በወቅቱ የመከላከያ ሚኒስተር የነበሩት አቶ ስየ አብርሃ
የድርጅታቸው ስብሰባ ላይ፦

declaration from abroad. Concentrat on the biggest challenge
at home i.e Professor Asrat. If we under the dergue
had got the chance which Professor Asrat enjoys today in
organizing and mobilizing his AAPO( መአህድ ) followers, it
would not have take us 17 years long to topple the Mengistu
regime ....ይህ የሚያመለክተው ወያኔ መአህድን ምን ያህል ፈርቶት እንደነበረ
ነው፡፡ ከመስከረም እስከ ሀምሌ 1985ዓ.ም ብቻ ከ40 በላይ የመአህድ
ማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ታስረዋል፡፡

ፕሮፌሰር አስራት ከአርባ አንዱ የዩኒቨርስቲ መምህሮች ጋር 'በአቅም ማነስ'
በሚል ፖለቲካዊ ስም ማጥፋት ታርጋ በገነት ዘውዴ በሚመራው ትምህርት
ሚኒስተር ተባረዋል፡፡ ይህ እንግዲህ የሚሆነው ከ Edinburgh university
የተመረቁትን ምሁር በደደቢት በረሀ ምሩቃን መሆኑ ነው፡፡

በ1986ዓ.ም መንግስታዊው ጁንታ እውቁን ምሁር ደብረ ብርሃን ስብሰባ ላይ
ባደረጉት ንግግር አማካኝነት  መንግስትን በሀይል ለመገልበጥ አሲረዋል ሲል
ሁለት አመት ፈረደባቸው፡፡ እዛው እስር ላይ እያሉ በ1988ዓ.ም እንደገና በሌላ
ክስ ሶስት አመት ጨመረባቸው፡፡ ይህ ሁሉ የሚሆነው ከ65 አመት በላይ የነበሩ
አዛውንት ላይ ነበር፡፡ ፕሮፌሰር ከዚህ አመት በኀላ ግን ጤና አጡ በተከታታይም
ሀኪሞች የውጭ ህክምና ያስፈልጋቸዋል ቢባልም መንግስት ሊቀበል
አልቻለም፡፡ በመጨረሻ ከተዳከሙ በኀላ በታህሳስ ወር 1991ዓ.ም ወደ ውጭ
እንዲሄዱ ቢፈቀድም በጣም ተዳክመው ስለነበር ከ5 ወር በኀላ ግንቦት 6

የዚህ ፅሁፍ ባለቤት ከተለያየ ቦታ የጨመቀውን ይችን ፅሁፍ የፃፈው አንድም
ታላቁን መምህር ለማስታወስ ነው፡፡ ሌላው የአሁኑ ትውልድ ከዚህ ምን
ይማራል? የሚለውን ሁሉም በየቤቱ እንዲያስብበት ነው ፡፡ በተጨማሪም

አማራዊነት ማሰብ ተመርጦ የሚገባበት ጉዳይ ሳይሆን ከመገፋት፣ ከጭቆና
የሚመጣ መሆኑን ለማጠየቅ ነው፡፡




#Article 300: ካዲዝ (235 words)


ካዲዝ (እስፓንኛ፦ Cádiz) በደቡብ እስፓንያ የሚገኝ ጥንታዊ ከተማ ነው። የካዲዝ ክፍላገር መቀመጫ ሲሆን 130፣000 ያህል ሰዎች ይኖሩበታል። በአካባቢው ዙሪያ 500፣000 ሰዎች አሉ። 

ይህ ከተማ ምናልባት ለጥንታዊነት በአውሮፓ ከሁሉ የላቀ ይሆናል። የተመሠረተው በፊንቄ (ከነዓን) ሰዎች ሲሆን፣ በ1112 ዓ.ክ.ል.በ. እንደ ሆነ የሚል ልማድ አለ። 

በከነዓን ቋንቋ ስሙን «ጋዲር» (גדר ማለት ግምብ፣ ግድግዳ) አሉት። በኋላ ዘመን ግሪኮች ይህን ወደ Γάδειρα /ጋዲራ/፣ /ጋዴራ/ ቀየሩት። በሮማይስጥም ስሙ Gades /ጋዴስ/ ተብሎ በአረብኛ ደግሞ ይህ قادس /ቃዲስ/ ሆነ። 

የጥንቱ ጋዲር ለፊንቄ ነጋዴዎች ከታርቴሶስ (ተርሴስ) ጋር ሲነግዱ እንደ ንግድ ጣቢያ ይጠቅማቸው ነበር። ከዚህ በላይ መጽሐፈ ኩፋሌ ምዕ. 9 የቦታውን ጥንታዊነት ይመሠክራል። በአማርኛ ትርጉም በ9፡11፣ 13 («ጋዴት» በሚል አጻጻፍ)፣ እና 25 («ጋዲር» ተጽፎ) መሠረት ሥፍራው በካም ርስትና በያፌት ርስት መካከል ያለው ጠረፍ የሚወስን ነው። ይህ ማለት ቅርብ የሆነውና በአፍሪካና በአውሮፓ መካከል የሚገኘው የጂብራልታር ወሽመጥ ሳይሆን አይቀርም። 

የፊንቄ ጣኦት 'መልቃርት' በዚህ ከተማ ትልቅ ቤተ መቅደስ ነበረው። በግሪኮች አስተያየት የመልቃርት መታወቂያ ከጀግናው ሄራክሌስ ጋር አንድላይ ነበር፤ ይህ ሄራክሌስም የጋዲራ መስራች መሆኑን አመኑ። በዚህም ቤተ መቅደስ ውስጥ ሁለት ግዙፍና ታላላቅ የነሐስ ዓምዶች ይገኙ ነበር። እነኚህ ዓምዶች 'የሄራክሌስ ዓምዶች' እንደ ነበሩ በሰፊ ይታመን ነበር። 

በ500 ዓክልበ. ገደማ ከተማው ለቃርጣግና ግዛት ወደቀ። ሃኒባል ከዚህ ደቡብ እስፓንያ ዘመቻ ያድርግ ነበር። በ213 ዓክልበ. ግን ከተማው ለሮማ መንግሥት ሠራዊት ወደቀ። 'ጋዴስ' ተብሎ ትልቅ ከተማ ሆነ። በ5ኛው ክፍለ ዘመን ዓ.ም. ጀርመናዊው ሕዝብ ዊዚጎቶች በወረሩ ጊዜ በጥንታዊ ሕንጻዎች ላይ ብዙ ጥፋት አደረጉ። በ704 ዓ.ም. እስላሞች ያዙትና ስሙን 'ቃዲስ' አሉት። ዘመናዊ ስም 'ካዲዝ' ከዚህ የወጣ ነው። በመጨረሻ በ1254 ዓ.ም. የካስቲል ንጉሥ 10ኛ አልፎንሶ እስላሞቹን አስወጣቸው።




#Article 301: ሦስቱ እኅትማማች (127 words)


በአዚሁ ዘዴ አስቀድሞ ብዙ ትንንሽ የአፈር ቁልል ይደረጋል። የእያንዳንዱ ቁልል ከፍታ 30 ሴንቲ ሜትር ሲሆን ስፋቱ 50 ሴንቲ ሜትር ይሆናል። በመሃሉ አያሌ የበቆሎ ዘር አንድላይ ይጨመራል።   በአንዳንድ ጎሣ ልማድ ደግሞ፣ ማዳበሪያ እንዲሆን የበሰበሰ ዓሣ ከዘሩ ጋር ይቀበራል። 

የበቆሎው ቁመት እስከ 15 ሴንቲ ሜትር ድረስ ሲወጣ፣ ባቄላውና ዱባው በመፈራረቅ እንዲከብቡት ይዘራሉ። 

እነዚህ ሦስት ሰብሎች በመጠቃቀም ይተባበራሉ። በቆሎው ለባቄላው መንጠላጠል የሚችል መዋቅር ስለሚሰጥ፣ ምሰሶ ማቆም አያስፈልግም። ባቄላውም ለሌሎቹ አትክልት በጣም አስፈላጊ የሆነውን ናይትሮጀን ወደ መሬት ለመጨመር ልዩ ችሎታ አለው። ዱባውም በመሬት ገጽ ላይ እጅግ ሲስፋፋ፣ መዓልቱን በመሸፈኑ አረምን ይከላከላል፤ እንዲሁም ሀረጉ ትንሽ እሾህ የመሰለውን ጸጉር ስላለው የሚጎዱ ነፍሳት ይከለከላል፤ ከዚህም በላይ የዱባ ቅጠል እርጥበት በመጠበቁ እንደ ማዳበሪያ ያገልግላል።   

ሦስቱ ተክሎች ስለዚህ በጣም የሚስማሙ በመሆናቸው የበለጠ መልካም ምርት ሊያስገኙ ይቻላል። ይህ ዘዴ በሰፊ እርሻ ወይም ገነት ላይ ሲጠቀም ሚልፓ ይባላል።




#Article 302: 5ኛው አብጋር (314 words)


በአንድ ጥንታዊ ትውፊት መሠረት፣ እሳቸው መጀመርያው ክርስቲያን የሆኑ ንጉሥ ነበሩ። ከኢየሱስ 72 ደቀ መዛሙርት አንዱ ታዴዎስ (ወይም ዓዳይ) እንዳጠመቋቸው ያባላል።

የቤተ ክርስቲያን ጳጳስና የታሪክ ጸሐፊ አውሳብዮስ በ317 ዓ.ም. ገዳማ በጻፉት ታሪክ ዘንድ፣ ኢየሱስ በሕይወቱ ስብከት ሳለ፣ የጎረቤት አገር ንጉሥ አብጋር ከበሽታ ታምመውና ስለ ኢየሱስ ተአምራዊ ዝና ሰምተው፣ ኢየሱስ መጥቶ እንዲፈውሳቸው አንድን መልእክተኛ (ሐናን) ወደ ኢየሩሳሌም ልከው ነበር። በዚሁ ደብዳቤ ንጉሡ በኢየሱስ መለኰታዊነት አምነው ረድኤቱን ይለምኑና በቤተ መንግሥታቸው መጠጊያ እንዲያገኝ ይጠይቁታል። ኢየሱስ ወደ ኤደሣ ለመሔድ ጊዜ ስላልነበረው፣ መልሱን በሐናን እጅ ወደ ንጉሡ ላከ። በመልሱም እየሱስ ከዐረገ በኋላ አንድ ሃዋርያ እንዲልክላቸው የሚል ቃል ሰጣቸው።

አውሳብዮስ ሁለቱን መልእክቶች በኤደሣ ሰነዶች ቤተ መዛግብት አንዳገኙ ብለዋልና በጽሕፈታቸው ውስጥ አሳተማቸው። የደብዳቤዎች ጽሑፍ እንዲህ ይላል፦

በአውሳብዮስ ታሪክ ከዚህ ትንሽ በኋላ በ21 ዓ.ም. ሀዋርያው ቶማስ ታዴዎስን («ዓዳይ» የተባለውን) ወደ ንጉሡ እንዲያጠምቋቸው ላከው። በአውሳብዮስ ዘመን የኖሩ ኤፍሬም ሶርያዊ ደግሞ ስለዚሁ ታሪክ ጽፈዋል። 

በ350 ዓ.ም. ገዳማ ትምህርተ ዓዳይ በጽርዕ (የሶርያ ቋንቋ) ታተመ። ይህ መጽሐፍ ተጨማሪ መረጃ አቀረበ፦ የእየሱስ ደብዳቤ ከመያዙ በላይ ይህ ሐናን የኢየሱስን ስዕል እንደ ሠራ ይህም ስዕል እስከዚያው ቀን ድረስ ቆይቶ በኤደሣ ቤተ ክርስቲያን እንደ ተጠበቀ አወራው። በዚሁ መጽሐፍ ዘንድ የሆነበት አመት 24 ዓ.ም. ነበረ። የአርመን ታሪክ ጸሐፊ ሙሴ ቆረናጺ (450 ዓ.ም. ያህል) እንዲህም አይነት ታሪክ ይናገራሉ።

በ487 ዓ.ም. ግን የሮማ ፓፓ 1ኛ ገላስዮስ በጉባኤ ደብዳቤዎቹን 'የማይቀበሉ ጽሑፎች' አሏቸው። ሆኖም በሶርያ ቤተ ክርስቲያን እስካሁን በጣም የሚከብሩ ናቸው።

በ550 ዓ.ም. ያህል የኤደሣ ጳጳስ ኤዋግርዮስ እንደ ገለጹት ደግሞ ይህ የኢየሱስ ስዕል እንዲያውም በሐናን የተፈጠረው ሳይሆን፣ ኢየሱስ እራሱ መልኩን በተአምር በጨርቅ ላይ ያሳተመው እንጂ 'ያለ እጅ የተሠራ' ተብሏል። ይህ ቅዱስ ስዕል አሁን ያለበት ቦታ በእርግጥ ባይታወቅም፣ በአውሮፓ አብያተ ክርስትያናት ውስጥ አንዳንድ ስዕል ለምሳሌ የጄኖቫ ቅዱስ መልክ ኦሪጂናል ቅጂ እንደሆነ የሚያምኑ አሉ። 

ይህን ታሪክ ወይም ትውፊት የማይቀበሉት ሊቃውንት ግን፤ በኦስሮኤና ኋለኛው ክርስቲያን ንጉሥ በ9ኛው አብጋር ዘመን (200 ዓ.ም. ያህል) በማቃወስ እንደ ተፈጠረ ያስባሉ። 

በምሥራቅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አብጋር ቅዱስ ሆነው ይቆጠራሉ። የግብራቸው ማስታወሻ ዕለታት May 11 እና October 28 ናቸው። በሶርያ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ ቀኑ August 1 ነው። እንዲሁም በአርሜናዊ ሃዋርያዊ ቤተ ክርስቲያን በሁልቀን ቅዳሴ ይከብራሉ። 




#Article 303: ዶን ወንዝ (143 words)


የዶን ወንዝ (ሩስኛ፦ Дон) በሩሲያ የሚገኝ ዋና ወንዝ ነው። መነሻው ኖቮሞስኮቭስክ በሚባለው ከተማ ሲሆን እስከ አዞቭ ባሕር ድረስ የፈስሳል። 

በጥንታዊ ዘመን አገሩ እስኩቴስ በተባለው ጊዜ ግሪኮች ወንዙን «ጣናይስ» አሉት። የግሪክ ነጋዴዎች ጣናይስ የተባለ ቅኝ ከተማም በአፉ መሠረቱ። 

ከ1722 ዓ.ም. አስቀድሞ ይህ ወንዝ የአውሮፓና የእስያ ጥንታዊ ጠረፍ ሆኖ ይቆጠር ነበር። በዚያን አመት የአውሮፓ ጠረፍ እስከ ኡራል ወንዝ እንዲዘረጋ የሚል ሀሣብ ለመጀመርያ ጊዜ ቀረበ። 

በመጽሐፈ ኩፋሌ መሠረት (9፡2፣ 6፣ 13) ከምሥራቁ ጫፍ («ራፋ») ጀምሮ በአዞቭ («ሜአት» ወይም «ሜኦት») ባሕር ወዳለው እስከ አፉ ድረስ፣ ይህ ወንዝ («ጤና ወንዝ» ተብሎ) ከኖኅ ልጆች ከሴምና ከያፌት ርስቶች መካከል የሆነው ጠረፍ ይሠራል። ጠረፉም ከዚያ ከምሥራቁ ጫፍ ቀጥታ ወደ ምሥራቅ ይሄዳል። በኩፋሌ 9፡21 ደግሞ፣ ከምሥራቁ ነጥብ እስከ መነሻው ድረስ ከዚያም ቀጥታ ወደ ስሜን የሆነ መስመር ከያፌት ልጆች ከጋሜርና ከማጎግ ርስቶች መካከል የሆነው ጠረፍ ነበር። ይህ በተለይ በአራማይስጥ ትርጉም ይታያል።

በሀንጋሪ አፈ ታሪክ ዘንድ፣ ወንድማማች ሁኖርና ማጎር በዚህ ሸለቆ አዳኞች ሆነው ኖሩ። 




#Article 304: ብራና መቅደስ (166 words)


ብራና መቅደስ በሙት ባሕር ብራናዎች መኃል አንድ ነው። ይህ ብራና ጥቅል በ1948 ዓ.ም. በዋሻ ቢገኝም እስከ 1959 ዓ.ም. ድረስ በሊቃውንት አልተተረጎመም ነበር። የተጻፈው በዕብራይስጥ ሲሆን ስለቤተ መቅደስ የሚነኩ የእግዚአብሔር ትዕዛዛት ለሙሴ ይከትታል። 

በነዚህ ትእዛዛት የዘላለማዊ ቤተ መቅደስ ዝርዝሮች፣ ሥርዓቶችና ደንቦች ለሙሴ ይገለጻሉ። ሆኖም በታሪክ የእስራኤል ንጉስ ሰሎሞን ቤተ መቅደስ በኢየሩሳሌም በሠሩ ጊዜ፣ አሠራሩ በዚህ አይነት እቅድ አልነበረም። በዚህ ብራና የተገለጸው ቤተ መቅደስ ገና መቸም አልተሠራም። ቤተ መቅደሱ በዚህ የተሰጠው መጠን በነቢዩ ሕዝቅኤል ራዕይ ከታየው ቤተ መቅደስ መጠን ይልቅ ይበልጣል (ትንቢተ ሕዝቅኤል ምዕ. 40-47)። በምዕራብ ሊቃውንት አስተያየት ዘንድ፣ ያልታወቀ ደራሲ፦ «የኢየሩሳሌም መቅደስ እንደ ሰሎሞን መቅደስ ሳይሆን እንዲህ መሆን ነበረበት» የሚል ሀሣብ ለማቅረብ ፈልጎ ነበር።

ብራናው በየዓመቱ ስለሚከበሩ በዓላት ስርዓቶች ይዘረዝራሉ።

መሠረቱ ቅዱስ ስለሚሆን፣ ፈሻሽ ነገር ያለበት ሰው ወደ መቅደሱ ግቢ ሳይገባ ለ7 ቀን በርኩስና መቆየት አለበት። እንዲሁም መቅደሱ ያለበት ከተማ (ዘላለማዊው ኢየሩሳሌም) በሙሉ ቅዱስ ስለሆነ ግብረ ስጋ ግንኙነት በከተማው ውስጥ ይከለክላል። ማንም ባለትዳር ወደ ከተማው ሳይገባ ከሩካቤ ሁሉ 3 ቀን መቆየት አለበት።  ነገር ግን በዚህ ብራና የተጻፉት እነዚህና ብዙ ሌሎች ደንቦች በታሪክ ውስጥ መቸም በተግባር አልታወቁም ነበር።  




#Article 305: ማዴ (291 words)


ማዴ ወይም ማዳይ (ዕብራይስጥ፦ מדי /ማዳይ/፤ ግሪክ፦ Μηδος /ሜዶስ/)  በኦሪት ዘፍጥረት 10 መሠረት የያፌት ልጅና ከኖህ 16 ልጅ ልጆች አንዱ ነው።  

በዮሴፉስና በሌሎች የድሮ ጸሐፊዎች ዘንድ፣ ማዴ በስሜን-ምዕራብ ፋርስ የኖሩት የሜዶን ሰዎች (ወይም «ሜዴስ») አባት ነበረ። በግሪክ «ሜዶን» የተባለው ሕዝብ በአሦርኛና በዕብራይስጥ «ማዳይ» ይባል ነበርና።  እንዲሁም ዛሬ በአካባቢ የሚኖሩት ኩርዶች እስካሁን ከሜዶን ሰዎችና ከማዳይ እንደተወለዱ ይላሉ። ሜዶን ከ700 ዓክልበ. ግድም ጀምሮ ሲታወቅ፣ በአካባቢያቸው የሌሎች ብሔር ስሞች ማቲዬኔ (650-617 ዓክልበ. ግድም)፣ ማናይ (850-650 ዓክልበ. ግድም) እና ሚታኒ (1507-1307 ዓክልበ. ግድም) ደግሞ ከማዴ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው ታሥቧል።

በመጽሐፈ ኩፋሌ ውስጥ ስሙ «ማዳይ» ሲጻፍ፣ የሴምን ልጅ ስለ አገባት በራሱ ርስት (በማጎግና በደሴቶቹ መካከል፣ ወይም ስሜን አውሮፓ፤ 9፡22) ከመኖር ይልቅ በሴም ዘር መካከል መኖር ፈለገ። ስለዚህ የሚስቱን ወንድሞች ኤላም፣ አሦርና አርፋክስድ ለምኖ በመጨረሻ ከሴም ልጆች ርስት መካከል አንድ አገር ተቀበለ።  ይህ አገር ስም በአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ «መቄዶን» ሲጻፍ (10፡21)፣ በጥንታዊ ቅጂዎች (በግሪክ፣ እብራይስጥ፣ አራማይስጥ) ወዘተ) ግን «ሜዶን» ነው። በነዚህ ቅጂዎች «ሜዶን» ደግሞ በ9፡10 ሲጠቀስ ስሙ በአማርኛ ትርጉም «መእዳይ» ሆኖ ይጻፋል። በዘመናት ላይ ቅጂዎችን የሠሩት ካህናት በአንዳንድ ስፍራ የሜዶንና የመቄዶን ስሞች በደንብ አለዩምና።   

በ8፡37 ደግሞ በአማርኛ ትርጉም የአርፋክስድ ልጅ ቃይንም ሚስት የያፌት ልጅ የአበዳይ ልጅ ሜልካ ነበረች ሲለን፣ በድሮ ልሳናት ግን በ«አበዳይ» ፋንታ «ማዳይ» ይላል። በዚህ ትውልድ መሠረት አብርሃም፣ ሰሎሞንና ኢየሱስ ሁላቸው የሴም ወይም የካም ዘር ብቻ ሳይሆን የያፌት ዘር ደግሞ አለባቸው።  

በሊቃውንት ዘንድ የሜዶን ሕዝብ የሕንዳዊ-ኢራናዊ ቋንቋዎች ቤተሠብ አባሎች ነበሩ። ሚታኒ  በጥንት ዘመን ከአራስ ወንዝ ዙሪያ ተነሥቶ ሶርያን የወረረ ሕዝብ ነበረ። በሶርያ ሑርኛ ተለመዱ፤ ስሞቻቸው ግን የሕንዳዊ-ኢራናዊ ቋንቋዎች ዘመዶች እንደነበሩ ይገልጻል። የሜዶን ሰዎች የዞራስተር (ዛራጡሽትራ) ሃይማኖት ተከታዮች ሆነው ከሁሉ ጥንታዊ በሆኑት መጽሐፍታቸው ዘንድ፣ መጀመርያ መኖርያቸው አገር «አይርያነም ቫኤጃህ» ሲባል በአራስ ወንዝ ሸለቆ አካባቢ ተገኘ (ቡንዳሂሽን 29፡12)። ይህ አውራጃ በኋላ አራን ተባለ፤ ከዚህም በላይ ይህ ወንዝ በአራራት ተራራ አጠገብ ይመንጫል።   
 
በተጨማሪ በስሜን በርማ (ምየንማ) በተገኘው ጂንግፖ (ካቺን) ነገድ እምነት ዘንድ፣ እነሱ «ማዳይ» ከተባለ ጥንታዊ ቅድመ-አያት ተወለዱ።




#Article 306: ፖለቲካ (118 words)


ፖለቲካ የሚለው ቃል ከግሪኩ πολιτικος («ዜጋ») ከሚለው ቃል የመጣ ነው። በአሁኑ ወቅት ፖለቲካ ማለት በቡድን ያሉ ግለሰቦች የጋራ ውሳኔ ላይ ለመድረስ የሚያስችላቸው ሂደት ነው። በዚህ ምክንያት ምንም እንኳ ፖለቲካ የሚለው ቃል ብዙ ጊዜ ከሃገርና ከመንግስት ጋር የተገናኘ ቢሆንም በሌላ አንጻር የሰው ልጆች በቡድን ሆነው በሚገኙበት ማናቸውም ስብስብ ይገኛል፣  ለምሳሌ በኩባንያወች፣ በትምህርት ቤቶች፣ በሃይማኖት መዋቅሮች፣ በቤተሰቦች ውስጥ ሳይቀር ፖለቲካ አለ።  የኃይል አመዳደብ፣ የቁጥጥር፣ የውሳኔ ላይ መድረስ፣ የምጣኔ ሃብት ክፍፍል ጥያቄወች በሁለትና ከዚያ በላይ ባሉ ሰወች መካከል ሲነሱ ያንን ጥያቄ ለመፍታት በሚደረግ ሂደት፣ በዚያ ፖለቲካ አለ።  ከዚህ አንጻር በአንዳንዶች አስተሳሰብ አብዮት፣ ጦርነት፣ ማህበረሳባዊ ግጭት ፖለቲካ ሳይሆኑ የፖለቲካ  ሂደቱ ክሽፈት ናቸው። በሌሎች አስተያየት እኒህም የአጠቃላይ ሂደቱ አካል ስለሆኑ እንደ ፖለቲካ ይወሰዳሉ። 

ፖለቲካን የሚያጠናው የትምህርት አይነት የፖለቲካ ሳይንስ ወይም  የፖለቲካ ጥናት ይባላል።




#Article 307: ጋያነሸጎዋ (128 words)


ጋያነሸጎዋ ወይም ካያነረኮዋ («ታላቅ ሕገ ሰላም») የሆደነሾኒ (ኢሮኳ) ኗሪ ብሔሮች የተባበሩበት ሕገ መንግሥት ነው።  በተለመደው ታሪክ ዘንድ፣ በ1100 ዓ.ም. ገደማ አለቃው ደጋናዊዳ በዛሬው ኒው ዮርክ ክፍላገር የሚኖሩትን 5 ብሔሮች በዚህ ሕግ  አባበራቸው። 5ቱ ብሔሮችም በስም ካንየንከሃካ (ሞሃውክ)፣ ኦንዮታአካ (ኦናይዳ)፣ ኦኖኝዳጌጋ (ኦኖንዳጋ)፣ ጋዮጎሆኖ (ካዩጋ)፣ እና ኦኖንዶዋጋ (ሰነካ) ናቸው።  በኋላም በ1706 ዓ.ም. ስድስተኛ ብሔር ተስከሮራ ተጨመረላቸው። 

የአሜሪካ ኗሪዎች ኅብረተሠብ እንደ አውሮፓውያን ኅብረተሠብ ፊዎዳል አገዛዝ ሳይሆን ዴሞክራስያዊ (ሕዝባዊ) ነበረ። ስለዚህ ይህ ሕግ በ1780 ዓ.ም. በተደረገው በአሜሪካ ሕገ መንግሥት ላይ ሰፊ ተጽእኖ ነበረው።  ለዚህም የሚቀርበው ታሪካዊ ሰነድ የላንካስተር ውል (1738 ዓም) ነው። 

ይህ ሕግ የተመዘገበው በተጻፈ ቋንቋ ሳይሆን በዋምፖም (ትንንሽ የዛጎል ዶቃዎች) አማካይነት ይታወስና ይወረስ ነበር። በኋላ ዘመን ነው ወደ እንግሊዝኛ የተተረጎመ። ሕጉ በ117 አንቀጾች ይከፈላል። የተባበሩት ሆደነሾኒ ብሔሮች የጥድ ዛፍ ምሳሌ ናቸው። እያንዳንዱ ጎሣ ወይም ነገድ በመንግሥት አመራር የተወሰነ ሚና ያጫውታል።




#Article 308: ጥላሁን ገሠሠ (358 words)


ክቡር ዶ/ር አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ (መስከረም ፲፯  ቀን ፲፱፻፴፫ እስከ ፳፻፩ ዓ.ም.) ዝነኛ ኢትዮጵያዊ ዘፋኝ ነበር።  

ከእናቱ ከወ/ሮ ጌጤ ጉሩሙ እና ከአባቱ  ከአቶ ገሠሠ ንጉሤ በአዲስ አበባ ልዩ ስሙ ጠመንጃ ያዢ እየተባለ ከሚጠራው  ሰፈር  የመስቀል ዕለት ተወለደ። እድሜው -  ፲፬ ዓመት  እንደሆነ ከአያቱ ጋር እንዲኖር ወደ ወሊሶ ተወሰደ በዚያም በራስ ጎበና በሚባለው አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ትምህርት ጀመረ። ጊዜ እያለፈ ሲሄድ ከፍተኛ የሆነ የሙዚቃ ፍቅር እይሳየ ሄደ ። አያቱ ግን ትኩረቱን በሙሉ በትምህርቱ ላይ እንዲያደርግ ይመክሩት ነበር። የራስ ጎበና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስተዳዳሪ የነበሩት ሱዳናዊው አቶ ሼዳድ  የጥላሁንን የሙዚቃ ፍቅር በማየት ወደ ሱዳን እንዲሄድና በዚያም ሙዚቃ እንዲያጠና ይመክሩት ነበር። ጥላሁን ወደ ሱዳን ባይሄድም ምክራቸውን ግን ትልቅ ቦታ ስጥቶት ነበር። ከሀገር ፍቅር ቲያትር ወ/ሮ ንጋትዋ ከልካይ እና አቶ ኢዮኤል ዮሃንስ ሌሎችም የሃገር ፍቅር ተዋንያን በትምህርት ቤታቸው ትርኢት ሊያሳዩ በመጡ ጊዜ ይህን እድል በመጠቀም ጥላሁን ለሙዚቃ ያለውን ፍቅር ከአቶ ኢዮኤል ጋር ባደረገው ውይይት በሙዚቃ መግፋት ከፈለገ ወደ አዲስ አበባ መሄድ እንዳለበት መከሩት። ጥላሁን  ትምህርቱን አቋርጦ ጉዞውን ወደ አዲስ አበባ አቀና። ኩብለላውን በእግር የጀመረው  ለአያቱ ሳይነግር ስለነበር ከቤት ሲጠፋ አያቱ ለአጎቱ ሁኔታውን በመንገር ጥላሁንን ይጠብቁ ጀመር።  ጥላሁንም የአሥራ አምስት ኪ/ሜ መንገዱን ጨርሶ ቱሉ ቦሎ ደረሰ ከዚያም ከአክስቱ ከወ/ሮ ተመኔ ባንቱ  ቤት አድሮ ወደመጣበት ወደ ወሊሶ አያቱ ዘንድ ተይዞ ተመለሰ ። በሙዚቃ ፍቅር በጣም የተቃጠለው ጥላሁን አያቱ ቤት አንድ ቀን ብቻ በማደር ጉዞውን እንደገና ወደ አዲስ አበባ አቀና በዚህ ጊዜ ግን በጭነት መኪና ላይ በመንጠልጠል ነበር።   
ጥላሁን አዲስ አበባ እንደገባ በሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት ተቀጠረ። በዚያም ጥቂት አመታት ከሰራ በኋላ ወደ ክብር ዘበኛ ባንድ በመቀላቀል ታዋቂና ዝነኛ ለመሆን በቃ።
ሆኖም በ ፲፱፻፶፫ ዓ/ም የታሕሣስ ግርግርትልቅ ችግር ውስጥ ወድቆ ነበር ። ለጥቂት ጊዜም ታስሮ ተፈትቷል። ከዚያም ወደ ቀድሞው ሀገር ፍቅር በመመለስ ተወዳጅና ታዋቂ ለመሆን በቅቷል። ግርማዊ ቀዳማዊ፡ኃይለ፡ሥላሴ ሀገር ፍቅር ቲያትር ቤትን በጎበኙበት ጊዜ ሦስት ጊዜ ወጥቶ ዘፍኗል ንጉሠ ነገሥቱም ጥሩ ድምጽ አለህ፣ እንዳታበላሸው የሚል አስተያየትም እንደሰጡት ይነገራል ።
የጥላሁን ብዙዎቹ ስራዎቹ የአማርኛ ዘፈኖች ሲሆኑ የተወሰኑ ዘፈኖችን ደግሞ በኦሮምኛ እና በሱዳንኛ ዘፍኗል። 
ጥላሁን ለኢትዮጲያ ሙዚቃ ላደረገው አስተዋጽኦ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ለማግኘት በቅቷል ሌላም ህይወቱን በሙሉ ለሙዚቃ በማበርከቱ 
ከኢትዮጵያ ኪነጥበብና የብዙህን መገናኛ ሽልማት ድርጅት «የሙሉ ዘመን» ሽልማት ተሸላሚ ለመሆን በቅቷል። 

ጥላሁን ባደረበት የስኳር በሽታ የትንሳዔ ዕለት ሚያዝያ ፲፩ ቀን፣ ፳፻፩ ዓ/ም  ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። ሥርዓተ ቀብሩም በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል።




#Article 309: ክሻትሪያ (317 words)


ክሻትሪያ የህንዳውያን ኅብረተሠብ በተለያዩ 4 መደባት የሚከፋፈልበት አንዱ የህብረተሰባዊ ክፍል (ካስት) ነው። በዚህ አከፋፈል ዘዴ የወታደሮችና የገዢዎች ክፍል እሱ ነው። ክሻትሪያ ከብራህሚን (ቄሳውንትና አስተማሮች) በታችና ከቫይስያ (ነጋዴዎች) እንዲሁም ከሹድራ (ሠራተኞች፣ አገልጋዮች) በላይ ሆኖ ይቆጠራል። 

በመጀመርያ በጥንት ይህ ደረጃ በሰው ችሎታ፣ ተግባርና ጸባይ ምክንያት ሊገኝ የቻላ ሲሆን፣ በዘመናት ላይ ግን የተወረሰ ማዕረግ (በዘር የሚዛወር) ብቻ ሆነ። በአንዳንድ ወቅት ደግሞ የክሻትሪያ (መኳንንት) ክፍል ከብራህሚኖች (ቄሳውንት) ክፍል ይልቅ ላየኛነቱን ይይዝ ነበር። ብራህሚኖችም በኋላ የበለጡት ከትግል በኋላ እንደ ሆነ ይታመናል። 

የቃሉ ሥር በሕንዳዊ-ኢራናዊ ቋንቋዎች ቤተሠብ «*ክሺ» 'መግዛት' ሲሆን ለዚሁ ብዙ የተዛመዱ ቃሎች (እንደ ሳንስክሪት «ክሻትራ» 'ግዛት') ይኖራሉ። በጥንታዊ ፋርስኛ በኩል «ሕሻጥራ» ማለት 'ሃይል፣ መንግሥት' ነበረ፤ የ«ሕሻያጢያ» ትርጉም የፋርስ ንጉሠ ነገስት ሆኖ ከዚህ በዘመናዊ ፋርስኛ ንጉሥ ሻህ ይባላል። በአማርኛ፣ ቼዝ (ሰንጠረዥ) የሚባል ጨዋታ ስም ከዚህ የመጣ ነው። በተጨማሪ በፋርስ ታሪክ የጠቅላይ ግዛት ወይም አገረ ገዥ ማዕረግ «ሕሻጥራ-ፓዋ» (የግዛት ጠባቂ) በኋላ «ሳትራፕ» ሆነ። ሌሎች ቃላት በታይላንድኛ «ካሳት» 'ንጉስ' በመላይኛም «ሳትሪያ» 'ጀግና' ከ«ክሻትሪያ» የተነሡ ናቸው።

በሕንዱ ሃይማኖት መጻሕፍት የክሻትሪያ ታሪክና ሚና ይወሰናል። በርግ ዌዳ ዘንድ እያንዳንዱ መደብ ወይም 'ዋርና' ከፈጣሪ አምላክ (ብራህማ) ሰውነት ተነሥቶ የክሻትሪያ መደብ የተነሣ ከትከሾቹና ከክንዶቹ ነበረ። በሌላ ትርጉም ከጥፋት ውሃ ያመለጠው ሕግ ሰጪ ማኑ የአርያን ኅብረተሰብ ባከፋፈለበት ጊዜ ክሻትርያዎቹ ማርሻል አርትስ (እንደ ጁዶ፣ ካራቴ ወዘተርፈ) የተማሩት ነበሩ። እያንዳንዱ ዋርና (ካስት) በልዩ ቀለም ሲመለከት የክሻትሪያ ቀለም ቀይ ሆነ። 

በሌሎች መጻሕፍት መሠረት፣ በዙሪያ የተገኙ ሕዝቦች በድሮ እንደ ክሻትርያ ቢቆጠሩም፣ የብራህሚኖችን ሃይማኖት ግን በደንብ ስላልጠበቁ፣ በኋላ ከክሻትርያው ሁኔታ ወደቁ። ከነዚህም፣ ሳካዎቹ (የእስኩቴስ ሰዎች)፣ ያዋኖቹ (የግሪክ ሰዎች)፣ ፓህላቮቹ (የፋርስ ሰዎች)፣ ድራዊዶቹ (የደቡብ ሕንድ ጥቁሮች) እና የቻይና ሰዎች ሁላቸው በቀድሞ ክሻትሪያዎች ነበሩ። ዛሬ ግን አብዛኞቹ ክሻትርያዎች በህንድ አገር የአርያኖች (ነጮች) ሕዝብ አባላት ናቸው። ከሕንድ አገር ውጭ ከክሻትርያ የተወለዱ ዘሮች በተለይ በኢንዶኔዥያ፣ በቬትናምና በሽሪ ላንካ ይገኛሉ። የዛሬው ክሻትርያ ቤተሠቦች በጠቅላላው ከመደባቸው ውጭ አይጋቡም። 

ከሕንድ አገር ስርወ ነገስታት በቀር፣ በታሪክ ውስጥ ሌሎች የተገነኑ ክሻትርያዎች የቡድሃ ሃይማኖት አስተማሪ ጎታማ ቡድሃ እና የጃይን ሃይማኖት አስተማሪ ማሃዊራ ናቸው። በቡድሂስትና በጃይን ሃይማኖቶች ግን የ'ክሻትርያ' ትርጉም «ጦረኛ» ሳይሆን «ገበሬ»፣ «ባለመሬት» ብቻ ነው። በህንድ ሃይማኖት በኩል፣ ዋና አማልክታቸው ራማ እና ክሪሽና ክሻትርያዎች ይባላሉ።




#Article 310: እፃዊ ተዋልዶ (113 words)


እፃዊ ተዋልዶ ለአትክልት የኢሩካቤያዊ መራቦ ዘዴ ነው። በዚህ ተፈጥሮአዊ ሂደት ያለ ምንም ዘር ወይም ዱኬ አዲስ ተክሎች ሊገኙ ይቻላል። ስለዚህ ለምጣኔ ሀብት ዋጋ ላላቸው ዛፎች ለማስፋፋት በተለይ በግብርና ሰፊ ጠቀሜታ አለው። 

በተፈጥሮ ሲታይ፣ በልዩ ልዩ ዘዴዎች ሊሆን ይችላል። ለአንዳንድ አትክልት፣ ተቀብሮ (ውስጠ ዘመት) ግንድ ከምድር በታች አዲስ ሥር ወይም ቡቃያ ያስወጣል። በሌሎች ዝርያ፣ ከምድር በላይ ተባዥ ሐረጎች አዲስ ሥር ወይም ቡቃያ ያስወጣል። ስሁት የሚባለው ሥር አለ። ደግሞ በእኩራች ወይም በድንቼ ስረግንድ የሚበዛ አትክልት (ለምሳሌ ነጭ ሽንኩርት) አለ።

በገነት ወይም በእርሻ ተግባር እፃዊ ተዋልዶ ማለት ከዛፍ አንድ ቅርንጫፍ አገዳ ከመሃል አንጓ በታች ተቈርጦ፣ በሌላ መሬት ውስጥ ተክሎ፣ አዲስ ሥር ሲያስገኝ ነው። በዚሁ ዘዴ ብዙ ጠቃሚ የአትክልት አይነቶች ያለ ምንም ዘሮች በቀላሉ ለማብዛት ይቻላል፤ ለምሳሌ፦ 




#Article 311: በለስ (267 words)


በለስ (ሮማይስጥ፦ Ficus) ቅጠሉ ሰፋፊ፣ ነጭ ፈሳሽ ያለው፣ ፍሬው የሚበላ የእፅዋት አስተኔ ነው። ፍሬውም ደግሞ በለስ ወይም ዕጸ በለስ ይባላል።

በበለሱ ቤተሠብ ውስጥ ብዙ ልዩ ልዩ የዛፍ አይነቶች አሉ፤ ከነዚህም ውስጥ፦ 

የበለስ 'ፍሬ' በዕውኑ ወደ ውስጥ ያበበ አበባ ነው። ይህ ክስተት ለሥነ ሕይወት ጥናት በጣም የሚያስገርም ድንቅ ነው። እነኚህ አበቦች ፅጌ ብናኝን (የአበባ ወንዴ ዘር) የሚያገኙበት ዘዴ በልዩ ብናኝ አርካቢ ጥቃቅን ተርብ አማካኝነት ነው። ይህች የበለስ ተርብ ወደ ፍሬው ውስጥ ገብታ በመኖር እንቁላሏን በዚያ ትጥላለች። አብዛኞቹ በለስ አይነቶች አለበለዚያ ብናኝ ዘርን ሊያገኙ አይችሉም። ተርቢቱ ዕንቁላሏን ጥላ በበለሱ ውስጥ ከሞተች በኋላ፣ በፍሬው ያለው ኤንዛይም በድኑን ፈጽሞ ይበላል። የዛፉ ጾታ አንስት ከሆነ፣ የተርቢቱ እንቁላል አይፈለፈለም፣ ፍሬውም በሰው ይበላል። የዛፉ ጾታ ግን ፍናፍንት ሲሆን፣ ዕንቁላሎቿ ይፈለፈላሉ፤ ፍሬው ለፍየል ሊሰጥ ይችላል እንጂ በሰዎች አይበላም። ተርቦች ከፍናፍንት ዛፍ ተወልደው ሴት ተርቦቹ የሴት ዛፍ እንዲያገኙ ገበሬው የፍናፍንት ዛፍ ቅጠል ከአንስት ዛፍ ቅርንጫፍ ይሰቅላል። አንዳንድ የበለስ አይነት ያለ ተርብ ያፈራል፤ ነገር ግን የነዚህ ፍሬዎች መካን ይሆናሉ። ዳሩ ግን በለሶች በእፃዊ ተዋልዶ ለማብዛት በተለይ ስለሚመቹ፣ ይህ ዘዴ የተለመደና ፈጣን የመራቦ ዘዴ ነው። 

በእስልምና፣ በሕንዱ፣ በቡድሂስትና በጃይን እምነቶች፣ በለሶች የተቀደሱ ዛፎች ሆነው ይቆጠራሉ። በክርስትናም በአይሁድም በኩል በለስ ወይም ሾላ በብሉይ ኪዳን ብዙ ጊዜ ይጠቀሳል። ለምሳሌ በአንዳንድ ሥፍራ በትንቢት፣ በእግዚአብሔር መንግሥት ሰው ሁሉ በራሱ ወይንና በለስ ሥር እንደሚቀመጥ ይላል። በተጨማሪ በኦሪት ዘፍጥረት 3፡7 ዘንድ አዳምና ሕይዋን ከበለስ ቅጠል ልብስ ሠሩላቸው። ከዚህ የተነሣ በተለይ በተዋሕዶ ቤ.ክ. የበለስ ፍሬ ወይም እፀ-በለስ እግዚአብሔር እንዳትበሉት ብሎ ያዘዛቸው ፍሬ መሆኑን በመገመት ይታመናል። ሆኖም በሌላ አስተሳስብ የተከለከለው ፍሬ መታወቂያ ወይን ወይም ቱፋህ ነበር። መታወቂያው በመጽሐፉ እርግጠኛ ስላልሆነ፣ በእርግጥ በለስ ማለቱ ነበር ልንል አንችልም። በአዲስ ኪዳን ውስጥ ደግሞ በለስ በክርስቶስ ምሳሌዎች ብዙ ጊዜ ይጠቀሳል፤ በማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ 11 መሠረት ኢየሱስም አንዲቱን በለስ ረግሞ ነበር። 




#Article 312: ጉራጌ (120 words)


ጉራጌ የኢትዮጵያ ብሔር ነው። ቋንቋቸው ጉራግኛ ከሴማዊ ቋንቋ የሚመደብ ሲሆን ብዛት ያላቸው የጉራጌ ብሔሮች አሉ። እነሱም፦ መስቃን፣ ሶዶ፣ ወለኔ፣ ሰባትቤት፣ ቀቤና፣ ዶቢ፣ እና ሌሎችም ይኖራሉ።  አማርኛ ግን ለሁሉም መግባቢያቸው ነው። አንዳንድ የታሪክ  አዋቂዎች ጉራጌ ከሰሜን ኢትዮጵያ  ጉራ አካለጉዛይ፣ ኤርትራ  ከሚባል  ቦታ ለም መሬት ፍለጋ ወደ መሃል ኢትዮጵያ የፈለሰ ሕዝብ እንደሆነ ይናገራሉ፤ ጉራጌ  የሚለው ስያሜም ከዚህ የተወሰደ ሊሆን ይችላል ብለው ያስባሉ። 

ጉራጌኛ የሚጻፈው በግዕዝ ፊደል ነው።

ታዋቂ ጉራጌዎችን ለመጥቀስ ያህል፡ ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ (የኢትዮጵያ የጦር ሚኒስቴር የነበሩ)፣ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ አርቲስት መሐሙድ አህመድ፣ ደጅአዝማች በቀለ ወያ፣ አትሌት አሰፋ መዝገቡ፣[አለምፀሀይ ወዳጆ]፣ቴዲ አፍሮ፣አብረሃም ወልዴዶ/ር ያኡቆብ ወልደማርያም ፕሮፌሰር ባኣሩ ዘውዴ ሜ/ጀ ተስፋዬ ወ/ማርያም እስከ1996 ድረስ የኢትዮጵያ አየር አይል ኮማንዶ አዛዥ ራስ ደስታ ዳምጠው ቀኝ አዝማች ገብረማርያም ጌር
ዮሴፍ ገብረ፣ባልቻ አባ ነፍሶ(አባ መላ) ከብዙ በጥቂቱ ይጠቀሳሉ::




#Article 313: ራያ (147 words)


፭ራያ ማለት በስሜን ወሎ እና በደቡብ ትግራይ ሰፍሮ የሚገኝ ህዝብ ነው።  ይህ ህዝብ የራሱ የሆነ ባህል እና ወግ፡ ማለትም እንደ አነጋገር፡ አለባበስ፡ የሰርግ ፡ የለቅሶ ስነስራአት ያለው ኩሩ እና ጀግና ህዝብ ነው። የራያ ህዝብ ከሚደነቅበትና ከሚያስደስት ባህሉ ሁሉም የእምነት ተከታዮች በተለይምሙስሊም ክርስቲያንሳይል በመቻቻል  በህብረት በአንድ ላይ ተከባበሮ የሚኖር ህዝብ ሲሆን የአለባበስ ባህሉ ሌላው የሚደነቅለት አና ባህላዊ ጭፈራው ሲያዩት የሚያስግርም አና የሚያስድስት ነው። ከባህላዊ ጭፈራዎቹ እንደ ጉማየ መጋልዋ ፡ ወዘተ መጥቀስ ይቻላል፡፡ ህዝቡ የሚኖርበት አከባቢ እንደሚከተለው ይዋሰናል። በሰሜን እንደርታ፡ በደቡብ የጁ፡ በምስራቅ አፋር እንድሁም በምእራብ ላስታ ያዋሱኑታል። የከተሞች ስም ለመጥቀስ ያክል አላማጣ፡ ቆቦ፡ ኮረም፡ ማይጨው፡ መሆኒ ጨርጨር በመባል ይታወቃሉ።  የህዝቡ አስተዳድር እንደየ መንግስቶቹ ስቀያየር የኖረ ሲሆን፡ ቀደም ስል ራያን በሁለት አውራጃዎች በመክፈል ራያ ና ቆቦ ማእከሉ አላማጣ፡ ራያ ና አዘቦ ማእከሉ ማይጨው በማድረግ በወሎ ጠቅላይ ግዛት ስር ይተዳድር ነበር።ራያ ቆቦ በአሁኑ ሠአት ወረዳ ሢሆን ማዕከሉ ቆቦ ነው በሥሩ ብዙ ቀበሌዎች አሉት ለምሣሌ 07 አቧሬ አንዷናት። ምንጭ ከራያ ኣባቶች




#Article 314: ኦጋም ጽሕፈት (105 words)


ኦጋም ጽሕፈት ለጥንታዊ አይርላንድኛ ቋንቋ የተጠቀመ አጻጻፍ ነበረ። በአይርላንድና በታላቅ ብሪታንያ ምዕራብ 400 ያህል በኦጋም ፊደል የተጻፉ ቅርጾች ተገኝተዋል። እነዚህ በብዛት ከ300 ዓ.ም. እስከ 1000 ዓ.ም. ድረስ በድንጋይ ወይም በእንጨት የተቀረጹ ናቸው። እንዴት እንደ ተለማ የሚገልጹ ሀሣቦች ብዙ ናቸው። በአይርላንድ ትውፊቶች ዘንድ በፌኒየስ ፋርሳ ወይም በኦግማ በጥንት ከባቢሎን ግንብ ቀጥሎ ተፈጠረ።  

ፊደሉ ለመቅረጫ በጣም ተስማሚ ነው። ለእያንዳንዱ ተናባቢ ድምጽ ከ1 እስከ 5 ምልክቶች ወይም ከመካከለኛው መስመር ግራ፣ ወይም ቀኝ፣ ወይም ሁለቱም አሉ። ሁለቱም ሲሆን ምልክቶች ካላንጋደዱ ግን አናባቢዎች ያመልከታሉ። ተራ ያልሆነ አናባቢ በልዩ ምልክትም ይጠቆማል።

በአንዳንድ ደራሲ እንደ ባሪ ፌል ዘንድ፣ ይህ አይነት አጻጻፍ ደግሞ በእስጳንያ፣ በፖርቱጋል እንዲሁም በስሜን አሜሪካ (ለምሳሌ በትርኪ ተራራ) በሰፊ ተገኝቷል።




#Article 315: ወጋየሁ ደግነቱ (455 words)


አርቲስት ሻለቃ ወጋየሁ ደግነቱ ከአባቱ ከአቶ ደግነቱ ጅማ ከእናቱ ከወ/ሮ አበራሽ ወዲጆ ጥር 12 ቀን 1940 ዓ/ም. በሀረርጌ ክ/ሀገር በወበራ አውራጃ በጐሮ ጉቱ ወረዳ ልዩ ስሙ መካኒሳ በተባለው ስፍራ ተወለደ። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በሐረር ልዑል ራስ መኮንን አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ተከታትሏል። በነበረው ልዩ የሙዚቃ ፍቅር የተነሳ መጋቢት 1 ቀን 1955 ዓ.ም. በሐረርጌ ክ/ሀገር ፖሊስ ሙዚቃ ክፍል በታዲጊነት ዕድሜው ተቀጠረ። ከ1957 ዓ/ም ጀምሮ በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅና ተፈቃሪ ድምፃዊ ለመሆን የበቃው ሻለቃ ወጋየሁ ደግነቱ በ1959 ዓ/ም ከድምፃዊነቱ በተጨማሪ የሐረር ፖሊስ ሙዚቃ ክፍል የተወዛዋዥ ቡድን አሰልጣኝ የዜማ እና የግጥም ደራሲ ሆኗል።

ይኸው ለኪነ-ጥበብ ያለው ፍቅር እየጐለበተ እያበበና እየጐመራ በመሄዱ ወጋየሁ በቀድሞ ፖሊስ ሠራዊት ውስጥ በ1960ዎቹ የተውኔት ባለሞያና አዘጋጅ የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋች የሙዚቃ መሣሪያዎች ቴክኒሻን ጭምር በመሆን የዘርፈ ብዙ ባለሞያዎች ባለቤት መሆኑን ለባልደረቦቹ እና ለአለቆቹ ለማሳየት ችሏል። ከሙዚቃ ስራው በተጓዳኝ የአቋረጠውን ትምህርት በማታው የትምህርት ክፍል በመከታተል ለተጨማሪ እውቀት የነበረውን ትጋትም አሳይቷል። በ1964 ዓ/ም የሙሉ 10 አለቅነት ማዕረግ ያገኘው ወጋየሁ ቀጥሎም የመኮንንነትን ኮርስ በሰንዲፋ ፖሊስ ኮሌጅ በመውሰድ ሚያዚያ 14 ቀን 1968 ዓ/ም በምክትል መቶ አለቃነት ማዕረግ ተመርቋል። በፖሊስ ሠራዊት ባልደረባነቱ ወቅት በቀድሞ ኤርትራ ክ/ሀገርና በመላው ሀገሪቱ ተዘዋውሮ በሙያው ሀገሩን ያገለገለው ወጋየሁ ኤርትራ ውስጥ በነበረው በ5ኛ ሻለቃ ፈጥኖ ደራሽ ሠራዊት ውስጥ የመቶ መሪ በመሆን ወቅቱ የጠየቀውን ሐገራዊ ግዳጅ ተወጥቷል። ሀገሩ እና ወገኖቹ ሁሉ ሊዘነጉት የማይቻላቸውን የጀግንነት ተግባርም በመወጣት በመኮንንነቱ የተዋጊ አዋጊነት ዘመን ፈጽሟል። ስለ እናት ኢትዮጵያ ክብር «የደስታሽ ሕይወት ተካፋይ ለችግርሽ ሆኜ ተወካይ መቆሜን አውቃለሁ ጠንቅቄ ታሪክሽን ለማኖር ጠብቄ…» ብሎ ያዜመው ስለ ወላጅ እናት ፍፁምነት እና መተኪያ አልባነት «የሰው የእንስሣት የአራዊት… እናት እኮነች መድኃኒት” በማለት ያንጐራጐረው እና “አርኬ የሁማ…» በተሰኘው ማሕበረሰባዊ ተወዳጅ የኦሮምኛ ዜማው የሚታወቀው ሻለቃ ወጋየሁ ደግነቱ ከጦር ግንባር ግዳጅ መልስ በመስከረም ወር 1969 ዓ.ም. የኤርትራ ክ/ሀገር ፖሊስ ሙዚቃ ክፍል አዛዥ ሆኖ አገልግሏል። በ1978 ዓ.ም. የሻለቅነት ማዕረግ እስካገኘበት ጊዜ ድረስ እና ከዚያም በኋላ በኪነ-ጥበብና በፖሊሳዊ ሙያው ከሀረርጌ ጫፍ እስከ አሰብና የቀድሞይቱ ኢትዮጵያ ደሴቶች ድረስ በመነቃነቅ ከእሱ ይጠበቅ የነበረውን የዜግነት ድርሻ ተወጥቷል። አርቲስት ሻለቃ ወጋየሁ ደግነቱ፤ በቀድሞ የኢትዮጵያ ፊናንስ ፖሊስ፣ የፖሊስ ሠራዊት የሙዚቃና የቴአትር እንደሁም በአዲስ አበባ ፖሊስ መምሪያ የ6ኛ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል መከላከል ክፍል ኃሊፊ ሆኖ ሰርቷል። ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲም የህግ ፋኩልቲ በማታው የትምህርት ክፍል የህግ ሙያን በመከታተል በ1984 ዓ/ም ወርሀ ታህሣስ የህግ ዲፕሎማውን የተቀበለው አርቲስት ወጋየሁ ደግነቱ ጅማ በጥብቅናና በህግ አማካሪነት ሙያ ሕብረተሰቡን በቅንነት ሲያገለግል የቆየ ስሙ ጥሩ ኢትዮጵያዊ ነበረ። በሳቂታነቱ፣ የተጣሉትን በማስታረቅ ተግባሩ፣ በተግባቢነቱና በጨዋታ አዋቂነቱ፣ በሥራ እና በወገን ወዳድነቱ በኢትዮጵያዊን ዘንድ ልዩ አክብሮትን ያገኘ ሰው ነበረ። ሻለቃ ወጋየሁ ባለትዳር እና የአንድ ሴት ልጅ አባት እንደዚሁም የአንድ ወንድ ልጅ አያት ሲሆን፤ ከወራት በፊት በአጋጠመው የጤና መታወክ ምክንያት በሕክምና ሲረዲ ቆይቶ በ61 ዓመቱ አርብ ሐምሌ 10 ቀን 2001 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቶናል ። የቀብር ስነ-ሥርዓትም ቅዳሜ ሐምሌ 11 ቀን 2001 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ በቀጨኔ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ወዳጅ ዘመዶቹ እና በርካታ አድናቂዎቹ በተገኙበት ከቀኑ በ10 ሰዓት ተፈጽሟል።

ቤተሰቦቹ ታሞ ህክምና እየተከታተለ በነበረበት ሰዓትም ሆነ በሐዘናቸው ጊዜ ከጐናቸው ላልተለዩ የአርቲስቱ ልባዊ ወዳጆች እና ለኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ የከበረ ምስጋና ያቀርባሉ።




#Article 316: ቦሩ ሜዳ (122 words)


ቦሩ ሜዳ በቀድሞ ወሎ የሆነ ትልቅ ገበያ ከተማ ነው። 

በመጋቢት 18 ቀን 1870 ዓ.ም. በቦሩ ሜዳ ላይ የሸዋ ንጉሥ (ምኒልክ) ለንጉሠ-ነግስት ዮሐንስ አራተኛ ተገዥ እንደሆኑ ቃላቸውን ገቡ።  በምላሽም ዮሐንስ በሸዋ ላይ የምኒልክን ንጉሥነት ተቀበሉ።   

ዮሐንስ በቦሩ ሜዳ ቤተክርስቲያንን ሠርተው በግንቦት 1870 አንድ ታላቅ የተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስብሰባ ተፈጸመበት። በዚህ ስብሰባ «የጸጋ ልጅ» ወይም «ሦስት ልደት» የተባለ ትምህርት ተከታዮች ከእንግዲህ እንደ ሃራ ጤቃ ይቆጠራሉ የሚል አዋጅ ወጣ። ከዚህ በላይ በአጼ ዮሐንስ ትእዛዝ ዘንድ የእስላም ሃይማኖት ለወሎ መኳንንት በግድ ተከለከለ። ይህ ከባድ ቃል ግን በሚከተለው ንጉሠ ነገሥት በ2 ምኒልክ አዋጅ ተሠረዘ። 

ስመ ጥሩ መምህር የሆኑት አለቃ አካለ ወልድ በወሎ ያለውን በተክርስቲያን በማጽናት እንዲረዱ ተመረጡ። በቦሩ ሜዳ ላይ የትምህርት ማእከል መሠረቱ። ቦሩ ሜዳ ሥላሴ የቤተክርስቲያን ከፍተኛ ትምህርት ማእከል ሲሆን ታውቆ ተማሪዎች ከአገሩ ሁሉ ወደዚያ ይመጡ ነበር። 




#Article 317: ደበበ ሰይፉ (631 words)


ደበበ ሰይፉ የአማርኛ ባለቅኔ ነበሩ።
ሚያዚያ 16 ቀን 1992 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ደበበ ሰይፉ ዘርፈ ብዙ የጥበብ ሰው ነው፡፡ ገጣሚ፣ ሃያሲ፣ መምህር፣ ጸሐፊ-ተውኔት፣ የሥነ-ጽሑፍ ተመራማሪ… ነው፡፡ “የብርሃን ፍቅር” እና “ለራስ የተጻፈ ደብዳቤ” የግጥም ሥብስቦቹ የተደጎሱባቸው መጻሕፍቱ ናቸው፡፡
ከዚህ ቀጥሎ ያለው መረጃ /አቀናባሪ አሉላ ከ EthioCurrent Assimba –Voice Room/ አማካኝነት /የደበበ ሰይፉን 7ኛ ዓመት የሙት ዓመት ምክንያት በማድረግ 
ሚያዝያ16,1999ዓ.ም የተቀናበረ ነው፡-

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በይርጋለምና በአዲስ አበባ ኮከበ ጽባህ ትምህርት
ቤቶች ተማረ። ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነ ጽሁፍ
ትምህርት ክፍል ከፍ ባለ ማዕረግ የመጅመሪያ ድግሪውን አገኘ። በእንግሊዘኛ ሥነ
ጽሁፍ የማስተር ድግሪውን ተቀበለ። ከ1966 እስክ 1984 በረዳት ፕሮፌሰርነት
አገለገለ። ለበርካታ ዓመታት የኢትዮጵያ ደራሲያን ማኅበር ፕሬዜዳንት ሆኖ ሰራ።
በቀድሞው ኩራዝ አሳታሚ ድርጅት ያልታተሙ መፃህፍት ገምጋሚም ነበር።
ከ1985 ዓ.ም. ጅምሮ ለሰባት ዓመታት ታሞ ማቀቀ። ሚያዝያ 16 ቀን 1992 ዓ.ም.
በተወለደ በሃምሳ ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። ሚያዝያ 17 ቀን 1992 ዓ.ም.
ንፋስ ስልክ በሚገኘው የቅዱስ ዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን መካነ መቃብር በድኑ አረፈ።
ከተማሪነቱ አንስቶ በርካታ ግጥሞች ጽፏል። «የብርሃን ፍቅር» የተሰኘ የመጀመሪያ
የግጥም መድበሉን በ1980 ዓ.ም. በኩራዝ አሳታሚ ድርጅት አሳተመ። የብርሃን
ፍቅር ሁለተኛ ክፍል የሆነውንና ፦ «ለራስ የተፃፈ ደብዳቤ» የተሰኘውን መድበሉን
ደግሞ በ1992 ዓ.ም. በሜጋ አሳታሚ ድርጅት ታተመ። በተውኔቱ ዘርፍ «የቲያትር
ጥበብ ከፀሐፌ ተውኔቱ አንፃር» የሚለው መጽሐፉ፤ «ሳይቋጠር የተፈታ» እና

በርካታ ናቸው።

አታልቅስ አትበሉኝ

አትሳቅስ በሉኝ

ግዴለም ከልክሉኝ፤

የፊቴን ፀዳል

አጠልሹት በከሰል፤

የግንባሬን ቆዳ

ስፉት በመደዳ፤

ጨጓራ አስመስሉት።

ግዴለም።

አትጫወት በሉኝ

ዘፈኔን ንጥቁኝ

ግዴለም።

ብቻ ፤
አታልቅስ አትበሉኝ

አትጩህ አትበሉኝ ።

ከሰባት ዓመት በፈት ደበበ ሰይፉ እንዳረፈ ሰሞን ስሙን፦ በጋዜጣ፤ በመጽሔት፤
በሬዲዮና በቴሌቪዥን ሲነሳ ሲወሳ ከርሟል። እስከዛሬም ይታወሳል። ዛሬም ሰባተኛ
የሙት ዓመቱን እንዘክረዋለን። ይህን የምናደርገው ፕሮፌሰር ስለሆነ ፤ ገጣሚ
ስለሆነ ፤ አንደበተ ርቱዕ ስለሆነ ፤ ፀሐፊ ተውኔት ስለሆነ ፤ ጠቢብ ስልሆነ ብቻ
አይደለም ። በዛሬው ዘመን ስለሱ ተወሳ - አልተወሳ ምንም ቁም ነገር የለውም።
ሳንታሮ ታኒካዋ ፅፎት ጆርጅ ጊሽ ጀር የተረጎመውን፦ “What the dead man left
behind” የሚለውን ግጥም አስታውሶ ትካዜ ባሟሸው ዝምታ ማለፍም ይቻል ነበር።
ነገር ግን ጋሽ ደበበ ሁሉንም «ልዩ» ነገር እንደነበር የማያውቁት እንዲያውቁት
ያስፈልጋል።
ጋሽ ደበበ ሁሉንም «ልዩ» ነገር ነበር። ልዩ ፕሮፌሰር፤ ልዩ ባለቅኔና ገጣሚ፤ ልዩ
ተናጋሪ (ኦራተር)፤ ልዩ ተፈላሳፊ፤ ልዩ ፀሕፊ ተውኔት፤ ልዩ ጠቢብ፤ ልይ ሩህሩህና
ደግ፤ ልዩ «ቅዱስ» አማፂ፤ ልዩ ልዩ ነበር።

ፍርሃት አዶከብሬ

ፍርሃት አዶከብሬ

አያ እናት አይምሬ

የቁም መቃብሬ

የቅዥት አገሬ።

ከሥጋ ከነብሴ ከደሜ ቆንጥሬ

ከአጥንቴ ሰንጥሬ፤

ምስህን ሰጥቼህ ላመልህ ገብሬ፤

ያው ነህ አንተገና

ልጓምህ አይላላ።

ትጋልበኛለህ በእሾህ በቆንጥር ላይ

ጨለማ እንደ ግራር በቅሎበት በሚታይ

አንዲት ዘሃ-ጮራ

በማትደፍርበት

እውነት - ፍቅር - ውበት

በተቀበሩበት።

ቅዱስ አማፂ ሆኖ ሳለ ከውስጡ አልነቀል ያለውን የፍርሃት ርዝራዥ በ«ፍርሃት
አዶከብሬ» ውስጥ ያሳየናል። ካልፈራህ እንዴት ቅዱስ አማፂ ትሆናለህ? ትፈራለህ፤
ትደፍራለህ። ድፍረት በፍርሃትህ ልክ ነው። በፈራኸው መጠን ትደፍራለህ።
የማትፈራ ከሆንክ፦ የማትደፍር ነህ። የማትደፍር ከሆንክ የማትደፈር ነህ፤ (ብዙ
ጊዜ)። የማትፈራም የማትደፍርም ከሆንክ ደግሞ በድን ነህ። ቅዱስ አማፂነትህ
የፍርሃትና የድፍረትህ ድምር ውጤት የሚሆንበት (አብላጫ) ጊዜ አለ።

ያኔ ተማሪ ነበር አሉ።
ስታዲየም ዙሪያ አንድ ምግብ ቤት ገባ። እርቦታል። ምግብ አዘዘ። የመብል
አምሮት የሠራው ምራቅ በአፉ ግጥም እያለ ትንሽ «አፋዊ» ኩሬ ይሰራል። ያዘዘው
ምግብ እስኪቀርብለት በመጠባበቅ ላይ እያለ አንድ ሰው በዝግታ ወደ ውስጥ ገባ።
ቡትቶ ለብሷል፤ ዓይኖቹ በደረቀ ፊቱ ውስጥ ተቀርቅረዋል። እንደራበው
ያስታውቃል። ተያዩ። የዓይን ግጭቱ ቁም ነገር ያዘለ ከባድ ሃሳብ ሰራ። ያ ሰው
ሊናገር ከሚችለው በላይ ለጋሽ ደበበ መልዕክቱ ደረሰው፦ «እርቦኛል ፤ በልተህ
ሲተርፍህ እንድትሰጠኝ» ነው ያሉት የሰውየው ዓይኖች። ጋሽ ደበበ ግን ከዚህ በላይ
ገባው።
አምሮት በሰራው ምራቅ ግጥም ያለ አፉ ክው አለ። የታዘዘው ምግብ እየመጣ
ነበር። እፈቱ ተቀመጠ። መብሉን አየው ጋሽ ደበበ። ከመቀመጫው ተነሳ። አነሳው
ምግቡን። ለሰውየው ሰጠው። መስጠት ጀምሮ መስጠቱ ከማብቃቱ በፊት በአንድ
ጊዜ ሁለት ነገሮች ሆኑ…ከውጭ ግር ያሉ ቡትቶ የለበሰው ሰውዬ ጉስቁል አጃቢዎች
መሻማት ጀመሩ። ይሄ አንዱ ነገር ነው። የምግብ ቤቱ ባለቤት ባለቡትቶውን ሰውዬ
መቀጥቀጥ ጀመሩ፤ ይሄ ደግሞ ሌላው ነገር ነው። ምግቡ ተደፋ። ጐስቋላው ሰውዬ
ደማ። ምግቡ፤ ደሙ፤ አሸዋው፤ አፈሩ፤ ጠጠሩ ሺህ ዓመት እዚያ ቦታ የቆመ ያህል
ተሰማው። ተነቀሳቀሰ። ወዴት እንደሚሄድ ሳያውቅ መራመድ ጀመረ።
ከዚያን ቅፅበት ጅምሮ በኮሚኒዝም ተጠመቀ።
ታላቁ መብረቅ ከሰባት ዓመት በፈት አመለጠ።
ትናንት ከኛ ጋር ነበር፤ ዛሬ የለም። የጊዜ ጉዳይ ነው። በጊዜ ላይ ሲፈላሰፍ
የቋጠራቸው ስንኞች ስለስብዕናው የሚሰጡት ስዕል አለ። 




#Article 318: ነሐሴ ፲፫ (189 words)


ነሐሴ ፲፫ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፵፫ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ  ፳፫ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፳፪  ቀናት ይቀራሉ። 

ከኢትዮጵያን ሪፖርተር ፦ ሆያ ሆዬ በሚል አርስት ነሐሴ ፲፫ ቀን  ፳፻፩ ዓ.ም የወጣ አንቀጽ

አረ እንደምን ሰነበቱ
ክፈትልኝ በሩን
የጌታዬን
ሆያ-ሆዬ-ሆ 

እያሉ ልጆች በዜማ እያወረዱ፣ በየመንደሩ እየተሽከረከሩ የሚጫወቱት ለቡሄ በዓላቸው ነው፡፡ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የኖረ፣ አሁንም እየቀጠለ ያለ ትውፊት ነው፡፡ 

ዛሬ ነሐሴ ፲፫ ቀን  የበዓሉ ክብር ነው፡፡ በተለይ ነባሩን ትውፊት ይዞ የሚገኘው በገጠር አካባቢ ነው፡፡ ቡሄኞቹ ልጆች ለበዓሉ አስቀድመው ይዘጋጃሉ፡፡ ጅራፍ ሲገምዱና ሲያጮሁ ይሰነብታሉ፡፡ እናቶችም ለበዓሉ የሚሆን ሙልሙል ዳቦ ያዘጋጃሉ፡፡ እየጨፈሩ ለሚመጡ ልጆችም ያበረክታሉ፡፡

በአዲስ አበባ ባሁን ጊዜ እየዞሩ ከሚጨፍሩት ሕፃናት ሌላ በከተማዋ ዳርቻ የሚኖሩ ጎረምሶችም በኦሮምኛ የቡሄ ጭፈራቸውን፣ ቄጠማ እያበረከቱ የሚያስኬዱበት ሥርዓት አላቸው፡፡

ቡሄ ጎላጣ፣ መላጣ ማለት እንደሆነ መጻሕፍት ይገልጻሉ፡፡ የክረምቱ ጨለማነት አልፎ ወደ ብርሃን፣ ወደ ጥቢ የሚያመራበት፣ ወደ መፀው የሚዘለቅበት ወገግታ የሚታይበት እንደሆነ ይታመንበታል፡፡

ከቡሄ በኋላ የጠነከረ ክረምት ስለማይኖርም ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፣ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት እየተባለም ይነገራል፡፡ 

ለባህላዊው በዓል መሠረት የሆነው፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በሚያስተምርበት ጊዜ በታቦር ተራራ ላይ (ደብረ ታቦር) ብርሃነ መለኮቱን፣ ክብረ መንግሥቱን የገለጠበት ዕለት እንደሆነ ይጠቀሳል፡፡ 




#Article 319: ነሐሴ ፲፮ (119 words)


ነሐሴ ፲፮ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፵፮ ኛው ዕለት  ነው።  ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ዮሐንስ ፳ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ማቴዎስ፤ ማርቆስ እና ሉቃስ ደግሞ ፲፱ ዕለታት ይቀራሉ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አማኞች በዛሬው ዕለት በየዓመቱ ነሐሴ ፩ ቀን የሚጀመረውን ጾመ ፍልሰታ የሚፈቱበት ቀን ነው።

፲፰፻፶፮ ዓ/ም በጦርነት የተማረኩ ሰዎችን መብት ስለማስጠበቅና ስለማክበር የተዘጋጀው የጋራ ድንጋጌ (የጀኒቫ ኮንቬንሽን) በአሥራ ሁለት መሥራች አገሮች ተፈረመ። የቀይ መስቀል ማኅበርም አብሮ ተመሠረተ።

፲፱፻፷፬ ዓ/ም የዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ሸንጎ (እንግሊዝኛ፡ International Olympic Committee) ሮዴዚያን (አሁን ዚምባብዌ) በዘረኛነቷ ምክንያት አባልነቷን ሠረዘ። 

፲፰፻፺፮ ዓ/ም በዘጠና ሦስት ዓመታቸው እስከሞቱ ድረስ  ለሀያ ሰባት ዓመታት ቻይናን የመሩት ዶንግ ዢያው ፒንግ ተወለዱ።

፲፱፻፸ ዓ/ም የመጀመሪያው የኬንያ መሪ ፕሬዚደንት ጆሞ ኬንያታ በተወለዱ በ ሰማንያ ስድስት ዓመታቸው አረፉ።




#Article 320: ቁርአን (149 words)


ቅዱስ ቁርአን ወይንም ቁርአን) የመሃከለኛዉ አለም  የእስልምና የቅዱስ መጽሃፍ ወይም የእምነት ጽሁፍ ነዉ፣ በዚህም ትምህርት ይህ ጽሁፍ የመጣዉ በአላህ ፈቃድ ቃሉን በጂብሪል አማካኝነት ለነብዩ ሙሀመድ የወረደ የአላህ ቃል ነው። ቅዱስ ቁርአን ለመጀመርያ ጊዜ በአረብኛ ነበር የተጻፈዉ። አላህ ለቁራን ቃል ገብቶለታል እሱም ማንም ሰዉ መበረዝ እንደማይችል እና ማንም ሰዉ ቃሉን ቀይሮ ህጉን ሊአሳስት እንደማይችል ነዉ። አላህ ሁልጊዜም ከመበረዝ የሚጠብቀዉ በአለም ላይ ያለ ብቸኛው መጽሃፍ ነዉ። ይኅም በአማርኛ የተተረጎመ ቁርዓን ነዉ። 

ቁርአን ሰዎች እና አጋንንት እንኳ ቢሰበሰቡ የሱን ተመሳሳይ አንቀጽ ወይም አረፍተ ነገር ማምጣት ይችሉ እንደሆነ ይሞክሩ በማለት ተአምረኛነቱን እና እውነተኛነቱን አረጋግጧል።
ቁርአን ከመበዘረዝ እና ከመከለስ የጠራ ነው። እንደዚህም የሰው ልጆች ሁሉ መመሪያ እንደሆነ ሳይበረዝ እና ሳይከለስ እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ ይቆያል፤ ምክንያቱም አላህ እጠብቀዋለሁ ብሎ ቃል ስለገባለት ቁርአንን በተመለከተ እስላምI am using new features, please update the new version to experience.ሙስሊሞች'

የሰው ልጆች በዚህ ምድርም ይሁን በመጭው አለም ሰiላም እና እርጋታ ከፈለጉ ሙስሊም ሆነው በቁርአን መመራት አለባቸው የሚል ትምህርት ያቀርባል።




#Article 321: ጉታውያን (307 words)


ጉታውያን ከመስጴጦምያ በላይ ባሉት ተራሮች «ጉቲዩም»፣ «ጉቲ» ወይም «ቁቲ» በተባለ ሀገር የመጣ ሕዝብ ነበረ። በ2010 ዓክልበ. ገደማ የአካድ መንግሥት በወደቀበት ዘመን ወርረው የሱመር አለቆች ሆኑ። 

ጉታውያን በመስጴጦምያ ጽሕፈቶች ዘንድ ኋላቀርና ሥልጣኔ የናቀ ሕዝብ ይመስላሉ። ከነገስታታቸው ስሞች በቀር፣ ስለ ቋንቋቸው ጸባይ አንዳችም ነገር ዛሬ አይታወቅም።

መጀመርያ በታሪክ መዝገብ የሚታዩ፣ ለአዳብ ንጉሥ ለሉጋል-አኔ-ሙንዱ መንግሥት (2130 ግ.) ግብር ከሚከፍሉ ሕዝቦች መካከል ሲዘረዝሩ ነው። በጽላት መዝገብ ዘንድ አገራቸው ከሹቡር ደቡብና ከኤላም ስሜን ይገኛል። በአካዳውያንም ዘመነ መንግሥት፣ ለንጉሥ ታላቁ ሳርጎን (2070 ግ.) ተገዥ ሁነው ከሉሉቢ ብሔር አጠገብ ነበሩ። ናራም-ሲን (2049-2030 ግ.) ደግሞ የጉቲዩም ንጉሥ ጉላዓን አሸንፎ አገሩን እንደ ያዘው በአንድ ሰነድ ይዘገባል። 

በ2021 ዓክልበ. ግ. የአካድ ንጉሥ ሻርካሊሻሪ የጉቲዩምን ንጉሥ ሻርላግን ማረከው፤ በ2018 ግ. «ቀንበር (ግብር) በጉቲዩም አደረገበት» ይዘገባል። የአካድ መንግሥት ግን ከዚያ ድካም ለመሆን ሲጀምር፣ ጉታውያን በመስጴጦምያ ላይ ብዝበዛ ያድርጉ ነበር። ሠራዊት እንደ ደረሰባቸው ግን ሸሽተው ነበር። ከቤት ማለፍ ወይም እንኳን በእርሻ መግባት አስጊ ሁኔታ ስለ ሆነ፣ የመስጴጦምያ ምጣኔ ሀብት ተበላሸና ራብ ሆነ። በመጨረሻ፣ (2010 ግ.) ጉታውያን አካድን ወረሩና ገዙት። እንዲሁም የጉቲ ሠራዊት ኡሩክንና ኤላምን የዛኔ ወረሩ።  የጉታውያን ንጉሥ ኤሪዱፒዚር እራሱን እንደ አካድ ነገስታት በማምሰል፣ ማዕረጉ 'የጉቲ ንጉሥና የ4 ሩቦች ንጉሥ' ተባለ። ጉታውያን በአገሩ ሁሉ የታሰሩት እንስሶች ከጉረኖአቸው ፈቱ። የጉታውያን ግዛት ለእርሻ ተግባርም ሆነ ለዜና መዋዕል ዝገባ ጥንቁቅ አልነበረም። በሱመራዊው ነገሥታት ዝርዝር በአንዳንድ ቅጂ 25 ዓመታት ብቻ እንደ ገዙ የሚለው አቆጣጠር ትክክል ይመስላል፤ በትንሽ ጊዜ ውስጥ አገሩ በጽኑ ረሃብ ተያዘ። የኤላም ንጉሥ ኩቲክ-ኢንሹሺናክ ከጉታውያን ዘመን በፊትና በኋላ ስለሚታወቅ ለ124 አመታት (እንደ ሌላ ቅጂ) ሊሆን አይችልም።

በ1985 ዓክልበ. ያሕል፣ የኡሩክ ንጉሥ ኡቱ-ኸጛል የጉታውያን ንጉሥ ቲሪጋንን እንዳሸነፈ ጉታውያንንም ከአገራቸው እንዳስወጣ ይባላል። ከዚህ በኋላ በ1974 ዓክልበ. የኡር ኡር-ናሙ ጉቲዩምን ዘረፈው። በ1742 ዓክልበ. የኤሽኑና ንጉሥ 2 ኢፒቅ-አዳድ የጉቲዩም ዋና ከተማ አራጳን ያዘ። በ1676፣ 1674ና 1669 ዓክልበ. የባቢሎን ንጉሥ ሃሙራቢ ጉቲዩምን እንደገና ድል አደረገው። 

በኋለኛ ዘመን፣ በአሦር መንግሥት 'ጉቲ' የሚለው ስም ለሜዶን ይጠቅም ነበር። በፋርስም ንጉሥ ቂሮስ ዘመን፣ ታዋቂ አለቃ ጉባሩ 'የጉቲ አገረ ገዥ' ተባለ። በተራሮቹ የሚገኘው የዛሬው ኩርድ ሕዝብ ከጉቲዎቹ እንደ ተወለዱ የሚያምኑ ብዙ ናቸው።




#Article 322: የሜዳ ቀይ ሕንዳውያን እጅ ምልክት ቋንቋ (138 words)


የሜዳ ቀይ ሕንዳውያን እጅ ምልክት ቋንቋ (Plains Indian Sign Language ወይም PISL) በዩናይትድ ስቴትስ ታላቅ ሜዳዎች ላይ በኖሩት በስሜን አሜሪካ ኗሪዎች (ቀይ ሕንዳውያን) የተፈጠረ የእጅ መነጋገሪያ ነበረ።

በአሜሪካና በካናዳ በሮኪ ተራሮች ምሥራቅና በሚሲሲፒ ወንዝ በስተ ምዕራብ ያለው አገር በብዛት ሰፊ ሜዳዎች ነው። በነዚህ ላይ ብዙ የተለያዩ የአገር ኗሪ ሕዝቦች ወይም ጎሣዎች ጎሽን እያደኑ ይመላለሱ ነበር። እነዚህም አገሮች ሁሉ የየራሳቸው ቋንቋ ነበራቸው። ከዚህ በላይ ልሳናታቸው ባልተዛመዱ ቤተሠቦች ውስጥ ስለሆነ እርስ በርስ በመነጋገር ትንሽ ተቸገሩ።  በዚህ ምክንያት ጎሣዎቹ ሁሉ የሚጠቀሙበት የእጅ መነጋገሪያ ቋንቋ ተለማና ተስፋፋ። 

ይህ ዘይቤ በአውሮፓውያን መጀመርያ በ1533 ዓ.ም. በስፓንያዊው አለቃ ኮሮናዶ ታየ። በ1877 ዓ.ም.፣ ቋንቋውን የቻሉት ኗሪዎች ቁጥር በ110፣000 ተገመተ። እነዚህ ከአልጎንኲን ቤተሠብ የሲክሲካ (ብላክፉት)፣ የጺጺስታ (ሻየን)፣ የሂኖኖኧይኖ (አራፓሆ) ተነጋሪዎች፣ እንዲሁም የካወጉ (ካዮዋ) እና የላኮታ (ሱ) ተነጋሪዎች ይጠቀልል ነበር። ነገር ግን በ1960ዎቹ 'ከዚህ ቁጥር በጣም ጥቂት ከመቶ' ቀሩ።  ዛሬም ጥቂት PISL የሚችሉ አሉ።

PISL ልዩ ስዋሰው አለው። 




#Article 323: መኮንን እንዳልካቸው (688 words)


ራስ ቢትወደድ መኮንን እንዳልካቸው፤ አርበኛ፣ ስደተኛ፣ የውጭ ጉዳይ አደራዳሪ፣ ታላቅ ደራሲና በንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት የመጀመሪያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉ ኢትዮጵያዊ ናቸው።

መኮንን እንዳልካቸው የካቲት ፲ ቀን ፲፰፻፹፫ ዓ/ም ከአባታቸው ከባላምባራስ እንዳልካቸው አብርቄ እና ከናታቸው ከወይዘሮ አቦነሽ ተክለ ማርያም በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ተጉለት፣ አዲስጌ ላይ ተወለዱ።

ትምህርታቸውን አዲስ አበባ በዳግማዊ ምኒልክ ትምህርት ቤት ካጠናቀቁ በኋላ ካርቱም ከሚገኘው የሶባት የጦር መኮንኖች ትምህርት ቤት ተመርቀዋል። በዳግማዊ ምኒልክ ትምህርት ቤት ሳሉ የትምህርት አቻዎቻቸው እነ ልጅ ተፈሪ መኮንን እና ልጅ ዕምሩ ኃይለ ሥላሴ ነበሩ።

ልጅ መኮንን እንዳልካቸው “የሕልም ሩጫ” በተባለው መጽሐፋቸው ላይ በዳግማዊ ምኒልክ ዘመን የጀመረው የሥልጣን እርምጃቸው የልጅ ኢያሱ ሞግዚት እና እንደራሴ የነበሩት አጎታቸው፣ ራስ ተሰማ ናደው ካረፉ በኋላ በተለያዩ ባለ ሥልጣናት እንደተገታ አሥፍረውልናል። 

በንግሥት ዘውዲቱ ዘመን የተማሪ ቤት ጓደኛቸው ራስ ተፈሪ መኮንን የአልጋ ወራሽነትን ሥልጣን እንደያዙ ወዲያው ‘ልጅ መኮንን’ ተብለው በ፲፱፻፱ ዓ/ም የወንበሮ፣ አብቹና ማሰት አውራጃ ገዥ ሆነው ተሹመው ለአራት ዓመታት ቆዩ።

በ፲፱፻፲፫ ዓ/ም የምድር ባቡር ተቆጣጣሪ ሆነው ተሹመው፣ እስከ ፲፱፻፲፰ ዓ/ም ሲያገለግሉ ከቆዩ በኋላ የንግድ ሚኒስትር ሆነው እስከ ፲፱፻፳፪ በሠሩበት ወቅት ፓሪስ ላይ በተካሄደው የጦር መሣሪያ ጉባዔ ላይ አገራቸውን ወክለው ተሳትፈዋል።

በብሪታኒያ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ቋሚ መላክተኛ ሆነው የተሾሙት ነጋድራስ (በኋላ ራስ ቢትወደድ) መኮንን እንዳልካቸው፣ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለንጉሥ ጆርጅ አምስተኛ ተወካይ ለአልጋ ወራሹ የዌልስ መስፍን (የወደፊቱ ንጉሥ ኤድዋርድ ስምንተኛ)  ኅዳር ፲ ቀን 1922ዓ/ም በባኪንግሃም ቤተ መንግሥት አቅርበዋል። በዚህም የሥራ መደብ ሁለት ዓመት አገልግለዋል። 

በብሪታኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚያዝያ ፳፮ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓ/ም ያወጣው “የኢትዮጵያ ትላልቅ ሰዎች ዝርዝር” ላይ በተራ ቁጥር ፹፪ ስለተመዘገቡት ነጋድራስ መኮንን እንዳልካቸው ሲተነትን፤ በጥቅምት ወር ፲፱፻፳፫ ዓ/ም ለተከናወነው የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የንግሥ በዓል ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው ሲገቡ፣ ያጋጠማቸው አዲስ አበባ ከተማ እንዳይገቡ የመታገድ ትዕዛዝ እንደነበረና ምክንያቱም ፓሪስ ላይ በወቅቱ የራስ ጉግሳ አርአያ ሚስት ከነበሩት የንጉሠ ነገሥቱ ታላቅ ወንድም ልጅ፣ ልዕልት የሻሸወርቅ ይልማ ጋር ባልገዋል በሚል እንደነበር፤ ራስ ጉግሳም በኋላ በዚሁ ምክንያት ሚስታቸውን እንደፈቱ እና ነጋድራስ የአሥር ሺ የኢትዮጵያ ብር ቅጣት እንደተጣለባቸው ዘግቧል።   

የዚህን ዘገባ ትክክለኛነት ከሌላ ምንጭ ማረጋግጥ ባይቻልም ወደሎንዶን ሥራቸው እንዳልተመለሱና በቋሚ መላክተኝነት በጅሮንድ ዘለቀ አግደው ተክተዋቸው የሹመት ደብዳቤያቸውን ሐምሌ ፲፮ ቀን ፲፱፻፳፫ ዓ/ም ማቅረባቸውን ‘የሎንዶን ጋዜት’ ይዘግባል።  በኋላም ከልዕልቲቱ ጋር በ፲፱፻፳፰ ዓ/ም ተጋብተው እስከ ዕለተ ሞታቸው ድረስ የትዳር ጓዶች እንደነበሩ ይታወሳል።

ከሎንድን ከተመለሱበት ጊዜ ጀምሮ ለቀጠሉት አሥራ አራት ወራት ገደማ በምን ሥራ ላይ ተሰማርተው እንደነበር መረጃዎች ባይገልጹም፣ የሚቀጥለው ምድባቸው በታኅሣሥ ወር ፲፱፻፳፬ ዓ/ም  ፰ኛው የአዲስ አበባ ከንቲባ ኾነው ተሹመው ለሁለት ዓመታት አገልግለዋል። ከዚህም ምደባ በኋላ የኢሉባቡር ጠቅላይ-ግዛት አገር ገዢ ሆነው የጠላት ወረራ ድረስ የሠሩ ሲሆን ወደዘመቻውም የሄዱት ከዚሁ ጠቅላይ ግዛት ሠራዊት ጋር ነበር።

በጦርነቱ ዝግጅት በሚደረግበት ወቅት፣ ደጃዝማች መኮንን እና ሌሎችም መሪዎች ለቀኙ ደቡብ ክፍል የጦር ሠራዊት አዝማች ሆነው ለተመደቡት ለሐረር መስፍን እንደራሴው ለደጃዝማች ነሲቡ ዘአማኔል ረዳት ሆነው ተመደቡ።   ጣልያኖቹ በቁጥር እና በዘመናዊ መሣሪያ የበለጡ ቢሆኑም በኦጋዴን በኩል የመጣው የጣልያን ግንባር-ቀደም ሠራዊት፤ በደጃዝማች መኮንን የተመራው የኢሉባቡር ሠራዊትን ጨምሮ፣ በሦስት ግንባር በተሰለፉት ኢትዮጵያውያን ጠንካራ ምክት ተቸግሮ ነበር። በተለይም   ከማይጨው ጦርነት ሽንፈት በኋላ ንጉሠ ነገሥቱ ከቤተሰባቸውና ከአንዳንድ መኳንንት ጋር በስደት ወደአውሮፓ ሲያመሩ፤ በኦጋዴን በኩል ሲከላከሉ የቆዩት ደጃዝማች መኮንን እና ሦስት ሌሎች የጦር አለቆች በስደት ወደ ኢየሩሳሌም አመሩ። 

በኢየሩሳሌም ደጃዝማች መኮንንን በሚመለከት በስደት ዘመን ስለተከሰቱ አንዳንድ ነገሮች፤ ደጃዝማች ከበደ ተሰማ፣ “የታሪክ ማስታወሻ” በተባለው መጽሐፋቸው ላይ ሲያወጉን፦  ጠላት እዚያ ተጠልለው የነበሩትን መሳፍንትና መኳንንት «አስጨንቆ ከጠላት እየታረቁ እንዲገቡና ንጉሠ ነገሥቱ የተሰደዱበትን ዓላማ ለማሳሳት በማሰብ ብዙ የማንገራበድና የማስፈራራት ሥራ ይሠሩ ነበር።» ይሉና በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳም ንብረት የነበረውን እጁ ለማግባት እና የገዳሙን ማስረጃ ሰነዶች ለመውሰድ፣ በገዳሙ የነበሩትን አንዳንድ ኤርትራዊ መነኮሳትን በመጠቀም ያዘጋጁትን ደባ በመስበርና፤ ሰነዶቹን በማሸግ ከተሳተፉት መኻል አንዱ ደጃዝማች መኮንን እንደነበሩ አስፍረውታል።  

ደጃዝማች ከበደ፤ በዚያው በኢየሩሳሌም፤ ቀድሞ ንግሥት ነገሥታት ዘውዲቱ ለገዳሙ መናንያኖችና ምዕመኖች መተዳደሪያ የገቢ ምንጭ እንዲሆን ያሠሩትን ቤት በፊት የኢትዮጵያ ቆንስል ያስተዳድር የነበረውን ጠባቂነቱ ተዛውሮ ወደስደተኞች ወኪል ወደተደረጉት ደጃዝማች መኮንን ተላልፎ ይሠራ እንደነበርም ዘግበዋል። 

የኢጣልያ መንግሥት ኢትዮጵያን የመንግሥቷ አካል እንዳደረገችና የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥትነትን ማዕርግ ለንጉሧ ለቪክቶር ኢማኑኤል ሣልሳዊ እንዳደርገች ግንቦት ፩ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓ/ም አወጀች። የብሪታንያ መንግሥት ግን ለዚህ አዋጅ የይፋ እውቅና ከመስጠቱ በፊት ግንቦት ፬ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓ/ም ለተፈጸመው የንጉሥ ጆርጅ ሳድሳዊ  የንግሥ በዓል እንዲገኙ ጃንሆይን ጋብዞ ነበር። ዳሩ ግን በዚሁ ሥነ ሥርዓት ላይ ሊገኝ ተጋብዞ የነበረው የኢጣልያው አልጋ ወራሽ (በኋላ ንጉሥ) ኡምቤርቶ እንደማይመጣ እና የኢጣልያም ጋዜጠኞች በሙሉ በሥነ-ሥርዓቱ ላይ እንዳይገኙ ሙሶሊኒ ማዘዙ ሲታወቅ፤  ደጃዝማች መኮንን እንዳልካቸው ወደ ሎንድን ተጉዘው ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን በመወከል ከአቶ ኤፍሬም ተወልደመድኅን ጋር ተገኝተዋል። 

ደጃዝማች መኮንን እንዳልካቸው፣ እንግሊዞች ጃንሆይን ወደሱዳን ካመጧቸው በኋላ በስደት በየቦታው የነበሩትን ኢትዮጵያውያን በሱዳን ሲያሰባስቡ ከነበሩበት ከኢየሩሳሌም ወደንጉሠ ነገሥቱ ከሄዱት መኳንንት መሀል አንዱ ነበሩ። 

ልብ-ወለድ

ተውኔት

ሥነ ልቡናና ሳይንስ

ፍልስፍናዊ አሳቤ

ሌሎች




#Article 324: አክሊሉ ሀብተ-ወልድ (1489 words)


ጸሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሰው ሲሆኑ በ ጣልያን ወረራ ጊዜ አምስቱን ዓመት ሙሉ በፓሪስ የኢትዮጵያ ጉዳይ ፈጻሚ፤ በዠኔቭ በዓለም መንግሥታት ማኅበር የኢትዮጵያ ዋና ጸሐፊ ከድል በኋላም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርነት እና እስከ አብዮት ፍንዳታ ድረስም በዓፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስቴር ነበሩ። ከአብዮቱ ፍንዳታ በኋላ  አቃቂ ታስረው ከቆዩ በኋላ ያለፍርድ ኅዳር ፲፬ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓ/ም ከስልሳ ሰዎች ጋር በደርግ ተረሽነው ሞቱ።

አክሊሉ መጋቢት ፭ ቀን ፲፱፻፬ ዓ/ም በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ቡልጋ ከተወለዱት አለቃ ሀብተወልድ ካብትነህ እና ከወይዘሮ ያደግድጉ ፍልፈሉ ተወልደው የአማርኛ ትምህርታቸውን አዲስ አበባ በሚገኘው የራጉኤል ቤተ ክርስቲያን አጠናቀቁ። ከዚያም በዳግማዊ ምኒልክ ትምሕርት ቤት ለሦስት ዓመታት ዘመናዊ ትምሕርት ከተከታተሉ በኋላ በ፲፱፻፲፯ ዓ/ም ወደ እስክንድርያ ትምሕርታቸውን እዚያ በሚገኘው የፈረንሳይ “ሊሴ” ትምህርት ቤት እንዲቀጥሉ በአልጋ ወራሽ ራስ ተፈሪ መኮንን ተላኩ።  እስክንድርያም እስከ ፲፱፻፳፫ ዓ/ም ከተማሩ በኋላ የሊሴ ትምሕርታቸውን አጠናቀው ለከፍተኛ ትምሕርት ወደ ፓሪስ እና ታዋቂው ሶርቦን ዩኒቨርሲቲ አምርተው የከፍተኛ የንግድ ሕግ እና ሽከታኪን (political science)  ትምሕርት ጀመሩ። ሶርቦን እስከ ፲፱፻፳፰ ዓ/ም ድረስ ተምረው የመጀመሪያ ሲማክቶ ጉላፕ (BA degree  )  በሸከታኪን እንዲሁም የ ሲማሕግ ጉላፕ (bachelors degree in law)  ተመርቀው ወጡ። ወዲያው ፋሽሽት ኢጣልያ ሀገራችንን ይወርና ወጣቱ አክሊሉ ሀብተወልድ ለውድ አገራቸው ነጻነት የአርበኝነት ትግላቸውን በቶፍካ (diplomacy)  እና በገቢ ሰብሳቢነት እዚያው ፈረንሳይ አገር ተሰማሩ።

በጦርነቱ ዋዜማ ኢትዮጵያ በዓለም መንግሥታት ማኅበር ሸንጎ ጣልያን በግፍ ልትወራት መነሳቷን እና በማኅበሩ ‘የጋራ ደህንነት’ ዋስትና (collective security principle) መሠረት አባላት አገሮች መሃል ገብተው ጣልያንን እንዲያስታግሱ በምትከረከርበት ጊዜ አክሊሉ በፈረንሳይ አገር ውስጥ ተማሪ ሆነው ሳሉ ለሀገራቸው የሚያደርጉትን ትግል በመመልከት ንጉሠ ነገሥቱ፤ በዠኔቭ የኢትዮጵያ ልዑካን መሪ ፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያት  ተክለ ማርያም ሥር ዋና ፀሐፊ አደረጓቸው። ፊታውራሪው ያንጊዜ በፈረንሳይ፣ በብሪታንያ እና በዠኔቭ የኢትዮጵያ ዋና ልዑክ ነበሩ። ጦርነቱ በይፋ ከመጀመሩ በፊት ወደዠኔቭ እየሄዱ በኢትዮጵያ ስም ከጣልያን ጋር በዓለም መንግሥታት ማኅበር ሸንጎ ይሟገቱ የነበሩት እነዚህ ሁለቱ ስዎች ነበሩ። 
ፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያት ወደአገራቸው ሲመለሱና ብላቴንጌታ ወልደ ማርያም በፓሪስ የኢትዮጵያ አምባሳዶር ሲሆኑ አክሊሉ የ”ፕሬስ አታሼ” ሆነው እንዲሠሩ ንጉሠ ነገሥቱ ቢያዟቸውም አምባሳደሩ “እምቢ ብለው አላስገባም አሉኝ። ቢሆንም እውጭ ሆቴል ቁጭ ብዬ እንደፕሬስ አታሼ ሆኜ ሥሠራ ነበር።” ( መስከረም ፲ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓ/ም ለደርግ የምርመራ ኮሚሽን ‘ዓለም በቃኝ’ እስር ቤት ሆነው በላኩት የታሪክ ማስተወሻተው) የሚሉን አክሊሉ ሀብተወልድ በዚሁ ሥራ አፈ ቀላጤ (spokesperson) ሆነው ለጋዜጠኞች ማብራሪያ እና ቃለ ምልልስ በመስጠት የኢትዮጵያን አቋም እና የተሰነዘረባትን ግፈኛ  ድርጊት ማስተዋወቃቸውን ቀጠሉ። 

ለመሆኑ ብላቴንጌታ ወልደ ማርያም ለምን ይሆን አክሊሉን አላስገባም ያሉት። ምናልባት ንጉሠ ነገሥቱ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ “ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ - ሁለተኛ መጽሐፍ” በተባለው መጽሐፋቸው ላይ “በፓሪስ የኛ ሚኒስቴር የነበረው ብላቴንጌታ ወልደማርያም አየለ እኛን ከድቶ ለጣልያኖች በገባ ጊዜ በዓለም መንግሥታት ማኅበር የኢትዮጵያ ጸሐፊ አቶ አክሊሉ ሀብተወልድ በፓሪስ የኢትዮጵያ ጊዜያዊ ጉዳይ አስፈጻሚ ሆኖ አገልግሎናል።” ብለው ያሠፈሩት ምክንያቱን ይጠቁም ይሆናል። 

በወቅቱ የፈረንሳይ ጠቅላይ ሚኒስቴር የነበረው ፒዬር ላቫል እና የብሪታንያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሳሙኤል ሆር በ ታኅሣሥ ወር ፲፱፻፳፯ ዓ/ም በምስጢር ዶልተው አዘጋጅተውት የነበረውን፤ ኢትዮጵያን የሚበልጠውን አገር (ሐረርን፣ ሲዳሞን፣ ባሌን) ለጣልያን ሰጥታ ጎጃምን፣ ጎንደርን እና ትግሬን አስቀርታ ተጣልያን ጋር እንድትታረቅ የሚደነግገውን የ”ሆር-ላቫል” ስምምነት የሚባለውን  ለጃንሆይ መስጠታቸው ሲሰማ አክሊሉ ሀብተወልድ ማዳም ታቡዴስ ለምትባለው የ”ራዲካል ፓርቲ” ጋዜጣ ኃላፊ ለነበረችው ታዋቂ ጋዜጠኛ በምስጢር ይገልጹላትና እሷ ሎንዶን ላይ በጋዜጣና በራዲዮ ይፋ አደረገችው። ጉዳዩ በብሪታንያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ትልቅ ውዝግብና ሙግት ተደርጎበት ሆርም ምክር ቤቱን ይቅርታ እንዲጠይቅና ስምምነቱም እንዲወድቅ አድርጎታል።

በሚያዝያ ወር ፲፱፻፳፰ ዓ/ም መደምደሚያ የፈረንሳይ የሕግ አውጪዎች ምክር ቤት አባላት ምርጫ በሚካሄድበት ጊዜ ወጣቱ አክሊሉ ለሦስቱ ዋና ፓርቲዎች የወቅቱ የፈረንሳይ ጠቅላይ ሚንስቴር የነበሩት ፒዬር ላቫል ሙሶሊኒን ለማስደሰት ሲል ኢትዮጵያን በመሸጥ “የጋራ ደህንነት” (collective security) የተባለውን የዓለም ጸጥታው ምክር ቤትን ዓላማ ማድከሙን፤ የኢትዮጵያ አቤቱታ እንዳይታይ እያደረገ እንደነ ሙሶሊኒና ሂትለርን እንዳበራታ ፣ በዚህም የዓለም ጦርነትን እንዲፋጠን ማድረጉን በዝርዝር ማስረዳትና ለፓርቲዎቹም የላቫልን መንግሥት ለመገልበጥ መሣሪያ መስጠት ለኢትዮጵያ ታላቅ ጥቅም እንደሚሰጥ በመገንዘብ በነዚህ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ስብሰባ እየተገኙ የኢትዮጵያን እሮሮ ማሰማት ጀመሩ።  የፈረንሳይም ጋዜጦች እነኚህን ስብሰባዎች በሚዘግቡ ጊዜ የአክሊሉ ሀብተወልድን ንግግርም ጨምረው ሲያትሙ ሀገራቸው የደረሰባትን የግፍ ወረራ ለመላው የፈረንሳይ ሕዝብ ሲያስተዋውቁ ቆዩ።

አዲስ የተመረጠውን የፈረንሳይ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሊዮን ብሎምን አነጋግረው ፈረንሳይ የሙሶሊኒ ፋሽሽት ኢጣልያ መንግሥት በኢትዮጵያ ላይ ያላትን ይዞታ መቼም ቢሆን እንደማያውቅ አረጋግጦላቸዋል። ወዲያው ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በስደት ወደብሪታንያ ሲመጡ አክሊሉም በዚያው በፓሪስ የኢትዮጵያ ጉዳይ ፈጻሚ ሆነው ሲያገለግሉ ቆዩ።  መስከረም ፲ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓ/ም ለደርግ የምርመራ ኮሚሽን ‘ዓለም በቃኝ’ እስር ቤት ሆነው በላኩት የታሪክ ማስተወሻተው   እንደነገሩን፤ “በ፲፱፻፴ ዓ/ም የእንግሊዝ ንጉሥና ንግሥት በግብዣ ለጉብኝት ፓሪስ በመጡ ጊዜ ተሌሎች አምባሳደሮች ጋር እኔም ተጠርቼ ሄጄ ነበር። በፕሮቶኮሉ ደንብ የኢትዮጵያና የጣልያን ጉዳይ ፈጻሚዎች አቀማመጣቸው ጎን ለጎን ስለነበር አጠገቡ በምሆንበት ጊዜያት ጣልያኑ በጣም ሲቆጣ እኔም ኃይለኛ ቃል ስለተናገርኩት ጠቡን ሁሉም ሰምተው የፕሮቶኮሉ ሹም በመካከላችን የሌላ አገር ጉዳይ ፈጻሚ አስቀመጠ።” ይላሉ

በወቅቱ ጣልያኖች በኢትዮጵያ ላይ “ኋላቀር፤ ባርያ ሻጭ፤ አውሬዎች…. የኛ ተልዕኮ ኢትዮጵያን ማሰልጠን ነው….” እያሉ ፕሮፓጋዳቸውን ያዛምቱ ስለነበር የፈረንሳይ ሕዝብ ስሜቱን ለኛ ስሞታውን ወደነሱ አዙሮ ነበር።  ይሄንን በዘለቄታማና ስኬታማ መንገድ ለመከላከል አክሊሉ (ሀ) ከልዩ ልዩ ጋዜጮች ጋር በመገናኘት እውነቱን በማስረዳት (ለ) ተነ ሙሴ ጃንጉል (በኋላ ኢትዮጵያ ውስጥ በማስታወቂያ ሚኒስቴር ሥር የፈረንሳይኛ ጋዜጣ ያቋቋመ) እና ከሌሎች ፈረንሳዮች ጋር በመተባበር ኢትዮጵያን የሚረዱ ሁለት ኮሚቴዎች (comité d’action Ethiopie እና association du peuple Ethiopie) በማቋቋምና በነዚህ ኮሚቴዎች በኩል የኢትዮጵያን ጉዳይ በብዙ ሺህ ለሚቆጠሩ ፈረንሳዮች በማሰራጨት የሕዝብ ዕርዳታ ለማስገኘት ችለዋል።  (ሐ) በነዚሁ ኮሚቴዎች ዕርዳታና መሥራችነት የኢትዮጵያን አቋምና የጣልያንን ግፍ በየጊዜው የሚያስረዳ “ኑቬል ደ ኤትዮፒ” (የኢትዮጵያ ዜና) የሚባል ጋዜጣ ተመሠርቶ እሳቸውም በየጊዜው በጋዜጣው ይጽፉ ነበር።

የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ሲያከትም የተሸናፊዎቹን የጀርመንን እና የጣልያንን ይዞታ፤ የካሳ ጉዳይ እና በድል ጊዜ ከጣልያን ወደ እንግሊዝ አስተዳደር ተላልፈው የነበሩትን የኤርትራን እና የኦጋዴንን ጉዳይ ለመወሰን በየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መሪነት “የሰላም ጉባዔ” በሚካሄድበት ጊዜ አቶ አክሊሉ ሀብተወልድ መጀመሪያ በፓሪሱ ጉባዔ በታዛቢነት በመጨረሻም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርነት አዲሱ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በተመሠረተበት በሳን ፍራንሲስኮ ከተማ የኢትዮጵያን ልዑካን በመምራት ተሳትፈዋል። 

አክሊሉ ሀብተወልድን ትልቅ የዲፕሎማሲ ሰው መሆናቸውንና በዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ መድረኮች ለኢትዮጵያ ብዙ መታገላቸውን የሚያስመሰክርላቸው ዘመን የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ካከተመበት ጊዜ ጀምሮ የኤርትራ እና የኢትዮጵያ በኅብረታዊ መንግሥት የመዋሐድ ጉዳይ እስከተፈረመበት ኅዳር ወር ፲፱፻፵፪ ዓ/ም ድረስ የነበረው ዘመን ነው። አክሊሉ በእንግሊዝና በኢጣሊያ ተሸንሽና የነበርቸውን አገራቸውን ረጅም ዓመት የፈጀ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት በማድረግ አንድ ያደረጉ ታላቅ ዲፕሎማት እንደነበሩ ስለሳቸው ብዙም የተጻፈ መረጃ ማግኘት ቢያስቸግርም በአምባሳደር ዘውዴ ረታ የተጻፈው ‘የኤርትራ ጉዳይ’ የተባለው መጽሐፍ ስለኚህ ሰው ታላቅ ተጋድሎ በሰፊው ተዘርዝሮ ይገኛል ::
አምባሳዶር ዘውዴ የኤርትራን ጉዳይ በተመለከተው በዓለም መድረክ ላይ ይካሄድ ስለነበረው ትግል ሲጽፉ ፤  በዚያን ጊዜ በአካባቢ ቡድን ብዛት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኃይል የነበራቸው የላቲን አሜሪካ አገሮች የጣልያን ወገን በመሆን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩን አክሊሉ ሀብተወልድን እጅግ በጣም ቢያናድዷቸው የተከተለውን ትንቢታዊ ንግግር ከማኅበሩ መድረክ ላይ አደርጉ፦

 ሲሉ ስሜታዊ ንግግራቸውን አሰምተዋል። እውነትም ይሄንን በተናገሩ በአሥር ዐመታት ውስጥ አፍሪቃውያን አገሮች በማኅበሩ ውስጥ ትልቁ አኅጉራዊ ቡድን ለመሆን በቁ።

በ፲፱፻፲፯ ዓ/ም መጀመሪያ ለትምሕርት ከአገራቸው፣ ከትምሕርታቸውም በኋላ በጣልያን የግፍ ወረራ ምክንያት አምስቱን ዓመታት አውሮፓ ቆይተው በተቻላቸውና በተሰጣቸውም መመሪያ ስለአገራቸው ሲታገሉ የኖሩት አክሊሉ፤ ከጠላትም ድል መደረግ በኋላ የሳቸው ዲፕሎማሲያዊ የትግል ሥራ እስከሚገባደድ ድረስ በድካም፤ በጭንቀት እና በህመምም ለብዙ ዓመታት በፓሪስ እና ኒው ዮርክ የኖሩት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከጥቂት የሥራ ጋደኞቻቸው ጋር በ፲፱፻፵፬ ዓ/ም ወደናፈቋት አገራቸው ተመለሱ። 

የኤርትራን ጉዳይ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስፈጽመው የተመለሱትን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአገራቸው ሕዝብ በተለይም ኤርትራውያን በጣም ሞቅ ባለ ሁኔታ ተቀበሏቸው። ቀደም ብሎ ንጉሠ ነገሥቱ፣ እቴጌ መነን፣  ፀሐፊ ትዕዛዝ ወልደ ጊዮርጊስ ወልደ ዮሐንስ፣ አቶ ይልማ ደሬሳ እና የወለጋ ጠቅላይ ግዛት አስተዳዳሪ የነበሩት ደጃዝማች መኮንን ደስታ የደስታ ቴሌግራም ተልኮላቸው ነበር። ሆኖም ንጉሠ ነገሥቱ መስከረም ፩ ቀን ፲፱፻፵፭ ዓ/ም የኤርትራን ከኢትዮጵያ ጋር በኅብረት መንግሥት መዋሐድ አስመልክተው ባደረጉት ንግግር አንዳንድ ኤርትራውያንን በስም ጠርተው ሲያመሰግኑ፤ ለዚህ ውጤት እጅግ ከፍ ያለ ትግል ያካሄዱትንና ታላቅ ዲፕሎማሲያዊ መስዋዕትነትን ላበረከቱት አክሊሉ ሀብተወልድ ግን በሕዝብ ፊት ምስጋና ያለማቅረባቸው ያሳዝናል። 

በሚያዝያ ወር ፲፱፻፵፯ ዓ/ም የአክሊሉ ዋና ደጋፊ የነበሩት እና እስከዚያ ጊዜ ድረስ በንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት ትልቅ ሥልጣን እና በንጉሠ ነገሥቱም ታማኝነትና ተሰሚነት የነበራቸው  ፀሐፊ ትዕዛዝ ወልደ ጊዮርጊስ ወልደ ዮሐንስ ፣ ትክክለኛ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ከዚህ ቁልፍ ቦታ ተነስተው መጀመሪያ የአሩሲ ጠቅላይ ግዛት አስተዳዳሪ ቀጥሎም የጋሙ ጎፋ ጠቅላይ ግዛት አስተዳዳድሪ ተደርጉ። 

አምባሳዶር ዘውዴ ረታ በመጽሐፋቸው ስለዚህ ጉዳይ ሲያወሱ፣ የኤርትራ ጉዳይ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሚካሄድበት ጊዜ አክሊሉ ሀብተወልድ የብሪታንያን የኤርትራ አቋም ነቅፈው በመዝለፋቸው የንጉሠ ነገሥቱ የግል ፀሐፊ የነበሩት እና የብሪታንያ ደጋፊ የሚባሉት አቶ ተፈራ ወርቅ (በኋላ ፀሐፊ ትዕዛዝ) ‘የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ አክሊሉ ለብሪታንያ ይቅርታ ይጠይቅ ሲሉ  ፀሐፊ ትዕዛዝ ወልደጊዮርጊስ ግን ያደረገው አግባብ ነው ይቅርታ መጠየቅ የለበትም በሚል ጉዳይ ተከራክረዋል ሲሉን የፀሐፊ ትዕዛዝ ወልደጊዮርጊስ ከሥልጣን መወገድ ምክንያት ዕውን ይሄ ይሆን ወይ? ሊያስብለን ይችላል።

ባህሩ ዘውዴ ደግሞ (A History of Modern Ethiopia 1855-1991) በተባለው መጽሐፉ ላይ የፀሐፊ ትዕዛዝ ወልደ ጊዮርጊስ ከሥልጣን መወገድ ዋና ምክኛት የነበሩት የግል ምስጢራዊ የስለላ ድር  የዳበሩት እና በዚህም የሚያገኙትን መረጃዎች ለንጉሠ ነገሥቱ በማካፈል ይወደዱ የነበሩት  የአክሊሉ ታላቅ ወንድም መኮንን ሀብተወልድ ናቸው ይለናል። እንዴት የፀሐፊ ትዕዛዝ ወልደ ጊዮርጊስ የመውደቅ ምክንያት እንደሆኑ ባያብራራልንም ምናልባት በዚሁ የምስጢራዊ ስለላ ድራቸው ‘ትልቅ ምስጢር አግኝተውባቸው ይሆን? ለማለት ያበቃናል።

ትክክለኛ ምክንያቱ ይህም ይሁን ያ፣ የፀሐፌ ትዕዛዝ ወልደጊዮርጊስ መወገድ  የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን አቶ አክሊሉን ግን ከንጉሠ ነገሥቱ ጋር የሚያቀራርበውን በፀሀፊ ትዕዛዝ ማዕረግ የፅህፈት ሚኒስቴርና እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴርነትን አፍርቶላቸዋል።

በክብር ዘበኛ ሠራዊት አዛዥ ጄነራል መንግሥቱ ንዋይ እና በታናሽ ወንድማቸው አቶ ገርማሜ ንዋይ የተጸነሰሰውና ታኅሣሥ ፬ ቀን ፲፱፻፶፫ ዓ/ም ተጀምሮ ዓርብ ታኅሣሥ ፯ ቀን አሥራ አምስት መኳንንት፣ ሚኒስቴሮች እና የጦር መኮንኖች መረሸን ያከተመው የታኅሣሥ ግርግር የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ፣ ለፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ በታላቅ ወንድማቸው አቶ መኮንን ሀብተወልድ መገደል ትልቅ የግል ሀዘን ላይ ቢጥላቸውም፤ በጊዜያዊ ጠቅላይ ሚኒስቴርነት የንጉሠ ነገሥቱን መንግሥት ይመሩ የነበሩት የራስ አበበ አረጋይ በአመጸኞቹ እጅ መገደል ለሳቸው የጠላይ ሚኒስቴርነቱን ማዕርግ እና ሥልጣን አስገኝቶላቸዋል።
በጠቅላይ ሚኒስቴርነት እና በፅሕፈት ሚኒስቴርነት በጥምር ሲያገለግሉ ዘመናዊውንና ጥንታዊውን ሥልጣናት በጃቸው በማግባት ለንጉሠ ነገሥቱ ቀርበው በተሰሚነት አብዮቱ እስከፈነዳ ድረስ ሠሩ።  

በ፲፱፻፷፭ ዓ/ም የተቀጣጠለው አብዮታዊ ሽብር በተማሪዎች ሰልፍ፣ የወታደሮች እንቅስቃሴ እንዲሁም የዓለምን ዱኛ (economy)   ያናጋው የነዳጅ ማዕቀብ ሲለኮሱ የደርግ ሥልጣንም እየጎለመሰ መጣ።  ወታደሮቹም መኮንኖችን ብቻ ሳይሆን የ መንግሥት ባለሥልጣናትንም ጭምር የማሠር ስልጣን እንደሚኖራቸው ንጉሠ ነገሥቱን አሳመኑ።  በየካቲት ወር ጠቅላይ ሚኒስቴሩ አክሊሉ ሀብተወልድ ከነ ሚኒስቴሮቻቸው ሥልጣናቸውን ለቀቁ። 




#Article 325: አሰልበርህት (212 words)


አሰልበርህት (552 -608 ዓ.ም.) ከ572 ወይም 582 ዓ.ም. አካባቢ እስከ 608 ዓ.ም. ድረስ የኬንት ንጉሥ ነበረ። ከእንግሊዝ ንገስታትም መጀመርያው የተጠመቀ እሱ ነበር። ስለዚህ በሮማ ካቶሊክ፣ በምሥራቅ ኦርቶዶክስና በአንግሊካን ሃይማኖቶች «ቅዱስ» ይባላል። 

በአንግሎ-ሳክሶን ዜና መዋዕል ዘንድ፣ እሱ አባቱን የኬንት ንጉሥ ኤዮርመንሪክን ተከተለ። የፍራንኮች ንጉሥ ቻሪበርት ልጅ ቤርታን አገባት። እሷ ክሪስቲያን ነበረችና ከዚህ የተነሣ ንጉሥ ተጠምቆ ክርስትና በእንግሊዝ ሕዝብ መካከል ይፋዊ ሆነ። አውግስጢኖስ ዘካንተርቡሪ ከሮማ በ589 ዓ.ም. ተልከው የእንግሊዝ ሕዝብ መጀመርያ ሊቀ ጳጳስ ሆኑ።

አሰልበርህት ከኬንት በላይ በዘመኑ መጨረሻ በሌሎች የእንግሊዝ ደሴት መንግሥታት በኤሴክስና ምሥራቅ ኤንግላ ላይ ገዥነት ነበረው። በእርሱ ተጽእኖ የኤሴክስ ንጉሥ ሳበርህት እና የምስራቅ ኤንግላ ንጉስ ራድዋልድ በ596 ዓም ግድም ተጠመቁ።

በተጨማሪ በ594 ዓ.ም. ንጉሥ አሰልበርህት ለአገሩ ሕገ መንግሥት አወጣ። ይህ ሕገ መንግሥት በሮማይስጥ ሳይሆን የተጻፈው በጥንታዊ እንግሊዝኛ ነበረ። በኋላ ዘመን የእንግሊዝ ንጉሥ ታላቁ አልፍሬድ ከዚህ ሕገ መንግሥት ወስደው የተሻሸለ ሕገ መንግሥት አወጡ። 

አሰልበርህት በ608 ዓ.ም. ካረፈ በኋላ ልጁ ኤድባልድ ተከተለው። ኤድባልድ ግን በመጀመርያ ወደ አረመኔነት ቢመልስም በኋላ ግን ክሪስቲያን ንጉሥ ሆነ። 

በአሰልበርህት ሕግ ፍትሕ ግድያ፣ ስርቆት፣ ዝርፍያ፣ ትግል፣ የሀብት ወይንም የሰውነት ጉዳት፣ ማመንዝር፣ ስላምን ማጥፋት ያደረጉ ሁሉ የገንዘብ መቀጮ ወይም ካሣ ነበረባቸው። የመቀጮው መጠኖች ግን እንደ ተበዳዩና በድለኛው መደቦች ወይም ማዕረጎች ልዩነት ትክክል አልነበሩም። ከሁሉ የተጠበቀው የቤተ ክርስቲያን ነዋይ ነበር፤ ፲፪ እጥፍ ካሣ ነበረበት። እንዲሁም ሁከት በሆነበት ጊዜ ለሰው መሣርያን መስጠት በገንዘብ መቀጮ ተከለከለ። 

ይህ ሕግ ፍትሕ የማጫ ሥርዓት እንዲህ ይቀምራል፦ 




#Article 326: ሶቪዬት ሕብረት (329 words)


ሶቭየት ሕብረት ሰብአዊ ሪፐብሊክ በ፲፱፻፲ ዓ.ም. የተከሰተውን የሩሲያ አብዮት ፍንዳታ፤ እንዲሁም ያንን ተከትሎ ለሦስት ዓመታት የተከናወነውን የሩሲያ «ውስጣዊ ሕዝባዊ የርስ በርስ ግጭት» ተከትሎ በኅብረተስብአዊ ሕገ መንግሥት (socialist constitution) በአራት ሪፑብሊኮች ቅንብርነት የተመሠረተ አገር ነበር። 

በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፍጻሜ ከቀድሞው የናዚ ጀርመን እጅ የተወሰዱ አገሮችን በማቀላቀል እንዲሁም በ፲፱፻፵፱ ዓ.ም በጉልበት ሌሎች የምሥራቅ አውሮፓ አገሮችን በመቀላቀል ኅብረቱ ዓሥራ ስድስት ሪፑብሊኮችን ያካተተ ነበር። በዘመን ቆይታና በጥንካሬም የጎለበተ ሕዝባዊ አብዮታዊ የኅብረት ሪፑብሊክ በመሆኑም በተለይ በ«ቀዝቃዛ ጦርነት» (cold war) በሚባለው በ«ምዕራብና በምሥራቅ» ዓለም ተከስቶ በነበረው ፍጥጫ ጊዜ፣ በዓለም ላይ ለሚመሠረቱ ሕዝባዊ መንግሥታት ዋና የሽከታ አርአያ የነበረ መንግሥት ነበር። 

በ ፲፱፻፵፯ ዓ.ም. የሁለተኛው ዓለም ጦርነት ፍጻሜ ጀምሮ ይሄ ኅብረት እስከፈረሰበት እስከ ፲፱፻፹፬ ዓ.ም ድረስ በተካሄደው የ«ቀዝቃዛ ጦርነት» ዘመን የሶቪየት ኅብረት በዓለም ከነበሩት ሁለቱ ተቃራኒ ኃያላን መንግሥታት አንዱ ሲሆን፤ በኢትዮጵያም ላይ በ፲፱፻፷፮ ዓ.ም የተመሠረተውን የአብዮት ወታደራዊ የደርግ መንግሥት በጦር መሣሪያ፤ በአማካሪነት፤ በገንዘብ፤ ወዘተረፈ፤ ዋነኛ ደጋፊና ታላቅ ተዋናይ አገር ነበር።

በሕዝባዊ አብዮታዊ እንቅስቃሴ መነሻነት በኃይልና በፖለቲካ ሚዛናት በሰባ ዓመታት ውስጥ ዳብሮ በዓለም ከሁለቱ ኃያላን መንግሥታት አንዱ እስከመሆን የደረሰው የሶቪየት ሕብረት በዕድሜው መግቻ ዓመታት ላይ በዓለም የተከሰቱ ሁለት ዓቢይ ጉዳዮች ለፍጻሜው ዋና ምክንያቶች እንደነበሩ ይገለጻል።

ኬኔዝ ኤስ ዴፊይስ (Kenneth S. Deffeyes) “Beyond Oil” ላይ እንዳሰፈረው አንደኛው፤ የአሜሪካው ፕሬዚደንት ሮናልድ ሬጋን ሳውዲ አራቢያ የነዳጅ ዋጋዋን እንድታወርድ በማበረታታቸው የሶቪዬት ኅብረት ከነዳጅ ሽያጥ የምታገኘውን ትርፍና የውጭ ምንዛሪ መጠን ክፉኛ ማመንመኑ፤ ሁለተኛ በሶቪዬት ሕብረት ሥልጣንን የተረከቡት ሚካይል ጎርባቾቭ በአገሪቱ ዱኛ (economy) እንዲሁም የኮሙኒስት አመራር ላይ ጥልቅ የሆኑ ፔሬስትሮይካ እና ግላስኖስት በሚል ስያሜ የሚታወቁትን ሁለት ሥር ነቅናቂ ለውጦችን መትግበራቸው ነው።

ለምሳሌ የጎርባቾቭ የግላስኖስት ውጅማ (policy)፣ ከዚህ በፊት በአስተዳደሩ መሣሪያዎች ከሕዝቡ በምስጢርነት ይደበቁ የነበሩ መንግሥታዊ/ሰብአዊ፤ ወ.ዘ.ተ. መረጃዎችን ማንኛውም ዜጋ የማግኘት መብቱን ያረጋገጠለት ዐቢይ ውጅማ ሲሆን፤ የፔሬስትሮይካ ስልት ደግሞ ከአብዮቱ ጀምሮ የማዕከላዊው የኮሙኒስት ሸንጎ በቁልፍ እጅ ይዞት የነበረውን ሥልጣን በማላቀቅ የቻራስፍና (democracy) ሥርዐት በሕዝቡ አእምሮ እንዲሰነጽ መንገድ የከፈተ ውጅማ ነው። 

የቀድሞው የሶቪዬት ኅብረት መጨረሻ ላይ ታኅሣሥ ፲፮ ቀን ፲፱፻፹፬ ዓ.ም ተደምስሶ በዓለም መንግሥታት እውቀትና ስምምነት ሕጋዊ ወራሽነት የሩሲያ መንግሥት እንደሆነ ታወጀ። ሩሲያም በዚህ መሠረት የቀድሞውን የሶቪዬት ሕብረት የውጭ ዕዳዎች እንዲሁም የውጭ ንብረቶች በፈቃዱ ተቀበለ። በቀድሞው የሶቪዬት ሕብረት ተፈርመው የነበሩም ዓለም አቀፍ ስምምነቶችንም ሩሲያ መቀበሏን አስታውቃለች።




#Article 327: ጥቅምት ፲፮ (183 words)


ጥቅምት ፲፮  በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፵፮ኛው ቀን ነው። ከዚህ ቀን በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፫፻፳ ቀናት በዮሐንስ፤ በማቴዎስ፤ እና በማርቆስ ዘመናት ደግሞ ፫፻፲፱ ቀናት ይቀራሉ

፲፱፻፵፬ ዓ.ም በብሪታንያ ብሔራዊ ምርጫ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንስቴር በነበሩት በዊንስተን ቸርቺል የሚመራው የኮንሰርቫቲቨ ፖለቲካ ቡድን አሸናፊ ሆኖ ቸርቺልም ለሁለተኛ ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆኑ።

፲፱፻፶፩ ዓ.ም. የፓን አሜሪካ አየር መንገድ ቦይንግ 707 አውሮፕላን ለመጀመሪያ ጊዜ ከኒው ዮርክ ከተማ ተነስቶ በፈረንሳይ አገር ፓሪስ ከተማ ድረስ በረረ።
 
፲፱፻፷ ዓ.ም ለ ሀያ ስድስት ዓመት በኢራን አልጋ ላይ ከተቀመጡ በኋላ ሞሐመድ ሬዛ ፓህላቪ በራሳቸው እጅ ዘውድ ጫኑ። የሚስታቸውን የንግሥት ፋራንም ዘውድ ጫኑላቸው።

፲፱፻፸፪ ዓ.ም የደቡብ ኮሪያው የጸጥታ ኃላፊ ኪም ጄ ክዩ ባልታሰበ አደጋ ፕሬዚደንታቸውን ፓርክ ቹንግ ሂን በሽጉጥ ገደሉ።

፲፱፻፹፯ ዓ.ም የአሜሪካው ፕሬዚደንት ቢል ክሊንተን በተገኙበት ስርዐት ዮርዳኖስ እና እስራኤል የዕርቅ ስምምነት ተፈራረሙ።

፲፱፻፺፬ ዓ.ም ብዙ ተችዎች በኢትዮጵያ በ ፳፻፩ ዓ.ም የኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ መንግሥት ያጸደቀውን “ጸረ ሽብር” ሕግ ምሳሌ ሆኖለታል የሚባለው የአሜሪካው “ፔትርዮትስ አክት” (Patriots Act) ህግ ሆኖ ጸደቀ። 

፲፱፻፲፪ ዓ.ም የመጨረሻው የኢራን ንጉሠ ነገሥት ሞሐመድ ሬዛ ፓህላቪ

፲፱፻፵ ዓ.ም የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚደንት ቢል ክሊንተን ሚስትና ስድሳ ሰባተኛዋ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሂላሪ ሮዳም ክሊንተን




#Article 328: ጥቅምት ፲፯ (141 words)


ጥቅምት ፲፯ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፵፯ኛው ቀን ነው። ከዚህ ቀን በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፫፻፲፱ ቀናት በዮሐንስ፤ በማቴዎስ፤ እና በማርቆስ ዘመናት ደግሞ ፫፻፲፰ ቀናት ይቀራሉ

፲፱፻፱ ዓ.ም. የወሎው ንጉሥ፤ የልጅ እያሱ አባት ንጉሥ ሚካኤል የልጃቸውን ከሥልጣን መውረድ አዋጅ ተቃውመው በጦር ኃይል ለማክሸፍ ከነሠራዊታቸው ወደ አዲስ አበባ ሲዘምቱ በአልጋ ወራሹ ራስ ተፈሪ መኮንን መሪነት እና በጦር ሚኒስቴሩ በፊታውራሪ ኃብተ ጊዮርጊስ አበጋዝነት የዘመተው ሠራዊት በሰገሌ ጠራ ሜዳ ወረዳ ላይ ገጥመው ከ፭ ሰዐት ውጊያ በኋላ የወሎ ሠራዊት ድል ሆነ። ንጉሡም ተማረኩ። 

፲፱፻፶፩ ዓ.ም. በፓኪስታን የአገሪቱ የመጀመሪያው ፕሬዚደንት ኢስካንደር ሚርዛ በ ጄኔራል አዩብ ካን በሚመራ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን ወረዱ።

፲፱፻፷፬ ዓ.ም. የኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ስሟን ቀይራ ዛይር ተብላ ተሰየመች።

፲፱፻፸፩ ዓ.ም ሦስተኛው የግብጽ ፕሬዚደንት አንዋር ሳዳት እና የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስቴር ሜናኽም ቤጊን የዓመቱ የኖቤል የሠላም ሽልማት ተሸላሚዎች መሆናቸው ይፋ ሆነ።

፲፱፻፵፰ ዓ.ም የማይክሮሶፍት መሥራችና ባለጸጋው የአሜሪካ ዜጋ ቢል ጌትስ




#Article 329: የአፍሪቃ አገሮች (129 words)


የአፍሪቃ አኅጉር ከዚህ የሚከተለው የአፍሪቃ 53 ነጻ አገሮችና 8 ጥገኛ ክልሎችን ያጠቃለለ ዝርዝር ሲሆን፤ ዋና ከተሞችን፣ ቋንቋቸውን፣ ገንዘባቸውን፣የሕዝቦቻቸውን ብዛት፣ የገጸ ምድራቸውን ስፋትና የብልጽግናቸውን መለኪያ (GDP per capita ) ያካትታል።  
የአፍሪቃ አህጉር ከምድር ጠቅላላ ስፋት ስድስት በመቶውን፤ ከመሬቷ ደግሞ ወደ ሃያ ተኩል በመቶውን ይሸፍናል። በገጸ ምድር ስፋትና በሕዝብ ቁጥር እስያን ተከትሎ ሁለተኛ መደብን የያዘ አህጉር ነው።  እ.ኤ.አ በ 2005 የአፍሪቃ ሕዝቦች ብዛት ከ ዘጠኝ መቶ ሚሊዮን በላይ ወይም ከጠቅላላው የዓለም ሕዝብ አሥራ አራት በመቶ እንደሆነ ተገምቷል።
አህጉሩ በሰሜን በሜዲተራንያ ባሕር ፤ በ ሰሜን ምስራቅ የሱዌዝ ቦይ እና የቀይ ባሕር} ፤ በደቡብ ምስራቅ የሕንድ ውቅያኖስ ፤ በምዕራብ ደግሞ በአትላንቲክ ውቅያኖስ የተከበበ ነው። ስምንት መቶ ዘጠና አምስት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሺህ ሕዝብን የሚያጠቃቅሉት የምዕራብ ሰሃራ ግዛት እንዲሁም ከሞሮኮ በስተቀር ሁሉም ነጻ ሉዐላዊ አገሮች የአፍሪቃ ኅብረት አባላት ናቸው።

ይህንን ይመልከቱ የሰሜን አሜሪካ ሀገሮች




#Article 330: ጥቅምት ፳፬ (170 words)


ጥቅምት ፳፬ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፶፬ኛ ቀን ነው። ከዚህ ቀን በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፫፻፲፪ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፫፻፲፩ ቀናት ይቀራሉ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዚህ ዕለት በየወሩ በ እቲሳ ቡልጋ የተወለዱት የኢትዮጵያዊው የቅዱስ አቡነ ተክለ ኃይማኖት መታሰቢያ ቀን አድርጋ ታከብረዋለች።

፲፬፻፹፮ ዓ.ም የጄኖአው ተወላጅ ክሪስቶፎሮ ኮሎምቦ (Christopher Colombus) የአትላንቲክ ውቅያኖስን ከአውሮፓ ወደምዕራብ የማቋረጥ ሁለተኛው ጉዞው፤ ለመጀመሪያ ጊዜ የዶሚኒካ ደሴትን አገኘ።

፲፰፻፹፮ ዓ.ም. ፓናማ በአሜሪካ ማበረታታት ተነስታ ከኮሎምቢያ ቅኝ ግዛትነት ነጻነቷን አወጀች። የአሜሪካው ፕሬዚደንት ቴዎድሮስ ሩዝቬልት የፓናማ ቦይን ለመቅደድ ፈልገው ኮሎምቢያ ለዚሁ ሥራ መከፈል የፈለገችውን ዋጋ ስላልተስማሙበት ፓናማ ነጻ አገር እንድትሆን ጥረታቸው ተሳካ።

፲፱፻፶ የሶቪዬት ሕብረት በጠፈር የመጀመሪያውን እንስሳ፤ ላይካ የተባለውን ውሻ፤ በስፑትኒክ ሁለተኛ መንኲራኩር ወደጠፈር ተኮሰች።

፲፱፻፷፫ ዓ/ም ሰባ ከመቶውን  የአዲስ አበባ ውሐ የሚያስተናግደው የለገዳዲ የውሐ ግድብ ተመርቆ አገልግሎቱን ጀመረ።
 
፲፱፻፺፯ ዓ.ም. የአሜሪካው ፕሬዚደንት ጆርጅ ወከር ቡሽ ለሁለተኛና ለመጨረሻ ጊዜ ተመረጡ።

፲፱፻፹፱ ዓ.ም የመካከለኛው አፍሪካ ሪፑብሊክ አገርን በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ከያዙ በኋላ ራሳቸውን በዘውድ ያነገሡት ዣን ቢዴል ቦካሳ በተወለዱ በሰባ አምስት ዓመታቸው አረፉ።




#Article 331: ኮንግ-ፉጸ (259 words)


ኮንግ-ፉጸ ወይም ኮንፉክዩስ (ቻይነኛ፦ 孔夫子) 558-487 ዓክልበ. የኖረ ቻይናዊ ፋላስፋ ነበረ። ፍልስፍናውና ትምህርቱ «የኮንግፉጸ ትምህርት» በተለይ በቻይና፣ በኮርያ፣ በጃፓንና በቬትናም አገር ባህሎች ላይ ጥልቅ ያለ ተጽእኖ አሳድሮዋል። በእርሱ ፍልስፍና፣ የግለሰብና የመንግሥት ግብረገብ፣ የኅብረተሠባዊ ግንኙነቶች ትክከለኛነት፣ የወላጆች ክብር፣ ፍርድና ቅንነት ልዩ ትኩረት አገኙ።

ኮንግ-ፉጸ በሉ ክፍላገር የተወለደ ሲሆን፣ በክፍላገሩ ውስጥ የፖለቲካ ሰው ነበር። በ509 ዓክልበ. የአንድ ከተማ ከንቲባ ከመሆኑ በኋላ፤ የክፍላገሩ ወንጀል ሚኒስትር ሆነ። ነገር ግን በፖለቲካ ረገድ በሙሉ ስኬታማ አልነበረም።  ከክፍላገሩ ሦስት ታላላቅ ኃይለኛ ቤተሠቦች ወገኖች፣ ሁለቱ አምባዎቻቸው እንዲፈርሱ በመጨረሻ ተስማሙ፣ እንጂ ሦስተኛው እምቢ ብሎ ለኮንግ-ፉጸ እቅድ  አልተከናወነለትም።  ስለዚህ በ505 ዓክልበ. ኮንግ-ፉጸ ከሉ ክፍላገር ሸሽቶ ለጊዜው በስደት ኖረ። 

ከዚያ እስከ 491 ዓክልበ. ድረስ ወደየክፍላገሩ ቤተ መንግሥት ጎብኝቶ የፖለቲካ ፍልስፍናውን ያስተምር ነበር፤ ሆኖም ሁላቸው ምክሩን ስላላስገቡ ይህ ደግሞ በጣም ስኬታም አልነበረም። በ491 ዓክልበ. ወደ ሉ በክብር ተመልሶ ከዚያ እስከ ዕረፍቱ ድረስ ወይም ለ4 ዓመታት ዕውቀቱን ለ77 ደቃ መዛሙርት (ተማሪዎች) ያስተምር ነበር። 

ኮንግ-ፉጸ ከዘመኑ በፊት የኖሩ ስድስት ዋና ማስተማርያ መጻሕፍት አቀነባበራቸው። እነዚህም «ስድስቱ ጽሁፎች»፦

በተጨማሪ የኮንግ-ፉጸ ጥቅሶች አናሌክትስ (ሉንዩ) በተባለ ጽሑፍ ተቀነባብረዋል። 

ከኮንግፉጸ ሕይወት በኋላ ትምህርቶቹ ተከታይነት አገኙ፤ በ148 ዓክልበ. የሃን ሥርወ መንግሥት የኮንግ-ፉጸ ትምህርት ይፋዊ አደረጉት። ወደ ማዕረግ ለመሾም ዕጩዎቹ በዚህ እምነት መጻሕፍት ይፈተኑ ነበር። ከ212 እስከ 1360 ዓም ድረስ ግን ልዩ ልዩ የቻይና ግዛቶች ዳዊስም ወይም ቡዲስም የመንግሥት ሃይማኖት አድርገው ነበር። እንደገና 1360-1903 ዓም ዘመናዊው የኮንግፉጸ ትምሕርት በቻይና ይፋዊ ሆነ።  

በዳዊስም ሃይማኖት ዘንድ፣ የእምነቱ መሥራች ላው ድዙ በ539 ዓክልበ. ያሕል ዳው ዴ ቺንግ እንደ ጻፈ፣ እንዲሁም አንዴ ከኮንግ-ፉጸ ጋራ እንደ ተገናኙ ይታመናል። በዘመናዊ ዳዊስም በኩል፣ ላው ድዙና ኮንግ-ፉጸ ሁለቱ እንደ አማልክት ይከብራሉ።  

በተለይ በፓኪስታን የሚታወቅ ከእስልምና የወጣ ክፍልፋይ አሕማዲያ እስልምና እንዳለው፣ ኮንግ-ፉጸ እና ላው ድዙ ሁለቱ የአላህ ነቢዮች ነበሩ። 




#Article 332: አርጀንቲና (6099 words)


አርጀንቲና ወይም በይፋ አርጀንቲናዊ ሬፑብሊክ (እስፓንኛ፦ República Argentina /ሬፑብሊካ አርሔንቲና/) በደቡብ አሜሪካ የሚገኝ አገር ነው። ዋና ከተማ ብዌኖስ አይሬስ ነው።

መደበኛው ቋንቋ እስፓንኛ ሲሆን ቀበሌኛው በእስፓንያ ከሚሰማው ትንሽ ይለያል። ሌሎችም ቋንቋዎች የሚናግሩ ሕዝቦች አሉ፣ ወይም ኗሪ ቋንቋዎች እንደ ቀቿ፣ ወይም አውሮፓዊ ቋንቋዎች (በተለይ ጣልኛ፣ ጀርመንኛ)

አርጀንቲና እ.ኤ.አ. ከ 1994 ጀምሮ በብሔራዊ መስተዳድር እና 24 ራሳቸውን በራሳቸው የሚያስተዳድሩ መንግስታት የተዋሃደ የፌዴራል መንግስት ነው የተደራጀችው

የአርጀንቲና ቅድመ-ኮሎምቢያ ታሪክ በስፔን ወረራ እና ቅኝ ግዛት ከመደረጉ በፊት የአርጀንቲና ሪ Republicብሊክ የአሁኑን የአካባቢ ባህላዊ እድገት ያመለክታል ፡፡

በአሁኑ ጊዜ በአርጀንቲና የሚቆጣጠሩት የመጀመሪያ የህዝብ ብዛት በሎስ ቶልዶስ እና በፒድራ ሞሱ ግኝት መሠረት በ 12 ኛው ወይም በ 13 ኛው ሺህ ዓመት AP ነው ፡፡ ፓፓታኒያ ፣ ፓምፓ እና ቾኮ አርሶ አደሮች በሰሜን ምዕራብ ፣ በኩዮ ፣ በሴራስራስ ደ ኮርዶባ እና በኋላ ደግሞ በሜሶpotጣሚያ ውስጥ ሰፈሩ ፡፡ በሰሜን ምዕራብ ትስታል በሰሜን ምዕራብ ትልቁ የቅድመ-ኮልበስያን ከተማ በአሁኑ ጊዜ በአርጀንቲና ክልል ውስጥ የሚገኝ ሲሆን የ 2000 ነዋሪ ህዝብ ብዛት ያለው ነው ፡፡.36

የአርጀንቲና የአገሬው ተወላጆች ህዝቦች በሁለት ትላልቅ ቡድኖች ተከፍለው ነበር-አዳኞች እና ሰብሳቢዎች ፣ ፓፓጋኒያ ፣ ፓምፓ እና ቻኮ የኖሩት ፡፡ አርሶ አደሮቹ በሰሜናዊው በኩዮ ፣ በሴሬስ ደ ኮርዶባ እና በኋላ ደግሞ በሜሶፖታሚያ ሰፈሩ ፡፡

በሰሜን ውስጥ ትስታይል በአሁኑ ጊዜ በአርጀንቲና ግዛት 3000 ነዋሪዎችን የያዘችና በአሁኗ የአርጀንቲና ክልል ውስጥ የሚገኝ ትልቁ የቅድመ-ኮምቢያን ከተማ ነበረች።

በዚህ ክልል ውስጥ የመጀመሪያዎቹ የሰዎች ሕይወት ትዝታዎች ከሶስት ሺህ ዓመታት በፊት የመጀመሪያውን የሜቶሊቲክ እና የኒዎሊቲክ ባህላዊ መዋጮን ካካተቱ የፓሊዮሎጂ ባህላዊ ደረጃዎች ጋር ይዛመዳል ፡፡ በሦስት ዋና ዋና ቡድኖች ሊከፋፈሉ ከሚችሉ የተለያዩ ማህበራዊ ድርጅቶች ጋር በተለያዩ የአገሬው ተወላጅ ሕዝቦች:

በ 14 ኛው እና በ 15 ኛው ክፍለዘመን የኢንኮ ግዛት አሁን ያሉትን የጁጁይ ፣ ሳልታ ፣ ካታማርካ ፣ በጣም ሩቅ ምዕራባዊ ቱትራን አውራጃን ፣ ላውን ሪዮጃጃና እና ሳን ጁዋን የሰሜን ምዕራብ ግዛት ሰሜናዊ ምዕራብን ድል አደረገ ፡፡ ሞንዶዛ እና ምናልባትም የሰሜናዊ ሳንቲያጎ ዴል ኤስትሮሮ ግዛቶ ofን የቱዋርትባኦ ደቡባዊ ክፍል ወይም የግዛቱ ግዛቶች ወደ ሆኑት ኮሱዮ በማካተት ይሆናል ፡፡

በተለምዶ ፣ ወረራ የሚከናወነው በኢንካ ንጉሠ ነገሥት ቱፋክ ዩፒንኩዊ ነው ፡፡ በክልሉ ውስጥ ያሉ በርካታ የጌትነት ጌቶች ፣ እንደ ኪቹቻስ ፣ መስኩዋናይ (አአካማ) ፣ ዋልድስ ፣ ዲያጉዋስ እና ሌሎችም ፣ ለመቃወም ቢሞክሩም ኢናስ በእነሱ ላይ የበላይነት ያላቸውን የቼቻ ነገዶች ወይም ከተባረረ ከ Chicha ነገዶች ፣ የአሁኑ የቦሊቪያ ክልል ደቡብ-ምዕራብ በሚባለው አካባቢ ይኖር ነበር። እንደ ሳውድ አከባቢዎች ፣ ሉሊት-ቶኖኮቴ እና ሄኒያ-ካሚር (ታዋቂው “ቀንድ አውሎን” በመባል የሚጠሩ) ያሉ ሌሎች ሰዎች የ Inca ወረራ በተሳካ ሁኔታ በመቃወም ገለልተኛ ጌትነት ኖረዋል ፡፡

የግብርና እና የጨርቃጨርቅ ማዕከላት ፣ ሰፈሮች (ኮላካ እና ታምቦስ) ፣ መንገዶችን (“ኢንካ ባቡር”) ፣ ምሽጎችን (ፓucካዎችን) እና ከፍተኛ የተራራ ሥፍራዎችን ፈጥረዋል ፡፡ አንዳንድ ዋናዎቹ የቲልካ ፣ የፓስካ ፣ የኢንካ ፣ የፓሉካ ፣ መቅደስ ፣ የሎንዶን ፍርስራሽ እና የኪልሜስ ፍርስራሾች ናቸው።

የስፔን ወረራ እና የአርጀንቲና ቅኝ ግዛት በ 16 ኛው ክፍለዘመን እና በ 19 ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ መካከል ያለውን የስፔን ግዛት በተቆጣጠረበት እና ከተቆጣጠረበት የ 19 ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ መካከል ያለውን ጊዜ ያመለክታል። በዚህ ጊዜ አርጀንቲና (ብሩ ሀገር) የሚለው አገላለጽ ከሪዮ ዴ ላ ፕላታ ወደ ሰሜን ምዕራብ የሚዘረዝር ድንበር ያለ ክልል ለመሰየም ለመጀመሪያ ጊዜ ብቅ ብሏል ፡፡ ይህ ጊዜ የስፔን ለመጀመሪያ ጊዜ የአርጀንቲና ግዛት ወደ ተለያዩ አካባቢዎች መምጣትን ያጠቃልላል ፣ በዚህ ጊዜ ውስጥ የአገሬው ተወላጆች ቀደም ሲል ያንን ክልል የጠሩበትን ስምም በሌሎችም በአዲስ ስም ሰየማቸው ፡፡

በአርጀንቲና የቅኝ ግዛት ዘመን በሦስት ጊዜ ይከፈላል-ግኝት እና ወረራ ፣ በዚህ ጊዜ ውስጥ የግዛቱ ፍተሻዎች እና ዋና ከተሞች መመስረት; የስፔን ሰፈሮች የአገሬው ተወላጅ በሆኑት ሕዝቦች ላይ ተዋግተው ጥቂት አካባቢዎችን እና ኢኮኖሚያዊ ለውጦችን በማስመዝገብ ማጠናቀር የሞከሩበት ገዥው ዘመን ፣ እና የስፔን ምክትል አባረረ እና የራስ-መንግስት ቦርድ እስከ ተሾመበት እስከ 1810 እ.ኤ.አ. ግንቦት 18 አብዮት ድረስ ያለውን የምክትል ጊዜ። የአርጀንቲና የነፃነት ጦርነት ብዙውን ጊዜ የአርጀንቲና ታሪክ አካል ተደርጎ ተጠቅሷል።

አውሮፓውያን ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ዘመናዊው የአርጀንቲና ክልል የገቡት ሁዋን ዲ íዝ ደ ሶስ ወደ ሪዮ ዴ ላ ፕላታ ወረደ። በኋላ ፣ በ 1520 የፈርናን ደ ማሌላንሌስ ጉዞው በሳንታ ጁሊያን የባህር ዳርቻ ፣ በሳንታ ክሩዝ አውራጃ ዛሬ መርከቦቹን አግዶላቸዋል። ፎርት ሳንቴይቲ መንፈስ ለመጀመሪያ ጊዜ የአውሮፓ ሰፈር ሲሆን በ 1527 በፓራና ወንዝ ዳርቻዎች ላይ ተጭኖ ነበር ፡፡ የሰሜን ምዕራብ እና የአገሪቱ የመጀመሪ ፍለጋ በ 1543 እ.ኤ.አ. በሴኔዶ ዴ ሮጃስ መግቢያ ነበር ፡፡ የአሱሱኒ (1537) ፣ f ሳንቲያጎ ዴል ኢስትሮ (1553) ፣ ኮሮዶባ (1573) እና ቡነስ አይረስ (1536/1580) ነበሩ ፡፡ በሰሜናዊው የአርጀንቲና ግዛት ሰሜናዊ አጋማሽ ላይ የታገደ የቅኝ ግዛት ማቋቋም መሠረቶች በስፔን ዘውዴ (የሪዮ ዴ ላ ፕላታ አስተዳደር) ተገ subject ናቸው። የስፔን ግዛት በርካታ ከተሞችን ያቋቋመ ሲሆን እ.ኤ.አ. በ 1860 የአርጀንቲና ሪ Republicብሊክን ለመመስረት ከተመሠረቱት አሥራ አራት አውራጃዎች ጋር በሚመደበው ሕዝብ ላይ የቅኝ ግዛት ሕግ አወጣ ፡፡ በቅኝ ገዥው ዘመን ማብቂያ ላይ የስፔን ግዛት የሪዮ ዴ ላ ፕላታ ተተኪ ግዛቶችን እና የወቅቱን የቦሊቪያ ፣ የፓራጓይ እና የዩራጓይ ግዛቶች ግዛትን የሚያካትት የሪዮ ዴ ላ ፕላታ ምክትል ፈጠራን ፈጠረ።

በ 1537 በፕሬስ ፖል ሦስተኛው የብሉሚሊስ ዴዩስ ቡልጋሪያ የአገሬው ተወላጅ የክርስትናን ተፅእኖ እና ችሎታ ሁሉ በማወጅ በአሜሪካ ውስጥ በስፔን ፣ በአንግሎ ሳክሰን እና በፈረንሣይ ቅኝ ግዛት መካከል ከፍተኛ ልዩነት ነበር ፡፡.42 በስፔን ግዛት ውስጥ ማህበራዊ አንድነት የተካሄደው በካቶሊክ ቤተክርስቲያን እምነት አንድነት ነበር ፡፡ የቅኝ ግዛት በአንደኛው ክፍለ ዘመን የስፔን ግዛት የአሁኑን የአርጀንቲናን ግዛት አንድ ሦስተኛ ያህል ድል በማድረግ ነዋሪዎ whoን ለሚኖሩት ሕዝቦች የመጀመሪያ ተገዥ በመሆን የስነ ሕዝባዊ ጥፋት አመጣ ፣ ለዚህም ነው የአውሮፓ ድል አድራጊዎች የተጠለፉ ባሮችን በጥቁር አፍሪካ ውስጥ አስገቡ ፡፡ በ 17 ኛው ክፍለዘመን የጁኢት ጓራኒ ተልእኮዎች የተቋቋሙት በጊራኒ እና በተዛመዱ ህዝቦች መካከል በኢየሱስ ማህበር የተቋቋሙት የሚስዮናውያን ማህበረሰቦች ነበር ፣ እነዚህ የአሁኖቹ የአገሬው ተወላጅዎች ባርነት በወንጌላዊነቱ ፣ በአገሬው ተወላጆች እና በፓራጓይ ክፍል የሚገኙትን ለመከላከል ነው ፡፡ እና ብራዚል ሥራቸውን በተሳካ ሁኔታ አጠናቅቀዋል ፡፡ እ.ኤ.አ. እስከ 1768 ድረስ የስፔኑ ንጉሥ ካርሎስ ሦስተኛው ኢየሱሶችን አባረረ ፡፡

የአሁኑ የአርጀንቲና ክልል እና ነዋሪዎቹ የአገሬው ተወላጅ ሕዝቦች በስፔን በቅኝ ግዛት ስር አልነበሩም ፣ በተለይም በቻኮ (በቺቺ እና በኬም) እና በፓምፓን-ፓፓጋኒያን (በቱሁቼ-ማpuቼ-ራኳል) ክልሎች ስር። . እ.ኤ.አ. ከ 1560 እስከ 1667 መካከል ባለው የወቅቱ አርጀንቲና ሰሜን ምዕራብ ውስጥ የካልኩኪ ጦርነቶች የሚባለውን የካልኩኪ ጦር መርከቦች በመባል የሚታወቁትን ጠንካራ ተቃውሞዎች ጠብቀዋል ፡፡

በአብዛኞቹ የቅኝ ግዛት ጊዜያት የአርጀንቲና ግዛት የፔሩ ምክትል አካል ነበር ፣ እስከ 1776 ድረስ የስፔን ንጉሥ ካርሎስ ካርሎስ ሦስተኛው ግዛቱ ሪዮ ዴ ላ ፕላታ ከሚባል ክልል ጋር እስኪተካ ድረስ። የቦነስ አይረስ ከተማ እንደ የንግድ ማእከል እያደገች በመሄ and እና በተቻለ መጠን የፖርቱጋልን ጥቃት በተሻለ መቃወም እንዲሁም በቀላል ተደራሽነት በመገኘቷ ዋና ከተማዋ ሆነች ፡፡

በ 18 ኛው ክፍለ ዘመን የዱር ከብቶች ተፈጥሮአዊ መባዛት እና በፓምፓ ማሳዎች ፣ በምስራቃዊ ሪዮ ደ ላ ፕላታ እና በደቡባዊ ብራዚል ውስጥ ፈረስ Gaucho ተብሎ በሚጠራ ፈረስ ላይ ልዩ ገለልተኛ ገበሬ እንዲመስል ምክንያት ሆኗል ፡፡ ለወንዶች እና ለቻይና በሴቶችም ፡፡ ጋውቾዎች የራሳቸውን ባህርይ ያዳበሩ ባህል ነበራቸው ፣ በ 19 ኛው ክፍለ ዘመን ሁለተኛ አጋማሽ እስከሚሸነፍ ድረስ የእንስሳትን እና የመሬትን የመጠቀም መብታቸውን ለማስጠበቅ የእራሳቸውን ባህሪዎች ባህል አደረጉ ፣ ተዋግተው ተዋግተዋል ፡፡ ይህ በዱር እንስሳት ውስጥ ያለው ይህ ሀብታም ከስፔን እና ክሪዮል ህዝብ ጋር የእንስሳት ሃብት የማይለዋወጥ ትግል የጀመረው በቻኮ ፣ ፓምፓ እና ፓራሲታኒያ ውስጥ የአገሬው ተወላጅ የእኩልነት ባህል እንዲታይ ምክንያት ሆኗል።

እስከ አሥራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ድረስ አብዛኛው ፓፓጋኒያ እና ፓምፓስ በተለያዩ የአገሬው ተወላጆች ቁጥጥር ሥር ነበሩ-በዋነኝነት ቾንኬኮች እና ከዚያም በፓትፓኒያ ውስጥ ያሉት ማpuchesች እና በፓምፓስ ሜዳዎች እስከ አሥራ ዘጠነኛው ክፍለ-ዘመን የመጨረሻ ሩብ ድረስ። በተመሳሳይም አብዛኛው የቻኮ ክልል ግዛቶች በአውሮፓውያን ቅኝ ግዛት አልነበሩም ፣ ነገር ግን እንደ ኪም ፣ ሞኮቭስ (ሞኮቪስ ወይም ሞኮቪስ) ፣ ፒላጊስ እና ichቺስ እስከ 20 ኛው ክፍለዘመን መጀመሪያ እስከሚጀምሩ ድረስ ተወስደዋል። የሚዘናጉ የአገሬው ተወላጆች ቁጥር በስፔን ሕዝብ ላይ በቋሚ ጥገኛ ግንኙነቶች ተገፍቷል ፡፡ ምንም እንኳን በትውልድ ትውልድ ሲያልፍ ምንም እንኳን እንደ “ክሪዮል” በሚባል የብሔራዊ መለያ ቁጥር ቢቆጠርም ፣ ይህ የክትትል ሂደት በአጠቃላይ በሰሜን ምዕራብ የአርጀንቲና ክልል ውስጥ ከፍተኛ የሕዝብ ተወላጅ ተሳትፎ በ 1780 ከታሪካዊ ክልል ጋር የተሳተፈ በመሆኑ የተረጋገጠ አይደለም ፡፡ በኢንካ ቱፋክ አማሩ II የሚመራው ኩዙኮ።

በአርጀንቲና ታሪክ እ.ኤ.አ. እ.ኤ.አ. በ 1810 እ.ኤ.አ. በግንቦት 18 አብዮት መካከል እና ሁሉንም ብሔራዊ ባለስልጣናት ባጠፋው አናarch መካከል መካከል የዘለቀ የነፃነት ዘመን በመባል ይታወቃል ፡፡

በዚህ ወቅት የተባበሩት የተባበሩት የሪዮ ዴ ላ ፕላታ የአሁኑ የአርጀንቲና ሪ Republicብሊክ የመጀመሪያ ስማቸው - ሉዓላዊ ሀገር በመሆን ህልውናቸውን የጀመሩት በተራዘመ የነፃነት ጦርነት አማካኝነት በተሳካ ሁኔታ ድጋፋቸውን በመግለጽ ነፃነታቸውን አወጁ ፡፡ ግን በዚህ ጊዜ ውስጥ እራሳቸው በቋሚነት በሁሉም ግዛቶቻቸው ተቀባይነት ያገኙ ማዕከላዊ መንግስት እና ህገ መንግስት አልሰጡም ፡፡

በተጨማሪም በዚህ ወቅት ነበር የሪዮ ዴ ላ ፕላታ ምክትል አካልነት ከአርጀንቲና ተለይተው የተለያዩባቸው ግዛቶች ፤ ፓራጉዋይ ፣ የራሳቸውን በራስ የመመራት ሂደት በመደገፋቸው። የላይኛው ፔሩ ፣ ከስፔን ኃይል ስር ለመቀጠል ፣ በኋላም እንደ ቦሊቪያ ሪ independentብሊክ ነፃ የምትሆንበት ፡፡ እና የምስራቅ ባንድ ፣ ከብራዚል ይወርሷታል ፣ እናም እንደ ምስራቃዊ የኡራጓይ መንግሥት ገለልተኛ ትሆናለች ፡፡

የወቅቱ መጀመሪያ የተቋቋመው የተባበሩት መንግስታት ግዛቶች የመጀመሪያው መንግስት የተፈጠረበት ቀን እና የካቲት 11 ቀን 1820 የመጨረሻው የካቲት (እ.አ.አ) የመጨረሻ የበላይ ጠቅላይ ሥራ አስፈፃሚ ሆሴ ሮዴን ለቅቆ ሲወጣ ነው ፡፡ ብሄራዊ ኮንግረስ ፡፡

በሪዮ ዴ ላ ፕላታ ስም የመጀመሪያው የሪፖርት ቦርድ በይፋ የሪዮ ዴ ላ ፕላታ ስም የሆነው ሚስተር ዶን ፈርናንዶ ስድስተኛ አርብ ግንቦት 25 ቀን 1810 እ.ኤ.አ. ፕሌታ ፣ ምክትል ቦልዛር ሂሊጎ ደ ሲኔኔሮ የተባረረ ሲሆን የተባበሩት መንግስታት የዩኒቨርስቲዎች የመጀመሪያ ቦርድ ፕሬዝዳንት ሆነው የሾሙት ሜይ አብዮት ድል እ.ኤ.አ. የመንግስት መቀመጫ የተቋቋመው በቦነስ አይረስ ፎርስ ውስጥ ሲሆን ፣ እ.ኤ.አ. ከ 1776 ጀምሮ የምክትል መስሪያ ቤቶች መኖሪያና የመንግሥት መስተዳድር በሚገኝበት የመንግሥት አዳራሽ ተቋቁሟል ፡፡ የመጀመሪያው ቦርድ እ.ኤ.አ. እስከ ታህሳስ 18 ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ ኖሮት ነበር ፣ ምክንያቱም ከውስጡ የውክልና ሃላፊዎችን በማካተት ለሪዮ ዴ ላ ፕላታ ማራዘሚያ ለረጅም ጊዜ የዘለቀ የነፃነት ጦርነት ያስመዘገበው ትልቁ ቦርድ ሆነ ፡፡ ከስፔን (1810-1824) ፡፡

የነፃነት ጦርነት እየተስፋፋ በነበረበት ጊዜም በ 1814 የእርስ በርስ ጦርነት መጀመሪያ ላይ በተነሳው እና በቋሚነት ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ የሚቆየውን የአዲሲቷ አዲስ መንግስት አወቃቀር ውዝግብ አስነስቷል ፡፡ የፌዴራል ክፍልፋዮች መሪ ፣ የምሥራቃዊ ጆሴ ገርቫሺዮ አርጊስ የነፃ ህዝቦች ህብረት ጠበቃ ፣ በቡኤነስ አይሪስ የመተዳደር እምቢተኛ የክልሎች ሊግ ተብሎ ተጠርቷል ፡፡ ኮንቴፔሲዮን ዴ ዩራ ኡራጓ የተባለ የምስራቅ ኮንግረስን አደራጅቷል ፣ ይህም የስፔን ገለልተኝነቱ እንደተገለፀው አሁንም ድረስ ማወጅ መቻሉን ወይንስ ክርክር አከራካሪ ነው ፡፡

እ.ኤ.አ. ሐምሌ 9 ቀን 1816 በሳን ሚጌል ደ ቱከም ከተማ ውስጥ ፣ በሰሜን ምዕራብ እና በማእከላዊ ምዕራባዊ የአገሪቱ ክልሎች የተወካዮች ምክር ቤት እና ከቡነስ አይረስ የተወሰኑት ከከፍተኛ ፔሩ ከተባረሩ የተወሰኑ ተወካዮች ጋር ተሰብስቧል ፡፡ የሚከተሉትን ቀመር በመጠቀም በደቡብ አሜሪካ የተባበሩት መንግስታት ግዛቶች ነጻነት ፡፡

የተሰረቁትን መብታቸውን ይመልሳሉ ፣ እናም ነፃ እና ገለልተኛ በሆነው የንጉሥ ፈርዲናንድ VII ፣ ተተኪዎቹ እና የከተማ […]

በደቡብ አሜሪካ የተለያዩ አካባቢዎች አዲሶቹ መንግስታት በክልሉ ውስጥ ያለውን የስፔን ንጉሣዊ ስልጣን ለማስመለስ የሚሞክሩትን የንጉሣዊያን ወታደራዊ ተቃራኒዎችን መቋቋም ነበረባቸው ፡፡ ለነፃነት ጦርነቶች ተጀመሩ ፡፡ የአንዳንድ ዋና አዛdersች ሰሜናዊ ጦር ሰራዊት አዛዥ የሆኑት ሆሴ ዴ ሳን ማርቲን የተባሉ የአንዲስ ጦር ሠራዊት ፈጣሪ ፣ ማርቲን ሚጌል ደ ጎሜዝ ፣ የጎጃው ጦርነት አዘጋጅ እና ጁና አዙሩዲ የተባሉ የጦር ኃይሎች ጦር አዛዥ የነበሩ ናቸው ፡፡ አልቶ ፔሩ. የአርጀንቲና ግዛት ሳን ማርቲንንን እንደ ነፃነቷ ታላቅ ወታደራዊ ጀግና እንደሆነች በመቁጠር “የአባት አባት አባት” የሚል ማዕረግ አከብረዋታል። ከሲሞን ቦሊቫር ጋር በመሆን ፣ በአህጉሩ ላይ የስፔን መኖር ለተቋረጠው የነፃነት ሥራዎች ሀላፊነታቸው ነበሩ ፡፡

የመጀመሪያዎቹ ዐሥርት ዓመታት ገለልተኛ አገር እንደመሆናቸው ግጭት ተጋርጦ ነበር-የዩኒተርስታዎችን ቅርስ በመጋፈጥ የፌደራል ፌዴሬሽኑ በተደጋጋሚ የየክልሎች ነፃነቶችን በመጠበቅ ይነሳሉ ፣ ይህም ከዓመቱ ኤክስሲ ተብሎ የሚጠራው - የአገሪቱ ክፍል ወደ በራስ-ገዝ ግዛቶች መከፋፈል ይመራል ፡፡ አገሪቱ በ 1825 እና በ 1827 መካከል ለአጭር ጊዜ ብቻ የምትቆይ አገር ብትሆንም በወታደሮች መሪዎች እስከ 1852 ድረስ የመንግሥት መንግሥት አልነበራትም ፡፡

የነፃነት ጦርነት እስከ 1825 ድረስ የቀጠለ ሲሆን በሰሜን ድንበር እና በፔሩ ግን በተሻለ ሁኔታ ተዋግቷል ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ምስራቃዊው አውራጃ በፖርቱጋል መንግሥት ወረራ ከነበረችበት ወደ ብራዚል መንግሥት ተሻገረ ፡፡ በዚህ የተነሳ የተከሰተው የብራዚል ጦርነት እ.ኤ.አ. በ 1828 በቀዳሚ የሰላም ስምምነት የተፈረጀውን ፣ በምስራቃዊ የኡራጓይ ግዛት ስም የተጠራጠረውን ክልል ገለልተኛ በሆነ በይፋ ባወጀው እ.ኤ.አ. በ 1825 የላይኛው ፔሩ የቦሊቪያ ሪ formedብሊክን ተቋቋመ ፡፡ ቀጥሎም የታራጃ ከተማና ግዛቱ ታከለ ፡፡

በተሻሻሉ ወታደራዊ ዘመቻዎች በሕንዶቹ ላይ የተካሄደ ዘመቻን በተወሰነ መጠን ከፍ ለማድረግ የረዳው ቀሪ ክልል በ 1820 ዎቹ አጋማሽ በይፋ ‹አርጀንቲና› የሚለውን ስም መጠቀም ጀመረ ፡፡ ዴ ላ ፕላታ በሕገ-ወጥነት ወደቀ ግን ቢሆንም በአገሪቱ ሕገ-መንግስት እንደ ሀገር አማራጭ ስም መጠቀሱ ቀጥሏል።

እ.ኤ.አ. በ 1830 ዎቹ መጀመሪያ የአርጀንቲና ኮንፌዴሬሽን ስም የተሰየመ ዝንቦች በመላው አገሪቱ ስኬታማ ሆነዋል ፡፡ ከሃያ ዓመታት በላይ የቦነስ አይረስ የፌዴራል ገዥው ጁዋን ማኑኤል ደ ሮዛ በእውነቱ ከፍተኛውን ብሔራዊ ባለሥልጣንን ይገምታል ፣ ምንም እንኳን በንድፈ ሀሳብ ምንም እንኳን የክልሎች የውጭ ወኪሎች የውጭ ወኪል ብቻ ቢሆንም ፡፡

በግርማዊ ቀዳማዊ አ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ፣ ተከታታይ የክፍለ-ጊዜ አመፅዎችን ፣ እንዲሁም የፈረንሳይ ሪዮ ዴ ላ ፕላታ እና ከዚያም የታላቋ ብሪታንያ እና የፈረንሳይ የጋራ ድንበር ተዋግቷል ፡፡ እንዲሁም በፔሩ-ቦሊቪያ ኮንፌዴሬሽን እና በኡራጓይያ ዋና ከተማ በሆነችው በሞንቴቪዲ በተባለችው የመከላከያ መንግሥት በተባበሩት የአርጀንቲና የእርስ በእርስ ጦርነትዎች መካከል የተደረጉ ግጭቶች ነበሩት ፡፡

ሊተገበር የሚችል ሰላም ቢኖርም እና በሊቶራል አውራጃዎች ውስጥ ቢያንስ ኢኮኖሚያዊ ዕድገቱ የሮዝያስ ጠላቶች በ Buenosairean ገዥው የጠፋውን የግለሰቦችን ፣ የፖለቲካ እና የመግለጫ ነፃነቶችን ጠይቀዋል ፡፡ የይገባኛል ጥያቄዎ ዋነኛው አገራዊ መንግስትን የሚያደራጅ እና የዜጎችን መብት የሚያረጋግጥ የፖለቲካ ህገ-መንግስት ማዕቀብ መጣል ነበር ፡፡

እ.ኤ.አ. በ 1852 ሮዛስ በ Grande ጦር ፣ በኢሬሬ ሪዮ ግዛቶች እና በቀሪዎቹ የኡራጓይ እና ሌሎች የብራዚል ቀይሮች መካከል ጥምረት የሆነው የሮዛስ ጦርነት በ ድል ተነሳ ፡፡ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንቱን በበላይነት የሚመሩት የኢሬሬ ሪዮ ገዥው የፌዴራል የፀረ-ሽብርተኛ ጁሱ ሆሴ ደ ኡራኪዛ ቡድን ግንባር ቀደም ነበር ፡፡

ከአንዳንድ ለውጦች ጋር እስከ ዛሬ ድረስ አገሪቱን ሲገዛ የቆየው ሕገ መንግሥት እስከሚሠራበት ጊዜ ድረስ በ 1853 ነበር ፡፡ የፌዴራሉን መንግሥት ተቀበለ ፣ ግን የቦነስ አይረስ ግዛት ዋና ከተማዋን በፓራን ከተማ መመስረት ካለባት ከአርጀንቲና ኮንፌዴሬሽን ተለየች ፡፡ እ.ኤ.አ. እ.ኤ.አ. በ 1859 ኮንፌዴሬሽን በሴፔ ጦርነት ቡናን አይኤስ ተብሎ የሚጠራውን የሳን ሆሴ ደ ፍሬስ ስምምነትን እንዲፈርም በማስገደድ እ.ኤ.አ. በ 1859 እ.ኤ.አ. ሆኖም በቡሮሞን ሜየር ሊቀመንበር ወቅት በፓenን ጦርነት (እ.ኤ.አ. 1861) በኋላ በቡነስ አይረስ መሪነት የመጨረሻው ውህደት ተገኘ ፡፡

እ.ኤ.አ. በ 1865 አርጀንቲና እንደገና በኡራጓይ የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ ገባች ፣ የፓራጓይ ከተማዎችን በቁጥጥሩ ስር በማድረግ ፓራጓይ ምላሽ ሰጡ ፡፡ አርጀንቲና ከብራዚል እና ከኡራጓይ ጋር የሶስትዮሽ ጥምረት ከፈረመች በኋላ አርጀንቲና አምስት ዓመታትን ያስቆጠረና አሥር ሺህ የአርጀንቲና ወታደሮችን ተሳትፎ የሚጠይቅ የሶስትዮሽ ህብረት ጦርነት ተካሂ .ል ፡፡ የወንዶቹ አብዛኛው ክፍል ሙሉ በሙሉ ወድሟል እና ሞቷል በአርጀንቲና ውስጥ የእርስ በእርስ ጦርነት እንዲነሳ ምክንያት የሆነው እጅግ በጣም ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ እና የሰው ሕይወት ቢኖርም ፣ ይህች ሀገር በሰሜን ምስራቅ ድንበሯን ማጠናከር ችላለች ፣ ድንበሩ በፒሊሴሲ ፣ ፓራጓይ እና በፓራና ወንዞች ውስጥ ነበር የተደረገው።

በሚርተር አስተላላፊዎች እና በተለይም የሳርሚንቲኖ እና አvelላላንዳ አርጀንቲና በትልቁ የባቡር አውታር እና የትምህርት ሥርዓቱ እድገት በሚታደግበት የዓለም ኢኮኖሚ እራሷን በዓለም ኢኮኖሚ ውስጥ አስገባች ፡፡ እ.ኤ.አ. በ 1874 እና በ 1880 ከሁለት የደም ካደጉ በኋላ በዚህ ዓመት ባለፈው ዓመት የቦነስ አይረስ ከተማ በፌዴሬሽኑ የተዋቀረች ሲሆን በክልሎችና በዋና ከተማው መካከል ዘላቂ ሚዛን ተፈጠረ ፡፡

በ 1878 እና በ 1884 መካከል የድንበር እና የቻኮ ውድድሮች በመባል የሚታወቁት በአገሬው ተወላጅ እና በክሬምለሎች መካከል የማያቋርጥ ግጭቶችን ለማቆም እና በአገሬው ተወላጅ ግዛቶች ላይ አግባብነት ያላቸውን ተጓዳኝ ግዛቶች እንዲመደቡ ለማድረግ ነበር ፡፡ ጁሊ ኤ ሮካ ያስተዋወቀው የመጀመሪያው ወረራ በዋናው ህዝብ ቁጥጥር ሥር ወደተባበሩት ፓምፓሶች እና ፓትጋኒሺያ ግዛቶች ተከታታይ ወታደራዊ ወረራዎችን ያቀፈ ነበር ፣ እናም የጉዞው ባለሀብቶች የገጠር ማኅበረሰብ አባላት ውስጥ ይከፋፍሏቸዋል። እስከ ምዕተ ዓመቱ መገባደጃ ድረስ በብሔራዊ ኢኮኖሚ ስርዓት ውስጥ የተካተተው ሙሉ ውህደቱ የተከናወነው ከእንጨት እና ታኒን ምርት የተወሰደው በጥጥ በማምረት ሲተካ ብቻ ነው ፡፡ የአርጀንቲና መንግስት እንደ ክሪዮስ እና አውሮፓውያን ተመሳሳይ መብቶች ሳይኖር የአገሬው ተወላጅን እንደ አናሳ ፍጡራን አድርጎ ይመለከታል።

እ.ኤ.አ. ከ 1880 እስከ 1916 ባለው ጊዜ ውስጥ በብሔራዊ በራስ ገዝ ፓርቲ (ፒኤን) በዘፈን ምርጫ ስርዓት መሠረት ስልጣንን በመጠቀም ሥልጣኑን ተረከበ እና ለ 25 ዓመታት ብቸኛው ሰው ጄኔራል ጁሊዮ አርጀንቲና ሮካ ነበር ፡፡ Conservative Republic ወይም Oligarchic Republic ተብሎ የሚጠራው በብሪታንያ ግዛት በወጣው ዓለም አቀፋዊ የሥራ ስምሪት የሠራተኛ ክፍፍል ላይ በመመርኮዝ ስኬታማ እና ዘመናዊ የግብርና ኤክስፖርት ሞዴልን አደራጅቷል ፡፡ በባህላዊው መለያ ሀገር በዚያን ጊዜ “የዓለም ዳቦ መጋገሪያ” ሆና ታየች ፡፡

ይህ ኢኮኖሚያዊ ሞዴል በጥቂት እጆች ውስጥ የሀብት ክምችት እንዲገኝ ከማድረጉ እና ከፓምፓስ ክልል ውጭ ያሉ የሰራተኛ የሥራ መደቦች እና ህዝቦች ማህበራዊ መገለል እንዲፈጠር አድርጓል ፡፡ ኢኮኖሚ በከፍተኛ ደረጃ ወደ አንድ ትልቅ የኢሚግሬሽን ፍሰት ደረጃ ላይ በመድረሱ በዋናነት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ጣሊያናውያን እና ስፓኖችን ያቀፈ ሲሆን የምስራቅ አውሮፓውያን እና የምዕራባዊያን እስያዎችን ተከትሏል ፡፡ እ.ኤ.አ. በ 1869 ከዓለም ህዝብ 0.13% የተወከለው የአርጀንቲና ህዝብ እ.ኤ.አ. በ 1930 0.55% ይወክላል ፣ ይህ መጠን ከዚያ ጊዜ ወዲህ የተረጋጋ ይሆናል ፡፡

የኢኮኖሚው ብልፅግና አብዛኛዎቹ ስደተኞች ወይም ዘሮቻቸው የሆኑትን አንድ በጣም መካከለኛ የመካከለኛ ደረጃ ዕድገት አስነስቷል ፡፡ የአውሮፓውያን ስደተኞችም እንዲሁ ሶሻሊዝም እና የሀገር ውስጥ ቅኝ ግዛት ያሉ አዲስ የፖለቲካ ሀሳቦችን አስተዋውቀዋል ፣ እንዲሁም ከአከባቢው ህዝብ በተለይም ከአፍሮ-አርጀንቲና ጋር በጋራ መረዳጃ ድርጅቶች እና ማህበራት በመፍጠር ተሳትፈዋል ፡፡63 ዘመናዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ብቅ አሉ ፡፡ እንደ ራቲካል ሲቪክ ህብረት (UCR) እና ሶሻሊስት ፓርቲ (ፒ.ሲ.)።

ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ የፖለቲካ እና ማህበራዊ ግጭቶች ፣ የምርጫ ማጭበርበሮች እና ከባድ የጭቆና ድርጊቶች በኋላ ፣ ሴኔዝ ፔና ህግ በ 1912 ተተላለፈ ፣ ይህም ለወንዶች ድምጽ አሰጣጦች ምስጢራዊ ፣ አስገዳጅ እና ሁለንተናዊ በቂነት እንዲመሰረት አደረገ ፡፡ በድብቅ በቂ በሆነ የመጀመሪ የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ወቅት ወግ አጥባቂዎች ከ1916 እስከ 1922 እና በ 1928 መካከል ፕሬዝዳንት በነበረው ሂፖሎ ዩሪigoyen በሚመራው አክቲቪስቶች ከስልጣን ተፈናቅለው ነበር ፡፡ በአሰቃቂ ሳምንት እና በአመፀኛው ፓትጋኒያ የተፈጸመውን እልቂት ያመጣ ዩኒቨርስቲ እ.ኤ.አ. በሁለቱም የዩሪጊየን መንግስታት መካከልም አክራሪው ማርሴሎ ቶርኮቶ ደ አልveር ፕሬዝዳንት ሆኖ ተመረጠ፡፡

እ.ኤ.አ. መስከረም 6 ቀን 1930 በአርጀንቲና የአርጀንቲና ወታደራዊ ቡድን ሂፖሎ ዩሪigoyen ከተገለበጠ በኋላ አምባገነናዊ አገዛዙን ለማቋቋም በወሰነ ጊዜ መስከረም 6 ቀን 1930 ተከስቶ ነበር ፡፡ ይህ መፈንቅለ መንግስት አንፀባራቂ ዲዳ በመባል ለሚታወቁ የማጭበርበር መንግስታት ቅደም ተከተል አስነሳ ፡፡

የአርጀንቲና agro-ወደ ውጭ መላኪያ ሞዴል በ 1929 በተከሰተው ቀውስ ምክንያት በዓለም አቀፍ ገበያዎች መዘጋት ምክንያት ወደ ቀውስ ውስጥ ገባ ፡፡ አገሪቱ ሰፊ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ያደገች የማስመጫ የመተካት ሂደትን ከፍ አድርጋ ነበር ፡፡ የሁለተኛ መፈንቅለ መንግስት መፈንቅለ መንግሥት ወታደራዊ መንግስት የገባበት በዚህ ጊዜ ውስጥ በሠራተኛ ማህበራት እና በፔሮኒዝም ለተነሳው አንዳንድ ወታደሮች መካከል ህብረት ይከናወናል ፡፡ ይህች ሀገር በ 1941 መገባደጃ ላይ በጃፓን ጥቃት በተሰነዘረበት ወቅት አሜሪካ ከአሜሪካ ግፊት ቢገጥምም አርጀንቲና በአብዛኛዎቹ የዓለም ሁለተኛው ጦርነቶች ሚያዝያ 27 ቀን አጋቾቹን በመቀላቀል ገለልተኛ ሆነች ፡፡ ጦርነቱ ከመጠናቀቁ ጥቂት ቀደም ብሎ በጄኔራል ኤድልሚሮ ፋረል መንግሥት እ.ኤ.አ. ማርች 1945 ፡፡

እ.ኤ.አ በ 1946 ሁዋን ዶንጎን ፔኖ በሠራተኛ ፓርቲ ውስጥ የተደራጁ የሠራተኛ ማህበራት ድጋፍ በመሆን ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ ፡፡ ፔርኒ ከባለቤቱ ኢቪታ ጋር በመሆን ፣ የማህበራዊ ፍትህ ፣ የፖለቲካ ሉዓላዊነት እና የኢኮኖሚ ነጻነት ላይ አፅን thatት የሚሰጥ አዲስ እንቅስቃሴን አመሩ ፡፡ በእሱ መንግሥት ውስጥ የሴቶች መሻሻል በ 1947 ተቋቋመ ፣ በቤተሰብ ሕግ ውስጥ የወንዶች እና የሴቶች እኩልነት ፣ በጋብቻ ውስጥ የተወለዱ ሕፃናት እኩልነት ፣ ነፃ የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ፣ የወባ በሽታ ፣ ወዘተ ፡፡

በኢቫ ፔሮን ፋውንዴሽን አማካይነት በአገሪቱ ውስጥ ታይቶ የማያውቅ ማህበራዊ ድጋፍ የተገነባ ሲሆን ይህም የገንዘብ ተጋላጭ ለሆኑ ዘርፎች የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ነበር ፡፡ የባቡር ሀዲድ እና የውጭ ንግድም እንዲሁ በሀገር ውስጥ የተካተቱ ሲሆን ከባድ ኢንዱስትሪን የሚያበረታታ ጠንካራ የኢንዱስትሪ ልማት የመነጨ ነበር ፡፡

እ.ኤ.አ. በ 1951 ፔሮን በአርጀንቲና ውስጥ ለወንድ እና ለሴቶች ሁለንተናዊ መሻሻል በሚደረግበት የመጀመሪያ ምርጫ ውስጥ 40% ድምጽን ለአዲስ ፕሬዝዳንትነት ምርጫ ተመረጠ ፡፡ በ 1952 ኢቪታ ሞተ ፡፡ ከ 60 ዓመታት በኋላ ፣ ቤንሴሜንታዊቷ ሴት በአርጀንቲና ታሪክ ውስጥ የሴቶች ሚና ምልክት ሆኖ ታወጀ ፡፡66 Peronism የሕዝቡን ሰፊ አድማጭ ነበረው ፣ ግን ደግሞ የተቃዋሚ ዘርፎችን ጠንካራ እምቢተኝነት ፣ የአርጀንቲና ማህበረሰብ በፔሮኒስቶች እና በፀረ-ፈረንሳሾች ውስጥ ፡፡ የእሱ ፖሊሲ የብሪታንያ ፍላጎቶችን የሚጎዳ ሲሆን በዚያን ጊዜ ተቃዋሚዎችን የሚደግፈው በኢኮኖሚ የበላይነት እስከሚገኝበት ጊዜ ድረስ ነው ፡፡ ከካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጋር የተፈጠረው ግጭት የተጀመረው ለሰፋፊ መስሪያ ቤቶች መንግስት ያለው ታማኝነት እንዲዳከም እና ተቃዋሚዎችን አንድ አድርጎታል ፡፡

እ.ኤ.አ. ሰኔ 16 ቀን 1955 እ.ኤ.አ. በፕላዛ ዴ ማዮ እና በሌሎች ቦታዎች በቦነስ አይረስ የተባሉትን የቦነስ አይረስ የቦንብ ፍንዳታ በመጠቀም በጥይት የተከሰሱ 308 ተጎጂዎች ሴራ - ሲቪል-ወታደራዊ ሴራ ፡፡ 23 ሴቶችን ጨምሮ 111 የሰራተኛ ንቅናቄዎችን ጨምሮ - በሽንፈት ምክንያት ሊታወቅ ያልቻለው ሞት እና ከ 700 በላይ የሚሆኑት ጉዳቶች ተገኝተዋል ፡፡

እ.ኤ.አ. በመስከረም ወር ónንዮን “ፉሺላራራ አብዮት” የሚል ቅጽል ስም የተሰየመ መፈንቅለ መንግስት የጀመረው ፔሮኒዝም ን የገደለበትን “ነፃ አውጭ አብዮት” በሚል ስያሜ በተሰየመ አዲስ መፈንቅለ መንግስት ተገለበጠ ፡፡ Ónንዮን በ 1973 እገዳው እስኪያበቃ ድረስ በግዞት ተገዶ ነበር ፡፡

በእገዳው ወቅት ronሮኒዝም በፖለቲካ እና በንግድ ህብረትነት ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩ ይቀጥላል - ይህም ብዙ ምርጫዎችን ያሸነፈበት አካባቢ - ሕገ-መንግስታዊ ባልሆኑ መንገዶች የተሾሙትን ባለሥልጣናት ሕጋዊነት በመካድ እና በመቋቋም ላይ የሚታወቅ ተቃራኒ እንቅስቃሴን በማዳበር ላይ ይገኛፈረንሳዊ.

እ.ኤ.አ. በ 1958 ፕሬዝዳንት አርቱሮ ፍሬሮዚዚ (ዩሲአይአይ) በፔሮንኒዝም ምርጫ ታግደው ነበር ነገር ግን እ.ኤ.አ. እ.ኤ.አ. ከፔን ጋር የምርጫ ስምምነት ከደረሱ በኋላ እ.ኤ.አ. በ 1962 በተካሄደው አዲስ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ተገለበጡ ፡፡ ፍሮndizi ከተሰረዘ እና ከተያዘ በኋላ በዚያው ቀን በሹመት የስልጣን ክፍፍል ክስ በመሰንዘር የፍትህ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው የተሾሙት ሲቪያ ሆሴ ማሪያ ጉዲ ናቸው ፡፡ ምንም እንኳን ጊዲ በፕሬዚዳንታዊነት መደበኛ ስልጣን ብትይዝም እውነተኛው የቁሳዊ ሀይል በወታደራዊ መስሪያ ቦታ ላይ ትገኛለች ፡፡ በስልጣን ዘመኑ አዙሌ እና ኮሎራዶ በመባል በሚታወቁ የአርጀንቲና ጦር ጦርነቶች መካከል ያሉ ግጭቶች ተባብሰው ወደ ትጥቅ ግጭቶች ይመራሉ ፡፡ የ “ሰማያዊ” ክፍሉ ድል ጄኔራል ጁዋን ካርሎስ ኦንጋኒ ጦርን መልሶ ለመቀላቀል አስችሎታል ፡፡

Ronሮኒዝም አሁንም ታግዶ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ፍሬሮይዚ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ፣ እ.ኤ.አ. በ 1963 አርቱሮ ኡምቤርቤሊያ ኢሊያ (UCRP) ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ ፤ እ.ኤ.አ. በ 1966 መንግስትን ወደ ኦንግጋኒያ የሚወስድ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ይወገዳል ፡፡

የእራሱ አምባገነናዊነት የራስ-ቅጥ ያለው የአርጀንቲና አብዮት (እ.ኤ.አ. 1966-1973) ከተመሰረተው የመጀመሪያው የሆነው ፣ እንዲሁም በላቲን አሜሪካ ከዩናይትድ ስቴትስ አማካይነት ጋር በመተባበር በጦር ኃይሎች ማዕቀፍ ውስጥ የተጫነ የመጀመሪያው ቋሚ አምባገነንነት ነበር ፡፡ የቀዝቃዛው ጦርነት ዓለም አቀፍ ማዕቀፍ የአሜሪካውያን ትምህርት ቤት እና የብሔራዊ ደህንነት አስተምህሮ። የፖለቲካ እንቅስቃሴን እና የመንግሥት ሽብርተኝነትን መሰረዙ እንደ ሞንቴሮንሮስ ፣ ኤአርአር እና ኢ.ፓ.ፒ. ያሉ በርካታ የደፈጣ ተዋጊ ድርጅቶች ብቅ እንዲሉ በማድረግ እና እንደ ኮርዶባዞ ያሉ በርካታ ቁጥር ያላቸው አመጽ ከተሞች እንዲታዩ ምክንያት ሆኗል ፡፡ ሮዛሪያዞ እና ቱኩማናዞ ፣ ሌሎችም አሉ ፡፡ የónንዮን ዕጩነት ቢያግደውም ፣ በታዋቂው አመፅ በመነሳት አምባገነናዊ አገዛዙ በፖሮኒዝም ተሳትፎ የምርጫ መውጫ አደራጅ ፡፡

እ.ኤ.አ. በ 1973 ሶስተኛው Peronism ተብሎ የሚጠራውን የፕሬዚዳንትነት ምርጫ በፕሬዚዳንታዊ ምርጫዎች ሕጋዊ ሆነ ፡፡ ፕሬዝዳንት ሄክተር ሆሴ ካማፖ ከለቀቁ በኋላ በዚያው ዓመት ጁዋን ዶንጎ Perንዮን ለሶስተኛ ጊዜ ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ ፡፡ ምክትል ፕሬዚዳንቱ እና ሚስቱ ማሪያ ኤቴላ ማርቲኔዝ ዴ ónሮን ተተካ። ይህ ጊዜ በ 1973 በተከሰተው የነዳጅ ቀውስ እና በሰፊው የፖለቲካ አመፅ የተነሳ የአርጀንቲና ፀረ-ኮሙኒስት ህብረት (ሶስቴ ኤ) ተብሎ በሚጠራው የፖሊስ ኃይል ጥምረት የተነሳው ውስጣዊ ሁኔታ በተፋጠነ ሁኔታ ተለይቶ ይታወቃል። እ.ኤ.አ. ከ 1973 ጀምሮ ፖሊሶች እና ወታደራዊ ኃይሎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎችን ገድለዋል - ብዙዎች “ታሳሪዎች ጠፍተዋል” - እንዲሁም እስረኞች በሚባሉ አዋጆች በተደነገገው የጭካኔ ማዕቀፍ ውስጥ የተጠረጠሩ የማቆያ ማዕከሎች መትከል ፡፡

እ.ኤ.አ. መጋቢት 24 ቀን 1976 በአገሮች ጥበቃ ስር በብሔራዊ ጥበቃ አማካኝነት በብሔራዊ መልሶ ማደራጀት ሂደት የሚጠራ አዲስ ዘላቂ አምባገነናዊ ስርዓት የሚሾም አዲስ የወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ተደረገ ፡፡ የተባበሩት በተመሳሳይ የዘር ማጥፋት ወንጀል በፍትህ በተገለፀው በሺዎች የሚቆጠሩ የጠፉ ሰዎች እና ማንነታቸው በመገደል የተጎዱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሕፃናትን በማጥፋት ፣ በማሠቃየት እና በተቃዋሚዎችን የማስወገድ ስርዓት ያለው እቅድ ተፈፃሚ ሆነ ፡፡

የመጀመሪያው የወታደራዊ unta ,ቴ ፣ ከግራ ወደ ቀኝ: - ኤሚሊ ማሳራ ፣ Vር Vይ ቪላ እና ኦርላንዶ አንጋስታ። በ 1985 በሰብአዊ መብት ላይ በተፈፀመ ወንጀል እስራት ተፈረደበት ፡፡

በምላሹም ‹የፕላዛ ዴ ማዮ እናቶች እና የፕላዛ ዴ ማዮ እናቶች አያቶች› ያሉ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች የተቋቋሙ ሲሆን ይህም በ ‹የጥፋተኞቹ የፍርድ እና የቅጣት ቅጣት› እና ማንነታቸው የተጎዱትን ሕፃናትን በማገገም ላይ ወሳኝ ሚና ይጫወታል ፡፡ ተሰር .ል። የሕብረቱ ንቅናቄ በጠቅላላው አጠቃላይ ጥቃቶችን ለማወጅ እስከሚታወቅ ድረስ ጠንካራ ተቃውሞ ተቋቁሟል ፣ የ CGT መበታተን እና የሰራተኞች ማህበራት ጣልቃ ገብነት ፡፡

አምባገነኑ መንግስታት ዋና ዋና የንግድ ቡድኖችን በንቃት የሚደግፍ ፣ የመንግስት ቁልፍ ተግባሮችን የሚይዝ ፣ እንዲሁም የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ፣ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ዋና ዋና ሚዲያዎች ከታዋቂ ጋዜጠኞች እና ኮሚዩኒኬሽኖች ጋር ነበሩ ፡፡ የኢኮኖሚው ዕቅድ የቺካጎ ትምህርት ቤት መመሪያዎችን ተከትሏል - ብዙውን ጊዜ ከኒዮሊቤራሊዝም ጋር ተለይቷል ፡፡ የሕዝቡ አስፈላጊ ክፍል አምባገነንነቱን ደግ supportedል ፣ ሌላ ክፍል ደግሞ እንደ Plaza de Mayo ያሉ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች መፈጠርን ወይም የሰራተኛ ማህበር እርምጃዎችን እና አድማዎችን በመቃወም ሌላ ዘርፍ ተቋቋመ ፡፡

እ.ኤ.አ. ከ 1983 ጀምሮ ዴሞክራሲያዊ መንግስትን የሚያስተካክል የውጭ ዕዳ እ.ኤ.አ. በ 1976 ከ 7,700 ሚሊዮን ወደ 45,000 ሚሊዮን ደርሷልእ.ኤ.አ. በ 1983 ዶላር ፣ በብዙ ሁኔታዎች የኢኮኖሚ ቡድኖችን እና ሁለገብ ኩባንያዎችን ጥቅም ለማስጠበቅ የወንጀል ክዋኔዎች ውጤት ፡፡ እ.ኤ.አ. በ 1978 በጊል ቻናል አካባቢ ገደቦችን በመከተል በከባድ ቀውስ የተነሳ ሁለቱ አገሮችን ወደ ጦርነት አመጣ ፡፡ እ.ኤ.አ. በ 1982 ከዩናይትድ ኪንግደም ጋር የፎልክላንድ ጦርነት እ.ኤ.አ. ለአርጀንቲና ሽንፈት ለወታደራዊው ስርዓት ውድቀት ካደረጓቸው ምክንያቶች መካከል አንዱና ለሚቀጥለው አመት አጠቃላይ ምርጫ ጥሪ እንዲቀርብ ጥሪ አቅርበዋል ፡፡

እ.ኤ.አ. ከ 1983 እስከ 2003 ባለው ጊዜ የአርጀንቲና ታሪክ እ.ኤ.አ. አምባገነናዊው መንግሥት በነበረው የሰብአዊ መብት ጥሰት ወንጀል የተከሰሱ ሰዎች ክስ ተመስርቶበት የጀመረው የአርጀንቲና ታሪክ ምልክት ተደርጎ ነበር ፡፡ ሌሎች በደቡብ አሜሪካ የተገኙት - ዲሞክራሲያዊ የውጭ ዕዳ ቀውስ ፣ ግሎባላይዜሽን ጅምር ፣ ኒዮሊቤራል ተሐድሶዎች እና እ.ኤ.አ. በ 1998 የተጀመረው ከባድ የኢኮኖሚ ውድቀት እ.ኤ.አ. በ 2001 እና በደርዘን የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች ተገደሉ ፡፡ እ.ኤ.አ. በታህሳስ 20 ቀን 2001 እ.አ.አ. በአርጀንቲና ታሪክ ለሁለት አስርት ዓመታት በዲሞክራሲያዊ ስርዓት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚዘልቅ ሲሆን ዴሞክራሲያዊ ፕሬዝዳንቶች ለሌላ ዲሞክራሲያዊ መንገድ ለተመረጡ የፖለቲካ ፓርቲ ተተኪዎች ስልጣናቸውን በሚረከቡበት ጊዜ ነበር ፡፡

ዲሞክራሲያዊው መንግሥት ታህሳስ 10 ቀን 1983 እንደገና ተቋቋመ ፡፡ አዲሱ ፕሬዝዳንት ራዩል አልፈሰን የተባሉት የሪicalብሊክ ሲቪክ ህብረት ሰብአዊ መብት ጥሰትን ለመመርመር የወሰነ ሲሆን ይህም እንደገናም እንደገና አይ የሚል ርዕስ ያለው ነው ፡፡ የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወታደራዊ ቦርዶች ተፈርዶባቸው የተወሰኑት አባሎቻቸውም ተፈርዶባቸዋል ፣ ምንም እንኳን በእሱ ትእዛዝ እና በወታደራዊ ግፊት ቁጥጥር የተደረገ ቢሆንም ፡፡ በ 1984 በኬል ቻናል ላይ ከቺሊ ጋር የድንበር ክርክር አብቅቷል ፡፡ እ.ኤ.አ. እ.ኤ.አ. በ 1985 በአዲሱ የብራዚል ፕሬዝደንት ሆሴ ሳርኒ ከአዲሱ የዴሞክራሲያዊ ፕሬዝዳንት ሆሴ ሳርኒ ጋር በመተባበር በሺኮርጅር ስም የሚወጣውን የአካባቢ ውህደት ሂደት ለመጀመር እ.ኤ.አ.

እ.ኤ.አ. እ.ኤ.አ. የ 1989 ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ከተደረገ በኋላ በሃይመሪነት ሂደት የአገሪቱን የበላይነት ላይ ተጽዕኖ ያሳደረ ሲሆን አልፍሬንሰን ከፕሬዚዳንቱ ለመልቀቅ እና ከስድስት ወር በፊት ትዕዛዙን ለመቆጣጠር ተገደው የፍትህ አካላት ፓርቲ የሆኑት ካርሎስ ሜሜ ፡፡ በ 1989 በዋሽንግተን ስምምነት እና ከ IMF ድጋፍ ጋር በሚስማማ መልኩ በሚኒስትር ዶንጊን ካቫሎ ጠንካራ የሥራ ድርሻ ላይ የዋጋ ግሽበትን አቆመ ፡፡ በማህበረሰቡ ውስጥ የጅምላ ሥራ አጥነት መጣ እና ወንጀል በከፍተኛ ሁኔታ ተባብሷል ፣ ሁለቱም በፖለቲካ አጀንዳ ላይ ማዕከላዊ ችግሮች ሆነዋል77 እ.ኤ.አ. በ 1991 አርጀንቲና በአሜሪካ ትእዛዝ መሠረት በብሔራዊ ኮንግረስ ፈቃድ ሳታደርግ ኢራን ላይ ጦርነት ገባች ፡፡78 እ.ኤ.አ. 1992 እ.ኤ.አ. በ 1994 ሁለት የእስራኤል የሽብር ጥቃቶች ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል ፡፡ በእስራኤል ኤምባሲ እና በኤኤምአይ ላይ የ 23 እና የ 85 ሰዎች ሞት በተፈጸመባቸው ወንጀለኞች ሳይገኙ ባለበት ሁኔታ በብዙ መሰናክሎች በመፈተሽ.799 ከ ቺሊ ጋር የድንበር ውዝግብ ተፈታ ፡፡ በሎጎ ዴል ዴርቶ ክልል ውስጥ ይገኛል ፡፡ እ.ኤ.አ. በ 1994 በአልሰንሰን እና በሜም መካከል የተደረገ ስምምነት ህገ-መንግስቱን እንዲሻሻል እና በሚቀጥለው ዓመት ሜም እንደገና ተሾመ ፡፡ ወደ ኢኳዶር እና ክሮሺያ የተደረገው የጦር መሳሪያ ዝውውር እንቅስቃሴ የሪዮ Tercero የጦር ፋብሪካን ፍንዳታ በመቃወም ፣ ከተማዋን እጅግ በመጎዳቱ ሰባት ሰዎችን ለህልፈት የዳረገው እና ​​ከፔሩ ጋር ያለውን ግንኙነት በከፍተኛ ሁኔታ ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል ፡፡ እና የፒክሴሮሮ እንቅስቃሴን ያስነሱ የመንገድ መሰናክሎች። እ.ኤ.አ. በ 1998 ለአራት ዓመታት የዘለቀ ውድቀት የጀመረው በአርጀንቲና ታሪክ ውስጥ እጅግ የከፋ ቀውስ አስከትሎ ነበር ፡፡

እ.ኤ.አ. በታህሳስ ወር 1999 የሕብረቱ አባል የነበረው የራሺያዊ ሲቪክ ህብረት ፈርናንዶ ዴ ላ ሩአ ፕሬዚዳንቱን ተረከበ። የሕዝቡን ጉድለትን ለመቀነስ እርምጃዎችን ወስ theል - የጡረታ ክፍያን ለመቀነስ እና የሠራተኛ መብቶችን ይበልጥ ተለዋዋጭ ለማድረግ ፣ IMF አመላካችነት ተከትሎ ፡፡ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ቀውስ እየተባባሰ ሲመጣ ፣ መንግሥት ደግሞ የቀድሞውን የፕሬዚዳንት ሚንሜን ሚኒስትሩን ዶንጎ ካቫሎ ሾመ ፡፡ በጠቅላላ ማህበራዊ አመፅ ምክንያት የተከሰተ የባንክ ተቀማጭ ገንዘብ (“ኤል ኮራልቶ” በመባል የሚታወቅ መለኪያ) እንዲታገድ ትእዛዝ ሰጠ ፣ እ.ኤ.አ. በታህሳስ 20 ቀን 2001 ፕሬዝዳንታዊ ሥልጣኑን ለመልቀቅ አስችሏል ፡፡ በሁለት ቀናት እርግጠኛ አለመሆን ፣ አገሪቱ በውጭ ዕዳ ላይ ​​የተዘበራረቀችበትን ሁኔታ በመግለጽ ሀገሪቱ ወደ ነባሪነት የታወጀችበትን የአዶልፎ ሮድሪጊዛን አጭር መንግስት ጨምሮ በርካታ ፕሬዚዳንቶች ተተክለው ነበር ፡፡

እ.ኤ.አ. ጃንዋሪ 2 ቀን 2002 የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት ኤድዋርዶ ዱሃዴሌን ከኦቲዮቲስታቲ ፓርቲ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት አድርጎ መረጠ ፡፡ ዱሃዴል “ኮሪልዮን. በዚህ ወቅት ድህነት ወደ የህዝብ ብዛት ወደ 56 ከመቶ አድጎ ደግሞ ወደ 26 በመቶ አድጓል ፡፡ ለሠራተኞች ላልሆኑ ሀላፊነቶች እቅዶች መመስረት እ.ኤ.አ. በግንቦት 2003 የሁለት ሚሊዮን እቅዶች ከፍተኛ ሆነ ፡፡ ወደ 135% የ GDP ፣ የዛ ዓመት የዋጋ ግሽበት 41% ነበር እና የምግብ ዋጋ ጭማሪ ደግሞ 74.9% ደርሷል።

አርጀንቲና ብዙ የተለያዩ ክልሎች አሏት-እርጥብ ፓምፓ ፣ ደረቅ ፓምፓ - አንዳንድ ጊዜ የፓምፓስ ክልል ተብሎ የሚጠራ አንድ ነጠላ ክልል ፣ ሲሪያራስ ፓም ሙዝ ፣ ኩዮ ፣ የአርጀንቲና ሰሜን ምዕራብ ወይም NOA ፣ የቻኮ ክልል ፣ መስጴጦሚያ ፣ ፓራጋኒያ እና አናታታዳ

የአርጀንቲና ተፈጥሮአዊ ሀብት እጅግ ሰፊ ነው ፡፡ ከዓለም አቀፉ የተፈጥሮ ሀብት (WWF) አርጀንቲና እጅግ በጣም የቅርብ ጊዜ ዘገባ መሠረት እጅግ በጣም ሀብትና ተፈጥሮአዊ ብዝሃነት ያለው ዘጠነኛው ሀገር (ከ 150 በላይ ከሆኑት) ነው ፡፡ እ.ኤ.አ. ) በዓለም ላይ ካሉ ሰባት ተፈጥሮአዊ ድንቅ ነገሮች እንደ አንዱ ተቀደሱ ፡፡

የአርጀንቲና አህጉራዊ ክልል በአንዲስስ ፣ በደቡብ አትላንቲክ ውቅያኖስ እና በአንታርክቲክ አህጉር መካከል ይገኛል ፡፡ በአገሪቱ ውስጥ ሦስት ትላልቅ በግልፅ የተቀመጡ ጂዮግራፊያዊ ስፍራዎችን መለየት ይቻላል-

በሰሜናዊ የአገሪቱ ክፍል ጥቅጥቅ ያሉ እፅዋት ክልሎች ይገኛሉ ፡፡ በአንዳንድ ዘርፎች ጫካ ውስጥ ሲሆን በሌሎች ጫካዎች ደግሞ በቻኮ ክልል እና በ አይቤታ አካባቢዎች ይገኙበታል ፡፡ እነዚህ የበለፀጉ ዕፅዋት አካባቢዎች ከሌሎች የዘንባባ እርሻዎች እና ከሣር መሬቶች ጋር ይደባለቃሉ ፡፡ የሚስዮናዊያኑ ክልል ልዩ ነው ፣ የብራዚል የተራራ ሰንሰለቶች ማራዘሚያ ፣ ዝቅተኛ ግን ረዣዥም ተራራማ አካባቢዎች ፣ ዝቅተኛ እርጥበት ያለው እና ጫካ እፅዋት ፡፡ የአገሪቱ ሰሜናዊ ምዕራብ በጣም ከፍተኛ በሆነ ጠፍጣፋ ክልል ውስጥ ይገኛል Puna ወይም Altiplano 201

በሀገሪቱ መሃል የፓምፓስ ሜዳ ይገኛል ፣ በሁለት ክልሎች ሊከፈል ይችላል-እርጥብ ፓምፓ እና ምዕራባዊ ወይም ደረቅ ፓምፓ። የኋለኛው ደግሞ የበለጠ አህጉራዊ የአየር ንብረት አለው ፡፡ እርጥበት ባለው ፓምፓ ውስጥ ሴራ ዴ ላ ቨንታና እና ታንዲሊያ (ከባህር ጠለል በላይ 500 ሜትር ከፍታ ካለው ከፍታ ጋር) 202 203 ብቸኛው የመሬት አቀማመጥ ሁኔታን የሚያፈርሱ እና የመሬት ውስጥ ፍሰት ናቸው በጣም ያረጀ የተራራ ክልል.202 የፓፓስ ሜዳ ለጥራጥሬ እና የቅባት እህሎች እንዲሁም ለእንስሳት እርባታ ተስማሚ ነው ፡፡

በሀገሪቱ መሃል-ምእራብ ምዕራብ ውስጥ በሳን ጁዋን ፣ ሚንዛዛ እና ሳን ሉዊስ ግዛቶች የተገነባው የኩዮ ክልል ነው ፣ አነስተኛ ተራራማ የሆነ እፎይታ ያለው ተራራዊ እፎይታ ይገኛል ፡፡

በደቡባዊ የሀገሪቱ ክፍል (የአርጀንቲና አንታርክቲካን ሳይቆጥር) ፓፓጋኒያን ነው ፣ ሰፊ የሆነ የፕላዝሃነስ እና ተራራማ አካባቢዎች የሪዮ ኔሮ ፣ የኑዊን ፣ ቹ ፣ የሳንታ ክሩዝ እና የዚራ ደሬ ፉዌጎ ግዛቶችን ያጠቃልላል። ፓራጋኒያ በሃይድሮካርቦኖች (ጋዝና ዘይት) የበለጸገ ፣ እንዲሁም የአርጀንቲና አህጉራዊ መደርደሪያዎች ፣ የአርጀንቲና ባሕረ ሰላጤ ፣ እንደ ሐይቅ ፣ ሳልሞን ፣ ወዘተ ባሉ ዝርያዎች የበለፀገ ነው። በግርጌዎች ውስጥ እንደ ዩራኒየም ፣ ብር ፣ ወዘተ ያሉ የተለያዩ ዝርያዎች የማዕድን ቁጠባዎች አሉ ፡፡

በጣም አስፈላጊ ወንዞች የሚገኙት በሰሜናዊ ምስራቅ እና በአገሪቱ ምስራቅ ምስራቅ ነው ፡፡ በምዕራባዊው ንፍቀ ክበብ ሶስተኛ ትልቁ ተፋሰስ ከሚገኘው የከዋንካ ዴልታ ፕላን ጋር ይዛመዳል ፡፡ የተጠቀሰው ተፋሰስ ዋና ዋና የፍሎረሰንት ኮርሶች የሚከተሉት ናቸው-ፓራጓይ ፣ ቤርሜሆ ፣ ፕሊሲሲ ፣ ሳላዶ (ዴ ኖት) ፣ ኡራጓይ እና ረዥሙ ፣ ፓራና። የመጨረሻዎቹ ሁለቱ አንድ ላይ በሪዮ ዴ ላ ፕላታ አከባቢ እስኪያገኙ ድረስ አብረው ይጓዛሉ ፡፡ ይህ አከባቢ በፕላኔቷ ላይ ትልቁ ሲሆን በአርጀንቲና ውቅያኖስ ወደሚገኘው የአትላንቲክ ውቅያኖስ ክፍል ይፈስሳል ፡፡ ሁለት አስፈላጊ ወንዞች ወደ ባሕሩ ይፈስሳሉ-ኮሎራዶ እና ኔሮro ወንዞች ፡፡ በሁለቱ ወንዞች መካከል ያለው መሬት መስጴጦሚያ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን በሚርሴስ ፣ ኮርሬሴርስ እና ኢሬሬስ ግዛቶች ይጋራል ፡፡

አርጀንቲና በአሜሪካ ውስጥ 4989 ኪ.ሜ የውቅያኖስ ዳርቻዎች አሏት ፡፡ በአትላንቲክ ውቅያኖስ አህጉር በአህጉራዊ መደርደሪያው ላይ ባልተለመደ ሁኔታ ሰፊ እና አስፈላጊ የአሳ እና የሃይድሮካርቦን ሀብቶች ያሉት አርጀንቲና ባህር ተብሎ ይጠራል ፡፡ የባሕሩን መታጠቢያ የሚያጠፉት ባሕሮች በቆፍሮች እና ገደሎች መካከል ይለያያሉ። የቀዝቃዛው አንታርክቲክ እና ሞቅ ያለ የብራዚል ተለዋጭ መተካት የባሕሩ ሙቀት የሙቀት መጠን ከቀዝቃዛው ፍጥነት ጋር ተመሳሳይነት እንዳይቀንሰው ያስችላል ፣ ግን ልዩነቶች አሉት ፡፡ የደሴቲ ደቡባዊ የባህር ዳርቻ የባህር ዳርቻዎች የ Drake ማለፊያ ሰሜን ዳርቻ ይመሰርታሉ።

ግራን ቻኮ ክልል እንደ ሰሜናዊ እፀዋት እጽዋት በአገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል ይገዛሉ ፡፡ የዛምበርግሊያ የዛፎች ዝርያ በጥሩ ሁኔታ የሚሰራጭ እና በአድባሩ ዛፍ እና በናባቾ ዛፍ ይወከላል ፡፡ ጥቁር እና ነጭ የካሮብ ዛፎች (ፕሮsosoስ አልባባ እና ፕሮሶፒስ nigra) እንዲሁ ታዋቂ ናቸው ፡፡ ሳቫን በደረቅ አካባቢዎች ውስጥ ሲሆን በአንዲስስ አቅራቢያ ይገኛል ፡፡ የውሃ እፅዋት እፅዋት በክልሉ ለምርጥ በሆኑ እርጥበታማ አካባቢዎች ይበቅላሉ ፡፡

በሀገሪቱ ማዕከላዊ ክፍል ረግረጋማ ፓምፓ የተባለ ትልቅ ሜዳዋ ነው ፡፡ በመጀመሪያ ፓፓው ምንም ዛፍ አልነበረውም። ነገር ግን በሰዎች ጣልቃ ገብነት ምክንያት እንደ አሜሪካን ሲካሞር ወይም የባህር ዛፍ ያሉ አንዳንድ ከውጭ የሚመጡ ዝርያዎች ይገኛሉ ፡፡ በአካባቢው ከሚኖሩት የአገሬው ተወላጆች አንዱ ኦምቡ ፣ ሁልጊዜ አረንጓዴ ነው ፡፡

የፓምፓስ ሜዳዎች መሬቶች ከፍተኛ መጠን humus አላቸው። ይህም ክልሉ ለእርሻ እጅግ ፍሬያማ ያደርገዋል ፡፡

የምእራብ ምዕራብ ፓፓ ወይም ደረቅ ፓምፖ ከ 500 ሚ.ሜ / ዓመት በታች የዝናብ መጠን ይቀበላል ፣ እና ጠንካራ የሣር ወይም የእንጀራ እርሻ ነው። የእሱ ጣውላ በአብዛኛው በምዕራባዊው ፓምፓ ማዕከላዊ ክልል ከሚገኘው ኮማዌ ጋር ተመሳሳይ ነው ፣ እና “ኮዴን” ተብሎ በሚጠራው የበሰበሰ ዛፍ ደኖች ተሸፍነዋል ፡፡ እሱ ከርዮባባ እና ከሳን ሉዊስ አውራጃዎች ወደ ላ ላፓም እና ቡኤነስ አይሪስ ደቡባዊ ወሰኖች በሚሄድ ዲያግራናል ላይ ይሰራጫል።

በአርጀንቲና ፓራጋኒያ ውስጥ አብዛኛዎቹ እፅዋት የተቆረቆረውን ደረቅ ሁኔታ ለመቋቋም በተለመዱ ቁጥቋጦዎችና እፅዋት የተሠሩ ናቸው። ሸለቆው ካልሆነ በስተቀር አፈሩ ጠንካራ እና ዐለት ነው እና ሰፋፊ እርሻን የማይቻል ያደርገዋል። በምዕራባዊ ፓራጋኒያ እና በቲሮራ ዴ ፉዌጎ ደሴት ላይ ጥሩ ደኖች ያድጋሉ። የክልሉ ተወላጅ የሆኑት ዝንቦች larch ፣ stringillera cypress ፣ guaiteca cypress ፣ huililahuán ፣ lleuque ፣ ማño ሴት እና አኩዋዋሪያ ሲሆኑ ፣ የአገሬው የብሮድባድ ዛፍ የተለያዩ የኖትፊግየስ ዝርያዎችን ጨምሮ ፣ ሎጋ እና ñር.

በደን ውስጥ ተክል ውስጥ የሚገኙት የውጭ ዛፎች ስፕሩስ ፣ ሳይፕረስ እና ጥድ ናቸው። የተለመዱ ዕፅዋቶች ኮፒሁ እና ኮላይሁ ናቸው። በኩዮ ውስጥ በከፊል ደረቅ-እሾህ ቁጥቋጦ ቁጥቋጦዎች እና ሌሎች የካሮፊቲክ እፅዋት በብዛት ይገኛሉ። በተለያዩ ዘይቶች ሁሉ ፣ የወንዝ ሳርዎችና ዛፎች ጉልህ በሆነ ቁጥር ያድጋሉ ፡፡ አካባቢው ለትላልቅ የወይን ተክል እድገት ዕድገት ምቹ ሁኔታዎችን ያቀርባል ፡፡ በሰሜን ምዕራብ አርጀንቲና ውስጥ በርካታ የከብት ዝርያዎች አሉ ፡፡ በከፍተኛ ከፍታ ላይ (ከ 4000 ማይል / በላይ) ፣ በከፍታው ከፍታ ምክንያት ምንም ዋና እፅዋት አያድጉም ፣ እናም አፈሩ ከማንኛውም የዕፅዋት ህይወት እጦት የለውም ፡፡

አብዛኛው አርጀንቲና የሚገኘው በ Neotropical phytogeoግራፊያዊ ክልል (ካሬራ ፣ 1976) ሲሆን በዚህ ክልል ውስጥ 4 ጎራዎች ይወከላሉ ፡፡ የአርጀንቲና ትልቁ የአበባ እፅዋት ሀብታም በሰሜናዊ የአገሪቱ ክፍል በሚገኙት የአማዞን ደን ደኖች ውስጥ ይገኛሉ ፡፡ የቼክኖ ጎራ በበኩሉ እጅግ በጣም ሰፊ ምስጥር ነው ፣ ከአትላንቲክ ውቅያኖስ እስከ አንዲያን አካባቢ ድረስ ባሉት ቋጥኞች እና ሳቫናዎች እንዲሁም ከቦሊቪያ እና ፓራጓይ እስከ ሰሜን እስከ ቹውት አውራጃ ባለው ድንበር ይገኝበታል ፡፡ ለአርጀንቲና ደቡባዊ እና ምዕራብ የአኔስ ፓትራጋኒያን ጎራ ነው ፣ ይህም የአንዲስስ ከፍታ ከፍታ ያላቸውን መናፈሻዎች ፣ የፓና እና የፓትጎሪያን ባሕረ ሰላጤዎችን ፣ እና ንዑስ-አንታርክቲካ ጎራዎችን በመያዝ እና ፓትጎኒያን አንዲስ.

የአርጀንቲና ክልል እንደ ኬክሮስ ፣ ከፍታ ፣ የአፈር ሁኔታ ፣ ወዘተ ባሉ የተለያዩ ሁኔታዎች ምክንያት በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ በርካታ የአዮሚኖች እና ባዮቶፖቶችን ያካትታል። ይህ ዓይነቱ ልዩነት በራስ-ሰርቶኒየስ ፋና ውስጥ ትልቅ ልዩነቶች አሉት ፡፡ የእንስሳትን ዝርያ መኖር ለመገንዘብ የእያንዳንዱ ሥነ ምህዳራዊ trophic አውታረመረብ ምን እንደ ሆነ እና በውስጡም እንደ እያንዳንዱ ባዮቴፔ ምን እንደሚመስል ለመረዳት አስፈላጊ ነው ፣ ነገር ግን አርጀንቲና በሚባልበት ሁኔታ በዝርዝር የተፈጥሮ ሥነ-ምህዳራዊ ልዩነት ምክንያት በዝርዝር መግለፅ አይቻልም ማለት ይቻላል።

አብዛኛዎቹ የአርጀንቲና አጥቢ እንስሳቶች ከሰሜን አሜሪካ በሺዎች ከሚቆጠሩ ዓመታት በፊት የመጡ ናቸው ፡፡ ከቀዳሚው የጎንዋና ሜጋ እስከ ዛሬ ድረስ በሕይወት የተረፉት ጥቂቶች ናቸው ፡፡ ከኋለኞቹ መካከል በጣም ታዋቂ የሆኑት አርማሞሎስ ፣ ውሃዎች ፣ እና እንደ ኦፖምስ ፣ የጫካው ትንሽ ዝንጀሮ ወይም የቀይ አረም እና የዱር እንስሳት (ሁሉም ድንቢጦች) ናቸው ፡፡

በዚህ መንገድ ፣ የአርጀንቲና ግዛቱ (እንደ መላው የደቡብ ኮይን ተመሳሳይ ነው) የሚመሰረተው የፊውዳጃ አካል እና የኒውኦሮፖሎጂ ምህዳሩ ነው ፣ የአብዛኛው ክልል የአየር ሁኔታ እና ቅዝቃዛ የአየር ንብረት ቅኝቶችን እና የግንኙነት እድገቶችን ያስገኛል እንዲሁም ፈጣን ማበረታቻዎችን ፈቅደዋል ከ 9 ሚሊዮን ዓመታት በፊት በታላቁ አሜሪካን ልውውጥ ምክንያት ከነበረው የሂሎቲክ ክልል የመጡ ዝርያዎች ወይም ግማሽ ሚሊኒየም ያመረቱ እና እስከ አሁን ድረስ።

ብዛት ያላቸው የእንስሳት ዝርያዎች የሚገኙት በሐሩር ክልል እና በተለይም በደቡብ ሰሜናዊ ክፍል ነው ፡፡ እንደ ያጊዋሬቴ ፣ maማ እና ኦዚል ያሉ ትልልቅ ድመቶች አሉ ፡፡ እንደ aguará guazú ወይም maned ተኩላ ያሉ ታላላቅ መርጃዎች ፣ እንደ ድብ ድብ የሚባሉት የበርገር ዝርያዎች ፣ እንደ አንበጣ ጦጣ) እንደ ሁለት ተጓዳኝ ዝርያዎች ሁሉ ትልቅ ባሕረኞች ፡፡ ሌሎች እንስሳት ደግሞ ታፓር ፣ ካፒቢባስ ፣ ሁለት የውቅያኖስ ዝርያዎች ፣ ታላቁ ታላቁ ፣ ሦስት የከብት ዝርያዎች ፣ ግዙፍ ኦተር ፣ ኮቲ እና በርካታ የባህር ኤሊ ዝርያዎች ናቸው ፡፡

በአርጀንቲና ድንበር ተሻጋሪ ክልል እንደ ሃርፒ ንስር (በአህጉሪቱ ላይ ትልቁ አዳኝ ወፍ) ፣ በደርዘን የሚቆጠሩ ትናንሽ የ hummingbirds ዝርያዎች ፣ ሶስት የፍሬዎዶስ ዝርያዎች ፣ አምስት ቱቱካኖች እና የተለያዩ የፓሮዎች ዝርያዎች ያሉ ብዙ ወፎች አሉ ፡፡ ማዕከላዊው ጸሎቶች በታይቱስ ፣ በቀለማት ያሸበረቁት እና በታይማን ወይም በደቡብ አሜሪካ ሰጎን ተሞልተዋል ፡፡ የተለያዩ አርኬቶች ፣ ዳክዬዎች እና ፍርስራሽዎች እንዲሁም በርካታ የአጋዘን እና ቀበሮዎች ዝርያዎችም እንዲሁ ይኖራሉ ፡፡ አንዳንድ ዝርያዎች ወደ ፓራጋኒያ ይዘራሉ።

የምእራባዊ ተራራዎች የተለያዩ እንስሳት መኖሪያ ናቸው ፡፡ ከነዚህም መካከል በደቡብ አሜሪካ ውስጥ በጣም የሚታወቁ ዝርያዎች የሆኑት ላላላ ፣ ታሩካ ፣ ጓዋንኮ እና ቫይኪን ናቸው ፡፡ በተጨማሪም በዚህ ክልል ውስጥ የአንዲያን ድመት እና ኮንዶር ናቸው ፡፡ የኋለኛው በዓለም ላይ ትልቁ የበረራ ወፍ እንዲሁም ወደ ከፍተኛ ከፍታ ከሚወጡት መካከል አንዱ ነው።

Umaም ፣ ሑሙል ፣ udዱ (በዓለም ላይ ትንሹ አጋዘን) እና አስተዋውቀው የነበረው የዱር ዋልታ በደቡብ አርጀንቲና ይኖራል። የፓራጎኒያ የባሕር ዳርቻ በእንስሳት ሕይወት ውስጥ የበለፀገ ነው-የዝሆን ማኅተም ፣ የባህሩ አንበሳ ፣ የባህር አንበሳ እና የተለያዩ የፔንግዊን ዝርያዎች። በደቡባዊው መጨረሻ ዓሦችን የሚመገቡት ኮርማዎች ናቸው ፡፡

የአርጀንቲና የመሬት ዳርቻዎች የውሃ ብዛት አላቸው ፡፡ እንደ ዶልፊኖች እና ዓሣ ነባሪዎች ያሉ አጥቢ እንስሳት አሉ ፡፡ በጣም አስደናቂ ከሆኑት ዓሳ ነባሪዎች አንዱ ትክክለኛው ዓሳ ነባሪ ነው ፣ ከነ ገዳይ ነባሪዎች ጋር የ Vላዴስ ባሕረ ገብ መሬት እና የፖርቶ ማሪያን የቱሪስት መስህብ ናቸው። የባህር ውስጥ ዓሳ ሳርዲን ፣ ሀክ ፣ ሳልሞን እና የውሻ ዓሳ ያጠቃልላል ፡፡ ስኩዊድ እና የሸረሪት ክሬም እንዲሁ በቲራራ ዴ ፉዌጎ ውስጥ ይገኛሉ ፡፡ በአርጀንቲና የሚገኙት ወንዞች እና ጅረቶች እንደ ትሩፋት ያሉ እንደ ትሬንት ያሉ trout እና የደቡብ አሜሪካ ዓሳ ዓሦች ብዙ ዝርያዎች አሉት ፡፡

አርጀንቲና እና የደቡብ አሜሪካ ንዑስ ንዑስ ንጥረ ነገር በብዝበዛ እና ያልተለመዱ የአቪፊና ዝርያዎች ተለይተው ይታወቃሉ ፣ በአህጉራዊ አሜሪካዊ አርጀንቲና ውስጥ በሁሉም ዓይነቶች 1400 የአእዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ ፣ ምንም እንኳን በጥቂቶች ጥቂቶች ብቻ ቢሆኑም ብዙዎች ግን ጎልቶ ወጥቷል (በሰው ልጆች ምክንያት) የመጥፋት አደጋ አነስተኛ ነው በዚህ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ በአገሪቱ ውስጥ ወደ 400 የሚጠጉ የእንስሳት ዝርያዎች አሉ (እ.ኤ.አ. በ 2019 ከአስር ዓመት ገደማ ጥናት በኋላ 15 አዳዲስ የአርጀንቲና አጥቢ እንስሳት ተገኝተዋል) ከአንድ ሩብ በላይ 239 (98) ዝርያዎች) የመጥፋት አደጋ ላይ ናቸው ፣ ሁሉም ማለት ይቻላል ከሰው ልጅ ምክንያቶች። በአርጀንቲና ውስጥ የሚኖሩት የኦፊድያ ዝርያዎች ቡኒ ገንቢውን ፣ መርዛማውን ባራራ እና ራታንlesnake ያካትታሉ።

የአርጀንቲና ባህል በብዙ ብሔረሰቦችና ባህላዊ ባሕሎች ፣ በሕዝቦ population እና በሌሎች ባህሎች ባሕል ፣ በባህላዊ አገላለ formsች ጠንካራ ትስስር እና መሻሻል እና ዘመናዊነት በብዙ ጎሳዎች መታወቅ እና ስሜት የአውሮፓ እና የላቲን አሜሪካ ባህሎች ፣ የተወሰኑ የእስያ እና የአፍሪካ መዋጮዎች ነበሩ።

የአርጀንቲና ባህል በስደቱ ዓመታት የተገኙት የሌሎች ድብልቅ መነሻ ነው። ርዕዮተ ዓለም ፣ ማህበራዊ-ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰባቸው እና ቋንቋቸው ፣ የነፃነታቸው እምነት ፣ ዴሞክራሲ እና ለሰብአዊ መብት መከበር ጎልቶ ይታያል ፡፡

በአገሪቱ ውስጥ የተለያዩ ባህላዊ እንቅስቃሴዎች እና አስፈላጊ የስነጥበብ እንቅስቃሴ ፣ በቲያትር ፣ በሥዕል ፣ በሥዕል ፣ በሙዚቃ እና በሥነ-ጽሑፍ ውስጥ ትልቅ የስነ-ጥበባት እንቅስቃሴ አለ ፡፡ ኮንፈረንሶች ፣ ኮንሰርቶች ፣ ኤግዚቢሽኖች ፣ ቤተ መዘክርዎች ፣ ኮርሶች ፣ ቲያትር እና የባሌ ዳንስ ትርኢቶች በየቀኑ በአገሪቱ ውስጥ በጣም አስፈላጊ ከተሞች እና በዋናነት በቡኖ አይሪስ ውስጥ ይሰጣሉ ፡፡ በሁሉም ትላልቅ ከተሞች ውስጥ ሲኒማቶግራፊ እና የትያትር ቤቶች ትርatersቶች በብዛት ይገኛሉ ፡፡ እንደ ታንጎ ፣ አፈ ታሪክ (ቀደም ሲል ታንጎ በቡኤነስ አይሪስ እና ሮዛሪየስ ከተሞች ውስጥ ያሉ ታዋቂ ሙዚየሞች ነበሩ) ፣ ነገር ግን ከ “ጋሊያ ቪያጃ” እና ከ tangos መጀመሪያ ጋር ፣ የፓስካል ኮንትራክተርስ እና ካርሎስ Gardel ዘፈን ቆሙ ፡፡ ከሌሎች ሙዚቀኞች ጋር እንደ አንዱ የተለመደ የአርጀንቲና ሙዚቃ ሙዚቃ አንዱ እንደመሆኑ በዓለም ዙሪያ የሚታወቅ ቢሆንም የአርጀንቲና ተረት ተረት ጠንካራ በመሆን የአርጀንቲና አፈ ታሪክ በጥብቅ ይሳተፉ ፡፡ የአርጀንቲና ባህላዊ ሙዚቃ) እና የአርጀንቲና ብሔራዊ ዓለት (በ 1960 እና 1980 መካከል “ተራማጅ ሙዚቃ” እና “ኒው አርጀንቲና የከተማ ሙዚቃ” የሚታወቅ) በልዩ ዝግጅቶች እና በጅምላ በተገኙባቸው ቦታዎች ይጨፈራሉ ፡፡




#Article 333: ኅዳር ፱ (165 words)


ኅዳር ፱ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፷፱ኛ ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ  ፪፻፺፯ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፺፮ ቀናት ይቀራሉ።
  

፲፬፻፹፮ ዓ.ም. - ክሪስቶፎሮ ኮሎምቦ የተባለው ኢጣልያዊ መርከበኛ በሰሜናዊ አሜሪካ ምሥራቃዊ ድንበር በአትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ የምትገኘውን የፑዌርቶ ሪኮ ደሴትን አገኘ።

፲፱፻፲፩ ዓ.ም. - በባልቲክ ባሕር የምትገኘው ላትቪያ ከሩስያ ነጻ የሆነች ሉዐላዊ አገር መሆኗን አወጀች።

፲፱፻፲፱ ዓ.ም. - በደብሊን አየርላንድ የተወለደው ታዋቂ የሥነ ጽሑፍ ሰው ጆርጅ በርናርድ ሾው በስነጽሑፍ የተሸለመውን የኖቤል ሽልማት ቢቀበልም ለዚሁ ሽልማት የተወሰነውን አንድ መቶ አሥራ ስምንት ሺህ አንድ መቶ ስድሳ አምሥት የስዌድ ክሮና ግን አልቀበልም አለ። በኋላ ግን በገንዘቡ በስዌድ ቋንቋ የተጻፉ መጻሕፍት ወደ እንግሊዝኛ እንዲተረጎሙበት አደርገ።  ጆርጅ በርናርድ ሾው የሽልማቱ አሸናፊነቱ ይፋ በሆነ ጊዜ፤ “አልፍሬድ ኖቤልን ዲናሚትን መፍጠሩን ይቅር ልለው እችላለሁ፤ ነገር ግን የኖቤል ሽልማትን ለመፍጠረ የሚበቃ ግን በሰው የተመሰለ ሰይጣናዊ መንፈስ ነው” አለ።

፲፱፻፷፱ ዓ.ም. - የእስፓኝ የሕዝብ ምክር ቤት፣ አገሪቱን ከ ሠላሳ ሰባት ዓመት የ”አምባገነን” መንግሥት ስርዐት በኋላ፣ ወደዴሞክራሲያዊ ስርዐት የሚያሸጋግር ህግ አጸደቀ።




#Article 334: ኅዳር ፲፰ (216 words)


ኅዳር ፲፰ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፸፰ኛ ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ  ፪፻፹፰ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፹፯  ቀናት ይቀራሉ።
  

፲፱፻፴፬ ዓ/ም የፋሺስት ኢጣልያን የመጨረሻውን ይዞታ ጎንደርን ለማስለቀቅ አባቶቻችን አርበኞች ከእንግሊዝ ሠራዊት ጋር በከተማዋ ዙሪያ ውጊያቸውን ጀመሩ።  በዚሁ ዕለት ጄኔራል ናሲ ከነሠራዊቱ እጁን ሰጥቶ የአገራችን ኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በፋሲለደስ ግንብ ላይ ተውለበለበ።  በታሪክ መዝገብ የድል ቀን ሚያዝያ ፳፯ ቀን ፲፱፻፴፫ ዓ/ም ቢባልም ኢትዮጵያ ከፋሺስቶች የተላቀቀችበት ዕለት ግን ኅዳር ፲፰ ቀን ፲፱፻፴፬ ዓ/ም  ነው።

፲፱፻፴፭ ዓ.ም. በከፊል በናዚ ጀርመን ቁጥጥር ስር፤ በከፊል ደግሞ በጀርመን ደጋፊው የቪሺ አስተዳደር ስር የነበረችው የፈረንሳይ የባሕር ኃይል ቱሎን ወደብ ላይ የተሰበሰቡትን መርከቦቿን፣ በናዚዎች ቁጥጥር ስር እንዳይውሉ አሰመጧቸው።

፲፱፻፶፯ ዓ.ም. የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስቴር ጃዋሃርላል ኔህሩ አሜሪካ እና የሶቪዬት ሕብረት የኑክሊዬር መሣሪያዎችን መፈተሻቸውን እንዲያቆሙና እንዲያውም ያላቸውን የኑክሊዬር መሣሪያዎች እንዲያጠፉ አቤቱታቸውን አቀረቡ። 

፲፱፻፷፫ ዓ.ም. የካቶሊክ ጳጳስ ጳውሎስ ስድስተኛ ለጉብኝት ፊሊፒን አገር ሲደርሱ በማኒላ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ የቄስ ልብስ የለበሰና ጩቤ የያዘ የቦሊቪያ ተወላጅ፣ ጳጳሱን በመውጋት አቆሰላቸው።
 
፲፱፻፹፫ ዓ.ም. በብሪታንያ በፖለቲካ የቀኙ ቡድን (Conservative party) መሪዋንና የአገሪቷን ጠቅላይ ሚኒስቴር ማርጋሬት ታቸርን ከሥልጣን ካወረደ በኋላ ተተኪ እንዲሆኑ ጆን ሜጀርን የቡድኑ መሪ አድርጎ መረጣቸው።

፲፰፻፷፯ ዓ.ም. የእስራኤል መንግሥት በግንቦት ፲፱፻፵፩ ሲመሠረት የመጀመሪያው ፕሬዚደንት የሆኑት ዶክተር ኻይም ዋይዝማን 

፲፰፻፹፯ ዓ.ም.  መጀመሪያ የማትሱሺታ ኤለክትሪክ ፋብሪካ በኋላ ፓናሶኒክ የተባለውን ኩባንያ የመሠረቱት የጃፓን ዜጋ ኮኖሱኬ ማትሱሺታ




#Article 335: ኅዳር ፳ (167 words)


ኅዳር ፳ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፹ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ  ፪፻፹፮ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፹፭  ቀናት ይቀራሉ።
  

፲፯፻፸፬ ዓ.ም. በሊቨርፑል የብሪታንያ ከተማ የተመዘገበ የአፍሪቃ ሰዎችን በግዳጅ ለአገልግሎት የሚሸጥ ድርጅት ንብረት የነበረችው “ዞንግ” የምትባለው መርከብ ከጫነቻቸው ሰዎች መቶ ሠላሳ ሦሥቱን አፍሪቃውያኖች መርከበኞቹ በሕይወት እያሉ ወደ ባሕር ጥለው ገደሏቸው። በአሥራ ስምንተኛው ክፍለ ዘመን ለባርነት የሚጫኑ የአፍሪቃ ዜጎች በአውሮፓ ሕግ ፊት እንደ ዕቃ ንብረት እንጂ እንደ ሰው ስለማይቆጠሩ፣ ይሄንን ታላቅ ወንጀል የፈጸሙት ሰዎች አልተከሰሱም።  የመርከቧ ባለቤቶች ግን  “ለጠፋው ንብረት’’ የዋስትና ውል የሰጣቸውን ድርጅት በፍርድ ቤት የኪሳራቸውን ዋጋ እንዲከፍላቸው ክስ አቀረቡ።

፲፰፻፳፫ ዓ.ም. በፖሎኝ የሩሲያን በላይነት እና አስተዳደር በመቃወም የ”ትጥቅ ትግል” ተጀመረ።

፲፱፻፵ ዓ.ም. የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ፍልስጥኤምን በሐይማኖት መሠረት ለሁለት ከፍሎ አንደኛው የይሁዳዊ መንግሥት፤ ሁለተኛውን ክፍል ደግሞ የአረብ መንግሥት እንዲመሠረት የሚያስችለውን “ውሳኔ ፻፹፩” አጸደቀ። ይሄው ውሳኔ በድምጽ ሠላሣ ሦስት አገሮች ሲደግፉት፤ አሥራ ሦሥት አገሮች ተቃውመው አሥር አገሮች ደግሞ የድጋፍም የቅራኔም ድምጽ ከመስጠት ተቆጥበዋል። ኢትዮጵያ እና ብሪታንያ ከነኝህ ከአሥር አገሮች መሀል ይገኛሉ።




#Article 336: ኅዳር ፳፩ (220 words)


ኅዳር ፳፩ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፹፩ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ  ፪፻፹፭ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፹፬  ቀናት ይቀራሉ።
  

፲፱፻፵፮ ዓ.ም. በኡጋንዳ የቡጋንዳ ንጉሥ ዳግማዊ ኤድዋርድ ሙቴሳ በአገሪቱ የብሪታንያ አስተዳደሪ ‘ሰር አንድሩው ኮሄን’ ተሽረው በስደት ወደለንደን ሄዱ።

፲፱፻፶፫ ዓ/ም ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በጋና፤ ላይቤሪያ፤ ቶጎ፤ ብራዚል ፤ ናይጄሪያ እና ካሜሩን የሚያካሂዱትን ጉብኝት ለመፈጸም ከአዲስ አበባተነሱ። ዳሩ ግን ዕቅዳቸውን ሳያጠናቅቁ በኢትዮጵያ የታኅሣሥ ግርግር መነሳት ምክንያት ጉዟቸውን አቋርጠው ይመለሳሉ።

፲፱፻፶፭ ዓ.ም. ዩ ታንት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በዋና ጸሐፊነት ተመረጡ። በዋና ጸሐፊነት ኮንጎ በአየር አደጋ የሞቱትን ዳግ ሃመርሾልድን  ይተካሉ።

፲፱፻፶፱ ዓ.ም. የባርባዶስ ደሴት ከብሪታንያ ነጻነቷን ተቀዳጀች።

፲፱፻፷ ዓ.ም. የየመን ሕዝባዊ ሪፑብሊክ ከብሪታንያ ነጻነቷን ተቀዳጀች።

፲፱፻፷ ዓ.ም. በፓኪስታን በኋላ የአገሪቱ መሪ የሆኑት እና በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን ወርደው በስቅለት ሞት የተቀጡት ዙልፊቃር አሊ ቡቶ የፓኪስታን ሕዝባዊ ፓርቲን መሠረቱ።

፲፱፻፷፯ ዓ/ም - በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የነዳጅ ክምችቱን ለማፈንዳት የተደረገው ሙከራ ከሽፏል

፲፱፻፺፰ ዓ.ም. በካምፓላ ኡጋንዳ የተወለዱት  ጆን ታከር ሙጋቢ ሴንታሙ ዘጠና ሰባተኛው የዮርክ ሊቀ ጳጳስ ሆኑ። በዚህ ቤተ ክርስቲያን ይሄንን ታላቅ ሥልጣን የተቀበሉት የመጀመሪያው ጥቁር ጳጳስ ናቸው።

፲፰፻፳፰ ዓ.ም.  ሳሙኤል ላንግሆርን ክሌመንስ የተባለው አሜሪካዊ እና በብዕር ስሙ ማርክ ትዌይን የሚባለው ታዋቂ ደራሲ 

፲፰፻፷፯ ዓ.ም. ታላቁ የሁለተኛው ዓለም ጦርነት መሪ እና የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዊንስተን ቸርቺል

፲፰፻፺፫ ዓ.ም. የጽሑፍ፣ የቅኔ እና የተውኔት ጠቢብ የአየርላንድ ተወላጁ ኦስካር ዋይልድ




#Article 337: ኅዳር ፳፪ (217 words)


ኅዳር ፳፪ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፹፪ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ  ፪፻፹፬ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፹፫  ቀናት ይቀራሉ።
  

፲፱፻፫ ዓ/ም - የአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያው የመድሐኒት መደብር (ፋርማሲ)፣ ዶክቶር ሜራብ በተባለ፣ የጆርጂያ ተወላጅ፤ የጊዮርጊስ ፋርማሲ ወይም የጆርጂያ ፋርማሲ (Pharmacie la Géorgie) በሚል ስም ተሠይሞ በዚህ ዕለት ተከፈተ።

፲፱፻፵፰ ዓ.ም. በአላባማ ግዛት ውስጥ በሞንትገመሪ ከተማ፣ ልብስ ሰፊዋ ሮዛ ፓርክስ ወጥቶ እብስ ላይ መቀመጫዋን፣ (በወቅቱ ዘረኛ የከተማዋ ሕግ መሠረት)፣ ለነጭ ሰው አልለቅም በማለቷ የ”ሞንትገመሪ ወጥቶ እብስ አድማ” ተከሰተ። 

፲፱፻፶፩ ዓ.ም. የፈረንሳይ ቅኝ ግዛት የነበረችው የመካከለኛው አፍሪካ ሪፑብሊክ በዛሬው ዕለት ነጻነቷን ተቀዳጀች።

፲፱፻፹፫ ዓ.ም. በእንግሊዝ ባህር ስር በብሪታንያ እና በፈረንሳይ አገሮች መካከል የውስጠ መሬት የባቡር መሥመር የተመሠረተበት ቡርቦራ ከባሕሩ በታች አርባ ሜትር ጥልቀት ላይ ተገናኘ።  

፲፱፻፺፬ ዓ.ም. የኢትዮጵያ አየር መንገድን የመሠረተው የአሜሪካው ትራንስ ወርልድ አየር መንገድ (Trans World Airlines) ከሰባ ስድስት ዓመታት አገልግሎት በኋላ በአሜሪካ አየር መንገድ  (American Airlines) ተገዛ።

፲፱፻፭ ዓ.ም. በኒው ዮርክ ከተማ በ፲፱፻፺፬ ዓ.ም. በሽብርተኛ አመጸኞት የወደሙትን ‘የዓለም የንግድ ማዕከል” (World Trade Center) የሚባሉትን መንታ ሕንጻዎች የነደፈው ሚኖሩ ያማሳኪ የተባለ ‘ትውልደ ጃፓን’ አሜሪካዊ በሲያትል ከተማ ተወለደ።

፲፱፻፷፮ ዓ.ም. የእስራኤልን ሉዐላዊ አገር የመሠረተውና የአገሪቱ የመጀመሪያው ጠቅላይ ሚኒስቴር ዳዊት ቤን ጉርዮን በሰማንያ ሰባት ዓመቱ አረፈ።

፲፱፻፹፯ ዓ.ም. ታዋቂው ደራሲ ፥ የሥነ ጽሑፍ መምሕር ፥ ገጣሚ እና የተውኔት ጠቢብ የነበረው ዳኛቸው ወርቁ




#Article 338: ተክለጻድቅ መኩርያ (253 words)


ከ ብርሃነ መስቀል ደጀኔ እና ጌታሁን ሽብሩ “ያሠርቱ ምእት፥ የብርዕ ምርት” የተወሰደ

ተክለጻድቅ መኩርያ በ፲፱፻፮ ዓ.ም. በተጉለትና ቡልጋ አውራጃ አሳግርት ልዩ ስሙ ሳር አምባ በተባለ ሥፍራ ተወለዱ።

ዕድሜያቸው ለትምሕርት ሲደርስ መጀመሪያ ከአባታቸውና ቀጥሎም በአጥቢያቸው ባህላዊውን ትምሕርት እስከቅኔ ያለውን ቀስመዋል። ከዚያም አዲስ አበባ መጥተው አሊያንስ ፍራንሴዝና ተፈሪ መኮንን ትምሕርት ቤት ገብተው የጊዜውን የትምሕርት ደረጃ አጠናቀዋል።

ኢጣልያ አገራችንን የወረረች ጊዜም በየካቲት ፲፪ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓ.ም. ፍጅት ተይዘው ወደ ሶማሌ ደናኔ ተግዘው ለሦስት ዓመታት ታስረዋል። ከነጻነትም መልስ አገራቸውን በተለያዩ የኃላፊነት ደረጃዎች አገልግለዋል።

መጀመሪያ ተቀጥረው ያገለገሉት በትምሕርትና ሥነጥበብ ሚኒስቴር ነበር። እዚያም ሳሉ በአገራችን ሰው የተጻፈ የአገራችን ታሪክ አንድም ባለመኖሩ በቁጭትና በመቆርቆር ነበር ‘መጻፍ አለብኝ’ ብለው በደንብ ከሚታወቀው ከቅርቡ ጊዜ በቅጡ ወደማይታወቀው የሩቁ ዘመን መጻፍ የጀመሩት። የመጀመሪያውን መጽሐፍ “የኢትዮጵያ ታሪክ ከዓፄ ቴዎድሮስ እስከ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ” የሚለውን በ ፲፱፻፴፰ ዓ.ም. አሳተሙ። ከጫፍ እስከ ጫፍ ጽፈው የመጨረቻውን መጽሐፍ፣ የታሪካችን መጀመሪያ የሚሆነውን “የኢትዮጵያ ታሪክ ኑብያ-አክሱም-ዛጉዬ እስከ ዓፄ ይኩኖ አምላክ ዘመነ መንግሥት” የሚለውን በ፲፱፻፶፩ ዓ.ም. አቅርበዋል። እኒህኑ መጻሕፍት ትምሕርት ሚኒስቴር ታሪክ ለማስተማሪያ በትምሕርት ቤት ተጠቅሞባቸዋል።

ተክለጻድቅ ከታሪክ ውጭ የጻፏቸው “የሰው ጠባይና አብሮ የመኖር ዘዴ” እና በሚዮቶሎዢያ (mythology አፈ ታሪክ) ላይ ያተኮረ “ከጣዖት አምልኮ እስከ ክርስትና” የሚሉም መጽሐፎች አሏቸው።

ተክለጻድቅ በምድር ባቡር በዋና ጸሐፊነት፥ በቤተ መጻሕፍት ወመዘክር ዋና ሥራ አስኪያጅነት፥ እንዲሁም በፈረንሳይ፥ በእስራኤል፥ በዩጎዝላቪያ በዲፕሎማሲ ሥራ በመጨረሻም የትምሕርትና የባህል ሚኒስቴር ሆነው አግልግለዋል። በፈቃዳቸው ጡረታም ከወጡ በኋላ በምርምር የታገዙ ሦስት ታላላቅ የታሪክ ሥራዎችን አቅርበዋል።

ተክለጻድቅ ከረጅም የአገልግሎት ዘመን በኋላ በተወለዱ በ ሰማንያ ስድስት ዓመታቸው ሐምሌ ፲፮ ቀን ፲፱፻፺፪ ዓ.ም. አርፈዋል።

የተክለጻድቅን ሥራዎች ዋጋ የምንሰጣቸው ለሚከተሉት ምክንያቶች ነው፦

ብርሃነ መስቀል ደጀኔ እና ጌታሁን ሽብሩ፣ “ያሠርቱ ምእት፥ የብርዕ ምርት ክፍል ፩” ፣ ጳጉሜን ፲፱፻፺፱ ዓ.ም.




#Article 339: ዳኛቸው ወርቁ (562 words)


ዳኛቸው ወርቁ በዛብህ «አደፍርስ» (፲፱፻፷፪ ዓ.ም.) በተሰኘ ልብ ወለድ ድርሰቱ ባነሳቸው ጭብጦች እና የተራቀቀ የአጻጻፍ ስልቱ የአማርኛን ዘመናዊ ልብ ወለድ ወደ ድንቅ ከፍ ካለ እርከን ያወጣ፥ «እምቧ በሉ ሰዎች» በሚለው የግጥም መድብሉ (፲፱፻፷፯ ዓ.ም.) ውስጥ በተካተቱ ግጥሞቹ ስለሀገሩ ልማትና ዕድገት ተቆርቋሪነቱን የገለጠ ዕውቅ የሥነ ጽሑፍ ምሁር፥ ሐያሲና ተርጓሚ የነበረ ሲሆን በልሳነ እንግልጣር (እንግሊዝኛ) በመጻፍም «The Thirteenth Sun» የኢትዮጵያን ሥነ ጽሑፍ በዓለም አቀፉ መድረክ ካስተዋወቁ በጣት ከሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ጸሓፍት አንዱ ነበር።

'የ ፊውዳል ኢትዮጵያን ሶሲዮሎጂና የታሪክ ጥራዞች ከማንበብ፥ «አደፍርስ» ድርሰቱን ማንበብ ይቀላል’ የተባለለት ዳኛቸው ወርቁ የካቲት ፲፮ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓ.ም. በሰሜን ሸዋ በይፋትና ጥሙጋ በደብረ ሲና ከተማ አቅራቢያ ከአቶ ወርቁ በዛብህና ከወይዘሮ አሰገደች ሀብተወልድ ተወለደ። ከቤተ ሰቡ አምሥት ልጆች ዳኛቸው በኩር ነበር።

ዳኛቸው ከ፲፱፻፴፮ ዓ.ም. እስከ ፲፱፻፵፪ ዓ.ም. ድረስ በተወለደበት አካባቢ በደብረ ሲናው አብዬ ትምሕርት ቤት የአንደኛ ደረጃ ትምሕርቱን ተከታተለ። እዚያ ሳለ ገና በ አሥራ ሦስት ዓመቱ፥ «ያላቻ ጋብቻ ትርፉ ሐዘን ብቻ» የተሰኘች ተውኔት ደርሶ በመተወን ታዋቂነት ያተረፈ ወጣት ነበር።

በ፲፱፻፵፫ ዓ.ም. አዲስ አበባ መጥቶ መጀመሪያ ሊሴ ገብረማርያም ኋላ ግን በኮተቤ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የሁለተኛ ደረጃ ትም?ህርቱን የተከታተለ ሲሆን በኮከበ ጽባሕ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ትምሕርት ቤት ይሰጥ የነበረውን የመምሕርነት ኮርስ ለአንድ ዓመት ተከታትሎ በመምሕርነት ተመርቋል። ከምረቃ በኋላ በሐረር መድኃኔዓለም ለሁለት ዓመታት፥ በአዲስ አበባ ተግባረ ዕድ ለሁለት ዓመታት ግዕዝና አማርኛ ያስተማረ ሲሆን፣ «ሰቀቀንሽ እሳት» የተሰኘ ተውኔቱን በመድረስ ተሰጥዖውን የገለጸ፥ «ሰው አለ ብዬ» የተውኔት ድርሰቱን በማሳተም ያበረከተ የፈጠራ ሰው ነበር።

ዳኛቸው በ፲፱፻፶፫ ዓ.ም. በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነ ጽሑፍ ትምሕርቱን እየተከታተለ የአራተኛ ዓመት ተማሪ ሳለ በረዳት መምሕርነት ጭምር በዩኒቨርሲቲው ያገለገለ ሲሆን ተመርቆ እስከወጣበት ጊዜም ድረስ በወቅቱ የተማሪው የለውጥ እንቅስቃሴ ውስጥ በመሳተፍ ከዘመነኞቹ የኮሌጅ ገጣሚዎች ከነታምሩ ፈይሳ፥ ዮሐንስ አድማሱ፥ አበበ ወርቄ፥ ይልማ ከበደ፥ ኢብሳ ጉተማ፥ ኃይሉ ገብረዮሐንስ፥ መስፍን ሀብተማርያም፥ ወዘተ ጋር እነ «ወጣቱ ፈላስማ» በመሳሰሉ ግጥሞቹ የለውጥ ሐሳቡን ሲያስተጋባ የነበረ ገጣሚም ነበር።

በ፲፱፻፶፮ ዓ.ም ተመርቆ፣ ከ፲፱፻፶፯ ዓ.ም. እስከ ፲፱፻፷፩ ዓ.ም. ድረስ እዚያው ዩኒቨርሲቲው በመምሕርነት ያገለገለ ሲሆን «ትበልጭ» የተሰኘ ተውኔቱን በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቴአትር ለመድረክ ያበቃ «ጸሐፌ-ተውኔት» ነበር። በ፲፱፻፷፪ ዓ.ም. በአሜሪካ ኦሃዮ ዩኒቨርሲቲ የፈጠራ ሥነ ጽሑፍ አጥንቶ በመመረቅ ‘የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ’ የሚል ማዕረግ ያገኘ፥ የመጀመሪያዎቹንም አጫጭር ልብ ወለዶች ደርሶ የታተሙለት ብርቅ ሰው ነበር።

ወደሀገሩ ተመልሶ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ በቋንቋ መምሕርነት እስከ ፲፱፻፷፭ ዓ.ም. ያገለገለው ዳኛቸው የ”ኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነ ጽሑፍ ክፍል”ን ከነ ጌታቸው ኃይሌ፥ ከነአብርሃም ደሞዝ፥ ዮሐንስ አድማሱ፥ ኃይሉ ፉላስ.. ወዘተ ጋር ያደራጀ፣ ወጣት የሥነ ጽሑፍ ባለሙያዎችን በማደራጀት አስተዋጽዖ ያደረገ ምሁር ሲሆን፥ ባነሳቸው በሳል የለውጥ ሐሳቦችና የተራቀቀ ሥነ ጽሑፋዊ የአቀራረብ ስልቱ የተደነቀውን የኢትዮጵያን የዘመናዊ ልብ ወለድ ሥነ ጽሑፍ ልዩ ልዩ በእድገት ምዕራፍ ያሸጋገረውን «አደፍርስ» ልብ ወለዱን በ፲፱፻፷፪ ዓ.ም. በማሳተም ታላቅ ጠቢብነቱን ማስመስከሩ ብቻ ሳይሆን፤ በወቅቱ ይታተሙ በነበሩ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ፥ የኢትዮጵያ ድምጽ እና አዲስ ዘመን ጋዜጦችም የኢትዮጵያን ሥነ ጽሑፍ የተመለከቱና የወጣት ደራሲያንን ሥራዎችን በመሔስ ለሀገሪቱ ሥነ ጽሑፍ ዕድገት ምሁራዊ ተልዕኮውን የተወጣበት ወቅት ነበር።

የዛሬዎቹን ወጣት ኢትዮጵያውያን በጥበቡ ዘርፍ የሚታደጉ የሥነ ጽሑፍ ጥበብ መመሪያ፣ የአማርኛ ፈሊጦች መጽሐፍት ያሳተመ ምሁር ሲሆን አንድም ለሀገሪቱ ቋንቋ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያላቸውን «የማርክሲዝም ሌኒንዝም መዝገበ ቃላት» እና «የሳይንስና ቴክኖሎጂ መዝገበ ቃላት» የመሳሰሉ ጥልቅ እና ምጡቅ ሥራዎች ዝግጅት ላይ በመሳተፍ ምሁራዊ ግዴታውን የተወጣ ኢትዮጵያዊ ነበር።

የሀገሩን እምነትና ባህል ጠንቅቆ የሚያውቅ፥ ለሥራ ነገን የማያውቅ፥ ለውጥ ፈላጊ፥ አገር ወዳድ፥ ስለሀገር ኋላ ቀርነት ሁሌ የሚቆረቆር ፥ ማጎብደድና ማቆሻበድ የማይወድ፥ ፊት ለፊት ተናጋሪ ባጠቃላይ በ«አደፍርስ» ልብ ወለድ ድርሰቱ ጠጣርና ምጡቅ ሐሳቦች በድንቅና ውብ የአጻጻፍ ስልት፥ ልዩ በሆነ የቋንቋ ኃይል የአማርኛ ሥነ ጽሑፍ ልዕልና ያሳየ - ዳኛቸው ወርቁ - በዚሁ ድርሰቱ የፈጠራ መጽሐፍ የሚነበብ ብቻ ሳይሆን ተደጋግሞ የሚነበብና የሚያወያይ መሆኑን - አዲስ ባህል የተከለ ብርቅ የጥበብ ሰው ነበር።

ዳኛቸው ወርቁ ኅዳር ፳፪ ቀን ፲፱፻፹፯ ዓ.ም. በድንገት ታሞ አርፎ በተወለደበት ደብረ ሲና ከተማ ቀብሩ ተፈጸመ። በሥራዎቹ ዛሬም ከእኛው ጋር ነው።

 




#Article 340: ኅዳር ፳፬ (176 words)


ኅዳር ፳፬ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፹፬ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ  ፪፻፹፪ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፹፩  ቀናት ይቀራሉ።
  
ይሄ ዕለት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጥቅምት ፬ ቀን ፲፱፻፹፭ ዓ.ም. ባጸደቀው ስምምነት ቁጥር ፵፯⁄፫ “የዓለም አቀፍ የ’ድውያን’ ቀን” ተብሎ ተሰይሟል።

፲፰፻፲፩ ዓ.ም. በመካከለኛው አሜሪካ የምትገኘው የኢሊኖይ ግዛት በሃያ አንድኛ ደረጃ ከአሜሪካ ሕብረት ጋር ተዋሃደች።

፲፱፻፳፪ ዓ/ም - አዲሱ የአዲስ አበባ የምድር ባቡር ጣቢያ ሕንፃ በዚህ ዕለት በአልጋ ወራሹ ራስ ተፈሪ መኮንን ተመርቆ ተከፈተ።

፲፱፻፷ ዓ.ም. በደቡብ አፍሪቃ የቀዶ ጥገና ሐኪም ዶክቶር ክርስቲያን ባርናርድ የመጀመሪያው የሰው ልብ በ ’ቀዶ ጥገና’ ጥበብ ከሟቹ ‘ዴኒስ ዳርቫል’ ወደተቀባዩ የልብ በሽተኛ ‘ሌዊስ ዋሽካንስኪ’  አጠናቀቁ።

፲፱፻፷፱ ዓ.ም. በጃማይካ የ’ሬጌ’ ሙዚቃ ባላባት ቦብ ማርሌይ ላይ የገደላ ሙከራ ተደረገ። በሁለት ጥይቶች ቢመታም ማርሌይ ከሁለት ቀን በኋላ መድረክ ላይ ወጣ። 

፲፱፻፸፬ ዓ.ም. ሕንድ አገር ውስጥ በቦፓል ከተማ ፥ የአሜሪካው ዩኒየን ካርባይድ ( Union Carbide) የኬሚካል ኩባንያ ውስጥ በተከሰተው አደጋ መርዛዊ ኬሚካል አየሩን በክሎት ሦስት ሺህ ስምንት መቶ ሰዎች ሲሞቱ እስከ ስድስት መቶ ሺህ ሰዎች በአደጋው ምክንያት ጤናቸው እንደተበላሸ ይገመታል።




#Article 341: ኅዳር ፳፭ (228 words)


ኅዳር ፳፭ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፹፭ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ  ፪፻፹፩ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፹  ቀናት ይቀራሉ።

፲፮፻፲፪ ዓ.ም. ሠላሣ ስምንት ከብሪታንያ የመጡ አቅኝዎች ቨርጂኒያ ላይ አርፈው ለ እግዚአብሔር ምስጋናቸውን አቀረቡ። ይሄም ድርጊት በአሜሪካ የመጀመሪያው የምሥጋና ሰርዐት ዕለት ነበር ይባላል።

፲፯፻፹፬ ዓ.ም. በዓለም የመጀመሪያው የ’ዕሑድ ጋዜጣ’ የብሪታንያው ‘ኦብዘርቨር’ ‘The Observer’ የተባለው ጋዜጣ የመጀመሪያው ዕትም ወጣ።

፲፱፻፴፰ ዓ.ም. በአሜሪካ የሕዝብ እንደራሴዎች ‘United States Senate’ አባላት በስድሳ አምሥት ለ ሰባት ድምጽ አሜሪካ ጥቅምት ፲፬ ቀን ፲፱፻፴፰ ዓ.ም. የተመሠረተው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዓባል እንድትሆን አጸደቁ። 

፲፱፻፶፩ ዓ.ም. የቀድሞዋ ዳሆሚ የዛሬዪቷ ቤኒን ከ ፈረንሳይ ቁጥጥር ውጭ ዕራሷን በራሷ የመግዛት ስርዐት ጀመረች።

፲፱፻፶፬ ዓ.ም. የብሪታንያ መንግሥት ለሴቶች ዜጋዎቹ የ’ጽንሰት መከላከያ’ መድሐኒት በብሔራዊ የጤና ጥበቃ አገልግሎት  በነጻ መቀበል እንዲችሉ አደርገ። 

፲፱፻፸ ዓ.ም. የመካከለኛው አፍሪካ ሪፑብሊክ ፕሬዚደንት ጃን ቤደል ቦካሳ ዕራሳቸውን በራሳቸው ቀዳማዊ ቦካሳ በሚል ስም በማንገሥ የአገሪቱም ስም ተቀይሮ ‘የመካከለኛው አፍሪካ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት’ በሚል ስም ተሰየመች።

፲፱፻፹፬ ዓ.ም. የፓን አሜሪካ አየር መንገድ ከ ስድሳ አራት ዓመታት አገልግሎት በኋላ አከተመ።

፲፱፻፹፭ ዓ.ም. በሶማሊያ አገር ውስጥ በተከሰተው የ’ዕርስ በርስ ጦርነት’ የአሜሪካው ፕሬዚደንት ጆርጅ ኸርበርት ዎከር ቡሽ የ’ሰብዓዊ ርሕራሔ’ ምክንያት በሚል መነሻ ሃያ ስምንት ሺህ የአሜሪካ ወታደሮችን ወደ ሶማሊያ ላኩ።

፲፰፻፸፭ ዓ.ም. እስፓኝን ለሠላሣ ስድስት ዓመታት በአምባገነንነት የመሩት ፍራንሲስኮ ፍራንኮ ተወለዱ።

፲፭፻፷ ዓ/ም - የዓፄ ልብነድንግል ሚስት እቴጌ ሰብለ ወንጌል በዚህ ዕለት አመድ በር በምትባል ሥፍራ አረፉ።




#Article 342: ኅዳር ፳፰ (136 words)


ኅዳር ፳፰ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፹፰ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ  ፪፻፸፰ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፸፯  ቀናት ይቀራሉ።

፲፱፻፴፬ ዓ.ም. የጃፓን ንጉሠ ነገሥት የባሕር ኃይል የአሜሪካንን የሰላማዊ ውቅያኖስ የባሕር ኃይል እና አብሮ የተሰለፈውን የጦር ኃይል በ ሃዋይ ደሴቶች ላይ ባለችው ፐርል ሃርበር ‘Pearl Harbour’ በተሰኘችው ወደብ ላይ እንዳሉ ከፍተኛ አደጋ ጥላባቸው አሜሪካን የሁለተኛው ዓለም ጦርነት ውስጥ እንድትገባ የገፋፋትን ታሪካዊ ሁኔታ ከሰተች።

፲፱፻፸፪ ዓ.ም. በሮዴዥያ የሽግግር መንግሥትን እንዲያስተዳድሩ የተመረጡት የዊንስተን ቸርችል አማች የነበሩት እንግሊዛዊው ‘ሎርድ ሶምስ’ (Lord Soames) እጩነታቸው ይፋ ተደረገ።

፲፱፻፹፰ ዓ.ም. የአሜሪካ የጠረፍ መንኲራኩር ‘ጋሊሌዎ’ ከምድር በተተኮሰች በስድስት ዓመቷ ጁፒተር ዘንድ ደረሰች።

፲፱፻፹፮ ዓ.ም. አገራቸውን አይቮሪ ኮስትን  ከፈረንሳይ ነጻነቷን ከተቀዳጀችበት ፲፱፻፶፫ ዓ.ም. እስከ ዕለተ ሞታቸው ድረስ በፕሬዚደንትነት የመሩት ፊሊክስ ሁፌ ቧኜ በተወለዱ በ ሰማንያ ስምንት ዓመታቸው አረፉ።




#Article 343: ኅዳር ፴ (175 words)


ኅዳር ፴ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፺ኛው ቀን እና የወሩ መጨረሻ ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ  ፪፻፸፮ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፸፭  ቀናት ይቀራሉ።

፲፰፻፴፭ ዓ/ም በአንኮበር እና ዙሪያዋ የተከሰተው የመሬት እንቅጥቅጥ ከተማዋን አወደማት።

፲፰፻፸፭ ዓ/ም በሉዊዚያና ግዛት ‘ ፒ. ቢ. ኤስ. ፒንችባክ’ የመጀመሪያው ጥቁር አሜሪካዊ ገዥ ሆነ ።

፲፰፻፺፰ ዓ/ም በፈረንሳይ መንግሥትን እና ቤተ ክርስቲያንን የሚለየው ህግ ጸደቀ።

፲፱፻፶፬ ዓ/ም የቀድሞዋ ታንጋኒካ ከብሪታንያ ነጻነቷን ተቀዳጀች። ከነጻነት በኋላ በዚሁ ዕለት በ፲፱፻፶፯ ዓ/ም ታንጋኒካ ከዛንዚባር ጋር ተዋሕዳ የዛሬይቱን የታንዛኒያ ሪፑብሊክ መሠረቱ።

፲፱፻፹፫ ዓ/ም በፖሎኝ አገር ሌክ ቫሌሳ የመጀመሪያው በሕዝብ የተመረጠ ፕሬዚደንት ሆነ ።

፳፻፩ ዓ/ም በአሜሪካ የኢሊኖይ ገዥ ሮድ ብላጎዬቪች በብዙ ወንጀሎች ተከሶ በፌዴራል ህግ አስከባሪዎች ተያዘ። ፈጽሟል ከተባሉት ወንጀሎች አንዱ በፕሬዚደንትነት የተመረጡትን የባራክ ኦባማን የእንደራሴዎች ምክር ቤት (United States Senate) አባልነት በገንዘብ ሊሸጥ ሞክሯል በመባል ነው ።

፲፱፻፱ ዓ/ም ስመ ጥሩው አሜሪካዊ የፊልም ተዋናይ ከርክ ዳግላስ

፲፰፻፵፰ ዓ/ም የሸዋው ንጉሥ እና የዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ አባት ንጉሥ ኃይለ መለኮት በኃይል ሊያስገብሯቸው ከመጡት ከዓፄ ቴዎድሮስ ጋር ለጦርነት ሲዘጋጁ በድንገት ታመው አረፉ።

 




#Article 344: ታኅሣሥ ፩ (203 words)


ታኅሣሥ ፩ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፺፩ኛው ቀን እና የወሩ መጀመሪያ ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ  ፪፻፸፭ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፸፬  ቀናት ይቀራሉ።

፲፰፻፲ ዓ/ም የአሜሪካ ኅብረት በዛሬው ዕለት የሚሲሲፒን ግዛት ሃያኛ የማኅበር ዓባል አድርጎ ተቀበለ። 

፲፰፻፷፩ ዓ/ም በዓለም የመጀመሪያው የመንገድ ተሽከርካሪዎች መቆጣጠሪያ መብራት በእንግሊዝ ዋና ከተማ በለንደን ላይ የፓርላማ ሕንጻ (የዌስትሚንስተር ቤተ መንግሥት) ‘Palace of Westminster’ ፊት ለፊት ተተክሎ አገልግሎት ላይ ዋለ።

፲፰፻፺፬ ዓ/ም ለመጀመሪያ ጊዜ የኖቤል ሽልማቶች ተሸለሙ።

፲፱፻፳፱ ዓ/ም በብሪታንያ በንጉሡ የፍቅረኛቸውን ምርጫ ምክንያት በተከሰተው ቀውስ፥ ንጉሥ ኤድዋርድ ስምንተኛ ሥልጣናቸውንና ዘውዳቸውን መልቀቅ የሚያስችላቸውን ህግና ስምምነት ፈረሙ።

፲፱፻፶፯ ዓ/ም በኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎ ላይ በተካሄደ ሥነ ሥርዐት ላይ ጥቁር አሜሪካዊው የሰብአዊ መብት ዋና ተሟጋችና ሰማዕት ማርቲን ሉተር ኪንግ የኖቤል ሰላማዊ ሽልማት ተቀበሉ።
 
፲፱፻፸፩ ዓ/ም የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስቴር ሜናኽም ቤጊን እና የግብጽ ፕሬዚደንት አንዋር ሳዳት የኖቤል ሰላማዊ ሽልማት ተካፋዮች ሽልማቱን ተቀበሉ።

፲፱፻፸፬ ዓ/ም  የብሪታንያው ቢ.ቢ.ሲ. በአሜሪካ አሥራ አምሥት ግዛቶች ውስጥ ‘ሰዶማውያን’ን የሚያጠቃ ያልታወቀ አዲስ በሽታ እንደገባ እና በእነኚሁ ግዛቶች ውስጥ ሰባ አምሥት ሰዎች፥ በእንግሊዝ አገር ደግሞ አንድ ሰው በዚሁ በሽታ መሞታቸውን ዘገበ። ይሄ በሽታ በኋላ ኤይድስ የተባለው በሽታ ሲሆን ሠላሣ ዓመታት እንኳን ባልሞላ ጊዜ ውስት በዓለም ላይ ወደ ሃያ አራት ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን ሕይወት ወስዷል።




#Article 345: ፋርስ (216 words)


ፋርስ አገር (ፋርስኛ፦ ایران /ኢራን/) ወይም የኢራን ኢስላማዊ ሬፑብሊክ (جمهوری اسلامی ایرا /ጆምሁሪ-የ ኤስላሚ-የ ኢራን) በእስያ ውስጥ የሚገኝ አገር ነው። ዋና ከተማው ቴህራን ነው።

ለኗሪዎቹ የሀገር ስም ከጥንት ጀምሮ ኢራን ሲሆን ከአገር ውጭ እንደ ፋርስ ወይም በመሰለ ስያሜ ይታወቅ ነበር። 
 
በ1927 ዓም ሻህ (ንጉስ) ሬዛ ሻህ ሀገሩ በውጭ አገራት ዘንድ «ኢራን» በመባል እንዲታወቅ ጠየቀ። (በዚህም ወቅት ያህል ደግሞ በመንግሥታት ማኅበር መሃል የኢትዮጵያ ስያሜ በ1923 ዓም ከ«አቢሲኒያ» ተቀየረ፤ የታይላንድም በ1932 ዓም ከ«ሲያም» ተቀየረ።) 

በ1951 ዓም ግን ልጁ ሻህ ሙሃመድ ሬዛ ፓሕላቪ ሁለቱ ስያሜዎች (ኢራን እና ፋርስ) አንድላይ በመለዋወጥ ትክክለኛ እንደ ተቆጠሩ አዋጀ።

ዞራስተር ባዘጋጀው በአቨስታ ዘንድ ሕዝቡ «አይርያ» (አርያኖች) ይባላሉ፤ መጀመርያ አገር ቤታቸው «አይርያነም ቫይጃህ» ሲባል ይህ በአራስ ወንዝ አካባቢ እንደ ተገኘ ይታመናል። ከዚህ መጀመርያ አገር በኋላ የተከተሉት አገራት በአፍጋኒስታንና በፋርስ አካባቢ ሲገኙ ይህም አውራጃ በጥንት «አሪያና» እና «አሪያ» ይባል ነበር። ሄሮዶቶስ 480 ዓክልበ.ግ. የሜዶን ብሔር ድሮ ስም «አሪዮይ» እንደ ነበር መሰከረ፤ የፋርስ አሓይመኒድ ነገስታት እንደ ፩ ዳርዮስ ብሔራቸውን «አሪያ» አሉት። ከሳሳኒድ ሥርወ መንግሥት ጀምሮ (218 ዓም) በመካከለኛ ፋርስኛ የሀገሩ ኗሪ ስም «ኤራን» ወይም «ኢራን» ሆኗል።

መጀመርያ በ800 ዓክልበ. ግድም ፓርሱማሽ ወይም ፓርሱዓሽ፣ ፓርሱ፣ ፓርሳ የሚባል አነስተኛ የአርያኖች ወገን በኡርሚያህ ሐይቅ ዳርቻ ተመዘገቡ፤ እነዚህም ከትንሽ በኋላ ወደ ቀድሞው ኤላም ሔደው ስማቸውን ለዛሬው ፋርስ ክፍላገር ሰጡ፤ የአሓይመኒድ ሥርወ መንግሥት መሠረቱ። ቋንቋቸውንም እስካሁን «ፋርሲ» (ፋርስኛ) ይሉታል። ስማችውና አገራቸው ከዚሁ በግሪክኛ «ፐርሲስ»፣ በሮማይስጥ «ፐርሲያ»፣ በዕብራይስጥ «ፐረስ»፣ በአማርኛም «ፋርስ» በመባል ታውቋል። 




#Article 346: ወልወል (131 words)


 

ወልወል በምሥራቅ ኢትዮጵያ ፥ በሶማሌ ክልል ውስጥ የምትገኝ ከተማ ነች ። ከተማዋ ከባህር ወለል በአምስት መቶ ሰባ ሜትር ከፍታ ላይ የምትገኝ ስትሆን    ላይ ትገኛለች። 

ኅዳር ፲፬ ቀን ፲፱፻፳፯ ዓ/ም በኦጋዴን ክልል በኢትዮጵያ እና በኢጣሊያዊ ሶማልያ ያለውን ድንበር እንዲያሠምሩ የተላኩት የብሪታንያ እና የኢትዮጵያ ልዑካን በዚሁ ክልል ውስጥ ለሥራ ይዘጋጁ ነበር። በዚህ ጊዜ ‘ሙስቲ’ በሚባል የኢጣሊያ መቶ ዓለቃ የሚታዘዙ ሁለት መቶ ሶማሌያዊ ወታደሮች የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው፤ ከሺህ በላይ የውሐ ጉድጓዶች የነበሯትን፤ በኢትዮጵያ ክልል ውስጥ ያለችውን ወልወልን ከበዋት ተገኙ። በወቅቱ የኦጋዴን ገዥ የነበሩት የፊታውራሪ ሺፈራው ወታደሮችና የኢጣልያን ወገን በሚመራው በሻለቃ ቺማሩታ ወታደሮች ለሁለት ሣምንታት ከተፋጠጡ በኋላ በኢትዮጵያና በፋሽስታዊ ኢጣልያ መካከል ለአምሥት ዓመታት የተከተለው ጦርነት ክብሪት ተጫረ። 

የፋሺስት ኢጣሊያ መሪ ቤኒቶ ሙሶሊኒ ለብዙ ዓመታት አገራችንን በኃይል ወርሮ ቅኝ ግዛት ለማድረግ ሲያቅድ የነበረውን ዓላማ በዚህ ግፍ ካካሄደ በኋላ በዓመቱ በጥቅምት ፲፱፻፳፰ ዓ.ም. በዚያው በኦጋዴን መሥመር ወረረ።




#Article 347: ታኅሣሥ ፫ (254 words)


ታኅሣሥ ፫ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፺፫ኛው ቀን  ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ  ፪፻፸፫ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፸፪  ቀናት ይቀራሉ።

ይቺ ዕለት በኢትዮጵያ ታሪክ ሁነኛ ስፍራ አላት። ታላቁ ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ አፄ ምኒልክና የጦሩ ፊታውራሪ፣ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ዲናግዴ ያረፉበት ዕለት ናት፡፡ ዕለቱ ተመሳሳይ ይሁን እንጂ ሁለቱ ያረፉት በተለያዩ ዓመታት ነው፡፡ ‹‹አባ ዳኘው›› የተባሉት፣ ዳግማዊ ምኒልክ ፳ኛው ምዕት ዓመት በባተ በስድስተኛው ዓመት ላይ በ፲፱፻፮ ዓ.ም. ሲያርፉ ‹‹አባ መላ›› የተሰኙት ፊታወራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ደግሞ በ፲፱፻፲፱ ዓ.ም. አርፈዋል።  ዓመታቱ ይለያዩ እንጂ ሁለቱም ያረፉት ዓርብ ታኅሣሥ ፫ ቀን ነበር፡፡ 

፲፱፻፬ ዓ/ም የቀድሞዋ የሕንድ ርዕሰ ከተማ ካልከታ በአዲሷ ደልሂ ተተካች። በዚሁ ዕለት የብሪታንያ ንጉሥ ጆርጅ አምሥተኛ (የዳግማዊት ንግሥት ኤልሳቤጥ አያት) እና ንግሥታቸው የ ሕንድ ንጉሠ ነገሥት እና እቴጌ የሚል ማእረግ ተጨመረላቸው።

፲፱፻፰ ዓ/ም የቻይና ሪፑብሊክ ፕሬዚደንት አገሪቱን ወደንጉዛት ሥርዐት መመለሳቸውንና  እራሳቸውንም ንጉሠ ነገሥት ማድረጋቸውን አወጁ።

፲፱፻፶፮ ዓ/ም ኬንያ ከብሪታንያ ነጻነቷን በመቀዳጀች በአፍሪቃ ሠላሣ አምሥተኛዋ ነጻ አገር ሆነች። 

፲፱፻፶፯ ዓ/ም የኬንያ የመጀመሪያው ጠቅላይ ሚኒስቴር ጆሞ ኬንያታ የአገሪቱ የመጀመሪያው ፕሬዚደንት ሆኑ።

፲፱፻፸፪ ዓ/ም የቀድሞዋ ሮዴዢያ ስሟን ቀይራ ዚምባብዌ ተባለች።

፲፰፻፲ ዓ/ም በኢትዮጵያ የዘመነ መሣፍንት ሲጀመር ከዙፋናቸው ወርደው አክሱም በስደት ላይ የነበሩት እና “ተፍጻሜተ ነገሥት” የሚባል ቅጽል ስም የተሰጣቸው ቀዳማዊ ዓፄ ተክለ ጊዮርጊስ አረፉ። 

፲፱፻፮ ዓ/ም መጀመሪያ የሸዋ ንጉሥ በኋላም የዘመናዪቱ ኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት፤ በአድዋ ጦርነት የኢጣሊያን ሠራዊቶች ድል የመቱት ታላቁ መሪ፤ “ዕምዬ ምኒልክ” ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ባደረባቸው ህመም በዛሬው ዕለት አረፉ።

፲፱፻፲፱ ዓ/ም በዳግማዊ ምኒልክ፣ በልጅ ኢያሱ እና በንግሥት ዘውዲቱ ዘመናት የጦር ምኒስትር የነበሩት ፊታውራሪ ሁብተ ጊዮርጊስ ዲናግዴ የሚወዷቸው ዕምዬ ምኒልክ ባረፉበት ዕለት ሞቱ።




#Article 348: ታኅሣሥ ፬ (136 words)


ታኅሣሥ ፬ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፺፬ኛው ቀን  ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ  ፪፻፸፬ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፸፩  ቀናት ይቀራሉ።

፲፮፻፴፭ ዓ/ም የሆላንድ ተወላጅ መርከበኛው አቤል ታስማን የዛሬይቱን ኒውዚላንድ አገኘ።

፲፱፻፶፫ ዓ/ም በወንድማማቾች መንግሥቱ ንዋይ እና ገርማሜ ንዋይ የተጠነሰሰው የታኅሣሥ ግርግር መፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ተጀመረ።

፲፱፻፹፫ ዓ/ም በሲሲሊ ደሴት ላይ የተከሰተው ትልቅ የመሬት እንቅጥቅጥ የአሥራ ስምንት ሰዎችን ሕይወት አጠፋ።

፲፱፻፹፫ ዓ/ም በደቡብ አፍሪቃ ፕሬዚደንት ደ ክለርክ በእሥራት ላይ ከነበሩት ከኔልሰን ማንዴላ ጋር እቢሯቸው ተገናኝተው የተጠላውን የጭቆና ሥርዐት (አፓርታይድ)ን የሚወድምበትን ሁኔታ ተመካከሩ።  

፲፱፻፹፱ ዓ/ም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታ ምክር ቤት አባላት የጋናውን ተወላጅ ኮፊ አናንድን ሰባተኛው የድርጅቱ ዋና ጸሐፊነት መረጧቸው።

፲፱፻፺፮ ዓ/ም የቀድሞው የኢራክ ፕሬዚደንት ሳዳም ሁሴን ከሥልጣናቸው ሸሽተው ከተደበቁ በኋላ በአሜሪካ ሠራዊቶች በተወለዱበት ቲክሪት ከተማ አካባቢ ጉድጓድ ውስጥ ተደብቀው ተገኙ።




#Article 349: ቱሉዝ (126 words)


ቱሉዝ (Toulouse) በደቡብ ምዕራብ የምትገኝ የፈረንሳይበስፋትዋ አራተኛ ከተማ ስትሆን አብዛኛዎቹ ህንፃዎችዋ የተሰሩት ከሸክላ በመሆኑ «ፅጌረዳማ ቀለሟ ከተማ» የሚለውን የቅፅል ስም እንድታገኝ አድርጓታል። ቱሉዝ በተማሪ ብዛትዋ በዩንቨርስቲዎችዋ በወይን–ጠጅ በሚመስለው አበባዋ፣የኤይር ባስ (Air bus) ዋና መቀመጫ በመሆንዋ ከምትታወቅባቸው ነገሮች ጥቂቶቹ ናቸው።
በ1998 የነዋርዎችዋ ብዛት 437 715 ሲደርስ በዙሪያዋ  ያሉት ነዋርዎችዋ  ሲጨመሩ 819 000 ይደርስ ነበር።

ቱሉዝ የሚለው ቃል ከየት እንደመጣ እርግጠኛበ ባይሆንም ቶሎዛ (Tolosa) ከሚለው የላቲን  ቃል የመጣ ነው በሚለው ሀሳብ ብዙዎች ይስማማሉ። ከቶሎዛ ወደ (Tholose) ከዛም፡ በኦክሲታንኛ፡ (Occitanie) የአነጋገር ዘይቤ ምክንያት ቱሉዝ እንደተባለች  ይገመታል።

ቱሉስ፡ በአመት፡ ውስጥ፡ አብዛናዎን፡ ገዛ፡ ፀሐያማ፡ ስትሆን፣ በየፈረንሳይ፡ ሞቃታማ፡ ከሚባሉት፡ ከተማዎች፡ ውስጥ፡ ትመደባለች፡፡ ከፍተኛ፡ ሙቀትዋ፡ ከ28°c እስከ 33°c ሲሆን፣ (እስከ 44°c የደረስበት፡ አመታት፡ ተመዝግበዋል) ዝቅተኛው፡ 0°c እስከ 3°c፡ ይደርሳል ። 
ጸደይ- ዝናባማና፡ መብረቅ፡ የበዛበት።
በጋ- ደረቅና፡ ሞቃታማ።
ክረምት- እርጦብና፡ ቀዝቃዛ፡ (በብዛት፡ ካለ፡ በረዶ)።




#Article 350: ኮረማሽ (362 words)


 

ኰረማሽ በአማራ ክልል ውስጥ፤ በሰሜን ሸዋ  በ   ላይ የምትገኝ  ወረዳ ናት።  

ከአዲስ አበባ በምሥራቅ በኩል ሰማንያ አምሥት ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ሥፍራ ስትሆን፣ በ ‘ስምጥ ሸለቆ’ (Rift Valley) ምሥራቃዊ ፍንጭ አናት ላይ ያላት ገዥ ይዞታ ከአፋር (የቀድሞው አዳል) እና ከሶማሌ በኩል በታሪክ ዘገባ ይመነጩ የነበረቱን እስላማዊ አጥቂዎች ለመከላከል የተመቸች ቦታ በመሆኗ የተመሠረተች ጥንታዊ ምሽግ ናት። ከፊት ለፊትዋ የመገዘዝ ተራራ፤ እንኮይ፤ ሰንበሌጥ፤ ቡልጋ እና ወደ ምሥራቅ የደረቂት እና አማሪት ወንዞች ከከሰም ወንዝ ጋር ሲቀላቀሉ እንዲሁም የመስኖ ዘንባባ ተራራ እና የመስኖ ማርያም ቤተ ክርስቲያን፤ ሜዳማው የሾላ ገበያ ወደደቡብ ምሥራቅ ደግሞ ከማዶ የክርስቶስ ሰምራ ትውልድ አገር  እና ምንጃር ቁልጭ ብለው ይታያሉ።

የአካባቢው ቃለ ታሪክ ሥፍራዋ በዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ አያት ንጉሥ ሣህለ ሥላሴ እንደተመሠረተች ሲያረጋግጥ፤ የልጅ ልጃቸው ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ  ደግሞ የሸዋ ንጉሥ በነበሩ ጊዜ እስካሁን ድረስ ያለውን ታላቅ የመሣሪያ ምሽግ እና በግቢው ውስጥ ያሉትን አሥራ አንድ ቤቶች እንዳሠሩ ብዙ የጽሑፍና የቃል ታሪኮች እንዲሁም ሕንጻዎቹ እራሳቸው ምስክር ናቸው።  ከነኚህ አሥራ አንድ ሕንጻዎች ሁለቱ በ ፲፱፻፸፯ ዓ/ም በሉተራን ኃይማኖታዊ ተልዕኮ ልገሣ ታድሰው የ ጥራ ጥሬ እና የ እህል ምርት ማከማቻ  ጎተራ ሆነዋል። ሌሎቹ ቤቶች የወረዳው ፍርድ ቤት፤ የቤተ ክህነት ጽ/ቤት ፤ የወረዳው የፖሊስ ጽ/ቤት እና የመሳሰሰሉ መንግሥታዊ ቢሮዎችን ይዘዋል።

በጥቅምት ወር ፲፱፻፱ ዓ/ም አዲስ በተመሠረተው የንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ እና የራስ ተፈሪ መኮንን መንግሥት ላይ ጦርነት አውጀው ከወሎ የዘመቱትን የልጅ እያሱ አባት ንጉሥ ሚካኤልን ሊከላከል የተሰለፈው የፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ሠራዊት ጥቃቱን ያደራጀው እዚሁ ኮረማሽ ላይ ሲሆን፡ ኋላም ዓርብ ጥቅምት ፲፯ ቀን ራስ ተፈሪና ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ሰገሌ ሜዳ ላይ ንጉሥ ሚካኤልን ድል ያደረጉት ከዚሁ ደጀን ቦታ ነው።

በዚች ወረዳ ውስጥ ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ያስገነቡት የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ይገኛል። 
በ፳፻፩ ዓ/ም ከ ዓለም ባንክ በተገኘ ብድር የኤሌክትሪክ መሥመር ተዘርግቶ ለዚች መንደርና ለአካባቢው የቡልጋ ሕዝብ የልማት መስፋፊያ ጮራ ተገልጾለታል።

በዘመናዊ መልክ የተገነባው የየለጥ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በተመረቀበት ዋዜማ፣ ጥቅምት ፳፩ ቀን ፳፻ ዓ.ም  ከሐሙስ ገበያ እስከ ኮረማሽ ድረስ ባለው የአሥራ ሦስት ኪሎ ሜትር የጥርጊያ መንገድ ላይ በሳምንት ሁለት ጊዜ፤ ማለትም ሐሙስ እና ቅዳሜ ለገበያ የሚያመች የሕዝብ መመላለሻ የአውቶቡስ መሥመር አገልግሎቱን ጀምሮ፣ በተለይም ቆለኞቹ ምርታቸውን ወደ ገበያ በማቅረብ ላይ የነበረባቸውን የእግር ጉዞ እንግልት ቀንሶላቸዋል። ወደፊትም ገብያቸውን ሐሙስ ገበያ ድረስ ከመሄድ እዚችው  ኰረማሽ ላይ ለመመሥረት ተስፋ ሰጥቷቸዋል። ለ የለጥ ቅዱስ ጊዮርጊስም ምረቃ ሥነ ስርዐት የተጓዙ እንግዶች በዚሁ የአውቶቡስ አገልግሎት ከሐሙስ ገበያ እስከ ኮረማሽ ድረስ ቢያንስ የሦስት ሰዐት የእግር ጉዞ ቀርቶላቸዋል።




#Article 351: ዎቮካ (369 words)


ዎቮካ (1848 ዓ.ም. አካባቢ እስከ 1925 ዓ.ም.) ወይም ጃክ ዊልሶን የስሜናዊ ፓዩት ጎሣ ሃይማኖታዊ መሪ ሲሆን «የመንፈስ ጭፈራ» የተባለውን እንቅስቃሴ መስራች ነበረ። የዎቮካ ትርጉም በስሜናዊ ፓዩትኛ 'እንጨት አጥራቢ' ነው። 

ዎቮካ በ1848 ዓ.ም. አካባቢ ከካርሶን ሲቲ፣ ኔቫዳ በስተደቡብ-ምሥራቅ በስሚስ ሸለቆ ዙሪያ ተወለደ። የቀደመው ፓዩት ሃይማኖታዊ መሪ ኑሙ-ታይቦ ትምህርት ለዎቮካ ትምህርት ተመሳሳይ ነበረና ይህ ኑሙ-ታይቦ ምናልባት የዎቮካ አባት ነበረ። ምንም ቢሆን፣ ዎቮካ እንደ ባለ መድኃኒት አንዳንድ መልመጃ እንደ ተቀበለ ግልጽ ነው።  የዎቮካ አባት በ1862 ዓ.ም. አካባቢ ካረፈ በኋላ፣ ልጁ በዬሪንግተን፣ ነቫዳ ገበሬ ዴቪድ ዊልሶንና በሚስቱ ሜሪ ቤተሠብ ውስጥ ታደገ። ዎቮካ በአቶ ዊልሶን እርሻ ላይ ይሠራና ከነጮች ጋር ስሙን 'ጃክ ዊልሶን' ተባለ። ዴቪድ ዊልሶን ጽኑዕ ክርስቲያን ስለሆነ፣ ዎቮካ በዚያ እየኖረ፣ የክርስትና ትምህርትና የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ከርሱ ተማረ። 

ዎቮካ ኃይለኛ ባለ መድኃኒት እንደ ሆነ ገናኝነት በወጣጥነቱ ቶሎ አገኘ፤ አሁንም ምታት እንዳወቀ ይታመናል። በአልፎ አልፎ ጊዜ አንድ ይሠራ የነበረው ድርጊት በረሽ መተኰሱ ሲሆን ይህ ምናልባት ጥይት ከአየር እንደመያዙ የመሰለ ትርዒት ሊሆን ይችላል። ስለዚሁ ትርዒት የተስፋፋው ወሬ የላኮታ ሕዝብ ጎበዞች 'የመንፈስ ሸሚዝ' ልብስ ቢለብሱ ጥይት ለማቆም እንደ ተቻላቸው ሊያሳምናቸው ችሎታው ነበረው። ዎቮካ ደግሞ ከመሬት የመስፈፍ ትርዒት እንዳሳየ ይባል ነበር። አየሩን ለማሠልጠን ችሎታ እንደያዘ የሚወራው አባባል በፓዩቶች ዘንድ ከሥልጣኑ ምንጮች ዋና ነበረ። ለምሳሌ በሙቀት ወራት የበረዶ ቊራጭ ከሰማይ እንዳወጣ ተባለ።   

በ1881 ዓ.ም. በፀሐይ ግርዶሽ መካከል ዎቮካ የትንቢት ራዕይ እንደነበረው አለ። የዎቮካ ራዕይ ስለ ሙታን ትንሣኤ ሲሆን 'ቀይ ሕንዶች' የተባሉ ባህሎች በሙታን ትንሣኤ (በዕለተ ፍትሕ) አገራቸውን (ስሜን አሜሪካ) በምላሽ ይቀብላሉ የሚል ራዕይ ነበረ።  የዚያን ጊዜ አገሩ ጎሽና አጋዘን የመላበት ደስተኛ እርሻ መሆኑ እንጂ ምንም እርጅና ወይም በሽታ አለመገኘቱ በዚያ ራዕይ ታየው። በዎቮካ ትምህርት ይህን ራዕይ ለማወቅ ለኗሪ ሕዝቦች የሚያስፈልገው ጽድቅ ተግባር እንዲኖሩ በየስድስቱም ሳምንት የ5 ቀን ጭፈራ እንዲጨፍሩ ነበር። ይህ ጭፈራ 'የመንፈስ ጭፈራ' (Ghost Dance) ይባላል። የዎቮካ ትምህርት በብዙ ኗሪ ጎሣዎች መካከል ተስፋፋ፤ በተለይም በላኮታ ሕዝብ ተስፋፋ።  
 
ዎቮካ የስለማዊነት መልእክት ብቻ አስተማረ፣ ግፍ ግን ጠቃሚ አለመሆኑን አስተማረ።  ሆኖም በላኮታዎች መንፈስ ጭፈራ እንቅስቃሴ ዘንድ፣ አንዳንድ ደቀ መዝሙር ነጮቹን ስለመቃወም ያስተምር ነበር። ስለዚህ እነዚህ ጭፈራዎች ብዙ ጭንቀትና ፍርሃት በመንግሥት ባለሥልጣናት ይፈጥሩ ጀመር። ይህ ሁኔታ በዉንደድ ኒ እልቂት (1883 ዓ.ም.) ከፍተኛ ሚና አጫወተ። 

በ1884 ዓ.ም. የአንትሮፖሎጂ መምህር ጄምስ ሙኒ ቃለ መጠይቅ ከዎቮካ ጋር አደረገ። በዚህ ቃለ መጠይቅ፣ ዎቮካ ወደ ሌሎቹ ጎሣዎች (ለምሳሌ ወደ ሻየን፣ አራፓሆ) የላከውን መልዕክት አሳየው። በዚህ መልእክት፣ እግዚአብሔር 'መሲሔ ኢየሱስ አሁን በምድር ላይ ነው' ብሎ እንዳሳወቀው ይላል። 

ዎቮካ በዬሪንግተን በ1925 ዓ.ም. አረፈና በሹርጽ፣ ኔቫዳ በፓዩት መቃበር ተቀብሯል።




#Article 352: የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ (318 words)


የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በሀገሪቱ ውስጥ ከፍተኛው የስፖርት ክንውን ነው። ይህ ሊግ በየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን 
ስር የሚተዳደር ሲሆን በየጊዜው የተለያዩ ስፖንሰሮች ደግፈውታል። ሊጉ በየ አመቱ የሚከናወን ሲሆን በ አመት ውስጥ በሁለት ክፍል (ሲዝን) ተከፍሎ ይካሄዳል። ሊጉን ለማሸነፍ 
አንድ ክለብ ከፍተኛ ነጥብ ይዞ አመቱን መጨረስ ይጠበቅበታል። ክለቦች እርስ በእርሳቸው በአመት ሁለት ጊዜ ይገናኛሉ። እያንዳንዱ ክለብ አንድ ጨዋታ በ ራሱ ሜዳ ሌላውን በባላጋራ ክለብ ሜዳ ያከናውናል።

የኢትዮጲያ ፕሪሚየር ሊግ የተመሰረተው በ 1994 ዓ.ም. ነው።  የሊጉ አርማ ከዚህ በላይ የሚገኘው ነው። ይህ ሊግ በ እ.አ.አ.2009/10 የውድድር ዘመን በ 18  
ክለቦች እየተከናወነ ነው። የሊጉ ችግሮች ተብለው ከጠቀሱት መካከል አብዘሃኛው ጨዋታዎች በአዲስ አበባ ስታዲየም መካሄዳቸው ነው። ይህን ችግር ለመቅረፍ ይመስላል የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ የራሱን ስታዲየም በ ዶ/ር ሼህ መሀመድ ሁሴን አሊ አላሙዲ እና በደጋፊው መዋጮ የራሱን ስታዲየም በማስገንባት ላይ ነው። ይህ ሊግ በ እ.አ.አ. 2007 ችግር አጋጥሞት ነበር። ለዚህም ቺግር 12 የ ሊጉ ክለቦች ( ሰባቱን የአዲስ አበባ ክለቦች ጨምሮ ማለት ነው። ) ራሳቸውን አግልለው ነበር። በዚህ ጊዜ ፌዴሬሽኑ ዋንጫውን ለ ሃዋሳ ከነማ ክለብ ሰጥቷል። ኢትዮጵያ በ አለም አቀፉ የ እግር ኳስ ማህበር ፊፋ እስከመታገድ የደረሰችበት ጊዜ ነበር። ይህ እገዳ ከብዙ አለም አቀፍ ውድድሮች እንድትታገድ ያደረጋት ሲሆን እገዳው በቅርቡ ተነስቶላታል። ሊጉ በአሁኑ ሰአት በቀድሞው አመራሮች መመራቱ ቀርቶ በ አዲስ አመራሮች መመራት ጀምሯል።

የቅዱስ ጊዮርጊስ የእግር ኳስ ክለብ ተጫዋች ነው።

ሊጉን በተደጋጋሚ በማሸነፍ ደረጃውን የያዙት ክለቦች የሚከተሉት ናቸው፡

አሸንፈዋል።

ጦር የእግር ኳስ ክለብ እ.አ.አ. ከ 1951 እስከ 1954 በተከታታይ 4 (አራት) ጊዜ በማሸነፍ ታሪክ ያለው ክለብ ነው። ይህ ክለብ በአሁኑ ጊዜ የለም። አሁን 
ካሉት ክለቦች ደግሞ ቅዱስ ጊዮርጊስ የእግር ኳስ ክለብ እ.አ.አ. ከ 1994 እስከ 1996 በተከታታይ ለ3 (ሶስት) ጊዜ ያህል 
በማሸነፍ ብቸኛው ክለብ ነው። በደጋፊ ብዛትም ቢሆን ብልጫውን እንደሚይዝ ብዙዎች ይናገራሉ።

በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ክለቦች የራሳቸው የድረ ገጽ አድራሻ ያላቸው ክለቦች 2 (ሁለት) ብቻ ናቸው። እነርሱም፡
ኢትዮጵያ ቡና የእግር ኳስ ክለብ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ የእግር ኳስ ክለብ ናቸው። እነሱም:- የቅዱስ ጊዮርጊስ
(
እንዲሁም የኢትዮጵያ ቡና የእግር ኳስ ክለብ ድረ ገጽ (ናቸው ።

በሊጉ ውስጥ በ፳፻፫ ዓ.ም. የሚሳተፉ ክለቦች 18 (አስራ ስምንት) ናቸው። እነዚህም፦ 




#Article 353: አዲስ መዝናኛ (125 words)


አዲስ መዝናኛ በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር መገናኛ ብዙሐን ኤጀንሲ ስር በኤፍ ኤም 96.3 ሬዲዮ ዘወትር ቅዳሜ ምሽት ከ3፡00 እስከ 6፡00 በተለይ በመረጃና ተግባቦት ቴክኖሎጂ ዙሪያ የተቀነባበሩ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ትንታኔዎችን ከሃገር ውስጥና ከውጭ ሙዚቃዎች ጋር አዋህዶ የሚያቀርብ በኢሉዥን የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሥራዎች እየተዘጋጀ የሚቀርብ የመረጃ ሰጭ መዝናኛ ፕሮግራም ነው።

አዲስ መዝናኛ ሰኔ 13፤2001 ዓ.ም. (June 20, 2009) ተመሠረተ። ፕሮግራሙ ለሕዝብ ጆሮ ከበቃበት ዕለት አንስቶ አዘጋጅና አቅራቢዎቹ አቶ አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ እና ወ/ሪት ኤዶም ካሣዬ ናቸው። የአዲስ መዝናኛ ፕሮዳክሽን ማኔጀር አቶ በፍቃዱ ኃይሉ ናቸው።

ኢሉዥን የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሥራዎች አዲስ መዝናኛን ከማስተዋወቁ በፊት በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የነበረ እና በመረጃና ተግባቦት ቴክኖሎጂ ዙሪያ የሚያጠነጥን አይሲቲ የተሰኘ የ30 ደቂቃ ሳምንታዊ የሬዲዮ ፕሮግራም በአዲስ አበባ በዛሚ ኤፍ ኤም 90.7 ላይ የሚያቀርብ የነበረ ሲሆን በሬዲዮ ጣቢያው የስርጭት ስፋት ማነስ ምክንያት ፕሮግራሙን ላልተወሰነ ጊዜ አቋርጦታል።




#Article 354: ፍርድ ቤት (111 words)


ፍርድ ቤት ፍርድ የመስጠት ስልጣን ያለው የ መንግስት አካል ነው። ከሶስቱ ከፍተኛ የመንግስት አካላት ማለትም ህግ አውጭ፣ ህግ ተርጓሚ እና ህግ አስፈጻሚ አንዱ ነው። ይህ አካል ህግ ተርጓሚ የሚባለው ነው። የወንጀለኛ መቅጫ ህግ፣ ሲቪል ህግ፣ አስተዳደራዊ ህግ እና ሌሎች ህጎችን በየህግ የበላይነት ላይ መሰረት በማድረግ ይተረጉማል።

ፍርድ በኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ ታሪክ ያለው ክንውን ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ በተለምዶ ወይም ባህል በበላ ልበልሃ እየታገዘ በመንደር ሽማግሌዎች ወይም በሀገረ ገዥዎች ፊት ይቀርብ ነበር። ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አገዛዝ ወዲህ በዘመናዊው የመንግስት መዋቅር የህግ ተርጓሚነትን የመንግስት ሰልጣን ተሰጥቶት መንግስት በሾማቸው ዳኞች ይመራል።

ይህ አካል በዘመናዊዉ የዴሞክራሲ መርህ ከየትኞቹም የመንግስት አካላት በገለልተኝነት ይንቀሳቀሳል። ሶስቱም የመንግስት አካላት ጣልቃ መግባት አይችሉም። በሃገሪቱ የሚገኝ ማንኛውም ዜጋ፣ አካል፣ ወይንም ተቋም ይዳኝበታል።




#Article 355: ህግ ተርጓሚ (112 words)


ህግ ተርጓሚ ወይም ፍርድ ቤት፡ ፍርድ የመስጠት ስልጣን ያለው የመንግስት አካል ነው። ከሶስቱ ከፍተኛ የመንግስት አካላት ማለትም ህግ አውጭ፣ ህግ ተርጓሚ እና ህግ አስፈጻሚ አንዱ። ይህ አካል ህግ ተርጓሚ የሚባለው ነው። የወንጀለኛ መቅጫ ህግ፣ ሲቪል ህግ፣ አስተዳደራዊ ህግ እና ሌሎች ህጎችን በየህግ የበላይነት ላይ መሰረት በማድረግ ይተረጉማል።

ፍርድ በኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ ታሪክ ያለው ክንውን ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ በተለምዶ ወይም ባህል በበላ ልበልሃ እየታገዘ በመንደር ሽማግሌዎች ወይም በሀገረ ገዥዎች ፊት ይቀርብ ነበር። ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አገዛዝ ወዲህ በዘመናዊው የመንግስት መዋቅር የህግ ተርጓሚነትን የመንግስት ሰልጣን ተሰጥቶት መንግስት በሾማቸው ዳኞች ይመራል።

ይህ አካል በዘመናዊዉ የዴሞክራሲ መርህ ከየትኞቹም የመንግስት አካላት በገለልተኝነት ይንቀሳቀሳል። ሶስቱም የመንግስት አካላት ጣልቃ መግባት አይችሉም። በሃገሪቱ የሚገን ማንኛውም ዜጋ፣ አካል፣ ወይንም ተቋም ይዳኝበታል።




#Article 356: ዴሞክራሲ (545 words)


ዴሞክራሲ  የፖለቲካ ሥርዓት ሲሆን ትርጓሜውም ሕዝባዊ መንግስት ማለት  ነው።  በሌላ አባባል ዲሞክራሲ ማለት ህዝብ የሚያስተዳድረውን አካል ያለምንም ተፅዕኖ ከመካከሉ መርጦ ሥልጣን የሚሰጥበት ሥርዓት ነው። 

ዴሞክራሲ  በተጠነሰሰበት ጥንታዊት ግሪክ ፣ ሰዎች ይኖሩ የነበረበት መሠረታዊ የፖለቲካ አሃድ (ዩኒት) ፣  ከተማዊ መንግስት ይባላል። ይህ በአሁን ዘመን ካለው አገር ወይንም ብሔራዊ መንግስት ይለያል።  ከተማዊ መንግስታት፣ ለምሳሌ አቴና  እንደ ከተማ አስተዳደርነቱ ፣ በቆዳ ስፋት አንስተኛ ስለነበር  የዘመኑ ዲሞክራሲ በቀጥተኛ ተሳትፎ  (በስብሰባ) ላይ የተመሰረተ ነበር።  ነገር ግን ይህ ዓይነት አሰራር  ከ፲፯ኛው ክፍለ ዘመን በኋላ ለተነሱት በንፅፅር ግዙፍ ለሆኑት ብሔረ መንግስታት  እማይቻል ስለነበር (ማለት ከአገሪቱ ግዙፍ የቆዳ ስፋት አንጻር ሁሉን ዜጋ በየሳምንቱ ለስብሰባ መጥራት ስለማይቻል)  በእንግሊዝ አገር ፓርላማ የተባለ አዲስ ሥርዓት ተፈጠረ። ይህም ማለት ሕዝቡ ተወካዮቹን (የፓርላማ ዓባላትን) ይመርጣል፤ ተመራጮችም መንግሥትን ይመሠርታሉ።  ይህ ዓይነት ሥርዓት (ቀጥተኛ ያልሆነ ዴሞክራሲ) በመባል ይታዎቃል። በአሁኑ ሰአት አብዛሃኛዎቹ የአለም ሃገራት የሚጠቀሙበት የመንግስት መዋቅር ነው።

አንድ ሥርዓት  ዲሞክራሲያዊ፣ በሌላ አነጋገግር   ከሕዝብ  ወይም  በሕዝብ የቆመ  ነው ከተባለ፣ ሕዝብ ማለት እዚህ ላይ ምንድን ነው?   አብዛኛውን ጊዜ ሕዝብ ማለት ዜጋ ማለትን ሲዎክል፣ እስከ ሃያኛው ክፍለ ዘመን ድረስ አብዛኞች ዲሞክራሲያዊ  ሃገሮች  ዜግነትን ትንሽ ለሆነ የህብረተሰብ ክፍል (ሴቶችን፣ ድሆችን፣ ዘሮችን ያገለሉ) ብቻ ያድሉ ነበር። እነዚህ ትንሽ ክፍሎች  ብቻ እሚሳተፉበት ዴሞክራሲ በአሁኑ ዘመን ተቀባይነትን ያጣ ነው። ባሁኑ ዘመን፣ ዲሞክራሲ ማለት ብዙኃኑ ኅብረተሰብ  መንግሥት የማዋቀር መብት አለው። የጥቂቶች መብት ደግሞ በህግ የተጠበቀ ነው።

ፖለቲካዊ ዜግነት ሕጻናትን  እንደማይጨምር አሁን ድረስ አብዛኞች ሃገራት  የሚሰሩበት ነው።  ይሁንና፣ በዚህ መንገድ  አላግባብ ሌሎችም የሕዝብ አካላት እየተገለሉ ሄደው፣ ዴሞክራሲው ወደ ሌላ ዓይነት ሥርዓት ሊቀየር ይችላል። ለምሳሌ በህብረተሰቡ ውስጥ ያሉ የተከበሩ ሰዎች ብቻ እሚሳተፉበት ሥርዓት ሲፈጠር  ሥርዓተ ልሂቅ ወይንም አሪስቶክራሲ ይባላል።  በሆነ አጋጣሚ ዕድል አግኝተው ጥቂት ቡድኖች ብቻ በማህበረሰቡ ላይ በሚተላለፉ ውሳኔዎች ሲሳተፉ  ሥርዓተ ጥቂት ወይንም ኦሊጋርኪ ይባላል።   ይህን ሁኔታ ለማዎቅ አንድ አንድ ጊዜ አስቸጋሪ ይሆናል ምክንያቱም ሙሉ በሙሉ ዴሞክራሲያዊ በሆነ ሥርዓት ሳይቀር፣ ጊዜ አግኝተው በፖለቲካው የሚሳተፉ  ግለሰቦች  ከአጠቃላይ ዜጋ ጥቂት ስለሆኑ። ይሁንና በዲሞክራሲ፣ የመሳተፍ መብቱ ለሁሉም ዜጋ ምንጊዜም ያለ ነው፣ ይጠቀሙበት አይጠቀሙበት።

እንደ ፈላስፋው ጆን ስቱዋርት ሚል  ሦስት ምክንያቶች ይጠቀሳሉChristiano, Tom, Democracy, The Stanford Encyclopedia of Philosophy (Fall 2018 Edition), Edward N. Zalta (ed.), forthcoming URL = 

ሕግ አርቃቂዎች የአንድን ሕብረተሰብ ጥቅም፣ መብት እና አስተሳሰብ በሚያረቁት ሕግ ውስጥ ግምት እንዲያስገቡ  ከሌሎች የፖለቲካ ሥር ዓቶች በላይ ዴሞክራሲ ያስገድዳቸዋል።   በዚህ ምክንያት ሰዎች በዚህ ሥርዓት ውስጥ የመጎዳታቸው ዕድል አንስተኛ ነው። ተመራማሪ ዓማርትያ ሴን ዋቢ ሲሰጥ «በማናቸው ዲሞክራሲያዊና  ሉዓላዊ መንግስታት ከፍተኛ ርሃብ  ተከስቶ አያቅም» ይላል።

ዴሞክራሲ አብዛኛውን ሕዝብ በውሳኔ አስጣጥ ላይ ስለሚያካፍል፣ ከሌሎች የፓለቲካ ሥርዓቶች በበለጠ ሥለ ሕዝቡ ጉዳይ  ያዎቀ  ሆኖ ይገኛል።  በውሳኔ አሰጣጥ የሚካፈለው ሕዝብ መብዛት በሌላ ጎን ትክክለኛ ውሳኔ ላይ ለመድረስ  እሚደረገውን ስራ ያግዛል፣ ተሳታፊዎችም ስለ ጉዳዮች የበለጠ የተተቸና የተብራራ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ይረዳል።

በዴሞክራሲ ሥርዓት ያሉ ሰዎች  በውሳኔዎች ላይ ስለሚሳተፉ፤ ከሌሎች ሥርዓት ሰዎች በተለየ እራሳቸውን ችለው እንዲያስቡ፣ በሃሳባቸው ምክንያታዊ እንዲሆኑ እና የሌሎችን መብቶች ግምት ውስጥ እንዲያስገቡ ስለሚገደዱ በሥነ ምግባር  እንዲሻሻሉ ይሆናሉ።

ከሚያስከትለው ጥቅም ውጭ ሌሎች ሥነ ምግባራዊ ጥቅሞች ይጠቀሳሉ። ለምሳሌ ሓርነት እና ዕኩልነት፣ እኩልነት፣ የሕግ የበላይነት፣ የመናገር መብት፣ ፍትህ ይጠቀሳሉ

ፕላቶ  የሥርዓተ ልሂቃን ዓይነት መንግስት ደጋፊ ስለነበር ዲሞክራሲን ከዚህ አቋሙ ተነስቶ ለመንቀፍ ሞክሯል። በእርሱ አስተሳሰብ  በዲሞክራሲ ሥር ዓት ወደ ሥልጣን ላይ መውጣት እሚችሉት የምርጫ ሥር ዓቱን  በማጭበርበር ወይንም በብልጥ ንግግር እና ስራ ሰውን በማታለል የተካኑ ሰዎች ይሆናሉ።  ምርጫን እሚያሸንፉ ሰዎች ደግሞ የግዴታ መንግስታዊ ኣስተዳደር ላይ ብቁ ሆነው ስለማይገኙ፣ ዴሞክራሲ መንግስትን ለንደዚህ ያለ ግሽበት ይዳርጋል ይላል።

የእንግሊዙ ቶማስ ሆብስ  በአንጻሩ የዘውድ ሥርዓትን በመደገፍ፤   የዴሞክራሲ ሥርዓት  መንግስት እንዳይረጋጋ እሚያረጉ ተቃውሞዎችን ያበረታታል በማለት ይነቅፋል።  

ዴሞክራሲ የመጣው የግሪክ ቃል ከሆኑት «ዴሞስ» ማለት «ህዝብ» እና «ክራቶስ» ማለት «ስልጣን» የመጣ ቃል ነው። በጥንታዊ የግሪክ ከተማ አቴንስ አገዛዝ ይተገበር ነበር።




#Article 357: ማርስ (104 words)


ማርስ ወይም ቀይዋ ፈለክ፡ መሬት በምትገኝበት ማለትም ሚልክ ዌይ ተብሎ በሚጠራው ረጨት ወይም የከዋክብት ስብስብ ውስጥ የሚገኝ ፈለክ ነው። ይህ ፈለክ ከፀሐይ ባለው ርቀት 4ኛ (አራተኛ) ነው። ከበፊቱ ሜርኩሪ፣ ቬነስ እና መሬት የተባሉ ፈለኮች ይገኛሉ። ኸበስተኋላው ደግሞ ጁፒተር፣ ሳተርን፣ ኡራኑስ፣ ነፕቲዩን እና ፕሉቶ የተባሉት ይገኛሉ።

ይህ ፈለክ በዚህ ረጨት ውስጥ ከሚገኙ ፕላኔቶች በግዝፈቱ የስድስተኛ ደረጃን ይይዛል። እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ህይወት ያለው ነገር ይኖርበታል ተብሎ ሲታመን ቆይቷል። ነገር ግን በቅርቡ የወጡ መረጃዎች ህይወት ያለው ነገር እንዳልተገኘ «ኢኮነም ድሉተ» መሆኑን ያመላክታሉ። በአብዛሃኛው በ ካርቦንዳይኦክሳይድ የተሞላ ቢሆንም በአንጻራዊ ሁኔታ ለ ህይወት ያላቸው ነገሮች ምቹ የሆነ ከባቢ አየር አለው። መጠኑ ከመሬት ያንሳል። በተለምዶ ቀይዋ ፈለክ እየተባለች ትጠራለች




#Article 358: ጁፒተር (132 words)


ጁፒተር፡ መሬት በምትገኝበት ማለትም ሚልክ ዌይ ተብሎ በሚጠራው ረጨት ወይም የከዋክብት ስብስብ ውስጥ የሚገኝ ፕላኔት ነው። ይህ ፈለክ ከፀሐይ ባለው ርቀት 5ኛ ( አምስተኛ ) ነው። ከበፊቱ ሜርኩሪ፣ ቬነስ፣ መሬት እና ማርስ የተባሉ ፈለኮች ይገኛሉ። ኸበስተኋላው ደግሞ ሳተርን፣ ኡራኑስ፣ ነፕቲዩን እና ፕሉቶ የተባሉት ይገኛሉ።

ይህ ፈለክ በዚህ ረጨት ውስጥ ከሚገኙ ፈለኮች በግዝፈቱ የመጀመሪያውን ደረጃ ይይዛል። ግዙፍ የጋዝ ክምችት እንደሆነ ይታመናል። ይህም የጸሃይን አንድ አንድ ሺኛ ( 1/1000ኛ ) ብቻ ክብደት እንዲኖረው ያደርገዋል። ነገር ግን የሌሎቹን ፈለኮች ድምር ክብደት በሁለት ከግማሽ እጥፍ ( 2.5x) ይሆናል። በረጨቱ ውስጥ የጋዝ ክምችት የሆኑት ፈለኮች ሳተርን፣ ኡራኑስ፣ ነፕቲዩን እና ራሱ ጁፒተር ናቸው። በአብዛሃኛው ሃይድሮጅን ከተባለ ጋዝ እና ሩቡን ( 1/4 ኛውን ) ክብደት ከሚይዘው ሂሊየም ከተባለ ንጥረነገር የተሰራ ነው።

ጁፒተር ስልሳ ሦስት ጨረቃዎች አሏት። ከእነዚህ ውስጥ አራቱ ማለትም አዮ ፣ዩሮፓ፣ ጋኒሜድ እና ካሊስቶ የጋሊሊዮ ጨረቃዎች በመባል ይታወቃሉ።




#Article 359: ማህፈድ (133 words)


ሳተርን፡ መሬት በምትገኝበት ማለትም ሚልክ ዌይ ተብሎ በሚጠራው ረጨት ወይም የከዋክብት ስብስብ ውስጥ የሚገኝ ፕላኔት ነው። ይህ ፕላኔት ከፀሐይ ባለው ርቀት 6ኛ ( ስድስተኛ ) ነው። ከበፊቱ ሜርኩሪ፣ ቬነስ፣ መሬት፣ ማርስ እና ጁፒተር የተባሉ ፕላኔቶች ይገኛሉ። ኸበስተኋላው ደግሞ ኡራኑስ፣ ነፕቲዩን እና ፕሉቶ የተባሉት ይገኛሉ።

ይህ ፕላኔት በዚህ ረጨት ውስጥ ከሚገኙ ፕላኔቶች በግዝፈቱ የሁለተኛነትን ደረጃ ይይዛል። ግዙፍ የ ጋዝ ክምችት እንደሆነ ይታመናል። በ ረጨቱ ውስጥ የጋዝ ክምችት የሆኑት ፕላኔቶች ጁፒተር፣ ኡራኑስ፣ ነፕቲዩን እና ራሱ ሳተርን ናቸው። በዚህም የተነሳ ጆቪያን ወይም ጁፒተርን መሳይ እየተባለ ይጠራል። በአብዛሃኛው ሃይድሮጅን ከተባለ ጋዝ እና በ ጥቂት መጠን ሂሊየም ከተባለ ንጥረነገር የተሰራ ነው።

ፕላኔቱ በተለይም ዙሪያውን በሚገኙ በቀለበቶቹ ይታወቃል። እነዚህ ቀለበቶች ከሳተርን ወገብ ከ6630 ኪ.ሜ. እስከ 120700 ኪ.ሜ. ርቀት ድረስ ይገኛሉ። በአማካይ እያንዳንዳቸው እስከ 20 ሜ. ድረስ ወፍረት ያላቸው ቀለበቶች ናቸው። የተሰሩት በአብዛሃኛው ከውሃ፣ ከበረዶ እና ከሌሎች ንጥረ ነገሮች ነው።




#Article 360: ኣጣርድ (149 words)


ኣጣርድ ወይም ሜርኩሪ፡ መሬት በምትገኝበት ማለትም ሚልክ ዌይ ተብሎ በሚጠራው ረጨት ወይም የከዋክብት ስብስብ ውስጥ የሚገኝ ፈለክ ነው። ይህ ፈለክ ከፀሐይ ባለው ርቀት ቅርቡ (1ኛው) ነው። ከበስተኋላው ዘጠኙም ፈለኮች ማለትም ቬነስ፣ መሬት፣ ማርስ፣ ጁፒተር፣ ሳተርን ኡራኑስ፣ ነፕቲዩን እና ፕሉቶ ይገኛሉ።ሜርኩሪ ጠንካራ ፣ የብረት ሰልፋይድ የውጪውን ንጣፍ ፣ ጥልቀት ያለው ፈሳሽ ንጣፍ እና ጠንካራ የውስጥ ኮርትን የሚሸፍን ጠንካራ የሰልፈር ክሬን እና ምንጣፍ ያለው ይመስላል።

ስሙ «ኣጣርድ» የተወረደ ከአረብኛው «ኡጣሪድ» ነበር። በድሮ ጊዜ ይህ የአረመኔ ጣዖት ስም ነበር። አሕዛብ ይህ የጥበብ ጣኦት እንደ ነበር ስላመኑ፣ የፈለኩ ስም ከዚህ ጣኦት ስም መጥቶ በየቋንቋው ይለያይ ነበር። ስለዚህ የፈለክም ሆነ የጣኦት ስም በፋርስኛ «ቲር»፣ በባቢሎንኛ «ናቡ»፣ በጥንታዊ እንግሊዝኛ «ዎደን»፣ በግሪክ «ሄርሜስ»፣ በሮማይስጥም «ሜርኩሪዩስ» ሆነ። «ሜርኩሪ» የሚለው እንግሊዝኛ ሲሆን ከዚሁ ሮማይስጥ ስም መጣ። በዕብራይስጥ ግን ስሙ «ኮካብ ሐማህ» ወይም «የፀሐይ ኮከብ» ይባላል። 

ይህ ፈለክ በዚህ ረጨት ውስጥ ከሚገኙ ፈለኮች በመጠኑ ትንሹ ነው። ዲያሜትሩ 2439.7 ኪ.ሜ ብቻ ነው። መዋቅሩ ከመሬት ጋር በተመሳሳይ ሁኔታ ቋጥኞች የበዙበት ነው።




#Article 361: ዘሃራ (181 words)


ዘሃራ ወይም ቬነስ፡ መሬት በምትገኝበት ማለትም ሚልክ ዌይ ተብሎ በሚጠራው ረጨት ወይም የከዋክብት ስብስብ ውስጥ የሚገኝ ፈለክ ነው። ይህ ፕላኔት ከፀሐይ ባለው ርቀት ሁለተኛ ቅርቡ (2ኛው) ነው። ከበስተኋላው ሰባቱ ፈለኮች ማለትም መሬት፣ ማርስ፣ ጁፒተር፣ ሳተርን ኡራኑስ፣ ነፕቲዩን እና ፕሉቶ ይገኛሉ። ከፊቱ የምትገኘው ብቸኛዋ ፈለክ ኣጣርድ ናት።

ዘሃራ የሚለው ስም ከአረብኛ «ዙህራ» ሲሆን ይህ ማለት ቁንጅና ወይም አበባ ነው። በአንድ ጥንታዊ የአረብ ትውፊት ዘንድ ዙህራ የተባለች ሴት በተዓምር ፈለክ ሆነች። አረቦች ይህን ትውፊት ከአይሁዶች፣ አይሁዶችም ከባቢሎን ሰዎች እንደ በደሩት ይታመናል። በአረመኔ እምነቶች ፈለኩ በፍቅር ጣዖት ስም ይባል ነበር፤ በእንግሊዝኛ ቬነስ የሚለው ስም ከሮማይስጥ የጣዖት ስም ነው። 

በእብራይስጥ ደግሞ ለዚሁ ፈለክ ያለው ስም «ኖጋህ» ሲሆን ይህ በአማርኛ ማለት «ንጋት» ነው (የንጋት ኮከብ)።

ይህ ፈለክ በመሬት ሰማይ ላይ ከሚታዩ አካላት እንደ ጨረቃ ሁሉ ግዙፉ አካል ነው። ይህን ፈለክ ለማየት ጥሩ ጊዜ የሚሆነው ጠዋት ፀሐይ ከመውጣቷ በፊት እንዲሁም ማታ ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ነው። ፈለኩ በነዚህ ሁለት ጊዜያት በደማቅ ቀይ ብርሃኑ ተለይቶ ይታወቃል። የተሰራው ከ መሬት ጋር በተመሳሳይ ሁኔታ ቋጥኝ ከበዛበት አካል ነው። ይህም ባህሪው ከ ሶስቱ ፈለኮች ማለትም ከ ሜርኩሪ፣ መሬት እና ማርስ ጋር ተመሳሳይ ባህሪ እንዲኖረው ያደርገዋል። እነዚህ በአንድነት በ ኢንግሊዝኛው ተሬስትሪያል ፈለኮች.በመባል ይታወቃሉ።




#Article 362: መሬት (708 words)


መሬት በሥርዓተ ፀሐይ ውስጥ ከፀሐይ ባላት ርቀት ሶስተኛ (3ኛ) በግዝፈት ደግሞ ከፕላኔቶች ሁሉ አምስተኛ ግዙፍ የሆነች ፈለክ ናት። በግዝፈት እና በይዘት ቋጥኛዊ ይዘት ካላቸው ወይንም በእንግሊዝኛው ተሬስትሪያል ፈለኮች ከሚባሉት የመጀመሪያውን ደረጃ ትይዛለች። በተለምዶ ዓለም ወይም ምድር እየተባለች ትጠራለች። በሳይንሳዊ የተለምዶ ስም ደግሞ «ሰማያዊዋ ፕላኔት» እየተባለች ትጠራለች። ይህች ፕላኔት የሰው ልጅን ጨምሮ ለብዙ ሚሊዮን ዝርያዎች መኖሪያ ናት። ከምድር ብዛት (ከላይ አፈር) አትክልት ሁሉ እየበቀሉ ሲሆን ለሰው ልጅና ለእንስሳ ያስፈለጉት እህል፣ ፍራፍሬ፣ መድኃኒቶችና ሌሎችም ሁሉ ታስገኛለች። ይህም የታወቀች ብቸኛዋ ህይወት ያለው ነገር መኖሪያ ያደርጋታል። ስለዚህ ነው በተለያዩ እምነቶች ዘንድ ምድራዊት እማማችን የተባለች። 

መሬት በመዋቅሯ ከእንቁላል ጋር ተመሳሳይ መዋቅር አላት። ውስጣዊ እና ውጫዊ ይዘቷ ባጠቃላይ በሶስት ይከፈላል። ይህም በእንቁላል አካል የውጨኛው ቅርፊት፣ የመካከለኛው ፈሳሽ እና የውስጠኛው አስኳል ብለን እንደምንከፍለው በመሬትም ተመሳሳይ አቀማመጥ ያላቸው ክፍሎች አሉ።

የመጀመሪያው ውጫዊው የመሬት ክፍል ወይም በእንግሊዝኛው ክረስት የሚባለው ሲሆን የመሬት ቅርፊት ልንለው እንችላለን። በአብዛኛው ከተለያዩ የቋጥኝ አይነቶች የተገነባ ሲሆን ህይወት ያላቸው ነገሮች በሙሉ የሚኖሩት በዚህኛው የመሬት ክፍል ላይ ነው። ይህ ክፍል ውፍረቱን በሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል። ምክንያቱ ደግሞ በውቅያኖሶች ስር ያለው የውፍረቱ መጠን እና በአህጉራት ላይ ያለው መጠን ስለሚለያይ ነው። የመሬት ቅርፊት በውቅያኖሶች ስር ያለው ውፍረት ከአምስት ሺህ ሜትር ( 3 ማይል) እስከ አስር ሽህ ሜትር ( 6 ማይል) ነው። ይህ ውፍረት በአህጉሮች ላይ ከሰላሳ ኪ.ሜ. (20 ማይል) እስከ ሃምሳ ኪ.ሜ. (30 ማይል) ነው።

ሁለተኛው የመሬት ክፍል መካከለኛው የመሬት ክፍል ወይም በእንግሊዝኛው ማንትል በመባል ይጠራል። ይህ የመሬት ክፍል ፈሳሻማ ይዘት አለው። ውፍረቱ እስከ 2890 ኪ.ሜ. (1800 ማይል) ይደርሳል። የመሬትን 84 በመቶ (84%) መጠን ይሆናል። በአብዛኛው በቅልጥ አለት ወይም ማግማ የተሞላ ነው። ይህም በእንቁላል የመካከለኛው ነጭ ፈሳሽ ይወከላል።

የመጨረሻው እና ሶስተኛው ደግሞ ውስጠኛው የመሬት ክፍል ወይም በእንግሊዝኛው ኮር የሚባለው ነው። በእንቁላል የውስጠኛው አስኳል መወከል ይቻላል። እጅግ በጣም ሞቃት ሲሆን የፀሐይን የውጨኛ ክፍል መጠነ ሙቀት ይኖርዋል። ይህ ክፍል መጠኑ አነስተኛ ሲሆን በራዲየስ እስከ 1220 ኪ. ሜ. ብቻ ነው። በዚህም የጨረቃን መጠን 70 በመቶ (70%) ጋር ይነጻጸራል።

የመሬትን ታሪክ ለማወቅ የተፈጥሮ ሳይንስ የበኩሉን ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። በዚህም የመሬት እድሜ ከ4.6 ቢሊዮን አመት ወዲህ ያሉትን አመታት በሙሉ የሚያጠቃልል ይሆናል። ይህም የጠቅላላ ሰማያዊ አካላት ወይም ዩኒቨርስን ሲሶ (አንድ ሶስተኛ) እድሜ ይሸፍናል። በዚህ ዘመን ነው እንግዲህ መልከዓ-ምድራዊም ሆነ ፍጥረታዊ ለውጦች የተከናወኑት። በአጠቃላይ የመሬትን ታሪክ ሳይንሳዊ በሆነ ወይም ሃይማኖታዊ በሆነ መልኩ ማየት ይቻላል። ሁለቱም በአሁኑ ጊዜ ተቀባይነት ያላቸው መላምቶች ናቸው። (ደግሞ «ባለሙያ ንድፍ»ን ይዩ።)

የመጀመሪያው እና ከተመሰረተ ከሁለት ሺህ አመታት በላይ ያስቆጠሩት ሃይማኖታዊ እምነቶች አሉ። በነዚህ መሰረት መሬት የተፈጠረችው የአለም ፈጣሪና ጌታ በሆነው በእግዚአብሔር ወይም በአላህ ለሰው ልጆች መኖሪያ ተብሎ ነው የሚል እምነት አለው። ይህ እምነት በአብዛሃኛው የአለም ሃይማኖታዊ ህዝቦች ተቀባይነት ያለው ነው። ይዘቱም በተለያዩ የእምነት አይነቶች የተለያየ ፈጣሪ እንደመኖሩ የሚለያይ ነው። ለዚህ አስተሳሰብ ከሚወክሉት መሃል አንዱ የቅብጥ ተዋሕዶ ቄስ አባ ታድሮስ ማላቲ እንደሚሉት፣ በትምህርተ ሂሳብ ረገድ የመሬቲቱ ስፋት ለአንድ ሚልዮን አመታት የሰው ልጅ ትውልድ መበዛት በቂ ሊሆን ከቶ አይችልም። እያንዳንዱ ቤተሠብ በአማካኝ 3 ልጆች ብቻ ቢወልዱ በሚልዮን አመታት የመሬት ስፋት አንድ ሺህ እጥፍ ቢሆንም እንኳ አይበቃም ይላሉ። ስለዚህ የምድር እድሜ ስፍር ቁጥር የሌለው ረጅም ጊዜ ቢሆንም፣ የስው ልጅ ትውልድ ግን ከ6000 ሺህ አመታት በላይ ብዙ ሊሆን አይችልም ይላሉ።

ይህ ቲዎሪ የተመሰረተው ሳይንስ ካገኛቸው የመሬት ላይ መረጃዎች ጥናት ላይ ነው። በአለማችን ረጅም እድሜ ያስቆጠረው አለት 4.0 ቢሊዮን አመት ነው።

የመሬትን ታሪክ በመሬት ጥናት ወይም ጂኦሎጂ በተለያዩ ዘመናት ወይም በእንግሊዝኛው ኢራ ከፋፍሎ ማየት ይቻላል። ይህም ሁሉ የሚታሰበው ከሳይንሳዊ ሊቃውንት ሃልዮ ምርመራ ዘንድ ነው። እነዚህ ዘመናት በቢሊዮን እና ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አመታት እድሜ ያላቸው ሲሆኑ በተለያዩ አነስተኛ ዘመናት ወይም ፔሬድስ ይከፋፈላሉ። ጂኦሎጂ የመሬትን ታሪክ በአራት ዋና ዘመናት ወይም ኢራስ ከፍሎ ያያል። እነዚህም፦

ይህ ዘመን ከ4500 ሚሊዮን አመታት በፊት ያለው የመሬት እድሜ ነው። የመሬትን ሰባት ስምንተኛ እድሜ የሚያጠቃልል ነው። ነገር ግን ስለዚህ ዘመን ዘመናዊው ሳይንስ ማወቅ የቻለው ጥቂት ነገር ብቻ ነው። በዚህ ዘመን ህይወት ያለው ነገር ለመፈጠሩ የተገኙ መረጃዎች አነስተኛ ቢሆኑም በምዕራብ አውስትራሊያ 3.46 ቢሊዮን አመታት ያስቆጠረ ህዋስ ወይም ባክቴሪያ ተገኝቷል።

ይህ ዘመን የሚሸፍነው ከ 542 ሚሊዮን እስከ 251 ሚሊዮን አመታት በፊት ያለውን የመሬት እድሜ ነው። የተለያዩ የዓሳ ዝርያዎችን ጨምሮ ትላልቅ የእንሽላሊት ዘሮች ወይም ዳይኖሰሮች በዘመኑ መገባደጃ አካባቢ ተከስተዋል።

ከ251 ሚሊዮን አመት እስከ 65.5 ሚሊዮን አመት በፊት ያለው ጊዜ በዚህ ዘመን የሚጠቃለል ነው።

ከ65.5 ሚሊዮን አመታት በፊት ጀምሮ አሁን እስካለንበት ያለውን ጊዜ የሚሸፍነው ይህ ዘመን አብዛሃኛው የመሬት ለውጦች ተከናውነውበታል።

የመሬት የከባቢ አየር በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ ይዘቶች ነበሩት። በውስጡ የሚገኙት ህይወት ላላችው ነገሮች አስፈላጊ የሆኑ ነገርችም ( የኦዞን ንጣፍን ጨምሮ) በየጊዜው ተለዋውዋል።ከባቢ አየራችን በውስጡ 78 በመቶ ናይትሮጅን፣ 21 በመቶ ኦክስጅን፣ 0.93 በመቶ አርገን፣ 0.038 በመቶ ካርቦን ክልቶኦክሳይድ የተባሉ ንጥረ ነገሮችን (ጋዞችን) በውስጡ ይዟል። አሁን ያለው ሁኔታ መሬት ለተጨማሪ 1.5 ቢሊዮን አመታት ህይወት ያላቸው ነገሮች እንዲኖሩባት ያስችላል ተብሎ ይታመናል።




#Article 363: ፍኖተ ሰላም (225 words)


የፍኖተሰላም ከተማ የምትገኘው በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምዕራብ ጎጃም ዞን ጃቢጠህናን ወረዳ ከአዲስ አበባ በ 387 ኪ.ሜ ከክልሉ ዋና ከተማ ባህርዳር ደግሞ 176 ኪ.ሜ ላይ ነው፡፡ አስትሮኖሚያዊ መገኛ ቦታዋም በ10º 41’ ሰሜን ላቲቲውድ እና 37º 16’ ምስራቅ ሎንግቲውድ ነው፡:1
ፍኖተ ሰላም (ፍ/ሰላም) በኢትዮጵያ ውስጥ በጎጃም እምብርት ላይ የምትገኝ ከተማ ናት። 

አመሰራረት

ፍኖተሰላም ከተማ የተቆረቆረችው በ 1933 ዓም ነው፡፡ፍኖተሰላም በክልሉ  ከሚገኙ የሪፎርም  ከተሞች ስትሆን፣ የከተማ አስተዳደር፣ ማዘጋጃ ቤት፣ 3 የከተማና 2 የገጠር ቀበሌዎች አላት፡፡ በ2003 ዓ.ም የተዘጋጀ መዋቅራዊ ፕላንም አላት፡፡
ፍኖተ ሰላም ማለት መልካም መንገድ ወይም ጉዞ እንደማለት ሲሆን ይህንንም ስም ያወጡላት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ እንደሆኑ ይነገራል።  ጃንሆይ ከጣሊያን ጦርነት በኋዋላ ከስደት ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ አሁን ፍኖተ ሰላም ያለችበት ቦታ ላይ ከአጃቢዎቻቸው ጋር እረፍት ያደርጋሉ።  እስከዚያን ጊዜ ድረስ ያደረጉት ጉዞም በሰላም የተሞላ ስለነበር ያንን ቦታ ፍኖተ ሰላም ብለው ሰየሙት። ከከተማዋ ወጣ ብሎ የሚገኝ አንድ የዋርካ ዛፍ ይገኛል። ይህንንም የዋንዛ ዛፍ የተከሉት ንጉሱ ስለነበሩ እስካሁን ድረስ የአባ ንጉስ ዋንዛ እየተባለ ይጠራል።

ፍኖተ ሰላም በብዙ ነገር ትታወቃለች። በአካባቢው ያሉ ገበሬዎች ጤፍ፣ በቆሎ፣ ዳጉሳ፣ ኑግ፣ በርበሬ እና ሌሎችንም የእህል አይነቶች ያበቅላሉ። በፍራፍሬ ሎሚ፣ ብርቱካን፣ ፓፓዬ እንደልብ ይገኛል። በጣም ጥራት ያለው ቡና የሚገኝባት አገር ናት - ፍ/ሰላም። የባከል ቡና በጣዕሙ ይታወቃል። ከከተማው ወጣ ብሎ የገራይ የውሃ ግድብ ስለሚገኝ በተለይ በፆም ጊዜ እጅ የሚያስቆረጥም አሳ ይገኛል። ፍ/ሰላም በወተትና በማር ሀብትም በጣም የታውቀች ከተማ ናት። በከተማዋ አንድ ሁለተኛ ደረጃና አንድ መሰናዶ ትመሀርት በቶች አንዲሁም አንድ መምህራን ማሰልጠኛ ኮለጅ ይግኛሉ።




#Article 364: የመንደሮቹ መኳያ ሰሌዳ (138 words)


የመንደሮቹ መኳያ ሰሌዳ ከጥንታዊ ግብጽ የተገኘ ቅርስ ሲሆን፣ ኩልን ወዘተ. ለማደባለቅ ከተጠቀሙት ሠሌዳዎች አንድ ነው። የተሠራበት ዘመን 3100 ዓክልበ. አካባቢ መሆኑ ይታመናል።   ይህም በፈርዖኖች ቅድመ-ዘመን ነበረ፤ በአባይ ወንዝ ሸለቆ የነበሩት ሀገራት በአንድ የግብጽ መንግሥት ገና ሳይዋሀዱ ማለት ነው። 

በሠሌዳው ፊት ላይ፣ በሦስት መስመሮች የሚራመዱ እንስሶች (ከብት፣ አህያና ፍየል) ይታያሉ። አራተኛውም መስመር አትክልትን ያሳያል። በአንዳንድ ሊቃውንት አስተሳሰብ ዘንድ፣ በአትክልቱ አጠገብ አንዱ ምልክት «ቴሄኑ» (ልብያ) የሚባል ሃይሮግሊፍ ነው፤ ስለዚህ ሠሌዳው ደግሞ የቴሄኑ ሠሌዳ ወይም የሊብያ ሠሌዳ ተብሏል።  ሌሎች ሊቃውንት ግን ምልክቱ «ቴሄኑ» አይደለምና የግዮን ሸለቆ ከቶሞች ይሆናሉ ብለዋል። 

በሠሌዳው ጀርባ ሰባት መንደሮች ወይም ከተሞች አሉ።  እነዚህ 7 ከተሞች በግድግዳዎች ውስጥ ሲሆኑ እያንዳንዱ ከተማ በውስጡና በላዩ ልዩ ልዩ ምልክት አለበት። በላዩ ያለው ምልክት መኰትኰቻ የያዘ አውሬ፣ ተኋን ወይም ወፍ አይነት ነው። ከዚህ ጭምር በየከተማው የቅያስ ምልክቶች በልዩ ልዩ መጠኖች አሉ። በድምሩ 28 ቅያሶች አሉ፤ ይህ ምናልባት የሕዝብ ወይም የሕንፃ ብዛት ያመልክታል። 




#Article 365: ቢላል (670 words)


በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ያ አላህ አንተ ካሳወቅከን በስተቀር እውቀት የለንምና ጠቃሚ እውቀትን ትሰጠን ዘንድ እንማጸንሀለን ::አሜን 

ቢላል ኢብን ረባህ በአረብኛ بلال بن رباح‎. የሚታወቅበት ስሞቹም ቢላል አል ሃበሽይ፣ ቢላል ኢብን ሪያህ፣እና ቢላል ኢብን ረባህ. ቢላል ታማኝ እና ኢማንነኛ ነበር በነብዩ ሙሀመድ ልብ ዉስጥ ልዩ ቦታ ነበረዉ. ቢላል የተወለደዉ ነብዩ ሙሀመድ ከተወለዱበት ቅዱስ ከተማ መካ ዉስጥ ነዉ የተወለደዉ ቤተሰቦቹ ገን በኢትዮጵያ ደማስቆ በምትባል ከተማ ዉስጥ ነዉ ተነስተዉ ወደ መካ ከአቢሲኒያ ኢትዮፕያ ዉስጥ በባርነት ተሽጠዉ ነበር የሀዱት የሚባለዉ. ቢላል ከባርነት ላወጣዉ እስልምና በሙአዚንነት ስያገለግል ነዉ የሞተዉ. በሙአዚንነቱ በእስልምና ታሪክ የመጀመርያዉ ሙአዚን ነዉ. ለመጀመርያ ሙአዚንነቱ የተመረጠዉ በነብዩ ሙሀመድ ነበር. ቢላል ከባርነት የወጣዉ በአቡበክር ነበር. ምክንያቱም ቢላል ባርያ ስለነበር አሳዳሪዉ ኡመያህ ከእስልምና ዉጣ  በነላት እና ኡዛ እመን ሲል በመካ በርሃ በጸሀይ በተቃጠለ አሽዋማ መሬት ላይ አስሮ ሆዱ ላይ ትልቅ ደንጋይ እየጣለ ሲቀጣዉ አሀዱን አሀድ እያለ ስቃዩን ለአላህ ስያደርግ ስቃዩን ለማስቆም አቡበክር ሰዉ ልኮ በፈለገዉ ያህል ገንዘብ እንዲገዛዉ ጠየቀዉ ኡመያህም እሽ ሲል ሸጠለት. ከዛም አቡበከር ለራሱ ባርያ ሊአደርገዉ አልፈለገም ነጻነትን ሰጠዉ. ከዛን ቀን ቡሃላ ባርነቱ አብቅትዋል. ቢላል ድምጸ መርዋው ህዝቦቹን በሚያምር ድምጹ የሚጣራ ይሉታል. ቢላል የሞተዉ በ638 እስከ 642 ባለዉ ነው. እስልምናን የተቀበለዉ የአስራ ስድስት አመት ወጠጤ እያለ ነበር. በስልምና የቢላል ታሪክ እስልምና ከመጣ ቡሃላ እንዴት ባርነት እንደቀነሰ ነዉ. 

ቢላል ኢብኑ ረባህ የምስጋና እና የሙገሳ ቃላትን ሲሰማ አንገቱን ይደፋ ነበር እናም አይኖቹን በትዝታ ገርበብ አድርጎ ትናንት ባሪያ የነበርኩ ሀበሻ ነኝ ይላል። እነሱ ግን የእኛ ልዑል ብለው ነበር የሚጠሩት። 
ኡመያ ኢብን ኸለፍ በመባል የሚታወቅ ቁረይሽ ባሪያ የነበረው ቢላል ነብዩ ሙሀመድ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም በነብይነት የመላካቸው ወሬ የመካን ህዝብ ሲያተራምስ ከቢላል ጆሮ ደረሰ። 
የቢላል አሳዳሪ ከእንግዶቹ ጋር ስለ ነብዩ መላክ እና ጣኦታቸውን እንደሚቃወም በንዴት እየተብሰለሰለ እና ሴራ እያውጠነጠነ ሲናገር ሙሐመድ ስለተንሱበት አላማ እና ምን እያሉም እንደሚያስተምሩ ሊቀነጭብ ቻለ።
አዲስ የመጣው ዲን ለአካባቢው እንግዳ እና ስር ነቀል ለማምጣት ያለመ ሙሀመድም ምንም እንኳን ነብይ ነኝ ብለው በመናገራቸው ተቃውሞ የገጠማቸው ቢሆንም ታማኝ :እውነተኛ እና በስነ ምግባር የታነጹ መሆናቸውን ከጠላቶቻቸው ቁንጮዎች አንደበት አድምጧል። «ሙሀመድ አንድም ቀን ዋሽቶ አያውቅም: ጠንቋይም ሆነ እብድ አልነበረም:... ዛሬ ግን እኛ እርሱን በነዙህ ነገሮች መጥራት ይኖርብናል። ወደ እርሱ የሚጎርፉትን ሰዎች መግታት የምንችለው በዚህ መንገድ ነው።»  በማለት ዚዶልቱ ቢላል ታዝቧል። 

ሙሐመድን የሚቃወሙት በቅድሚያ የአባቶቻቸውን እምነት ቀጣይነት ለማረጋገጥ ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ የቁረይሽን የበላይነት የሚያከስም መስሎ ስለተሰማቸው ነው። ቁረይሽ በመላው አረብ ለጣኦታዊ እምነት ማዕከል በሆነችው በመካ የሚገኝ ነገድ በመሆኑ ተፈሪነቱ እና ከበሬታው የላቀ ነበር። በ 3ኛ ደረጃ በኒ ሀሽም ተብሎ በሚታወቀው የነብዩ ሙሐመድ የዘር ሀረግ ቤተሰብ ላይ ያሳደሩት ቅናት እና ምቀኝነት ነበር። ከበኒ ሀሽም ቤተሰብ ነብይ እና መልእክተና መምጣቱን እንደ ሽንፈት ቆጥረውታል ? ሁሉም ጎሳ እና ቤተሰብ ከራሱ ወገን ነብይ እንዲወጣ ይመኝ ነበር። 
ከ እለታት አንድ ቀን ቢላል ኢብኑ ረባህ የኢማን ብርሀን ፈነጠቀበት : ምርጫውን ይፋ ማድረግ እንዳለበት ወሰነ። ወደነብዩ ሙሀመድ በመሄድም ለኢስላም እጁን መስጠቱን ይፋ አደረገ። የቢላል መስለም በመካ ምድር ተሰማ። የበኒ ጁመህ መሪዎች በቁጣ ተወጠሩ : በተለይ አሳዳሪው የኢስላም ጠላት ኡመያ ኢብን ኸለፍ ሀበሻዊ ባሪያው መስለሙ እንደ ታላቅ ነውር እና ንቀት ቆጥሮታል። ለዚህም እንዲህ አለ «-ይህ ኮብላይ ባሪያ በመስለሙ ጸሀይ ተመልሳ የምትጠልቅ አይመስለኝም...»  ሲል ቁጭቱን ገለጸ።

ቢላል ግን ለኢስላም ብቻ ሳይሆን ለመላው የሰው ዘር የሚያኮራ አቋም ከመውሰድ ወደ ሁዋላ አላለም። አላህ የአንድ ሰው የቆዳ ቀለሙ መጥቆር ከፍተኛውን የኢማን ደረጃ ለማግኘት የሚያግደው እንደማይሆን በቢላል ተምሳሌነት አስተምሯል። ቢላል ለዘመኑ ሰዎች እና ከ እሱ በሁዋላ ለመጣው ትውልድ እንዲሁም እምነቱን ለሚጋሩት እና ለማይጋሩትም ወገኖች ያስተማረው ትምህርት ቢኖር የህሊና ነጻነት እና ሉአላዊነት ምድርን የሞላ ንዋይም ሆእን አሰቃቂ ቅጣት ሊበግረው እንደማይችል ነው። ቢላል እርቃኑን በትኩስ አሸዋማ መሬት ላይ እንዲንከባለል እና ቋጥኝ ድንጋይም ደረቱ ላይ እንዲጫን ተደርጓል። ግን እምነቱን ሊቀይር አልፈቀደም። በተከታታይ እና በተደጋጋሚ ኢ -ሰባአዊ ድርጊት ተፈጽሞበታል። የቁረይሽ ሹማምንት አንድን ባሪያ ሊያሳምኑ እና ወደ ቀድሞው እምነቱ ሊመልሱት ባለመቻላቸው ቁጭት እና ሀፍረት ስለተሰማቸው ክብራቸውን ለመጠበቅ ሲሉ ቢላል ቢያንስ ቢያንስ ስለ አማልክቶቹ ጥቂት በጎ ነገር እንዲናገር ቢጠይቁትም አሻፈረኝ አለ። ህይወቱን ከስቃይ ምናልባትም ከሞት ለማዳን ቢያንስ ስለ አማልክቶቻቸው ከልቡ እንኳ ባይሆን ማመስገን በቂ ነበር። ታላቁ ቢላል ግን ከስጋዊ ህመም መንፈሳዊ የበላይነትን በመምረጡ ለጠላቶቹ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም። ይልቁንም በተደጋጋሚ አሀድ አሀድ ... በማለት የአምላክን አንድነት ያውጅ ነበር። ላት እና ኡዛ የተሰኙ ጣኦታትን እንዲያወሳ ያለመታከት ይጠይቁታል። መልሱ ግን አሁንም አሀድ ...አሀድ ...ነበር። እኛ የምንለውን ደግመህ በል በማለት ይገርፉታል : በምጸታዊ ቃልም እናንተ የምትሉትን ለመናገር ምላሴ አይችልም ይላቸዋል .... ከዛም ህመሙን ለመቀነስ እና ነጻነቱብ ለመስጠት አቡበከር ከኡመያ ቢላልን ገዛዉ ከዛም ነጻ አወጣዉ.




#Article 366: የጊንጥ ዱላ (132 words)


የጊንጥ ዱላ የግብጽ ጥንታዊ መንግሥት ቅርስ ሲሆን በነቀን (ሄራኮንፖሊስ) ከተማ የተገኘ  ስብብር የዱላ ራስ ነው። ከበሀ ድንጋይ ተሠራ። በትልቁ ክፍል የተቀረጸው ትርዒት ንጉሥ ጊንጥ ስለሚያሳይ፣ ቅርሱ «የጊንጥ ዱላ» ተብሏል። 

ይህ «ንጉሥ ጊንጥ» ከፈርዖኖች ዘመን አስቀድሞ በግብጽ የነገሠ አለቃ መሆኑ ይታወቃል። ጥንታዊው መንግሥት በ«ሔሩ ወገን» እንደ ተመሠረተ ሁሉ፣ ዱላው በአረመኔው አምላክ በሔሩ ቤተ መቅደስ ፍርስራሽ በ1890 ዓ.ም. ተገኝቶ ነበር።  በተቀረጸው ትርዒት፣ አለቃው ከሰው ረጅም ሆኖ መኮትኮቻም ይዞ በራሱ ላይ «የላይኛ ግብጽ ነጭ ዘውድ» አለበት።  አጠገቡ የጊንጥ ምልክት አለ፤ የዚሁ ቃል ግብጽኛ አጠራር ምናልባት «ሠልክ» ነበር።  

አለቃውን የሚያገልግሉት ሰዎች በመነጻጸር በጣም አጭር ሆነው ያሳያል። ከሱም በላይ የዓላማዎች ተርታ ሊታይ ይችላል።  ከነዚህ ሁለቱ ዓላማዎች «የሴት ወገን» ምልክት እሱም «የሴት እንስሳ» (አዋልደጌሳ ወይም ቀበሮ) አለባቸው። ከየአላማው ደግሞ እንደ ወፍ የሚመስል ፍጡር በአንገት ይሰቀላል። የዚህ ትርዒት ትርጉም በእርግጥ ባይታወቅም፣ በጥንታዊ ግብጽ ለመግዛት የተነሡት ወገኖች ታሪክ እንደሚነካ ይገመታል። 




#Article 367: የሻባካ ድንጋይ (130 words)


የሻባካ ድንጋይ ከግብጽ አዲስ መንግሥት (ምሥር) 25ኛ ሥርወ መንግሥት (ከ700 ዓክልበ. ገደማ) የደረሰ ቅርስ ነው። በዚህ ታላቅ ድንጋይ የተቀረጸው የሃይሮግሊፍ ጽሑፍ በኩሻዊው ንጉሥ ሻባካ ትዕዛዝ ትል ከበላ ከጥንታዊ ብራና እንደ ተቀዳ ይላል። ሻባካ የብራናውን ወረቀት በአንድ የሜምፎስ ቤተ መቅደስ አገኝቶት ቃሉ እንዳይጠፋ እንዲቀረጽ አዘዘ ይላል። ሆኖም በኋለኛ ዘመን ድንጋዩ እንደ ወፍጮ ተጠቅሞ ብዙ ሃይሮግሊፍ ጠፋ፤ ከዚህ ጉዳት የተነሣ በሙሉ ማንበቡ አይቻልም። 

ጽሑፉ በተለይ የጥንታዊ ግብጽ አፈ ታሪክ ይገልጻል። በጥንታዊ ግብጻውያን እምነት ሴት የተባለው ትንሽ ወንድሙን ዖሴሮስን (ቄንቲያሜንቱን) በታቸኛ አባይ ወንዝ (ስሜን ግብጽ) አሰጥሞ ከገደለው በኋላ፣ እሱ ደቡብ ግብጽ ተሸለመው። የዖሴሮስ በኲር ሔሩ እንዲሁም ስሜኑን ተቀበለ። ትንሽ ጊዜ አልፎ ግን ሔሩ የአማልክት ሞገስ አገኝቶ ሁለቱን አገሮች ያዘ። ከብዙ ትግል በኋላ ሁለቱ ወንድሞች ተስማሙና አብረው ፈርዖኖቹን ወለዱ። 

ይህ አፈ ታሪክ ምናልባት ስለ ላይኛ ግብጽና ታችኛ ግብጽ ታሪካዊ ውሕደት በጣም የተዛበ ወሬ ይሆናል።




#Article 368: ሲቪል ኢንጂነሪንግ (1590 words)


ሲቪል ምህንድስና ወይም ሲቪል ኢንጂነሪንግ አንዱ እና ታዋቂው የምህንድሥና (ኢንጂነሪንግ) ዘርፍ ነው። 

ሲቪል ምህንድስና ስለ ግንባታ አካላት አስፈላጊነት ቅድመ ጥናት የሚያደርግ እንዲሁም የግንባታ አካላቱ አስፈላጊነት ከታመነበት በኋላ፤ የንድፍ ስራና የግንባታ ሂደትን የሚከታተልና የሚያስፈጽም እንዲሁም የግንባታ አካላቱ አገልግሎት ላይ ከዋሉ በኋላ የአገልግሎት እድሜያቸው እስከሚያበቃ ድረስ የሚፈለግባቸውን አገልግሎት እየሰጡ እንዲቆዮ የጥገና ስራዎችን የሚያጠናና የሚተገብር የሙያ ዘርፍ  ነው።

ከግንባታ አካላት ውስጥ መንገዶች፣ ድልድዮች፣ ህንጻዎች፣ ግድቦች፣ የአየር ማረፊያ አስፋልት ንጣፎች፣ የውሃ ተፋሰስ መስመሮች፣ ለተለያዮ አገልግሎቶች የሚውሉ ትቦዎች፣ የባቡር ሃዲዶች፣ ለትራንስፖርት አገልግሎት የሚውሉ ሰው ሰራሽ ወንዞች እና ሌሎችም ይገኙበታል።

ሲቪል ምህንድስና በጥንታዊነት ከወታደራዊ ምህንድስና ቀጥሎ ሁለተኛውን ደረጃ ሲይዝ፣ የሙያ ዘርፉ የግንባታ አካላቱ ላይ እንዲሁም የግንባታ ሂደቱ ላይ ተሞርኩዞ በተለያዮ የሙያ ዘርፎች ይከፋፈላል። የሙያ ዘርፉም ከማህበረሰብ አገልግሎቶች ጀምሮ (ለምሳሌ እንደ መንገድ ግንባታ) እስከ ግለሰብ ደረጃ ድረስ (የግለሰብ መኖሪያ ቤት) የሚተገበር ነው።

ሲቪል ምህንድስና የተፈጥሮ ህግጋትንና የሳይንስ መርሆችን በመጠቀም የአንድን ማህበረሰብ ተግዳሮቶች ለመፍታት የሚጥር የሙያ ዘርፍ በመሆኑ ታሪካዊ እድገቱ ከተፈጥሮ ህግጋት ሳይንስ (ቪዚክስ) እና ከሂሳብ ሳይንስ የግንዛቤ እድገት ጋር የተያያዘ ነው።

ሲቪል ምህንድስና ዘርፍ፤ የአወቃቀር ሳይንስ ()፣ የከርሰ ምድር ሳይንስ፣ የአፈር ሳይንስ፣ የውሃ ሳይንስ (hydrology) ፣ የአካባቢ ሳይንስ ፣ ሜካኒክስ (አንድ ቁስ በጫና አማካኝነት የሚያሳየው የለውጥ ሂደት የሚያጠና ዘርፍ ነው) ፣ የቁስ አወቃቀር ሳይንስ (material science)፣ የመልክዓ ምድር ሳይንስ እና የመሳሰሉትን ዘርፎች የሚያካትት ስለሆነ እድገቱም ከእነኚህ በውስጡ ከሚገኙ የሙያ ዘርፎች እድገት ጋር የተያያዘ ነው።

ሲቪል ምህንድስና ሰፊ የሙያ ዘርፍ እንደመሆኑ በውስጡ ብዛት ያላቸው ሌሎች የሙያ ዘርፎችን ይይዛል። አማካሪ ሲቪል መሀንዲሶች (specialized civil engineers) ከእነኚህ የተለያዮ የሙያ ዘርፎች በአንዱ ላይ ጠለቅ ያለ ስልጠናና ትምህርት ወስደው፤ በወሰዱት የስልጠና መስክ የአማካሪነት ሚና ሲኖራቸው፤ አጠቃላይ ሲቪል መሀንዲሶች (General civil engineers or site engineers) ደግሞ ስለ ሁሉም የሲቪል ምህንድስና ዘርፎች መሰረታዊ እውቀት ኖርዋቸው በተለያዮ ዘርፍሮች ከሰለጠኑት አማካሪ ሲቪል መሀንዲሶችና እንዲሁም የቅየሳ ባለሙያዎች ጋር በመሆን አንድን የተወሰነ የመሬት ይዞታን ከነበረበት የአገልግሎት ሁኔታ ወደሚፈለግበት የአገልግሎት ሁኔታ በግንባታ አማካኝነት የመለወጥ ስራን ያከናውናሉ። አጠቃላይ ሲቪል መሀንዲሶች አብዛኛውን ጊዜያቸውን የግንባታ ስራዎን በመጎብኘትና በመቆጣጠር፣ ከግንባታ አካላቱ ባለቤቶች፣ ስራ ተቋራጮችና ሌሎች ከግንባታ አካላቱ ጋር ግንኙነት ካላቸው አካላት ጋር በመገናኘትና ስለ ግንባታው ሂደት መረጃ በመለዋወጥ፤ የግንባታ እቅዶችን በማውጣትና በመቆጣጠር እንዲሁም ሌሎች ተዛማጅ ስራዎችን ለመስራት ያውላሉ። 

ሲቪል መሀንዲሶች የመሬት ምህንድስና ፣ የአወቃቀር ምህንድስና ፣ የአካባቢ ሳይንስ ምህንድስና ፣ የመጓጓዣ ምህንድስና ፣ የግንባታ ምህንድስና እና ሌሎች ተዛማጅ የምህንድስና መስኮችን በመጠቀም ለመኖሪያ ፣ ለንግድ፣ ለኢንዱስትሪ እንዲሁም ለማህበረሰብ አገልግሎቶች የሚውሉ አነስተኛ እንዲሁም ግዙፍ ግንባታዎችን ያከናውናሉ።

የወደብ ምህንድስና የወደብ አካባቢን የማልማትና የማስተዳደር ስራዎችን የሚያከናውን ሲሆን፣ ወደብን ለመጓጓዣ ስራ ከማዋል በተጨማሪ፣ በወደብ አካባቢ የሚከሰቱ የውሃ መጥለቅለቅ አደጋዎችን፣ የአፈር መሸርሸርና እና የመሳሰሉ የተፈጥሮ አደጋዎችን የመከላከል ስራ የሚያከናውን የምህንድስና ዘርፍ ነው።

የግንባታ ምህንድስና የግንባታ ሂደትን የማቀድ፣ የማስፈጸም፣ ለግንባታው የሚያስፈልጉ የግንባታ ቁሳቁሶችን የማጓጓዝና የማቅረብ፣ እንዲሁም የግንባታ ቦታውን ለሚፈለገው የግንባታ አካል እንዲውል በግንባታው አካባቢ የሚገኙ የተፈጥሮ ሀብቶች ጥበቃ መሟላቱን የማረጋገጥ፣ የግንባታ ቦታው ለግንባታ ስራ ደህንነትና ምቹነት ያለው መሆኑን የማረጋገጥ እንዲሁም አግባብ የሆነ የግንባታ መሬት አጠቃቀምን  የሚከታተልና የሚያስፈጽም የምህንድስና ዘርፍ ነው።
የግንባታ ተቋራጮች በሌሎች የሲቪል ምህንድስና አገልግሎቶች ላይ ከተሰማሩ የአገልግሎት ተቋሞች አንጻር የተሰማሩበት መስክ ከፍተኛ የንግድ አደጋ ወይም መዋዠቅ ስለሚከሰትበት የግንባታ መሃንዲሶች አብዛኛውን ጊዜያቸውን ንግድን በተመለከቱ ጉዳዮች ለምሳሌ ያህል የግንባታ ውሉን በመገምገም እና ማስተካከያ የሚያስፈልጋቸውን ጉዳዮች በማርቀቅ፣ የግንባታ ግብአቶችን አቅርቦት ፍሰት በመቆጣጠር፣ እንዲሁም የግንባታ እቃዎች የገበያ ዋጋ መረጃን በመሰብሰብ ላይ ያውላሉ።

የመሬት ርዕደት ምህንድስና መሬት ርዕደት በሚያይልባቸው አካባቢዎች የሚሰሩ የግንባታ አካላት፤ የመሬት ርዕደትን ተቋቁመው እንዲዘልቁ ለማድረግ የግንባታ አካላቱን አወቃቀር በተለየ መልኩ ትኩረት በመስጠት የሚያጠናና መፍትሄ የሚሰጥ የምህንድስና ዘርፍ ነው። ይህ የምህንድስና ዘርፍ የአወቃቀር ምህንድስና ዘርፍ አካል ነው። የመሬት ርዕደት ምህንድስና ዋነኛ አላማው በመሬትና በግንባታ አካሉ እንዲሁም በግንባታ አካላቱ መካካል በመሬት ርዕደት ጊዜ የሚኖረውን መስተጋብር መረዳትና የግንባታ አካሉ የመሬት ርዕደት ሂደቱን አልፎ አገልግሎት እንዲሰጥ አወቃቀሩን፣ የግንባታ ቁስ አመራረጡን እንዲሁም መሰል የግንባታ መፍትሄዎችን በየሀገራቱ ጥቅም ላይ ከዋሉ የግንባታ መስፈርቶች ጋር በሚስማማ መልኩ መተግበር ነው።

የአካባቢ ጥበቃ ምህንድስና ከጤና ጥበቃ ምህንስና ጋር ተጓዳኝ የሆነ የምህንድስና ዘርፍ ሲሆን፣ የጤና ጥበቃ ምህንድስና በአመዛኙ የንጹህ ውሃ መጠጥ አቅርቦትና የአካባቢ ቆሻሻ ፍሳሽ አወጋገድ ላይ ሲያተኩር፤ የአካባቢ ጥበቃ ምህንድስና ሰፋ ባለ መልኩ የአካባቢ ብክለት የሚያስከትሉና ለጤና ጠንቅ የሆኑ ጎጂ ኬሚካሎችን እና ቆሻሻዎችን መቆጣጠርና ማስወገድ ይጨምራል። የአካባቢ ጥበቃ ምህንድስና፤ የማህበረሰብ ጤና ምህንድስና እና የአካባቢ ጤና ምህንድስና በሚል አጠራርም ይታወቃል።

የአካባቢ ጥበቃ ምህንድስና በኬሚካል ውህደቶች፣ በባዮሎጂካል ሂደቶች እንዲሁም በሙቀት ለውጥ አማካኝነት የሚፈጠሩ ቆሻሻዎችን የማጥራትና የማስወገድ፣ አየርንና ውሃን የማጣራት፣ እንዲሁም በአደጋ ወይም በቆሻሻ ክምችት የተበከለን የመሬት አካል ወደ ተፈጥሮዋዊ ይዘቱ የመመለስ ስራዎች የሚያከናወኑበት የምህንድስና ዘርፍ ነው። በአካባቢ ጥበቃ ምህንድስና ትኩረት ከሚደረግባቸው ዋና ነጥቦች ውስጥ የመርዝ ወይም የኬሚካል እንቅስቃሴ ወይም ጉዞ (ከመሬት ላይና ከመሬት በታች)፣ የውሃ ማጣራት፣ የቆሻሻ ፍሳሽ ማጣራት፣ የአየር ብክለት፣ የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድና የአደገኛ ቆሻሻዎች አያያዝ ይገኙበታል።  የአካባቢ ጥበቃ መሃንዲሶች ብክለትን የመቀነስ፣ የአረንጓዴ ምህንድስና ዘርፍ ስራዎች (የአካባቢ ብክለትን የሚቀንሱ የግንባታ መንገዶችንና ቁሶችን የኢኮኖሚ አቅምን ባገናዘበ መልኩ የማጥናት ስራ)፤ እንዲሁም የኢንዱስትሪዎችን የቁሳቁስና የሃይል አጠቃቀም ፍሰት የማጥናት ስራዎችና (industrial ecology) የመሳሰሉት ላይ ይሳተፋሉ። ከዚህም በተጨማሪ የአካቢቢ ጥበቃ መሃንዲሶች ድርጊቶች (ለምሳሌ የአንድ የግንባታ አካል ትግበራ) በአካባቢው ላይ ሊያስከትሉ የሚችሉትን ተጽእኖ በመገምገም መረጃ ያዘጋጃሉ። 

የምርመራ ምህንድስና የግንባታ አካላት የሚፈለግባቸውን ጥቅም ሳይሰጡ ለአገልግሎት ከታቀደላቸው ጊዜ በፊት በመፍረስ አገልግሎት መስጠት ሲያቆሙ፣ እንዲሁም የመፍረስ አደጋው  በሰው ወይም በንብረት ላይ አደጋ በሚያደርስበት ጊዜ የግንባታ አካሉን አወቃቀር ፣ የተሰራበትን ቁስ ፣ የግንባታውን ጥናት እንዲሁም መሰል ተዛማጅ ጉዳዮችን በመመርመር ተጠያቂ የሚሆነውን አካል ለማወቅና የፍርድ ሂደትን ለማገዝ የሚያገለግል የሲቪል ምህንድስና ዘርፍ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ይህ የምህንድስና ዘርፍ ከምርመራ ውጤቶች በመነሳት የግንባታ ቁሶችን ወይም የግንባታ አካላት ጥራትን እንዲሁም የግንባታ አካላት አወቃቀርን የማሻሻል ስራዎን ለመስራት የሚያስችል የሲቪል ምህንድስና ዘርፍ ነው።  ልዮ የሆነ የባለቤትነት ፍቃድ (patent) ያላቸውን የግንባታ ቁሶች ፣ አካላት ፣ ወይም የግንባታ ዘዴዎች የፍቃድ ባለቤቱን ይሁንታ ሳያገኙ በሚፈጸሙ ግንባታዎች ላይ የባለቤትነት ጥያቄዎችን ለመመለስ በሚደረጉ ህጋዊ ሂደቶች ላይ ይህ የምህንድስና ዘርፍ ቁልፍ ቦታ አለው። 

መሬት ነክ ምህንድስና የግንባታ አካላትን የሚሸከሙ አለቶችና አፈሮችን የምህንድስና ጠባይ የሚያጠና የሲቪል ምህንድስና ዘርፍ ነው። ይህ ዘርፍ ከአፈር ሳይንስ፣ ከቁስ ሳይንስ ፣ ከሜካኒክስ እንዲሁም የፍሰት ሳይንስ  (hydraulics) እውቀቶችን በመጠቀም ደህንነታቸው የተጠበቀና የገንዘብ አቅምን ያገናዘቡ የግንባታ መሰረቶችን፣ የመጠበቂያ ግድግዳዎችን፣ ግድቦችን፣ ዋሻዎችን የመሳሰሉ የግንባታ አካላትን መንደፍና መገንባት ላይ ትኩረት ያደርጋል ።

የከርሰ ምድር ውሃን በተለያዮ ምክንያቶች ከመበከል የመጠበቅ እንዲሁም የቆሻሻ ክምችትን በአግባቡ ለመቆለልና ክምችቱ የአፈርና የከርሰ ምድር ውሃን እንዳይበክል የማድረግ ስራዎችም በዚሁ የምህንድስና ዘርፍ የሚተገበሩ ናቸው።

የአፈርን የምህንድስና ጸባይ የማወቅ ተግባር ለመሬት ነክ መሃንዲሶች ፈታኝ ነው። በሌሎች የሲቪል ምህንድስና ዘርፎች የግንባታ ቁሶች ጸባይ (ለምሳሌ እንደ ብረት እና ኮንክሪት) በሚገባ የሚታወቅ ሲሆን፤ በግንባታ አካባቢ የሚገኝን የአፈር ጸባይ ማወቅ ግን ከተለዋዋጭነቱና በናሙና በሚደረጉ  ሙከራዎች መፈተሽ የሚቻለው ከጠቅላላውን የተወሰነውን ብቻ በመሆኑ በጣም አዳጋች ነው።

ከዚህም በተጨማሪ አፈር በጭነት ምክንያት የሚያደርገው የቅርጽ ለውጥ ከጫናው ጋር ቀጥተኛ ያልሆነ (nonlinear) ተዛምዶ ስላለው፤ ማለትም አነስተኛ እና ከፍተኛ ለሆኑ ጫናዎች የተለያየ ጥንካሬ(strength)፤ ጠጣርነት(stiffness)፤ የቅርጽ ለውጥ   ስለሚኖረው፤ የአፈርን የምህንድስና ጸባይ በተሟላ ሁኔታ ለማወቅ የዳግታል።

መሬት ነክ መሃንዲሶች አብዛኛውን ጊዜ ከከርሰ ምድር ባለሙያዎችና የአፈር ሳይንቲስቶች ጋር በትብብር ይሰራሉ።

የቁሶች ጥናት ሳይንስ ወይም ምህንድስና በሲቪል ምህንድስና ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ሚና ይይዛል። የቁሶች ጥናት ሳይንስ ወይም ምህንድስና የቁሶችን ተፈጥሮዋዊ ባህሪ የሚያጠና የሳይንስ ወይም የምህንድስና ዘርፍ ነው። ለግንባታ ከሚውሉ ቁሳቁሶች ውስጥ ኮንክሪት፣ የአስፋልት ኮንክሪት፣ እንደ ብረት እና አልሙኒየም ያሉ ጠንካራ ብረታ ብረቶች ፣ የፕላስቲ ውጤቶችና የመሳሰሉት ይገኙበታል። የቁሶች ጥናት የግንባታ አካላትን ከተለያየ ጥቃት ለመከላከል የሚውሉ ቅባቶችና የመከላከያ ንጣፎችን፣ እንዲሁም አንድን የብረት አይነት ከሌላ የብረት አይነት ጋር በማደባለቅ ለግንባታ ተስማሚ የሆነ ሌላ አይነት የብረት አይነት ማምረት የመሳሰሉ ስራዎችንም ያጠቃልላል። 

የቁሶች ጥናት የትግበራ ፊዚክስና (applied physics) የኬሚስትሪ እውቀቶችን የያዘ የምህንድስና ዘርፍ ነው። በቅርቡ እየተስፋፋ የመጣው የናኖ ሳይንስ ወይም ቴክኖሎጂን (ናኖ ሳይንስ የአንድን ቁስ የአቶምና የሞሎኪዮል አወቃቀር በመቀየር በተፈጥሮ የማይገኙ ለየት ያለ ባህሪ ያላቸውን ቁሶች ለመስራት የሚደረግ ጥረት ነው) ደረጃ ተንተርሶ በአሁኑ ጊዜ የቁሶች ጥናት ከፍተኛ የሆነ የምርምር ድርሻን ይዞ ይገኛል። የቁሶች ጥናት ምህንድስና በምርምር ምህንድስናና የግንባታ አካላት ከጥቅም ውጪ የመሆን መንስኤን ለማጥናት በሚደረጉ ስራዎች ላይ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል። 

የአወቃቀር ምህንድስና የህንጻዎችን፣ የድልድዮችን፣ የማማዎችን፣ የመንገድ ማቋረጫ ድልድዮችን፣ የዋሻዎችን፣ በባህርና ላይ የሚገነቡ ለነዳጅ ወይም ለዘይት ማውጫ የሚያገለግሉ ሰው ሰራሽ መሬቶችን እና ማማዎችንና እንዲሁም እነኚህን የመሳሰሉ የግንባታ አካላትን በተመለከተ የአወቃቀር ንድፍና (structural design) የአወቃቀር ትንታኔ (structural analysis) ላይ የሚያተኩር የሲቪል ምህንድስና ዘርፍ ነው።

የአወቃቀር ትንታኔ (structural analysis) ጉልበቶች በግንባታ አካላት ላይ የሚያሳድሩትን ተጽእኖ መመዘን ላይ ትኩረት ያደርጋል። የአወቃቀር ምህንድስና በግንባታ አካላት ላይ የሚያርፉ ጉልበቶችን ለምሳሌ የራሱ የግንባታ አካሉ ክብደት፣ በግንባታ አካሉ ላይ የሚያርፉ ሌሎች ቋሚና ተቀሳቃሽ ክብደቶች፣ የንፋስ ግፊት ፣ የሙቀት ለውጥ፣ የውሃ ግፊት፣ የመሬት ጫና፣ የመሬት ርእደት፣ በረዶ እና የመሳሰሉትን የመለየትና፣ በእነኝህ ጉልበቶች አማካኝነት በግንባታ አካላቱ ውስጥ የሚከሰቱ ውስጣዊ ጫናዎችንና ጉልበቶችን (internal stresses and forces) የማስላትና የግንባታ አካላቱ እነኝህን ጉልበቶች ተቋቁመው አገልግሎት እንዲሰጡ መጠናቸውንና የሚሰሩበትን ቁስ መንደፍ ላይ ያተኩራል። የአወቃቀር ምህንድስና ባለሙያው የግንባታ አካላቱ  ተጠቃሚዎችን ደህንነትን በሚጠብቅ መልኩ (llimit state of carrying capacity) እንዲሁም ግንባታ አካላቱ ከተሰሩበት አላማ አንጻር የሚጠበቅባቸውን አገልግሎት እንዲሰጡ አድርጎ  (limit state of serviceablity) መንደፍ ይጠበቅበታል። 

እንደ ንፋስ እና የመሬት ርእደት አይነት ጉልበቶች በቀላሉ ለመተንበይ አስቸጋሪ በመሆናቸው በአወቃቀር ምህንድስና ስር እንደ ንፋስ ምህንድስና እና የመሬት ርእደት ምህንድስናን የመሳሰሉ ንኡስ ዘርፎች እንዲፈጠሩ ምክንያት ሆኖዋል።

በአወቃቀር ምህንድስና ውስጥ የንድፍና የትንታኔ ስራ የግንባታ አካሉ ቋሚ ጉልበቶችን ፣ተለዋዋጭ ጉልበቶችን (እንደ ንፋስና የመሬት ርእደት ያሉ) ወይም ጊዜያዊ ጉልበቶችን (ለምሳሌ በግንባታ ጊዜ ጥቅም ላይ የሚውሉ የግንባታ ማሽኖች ክብደት፣ በግንባታ አካሉ ላይ በተንቀሳቃሽ ነገሮች አማካኝነት ሊከሰቱ የሚችሉ ግጭቶች እና የመሳሰሉት) ለመሸከም  የሚያስፈልገውን ጥንካሬና ጠጣርነት መወሰን እንዲሁም የግንባታ አካሉ ሚዛኑን ጠብቆ መቆም መቻሉን ማረጋገጥ ያካትታል። ከዚህም በተጨማሪ የንድፍና ትንታኔ ስራ የግንባታውን ዋጋ መተመን፣ የግንባታውን ተግባራዊነት ማረጋገጥ፣  ግንባታው ውበት የተላበሰ መሆኑን ማረጋገጥ እንዲሁም የሃብት አጠቃቀምና የተፈጥሮ  ሚዛንን በጠበቀ መልኩ ግንባታው እንዲከናውን ማስቻልን ያካትታል።

ቅየሳ የአንድን የመሬት ገጽ ወይም የግንባታ አካል አቀማጥ ለማወቅ የሚደረግ የልኬት ስራ ነው። የቅየሳ ስራ ለቅየሳ ስራ የሚውሉ እንደ ውሃ ልክ (level) ወይም ቴዎዶላይት (አግድምና ሽቅብ ማእዘንን ለመለካት የሚችል አጉሊ መነጽር) ያሉ መሳሪያዎች በመጠቀም በሁለት የልኬት ቦታዎች መካከል ከልኬት ቦታው አንጻር የሚኖረውን የቦታ ልዮነት ለማወቅ  የማእዘን (angle) ፣ የአግድም ቁመትና የሽቅብ ቁመት ልኬቶችን በመውሰድና የሂሳብ ስሌትን በመጠቀም የመሬት ገጽን ወይም የግንባታ አካልን አቀማመጥ የመወሰን ተግባር ነው። ከኮምፒውተር እውቀት ማደግ ጋር በተያያዘ አውቶማቲክ የሆኑ እንደ የኤሌክትሪክ ርቀት መለኪያዎች በመፈልሰፋቸው እንደ ቶታል ስቴሽን፣ ጂፒኤስ፣ የጨረር ዳሰሳ (laser scanning) የመሳሰሉ መሳሪያዎች ባህላዊ የሆኑ መሳሪያዎችን በመተካት ላይ ናቸው።

የትራንስፖርት ምህንድስና ሰዎችንና ቁሳቁስን ከቦታ ወደ ቦታ በደህንነት ፣ በተቀላጠፈና ምቹ በሆነ መንገድ ማጓጓዝ ላይ ትኩረት ያደርጋል። ይህንን አላማማ ለማሳካትም የመኪና፣ የባቡር፣ የውሃና የአየር ማረፊያ መንገዶች እንዲሁም የወደቦች ንድፍ፣ ግንባታና ጥገና ስራዎች በትራንስፖርት ምህንድስና ውስጥ ሰፊ ድርሻ ይይዛሉ። የትራንስፖርት ምህንድስና በውስጡ የትራንስፖርት ንድፍ ስራ (transportaion design)  ፣ የትራንስፖርት ግንባታ እቅድ (transportation planning)፣ የትራፊክ ምህንድስና (traffic engineering)፣ የከተማ ልማት ምህንድስና፣ የመንገድ ንጣፍ ምህንድስና የመሳሰሉ ንኡስ የሙያ ዘርፎችን የያዘ ነው።




#Article 369: ቴክሳስ (158 words)


ቴክሳስ በአሜሪካ የሚገኝ ግዛት ነው። ይህ ግዛት በስፋቱም ሆነ በህዝብ ብዛቱ በሃገሪቱ ውስጥ ከሚገኙ ግዛቶች ሁሉ ሁለተኛ ነው። ይህም ማለት ከካሊፎርኒያ ከጥላ ማለት ነው። የቴክሳስ ስም የመጣው ቴካስ ከሚለው የካኡው ነገድ ሲሆን ትርጉሙም ጓደኛ ወይም ባለ ቃልኪዳን ማለት ነው። ቴክሳስ ተገንጣይዋ ኮከብ ማለትም ነው፤ ይህ ብቻ አይደለም ቴክሳስ የራሷ የሆነ ባንዲራ እና ወሰንም ነበራት። ቴክሳስ በስፋቷ ትልቅ በመሆኗ በእንግሊዝኛ መዝገበ ቃላት ግዙፍ የሚል ትርጓሜ አለው። ቴክሳስ በኢንዲያውያን ነገዶች ስትገዛ የኖረች ስትሆን ስፔን የመጀመሪያዋ ሀገር ነበረች ቴክሳስን ለማጠንከር የፈለገችው ስለዚህም በ 1820 አውሮፓውያንን በማስገባት የበለጠ ኗሪ እና ጠንካራ ህዝብ እንድትሆን አድርጋት ገዝታት ነበር ነገር ግን  በ 1821 ቴክሳስ ከስፔን ግዛት ነጻ መሆኗን ሜክሲኮ አውጃ በራሷ በሜክሲኮ አገዛዝ ስር አደረገቻት። በ 1836 በማርች ወር ከሜክሲኮ ግዛት ነጻነቷን አወጀች። በ 1845 በአሜሪካ ፌዴራላዊ የተባበሩት ሀገራት መንግስት 28 ሀገር በመሆንና 4ኛዋ ከጥምር በፊት የራሷ የሆነ ስልጣን ያላት ሀገር መሆን ችላለች።
በ20ኛው መቶ ክ/ዘመን መጀመሪያ ቴክሳስ ውስጥ ነዳጅ ተገኘ ይህም የቴክሳስ ኗሪወች ቁጥር እንዲቸምርና ኒው ዮርክን በመብለጥ በህዝብ ብዛት ሁለተኛ ሀገር እንድትሆን ያደረጋት።




#Article 370: ማይክል አንጄሎ ቡናሮቲ (2999 words)


ማይክል አንጄሎ ዲ ሎዶቪኮ ቡናሮቲ ሲሞኒ (6 ማርች 1475 - 18 ፌብሩዋሪ 1564) በተለምዶ ማይክል አንጄሎ እየተባለ ይጠራ የነበረው የእንደገና መወለድ ተብሎ በሚጠራው ዘመን ይኖር የነበረ ኢጣሊያዊ ሰዓሊ ፤ ቀራጭ፤ ህንጻ ሰሪ፤ ገጣሚ፤ እና መሀንዲስ ነበር። ምንም እንኳን ቅንድብን ወደ ላይ ከማስነሳቱ ባሻገር ይጠቀምባቸው የነበረው ስነ ስርአቶች እጅግ በጣም ከፍተኛ ደረጃ በመሆናቸው የእንደገና መወለድ ሰው የሚል ቅጽል ስም አሰጥቶት ነበር። እሱን በመሳሰሉ ታላላቅ ሰዓሊዎች ለምሳሌ ሊዮናርዶ ዳቪንቺ። ማይክል አንጄሎ በረጅም የእድሜ ዘመኑ በሰራቸው በማናቸውም የስራ ውጤቶቹ እጅግ በጣም ከፍተኛ ነበሩ። ታሪካቸው በደንብ ከተመዘገበላቸው የ16ኛው ክፍለ ዘመን ሰአሊዎችም አንዱ አድርጎታል። እጅግ በጣም ከሚወደዱት ሁለት ስራዎቹ መሀከል ፒየታ = ሐዘን እና ዳዊት የሚባሉትን ሰርቶ የጨረሰው እድሜው ሠላሳ ከመሆኑ በፊት ነበር። ምንም እንኳን ለስዕል የነበረው አመለካከት በጣም ዝቅተኛ ቢሆንም ማይክል አንጄሎ ሁለት ድንቅ የተባሉ ስእሎችን በጄሶ ላይ በመስራት ለምዕራቡ አለም አበርክቷል። ዘፍጥረትን ሲስቲኒ በሚባለው ቤተ ክርስቲያን ጣራ ላይ እና የፍርድ ቀን የተባለውን ደግሞ በሲስቲኒ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከመንበሩ በስተጀርባ በኩል በሮማ ከተማ ውስጥ ይገኛሉ። ማይክል አንጄሎን ልዩ ከሚያደርገው አንዱ ነገር የመጀመሪያው የምእራብ አለም ሰዓሊ በህይወት ዘመኑ እያለ የህይወት ታሪኩ የተጻፈለትም በመሆኑ ነው። ሁለት የተለያዩ ጸሃፊዎች በህይወት እያለ ታሪኩን ጽፈውታል። አንደኛው ጂዮርጂዮ ቫሳሪ ሲሆን እርሱም ማይክል አንጄሎ እንደገና መወለድ ካፈራቻቸው የኪነ ጥበብ ሰዎች አናት ነው ብሎ ከፍተኛውን ስፍራ ይሰጠዋል። እስከ አሁን ድረስም ይህ አባባል እንደቀጠለ ይገኛል። በህይወት ዘመኑም እያለ የተቀደስው ወይም የተባረከው የሚል ቅጽል ስም አሰጥቶት ነበር[13]።

የሎሬንዞ ዲ ሜዲቺ ሞት በ 8 አፕሪል 1492 ለማይክል አንጄሎ ትልቅ ለውጥ አምጥቶለታል[14]ማይክል አንጄሎ የሜዲቺን አጥር ግቢ ትቶ ወደ አባቱ ቤት ተጓዘ። በሚቀጥሉት ወራትም ከእንጨት (1493) የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ስቅለት ከእንጨት ቀርጾ ለፍሎሬንቲን ቤተ ክርስቲያን ሳንቶ ስፒሪቶ በስጦታ አበረከተ። በአንጻሩም በቤተክርስቲያኑ ሆስፒታል በነበረው ውስጥ የሰውነትን ቅርጽ እና አሰራር በሞቱ ሰዎች አስከሬን በሆስፒታሉ ውስጥ ተለማምዷል። [15] ከ 1493 እና 1494 ግዙፍ የሆነ ዕምነ በረድ ገዝቶ ሄርኩለስን ቀረጸ። ይህ ቅርጽ በሺያጭ ወደ ፈረንሳይ ሄዶ የደረሰበት ጠፋ 1700.[12][c] በ 20 ጄንዋሪ 1494 በጣም ከፍተኛ በረዶ ከጣለ በኋላ ሎሬንዞ ፒኤሮ ዲ ሚዲቺ የበረዶ ቅርጽ ውድድር አዘጋጀ። ማይክል አንጄሎም ወደ ሜዲቺ ቅጥር ግቢ ለውድድር እንደገና ገባ።

በዚያው አመት የሜዲቺ ቤተሰብ ከፍሎሬንስ ከስልጣን በሳቮናሮላ ተወገዱ። ማይክል አንጄሎ የፖለቲካው ግርግር ከማለቁ በፊት ፍሎሬንስን ትቶ ወደ ቬኒስ ከዚያም ወደ[14] ቦሎኛ አቀና። በቦሎኛ አንድ ውል ተዋዋለ። ውሉም ተጀምሮ ያላለቀ የነበረ አንድ ትንሽ የዶሜኒኮ ሽራይንን ሀውልት ለመጨረስ ነበር። 
ይህም ቅርጽ የተሰራው ለዶሜኒኮ ማስታወሻ በሆነው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነው። በ1494 መጨረሻ ግድም በፍሎሬንስ የፖለቲካው ሁኔታ ተረጋጋ ። ቀደም ሲል ከተማዋ በፈረንሳይ ትወረራለች የሚል ፍርሀት ነግሶ ነበር። ነገር ግን ቻርልስ ፰ኛው ሽንፈት ስለገጠመው ፍርሀቱ ተወግዶ ነበር። ማይክል አንጄሎ ወደ ፍሎሬንስ ተመለስ። ነገር ግን ከአዲሱ ሳናቫሮላ መንግስት ምንም አይነት ስራ አላገኘም። ከዚያም ወደ ሚዲቺ በመሄድ ስራ ከዚያ ጀመረ። .[16]

ፍሎሬንስ ባሳለፈው ግማሽ አመት ውስጥ ሁለት ትንንሽ ቅርጾችን ቀርጿል የመጀመሪያው መጥምቁ ዮሀንስ በልጅነቱ እና ሁለተኛው ደግሞ ኩፒድ የተኛው የፍቅር አምላክ የሚባሉ ነበሩ። ኮንዲቪ እንደሚለው ለሎሬንዞ ዲ ፒዬሬ ዲ ሜዲቺ ነበር መጥምቁ ዮሀንስን የቀረጸው። ነገር ግን ሌላኛውን «ተቀብሮ እንደተገኘ አሮጌ አስመስለው» ጥሩ ዋጋ እንዲያወጣልን በማለት ይነግረዋል። ከዚያም እንደተባለው ያደርግርጋል ። ከዚያም ቅርጹ እንደ አሮጌ ተደርጎ በሶስተኛ ሰው አማካኝነት ወደ ሮማ በመላክ ከዚያ ገዢ ተገኝቶ ይሸጣል። ሁለቱም ሎሬንዞ እና ማይክል አንጄሎ ክፉኛ ከተታለሉ በኋላ ራፋኤል ሪያሪዮ ቅርጹን ከሎሬንዞ የገዛው ሰው እንደተባለው አሮጌ እንዳልሆነ አወቀ። ነገር ግን በቅርጹ ጥራት እና ውበት በመማረኩ ቀራጩን ወደ ሮማ እንዲመጣ ጋበዘው። [17] [d] ይህ ያልታሰበና የተቃና እድል ቅርጹን ከወግ አጥባቂዎች ፍሎሬንታውያን ውጭ ገዢ እና ተቀባይ ማግኘቱ ማይክል አንጄሎን ጥሪውን ተቀብሎ ወደ ሮማ ለመሄድ አበቃው ።

ማይክል አንጄሎ ሮማ በ25 ጁን 1496[18] ገባ እድሜውም 21 ነበር። በ 4 ጁላይ በዚያው አመት ከራፋኤል ሪያሪዮ ጋር በመዋዋል ስራ ጀመረ ። ስራውም ሮማውያን ባከስ የወይን አምላክ ብለው የሚጠሩት ነበር ። ነገር ግን ሀውልቱ ተሰርቶ ሲጠናቀቅ ካርዲናሉ ስላልወደዱት በወቅቱ የባንክ ሰራተኛ የነበረ ጃኮፖ የሚባል ሰው ለግቢው አታክልት ማጌጫ ገዛው ። በኖቬምበር 1497 የፈረንሳይ አምባሳደር ጋር አንድ ውል ተዋዋለ ይህም ውል እጅግ በጣም ውብ እና ድንቅ የሆነው ፒየታ (ሐዘን) የሚባለው ነበር ። ውሉ የተፈረመው በኦገስት ወር በሚቀጥለው አመት ነበር ። በወቅቱ የተሰጠውም አስተያየት በእውነቱ ይህ ተአምር ነው ምንም ቅርጽ ከሌለው እምነ በረድ ድንጋይ ይህን የመሰለ ቅርጽ መውጣቱ ፤ ተፈጥሮ እንኳን እንዲህ ያለውን መስራት አይቻላትም የሚል ነበር ። 
ማይክል አንጄሎ በሮም ውስጥ ሳንታ ማርያ ዲ ሎሬቶ አካባቢ ይኖር ነበር። እዚህም በሚኖርበት አካባቢ ቪቶሪያ ኮሎና ማርኩዚዬ ፔስካራ እና ገጣሚ ሴት ጋር ፍቅር ይዞት እንደነበር ይነገራል ። ይኖርበት የነበረው ቤት በ1874 ተደምስሷል ቀሪው አንዳንድ ተርፈው የነበሩ እና በአዲሱ ባለቤት ተቀምጠው የነበሩ እቃዎችም እንደገና በ1930 የመደምሰስ እጣ ገጥሟቸዋል። 
ዛሬ አዲስ የተሰራ የማይክል አንጄሎ ቤት የሚባል በጃኒኮሎ ኮረብታማ ቦታ ላይ ይገኛል ። በዚሁ ዘመን ነበር ማይክል አንጄሎ ላኩን እና ልጆቹ የሚባለውን ሀውልት ቀርጾ የጨረሰው ዛሬ ቅርጹ በቫቲካን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሮም ይገኛል[19]

ማይክል አንጄሎ ወደ ፍሎሬንስ ተመለሰ ከ1499–1501 ነገሮች በሪፐብሊክ አስተዳደሩ በኩል በጣም ተቀያይረዋል። በተለይም ጸረ እንደገና መወለድ ተቃዋሚ የነበረው ቄስ እና የፍሎሬንስ አስተዳዳሪ የነበረው ጂሮላሞ ሳቮናሮላ ( በ1498 ከተገደለ በኋላ ) እና የጎንፋላኖሪ ፒየር ሶዴሪኒ ከተነሳ በኋላ ። በወቅቱ አስተዳዳሪ የነበረው ጊልድ ዉል አንድ ጥያቄ ለማይክል አንጄሎ አቀረበለት ጥያቄውም አንድ ከአርባ አመት በፊት በአጎስቲኖ ዲ ዱቺዮ ተጀምሮ ያላለቀ ቅርጽ ነበር ። ቅርጹም እጅግ በጣም ግዙፍ የሆነ ለፍሮንቴናውያን የነጻነት ምልክት የነበረው ጎሊያድን በወንጭፍ መትቶ የገደለውን የዳዊት ሐውልት ነበር ። ቅርጹም ሊቀመጥ የነበረው ፒያዛ ዴላ ሲኞሪያ ሲሆን ይህ ቦታ የሚገኘው ከፓሎዞ ቪኪዮ ፊት ለፊት ነው ። ማይክል አንጄሎም የቀረበለትን ጥያቄ በሚገባ ሁኔታ ከተቀበለ በኋላ የዳዊትን ሀውልት ቅርጽ ከስራዎቹ ሁሉ በጣም ከሚወደዱት አንዱ የሆነውን ጨርሶ በ1504 አስረከበ ። ይህ አስደናቂ ቅርጽ ከአንድ ወጥ እምነበረድ ከካራራ ካብ ከወጣ እምነበረድ የተሰራ ሲሆን ቀደም ሲል በሌላ ሀውልት ቀራጭ ተጀምሮ ያልተጨረሰ ሲሆን ማይክል አንጄሎ ምን ያህል ከፍተኛ ችሎታ እና አስተሳሰብ እንዳለው ያስመሰከረበት ሐውልት ነው ። 
በዚሁ ዘመን ማይክል አንጄሎ የቅዱሳን ቤተሰብ እና ቅዱስ ዮሀንስ በሌላ ስሙ ዶኒ ቶንዶ ወይም ቅዱስ ቤተሰብ የሚባለውን ስእል ሰርቶ ጨርሷል ። ይህ ስእል የተሰራው ለአንጄሎ ዶኒ እና ማዳሌና ስቱሮዚ ጋብቻ ስጦታ ነው በ17ኛው ክፍለ ዘመንም ትሪቡን ኡፉዚ በሚባል ክፍል ውስጥ ተስቅሎ ይታይ ነበር ። ምናልባትም እመቤተ ማርያም እና ልጇንም ከመጥምቁ ዮሀንስ ጋር በሌላ ስሙ የማንቼስተር እመቤቴ ማርያም የሚባለውንም ስእል በዚሁ ዘመን ሰርቶ ጨርሷል ። ይህ ስእል በአሁኑ ጊዜ በለንደን ከተማ ብሄራው ጋሌሪ ሙዚየም ውስጥ ይገኛል።

በ1505 ማይክል አንጄሎ በአዲሱ ጳጳጽ ጁሊዬስ 2ኛው ጋባዥነት ወደ ሮም ተመለሰ ። ከዚያም አንድ ውል ተዋዋለ ውሉም ለጳጳጹ መቀበሪያ ለማሰናዳት ነበር ። ክፍያውም በቀጥታ ከፓፓጹ ነበር ። ማይክል አንጄሎ ይህን ስራ ብዙ ጊዜ እያቋረጠ ሌሎች ስራዎችን ያከናውን ነበር ። በዚህም የተነሳ ማይክል አንጄሎ በዚህ የመቃብር ስራ ላይ 40 አመት ፈጅቷል ። በመቃብሩ መካከል የሚገኘው የሙሴ ሀውልት ማይክል አንጄሎ እንደፈለገው አልተፈጸመም ። ዛሬ ይህ የሙሴ ሀውልት በቅዱስ ጴጥሮስ ቤተ ክርስቲያን በቪንኮሊ ሮማ ቫቲካን ውስጥ ይገኛል ። በዚያው ዘመን ሌላ ውል ተዋዋለ ውሉም በሲስቲኒ ቤተክርስቲያን ጣራ ላይ ስእል ለመስራት ነበር ። ይህን ስእል ስርቶ ለመጨረስ አራት አመት ፈጅቶበታል (ከ1508 እስከ 1512 ) ማይክል አንጄሎ እንዳለው ብራማንቴ እና ራፋኤል ጳጳጹን አሳምነው ማይክል አንጄሎ ብዙ በማይወደው እና ብዙ ልምድ በሌለው የጄሶ ላይ ስእል ስራ ውል እንዲዋዋል አደረጉት ። ይህንንም ያደረጉት በወቅት በዚያን ዘመን ራፋኤል በጄሶ የስእል ስራ ከፍተኛ ከሚባለው ደረጃ ላይ ስለነበር በማይክል አንጄሎ ስቃይ እና ውድቀት ራሳቸውን ትልቅ አድርገው ለማሳየት ነበር ። ነገር ግን ይህን ታሪክ ዘመናዊ የታሪክ ተመራማሪዎች ይህን የሚያሳይ መረጃ ባለማግኘታቸው ታሪኩን አይቀበሉትም ። እንዲያውም ይህ የማይክል አንጄሎ አመለካከት ሊሆን ይችላል ይላሉ ። 
ማይክል አንጄሎ በመጀመሪያ የተዋዋለው የ12 ቱን ደቀ መዝሙሮች ስእል ለመስራት ነበር ። ነገር ግን ማይክል አንጄሎ በጣም የረቀቀ እና የተወሳሰበ ስእል እንዲሰራ አበክሮ ተከራከረ ለምሳሌ ዘፍጥረትን ያካተተ እንዲሁም የሰውን ልጅ ውድቀት እና በፈጣሪው የተገባለትን ቃል ኪዳን ከልጅ ልጅህ ተወልጄ ነጻ አውጣሀለሁ የሚለውን የኢየሱስ ታሪክ እና እንዲሁም ስለ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን እምነት በስፊው እንዲያካትት ነበር ። ስእሉ በአጠቃላይ 300 ሰዎችን ያካተተ ሲሆን መሀሉም ዘጠኝ ክፍሎች አሉት ዘፍጥረትን ያካተቱ በሶስት ምድብ የተከፈሉ እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ሲፈጥር ፡ እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ሲፈጥር እና የግዚአብሐርን ቃል እንዴት መጠበቅ እንዳቃታቸው እና አህዛብን የሚወክለው ኖሕ እና ቤተስቡ ናቸው። የቤተክርስቲያኑን ጣራ መጋጠሚያዎች ላይ ደግሞ አስራ ሁለት ወንድ እና ሴት ነቢዮች የጌታችን የመዲሀኒታችን ኢየሱስ መምጣት ሲስብኩ ተስሏል ። ከእነዚህም ሰባት የእስራኤል ነቢያት ሲሆኑ አምስቱ ሴቶች ደግሞ ከሌላው አለም የተወከሉ ነበሩ ። በጣም ከሚወደዱት እና ከሚደነቁት እነዚህ ስእሎች መሀከል የአዳም አፈጣጠር እና ፡ አዳም እና ሔዋን በገነት የአትክልት ስፍራ ውስጥ የጥፋት ውሀ ፡ ነቢዮ ኢሳይያስ እና የሲቢል ነቢያት እና እንዲሁም የኢየሱስ ክርስቶስ ዘረ ሐረግ ናቸው ።

በ 1513 ጳጳጽ ጁሊየስ 2ኛው ሞቱ ። እሳቸውን የተካው ጳጳጽ ሌዮ ኤክስ ይባላል ። ማይክል አንጄሎ ክሜዲቺ ጋር አንድ ውል ተዋዋለ ውሉም በፍሎሬንስ የሚገኘውን የባሴሊካን ሳን ሎሬንዞ ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊቱን አፍርሶ የተለያዩ ቅርጾች እና ሐውልቶች ጨምሮ በተሻለ ሁኔታ ለመስራት ነበር ። ማይክል አንጄሎም በሀሳቡ ወዲያውኑ ተስማማ ። ከዚያም ለሶስት አመታት ለስራው የሚያስፈልገውን የስእል ንድፍ እና ለሐውልቶቹም የሚያስፈልገውን ንድፍ እና እቅድ አውጥቶ በአካባቢውም ለሐውልቶቹ ቅርጾች የሚያስፈልግውን የእምነ በረድ ካብ በፒዬትርራሳንታ ቁፋሮ ማካሄድ ካስጀመረ በኋላ በገንዘብ እጦት ምክንያት ስራው ተቋረጠ ። ማይክል አንጄሎ በህይወት ዘመኑ በጣም የተማረረበት የስራ ውል ነበር። ቤተ ክርስቲያኑም ምንም ለውጥ ሳይደረግለት እስከ ዛሬ ድረስ አለ ። 
ሜዲችም ቀደም ብለው በሰረዙት የስራ ውል ሳያፍሩ ማይክል አንጄሎን ሌላ ስራ እንዲሰራላቸው ጠየቁት ። በዚህ ጊዜ ደግሞ ለቤተሰባቸው የሚሆን የመቃብር ቤት በባሴሊካ ሳን ሎሬንዞ እንዲሰራላቸው። ይህ ስራ ከ 1520 እስከ 1530 ማይክል አንጄሎ ብዙ ጊዜ ሰርቶበታል ነገር ግን ስራው እስከ አሁን አልተፈጸመም ። ነገር ግን ማይክል አንጄሎ ምን ያህል ሐውልትን የመቅረጽ እና የምህንድስና ችሎታ እንዳለው የሚያሳይ ትልቅ ማስረጃ ነው ። ማይክል አንጄሎ ሐውልቶቹን እና የህንጻውን የውስጥ ፕላን በማውጣት ምን ያህል ከፍተኛ እና ድንቅ የሆነ ችሎታ እንዳለው አስመስክሯል ። እንደዘበት ብዙ ያስገረመው መቃብር የሁለቱ የማይታዩ ሜዲቺ በወጣትነታቸው የሞቱ የሎሬንዞ ll ማግኒፊኮ ልጅ እና የልጅ ልጅ እና እራሱ ሎሬንዞ ማግኒፊኮ የተቀበሩበት ያልተጨረሰ እና ብዙ የማያምር ባንድ ጎኑ በኩል ከቤተ ክርስቲያኑ ጋር የሚዋሰን ነው ። በመጀመሪያ እንደታቀደው እመሬት ላይ የቆመ ቅርጽ የለውም ። 

በ 1527 የፍሎሬንስ ዜጎች በሮም አስተዳደር በመደገፍ ሜዲቺን ከስልጣን አስወግደው ሪፐብሊካን ስልጣን ላይ ወጡ። ከተማውን በመክበብ የትርምስ ጊዜ ሆነ ። ማይክል አንጄሎም የሚወዳትን ፍሎሬንስ በመርዳት ከ1528 እስከ 1529 በወታዳራዊ ተቋሞች ውስጥ በመስራት አገልግሏል ። በ 1530 የከተማዋ በሜዲቺ አስተዳደር ውስጥ ወደቀ ። ሜዲቺም ስልጣን ላይ ወጡ በሙሉ ስምምነት ከጨካኝ እና ጨቋኝ ከሆነው ዱካል ሜዲቺ ጋር ። ማይክል አንጄሎ ፍሎሬንስን በ 1530 ለቆ ወጣ ። የሜዲቺንም ቤተ ክርስቲያን እንዲጨርስ ስራውን ለሌላ ስው ስጥቶ ። ከአመታት በኋላም የማይክል አንጄሎ አስከሬን ከሮም ወደ ባሴሊካ ዲ ሳንታ ክሮሼ ለቀብር መቶ ነበር። ነገር ግን በማይክል አንጄሎ ኑዛዜ መሰረት እጅግ በጣም በሚወዳት ቱስካኒ የመጨረሻ ማረፊያው ሆነ

በጄሶ ላይ የፍርድ ቀን የተባለው የግርግዳ ላይ ስእሉ የተሰራው በሲስቲኒ ቤተ ክርስቲያን ከመንበሩ በስተ ጀርባ በኩል ነው። ይህ ውል የተፈጸመው ከጳጳጽ ክሌሜንቴ 8ኛው ጋር ነበር። ነገር ግን ጳጳጹ ውሉን በተዋዋሉ በጥቂት ጊዜ ውስጥ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ። ፓውሎስ 3ኛው የዚህ ስራ ተቆጣጣሪ ነበሩ ማይክል አንጄሎም ስራውን ጀምሮ እስኪፈጽም ድረስ። ማይክል አንጄሎ በዚህ ስራ ላይ ከ 1534 እስከ 1541 ለሰባት አመት ሰርቷል። ስራው በጣም ግዙፍ እና ከመንበሩ በስተጀርባ ያለውን ገድግዳ ሙሉ በሙሉ ከጭፍ እስከ ጫፍ ያካተተ ነበር። የመጨረሻው የፍርድ ቀን የሚባለው ስእል የጌታችን የመድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግመኛ ወደ ምድር ከጻድቃን ጋር ለፍርድ ቀን እንዴት እንደሚመጣ ለማሳየት የተሰራ ስእል ነው። 
ስእሉ ተስርቶ እንዳለቀ የብዙዎቹ ስእሎች ራቁታቸውን መሆን ጳጳጹ በሚጸልዩበት ቤተ ክርስቲያን በጣም ነውር እና አሳፋሪ ከምንሰራው ስራ ጋር የማይሄድ ነው በማለት ጳጳጽ ካራፋ እና ሞንሲኞር ሴሪኒኒ (የማንቱአ አምባሳደር) ስእሉ እንዲጠፋ ወይም ሀፍረተ ስጋቸው እንዲሸፈን ሲሉ በከፍተኛ ደረጃ ተቃወሙ። ነገር ግን በወቅቱ የነበሩት ፓፓጽ ስእሉ አይጠፋም ወይም አይቀየርም ሲሉ ክፉኛ ተከራከሩ። 

ማይክል አንጄሎ ከሞተ በኋላ ግን ሀፍረተ ስጋቸውን ለመሸፈን ተስማሙ። ከዚያም የማይክል አንጄሎ ተማሪ ከነበረው ዳኒኤሌ ዳ ቮልቴራ ጋር ውል በመዋዋል ሀፍረተ ስጋቸውን በጨርቅ መሸፈን ተያያዙት። በ 1993 ስእሎቹ እድሳት ሲደረግላችው ወግ አጥባቂዎች በጣም በመከራከር ቀደም ሲል ዳኒኤሌ ሸፍኗቸው የነበሩትን ስእሎች ቀድሞ ማይክል አንጄሎ እንደሰራቸው ማስመለስ ችለዋል። አንዳንዶቹንም ለታሪክ በማለት ጨርቅ እንደለበሱ ትተዋቸዋል። የማይክል አንጄሎ ስራዎች አሳፋሪ በሚል በሌላ ሰአሊ በመበላሸታቸው ዋናውን የማይክል አንጄሎ ዋና ስራ በማንም ያልተነካውን በማርቼሎ ቬኑስቲ የተሰራውን በካፖዲሞንቴ ሙዚየም ውስጥ ኔፕልስ ማየት ይቻላል። 
ሳንሱር ሁልጊዜ ማይክል አንጄሎን ይከታተለው ነበር ይባላል። ማይክል አንጄሎ በአንድ ወቅት የሚያሳፍር ስራ ፈጣሪ የሚል ስም ተሰጥቶት ነበር። ብዙ የማይወደደው የአሳማ ነገር በመባል የሚታወቀው የጸረ እንደገና መወለድ እንቅስቃሴ በዘመኑ የነበሩትን ቅርጽ እና ስእሎች በሙሉ ሀፍረተ ስጋ መሸፈን የተጀመረው በማይክል አንጄሎ ስራዎች ነው። ማስረጃ ለመስጠት ያህል የክርስቶስ ዴላ ሚንሬቫ ቤተክርስቲያን ሳንታ ማሪያ ሶፕራ ሚንሬቫ ሮም በጨርቅ እንዲሸፈኑ ተደርጓል እስከ ዛሬ ድረስ። ሌላው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሐውልት በልጅነቱ እራቁቱን የብሩጌስ ማዶና ። በቤልጂየም የሚገኘው የእመቤታችን ቤተ ክርስቲያን ለብዙ ዘመን ሀውልቱ በጨርቅ ተሸፍኖ ይኖር ነበር። 
በለንደን በካስት ኮርትስ (ቪክቶሪያ እና አልበርት ሙዚየም ) ውስጥ የዳዊት ሀውልት ቅጂ ከበስተጀርባው ቅጠል በሳጥን ውስጥ ተደርጎ ይኖራል ምክንያቱም የንጉሱ ቤተሰቦች ሊያዩት ከመጡ እራቁቱን እንዳያዩት ለመሸፈን ተብሎ ነው። በ1546 ማይክል አንጄሎ የቅዱስ ፔጥሮስ ቤተክርስቲያን መሀንዲስ ሆኖ ተቀጠረ ። ከዚያም የቤተ ክርስቲያኑን አናት ግማሽ ክብ ንድፍ አውጥቶ ስራው ተጀመረ በዚያን ጊዜም ከፍተኛ ስጋት ነበር። ስጋቱም ስራው ከመጠናቀቁ በፊት ማይክል አንጄሎ ይሞታል የሚል ፍርሀት ነበር። ነገር ግን ግማሽ ስራው እንደተገባደደ ስራውን እንደሚፈጽሙት አረጋገጡ።

በዲሴምበር 7 2007 የማይክል አንጄሎ በቀይ ቾክ የተሰራ የቅዱስ ጴጥሮስ ባሴሊካ ንድፍ ተገኘ። በ 1564 ከመሞቱ በፊት። የተገኘውም በቫቲካን ግምጃ ቤት ውስጥ ነው። በጣም የሚያስገርም ነገር ነበር። ማይክል አንጄሎ ጥሩ ያልሆኑ የሚላቸውን ስራዎቹን በሙሉ በእሳት አቃጥሏቸዋል። የተገኘው ንድፍ ከቋሚዎቹ የአንዱ ሲሆን የቅዱስ ጴጥሮ ኩፖላ ድረም በመባል ይታወቃል። [20]

ማይክል አንጄሎ በሌሎች ሰዎች ተጀምረው ባላለቁ በብዙ ስራዎች ላይ ተሳትፏል። በጉልህ ከሚታዩት ለምሳሌ የቅዱስ ጴጥሮስ ባሴሊካ እና ካምፒዶጊሊዮ ፕላናቸውን ያወጣው ማይክል አንጄሎ ነው። የሮማን ካፒቶል ሂልም ንድፍ ያወጣው ማይክል አንጄሎ ነበር። ቅርጹም ሮምቦይድ ነበር ከአራት ማእዘን ይልቅ ይህንንም ያደረገበት ምክንያት በቦታው ጥበት የተነሳ የተመልካቹን አይን ለማታለል ነው። ሌላው የህንጻ ስራዎቹ በፍሎሬንስ ሳን ሎሬንዞ እና የሎውሬንቲን ቤተ መጻህፍት እና ለውትድርና የሚያገለግሉ ምሽጎች እና ማማዎች ናቸው። በሮም ከሰራቸው ደግሞ የቅዱስ ጴትሮስ ቤተ ክርስቲያን ፤ ፓላዞ ፋርኔሴ ፤ ሳን ጆቫኒ ዴዪ ፊዮሬንቴኒ ፤ ዘ ስፎዛ ቤተክርስቲያን (ካፔላ ስፎርዛ) በ ባሴሊካ ዲ ሳንታ ማሪያ ማጆሬ ፤ ፖርታ ፒያ እና ሳንታ ማሪያ ዴጂሊ አንጄሊ ናቸው።

በ 1530 ማይክል አንጄሎ የላውሬንቲን መጽህፍት ቤት በፍሎሬንስ ንድፍ አወጣ። መጻህፍት ቤቱ ከሴንት ሎሬንዞ ቤተ ክርስቲያን ጋር የተያያዘ ነው። በዚህ ስራው ላይ ፒላስተርስ የሚባል አዲስ ዘዴዎችን በመጠቀም። ሌላው ከስር ከስተው ወደ ላይ እየወፈሩ የሚሄዱ ዘዴዎችን በመጠቀም ። ደረጃዎችን ደግሞ አራት ማእዘን እና ግማሽ ክብ አድርጎ በመፍጠር ነበር።

ማይክል አንጄሎ የሜዲቺን ቤተክርስቲያን ንድፍ አወጣ። በሜዲቺ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተለያዩ ሐውልቶች አሉ ለተለያዩ የሜዲቺ ቤተሰቦች የተሰሩ። ማይክል አንጄሎ ስራውን በሙሉ አልጨረሰውም። የሱ ሰራተኞች የነበሩ በኋላ ጨርሰውታል። ሎሬንዞ ዘ ማግንፊሰንት የተቀበረው ከመግቢያው ፊት ለፊት ነው። የእመቤቴ ማርያም እና ልጇ እንዲሁም የሜዲቺ አለቃ የሆኑት የቅዱስ ኮስማስ እና ዳሚያን ከመቃብሩ በላይ በሐውልት ተቀርጸዋል። የእመቤቴ ማርያም እና ልጇ ሐውልትም የተቀረጸው በማይክል አንጄሎ ነው።

ማይክል አንጄሎ ብዙ ጊዜ እብሪት ለሌሎች ያሳይ ነበር እና በራሱም ብዙ አይደሰትም ነበር። ኪነ ጥበብ ከባህል እና ከውስጥ የሚመነጭ ስሜት እንደሆን ይናገር ነበር። በወቅቱ ተፎካካሪው ከነበረው ከሌዎናርዶ ዳቬንቺ በተቃራኒው። ማይክል አንጄሎ ተፈጥሮን እንደ ጠላት ነበር የሚያየው ስለዚህም መሸነፍ አለበት ይል ነበር። የሚሰራቸው ስራዎች በሙሉ እያንዳንዳቸው በየራሳቸው መንገድ አስደናቂ እና አስገራሚ ነበሩ በዘመኑ ከሚታዩት ሐውልቶች ። ማይክል አንጄሎ የሐውልት ቀራጭ ስራ የሚፈለገውን ቅርጽ ከ እምነበረዱ ውስጥ ማላቀቅ ነው ይል ነበር። ማይክል አንጄሎ እያንዳንዱ እምነበረድ በውስጡ ቅርጽ አለ ብሎ ይል ነበር የቀራጭም ስራ የማያስፈልገውን ቅርጹን የሸፈነውን እና የቅርጹ አካል ያልሆነውን እምነበረድ ከላዩ ላይ በመዶሻ እና በመሮ መቅረፍ ወይም ማለያየት ነው ይል ነበር። በወቅቱ ይነገር ከነበረው አፈ ታሪክ የማይክል አንጄሎ ችሎታ በተለይም ሐውልት በመቅረጽ ላይ በወቅቱ በጣም የተወደደ ነበር። 
ሎሬንዞ ደ ሚዲቺ በማይክል አንጄሎ ትንሽ ገንዘብ ሊሰራ ፈለገ።

ማይክል አንጄሎንም የፍቅር አምላክ የሚባለውን ሐውልት እንዲሰራ እና አሮጌ እንዲያስመስለው ጠየቀው። ሎሬንዞ ለማይክል አንጄሎ ለፍቅር አምላክ ለሚባለው ቅርጽ 30 ዱካት ከፈለው። ነገር ግን ሎሬንዞ ቅርጹን አሮጌ ቅርጽ ለሚሸጡ ሰዎች በ 200 ዱካት ሸጠው። ቅርጹን የገዛው ካርዲናል ራፋኤል ሪያሪዮ ቅርጹ አሮጌ መሆኑን በጣም ስለተጠራጠረ የቅርጹን ታሪክ የሚያጠናለት ሰው ቀጠረ። ሰውየውም ማይክል አንጄሎን ካገኘው በኋላ የፍቅር አምላክ የሚባልውን ሐውልት በወረቀት ላይ ንድፉን እንዲሰራ እና እንዲያሳየው ጠየቀው ማይክል አንጄሎም ስርቶ አሳየው። 
በዚህን ጊዜ ሰውየው ከአንተ የፍቅር አምላክ የሚባለውን ቅርጽ በ 30 ዱካትስ ገዝቶ በ200 ዱካትስ እንደሸጠው ነገረው። ማይክል አንጄሎም ቅርጹን እሱ እንደቀረጸው ተናዘዘ ነገር ግን ይህን ያህል መታለሉን አላወቀም ነበር። እውነቱ ከወጣ በኋላ ካርዲናሉ ቅርጹን የገዛው ማይክል አንጄሎ በእርግጥም ልዩ ችሎታ እንዳለው ካረገገጠ በኋላ ባከስ ወይም የወይን አምላክ የሚባለውን እንዲሰራለት ውል ተዋዋሉ። ሌላው ሰለ ማይክል አንጄሎ የሚነገረው ታሪክ ሙሴ የሚባለውን ሐውልት ሰርቶ ሲጨርስ ይቀርጽበት በነበረው መዶሻ የሙሴን ሀውልት ጉልበቱን በመዶሻው በመምታት “ለምን አታናግረኝም” ብሎ እንደመታው ይነገራል። በግል ህይወቱ ማይክል አንጄሎ በጣም ቁጥብ ነበር ። ተማሪው ለነበረውአስካኒዮ ኮንዲቪ “ምንም ሀብታም ብሆን የኖርኩት ግን እንደ አንድ ድሀ ነው ብሎት ነበር።[21 ] ኮንዲቪ እንዳለው ለምግብ እና ለመጠጥ ብዙም ግድ አልነበረውም። የሚበላው ሲርበው ብቻ እንጂ በምግብ ለመደስት ብሎ በልቶ አያውቅም። [21] ወደ አልጋውም ሲሄድ እስከ ልብሱ እና ጫማው ይተኛ ነበር።[21] ይህ ጸባዩ በብዙዎች ዘንድ የተወደደ አልነበረም። ይህ ጸባዩ በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅ እንዳይሆን አድርጎታል። ታሪኩን የጻፈው ፓኦሎ ጂኦቪዮ እንዳለው “ተፈጥሮው በጣም አስቸጋሪ እና ግልጽ ያልሆነ ነው። የቤት ውስጥ አያያዙም ባህሪውም ቆሻሻ ነበር። በዚህም የተነሳ ብዙ ተከታይ አልነበረውም ይላል። [22] ማይክል አንጄሎ ግን ግድ አልነበረውም። በተፈጥሮው ከሰው ጋር ብዙ መገናኘት ስለማይወድ። ብዙዎችም ጉደኛው እና አስገራሚው ይሉት ነበር። ማይክል አንጄሎ እራሱን ከሰዎች አግልሎ ነበር ህይወቱን የኖረው። [23]

የማይክል አንጄሎ መሰረታዊ የኪነ ጥበብ ስራ መስረት ያደረገው የወንድን ጡንቻማ አካል በ መውደድ ላይ ነው። ወደዚህም የተሳበው ተፈጥሮን በጣም ስለሚወድ እና ስሜታዊ ስለነበር ነው። በከፊል የእንደገና መወለድ አገላለጽ እና አምልኮ ነበር። የማይክል አንጄሎም የስራ ውጤቶች ተፈጥሮን መውደዱን በግልጽ የሚያንጸባርቁ ነበሩ [24] የሚቀርጻቸውም ቅርጾች ፍቅርን እና ተፈጥሮን የሚገልጹት በኒዮፕላቶኒያን እና በእርቃነ ስጋ ላይ ያተኮረ ነበር። ለምሳሌ ቺቺኖ ዴዪ ብራቺ በተዋወቁ በአመቱ በ 1543 ከዚህ አለም በመለየቱ አርባ ስምንት የሀዘን እንጉርጉሮ ግጥም ጽፎለታል። አንዳንድ ሰዎች ይህን በመመልከት ግንኙነታቸው ከጓደኝነት በላይ ነበር ይላሉ። ሌሎች ሰዎች ደግሞ የፕላቶኒያን ፍቅር መግለጫ መንገድ ነበር ይሉታል። በወቅቱ ሀፍረት የሌለበት ግጥም ለሚወዱት ሰው መግጠም እውነተኛ የፍቅር መግለጫ ነበር ይላሉ። 

በ 16 ኛው ክፍለ ዘመን የነበረው የሞያ ፍቅር ከዛሬው የሞያ ፍቅር በጣም የበለጠ ነበር። [26] በወቅቱ የነበሩ አንዳንድ ወሮ በላዎችም ይህንን አጋጣሚ ገንዘብ ለማግኛ ተጠቅመውበታል። ፌቦ ዲ ፖጂዮ በ 1532 ማይክል አንጄሎ የጻፈለትን የፍቅር ደብዳቤ ይዞ ይዞር ነበር። ቀደም ሲል ጌራርዶ ፔሪኒ በ 1522 ያለ ሀፍረት ዘርፎታል። ማይክል አንጄሎ ራሱን ከሰው ያገል ነበር። አንድ የጓደኛው ሰራተኛ የነበረ ኒኮላ ኳራቴሲ የሚባል ሰው ልጁን ከማይክል አንጄሎ ጋር ተማሪ ሆኖ እንዲሰራ ሲጠይቀው አልጋም ላይ ጥሩ ነው ብሎት ነበር። ማይክል አንጄሎ ግን ወዲያውኑ ግብረ ሰዶም ለእሳት ይዳርጋል ብሎ መልስ ሰጥቶታል። ከፍተኛው የፍቅር ደብዳቤ ተጽፎ የተገኘው ለቶማሶ ዴዪ ካቫሌሪ ነው ( 1509–1587) በወቅቱ እድሜው 23 አመት ሲሆነው ነው ከማይክል አንጄሎ ጋር የተገናኙት በ1532 ማይክል አንጄሎ 57 አመቱ ነበር ። ካቫሌሪ በእድሜ ከገፉ ሰዎች ጋር ይውል ነበር። ፍቅራችሁን እመልሳለሁ እያለም ይምል ነበር። እንዳንተ የወደድኩት ሰው የለም እያለም ይናገር ነበር። ጓደኝነትህንም ከማንም በላይ እፈልገዋለሁ እያለም ይናገር ነበር። ካቫሌሪም ማይክል አንጄሎ እስከሞተበት ጊዜ ድረስ ጓደኝነታቸው የጸና ነበር። ማይክል አንጄሎም ከሶስት መቶ በላይ ግጥሞች እና እንጉርጉሮ ጽፎለታል። አንዳንዶች እንደሚሉት ግን ይህ ፍጹም ንጹህ የሆነ ወንድማዊ የፕላቶኒያን ፍቅር መግለጫ ነው ይላሉ። እንዲያውም ማይክል አንጄሎ ካቫሌሪ ልጅ ቢኖረው ወስዶ ለማሳደግ ይፈልግ ነበር።[27] ነገር ግን በወቅቱ ፍቅራቸው በግልጽ የሚታይ ነበር። ማይክል አንጄሎ ለግጥም እና ለቪቶሪያ ኮሎና ለምትባል ሴት ከፍተኛ ፍቅር ነበረው። የተገናኙት ሮም ውስጥ በ 1536 ወይም በ 1538 ነበር። ሲገናኙም ቪቶሪያ በ አርባዎቹ አመታት ውስጥ ነበረች። እስከሞተችበት ጊዜም ድረስ ግጥም ይጻጻፉ ነበር። ግንኙነታቸው ምን እንደነበር ለመገመት አስቸጋሪ ነበር። ኮንዲቪ ግን የመነኩሴ ንጹህ ፍቅር ነው ይል ነበር። [28] ነገር ግን በግጥሞቹ እና በሰራቸው ስራዎቹ አስተሳሰቡን መገመት እንችላለን[29]

The asteroid 3001 Michelangelo and a crater on the planet Mercury were named after Michelangelo. The character Michelangelo from Teenage Mutant Ninja Turtles was named after Michelangelo.

The 1965 film The Agony and the Ecstasy features the story of Michelangelo and his travails in painting the Sistine Chapel. He is portrayed in the film by Charlton Heston.




#Article 371: ፔትሮሊየም (338 words)


ፔትሮሊየም ወይም ክሩድ ዘይት በተፈጥሮ ከመሬት በታች የሚገኝ የተቀጣጣይነት ጸባይ ያለው ፈሳሽ ነው። የተገነባው ከውስብስብ የሀይድሮካርቦን እና ሌሎች ውህዶች ጥምረት ነው።

የ«ክሩድ» (እንግሊዝኛ፦ crude ማለት «ጥሬ») ዘይት (የድፍድፍ ነዳጅ ዘይት) በዓለም ውስጥ በብዛት የሚገዛና የሚሸጥ ፤ ጠቀሜታውም ከሃምሳ በመቶ በላይ የሆነውን በዓለም ላይ የሚገኝ የቤትና የመስሪያ ቤት፣ የፋብሪካና የማምረቻ ቦታዎችን፣ እንዲሁም የመንቀሳቀሻና የመጓጓዣ ንብረቶችን እንዲሠሩ የሚያደርግ ልዩ የተፈጥሮ የማዕድን ዘይት ነው። ከነዚህም የተለያዩ ግልጋሎቶች መካከል ፤ እንደየተጥቃሚው ፍላጎት ፣ከምግብ ማብሰያ ኬሮሲን እስከ መኪና ቤንዚን እና የጭነት መኪና ናፍጣ እንዲሁም የአውሮፕላን ማብረሪያ ልዩ ቤንዚን፣ የሞተር ዘይትና የፋብሪካ ማሺን ማንቀሳቀሻ ጠቀሜታው ያለውና ተፈላጊነትም ለሁልጊዜ ያለው ነው።
  
ክሩድ ዘይት ከመሬት ውስጥ ሲወጣ የተለያየ አይነት ጥራት ይዞ ነው የሚገኘው ። ክሩድ ዘይትን ከኮሞዲቲ መለዋወጫ ቦታ ላይ ለመግዛት በሚፈለግበት ጊዜ የጥራቱን ዓይነት በስሙ ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል።  ምክንያቱም የዋጋው ሁኔታ በዘይቱ ጥራት ይለያያል። ይህ ክሩድ ዘይት በሁለት የመለያያ ዘዴዎች ይመደባል።
 
አንደኛው ላይት ኤንድ ስዊት ፤ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ሄቪይ ኤንድ ሳዎር ይባላል።

ስሙ በእንግሊዘኛ ሲሆን የሚነገደውም በዚሁ ስም ነው - የመገበያያው ስም (በሲምቦል  (የአብሪቬሽን)) ስም ቢኖረውም ሁሉንም በእንግሊዘኛው ቃላት ማንበብ ስለ ክሩድ ዘይቱ አነጋገድ ሁኔታ ለማስታወስ ይቀላል።

የክሩድ ዘይት በሁለት ዓይነት የጥራት ልዩነት መደብ የተደረገበት ዋንኛው ምክንያት የዘይቱ ውፍረትና የሠልፈር ፐርሰንት መጠን በመለያየቱ የተለየ ስለሆነ ነው። የዘይቱ ወፍራምነት ዘይቱ በምን ጥቅም ላይ እንዲውል የሚያስረዳ ሲሆን በሚወፍርበት ወይም በሚቀጥንበት ጊዜ የመገልገያና የመጠቀሚያ ሞተሮች ከመኪና ጀምሮ እስከ አውሮፕላን ፣የቤት ወይም የመስሪያ ቤት ተጠቃሚዎች፣ የፋብሪካና የምርት መሣርያ መጠቀሚያዎች ፍላጎት ከነዚህ ሁለት  (ላይት ኤንድ ስዊት ክሩድ ዘይት ወይንም ሄቪይ ኤንድ ሳዎር ክሩድ ዘይት) ጥራት መደብ ይነት አይለይም። 

እንደዙሁም ሠልፈር መጠን የአንደኛው መለያ የሆነበት ዘይቱ ምን ያክል አሲድ እንዳለውና የዘይቱን ንፅህና ይገልፃል። በዚህም ምክንያት ብዙ ሠልፈር ያልው ሳዎር ክሩድ ዘይት ሲባል አነስተኛ ሠልፈር ያልው ደግሞ ስዊት ክሩድ ዘይት ይባላል።

የክሩድ ዘይት አይነቶች እነዚህ ናቸው፦

የተጣራ ነዳጅ  ዘይት አይነቶች እነዚህ ናቸው፦

የተጣራ ዘይት ምርት ውጤቶች ወይንም ሪፋይንድ ክሩድ ኦይል መደብ ውስጥ የሚገኙና በገበያ ላይ የዋጋ ልዪነት በየጊዜው የሚያሳዩ፣ ለመግዛትም ሆነ ለመሸጥ የሚያጓጉ ከዚህ በታች ይገኛሉ።

የድፍድፍ ዘይት ይሚለካው በ ባሬል ( ጉርድ በርሚል በሚመስል) መያዣ ሲሆን ፤ አንድ ባሬል ክሩድ ዘይት አርባ ሁለት ጋሎን ወይንም አንድ መቶ ሃምሳ ዘጠኝ ሊትር ነው። በኮሞዲቲ ገበያ ላይ ሲሸጥም በ ሲ.ኤል. (CL) ስም ነው።




#Article 372: ኃይሉ ገብረዮሐንስ (ገሞራው) (139 words)


አንድነት ግጥም (እማማ አፍሪካን ለማስታወስ) 1984 87 ገጽ 
በረከተ መርገም	 1987 	ISBN 91-7328-627-3 96 ገጽ 
የበሰለው ያራል 	1988 	ISBN 91-7328-638-9 224 ገጽ 
በናቴኮ ሴት ነኝ	 1989 	243 ገጽ 
እናትክን በሉልኝ	 1989 	ISBN 91-7328-774-1 134 ገጽ 
የሽግግር ደባ (?)	 1990 	ISBN 91-7328-675-3  353 ገጽ
ዛር ነው በሽታዋ	 1991 	208 ገጽ 
ቅኔ ለዘመን 	1992 	ገጽ274 
ቆርጠሃት ታለለ (?)	 1992 	290 ገጽ
የመንጎል ጥሪ 	 1994 	ISBN 91-630-2924-3 108 ገጽ 
ዜሮ ፊታውራሪ 	1995 	ISBN 91-7328-768-7  55 ገጽ  

Mao Zedong, Weida de jinbu zhi fu! - Stockholm : F�rfattares bokmaskin : [Stockholm] : [G.Y. Hailu], 1986. - 38 s. : ill. - ISBN 91-7328-536-6

Hanying chengyu di xiaojia = A tiny home of Chinese-English idiomatic phrases / compiled by Hailu - [Stockholm] : [F�rfattares bokmaskin] : [Stockholm] : [G.Y. Hailu], 1987. - xxxix, [1], 478 s. - ISBN 91-7328-598-6
ምንጭ ስዊዲን አብያተ መጻሕፍት ዝርዝር




#Article 373: ቢዮንሴ (112 words)


ቢዮንሴ ጊሴሌ ኖውለስ (Beyoncé Giselle Knowles) ሙሉ ስሟ ሲሆን የአሜሪካ ዜግነት ያላት የአር አንድ ቢ (R and B) የሙዚቃ ዘርፍ አቀንቃኝ፣ የሙዚቃ አዘጋጅ፣ ተዋናይት፣ ሞዴል እና የሙዚቃ ደራሲ ናት። እ.አ.አ. በሴፕቴምበር 4 1981 ሀውስተን በቴክሳስ ውስጥ ተወለደች። በልጅነቷ ጀምሮ ማቀንቀን ትወድ የነበረችው ይህች አርቲስት ገና በወጣትነት እድሜዋ ዴስትኒስ ቻይልድስ የተሰኘ የሙዚቃ ቡድን ከ ባልደረቦቿ ኬሊ ሮላንድ እና ዊሊያምስ ጋር በመሆን እ.አ.አ. በ 1997 ቴክሳስ ውስጥ አቋቋመች (የኋላ ኋላ ግን ቡድኑ ፈርሶ እ.አ.አ ከ2006 ጀምሮ ለብቻዋ መስራት ጀምራለች)። ቡድኑ እስከፈረሰበት አመት ድረስ በተለያዩ ስራዎች ውጠታማ ነበር። በተለይ ከባልተቤቷ ጄዚ ጋር የሰራችው ክሬዚ እን ላቭ የተሰኘው ዜማ ከፍተኛ ዝናን አትርፏል። በ2008 እ.አ.አ ያወጣችው I'm... sasha fierce አልበሟ አሁን ለደረሰችበት ከፍተኛ እውቅና ዋናውን ድርሻ ይይዛል።




#Article 374: ጋሞጐፋ ዞን (318 words)


አርባ ምንጭ ከተማ ከ1955 እስከ 1993 ዓ.ም ድረስ የጋሞ ጐፋ ጠቅላይ ግዛት፣ የሰሜን ኦሞ አስተዳደር አካባቢና ከዚያም የሰሜን ኦሞ ርዕሰ ከተማ በመሆን ለቀድሞዎቹ የጋሞ፣ የጐፋ፣ የጋርዱላና ሐመር ባኮ አውራጃዎች ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ማዕከል ሆና ያገለገለች ስትሆን ከ1993 ዓ.ም ወዲህ ባሉት ዓመታት ደግሞ አስራ አምስት ወረዳዎችንና ሁለት የከተማ አስተዳደሮችን አቅፎ ለያዘው ጋሞ ጐፋ ዞን ዋና ከተማ በመሆን እያገለገለች የምትገኝ ከተማ ነች፡፡ በዞኑ ውስጥ የሚገኙ የጋሞ፣ የጎፋ፣ የዘይሴ ፣ የጌዲቾና የኦይዳ ብሄረሰቦችን ጨምሮ ጥቂት የማይባሉ ሌሎች የሀገራችን ብሔር ብሔረሰቦች ተወላጆች ተከባብረውና ተቻችለው በፍቅርና በሰላም የሚኖሩባት አርባ ምንጭ ከተማ በቀለማት አደራደሩ ትኩረትና ተወዳጅነት የማይለየው የጋሞ ብሔረሰብ የክብርና የማዕረግ ልብስ እንዲሁም መታወቂያው የሆነውንና ዱንጉዛ በመባል የሚታወቀው ባህላዊ ልብስ ጨምሮ ሌሎች የኢትዮጵያ የሸማ ጥበብ አልባሳት ሥራዎች መፍለቅያ አካባቢዎች እምብርት ከመሆኗም በተጨማሪ በባህላዊ ቤት አሰራራቸው በለቅሶና ሠርግ ስርዓታቸው በባህላዊ የማምረቻና የመገልገያ ቁሳቁሶቻቸው የብዙዎችን አድናቆትና አግራሞትን ላስጫሩት የጋሞ፣ የጐፋ፣ የዘይሴ፣ የጌዲቾና የኦይዳ ብሔረስብ ህዝቦች መዲና ነች፡፡

በተፈጥሮ ውበት በታደለው ድንቅ ከተማ እንደመከተሟ አርባዎቹ ምንጮች የሚመነጩባትን የአባያና ጫሞ አስደናቂ የስምጥ ሸለቆ ሀይቆች ያለሀሳብ የሚፈነጩባትን ፤ የነጭ ሣር ብሔራዊ ፖርክ፤ የአዞ እርባታ ጣቢያ፤ የአዞ ገበያን በአካባቢው ታይተው የማይጠገቡ የዱር እንሰሳት እና የተፈጥሮ ደኖችን ይገኛሉ፡፡     

የዞኑን አስደናቂ የቱሪስት መስህቦች እንግዶቻችንን በማስጎብኘት ከታዋቂ የዓሳ ምርታችን ፣ ከማንጎ ፤ ከሙዝ እና በአፕል ማሳችን እየተንሸራሸርን የማይረሱ ትዝታዎችን ጥለው ያልፋሉ

ከተፈጥሯዊ መስህቦች መካከል በጥልቀታቸውና በስፋታቸው እንዲሁም በልዩ አቀማመጣቸው ማራኪና ውብ ከሆኑት የስምጥ ሽለቆ ሃይቆች መካከል በመጀመሪያ ደረጃ የሚቀመጡት የአባያና የጫሞ ሃይቆች እያንዳንዳቸው ለምግብነት አገልግሎት የሚውሉ ዓሳዎችን ከማስገኘታቸው ባለፈ ተደራሽና ተመራጭ የቱሪዝም ክልል ናቸው፡፡ ከ514 ካ.ሜትር እስከ 1110 ካ.ሜትር ስፋትና ከ9 ሜትር እስከ 13 ሜትር ጥልቀት አላቸው፡

Medre Genet Arba Minch ምድረ ገነት አርባምንጭ ምድረ ገነት አርባ ምንጭ ፌስ ቡክ የጋሞ ጐፋ ዞን ባህል … የተፈጥሮ ሐብት ስፖርት … ለዞኑ እድገት የሰሩ ግለሰቦች ይመሰገኑበታል … ሙዚቃ … የጉዞ ማስታወሻ … ጥያቄ ና መልስ አዝናኝና አስተማሪ ጹሑፎች ቪድዮ ይቀርቡበታል እርሶም ምድረ ገነት አርባ ምንጭ 2 ወይም ጋሞ ጐፋ አርባ ምንጭ ፌስቡክን ላይክ እና ሼር ያድርጉ To connect with Please Visit / Like our page. LIKE, TAG  SHARE for inspiring us., sign up for Facebook 




#Article 375: ጨረቃ (416 words)


ጨረቃ የመሬት ብቸኛዋ ሳተላይት ስትሆን በሥርዓተ-ፀሐይ ውስጥ አምስተኛ ትልቅ ሳተላይት ናት። ከመሬት መሀል እስከ ጨረቃ መሀል ድረስ ያለው አማካይ ርቀት 384,403 ኪ.ሜ. (238,857 ማይል) ያህል ነው። ይህ ርቀት ከመሬት አንድ ጫፍ እስከ ሌላኛው ተቃራኒ ጫፍ (diameter) ያለውን ርቀት ሰላሳ (30X) ይበልጣል። ሁለቱ አካላት ሥርዓታቸውን የሚጠብቁበት ማዕከላዊ ነጥብ 1,700 ኪ.ሜ. (1,100 ማይል) ማለትም የመሬትን ራዲየስ አንድ አራተኛ (1/4) ከመሬት ጠለል ዝቅ ብሎ ይገኛል። ጨረቃ በመሬት ዙሪያ በየ27.3 ቀናት አንድ ሙሉ ዙር ታጠናቅቃለች። ይህም መዞር ለጨረቃ በየ29.5 ቀናት የሞላና የጎደለ መመልክ መያዝ ዋና ምክንያት ነው።
የጨረቃ ከአንድ ጫፍ እስከ ሌላኛው ተቃራኒ ጫፍ (diameter) ያለው ርቀት 3,474 ኪሜ (2,159 ማይል) ሲሆን ከመሬት ተመሳሳይ አንድ አራተኛ (1/4 X የመሬት ዲያሜትር) በትንሽ ይበልጣል። የመሬትን አንድ አራተኛ ስፋት ሲኖራት ይዘቷ (volume) ግን የመሬትን ሁለት በመቶ (2%) ብቻ ነው። የጨረቃ ስበት የመሬት ስበትን አስራ ሰባት በመቶ (17%) ጋር ይነጻፀራል።
ጨረቃ የሰው ልጅ ያረፈባት ብቸኛዋ የጠፈር አካል ናት።

በ2011 የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ ሳይንቲስቶች ሮቦቶችን ወደ ጨረቃ ልከው የጎመንዘር አይነት (Brassica napus)፣ የድንችና የጥጥ ዘሮችን በጨረቃ ላይ በመያያዣ ውስጥ ማብቀል እንደተቻለ አስረዱ። ወደፊት ሰዎች ወደ ጨረቃ ቢመልሱ ኖሮ፣ በነዚህ ሦስት ምርቶች፦ ጎመንዘር ለዘይት፣ ድንች ለምግብ፣ ጥጥም ለልብስ፦ እንደሚረዷቸው አሉ። እንዲሁም የድንጋይ ፌጦ (Arabidopsus spp)፣ እርሾና የፍራፍሬ ዝንብ በሙከራው ውስጥ እየታደጉ ነበር። ሆኖም ከ፫ ቀን በኋላ ናሙናዎቹ ሁሉ ከጨረቃ አየር ሙቀት የተነሣ በርደው አርፈው ነበር።

ይህች የመሬት ብቸኛ ሳተላይት በአማርኛ ጨረቃ ስትሆን በእንግሊዝኛው ደግሞ the Moon ትባላላለች። Moon የጀርመንኛ ቃል ሲሆን ከላቲን mensis እና ከጥንታዊ ግሪክ μήνας ተመሳሳይ የሆነ ወር የሚል ትርጉም አላቸው። ለቃሉ መፈጠር ከወር በተጨማሪ እንደ ሰኞ እና የወር አበባ የመሰሉ ቃላት አንድም በእንግሊዝኛው ትርጉማቸው ከቃሉ ጋር ተመሳሳይ አጀማመር በመኖሩ አልያም በሂደታቸው ርዝማኔ ከጨረቃ ጋር ስለሚገናኙ አስተዋጽዖ አላቸው።

ጨረቃ ከመሬት አንፃር ስትትታይ ግዙፍ አካል ናት። ይህም ከላይ ለማነፃፅእር እንደተሞከረው የመሬትን አንድ አራተኛ ዲያሜትር መኖሯ እና የመሬትን አንድ ሰማኒያኛ (1/80 X የመሬት ክብደት) መመዘኗ ያረጋግጣል። እህ እንግዲህ ሳተላይቷ ከባለቤት ፕላኔቷ ጋር ምን ያህል የመጠን ቅርርብ እንዳላት ያሳያል (ምንም እንኳን ቻሮን የተባለችው የፕሉቶ ሳተላይት በንፅፅር ግዙፍ ብትሆንም)።

ከላይ እንደተገለፅእው ጨረቃ በመሬት ዙሪያ አንድ ሙሉ ዙር ለመዞር 27.3 ቀናት ይፈጅባታል። ነገር ግንመሬትም ከፀሐይ አንፃር በራሷ ምህዋር በተመሳሳይ ጊዜ ስለምትጓዝ የጨረቃን ገጽታ በየ29.5 ቀናት ሲቀያየር እናየዋለን።
ጨረቃ በመሬት ዙሪያ እንድትሽከረከር የሚያደርጋትን ኃይል የምታገኘው ከመሬት ስበት እና ከፀሐያዊ የስበት ሥርዓት ነው። 

በጨረቃ ገፅ ላይ የወቅቶች መፈራረቅ በጥቂቱም ቢሆን ይከሰታል። ይህም ለመለየት በሚያስቸግር መልኩ የተከፋፈሉ የበጋ እና የክረምት ወቅቶችን መታዘብ ተችሏል። ለዚህም ምክንያቱ በጨረቃ እና በፀሐይ መካከል ያለው የመፋጠጫ አንግል ትንሽ ስለሆነ (1.54 ዲግሪ) ነው።

ግርዶሽ የሚፈጠረው ፀሐይ፣ መሬት እና ጨረቃ በአንድ መስመር ላይ ሲሆኑ ነው። በተለይም የጨረቃ ግርዶሽ የሚባለው የሚከሰተው ጨረቃ በመሬት እና በፀሐይ መካከል እትሆን ብቻ ነው። በተቃራኒው የመሬት ግርዶሽ የሚፈጠረው መረት በፀሐይ እና በጨረቃ መካከል ስትሆን ነው።
 




#Article 376: ስልክ (171 words)


ስልክ ወይም ቴሌፎን (የግሪክ ቃል ከሆኑት τῆλε - ቴሌ፣ [ሩቅ ማለት ሲሆን] እና φωνή - ፎኔ፣ [ድምፅ ማለት ሲሆን] የመጣ ቃል ነው።) የመግባቢያ መሳሪያ ሲሆን ድምፅን (በዋናነት የሰዎችን) የመቀበል እና የማስተላለፍ ተግባር ያከናውናል። ይህ መሳሪያ በረዥም ርቀት ያሉ ሁለት ሰዎችን በድምፅ እንዲገናኙ ያስችላል።

ድምፅ ሞገድ ስለሆነ አንዴ ከፍ አንዴ ዝቅ የሚል አቅም አለው። በተረፈ፣ የተለያዩ ድምጾች የተለያየ የሞገድ ይዘት ይኖራቸዋል፣ ስለሆነም የተለያዩ ቃላት እነሱን ሊለይ በሚችል መልኩ የራሳቸው የሆነ ሞገድ አላቸው። ስልክ የሚሰራው ይህን የድምጽ ጠባይ በመጠቀም ነው። 

ከጎን እንደሚታየው፣ ሰውየው ቃላትን ሲናገር ከጥላሸት (ካርቦን) ዱቄቱ ፊት ለፊት ያለው ሽፋን ይርገበገባል፣ አንድ አንድ ቃላት ሽፋኑ በሃይል እንዲርገበገብ ሲያደርጉ ሌሎች በቀስታ ይሆናል። ይህ መርገብገብ በተራው የጥላሸቱ ዱቄት አንዴ በሃይል እንዲታመቅ ሌላ ጊዜ በላላ ሁኔታ እንዲሆን ያረጋል፣ የጥላሸቱ መታመቅና ፈታ ማላእት በተራው ከባትሪው መንጭቶ በውስጡ የሚያልፈው የኤሌክትሪክ ጅረት አንዴ ደመቅ አንዴ ቀዝቀዝ እንዲል ያደርጋል። የኤሌክትሪኩ ጅረት ሌላኛው ሰውየ ማዳመጫ ሲደርስ ማዳመጫው (ስፒከሩ) ከመጅመሪያው ሰውየ ንግግር አንጻር አንዴ ደመቅ አንዴ ደከም ብሎ እንዲርገበገብ ያደርጋል። በሌላ አነጋገር የመጀመሪያው ሰውየ የተናገረው ንግግር በዚህ መልኩ በሽቦው ውስጥ ይሻገራል። አሌክሳንደር ግርሃም ቤል የፈለሰፈው ስልክ ይህን አይነት ይዞታ ነበረው።




#Article 377: ሃይድሮጅን (136 words)


ሀይድሮጅን

እያንዳንዱ የውሃ ሞለኪዩን ከሁለት የሃይድሮጅን አተም ና ከአንድ የኦክሲጅን አተም የተሰራ ነው። ነገር ግን እኒህ አተሞች በከፍተኛ ጉልበት ስለተጣበቁ እርስ በርሳቸውን አላቆ አተሞቹን ለማግኘት ጉልበት ያስፈልጋል። ለዚህ ተግባር የሚውሉ ብዙ መንገዶች ቢኖሩም፣ በጣም ቀላሉና ማንም ሰው እቤቱ እኒህን ጋዞች (ኦክሲጅን እና ሃይድሮጅን) ለማግኘት ሊጠቀምበት የሚችል መንገድ ቢኖር  ይባላል።

ጨው የሟሟበት ውሃ በቱቦወቹ ከተሞላ በኃላ፣ የኤሌክትሪክ ገመዶቹ ውሃው ውስጥ በስዕሉ በሚታየው መልኩ ይቀመጣሉ። ከባትሪው ጋር ገመዱ ሲገናኝ ውሃው አረፋ መድፈቅ ይጀምራል። ይህ ከመሆኑ በፊት ግን የቱቦወቹን አፎች በፊኛወች መዝጋት በጣም ጠቃሚ ነው። በዚህ ሁኔታ ከባትሪው ፖዚቲቭ በሚመጣው ገምድ ጎን ባለው ቱቦ ላይ የተገጠመው ፊኛ በሃይድሮጅን ጋዝ ይነፋል። በኔጌቲቩ ጎን ደግሞ ንጹህ ኦክሲጅን ፊኛውን ይሞላል። በዚህ መንገድ እኒህን ሁለት ጋዞች ከውሃ ይመረታሉ።
ማስጠንቀቂያ lt;font color = red ሃይድሮጅን እጅግ ተቀጣጣይ ጋዝ ስለሆነ በጥንቃቄ መያዝ አለበት! ንጹህ ኦክሲጅን እንዲሁ እሳት ሲያገኝ ቦግ ብሎ የሚቀጣጠል አደገኛ ጋዝ ነው lt;/font 




#Article 378: ኦክሲጅን (143 words)


ኦክስጅን ከግሪክ ὀξύς (ኦክሲስ) 'አሲድ' ወይም የአሲድ ጣእም ያለው እና γενής (ጀነስ) 'አባት'ከሚሉት ቃላት የመጣ ነው። የዚህ ንጥረ ነገር አቶማዊ ቁጥር 8 ሲሆን የሚወከልበት ውክል O ነው። በከፍተኛ ሁኔታ የመፀግበር ባህሪ ያለው ሲሆን የንጥረ ነገሮች ሠንጠረዥ ውስጥ የፔሬድ ሁለት ኢ-ብረታ ብረት ንጥረነገሮች አባል ነው። 

ኮምጣጤ-ዘር ኮምጣጤ-ጂን በፈርንሳይኛ እንዲሁም በጀርመንኛ ቃል በቃል ይህን በኖርማል ሁኔታ ዉስጥ የጋዝ ዘር ሲተረጎም ኮምጣጤ ዘር ማለት ነው ፡፡ ጀርመኛዉን እንውሰድ ስያሜው ከሁለት ቃል የተዎጣነው የመጀመርያው ቃል sauer ቃል በቃል ሲተረጎም ኮምጣጣ ማለት ነው፡ ሆለተኛው stoff የሚለው ቃል ነገር ማለት ነው፡( ዛወር- ሽቶፍ)የሄምስጥሪ ኬምስትሪ ሰንጠረዥ አባት በሆነው በዲምትሪ ሜንዴሌቭ ቋንቋ በሩስያዊኛ ምን እንደሚባል እንመልከት፡ ኪስላ- ሮድ፡ ኪስልይ ማለት ቃል በቃል ኮምጣጥጤ ማለት ነው ``ሮድ`´ ማለት `´ዘር`` ማለት ነው። አኦክስጅን ፡ ኮምጣጤ -ዘር የሚለው የአማርኛ ስያሜ አብሮ ቢጻፍ የበለጠ ነገሩን ያብራራዋል።
ማኦክሰድ ከንጥረ ነገር ዉስጥ የውሃን -ዘር ማትነን ማጥፋት መበተን ወይም ከሌሎች ንጥረ ነገሮች ዘር ጋር ስገናኝ የሚያስየው ሄሚካልዊ ባህርዩ።




#Article 379: ሳህሌ ደጋጎ (427 words)


ኮሎኔል ሣህሌ ደጋጎ ከእናታቸው ከወይዘሮ ደጊቱ ፈይሣ እና ከባላንባራስ ደጋጎ አለቤ አብራክ በ1923 ዓ/ም  በምዕራብ ወለጋ ልዩ ስሙ ነጆ ከተባለው ሥፍራ ተወለዱ።  እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ  በነቀምት አንደኛ ደረጃ እና በአዲስ አበባ ተፈሪ መኮንን ት/ቤት ዘመናዊ ትምህርቱን ከተከታተለ በኋላ በነበረው ልዩ የውትድርና ፍቅር በቀድሞ 1ኛ ክፍለ ጦር በኋላም ማዕከላዊ ዕዝ ተብሎ በተጠራው የክ/ዘበኛ የጦር ክፍል ውስጥ በ1942 ዓ/ም ተቀጥሯል። በነበረው ሙያዊ ብቃትና ወታደራዊ ሥነ ሥርዓት አክባሪነት  ከተራ ወታደርነት በአንድ ጊዜ የሃምሳ አለቅነት ማዕረግ ማግኘት የቻለው ሣህሌ፤ በሂደት እስከ ኮሎኔል ደረጃ ደርሷል። ወደ ሙዚቃ ቀማሪነት፣ ዜማና ግጥም ደራሲነት እንደዚሁም ወደ የማዕከላዊ ዕዝ የሙዚቃ ባንድ ኃላፊነት ከመሸጋገሩ በፊት በእግረኛ ባንድ ውስጥ “ክላርኔት” የተሰኘው የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዎች የነበረው ሣህሌ ደጋጎ፣ የሙዚቃን ትምህርት የቀሰመው ከፈረንሣዊው መምህሩ ሙሴ ኒኮ መሆኑን የሕይወት ታሪኩ ላይ ተጠቅሷል። ከክላርኔት በተጨማሪ “አኮርዲዮን፣ አልቶ-ሳክስ፣ ፒያኖ” የተሰኙትን የሙዚቃ መሣሪያዎችንም በብቃት ይጫወት ነበር። 

በጠቅል ራዲዮ ጣቢያ (በተቋቋመ ጊዜ ) በአኮርዲዮን ጥዑም ዜማ ለጣቢያው አድማጮች ሲያንቆረቁር ከነበሩት የሙዚቃ ሰዎች መካከል ሣህሌ ደጋጎ የመጀመሪያው ነበር። 
ከእነ ሻለቃ ግርማ ይህደጎ፣ ሻምበል አፈወርቅ ዮሐንስ እና ከሻለቃ ባሻ ገብረዓብ ተፈሪ ጋር በመሆን የክቡር ዘበኛ ኦርኬስትራን ስም እፁብ ድንቅ በማድረጉ በኩል የበኩሉን ሚና ተጫውቷል። ግጥምና ዜማ ደራሲ ከመሆኑም ባሻገር የአጫጭር እና ረዣዥም ድራማዎች ፀሐፊ የነበረው ሣህሌ፣ «ሁለገብ የታሪክ ማኅደር» ያሰኘውን ተግባር በሕይወት ዘመኑ አከናውኗል። 

ክቡር ዶ/ር ጥላሁን ገሠሠ ከተጫወታቸው ሙዚቃዎች ውስጥ “ስቆ መኖር”፣ “እውነት ማሪኝ”፣  የሚሉትን ግጥሞች፣ “ዋይ ዋይ ሲሉ”፣ “ውሸት ለመናገር”፣ “ልብሽን ለአፈርሰው”፣ “ኮቱሜ”፣  የሚሉትን ዘፈኖች ግጥምና ዜማዎች የደረሰው ሌ /ኮሎኔል ሣህሌ ደጋጎ እንደሆነ ይታወቃል።

ከዚህም ሌላ ለድምፃዊት ብዙነሽ በቀለ “አይወጣኝም ክፉ ነገር” በሚል የዘፈነችውና በብዙኀን ዘንድ ተወዳጅነት ያለውን (“ወደመጣሁበት ምድር፣ እስክመለስባት በክብር፣ ሰውን ከማስደሰት በቀር፣ አይወጣኝም ክፉ ነገር፣ ...” ) ሙዚቃውን ያቀናበረው ሌ /ኮሎኔል ሣህሌ ነው። ሌ /ኮሎኔል ሣህሌ “ፍላጎቴ”፣ “ምን ነበር”፣ “ምንድነው ትዝታህ”፣ ... የተሰኙትን የብዙነሽ በቀለን ዘፈኖች ያቀናበረ ሲሆን፣ “ከንቱ ሥጋ” የሚለውንና ሌሎችንም ዘፈኖችዋን ግጥም ደርሶላታል። “አታሳየኝ ጭንቁን”፣ “የፍቅር ወጋገን”፣ “ቃልኪዳን”፣ “በብር አይጋዛም”፣ “ፍቅርህ ቀሰቀሰኝ”፣ … የተሰኙትን ዜማና ግጥሞች ያዘጋጀው ሣህሌ ደጋጎ እንደነበረ ይታወቃል። 

በዕድሜ ዘመን የኪነ ጥበብ አገልግሎት የክብር ሜዳሊያ እና የ 20 ሺህ ብር ተሸላሚ የሆነው ሣህሌ ደጋጎ፤ የ 30፣ የ 20 እና የ 10 ዓመት የረዥም ዘመን አገልግሎት የወርቅ፣ የብርና የነኀስ እንደዚሁም የተዋጊ ወታደርነት የደረት ዓርማ ኒሻን ተሸለሚም ነበር። ሙዚቃ ቀማሪው ሣህሌ ደጋጎ ከባለቤታቸው ከወ /ሮ ወይንሸት ተክሉ 4 ሴት እና 3 ወንድ ልጆችን አፍርቶ የ 10 ልጆች አያት ለመሆን በቅቷል። በቀብር ሥነ ሥርዓቱም ላይ ከቤተሰቡ ውጪ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ወዳጅ ዘመዶቹ፣ የቀድሞ የሥራ ባልደረቦቹ እና አድናቂዎቹ፣ የመኖሪያ አካባቢያው ሰዎች ተገኝተው በዕንባ ሸኝተውታል። የአበባ ጉንጉንም አኑረዋል። 

ኢህአዲግ ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ .ም . ኢትዮጵያን ከተቆጣጠረ በኋላ ሌ /ኮሎኔል ሣህሌ ደጋጎ ለሰባት ወራት በጦላይ የጦር ማሠልጠኛ ማዕከል ታስሮ እንደነበር ይታወቃል። 

በዚህ አጋጣሚ ለመላው የሌተናል ኮሎኔል ሣህሌ ደጋጎ ቤተሰብ አባላት፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ እና ለአድናቂዎቹ ፈጣሪ አምላክ ልባዊ መጽናናትን እንዲሰጥ እንመኛለን ።




#Article 380: ሳዑዲ አረቢያ (329 words)


የሣውዲ አረቢያ ግዛት 28.7 ሚሊዬን  የሚሆን ህዝብ ብዛት የያዘ ሲሆን 2ዐ ሚሊዬኑ የሣውዲ ዜጎች ሲሆኑ 8 ሚሊዬኑ የሌላ አገር ዜጎች ናቸው፡፡

ሳውዲ አረቢያ በምዕራብ ኤዥያ ከሚገኙ አገሮች በሙሉ በቆዳ ስፋቷ አንደኛ ናት፡፡  የአገሪቱ መሬት ስፋት 2,15ዐ,ዐዐዐ ኪሎ ሜትር ስኩኤር ነው፡፡  ጆርዳን እና ኢራቅ በሰሜን፣ ኩዌት ደግሞ በሰሜን ምስራቅ ኳታር ባህሬን እና የዩናይትድ አረብ ኤምሬት በምስራቅ ኦማን በደቡብ ምስራቅ እና በስተመጨረሻ የመን በደቡብ በኩል ሣውዲ አረቢያ ያዋስኗታል፡፡  የቀይ ባህር እና የፐርዢያን ገልፍ ባህርን የያዘ ብቸኛ አገር ሲሆን የሣውዲ መሬት ለመኖር በሚያስቸግር በረሃ የተከበበ ነው፡፡

አሁን ያለው የሣውዲ ግዛት በፊት ጊዜ አራት ቦታዎችን ያጠቃለለ ነበር፡፡  ሄጃዝ፣ ናጅድ፣ አል አሻ እና አስርን የያዘነው፡፡  የሣውዲ አረቢያ ግዛት ተመሠረተው በ1932 እ.ኤ.አ. በኢብን ሣኡድ በተባለ ሰው ነው፡፡  ኢብን ሣኡድ ቀድሞ በ1894 ዓም (1902 እ.ኤ.አ.) ከብሪታንያ ግዛት ከኩወይት ዘምቶ ሪያድን ያዘ። ኢብን ሳኡድ አራት የነበሩትን የተለያዩ ግዛቶች አንድ በማድረግ ሣውዲ አረብያን ከተመሠረተ ጀምሮ እስከአሁን ድረስ ሀገሪቱ በዘውድ አገዛዝ እና በእስልምና ሃይማኖት መሠረት እየተዳደረች ትገኛለች፡፡ እስልምና ሃይማኖትን በተመለከተ ዋሀቢ እስላም የሣውዲ አረቢያ አንደኛ እምነት ነው ተብሎ ይታሰባል፡፡  ለእስልምና እምነት ትልቅ ቦታ የሚይዙት ቅዱስ ስፍራ ተብለው መካ እና መዲና በሣውዲ ስለሚገኙ ሣውዲ አረቢያ አብዛኛው ጊዜ የተቀደሱትን ሁለት መስጊዶች የያዘው መሬት ተብሎ ይታወቃል፡፡

ሣውዲ አረቢያ በዓለም ላይ ካሉ ትልቅ የነዳጅ አምራች ሀገራት ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ በተጨማሪም ሣውዲ አረቢያ በዓለም ላይ ካሉ ሀይድሮ ካርቦን ክምችት ካላቸው አገሮች  በሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡  በሀገሪቱ ባለው የተፈጥሮ ሀብት ከፍተኛ ክምችት ምክንያት ከፍተኛ የኢኮኖሚ ገቢ እና የህዝብ ቁጥር እድገት ከያዙ ሀገራት ጋር ትመደባለች፡፡  ሣውዲ አረቢያ G-2ዐ ተብለው ከሚታወቁት ከፍተኛ የኢኮኖሚ አቅም ካላቸው የሀገራት ቡድን ውስጥ ብቸኛዋ የአረቡ ዓለም አገር ናት፡፡  ይህም ቢሆን የሣውዲ ኢኮኖሚ  በአብዛኛው በአንድ ቡድን የተያዘ ነው፡፡  የሣውዲ አረብያን ፈላጭ ቆራጭ በሆነ የመንግስት ስርዓት በመመራት “ነጻነት የለም” በሚል “ነጻነት ቤት” በሚል በሚታወቀው ድርጅት ተሰይማለች፡፡

ሣውዲ አረቢያ በዓለም ላይ ለጦር ሀይል ከፍተኛ ገንዘብ ከሚያወጡ አገሮች ዝርዝር በአራተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡  እ.ኤ.አ. ከ2ዐ1ዐ-2ዐ14 በስኘሪ ተብሎ በሚታወቅ ድርጅት በተደረገው ጥናት ሣውዲ አረቢያ ዓለም ላይ ከሚገኙ የጦር መሣሪያዎች በከፍተኛ ደረጃ በማስገባት ሁለተኛዋ ሀገር ናት፡፡  ሣውዲ አረቢያ በአካባቢው ካሉ ሀገሮች በዓለም ላይ ከፍተኛ አስተዋጾኦ በማድረግ ላይ ያለች አገር ናት፡፡ የኦፔክ፣ ጂሲስ እና የእስላም ግሩፕ አባል ናት፡፡




#Article 381: ዩራኒየም (454 words)


ዩራኒየም (uranium) የንጥረ ነገሮች ሠንጠረዥ ውስጥ ኬሚካዊ ውክሉ U ነው። አቶማዊ ቁጥሩም 92 ነው። የራዲዮ አክቲቭ ሃይል መስሪያ ነው።

የዩራንየም (uranium) ነጣ ያለ ብርማ ቀለም ያለው የብረት ዘር ሲሆን፣ በኬሚካል ባሕሪው በፔሪዲክ ቴብል ላይ በአክታናይዶች ዝርዝር (actinide series) ውስጥ ይመደባል። የአቶም ቁጥሩም 92 ሆኖ የአቶሚክ ምልክቱ ደግሞ U ነው። የዩራንየም አቶም 92 ፕሩቶኖች እና 92 ኤሌትሮኖች ሲኖሩት፣ ከነዚህ ውስጥ 6ቱ ቫላንስ ኤሌትሮኖች (በመጨረሻ ሼል ላይ የሚገኙ) ናቸው። የዩራንየም ኑክለስ ደግሞ ከ141 እስከ 146 ኑትሮኖችን የሚይዝ ሲሆን ይህም ማለት ዩራንየም ስድስት አይሶቶፖች (ከU-233 እስከ U-238) አሉት ማለት ነው። ከነዚህ አይሶቶፖች ውስጥ ዩራንየም-238 (146 ኑትሮን) እና ዩራንየም-235 (143 ኑትሮን) በአብዛኛው በመደበኛነት የሚገኙ ናቸው። እነዚህ ስድስቱም አይሶቶፖች ያልተረጋጉ (unstable) እንዲሁም ዩራንየም ዝቅተኛ (ዘገምተኛ) የሆነ ራዲዮአክቲቭ ቁስ ነው። ዩራንየም ከፕሉቶንየም-244 ቀጥሎ በተፈጥሮ የሚገኝ ትልቅ የግዝፈት ቁጥር ያለው ሁለተኛ አቶም ነው። የጥቅጥቃት (density) መጠኑ እርሳስን (lead) ከ70% (እጅ) በላይ የሚበልጥ ሲሆን፣ ከወርቅና ተንግስተን ጋር ሲወዳደር ግን ዝቅተኛ ነው። ዩራንየም በተፈጥሮ ከምድር የላይኛው ክፍል (crust) በአፈር ውስጥ፣ ከአለትና ከውኃ ጋር ከሚሊዮን ውስጥ እስከ አራት እጅ (4 ppm) ያህል ይገኛል። ይህም ከወርቅና ብር በተሻለ መልኩ በዚህኛው የመሬት አካል ውስጥ እንደሚገኝ ያሳያል። እንደ uraninite ካሉ ዩራንየም ከሚገኝባቸው ማዕድኖች ይመረታል።

በተፈጥሮ በሚገኘው የዩራንየም (uranium) አቶም ውስጥ በዋናነት ሁለት የተለያየ ክብደት ያላቸው የዩራንየም ዓይነቶች ይገኛሉ፣ እነሱም U-238 እና U-235 ይባላሉ። U-235 በቀላሉ ፊሽን ማድረግ የሚችል አይሶቶፕ ነው፤ ነገር ግን በተፈጥሮ ከሚገኘው ዩራንየም ውስጥ መጠኑ 0.7% ብቻ ሲሆን፣ ሌላው ዓይነት U-238 ደግሞ 99.3% የሚገኝ ነው። በመደበኛው (Pressurized Water Reactor - PWR) የኑክሌር ማብላያ ውስጥ ፊሽንን በቀጣይነት (ሰንሰለታዊ አፀግብሮት - chain reaction) ለማከናወን የኑክሌር ፊዩሉን የU-235 መጠን ቢያንስ እስከ 3.9-5% ማበልፀግ (enriched) ያስፈልጋል። በዚህ የU-235ን የማበልፀግ ሂደት በዩራንየም ውስጥ በተፈጥሮ ከሚገኘው 0.7% የU-235 መጠን ለኑክሌር ፊዩል ወደሚፈለገው 5% ድረስ እንዲጨምር ሲደረግ፣ በሌላ በኩል መጀመሪያ በተፈጥሮ ከነበረው ዩራንየም ውስጥ የU-235 መጠን እያነሰ (depleted) በመሄድ የU-238 መጠን ይጨምራል። ይህም በተለምዶ depleted uranium ይባላል። ይህ በዩራንየም የማበልፀግ ሂደት የሚገኝ ተረፈ-ምርት - depleted uranium የጥቅጥቃት (density) መጠኑ ከፍተኛ በመሆኑ ማሽኖች ሲፈበረኩ ክብደትን ለመቆጣጠርና በተለይ ለመድፍና ሚሳይል አረር ጫፎች ላይ በማድረግ ጥቅም ላይ ይውላል (ይህም ታንኮችንና ጠንካራ ምሽጎችን ለመብሳት/መደርመስ እንዲሁም ማቃጠል የሚችል በመሆኑ ነው)። ይህ ተረፈ-ምርት - depleted uranium - የጋማና የኤክስሬይ ጨረራን በጥሩ ሁኔታ ለመከለል ሥራ (shielding) ላይም ይውላል። ሆኖም የአልፋን፣ ቤታና ኑትሮን ጨረራን ለመከለል አያገለግልም። 

U-238 እንደ U-235 በኑክሌር ማብላያ ውስጥ በኑትሮን ሲመታ ፊሽን በቀጥታ ማድረግ አይችልም። ሆኖም በቂ የኢነርጂ መጠን ያለውን ኑትሮን በመያዝ/በመዋጥ (neutron capture reaction ይባላል) ወደ Pu-239 በመቀየር ልክ እንደ U-235 ፊሽን የሚያደረግ አይሶቶፕ ይቀየራል። በመሆኑም U-238 እንደ U-235 (ወይም Pu-239) fissile ሳይሆን fertile ይባላል። (ማስታወሻ፣ fissile የሚባሉት የአቶም ቁጥራቸው ጎዶሎ መሆኑን ልብ ይበሉ።)

ዩራንየም-238 አንዱ በተፈጥሮ የሚገኝ ራዲዮአክቲቭ ቁስ ሲሆን አልፋ እኑሶችን (የአልፋ ጨረራ) የሚፈጥር/የሚለቅ ነው። 

የዩራኒየምን ማዕድን ከወጣ በኋላ ተፈጭቶ በኬሚካል ዘዴ ዩራኒየሙ እንዲለይ ይደረጋል፣ ይህም በተለምዶ ‘ቢጫ ኬክ’ (‘yellow cake’ - urania - ammonium diuranate) ተብሎ የሚታወቀው ሲሆን፣ ይህንን ወደ ፊዩል ማዘጋጃ ፋሲሊቲ በመላክ እንደ ኃይል ጣቢያው የማብላያ ዲዛይን መሰረት የኒውክሌር ፊዩል ይዘጋጃል።




#Article 382: ሞዚላ ፋየርፎክስ (164 words)


የፋየርፎክስ ተቀጣዮች በአብዛኛው በጃቫ ስክሪፕትና በኤክስዩኤል የሚፃፉና በፋየር ፎክስ ላይ ተደምረው የሚሰሩ ፕሮግራሞች ናቸው። የፋየርፎክስ ተቀጣይ አፃፃፍ ከድረ ገፅ አፃፃፍ ጋር ተመሳሳይ ቢሆንም፡ የፋየርፎክስ ተቀጣይ ልክ እንደፋየርፎክስ አካል ሆኖ ስለሚታይ ከድረገፅ ጃቫ ስክሪፕት የሰፋ የመግቢያ መብቶች አሉት። ቢሆንም፡በተለይ ከፋየርፎክስ ተተካይ ጋር ሲነጻጸር በብዛት በጥቅም ላይ የሚገኘው የማዳቀል መንገድ ተቀጣዮች ላይ መሰረታዊ ቁጥብና ይፈጥራል። በዚህ የማዛመድ ዘዴ፡ ተቀጣዩ ከፋየርፎክስ ነባር ክንዶች አንዱ ላይ በመሰካትና ተዛማጅ የስራ ችሎታውን በማብዛት ያራዝመዋል።

የፋየርፎክስ ተተካይ ኮምፓይል የተደረገ፡ ከተጀመረበት ከNPAPI የተላለፈ ሎድ የሚደረግ ሞጁል ነው። ተተካይ ከፋየርፎክስ ፕሮሰስ ክልል ውጪ መኖር የሚችል ሲሆን፡ በጣም የሚታወቁት ምሳሌዎች ፍላሽና ጃቫ የፋየርፎክስን ስራ የሚሰሩት የድረገጹ መሰረታዊ አካል የሆነው የHTML5ን ካንቫስ ሳይሆን፡ የቪውፖርት ክፍለመስኮት ወይም ደግሞ የካንቫስ ክፍለመስኮት በመጠየቅና ስራውን እራሳቸው፡ በብዛት ከፋየርፎክስ በተገለለ ሁኔታ በመስራት ነው።

እነዚህ ደንቦች፡ በ፪፭፮ ካራክተሩ ASCII፡ የተራዘመውን ASCII (ከ፩፪፰ እስከ፪፭፭) ጨምሮ ማለት ነው፡ በ፪፭፮ ካራክተርስ እንደገና ለመፍጠር ላልተቻሉ ፊደላት መፍትሄ ተብለው በተለያዩ ኮሚቴዎች በየቅል የተዋቀሩ ደንቦች ናቸው። ከዛ ደግሞ፡ እንደፋየርፎክስ ላሉ ሁሉገብ ግብአቶችና ከፕሮግራሚንግ አስተያየት ለአንዱ ማሽን የተፃፈው በየትኛው ማሽን እንደሚነበብ የማይታወቅበት ጊዜን ጨምሮ ግን፡ ግር የሚያሰኙ ናቸው። 




#Article 383: ሪቻርድ ኒክሰን (114 words)


ሪቻርድ ሚልሆስ ኒክሰን (ከጃንዌሪ 9፣ 1913 እ.ኤ.አ. እስከ ኤፕሪል 22፣ 1994 እ.ኤ.አ. የኖሩ) ከ1969 እስከ 1974 እ.ኤ.አ. (1962-1966 ዓ.ም.) ባለው ጊዜ ውስጥ 37ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት በመሆን አገልግለዋል።

ከአሜሪካ ፕሬዚዳንቶች ማዕረጋቸን የተዉት እሳቸው ብቻ ሆነው፤ ምክትላቸው ጄራልድ ፎርድ የዘመናቸውን ትርፍ ጨረሱ። 

መንግሥታቸው በሁከቶች የተመላ ነበር። ከመጀመሩ ቀዳሚው ሊንደን ጆንሰን ጦርነት በቬት ናም አወረሷቸው። ይህም ጦርነት በአሜሪካ ውስጥ ብዙ ተቃራኒዎች ነበሩት። ኒክሰን ግን ጦርነቱን ስላልጨረሱት፣ ነገር ግን ወደ ላኦስና ካምፖድያ ስላስፋፉት፣ ለሰላም የሚጮህ ወገን በሃይል ሠለፉ። በሠልፎቹ ጫፍ በኤፕሪልና በመይ 1971 እ.ኤ.አ.፣ በዋሺንግቶን ዲሲ የጸረ ጦርነት ሰልፈኞች እጅግ በዙና ከተማው ተሞላባቸው። ሠራዊቱ ተጠራና ፖሊሶቹ ከ12 ሺ በላይ ያዙ። ኒክሰን ከዚህ በኋላ ጦርነቱን አስጨረሱ፣ ለሁለተኛ ዘመን በ1972 እ.ኤ.አ. ተመረጡ። በዚህ ዘመን በዋተርጌት ቀውስ በወንጄል ተከሰሱና ማዕረጋችውን ተዉ። 




#Article 384: ማንችስተር ዩናይትድ (125 words)


ማንችስተር ዩናይትድ የእግር ኳስ ቡድን ሲሆን በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውስጥ ዋና ተካፋይ ነው። የሚጫወተው በራሱ ሜዳ ኦልድ ትራፎርድ ውስጥ ነው። ክለቡ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 20 የሊግ ዋንጫዎችን በማንሳት ሪከርድ ያለው ሲሆን 12 ጊዜ የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫ በማንሳትም ታሪክ ያለው ክለብ ነው። በሀብት እና በደጋፊ ብዛት ታላላቅ ከሆኑት የአለማችን ውጤታማ ክለቦች አንዱ ነው። ይህ ቡድን በቅጽል ስሙ ቀያይ ሰይጣኖች ወይም በእንግሊዝኛው The Red Devils በመባል ይታወቃል።
ክለቡ የተመሰረተው ቤ.አ.አ. 1878 Newton Heath LYR F.C. በሚባለው የመጀመሪያ መጠሪያው ነበር። ከዚያም የሀገሪቱን ሊግ የተቀላቀለው እ.አ.አ. በ1892 ነበር. ከ1938 እ.አ.አ. ጀምሮ የሀገሪቱ ዋና የእግር ኳስ ክፍል መጫወት (ከእ.አ.አ. 1974-75 አመት በስተቀር) ጀመረ። የአውሮፓን ዋንጫ በእ.አ.አ. 1968 በማሸነፍ እና የሶስትዮሽ ዋንጫን እ.አ.አ. በ1999 በማሳካት የመጀመሪያው የእንግሊዝ ክለብ ነው። እ.አ.አ. በኖቬምበር 6፣ 1986 የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ይባላሉ።




#Article 385: መርካቶ (150 words)


መርካቶ ገበያ ወይም አዲስ መርካቶ (ከጣልያንኛው ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙ ደግሞ ገበያ ማለት ነው።) በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ ውስጥ በዋነኛነት አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ እና በአጎራባች አከባቢዎች የተካለለ ሠፊ ገበያ ነው። መርካቶ በአፍሪካ ሠፊው ገላጣ ገበያም ነው። በዚህም በብዙ ካሬ ኪሎሜትር በሚቆጠር መሬት ላይ ከ13,000 በላይ ሠዎችን በ7,100 የሚደርሡ የንግድ ሠቆች ውስጥ የያዘ እንደሆነ ይገመታል።

በዚህ ገበያ ውስጥ በአብዛሃኛው ጊዜ የሚዘወተሩት በተለምዶ ሀገር በቀል የሆኑ የጥራጥሬ ምግቦች እና ፍራፍሬዎች እንዲሁም በዋነኛነት ቡና ናቸው። ይህ ገበያ የተዋቀረው በዘረኛ የጣልያን ገዥዎች ፖሊሲ ሲሆን ያደረጉትም ታሪካዊውን የቅዱስ ጊዮርጊስ መርካቶ ለጣልያናዊያን ብቻ በመከለል ዋናዎቹን የአረብ ነጋዴዎች ወደ መዕራብ ከግማሽ ማይል በላይ ርቀው እንዲነግዱ በማስገደድ ነበር። ቀስ በቀስ እነዚህን የአረብ ነጋዴዎች የሀገሪቱ ተወላጅ በሆኑ ነጋዴዎች በመተካት ከእ.አ.አ. 19 60 ጀምሮ ሀገርኛ ቃና ያለው ገበያ ሊሆን ችሏል።
የአዲስ አበባ መርካቶ ከ120 በላይ ሡቆች እና አንድ ትልቅ የገበያ አዳራሽ (በውስጡ ከሠባ አምስት በላይ ሠቆችን የያዘ) ይዟል። በዚህ ቦታ ውስጥ የማይዘነገት የአንዋር መስጊድ እና የራጉኤል ቤተክርስቲያን ይገኛሉ።




#Article 386: ጅማ ዩኒቨርስቲ (415 words)


ጅማ ዩኒቨርስቲ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አንዱ ነው። ይህ ተቋም የሚገኘው በኦሮሚያ ክልል፣ ጅማ ዞን (ጅማ) ውስጥ ነው። ተማሪዎችን በተለያዩ ዘርፎች በዲግሪ እና በተለያዩ ደረጃዎች ያሠለጥናል። በቀድሞው ስሙ ጅማ የግብርና ኮሌጅ እና የጅማ የጤና ሳይንስ ተቋም በጋራ የነበረ ሲሆን ከታኅሣሥ 1992 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ ዩኒቨርስቲ ሊያድግ ችሏል። ዋናው ካምፓስ የሚገኘው ከቀድሞው የጅማ ንጉስ አባ ጅፋር  ቤተ መንግስት ቀጥሎ ነው።

ጅማ ዩኒቨርሲቲ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 63/1999 እ.ኤ.አ. ዲሴምበር 22 ቀን 1999 ዓም በወቅቱ የግብርና ኮሌጅና የጤና ሳይንስ ኢንስቲተዩት ተብለው የሚጠሩ ሁለት ተቋማት በመዋሃድ የተቋቋመ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ነው፡፡ ዛሬ በአገሪቱ ካሉ አንጋፋና በተለይ በማህበረሰብ አቀፍ ትምህርት ፍልስፍናው ፈር-ቀዳጅና መሪ የሆነው ጅማ ዩኒቨርሲቲ “We Are in The Community” በሚለው መርህ የታወቀ ተቋም ሲሆን ከምስረታው ጀምሮ በስልጠና፣ በምርምርና በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ በርካታ ድሎችን ያስመዘገበና በትምህርት አሰጣጥ ጥረቱ ለአምስት ተከታታይ ዓመታት በኢትዮጵያ አንደኛ የወጣ ብቸኛ ተቋም ነው፡፡

ተቋሙ በምስረታው ወቅት በጥቂት የጤና፣ ህክምናና ግብርና መስኮች በአብዛኛው ዲፕሎማ መርሃ-ግብሮችን በማስተማር ላይ ተወስኖ የነበረ ሲሆን ይህ ሁኔታ ዛሬ በአስገራሚና ፈጣን ለውጥ ተቀይሮ በዚህ ዓመት በ62 የቅድመ-ምረቃ፣ በ139 ሁለተኛ ዲግሪና በ35 ሶስተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች 40587 ተማሪዎች ተቀብሎ ያስተምራል፡፡ አምስት ካምፓሶች ያሉት ጅማ ዩኒቨርሲቲ በአጠቃላይ 7864 ሰራተኞች ያሉት ሲሆን ከዚህ መካከል 6016 የአስተዳደርና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞችና 1848 ኢትዮጵያዊ መምህራኖችን የያዘ ግዙፍ ተቋም ነው፡፡

ዋናው ካምፓስ ውስጥ የዩኒቨርሲቲዉ የበላይ አመራር፤ ማዕከል ቢሮዎች፣ ሦስት ኮሌጆችና የተቋሙ መማሪያ ሆስፒታል የሚገኙ ሲሆን ከዋናው ግቢ በ4 ኪሜ ርቀት ላይ የሚገኘው የግብርናና እንስሳት ህክምና ኮሌጅ ስምንት ትምህርት ክፍሎች ያሉት ካምፓስ ነው፡፡ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ኪቶ ፉርዲሳ ካምፓስም ከዋናዉ ግቢ በ6 ኪሜ ርቆ የሚገኝ ሲሆን ከዋናው ግቢ አጥርና መንገድ ባሻገር በስተደቡብ የሚገኘው የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ካምፓስ 4 የትምህርት ክፍሎች ይዟል፡፡ ከጅማ ከተማ 42 ኪሜ ርቆ የሚገኘው የአጋሮ ካምፓስ በግንባታ ላይ ሲሆን ይህም አምስተኛው ካምፓስ ነው፡፡

በአገሪቱ እጅግ ልዩ በሆኑ የትምህርት ፕሮግራሞች በተለይም በባዮሜዲካል ኢንጂነሪንግና ጥርስ ህክምና ትምህርት ዘርፎች ፈር ቀዳጅ የሆነው ጅማ ዩኒቨርሲቲ የላቀ ትምህርት ባህልን በመገንባትና መሰረታዊ ችግሮችን መፍታት የሚያስችል ምርምሮች በማካሄድ ዓለማቀፋዊነትን በማስፋፋትና መላሽ ሰጪ አገልግሎቶች በመስጠት በርካታ ስራዎችን እያከናወነ ነው፡፡ አገራችንን ከድህነት አረንቋ ለመታደግና መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገራት ተርታ ለማሰለፍ በሠው ኃይል አቅም ግንባታ ዘርፍ አያሌ ሚና በመጫወት ላይ ያለው ጅማ ዩኒቨርሲቲ መሠረታዊ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ተመርኩዞ የተቀናጀ፣ ቀልጣፋና ስትራቴጂካዊ ስልቶችን ማስተግበር የሚያስችል ዓመታዊ ዕቅድ በማውጣት በርካታ ስራዎች በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ የዩኒቨርሲቲያችን ዋነኛ ተልዕኮ የሆኑትን መማር/ማስተማር፤ ምርምርና የህብረተሰብ አገልግሎት ተልዕኮዎች ለማሳካት ጥረት እየተደረገ ነው፡ ፡በተመሳሳይ ማህበረሰባችን የራሱን ችግሮች በራሱ እንዲፈታ ለማስቻል፣ የኢንቬስትመንት አቅማችንን ለመገንባትና ከባለድርሻዎቻችን ጋር እኩል ተጠቃሚ የሚያደርጉ ትስስሮችን በመፍጠር ራዕይ ዕውን ለማድረግ ርብርብ እየያደረገ ሲሆን በዚህም አዳዲስ ዕውቀትና ክህሎት ማንጨት የሚያስችሉ አመቺ ሁኔታዎች ተፈጥረዋል፤ ለአገሪቱ አንገብጋቢ ችግሮች አዎንታዊ ለውጥ ማምጣት በሚያስችሉ የትኩረት መስኮች ግንባር ቀደም ሚና በመጫወት ላይ ይገኛል፡፡ 




#Article 387: ሳትያግራሃ (178 words)


ሳትያግራሃ (ሳንስክሪት፦ सत्याग्रह satyāgraha) ማለት ማህተማ ጋንዲ የጀመሩት የሰላማዊ መቃወም ዘዴ ነው። ጋንዲ በሕንድ ነጻነት እንቅስቃሴ እንዲሁም ከዚህ ቀድሞ በደቡብ አፍሪካ ትግል ይጠቀማቸው ነበር። ከዚህ በላይ የሳትያግራሃ ፍሬ ሂሳብ ለኔልሰን ማንዴላ፣ ለማርቲን ሉተር ኪንግና ለሌሎች ትግል መሪዎች ከፍተኛ ተጽእኖ አሳድሯል። ሳትያግራሃ የሚፈጽመው ሰው ሳትያግራሂ ይባላል። 

ሳትያግራሃ የሚለው ቃል ከሳንስክሪት ቃላት ሳትያ (ዕውነት) እና አግራሃ (ጽናት ወይም አጥብቆ መያዝ) ይመጣል። ለጋንዲ፣ ሳትያግራሃ ዝም ብሎ ከመቃወም በላይ ሲሆን ሰላማዊነታቸው ብርታታቸው ሆነ። እሳቸው እንዳሉት፣ ዕውነት ፍቅር ነው፣ ጽናትም ኃይል ነው፣ ስለዚህ የሳንስክሪት ስም ከእውነትና ከፍቅር (ወይም ሰላም) የተወለደው ሃይል መሆኑን ያሳያል አሉ። ሌላ የሰጡት ትርጉም «የፍቅር ሃይል» ወይም «የነፍስ ሃይል» ነበረ። 

አብዛኛው ጊዜ «ትግል» ማለት ባላንጣውን ማሸነፍ - ወይም ዓላማውን በመከልከል ወይም ባላንጣው የከለከለውም ዓላማ በመፈጸም - ይሆናል። በሳትያግራሃ ግን አላማው እንዲህ አይደለምን። በዚህ ፋንታ፣ ጋንዲ እንዳሉ፣ አላማው የበደለኛውን ዐእምሮ መቀይሩ ነው ኢንጂ ማስገደድ አይሆንም። እንግዲህ ማሸነፍ ወይም መከናወን ማለት ከባላንጣው ጋራ ተስማምቶ ምናልባት በደል መሆኑን ያልገነዘቡት እንደ ሆነ በደሉ በደንብ እንዲስተካከል ነው። ይህም ሊያልፍ እንዲመጣ፣ ባላንጣው ለትክክለኛው ፍች መሰናከል መሆኑን እንዲገነዝብ፣ አዕምሮው ሊለወጥ አለበት።

ጋንዲ ሳትያግራህያን እነዚህን ደንቦች እንዲጠብቁ ጠየቁዋቸው፦

ሌላ ጊዜ ጋንዲ ሰባት ቁም ነገር የሆኑት ደንቦች አወጡ። ሳትያግራሂው፦ 




#Article 388: ግመል (128 words)


ግመል ሙሉ ጣት ሸሆኔ ካላቸው እንስሳ የሚመደብ ለማዳ የቤት እንስሳ ወገን ነው። በዋነኛነት ጀርባው ላይ ባለው በስብ የተሞላ አካል (ሻኛ) ይታወቃል። ይህ ሻኛ የአረቦች ግመል በሚባለው ዝርያ ላይ አንድ ብቻ ሲሆን፣ ሌላው ዝርያ በሰሜን ምስራቅ እስያ የሚገኘው ባክትሪያን ግመል ደግሞ ሁለት ነው። በአብዛኛው ደረቅ በረሀ ለመኖር የሚመቻቸው ሲሆን በብዛት በምዕራብ እስያ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ እስያ ይገኛሉ። የሠው ልጅ የሚያለምዳቸው ለወተት ምርት፣ ለስጋ፣ ለግመል ጽጉር ልብስ (በተለይ ከባክትሪያን ግመል) እንዲሁም አልፎ አልፎ ለመጓጓዣ ስለሚጠቅሙ ነው።

የግመል ወተት በብዙ አገራት ይገዛልና ይጠጣል። በአረቢያ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ሶማሊያ፣ ሞሪታኒያና አሜሪካ በሱቅ ይሸጣል።  የግመል ወተት የሚያስገኙ ዋና አገራት ሶማሊያ፣ ኬንያ፣ ማሊ፣ ኢትዮጵያ፣ ኒጄር፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ እና ሱዳን ናቸው። 

የግመል ሥጋ ደግሞ ለብዙ አገራት ምግብነት ከፍ ያለ ዋጋ አለው። በተለይ የግመል ሥጋ የሚበላው በኤርትራ፣ ኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ፣ ጂቡቲ፣ ሱዳን፣ ግብጽ፣ ሊብያ፣ ሶርያ፣ አረቢያና ካዛክስታን ይበላል።  




#Article 389: ዓሣ (302 words)


አሳ ማንኛውም በውሃ ውስጥ የሚኖር ባለጥንድ ስንጥብ እና ብዙ ነጠላ ስንጥቦች የጀርባ አጥንት ያለው እንስሳ ነው። አብዛሀኛዎቹ የአሳ ዝርያዎች ደመ ቀዝቃዛ ሲሆኑ እንደ ውሀው መጠነ ሙቀት የራሳቸውን ሰውነት አስማምተው መኖር ይችላሉ።

ትልቅ-አፍ ባስ የሚባለው የለጋ ውሃ የዓሣ ዝርያ ሲሆን፡ በአማካኝ እስከ 11ኪሎ ድረስ ይደርሳል። ባስ የሠንፊሽ፡ ማለትም የፀሃይ ጨረር መሳይ ስንጥብ ያላቸው አሳዎች ቤተሰብ ነው።

ሙሉ ለሙሉ ያደገ የጅረት ቀስተደመና ትራውት ዓሣ ከ0.5 እስከ 2.3ኪሎ ሲመዝን፤ በሀይቅ ውስጥ የሚኖር ቀስተደመና ትራውት ደግሞ እስከ 9.1ኪሎ ድረስ ይመዝናል።  

ካትፊሽ (አምባዛ)

ሳመን በለጋ ውሃ ተወልደው ወደ ውቅያኖስ ከሚፈልሱት የዓሣ ዝርያዎች አንዱ ነው። ሆኖም በርካታ የሳመን መንጋዎች እድሜያቸውን ሙሉ በለጋ ውሃ ለማሳለፍ የተወሰኑ በመሆናቸው የለጋ ውሃ አኗኗር ዘዴዎችን መርጠው እንደሚኖሩ ይታወቃል። የሳመን እንቁላል፡ 

ያደገ ናይል ፐርች በአማካኝ እስከ 121–137ሴ.ሜ. የሚደርስ የዓሣ ዝርያ ሲሆን፡ በጣም ትልቅ የሚባለው እስከ 200ኪሎ ድረስ ይመዝናል።

ብሉጊል የሠንፊሽ ቤተሰብ የለጋ ውሃ ዓሣ ነው። ብሉጊል፡ ወይንም ሰማያዊ-ስንጥብ የሚባለው የስንጥቦቹ ማለቂያ ደማቅ ሰማያዊ ስለሆነ ነው።

የለጋ ውሃ ሎብስተር (ጐርምጥ)፣ ክሮውፊሽ፣ ወይንም ደግሞ ክሬይፊሽ ተብሎ የሚታወቀው እስከ 17.5ሴ.ሜ ድረስ ይረዝማል።

ተላፒያ ወደመቶ የሚሆኑ የተለያዩ ዓሣዎች ቤተሰብ የጋራ መጠርያ ነው። ተላፒያ በጠቅላላው ከ21 ዲግሪ ሴንቲግሬድ የማያንስ ሙቀት ያለው ለጋ ውሃ ውስጥ የሚኖሩ ዓሣዎች ናቸው።

ክራፒ፡ ወይንም ሳክ-ኦ-ሌ፡ የሠንፊሽ ቤተሰብ ሲሆን፡ ከለጋ ውሃ ዓሣዎች በጣፋጭነቱ ይታወቃል።

ስትራይፕድ ባስ በአማካኝ ከ67 እስከ100ሴ.ሜ. ረዝሞ ከ4.5 እስከ14.5 ድረስ የሚመዝን የሮክፊሽ አይነት ነው። ስትራይፕድ ባስ ሥጋ ነጭ ቀለም፣ ልዝብ ጣዕምና መካከለኛ ገጽታ አለው፤ 
እጅግ በጣም ሁለገብ በመሆኑም በተለያየ አይነት መልክ ማብሰል ይቻላል፦ በመጥበሻ መለብለብ፣ በግሪል መጥበስ፣ በእንፋሎት ማብሰል፣ በ ፖች ማድረግ፣ አሮስቶ፣ በኦቨን ብሮይልድ፣ ሳውቴ የተደረገ፣ ፍራይድ ወይንም ደግሞ ባተር ተደርጎ ፍራይድ። የስትራይፕድ ባስ ሥጋ ጥሬ ወይንም ደግሞ ፒክል አድርጎም መመገብ ይቻላል።

ማከረል የኦሜጋ-3 ዘይት ይዘቱ ከፍተኛ ስለሆነ፡ በዓሣ አጥማጆች በጣም የሚፈለግ የዓሣ ዝርያ ነው። ማከረል በማንኛውም ውቅያኖስ የሚገኝ ሲሆን፡ በ2009እ.ኤ.አ፡ ከአምስት ሚሊዮን ቶን በላይ ማከረል ዓሣ ተጠምዿል።

የአውሮፓ ባስ የውቅያኖስ ዓሣ ሲሆን፡ አንዳንድ ጊዜ ግን በለጋ ውሃ ውስጥ ይገኛል።

በአለም ላይ ካለው ሽርምፕ (ሸርጥ አሣ) ወደሩብ የሚሆነው በለጋ ውሃ ይገኛል። 




#Article 390: ሊያ ከበደ (546 words)


ሊያ ከበደ (እንግሊዝኛ: Liya Kebede) የተወለደችው በእ.አ.አ. ጃንዌሪ 3፣ 1978 ሲሆን ታዋቂ ኢትዮጵያዊ ሡፐር ሞዴል፣ ተዋናይት፣ የልብስ ዲዛይነር እንዲሁም የአለም የጤና ድርጅት በእናቶች፣ አዲስ በሚወለዱ ህፃናት እና የሕፃናት ጤና ጥበቃ አምባሳደር ናት፡፡ ሊያ Vogue በተባለ የአሜሪካ የፋሽን መፅሔት ላይ ሁለት ጊዜ የውጭ ሽፋን ላይ በዋናነት በመውጣት ትታወቃለች። እንደ ፎርብስ መረጃ መሠረት በእ.አ.አ. 2007 አመት ከዓለማችን 11ኛ ከፍተኛ ተከፋይ ሡፐር ሞዴልነት ደረጃን አግኝታለች።

ሊያ ከበደ የተወለደችው በኢትዮጵያ ውስጥ በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ እ.አ.አ. ጃንዌሪ 3፣ 1978 ነው። አንድ የፊልም ዳይሬክተር ነበር Lycee Guebre Mariamን በመታደም ላይ ሳለች ያያት እናም ከፈረንሣይ የሞዴል ባለሙያ ጋር ያስተዋወቃት። ጥናቷን ካጠናቀቀች በኋላ ነበር ከፐርሺያ ኤጀንሲ ጋር ለመስራት ወደ ፈረንሣይ ያቀናችው። በኋላም ወደ ኒው ዮርክ ከተማ ተዛወረች። እናም የውጭው አለም የፋሽን መድረክ ከሀገርኛው ጋር ፍፁም የተለያየ መሆኑን ተገነዘበች።

ሊያ ትልቁ ወደሆነው የህይወቷ ምዕራፍ የተሸጋገረችው ቶም ፎርድ የተባለ ግለሠብ Gucci ለተባለ የክረምት ፋሽን ትርኢት እ.አ.አ. 2000 ላይ እንድትካፈል ከጠየቃት በኋላ ነበር። የሊያ እውቅና እጅጉን የጨመረው በእ.አ.አ. 2002 Paris Vogue መፅሔት እትም ላይ የውጭ ሽፋን ከሠጣት እና ሙሉ ይዘቱን ማለት ይቻላል ስለ እርስዋ ካደረገ በኋላ ነበር።

ሊያ በተመሳሳይ በጣልያን፣ ጃፓን፣ አሜሪካ፣ ስፔን፣ ፈረንሣይ Vogue መፅሔት እትሞች ላይ እና በTime's Style  Design ላይ የሽፋን ቦታን በተለያዩ ጊዜያት አግኝታለች። እ.አ.አ. በ2003 ለEstée Lauder ኮስሞቲክስ በ57 አመት ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊ ተወካይ በመሆን የ3 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ፈርማለች።

በፎቶ ትዕይንቶች ላይ ጎልተው ከሚታዩ ጥቂት የአፍሪካ ሞዴሎች አንዷም ናት። በነዚህም ታዋቂነቶቿ እና በመልካም ተግባሯ እ.አ.አ. በ2005 የአለም የጤና ድርጅት በእናቶች፣ አዲስ በሚወለዱ ህፃናት እና የሕፃናት ጤና ጥበቃ አምባሳደር ሆናለች። እ.አ.አ. በ2005 American Vogue መፅሔት ይህንኑ ሠብዓዊ ተግባሯን በመጥቀስ እና የፊት ገፅ ላይ ምስሏን በማውጣት ከጥቂት ጥቁር ሞዴሎች ተርታ እንድትሰለፍ አስችሏታል። በአንድ ወቅት ሊያ ስለአፍሪካ ስትናገር ይህንን ስሜት የፈጠረብኝ አፍሪካ ውስጥ ተወልጄ ማደጌ ነው። በድኅነት ተከቦ እየኖሩ ስለድኅነት አለማሰብ ፈፅሞ የማይቻል ነገር ነው። ልጅህን በምትወልድበት በዚያችው ደቂቃ ነው ለልጅህ የተሻለች ዓለም ትተህ ማለፍ እንዳለብህ ማሰብ የምትጀምረው ብላ ነበር።

 በጁሌይ 2007 እ.አ.አ. ላይ ፎርብስ በግንቦት 10 ቀን 2010 የታይም መፅሔት እትም ላይ ተፅዕኖ ማሣደር ከሚችሉ 100 የአለማችን ምርጥ ሠዎች (The 100 most INFLUENTIAL PEOPLE IN THE WORLD) ብሎ ካወጣቸው ታዋቂ ሠዎች ስም ዝርዝር ውስጥ ኢትዮጵያዊቷ ሊያ ከበደ አንዷ ነበረች።መፅሔቱ Leaders, Artists, Thinkers እና Heroes በሚሉ ታላላቅ ዘርፎቹ ስር ነው የሠዎቹን ስም ዝርዝር ያሠፈረው። ከሊያ ከበደ ጋር ከተጠቀሡት ታላላቅ ሠዎች መካከል ዲዲዮር ድሮግባ፣ ስኮት ብራውን፣ ጀምስ ካሜሮን፣ ዛሃ ሀዳድ፣ ቤንስቴለር፣ አሽተን ኩቸር፣ ሣራ ፖሊን፣ ቢል ክሊንተን፣ ካትሪን ቢግሎው፣ ሳንድራ ቡሎክ፣ ሳይመን ኮዌል፣ ሀን ሀን፣ ኦፕራ ዌንፍሬይ፣ ባራክ ኦባማ እና ሌሎችም ይገኙበታል።

ሊያ በተለያዩ እንደ The Good Shepherd እና Lord of War የተባሉ የሆሊውድ ታላላቅ ፊልሞች ላይ እንደ አነስተኛ ተዋናይትነት ተሳትፋለች። ነገር ግን በ2009 እ.አ.አ. የትለቀቀው Desert Flower የተሠኘው በመሪ ተዋናይትነት የቀድሞዋን ሡፐር ሞዴል Waris Dirieን በመሆን የተሳተፈችበት ፊልም ከፍተኛ ዕውቅና እንድታገኝ አስችሏታል።

 በጁላይ 2007 እ.አ.አ. ላይ ፎርብስ ለምለም እ.አ.አ. በ2008 የተከፈተ የሊያ ከበደ የልብስ አምራች ድርጅት ነው። ድረ-ገፁ ሲሆን የሀበሻ እጅ ጥበብ ያረፈባቸውን የህፃናትና የሴቶችን ልብሶች ያመርታል። ሊያ ይህን የጀመረችው የኢትዮጵያን ባህል ለማስተዋወቅ እና የሀገሯን ኢኮኖሚ ለማገዝ ብላ መሆኑ ታውቋል። ምርቶቹ በBarney’s፣ J.Crew፣ Net-a-Porter.com እና በሌሎች ቡቲኮች ይሸጣሉ። ሠዎችን እንደመርዳት የሚያስደስት ነገር የለም የምትለው ሊያ ይህ ጅምር ለሀገሯ ትልቅ ለውጥ እንደሚያመጣ ታምናለች።

ሊያ ከበደ የhedge fund ማናጀር ከሆነው ባለቤቷ ኬሲ ከበደ ጋር በትዳር የተሳሰሩት እ.አ.አ. በ2000 ሲሆን የሁለት ልጆች እናት ናት። ስሁል የሚባለው ልጇ በእ.አ.አ. በ2001 የተወለደ ሲሆን ሬይ የተባለችው ልጇ ደግሞ እ.አ.አ. በ2005 ነው የተወለደችው። እ.አ.አ. በ2007 ቤተሠባቸው በኒው ዮርክ ከተማ መኖር ጀመረ። ሊያ ከበደ በግሏ የምታስተዳድረው ሳይት ያላት ሲሆን አድራሻውም ነው። በዚህም ድረ-ገፅ የራሷን ማስታወቂያ እና የዕርዳታ ጥሪዎቿን ለማስተላለፊያነት ትጠቀምበታለች።




#Article 391: የአክሱም ሐውልት (448 words)


 
የአክሱም ሃውልት (እንግሊዝኛ: Obelisk of Axum) ወይም Rome Stele እየተባለ በተለምዶ የሚጠራው በኢትዮጲያ በአክሱም ከተማ የሚገኝ የአለማችን ረጅሙ ትክል የድንጋይ ሃውልት ነው። ይህ ሀውልት 1700 ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን የ24 ሜትር (78 ጫማ) ርዝመት አለው።  160 ቶን የሚመዝነው ይኽው ግዙፍ ድንጋይ መሠረቱ አከባቢ ሁለት የሀሠት በር መሣይ ፍልፍሎች አሉት። የዚህ ሀውልት ጌጥ ይህ ብቻም አይደለም በያንዳንዱ ጎን የመስኮት ቅርጽ የያዙ ፍልፍሎች ሲኖሩት በመጨረሻው ጫፍ ላይ ደግሞ በብረት ፍሬም የታገዘ የግማሽ ክብ ቅርጽ የያዘ ነው።

በአክሱም ዘመነ መንግስት እንዲገነባ የተደረገው ይህ ሀውልት ወይም በእንግሊዝኛው stele የሚባለው በአክሱም ከተማ ከሌሎች መሠል ሀውልቶች ጋር ኢንዲቆም የተደረገው በ4ኛው ምዕተ አመት አካባቢ ሲሆን የወንድ ብልት ምስል ነው። ይህም የጥንታዊ አክሱም ምን ያህል ስልጣኔ እንደነበራት ጠቋሚ ነው። ከኩሻይቲክ የሜሮይ አገዛዝ የተወሰደ እንደሆነ የሚነገርለት ይህ ሀውልቶችን የማቆም ስራ አሁንም ድረስ በአከባቢው ተመሳሳይ ስራዎችን መመልከት ይቻላል። እነዚህ ሀውልትኦች የሚቆሙት በመሠረታቸው ለሚቀበሩ ንጉሳዊ ቤተሠቦች እንደሆነም ታውቋል። በዚህም ከፍተኛ ስልጣን የነበራቸው መሳፍንቶች መቃብር ላይ የሚቆሙት ሀውልቶች በብዛት በተፈለፈሉ የሀሰት በር እና መስኮቶች ያጌጡ ናቸው። እንዲሁም የሟቹ ንጉሳዊነት በቀነሠ ቁጥር በመቃብሩ ላይ የሚቆሙት ሀውልቶችም ውበት (የሚፈለፈሉት የሀሰት በር እና መስኮት መሠል ቅርጾች ብዛት) በዚያው ልክ ይቀንሳል። ለዚህም ነው ብዛት ያላቸው ቅርጽ አልባ ሀውሎቶችን በየቦታው መመልከት የሚቻለው። ትልልቅ የሚባሉት ደግሞ አነስተኛ ቁጥር አላቸው። 

 
ከሀውልቶች ሁሉ በመጨረሻ አክሱም ላይ ማለትም በ4ኛው ክፍለ ዘመን እንደቆመ የሚታወቀው የንጉስ ኢዛና ሀውልት ነው።  ኢዛና ይህን ጣኦታዊ የሆነ ሀውልቶችን የማቆም ስራ እንዲቆም እና ክርስቲያናዊነት በኢትዮጵያ እንዲስፋፋ በግሉ ክርስቲያን በመሆን ጥሯል። አብዛሀኛዎቹ ትክል ድንጋዮች በመሰረት ጥንካሬ ማነስ የወደቁ ሲሆን ከነዚህም መካከል ተጠቃሽ የሚሆነው በእርዝመቱ ተወዳዳሪ የሌለው (የ33 ሜትር ርዝማኔ ያለው) ታላቁ ሀውልት በመሬት ላይ መውደቁ ነው። በሀውልቶቹ ላይ የደረሱት ችግሮች ብዙ ናቸው። ከነዚህም ውስጥ በተደጋጋሚ የሚከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ (የአክሱም ከተማ ለመሬት መንቀጥቀጥ በአንፃራዊ ሁኔታ የተጋለጠች ነች።) እንዲሁም በግራኝ አህመድ የእስላማዊ ዘመቻ ወይም የአዳል ጦርነት (ከእ.ኤ.አ. 1529 እስከ 1543 ድረስ የቆየው) እንዲፈርሱ ትዕዛዝ አስተላልፎ ነበር። በ19ኛው ምዕተ-አመት ከዋና ዋናዎቹ የንጉስ ሀውልቶች መካከል የንጉስ ኢዛና ሀውልት ብቻ ሳይወድቅ ተገኝቷል።

በ1935 እ.ኤ.አ. ጣልያን ኢትዮጵያን በወረረችበት ጊዜ ይህን ሀውልት በጊዜው በነበረው የፋሽስት ኢጣሊያ ገዝ ትዕዛዝ መሰረት የጣልያን ወታደሮች የኣክሱምን ሓውልት ከወደቀበት ኣንስተው ወደ ሮም ወሰዱት። በዚህ ጊዜ የፋሺስት አገዛዝ እንደ ጦር ምርኮ እና የሮም ግዛት መስፋፋት ምልክት አድርጎ በመውሰድ በሮም አደባባይ ላይ እንዲተከል አድርጓል (ምንም እንኳን አገዛዙ በአምስት አመታት ወስጥ የነበረ ቢሆንም ይህም እ.ኤ.አ. ከ1935 በ1941 ንጉሠ ነገስት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ወደ ኢትዮጵያ እስከተመለሱበት ጊዜ ያለው ማለት ነው)።

ሁለተኛው የዓለም ጦርነት እንዳለቀ ጣልያን የዘረፈችውን የኣክሱም ሃውልት ለኢትዮጵያ እንድትመልስ በተስማማችው መሠረት ላለመፈጸም እስከ የካቲት ፲፱፻፷፮ ዓ.ም. ብዙ ግለሰቦች ቢማጸኑም ኣሻፈረኝ ኣለች። የመጨረሻውም ምክንያት ጣልያን ገንዘብ፣ ኣሜሪካ ኣውሮፕላን ስለከለከሉ ነበር። በእነዚህ ምክንያቶች ያልተደሰቱት ዶ/ር ኣበራ ሞላ ኢንተርኔትን በመጠቀም የመላኪያ ገንዘብ ለማስባስብና ሐውልቱንም በትናንሹ ኣስቆርጦ መላክ እንደሚቻል ለጣሊያኖች ካሳወቁ በኋላ ኣጣብቂኝ ውስጥ የገቡት ጣልያኖች እራሳቸው ወጪውን ከፍለው ከወሰዱበት እንደሚመልሱት ተስማሙ። በእዚሁ መሠረት የጣልያን መንግሥት ወደ ኣሥር ሚሊዮን ዶላር ኣውጥቶ ሐውልቱ ኣክሱም ከተማ ተመልሶ ተተክሎ ነሓሴ ፳፱ ቀን ፳፻ ዓ.ም. ተመርቋል።

የሓውልቱ  ከሮም ወደ ኢትዮጵያ ኣመላለስ

   
 




#Article 392: መጽሐፈ ኩፋሌ (237 words)


መጽሐፈ ኩፋሌ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዲዩትሮካኖኒካል መጻሕፍት አንዱ ነው። በሌሎቹ አብያታ ክርስትያናት ግን ዛሬ የማይቀበል መጽሐፍ ወይም ሲውዴፒግራፋ ይባላል።  ነገር ግን ለቀድሞው የቤተ ክርስቲያን አበው ታውቆ የጥቅስ ምንጭ ሆነላቸው። የመጽሐፉ ግሪክ ትርጉም የሚታወቀው ከቅዱስ ኤፒፋንዮስ ጥቅሶች ባቻ ሳይሆን እንዲሁም በዩስቲን ሰማዕት፣ በኦሪጄን፣ በዲዮዶሮስ ዘአንጥያክያ፣ በኢሲዶር ዘሰቪላ፣ በአሲዶር ዘእስክንድርያ፣ በዩቲክዮስ (አቡነ እስክንድርያ)፣ በዮሐንስ ማላላስ፣ በጊዮርጊስ ሱንኬሎስና በቄድሬኖስ ጥቅሶች በከፊል ይታወቃል።  

ሆኖም መጽሐፉ በአይሁድ ሳንሄድሪን ከ1ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ እንደ ቅዱሳን መጻሕፍት አልተቀበለም ነበር።  አንዳንድ ክፍል በቁምራን ዋሻ በ1939 ዓ.ም. እስከተገኘ ድረስ፣ የመጽሐፉ ዕብራይስጥ ትርጉም በሙሉ ጠፍቶ ነበር።  ስለዚሁ ሁኔታ (የዕብራይስጥ ትርጉም በማጣት) መጽሐፉ በኋላ ዘመን በሮማ ቤተ ክርስቲያን አለቆች አልተቀበለም። ሆኖም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ዘንድ እንዲሁም በቤተ እስራኤል አይሁዶች ዘንድ፣ መጽሐፉ በግዕዝ ስለ ተገኘ እስከ ዛሬ ድረስ ቅዱስ ተብሎ ተከብሯል። 

መጽሐፉ እንደሚለው መላእክት የዓለሙን ታሪክ ከፍጥረት ጀምሮ እስከ ኦሪት ዘጸአት ድረስ (2,410 ዓመታት ሲቆጠሩ) ለሙሴ በደብረ ሲና ይተርካሉ።  ዘመናት በኢዮቤልዩ ወይም በ49 ዓመታት ይከፋፈላሉ።  ኢያንዳንዱ ኦዮቤልዩ 7 ሱባዔ ወይም የዓመት ሳምንት (7 አመት) ነው። ከማየ አይህ አስቀድሞ ደቂቃ ሴት ከእግዚአብሔር አምጸው ወደ ቃየን ልጆች እንደ ሔዱና እንደ ከለሱ ይላል። ክልስ ልጆቻቸውም ክፉ ረጃጅሞች (ናፊሊም) ሆነው በማየ አይህ ጠፉ። ከዚህ በኋላ የኖህን ልጆች አሳቱ። ጣኦት ሠሩ፣ መንግሥት አጸኑ፣ የኖህ ልጆች ምድርን ሁሉ ያካፈላሉ፣ የባቢሎን ግንብ ከወደቀ ቀጥሎ ወደ ርስቶቻቸው ተበተኑ።  መላእክትም ለአብርሃም ቅዱስ ቋንቋን አሳውቁት። 

ከተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ውጭ እንደ «ሲውደፒግራፋ» በመቆጠሩ አንዳንድ ሊቃውንት በ150 ዓክልበ. ገደማ እንደ ተሠራ ይገምታሉ።  ለዚሁ አስተሳሰብ ግን ምንም ማስረጃ አልተገኘም።

ስዕል:3-apoch-2-cr.pdf|thumb|left|300px| የሚያዩት ገጽ ላይ ወይም እዚህ ላይ   በመጫን የመጽሐፉን  ገጾች   ማንበብ ይችላላሉ|page=11




#Article 393: ኮምፒዩተር ምህንድሥና (299 words)


የኮምፒዩተር(መንሰላስል)  ምህንድስና  የኤሌክትሪክና እና የኤሌክትሮኒክስ ምህንድስናን ከኮምፒዩተር ሳይንስ ጋር አዋህዶ የሚያጠና የእውቀት ዘርፍ ነው ። የኮምፒውተር መሃንዲሶች ብዙ ጊዜ የኤሌክትሮኒክስ ምህንድስናን፣ የሶፍትዌር እቅድና የተጨባጭ እና የማይጨበጥ የኮምፒውተር ክፍል ውህደት በማጠቃለል ያጠናሉ። እነዚህ መሃንዲሶች በብዙ አይነት የማንሰላሰል (ኮምፒውቲንግ) ስራ ላይ ይሳተፋሉ። ለምሳሌ በማይክሮፕሮሰሰር፣ በግል መንሰላስል (ኮምፒውተር) እና በታላላቆቹ መንሰላስሎች (ሱፐር ኮምፒውተሮች) ትልም ላይ ዋና ተዋንያን ናቸው። አልፎም ተርፎም በነዚህ ኮምፒወተሮች የሽቦወች ዑደት (ሰርኪዩት ዲዛይን) አቅድ አወጣጥ ሳይቀር ይሳተፋሉ። በዚህ ምክንያት የዚህ እውቀት ዘርፍ ተሳታፊወች አጠቃላይ የመንሰላስል ስርአት አካሄድን ብቻ ሳይሆን እንዴት መንሰላስሎች እርስ በርሳቸው እንደሚዋሃዱ ሁሉ ጥናት ያካሂዳሉ።

የመንሰላስል መሃንዲስ አብዛኛው ስራው የሚመለከተው 1) ሶፍትዌርና ፊርምዌር ለታቃፊ ማይክሮኮንትሮለሮች መጻፍ 2)  VLSI የተሰኙትን የኮምፒውተር አካል ቁራጮች እቅድ መንደፍ  3) አናሎግ የስሜት ህዋሳትን  መተለም 4) በቀጥተኛ እና በተርገብጋቢ ኤሌክትሪክ የሚሰሩ የተደባለቁ የሽቦ ዑደቶችን መዘየድ 5) ከዚያም ተርፎ የኮምፒውተር ኦፕሬቲንግ ስርዓትን መጻፍና መተለምን ያጠቃልላሉ። 

የመንሰላስል መሃንዲሶች ከላይ በጠቀስናቸው ጥናቶች ስለሚሳተፉ የሮቦት ምህንድስናና ተመሳሳይ ቴክኖሎጂወች ላይ ከፍተኛ ተሳትፎ ማሳየት ይችላሉ።

በአሜሪካን አገር የመጀመሪያው ህጋዊ እውቅና ያገኘ የኮምፒውተር ምህንድስና ዲግሪ ትምህርት የተሰጠው በ Case Western Reserve University  በ1971 እ.ኤ.አ. ነው። ከጥቅምት 2004 እ.ኤ.አ ጀምሮ በአሜሪካ ውስጥ 170 የኮምፒውተር ምህንድስና ትምህርት የሚሰጡ ህጋዊ እውቅና የተሰጣቸው የትምህርት ቤቶች አሉ።  ይህ የሆነበት ምክንያት ከምንጊዜም የበለጠ ከኮምፒውተር መሃንዲሶች የሚጠበቀው የስራ ተዋጾ እያደገ በመሄዱ ድሮ በሶፍትዌር መሃንዲሶች ወይም በኤሌክትሮኒክስ መሃንዲሶች የሚከናወኑት ስራወች  መጠናቸው እየሰፋና በተወሰኑ የእውቀት ዘርፍ ባተኮሩ ጠበብት ብቻ የሚከናወኑ እየሆኑ በመሄዳቸው ነው። ኮምፒውተር ምህንድስና እንደ ኤሌክትሮኒክስ ምህንድስና የቀጥተኛና ተርገብጋቢ ኤሌክትሪክ ሽቦ ዑደት ትልም ያጠናል። እንደ ሌሎቹ የምህንድስና ትምህርቶች ከተማሪው ጠለቅ ያለ የሳይንስና የሒሳብ እውቀትን ይጠይቃል።

የኮምፒውተር ትልምና ጥቅም በጣም ሰፊ እየሆነ በመሄዱ አብዛኞቹ የክፍተኛ ትምህርት ተቆአማት ባሁኑ ጊዜ  በጁኒየርና በሲኒየር የዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ባንድ በተወሰነ ርእስ ዙሪያ እንዲያተኩሩ ይመክራሉ። የIEEE/ACM Curriclum Guidlines እንደሚያመለክተው ዋና የኮምፒውተር ምህንድስና ክፍሎች በነዚ ይክፈላሉ 
. 

በኮምፒውተር ምህንድስና የሚጠናው የትምህርት ክፍል ከላይ በተጠቀሱት ብቻ አይወሰነም፤ እንዴያውም ከብዙ የምህንድስና ክፍሎች ሁሉ ጋር ተያያዥ ክፍሎች አሉት። 

በአሜሪካን አገር አንድ ኮምፒውተር እንጂነሪንግ ተምሮ የተመረቀ ተማሪ በአማካይ $61738 ያገኛል።  




#Article 394: አምክንዩ ምክነት (148 words)


አምክንዮ  ማለት  አንድን  እውነት  ከሌላ  እውነት  ጋር  የሚያያይዝ  መሳሪያ  ማለት ነው ። ይህ የሚያሳየው የአምክንዮ ተፈጥሮ እውነትን ማግኘት ሳይሆን፣ እውነትን ማስተሳሰር ነው።  በዚህ ትስስር ላይ ግን ፣ ብዙ ስህተቶች ይፈጠራሉ ( የማይያዙ እዉነታወችን ማያያዝ ፣ ያልተያያዙ እውነታወችን የተያያዙ ማስመሰል ፣ ወዘተ .. )።  እነዚህን ስህተቶች የፍልስፍናና ሒሳብ ተማሪወች የአምክንዮ -ምክነት logical fallacy በማለት ሰብስበዋቸዋል ። 

ምሳሌ ፦ 

እዚህ ላይ ፣ መሰረት የሰራችው ስራ adhominem/እሱኮ ይባላል ምክንያቱም አበበ ያነሳውን ጥሩ ነጥብ ከመወያየት ይልቅ ከነጥቡ ጋር ጭራሽ ግንኙነት የሌለ ነገር አንስታ ውይይቱን ዘጋች ።

ምሳሌ ፦ 

ማሞ እንግዲህ ለማለት የፈለገው አሜሪካ ባትገባ ኑሮ ይህን ነጥብ አታነሳም ነበር ። የማያነሳበት ምክንያት ፣ ምግብ ስለተትረፈረፍ ሳይሆን ፣ ይህን ነጥብ ቢያነሳ ሚደርስበት ነገር ስላለ ነው ። ይህ ዋ ! የሚባለው ምክነት ነው ።

ይህ እንግዲህ ያልተገናኝቶ-ገብያ ዋና መሰረት ነው። አንድ ሰው የሚናገረው ነጥብ ደስ ሳይለን ሲቀር ፣ ሌላ የማይገኛኝ ነገር አንስተን በመሸወድ ሀሳቡን እንዳይጨርስ ስናደርግ ሽወዳ red herring ይባላል ።

ሌላ ምሳሌ ፦ 




#Article 395: ያልተገናኝቶ ገበያ (126 words)


ያለተገናኝቶ  ገብያ  - ይህ  እንግዲህ  ባለተያያዙ እውነታወች ላይ ተነሰቶ ስህተት  ውሳኔ  ላይ  መድረስ  ማለት  ነው ።

እዚህ ላይ፣ መሰረት የሰራችው ስራ adhominem/እሱኮ ይባላል ምክንያቱም አበበ ያነሳውን ጥሩ ነጥብ ከመወያየት ይልቅ ከነጥቡ ጋር ጭራሽ ግንኙነት የሌለ ነገር አንስታ ውይይቱን ዘጋች።

ማሞ እንግዲህ ለማለት የፈለገው አሜሪካ ባትገባ ኑሮ ይህን ነጥብ አታነሳም ነበር ። የማያነሳበት ምክንያት ፤ ምግብ ስለተትረፈረፍ ሳይሆን ፤ ይህን ነጥብ ቢያነሳ ሚደርስበት ነገር ስላለ ነው ። ይህ ዋ ! የሚባለው ምክነት ነው ።

ይህ እንግዲህ ያልተገናኝቶ-ገብያ ዋና መሰረት ነው። አንድ ሰው የሚናገረው ነጥብ ደስ ሳይለን ሲቀር ፣ ሌላ የማይገኛኝ ነገር አንስተን በመሸወድ ሀሳቡን እንዳይጨርስ ስናደርግ ሽወዳ red herring ይባላል ።

ሌላ ምሳሌ ፦ እናት ለአስተማሪ ፦ ልጀ ፈተና ላይ ኮርጃለች ብለህ ታምን ይሆናል ፣ ነገር ግን ይችን ትንሽ ምስኪን ልጅ እንደገና ፈተና እንድትወስድ ስታደርግ ለህሊናህ አይከብደህም




#Article 396: ድንግርግሮሽ (200 words)


ድንግርግሮሽ
እነዚህ አይነት ምክነቶች የሚነሱት፣ ቋንቋን በጠራ መልኩ ካለመጠቀም ነው። በዚህ ዋና ክፍል ስር Equivocation/ስርቅ እና Strawman/ወፍ -ማስፈራርያ ይገኙበታል። 

ስርቅ /equivocation

ይህ ምክነት የሚነሳው፣ በአብዛኛው፣ በአንድ አ /ነገር ወይም ንግግር ውስጥ አንድን ቃል በሁለት አይነት ትርጉም /መንፈስ ስንጠቀም ነው።

ምሳሌ፦ 

እዚህ ላይ፣ 3ኛው አ /ነገር ስሜት አይሰጥም፤ ምክንያቱም በላ የሚለው ቃል በፊተኞቹ አ /ነገሮች አንድ ጊዜ ለበሶ፣ አንድ ጊዜ ለእንጀራ እንጂ፣ ሁለት ጊዜ ለእንጀራ አልተጠቀምንም።

ሌላ ምሳሌ፦-

ወፍ ማስፈሪያ /Straw-man/attacking the pillow/putting words in somebody's mouth

ይህ አይነት ምክነት የሚነውሳው የሌላን ሰው ሀሳብ አጣሞ በመወከል፣ ይህን የተጣመመ ሀሳብ በማጥቃት፣ ዋናውን ሀሳብ ያጠቁ ማስመምሰል ነው። በሌላ አገላለጽ የወፍ-ማስፈራሪያ ማቆም ማለት፣ ከአንድ ሰው ሀሳብ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ነገር ግን በቀላሉ ሊሸነፍ የሚችል ሀሳብ በማቅረብ፣ ይህን ሀሳብ በማጥቃት፣ የመጀመሪያውን ሀሳብ ያጠቁ ማስመሰል ነው። ወፎችን፣ ሰው የመሰለ ነገር በማስቀመጥ ማስፈራራት /ማጥቃት እንደሚቻል ሁሉ።
እጅግ በጣም የተንሰራፋ የአምክንዮ-ምክነት ቢኖር ይህ ነው።

ለምሳሌ፦

እዚህ ላይ መረዳት ያለብን፣ የስላሴ ትምህርት አንድ ይሆናል ሶስት የሚል ትምህርት አያስተምርም ። ነገር ግን ሁለተኛው እና ሶስተኛው አ /ነገር ይህን ነገር አጥቅተው፣ ዋናውን ትምህርት እንዳጠቁ ያስመስላሉ።

ሌላ ምሳሌ፦

የዚህ ስህተተ እንግዴህ ፡ 1 ብቁ ያልሆነ ዘበኛ ተባረረ ማለት፣ ሌባ ዘረፈን ማለት አይደለም። ነገር ግን ተናጋሪው፣ የአቶ አበበን ሀሳብ በቀጥታ ከመቃወም ይልቅ፣ የተጋነነ ፍርሀትን (በሌባ መዘረፍን) በማቅርብ የአቶ አበበን ስራ ለማጨናገፍ ሲሞክር ይታያል።




#Article 397: መሰረት መፋለስ (277 words)


የአምክንዮ -ምክነት   ብዙ ጊዜ ሚመጣው  አንድን  ወይም  ብዙን  እውነት  ከሌላ  ከፍተኛ  እውነት  ጋር  ለማያያዝ  በሚሞከርበት  ጊዜ   በሚደረግ  ስህተት  ነው።

ከዚህ በተረፈ ግን፣ የሒሳብና የፍልስፍና ተማሪወች በተለምዶ የአምክንዮ-ምክነት የሚሉት የፕሮፖጋንዳ መሳሪያ አለ። እሱም የመሰረት-መፋለስ ይባላል። ይህ ምክነት፣ ጸጉር እንሰንጥቅ ከተባለ፣ የአምክንዮ ምክነት አይደለም። እውነትን ከእውነት በማስተሳሰር ላይ የትነሳ ምክነት ሳይሆን፣ ገና ከመነሻው በውሽት ላይ የተመሰረተ ውድቀት ነው። በዚህ ዋና ዘርፍ ስር የሚንቀሳቀሱ 3 ዋና ዋና ምክነቶች ይገኛሉ፦ 

በአንድ ሁኔታ /አጋጣሚ , ከሁለት በላይ ምርጫ እያለ , ሁለት ብቻ ምርጫ ማቅረብ ::

ምሳሌ :-

ይህ አባባል እንግዲህ አንድ ሰው ከሁለቱም ውጭ መሆን እንደሚችል ከስረ -መሰርቱ በሀሰት ክዷል።

ምሳሌ፦ 

አበበ (በስልክ )- ረጅም ነሽ ?
አለሚቱ (በስልክ )- አይደለሁም !
አበበ - እንግዳው አጭር ነሽ ማለት ነው።

አበበ ያለተረዳው፣ አለሚቱ መካከለኛ ቁመት ሊኖራት እንደሚችል ነው።

ምሳሌ

ፖሊስ ለአለሙ : «የሰው ቤት መዝረፍክን አቆመሀል ?»

እንግዲህ አለሙ፣ አወ ካለ ካሁን በፊት ሲዘርፍ ነበር ማለት ነው። አይ ካለ ደግሞ በስራው እየቀጠለበት ነው ማለት ነው። ይህ እንግዲህ የ ከዝንጀሮ -ቆንጆ አይነት ምክነት ነው። ጥያቄው በራሱ፣ ከስር መሰረቱ ምርጫን በሰው -ሰራሽ መንገድ በ 2 በመወሰን ምክነት ሰርቷል።

መነሻ የመድረሻ ደጋፊ ነው የመነሻ Laughing ክብ እየሰሩ አንድን ነገር ለማሳመን መሞከር ማለት ነው።

ምሳሌ፦ 

ደበበ ፦ አቶ አለሙ የሚያምኑበትን ብቻ ነው ሚናገሩት።
ደበበ ፦ ስለዚህ አቶ አለሙ አይዋሹም።

አንድ ሰው የሚያምነው ነገር ውሸት ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ፦ ወባ ሲይዘው ቡዳ በላኝ ብሎ ሊያምን ይችላል። ያ ሰው የሚያምንበትን ቢናገር የግዴታ እውነት ተናገረ ማለት አይደለም። አቶ አለሙ አይዋሹም የሚለው አባባልና አቶ አለሙ ያመኑበትን ይናገራሉ የሚለው፣ ህሉለት በክባ ሁኔታ ተቆራኝተዋል፣ አንዱ አንዱን ይደግፋል ለዛም ነው የነገሩን ስህተት በቀላሉ ማወቅ ሚያዳግተው።

ምሳሌ ፦

አለሚቱ ፦ አቶ ማሞ እኮ ሚስታቸውን ፈተው የሚስታቸውን እህት አገቡ ::
በቀለ ፦ እዉነተኛ ኢትዮጵያዊ እንዲህ አያደርግም
አለሚቱ ፦ አቶ ማሞ እዉነተኛ ኢትዮጵያዊ አይደሉም
በቀለ ፦- ልክ ነሽ




#Article 398: ስነ አምክንዮ (255 words)


አምክንዮ ምንድን ነው? 

ሥነ - አምክንዩ  የምክንያት አሰጣጥ (1) ጥናት ማለት ነው። ምንም እንኳ አምክንዮ ለሁሉም የዕውቀት ዘርፍ አስፈላጊ ቢሆንም፣ ትኩረት ተሰጦት የሚጠናው ግን በ ፍልስፍና ፡ በ ሒሳብ እና በ ኮምፒውተር ሳይንስ የዕውቀት ዘርፎች ዘንድ ነው። አምክንዮ አጠቃላይ የክርክርን ቅርፅ፣ የትኛው የክርክር ቅርፅ ትክክል ነው፣ የትኛው ስህተት ነው የሚሉትን ጥያቄወች ይፈትሻል። በፍልስፍና የጥናት ዘርፍ፣ ስነ አምክንዮ ኢፒስቲሞሎጂ በሚባለው የጥናት ክፍል ይመደባል። ይኸውም ክፍል እውቀታችንን እንዴት ልናውቅ ቻልን? ለሚለው ጥያቄ መልስ ለመስጠት የሚጥር ነው። በሒሳብ ደግሞ የተረጋገጠ መስተሳስር ጥናት በምባል ይታወቃል። 

ምንም እንኳ አምክንዮ ከሰው ልጅ ጋር አብሮ የኖረ ቢሆንም፣ የግሪኩ ፈላስፋ አሪስጣጣሊስ ሥነ-አምክንዮን እራሱን እንደቻለ የትምህርት ክፍል እንደከፈተ ይነገርለታል። ከሱ በኋላ የተነሳው የ12ኛው ክ/ዘመን የሞሮኮው ፈላስፋ አቮሮዝ አምክንዮ ማለት እውነትንና ውሸትን ለይተን ለማወቅ የሚያስችል መሳሪያ ነው በማለት ተርጉሞታል(2)። ሌሎችም የተለያየ ትርጉም ለአምክንዮ ሰጥተቃል። ለምሳሌ ሪቻርድ ዋትሊ አምክንዮ ማለት የምክንያት አሰጣጥ ጥበብና ሳይንስ ነው በማለት ተርጉሞታል። እንዲሁም የጀርመኑ ፍሬጄ አምክንዮ ማለት ከሁሉ በላይ አጠቃላይ የሆኑቱን ህጎች ማጥኛ ሳይንስ ነው ብሎታል። 

ባሁኑ ጊዜ ሥነ-አምክንዮ በሁለት ይከፈላል፡ ትንቢት አምክንዮ (Inductive reasoning) እና መንስኤ አምክንዮ (deductive reasoning) ይባላሉ ። የመጀመሪያው የአምክንዮ አይነት ከተቆራረጡ ምሳሌወች ተነስተን አጠቃላይ ድምዳሜ ላይ የሚያስደርሰን የእውቀት ዘርፍ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ክትርጉምና ጥርጥር ውስጥ መግባት ከማይችሉ እውነታወች ተነስቶ አናሳ ምክንያታዊ ድምዳሜወች ላይ የሚያስደርሰን የዕውቀት ዘርፍ ነው። ከዚህ አንጻር አሪስጣጣሊስም ተመሳሳይ የሥነ አምክዮ ክፍሎችን አቅርቦአል እነሱም መፍታት(Analysis) እና ቋጠሮ(Synthesis) ይባላሉ። የመጀመሪያው አንድን ነገር በመውሰድ የተለያዩ ክፍሎቹን በመፈታት ያጠናል። ሁለተኛው ደግሞ እንዴት የተለያዩ ክፍሎች/ብልቶች ተጋጥመው አንድን ነገር ይሰራሉ ? የሚለውን ያጠናል።

ስነ አምክንዮ በ ክርክር ርዕዮት የዕውቀት ዘርፍ ሁሉ ይጠናል።

ትንቢት አመክንዮ ማለት ከትልቁ/ከአጠቃላዩ ተነስቶ ዉስጣዊ ነገሮችን የሚዳስ ማለት ነዉ::
___መንስኤ አመክንዮ ከጥቃቅን ነገሮች በመነሳት ምክንያታዊ መሆን




#Article 399: ደብረ ታቦር (ከተማ) (2122 words)


 

ደብረ ታቦር  (በሌላ ስሟ  ጁራ  )  በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ከጣና ሓይቅ  ሰሜናዊ ምስራቅ 50 ኪሎ ሜተር  ርቃ የምተገኝ በተራሮች የተከበበች ከተማ ናት። በከተማይቱ ዙሪያ 48 ምንጮች መኖራቸው ለከተማይቱ እድገት ከፍትኛ አስተዋጾ ቢያደርጉም  በ20ኛው ክፍለ ዘመን የባህር ዛፍ ተክል በከተማይቱ መሰራጨት ምንጮቹ እንዲደርቁ አድርጓል።  የደብረታቦርን መሰረት የጣለው የ14ኛ ክፍለዘመን ንጉስ አጼ ሰይፈ አርድ (1344-1372) ነበር።  በዚህ ንጉስ ዘመን የታቦር እየሱስ  ቤ/ክርስቲያን በደብረ ታቦር ተራራ ላይ ታነጸ።  ራሱና ልጆቹ ለከተማይቱ መቋቋም አስተዋጾ ቢያበረክቱም ከተማይቱ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በሰፊው የምትጠቀሰው አጼ ቴወድሮስ እና ከዚያም ቀጥሎ አጼ ዮሐንስ ፬ኛ እንደ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ  በማገልገል ነው። ከዚያም በዳግማዊ ቴዎድሮስ ንጉሰ ነገስት ዘኢትዮጵያ ታላቁ ደብረ ታቦር መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያንን  ልዑለ አድባራት ና  የከተማይቱ እንቁ ተደርጎ አሁንም ድረስ የደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት መንበረ ጵጵስና በመሆን ለሌሎች አድባራት ሳይቀር ጥቅም እየሰጠ ነው። ዛሬ ከተማይቱ ስትነሳ ልዑለ አድባራት ደብረ ታቦር መድኃኔዓለምን የማያስብ የለም ለጉብኝት የመጣም ሳይጎበኘው መሄድ አይታሰብም   ለዛም ነው ደብረታቦር መድኃኔዓለም የደብረታቦር ሁለተና የሚባለው። የከተማይቱም ሕዝብ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያንን እንደ አይኑ ያየዋልልዑለ አድባራት ደብረታቦር መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን በንጉሰ ነገስት ዳግማዊ ቴዎድሮስ የተመሰረተ ሲሆን በወቅቱ ከግብፅ በመጡ አራት ጳጳሳት ተባርኮ የአሁኑ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በአፄ ኀይለሥላሴ ተገነባ  ለሌሎች አድባራት በኩራት የሚጠቀስ ለ ደብረ ታቦር ከተማም  ታላቅ ውበቷ ነው ዝርዝር የደብሩ ታሪክ በpdf የተዘጋጀ ሲሆን በቅርቡ እንለቃለን  ከሞላ ጎደል  ደብረ ታቦር(ጁራ) የ19ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ ዋና ከተማ በመሆን አገልግላለች። ተጭነው  ስለተለያዩ የከተማይቱ ክፍሎች መርጃ የሚያገኙበት ካርታ እዚህ ይገኛል።

አጼ ሰይፈ አርድ (1344-1372) በደብረታቦር ተራራ (እየሱስ ተራራ) ላይ የእየሱስ ቤክርስቲያንን መሰረቱ ። ይህ ቤ/ክርስቲያን አሁን ድረስ ከዚያ ዘመን የመነጩ ቅርጻቅርጾች ሲኖሩት ነገር ግን በ18ኛው ክፍለ ዘመን  መገባደጃ ላይ ራስ ጉግሳ ሙርሳ በቤተክርስቲያኑ አጠቃላይ ለውጥ አድርገዋል። ስለሆነም በቤ/ክርስቲያኑ የሚገኙ ስዕሎች ባብዛኛው ከ19ኛው ክፍለ ዘመን ዋዜማ የሚመነጩ ናቸው። ለደብረ ታቦር ከ ደብረ ታቦር መድኃኔዓለም ቀጥሎ የሚጠራ ደብርም ነው። 

የደብረታቦር ስም  በአጼ ልብነ ድንግል ዜና መዋዕል ላይ  ሰፈረ።

በ1700ወቹ መጨረሻ አካባቢ አሊ ጓንጉል (ትልቁ አሊ) የተባለ የየጁ ስርወ መንግስት መሪ በደብረ ታቦር አካባቢ ሃይለኛ መሪ በመሆን ከሱ በኋላ ለ80 ዓመታት  ያክል የጸና ስርዓት  በአካባቢው እንዳንሰራፋ  ባህሩ ዘውዴ መዝግቧል   እንደ ታሪክ አጥኝው ሞርድካይ አብር አስተያየት የደብረታቦርን ከተማ የመሰረታት ይሄው ትልቁ አሊ ነበር። እንደ ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክኸርስት  ግን ራስ ጉግሳ ሙርሳ ነበር።

በ1800 አካባቢ ራስ ጉግሳ ሙርሳ የተባለው የበጌምድር መሪ (1803-25) ደብረ ታቦርን እንደ ጦር ቅጥር በተራሮች መካከል መሰረተ።  በትውፊት ሲነገር ራስ ጉግሳ ደብረታቦርን የመረጠበት ምክንያት አንድ መነኩሴ «ሴት አቦ ሸማኔ አድነህ በምትገልበት ቦታ ከተማህን አሰራ» ብሎ ስላዘዘው ነበር ይባላል።  ሮቢንሰን የተባለ የታሪክ አጥኝ ስለ ራስ ጉግሳ ሲናገር «በዚህ በ19ኛ ክፍለ ዘመን አጥቢያ ላይ ራስ ጉግሳ ከሁሉ የኢትዮጵያ መሳፍንት ይልቅ የአገሪቱን አንድነት የበለጠ የሚወክል ነበር። በዚህ ምክንያት ከሞተም በኋላ ደብረታቦር የአገሪቱ የፖለቲካ ማዕከል እና መምሪያ ልትሆን በቃች» ራስ ጉግሳ 1825 ላይ ደብረታቦር ላይ ሲሞቱ  እ.ኤ.አ ግንቦት 25፣ ሰኞ ዕለት  እየሱስ ቤተ ክርስቲያን ቀብራቸው ሆነ።  ዘመኑ በታሪክ ዘመነ መሳፍንት ተብሎ የሚታወቀው ሲሆን ለ27 ዓመት ራስ ጉግሳ የአገሪቱ  እንደራሴ በመሆን አገልግለዋል።  በእየሱስ ቤ/ክርስቲያን  የርሱ ተከታይ መሪወች ኢማም፣ ማርየ እና ዶሪ የተባሉትና የዶሪ የአጎት ልጅ ራስ አሉላ አሊ (ትንሹ አሊ)  እንዲሁ ተቀብረዋል። እንደ ታሪክ አጥኝው ማቲወስ  ለኒህ መሪወች ማስታወሻ በጎንደር ግንብ ዘዴ የተሰራ  የእንቁላል ግንብ በእየሱስ ቤ/ክርስቲያን ቅጥር ግቢ ቆሟል።  ከቤ/ክርስቲያኑ አጠገብም ቤ/መንግስቱ ይገኝ ነበር። አሊ አሉላ  (አሊ ትንሹ) በቤተመንግስቱ የውጭ ቆንጽላወችን ያስተናግድ እንደንበርና እስካሁን ድረስ ለፍርድ እርሱ ይቀመጥበት የነበር የሚባል የድንጋይ ዙፋን በአካባቢው እንደሚገኝ ማቲወስ የተሰኘ የታሪክ አጥኝ ይገልጻል። 

በ1830 ራስ ማርየ በድብረ አባይ ጦርነት ላይ ሲወድቅ የርሱ ወንድም ራስ ዶሪ ተተክቶ ስልጣን ላይ ወጣ።   በ1830 መጨረሻ ላይ  ከ ማይ እስላማይ ጦርነት መልስ ራስ ዶሪ በጸና ታሞ ደብረ ታቦር ላይ ሲደርስ በሞት አለፈ። የገዛበትም ዘመን 3 ወር ብቻ ነበር ። የደብረታቦር መሪወችና አለቆች የዶሪን የአጎት ልጅ የሆነው ትንሹ አሊን በ12 ዓመቱ ለመሪነት መረጡት። የአሊ አባት አሉላ በወቅቱ በህይወት አልነበረም።  አሊ ሞግዚቶች የነበሩት ቢሆንም በርግጥ እናቱ ወይዘሮ መነን በርሱ ቦታ አገሪቱን ለሚቀጥሉት 10 ዓመታት አስተዳድራለች። ወይዘሮ መነን በተለይ በታሪክ የምትታወቀው አባ ገብረ ሐናን በተለያዩ ገዳማት እየላከች ስላስተማረች ነው።  በነዚህ ዘመናት የከተማይቱ የህዝብ ቁጥር ማደግና ማነስ አሳይቷል፣ ይህም ከነበረው ከፍተኛ ጦርነት የተነሳ ነበር።  ገንዘብ በ10% አራጣ የሚያበድር ኪዳነ ማርያም የሚባል ነጋዴ በከተማይቱ እንደነበር የፈረንሳይ ተጓዦች ሳይጠቅሱ አላለፉም  

በ1841 መጨረሻ ላይ የጎጃም አስተዳዳሪ  ብሩ ጎሹ እና የሰሜኑ ራስ ውቤ ሃይላቸውን በማቀናጀት በራስ ዓሊ ትንሹ ላይ ዘመቻ አደረጉ። ራስ ዓሊ  ለጦርነቱ መሰናዶ ስላላደረገ ስለሆነም የመዋጋት ፍላጎትም ስላልነበረው እጅግ የተመሳቀለውና  በታሪክ የደብረ ታቦር ጦርነት  ተብሎ የሚታወቀው ውጊያ  እ.ኤ.አ ታህሳስ 7፣  1842 ተካሄደ። በመጀመሪያ ላይ የአሊ ሰራዊት ስለተሸነፈ አሊ ሽሽት አደረገ። በዚያኑ ቀን ማምሻው ላይ እነ ራስ ውቤ ድላቸውን በመጠጥ እያከበሩ በሚሳከሩበት መካከል የአሊ ዘመድ የነበረው ብሩ አሊጋዝ  እጁን ለመሰጠት እጦር ካምፓቸው ገባ። ሆኖም ግን መሳከራቸውንና በቀላሉ ሊሸነፉ እንዲችሉ ስላተረዳ እጅ ከመስጠት ይልቅ ጥቂት ወታደሮችን በማነሳሳት ያለምንም ችግር  ራስ ውቤን ማረከ። ብሩ ጎሹ የሁኔታውን አለማማር በመገንዘብ ወደ ጎጃም ሽሽት አደረገ። እኒህ ሁለት ሰራዊት በንዲህ ሁኔታ ቢሸነፉም ራስ አሊ ግን ለብዙ ቀናት ከሸሸበት ዜናው ስላልደረሰው  ወደ ደብረ ታቦር ሊመለስ አልቻለም። ቆይቶ ግን መመለሱ አልቀረም።   በአቡነ ሰላማ ተማጽኖ ራስ ውቤና ልጃቸው  ከእስር ተለቀቁ።   

በ1848ና 49 ቆንጽል ፕላውዴን ከራስ አሊ ጋር የጋራ ስምምነት ውሎችን በደብረታቦር ከተማ ተፈራረመ።

የወደፊቱ አጼ ቴወድሮስ፣ የዛን ዘመኑ ደጃዝማች ካሳ በጣቁሣ ጦርነት ድል  ጥላ ስር   እ.ኤ.አ  ሚያዝያ 1853 ወደ ደብረ ታቦር ዘመቻ ጀመረ።  በመካከሉ ራስ አሊ ወደ አይሻል ሜዳወች በመንቀሳቀስ ደብረታቦርን ለቀቀ። ካሳ ግን ደብረታቦርን በእሳት ካጋየ በኋላ አሊን እስከ ቆራጣ ድረስ ተከተለው።   በ1854፣ አዲሱ ንጉሰ ነገስት ዳግማዊ አጼ ቴወድሮስ ደብረታቦር ላይ መቀመጫቸውን ሲያደርጉ ራስ አሊ እንደገና ደብረ ታቦርን ለመቆጣጠር ዘመቻ አድርጎ ተሸነፈ።  ከዚህ በኋላ ንጉሱ በ1857 ወደ ጎጃም ሊያደርጉት ላቀዱት ዘመቻ ሃይላቸውን ደብረታቦር ላይ እንዳጠናክሩና መሰናዶ እንዳደረጉ ደብረ ታቦር መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን እዳሳነፁ ሮቢንሰን ያትታል 

እምነት ማሪያም ክብረቱ የተባለ  ሰው ሲጽፍ   ቋረኛ  ካሳ በአሁኑ ጊዜ (ጥቅምት 7፣ 1860)  ደብረታቦር ላይ  ደጃች ውቤን ከእስር ለቆ የውቤን ልጅ አግብቶ ደብረታቦር ይኖራል ብሏል  አጼ ቴወድሮስ  በዚህ ዘመን መቀመጫቸው ደብረ ታቦር ሆኖ ከከተማው ትንሽ ራቅ ብሎ በሚገኘው የድሮው የእጅ ጠቢባን መናኽሪያ ( ጋፋት )የመድፍና የብረታብረት ማሰሪያ  በአውሮጳ ሚሶኖችና በአካባቢው ቀጥቃጮች  ሰራተኛነት አስከፈቱ። ሌሎች የአውሮጳ እስረኞች ከመቅደላ ወደ ቆራጣ ከተዛወሩ በኋላ ዘጌ ላይ ፍርድ ተበይኖባቸው ደብረ ታቦር ላይ እ.ኤ.አ ሰኔ 1866 ላይ እስር ቤት ገቡ።   እ.ኤ.አ መስከረም 21፣ 1867 ላይ ታዋቂው ሴቫስቶፕል መድፍ ጋፋት ላይ ተሰርቶ ተመረቀ።  በዚህ ቀን  አጼ ቴወድሮስ ደብረታቦር ላይ እንደነበሩ አስጋኸኝ የተባለ የአይን እማኝ መዝግቧል    ከዘመቻ መልስና በየክረምቱ  አጼ ቴወድሮስ መኖሪያቸውን በደብረ ታቦር ያደርጉ ነበር። ጥቅምት 3፣ 1867 ላይ  የልጅቱ ማሪያምንና የእናቲቱ ማርያም ቤ/ክርስቲያን ታቦቶችን አንድ ላይ በማድረግ በመጠበቂያ ንጉሱ እንዳስቀመጡ  እምነተማርያም ክብረቴ የተባለ ጸሃፊ መዝግቧል። 

ንጉሱ ጥቅምት11፣ 1867 ላይ ፣ የእንግሊዞቹ ሰራዊት ምጽዋ ከማረፋቸው 10 ቀን ቀደም ብሎ ከደብረ ታቦር መቅደላ ጉዟቸውን ጀመሩ። የዚህ መንገድ ርቀት ከምጽዋ መቅደላ ካለው ርቀት 3 እጥፍ ቢሆንም ከእንግሊዞቹ ቀድመው  ለመድፋቸውና ሰራዊታቸው በአስቸጋሪ ተራሮችና ገደሎች ጥርጊያ ሰፊ መንገድ እያሰሩ መቅደላ ለመድረስ ቻሉ። ከጉዞው በፊት ግን የደብረ ታቦርን ህዝብ ከከተማው አስለቅቀው  አብዛኛውን ክፍል (ከታቦር መድሃኔ አለም ቤ/ክርስቲያን ውጭ)  በእሳት አጋይተውት ነበር። ታቦር መድሃኔ አለም  በራሳቸው በአጼ ቴወድሮስ እጅ በቤተ መንግስታቸው ምትክ የተሰራ   ነው። በዚሁ ቤ/ክርስቲያን እጅግ  ትልቅ  ደወል አለ።  ከክብደቱ የተነሳ ሊሰቀል ስላልቻለ መሬት ላይ ወድቆ ይገኛል።  ይሄ ደወል ከደጃዝማች ውቤ ቤ/ክርስቲያን በአጼ ቴወድሮስ ተወስዶ ለመድሃኔ አለም ቤ/ክርስቲያን የተበረከተ ነው።  ደወሉ  በ1844 የሮማው ፓፓ ግሪጎሪ 16ኛ ለደጅ አዝማች ውቤ በስጦታነት የተላከ ነበር።  በጣሊያን ወረራ ደወሉን ለመስቀል ግንብ ቢሰራም ግንቡ በመብረቅ ተመቶ በመፍረሱ አሁንም ደወሉ መሬት ላይ ይገኛል። 

በዋግሹም ጎበዜ የጎጃም አስተዳዳሪ ሆነው የተሾሙት የደብረታቦሩ ራስ አዳል ሃላቸውን በማጠናከር በመጨረሻ ል ላይ በ1870 ንጉስ ተክለ ሃይማኖት  ተብለው ስልጣን ላይ ወጡ። ከዚህ ዘመን በኋላ አጼ ዮሐንስ መኖሪያቸውን በደብረ ታቦር አደረጉ። አጼ ምኒልክም በ1877 ከሰራዊታቸው ጋር በደብረ ታቦር ለአንድ ወር እንደቆዩ ታሪክ ያትታል። ስለኢትዮጵያ የባህር ወደብ ጥያቄ የእንግሊዙ በካርቱም ቆንጽላ ዊንስታንሊ እና አጼ ዮሐንስ ደበረ ታቦር ላይ በጥር 1879 ውይይት እንዳደረጉ ታሪክ ይመዘግባል። ግንቦት 23፣ 1879 ላይ ጣሊያኖቹ ጊኮሞና  ናሬቲ ለአጼ ዮሓንስ የጠመንጃና ድንኳኖች እንዲሁም አንዳንድ የጣሊያን ኢንዱስትሪ ውጤቶችን ስጦታ ይዘው ደብረ ታቦር ላይ  እንዳቀረቡና አጼ ዮሓንስም  ሁለት የአንበሳ ግልገል ስጦታወች በምትኩ እንደላኩ ታሪክ ያትታል። አጼ ዮሓንስ ናሬቲ  የህሩይ ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን  እንዲያንጽ ጠይቀውት ነበር። ይህ ቤ/ክርስቲያን በዚሁ  በአጼ ዮሃንስ ዘመን ተሰራ።  ከተላኩት ጣሊያኖች ጋር የመጡ ስዊድኖች ሃይማኖት ለመስበክ ከንጉሱ ፍቃድ ቢጠይቁም  ሚስዮኖቹ ለእስላሞችና ለአይሁዶች ክርስትናን ከመሰበክ ይልቅ ለክርስቲያኖቹ ስለሚሰብኩ ወዲያውኑ ወደ አድዋ እንዲባረሩ አደረጉ።  በዚሁ ዘመን (1879)  ወልደ ሚካኤል የተባለው የመረብ ምላሽ አስተዳዳሪ በራስ አሉላ ተይዞ ወደ ደብረታቦር ለፍርድ ቀርቧል። በኋላም  አምባ ስላማ ላይ  ከነልጆቹ እንዲታሰር አጼ ዮሓንስ አዘዙ 

የካቲት 1881 ላይ ራስ አዳል የጎጃም ንጉስ ሆነው ተክሊል በደብረ ታቦር ጫኑ  በ1883 ራስ ገብረ ኪዳን ና ራስ አሉላ ከአጼ ዮሐንስ ጋር በመሆን ምዕራባዊ ወሎ ላይ ዘመቻ አድረጉ። በሗላም ወደ ደብረ ተቦር መጥተው ዕረፍት አደርጉ በዚህ ዘመን  ደብረ ታቦር ሳማራ በመባል ትታወቅ ነበር።  በ80ወቹ ከመሃዲስቶች ጋር ከፍተኛ ጦርነት የተነሳበት ዘመን ነበር። መሃዲስቶች ንጉስ ተክለ ሃይማኖትን በሳር ውሃ ላይ አሸንፈው  ለመቆጣጠር ሲሞክሩ አጼ ዮሐንስ ንጉስ ምንሊክ ወደ ሰሜን እንዲዘምቱ ላኩ። በዚህ ምክንያት አጼ ምንሊክ ደብረታቦር ላይ መጋቢት 10፣ 1888 አርፈው ወደ ጎንደር ዘመቻ አደረጉ። ነገር ግን መሃዲስቶቹ  ወደ መተማ  ስለሸሹ ጦርነቱ ሳይካሄድ ቀረ።  ሐምሌ7፣ 1888 አጼ ዮሐንስ  ንጉስ ተክለሃይማኖትን ለመውጋት ወደ ደብረታቦርና ጎጃም እንደዘመቱ ታሪክ ይመዘግባል።
አጼ ዮሐንስ የአገሪቱን ዋና ከተማ መቀሌ ካደረጉ በሗላም ቢሆን የደብረታቦር ከተማ በጎንደርና በላሊበላ መካከል ለሚካሄደው ንግድ ዋና ማዕከላዊ ቦታ ነበረች። አላማኒ የተባለ ታሪክ ተመራማሪ እንደገመዘገበ በ1880 ወቹ መጨረሻ አካባቢ 70፣000 በሬወች፣ 8፣000 ላሞች፣ 14፣000 ፍየሎችና 8፣000 በጎች በከተማይቱ በየአመቱ ለገበያ ይቀርቡ ነበር 

ሼክ ዘካሪያስ የተሰኘ ሰው በደብረ ታቦርና ሰቆጣ ለሚገኙ እስላሞች  ክርስትናን መስበክ ጀመረ። ስለዚህም ከምንሊክ 100 ጠመንጃወች እና 4000 ማሪያ ቴሬሳ ተሰጠው 

ራስ ጉግሳ ወሌ (ከ1918 - 1930 የበጌምድር አስተዳዳሪ) በደብረታቦርና አካባቢው ብዙ ቤ/ክርስቲያኖችን ያሠሩት በዚሁ ጊዜ ነበር። አስተዳዳሪው ከመጠን በላይ አዳዲስ ቤ/ክርስቲያኖችን የመገንባት አባዜ እንደነበረባቸው  የእንግሊዙ ቆንጽላ ቺዝማን መዝግቧል።  የእናቲቱ ማርያም ቤ/ክርስቲያን ከንደገና የታነጸው በዚሁ ዘመን በራስ ጉግሳ ወሌ ነበር    የ16 አመቱ  ጀምበሬ ሃይሉ እና አጎቱ አለቃ አለሙ የእናቲቱን ማሪያምን  ቤ/ክርስቲያን ምስሎች እንዲስሉ ተጠይቀው ራስ ጉግሳ እስካመጹበት 1930 ድረስ ያለምንም ማቋረጥ እንደሳሉ ታሪክ የመዘግባል። 

ራስ ጉግሳ ወሌ ከደብረ ታቦር አጠገብ በአንቺም ጦርነት  መጋቢት 31፣ 1930 ላይ ወደቁ።  በወቅቱ ብዙ ጅቦች በደብረታቦር ዙርያ ይኖሩ እንደነበር ተጓዦች መዝግበዋል። 

የኢትዮጵያ ባንክ በ1931 ሲፈጠር ደብረታቦር ውስጥ ቅርንጫፍ ቢሮ  በሁለት ተቀጣሪወች  በዚያኑ አመት ተከፈተ። በዚህ ጊዜ የደብረ ታቦር ፖስታ ቤት ሃላፊ አቃቢ ክፍሌ ይባል ነበር።

ከራስ ጉግሳ ሞት በኋላ የበጌምድር አስተዳዳሪ የነበሩት ራስ ካሳ ልጃቸውን  ደጃዝማች ወንድ በወሰን የደብረታቦር አስተዳዳሪ አድርገው ሾሙ። እንግሊዛዊ ቺዝማንን በዚህ ወቅት ደብረታቦር የተቀበላቸው ግራዝማች አበበ የሚባል የወንድ ወሰን ሹም ነበር።  

ሚያዚያ 24፣ 1936 እ.ኤ.አ. ላይ የሳርቼ ጦር ሁለት ባታሊዮን (የሙሶሊኒ ጥቁር ሸሚዝ የሚባሉትና 111ኛ ኔቲቭ) ድንገተኛ ጥቃት በከተማው ላይ አደረሱ። ራስ ካሳ በዚህ ጥቃት ጊዜ ከከተማው ርቀው የነበሩ  ሲሆን ደጃች አያሌው ብሩ ግን ጣሊያኖቹ ከተማይቱን ሲቃረብ እርሳቸው ከታማይቱን ለውቀው ሄዱ። ሚያዚያ 28 ላይ ከባህር ዳር ተነጥሎ የመጣው ይህ የጣሊያን ሰራዊት ደብረታቦርን ያዘ። ደጅ አዝማች አያሌው እጃቸውን እንዲሰጡ በዚሁ ወቅት ተደርጉ። ማጆር ዩጎሊኒ በተባለ የሚመራ 2 የጣሊያን ባታሊዮን ጦር በከተማይቱ በቋሚነት ሰፈረ።  በሚቀጥለው አመት የቴለግራፍና የጣሊያን ፖስታ ቤት ፋሺስቶቹ ሲያቋቁሙ ወዲያውም ከፍተኛ ጥቃት በደብረታቦርና በባህር ዳር በአንድ ጊዜ  ከአካባቢው ህዝብ ደረሰባቸው። 

በ1938 ፋሺስቶች ከደሴ ጎንደር የሚመላለስ መንገድ አሰሩ፣ የደብረታቦር የመጀመሪያ  መስጊድም በዚህ ጊዜ ታነጸ። የባህር ዛፍ ተክልም በበለጠ እንዲስፋፋ ተደረገ። 

ግንቦት 5፣ 1941 አጼ ኃይለ ሥላሴ  ወደ አዲስ አበባ ይመለሱ እንጂ በዚህ ወቅት የኮሎኔል አንጀሊኒና የፊትዋራሪ ብሩ/ሲሞኖድ ሰራዊት ደብረ ታቦር ላይ እንደ ተፋጠጡ ነበር። ሆኖም ግን  ወረራው መፈናፈኛ ስላልነበረው ኮሎኔል አንጀሊኒ ለፊታውራሪ ብሩ፣ ሲሞኖድ እና ማክሊን ሃይሎች  ሐምሌ7፣ 1941  ላይ ከ4000 ወታደሮች ጋር  እጃቸውን ሰጡ።  

ተመራማሪው ሲሞን ስለደብረ ታቦር ጥናት በዚህ ዘመን አደረገ። በጥናቱ መሰረት በየቀኑ የሚክሄደው ገበያ በሳምንት አንድ ጊዜ ከሚካሄደው ግማሽ አይነት እቃን  እንደሚያቀረብ፣ የየቀኑ ገበያ ምግብና ማብሰያ እንጨትን በብዛት እንደሚሸጥ፣ በጣሊያን ጦርነት በፈረሱት ድልድዮች ምክንያት ወደ ደብረታቦር እቃ በጭነት መኪና እንደማይመጣ፣ አብዛኛው ደብረታቦር የሚሸጠው እቃ ከከተማው 3 ቀን ጉዞ ርቀት በታች ካሉት መንደሮች እንደሚመነጭ ጨው፣ ቡናና ጥጥ ግን ራቅ ካሉ ቦታወች እንደሚመጡ፣ ደብረታቦር የሚበቅለው ድንች ከተቀረው ያገሪቱ ክፍል ከሚበቅለው በይዘቱ ትልቅ እንደሆነ፣ እዚህ አካባቢ የሚገኙ አህዮችም ከተቀረው ተለቅ እንደሚሉና ጠንካራ እንደሆኑ፣  ትንባሆ ለኢንደስትሪ ባይበቅልም ነገር ግን አንድ አንድ ገበሬወች ለእንስሳት ህክምናና በጌሾ ምትክ ለጠላ መጥመቂያ እንደሚጠቀሙበት፣ ጅቦችም በብዛትና በጥንካሬ እንደሚገኙ  መዝግቧል። 

በ1858 ደበረ ታቦር ከሌሎች 27 የኢትዮጵያ ከተሞች ጋር በመሆን  አንደኛ ደረጃ ከተማ ተባለች።  በ1958 የትክትክ ክትባት በከተማዋ ሲደረግ በ1959 የአውራጃው አስተዳዳሪ ደጃዝማች ሞላ መሸሻ ነበሩ።  

ከአብዮቱ ፍንዳታ በኋላ በ1975 የአካባቢው ርስተኞችና ተከታዮቻቸው ደብረ ታቦርን መስከረም 1975 ላይ ተቆጣጠሩ። የአጠቃላይ በጌምድር አስተዳዳሪ  በዚህ አመጽ ሲገደል መንገድ ሰሪ ቻይኖችና የሆስፒታል አስተዳዳሪ አድቬንቲስት ሚስዮኖች ተባረሩ። የዚህ አመጽ ቀስቃሽ መልዕክት ደርግ የአረቦች ሴራ  ነው የሚል ነበር።   የክፍለ ሃገሩ አስተዳዳሪ በዛብህ ገብሬ( 43 )  ምንም እንኳ ደበረ ታቦር የተወለደ ሰው ቢሆም የደርግ ተወካይ ነው ተብሎ ስለታመነ በአመጹ ተገደለና በዚያው በመስከረም ተቀበረ።  በአፋር በርሃወች የጥንት አጽሞችን ከሚፈልጉት ሰወች አስተዋጾ ያበረከተው ስለሺ ተበጀ በዚህ ወቅት በደብረ ታቦር የዘመቻ ተማሪ ነበር። 

መጋቢት 1989 መጨረሻ አካባቢ በወቅቱ በነበረው የኢትዮጵያ መንግስት ኢሰፓ እና ኢህአዴግ  ወታደሮች በተደረገው ጦርነት ደብረታቦር በኢህአዴግ ቁጥጥር ወደቀች። ከወር በኋላ የመንግስቱ ወታደሮች እንደገና ተቆጣጠሯት። «ህወሃት  [በዚህ ወቅት] 8000 የመንግስት ወታደሮችን እንደገደለ ቢናገርም ገለልተኛ የሆኑ አይን እማኞች ግን አላጣሩትም»   

ጥር 20 1990 ላይ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ዜና ተቋም  ( ENA news agency) ደብረ ታቦርን መንግስቱ እንደተቆጣጠረ አስታወቀ።  የህወሃት ራዲዮ ጣቢያ ጥር 22-24፣ 1990 ደብረ ታቦር ላይ  ከባድ ድል እንዳስመዘገበ አስታወቀ። ይሄው ራዲዮ ጣቢያ ኢሃዴግ 3፣914  የመንግስት ወታደሮችን እንደገደለና 270 ደግሞ እንደማረከ አስታወቀ። ጥር25፣ 1990 ላይ ከመንገድ ቦይ ስር ተጠልለው የነበሩ 15 ሰወች በአውሮፕላን ቦምብ ተገደሉ።

ከትንሽ ቀናት በኋላ የመንግስት ወታደሮች እንደገና ከተማይቱን ተቆጣጠሩ። ህወሃት ከ3 ቀን ጦርነት በኋላ ከተማይቱን መጋቢት መጨረሻ ላይ እንደተቆጣጠረ አስታወቀ።  መጋቢት 13፣ 1991 በደብረታቦር ላይ በተካሄደው የአውሮፕላን ድብደባ 2 ሰወች በቦምብ ሲገደሉ 10 ደግሞ ቆሰሉ።   በዚህ ወቅት እንግሊዛዊው ሃሞንድ ደብረታቦር በመሄድ ስለከተማው ሆስፒታል እና ሀወሃት አቋቁሞት ስለነበረው የሜዳ ሆስፒታል ቃለ ምልልስና ጥናት አካሂዷል።  

መስከረም 2000 ላይ አንድ የኢለመንታሪ ትምህርት ቤት ታድሶ  በካናዳ አምባሳደር ተመርቀ። ትምህርት ቤቱን ለማሳደስ ከወጣው 400፣000 ብር 230፣000ውን ካናዳ እንደሸፈነ አዲስ ትሪቢዩን መዝግቧል።  በ2001 የህዝቡ ቁጥር  27,600  ነበር። ጥቅምት 18፣ 2001 ላይ  የእንግሊዝ ኢምባሲ 251፣444 ብር አውጥቶ ያሰራው የዳግማዊ አጼ ቴወድሮስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቤተ መጻህፍት ተከፈተ።.

 




#Article 400: ብርሃን (2654 words)


ብርሃን  ነገሮች በዓይን እንዲታዩ የሚያደርግ የተፈጥሮ ሞገድ ነው።  የብርሃን ሞገድ  ከኤሌክትሪክ እና ከመግነጢስ  የተሰራ ስለሆነ ሞገዱ  የ ኤሌክትሮመግነጢስ ጨረራ ይባላል።  ይሁንና፣ የኤሌክትሮመግነጢስ ጨረራ ብርሃንን ብቻ ሳይሆን የብርሃንን ታናናሽና ታላላቅ ወንድሞች ሳይቀር ያፈልቃል። ከብርሃን ታናናሽ ወንድሞች፣ ሬዲዮ፣ ራዳር እና ታህታይ ቀይ ይገኙበታል።  ታላላቅ ወንድሞቹ ቢባል፣ ላዕላይ ወይን ጠጅ፣  ኤክስ  ሬይ፣ ጋማ ጨረር  ይገኛሉ።  እነዚህ የብርሃን ወንድሞች  በተፈጥሯቸው ከብርሃን ጋር አንድ ቢሆኑም ፣ የሰው ዓይን ሊያያቸው ስለማይችል ብርሃን አይባሉም።  ሆኖም ግን አንድ አንድ እንስሳት እነዚህን ሞገዶች መመልከት ይችላላሉ። ለምሳሌ ታህታይ ቀይ የሚባለው የብርሃን ታናሽ ወንድም፣ ለሰዎች እንደ ሙቀት ሆኖ ይሰማል። ለምሳሌ የፀሐይ መሞቅ ከምትተፋው የታህታይ ቀይ ጨረራ ይመነጫል። በበረሃ የሚንከላዎሱ እባቦች ይህን ሞገድ በአይናቸው መመልከት ስለሚችሉ፣ ሙቀት ያለውን ማንኛውንም ነገር በጭለማ ሳይቀር ማየት ይችላሉ።  ንቦች በተቃራኒ፣ የሰው ልጅ እማያየውን ላዕላይ ወይን ጠጅ ሞገድ በዓይናቸው ማየት ስለሚችሉ፣ አበቦች ለንቦች ከሰው ልጅ የተለየ መልክና መልዕክት ያስተላልፋሉ።  

ብርሃን ሞገድ ብቻ ሳይሆን፣ እንደሌሎቹ ጨረራዎች  የሞገድና እኑስ ሁለትዮሽተፈጥሮን አዋህዶ የያዘ ነው። ስለዚህና ስለመሳሰሉት መሰረታዊ የብርሃን ባህርያት የሚያጠናው የዕውቀት ዘርፍ ሥነ ብርሃን (ኦፕቲክስ) በመባል ይታወቃል። የተፈጥሮ ህግጋት ጥናት (ፊዚክስ) ምርምር ዋና ክፍል ነው።

የብርሃን ፍጥነት
ብርሃን በመቅጽበት ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ አይጓዝም። ይልቁኑ ብርሃን የሚጓዘው  በከፍተኛ፣ ነገር ግን ውሱን ፍጥነት ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ የብርሃንን ፍጥነት በተሳካ ሁኔታ የለካው ሮመር የተባለ የዴንማርክ ሰው  ሲሆን ይህም  በ1676 ዓ.ም. ነበር። ከርሱ በኋላ የተነሱ ሳይንቲስቶች፣ በተሻሻለ መንገድ ፍጥነቱን ለክተዋል። በአሁኑ ዘመን የሚሰራበት የብርሃን የኦና ውስጥ ፍጥነት 299,792,458 ሜትር በሰከንድ ነው። በሌላ አነጋገር አንድ የብርሃን ጨረር በያንዳንዷ ሰከንድ ወደ ሶስት መቶ ሚሊዮን ሜትር  የሚጠጋ ርቀት ይጓዛል። ይህ የጠፈር ውስጥ ፍጥነት በ c ምልከት ሲወከል፣ ለተፈጥሮ ህግጋት ጥናት ከፍተኛ ፋይዳ ያለው የተፈጥሮ ቋሚ ቁጥር ነው። 

ብርሃን፣ ከኦና ወጥቶ በቁስ አካል ውስጥ (ለምሳሌ በአየር ውስጥ) ሲጓዝ ፍጥነቱ ይቀንሳል። የዚህ ቀስተኛ ፍጥነት መጠን በቁሱ ዳይኤሌክትሪክ ባህርይና በብርሃኑ አቅም ይወሰናል። ብርሃን ኦና ውስጥ ያለው ፍጥነት cበአንድ ቁስ ውስጥ ላለው ፍጥነቱ ሲካፈል ውጤቱ የዚያ ቁስ የስብራት ውድር ይባላል። በሒሳብ ቋንቋ ሲጻፍ፦

እዚህ ላይ n = የቁሱ የስብራት ውድር ሲሆን፣ v ደግሞ በቁሱ ውስጥ ያለው የብርሃን ፍጥነት ነው።

ብርሃን በቀጥተኛ መንገድ እንደሚጓዝ ከጥንት ጀምሮ የታዎቀ ሃቅ ነው።  ደግሞም የብርሃን ቀጥተኛ ጉዞ አልፎ አልፎ ሊስተጓጎል እንደሚችል ሌላው የሚታዎቅ ሃቅ ነው። ብርሃን የሚጓዝበትን አቅጣጫ በሦስት መንገዶች ይቀይራል፦ እነርሱም በመንጸባረቅ፣ በመሰበር እና በመወላገድ ናቸው። 

የብርሃን ነጸብራቅ
ብርሃን አንድ ቁስን ሲመታ የቁሱ አተሞች የተወሰነውን ብርሃን ውጠው የተቀረውን መልሰው በተለያየ አቅጣጫ ወደ ውጭ ይረጫሉ። ይህ ጉዳይ የብርሃን መበተን ይሰኛል። ቁስ ነገሮች የመታየታቸው ምስጢር ከዚህ የብርሃናዊ መፍካት አንጻር ነው።  ከነዚህ ቁሶች በተለየ መልኩ፣ እንደ መስታውት ያሉ፣ ገጽታቸው ልስልስ የሆኑ አካላት፣  ብርሃን ከገጽታቸው ሲንጸባረቅ በሚነሳው የሞገድ መጠላለፍ ምክንያት አብዛኛው  የሚፈካው ጨረራ እርስ በርሱ ይጣፋል። በዚህ መጠፋፋት ወቅት ጸንቶ የሚቀረው፣ ብርሃኑ በአረፈበት ማዕዘን ትክክል ተገልብጦ ያለው የሞገድ ስብስብ ብቻ ነው፣ ይኸውም የብርሃን ነፀብራቅ ይሰኛል። በሌላ አባባል፣ ብርሃን አንድ ገጽታ ላይ ሲያርፍ እና ሲንጸባረቅ በነጸብራቁና በመጤው ጨረር መካከል ያለው ማዕዘን ከሁለት እኩል ቦታ ይከፈላል፣ የሚያካፍላቸውም የገጽታው ቀጤ ነክ ነው። 

ከዚህ በተጨማሪ በብርሃን ስብረት አማካይነት ብርሃን ሊንጸባረቅ ይችላል። ይህ የሚሆነው አንድ የብርሃን ጨረር ያለበትን አካል ለማምለጥ ያለው ፍጥነት በቂ ሆኖ ሳይገኝ ሲቀር ነው። ጨረሩ የቁሱን ድንበር ከተወሰነ ማዕዘን በላይ በሆነ አቅጣጫ ሲመታ በጣም ከመሰበሩ የተነሳ ተመልሶ ወደ ቁሱ ይንጸባረቃል። ይህም አጠቃላይ ውስጣዊ ነጸብራቅ እሚባለው ነው። የአልማዝ ፈርጦች መጭለቅለቅ ከዚህ የተነሳ ነው። 

ብርሃን በዘፈቀደ ሲንጸባረቅ ተበተነይባላል። እንደ መስታዎት ነጸብራቅ አቅጣጫን የተከተለ ሳይሆን እንደ ግድግዳ መፍካት ወይንም እንደብርሃን ጸዳል በሚተን ውሃ ውስጥ መፍካት ነው። የሰማይ ሰማያዊ ቀለም የሚመነጨው ብርሃን በከባቢ አየር ስለሚበተን ነው። የደመና እና ወተት ነጭነት እንዲሁ ብርሃን በውሃ እና በካልሲየም ስለተበተነ ነው። 

የብርሃን ስብረት
የብርሃን ስብረት እምንለው የብርሃን ጨረር ካንድ ብርሃን አሳላፊ ወደ ሌላ አሳላፊ አካል ሲጓዝ የሚገጥመውን ፈጣን የአቅጣጫ መቀየር ሁኔታ ነው። ይህ የመጉበጥ ሁናቴ በስኔል ህግ እንዲህ ሲባል በሒሳብ ቋንቋ ይገለጻል፦

እዚህ ላይ  በብርሃኑ ጨረርና በአንደኛው ብርሃን አስተላላፊ አካል ቀጤ ነክ መካከል ያለውን ማዕዘን ሲዎክል  ደግሞ በሁለተኛው አካል ቀጤ ነክና በብርሃኑ ጨረር መካከል ያለውን ማዕዘን ይወክላል። n1 እና n2 የብርሃን አስተላላፊዎቹ የስብራት ውድር ናቸው፣ n = 1 ለጠፈር ሲሆን n  1 ደግሞ ለማናቸው ብርሃን አስተላላፊና በከፊል አስተላላፊ ቁስ አካሎች የሚሆን ነው።

አንድ ጨረር ከአንድ አካል ወጥቶ ወደሌላ አካል ሲገባ የጨረሩ የሞገድ ርዝመትና ፍጥነት ይቀየራል። ሆኖም ግን ድግግሞሹ ባለበት ይጸናል። ያ ጨረር ለሚገባበት አካል ገላ ቀጤ ነክ ካልሆነ የሞገድ ርዝመቱ ወይም ፍጥነቱ መቀየር ብርሃኑ እንዲጎብጥ ወይም አቅጣጭ እንዲቀይር ያደርገዋል። አንድ መኪና አንድ ጎን ጎማዎቹ ቀጥ ቢሉና ሌሎች ጎን ጎማዎቹ ቢሽከረከሩ ሳይወድ በግድ እንደሚታጠፍ ነው። የብርሃን አቅጣጫ መቀየር የብርሃን ስብረት በመባል ይታወቃል።

የተለያዩ የብርሃን ቀለማት እኩል አይሰበሩም። ቀይ ብርሃን ቀስ ብሎ ሲሰበር ወይን ጸጅ ደግሞ በከፍተኛ ሁናቴ ይሰበራል። ስለሆነም ከሁሉም ቀለም የተሰራ ነጭ ብርሃን በብርሃን ሰባሪ አካላት፣ ለምሳሌ ፕሪዝም ወይንም የእስክርፒቶ ቀፎ ውስጥ ሲያልፍ ይበተንና ኅብረ ቀለማትን ይፈጥራል። የቀስተ ደመና መፈጠር ብርሃን በከባቢ አየር ባሉ የውሃ ሞለኪሎች መሰበር ምክንያት ነው። 

የብርሃን መወላገድ
ሞገዶች እንቅፋት ወይም ጠባብ ክፍተት ሲያጋጥማቸው በእንቅፋቱ ዙርያ የመጠምዘም ባህርይ ያሳያሉ። ለምሳሌ ከአንድ ክፍል ሆኖ ከሌላ ክፍል የሚወራን ወሬ ማዳመጥ መቻሉ የድምጽ ሞገድ በግድግዳወችና በሮች ዙሪያ መጠማዘዝ በመቻሉ ነው። ከዚህ በተጻራሪ የዕለት ተለት ተመክሯችን እንደሚያረጋግጥልን ብርሃን በቀጥተኛ መንገድ እንደሚጓዝ ነው፣ ሰሆነም አንድ ክፍል ሆነን ሌላ ክፍል የሚሆነውን ማየት አንችልም። ነገር ግን በጥንቃቄ ስናስተውል ይሄ ሙሉ በሙሉ እውነት ሆኖ አናገኘውም። ለምሳሌ በጣም ስል የሆኑ ጠርዞች የሚያሳርፉትን ጥላ በጥንቃቄ ስንመረምር አንድ ወጥ ከመሆን ይልቅ በፈርጅ በፈርጁ የደመቀና የጨለመ ሆኖ እናገኛለን። ብርሃን በቀጥታ እሚጓዝ ከሆነ ለምን ይሄ ሆነ? አንድ ክፍል ሆነን ሌላ ክፍል የሚሆነውን የማናይበት ምክንያት የብርሃን ሞገድ ርዝመት ከድምጽ ሞገድ ርዝመት በጣም ስለሚያን የድምጽን ያህል መጠማዘዝ ስለማይችል ነው። 

ብርሃን ሁል ጊዜ በቀጥታ መንገድ አይጓዝም። ይልቁኑ የብርሃን ጨረር እንቅፋት ሲያጋጥመው ወይም ጠባብ ክፍተት ውስጥ ሲገባ ይጎብጣል። ይህ ኩነት የብርሃን መወላገድ ይሰኛል። በጠባብ ቀዳዳዎች አጮልቀን ስንመለከት ነገሮች ተንጋደው የሚታዩት ስለዚህ ምክንያት ነው። ከብርሃን መንጸባረቅና መሰበር ውጭ የብርሃንን አቅጣጫ የሚቀይረው ይሄ መወላገድ ነው። 

የብርሃን መጠላለፍ
የብርሃን መጠላለፍ እንደማንኛውም ሞገድ መጠላለፍ ነው እንጂ ልዩ አይደለም። ለምሳሌ አንድ የረጋ ውሃ ላይ ሁለት ልጆች የተለያየ ቦታ ላይ ጠጠር ቢጥሉ፣ ከጠጠሮቹ እየከበቡ የሚሰፉት ሞገዶች የሚሰሩት መጠላለፍ አንድ ቦታ በሃይል እንዲጎብጡ፣ ሌላ ቦታ እንዲያንሱ እያደረገ ለአይን የሚስብ የመጠላለፍ ቅርጾች በውሃው ገጽታ ላይ ይሰራሉ። ብርሃንም እንዲህ አይነት የመጠላለፍ ባህርይ ያሳያል። ጉዳዩን በቀላሉ ለማየት የያንግን ሙከራ ማካሄድ ይረዳል። የያንግ ሙከራ ምንድን ነው፣ አንድ አይነት ቀለም ያለው ብርሃን አንድ በቀጭኑ የተሸነተረ ካርድ ላይ ይበራል። ከዚህ ሽንትር ካርድ ብርሃኑ እየተወላገደ ይሄድና ሌላ ሁለት ቦታ ላይ የተሸነተረ ካርድ ላይ እንዲያርፍ ይደረጋል። ከኒህ ሁለት ሽንትሮች ያመለጠው ሁለት ጊዜ የተወላገደ ብርሃን ንጹህ ግድግዳ ላይ እንዲያርፍ ይደረጋል። የብርሃንን መጠላለፍ በደንብ በሚያሳይ መልኩ ይህ የሚያርፈው ብርሃን ብዙ ደማቅና ጨለማ ሸንተረሮች በግድግዳው ላይ ይፈጥራል። ከዚህ በተረፈ የብርሃን መጠላለፍ በተፈጥሮም እንዳለ ለማስተዋል ይቻልል። ለምሳሌ ሥሥ የዘይት ወይም ቤንዚን እድፍ በውሃ ላይ ተንጣሎ ሲገኝ የሚፈጥረው ኅብረ ቀለም ከብርሃን መጠላለፍ የሚመጣ ነው። የሲዲ ገጽታም ኅብረ ቀለም ማሳየቱ ብርሃን መጠላለፍ የሚመነጭ ነው። 

የብርሃን መዋልት
የብርሃን ሞገድ ልከ አንድን ገመደ ወደላይ ወደታች ስናደርግ እንደምናገኘው ሞገድ ነው። ማለት የሞገዱ ጉዞ ወደፊት ሲሆን ሞገዱ የሚርገበገበው ወደ ላይ-ወደ ታች ነው። ሞገዱ የሚርገበገብበት አቅጣጫ የሞገዱ ዋልታ ይሰኛል። የሞገዱ የጉዞ አቅጣጫና የሞገዱ ዋልታ አንድ ወጥ አይደሉም። ይልቁኑ ሞገዱ በአንድ አቅጣጫ እየተጓዘ እያለ የሞገዱ ዋልታ ሊቀየር ይችላል። ለምሳሌ የአንድ ሞገድ ዋልታ ወደ ላይ ወደታች ከሆነ፣ ይህን ቀይሮ ወ ጎንና ወደ ጎን ሊርገበገብ ይችላል። ይህ የብርሃን ባህርይ መዋልት ይባላል። ጉዳዩን በገሃዱ አለም ማየት ይቻላል። ብዙ የጸሐይ መነጽሮች የሚሰሩት ብርሃንን ዋልታ ከሚለዩ ንጥር ነገሮች ነው። ስለሆነም የመነጽሮቹ መስታወቶች የሚያሳልፉት ከነርሱ ዋልታ ጋር የሚስማማውን ክፍል ብቻ ነው። ስለዚህ ሁለት የጸሓይ መነጽሮችን በተለያየ ማዕዘን በማስቀመጥ ከአንዱ ያለፈውን የዋለታ ብርሃን በሌላው መነጽር እንደገና በማጥራት የተለያየ የብርሃን መጠን እንዲያልፍ ማድረግ ይቻላል። በርግጥ ሁለቱ መነጽሮች ደርቦ በማስቀመጥና አንዱን ከሌላው አንጻር በማዞር ከከፍተኛ ብርሃን እስከ ሙሉ በሙሉ ጨለማ እንዲያስተላልፉ ማድረግ ይቻላል። 

ብርሃን በተጨባጭ ግፊት ማድረግ ይችላል። ይህን የሚያደርገው ፎቶኖች የተሰኙት የብርሃን እኑሶች የቁስን ገጽታ በመደብደብ ግፊታቸውን በማሳረፍ ነው። የብርሃን ግፊት እሚለካው የአንድን ብርሃን ጨረር ሃይል ለብርሃን ፍጥነት በማካፈል ነው። የብርሃን ፍጥነት እጅግ ግዙፍ ስለሆነ ክብርሃን የሚገኘው ግፊት በጣም አንስተኛ ነው። ስለዚህ አንዲት ሳንቲም በብርሃን ለማንሳት 30 ቢሊዮን የ1 ዋት ሌዘር ፖይነተሮች በአንድ ላይ መሳተፍ አለባቸው፡፡  የሆኖ ሆኖ የብርሃን ግፊት በናኖ ሜትር ደረጃ ባለው አንስተኛው አለም ውስጥ የማይናቅ ሚና ይቻወታል። ስለሆነም ጥቃቅን የናኖ ሜትር ማብሪያ ማጥፊያወችን በብርሃን ግፊት ለመቆጣጠር ጥናት ይካሄዳል።
 

ፎቶኬሚስትሪ

አንድ አንድ ቅመሞች (ኬሚካልስ) ብርሃን ሲያርፍባቸው ጠባያቸው ይቀየራል። ግማሾቹ የብርሃኑን አቅም ገንዘብ በማድረግ ከፍተኛ አቅም ገዝተው ከሌላ ቁስ ጋር የኬሚካል ግንኙነት ያደርጋሉ፣ ገሚሶቹ ያላቸውን ግንኙነት አቋርጠው ለብቻቸው ይሆናሉ። የተክሎች ምግብ ዝግጅት (ፎቶ ሲንቴሲስ) ከዚህ ወገን ነው። እፅዋት የተለያዩ የስኳር አይነቶች የሚሰሩት ከውሃ፣ የተቃጠለ አየርና ከብርሃን ነው። የሰው ልጅ ቆዳ እንዲሁ ቫይታሚን ዲ የሚፈጥረው የብርሃንን አቅም በመጠቀም ነው። ዓይንም ብርሃንን የሚመለከተው ከአይን ውስጥ ያሉ ኬሚካሎችን በብርሃን የመቀየር ጠባይ በመጠቀም ነው። የፎቶ ፊልም እንዲሁ ከብርና-ናይትሮጅን ኬሚካል የተሰራ ሲሆን ብርሃን ሲያርፍበት ጠባዩን ስለሚቀያይር ፎቶ ለማንሳት ያስችላል።

ብዙ የብርሃን ምንጮች በአለም ላይ ይገኛሉ። ብዙ ጊዜ የብርሃን ምንጮች በመጋል የፋሙ ነገሮች ናቸው። ማናቸውም ሙቀት ያላቸው ነገሮች የጥቁር አካል ጨረራ ያመነጫል። ለምሳሌ የፀሐይ አካል ገጽታ ሙቀት መጠን 6,000 ኬልቪን ሲደሰርስ በዚህ ምክንያት ከገጽታው የሚመነጨው የፀሐይ ጨረራ ለአይን የሚታይ ብርሃንንም ይጨምራል

ከጥንቶቹ በኋላ የአረቡ አል ሃዘን፣ ፈረንሳዩ ደካርት እንዲሁም እንግሊዙ ቤከን እርስ በርሳቸው በሂደት እየተተራረሙ የብርሃንን ምንነት ለማወቅ ሞክረዋል። ሆኖም ደካርት የብርሃንን ጸባይ በአካላዊ መንገድ (ያለ መንፈሳዊ መንገድ) ለመግልጽ ስለቻለ የዘመናዊ የብርሃን ትምህርት አባት በመባል ይታወቃል።  የዘመናዊው የብርሃን ኅልዮት ከሁለት የብርሃን ተፈጥሮ ደጋፊወች ቅራኔ ያደገ ነው። አንደኛው ወገን ብርሃን እኑስ (ጠጣር፣ ደቂቅ፣ ፓርቲክል) ነው ሲል፣ ሌላኛው ደግሞ ብርሃን ሞገድ (ዌቭ፣ ፈሳሽ ዓይነት፣ የማይቆራረጥ) ነው የሚል ነበር።

እኑስ ስንል እዚህ ላይ ደቂቅ ጠጣር አንስተኛ ነገር እንደማለት ነው። ከነደካርት ቀጥሎ ከፍተኛውን እርምጃ ወደፊት የወሰደው ፒር ጋሲንዲ (1592–1655) ብርሃን በጣም ጥቃቅን እኑሶች ክምችት ነው በማለት አስረዳ። ኢሳቅ ኒውተን ገና በወጣትነቱ የጋሲንዲን ጥናት በማንበቡ እርሱም የብራሃንን እኑስነት መሰረት በማድረግ ጥናት አቅርቧል። ለዚህ ምክንያቱን ሲያቀርብ ሞገዶች፣ ለምሳሌ የድምጽ ሞገድ በቀጥታ ከመሄድ ይልቅ በእንቅፋት ዙሪያ መጓዝ ይችላሉ። ነገር ግን ብርሃን በቀጥታ እንጂ እንቅፋትን የመዞር ችሎታ የለውም። ኒውተን የብርሃን ነጸብራቅንና ጥላን በዚሁ ኅልዮቱ ለመግለጽ ችሏል። የብርሃን ስብረትንም በተሳሳተ መልኩ በዚሁ ኅልዮቱ ገልጿል። ኢሳቅ ኒውተን በነበረው የገነነ ክብር ምክንያት 18ኛው ክፍለ ዘመን የርሱን የብርሃን እኑስ ኅልዮት በመከተል ተጠናቀቀ። ይሁንና በ19ኛው ክፍለ ዘመን ይህን አስተሳሰብ የሚቃወሙና የብርሃንን ሞገደኝነት የሚያስተምሩ ጥናቶች መታየት ጀመሩ።

በኒውተን ዘመን የተነሱት ሮበርት ሁክ እና ክርስቲያን ሁይገንስ የብርሃንን ሞገዳዊነት የሚያስረግጡ ጥናቶችን አሳተመው ነበር። ነገር ግን ኒውተን ከነበረው ክብር አኳያ ብዙወች ችላ ብለዋቸው ነበር። የብርሃን ሞገዳዊ ኅልዮት ብርሃን ልክ እንደ ድምፅ እንደሚጠላለፍ የተነበየ ነበር። በ19ኛው ክፍለ ዘመን የተነሳው ቶማስ ያንግ ይህን ጉዳይ በሙከራ ለማሳየት ቻለ። በተረፈ እንደማንኛውም ተራማጅ ሞገድ እንደሚዋልት በዚህ ወቅት በሙከራ ተረጋገጠ። ያንግ በዚህ ሳይወሰን ብርሃን እንደሚወላገድ በሁለትዮሽ ሽንትር ካርድ ሙከራ ለማሳየት ቻለ። የተለያዩ ቀለማት መፈጠር ምክንያቱ በተለያዩት የብርሃን ሞገዶች ውስጥ ባለ የሞገድ ርዝመት ምክንያት እንደሆነ በጥናቱ አቀረበ። ይህ ሁሉ የብርሃንን ሞገዳዊነት ያጠናከረ ጥናትና የብርሃንን እኑስ አለመሆን ለጊዜው ሳይንቲስቶች ያሳመነ ነበር። ላዮናርድ ኦይለር፣ ኦግስቲን ፍሬስነል፣ ሲሞን ፖይሰን የብርሃንን ሞገድ የሂሳብ ቀመሮች ሊጠረጠር በማይችል ሁኔታ መሰረት ሰጡት። ፍሬስነል በ1821 የብርሃን ዋልታዊነት በሞገድ ኅልዮት ብቻና ብቻ የሚገለጽ እና እንዲሁም ብርሃን ተራማጅ ሞገድ እንጂ ፊት-ኋላ የሚል ሞገድ ቅንብር እንዳልሆነ በሂሳብ ቀመሩ ለማስረገጥ ቻለ። ይህ እንግዲህ የኒውተንን የእኑስ ኅልዮት ጥያቄ ውስጥ የጣለ ሂደት ነበር። እንደ ኒውተን ኅልዮት፣ የብርሃን ጨረር ከቀላል ነገር ወደ ጭፍግ (ዴንስ) ያለ ነገር ሲሻገር በግስበት ምክንያት ፍጥነቱ ይጨምራል። ሆኖም ግን ላዮን ፎካልት በ1850 ባደረገው ጥንቃቄ የተመላበት የፍጥነት ልኬት፣ ብርሃን እንዲያውም ጭፍግ ያለ አካል ውስጥ ሲጓዝ ቀስ እንደሚል አረጋገጠ ። ይህ እንግዲህ የኒውተን እኑስ ኅልዮት ሙሉ በሙሎ እንዲጣልና የሞገድ ኅልዮቱ ተቀባይነት እንዲያገኝ ያደረገ ሁናቴ ነበር። 

የሞገድ ኅልዮት በራሱ ድክመት ነበረው። ድምጽ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ለመጓዝ በመሃከሉ ሞግዱን ተሸካሚ አካል ያስፈልገዋል። ለምሳሌ አንድ ሰው በጠፈር ውስጥ ቢናገር በሌሎች አይሰማም ምክንያቱም የድምጹን ሞገድ የሚያስተላልፍ አየር የለምና። ልክ እንዲሁ ብርሃንን አስተላላፊ አካል ያስፈልጋል። ነገር ግን ብርሃን በባዶ ጠፈር ውስጥ ከፀሐይ መንጭቶ መሬት ይደርሳል። ስለሆነም የጥንቶቹ ሳይንቲስቶች ጠፈር ውስጥ የሚኖር ኤተር የተባለ በአይን የማይታይ ነገር ሞገዱን እንደሚያስተላልፍ መላ ምት አደርጉ። 

ሚካኤል ፋራዳይ በ1845 ዓ.ም. የብርሃንን ዋልታ በመግነጢስ መቀየር እንደሚቻል አስተዋለ። ። ይህ እንግዲህ ብርሃን ከኮረንቲና መግነጢስ ጋር ግንኙነት እንዳለው ያሳየ የመጀመሪያው መረጃ ነበር። ይሄው ፋራዳይ ከ2 አመት በኋላ ብርሃን በጣም ከፍተኛ ድግግሞሽ ያለው ኤሌክትሮመግነጢሳዊ ረብሻ እንደሆነ ጻፈ። 

በፋራዳይ ስራ ተመስጦ ቀጣዩን ጥናት ያካሄደው ጄምስ ክላርክ ማክስዌውል በ1862 ዓ.ም. ባወጣው ጥናቱ፣ የኤሌክትሮማግኔቲክ ሞገዶች (ማዕበሎች) አንዴ ከተፈጠሩ በኋላ ያለምንም እርዳታ በኅዋ ውስጥ በቋሚ ፍጥነት መጓዝ እንዲችሉ አሳየ። በሂሳብ ቀመሩ እንዳሰላ ይህ የኤሌክትሮመግነጢሳዊ ሞገድ ፍጥነት ሌሎች ሳይንቲስቶች በሙከራ ካገኙት የብርሃን ፍጥነት ጋር አንድ ሆነ። ከዚህ ተነስቶ፣ ማክስዌል፣ ብርሃን የኤሌክትሮማግኔቲክ ሞገድ እንደሆነ አስረዳ። በ1873ዓ.ም. ማክስዌል የብርሃንና የኤሌክትሮማግኔትን ባህርይ እንዲሁም የመግነጢስ መስክንና የኤሌክትሪክ መስክን ጠባይ በሂሳብ ቀመር ግልጽ አድርጎ አስቀመጠ። ሄኔሪክ ኸርዝ በበኩሎ የማክስዌልን ሂሳብ በመጠቀም የራዲዮ ሞገድን ላብሯረተሩ ውስጥ በመፍጠርና በመጥለፍ እንዲሁም ልክ እንደ ብርሃን ሞገዶቹ የመንጸባረቅ፣ መሳበር፣ መወላገድና መጠላለፍ ባህርያትን እንደሚያሳዩ በተጨባጭ በማረጋገጥ የብርሃንን ኤሌክትሮመግነጢሳዊ ሞገድነት ሙሉ በሙሉ አሳማኝ በሆነ መልኩ አረጋገጠ። በአውሁኑ ወቅት እንደሚታወቀው የኤሌክትሮመግነጢሳዊ ማዕበል ከኤሌክትሪክና መግነጢስመስኮች የተሰራ ሲሆን እኒህ መስኮች እርስ በርሳቸው ቀጤ ነክ ናቸው። 

የማክስዌል ኅልዮትና የኸርዝ ሙከራወች ራዲዮ፣ ራዳር፣ ቴሌቪዥን፣ ገመድ አልባ ግንኙነት እንዲፈጠሩ አደርጉ።

ልዩ አንጻርዊ ኅልዮት

የሞገድ ኅልዮቱ በጣም የተሳካ ከመሆኑ የተነሳ አብዛኛውን የብርሃን እይታዊና ኤሌክትሮመግነጢሳዊ ባህርይ ለመተንተን ያስቻለ ነበር። ይህም የ19ኛው ክፍለ ዘመን ፊዚክስ ታላቁ ድል ተደርጎ ይቆጠራል። ነገር ግን በክፍለ ዘመኑ መዝጊያ ወራት ልዩ ልዩ፣ በሙከራ የተጋለጡ ተቃርኖወችና በኅልዮቱ አጥጋቢ ሁናቴ ሊተነተኑ የማይችሉ የብርሃን ክስተቶች ብቅ ማለት ጀመሩ። አንደኛውና ዋና እራስ ምታት የነበረው የብርሃን ፍጥነት ነበር። የጥንቱ ሳይንቲስት ጋሊልዮ ጋሊሊ እንዳስረዳ ማናቸውም ፍጥነት አንጻራዊ ነው። ስለሆነም አንድ ሰው የሚንቀሳቀስ መኪና ላይ ቢረማመድ ፍጥነቱ የርሱ የመራመድ ፍጥነት ሲደመር የመኪናው ፍጥነት ነው። ነገር ግን የማክስዌል ቀመር ያስረዳ እንደነበር የብርሃን ፍጥነት ምንጊዜም ቋሚና አንድ ነው። ለምሳሌ በሚነዳ መኪና ፊት ያሉ መብራቶች የሚያመነጩት ብርሃን ፍጥነት ከቆመ መኪና ብርሃን ጋር እኩል ነው። ይህ እንግዳ ውጤት በሚኬልሰን ሞርሌ ሙከራ የተረጋገጠ የውኑ አለም ባህርይ ነበር። 

በ1905 አልበርት አይንስታይን ይህን እንቆቅልሽ እስከፈታ ድረስ እንቆቅልሽ ሆኖ ቆይቶ ነብር። አይንስታይን እንዳስረዳ፣ ኅዋና ጊዜ ቋሚ ነገር ሳይሆኑ የሚለጠጡና የሚኮማተሩ ነገሮች ናቸው። ስለዚህ የብርሃን ፍጥነት (በጠፈር) ምንጊዜም ቋሚ የመሆኑ ምስጢር የኅዋና ጊዜ መኮማተር እንደሆነ አስረዳ። በዚያውም አይንስትያን ከዚይ በፊት የማይታወቀውን የግዝፈት እና የአቅምን ተመጣጣኘት በሚከተለው ቀመሩ አስረገጠ ፡

ማለቱ E አቅም ሲሆን፣ m የዕረፍት ግዝፈት እና c ደግሞ የብርሃን ፍጥነት በጠፈር ውስጥ ናቸው።

በሙከራ ከተደረሰበት ሌላ እንግዳ ጠባይ በአሁኑ ዘመን የፎቶኤሌክትሪክ ተጽዕኖ የሚባለው የብርሃን ፀባይ ነበር። ብርሃን ከብረታ ብረቶች ገጽታ ጋር ሲገናኝ የገጽታውን ኤሌክትሮኖች ከአተሞቻቸው በማፈናጠር የኤሌክትሪክ ጅረት(ከረንት) እንዲፈጠር ያደርጋል። በጥንቃቄ በተደረጉ ሙከራወች መሰረት የተፈናጣሪወቹ ኤሌክትሮኖች አቅም በሚያርፍባቸው የብርሃን ድምቀት (ኢንተንስቲ) ሳይሆን የሚወሰነው በብርሃኑ ድግግሞሽ መጠን ነበር። እያንዳንዱ አይነት ብረታብረት ከተወሰነ የድግግሞሽ መጠን በታች ያለ ብርሃን ካረፈበት ከነጭርሱኑ ኤሌክትሮኖቹ አይንቀሳቀሱም (የፈለገ ብርሃኑ የደመቀ ቢሆንም)። እኒህ ተስተውሎወች (የሙከራ ውጤቶች) የብርሃንን የሞገድነት ተፈጥሮ የሚቃረኑ ነበሩ። ለብዙ አመታት ሳይንቲስቶች እኒህን ተቃርኖወች ከሞገድ ኅልዮት ጋር ለማስታረቅ ሞክረዋል፣ ነገር ግን አልተሳካላቸውም።

አልበርት አይንስታይን በ1905 ዓ.ም. ለችግሩ መፍትሔ አቀረበ። ይህን ያደረገው የብርሃንን እኑስ ኅልዮት እንደገና እንዲንሰራራ በማድረግ ነበር። ሆኖም ግን ለሞገድ ኅልዮት እጅግ ብዙ መረጃ ስለነበር በመጀመሪያ የአይንስታይን መፍትሔ በዘመኑ በነበሩ ሳይንቲስቶች ዘንድ ተቀባይነት አልነበረውም። ነገር ግን የ የፎቶኤሌክትሪክ ተጽዕኖን የአይንስታን ትንታኔ በበቂ ሁኔታ ስለገለጸ ቀስ በቀስ ተቀባይነትን አገኘ፣ ስለሆነም አይንትስታን ለዚህ ስራው የኖቤል ሽልማትን አገኘ። ይህ የአንስታይን የፎቶኤሌክትሪክ ኅልዮት ለቀጣዩ የኳንተም ኅልዮት መሰረትና አሁን ተቀባይነት ላለው የብርሃን ሁለት ጸባይነት መሰረት የጣለ ነበር። 

ኳንተም ኅልዮት
በ19ኛው ክፍለ ዘመን ከተደረጉ ሙከራወች የተነሳ ሌላ ቀውስ ተፈጠረ፣ ይኸውም የኤሌክትሮማግኔቲክ ኅልዮት በሚለውና በተጨባጭ ሙከራወች ውጤት መካከል የነበር ልዩነት ነው። ማናቸውም ሙቀት ያላቸው ቁሶች የሙቀት ጨረራ ይረጫሉ፣ ነገር ግን ጨረራቸው ያልተቆራረጠ አልነበርም። በ1900፣ ማክስ ፕላንክ የተሰኘው ጀርመናዊ ተማሪ የዚህን ጉዳይ ስረ መሰረት ለማወቅ ባደረገው ጥናት ማናቸውም ነገሮች (ጥቁር አካላት) ኤሌክትሮማግኔት ጨረራ የሚረጩት በጠጣር በጠጣር ቁርጥራጭ እንጂ በተቀጣጣይ እንደፈሳሽ አለነበረም። እኒህ ጠጣር የኤሌክትሮማግኔት ጨረራ ቁራጭ መሰረቶች ፎቶን ተባሉ። የሚይዙት ጠጣር ቁራጭ አቅም ኳንታ እንዲባል አንስታይን አሳወቀ። ፎቶን መባሉ በዚሁ ዘመን ኤሌክትሮኖች እና ፕሮቶኖች የታወቁበት ዘመን ስለነበር ለመለየት ነበር። 

ፎቶን አቅም E ሲኖረው, መጠኑም ከአለው ድግግሞሽ, f,ጋር ቀጥተኛ ውድር አለው። በሒሳብ ሲቀመጥ

ማለቱ፦ h የ ፕላንክ ቋሚ ቁጥር,  የሞገድ ርዝመት፣ እና c ደግሞ የብርሃን ፍጥነት ናቸው። ልክ እንዲሁ፣ የፎቶን እንድርድሪት (ሞመንተም) p ከሞገዱ ድግግሞሽና ጋር ቀጥተኛ ውድር ሲኖረው ከየሞገዱ ርዝመት ጋር ግን ተገልባጭ ውድር አለው። ወደሒሳብ ቋንቋ ሲተረጎም፦

ይሁንና ይህ የፕላንክ ጥናት የፎቶንን ጠጣር የሚመስል ባህርይ በአጥጋቢ ሁኔታ የገለጸ አልነበረም።

የብርሃንን ተፈጥሮ የሚገልጸው የአሁኑ ዘመናዊ ኅልዮት በአልበርት አይንስታይን የፎቶኤሌክትሪክ ተጽዕኖ ኅልዮትና በማክስ ፕላንክ የፎቶን ጥናት ላይ የተመሰረት ነው። የአይንስታን ትንታኔ በእኑስነት ላይ ያተኮረ ሲሆን የፕላንክ ደግሞ በሞገድነት ላይ ያተኮረ ነበር። የዘመናዊው ኅልዮት እሚለው ብርሃን የሞገድ-እኑስ ሁለትዮሽ ተፈጥሮ አለው ይላል። ማለቱ ብርሃን፣ ሞገድም፣ እኑስም ነው። አይንስታይን እንዳስተማረ፡ የፎቶን አቅም ከፎቶኑ ድግግሞሽ ጋር ቀጥተኛ ውድር አለው ( ማለት ድግግሞሹ ሲበዛ፣ አቅሙም ይበዛል፣ ሲያንስ ያንሳል)። ይህ ሃልዮት ሲሰፋ ማናቸውም የአለም አካላት እኑስም ሞገድም ናቸው ብሎ ያስቀምጣል። ብርሃን ብቻ ሳይሆን፣ ማንኛውም ነገር የእኑስነቱን ወይም ደግሞ የሞገድነቱን ባህርይ ለይቶ ሊያወጣ የሚችል ሙከራ ሊካሄድበት ይችላል። አንድ ነገር ግዝፈቱ ትልቅ ከሆነ የእኑስነቱ ባህርይ ገኖ ይወጣል። ስለሆነም የአለምን ሞገዳዊነት በዘልማድ ለማወቅ አስቸጋሪ ነው። ሉዊ ደ ብሮይ በ1924 አፍረጥርጦ የኤሌክትሮንን የእኑስና ሞገድ ሁለትዮሽ ፀባይን እስከተነተነ የሁለቱ ጸባይን የያዘ ብርሃን ብቻ ነው ብሎ ሳይንቲስቶች ያስቡ ነበር። የኤሌክትሮን ሞገዳዊ ባህርይ በ1927 ዓ.ም. በዳቪሰንና ገርመር በተጨባጭ ተመክሮ ተረጋገጠ። 

የኳንተም መካኒካል ኅልዮት በብርሃንና ኤሌክትሮማግኔቲካዊ ጨረራ ያለው አስተሳሰብ ቀስ በቀስ እየተቀየረ 1920ወቹ አልቀው 1930ዎቹ ተደግሙ። በ1940ወቹ ይህ ኅልዮት አብቦ አሁን የሚታወቀውን የኳንተም ኤለክትሮዳይናሚክስ (QED) ወይንም በሌላ ስሙ የኳንተም መስክ ኅልዮት ወለደ። ይህ አዲሱ ኅልዮት በብዙ ሙከራወች የተፈተነና ጸንቶ የቆመ ሲሆን በሌላ ጎን ስፋት ያላቸውን የተፈጥሮ ክስተቶች በአጥጋቢ ሁኔታ መተንተን የሚያስች ሆኖ እስካሁን ጸንቶ ይገኛል። ኳንተም ኤሌክትሮዲናሚክስን ያቋቋሙት ሳይንቲስቶች ሪቻርድ ፌይማን፣ ፍሪማን ዴይሰን፣ ጁሊያን ሽዊንገር፣ እና ሽን-ኢችሮ ቶሞናጋ ናቸው። ፌይማን፣ ሽዊንገር እና ቶሞናጋ የ1965 ኖቤል ሽልማት ስለዚህ ስራቸው አሸንፈዋል።




#Article 401: ኮረንቲ (115 words)


 
ኮረንቲ ወይም ኤሌክትሪክ የሚባለው በኮረንቲ አስተላላፊ ቁስ አካል ውስጥ የሚገኙ ኤሌክትሮኖች በኤሌክትሪካዊ ሙል ተሞልተው (ቻርጅ ተደርገው) ወይም በመግነጢሳዊ ኃይል ተገፍተው ካንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ሲንቀሳቀሱ ነው። ኮረንቲ እንግዲህ በተለያዩ ክስተቶች ዘንድ የመገኘት ባህርይ አለው።በስታቲክ ኤሌክትሪሲቲ በመፋተግ፣በሙቀት ልዩነት፣ጨረራ፣ኬሚካላዊ አጸግብሮት፣ኬሚካላዊ ንትበት(ዲኬይ) ለምሳሌ ያልን እንደሆን በመብረቅ፣ ጸጉራችንን በሚዶ በማበጠር በሚነሳው ቋሚ ኮረንቲ(ዲሲ ከረንት) እና እንዲሁም በተለዋዋጭ ማግኔት ማእበል መስክ ውስጥ የሚያቋርጥ በኮረንቲ አስተላላፊ(ኮንዳክተር) አካል ውስጥ የሚፈጠር ተለዋዋጭ ኮረንቲ(ኤሲ ከረንት) ሊገኝ ይችላል።
ኮረንቲ በሁለት ምድብ ይከፈላል። ይኽዉም በ እንግሊዝኛ አባባል ኦልተርኔት ከረንት ወይም ኤሲ በመባል ሲታወቅ ሁለተኛው ደግሞ ዳይሬክት ከረንት ወይም ዲሲ በመባል ይታወቃል። ኮረንቲ በሁለት ተቃራኒ አውታር(ፖል) የሚፈስ ከሆነ ኦልተርኔት ከረንት ወይም ኤሲ የሚባል ሲሆን ኮረንቲ በአንድ አውታር(ፖል) ብቻ የሚፈስ ከሆነ ዳይሬክት ከረንት ወይም ዲሲ በመባል ይታወቃል።




#Article 402: ቁጥር (310 words)


ቁጥር ፦ ለመቁጠር ወይም ደግሞ ለመለካት የምንጠቀምበት የሂሳብ ቁስ ነው።   ቁጥሮች  ከዚህ ከሁለቱ ጥቅማቸው ውጭ በአሁኑ ጊዜ ለልዩ ልዩ ጥቅም ይውላሉ። ለምሳሌ፦  አንድን ነገር ለመለየት (ምሳሌ ስልክ ቁጥር)፣ ለመደርደር (ሲሪያል ቁጥር)፣   ኮድ ለማበጀት (ISBN ቁጥር) ከብዙ በጥቂቶቹ ናቸው። 

አንድንድ ሂደቶች አንድ ወይም ሁለት ቁጥሮችን ወስደው ሌላ ቁጥርን ይሰጡናል። እኒህ ሂደቶች ኦፕሬሽን ይባላሉ። ለምሳሌ ቁጥር ሲስጠን ቀጣዩን ቁጥር የምናገኝ ከሆነ ይህ ሂደት ቀጣም በመባል ይታወቃል፣ የሚወስደውም ቁጥር ብዛት አንድ ብቻ ስለሆነ ዩናሪ ኦፐሬሽን ይባላል። እንደ መደመር፣ መቀነስና፣ ማባዛት፣ ማካፈል ያሉት ደግሞ  ባይናሪ ኦፕሬሽን ይባላሉ። እንደዚህ ያሉትን የቁጥር ኦፕሬሽን የሚያጠናው የሂሳብ ክፍል ሥነ ቁጥር ወይም አርቲሜቲክ (በእንግሊዝኛ Arithmetic) ይሰኛል።

የቁጥሮችን ቁመና በግሩፕ፣ ቀለበት ና ሜዳ የሚያጠናው የሂሳብ ክፍል የነጠረ አልጀብራ ተብሎ ይታወቃል።

የሕንዳዊ-አረባዊ ቁጥሮች ምልክቶች (0123456789) በዘመናዊ ቅርጾቻቸው በአውሮፓ ከ1550 ዓም ግድም ጀምሮ ነው። ከዚያ በፊት በነባሮች ቅርጾቻቸው በአውሮፓ ከ968 ዓም ጀምሮ ይታወቁ ነበር። እነርሱም ከአረብኛ ቁጥሮች ተወሰዱ። አረቦችም የሕንድ ቁጥሮች የበደሩ ከ768 ዓም ጀምሮ ነበር። የአረብ ሊቃውንት ከአውሮፓ ሊቃውንት በነዚህ ፪ መቶ አመታት በዜሮ (0) ጥቅም ቅድምትነታቸው ምክንያት፣ በሥነ ቁጥር ብቻ ሳይሆን በሌሎች ሳይንስ ዘርፎች ሥነ ቁጥሮች በመቀለላቸው በኩል፣ ለጊዜው የአረብ አለም ሊቃውንት በይበልጥ ለመግፋት ቻሉ። ሕንዶችም የዜሮ ጥቅም ያወቁት ቢያንስ ከ620 ዓም ጀምሮ ነበር። ለያንዳንዱ ሕንዳዊ-አረባዊ ቁጥር ምልክት አደረጃጀት፣ በየአማርኛ ስሙ አንድ ሁለት ሦስት አራት አምስት ስድስት ሰባት ስምንት ዘጠኝ ይዩ።

የግዕዝ ቁጥሮች ምልክቶች በቀጥታ ከግሪክ ፊደል ቁጥሮች ተበደሩ፤ እንዲሁ፦

ይህ የግሪኮች ዘዴ የተለማ ምናልባት 400 ዓክልበ. ግድም ሲሆን፣ ከዚያ ቀድሞ ሌላ የአቆጣጠር ዘዴ ለግሪኮቹ ነበራቸው። የግዕዝ ቁጥር ቅርጾች ከ500 ዓም ያህል ጀምሮ ናቸው (የአባ ገሪማ ብራናዎች)።  

በአውሮፓ ከሕንዳዊ-አረባዊ ቁጥሮች በፊት የነበረው ዘዴ ሮማዊ ቁጥሮች በአንዳንድ ቦታ እስካሁን ይገኛል። በዚህም፦

እነዚህ ቅርጾች እንደ ላቲን አልፋቤት ፊደላት I, V, X, L, C, D, M ለመምሰል የጀመሩ ከ1 ዓም አካባቢ ነው። ሆኖም በውነት ከጥንታዊ ኤትሩስክኛ ቁጥሮቹ ምልክቶች («𐌠, 𐌡, 𐌢, ⋔, 𐌚, ⊕» ለ«I, V, X, L, C, M») የተለሙ ናቸው። 

ከነዚህ ዘዴዎች በቀር በጣም ብዙ ሌሎች የአቆጣጠር ምልክቶች ዘዴዎች ከቦታ ወደ ቦታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተለያዩ በሰው ልጆች ታሪክ ላይ ተገኝተዋል። 




#Article 403: ጊዜ (1304 words)


ጊዜ ኩነቶችን (ክስተቶችን) ለመደርደር፣ ቆይታቸውን ለማነጻጻር፣ በመካከላቸውም ያለፈውን ቆይታ ለመወሰን በተረፈም የነገሮችን እንቅስቃሴ መጠን ለመለካት የሚያገለግል ነገር ነው። ጊዜ በፍልስፍና፣ ሃይማኖት፣ ሳይንስ ውስጥ ብዙ ጥናት የተካሄደበት ጽንሰ ሃሳብ ቢሆንም ቅሉ እስካሁን ድረስ በሁሉ ቦታ ለሁሉ የሚሰራ ትርጓሜ አልተገኘለትም።

የጊዜ መተግበሪያ ትርጉም ለዕለት ተለት ኑሮ ጠቃሚነቱ ስለታመነበት ከዘመናት በፊት ጀምሮ እስካሁን ይሰራበታል። ይህ መተግበሪያ ትርጉም ለምሳሌ ሰከንድን በመተርጎም ይጀምራል። ማለት በቋሚ ድግግሞሽ የሚፈጠሩ ኩነቶችን/ክስተቶችን በማስተዋል የተወሰነ ድግግማቸውን አንድ ሰከንድ ነው ብሎ በማወጅ የመተግበሪያ ትርጉሙ (ለስራ የሚያመች ትርጉሙ) ይነሳል። ለምሳሌ የልብ ተደጋጋሚ ምት፣ የፔንዱለም ውዝዋዜ ወይም ደግሞ የቀኑ መሽቶ-ነግቶ-መምሸት ወዘተ.. እነዚህ ኩነቶች እራሳቸውን በቋሚነት ስለሚደጋግሙ ከነሱ በመነሳት ሰዓትንና ደቂቃን ማወጅ ይቻላል (መሽቶ ሲነጋ 24 ሰዓት ነው፣ ልብ ሲመታ ወይም ፔንዱለም አንድ ጊዜ ሄዶ ሲመለስ አንድ ሰኮንድ ነው፣ ወዘተ..) ። የመተግበሪያ ትርጉሙ ተግባራዊ ጥቅም ይኑረው እንጂ «ጊዜ በራሱ ምንድን ነው?» ፣ ወይም ደግሞ «ጊዜ አለ ወይ?» ወይም ደግሞ «ጊዜ የሚባል ነገር በራሱ አለ ወይ?» ለሚሉት ጥያቄወች መልስ አይሰጥም። 

በአሁኑ ወቅት ጊዜ በሁለት አይነት መንገድ ይታያል፦ 

ሳይንቲስቶችና ቴክኖሎጂስቶች ጊዜን በሰዓት ለመለካት ብዙ ጥረት አድርገዋል። ይህ ጥረት ለከዋክብት ጥናትና ለተለያዩ ያለም ዙሪያ ጉዞወች እንደመነሳሻ ረድቷል። በቋሚ መንገድ እራሳቸውን የሚደጋግሙ ክስተቶች/ኩነቶች ከጥንት ጀምሮ ጊዜን ለመልካት አገልግለዋል። ለምሳሌ ጸሃይ በሰማይ ላይ የምታደርገው ጉዞ (ቀን)፣ የጨረቃ ቅርጾች(ወር)፣ የወቅቶች መፈራረቅ(ዓመት)፣ የፔንዱለም መወዛወዝ (ሰኮንድ) ወዘተ...ይገኙበታል። በአሁኑ ጊዜ ሰኮንድ የምትለካው የሴሲየም አረር ሲወራጭ በሚያሳየው ቋሚ ድግግሞሽ ነው። 

ሬይ ከሚንግ የተባለው ልብ ወለድ ጸሃፊ በ1920 ስለ ጊዜ ሲጽፍ  ሁሉ ነገር በአንድ ጊዜ እንዳይፈጸም የሚያደርገው ነገር....ጊዜ ነው  በማለት እስካሁን ድረስ ታዋቂ የሆነችውን ጥቅስ መዝግቦ አልፏል,
ይቺ አባባል በብዙ ሳይንቲስቶችም ስትስተጋባ ተሰምታለች፣ ለምሳሌ በኦቨርቤክ,
እና ጆን ዊለር.

ጊዜአዊ ጊዜ አለካክ ሁለት መልኮች አሉት እነሱም፡ ካሌንደር ና ሰዓት ናቸው። ካሌንደር የሂሳብ ንጥር ሲሆን ሰፋ ያለ ጊዜን ለመለካት የሚጠቅመን ነው።  ሰዓት ደግሞ በተጨባጭ ቁሶች ተጠቅመን የጊዜን ሂደት የምንልካበት ነው። በቀን ተቀን ኑሯችን ከአንድ ቀን ያነሰን ጊዜ ለመለካት ሰዓት ስንጠቀም ከዚያ በላይ የሆነውን ደግሞ በካሌንደር እንለካለን። 

ኦግስጢን የተባለው የካቶሊክ ፈላስፋ ጊዜ ምንድን ነው? በማለት እራሱን መጠየቁን በመጽሃፉ አስፍሯል። ሲመልስም ሌላ ማንም ካልጠየቀኝ መልሱን አውቀዋለሁ፣ ነገር ግን ለሌላ ሰው ለመግለጽ ብሞክር ምን እንደሆነ ይጠፋብኛል በማለት ካስረዳ በኋላ ጊዜ ምን እንደሆነ ከማወቅ ይልቅ ምን እንዳልሆነ ማወቁ እንደሚቀል አስፋፍቶ መዝግቧል።  

የጥንቶቹ ግሪክ ፈላስፎች ጊዜ ማለቂያ የለለው፣ ወደሁዋላም ሆነ ወደፊት የትየለሌ ነው ብለው ሲያስቀምጡ፣ የመካከለኛው ዘመን አውሮጳውያን ደግሞ ጊዜ መነሻም ሆነ መድረሻ ያለው አላቂ ነገር ነው በማለት አስረግጠው አልፈዋል። ኒውተን በበኩሉ በሁሉ ቦት አንድ አይሆነ ቋሚ ጊዜ እንዳለና መሬት ላይ ያለው ጊዜ ከዋክብት ላይ ካለው ጊዜ ጋር እኩል የሚጎርፍ ነው በማለት አስረድቷል። በአንጻሩ ሌብኒትዝ ጊዜ ማለት አንድ አይነትና ቋሚ ሳይሆን አንጻራዊ እንደሆነ አስቀምጧል።  ካንት ባንጻሩ ጊዜን ሲተንትን ጊዜ ማለት ከልምድ ውጭ ገና ስንወለድ አብሮን የሚወለድ ቀደምት እውቀት ሲሆን የገሃዱን አለም እንድንረዳ የሚረዳን አዕምሮአችን የሚያፈልቀው መዋቀር ነው ብሎታል።. በርግሰን የተባለው ፈላስፋ ደግሞ ጊዜ ማለት ቁስ አካልም ሆነ የአእምሮአችን ፈጠራ አይደለም በማለት ሁለቱንም ክዷል። ይልቁኑ ጊዜ ማለት ቆይታ ማለት ሲሆን፣ ቆይታ በራሱ ደግሞ የውኑ አለም አስፈላጊ ክፍል ሲሆን ከ ፈጠራና ትዝታ ይመነጫል ብሏል።

ከክርስቶስ ልደት በፊት የነበረው ግሪካዊ ፈላስፋ አንቲፎን እንደጻፈው ጊዜ እውን ሳይሆን በርግጥም ጽንሰ ሃሳብ ወይም ልኬት ነው ብሎታል። ፓራመንዴስ የተባለው ግሪካዊም ጊዜ፣ እንቅስቃሴና፣ ለውጥ በሙሉ የውሽት ራዕይ እንጂ በርግጥ በግሃዱ አለም ያሉ አይደሉም ብሏል። በቡዲሂስቶችም ዘንድ ጊዜ የውሸት ራዕይ ነው የሚለው አስተሳሰብ እስካሁን ይሰራበታል። ,

በተፈጥሮ ህግጋት አጥኝወች ዘንድ ግን ጊዜ እውን እንደሆነ ይታመናል። በርግጥ አንድ አንድ የፊዚክስ አጥኝወች ኳንትም ሜካኒክስ በይበልጥ እንዲሰራ እኩልዮሹ ያለጊዜ መቀመጥ አለባቸው ይላሉ። ይህ ግን ያብዛናው ሳይንቲስቶች አስተያየት አይደለም።.

አልበርት አንስታይን የጊዜን ትርጉም እስከለወጠበት ዘመን ድረስ የጊዜ ትርጓሜ ኢሳቅ ኒውተን ባስቀመጠው መልኩ ይሰራበት ነበር። ይህም ኒውተናዊ ሲባል ጊዜ ሁሉ ቦታ ቋሚ የሆነ፣ ምንጊዜም የማይቀየርና በሁሉ ቦታና ዘመን እኩል የሚፈስ (ለምሳሌ በከዋክብትና በመሬት ያለው ጊዜ በአንድ አይነት መንገድ ይሚፈስ/የሚለወጥ) ነው የሚል ነው።. በክላሲካል ሳይንስ የሚሰራበት ጊዜ ኒውተናዊ ነው።

በ19ኛው ክፍለዘመን፣ የተፈጥሮ ህግን የሚያጠኑ ሰወች በነኒውተን ይሰራበት የነበረው የጊዜ ትርጓሜ የኮረንቲንና ማግኔት ን ጸባይ ለማጥናት እንደማይመች/እንደማይሰራ ተገነዘቡ። አንስታይን ሳይንቲስቶቹ የገቡበትን ችግር በማስተዋል በ1905 መፍትሄ አቀረበ። ይህም መፍትሄ የብርሃን ፍጥነትን ቋሚነት የተንተራሰ ነበር። አንስታይን እንደበየነው (postulation) በጠፈር ውስጥ የብርሃን ፍጥነት ባማናቸውም ተመልካቾች (ቋሚም ሆነ ተንቀሳቃሽ) ዘንድ አንድ ነው፣ በዚህ ምክንያት በተንቀሳቃሽ ሳጥን ውስጥ የሚፈጠጥ ኩነት የሚወስደው የጊዜ ቆይታ ከሳጥኑ ውስጥ ላለ ተመልካችና ከሳጥኑ ውስጥ ላለ ተመልካች አንድ አይደለም ብሏል። ለምሳሌ እሚንቀሳቀሰው ሳጥን ውስጥ ለ5 ደቂቃ ያክል ቦምብ ቢፈነዳ (ኩነት) ፣ የማይንቀሳቀሰው ከውጭ ያለ ተመልካች ቦምቡ ለ5.5 ደቂቃ እንደፈነዳ ሊያስተውል ይችላል። ሌላ ታዋቂ ምሳሌ ብንወስድ፣ ሁለት መንትያ እህትማማቾች ቢኖሩና አንዱዋ በመንኮራኩር ከመሬት ተነስጣ በብርሃን ፍጥነት በሚጠጋ ፍጥነት ጠፈርን አሥሳ ከስልሳ አመት በኋላ ብትመለስ፣ መንትያዋን አርጅታ ስታገኛት፣ ተመላሿ ግን ገና ወጣት ናት። የዚህ ምክንያቱ፣ አንስታይ እንዳስረዳ፣ የተንቀሳቃሽ ነገሮች ሰዓት ዝግ ብሎ ሲሄድ የማይንቀሳቀሱ ግን ቶሎ ስለሚሄድ ነው።

ባጠቃላይ፣ የሚንቀሳቀሱ ተመልካቾች ከማይንቀሳቀሱ ተመልካቾች ጋር የተለያየ ጊዜ ለአንድ አይነት ኩነት ይለካሉ።

መቼት የሚለው ቃል ከመቼ እና የት ቃላቶች የመጣ ሲሆን የጊዜና ኅዋን ጥምረት ያሳያል። ከድሮ ጀመሮ፣ ሰወቸ ጊዜንና ህዋን በማዛመድ ተመልከተዋቸዋል። በተለክ ከ አንስታይን የልዩ አንጻራዊነት እና አጠቃላይ አንጻራዊነት ርዕዮተ አለሞች ወዲህ የጊዜና ኅዋ ጥምረት (መቼት) ለሳይንስ እንደመሰረታዊ ነገር ያገለግላል። በርዕዮቶቹ መሰረት፣ መቼት፣ በእንቅስቃሴ ምክንያት ከአንድ ተመልካች ወደሌላ ተመልካች የሚለያይ እንጂ በአንድ ዋጋ ለሁሉ ተመልካች አይጸናም። በርዕዮቶቹ መሰረት፣ ያለፈው ጊዜ የሚባለው ብርሃን ለአንድ ተመልካች መላክ የሚችሉ ኩነቶች (ክስተቶች) ስብስብ ሲሆን ፣ መጪው ጊዜ ደግሞ አንድ ተመልካች ብርሃን ሊልክባቸው ይሚችላቸው ኩነቶች ስብስብ ነው።

 

አንስታይን በምናባዊ ሙከራው እንዳሳየ፣ በተለያየ ፍጥነት የሚጓዙ ሰወች በሚያዩዋቸው ኩነቶች (ክስተቶች) መካከል ያለው የጊዜ ልዩነት በሁሉም ተመልካቾች አንድ አይነት ሳይሆን የተለያየ ነው። ማልተ ሁለት ቦምቦች ቢፈነዱና አንዱ ተመልካች 5 ሰከንድ በሁለት ቦምቦች ፍንዳታ መካከል ቢለካ፣ ሌላኛው ደግሞ 6 ሰኮንድ ሊለካ ይችላል (እንደ ፍጥነቱ ይወሰናል)። በተረፈ የቦምቦቹ ፍንዳታ በአማካኝነት (causality) ካልተያያዙ (ማለት ያንዱ ቦምብ ፍንዳታ ለሌላው ቦምብ መፈንዳት ምክንያት ካልሆነ/መንስዔ ካልሆነ)፣ የኩነቶቹ ድርድር ሁሉ ሊለወጥ ይችላል። አንዱ ተመልካች ቀዩ ቦምብ መጀሪያ ከዚያ አረንጓዴው ሲፈንዳ ካየ ሌላው ደግሞ አረንጓዴ መጀመሪያ ከዚያ ቀዩ ሲፈንዳ ሊያስተውል ይችላላ (መረሳት የሌለበት፣ ይህ ሁሉ የሚሆነው ሰወች በብርሃን ፍጥነት አካባቢ እሚጓዙ ከሆነ ብቻ ነው)። 

እንደ አንስታይን አገላለጽ፣ ሁለት ኩነቶች በ ነጥብ A እና B ቢፈጠሩ እና ነጥቦቹ በ K ስርዓት ውስጥ ታቃፊ ቢሆኑ፣ ሁለቱ ኩነቶች ባንዴ ናቸው (ባንድ ላይ ተከስቱ) የምንለው ከመሃላቸው ባለው ነጥብ M ላይ ያለ ተመልካች ሁለቱም ኩነቶች ባንድ ቅጽበት ሲከስቱ ሲያይ ብቻ ነው። ስለዚህ ጊዜ ማለት ከስርዓት K አንጻር ባንዴ የሚፈጠሩ ክስተቶችን ባንዴ እንደተፈጠሩ የሚያሳዩና በሥርዓቱ ውስጥ የማይነቀሳቀሱ ሰዓቶች ስብስብ ነው።

ሥዕሉ የሚያሳየው በአንጻራዊ እና በኒውተናዊ ጊዜ መካከል ያለውን ልዩነት ነው። ይህ ልዩነትም የሚነሳው በጋሊልዩ ለውጥ እና በሎሬንዝ ለውጥ መካከል ባለ አለመጣጣም ነው። የጋሊሊዩ ለኒውተን ሲሰራ የሎሬንዝ ለአንስታይን ይሰራል። ከላይ ወደታች የተሰመረው መሰመር ጊዜን ይወክላል። አድማሳዊው ወይም አግድሙ መስመር ደግሞ ርቀትን ይወካልል (አንድ የኅዋ ቅጥ መሆኑ ነው)። ወፍራም የተቆራረጠው ጠማማ መስመር ደግሞ የተመልካችን መቼት ይወካልል፣ ይህ መስመር የዓለም መስመር ይባላል። ትናንሾቹ ነጠብጣቦች ደግሞ አላፊንና መጪን መቼታዊ ኩነቶች ይወክላሉ።

የዓለም መሰመር ኩርባ ደግሞ የተመልካችን አንፃራዊ ፍጥነት ይሰጣል። በሁለቱም ሥዕሎች እንደምናየው ተመልካቹ ፍጥንጥን ባለ ጊዜ የመቼቱ እይታው ይቀየራል። በኒውተናዊ ትንታኔ እነዚህ ለውጦች የጊዜን ቋሚነት አይቀየሩም ስለዚህም የተመልካቹ እንቅስቃሴ ኩነቱ አሁን መፈጠሩን ወይም አለመፈጠሩን አይለውጠውም (በስዕሉ መሰረት፣ ክስተቱ በአግድሙ መስመር ማለፉን ወይም አለማለፉን )።

በአንጻራዊ ጊዜ ትንታኔ መሰረት ግን፡ ክስተቶችን የምንመለከትበት ጊዜ ቋሚ የማይናወጥ ሆኖ ስላ፡ ማለተ የተመልካቹ እንቅስቃሴ የተመልካቹን የብርሃን አሹሪት ማለፉን ወይም አለምፉን አይለውጥም። ነገር ግን ከኒውተናዊ (ፅኑ ትንተና) ወደ አንጻራዊ ትንተና በተሻገርን ወቅት ፣ የጽኑ ጊዜ ጽንሰ ሃሳብ አይሰራም፣ በዚህ ምክንያት ሥዕሉ ላይ እንደምናየው ክስተቶች/ኩነቶች ወደ ላይና ወደታች ከጊዜ አንጻር ይሄዳሉ፣ ይህን የሚወስነው እንግዲህ የተመልካቹ ፍጥንጥነት ነው።

ከለተ ተለት ኑሮ እንደምንረዳው ጊዜ አቅጣጫ ያለው ይመስላል፦ ያለፈው ጊዜ ተመለሶ ላይመጣ ወደ ኋላ ይቀራል፣ የወደፊቱ ደግሞ ከፊትለፊት እየገሰገሰ ይመጣል። በዚህ ምክንያት የጊዜ ቀስት ካለፈው ወደ ወደፊቱ ያለማመንታት ይገሰግሳል። ሆኖም ግን አብዛኛወቹ የተፈጥሮ ህግጋት ጥናት (ፊዚክስ) ህጎች የጊዜን አንድ አቅጣጫ መከተል ዕውቅና አይሰጡም። ለዚህ ተጻራሪ የሆኑ አንድ አንድ ህግጋት በርግጥ አሉ። ለምሳሌ ሁለተኛው የሙቀት እንስቃሴ ህግ እንደሚለው የነገሮች ኢንትሮፒ ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ እንጂ እየቀነሰ አይሄድም የሚለው ይገኝበታል። የስነ ጠፈር ምርምርም በዚህ አንጻር የጠፈር ጊዜ ከመጀመሪያው ታላቁ ፍንዳታ እንደሚሸሽ ሲያስቀምጥ፣ የስነ-ብርሃን ትምህርት ደግሞ የብርሃን ጨረራዊ ሰዓት በአንድ አቅጣጫ እንደሚተምም ያስቀምጣል። ማንኛውም የመለካት ስርዓት በኳንተም ጥናት፣ ጊዜ አቅጣጫ እንዳለው ያሳያል።

የጊዜ ጠጣርነት ምናባቂ ጽንሰ ሃሳብ ነው። በዘመናዊ ፊዚክስና በ አጠቃላይ አንጻራዊነት ትምህርት ጊዜ ጠጣር አይደለም። 

የፕላንክ ጊዜ ተብሎ የሚታወቀው (~ 5.4 × 10−44 ሰከንድ ሲሆን፣ ባሁኑ ጊዜ ያሉት ማናቸውም የተፈጥሮ ህግ ርዕዮተ አለሞች ከዚህ ጊዜ ባነሰ የጊዜ መጠን እንደማይሰሩ ይታመናል (ልክ የኒውተን ህጎች ወደብርሃን ፍጥነት በተጠጋ ስርዓት ውስጥ እንደማይሰሩ)። የፕላንክ ጊዜ ምናልባትም ሊለካ የሚችል የመጨረሻ ታናቹ የጊዜ መጠን ነው፣ በመርህ ደርጃ እንኳ ከዚህ በታች ሰዓት ላይለካ እንዲችል ባሁኑ ጊዜ ይታመናል። በዚህ ምክንያት የጊዜ ጠጣሮቹ መስፈርቶች የ(~ 5.4 × 10−44 ሰከንድ ቆይታ አላቸው ማለት ነው።




#Article 404: ኦይለር ቁጥር (114 words)


የኦይለር ቁጥር በእንግሊዝኛ e  የሚል ምልክት ያለው ለሒሳብ ጥናት አስተዋጾ እያደረገ የሚገኝ ለየት ያለ ቁጥር ነው።  ቁጥሩ በ2 እና በ3 መካከል የሚገኝ ሲሆን ዋጋውም ከሞላ ጎደል 2.71828..  ነው። የቁጥሩ ስም የመጣው ከስዊዘርላንዱ ሂሳብ ተመራማሪ ላዩናርድ ኦይለር (Leonhard Euler)  ነው። 

e ከሌሎች ቁጥሮች ለየት የሚልበት ምክንያት  ይህን ቁጥር በ x  ከፍ ስናረገው፣ f(x) = ex፣  የሚያስገኘው ዳገት ኩርባ (slope) x ባዶ ሲሆን አንድ ነው። ይህንንም በሰተቀኝ ከሚታየው የመለኪያ ሰንጠረዥ መረዳት ይቻላል። ባጠቃላይ መልኩ የf(x) ኩርባ ማንኛውም ቦታ ላይ ከf(x) ጋር አንድ ነው።

በተመሳሳይ ከ አንድ ወደ ዜሮ እየተጠጉ የሚሄዱ ቁጥሮች ቀስ በቀስ እየደመርን በግልባጫቸው ደግሞ ውጤቱን ከፍ ብናደርግ አሁንም ውጤቱ ወደ ኦይለር ቁጥር እየተጠጋ ይሄዳል ማለት ነው።

]

n! ሲነበብ  የ n  ፋክትሮሪያል ማለት ነው። 




#Article 405: ኒኑስ (357 words)


ኒኑስ በጥንታዊ የግሪክ ታሪክ ጸሃፊዎች ዘንድ የነነዌ መስራችና የአሦር ንጉስ ነበረ። ለዘመናዊ ሥነ ቅርስ የታወቀ አንድ ግለሰብ አይመስልም፤ ዳሩ ግን የአያሌ ታሪካዊ ወይም አፈ ታሪካዊ ግለሰቦች ትዝታ በአንድ ስም በግሪኮች በኋለኛ ዘመን እንደ ተዘከረ አሁን ይታስባል። 

የንጉሥ ኒኑስና ሚስቱ ንግሥት ሴሚራሚስ ስሞች በጽሁፍ መጀመርያ የተገኘው ክቴስያስ ዘክኒዱስ (400 ዓክልበ. ገዳማ) በጻፈው በፋርስ አገር ታሪክ ነው። ክቴስያስ ለ2 አርጤክስስ (2 አርታሕሻጽታ) የመንግሥት ሀኪም ሆኖ የፋርስ ነገሥታት ታሪካዊ መዝገቦች አንብቤያለሁ ብሎ አሳመነ። ከዚህ በኋላ የግሪክ ታሪክ ጸሐፊ ዲዮዶሮስ ሲኩሉስ የክቴስያስን ወሬ አስፋፋ። የአለም ታሪክ ሊቃውንት እስከ 1880ዎቹ ድረስ የኒኑስ ታሪክ ዕውነት መሆኑን ይቈጠሩት ነበር። በዚያን ጊዜ የኩኔይፎርም ጽሕፈት ፍች ስለ ተፈታ፣ በሜስፖጦምያና በነነዌ ብዙ ቅርሶችም በመገኘታቸው፣ የአሦር ትክክለኛ ታሪክ ዕውቀት ተጨመረልን። 

ኒኑስ የቤሉስ ወይም ቤል ልጅ ተባለ፤ ይህም ምናልባት በሴማዊ ቋንቋ ሥር «ባል» (ጌታ) የመሰለ ማዕረግ ሊሆን ይችላል። በካስቶር ዘሮድስ ዘንድ ኒኑስ ለ52 ዓመታት ነገሰ፤ ክቴስያስም እንዳለው መጀመርያው ዓመተ መንግሥቱ 2198 ዓክልበ. ነበረ። በ17 አመታት ውስጥ ኒኑስ በአረቢያ ንጉስ አርያዎስ እርዳታ ምዕራብ እስያን በሙሉ እንዳሸነፈ ተብሏል። ከዚህ ቀጥሎ የአርመን ንጉስ ባርዛኔስን (ይቅርታ የሰጠውን) እና የሜዶን ንጉስ ፋርኖስን (በስቅለት ይሙት በቃ የሰጠውን) ድል በማድረግ የአለም መጀመርያ ንጉሠ ነገስት እንደ ሆነ ተብሏል። 

ግሪኮቹ እንደ ተረኩት፣ ይህ ኒኑስ በዙርያው ያሉትን እስያዊ አገሮች ከሕንድና ከባክትርያና በስተቀር በሙሉ አሸነፋቸው። ከዚያ ወዲያ ኒኑስ በ2 ሚሊዮን ወታደሮች ሠራዊት በባክትርያና ንጉሥ በኦክስያርቴስ ላይ ወረራ ጀመረ። አገሩ ሁሉ ቢወድቅም ዋና ከተማው ባክትራ ግን አልወደቀምና ሠራዊቱ ከበቡት። ባክትራን ሲከብቡት ኒኑስ የመኮነኑ ኦኔስ ሚስት ሴሜራሚስ አገኛትና ከባልዋ ነጥቆ እንደ ራሱ ሚስት ልትሆን ያዛት። ልጃቸው የኒኑስ ተከታይ ኒንያስ ሆነ። 

ከሮማዊ ታሪክ ጸሃፊ ኬፋልዮን (120 ዓ.ም. ገደማ) ጀምሮ፣ አንዳንድ ታሪክ ሊቅ የኒኑስ ተቃዋሚ ኦክስያርቴስ ሳይሆን፣ በዕውነት የባክትርያ ንጉሥ ዞራስተር እንደ ነበር ጽፈዋል። 

በቅሌሜንጦስ ጽሁፎች በአንዱ ዕትም፣ የኒኑስ መታወቂያ ከናምሩድ ጋራ አንድላይ ነው በማለት ደራሲው ይኸው ሰው የእሳት አምልኮት ለፋርሶች ያስተማረ ነው ይነግረናል። በኦሪት ዘፍጥረት 10፡11-12 መሠረት የነነዌ መስራች የሴም ልጅ አሦር ቢባልም፣ በአንዳንድ ትርጉም ከእብራይስጥ መጽሐፍ ቅዱስ፣ የነነዌ መስራች ናምሩድ እንደ ነበር ይመስላል። 

በ19ኛው ክፍለ ዘመን ሁለቱ ባቢሎኖች የጻፈው አሌክሳንድር ሂስሎፕ ሃልዮ፣ የናምሩድና የኒኑስ (እንዲሁም የዞራስተር) መታወቂያ አንድ መሆኑ ዋና ነጥብ ነው። 

ክቴስያስና ዲዮዶሮስ እንዳወሩት፣ ከኒኑስ ሞት በኋላ ሴሜራሚስ እንደ ገደለችው ተከሰሰች። እርስዋ ግን ታላቅ መቅደስ ግንብ በባቢሎን ለማስታወሻው አሠራች። እርስዋ በተጨማሪ በእስያ መጨረሻው ነፃ ንጉሥ በሕንድ ንጉሥ ስትራቶባቴስ ላይ ዘመቻ እንዳደረገች አወሩ። ነገር ግን ድል ሆና ለልጅዋ ለኒንያስ ዙፋኗን ተወች ነበር። 




#Article 406: ንብ (168 words)


ንብ በራሪ ነፍስinsect ናት፤ ከሶስት አፅቂዎች የምትመደብ ስትሆን ልክ እንደ ጉንዳን ካሉ Hymenoptera ቤተሰብ ትመደባለች፤ ይህቺ በራሪ ነፍስ በማር እና በሰም ምርቷ ትታወቃለች፤ በምድራችን ላይ ከ20,000 በላይ የታወቁ የንብ ዝርያዎች ሲኖሩ እነዚህም በዘጠኝ ታዋቂ ቤተሰቦች ተከፋፍለዋል፤ ምን አለፋን ከተጠቀሰው ቁጥር በላይ ዝርያዎች ሊኖሯቸውም ይችላል። 
ንብ የራሷን ቤቶች የምትሰራው ከተራራዎች፣ ከዛፍም፣ ሰዎች ከሚሠሩትም ቀፎ ነው፤ ይህንን ሥርአት በደመነፍስ (አረብኛ ዋሂ) ያሳወቃት ንድፍ አውጪው አምላካችን አላህ መሆኑ በቁራን ይጠቀሳል፦

 
ንብ አበባዎች ባሉበት ሁሉ ትገኛለች፤ የንብ አካላቷ በሦስት ክፍል ይከፈላል፤  አንደኛው ክፍል የምታሸትበት፣ የምትዳስስበት፤ የምትሰግበት፣ በግንባሯ በስተቀኝና በስተግራ ሁለት ቀጫጭን ነገሮች እንደ ቀንድ የሆኑ አሏት፤  ደግሞ በዚህ በገጿ ላይ ሁለት ትልልቅ ጠፍጣፋ ዓይኖች በግራና በቀኝ ሆነው ለማየት የሚያስችሏት በሌሎች ትንንሽ ዓይኖች የተሞሉ አሏት። 
ሁለተኛው ክፍል የአካሏ ክፍል  ፀጉራሞች የሆኑ በአበባ ውስጥ ያለውን ኔክታር ማለትም ፈሳሽ ነገር ስትመጥ የአበባ ዱቄት የምታመጣባቸው ስድስት እግሮች፣ ሁለት ወፈር ያሉ ክንፎችና ሌሎች ሁለት ሳሳ ያሉ ክንፎች በጠንካሮች ሥር የሆኑ አሏት። 
በሦስተኛው የአካላት ክፍሏ እንደ አንጓ ክርክር ያላቸው መተንፈሻዎች የምትነድፍበትና የተበላሸውን የምታስወጣበት አሏት።
ከፍራፍሬ ከሚገኘው የአበባ ዱቄት ምግቧን ትብላለች፤ ይህንን የተፈጥሮ ሥርአት የነደፈላት አምላካችን አላህ ነው፦

ኡስታዝ ወሒድ ዑመር




#Article 407: የዕብራውያን ታሪክ (2034 words)


በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት የዕብራውያን ታሪክ በዔቦር ተወላጅ በአብርሃም (መጀመርያ አብራም ተብሎ) ይጀምራል።

እንደ ብሉይና ሐዲስ ኪዳን አቆጣጠር አብርሃም (አብራም) ለአዳም ፳፩ኛ ትውልድ ነው። የተወለደውም ከአርፋክስድ ወገን በከለዳውያን ከተማ በከላውዴዎን ዑር ነው።  ኦሪት ዘፍጥረት 11፡31 እንደሚለው፣ ይህ አብራም ከአባቱ ከታራ ቤተሠብ ጋራ ከዑር ተነሥተው ወደ ከነዓን ይሄዱ ዘንድ በካራን አገር ተቀመጡ። ስለዚህ ዑርና ካራን የተለያዩ ቦታዎች ናቸው። የከለዳውያን ዑር የሚባለው ስፍራ በአርፋክስድ ርስት ሲሆን፣ አብርሃም የደረሰበት ሥፍራ ካራን ግን በአራም ርስት በፓዳን-አራም ወይም አራም-ናሓራይም (አራም በሁለቱ ወንዞች መካከል ወይም መስጴጦምያ) ተገኘ። 

አብርሃም በዚህ ስፍራ በልማድም በዝምድናም ተሳስሮ አብሮ ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር ተገለጠለትና እንዲህ ሲል አዘዘው። «ካገርህ ውጣ፤ ከዘመዶችህም ካባትህም ቤት ተለይ እኔ ወደማሳይህ ምድር ሂድ፤ ታላቅም ሕዝብ አደርግኻለሁ። ለበረከትም ትሆናለህ» (ዘፍ፡ ም፡ ፲፪፡ ቁ፡ ፩-፲።) ይህ ዘመን ከክርስቶስ ልደት በፊት ምናልባት 2119 ዓመት ግድም ነው። እንግዲህ አብርሃም በአንዱ እግዚአብሔር በቻ ለማምለክና እሱና ዘሩ ለእግዚአብሔር የተመረጡ እንዲሆኑ የተጠራበት ዘመን ነበር። ከዚህም ዘመን አስቀድሞ፣ ኦሪት ዘፍጥረትና መጽሐፈ ኩፋሌ እንደሚተርኩት፣ አሕዛብ ሁሉ እንደየኖኅ ልጆች ወገኖች ከባቢሎን ግንብ ሥፍራ ከሰናዖር ወደየአገራቸው ተበትነው ነበር። የካም ልጅ ከነዓን ግን የኩፋሌ ውላቸውን ፈርሶ ወደ ማዶ ባሕር በመርከብ ለመጓዝ ፈቃደኛ ሳይሆን በአርፋክስድ (በሴም) ርስት ተቀመጠና በልጁ ሲዶና ስም ከተማ ሠራ። በዚያው ዘመን አሕዛብ ሁሉ በስኅተት ተመርተው ወደ ጣኦት ቢዞሩም በከነዓን የተነሡት ሕዝቦች ልማድ በተለይ እግዚአብሔርን እንዳስጠላው ይላል። 

አብርሃም ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ ታዘዘ ከወገኖቹ ከከለዳውያን ተለይቶ ቤተሰቡን ይዞ ወንድሙን ሎጥን፤ ከነቤተሰቡ አስከትሎ ወደ ከነዓን አገር (ዛሬ ኢየሩሳሌም ወይም ፓለስቲን ወደሚባለው) ሄዶ ተቀመጠ። በዚያም ሲኖር ከሸመገለ በኋላ ይስሐቅን ከሚስቱ ከሳራ፤ እስማኤልን ከገረዱ ከአጋር ወለደ። ነገር ግን ከገረዱ የተወለደው ወደ ፊት ለአብርሃምና ለዘሩ የተመደበውን አገርና ዕድል አይወርስም ተብሎ በእግዚአብሔር ትዕዛዝ እስማኤልን ከነናቱ አስወጥቶ ወደ ፋራን በረሓ (ዐረብ) ሰደዳቸው። ዛሬ እስላሞች ሁሉ ዓረቦች በእስማኤል በኩል የአብርሃም ልጆችና ወራሾች ናቸው ይላሉ። በተለይ ፳ኤሎች ግን በአብርሃም ልጅነት የሚመኩት በደንበኛው ልጁ በይስሐቅ በኩል የመጣውን ትውልድ በመከተል ነው። አንዳንድ ክርስቲያን ደግሞ እንደ ዮሐንስ ምጥምቁ ቃል መዳን በአብርሃም ተወላጅነት የሚሰጥ አይደለም ባዮች ናቸው። (ማቴ 3፡9፤ ሉቃስ 3፡8)

ይስሐቅም ከሚስቱ ከርብቃ ኤሳውንና ያዕቆብን ወለደ። ያዕቆብ የኤሳው ታናሽ ሆኖ ሳለ ብኵርናን በምስር ወጥ ከኤሳው ከገበየ በኋላ ዐሥራ ሁለቱን የእስራኤልን የነገድ አባቶች ወለደ። ከዐሥራ ሁለቱም አንዱ ከብንያም በላይ የመጨረሻው ልጅ ዮሴፍ ነው። በዛሬ አባቶች ዘንድ እንደ ተለመደ ትንሹን ዮሴፍን አባቱ ያዕቆብ ከሌሎቹ አብልጦ ይወደው ነበርና በዚሁ ቅናት የያዛቸው ወንድሞቹ ከምድያም በከነዓን በኩል ወደ ግብፅ ለሚሔድ ነጋዴ ዮሴፍን ሸጡት። ገዥውም ዮሴፍን ይዞ ወደ አገሩ ወደ ግብፅ ከገባ በኋላ ለጶጢፋር ሸጠው። ጶጢፋርም በቤቱ እንደ አሽከር አድርጎ አስቀመጠው። ጌታውም ለጉዳዩ ወደ ውጭ በሔደበት ሰዓት የጌታው ሚስት ለሥጋ ፈቃድ ተመኘችውና ጠየቀችው። እሱም «ጌታዬ ባያይ እግዚአብሔር ያያል» የሚል የሚያስደነግጥ መልስ ሰጠና እንቢ አላት። እሷ ግን ሳታፍር ሳትደነግጥ ለማስገደድ ልብሱን ብትይዘው ልብሱን ተወላትና ወደ ውጭ ሸሸ።

ከዚህ በኋላ ጌትዮው ከመንገድ ሲገባ «ይኸ ለአሽከርነት ያመጣኸው ዕብራዊ ካላነቅሁሽ ብሎ ስንተናነቅ ብጮኽበት ልብሱን ጥሎኝ ሔደ» ብላ አሳየችው። ጌትዮም ነገሩን ሳይመረምር የሚስቱን ቃል ብቻ በማመን ጻድቁን እንደ ኅጢአተኛ እወህኒ ቤት አገባው። ከዚህ ከወህኒ ቤት በሕልም አፈታት ምክንያት ወጥቶ ከግብፅ ንጉሥ ከፈርዖን ጋራ ተዋወቀና ባለሟል ሆነ። ቀጥሎም ዮሴፍ የንጉሡ የፈርዖን እንደራሴ ለመሆን በቃ። በዚህ ዘመን ግብፅን ይገዙ የነበሩት የመካከለኛው መንግሥት ፈርዖኖች ነበሩ።

በዚህ ዘመን በከነዓን አገር ረኃብ ተነሥቶ ነበርና፤ የሚሸመት እኽል ለመፈለግ የሸጡት ወንድሞቹ ከከነዓን ወደ ግብፅ መጡ። እሱም ወንድሞቹን ዐወቃቸው፤ የሚፈልጉትንም እኽል ሰጣቸው። የአባቱንም ሕይወት ጠይቆ ከተረዳ በኋላም ከአባታቸው ከያዕቆብና ከሚስቶቻቸው ጋራ ከከነዓን ወደ ግብፅ መጥተው እንዲቀመጡ ነገራቸው። ከዚህ በኋላ ከእግዚአብሔር ለአባታቸው ለአብርሃምና ለዘሩ የተሰጣቸውን አገራቸውን ከነዓንን ትተው ያዕቆብና ልጆቹ በድምሩ ፸ ነፍስ ሆነው ግብፅ መጥተው ተቀመጡ። ወደ ግብጽ የወረዱበት ጊዜ፣ በመጽሐፈ ኩፋሌ ሲቆጠሩ፣ ከፍጥረት 2172 ዓመታት አለፉ፣ ይህም ከክርስቶስ ልደት በፊት 1900 ዓመታት ያህል ነው።  ዮሴፍ ካለፈ በኋላ፣ በአባይ ወንዝ አፍ ወይም በጌሤም ለትንሽ ጊዜ ለእጭታዊ (ለ13ኛው ሥርወ መንግሥት) ተገዥ 14ኛ ሥርወ መንግሥት ተነሣ፤ እነዚህ ከከነዓን የደረሱ ሴማዊ እረኞችና ነጋዴዎች ሲባሉ የዕብራውያን ዘመን በግብጽ ሊያብራራ ይችላል።

በግብፅ ፻ ዓመት ያኽል እንደ ተቀመጡ ዘራቸው በረከተና የግብፅን መንግሥት እማሥጋት ደረሱ። ስለዚህ በበረከቱበት በመጨረሻ ጊዜ የነበረው የግብፅ ንጉሥ በእስራኤሎች ላይ በኃዘን እስኪጮሁ ድረስ አገዛዝ አጸናባቸው። ይህ ጭቆና ሙሴ በተወለደበት ሰዓት ያህል ጀመረ። እግዚአብሔር ግን ለበረከት ትሆናላችው ብሎ ለራሱ አምልኮ የመረጣቸው ሕዝቦች ናቸውና ሥቃያቸውን ተመልክቶ አዘነላቸው። ሙሴም አድጎ ወደ ምድያም ሸሽቶ የያህዌን ራዕይ በደብረ ሲና ላይ አይቶ ሕዝቡ ከግብጽ እንዲያመልጡ ታዘዘ። በሙሴም አማካይነት በልዮ ልዮ ተአምራት ከግብፅ አወጣቸው። ፈርዖኑም ከግብጽ በር ስያባርራቸው ሥራዊቱ በታላቅ ተዓምር  በቀይ ባሕር ጠፋ። 

የዚህ ፈርዖን መታወቂያ በሰፊ ተከረክሯል። ለምሳሌ ዳግማዊ ራምሴስ እንደ ነበር የሚያስቡ ብዙ አሉ። ሆኖም ይህ ፈርዖን የገዛ በ1200 ዓክልበ. ግድም ስለ ሆነ፣ ከዳዊት ዘመን በፊት ለእስራኤል ዘመነ መሳፍንት (በመጽሐፈ መሳፍንት) ከዘጸዓት በኋላ ጊዜው አይበቃም።  በመጽሐፈ ኩፋሌ ቁጥጥር ከግብጽ ታሪክ ጋር ሲስማማ፣ ዘጸዓት የሆነው በ1661 ዓክልበ. ስለ ሆነ የጠፋው ፈርዖን መርነፍሬ አይ (ከ13ኛው ሥርወ መንግሥት) ይመስላል። በመርነፍሬ አይ ዘመን መጨረሻ፣ ዕብራውያን የወጡበት ዓመት፣ የግብጽ ኃይል እጅግ ደክሞ አንድ አሞራዊ ወገን «ሂክሶስ» ወይም 15ናው ሥርወ መንግሥት ወደ ግብጽ ስሜን ወረረ፤ እነዚህ ከከነዓን ስለ ደረሱ ብዙ ጊዜ ከእብራውያን ጋር ተደናግረዋል። ኢያሱ ወልደ ነዌ ከነዓንን እያሸነፈው፣ ሂክሶስ መላውን ግብጽ ያሸነፉ ተዋጊዎች ነበሩ፣ በ1548 ዓክልበ. ፈርዖኑ አህሞስ ሂክሶስን ከግብጽ አባረራቸው እንጂ ይህ የእብራውያን ዘጸአት አልነበረም። ለእስራኤል ወደ ፊትም የሚተዳደሩበትን ሕግ በሙሴ አማካይነት ሰጣቸው። ከዚያም በኢያሱ መሪነት የከነዓንን ነገሥታት አሸንፈው ለአባታቸው ወደ ተሰጠው ወደ ከነዓን አገር ገቡ።

በአብርሃምና በያዕቆብ ጊዜ ያንድ የትልቅ ሰው ቤተሰብ ብቻ የነበሩት አሁን ግን ከያዕቆብ እስከ ሳሙኤል ድረስ ፷፻ ዓመት በሚያኽል ጊዜ ውስጥ በርክተው በበረቱባቸው ጊዜዎች መንግሥት ለማቆም በቁ። መጽሐፈ መሳፍንት እንደሚተርክ፣ በሌሎች ወቅቶች በአረመኔ ጎረቤታቸው በአሕዛብ ጣኦታት ከተሳሳቱ በኋላ፣ አይሁዶች ለጊዜ ተገዥ ይሆኑ ነበር። በየተራ ለሶርያ፣ ለሞአብ፣ ለአሞን፣ ለምድያም ወዘተ.  ይገዙ ነበር፣ እያንዳንዱም ጊዜ ዕብራውያን ወደ እግዜር በተመለሱበት ወቅት የሚያድናቸው ፈራጅ ወይም አለቃ ይልካቸው ነበር። ጎቶንያል፣ ናዖድ፣ ዲቦራና ባራክ፣ ጌዴዎንም በዚህ አይነት ነበሩ፣ የአረመኔ ሃይሎችን ያሸንፉ ነበር። በነዚህም ክፍለዘመናት በሥነ ቅርስ በተገኙት በሌሎች ታሪካዊ ሰነዶች እንደሚታወቅ፣ «ሃቢሩ» ወይም «አፒሩ» የተባለ ብርቱ ወገን ከከነዓናዊ ጎረቤቶቻቸው ጋራ  ይታገሉ ነበር፤ ሆኖም የነዚህ «ሃቢሩ» መታወቂያ ለዘመናዊ ምዕራባውያንና አይሁዳውያን ሊቃውንት የ«ሚኒማሊስም» (ክህደት) ፍልስፍና ተከታዮች ስለ ሆኑ አጠያያቂ ጉዳይ ሆኗል።  

ከጌዴዎን ቀጥሎ አቢሚለክ ለሦስት ዓመታት (1252-1249 ዓክልበ. ያህል) የእስራኤላውያን አምባገነን በሴኬም ተደረገ። በእርሱ አስተዳደር ግን ሃይማኖታቸው የአረመኔ ጣኦት በአልብሪት አምልኮት ሆነ። መጨረሻውም በእርስ በርስ ጦርነት ደረሰ (መሳፍንት 9)።   በሚከተሉት ፈራጆች ዘመን ዕብራውያን በተለይ በገለዓድና ኤፍሬም ሠፈሮች ይጠቀሳሉ እንጂ መላውን አገር እንዳልያዙ ይመስላል።  በ1155 ዓክልበ. ግን እንደገና ፍልስጥኤም በርቶ እስራኤልን ይገዛ ጀመር። በ1135 ዓክልበ. በፍልስጥኤማውያን ሥር እየቆዩ ሶምሶን የእስራኤላውያን አለቃ ሆነ። በ1115 ዓክልበ. ኤሊ የእስራኤል ፈራጅ ሆነ። በ1076 ዓክልበ. ፍልስጥኤማውያን ታቦትን ማረኩ፤ በሚከተለው አመት ግን ሳሙኤል አስመለሰው። 

ስለዚህ በመጀመሪያ ጊዜ በነጌዴዎን፤ በነሶምሶን በመሳፍንቱ፤ ከዚያም በነኤሊ፤ በነሳሙኤል በካህናቱ ሲተዳደሩ ቆይተው በመጨረሻ እንደ ጎረቤቶቻቸው እንደ ፍልስጥኤማውያን፤ እንደ ሞዓባውያንና እንደ አሶራውያን «ንጉሥ» ይደረግልን ብለው ጠየቁና በእግዚአብሔር ፈቃድ  በ1055 ዓክልበ. ሳሙኤል ሳኦል የእስራኤል ንጉሥ እንዲሆን አደረገ።

ከዚያም ዳዊት ቀጥሎም ልጁ ሰሎሞን ነገሠ። በዳዊትና በሰሎሞን ዘመነ መንግሥት የእስራኤል ልጆች መንግሥታቸው ታላቅ መሆኑ በሁሉ ዘንድ ታወቀ። እነዚህ የእስራኤል ዘሮች ምንም እንኳን ቀድሞ በግብፅና በሲና በረሓ በኋላም በአገራቸው በከነዓን ሳሉ አንዳንድ ጊዜ አብረው በአሉት ሕዝብ ልማድና አምልኮ እየተዋጡ ጣዖት ማምለካቸው ባይቀር ከአብርሃም ጀምሮ እስከዚህ እስከ ሰሎሞን መንግሥት ድረስ፤ ከሰሎሞን ጀምሮም እስከ ዛሬ ድረስ በአንዱ በእግዚአብሔር ያመልካሉ። በሰሎሞንም ጊዜ ለእግዚአብሔር ትልቅ ቤተ መቅደስ ተሠራ። ስለዚህ የእውነተኛው እግዚአብሔርና የነሱም የዳዊትና ይልቁንም የሰሎሞን ስም በዓለም ታወቀ። ከክርስቶስ ልደት በፊት በሺ ዓመት ላይ ንግሥታችን ንግሥተ ሳባ የሰሎሞንን ጥበብ ለማየት ወደ ይሁዳ ከተማ ወደ ኢየሩሳሌም የሔደቸው በዚህ ምክንያት ነው።

ነገር ግን ከዚያ ወዲህ የተነሡት የሰሎሞን ተከታዮች አንዳንድ ነገሥታት የጎረቤቶቻቸውን የጢሮስንና የሲዶናን የባቢሎንንም አማልክት ብኤልንና ሞሎክን እያመለኩ እግዚአብሔርን አሳዘኑት። አንዱ ንጉሥ ተነሥቶ ለጣዖት አትስገድ አታምልክ፤ የሰገድህ አንደ ሆነ በአሕዛብ እጅ ትወድቃለህ የሚለውን የኦሪትን ቃል በካህናቱና በነቢያቱ አፍ ለሕዝቡ እያስነበበ ጣዖታቱን እንዲያጠፉና ሕዝቡ እውነተኛውን እግዚአብሔርን ብቻ እንዲያመልክ ሲያደርግ፤ አንዱ ንጉሥ ደግሞ የማይታየውን እውነተኛውን እግዚአብሔርን ከማምለክ የሚታየውን ሐሰተኛውን ጣዖት ማምለክ ስለ መረጠና ሕዝቡም ስለ ተከተለው እስራኤል ከአምላካቸው ከእግዚአብሔር ተጣሉ። የውድቀታቸውም ዋዜማ ሲሆን ወደ ሁለት መከፈል ጀመሩ። ከሙሴ ጀምሮ እስከ ሰሎሞን ድረስ በ፩ መሪ ይተዳደሩ የነበሩት አሁን በሮብዓም ዘመን ወደ ሁለት ተከፈሉና ዐሥሩ ነገዶች ከኢየሩሳሌም በሰሜን በኩል ያለውን ሰማርያን ያዙ። የመጀመሪያውም ንጉሣቸው ኢዮርብዓም ሆነ። ሁለቱ የይሁዳና የብንያም ወገኖች በታችኛው በዚሁ በኢየሩሳሌም ቀርተው ለየብቻ ይተዳደሩ ጀመር። ስማቸውም የላይኛው የእስራኤል መንግሥት የታችኛው የይሁዳ መንግሥት ይባል ጀመር።

እነዚህ ወደ ሁለት የተከፈሉት መንግሥታት አንዳንድ ጊዜ እየተጣሉ እርስ በራሳቸው ሲዋጉ፤ አንዳንድ ጊዜ እየተፋቀሩ አንድ ሆነው የእስራኤልን መንግሥት ጠላት አሶርን የይሁዳን መንግሥት ጠላት ባቢሎንን ሲወጉ ብዙ ዘመን በነጻነት ቆዩ። ከዚህ ቀጥሎ ግን ነፃነታቸው በአሶርና በባቢሎን ተደምስሶ በሰማርያ ከነገሡት ነገሥታት እነአክዓብ (አሐብ) በይሁዳ ከነገሡት እነሮብዓም፤ እነምናሴ «እኔ ነኝ አምላካችሁ ከባርነት ቤት ከምድረ ግብፅ ያወጣኋችሁ፤ ከኔ በቀር ለሌሎች አማልክት አትስገዱ» ያለውን ችላ እያሉ ሞሎክንና ብዔልን እያመለኩ ስለ አስቸገሩት፤ በወሰናቸው ያሉት በእርሱ የማያመልኩት የአሶርና የባቢሎን መንግሥታት እንዲያይሉባቸው አደረገ።

ስለዚህ በሰሜን ያለውን የእስራኤልን መንግሥት አሶራውያን፤ በደቡብ በኩል ያለውን የይሁዳን መንግሥት ባቢሎናውያን በጦርነት ደመሰሱት። በሰሎሞን ጊዜ አምሮ የተሠራውም ቤተ መቅደስ ፈረሰ። የዚህ ቤተ መቅደስና የነገሥታቱም መሣሪያ ከነገሥታቱና ከሕዝቡ ጋራ በምርኮ ወደ ባቢሎን ተጋዘ። ወደ ኢየሩሳሌምም ከባቢሎን ከአሶር ከሰማሪያ ድብልቅ ዘሮች ከሰሜን፤ የኤዶምያስ ሰዎች ከደቡብ እየመጡ በየቀኑ ተሰደዱበት።

እንግዲህ እሰከ አሁን ድረስ ምንም እንኳን በየስፍራቸው የሰዎቹ መኖር የታወቀ ቢሆን ፋርሶችም ግሪኮችም ሮማውያንም ታናሽ እስያንና የአፍሪካን ሰሜን ወረው ገና በገናንነት አልተነሡም። ነገር ግን ከኋላ ከረጅም ጊዜ በግምት ከ፬ ሺሕ ዓመት ጀምሮ እስከ አሁን እስከ ፮ኛው መቶ ዓመት ድረስ ከክርስቶስ ልደት በፊት የታወቁም ሥልጣኔም ኃይልም ያላቸው ግብፅ፤ አሶር፤ ባቢሎን፤ ኢትዮጵያ (ናፓታ)፤ ህንድ፤ ቻይና ናቸው። ነገር ግን በኋላ የታናሽ እስያን አገሮችና ግብፅን እስራኤሎችን ጭምር ቀጥቅጦ የገዛውን በነናቡከደነጾር ጊዜ የገነነውን የባቢሎንን መንግሥት የሚጥል የፋርስ መንግሥት ተነሣ። ከፋርስ በፊት ጎረቤቱ የሜዶን (ሚድያ) መንግሥት ለጥቂት ዘመን አይሎ ነበር። እስከ ባቢሎንና እስከ አሶር እስከ ኢየሩሳሌምም ደርሶ ነበር። ፋርስንም የራሱ ግዛት አድርጎት ነበር። ነገር ግን ፋርሶች ጊዜ ሲመቻቸው ከውስጣቸው ቂሮስ የሚባለውን ብልኅ ንጉሥ ባነገሡ ጊዜ የሜዶንም የአሶርም የባቢሎንም ትልቅነት ወደ ውድቀት ማዘንበል ጀመረ።

ቂሮስ ከክርስትና በፊት በ፭፻፶ ዓመት በፋርስ ላይ ነገሠና መጀመሪያ የሜዶንን ቀጥሎ የልድያን መንግሥት አሸንፎ ያዘ። ከዚያም በናቡናኢድ ዘመነ መንግሥት ትልቁን የባቢሎንን ከተማ በ፭፻፴፰ ዓመት ከቦ አስጨነቀ። በመጨረሻም በጦር ኃይል አሸንፎ ያዘና ትልቁን የባቢሎንን ግዛት የፋርስ የአውራጃ ግዛቱ አደረገው። ከዚህ በኋላ በናቡከደናጾር ጊዜ በምርኮ የሄዱት የኢየሩሳሌም (የእስራኤል) ሹማምንት ተፈትተው ሁሉም ተሰብስበው ድል አድራጊው ቂሮስ ፊት በቀረቡና ባያቸው ጊዜ አዘነላቸው።

ስለዚህ ምርኮኞቹ ፳ኤሎች አለቆቻቸውን ዕዝራን ነሕምያን ዘሩባቤልን ይዘው በነፃነት ወደ አገራቸው ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመለሱ ፈቀደላቸው። ከኢየሩሳሌም ቤተ መንግሥትና ከቤተ መቅደስም ተዘርፎ በባቢሎን ከተማ ለጊዜው የተገኘውን ንዋየ ቅድሳት ይዘው ሄደው የፈረሰውን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ መልሰው እንዲሠሩ አዘዛቸው። ከራሱም እርዳታ ጨመረላቸው። እስራኤሎችም ቂሮስን ተሰናብተው በሹማምንት በነዘሩባቤል በሊቀ ካህናቱም እየተመሩ በደስታ ወደ አገራቸው ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው የከተማውንና የቤተ መቅደሱን ሥራ ጀመሩ። ሥራውንም እጅ በእጅ ብለው ቅጥሩን ሠርተው አዳረሱት። ዳሩ ግን በመካከሉ የሚያሳዝን ነገር መጣ። «እነዚህ ሰዎች ከተማቸውንና ቅጥራቸውን ሠርተው ከፈጸሙ በኋላ አይታዘዙልህም፤ የቀድሞ ታሪካቸውንም ስንመረምር አዋኪ ሰዎች መሆናቸውን ተረድተናል» ብለው ነገረ ሠሪዎችና የፋርስ መንግሥት ተመልካቾች ለንጉሡ ላኩ። ንጉሡም ምንም ደግና ብልኅ ቢሆን በእንደዚህ ያለ ዘውዱንና ገዥነቱን በሚያሠጋ ነገር መገንገኑ አይቀርምና ሥራው ይቁም የሚል ትእዛዝ አስተላለፈ። ቢሆንም በቂሮስም በዳርዮስም ጊዜ ሲከለከልም ሲፈቀድም በቀን ብዛት የኢየሩሳሌም ከተማና ቤተ መቅደስ ተሠርቶ አለቀ። ይህ ሁሉ በብሉይ ኪዳን በመጽሐፈ ነገሥትና በመጽሐፈ ዕዝራ በመጽሐፈ ዜና መዋዕል፤ በመጽሐፈ መቃያንና በዜና አይሁድም ተጽፏል።

የፋርስ መንግሥት በቂሮስና በነዳርዮስ ዘመን ቅልቅ የንጉሠ ነገሥት መንግሥት ሆኖ እስከ ፫፻፴፬ ዓመት ድረስ ከቆየ በኋላ በዚህ ዘመን ከመቄዶንያ (ግሪክ) ትልቁ እስክንድር ተነሥቶ ጦሩን ይዞ ከመጨረሻው ከፋርስ ንጉሥ ከዳርዮስ ፫ኛ ጋራ ተጋጥሞ አሸንፏል። እስክንድርም የዳርዮስን ጦር ካሸነፈ በኋላ የፋርስና የግዛቱ የባቢሎን የአሶር የፓለስቲን የግብፅ ባለቤት ሆኖ፤ እስከ ህንድ ወንዝ ድረስ ገፍቷል። እስክንድር በነገሠ በ፲፫ በተወለደ በ፴፫ ዓመቱ ስለ ሞተ ግዛቱን «ዲያዶክ» የሚባሉት የጦር አለቆች ተከፋፍለው እስከ ሮማውያን መምጣት ድረስ ገዝተዋል።

በፓለስቲን ያሉት እስራኤሎች ከባቢሎን ወደ ፋርስ፤ ከፋርስ ወደ ግሪክ (ከገዥ ወደ ገዥ) ከዚያም ወዲህ ቶሎሜውስ (በጥሊሞስ) በሚባሉት በግብፅ ገዥዎች ቀጥሎ ደግሞ ሴሌውሲድ በሚባሉት በሶርያ ነገሥታት ውስጥ ጥገኛም ተገዥም እየሆኑ ከክርስቶስ ልደት በፊት የሁለቱንና የአንደኛውን መቶ ዓመት ጊዜያቸውን አሳለፉ።

ቶሎሜውስና ሴሌውኩስ የሚባሉት የትልቁ እስክንድር ፪ የጦር አለቆች ነበሩ። እስክንድር ከሞተ በኋላ ቶሎሜውስ በግብፅ ነገሠና ቶሎሜይ የተባለውን፤ ሴሌውኩስ በአሶርና በባቢሎን ነግሦ ሴሌውሲድ የተባለውን ቤተ መንግሥት (ዲናስቲ) የመሠረቱ ናቸው።

ከዚህ በኋላ ሮማውያን ከኢጣሊያ ተነሥተው እነሺፒዮኔ የአፍሪካን፤ ሰሜን፤ እነማሪዮ እነቼዛሬ ኦታቪያኖ የፈረንሳዊን የኤስፓኝን የእንግሊዝን (ጋልያና ብሪታንያን ኤስጳንያን)፤ እነሲላ እነፓምፔዎ የባልካንን አገሮችና የታናሽ እስያን መንግሥታት ሲወሩ ፓምፔዎ (ዮሐንስ መደብር ፉምፍዮስ የሚለው) እንደ ኤውሮፓ አቆጣጠር በ፷፪ ዓመት ላይ ድል አድርጎ ፓለስቲንን ያዘ።

ከዚህ በኋላ በ፳፱ ዓመት ከክርስቶስ ልደት በፊት ሮማውያንን ካዩ ጁሊዎ ቼዛሬ አታቪያኖ የሚሉት በኋላ ግርማ ያለው ጠቅላይ አለቃ ለማለት «አውግስጦስ» የሚባል የማዕረግ ስም የተጨመረለት፤ እኛ ኢትዮጵያውያን በዚሁ ይዞታ አውግስጦስ ቄሳር የምንለው በሮማ ነገሠ። ከአውግስጦስ ቄሳር ንጉሥ ቀደም ብሎ በዮልዩስ ቄሳር ጊዜ በሮማ የበላይ ገዥነት ውስጥ ትልቁ ሄሮድስ የሚባለው ንጉሥ ተብሎ ከሮማ ምክር ቤት በአርባ ዓመት ከክርስቶስ ልደት በፊት ተፈቅዶ በይሁዳ (ፓለስቲን) ተሾሟል።

ሄሮድስ የኤዶምያስ ተወላጅ ነው። የኤዶምያስም ዘር ከያዕቆብ ታላቅ ወንድም ከኤሳው ትውልድ የመጣ ነው ይባላል።

ሄሮድስ በይሁዳ በነገሠ ጊዜ የግሪክና የሮማን ሥልጣኔ በአገሩ ለማስገባት ፈቃደኛ ሆነ። በሮማ የነገሠውን አውግስጦስ ቄሳርንም ከልቡ ይወደው ነበርና በቀያፉ በታች በባሕር ዳር የምትገኘዋን ከተማ አሠርቶ ለእርሱ ስም መታሰቢያ እንድትሆን ቂሳርያ ብሎ ሰየማት። በዚህ ሁሉ ምክንያት ሄሮድስ በሮማውያን ዘንድ የታመነና የተወደደ ሆኖ በፓለስቲን በንጉሥነት ብዙ ጊዜ ቆየ። እንዲሁም ምንም እንኳን ባህሪዮና ምግባሩ እንደ ወገኖቹ እንደ ኤዶምያስ ቢሆን፤ ሃይማኖቱ ወደ እስራኤል የሚያደላ ስለነበር የአይሁድን ሃይማኖትና ልማድ ያከብርና ነበርና እነሱም እርሱን ይፈሩትና ያከብሩት ነበር። ዛሬ ግን በክርስቲያኖች ዘንድ ጌታችን የተወለደ ጊዜ ንጉሥ የሚሆን ሕፃን ተወለደ ማለትን ሰምቶ ከኔ በቀር ማን ንጉሥ ሊሆን ነው ብሎ ጌታችንን አብሮ ያገኘ መስሎት ብዙ ሕፃናት በማስፈጀቱ ለወዳጁ ለሄሮድያዳ ሲል የዮሐንስ መጥምቁን ራስ በማስቆረጡ እንደ ትልቅ ጨካኝና አመፀኛ የተቆጠረ ሰው ነው።

ይህ በመጽሐፍ ቅዱስ የሚገኘው የ፳ኤሎች ታሪክ ነው።




#Article 408: የጆሜትሪክ ድርድር (129 words)


የጂኦሜትሪክ ድርድር የምንለው  የቁጥሮች ድርድር  (ሰልፍ) ሲሆን እኒህ የተሰለፉ ቁጥሮች የኋለኛው የከፊተኛው ቋሚ ብዜት ውጤት ሲሆን ነው። ይህ ቋሚ ቁጥር የጋራ ውድር በመባል ይታወዋል። ለምሳሌ ይህን ድርድር እንመልከት 2, 6, 18, 54, ...፣  እያንዳንዱ ተከታይ ቁጥር የፊተኛውን ቁጥር በጋራ ውድሩ (3) ስናበዛ እናገኛለን፣ ስለዚህም የጅኦሜትሪክ ድርድር ይሰኛል። በተመሳሳይ ሁኔታ 10, 5, 2.5, 1.25,...  የጂኦሜትሪክ ድርድር ነው ምክንያቱም የጋራ ውድሩ   1/2 ነውና!   

የጆሜትሪክ ድርድር ቁጥሮችን ስንደምር የምናገኘው የሂሳብ ስርዓት ጆሜትሪክ ዝርዝር ይባላል።  ልዩነቱን ለማስተዋል ያክል፦

የጆሜትሪክ ድርድር አጠቃላይ ቅርጽ ይህን ይመስላል፦

የጆሜትሪክ ዝርዝር ደግሞ ይህን ይመስላል፦

እዚህ ላይ የጋራ ውድሩ  r ≠ 0  ሲሆን   a  ደግሞ ማጉያ መነሻ ይባላል ምክንያቱም የድርድሩ የመጀመሪያ ቁጥር ነውና! 

የጋራ ውድሩና ማጉያ መነሻው የታወቀ ማንኛውም የጆሜትሪክ ድርድር አጠቃላይ  n-ኛ  ቁጥር እንዲህ ሲደረግ በትክክል ይተነበያል

እኒህ አይነት ድርድሮች ሌላም ሂሳባዊ ቀመር አላቸው፣ ይኽውም  በአጣቃሽ ዝምድና ሲጻፍ




#Article 409: ይኩኖ አምላክ (216 words)


ዓጼ ይኵኖ አምላክ (የዘውድ ስም ተስፋ እየሱስ)  ከነሐሴ ፫ ቀን ፲፪፻፵፭ ዓ/ም ጀምሮ ለ አሥራ አምስት ዓመታት ነግሠዋል። በአባታቸው በተስፋ እየሱስ በኩል ከዛግዌ ስርወ መንግስት መነሳት በፊተ ከነበሩት የአክሱም ንጉስ  የአጼ ድል ናኦድ ጋር እንደሚዛመዱ ይጠቀሳል።  

ይኩኖ አምላክ ማለት አምላክ ጠባቂና ረዳት ይሁነው ሲሆን የተወለዱበትም እዚያው ወሎ ውስጥ ከደሴ ከተማ ወጣ ብላ በምትገኘው ሰገርት የምትባል ከተማ ነበር። ትህምህርታቸውንም ያጠናቀቁት ከአምባሰል ቀረብ ብሎ በሚገኘው ሃይቅ በሚባለው አካባቢ በ ሃይቅ እስጢፋኖስ ገዳም ነበር።  ትምህርታቸውን በቅዱስ እየሱስ ሞዓ ወይም በቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ወይም በሁለቱ ስር እንደወሰዱ የተጻፉ የተለያየ ዘመን ገድላቶች አሉ። ይሁንና የዛግዌን ስርወ መንግስት በሰለሞናዊ ስርወ መንግስት ከትምህርታቸው መገባደድ በኋላ ወይ በጦርነት ወይ በሰላም እንደቀየሩ ታሪክ ይመዘግባል።

ምንም በማያጠረጣር ሁኔታ፣  ጸሃፊው ዋሊስ በድጅ  እንደመዘገበ፣ ይኩኖ አምላክ ከቢዛንታይን ንጉስ ሚካኤል 8ኛ ጋር ደብዳቤ ተቀያይሯል እንዲሁም ለቤዛንታይኑ ንጉስ ብዙ ቀጭኔወችን በስጦታ እንደላከ አሁን ድረስ ማስረጃ አለ።   ለግብጹ ማምሉክ ሱልጣን ባይባርስም ከእስክንድርያ ፓትሪያርክ ሾሞ እንዲልክለት በ1273 በተደጋጋሚ እንደጻፈ ታሪክ መዝግቦ አልፏል። የተፈገውም ጳጳስ በጊዜው ስላለመጣ ከጎረቤት እስላም መሪወች በመጀመሪያው የመንግስቱ ዘመን የነበረው ስለማዊ ግንኙነት ተቋረጠ። 

ቀጥሎም የ ቆብጥ ፓትሪያርክ ባለመምጣቱ ይኩኖ አምላክ ወደ ሶሪያ ቄሶች እንዳዘነበለ ታደሰ ታምራት መዝግቧል።  እናም በዚህ ንጉስ ዘመን ከግብጾች ይልቅ የሶሪያወች ተሳትፎ በቤተክርቲያን ዙሪያ ይታይ ነበር።

ወሎ ውስጥ፣ ገነተ ማርያም የተሰኘውን ቤ/ክርስቲያን ያሰሩ እኒሁ ንጉስ  ናቸው ። ባረፉ ጊዜ የተቀበሩትም ደጋ ደሴት ተብላ በምትታወቀው የጣና ሃይቅ ደሴት ውስጥ  የወንድማቸው ልጅ ሂሩተ አምላክ ባሰራው ደጋ እስጢፋኖስ ነው። 




#Total Article count: 408
#Total Word count: 199996